You are on page 1of 74

የጤናና ሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት

የመምህር መምሪያ
8ኛ ክፍል

አዘጋጆች
ይማም አራጌ ዳኛው
ዶ/ር ደምሴ ጋሹ ዋለ
አርታኢዎች
ዶ/ር አምባቸው አመዴ
መልሴ ጠቋሬ ፈለቀ
ግርማሞገስ ይታይው
ቡድን መሪ
ዶ/ር ተከተል አብርሃም
ዲዛይነር
አትርሳው ጥግይሁን ወረቀት

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ

ይህ መጽሐፍ የተዘጋጀው በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በተመደበ በጀት
በአብክመ ትምህርት ቢሮና በምሁራን መማክርት ጉባዔ ትብብር ነው።

የመጽሐፉ ሕጋዊ የቅጂ ባለቤት © 2015 ዓ.ም. አብክመ ትምህርት ቢሮ ነው።

ምሁራን መማክርት ጉባዔ

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ

ማውጫ
ምዕራፍ 1
የሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት እና ስፖርት
1.1 የሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ጠቀሜታ................................................................................................................................. 1
1.2. የሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ከሌሎች ሙያዎች ጋር ያለው ግንኙነት.............................................................................. 2
1.3. የኢትዮጵያ ተሳትፎ በኦሎምፒክ ጨዋታ.............................................................................................................................. 3
1.4. የኢትዮጵያ ዝነኛ ስፖርተኞች በኢንቨስትመንት’ በፖለቲካ እና ማህበራዊ ጉዳይ.............................................................4
ምዕራፍ 2
ማሕበራዊ መስተጋብር እና ስሜታዊነት በሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት
2.1 ራስን የማወቅ እና በአግባቡ የመምራት ክህሎትን ለማዳበር የሚረዱ አካላዊ እንቅስቃሴዎች............................................8
2.2. ማሕበራዊ ግንዛቤን እና የመግባባት ክህሎትን ለማዳበር የሚረዱ አካላዊ እንቅስቃሴዎች.............................................10
2.3. ሀላፊነት የተሞላበት ውሳኔ የመወሰን ክህሎትን ለማዳበር የሚረዱ አካላዊ እንቅስቃሴዎች............................................12
2.4. በጥልቀት የማሰብ ክህሎትን ለማዳበር የሚረዱ አካላዊ እንቅስቃሴዎች...........................................................................14
2.5. የመግባባት እና የመተባበር ክህሎትን ለማዳበር የሚረዱ አካላዊእንቅስቃሴዎች.............................................................15
ምዕራፍ 3
ጤናና የአካል ብቃት
3.1. የአካል ብቃትን የሚያዳብሩ እንቅስቃሴ አይነቶች...............................................................................................................17
3.2 የልብና የአተነፋፈስ ሥርዓት ብርታት የሚያዳብሩ እንቅስቃሴዎች....................................................................................19
3.3. የጡንቻ ብርታት የሚያዳብሩ እንቅስቃሴዎች.................................................................................................................. 24
3.4. የመተጣጠፍ ችሎታን የሚያዳብሩ እንቅስቃሴዎች...........................................................................................................27
3.5. የፍጥነት ችሎታን የሚያዳብሩ እንቅስቃሴዎች................................................................................................................. 28
3.6. የስፖርት አበረታች ቅመሞችን (ዶፒንግ) መከላከል..........................................................................................................31
ምዕራፍ 4
አትሌቲክስ
4.1 በአፍሪካ የአትሌቲክስ ታሪክ..................................................................................................................................................33
4.2. የመሰናክልሩጫ....................................................................................................................................................................35
4.3 የአለሎ ውርወራ....................................................................................................................................................................37
4.4. የዲስከስ ውርውራ.............................................................................................................................................................. 38
4.5. የከፍታ ዝላይ...................................................................................................................................................................... 40

የጤናና ሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ~ 8ኛ ክፍል ~ የመምህር መምሪያ ~ iii

ምዕራፍ 5
ጅምናስቲክስ
5.1. የጅምናስቲክስመሰረታዊ ህጎች..............................................................................................................................................41
5.2. የነጻ ጅምናስቲክስ............................................................................................................................................................... 42
5.3.የመሣሪያ ጅምናስቲክስ........................................................................................................................................................ 48
ምዕራፍ 6
የኳስ ጨዋታዎች መሠረታዊ ክህሎት
6.1. የቮሊቦል ኳስን ከላይ ወደታች መለጋት............................................................................................................................. 50
6.2. የእግር ኳስን ወደጎል መምታት............................................................................................................................................53
6.3. በዝላይ ኳስንወደ ቅርጫት መወርወር............................................................................................................................... 56
6.4 የእጅ ኳስን በመስፈንጠር ወደ ግብ መወርወር................................................................................................................. 58
ምዕራፍ 7
የኢትዮጵያና የአለም ባህላዊ ጨዋታዎች
7.1 የኢትዮጵያ ባሕላዊ ጨዋታዎች............................................................................................................................................ 60
7.2 የተወሰኑ የአለም ሀገራት ባህላዊ ጨዋታዎች...................................................................................................................... 68

የጤናና ሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ~ 8ኛ ክፍል ~ የመምህር መምሪያ ~ iv

ምዕራፍ 1 የሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት እና ስፖርት

ምዕራፍ

1 የሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት እና

ስፖርት
የክፍለ ጊዜ ብዛት፡ 9

አጠቃላይ ዓላማዎች፡

ተማሪዎች ይህንን ምዕራፍ ተምረው ካጠናቀቁ በኋላ:-

ƒƒ የሰውነት ማጎልመሻ ትምህርትን ጠቀሜታ ይገነዘባሉ።
ƒƒ የሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ከሌሎች ሙያዎች ጋር ያለውን ግንኙነት ያደንቃሉ።
ƒƒ ኢትዮጵያ በኦሎምፒክ ጨዋታ ያላትንተሳትፎ ያደንቃሉ::
ƒƒ የኢትየጵያ ዝነኛ ስፖርተኞች የተለያዮ ተግባራቶቻቸውን ያብራራሉ::

መግቢያ
ይህ ምዕራፍ የሚያተኩረው የሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ጠቀሜታ፤ የሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ከሌሎች ሙያዎች ጋር ያለው
ግንኙነት፤የኢትየጵያ ዝነኛ ስፖርተኞች በተለያዮ ተግባራትና ኢትዮጵያ በኦሎምፒክ ጨዋታ ተሳትፎ በሚሉት ነጥቦች ላይ ይሆናል።

1.1 የሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ጠቀሜታ (1 ክ/ጊዜ)

ዝርዝር ዓላማ:-ተማሪዎች ይህንን ርዕስ ተምረው ካጠናቀቁበኋላ:-
ƒƒ የሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት በህይወት ዘመናቸው ከሚሰጣቸው ጠቀሜታዎች መካከል ቢያንስ አራቱን ይገልጻሉ::
ƒƒ በሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት መሳተፋቸው በህይወት ዘመናቸው የሚጠቅማቸው መሆኑን ያደንቃሉ::
ƒƒ በሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት አማካኝነት የተሻለ የአካል ብቃትና ጤናማ ሰዎችን ያደንቃሉ::

መሠረታዊ ጽንሰ-ሀሳብ (ለመምህሩ/ሯ የመነሻ ሀሳብ):-

ƒƒ በመማሪያ መጽሐፉ የተጠቀሰው ጽንሰ-ሀሳብ በቂ ነውተብሎ ይገመታል::

የመማር-ማስተማር መርጃ መሣሪያዎች እና ሥፍራዎች:-

መርጃ መሣሪያዎች:-ከትምህርቱ ጋር ተያያዥነት ያላቸው ሥዕሎችና ጽሁፎች፣

ሥፍራ:-የንድፈ ሀሳብ ትምህርት በሚሰጥበት ክፍል ውስጥ፣

የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል:-

ƒƒ አጠቃላይ የምዕራፉን ዓላማ፣ ይዘትና የምዘናና ግምገማ ሁኔታን ለተማሪዎች መግለጽ፣

የጤናና ሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ~ 8ኛ ክፍል ~ የመምህር መምሪያ ~ 1

ምዕራፍ 1 የሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት እና ስፖርት

ƒƒ የእለቱን ትምህርት ርዕሰና አላማ ለተማሪዎች ማስተዋወቅ፣

ƒƒ ተማሪዎች በጥንድ በጥንድ ሆነው እንዲደራጁ ማበረታታትና የሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ጠቀሜታን የሚያውቁትን
ያህል እንዲዘረዝሩ ማበረታታት፣ የተወያዮበትን እንዲያቀርቡ መገፋፋት፣
ƒƒ ከ3 እስክ 4 አባላት ያለው ቡድን በማደራጀት የዘረዘሯቸውን ጠቀሜታዎች እንዴት በሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት
ሊጎለብቱ እንደሚችሉ እንዲወያዮና በተወካይ አማካይነት እንዲያንፀባርቁ ማበረታታት፣
ƒƒ ተማሪዎች ከገለጹት አንጻር በመነሳት የሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ጠቀሜታን በመዘርዘር ማስረዳት፣
ƒƒ ከተሰጠው ማብራሪያ በመነሳት ያልገባቸውን እንዲጠይቁ እድል መስጠት፣
ƒƒ የተጠየቁትን ጥያቄ በተማሪዎችና በመምህሩ/ሯ መመለስ፣
ƒƒ ለሚቀጥለው ክፍለጊዜ ሰርተው የሚመጡትን ተግባር መስጠት፣

ክትትልና ግምገማ:-
ƒƒ ስለሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ጠቀሜታ የቃል ጥያቄዎችን በመጠየቅ ማረጋገጥ፣
ƒƒ የእለቱን ትምህርት ዝርዝር አላማዎች በትክክል መተግበሩን በጥያቄና መልስ፣ በሚያቀርቡት ውይይት እንዲሁም
ጓደኞቻቸው በሚያስተካክሏቸው ሀሳብ መሰረት መገምገም ይቻላል።

1.2. የሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ከሌሎች ሙያዎች ጋር ያለው

(1 ክ/ጊዜ)
ግንኙነት
ዝርዝር ዓላማ:-ተማሪዎች ይህንን ርዕስ ተምረው ካጠናቀቁበኋላ:-
ƒƒ ከሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ጋር ይበልጥ ግንኙነት ከአላቸው ሙያዎች መካከል ቢያንስ አራቱን ይገልጻሉ።
ƒƒ የሰውነት ማጎልመሻ ትምህርትና ሌሎች ሙያዎች ያላቸውን ግንኙነት ያደንቃሉ።

መሠረታዊ ጽንሰ-ሀሳብ (ለመምህሩ/ሯ የመነሻ ሀሳብ):-

ƒƒ በመማሪያ መጽሐፉ የተጠቀሰው ጽንሰ-ሀሳብ በቂ ነው ተብሎ ይገመታል::

የመማር-ማስተማር መርጃ መሣሪያዎች እና ሥፍራዎች:-

መርጃ መሣሪያዎች:-ከትምህርቱ ጋር ተያያዥነት ያላቸው ሥዕሎችና ጽሁፎች፣

ሥፍራ:-የንድፈ ሀሳብ ትምህርት በሚሰጥበት ክፍል ውስጥ፣

የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል:-

ƒƒ የባለፈውን ትምህርት በጥያቄና መልስ መከለስ፣
ƒƒ የእለቱን ትምህርት ርዕሰና አላማ ለተማሪዎች ማስተዋወቅ፣
ƒƒ ተማሪዎች በየግላቸው ሙያ ምን ማለት እንደሆነ እንዲያሰላስሉ ማበረታታትና የደረሱበትን ሀሳብ ለክፍሉ ተማሪዎች
እንዲገልጹ መገፋፋት።
ƒƒ ከተማሪዎች ሀሳብ በመነሳት ሙያ ሲባል አንድ ግለሰብ ከአንድ ተቋም ወይም መሰል ድርጅት አንድ የስራ ክህሎትን
በመሰልጠን (በማግኘት) የዕለት ኑሮውንም ሆነ አስፈላጊውን ሁሉ ሊያከናውንበት የሚያስችለው ችሎታ መሆኑን በገለጻ
ማስረዳት፣

የጤናና ሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ~ 8ኛ ክፍል ~ የመምህር መምሪያ ~ 2

ምዕራፍ 1 የሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት እና ስፖርት

ƒƒ ተማሪዎችበጥንድ በጥንድ ሆነው የሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ከሌሎች ሙያዎችጋር ያለው ግንኙነት እንዲወያዮ
ማበረታታት፣
ƒƒ ተማሪዎች የተወያዮበትን ለክፍሉ ተማሪዎች እንዲያቀርቡ ማበረታታት፣
ƒƒ ተማሪዎች ከሰጡት ሀሳብ በመነሳት የሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ከሌሎች ሙያዎችጋር ያለው ግንኙነት በገለጻ
ማስረዳትና በተጨማሪምየሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ከሌሎች ሙያዎች ጋር ሲነፃፃር አስተዋፆኦ ምን እንደሆነ
በጥያቄና መልስ ማስረዳት፣
ƒƒ ተማሪዎች ያልገባቸውን እንዲጠይቁ ማበረታታትና ለተነሱት ጥያቆዎች በተማሪዎችና በመምህሩ/ሯ መልስ መስጠት፣
ƒƒ ለሚቀጥለው ክፍለጊዜ ሰርተው የሚመጡትን ተግባር መስጠት (በመማሪያ መጽሐፉኢትዮጵያ ተሳትፎ በኦሎምፒክ
ጨዋታ የተቀመጡትን ተግባራት ጠይቀው እንዲመጡ ማበረታታት)፣

ክትትልና ግምገማ:-
ƒƒ የሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ከሌሎች ሙያዎች ጋር ያለው ግንኙነትየቃል ጥያቄዎችን በመጠየቅ ማረጋገጥ::

1.3. የኢትዮጵያ ተሳትፎ በኦሎምፒክ ጨዋታ (3 ክ/ጊዜ)

ዝርዝር ዓላማ:-ተማሪዎች ይህንን ርዕስ ተምረው ካጠናቀቁበኋላ:-
ƒƒ በኦሎምፒክ ጨዋታ የኢትየጵያን ተሳትፎ በሚገባ ይገልጻሉ::
ƒƒ ኢትዮጵያ በተለያዮ የኦሎምፒክ ጨዋታዎች ከአስመዘገበቻቸው ውጤቶች መካከል የተወሰኑትን ይዘረዝራሉ::
ƒƒ ኢትዮጵያ በኦሎምፒክ ጨዋታ ያላትን ተሳትፎ ያደንቃሉ::

መሠረታዊ ጽንሰ-ሀሳብ (ለመምህሩ/ሯ የመነሻ ሀሳብ):-

ኢትዮጵያ በኦሎምፒክ ጨዋታ ያላትን ተሳትፎ በመማሪያ መፅሀፉ የተጠቀሰው መረጃ እንደተጠበቀ ሆኖ ለዚህ ርዕስ ተጨማሪ
ከአስፈለገ በኦሎምፒክየሜዳሊያተሸላሚ ኢትዮጵያዊ ጀግኖችን ስም ዝርዝር የያዘ ከተለያዮ ድህረ-ገፆች (ከኢተርኔት) መፈለግ
ይቻላል::

የሀገራችንን ስም በየጊዜው በኦሎምፒክ ጨዋታ ያስጠሩ ሰንደቅ ዓላማችንን ከፍ ብሎ እንዲውለበለብ ካደረጉ ብርቅየና ጀግኖች
አትሌቶቻችን ጥቂቶቹበዚህ ክፍል የምንማራቸው የሚከተሉት ናቸው:-

1. ሻምበል አበበ ቢቂላ

ƒƒ በ1960እ.ኤ.አ በሮም፣ በ1964እ.ኤ.አ በቶክዮ የኦሎምፒክ ጨዋታዎች በማራቶን የወርቅ ሜዳሊያዎች ባለቤት ነው።

2. ሻለቃሀይሌገ/ስላሴ
ƒƒ በ1996እ.ኤ.አ አትላንታ ኦሎምፒክ ጨዋታ እና በ2000እ.ኤ.አ ኦሎምፒክ ጨዋታ በ10000ሜትር የሁለት ወርቅ ሜዳሊያ
ባለቤት ነው።

4. ኮማንደር ደራርቱ ቱሉ
ƒƒ በ1992እ.ኤ.አ ባርሴሎና ኦሎምፒክ ጨዋታ፣ በ2000እ.ኤ.አ ሲድኒ የኦሎምፒክ ጨዋታ በ10000 ሜትር የሁለት ወርቅ
ሜዳሊያዎች አሸናፊ ናት።

የጤናና ሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ~ 8ኛ ክፍል ~ የመምህር መምሪያ ~ 3

ምዕራፍ 1 የሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት እና ስፖርት

5 ጌጤ ዋሚ
ƒƒ በ1996እ.ኤ.አ በአትላንታ ኦሎምፒክ ጨዋታ በ10000 ሜትር የነሀስ ሜዳሊያ፣ በ2000 እ.ኤ.አሲድኒ የኦሎፒክ ጨዋታ
በ10000 ሜትር የነሀስ ሜዳሊያ አሸናፊ ናት።

6. ገዛሀኝ አበራ
ƒƒ በ2000እ.ኤ.አ ሲድኒ ኦሎምፒክ ጨዋታ በ5000 ሜትር የወርቅ ሜዳሊያ ባለቤት ነው።

የመማር-ማስተማር መርጃ መሣሪያዎች እና ሥፍራዎች:-

መርጃ መሣሪያዎች:- በኦሎምፒክ ጨዋታ የኢትዮጵያን ተሳትፎ የሚገልጹ ፖስተሮች፤ ስዕሎች፤ ቻርቶች፤ ፊልሞች
ፎቶዎችና ጽሁፎች፣
ሥፍራ:-የንድፈ ሀሳብ ትምህርት በሚሰጥበት ክፍል ውስጥ፣

የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል:-

ƒƒ የባለፈውን ትምህርት በጥያቄና መልስ መከለስ፣
ƒƒ የእለቱን ትምህርት ርዕሰና አላማ ለተማሪዎች ማስተዋወቅ፣
ƒƒ ስለኦሎምፒክ ትርጉም እና ታሪክ በ6ኛ እና 7ኛ ክፍሎች የተማሯቸውን በአዕምሮ ጨመቃ ስልት እንዲያሰላስሉ ማድረግ፣
ƒƒ ተማሪዎችን በጥንድ በጥንድ በማደራጀት ኢትዮጵያ በኦሎምፒክ ጨዋታ ያላትን ተሳትፎ እንዲያብራሩ ማበረታታት፣
ƒƒ ተማሪዎች የተወያዮበትን እንዲያቀርቡ ማበረታታትና እነሱ ከገለጹት አንጻርኢትዮጵያ በኦሎምፒክ ጨዋታ ያላትን
ተሳትፎ በመዘርዘር ማስረዳት፣
ƒƒ ከተሰጠው ማብራሪያ በመነሳት ያልገቧቸውን ጥያቄ እንዲጠይቁ ተጨማሪ እድል መስጠት፣
ƒƒ የተጠየቁትን ጥያቄዎች በመመለስ ለሚቀጥለው ክፍለጊዜ የቤት ሥራ ሰርተውት የሚመጡትን ጥያቄ መስጠት፣
ƒƒ ይህ ንዑስ-ርዕስ ለሦስት ክፍለጊዜ ስለሆነ በአካባቢያቸው ከሚገኙ ባለሙያዎችበመጠየቅ ወይም ከተለያዮ ድህረ-ገፆች
(ኢንተርኔት) በመፈለግ ኢትዮጵያ በተለያዮ የኦሎምፒክ ጨዋታዎች ያልተሳተፈችባቸውን ጊዜና በተሳተፈችባቸው
ጊዚያት አትሌቶች ያገኙትን ሜዳሊያበተጨማሪም በመማሪያ መጽሐፉ የተጠቀሱትን ተግባራት ለሚቀጥለው ክፍለጊዜ
የቤት ሥራ በመስጠት ማስተማር ተገቢ ይሆናል::

ክትትልና ግምገማ:-
ƒƒ ኢትዮጵያ በኦሎምፒክ ጨዋታ ያላትን ተሳትፎ በግልና በቡድን ፅብረቃ ሲያደርጉ መከታተል፣
ƒƒ ኢትዮጵያ በኦሎምፒክ ጨዋታ ያላትን ተሳትፎ በተመለከተ የቃል ጥያቄዎችን በመጠየቅ ማረጋገጥ፣

1.4. የኢትዮጵያ ዝነኛ ስፖርተኞች በኢንቨስትመንት’ በፖለቲካ እና

(3 ክ/ጊዜ)
ማህበራዊ ጉዳይ
ዝርዝር ዓላማ:-ተማሪዎች ይህንን ርዕስ ተምረው ካጠናቀቁበኋላ:-
ƒƒ በኢትዮጵያ ከሚገኙ ዝነኛ ስፖርተኞች መካከል ቢያንስ አራቱን ይዘረዝራሉ::
ƒƒ በኢትዮጵያ ከሚገኙ ዝነኛ ስፖርተኞች መካከል የሶስቱን በኢንቨስትመንት፣ በፖለቲካና በማህበራዊ ጉዳይ ያላቸውን
ተሳትፎ ያብራራሉ::

የጤናና ሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ~ 8ኛ ክፍል ~ የመምህር መምሪያ ~ 4

ምዕራፍ 1 የሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት እና ስፖርት

ƒƒ በኢትዮጵያ ከሚገኙ ዝነኛ ስፖርተኞችን መልካም ተግባሮቻቸውን በመገንዘብ እንደነሱ ታዋቂ ለመሆን ይነሳሳሉ::

መሠረታዊ ጽንሰ-ሀሳብ (ለመምህሩ/ሯ የመነሻ ሀሳብ):-

ƒƒ በመማሪያ መጽሐፉ የተጠቀሰው ጽንሰ-ሀሳብ እንዳለ ሆኖ በዚህ ርዕስ ላይ ከተለያዮ ድህረ-ገፆች (ኢንተርኔት)ተጨማሪ
መረጃዎችን ማጠናቀር ያስፈልጋል::

የመማር-ማስተማር መርጃ መሣሪያዎች እና ሥፍራዎች:-

መርጃ መሣሪያዎች:- ስለዝነኛ ስፖርተኞቹ የሚገልጹ ፖስተሮች፤ ስዕሎች፤ ቻርቶች፤ ፊልሞች ፎቶዎችና ጽሁፎች
ሥፍራ:-የንድፈ ሀሳብ ትምህርት በሚሰጥበት ክፍል ውስጥ፣

የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል:-

ƒƒ የባለፈውን ትምህርት በጥያቄና መልስ መከለስ፣
ƒƒ የእለቱን ትምህርት ርዕሰና አላማ ለተማሪዎች ማስተዋወቅ፣
ƒƒ ተማሪዎች ጥንድ ጥንድ ሆነው እንዲደራጁ ማበረታታትና በሀገራችን በኦሎምፒክ ደረጃ አሸናፊ የሆኑ ታዋቂ አትሌቶች
እነማን እንደሆኑ ከአካባቢያቸው ባለሙያ ጠይቅው ወይም ከተለያዮ ድህረ-ገጾች (ኢንተርኔት) በመጠቀም ያገኙትን
መረጃ እንዲሁም የሚያውቁትን ያህል እንዲዘረዝሩ ማበረታታት፣
ƒƒ ከላይ በተደራጁበት ሁኔታ በአካባቢያቸው ታዋቂ የሆኑ የስፖርት ሰዎች እንዳሉና እነማን እንደሆኑ የሚያውቁትን
እንዲጠቅሱ ማበረታታት፣
ƒƒ ተማሪዎች ከገለጹት አንጻርበመነሳት በሀገራችንበኦሎምፒክ ደረጃ አሸናፊ የሆኑ ታዋቂ አትሌቶች ብዙ እንደሆኑና በ5ኛ፣
በ6ኛ እና 7ኛ ክፍሎች የተማሯቸው እንዳሉ በማስታወስ በዚህ ክፍል ደረጃ ለምሳሌ የቀረቡትን በመዘርዘር ማስረዳት፣
ƒƒ ተማሪዎች አራት አራት በመሆን እንዲደራጁ ማድረግና ሻምበል አበበ ቢቂላ፣ ሻለቃ ሀይሌ ገ/ስላሴ፣ ኮማንደር ደራርቱ
ቱሉ እና ጌጤ ዋሚየተሳተፉበትን የውድድር ርቀትና ያገኙትን ሽልማት እንዲያብራሩ ማበረታታት፣
ƒƒ ተማሪዎች የተወያዮበትን እንዲያቀርቡ ማበረታታትና ከገለጹት አንጻር በመነሳት ከላይ በመሠረታዊ ጽንሰሀሳብ
ከተገለፀው ተጨማሪ መረጃ በመጨመር ዋናዋና ሀሳቦችን ማስረዳት፣
ƒƒ ከተሰጠው ማብራሪያ በመነሳት ያልገቧቸውን ጥያቄ እንዲጠይቁ ተጨማሪ እድል መስጠት
ƒƒ የተጠየቁትን ጥያቄዎች በመመለስ ለሚቀጥለው ክፍለጊዜ የቤት ሥራ ሰርተውት የሚመጡትን ጥያቄ መስጠት፣
ƒƒ ይህ ርዕስ ለሦስት ክፍለ-ጊዜ ስለሆነ ሻምበል አበበ ቢቂላ፣ ሻለቃ ሀይሌ ገ/ስላሴ፣ ኮማንደር ደራርቱ ቱሉ እና ጌጤ ዋሚ
በኦሎምፒክ ጨዋታ ያገኙትን ሽልማት፤ በኢንቨስትመንት፤ በፖለቲካ እና ማህበራዊ ጉዳይ ላይ ያላቸውን ተሳትፎ የቤት
ሥራ በመስጠት ማስተማር ተገቢ ይሆናል::

ክትትልና ግምገማ:-
ƒƒ ስለሀገራችን ዝነኛ ስፖርተኞች በተመለከተ በግልና በቡድን ፅብረቃ ሲያደርጉ መከታተል፣
ƒƒ ስለሀገራችን ዝነኛ ስፖርተኞች በተመለከተ የቃል ጥያቄዎችን በመጠየቅ ማረጋገጥ፣

የጤናና ሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ~ 8ኛ ክፍል ~ የመምህር መምሪያ ~ 5

ምዕራፍ 1 የሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት እና ስፖርት

የምዕራፉ መልመጃ መልስ

1. መ 2. ሀ

3. የህክምና ባለሙያ ማህበረሰቡ ጤናውን በመጠበቅ የተሻለ የአኗኗር ዘይቤ እንዲከተል ብርቱ ጥረት ያደርጋሉ:: ከዚህም በተጨማሪ
አንድ ሰው የአካል፣ የአዕምሮ፣ የማህበራዊና የመንፈስ ደህንነቱ እንዲሟላ በርካታ ስረዎች ይሰራሉ:: እነዚህ የተጠቀሱት ሀሳቦች
በሰውነት ማጎልመሻ ትምህርትም ዜጎች እንዲያሟሏቸው ይፈለጋል:: ስለሆነም የሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ከህክምና ሙያ ጋር
በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ግንኙነት እንዳለው መግልጽ ይቻላል:: ተማሪዎች ሌሎች ተቀራራቢ ሀሳቦችን ሊያቀርቡ ይችላሉ::

4. በተለየዮ የሆቴል ኢንዱስትሪ፣ በተለያዮ የስፖርት ፌድሬሽን በአማተርነት በማገልገል፣ ለተቸገሩ ወገኖች በመርዳት፣ ትምህርት
ቤት በመገንባት ወ.ዘ.ተ

5. በተለያዮ የፖለቲካ ምክንያቶች:: ሌሎች መረጃዎችን በማገናዘብ ማብራሪያ መጨመር ይቻላል::

የጤናና ሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ~ 8ኛ ክፍል ~ የመምህር መምሪያ ~ 6

ምዕራፍ 2 ማሕበራዊ መስተጋብር እና ስሜታዊነት በሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት

ምዕራፍ

2 ማሕበራዊ መስተጋብር እና ስሜታዊነት

በሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት
የክፍለ ጊዜ ብዛት፡ 9

አጠቃላይ ዓላማዎች፡

ተማሪዎች ይህንን ምዕራፍ ከተማሩ በኋላ፡-

ªªአካላዊ እንቅስቃሴዎች ወይም ጨዋታዎች ራስን የማወቅ፣ ራስን የመምራት፣ ማሕበራዊ ግንዛቤን እና የመግባባት
ክህሎትን እንደዚሁም በጥልቀት የማሰብ እና ሀላፊነት የተሞላበት ውሳኔ የመወሰን እና የመተባበር ክህሎትን ለማዳበር
እንደሚረዳ ይገነዘባሉ።
ªªአካላዊ እንቅስቃሴዎች ወይም ጨዋታዎች ራስን የማወቅ፣ ራስን የመምራት፣ ማሕበራዊ ግንዛቤን እና የመግባባት
ክህሎትን እንደዚሁም ሀላፊነት የተሞላበት ውሳኔ የመወሰን፣ በጥልቀት የማሰብ፣ እና የመተባበር ክህሎትን ለማዳበር
ያላቸውን ሚና ያደንቃሉ፡።
ªªአካላዊ እንቅስቃሴዎች ወይም ጨዋታዎች ራስን የማወቅ፣ ራስን የመምራት፣ ማሕበራዊ ግንዛቤን እና የመግባባት
ክህሎትንእንደዚሁም ሀላፊነት የተሞላበት ውሳኔ የመወሰን፣ በጥልቀት የማሰብ፣ እና የመተባበር ክህሎታቸውን
ያዳብራሉ።

መግቢያ
ስፖርታዊ ጨዋታዎች የማሕበራዊ ሕይወት ክህሎቶችን ለማጎልበት የማይተካ ሚና አላቸው። ጨዋታዎች በቡድን በውድድር
መልክ ሲከወኑ ደግሞ ምክንያታዊ ትውልድን ከመፍጠር አንፃር የጎላ ሚና ይኖራቸዋል። እያንዳንዱ ተማሪ ራሱን ብሎም የሌሎችን
ስሜት እንዲረዳ የስፖርታዊ ጨዋታዎች እገዛ እጅግ የደመቀ ነው።

እድገት፣ ሀብት እና ልማት ትርጉም የሚኖረው ከሰው ልጅ ጋር በጋራ መተባበር እና መቻቻል ሲቻል እንደሆነ ለማስተማር ከስፖርታዊ
ጨዋታዎች ውጪ ሌላ አማራጭ የሚኖር አይመስልም። የሰው ልጅ ራሱን ከስኬት ማማ ላይ ለማድረስ ራሱን ማወቅ እና ራሱን
በአግባቡ መምራት ይኖርበታል። ማሕበረሰቡን ሳያውቁ የመተባበር እና የመግባባት ክህሎታቸውንም ሳያሳድጉ የሚፈልጉት ደረጃ
ላይ መድረስ እጅግ አስቸጋሪ እንደሆነ ተሞክሮዎች ያሳያሉ። በጥልቀት የማሰብ እና ምክንያታዊ ውሳኔ የመወስን ክህሎታችንም የዛሬ
እና የነገን ስኬታችንን የሚወስኑ ጉዳዮች ናቸው። የእነዚህን ወሳኝ ክህሎቶች ለማሳደግ እና ለማጎልብት ደግሞ የተመረጡ ስፖርታዊ
ጨዋታዎች የጎላ ሚና አላቸው። ይህ ምዕራፍ በእነዚህ ቁልፍ ጉዳይ ላይ ትኩረት የሚያደርግ ነው።

የጤናና ሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ~ 8ኛ ክፍል ~ የመምህር መምሪያ ~ 7

ምዕራፍ 2 ማሕበራዊ መስተጋብር እና ስሜታዊነት በሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት

2.1 ራስን የማወቅ እና በአግባቡ የመምራት ክህሎትን ለማዳበር

(3 ክ/ጊዜ)
የሚረዱ አካላዊ እንቅስቃሴዎች

2.1.1 ከአደጋ ማዳን (1 ክ/ጊዜ)

ዝርዝር ዓላማ:-ተማሪዎች ይህንን ርዕስ ከተማሩ በኋላ፦
ƒƒ ጨዋታው ራስን የማወቅና በአግባቡ ከመምራት ክህሎት ጋር ያለውን ግንኙነት በትክክል ያበራራሉ።
ƒƒ ከአደጋ ማዳን ጨዋታ ሲጫዎቱ ራሳቸውን በማወቅና በአግባቡ ለመምራት ተነሳሽነት ያሳያሉ።
ƒƒ ከአደጋ ማዳን ጨዋታ እንቅስቃሴን በትክክል ይሰራሉ።

መሠረታዊ ጽንሰ-ሀሳብ (ለመምህሩ/ሯ የመነሻ ሀሳብ):-

ƒƒ በመማሪያ መጽሐፉ ሰለጨዋታው የተጠቀሰው አጨዋወት እና የጨዋታው ሕግ እንዳለ ሆኖ ይህን ዓላማ ሊያሳካ
የሚችል አማራጭ ልዮ ልዮ ጨዋታዎችን መጠቀም ይቻላል::

የመማር-ማስተማር መርጃ መሣሪያዎች እና ሥፍራዎች:-

መርጃ መሣሪያዎች:- የሜዳ ማዘጋጃ ኖራ ወይም አመድ፣

ሥፍራ:- የተግባር ትምህርት የሚሰጥበት የስፖርት ሜዳ፣

የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል:-

ƒƒ የባለፈውን ትምህርት በጥያቄና መልስ መከለስ፣
ƒƒ የእለቱን ትምህርት ርዕሰና አላማ ለተማሪዎች ማስተዋወቅ፣
ƒƒ ተማሪዎችን በአራት ምድብ በማደራጀት የሰውነት ማሟሟቅያ እንቅስቃሴዎች ከቀላል እንቅስቃሴዎች በመጀመር
ለዋናው የእለቱ ተግባር ቅድመ ዝግጅት እንዲያደርጉ ማበረታታት፣
ƒƒ ተማሪዎች ከእለቱ ተግባር ወይም ትምህርት ጋር ተቀራራቢነት ያለው የሰውነት ማሟሟቂያ እንቅስቃሴ እንዲሰሩ
ማበረታታትና ተማሪዎች እንቅስቃሴዎችን ሲሰሩ በመከታተል ማስተካከያ መስጠት፣
ƒƒ ከ20 እስከ 30 ሜትርበሆነርቀትበሁለትትይዩቀጥታመስመሮችየተከለለሜዳ ማዘጋጀት፣
ƒƒ እንደተማሪዎቹ ቁጥር ብዛት ከ2 እስከ 4 ቡድን በማደራጀት ከአንደኛው መስመር በየቡድናቸው በስተኋላ መስመር
እንዲቆሙ ማድረግ፣
ƒƒ እያንዳንዱቡድንአንድአንድመሪ(አዳኝ)መርጦቡድኖቹከቆሙበትመስመርፊትለፊትካለውመስመርበኋላከእነርሱትይዩእ
ንዲቆሙ ማድረግና የጨዋታውን ህግ እና ደንብ መልሶ ማስገንዘብ፣
ƒƒ ጨዋታውን ለማስጀመር “በቦታህ”(“ተዘጋጅ”) ወይም “ሂድ”የሚል ትዕዛዝበመስጠትየየቡድኑመሪዎችከቆሙበትመስ
መርተነስተውበመሮጥከየቡድናቸውየመጀመሪያውንሯጭእጅይዘውተመልሰውወደነበሩበት እንዲደርሱ ማድርግ፣
ƒƒ ከዚያምመሪዎችይቀየሩናእየተጎተቱ የተወሰዱትተጫዋቾችወደቡድናቸውተመልሰውበመሮጥበተራየቆሙትንሯጮችእ
ጅይዘውበመሳብወደየአለቆቻቸው (የቡድን መሪዎቻቸው) እንዲመለሱ ማበረታታት፣
ƒƒ በዚህአኳኋን ተጨዋቾቹ ሁሉመሪዎቻቸውኋላእስኪሆኑድረስጨዋታውን ማስቀጠል፣
ƒƒ ጨዋታውን ሲያከናውኑ እርምትና ክትትል ማድረግ፣

የጤናና ሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ~ 8ኛ ክፍል ~ የመምህር መምሪያ ~ 8

ምዕራፍ 2 ማሕበራዊ መስተጋብር እና ስሜታዊነት በሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት

ƒƒ በመማሪያ መፅሀፉ በተጠቀሰው መሰረት ከመሪውበኋላበመጀመሪያተሰልፎየተገኘቡድንየጨዋታውአሸናፊይሆናል፣

ƒƒ ከተማሪዎች የእድገት ደረጃና አካል ብቃት ደረጃ መሰረት ጨዋታውን በመደጋገም እንዲጫዎቱ እድል መስጠት፣
ƒƒ በመቀጠልም የሰውነት ማቀዝቀዣ እና ማሳሳቢያ እንቅስቃሴ እንዲያደርጉ ማድረግ፣
ƒƒ የተወሰነ ጊዜ በመስጠት ጨዋታው ራስን ከማወቅ እና በአግባቡ ከመምራት ጋር የነበራቸውን ሚናና ስሜት እንዲገልፁ
ማበረታታት፣
ƒƒ የእለቱ ትምህርት ምን ያህል እንዳዝናናቸውና እንደሳባቸው እንዲሁም ለምን ጥቅም እንደሆነ እንዲገልጹ ማድረግና
ማጠናቀቅ፣

ክትትልና ግምገማ:-
ƒƒ በጨዋታው ራስን የማወቅ እና በአግባቡ የመምራት ክህሎት ከስሜታዊነት እና ከምክንያታዊነት ጋር ያለውን ግንኙነት
ሲገልጹና በጨዋታው ሲያንፀባርቁ በምልከታና በጥያቄና መልስ ማረጋገጥ፣
ƒƒ በጨዋታው ምን ያህል ስሜታቸውን እንደሚገልፁ በምልከታ ማረጋገጥ፣

2.1.2 ቦታ ለውጥ (1 ክ/ጊዜ)

ዝርዝር ዓላማ:-ተማሪዎች ይህንን ርዕስ ከተማሩ በኋላ፦
ƒƒ ጨዋታው ራስን የማወቅና በአግባቡ ከመምራት ክህሎት ጋር ያለውን ግንኙነት በትክክል ያበራራሉ።
ƒƒ የቦታ ለውጥ ጨዋታ ሲጫዎቱ ራሳቸውን በማወቅና በአግባቡ ለመምራት ተነሳሽነት ያሳያሉ።
ƒƒ የቦታ ለውጥ ጨዋታ እንቅስቃሴን በትክክል ይሰራሉ።

መሠረታዊ ጽንሰ-ሀሳብ (ለመምህሩ/ሯ የመነሻ ሀሳብ):-

ƒƒ በመማሪያ መጽሐፉ ሰለጨዋታው የተጠቀሰው አጨዋወት እና የጨዋታው ሕግ እንዳለ ሆኖ ይህን ዓላማ ሊያሳካ
የሚችል አማራጭ ልዮ ልዮ ጨዋታዎችን መጠቀም ይቻላል::

የመማር-ማስተማር መርጃ መሣሪያዎች እና ሥፍራዎች:-

መርጃ መሣሪያዎች:- የሜዳ ማዘጋጃ ኖራ ወይም አመድ፣

ሥፍራ:- የተግባር ትምህርት የሚሰጥበት የስፖርት ሜዳ፣

የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል:-

ƒƒ የባለፈውን ትምህርት በጥያቄና መልስ መከለስ፣
ƒƒ የእለቱን ትምህርት ርዕሰና አላማ ለተማሪዎች ማስተዋወቅ፣
ƒƒ ተማሪዎች በአራት ወይም በአምስት ምድብ በማደራጀት የሰውነት ማሟሟቂያ እንቅስቃሴዎች ከቀላል እንቅስቃሴዎች
በመጀመር ለዋናው የእለቱ ተግባር ቅድመ ዝግጅት እንዲያደርጉ ማበረታታት፣
ƒƒ እንደተማሪዎቹ ቁጥር ብዛት እኩል በሆነ በሁለት ወይም ከዚያ በላይ በቡድን ማደራጀት፣
ƒƒ ከ20 እስክ 30 ሜትርበመራራቅበሰልፍትይዩበመሆን መቆምና መሀከልአንድ ተጨዋች አዳኝሆኖእንዲቆምማድረግ፣

የጤናና ሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ~ 8ኛ ክፍል ~ የመምህር መምሪያ ~ 9

ምዕራፍ 2 ማሕበራዊ መስተጋብር እና ስሜታዊነት በሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት

ƒƒ መሀል የቆመው አዳኙ“የቦታለውጥ’’ብሎ ድምፅሲያሰማሁለቱምቡድኖችየተቃራኒያችውንመሥመርለመያዝይሯሯ

ጣሉ። በዚህን ጊዜ አዳኙምአጥምዶይይዛቸውናረዳትአዳኝያደርጋቸዋል። ጨዋታውበዚህሁኔታአንድ ተጨዋች
እስኪቀርይቀጥላል። በመጨረሻሳይያዝ የቀረውን ተጨዋች አዳኝበመሆን ጨዋታውንበድጋሚእንዲመራ ማበረታታት፣
ƒƒ በመጨረሻሳይያዝየቀረው ተጨዋች (ተማሪ) በግልአሸናፊሲሆንእሱየነበረበትንቡድንም አሸናፊእንዲሆን ማድረግ፣
ƒƒ ከተማሪዎች የእድገት ደረጃና አካል ብቃት ደረጃ መሰረት ጨዋታውን በመደጋገም እንዲጫዎቱ እድል መስጠት፣
ƒƒ በመቀጠልም የሰውነት ማቀዝቀዣ እና ማሳሳቢያ እንቅስቃሴ እንዲያደርጉ ማድርግ፣
ƒƒ የተወሰነ ጊዜ በመስጠት ጨዋታው ራስን ከማወቅ እና በአግባቡ ከመምራት ጋር የነበራቸውን ሚናና ስሜትበተጨማሪም
በመማሪያ መፅሀፉ የተቀመጠውን ተግባር እንዲገልፁ ማበረታታት፣
ƒƒ የእለቱ ትምህርት ምን ያህል እንዳዝናናቸውና እንደሳባቸው እንዲሁም ለምን ጥቅም እንደሆነ እንዲገልጹ ማድረግና
ማጠናቀቅ፣

ክትትልና ግምገማ:-
ƒƒ በጨዋታው ራስን የማወቅ እና በአግባቡ የመምራት ክህሎት ከስሜታዊነት እና ከምክንያታዊነት ጋር ያለውን ግንኙነት
ሲገልጹና በጨዋታው ሲያንፀባርቁ በምልከታና በጥያቄና መልስ ማረጋገጥ፣
ƒƒ በጨዋታው ምን ያህል ስሜታቸውን እንደሚገልፁ በምልከታ ማረጋገጥ፣

2.2. ማሕበራዊ ግንዛቤን እና የመግባባት ክህሎትን ለማዳበር የሚረዱ

(2 ክ/ጊዜ)
አካላዊ እንቅስቃሴዎች

2.2.1 በጥንድ ማደን (1 ክ/ጊዜ)

ዝርዝር ዓላማ:-ተማሪዎች ይህንን ርዕስ ከተማሩ በኋላ፦
ƒƒ ጨዋታው ማሕበራዊ ግንዛቤን እና የመግባባት ክህሎት ጋር ያለውን ግንኙነት በትክክል ያብራራሉ።
ƒƒ በጥንድ ማደን ጨዋታ ሲጫዎቱ ማህበራዊ ግንዛቤያቸውንና የመግባባት ክህሎታቸውን ለማጎልበት ተነሳሽነት ያሳያሉ።
ƒƒ በጥንድ ማደንጨዋታ እንቅስቃሴን በትክክል ይሰራሉ።
ƒƒ በጨዋታውበአብሮነት ከመስራት ጋር ያለውን ግንኙነት ያብራራሉ።

መሠረታዊ ጽንሰ-ሀሳብ (ለመምህሩ/ሯ የመነሻ ሀሳብ):-

ƒƒ በመማሪያ መጽሐፉ ሰለጨዋታው የተጠቀሰው አጨዋወት እና የጨዋታው ሕግ እንዳለ ሆኖ ይህን ዓላማ ሊያሳካ
የሚችል አማራጭ ልዮ ልዮ ጨዋታዎችን መጠቀም ይቻላል::

የመማር-ማስተማር መርጃ መሣሪያዎች እና ሥፍራዎች:-

መርጃ መሣሪያዎች:- የሜዳ ማዘጋጃ ኖራ ወይም አመድ፣

ሥፍራ:- የተግባር ትምህርት የሚሰጥበት የስፖርት ሜዳ፣

የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል:-

ƒƒ የባለፈውን ትምህርት በጥያቄና መልስ መከለስ፣

የጤናና ሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ~ 8ኛ ክፍል ~ የመምህር መምሪያ ~ 10

ምዕራፍ 2 ማሕበራዊ መስተጋብር እና ስሜታዊነት በሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት

ƒƒ የእለቱን ትምህርት ርዕሰና አላማ ለተማሪዎች ማስተዋወቅ፣

ƒƒ ተማሪዎች በአራት ወይም በአምስት ምድብ በማደራጀት የሰውነት ማሟሟቅያ እንቅስቃሴዎች ከቀላል እንቅስቃሴዎች
በመጀመር ለዋናው የእለቱ ተግባር ቅድመ ዝግጅት እንዲያደርጉ ማበረታታት፣
ƒƒ የክፍሉ ተማሪዎች በትልቅ ክብ ዙሪያ እንዲቆሙ ማድረግና ሁለት ተማሪዎችበመምረጥ ከክቡ መሀከል እጅ ለእጅ
ተያይዘው “አዳኝ” እንዲሆኑ ማድረግ፣
ƒƒ ጨዋታውን ለማስጀመር ትእዛዝ ሲሰጥ ሁለቱ እጅ ለእጅ የተያያዙት አዳኞች ወደክቡ ዙሪያ በመሮጥ በክቡ ዙሪያ ካሉት
ተማሪዎችእንዲነኩ ማበረታታት፣
ƒƒ የተነካው ተማሪ ከሁለቱ ጋር በአንደኛው ወገን እጅ ለእጅ ይያያዝና አብረው ያድናሉ፣
ƒƒ በክቡ ዙርያ ያሉት በአዳኞች ላለመነካት ወደክቡ ውስጥ በመግባትም ሆነ በሰውነት አቅጣጫን በማስለወጥ ይችላሉ።
አዳኞቹ እጃቸውን መላቀቅ አይፈቀድላቸውም። አዳኞቹ አራት ሲሆኑ ከሁለት በመከፈል እንዲያድኑ ማድረግ፣
ƒƒ በአዳኞች ሳይነካ በመጨረሽ የቀረው ተማሪ አሸናፊ እንዲሆን ማድረግ፣
ƒƒ ከተማሪዎች የእድገት ደረጃና አካል ብቃት ደረጃ መሰረት ጨዋታውን በመደጋገም እንዲጫዎቱ እድል መስጠት፣
ƒƒ በመቀጠልም የሰውነተ ማቀዝቀዣ እና ማሳሳቢያ እንቅስቃሴ እንዲያደርጉ ማድረግ፣
ƒƒ የተወሰነ ጊዜ በመስጠት ጨዋታው ማሕበራዊ ግንዛቤን እና የመግባባት ክህሎት ከማጎልበት ጋር የነበራቸውን ሚናና
ስሜት እንዲገልፁ ማበረታታት፣
ƒƒ የእለቱ ትምህርት ምን ያህል እንዳዝናናቸውና እንደሳባቸው እንዲሁም ለምን ጥቅም እንደሆነ እንዲገልጹ ማድረግና
ማጠናቀቅ፣

ክትትልና ግምገማ:-
ƒƒ በጨዋታው ማሕበራዊ ግንዛቤን እና የመግባባት ክህሎት ጋር ያለውን ግንኙነት ሲገልጹና በጨዋታው ሲያንፀባርቁ
በምልከታና በጥያቄና መልስ ማረጋገጥ፣
ƒƒ በጨዋታው ምን ያህል ስሜታቸውን እንደሚገልፁ በምልከታ ማረጋገጥ፣

2.2.2 ገመድ ጉተታ ጨዋታ (1 ክ/ጊዜ)

ዝርዝር ዓላማ:-ተማሪዎች ይህንን ርዕስ ከተማሩ በኋላ፦
ƒƒ ጨዋታውበአብሮነት ከመስራት ጋር ያለውን ግንኙነት ያብራራሉ፤
ƒƒ በጨዋታውይደሰታሉ።
ƒƒ አብሮ የመስራትና የመተጋገዝ ክህሎታቸውን ይፈትሻሉ።
ƒƒ በምክንያት የመወሰንክህሎታቸውንያዳብራሉ።
ƒƒ ስሜትን የመቆጣጠር አቅማቸውን ያሳያሉ።

የመማር-ማስተማር መርጃ መሣሪያዎች እና ሥፍራዎች:-

መርጃ መሣሪያዎች:- መስመር ማስመሪያ ኖራ ወይም አመድ ወይም ዘንግ እንጨት፤ ከ40 ሜትር የማያንስ ወፈር ያል
ገመድ፣
ሥፍራ:- የተግባር ትምህርት የሚሰጥበት የስፖርት ሜዳ፣
የጤናና ሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ~ 8ኛ ክፍል ~ የመምህር መምሪያ ~ 11
ምዕራፍ 2 ማሕበራዊ መስተጋብር እና ስሜታዊነት በሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት

የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል:-

ƒƒ የባለፈውን ትምህርት በጥያቄና መልስ መከለስ፣
ƒƒ የእለቱን ትምህርት ርዕሰና አላማ ለተማሪዎች ማስተዋወቅ፣
ƒƒ ተማሪዎች በአራት ወይም በአምስት ምድብ በማደራጀት የሰውነት ማሟሟቂያ እንቅስቃሴዎች ከቀላል እንቅስቃሴዎች
በመጀመር ለዋናው የእለቱ ተግባር ቅድመ ዝግጅት እንዲያደርጉ ማበረታታት፣
ƒƒ ተማሪዎችን እንደችሎታቸውና ፍላጎታቸው ሦስት ሦስት ወይም አራት የቡድን አባላት ያላቸው ቡድኖችን ማደራጀት፣

በመማሪያ መጽሀፉ ላይ በተገለፀው መሰረት ጨዋታውን እንዲጫዎቱ ማበረታታት፣

በጨዋታ ጊዜ በአብሮነት መተጋገዛቸውን በመከታተል ማበረታታት፤ ስሜታዊነትና ራስን አለመግዛት ካለ ማረምና መምከር
ያስፈልጋል፤
ƒƒ ከተማሪዎች የእድገት እና አካል ብቃት ደረጃ መሰረት ጨዋታውን በመደጋገም እንዲጫዎቱ እድል መስጠት፣
ƒƒ በመቀጠልም የሰውነት ማቀዝቀዣ እና ማሳሳቢያ እንቅስቃሴ እንዲያደርጉ ማድረግ፣
ƒƒ የተወሰነ ጊዜ በመስጠት ጨዋታው ማሕበራዊ ግንዛቤን እና የመግባባት ክህሎት ከማጎልበት ጋር የነበራቸውን ሚናና
ስሜት እንዲገልፁ ማበረታታት፣
ƒƒ በመማሪያ መፅሀፉ የተቀመጠውን ተግባር እንዲሰሩ ማበረታታት፣
ƒƒ የእለቱ ትምህርት ምን ያህል እንዳዝናናቸውና እንደሳባቸው እንዲሁም ለምን ጥቅም እንደሆነ እንዲገልጹ ማድረግና
ማጠናቀቅ፣

ክትትልና ግምገማ:-
ƒƒ በጨዋታው ማሕበራዊ ግንዛቤን እና የመግባባት ክህሎት ጋር ያለውን ግንኙነት ሲገልጹና በጨዋታው ሲያንፀባርቁ
በምልከታና በጥያቄና መልስ ማረጋገጥ፣

2.3. ሀላፊነት የተሞላበት ውሳኔ የመወሰን ክህሎትን ለማዳበር የሚረዱ

(2 ክ/ጊዜ)
አካላዊ እንቅስቃሴዎች

2.3.1 የሁለት ቤት ጨዋታ (1 ክ/ጊዜ)

ዝርዝር ዓላማ:-ተማሪዎች ይህንን ርዕስ ከተማሩ በኋላ፦
ƒƒ ጨዋታው ሀላፊነት የተሞላበት ውሳኔ የመወሰን ክህሎትጋር ያለውን ግንኙነት በትክክል ያበራራሉ።
ƒƒ የሁለት ቤት ጨዋታ ሲጫዎቱ ራሳቸውን በማወቅና በአግባቡ ለመምራት ተነሳሽነት ያሳያሉ።
ƒƒ የሁለት ቤት ጨዋታ እንቅስቃሴን በትክክል ይሰራሉ።
ƒƒ በጨዋታውይደሰታሉ።

የመማር-ማስተማር መርጃ መሣሪያዎች እና ሥፍራዎች:-

መርጃ መሣሪያዎች:- የእግር ኳስ

ሥፍራ:- የተግባር ትምህርት የሚሰጥበት የስፖርት ሜዳ፣

የጤናና ሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ~ 8ኛ ክፍል ~ የመምህር መምሪያ ~ 12

ምዕራፍ 2 ማሕበራዊ መስተጋብር እና ስሜታዊነት በሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት

የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል:-

ƒƒ ተማሪዎችን በቁመታቸው መሰረት በሁለት ሰልፍ በማሰለፍ ከክፍል ይዞ መውጣት፣
ƒƒ ባለፈው ክፍለ ጊዜ የሰሩት እንቅሴቃሴ ምን ዓይነትና ለምን እንደሚጠቅም እየወጡ እንዲገልጹ ማድረግ፣
ƒƒ የእለቱ እንቅስቀሴ የሁለት ቤት ጨዋታ እንደሆነና በመማሪያ መፅሀፋ በተገለፀው የአጨዋወት ህግ መሰረት እንደሚሰሩ
መግለጽና ከእነሱም የሚጠበቅባቸው ህጉን ጠብቀው በጋራ በመተባበር መስራት መሆኑን መግለጽ፣
ƒƒ ከተማሪዎች የእድገት ደረጃና የአየር ንብረት አንፃር የተመጣጠነ የሰውነት ማሟሟቂያ እና ማሳሰቢያ እንቅስቃሴ
በማሰራት ለተግባሩ ዝግጁ ማድረግ፣
ƒƒ በመማሪያ መፅሀፉ በተገለፀው የጨዋታው ህግና አጨዋወት መሰረት ተማሪዎችን በማደራጀት እንዲጫዎቱ ማድረግ፣
ƒƒ ጨዋታውን ሲያከናዉኑ ማስተካከያና ማበረታቻ መስጠት፣
ƒƒ ከተማሪዎች የእድገት እናየአካል ብቃት ደረጃ መሰረት ጨዋታውን በመደጋገም እንዲጫዎቱ እድል መስጠት፣
ƒƒ በመቀጠልም የሰውነት ማቀዝቀዣ እና ማሳሳቢያ እንቅስቃሴ እንዲያደርጉ ማድረግ፣
ƒƒ የተወሰነ ጊዜ በመስጠት ጨዋታው ሀላፊነት የተሞላበት ውሳኔ የመወሰንከማጎልበት ጋር የነበራቸውን ሚናና ስሜት
እንዲገልፁ ማበረታታት፣
ƒƒ የእለቱ ትምህርት ምን ያህል እንዳዝናናቸውና እንደሳባቸው እንዲሁም ለምን ጥቅም እንደሆነ እንዲገልጹ ማድረግና
ማጠናቀቅ፣

ክትትልና ግምገማ:-
ƒƒ በጨዋታው ሀላፊነት የተሞላበት ውሳኔ የመወሰንክህሎት ጋር ያለውን ግንኙነት ሲገልጹና በጨዋታው ሲያንፀባርቁ
በምልከታና በጥያቄና መልስ ማረጋገጥ፣

2.3.2 የካንጋሮ ሩጫ (1 ክ/ጊዜ)

ዝርዝር ዓላማ:-ተማሪዎች ይህንን ርዕስ ከተማሩ በኋላ፦
ƒƒ ጨዋታው ሀላፊነት የተሞላበት ውሳኔ ከመወሰን እና ስሜትን ከመቆጣጠር አንፃር ያለውን ትስስር ይተነትናሉ።
ƒƒ ጨዋታው ሀላፊነት የተሞላበት ውሳኔ የመወሰንና ከምክንያታዊነት ጋር ያለውን ግንኙነት ያብራራሉ።
ƒƒ የካንጋሮ ሩጫ ጨዋታን እንቅስቃሴ በትክክል ይሰራሉ።

የመማር-ማስተማር መርጃ መሣሪያዎች እና ሥፍራዎች:-

መርጃ መሣሪያዎች:- ግማሽ ሜትር ገመድ (በቁጥር 8)፣ ጆንያ ወይም ኬሻ

ሥፍራ:- የተግባር ትምህርት የሚሰጥበት የስፖርት ሜዳ፣

የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል:-

ƒƒ የመማር-ማስተማርሂደት- በዚሁ ምዕራፍ በንዑስ ርዕስ 2.3.1(የሁለት ቤት ጨዋታ)የተገለፀውን የመማር ማስተማር
ሂደት ይከተሉ፤

የጤናና ሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ~ 8ኛ ክፍል ~ የመምህር መምሪያ ~ 13

ምዕራፍ 2 ማሕበራዊ መስተጋብር እና ስሜታዊነት በሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት

2.4. በጥልቀት የማሰብ ክህሎትን ለማዳበር የሚረዱ አካላዊ

(1 ክ/ጊዜ)
እንቅስቃሴዎች

2.4.1 የክብ ኢላማ (1 ክ/ጊዜ)

ዝርዝር ዓላማ:-ተማሪዎች ይህንን ርዕስ ከተማሩ በኋላ፦
ƒƒ ጨዋታውበጥልቀት የማሰብ ክህሎትጋር ያለውን ግንኙነት በትክክል ያብራራሉ።
ƒƒ የክብ ኢላማ ጨዋታ ሲጫዎቱ ራሳቸውን በማወቅና በጥልቀት የማሰብ ፍላጎታቸውን ያሳያሉ።
ƒƒ የክብ ኢላማ ጨዋታ እንቅስቃሴን በትክክል ይሰራሉ።

የመማር-ማስተማር መርጃ መሣሪያዎች እና ሥፍራዎች:-

መርጃ መሣሪያዎች:- ለስላሳ ኳስ፣ ጠፍጣፋ ድንጋይ፣ እንጨት፣

ሥፍራ:- የተግባር ትምህርት የሚሰጥበት የስፖርት ሜዳ፣

የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል:-

ƒƒ የባለፈውን ትምህርት በጥያቄና መልስ መከለስ፣
ƒƒ የእለቱን ትምህርት ርዕሰና አላማ ለተማሪዎች ማስተዋወቅ፣
ƒƒ ተማሪዎችን በአራት ምድብ በማደራጀት የሰውነት ማሟሟቂያ እንቅስቃሴዎች ከቀላል እንቅስቃሴዎች በመጀመር
ለዋናው የእለቱ ተግባር ቅድመ ዝግጅት እንዲያደርጉ ማበረታታት፣
ƒƒ ሶስት ክቦች ከአንድ የመነሻ ነጥብ ላይ በ1ሜትር፣ በ2ሜትር፣ በ3 ሜትር ስፋት የመጫወቻ ሜዳ ማዘጋጀት፣
ƒƒ በተዘጋጀው የመጫዎቻ ሜዳ ልክ በቡድን በመከፋፈል ከየመጫወቻው ሜዳ ከ15 እስከ 30 ሜትር ርቀት በረድፍ
ማቆምና በየቡድኑ ያሉት ተጫዋቾች ጠፍጣፋ እንጨት(ጠጠር) እንዲይዙ ማድረግ፣
ƒƒ ጨዋታውን ለመጀመር ከየቡድኑ ያሉት ተጫዋቾች በተራ የያዙትን ጠፍጣፋ ጠጠር በመወርወር ክቦቹ ውስጥ ለማሳረፍ
ይሞክራሉ። መስመሩን የነካ ጠፍጣፋ ጠጠር እንደተቃጠለ ተቆጥሮ ለወርዋሪውም ሆነ ለቡድኑ ነጥብ አይሰጥም፣
ƒƒ ጨዋታው ለተወሰነ ጊዜ(ደቂቃ) ወይም ለተወሰነ /ቁጥር/ እያንዳንዱ ተጫዋች እንዲወረውር ማድረግ፣
ƒƒ በመማሪያ መፅሀፉ በተገለጸው መሰረት ውጤት በመያዝ አሸናፊውን ቡድን መለየትና ማበረታታት፣
ƒƒ ጨዋታውን በመደጋገም እንዲጫዎቱ እድል መስጠት፣
ƒƒ በመቀጠልም የሰውነተ ማቀዝቀዣ እና ማሳሳቢያ እንቅስቃሴ እንዲያደርጉ ማድረግ፣
ƒƒ የተወሰነ ጊዜ በመስጠት ጨዋታው ሀላፊነት የተሞላበት ውሳኔ የመወሰንከማጎልበት ጋር የነበራቸውን ሚናና ስሜት
በመማሪያ መፅሀፉ ተግባር ጋር በማገናዘብ እንዲገልፁ ማበረታታት፣
ƒƒ የእለቱ ትምህርት ምን ያህል እንዳዝናናቸውና እንደሳባቸው እንዲሁም ለምን ጥቅም እንደሆነ እንዲገልጹ ማድረግና
ማጠናቀቅ፣

ክትትልና ግምገማ:-
ƒƒ በጨዋታው በጥልቀት የማሰብ ክህሎትጋር ያለውን ግንኙነት ሲገልጹና በጨዋታው ሲያንፀባርቁ በምልከታ፣ በጥያቄና
መልስ ማረጋገጥ፣
የጤናና ሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ~ 8ኛ ክፍል ~ የመምህር መምሪያ ~ 14
ምዕራፍ 2 ማሕበራዊ መስተጋብር እና ስሜታዊነት በሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት

ƒƒ ማሳሰቢያ በመማሪያ መፅሀፉ በስዕል እንደተገለጸው በትልቅ ክብ ውስጥ ስድስት ክቦች በመስራት ለእያንዳንዱ ክብ ቁጥ
በመስጠት ማጫዎት ይቻላል፣

2.5. የመግባባት እና የመተባበር ክህሎትን ለማዳበር የሚረዱ

(2 ክ/ጊዜ)
አካላዊእንቅስቃሴዎች

2.5.1 ኳስ በሳጥን (1 ክ/ጊዜ)

ዝርዝር ዓላማ:-ተማሪዎች ይህንን ርዕስ ከተማሩ በኋላ፦
ƒƒ ኳስ በሳጥን ጨዋታ የመግባባት እና የመተባበር ከህሎትጋር ያለውን ግንኙነት በትክክል ያበራራሉ።
ƒƒ ኳስ በሳጥን ጨዋታ ሲጫዎቱ ራሳቸውን በማወቅና በአግባቡ ለመተባበር ተነሳሽነት ያሳያሉ።
ƒƒ ኳስ በሳጥን ጨዋታ እንቅስቃሴን በትክክል ይሰራሉ።

የመማር-ማስተማር መርጃ መሣሪያዎች እና ሥፍራዎች:-

መርጃ መሣሪያዎች:- ኳስ፣ ካርቶን፣ ሳጥን፣

ሥፍራ:- የተግባር ትምህርት የሚሰጥበት የስፖርት ሜዳ፣

የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል:-

ƒƒ የባለፈውን ትምህርት በጥያቄና መልስ መከለስ፣
ƒƒ የእለቱን ትምህርት ርዕሰና አላማ ለተማሪዎች ማስተዋወቅ፣
ƒƒ ተማሪዎችን በአራት ወይም በስድስት ምድብ በማደራጀት የሰውነት ማሟሟቂያ እንቅስቃሴዎች ከቀላል እንቅስቃሴዎች
በመጀመር ለዋናው የእለቱ ተግባር ቅድመ ዝግጅት እንዲያደርጉ ማበረታታት፣
ƒƒ ተማሪዎች ከእለቱ ተግባር ወይም ትምህርት ጋር ተቀራራቢነት ያለው የሰውነት ማሟሟቂያ እንቅስቃሴ እንዲሰሩ
ማበረታታትና ተማሪዎች እንቅስቃሴዎችን ሲሰሩ በመከታተል ማስተካከያ መስጠት፣
ƒƒ በመማሪያ መፅሀፉ በተገለፀው መሰረት የጨዋታው ህግና አጨዋወት መሰረት ተግባራዊ ማድረግ፣
ƒƒ ጨዋታውን በመደጋገም እንዲጫዎቱ እድል መስጠት፣
ƒƒ በመጨረሻም የሰውነት ማቀዝቀዣ እና ማሳሳቢያ እንቅስቃሴ እንዲያደርጉ ማድረግ፣
ƒƒ የተወሰነ ጊዜ በመስጠት ጨዋታው ሀላፊነት የተሞላበት ውሳኔ የመወሰንከማጎልበት ጋር የነበራቸውን ሚናና ስሜት
እንዲገልፁ ማበረታታት፣
ƒƒ የእለቱ ትምህርት ምን ያህል እንዳዝናናቸውና እንደሳባቸው እንዲሁም ለምን ጥቅም እንደሆነ እንዲገልጹ ማድረግና
ማጠናቀቅ፣

ክትትልና ግምገማ:-
ƒƒ በጨዋታው የመግባባት እና የመተባበር ክህሎትጋር ያለውን ግንኙነት ሲገልጹና በጨዋታው ሲያንፀባርቁ በምልከታና
በጥያቄና መልስ ማረጋገጥ፣

የጤናና ሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ~ 8ኛ ክፍል ~ የመምህር መምሪያ ~ 15

ምዕራፍ 2 ማሕበራዊ መስተጋብር እና ስሜታዊነት በሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት

2.5.2. ልዩ የቅርጫት ኳስ ጨዋታ (1 ክ/ጊዜ)

ዝርዝር ዓላማ:-ተማሪዎች ይህንን ርዕስ ከተማሩ በኋላ፦
ƒƒ ጨዋታውየመግባባት እና የመተባበር ክህሎትጋር ያለውን ግንኙነት በትክክል ያብራራሉ።
ƒƒ ልዩ የቅርጫት ኳስ ጨዋታ ሲጫዎቱ ራሳቸውን በማወቅና በአግባቡ ለመተባበር ተነሳሽነት ያሳያሉ።
ƒƒ ልዩ የቅርጫት ኳስ ጨዋታ እንቅስቃሴን በትክክል ይሰራሉ።

የመማር-ማስተማር መርጃ መሣሪያዎች እና ሥፍራዎች:-

መርጃ መሣሪያዎች:- አግዳሚ ወንበር፣ የቅርጫት ኳስ፣

ሥፍራ:- የተግባር ትምህርት የሚሰጥበት የስፖርት ሜዳ፣

የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል:-

ƒƒ የባለፈውን ትምህርት በጥያቄና መልስ መከለስ፣
ƒƒ የእለቱን ትምህርት ርዕሰና አላማ ለተማሪዎች ማስተዋወቅ፣
ƒƒ ተማሪዎችን በአራት ወይም በስድስት ምድብ በማደራጀት የሰውነት ማሟሟቂያ እንቅስቃሴዎች ከቀላል እንቅስቃሴዎች
በመጀመር ለዋናው የእለቱ ተግባር ቅድመ ዝግጅት እንዲያደርጉ ማበረታታት፣
ƒƒ ተማሪዎች ከእለቱ ተግባር ወይም ትምህርት ጋር ተቀራራቢነት ያለው የሰውነት ማሟሟቂያ እንቅስቃሴ እንዲሰሩ
ማበረታታትና ተማሪዎች እንቅስቃሴዎችን ሲሰሩ በመከታተል ማስተካከያ መስጠት፣
ƒƒ በመማሪያ መፅሀፉ በተገለፀው መሰረት የጨዋታው ህግና አጨዋወት መሰረት ተግባራዊ ማድረግ፣
ƒƒ ጨዋታውን በመደጋገም እንዲጫዎቱ እድል መስጠት፣
ƒƒ በመቀጠልም የሰውነት ማቀዝቀዣ እና ማሳሳቢያ እንቅስቃሴ እንዲያደርጉ ማድረግ፣
ƒƒ የተወሰነ ጊዜ በመስጠት ጨዋታው ሀላፊነት የተሞላበት ውሳኔ የመወሰንከማጎልበት ጋር የነበራቸውን ሚናና ስሜት
እንድሁም በመማሪያ መፅሀፉ በተግባሩ የተጠቀሱትን እንዲገልፁ ማበረታታት፣
ƒƒ የእለቱ ትምህርት ምን ያህል እንዳዝናናቸውና እንደሳባቸው እንዲሁም ለምን ጥቅም እንደሆነ እንዲገልጹ ማድረግና
ማጠናቀቅ፣

ክትትልና ግምገማ:-
ƒƒ በጨዋታው የመግባባት እና የመተባበር ክህሎትጋር ያለውን ግንኙነት ሲገልጹና በጨዋታው ሲያንፀባርቁ በምልከታ፣
በጥያቄና መልስ ማረጋገጥ፣
ƒƒ ማሳሰቢያ:- በዚህ ምእራፍ ስር በመማሪያ መፅሀፉ የተቀመጡትን ተግባሮችና መልመጃዎችን በእያንዳንዱ ጨዋታ
ክፍለጊዜ ታቅዶ ትምህርቱ በሚሰጥበት ጊዜ ነጥቦችን በማካተት ማስተማር ያስፈልጋል፣

የጤናና ሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ~ 8ኛ ክፍል ~ የመምህር መምሪያ ~ 16

ምዕራፍ 3 ጤናና የአካል ብቃት

ምዕራፍ

3 ጤናና የአካል ብቃት

የክፍለ ጊዜ ብዛት፡ 14

አጠቃላይ ዓላማዎች፡

አጠቃላይ ዓላማ:-ተማሪዎች ይህንን ምዕራፍ ተምረው ካጠናቀቁ በኋላ:-

ªªየአካል ብቃትን ማዳበሪያ ልምምዶችንና እንቅስቃሴዎችን ይተነትናሉ::
ªªየአካል ብቃት እንቅስቃሴዎችን ተግባራዊ ያደርጋሉ::
ªªበአካል ብቃት እንቅስቃሴ ለመሳተፍ ፍላጎት ያሳያሉ::
ªªየአበረታች ቅመሞችን (ዶፒንግን) መጠቀም የተከለከለበትን ምክንያት ያውቃሉ::

መግቢያ
ጤና ማለት በበሽታ አለመያዝ ብቻ ሳይሆን በፍፁም የተሟላ የአካል፣ የአዕምሮ፣ የማህበራዊና የስሜት ደህንነት ማለት ነው:: እነዚህን
ለማሟላት ደግሞ የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎችን በትምህርት ቤትም ሆነ በመኖሪያ አካባቢ መስራት ያስፈልጋል::

ጤናን ለመጠበቅና የአካል ብቃትን ለማዳበር እንቅስቃሴዎችን በዘለቄታነት በመደበኛ ፕሮግራም ለመሥራት የሚያስችል የግንዛቤና
የአመለካከት ለውጥ ማምጣት የሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ዋነኛ ግቡ ነው። ስለሆነም ይህንን ግብ ለማሳካት ከታችኛው የክፍል
ደረጃ ጀምሮ የተማሪዎችን የግንዛቤና የመሥራት አቅም ባገናዘበ መልኩ እየተሰጠ መሆኑ ይታወቃል።

ስለሆነም በዚህ ክፍል ደረጃ በምዕራፉ ውስጥ የተካተቱት ንዑስ ርዕሶች የአካል ብቃትን ማዳበሪያ መንገዶች፣ የልብና የአተነፋፈስ
ሥርዓት ብርታት፣ የጡንቻ ብርታት እና የመተጣጠፍ ችሎታ የሚያዳብሩ እንቅስቃሴዎችንተማሪዎች እንዲለዩ፣ እንዲያነጻጽሩና
እንዲለማመዱ በማድረግ ላይ ነው። እንዲሁም የስፖርትአበረታች ቅመሞችን (ዶፒንግን) መከላከል ላይ ያተኮረ ነው። የአካል
ብቃትእንቅስቃሴዎችን በምናሰራበት ጊዜ የተሳታፊዎቹን ዕድሜ፣ ፆታና የግል ተሰጥኦ ሁኔታ ግምት ውስጥ ማስገባት ያስፈልጋል።

3.1. የአካል ብቃትን የሚያዳብሩ እንቅስቃሴ አይነቶች (2 ክ/ጊዜ)

ዝርዝር ዓላማ:-ተማሪዎች ይህንን ርዕስ ተምረው ካጠናቀቁበኋላ:-
ƒƒ የአካል ብቃትን እንዴት ማጎልበት እንደሚቻል በሚገባ ያብራራሉ።
ƒƒ የአካል ብቃትን ለማሻሻል የምንጠቀምባቸውን የልምምድ አይነቶች ይዘረዝራሉ።
ƒƒ የአየራዊና ኢ-አየራዊ ልምምዶችን ልዮነት በመገንዘብ በአካል ብቃት ልምምድ ጊዜ ተግባራዊ ለማድረግ ቁርጠኛ ይሆናሉ።

የጤናና ሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ~ 8ኛ ክፍል ~ የመምህር መምሪያ ~ 17

ምዕራፍ 3 ጤናና የአካል ብቃት

መሠረታዊ ጽንሰ-ሀሳብ (ለመምህሩ/ሯ የመነሻ ሀሳብ):-

አንድ አትሌት ወይም ግለሰብ ልምምድ ሲያደረግ ሁለት የልምምድ አይነቶችን ሊከተል ይችላል:: እነሱም:-

ሀ. አየራዊ ወይም ኦክስጅን በመጠቀም ልምምድ (Aerobic training)

ለ. ኢ- አየራዊ ወይም ያለ ኦክስጅን ልምምድ (Anaerobic training) ናቸው።
ሀ. አየራዊ ኦክስጅን በመጠቀም ልምምድ (Aerobic training)

የአየራዊ ወይም አክስጅንን በመጠቀም ልምምድ ማለት ቀለል ባለ የልምምድ ጫና የሚከናወኑ አካላዊ እንቅስቃሴዎችን የሚያካትት
ሲሆን በእንቅስቃሴዎቹ አማካኝነት የስርአተ-ትንፈሣ፣ የልብና የደም ዝውውር ስርአትን በማሻሻል ኦክስጅንና ምግብ (ግሉኮስ/
Glucose) በፍጥነትና በበቂ ሁኔታ ወደሁሉም የሰውነት ክፍል እንዲደርሰ ከማስቻሉም በላይ በሰውነታችን የውስጥ አሰራር ምክንያት
የሚጠራቀሙ ቆሻሻዎችን ለምሳሌ ላብና የተቃጠለ አየርን(ካርቦንዳይ ኦክሳድ (CO2) ለማስወገድ ይጠቅማል።

የአየራዊ እንቅስቃሴ የሚከናወነው የእንቅስቃሴውን ክብደት በመቀነስ ለረጅም ጊዜ በእንቅስቃሴው ውስጥ የምናሳልፈውን የጊዜ
ቆይታ በመጨመር የሚከናወን ተግባር ነው። ተግባሮችም እርምጃ፣ ረጅምርቀት ሩጫ፤ ሶምሶማ እና በዝግታ ብስክሌት መንዳት
ከሚጠቀሱት ውስጥ ጥቂቶቹ ናቸው።

ለ. ኢ- አየራዊ ልምምድ ወይም ያለ ኦክስጅን ልምምድ (Anaerobic training)

ኢ- አየራዊ ልምምድ (Anaerobic training) ከአየራዊ የልምምድ (Aerobic training) አይነት ተቃራኒ ሲሆን ቃል በቃል
ስንተረጉመው ያለኦክስጅን ወይም ኦክስጅን ሣንጠቀም በፍጥነት ሊጠናቀቁ የሚችሉ የአጭር ጊዜ እንቅስቃሴዎችን የሚያጠቃልል
የልምምድ ዓይነት ነው።

አየራዊ እንቅስቃሴዎች የተሳታፊዎችን (የአትሌቶችን) ብርታትን ለማሳደግ ተመራጭ የእንቅስቃሴ ዓይቶች ሲሆኑ ኢ-አየራዊ
እንቅስቃሴዎች በአንጻሩ ጥንካሬን፣ ፍጥነትን፣ ጉልበትን ወይም ሀይልን እንዲሁም ጡንቻን ለማዳበር ተመራጭ ናቸው። እነዚህ
ክህሎቶች (ጥንካሬ፣ ፍጥነት፣ ጉልበት ወይም ሀይል) የአትሌቶችን ኢ-አየራዊ ልምምድ (Anaerobic training) የመስራት
ችሎታቸውን ወይም ብቃታቸውን የበለጠ እንዲያሳድጉ ይረዷቸዋል።

ኢ-አየራዊልምምድ (Anaerobic training) የሚያካትታቸው የእንቅስቃሴ አይነቶች የ30 ሜትር የፍነት ሩጫ፤ 100 ሜትር ሩጫ፤100
ሜትር የዉሀ ዋና እና ሌሎችም ይካተታሉ።

የመማር-ማስተማር መርጃ መሣሪያዎች እና ሥፍራዎች:-

መርጃ መሣሪያዎች:- የአካል ብቃት እንቅስቃሴ አይነቶችንየሚገልጹ ፖስተሮች፤ ስዕሎች፤ ፊልሞች፤ ፎቶዎችና ጽሁፎች
ሥፍራ:-የንድፈ ሀሳብ ትምህርት በሚሰጥበት ክፍል ውስጥ፣

የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል:-

ƒƒ ያለፈውን ትምህርት በጥያቄና መልስ መከለስ፣
ƒƒ የዕለቱን ትምህርት ርዕስና አላማዎቹን ማስተዋወቅ፣
ƒƒ ተማሪዎች በየግላቸው በመሆን አዕምሮ ማሰላሰልን በመጠቀም የአካል ብቃት ምን ማለት እንደሆነና የአካል ብቃታቸውን
እንዴት ማዳበር እንደሚችሉ ጥያቄ መጠየቅ፣
ƒƒ ለተጠየቁት ጥያቄ በየግላቸው እንዲያንፀባርቁ ማበረታታትና የአካል ብቃትን እንዴት ማሻሻል እንደሚቻል አጭር
ማብራሪያ መስጠት፣

የጤናና ሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ~ 8ኛ ክፍል ~ የመምህር መምሪያ ~ 18

ምዕራፍ 3 ጤናና የአካል ብቃት

ƒƒ ተማሪዎችን በጥንድ ወይም በትንሽ ቡድን በማደራጀት የአካል ብቃትን የሚያጎለብቱ እንቅስቃሴዎች ከኦክስጅን
አጠቃቀምና ጫና አንፃር በስንት አይነት እንደሚከፈሉና ልዮነታቸውን በስፋት በምሳሌ እንዲያብራሩ ማበረታታት፣
ƒƒ ተማሪዎች ሀሳብ የተለዋወጡበትን በጥያቄና መልስ እንዲያቀርቡ ማድረግ፣
ƒƒ ተማሪዎች ከገለጹት አንጻር የሚገናኙ ሀሳቦችን በመጥቀስ ስለአየራዊና ኢ-አየራዊ የልምምድ አይነቶች የመግቢያ ሀሳብ
በመስጠት የሚቀጥለውን ተግባር እንድሰሩ ማበረታታት፣
ƒƒ አየራዊ የልምምድእንቅስቃሴዎች ማን ማን እንደሆኑና እንዴት የልብና የአተነፋፈስ ብርታትን እንደሚያዳብሩ
እንዲጠያየቁ ማመቻቸት፣
ƒƒ ተማሪዎች የተወያዮበትን እንዲያቀርቡ ማበረታታትና ከገለጹት አንጻር አየራዊ የልምምድእንቅስቃሴዎች ዓይነቶችንና
የልብና የአተነፋፈስ ብርታትን እንዴት እንደሚያዳብሩ አጭር ማብራሪያ መስጠት፣
ƒƒ ተማሪዎችን በጥንድ ወይም በግል ሆነው ኢ-አየራዊ ልምምድጥንካሬን፣ ፍጥነትን፣ ጉልበትን ወይም ሃይልን ለማዳበር
እንዴት ተመራጭ እንደሆነ ምክንያቱን እንዲያብራሩ ማበረታታት፣
ƒƒ በጥያቄና መልስ ሀሳባቸውን በመቀበል ሀሳቡን በአጭሩ መግለፅና ያልገባቸው ካለ ጥያቄ እንዲጠይቁ እድል መስጠት፣
ƒƒ ተማሪዎች የተማሩትን ትምህርት መረዳታቸውን ለማረጋገጥ የቃል ጥያቄ በመጠየቅ ማረጋገጥ፣
ƒƒ ይህ ርዕስ ለሁለት ክፍለጊዜ ስለሆነ ከላይ የተጠቀሱትን ሀሳቦች ለመነሻነት በመጠቀም ለሁለት ክፍለጊዜ የሚሆን
ትምህርት ማዘጋጀት ይቻላል።

ክትትልና ግምገማ:-
ƒƒ የእለቱን ትምህርት ዝርዝር አላማዎች በትክክል መተግበሩን በጥያቄና መልስ፣ በሚያቀርቡት ውይይት እንዲሁም
ጓደኞቻቸው በሚያስተካክሏቸው ሀሳብ መሰረት መገምገም ይቻላል።

3.2 የልብና የአተነፋፈስ ሥርዓት ብርታት የሚያዳብሩ እንቅስቃሴዎች (4 ክ/ጊዜ)

ዝርዝር ዓላማ:-ተማሪዎች ይህንን ርዕስ ተምረው ካጠናቀቁበኋላ:-
ƒƒ የልብና የአተነፋፈስ ሥርዓት ብርታትን ትርጉም በትክክል ይገልጻሉ።
ƒƒ የልብና የአተነፋፈስ ሥርዓትብርታትን ለማዳበር ጠቃሚ ከሆኑ እንቅስቃሴዎች መካከል ቢያንስ አራቱን ይዘረዝራሉ።
ƒƒ አየራዊ እንቅስቃሴዎች የልብና አተነፋፈስሥርዓት ብርታትን እንደሚያዳብሩ በሚገባ ያብራራሉ።
ƒƒ የልብና አተነፋፈስ ሥርዓትብርታትን የሚያዳብሩ የተለያዮ እንቅስቃሴዎችን በደረጃቸው በሚመጥን ሁኔታ በተግባር
ይሰራሉ።
ƒƒ የልብና የአተነፋፈስ ሥርዓትብርታትን የሚያዳብሩ እንቅስቃሴዎችን በፍላጎት ይሰራሉ።

መሠረታዊ ጽንሰ-ሀሳብ (ለመምህሩ/ሯ የመነሻ ሀሳብ):-

ƒƒ በመማሪያ መጽሐፉ የተጠቀሰው ጽንሰ-ሀሳብ በቂ ነው ተብሎ ይገመታል::

የመማር-ማስተማር መርጃ መሣሪያዎች እና ሥፍራዎች:-

መርጃ መሣሪያዎች:-
ƒƒ የልብና የአተነፋፈስ ሥርዓትብርታት ምን እንደሆነና ይህን ለማዳበር የሚሰሩ እንቅስቃሴዎችን የሚገልጹ ፖስተሮች፤
ስዕሎች፤ ፊልሞች፤ ፎቶዎችና ጽሁፎች፤
የጤናና ሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ~ 8ኛ ክፍል ~ የመምህር መምሪያ ~ 19
ምዕራፍ 3 ጤናና የአካል ብቃት

ƒƒ የመዝለያ ገመዶች፤ ኮን ወይም ምልክቶች

ƒƒ ሳጥን፤

ሥፍራ:-የተግባር ትምህርት የሚሰጥበት ሜዳ፣

የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል:-

ƒƒ ያለፈውን ትምህርት በጥያቄና መልስ መከለስ፣
ƒƒ የዕለቱን ትምህርት ርዕስና አላማዎቹን ማስተዋወቅ፣
ƒƒ የልብና የአተነፋፈስ ሥርዓትብርታት ምን ማለት እንደሆነና ጤናን ለመጠበቅ ያለውን አስተዋጽዖ ከአሁን በፊት በ7ኛ
ክፍል ከተማሩት ጋር በማገናዘብ በጥያቄና መልስ ተግባራዊ ማድረግ፤
ƒƒ ተማሪዎችን በሦስት በሦስት በማደራጀት የልብና የአተነፋፈስ ሥርዓትብርታት የሚያዳብሩ እንቅስቃሴዎችን እንዲዘረዝሩ
ማበረታታት፤
ƒƒ ተማሪዎች ከሰጡት ሀሳብ በመነሳት የልብና የአተነፋፈስ ሥርዓትብርታት የሚያዳብሩ እንቅስቃሴዎችበዚህ ክፍል
የሚማሯቸው በቦታ ላይ መሮጥ፤በመሰናክሎች መካከል በዚግዛግ መሮጥ፤ ገመድ መዝለል፤ ቁጠጥ ከማለት ጀምሮ
ወደላይ መዝለል እና የምት አየራዊ እንቅስቃሴዎች (Rhythmic Aerobic exercise) በመግለፅ ማበረታታት፤
ƒƒ ተማሪዎች የተማሩትን ትምህርት መረዳታቸውን ለማረጋገጥ የቃል ጥያቄበመጠየቅ ማረጋገጥ፤
ƒƒ ይህ ርዕስ ለአራት ክፍለ ጊዜ ስለሆነ ጽንሰ ሀሳቡንና ተግባሩን በማቀናጀት በመማሪያ መጽሀፍ የተጠቀሱትን በቦታ ላይ
ሩጫ፤በመሰናክሎች መካከል በዚግዛግ መሮጥ፤ ገመድ መዝለልእና ቁጠጥ ከማለት ጀምሮ ወደላይ መዝለል እና የምት
አየራዊ እንቅስቃሴዎችማስተማርያስፈልጋል።

1. በቦታ ላይ ሩጫ
ƒƒ በቦታ ላይ ሩጫ በዚህ የክፍል ደረጃ የአንድ ክፍለ ጊዜ ብቸኛ ይዘት ሆኖ አይዘጋጅም። ከሌሎች የተግባራዊ ትምህርት
ይዘቶች ጋር በማቀናጀት ተካቶ ተማሪዎች ለተወሰኑ ደቂቃዎች የሚሰሩት ይሆናል፤ ነገር ግን የዕለቱ ትምህርት አንዱ
ዓላማ የልብና የአተነፋፈስ ሥርዓት ብርታት ማዳበር በሆነበት ጊዜ በቦታ ላይ ሩጫ ሆነ በመሰናክሎች መካከል መሮጥ፤
ገመድ መዝለል፤ቁጢጥ ከማለት ጀምሮ ወደላይ መዝለልእንደአንድ ይዘት ሆኖ ሊካተቱይችላሉ::
ƒƒ የባለፈውን ክፍለ ጊዜ ትምህርት ተማሪዎች እንዲያስታውሱ ማበረታታት፤
ƒƒ የእለቱን ትምህርት ርዕሰና አላማ ለተማሪዎች ማስተዋወቅ፤
ƒƒ በቦታ ላይ የመሮጥ እንቅስቃሴ በቀላሉ የሚከናወን፣ ቦታ የማይወስድ እና የልብና የደም ዝውውር ብርታትን ለማዳበር
ጠቃሚ ከሆኑት እንቅስቃሴዎች አንዱ መሆኑን ማስረዳት፤
ƒƒ እንደክፍሉ ተማሪዎች ቁጥር ብዛት ተማሪዎችን ከ3 እሰከ 5 ረድፍ በማሰለፍ የተግባር ትምህርት ለመማር የተሟላ
የስፖርት ትጥቅ መልበሳቸውንና ጤንነታቸው የተሟላ መሆኑን ማረጋገጥ፤
ƒƒ ተማሪዎች በተሰለፍበት ረድፍ(ቡድን) አጠቃላይና ውስን የሰውነት ማሟሟቂያ እንዲሰሩ ማበረታታትና ድጋፍ
ማድረግ፤
ƒƒ በቦታ ላይ ሩጫ የሚሮጡበት ሜዳ የተስተካከለና አመች መሆኑን በማረጋገጥ አሯሯጡን በቅድሚያ ማሳየትና በዝግታ
ጀምረው ቀስ በቀስ ፍጥነት እየጨመሩ እንዲሮጡ ማበረታታት፤
ƒƒ እንቅስቃሴውን ሲሰሩ የእግሮችና የእጆች የተቀናጀ እንቅስቃሴ መኖሩን እንዲሁም ከወገብ በላይ ያለው ሰውነት
አቀማመጥ ትክክል መሆኑን ማረጋገጥና ማስተካከያ መስጠት፤

የጤናና ሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ~ 8ኛ ክፍል ~ የመምህር መምሪያ ~ 20

ምዕራፍ 3 ጤናና የአካል ብቃት

ƒƒ ትክክለኛ በቦታ ላይ አሯሯጥን ሁሉም ተማሪዎች በሚገባ መሥራት ከቻሉ በኋላ ትኩረትን ፍጥነትን ተቆጣጥሮ ለረዥም
ደቂቃ መሥራት መቻላቸው ላይ ማድረግ እንዳለባቸው ማስገንዘብ፤
ƒƒ በቦታ ላይ ሩጫውን በአንድ ጊዜ በተከታታይ ማሰራት ሳይሆን በመካከል የእርምጃን እንቅስቃሴ እየሰሩ እንዲያርፉ
ማድረግ ያስፈልጋል፤
ƒƒ ከወገብ በታች የአካል ጉዳት ካለባቸውና እንቅስቃሴ ከሚከለክላቸው ተማሪዎች በስተቀር በአብዛኛው የአካል ጉዳተኛ
ተማሪዎች በዚህ እንቅስቃሴ መሣተፍና በትክክል መሥራት እንዲችሉ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ ተገቢውን ድጋፍ ማድረግ
ያስፈልጋል፤
ƒƒ በመጨረሻም የሰውነት ማቀዝቀ¹ እንቅስቃሴ በየቡድናቸው እንዲሰሩ ማበረታታትና በእለቱ ትምህርት እንቅስቃሴያቸውን
አስመልክቶ ደረጃቸውን መግለፅና ለሚቀጥለው ማሻሻል እንደሚኖርባቸው ማሳሰብ።

ክትትልና ግምገማ:-
ƒƒ ተማሪዎች እንቅስቃሴዎችን ሲሰሩ በንቃት እየተሣተፉ ለመሆናቸው በምልከታ ማረጋገጥ፤
ƒƒ የእለቱን ትምህርት ዝርዝር አላማዎች በትክክል መተግበሩን በጥያቄና መልስ፤ በምልከታ እንዲሁም ጓደኞቻቸው
በሚያስተካክሏቸው መሰረት መገምገም ይቻላል።

2. በመሰናክሎች መካከል በዚግዛግ መሮጥ

ƒƒ የባለፈውን ክፍለ ጊዜ ትምህርት ተማሪዎች እንዲያስታውሱ ማበረታታት፤
ƒƒ የእለቱን ትምህርት ርዕሰና አላማ ለተማሪዎች ማስተዋወቅ፤
ƒƒ ተማሪዎች በቦታ ላይ ሩጫን ሲሮጡ በተደራጁበት በማሰለፍ የተግባር ትምህርት ለመማር የተሟላ የስፖርት ትጥቅ
መልበሳቸውንና ጤንነታቸው የተሟላ መሆኑን ማረጋገጥ፤
ƒƒ ተማሪዎች በተሰለፍበት ረድፍ (ቡድን)አጠቃላይና ውስን የሰውነት ማሟሟቂያ እንዲሰሩ ማበረታታት፤
ƒƒ ተማሪዎችን በተዘጋጀው በዚግዛግ የመሮጫ ምልክቶች መሰረት ማደራጀትና በመሰናክሎች መካከል በሶምሶማና
በፍጥነት የመሮጥ እንቅስቃሴ ከታች ክፍል ጀምረው እንደተማሩት በማስታወስ የእንቅስቃሴውን ጠቀሜታና እንዴት
እንደሚሰራ እንዲያብራሩ በመጠየቅ በአጭሩ መወያየትና ፈቃደኛ የሆኑ ተማሪዎች እንቅስቃሴውን ሰርተው እንዲያሳዮ
ማበረታታት፤
ƒƒ የክፍሉን ተማሪዎች በሁለት ሜትር ርቀት በመስመር በተደረደሩ የመሰናክል መሮጫ በእያንዳንዱ መስመር ትይዩ ከ6
ሜትር ርቀት በኋላ እንዲቆሙ ማድረግና መሰናክሎች መሀል በዚግዛግ በሶምሶማ መሮጥን በየረድፋቸው ተራቸውን
ጠብቀው እንዲለማመዱ ማበረታታት፤ የሚቀመጡት የመሰናክሎች ብዛት የተማሪዎችን የእድገት ደረጃ ባገናዘበ መልኩ
ከ6 እስክ 10 ምልክቶች ሊሆኑ ይችላሉ፤
ƒƒ በየእንቅስቃሴው መካከል እረፍት እየወሰዱ በመደጋገም እንዲለማመዱ ማበረታታት፤
ƒƒ እንቅስቃሴውን በውድድር መልክ በማድረግ ማለማመድ ይቻላል፤
ƒƒ በዚግዛግ ሩጫ ላይ ግጭት እንዳይፈጠር ቀጣዮቹ የሚሮጡት የመጀመሪያዎች ደርሰው ከተመለሱ በኋላ መሆኑን
ማስገንዘብ ያስፈልጋል፤
ƒƒ ከወገብ በታች የአካል ጉዳት ካለባቸውና እንቅስቃሴ ከሚከለክላቸው ተማሪዎች በስተቀር በአብዛኛው የአካል ጉዳተኛ
ተማሪዎች በዚህ እንቅስቃሴ መሣተፍና በትክክል መሥራት እንዲችሉ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ ተገቢውን ድጋፍ ማድረግ
ያስፈልጋል፤

የጤናና ሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ~ 8ኛ ክፍል ~ የመምህር መምሪያ ~ 21

ምዕራፍ 3 ጤናና የአካል ብቃት

ƒƒ በመጨረሻም የሰውነት ማቀዝቀ¹ እንቅስቃሴ በየቡድናቸው እንዲሰሩ ማበረታታትና በእለቱ ትምህርት እንቅስቃሴያቸውን
አስመልክቶ ደረጃቸውን መግለፅና ለሚቀጥለው ማሻሻል እንደሚኖርባቸው ማሳሰብ::

ክትትልና ግምገማ:-
ƒƒ ተማሪዎች በእንቅስቃሴዎች በንቃት እየተሣተፉ ለመሆናቸው በምልከታ ማረጋገጥ፤
ƒƒ በእንቅስቃሴው ጊዜ ትክክለኛ አሯሯጥ መሮጣቸውን በምልከታ መከታተልና እርማት መስጠት፤
ƒƒ የእለቱን ትምህርት ዝርዝር አላማዎች በትክክል መተግበሩን በጥያቄና መልስ፤ በምልከታ እንዲሁም ጓደኞቻቸው
በሚያስተካክሏቸው መሰረት መገምገም ይቻላል::

3.ገመድ መዝለል
ƒƒ የባለፈውን ክፍለ ጊዜ ትምህርት ተማሪዎች እንዲያስታውሱ ማበረታታት፤
ƒƒ የእለቱን ትምህርት ርዕሰና አላማ ለተማሪዎች ማስተዋወቅ፤
ƒƒ ተማሪዎች በቦታ ላይ ሩጫን ሲሮጡ በተደራጁበት በማሰለፍ የተግባር ትምህርት ለመማር የተሟላ የስፖርት ትጥቅ
መልበሳቸውንና ጤንነታቸው የተሟላ መሆኑን ማረጋገጥ፤
ƒƒ ተማሪዎች በተሰለፉበት ረድፍ (ቡድን) አጠቃላይና ውስን የሰውነት ማሟሟቂያ እንዲሰሩ ማበረታታትና በተለይ
በገመድ ዝላይ ወቅት ጫናው የሚያርፈው በጉልበት፣ በቁርጭምጭሚት፣ በትከሻ መገጣጠሚዎችና በእጅ አጥቆች ላይ
በመሆኑ በልዩ የሰውነት ማሟሟቂያ ወቅት እነዚህን መገጣጠሚያዎች ለማዘጋጀት ትኩረት ማድረግ ያስፈልጋል፤
ƒƒ ተማሪዎችን እንደ መዝለያ ገመድ ብዛት በግል ወይም በጥንድ ካልሆነም በቡድን አድርጎ ማደራጀት፤
ƒƒ ገመድ መዝለልን ከአንደኛ ክፍል ጀምሮ ሲሰሩት የነበረ እንቅስቃሴ በመሆኑ ሁሉም ተማሪዎች በቂ ቦታ በመያዝ
በአንድ ላይ ወይም ተራ በተራ ገመዱን ከፊት ወደኋላ በማዞር እንዲሰሩ ማድረግና ያላቸውን ገመድ የመዝለል ልምድ
በመገምገም ግብረ-መልስ መስጠት፤
ƒƒ አንድ አይነት የገመድ ዝላይን እንቅስቃሴ በመስራት እንዳይሰለቹ በእንቅስቃሴው በመደሰት መተባበርን እንዲያጎለብቱ
ፊትና ኋላ በመሆን በጥንድ ገመድ ዝላይ፤ረዥም ገመድ ሌሎች ይዘው ሲያወዛውዙ ሪትም ጠብቆ ረዘም ላለ ጊዜ
መዝለልን ተራ በተራ እንዲለማመዱ ማበረታታት፤
ƒƒ በእያንዳንዱ እንቅስቃሴ መካከል እረፍት እንዲወስዱ በማድረግ ማለማመድ፤
ƒƒ የገመድ ዝላይን ሲሰሩ እግር ከመሬት አነሳሳቸው፣ የእጅ ውዝዋዜና መሬት አስተራረፍ ትክክል ስለመሆኑ መመልከትና
የተወሰኑት ተማሪዎች ሲሰሩ ሌሎች አስተያየት እንዲሰጡ ማድረግ፤
ƒƒ በተሰጠው አስተያየት መሰረት የገመድ ዝላዮን እንደገና በመደጋገም እንዲለማመዱ ማበረታታት፤
ƒƒ የአካል ጉዳተኛ ተማሪዎች ክፍል ውስጥ ካሉና የአካል ጉዳታቸው በገመድ ዝላዮ ለመሣተፍ የሚፈቅድላቸው ከሆነ ልዩ
ትኩረት አድርጎ እንዲሳተፉ ማድረግ። የማያሳትፋቸው ከሆነ ግን በሌላ ተመሣሣይ እንቅስቃሴ እንዲሳተፉ ማድረግ፤
ƒƒ በመጨረሻም የሰውነት ማቀዝቀ¹ እንቅስቃሴ በየቡድናቸው እንዲሰሩ ማበረታታትና በእለቱ ትምህርት እንቅስቃሴያቸውን
አስመልክቶ ደረጃቸውን መግለፅና ለሚቀጥለው ይህን እንቅስቃሴ ማሻሻል እንደሚኖርባቸው ማሳሰብ::

ክትትልና ግምገማ:-
ƒƒ የእለቱን ትምህርት ዝርዝር አላማዎች በትክክል መተግበሩን በጥያቄና መልስ፤ በምልከታ እንዲሁም ጓደኞቻቸው
በሚያስተካክሏቸው መሰረት መገምገም ይቻላል::

የጤናና ሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ~ 8ኛ ክፍል ~ የመምህር መምሪያ ~ 22

ምዕራፍ 3 ጤናና የአካል ብቃት

4.ቁጢጥ ከማለት ጀምሮ ወደላይ መዝለል

ƒƒ የባለፈውን ክፍለ ጊዜ ትምህርት ተማሪዎች እንዲያስታውሱ ማበረታታት፤
ƒƒ የእለቱን ትምህርት ርዕሰና አላማ ለተማሪዎች ማስተዋወቅ፤
ƒƒ ተማሪዎች ከ4 እሰክ 6 ረድፍ በማሰለፍ የተግባር ትምህርት ለመማር የተሟላ የስፖርት ትጥቅ መልበሳቸውንና
ጤንነታቸው የተሟላ መሆኑን ማረጋገጥ፤
ƒƒ ተማሪዎች በተሰለፍበት ረድፍ (ቡድን) አጠቃላይና ውስን የሰውነት ማሟሟቂያ እንዲሰሩ ማበረታታትና ቁጠጥ
ከማለት ጀምሮ ወደላይ በሚዘሉበት ወቅት ጫናው የሚያርፈው በጉልበት፣ በቁርጭምጭሚትና በእግር ጡንቻዎች
ላይ ስለሆነ በልዩ የሰውነት ማሟሟቂያ ወቅት እነዚህን የሰውነት ክፍሎች ለማዘጋጀት ትኩረት ማድረግ ያስፈልጋል፤
ƒƒ ተማሪዎች በተሰለፍበት ረድፍ (ቡድን) በአሉበት ቦታ ላይ ከጉልበታቸው ትንሽ ሸብረክ በማለት ነጠር ነጠር እያሉ
እጃቸውንና እግራቸውን በማቀናጀት እንዲዘሉ ማበረታታት፤
ƒƒ ከአሁን በፊት 7ኛ ክፍል ከተማሩት ይህ እንቅስቃሴ የሚለየው የአሰራር ቅድም ተከተሉ ሲሆን በመማሪያ መጽሀፉ ላይ
በስዕል በተገለፀው መሰረት መጀመሪያ ቁጢጥ ማለት ከዚያም ሁለቱንም እግር ወደኋላ በመዘርጋት በፑሽ አፕ አሰራር
መሆንና ሁሉንም የሰውነት ክፍል በማስተባበር ወደላይ መዝለል ነው፤
ƒƒ ቁጠጥ ከማለት ጀምሮ ወደላይ መዝለልበተግባር መሥራት የሚችሉ ተማሪዎች ለክፍሉ እንዲያሳዩ መጠየቅና ሁሉም
አሰራራቸውን እንዲያዮ ማበረታታት፤
ƒƒ
ƒƒ ሁሉም የክፍሉ ተማሪዎች በቂ ቦታ እንዲይዙ ማድረግና እንቅስቃሴውን በተመሳሳይ አንድ ላይ እንዲሰሩ ማበረታታት፤
ƒƒ በመካከል እረፍት በመስጠት የእንቅስቃሴውን ድግግሞሽ በመጨመር እንዲለማመዱ ማበረታታት፤
ƒƒ የአካል ጉዳተኛ ተማሪዎች ክፍል ውስጥ ካሉና የአካል ጉዳታቸው ቁጠጥ ከማለት ጀምሮ ወደላይ መዝለልን ለመሣተፍ
የሚፈቅድላቸው ከሆነ ልዩ ትኩረት አድርጎ እንዲሳተፉ ማድረግ፤ የማያሳትፋቸው ከሆነ ግን በሌላ ተመሣሣይ
እንቅስቃሴ እንዲሳተፉ ማድረግ፤
ƒƒ በመጨረሻም የሰውነት ማቀዝቀ¹ እንቅስቃሴ በየቡድናቸው እንዲሰሩ ማበረታታትና በእለቱ ትምህርት እንቅስቃሴያቸውን
አስመልክቶ ደረጃቸውን መግለፅና ለሚቀጥለው ይህን እንቅስቃሴ ማሻሻል እንደሚኖርባቸው ማሳሰብ፤
ƒƒ የምት አየራዊ እንቅስቃሴዎች (Rhythmic Aerobic exercise) ምን ማለት እንደሆነና እንዴት እንደሚሰራ ከተለያዮ
ድህረ-ገጾች (ከኢንተርኔት) በመፈለግ ለሚቀጥለው ክፍለ ጊዜ የቤት ስራ መስጠት::

ክትትልና ግምገማ:-
ƒƒ የእለቱን ትምህርት ዝርዝር አላማዎች በትክክል መተግበሩን በጥያቄና መልስ፤ በምልከታ እንዲሁም ጓደኞቻቸው
በሚያስተካክሏቸው መሰረት መገምገም ይቻላል::

5.የምት አየራዊ እንቅስቃሴዎች (Rhythmic aerobic exercise)

ƒƒ የባለፈውን ክፍለ ጊዜ ትምህርት ተማሪዎች እንዲያስታውሱ ማበረታታት፤
ƒƒ የእለቱን ትምህርት ርዕሰና አላማ ለተማሪዎች ማስተዋወቅ፤
ƒƒ ተማሪዎች ከ4 እሰክ 6 ረድፍ በማሰለፍ የተግባር ትምህርት ለመማር የተሟላ የስፖርት ትጥቅ መልበሳቸውንና
ጤንነታቸው የተሟላ መሆኑን ማረጋገጥ፤
ƒƒ ተማሪዎች በተሰለፍበት ረድፍ (ቡድን) አጠቃላይና ውስን የሰውነት ማሟሟቂያ እንዲሰሩ ማበረታታት፤

የጤናና ሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ~ 8ኛ ክፍል ~ የመምህር መምሪያ ~ 23

ምዕራፍ 3 ጤናና የአካል ብቃት

ƒƒ የምት አየራዊ እንቅስቃሴዎች ሁሉንም ተማሪዎች በአንድ ላይ የሚያሳትፍ በመሆኑ ለምት አየራዊ እንቅስቃሴ አሰራር
ፍላጎት የሚያሳድሩ ሙዚቃዎችን በመጠቀም ማለማመድ ይቻላል፤
ƒƒ የምት አየራዊ እንቅስቃሴ በአብዛኛው በህብረት የሚሰራ በመሆኑ ሁሉም ተማሪዎች ተሳታፊ መሆናቸውንና ፍላጎታቸውን
በመከታተል አስተያየት መስጠት፤
ƒƒ ተማሪዎችን በተወሰነ ቁጥር በቡድን በመክፈል የቻሉትን ያህል ከሙዚቃው ጋር የሚሄድ የምት አየራዊ እንቅስቃሴ
እንዲለማመዱ ማበረታታት፤
ƒƒ በመካከል እረፍት በመስጠት የእንቅስቃሴውን ድግግሞሽ በመጨመር እንዲለማመዱ ማበረታታት፤
ƒƒ በመጨረሻም የሰውነት ማቀዝቀ¹ እንቅስቃሴ በየቡድናቸው እንዲሰሩ ማበረታታትና በእለቱ ትምህርት እንቅስቃሴያቸውን
አስመልክቶ ያሳዮትን ፍላጎትና ተነሳሽነት መግለፅና ለሚቀጥለው ይህን እንቅስቃሴ በግልም ሆነ በቡድን የአካል
ብቃታቸውን ለማሻሻል መስራት እንዳለባቸው ማሳሰብ፤

ክትትልና ግምገማ:-
ƒƒ የእለቱን ትምህርት ዝርዝር አላማዎች በትክክል መተግበሩን በጥያቄና መልስ፤ በምልከታ እንዲሁም ከጓደኞቻቸው ጋር
በትብብር እንቅስቃሴውን ለመስራት በሚያሳዮት ፍለጎት መሰረት መገምገም ይቻላል::

3.3. የጡንቻ ብርታት የሚያዳብሩ እንቅስቃሴዎች (4 ክ/ጊዜ)

ዝርዝር ዓላማ:-ተማሪዎች ይህንን ርዕስ ተምረው ካጠናቀቁበኋላ:-
ƒƒ የጡንቻ ብርታት ትርጉምን በትክክል ይገልጻሉ::
ƒƒ የጡንቻ ብርታት ለማሻሻል ጠቃሚ የሆኑ ቢያንስ አራት እንቃሴዎችን ይዘረዝራሉ::
ƒƒ የጡንቻ ብርታትን ከሚያዳብሩ እንቅስቃሴዎች መካከል ቢያንስ አራቱን በትክክል ይሰራሉ::
ƒƒ በተመረጡ እንቅስቃሴዎች አማካኝነት የጡንቻ ብርታታቸውን ያሻሽላሉ::
ƒƒ የጡንቻ ብርታትን የሚያዳብሩ እንቅስቃሴዎችን ለመስራትፍላጎት ያሳያሉ::

መሠረታዊ ጽንሰ-ሀሳብ (ለመምህሩ/ሯ የመነሻ ሀሳብ):-

ƒƒ በመማሪያ መጽሐፉ የተጠቀሰው ጽንሰ-ሀሳብ በቂ ነው ተብሎ ይገመታል::

የመማር-ማስተማር መርጃ መሣሪያዎች እና ሥፍራዎች:-

መርጃ መሣሪያዎች:-
ƒƒ የጡንቻ ብርታት ምን እንደሆነና ይህን ለማዳበር የሚሰሩ እንቅስቃሴዎችን የሚገልጹ ፖስተሮች፤ ስዕሎች፤ ፊልሞች፤
ፎቶዎችና ጽሁፎች፤
ƒƒ አግዳሚ ወንበር
ƒƒ ፍራሽ

ሥፍራ:-የተግባር ትምህርት የሚሰጥበት ሜዳ፣

የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል:-

ƒƒ ያለፈውን ትምህርት በጥያቄና መልስ መከለስ፤

የጤናና ሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ~ 8ኛ ክፍል ~ የመምህር መምሪያ ~ 24

ምዕራፍ 3 ጤናና የአካል ብቃት

ƒƒ የዕለቱን ትምህርት ርዕስና አላማዎቹን ማስተዋወቅ፤

ƒƒ የጡንቻ ብርታት ምን ማለት እንደሆነ በጥያቄና መልስ ተግባራዊ ማድረግ፤
ƒƒ ተማሪዎችንጥንድ ጥንድ በማደራጀት የጡንቻ ብርታትን ለማጎልበት የሚያስችሉ እንቅስቃሴዎችን በ7ኛ ክፍል ከተማሩት
ጋር በማገናዘብ እንዲዘረዝሩ ማበረታታት፤
ƒƒ ተማሪዎች ከሰጡት ሀሳብ በመነሳት የጡንቻ ብርታትን ለማጎልበት የሚያስችሉ እንቅስቃሴዎች በዚህ ክፍል የሚማሯቸው
ከወገብ በላይ የሚገኙ ጡንቻዎችን ለማዳበር የሚሰሩ እንቅስቃሴዎች (በፑሽ አፕ አሰራር ሁኔታ በክርን ክብደትን
በመያዝ መቆየት፤ ደረጃ ላይ እጅን ከኋላ በመደገፍ እጅን ወደላይና ወደታች ማድረግ)፤የሆድና የጀርባ ጡንቻዎችን
ለማዳበር የሚሰሩ እንቅስቃሴዎች (v-ቅርፅን መስራት፤ከርል አፕ)፤ ከወገብ በታች የሚገኙ ጡንቻዎችን ለማዳበር
የሚሰሩ እንቅስቃሴዎች (በቦታ ላይ ዝላይ፤ቁጢጥ ከማለት መዝለል) መሆኑን በመግለፅ ማበረታታት፤
ƒƒ ተማሪዎችየተማሩትን ትምህርት መረዳታቸውን ለማረጋገጥ የቃል ጥያቄ በመጠየቅ ማረጋገጥ፤
ƒƒ ይህ ርዕስ ለአራት ክፍለ ጊዜ ስለሆነ ጽንሰ ሀሳቡንና ተግባሩን እንደአመችነቱ በመከፋፈል
ƒƒ ተማሪዎች አዕምሮታዊ፤ አመለካከታዊ እና ክህሎታዊ የባህሪ ፈርጆችን በተሻለ እንዲያዳብሩ በማቀናጀት ማስተማር
ያስፈልጋል። ከዚህ በተጨማሪም ተማሪዎቹ የጡንቻ ብርታትን የሚያዳብሩ እንቅስቃሴዎች በ7ኛ ክፍል ስለተማሩ
ሁለት ወይም ከዚያ በላይ የሆኑትን እንቅስቃሴዎች በጣቢያ የማስተማር ዘዴ በመጠቀም ተግባራዊ ማድረግ ይቻላል።

1. ቁጢጥ ከማለት መዝለል፤ በፑሽ አፕ አሰራር ሁኔታ በክርን ክብደትን በመያዝ መቆየት እና
በቦታ ላይ ዝላይ
ƒƒ የእለቱን ትምህርት በተለያዩ ጣቢያዎች ላይ የሚከናወኑ ተግባራት ስለመሆኑ ለተማሪዎች መግለጽና ማብራሪያ መስጠት፤
ƒƒ ተማሪዎችን ከአራት እሰክ ስድስት ረድፍ ድረስ በማሰለፍ የተግባር ትምህርት ለመማር የተሟላ የስፖርት ትጥቅ
መልበሳቸውንና ጤንነታቸው የተሟላ መሆኑን ማረጋገጥ፤
ƒƒ ተማሪዎች በተሰለፉበት ረድፍ (ቡድን) አጠቃላይና ውስን የሰውነት ማሟሟቂያ እንቅስቃሴ እንዲሰሩ ማበረታታትና
ድጋፍ ማድረግ፤
ƒƒ እንደተማሪዎቹ ቁጥር ብዛት ከአራት እሰከ ስድስት ቡድን ማደራጀትና በ3 ጣቢያ የሚሰሩ እንቅስቃሴዎችን መከፋፈል፤

ጣቢያ 1 ቂጢጥ ከማለት

መዝለል

ጣቢያ 2 በክርን ክብደትን

ጣቢያ 3 በቦታ ላይ በመያዝ መቆየት

ƒƒ በመማሪያ መፅሀፉ በሥዕልና በፁሁፍ በተገለፀው መሰረት እንቅስቃሴዎችን በተግባር ሰርቶ ማሳየትና ገለፃ ማድረግ
ƒƒ ከላይ በተገለፀው መሰረት ተማሪዎች ከጣቢያ ወደጣቢያ በመዘዋወር ለእያንዳንዱ ጣቢያ የተመደበውን ተግባር
እንዲሠሩ ማበረታታትና በአንድ ጣቢያ ላይ ቢያንስ ለ5 ደቂቃ ተግባሩን እንዲለማመዱ ማድረግ፤

የጤናና ሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ~ 8ኛ ክፍል ~ የመምህር መምሪያ ~ 25

ምዕራፍ 3 ጤናና የአካል ብቃት

ƒƒ ከአንዱ ጣቢያ ወደሌላው ጣቢያ የሚዘዋወሩት መምህሩ/ሯ በሚሰጣቸው ምልክት ሲሆን በመካከል የ1 ደቂቃ እረፍት
በመስጠት በየጣቢያው የሚሰራውን እንቅስቃሴ በመደጋገም እንዲለማመዱ ማበረታታት፤
ƒƒ በመጨረሻም የሰውነት ማቀዝቀ¹ እንቅስቃሴ በየቡድናቸው እንዲሰሩ ማበረታታትና በእለቱ ትምህርት እንቅስቃሴያቸውን
አስመልክቶ ያሳዮትን ፍላጎትና ተነሳሽነት መግለፅና ለሚቀጥለው ይህን እንቅስቃሴ በግልም ሆነ በቡድን የአካል
ብቃታቸውን ለማሻሻል መስራት እንዳለባቸው ማሳሰብ፤

ክትትልና ግምገማ:-
ƒƒ የእለቱን ትምህርት ዝርዝር አላማዎች በትክክል መተግበሩን በጥያቄና መልስ፤ በምልከታ እንዲሁም ከጓደኞቻቸው ጋር
በየጣቢያው በሚሰሩትና እንቅስቃሴውን ለመስራት በሚያሳዮት ፍላጎት መሰረት መገምገም ይቻላል::

2. V-ቅርፅን መስራት፤ ከርል አፕ፤አግዳሚ ወንበር ላይ እጅን ከኋላ በመደገፍ ፑሽ አፕ መስራት

ƒƒ የእለቱን ትምህርት በተለያዩ ጣቢያዎች ላይ የሚከናወኑ ተግባራት ስለመሆኑ ለተማሪዎች መግለጽና ማብራሪያ መስጠት፤
ƒƒ ተማሪዎችን ከአራት እሰክ ስድስት ረድፍ ድረስ በማሰለፍ የተግባር ትምህርት ለመማር የተሟላ የስፖርት ትጥቅ
መልበሳቸውንና ጤንነታቸው የተሟላ መሆኑን ማረጋገጥ፤
ƒƒ ተማሪዎች በተሰለፍበት ረድፍ (ቡድን) አጠቃላይና ውስን የሰውነት ማሟሟቂያ እንቅስቃሴ እንዲሰሩ ማበረታታትና
ድጋፍ ማድረግ፤
ƒƒ እንደተማሪዎቹ ቁጥር ብዛት ከአራት እሰከ ስድስት ቡድን ማደራጀትና በ6 ጣቢያ የሚሰሩ እንቅስቃሴዎችን መከፋፈል፤

ጣቢያ-1 V-ቅርፅን
መስራት

ጣቢያ-6 አግዳሚ ወንበር ላይ

ጣቢያ-2 ከርል አፕ
እጅን ከኋላ በመደገፍ ፑሽ አፕ
መስራት

ጣቢያ -3

አግዳሚ ወንበር ላይ እጅን ከኋላ ጣቢያ-5 ከርል አፕ

በመደገፍ ፑሽ አፕ መስራት

ጣቢያ- 4 V-ቅርፅን
መስራት
ƒƒ በመማሪያ መፅሀፉ በሥዕልና በጹሁፍ በተገለፀው መሰረት ሦስቱን እንቅስቃሴ በተግባር ሰርቶ ማሳየትና ገለፃ ማድረግ፤
ƒƒ ከላይ በተገለፀው መሰረት ተማሪዎች ከጣቢያ ወደ ጣቢያ በመዘዋወር ለእያንዳንዱ ጣቢያ የተመደበውን ተግባር
እንዲሠሩ ማበረታታትና በአንድ ጣቢያ ላይ ቢያንስ ለ5 ደቂቃ ተግባሩን እንዲለማመዱ ማድረግ፤
ƒƒ ከአንዱ ጣቢያ ወደሌላው ጣቢያ የሚዘዋወሩት መምህሩ በሚሰጣቸው ምልክት ሲሆን በመካከል የ1 ደቂቃ እረፍት
በመስጠት በየጣቢያው የሚሰራውን እንቅስቃሴ በመደጋገም እንዲለማመዱ ማበረታታት፤

የጤናና ሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ~ 8ኛ ክፍል ~ የመምህር መምሪያ ~ 26

ምዕራፍ 3 ጤናና የአካል ብቃት

ƒƒ በመጨረሻም የሰውነት ማቀዝቀ¹ እንቅስቃሴ በየቡድናቸው እንዲሰሩ ማበረታታትና በእለቱ ትምህርት እንቅስቃሴያቸውን
አስመልክቶ ያሳዮትን ፍላጎትና ተነሳሽነት መግለፅና ለሚቀጥለው ይህንን እንቅስቃሴ በግልም ሆነ በቡድን የአካል
ብቃታቸውን ለማሻሻል መስራት እንዳለባቸው ማሳሰብ::

ክትትልና ግምገማ:-
ƒƒ የእለቱን ትምህርት ዝርዝር አላማዎች በትክክል መተግበሩን በጥያቄና መልስ፤ በምልከታ እንዲሁም ከጓደኞቻቸው ጋር
በየጣቢያው በሚሰሩትና እንቅስቃሴውን ለመስራት በሚያሳዮት ፍላጎት መሰረት መገምገም ይቻላል::

3.4. የመተጣጠፍ ችሎታን የሚያዳብሩ እንቅስቃሴዎች (4 ክ/ጊዜ)

ዝርዝር ዓላማ:-ተማሪዎች ይህንን ርዕስ ተምረው ካጠናቀቁበኋላ:-
ƒƒ የመተጣጠፍ ችሎታ ትርጉምን በትክክል ይገልጻሉ::
ƒƒ የመተጣጠፍ ችሎታን ለማሻሻል ጠቃሚ የሆኑ ቢያንስ አራት እንቅስቃሴዎችን ይዘረዝራሉ::
ƒƒ የመተጣጠፍ ችሎታን ከሚያዳብሩ እንቅስቃሴዎች መካከል ቢያንስ አራቱን በተግባር ሠርተው ያሳያሉ::
ƒƒ በተመረጡ እንቅስቃሴዎች አማካኝነት የመተጣጠፍ ችሎታቸውን ያሻሽላሉ::
ƒƒ የመተጣጠፍ ችሎታን የሚያዳብሩ እንቅስቃሴዎችን በግል ለመስራት ተነሳሽነት ያሳያሉ::

መሠረታዊ ጽንሰ-ሀሳብ (ለመምህሩ/ሯ የመነሻ ሀሳብ):-

ƒƒ በመማሪያ መጽሐፉ የተጻፈው እንዳለ ሆኖ በተጨማሪም ከተለያዮ ድህረ-ገጾች በመፈለግ ሀሳቦችን ማበልጸግ ይቻላል::

የመማር-ማስተማር መርጃ መሣሪያዎች እና ሥፍራዎች:-

መርጃ መሣሪያዎች:-
ƒƒ የመተጣጠፍ ችሎታን ለማሻሻል የሚሰሩ እንቅስቃሴዎችን የሚገልጹ ፖስተሮች፤ ስዕሎች፤ ፊልሞች፤ ፎቶዎችና ጽሁፎች፤

ሥፍራ:-የተግባር ትምህርት የሚሰጥበት ሜዳ፣

የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል:-

ƒƒ ያለፈውን ትምህርት በጥያቄና መልስ መከለስ፤
ƒƒ የዕለቱን ትምህርት ርዕስና አላማዎቹን ማስተዋወቅ፤
ƒƒ የመተጣጠፍ ችሎታ ምን ማለት እንደሆነ በጥያቄና መልስ ተግባራዊ ማድረግ፤
ƒƒ ተማሪዎችን በጥንድ በጥንድ በማደራጀት የመተጣጠፍ ችሎታ ለማጎልበት የሚያስችሉ እንቅስቃሴዎችን እንዲዘረዝሩና
ሀሳብ እንዲለዋወጡ ማበረታታት፤
ƒƒ ተማሪዎች ከሰጡት ሀሳብ በመነሳት የመተጣጠፍ ችሎታን ለማጎልበት የሚያስችሉ እንቅስቃሴዎች መካከል ከወገብ
በላይ ያለውን የሰውነት ክፍል ማሳሳብ፤ሆድና ዳሌ ማሳሳብ፤ቁጭ ብሎ ወደፊት መሣብ ወ.ዘ.ተ መሆኑን በመግለፅ
ማበረታታት፤
ƒƒ ተማሪዎችን በጥንድ በጥንድ በማደራጀት በመተጣጠፍ የትኛው የሰውነት ክፍል ተሳታፊ እንደሚሆንና
የመተጣጠፍችሎታን መጎልበቱ ለምን እንደሚጠቅም ሀሳብ እንዲለዋወጡ ማበረታታት፤
ƒƒ በጥንድ ሀሳብ የተለዋወጡትን ለክፍል ጓደኞቻቸው እንዲያቀርቡ መገፋፋትና በተሰጠው ሀሳብ ላይ ማብራሪያ መስጠት፤

የጤናና ሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ~ 8ኛ ክፍል ~ የመምህር መምሪያ ~ 27

ምዕራፍ 3 ጤናና የአካል ብቃት

ƒƒ ተማሪዎችየተማሩትን ትምህርት መረዳታቸውን ለማረጋገጥ የቃል ጥያቄ በመጠየቅ ማረጋገጥ፤

ƒƒ ይህ ርዕስ አንድ ክፍለ ጊዜ ብቻ የተሰጠው ስለሆነ በተሰጠው ሰዓት ጽንሰ-ሀሳቡንና ተግባሩን በማቀናጀት መስጠት
ያስፈልጋል፤
ƒƒ በመማሪያ መጽሐፉ በስዕል በተገለጸው መሰረት ከላይኛው የሰውነት ክፍል ጀምሮ የሚሰሩ የመተጣጠፍ
እንቅስቃሴዎችንየተለያዮ ጡንቻዎችን ለማሳሳብና የመለጠጥ ችሎታን ለመጨመር የሚሰሩ ናቸው።
ƒƒ ተማሪዎች ከ4 እሰክ 6 ረድፍ በማሰለፍ የተግባር ትምህርት ለመማር የተሟላ የስፖርት ትጥቅ መልበሳቸውንና
ጤንነታቸው የተሟላ መሆኑን ማረጋገጥ
ƒƒ ተማሪዎች በተሰለፍበት ረድፍ (ቡድን) አጠቃላይና ውስን የሰውነት ማሟሟቂያ እንዲሰሩ ማበረታታት
ƒƒ ተማሪዎች በተሰለፍበት ረድፍ (ቡድን) በቂ ቦታ እንዲይዙ ማድረግና የእንቅስቃሴዎችን ትክክለኛ አሰራር በቅደም
ተከተላቸው መሰረት ሰርቶ በማሳየት ሁሉም ተማሪዎች በተመሳሳይ ሁኔታ እንዲሰሩ ማለማመድ፤
ƒƒ ሰውነትን በማሳሳብ ጊዜ እንቅስቃሴው ከሰውነት የመለጠጥ አቅም በላይ መሆን የለበትም፤
ƒƒ የመተጣጠፍእንቅስቃሴዎችን ሲሰሩ የመጨረሻው ተለጥጦ የደረሰበት ቦታ ላይ ይዞ ለ10 ሴኮንድ ያህል መቆየትን
በመግለፅ በቅድም ተከተላቸው መሰረት እንቅስቃሴዎችን እንዲለማመዱ ማበረታታት፤
ƒƒ በመጨረሻም የሰውነት ማቀዝቀ¹ እንቅስቃሴ በየቡድናቸው እንዲሰሩ ማበረታታትና በእለቱ ትምህርት እንቅስቃሴያቸውን
አስመልክቶ ደረጃቸውን መግለፅና ለሚቀጥለው ይህን እንቅስቃሴ ማሻሻል እንደሚኖርባቸው ማሳሰብ፤
ƒƒ የአካል ብቃት እንቅስቀሴ መፅሐፍትን በማንበብ፤ የተለያዮ ድህረ-ገጾችን (የኢንተርኔት) ምንጭ በመፈለግ ሌሎች
የመተጣጠፍ እንቅስቃሴዎችን እንዲዘረዝሩና አሰራራቸውን እንዲያብራሩ የቤት ሥራ መሥጠት፤

ክትትልና ግምገማ:-
ƒƒ በተግባር ልምምድ ጊዜ እንቅስቃሴዎቹን በትክክል እየሰሩ ስለመሆናቸው ምልከታ ማድረግና እርማትና አስተያየት
መስጠት፤
ƒƒ የእለቱን ትምህርት ዝርዝር አላማዎች በትክክል መተግበሩን በጥያቄና መልስ ማረጋገጥ ይቻላል፣

3.5. የፍጥነት ችሎታን የሚያዳብሩ እንቅስቃሴዎች (2 ክ/ጊዜ)

ዝርዝር ዓላማ:-ተማሪዎች ይህንን ርዕስ ተምረው ካጠናቀቁበኋላ:-
ƒƒ የፍጥነትን ትርጉምን በትክክል ይገልጻሉ::
ƒƒ የፍጥነትን ችሎታን ለማዳበር ጠቃሚ የሆኑ ቢያንስ አራት እንቅስቃሴዎችን ይዘረዝራሉ::
ƒƒ የፍጥነት ችሎታን ከሚያዳብሩ እንቅስቃሴዎች መካከል ቢያንስ አራቱን በተግባር ሠርተው ያሳያሉ::
ƒƒ በተመረጡ እንቅስቃሴዎች አማካኝነት የፍጥነት ችሎታቸውን ያሻሽላሉ::
ƒƒ የፍጥነት ችሎታን የሚያዳብሩ እንቅስቃሴዎችን በግልና በቡድን ለመስራት ተነሳሽነት ያሳያሉ::

መሠረታዊ ጽንሰ-ሀሳብ (ለመምህሩ/ሯ የመነሻ ሀሳብ):-

ƒƒ በመማሪያ መጽሐፉ የተጻፈው እንዳለ ሆኖ በተጨማሪም ከተለያዮ ድህረ-ገጾች በመፈለግ ሀሳቦችን ማበልጸግ ይቻላል::

የጤናና ሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ~ 8ኛ ክፍል ~ የመምህር መምሪያ ~ 28

ምዕራፍ 3 ጤናና የአካል ብቃት

የመማር-ማስተማር መርጃ መሣሪያዎች እና ሥፍራዎች:-

መርጃ መሣሪያዎች:-
ƒƒ የፍጥነት ችሎታን ለማዳበር የሚሰሩ እንቅስቃሴዎችን የሚገልጹ ፖስተሮች፤ ስዕሎች፤ ፊልሞች፤ ፎቶዎችና ጽሁፎች፤
ƒƒ ኮን፤ ገመድ (ዱላ)
ƒƒ መሬት ላይ የሚቀመጡ ምልክቶች
ƒƒ ቀለበት

ሥፍራ:-የተግባር ትምህርት የሚሰጥበት ሜዳ፣

የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል:-

ƒƒ ያለፈውን ትምህርት በጥያቄና መልስ መከለስ፣
ƒƒ የዕለቱን ትምህርት ርዕስና አላማዎቹን ማስተዋወቅ፣
ƒƒ ፍጥነት ምን ማለት እንደሆነ በጥያቄና መልስ ተግባራዊ ማድረግ፣
ƒƒ ተማሪዎችን በጥንድ በጥንድ በማደራጀት የፍጥነት ችሎታ ለማጎልበት የሚያስችሉ እንቅስቃሴዎችን እንዲዘረዝሩና ሀሳብ
እንዲለዋወጡ ማበረታታት፣
ƒƒ ተማሪዎች ከሰጡት ሀሳብ በመነሳት የፍጥነት ችሎታ ለማጎልበት የሚያስችሉ እንቅስቃሴዎች መካከል ተከታትሎ
መሮጥ(pursuit runs) ፤ ከ20 እስከ 40 ሜትር በፍጥነት መሮጥ፤በከቡ ዙሪያ በቡድን በመሆን ከ5 እስከ 8 ደቂቃ ድረስ
መሮጥ ወ.ዘ.ተ መሆኑን በመግለፅ ማበረታታት
ƒƒ ተማሪዎችየተማሩትን ትምህርት መረዳታቸውን ለማረጋገጥ የቃል ጥያቄ በመጠየቅ ማረጋገጥ።
ƒƒ ይህንይዘት በሁለት ክፍለጊዜ የሚማሩት ስለሆነ አንድ ክፍለ ጊዜ ለጽንሰ-ሀሳብ ብቻ መስጠቱ ተገቢ ስለማይሆን ከላይ
ያለውን የጽንሰ ሀሳብ ትምህርት ከተግባር ትምህርቱ ጋር በማቀናጀትማስተማር ያስፈልጋል። ከዚህ በተጨማሪም
በጣቢያ የማስተማር ዘዴን በመጠቀም ተግባራዊ ማድረግ ይቻላል።

1. ተከታትሎ መሮጥ (pursuit runs)

ƒƒ ተማሪዎች ከ4 እሰክ 6 ረድፍ በማሰለፍ የተግባር ትምህርት ለመማር የተሟላ የስፖርት ትጥቅ መልበሳቸውንና
ጤንነታቸው የተሟላ መሆኑን ማረጋገጥ፤
ƒƒ ተማሪዎች በተሰለፍበት ረድፍ/ቡድን አጠቃላይና ውስን የሰውነት ማሟሟቂያ እንዲሰሩ ማበረታታት፤
ƒƒ በመማሪያ መጽሐፉ በሥዕልና የእንቅስቃሴው አሰራር በተገለፀው መሰረት ተከታትሎ መሮጥን ለማሰራት በአለው ዱላ
ወይም ገመድ መሰረት ተማሪዎችን ጥንድ ጥንድ በማድረግ ማደራጀት፤
ƒƒ ተማሪዎች በተደራጁበት መሰረት 1.5 ሜትር ርዝመት ያለው ገመድ ወይም ዱላ ጫፍና ጫፍ በመያዝ በተሰመረ መስመር
ላይ በሶምሶማ መሮጥ ከዚያም ከፊት ያለው ሯጭ ገመዱን (ዱላውን) በመልቀቅ ሲሮጥ ተከታዮ አሱን ለመያዝ ይሮጣል፤
ƒƒ እንቅስቃሴውን አባራሪ የነበረው ተባራሪ በመሆን በመደጋገም ማለማመድ፤
ƒƒ እንቅስቃሴውን በመደጋገም እንዲለማመዱ ማበረታታትና ከፊት ያለው ሯጭ ዱላውን ከእጁ በሚለቅበት ጊዜ ወደታች
መሬት ላይ መሆኑን ማስገንዘብ ያስፈልጋል፤

የጤናና ሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ~ 8ኛ ክፍል ~ የመምህር መምሪያ ~ 29

ምዕራፍ 3 ጤናና የአካል ብቃት

ƒƒ የአካል ጉዳተኛ ተማሪዎች ክፍል ውስጥ ካሉና የአካል ጉዳታቸው የፍጥነት ችሎታን ለማዳበር የሚሰሩ እንቅስቃሴዎች
ላይ ለመሣተፍ የሚፈቅድላቸው ከሆነ ልዩ ትኩረት አድርጎ እንዲሳተፉ ማድረግ፤ የማያሳትፋቸው ከሆነ ግን በሌላ
ተመሣሣይ እንቅስቃሴ እንዲሳተፉ ማድረግ፤
ƒƒ በመጨረሻም የሰውነት ማቀዝቀ¹ እንቅስቃሴ በየቡድናቸው እንዲሰሩ ማበረታታትና በእለቱ ትምህርት እንቅስቃሴያቸውን
አስመልክቶ ደረጃቸውን መግለፅና ለሚቀጥለው ጊዚያት በመለማመድ ፍጥነታቸውን ማሻሻል እንደሚኖርባቸው
ማሳሰብ፣

ክትትልና ግምገማ:-
ƒƒ በልምምድ ጊዜ እንቅስቃሴዎቹን በተጠቀሰው አሰራር መሠረት እየሰሩ ስለመሆናቸው ምልከታ በማድረግ እርማትና
አስተያየት መስጠት፤
ƒƒ በፍጥነት ሩጫ ልምምድ ወቅት ትክክለኛ የአሯሯጥ ቴክኒክ ተግባራዊ ማድረጋቸውን በምልከታ መከታተልና ማስተካከያ
መስጠት፤

2.ከ20ሜ.እስክ 30ሜ. የፍጥነት ሩጫ

ƒƒ ተማሪዎች ከ4 እሰክ 6 ረድፍ በማሰለፍ የተግባር ትምህርት ለመማር የተሟላ የስፖርት ትጥቅ መልበሳቸውንና
ጤንነታቸው የተሟላ መሆኑን ማረጋገጥ፣
ƒƒ ተማሪዎች በተሰለፍበት ረድፍ (ቡድን) አጠቃላይና ውስን የሰውነት ማሟሟቂያ እንዲሰሩ ማበረታታት፣
ƒƒ በመማሪያ መጽሐፉ በሥዕልና የእንቅስቃሴው አሰራር በተገለፀው መሰረት ከ20 ሜትር እስክ 30ሜ የፍጥነት
ሩጫለማሰራት ተማሪዎችን ከ3 እሰከ 5 ቡድን ድረስ ማደራጀትና አንቅስቃሴው እንዴት እንደሚሰራ ሰርቶ ማሳየትና
ገለጻ ማድረግ፤
ƒƒ በመማሪያ መጽሐፉ በተገለፀው መሰረት የመነሻ ትእዛዝ በመስጠት ሁሉም የቡድኑ አባላት እንዲሳተፍ ማበረታታትና
በመደጋገም ማሰራት፤
ƒƒ የአካል ጉዳተኛ ተማሪዎች ክፍል ውስጥ ካሉና የአካል ጉዳታቸው የፍጥነት ችሎታን ለማዳበር የሚሰሩ እንቅስቃሴዎች
ላይ ለመሣተፍ የሚፈቅድላቸው ከሆነ ልዩ ትኩረት አድርጎ እንዲሳተፉ ማድረግ፤ የማያሳትፋቸው ከሆነ ግን በሌላ
ተመሣሣይ እንቅስቃሴ እንዲሳተፉ ማድረግ፤

3. እንደመሰላል መሬት ላይ በተሰሩ መስመሮች መካከል መሮጥ/Speed ladder/

ƒƒ በመማሪያ መጽሐፉ በስዕል በተገለፀው መሰረት የመሮጫ መስመርን የተወሰነ ርቀት ባላቸው አግዳሚ ምልክቶች
ማዘጋጀት፤
ƒƒ የክፍሉን ተማሪዎች በተዘጋጁት መስመሮች ልክ በመስመር ማደራጀትና እንቅስቃሴውን ሰርቶ ማሳየትና ገለጻ ማድረግ፤
ƒƒ ተማሪዎች በተሰመሩት መስመር መካከል ርቀቱን ጠብቀው በእርምጃ እንዲለማመዱ ማበረታታት፤
ƒƒ ፍጥነታቸውን በመቀያየር እንዲለማመዱና በሩጫ ጊዜ በእግራቸው መዳፍ መነሳትን ትኩረት እንዲያደርጉ ማስገንዘብ፤
ƒƒ ተማሪዎች ማስተካከል ያለባቸውን ግብረ መልስ በመስጠት በመደጋገም እንዲለማመዱ ማበረታታት፤
ƒƒ ተገቢውን የሰውነት ማቀዝቀ¹ እንቅስቃሴ በመስራት ሰውነታቸውን እንዲያቀዘቅዙ ማድረግ፤

ክትትልና ግምገማ:-
ƒƒ ተማሪዎች ትክክለኛ የእግር አስተራረፍ በመጠቀም ማረፋቸውን በምልከታ ማረጋገጥና ተገቢውን እርምት መስጠት፤
የጤናና ሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ~ 8ኛ ክፍል ~ የመምህር መምሪያ ~ 30
ምዕራፍ 3 ጤናና የአካል ብቃት

ƒƒ በፍጥነት ሩጫ ልምምድ ወቅት ትክክለኛ የአሯሯጥ ቴክኒክ ተግባራዊ ማድረጋቸውን በምልከታ መከታተልና ማስተካከያ
መስጠት፤

3.6. የስፖርት አበረታች ቅመሞችን (ዶፒንግ) መከላከል (2 ክ/ጊዜ)

ዝርዝር ዓላማ:-ተማሪዎች ይህንን ርዕስ ተምረው ካጠናቀቁበኋላ:-
ƒƒ ስፖርተኞች የስፖርት አበረታች ቅመሞችን(ዶፒንግ) እንዳይጠቀሙ መከላከያ ዘዴዎችን በሚገባ ይገልጻሉ::
ƒƒ የስፖርት አበረታች ቅመሞችን(ዶፒንግ) መጠቀም የተከለከሉበትን ምክንያት ይዘረዝራሉ::
ƒƒ የስፖርት አበረታች ቅመሞችን (ዶፒንግ) መጠቀም የሚያስከትለውን ተፅዕኖ በመረዳት ለመከላከል ይነሳሳሉ::

መሠረታዊ ጽንሰ-ሀሳብ (ለመምህሩ/ሯ የመነሻ ሀሳብ):-

የስፖርት አበረታች ቅመሞች ማለትበስፖርታዊ ውድድሮች ወይም እንቅስቃሴዎች ወቅት ሁለንተናዊ ብቃትን የሚጨምሩ የተከለከሉ
የስፖርት አበረታች ቅመሞችን በመጠቀም ያልተገባ ውጤት ማስመዝገብ ወይም ለማስመዝገብ መሞከር እና በአለም አቀፉ የፀረ-
ዶፒንግ ህግ የተደነገጉ የተለያዩ የህግ ጥሰቶችን መፈፀም ነው። በመማሪያ መፅሀፉ የተገለፀው ሀሳብ እንዳለ ሆኖ ከተለያዮ ድህረ-ገፆች
መረጃዎችን በመፈለግ ሀሳቡን ማዳበር ያስፈልጋል።
ƒƒ የስፖርት አበረታች ቅመሞችን መጠቀም በዜጎች ላይ በተለያየ መልኩ የጤና፤ የስነልቦና፤ የማህበራዊ፤ ኢኮኖሚያዊ እና
ፖሊቲካዊ ተፅዕኖዎችን ያስከትላል።
ƒƒ ለምሳሌ በጤና ላይ ከሚያስከትለው ችግር :-የብጉር መብዛትና መጠኑ መጨመር፤ የፀጉር መነቀል፤ በሴቶች ላይ
ወንዳዊ ባህርያትን መላበስ፤(ለምሳሌ፡- የድምፅ መጎርነን፤ የፂም ማውጣት፤ የወር አበባ መዛባትና መቅረት)፤ በወንዶች
ላይ የሴትነት ባህሪ ማሳየት(ለምሳሌ፡- የጡትእድገት፤ የሆርሞን ለውጥ፤የብልት መሟሸሽ እና ለስንፈተ ወሲብ ጉዳት
መዳረግ፤ የዘር ፍሬመቀነስ)፤የጉበትና የማህፀን በሽታዎች ወ.ዘ.ተ

የመማር-ማስተማር መርጃ መሣሪያዎች እና ሥፍራዎች:-

መርጃ መሣሪያዎች:- ከትምህርቱ ጋር ተያያዥነት ያላቸው ሥዕሎች፣ ፖስተሮችና ጽሁፎች፣

ሥፍራ:-የንድፈ ሀሳብ ትምህርት በሚሰጥበት ክፍል ውስጥ፣

የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል:-

ƒƒ የእለቱን ትምህርት ርዕሰና አላማ ለተማሪዎች ማስተዋወቅ፣
ƒƒ ተማሪዎችን ጥንድ ጥንድ ሆነው እንዲደራጁ ማበረታታትናየስፖርት አበረታች ቅመሞች ምን ማለት እንደሆነ በጥያቄና
መልስ ተግባራዊ ማድረግ፣
ƒƒ ተማሪዎችን ጥንድ ጥንድ ሆነው እንዲደራጁ ማበረታታትናስፖርተኞች የስፖርት አበረታች ቅመሞችን እንዳይጠቀሙ
የተከለከለበት ምክንያት ምንድን ነው? እንዳይጠቀሙስ እንዴት መከላከል ይቻላል? የሚለውን ጥያቄ እንዲወያዮበት
ማበረታታት፣
ƒƒ ተማሪዎች የተወያዮበትን ተራ በተራ እንዲያቀርቡ ማድረግና ተማሪዎች ከገለጹት አንጻር ከላይ በመሰረታዊ ጽንሰ-ሀሳብ
የተገለፁትን ነጥቦች እና በመማሪያ መፅሀፉ በተገለፀው መሰረት በማድረግ በአለም አቀፍ ኦሎምፒክ ኮሚቴና በአለም
አቀፉን የፀረ-አበረታች ቅመሞች ኤጀንሲ (WADA)በወጡ ደንቦች መሰረት መከላከል እንደሚቻልበአጭሩ ማብራራይ፣
ƒƒ ከተሰጠው ማብራሪያ በመነሳት ተማሪዎች ያልገባቸውን እንዲጠይቁ እድል መስጠት፣

የጤናና ሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ~ 8ኛ ክፍል ~ የመምህር መምሪያ ~ 31

ምዕራፍ 3 ጤናና የአካል ብቃት

ƒƒ የተጠየቁትን ጥያቄ በተማሪዎችና በመምህሩ/ሯ መመለስ፣

ƒƒ ተማሪዎች ከ3 እሰከ 5 አባላት ያለው ቡድን ሆነው በማደራጀት ስለስፖርት አበረታች ቅመሞች (ቅመሞችን) ለምን
እንድትማሩ አስፈለገ? የሚለውን ጥያቄበመጠየቅ እንዲወያዮበት ማድረግ፣
ƒƒ ተማሪዎች የተወያዮበትን ሀሳብ እንዲያቀርቡ ማድረግና ተማሪዎች ከገለጹት አንጻር በመማሪያ መፅሀፉ በተገለፀው
መሰረት እና ከሌሎችም መረጃ ምንጮች በመጨመርበአጭሩ ማብራራት፣
ƒƒ ተማሪዎችን ጥንድ ጥንድ ሆነው እንዲደራጁ ማበረታታትና የስፖርት አበረታች ቅመሞችን መጠቀም በጤና ላይ ምን
ጉዳት እንደሚያስከትል ሀሳብ እንዲለዋወጡ ማበረታታትና የተወያዮበትን ሀሳብ እንዲያንፀባርቁ ማድረግ፣
ƒƒ ተማሪዎች ከገለጹት አንጻር ከላይ በመሰረታዊ ጽንሰ ሀሳብ በተገለፀውና ሌሎች የመረጃ ምንጮችን በመጠቀም
በአጭሩ ማብራራትና በተለይ የስፖርት አበረታች ቅመሞችን መጠቀም በዜጎች ላይ በተለያየ መልኩ የጤና፤ የስነልቦና፤
የማህበራዊ፤ ኢኮኖሚያዊ እና ፖሊቲካዊ ተፅዕኖዎችን የሚያስከትል መሆኑን ማስገንዘብ፣
ƒƒ ተማሪዎችየተማሩትን ትምህርት መረዳታቸውን ለማረጋገጥ የቃል ጥያቄ በመጠየቅ ማረጋገጥ።

ክትትልና ግምገማ:-
ƒƒ የእለቱን ትምህርት ዝርዝር አላማዎች በትክክል መተግበሩን በጥያቄና መልስ፣ በሚያቀርቡት ውይይት እንዲሁም
ጓደኞቻቸው በሚያስተካክሏቸው ሀሳብ መሰረት መገምገም ይቻላል።

የምዕራፉ መልመጃ መልስ

1. መ 2. መ 3. መ 4. ሀ

5.
ªªየአየራዊ ልምምድ ማለት ቀለል ባለ የልምምድ ጫና የሚከናወኑ አካላዊ እንቅስቃሴዎችን የሚያካትት ነው።
ªªየአየራዊ እንቅስቃሴ የሚከናወነው የእንቅስቃሴውን ክብደት በመቀነስ ለረጅም ጊዜ / በእንቅስቃሴው ውስጥ የምናሳልፈውን
የጊዜ ቆይታ በመጨመር የሚከናወን ተግባር ነው።
ªªኢ- አየራዊ ልምምድ ያለኦክስጅን ወይም ኦክስጅን ሣንጠቀም በፍጥነት ሊጠናቀቁ የሚችሉ የአጭር ጊዜ እንቅስቃሴዎችን
የሚያጠቃልል የልምምድ ዓይነት ነው።

6. የስፖርት አበረታች ቅመሞች መጠቀም የተከለከለበት በርካታ ምክንያቶች አሉ። እነዚህም:-

ªªየስፖርቱን አዝናኝነት የሚቀንስ፣ የሰዎችንና የስፖርቱን በጐ ገጽታ የሚያጠፋ በመሆኑ ነው፣
ªªተገቢ ባልሆነ መንገድ ውጤት ለማግኘት የሚጣጣረውን ስፖርተኛ ለመከላከል
ªª የጤና መታወክ ለመታደግ፣
ªªበተለያዩ የኢኮኖሚ ደረጃ የሚገኙ ተወዳዳሪዎችን እኩል ተሳታፊ ለማድረግ ስለሚያስችል ነው ወ.ዘ.ተ

የጤናና ሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ~ 8ኛ ክፍል ~ የመምህር መምሪያ ~ 32

ምዕራፍ 4 አትሌቲክስ

ምዕራፍ

4 አትሌቲክስ

የክፍለ ጊዜ ብዛት፡ 8

አጠቃላይ ዓላማዎች፡

ተማሪዎች ይህንን ምዕራፍ ከተማሩ በኋላ፡-

ƒƒ በአፍሪካ ዋና ዋና የአትሌቲክስ ታሪክን ይገነዘባሉ።
ƒƒ የመሰናክል ሩጫ አሰራር ስልቶች ያውቃሉ።
ƒƒ የዲስከስ እና የአለሎ ውርወራ የአሰራር ስልቶችን ይረዳሉ።
ƒƒ በመሰናክል ሩጫ፣ በዲስከስ ውርወራ እና አለሎ ውርወራ ተግባራት ይሳተፋሉ።
ƒƒ የመሰናክል ሩጫ፣ የአለሎ እና የዲስከስ ውርወራ ክህሎታቸውን ያዳብራሉ።
ƒƒ የከፍታ ዝላይ ክህሎታቸውን ያዳብራሉ።

መግቢያ
አትሌቲክስ ተፈጥሮአዊ ይዘት ያለዉ የስፖርት አይነት ነው። አትሌቲክስ ሰፊ የስፖርት አይነት ሲሆን በዚህ ምዕራፍ በቅድሚያ
የአትሌቲክስ ዘርፎችን እና የአፍሪካን ውጤታማነት እንመለከታለን። በተጨማሪም የመሰናክል ሩጫ፣ የአለሎ ውርወራ፣ የዲስከስ
ውርወራ እና የከፍታ ዝላይ ተግባራትም በዚህ ምዕራፍ ይዳሰሳሉ።

4.1 በአፍሪካ የአትሌቲክስ ታሪክ (1 ክ/ጊዜ)

ዝርዝር ዓላማ:-ተማሪዎች ይህንን ርዕስ ከተማሩ በኋላ፦
ƒƒ የአትሌቲክስ ዘርፎችን በትክክል ይገልጻሉ።
ƒƒ በአፍሪካ የአትሌቲክስ ታሪክ የትኞቹ የአፍሪካ ሀገራት በኦሎምፒክ እና በአለም ሻምፒዮና የተሻለ (ሜዳሊያ በማግኘት)
ውጤት እንዳላቸው ይለያሉ።
ƒƒ ሀገራችን ኢትዬጵያ ጥሩ ውጤት ያስመዘገበችባቸውን ቢያን ሁለት የአትሌቲክስ ተግባሮችን ይለያሉ።
ƒƒ በአፍሪካ የአትሌቲክስን ታሪክ ለማወቅ ተነሳሽነት ይኖራቸዋል።

የጤናና ሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ~ 8ኛ ክፍል ~ የመምህር መምሪያ ~ 33

ምዕራፍ 4 አትሌቲክስ

መሠረታዊ ጽንሰ-ሀሳብ (ለመምህሩ/ሯ የመነሻ ሀሳብ):-

የአትሌቲክስ ዘርፎች ሁለት ናቸው። እነርሱም የመም እና የሜዳ ተግባራት ይባላሉ። የመም ተግባራት የሚባለው ሩጫን ሲይዝ የሜዳ
ተግባራት ደግሞ ውርወራ እና ዝላይን ያካትታል።

ሩጫ በራሱ የተለያዩ ክፍሎች አሉት። አጭር ርቀት ሩጫ፣ መካከለኛ እና ረጅም ርቀት ሩጫ በመባል በሶስት ይከፈላል። አጭር
ርቀት ሩጫ የሚባሉት100ሜ፣ 200ሜ እና 400ሜ ሲሆኑ እነዚሁ 100ሜ፣ 200ሜ እና 400ሜ መሰናክል ሩጫንም ያካትታሉ። የዱላ
ቅብብል ሩጫም የአጭር ርቀት ሩጫ አካል ነው። መካከለኛ ርቀት 800ሜ፣ 1500ሜ ሲሆን ረጅም ርቀት ሩጫ ደግሞ 3000ሜ፣
5000ሜ፣ 10000ሜ፣ 21 ኪሜ እና 42 ኪሜ ከ195 ሜ. ያካትታል።

ውርወራ አለሎን፣ ዲስክስን፣ ጦርን እና መዶሻን ያካትታል።

ዝላይ በተመሳሳይ ርዝመት፣ ስሉስ፣ ከፍታ እና ምርኩር በመባል በአራት ይከፈላል።

የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት ማለትም ኢትዬጵያ፣ ኬንያ፣ ኤርትራ እና ዩጋንዳ በረጅም ሩጫ የተሻሉ ሲሆኑ ምዕራብ አፍሪካውያን
(ናይጄሪያ፣ ጋና ወ.ዘ.ተ) ደግሞ በመም ተግባራት የተሻሉ ናቸው። ከሰሜን አፍሪካ ሀገራት ሞሮኮ በመካከለኛ እና ረጅም ሩጫ
የሚጠቀሱ ጥቂት ስፖርተኞች ቢኖራትም የተሻለች ሀገር ናት ማለት አይቻልም።

ሀገራችን ኢትዬጵያ በረጅም ሩጫ ግንባር ቀደም ከሆኑ ሀገራት ውስጥ ተጠቃሽ ናት። ኢትዬጵያ በ3000ሜ፣ በ5000ሜ፣ በ10000ሜ፣
በ21 ኪሜ እና በ42 ኪሜ ከ195ሜ. ሪከርድ የሰባበሩና በሜዳሊያዎች የተጥለቀለቁ አትሌቶች ባለቤት ናት። ከአለም በረጅም ሩጫ
የምትፎካከራት ሀገር ኬንያ ብቻ ናት። ኢትዬጵያ በረጅም ሩጫ ግንባር ቀድም የሆነችበት ምክንያት በውል ባይታውቅም የኑሮ
ዘይቤያችን፣ ከምድር ወለል በላይ ያለን ከፍታ እና አመጋገባችን አስተዋፆኦ እንዳለው ይገመታል።

የመማር-ማስተማር መርጃ መሣሪያዎች እና ሥፍራዎች:-

መርጃ መሣሪያዎች:- የአፍሪካ የአትሌቲክስታሪክሚገልጹ ፖስተሮች፤ ስዕሎች፤

ƒƒ ፊልሞች፤ ፎቶዎችና ጽሁፎች

ሥፍራ:-የንድፈ ሀሳብ ትምህርት በሚሰጥበት ክፍል ውስጥ፣

የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል:-

ƒƒ የዕለቱን ትምህርት ርዕስና አላማዎቹን ማስተዋወቅ፣
ƒƒ ተማሪዎችን በጥንድ በጥንድ በማደራጀት የአትሌቲክስ ዘርፎች እነማን እንደሆኑ በጥያቄ ሀሳብ እንዲለዋወጡ
ማበረታታትና የተወያዮበትን ለክፍሉ ተማሪዎች እንዲያቀርቡ ማድረግ፣
ƒƒ ተማሪዎችን ከ3 እሰክ 4 ቡድን ድረስ በማደራጀት የትኞቹ የአፍሪካ ሀገራት በኦሎምፒክ እና በአለም ሻምፒና የተሻለ
ውጤት እንዳለቸው ተራ በተራ ሃሳብ እንዲለዋወጡ ማድረግ፣
ƒƒ ተማሪዎችን ከ5 እሰክ 6 ቡድን ድረስ በማደራጀት ሀገራችን ኢትዬåያ ጥሩ ውጤት ያስመዘገበችበት የአትሌቲክስ ዘርፍ
የትኞው ነው? ለምን ይመስላችኋል? ብሎ በመጠየቅ በየቡድናቸው እንዲወያዮበት ማድረግ፣
ƒƒ የየቡድናቸው ተወካይ የተወያዮበትን እንዲያንፀባርቁ ማበረታታት፣
ƒƒ ተማሪዎች ከሰጡት ሀሳብ በመነሳትበመሰረታ ጽንሰ ሀሳብ በተገለፀው መሰረት በማገናዘብ ማስረዳት፣ በተጨማሪም
ከድህረ-ገጽ (ኢንተርኔት) በመፈለግ ሀሳብ ማግኘት ይቻላል።
ƒƒ ተማሪዎች የተማሩትን ትምህርት መረዳታቸውን ለማረጋገጥ የቃል ጥያቄ በመጠየቅ ማረጋገጥ።

የጤናና ሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ~ 8ኛ ክፍል ~ የመምህር መምሪያ ~ 34

ምዕራፍ 4 አትሌቲክስ

ክትትልና ግምገማ:-
ƒƒ የእለቱን ትምህርት ዝርዝር አላማዎች በትክክል መተግበሩን በጥያቄና መልስ፣ በሚያቀርቡት ውይይት እንዲሁም
ጓደኞቻቸው በሚያስተካክሏቸው ሀሳብ መሰረት መገምገም ይቻላል።

የተግባር ጥያቄዎች መልስ

የተማሪዎች ምላሽ እንዳለ ሆኖ የሚከተሉትን ሀሳቦች ቢያካትት ምልካም ነው

1. የአትሌቲክስ ተግባራት ሁለት ናቸው። እነርሱም የመም እና የሜዳ ተግባራት ይባላሉ። የመምህሩ ተግባራት የሚባለው ሩጫን
ሲይዝ የሜዳ ተግባራት ደግሞ ውርወራ እና ዝላይን ያካትታል።
ƒƒ ሩጫ በራሱ የተለያዩ ክፍሎች አሉት። አጭር ርቀት ሩጫ፣ መካከለኛ እና ረጅም ርቀት ሩጫ በመባል በሶስት ይከፈላል።
አጭር ርቀት ሩጫ የሚባሉት100ሜ፣ 200ሜ እና 400ሜ ሲሆኑ እነዚሁ 100ሜ፣ 200ሜ እና 400ሜ መሰናክል ሩጫንም
ያካትታሉ። የዱላ ቅብብል ሩጫም የአጭር ሩጫ አካል ነው። መካከለኛ ርቀት ሩጫ (800ሜ፣ 1500ሜ) ሲሆን ረጅም
ርቀት ሩጫ ደግሞ 3000ሜ፣ 5000ሜ፣ 10000፣ 21 ኪሜ እና 42 ኪሜ ከ195 ሜትርን ያካትታል።
ƒƒ ውርወራ አሎሎን፣ ዲስከስን፣ ጦርን እና መዶሻን ያካትታል።
ƒƒ ዝላይ በተመሳሳይ ርዝመት፣ ሱልስ፣ ከፍታ እና ምርኩር በመባል በአራት ይከፈላል።

2. የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት ማለትም ኢትዬጵያ፣ ኬንያ፣ ኤርትራ እና ዩጋንዳ በረጅም ሩጫ የተሻሉ ሲሆኑ ምዕራብ አፍሪካውያን
(ናይጄሪያ፣ ጋና)ደግሞ በመም ተግባራት የተሻሉ ናቸው። ከሰሜን አፍሪካ ሀገራት ሞሮኮ በመካከለኛ እና ረጅም ሩጫ የሚጠቀሱ
ጥቂት ስፖርተኞች ቢኖራትም የተሻለች ሀገር ናት ማለት አይቻልም።

3. ሀገራችን ኢትዬጵያ በረጅም ሩጫ ግንባር ቀደም ከሆኑ ሀገራት ውስጥ ተጠቃሽ ናት። ኢትዬጵያ በ3000ሜ፣ በ5000ሜ፣ በ10000፣
በ21 ኪሜ እና በ42 ኪሜ ከ195 ሜ ሪከርድ የሰበሩ በሜዳሊያዎች የተጥለቀለቁ ስፖርተኛች ባለቤት ናት። ከአለም በረጅም ሩጫ
የምትፎካከራት ሀገር ኬንያ ብቻ ናት። ኢትዬጵያ በረጅም ሩጫ ግንባር ቀድም የሆነችበት ምክንያት በውል ባይታውቅም የኑሮ
ዘይቤያችን፣ ከምድር ወለል በላይ ያለን ከፍታ እና አመጋገባችን አስተዋፆኦ እንዳለው ይገመታል።

4.2. የመሰናክልሩጫ (2 ክ/ጊዜ)

ማሳሰቢያ:- ለመሰናክል ሩጫ ሁለት ክፍለጊዜ የተሰጠ ስለሆነ አንድ ክፍለጊዜ የፅንሰ-ሀሳብ ሲሆን ይህንም ከላይ የፅንሰ-ሀሳብ
የመማር-ማስተማር እቅድ መሰረት ማስተማር። አንዱ ክፍለ ጌዜ ደግሞ የተግባር ክፍለ ጊዜ ነው።
ዝርዝር ዓላማ:-ተማሪዎች ይህንን ርዕስ ከተማሩ በኋላ፦
ƒƒ የመሰናክል ሩጫ ከሌሎች የሩጫ አይነቶች በምን እንደሚለይ በትክክል ይለያሉ።
ƒƒ የመሰናክል ሩጫ ስልትን በዝርዝር ያብራራሉ።
ƒƒ የመሰናክል ሩጫ ስልትን ደረጃ በደረጃ በተግባር ሰርተው ያሳያሉ።

መሠረታዊ ጽንሰ-ሀሳብ (ለመምህሩ/ሯ የመነሻ ሀሳብ):-

ƒƒ በመማሪያ መጽሐፉ የተጻፈው እንዳለ ሆኖ በተጨማሪም ከተለያዮ ድህረ-ገጾች በመፈልግ ሀሳቦችን ማበልጸግ ይቻላል::

የመማር-ማስተማር መርጃ መሣሪያዎች እና ሥፍራዎች:-

መርጃ መሣሪያዎች:- 50 ሳ.ሜ እና 60 ሴሜ ከፍታ ያላቸው መሰናክሎች

የጤናና ሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ~ 8ኛ ክፍል ~ የመምህር መምሪያ ~ 35

ምዕራፍ 4 አትሌቲክስ

ሥፍራ:-የተግባር ትምህርት በሚሰጥበት ቦታ፣

የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል:-

ƒƒ የባለፈውን ክፍለ ጊዜ ትምህርት ተማሪዎች እንዲያስታውሱ ማበረታታት፣
ƒƒ የእለቱን ትምህርት ርዕሰና አላማ ለተማሪዎች ማስተዋወቅ፣
ƒƒ ተማሪዎችን በአራት ረድፍ በማሰለፍ የተግባር ትምህርት ለመማር የተሟላ የስፖርት ትጥቅ መልበሳቸውንና ጤንነታቸው
የተሟላ መሆኑን ማረጋገጥ፣
ƒƒ ተማሪዎችን በተሰለፍበት ረድፍ/ቡድን አጠቃላይና ውስን የሰውነት ማሟሟቂያ እንዲሰሩ ማበረታታትና ድጋፍ
ማድረግ፣
ƒƒ ተማሪዎችን በአራት ረድፍ በማደራጀት በመማሪያ መፅሀፉ በተገለጸው የተግባር ልምምድ መሰረት ከ20ሜ. እስከ 30ሜ.
መሰናክል በሌለበት በፍጥነት መሮጥን ማለማመድ፣
ƒƒ ተማሪዎችን በሦስት ረድፍ እንዲደራጁ ማድረግና በመማሪያ መፅሀፉ በተገለጸው የተግባር ልምምድ መሰረት በአጫጭር
መሰናክሎች ላይ በሩጫ ማለፍን በመደጋገም እንዲያከናውኑ ማበረታታት፣
ƒƒ ተማሪዎችን በሁለት ረድፍ እንዲደራጁ ማድረግና በእንብርክክ አነሳስ ትክክለኛ የሆነውን
ƒƒ የመሰናክል ሩጫ ስልት በመደጋገም እንዲለማመዱ ማበረታታት፣
ƒƒ በመጨረሻም የሰውነት ማቀዝቀ¹ እንቅስቃሴ በየቡድናቸው እንዲሰሩ ማበረታታትና በእለቱ ትምህርት እንቅስቃሴያቸውን
አስመልክቶ ደረጃቸውን መግለፅና ለሚቀጥለው ይህን ክህሎት ማሻሻል እንደሚኖርባቸው ማሳሰብ፣

ክትትልና ግምገማ:-
ƒƒ የእለቱን ትምህርት ዝርዝር አላማዎች በትክክል መተግበሩን በጥያቄና መልስ፣ በምልከታ እንዲሁም ጓደኞቻቸው
በሚያስተካክሏቸው መሰረት መገምገም ይቻላል።

የተግባር ጥያቄዎች መልስ

የተማሪዎች ምላሽ እንዳለ ሆኖ የሚከተሉትን ሀሳቦች ቢያካት መልካምነው።

1. የመሰናክል ሩጫ ጥቅም በሶስት ከፍለን ማየት እንችላለን። ለተሳታፊ፣ ለቤተሰብ እና ለሀገር ይጠቅማል።
ƒƒ ሀ. ለተሳታፊው፦ ጥንካሬ እና ሌሎች ሀሳቦች ሊጠቀሱ ይችላሉ
ƒƒ ለ. ለቤተሰብ ፦ ደስታ እና ሌሎች ሀሳቦች ሊጠቀሱ ይችላሉ
ƒƒ ሐ. ለሀገር፦ ለኢኮኖሚ እና ሌሎች ሀሳቦች ሊጠቀሱ ይችላሉ

2. ጎበዝ የነበሩት ተማሪዎች ብዙ ናቸው። እኔም የቸገረኝ ነገር አልነበረም። ምናልባት የመሰናክሉ ቁመት ቢጨምር የተሻለውን/ችውን
ተማሪ ማወቅ ቀላል ይሆን ነበር። ወደፊት የመሰናክሉን ቁመት ጨምረው ሴትና ወንዶችን ለየብቻ ቢያወዳድሩን ደስ ይለኛል።

3. በመሰናክልሩጫ ወቅት ላለመጎዳት ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈለጋል። ሌሎችጥንቃቄዎች እንዳሉ ሆነው ከአቅም በላይ የሆነ መሰናክል
ለመሮጥ መሞከር አደገኛ ስለሆነ ጥንቃቄ ማድረግ አስፈላጊ ነው።

የጤናና ሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ~ 8ኛ ክፍል ~ የመምህር መምሪያ ~ 36

ምዕራፍ 4 አትሌቲክስ

የመልመጃ ጥያቄዎች መልስ

የተማሪዎች ምላሽ እንዳለ ሆኖ የሚከተሉት ሀሳቦችን ቢያካትት መልካም ነው።

1. ከአትሌቲክስ የመም ተግባር ውስጥ አንዱ የመሰናክልሩጫ በመሆኑ የተገናኙ ናቸው።

2. የመሰናክልሩጫከተለመደውሩጫ የተለየነገሩ በመሰናክል ላይእየሮጡ ስለሚከናወን ተጨማሪ ጉልበት እና ስልት ይፈልጋል።

3. ሩጫና የመሰናክል ሩጫ ሁለቱም የመም ተግባር ናቸው።

4.3 የአለሎ ውርወራ (2 ክ/ጊዜ)

ማሳሰቢያ:- ለአሎሎ ውርወራ ሁለት ክፍለጊዜ የተሰጠ ስለሆነ አንድ ክፍለጊዜ የፅንሰ-ሀሳብ ሲሆን ይህንም ከላይ የፅንሰ-ሀሳብ
የመማር-ማስተማር እቅድ መሰረት ማስተማር። አንዱ ክፍለ ጌዜ ደግሞ የተግባር ክፍለ ጊዜ ነው።
ዝርዝር ዓላማ:-ተማሪዎች ይህንን ርዕስ ከተማሩ በኋላ፦
ƒƒ የአለሎ አወራወር ስልትን በሚገባ ይዘረዝራሉ።
ƒƒ ለአለሎ ውርወራ አወንታዊ አመለካከት ያዳበራሉ።
ƒƒ በመስመራዊ አወራወር ስልት ከሶስት ሙከራ ቢያንስ አንዱን አለሎ በትክክል ይወረውራሉ።

የመማር-ማስተማር መርጃ መሣሪያዎች እና ሥፍራዎች:-

መርጃ መሣሪያዎች:- ትንንሽ ኳሶች፣ አለሎ

ሥፍራ:-የተግባር ትምህርት በሚሰጥበት ቦታ፣

መሠረታዊ ጽንሰ-ሀሳብ (ለመምህሩ/ሯ የመነሻ ሀሳብ):-

ƒƒ በመማሪያ መጽሐፉ የተጻፈው እንዳለ ሆኖ በተጨማሪም ከተለያዮ ድህረ-ገጾች በመፈለግ ሀሳቦችን ማበልጸግ ይቻላል::

የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል:-

ƒƒ የባለፈውን ክፍለ ጊዜ ትምህርት ተማሪዎች እንዲያስታውሱ ማበረታታት፣
ƒƒ የእለቱን ትምህርት ርዕሰና አላማ ለተማሪዎች ማስተዋወቅ፣
ƒƒ ተማሪዎችን በአራት ረድፍ በማሰለፍ የተግባር ትምህርት ለመማር የተሟላ የስፖርት ትጥቅ መልበሳቸውንና ጤንነታቸው
የተሟላ መሆኑን ማረጋገጥ፣
ƒƒ ተማሪዎችን በተሰለፍበት ረድፍ/ቡድን አጠቃላይና ውስን የሰውነት ማሟሟቂያ እንዲሰሩ ማበረታታትና ድጋፍ
ማድረግ፣
ƒƒ በሰውነት ማሟሟቂያ ሲሰሩ በተደራጁበት መሰረት ከመሳሪያዉ ጋር በመጀመሪያ ማሰተዋወቅ፣
ƒƒ ኳስ ቀላል ድንጋዮችና የመሳሰሉትን ከዉርወራዉ ስልት ዉጭ እንዲወረውሩ ማድረግ፣
ƒƒ የአለሎዉን አያያዝ ማለማመድ (የአያያዝ መሰረታዊ ስልት)፣
ƒƒ ለመወርወሪያ ከተዘጋጀው ሜዳ ዉጭ በመሆን በየደረጃዉ በመከፋፈል የመስመራዊ የውርወራ ስልትን ያለመሳሪያ
እንዲሰሩ ማበረታታት፣

የጤናና ሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ~ 8ኛ ክፍል ~ የመምህር መምሪያ ~ 37

ምዕራፍ 4 አትሌቲክስ

ƒƒ አለሎ ወይም ትንሽ ኳስ እንዲይዙ በማድረግ በየደረጃዉ የአሰራር ቅደም ተከተሉን በመደጋገም ማለማመድ፣
ƒƒ በመወዳደሪያ ቦታ ወይም በክብ ውስጥ በመግባት ትክክለኛዉ የመስመራዊ አወራወር ስልት በመጠቀም በተደጋጋሚ
እንዲሰሩ ማድረግ፣
ƒƒ በመጨረሻም የሰውነት ማቀዝቀ¹ እንቅስቃሴ በየቡድናቸው እንዲሰሩ ማበረታታትና በእለቱ ትምህርት እንቅስቃሴያቸውን
አስመልክቶ ደረጃቸውን መግለፅና ለሚቀጥለው ይህን ክህሎት ማሻሻል እንደሚኖርባቸው ማሳሰብ፣

ክትትልና ግምገማ:-
ƒƒ የእለቱን ትምህርት ዝርዝር አላማዎች በትክክል መተግበሩን በጥያቄና መልስ፣ በምልከታ እንዲሁም ጓደኞቻቸው
በሚያስተካክሏቸው መሰረት መገምገም ይቻላል።

4.4. የዲስከስ ውርውራ (2 ክ/ጊዜ)

ማሳሰቢያ:- ለዲስከስ ውርወራ ሁለት ክፍለጊዜ የተሰጠ ስለሆነ አንድ ክፍለጊዜ የፅንሰ-ሀሳብ ሲሆን ይህንም ከላይ የፅንሰ-ሀሳብ
የመማር-ማስተማር እቅድ መሰረት ማስተማር። አንዱ ክፍለ ጌዜ ደግሞ የተግባር ክፍለ ጊዜ ነው።
ዝርዝር ዓላማ:-ተማሪዎች ይህንን ርዕስ ከተማሩ በኋላ፦
ƒƒ የዲስከስ አወራወር ስልትን በሚገባ ይዘረዝራሉ።
ƒƒ የዲስከስውርወራ አወንታዊ አመለካከት ያዳበራሉ።
ƒƒ በዲስከስ ውርወራ ሽክርክራዊ አወራወር ስልት ከሶስት ሙከራ ቢያንስ አንዱን ዲስከስ በትክክል ይወረውራሉ።

መርጃ መሣሪያዎች:- ጠፍጣፋ ጣውላ፣ ዲስከስ

ሥፍራ:-የተግባር ትምህርት በሚሰጥበት ቦታ፣

መሠረታዊ ጽንሰ-ሀሳብ (ለመምህሩ/ሯ የመነሻ ሀሳብ):-

ƒƒ በመማሪያ መጽሐፉ የተጻፈው እንዳለ ሆኖ በተጨማሪም ከተለያዮ ድህረ-ገጾች በመፈልግ ሀሳቦችን ማበልጸግ ይቻላል::

የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል:-

ƒƒ የባለፈውን ክፍለ ጊዜ ትምህርት ተማሪዎች እንዲያስታውሱ ማበረታታት፣
ƒƒ የእለቱን ትምህርት ርዕሰና አላማ ለተማሪዎች ማስተዋወቅ፣
ƒƒ ተማሪዎችን በአራት ረድፍ በማሰለፍ የተግባር ትምህርት ለመማር የተሟላ የስፖርት ትጥቅ መልበሳቸውንና ጤንነታቸው
የተሟላ መሆኑን ማረጋገጥ፣
ƒƒ ተማሪዎችን በተሰለፍበት ረድፍ/ቡድን አጠቃላይና ውስን የሰውነት ማሟሟቂያ እንዲሰሩ ማበረታታትና ድጋፍ
ማድረግ፣
ƒƒ በሰውነት ማሟሟቂያ ሲሰሩ በተደራጁበት መሰረት ከመሳሪያዉ ጋር በመጀመሪያ ማስተዋወቅ፣
ƒƒ በፊት በተደራጁበት መሰረት የዲስከሱን አያያዝ ማለማመድ፣
ƒƒ በፊት በተደራጁበት አንድ እግርን ወደ ፊት በማስቀደም ዲስከሱን ወደ ፊት ማሽከርከርን ማለማመድ፣
ƒƒ በፊት በተደራጁበት ዲስከስ ወደ ላይ እየወረወሩ በጠርዙ መሬት ላይ እንዲያርፍ ማድረግ

የጤናና ሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ~ 8ኛ ክፍል ~ የመምህር መምሪያ ~ 38

ምዕራፍ 4 አትሌቲክስ

ƒƒ በፊት በተደራጁበት ያለመሳሪያ ሽክርክራዊ ስልትን በመከፋፈል በየደረጃዉ ማለማመድ

ƒƒ በፊት በተደራጁበት በዲስከሱ ሽክርክራዊ ስልትን በመከፋፈል በየደረጃዉ ማለማመድ፣
ƒƒ በፊት በተደራጁበት በትክክለኛዉ የዲስከስ መወርወሪያ ሜዳ ወይም ክብ በግባት አጠቃላይ ስልቱን በመጠቀም
ማለማመድ፣
ƒƒ በፊት በተደራጁበት የዲስከሱን ዉርወራ በመደጋገም ማለማመድና የሚሰሩ ስህተቶችን እየተከታተሉ ማረም፣
ƒƒ በመጨረሻም የሰውነት ማቀዝቀ¹ እንቅስቃሴ በየቡድናቸው እንዲሰሩ ማበረታታትና በእለቱ ትምህርት እንቅስቃሴያቸውን
አስመልክቶ ደረጃቸውን መግለፅና ለሚቀጥለው ይህን ክህሎት ማሻሻል እንደሚኖርባቸው ማሳሰብ፣

ክትትልና ግምገማ:-
ƒƒ የእለቱን ትምህርት ዝርዝር አላማዎች በትክክል መተግበሩን በጥያቄና መልስ፣ በምልከታ እንዲሁም ጓደኞቻቸው
በሚያስተካክሏቸው መሰረት መገምገም ይቻላል።

የተግባር ጥያቄዎች መልስ

የተማሪዎች ምላሽ እንዳለ ሆኖ የሚከተሉትን ሀሳቦች ቢያካትት መልካምነው።

1. የዲስከስ ውርወራን መለማመድ ከወገብ በላይ ያለውን የሰውነት ክፍል ያዳብራል፤የሰውነት ሚዛን መጠበቅን ያለማምዳል ወ.ዘ.ተ

2. የዲስከስ ውርወራ እንቅስቃሴ የሚከብድ የሰውነት ሚዛን መጠበቅ ነው፤

3. የዲስከስ ውርወራ እንቅስቃሴ ያልተጠበቀ ከፍተኛ ጉዳት ሊያደርስ ስለሚችል ከፍተኛ ጥንቃቄ ያስፈልጋል። ዲስከስ ሳይወረወር
ከእጅ ሊያፈተልክ ስሊሚችል አንድ ተማሪ በማይወረበርበት አቅጣጫ ከወርዋሪው ቢያንስ10 ሜትር መራቅ አለበት።

የመልመጃ መልስ
የተማሪዎችምላሽእንዳለሆኖየሚከተሉትንሀሳቦችቢያካትት መልካምነው።

1. የዲስከስ ውርወራ የአሰራር ስልቶች የሚከተሉት ናቸው።

ƒƒ ዲስከስ አያያዝና መሰረታዊ አቋቋምን ማወቅ፤
ƒƒ ኃይል ለመሰብሰብ የእጅ ዉዝዋዜን በሚገባ መከወን መቻል፤
ƒƒ ሚዛንን ሳይስቱ በፍጥነት መሽከርከር መቻልእና
ƒƒ ዲስከሱን በሚገባ ወርውሮ የሰውነት ሚዛን መጠበቅ ናችው።

2. እንደተማሪው/ዋ ይወሰናል፤ ዋናው ቁምነገር ምክንያታቸው ነው።

3. በዲስከስ ውርወራ ቀዳሚ ለመሆን ጠንካራ እና ቀልጣፋ መሆን ይጠይቃል፤ጠንካራ በርቀት ለመወርወር እና ሚዛን ለመጠበቅ
ደግሞ ቅልጥፍና ወሳኝ ነው። ከስነ-ልቦና አንፃርም በራስ መተማመን፣ ቁርጠኝነት ከሌለ አይሆንም።

4. በዲስከስ ውርወራ ሀገራችን ሊያስጠር የሚችል ስፖርተኛ አለ ከተባል ለምን? አል ካልተባለም ዋናው ምክንያቱ ስለሆን
ምክንያታቸውን እንዲያሟግቱ እድል ይስጡ። ባንዲራችን በአለም አቀፍ ደረጃ ያውለበለቡ በአብዛኛው ተማሪ የነበሩ ናቸው።

የጤናና ሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ~ 8ኛ ክፍል ~ የመምህር መምሪያ ~ 39

ምዕራፍ 4 አትሌቲክስ

4.5. የከፍታ ዝላይ (2 ክ/ጊዜ)

ዝርዝር ዓላማ:-ተማሪዎች ይህንን ርዕስ ከተማሩ በኋላ፦
ƒƒ በከፍታ ዝላይ ውስጥ የሚገኙ የዝላይ አይነቶችን በትክክል ይዘረዝራሉ።
ƒƒ የከፍታ ዝላይ ስልቶን በዝርዝር ያብራራሉ።
ƒƒ ከከፍታ ዝላይ የስትራድል ስልትን ደረጃ በደረጃ በተግባር ሰርተው ያሳያሉ።

መርጃ መሣሪያዎች:- ለከፍታ ዝላይ የሚያገለግሉ ቋሚ፣ አግዳሚ እና ፍራሽ

ሥፍራ:-የተግባር ትምህርት በሚሰጥበት ቦታ፣

መሠረታዊ ጽንሰ-ሀሳብ (ለመምህሩ/ሯ የመነሻ ሀሳብ):-

ƒƒ በመማሪያ መጽሐፉ የተጻፈው እንዳለ ሆኖ በተጨማሪም ከተለያዮ ድህረ-ገጾች በመፈለግ ሀሳቦችን ማበልጸግ ይቻላል::

የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል:-

ƒƒ የባለፈውን ክፍለ ጊዜ ትምህርት ተማሪዎች እንዲያስታውሱ ማበረታታት፣
ƒƒ የእለቱን ትምህርት ርዕሰና አላማ ለተማሪዎች ማስተዋወቅ፣
ƒƒ ተማሪዎችን በአራት ረድፍ በማሰለፍ የተግባር ትምህርት ለመማር የተሟላ የስፖርት ትጥቅ መልበሳቸውንና ጤንነታቸው
የተሟላ መሆኑን ማረጋገጥ፣
ƒƒ ተማሪዎችን በተሰለፍበት ረድፍ/ቡድን አጠቃላይና ውስን የሰውነት ማሟሟቂያ እንዲሰሩ ማበረታታትና ድጋፍ
ማድረግ፣
ƒƒ ተማሪዎችን በሁለት ረድፍ እንዲደራጁ ማድረግና በቀጥታ ዝላይ በፍራሽ ላይ እየዘለሉ ማረፍን ያለአግዳሚና በአግዳሚ
እንዲሰሩ በመደጋገም ማበረታታት፣
ƒƒ አገዳሚውን በከፍታ መካከለኛ በማድረግ የመቀስ ዝላይን በመደጋገም እንዲያከናውኑ ማበረታታት፣
ƒƒ ተማሪዎችን በሁለት ረድፍ እንዲደራጁ ማድረግና የስትራድል ስታይል ዝላይን በመደጋገም እንዲለማመዱ ማበረታታት፣
ƒƒ በመጨረሻም የሰውነት ማቀዝቀ¹ እንቅስቃሴ በየቡድናቸው እንዲሰሩ ማበረታታትና በእለቱ ትምህርት እንቅስቃሴያቸውን
አስመልክቶ ደረጃቸውን መግለፅና ለሚቀጥለው ይህን ክህሎት ማሻሻል እንደሚኖርባቸው ማሳሰብ፣ በተጨማሪም
በመማሪያ መፅሀፉ በተቀመጠው መልመጃ ላይ መልሳቸውን ምን እንደሆነ መቀበል።

ክትትልና ግምገማ:-
ƒƒ የእለቱን ትምህርት ዝርዝር አላማዎች በትክክል መተግበሩን በጥያቄና መልስ፣ በምልከታ እንዲሁም ጓደኞቻቸው
በሚያስተካክሏቸው መሰረት መገምገም ይቻላል።

የጤናና ሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ~ 8ኛ ክፍል ~ የመምህር መምሪያ ~ 40

ምዕራፍ 5 ጅምናስቲክስ

ምዕራፍ

5 ጅምናስቲክስ

የክፍለ ጊዜ ብዛት፡ 9

አጠቃላይ ዓላማዎች፡

አጠቃላይ ዓላማ:-ተማሪዎች ይህንን ምዕራፍ ከተማሩ በኋላ፡-

ƒƒ የጅምናስቲክስን መሰረታዊ ህጎችን ይረዳሉ።
ƒƒ የወለል ጅምናስቲክስን የተግባር ስራን ያዳብራሉ።
ƒƒ የተለያዩ የመሳሪያ ጅምናስቲክስ እንቅስቃሴዎችን የተግባር ስራን ይገነዘባሉ።
ƒƒ የጅምናስቲክስ እንቅስቃሴዎች የሚሰጡትን ጥቅም ያደንቃሉ።

መግቢያ
የጅምናስቲክስ ስፖርት ረጅምና ውስብስብ ታሪካዊ ሂደቶችን ያለፈ ከመሆኑም ባሻገር ዓለም አቀፋዊ ይዘት ያለውና ለሁሉም ስፖርት
መሰረት ነው። ስለሆነም በዚህ ምዕራፍ ውስጥ ተካተው መማር ያለብን ርዕሶች መካከል የጅምናስቲክስ መሰረታዊ ህጎች፣ በረጅም
ወደፊት መንከባለል፣ በእጅ መቆም፣ በእጅ መቆምና ወደፊት መንከባለል እና በጥንድ አግዳሚ ዘንግ ላይ የሚሰሩ ተግባሮችን ነው።

5.1. የጅምናስቲክስመሰረታዊ ህጎች (1 ክ/ጊዜ)

ዝርዝር ዓላማ:-ተማሪዎች ይህንን ርዕስ ተምረው ካጠናቀቁበኋላ:-
ƒƒ መሰረታዊ የጅምናስቲክስ ህጎችን ይገነዘባሉ።
ƒƒ በኦሎምፒክ ጨዋታዎች ላይ ከሚቀርቡ የጅምናስቲክስ ውድድሮች መካከል ቢያንስ አራቱን ይዘረዝራሉ።
ƒƒ የጅመናስቲክስ የውድድር ህጎችን በመለየት ለወደፊቱ ተሳታፊ ለመሆን ፍላጎት ይኖራቸዋል።

መሠረታዊ ጽንሰ-ሀሳብ (ለመምህሩ/ሯ የመነሻ ሀሳብ):-

የጅምናሰቲክስ እንቅስቃሴዎች እንደ አንድ የውድድር ስፖርት ከተካተቱበት ጊዜ ጀምሮ የውድድር ዓይነት፤ፆታ፤ውድድሩ
የሚመራበት ህግና ስርዓት፤ ውድድሩን የሚመሩትን ዳኞች እና የነጥብ አሰጣጥን በተመለከተ በዝርዝር ህግ ወጥቶለታል።

የአርትስቲክ ጅምናሰቲክስ የውድድር ዓይነቶች ለወንዶች 6 ለሴቶች 4 የጅምናስቲክስ ውድድር ሲሆን ቁጥራቸው ከ4-9 የሚደርሱ
የዳኞች ቡድን ውድድሩን እንዲመሩት ይደረጋል። በተወሰነ የውድድር ክፍለ ጊዜ ሰዓት ተወዳዳሪዎች በተጠቀሱት የውድድር

የጤናና ሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ~ 8ኛ ክፍል ~ የመምህር መምሪያ ~ 41

ምዕራፍ 5 ጅምናስቲክስ

ዓይነቶች ሰርተው በተገኘው ድምር ውጤት አሸናፊው ይለያል። ይህ ህግ በሀገር፤ በአህጉርና በዓለም አቀፍ ደረጃ ለሚካሄዱት
የውድድር ዓይነቶች የሚተገበር ሲሆን እንደየሀገሩ የጅምናሰቲክ ስፖርት ዕድገትና የዳኞች ቁጥር ከፍና ዝቅ ሊል ይችላል።

የመማር-ማስተማር መርጃ መሣሪያዎች እና ሥፍራዎች:-

መርጃ መሣሪያዎች:- የጅምናስቲክስ የውድድር ህጎችን የሚገልጹ ፖስተሮች፤ ስዕሎች፤

ƒƒ ፊልሞች፤ ፎቶዎችና ጽሁፎች

ሥፍራ:-የንድፈ ሀሳብ ትምህርት በሚሰጥበት ክፍል ውስጥ፣

የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል:-

ƒƒ የዕለቱን ትምህርት ርዕስና አላማዎቹን ማስተዋወቅ፣
ƒƒ ተማሪዎችን በጥንድ በጥንድ በማደራጀት የጅምናስቲክስ ህግን ለምን መማር አስፈለገ ለሚለውን ጥያቄ ሀሳብ
እንዲለዋወጡ ማበረታታትና የተወያዮበትን ለክፍሉ ተማሪዎች እንዲያቀርቡ ማድረግ፣
ƒƒ ተማሪዎችን ከ3 እሰክ 4 ቡድን ድረስ በማደራጀት የጅምናስቲክስ የውድድር አይነቶች ለምን በሁለት መክፈል አስፈለገ?
እና የጅምናስቲክስ ስፖርተኛ የውድድር ሕግን አለማወቅ ወይም አለመተግበር ምን ጉዳት አለው? በሁለቱ ጥያቄዎች
ላይ ተራ በተራ ሀሳብ እንዲለዋወጡ ማድረግ፣
ƒƒ ከየቡድኑ በተወካያቸው አመካኝነት የተወያዮበትን ሀሳብ እንዲያንፀባርቁ ማበረታታት እና በመማሪያ መፅሀፉ በተሰጠው
ፅንሰሀሳብ መሰረት ለተግባሩ የማጠቃለያ ሀሳብ መስጠት፣
ƒƒ በመጨረሻም በኦሎምፒክ ጨዋታ እና በአለም አቀፍ ሻምፒዮና ላይ የሚቀርቡ የጅምናስቲክስ የውድድር አይነቶችን
በአጭሩ በማስረዳት ማጠቃለል፣
ƒƒ ተማሪዎች የተማሩትን ትምህርት መረዳታቸውን ለማረጋገጥ የቃል ጥያቄ በመጠየቅ ማረጋገጥ።

ክትትልና ግምገማ:-
ƒƒ የእለቱን ትምህርት ዝርዝር አላማዎች በትክክል መተግበሩን በጥያቄና መልስ፣ በሚያቀርቡት ውይይት እንዲሁም
ጓደኞቻቸው በሚያስተካክሏቸው ሀሳብ መሰረት መገምገም ይቻላል።

5.2. የነጻ ጅምናስቲክስ (4 ክ/ጊዜ)

5.2.1 በረጅም ወደፊትመንከባለል (Dive roll) (- ክ/ጊዜ)

ዝርዝር ዓላማ:-ተማሪዎች ይህንን ርዕስ ተምረው ካጠናቀቁበኋላ:-
 በረጅም ወደፊት መንከባለልን የእንቅስቃሴ አሠራር ቅደም ተከተልን በትክክል ይገልፃሉ።

 በረጅም ወደፊት መንከባለል እንቅስቃሴን በተግባር ሰርተው ያሳያሉ።

 በረጅም ወደፊት መንከባለል እንቅስቃሴን በትክክል የሚሰሩ ጓደኞቻቸውን ያደንቃሉ።

የመማር-ማስተማር መርጃ መሣሪያዎች እና ሥፍራዎች:-

መርጃ መሣሪያዎች:-
ƒƒ ከትምህርቱ ጋር ተያያዥነት ያላቸው ሥዕሎችና ፎቶዎች

የጤናና ሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ~ 8ኛ ክፍል ~ የመምህር መምሪያ ~ 42

ምዕራፍ 5 ጅምናስቲክስ

ƒƒ ፍራሽ

ሥፍራ:-የተግባር ትምህርት የሚሰጥበት በሳር የተሸፈነ ሜዳ፣

የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል:-

ƒƒ የባለፈውን ክፍለ ጊዜ ትምህርት ተማሪዎች እንዲያስታውሱ ማበረታታት፤
ƒƒ የእለቱን ትምህርት ርዕሰና አላማ ለተማሪዎች ማስተዋወቅ፤
ƒƒ ተማሪዎችን ከ4 እስከ 6 ቡድን (ምድብ) በማደራጀት የሰውነት ማሟሟቅያ እንቅስቃሴዎች ከቀላል እንቅስቃሴዎች
በመጀመር ለዋናው የእለቱ ተግባር ቅድመ ዝግጅት እንዲያደርጉ ማበረታታት፤በውስን የሰውነት ማሟሟቂያ ጊዜ
ለአንገት፤ለእጆችና ለትከሻቸውን አካባቢ ትኩረት መስጠት እንዳለባቸው ማስገንዘብ፤
ƒƒ ለመስሪያ በተዘጋጀው ፍራሽ ቁጥር ልክ ተማሪዎችን ማደረጀትና ወደፊት መንከባለልን እንቅስቃሴ እንዲለማመዱ
ማድረግ፤
ƒƒ ሁሉም ተማሪዎች በሚመለከቱበት ቦታ ሆነው በረጅም ወደፊት መንከባለልን መስራት የሚችሉ ተማሪዎችን በመጋበዝ
ሰርተው እንዲያሰዮ ማበረታታትና ሌሎችም በሚገባ እንዲመለከቱ ማድረግ፤
ƒƒ በረጅም ወደፊት መንከባለልን አሰራር የሚያሳይ ገላጭ ስዕል ካለ ማሳየትና ካዩትም በመነሳት ስለአሰራሩ አስተያየት
እንዲሰጡ መጠየቅ፤
ƒƒ በረጅም ወደፊት እንደት እንደሚሰራ በመማሪያ መጽሀፉ የተጠቀሰውን የአሰራር ቀደም ተከተል በአጭሩ ማብራራት፤
ƒƒ የክፍሉን ተማሪዎች እንደቀረበው የፍራሽ መጠንና ቁጥር ወይም የቦታ ስፋት በቡድን ማደራጀትና በረጅም ወደ ፊት
መንከባለል ከመጀመራቸው አስቀድሞ በአጭር ወደ ፊት መንከባለልን እንዲለማመዱ ማድረግ፤
ƒƒ ተማሪዎችን በተጠቀለለ ፍራሽ ፊት ለፊት በረድፍ በማደራጀት በተጠቀለለው ፍራሽ ላይ በረጅም ወደፊት መንከባለልን
ከአንድ እርምጃ ርቀትና ከዚያም የተወሰነ ርቀት በመንደርደር እነዲለማመዱ ማበረታታት፤ይህን እንቅስቃሴ ሲሰሩ
ከጎናቸው ሆኖ ድጋፍ ማድረግ ያስፈልጋል
ƒƒ የተጠቀለለውን ፍራሽ በማንሳት በተዘረጋው ፍራሽ ላይ ከላይ በተገለጸው መሰረት በረጅም ወደፊት መንከባለልን
እንዲሰሩ ማለማመድና ይህንን እንቅስቃሴ ሲሰሩ ፍራሹ ላይ ራቅ ብሎ እጅ የሚያርፍበትን ቦታ ምልክት ማድረግና
ይህንን ምልክት በመጠቀም እግሮቻቸውን ከጉልበት ሳያጥፉ በእጆቻቸው ለመድረስ ሙከራ እያደረጉ እንዲንከባለሉ
ማድረግ፤ከጎናቸው ሆኖ ድጋፍ ማድረግ ያስፈልጋል፤
ƒƒ ይህንን እንቅስቃሴ ሲሰሩ በጣም ትኩረት መስጠት የሚያስፈልገው አንገት ወደ ደረት መቀበርና መሬት ቀድሞ ማረፍ
ያለበት ማጅራት መሆኑን ማስገንዘብ ያስፈልጋል፤
ƒƒ ከተማሪዎች መካከል በትክክል የሰሩትን በመለየት ወጥተው ለሁሉም ተማሪዎች ሰርተው እንዲያሳዮ እድል መስጠት፤
ƒƒ ሌሎች ተማሪዎችም ጓደኞቻቸው በሰሩት መሰረት ስህተታቸውን በማሰተካከል እንዲለማመዱ ተከታታይ ግብረመልስ
መስጠት፤
ƒƒ የአካል ጉዳተኛ ተማሪዎች ክፍል ውስጥ ካሉና የአካል ጉዳታቸው በረጅም ወደፊት መንከባለልን ለመስራት የሚፈቅድላቸው
ከሆነ ልዩ ትኩረት አድርጎ እንዲሳተፉ ማድረግ፤ የማያሳትፋቸው ከሆነ ግን በሌላ ተመሣሣይ እንቅስቃሴ እንዲሳተፉ
ማድረግ፤
ƒƒ በመጨረሻም የሰውነት ማቀዝቀ¹ እንቅስቃሴ በየቡድናቸው እንዲሰሩ ማበረታታትና በእለቱ ትምህርት እንቅስቃሴያቸውን
አስመልክቶ ደረጃቸውን መግለፅና ለሚቀጥለው ጊዚያት በመለማመድ በረጅም ወደፊት መንከባለል በመለማመድ
ማሻሻል እንደሚኖርባቸው ማሳሰብ፤
የጤናና ሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ~ 8ኛ ክፍል ~ የመምህር መምሪያ ~ 43
ምዕራፍ 5 ጅምናስቲክስ

ክትትልና ግምገማ:-
ƒƒ የአሰራር ቅደም ተከተሉን ተግባራዊ በማድረግ እየተለማመዱ ስለመሆናቸው ምልከታና ግብረመልስ መስጠት፤
ƒƒ በረጅም ወደፊት ለመንከባለል ለመስራት ወሳኝ የሆኑ የአሰራር ቅደም ተከተሎችን እንዲያስረዱ የቃል ጥያቄ በመጠየቅ
ማረጋገጥ፤

5.2.2. በእጅ መቆም (- ክ/ጊዜ)

ዝርዝር ዓላማ:-ተማሪዎች ይህንን ርዕስ ተምረው ካጠናቀቁበኋላ:-
ƒƒ በእጅ ለመቆም የምንከተላቸውን የአሰራር ቅድም ተከተል በትክክል ይገልጻሉ::
ƒƒ በእጅ መቆምን በተግባር ሰርተው ያሳያሉ::
ƒƒ በእጅ መቆምን በፍላጎት ይሰራሉ::

የመማር-ማስተማር መርጃ መሣሪያዎች እና ሥፍራዎች:-

መርጃ መሣሪያዎች:-
ƒƒ ከትምህርቱ ጋር ተያያዥነት ያላቸው ሥዕሎችና ፎቶዎች
ƒƒ ፍራሽ

ሥፍራ:-የተግባር ትምህርት የሚሰጥበት በሳር የተሸፈነ ሜዳ፣

የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል:-

ƒƒ የባለፈውን ክፍለ ጊዜ ትምህርት ተማሪዎች እንዲያስታውሱ ማበረታታት፣
ƒƒ የእለቱን ትምህርት ርዕሰና አላማ ለተማሪዎች ማስተዋወቅ፣
ƒƒ ተማሪዎችን ከ4 እስከ 6 ቡድን (ምድብ) በማደራጀት የሰውነት ማሟሟቅያ እንቅስቃሴዎች ከቀላል እንቅስቃሴዎች
በመጀመር ለዋናው የእለቱ ተግባር ቅድመ ዝግጅት እንዲያደርጉ ማበረታታት፤በውስን የሰውነት ማሟሟቂያ
ጊዜየክንዶች፤የእጆችና የትከሻቸውን አካባቢ ትኩረት መስጠት እንዳለባቸው ማስገንዘብ፤
ƒƒ የክፍሉን ተማሪዎች እንደቀረበው የፍራሽ መጠንና ቁጥር ወይም የቦታ ስፋት በቡድን ማደራጀትና በእጅ መቆምን
መስራት የሚችሉ ተማሪዎች ካሉ ሰርተው እንዲያሳዮመጠየቅና ሌሎች ሲሰሩ እንዲመለከቱ ማድረግ
ƒƒ ትክክለኛውን የድጋፍ አሰጣጥ በመጠቀም በመማሪያ መጽሐፉ በስዕልና የእንቅስቃሴው አሰራር በተገለፀው መሰረት
በእጅ መቆምን ሰርቶ ማሳየት፤
ƒƒ ፍራሾቹ ሊያስተናግዱ በሚችሉት ቁጥር ልክ የክፍሉን ተማሪዎች በቡድን መክፈልና በመስመር እንደተሰለፉ ተራ
በተራበጓደኛቸው ድጋፍ እየተደረገላቸው እንዲለማመዱ ማድረግ፤
ƒƒ ከመቆም በአንድ እግር እርምጃ ወስዶ በእጆች መቆምን ነጻ ሆነው እንዲለማመዱ ማድረግና ተገቢውን የልምምድ ጊዜ
መስጠት፤
ƒƒ ከመንደርደር በእጅ መቆምን እንዲለማመዱ ማድረግና የተሻለ የሰሩትን ተማሪዎች ወጥተው እንዲሰሩ ማበረታታት፣
ƒƒ ሌሎች ተማሪዎችም ጓደኞቻቸው በሰሩት መሰረት ስህተታቸውን በማሰተካከል እንዲለማመዱ ተከታታይ ግብረመልስ
መስጠት፣

የጤናና ሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ~ 8ኛ ክፍል ~ የመምህር መምሪያ ~ 44

ምዕራፍ 5 ጅምናስቲክስ

ƒƒ ተማሪዎች ሲለማመዱ ትኩረት መስጠት ያለባቸውን ነጥቦች ማስገንዘብ ሲሆን እነዚህም እጆች ቀጥ ብለው መዘርጋትና
ክብደትን መሸከም አለባቸው፤ እግሮች ሲነሱ መጠነኛ ኃይል መጠቀም ያስፈልጋል፤ በፍጥነት ተወርውረው እንዳይሄዱ
ማስገንዘብ፣
ƒƒ የአካል ጉዳተኛ ተማሪዎች ክፍል ውስጥ ካሉና የአካል ጉዳታቸው በእጅ መቆምን ለመስራት የሚፈቅድላቸው ከሆነ ልዩ
ትኩረት አድርጎ እንዲሳተፉ ማድረግ፤ የማያሳትፋቸው ከሆነ ግን በሌላ ተመሣሣይ እንቅስቃሴ እንዲሳተፉ ማድረግ፤
ƒƒ በመጨረሻም የሰውነት ማቀዝቀ¹ እንቅስቃሴ በየቡድናቸው እንዲሰሩ ማበረታታትና በእለቱ ትምህርት እንቅስቃሴያቸውን
አስመልክቶ ደረጃቸውን መግለፅና ለሚቀጥለው ጊዚያት በመለማመድ በእጅ መቆም በመለማመድ ማሻሻል
እንደሚኖርባቸው ማሳሰብ

ክትትልና ግምገማ:-
ƒƒ የአሰራር ቅደም ተከተሉን ተግባራዊ በማድረግ እየተለማመዱ ስለመሆናቸው ምልከታና ግብረመልስ መስጠት፤
ƒƒ በእጅ መቆምን ለመስራት ወሳኝ የሆኑ የአሰራር ቅደም ተከተሎችን እንዲያስረዱ የቃል ጥያቄ በመጠየቅ፤
ƒƒ በዚህ ክፍለ ጊዜ ውስጥ የተለማመዱትን እንቅስቃሴ በትርፍ ጊዚያቸው ከግድግዳ ጋር ወይም በሰው ድጋፍ በጥንቃቄ
መለማመድ እንዳለባቸው ማስገንዘብ፣

5.2.3. በእጅ መቆምና ወደፊት መንከባለል (- ክ/ጊዜ)

ዝርዝር ዓላማ:-ተማሪዎች ይህንን ርዕስ ተምረው ካጠናቀቁበኋላ:-
ƒƒ በእጅ መቆምና መንከባለልን ለመስራት ወሳኝ የሆኑትን የአሰራር ቅደም ተከተሎችን ይለያሉ::
ƒƒ በእጅ መቆምና ወደፊት መንከባለልን በተግባር ሰርተው ያሳያሉ::
ƒƒ በእጅ መቆምና ወደፊት መንከባለልን በተሻለ ሁኔታ ለመስራት በልምምድ ጊዜ ፍላጎት ያሳያሉ::

የመማር-ማስተማር መርጃ መሣሪያዎች እና ሥፍራዎች:-

መርጃ መሣሪያዎች:-
ƒƒ ከትምህርቱ ጋር ተያያዥነት ያላቸው ሥዕሎችና ፎቶዎች፣
ƒƒ ፍራሽ

ሥፍራ:-የተግባር ትምህርት የሚሰጥበት በሳር የተሸፈነ ሜዳ፣

የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል:-

ƒƒ የባለፈውን ክፍለ ጊዜ ትምህርት ተማሪዎች እንዲያስታውሱ ማበረታታት፣
ƒƒ የእለቱን ትምህርት ርዕሰና አላማ ለተማሪዎች ማስተዋወቅ፣
ƒƒ ተማሪዎችን ከ4 እስከ 6 ቡድን (ምድብ) በማደራጀት የሰውነት ማሟሟቅያ እንቅስቃሴዎች ከቀላል እንቅስቃሴዎች
በመጀመር ለዋናው የእለቱ ተግባር ቅድመ ዝግጅት እንዲያደርጉ ማበረታታት፤በውስን የሰውነት ማሟሟቂያ
ጊዜለክንዶች፣ ለእጆችና ለትከሻቸውን አካባቢ ትኩረት መስጠት እንዳለባቸው ማስገንዘብ፤
ƒƒ የክፍሉን ተማሪዎች እንደቀረበው የፍራሽ መጠንና ቁጥር ወይም የቦታ ስፋት በቡድን ማደራጀትና በእጅ መቆምና ወደፊት
መንከባለልን መስራት የሚችሉ ተማሪዎች ካሉ ሰርተው እንዲያሳዮ መጠየቅና ሌሎች ሲሰሩ እንዲመለከቱ ማድረግ፤
ƒƒ በተደራጁበት ሁኔታ ከአሁን በፊት የተማሩትን በእጅ መቆምን በተወሰነ ድግግሞሽ እንዲሰሩ ማበረታታት፤
የጤናና ሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ~ 8ኛ ክፍል ~ የመምህር መምሪያ ~ 45
ምዕራፍ 5 ጅምናስቲክስ

ƒƒ በእጅ መቆምና ወደፊት መንከባለልን በተግባር ሰርቶ ማሳየትና በእጅ መቆምና ወደፊት መንከባለልን ለመስራት
የሚጠቅሙ አስፈላጊ የሆኑ የሰውነት ሁኔታዎችንና የአሰራር ቅድም ተከተሎችን ማስገንዘብ፤
ƒƒ በእጅ መቆምና ወደፊት መንከባለልን በድጋፍ (በረዳት) እንዲለማመዱ ማበረታታትና የተሻለ የሰሩትን ተማሪዎች
ወጥተው እንዲሰሩ ማድረግ፤
ƒƒ ሌሎች ተማሪዎችም ጓደኞቻቸው በሰሩት መሰረት ስህተታቸውን በማሰተካከል እንዲለማመዱ ተከታታይ ግብረመልስ
መስጠት እንድሁም ይህ እንቅስቃሴ ሲሰረ ትኩረት መደረግ ያለበት ከረዳት ጋር ሆኖ ቢሰራ ይመረጣል፤
ƒƒ በግብረ መልሱ የሚካተቱ ዋናዋና ነጥቦች ከመንከባለል በፊት መጀመሪያ በእጅ መቆማቸውን ርግጠኛ መሆን
እንዳለባቸው፤ ወደፊት ለመንከባለል የራስ ወደ ደረት መቀበር መረሳት እንደሌለበት፤ አንገት ወደ ደረት መቀበርና መሬት
ቀድሞ ማረፍ ያለበት ማጅራት መሆኑን በጥብቅ ማስገንዘብ፤
ƒƒ የአካል ጉዳተኛ ተማሪዎች ክፍል ውስጥ ካሉና የአካል ጉዳታቸው በእጅ መቆምና ወደፊት መንከባለል ለመስራት
የሚፈቅድላቸው ከሆነ ልዩ ትኩረት አድርጎ እንዲሳተፉ ማድረግ፤ የማያሳትፋቸው ከሆነ ግን በሌላ ተመሣሣይ
እንቅስቃሴ እንዲሳተፉ ማድረግ፤
ƒƒ በመጨረሻም የሰውነት ማቀዝቀ እንቅስቃሴ በየቡድናቸው እንዲሰሩ ማበረታታትና በእለቱ ትምህርት እንቅስቃሴያቸውን
አስመልክቶ ደረጃቸውን መግለፅና ለሚቀጥለው ጊዚያት በመለማመድ በእጅ መቆምና ወደፊት መንከባለል በመለማመድ
ማሻሻል እንደሚኖርባቸው ማሳሰብ፤

ክትትልና ግምገማ:-
ƒƒ የአሰራር ቅደም ተከተሉን ተግባራዊ በማድረግ እየተለማመዱ ስለመሆናቸው ምልከታና ግብረመልስ መስጠት፤
ƒƒ በእጅ መቆምና ወደፊት መንከባለልን ለመስራት ወሳኝ የሆኑ የአሰራር ቅደም ተከተሎችን እንዲያስረዱ የቃል ጥያቄ
በመጠየቅ፤
ƒƒ በዚህ ክፍለ ጊዜ ውስጥ የተለማመዱትን እንቅስቃሴ በትርፍ ጊዚያቸው በጥንቃቄ መለማመድ እንዳለባቸው
ማስገንዘብ(እንቀስቃሴ ሲሰራ ከረዳት ጋር ሆኖ ቢሰራ ይመረጣል)፤

5.2.4 በእጅ መስፈንጠር (- ክ/ጊዜ)

ዝርዝር ዓላማ:-ተማሪዎች ይህንን ርዕስ ተምረው ካጠናቀቁበኋላ:-
ƒƒ በእጅ ወደፊት መስፈንጠርን ለመስራት ከአሰራር ቅደም ተከተሎች መካከል ቢያንስ ሦስቱን ይገልጻሉ::
ƒƒ በእጅ ወደፊትና ወደኋላ መስፈንጠርን በፊት ከሚሰሩት በተሻለ በተግባር ይስራሉ::
ƒƒ በእጅ ወደፊትና ወደኋላ መስፈንጠርን በግላቸው ለመስራት ተነሳሽነት ያሳያሉ::

የመማር-ማስተማር መርጃ መሣሪያዎች እና ሥፍራዎች:-

መርጃ መሣሪያዎች:-
ƒƒ ከትምህርቱ ጋር ተያያዥነት ያላቸው ሥዕሎችና ፎቶዎች
ƒƒ ፍራሽ

ሥፍራ:-የተግባር ትምህርት የሚሰጥበት በሳር የተሸፈነ ሜዳ፣

የጤናና ሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ~ 8ኛ ክፍል ~ የመምህር መምሪያ ~ 46

ምዕራፍ 5 ጅምናስቲክስ

የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል:-

ƒƒ የባለፈውን ክፍለ ጊዜ ትምህርት ተማሪዎች እንዲያስታውሱ ማበረታታት፤
ƒƒ የእለቱን ትምህርት ርዕሰና አላማ ለተማሪዎች ማስተዋወቅ፤
ƒƒ ተማሪዎችን ከ4 እስከ 6 ቡድን (ምድብ) በማደራጀት የሰውነት ማሟሟቅያ እንቅስቃሴዎች ከቀላል እንቅስቃሴዎች
በመጀመር ለዋናው የእለቱ ተግባር ቅድመ ዝግጅት እንዲያደርጉ ማበረታታት፤በውስን የሰውነት ማሟሟቂያ ጊዜ
ለክንድ፤ለእጆችና ትከሻ አካባቢ ትኩረት መስጠት እንዳለባቸው ማስገንዘብ፤
ƒƒ ለመስሪያ በተዘጋጀው ፍራሽ ቁጥር ልክ ተማሪዎችን ማደረጀትና በእጅ ወደፊት መስፈንጠርን ከአሁን በፊት ሰርተው
የሚውያቁና እንዴት እንደሰሩት በቃል እንዲያብራሩ ማበረታታት፤
ƒƒ በእጅ ወደፊት መስፈንጠርን በተሻለ ሁኔታ የሚሰሩ ተማሪዎች ካሉ ከፊት ለፊት ወጥተው እንቅስቃሴውን ሰርተው
እንዲያሳዮ ማበረታታትና በእጅ ወደፊት መስፈንጠርን የአሰራር ቅደም ተከተልን ማብራራት፤
ƒƒ በተጠቀለለ ፍራሽ ፊት ለፊት ተማሪዎችን በረድፍ እንዲቆሙ በማድረግ ከቅርብ ርቀት በመንደርደር ከተጠቀለለው
ፍራሽ ላይ ወደፊት በእጅ መስፈንጠርን እንዲለማመዱ ማበረታታትና ከጎን በኩል ድጋፍ በማድረግ ማለማመድ፤
ƒƒ በመማሪያ መጽሀፉ በተገለፀው የእንቅስቃሴው አሰራር መሰረት ተገቢውን ግበረ-መልስ በመስጠት በተደጋጋሚ
እንዲለማመዱ ማድረግ፤
ƒƒ ከተማሪዎቹ መካከል የተሻለ የሰሩትን በመለየት በመማሪያ መጽሀፉ በስዕል በተገለፀው መሰረት መጀመሪያ ሁለት ሁለት
ሆነው ቀጥለው ደግሞ በተጠቀለለ ፍራሽ ላይ ወደኋላ በእጅ መስፈንጠርን እንዲለማመዱ እድል መስጠት፤
ƒƒ በእንቅስቃሴያቸው የተሻሉ ሆነው ወደኋላ በእጅ መስፈንጠርን የሰሩ ተማሪዎች ለሌሎች ከላይ በተገለፀው ቅደም
ተከተል መሰረት እንዲሰሩ ማበረታታት፤
ƒƒ በእጅ ወደፊትና ወደኋላ መስፈንጠር በብዙ ጊዜ ልምምድ የሚሻሻል መሆኑን በመግለፅ በትርፍ ጊዚያቸው በጥንቃቄ
እንዲለማመዱ ማስገንዘብ፤
ƒƒ የአካል ጉዳተኛ ተማሪዎች ክፍል ውስጥ ካሉና የአካል ጉዳታቸው በእጅ ወደፊትና ወደኋላ መስፈንጠርን ለመስራት
የሚፈቅድላቸው ከሆነ ልዩ ትኩረት አድርጎ እንዲሳተፉ ማድረግ፤ የማያሳትፋቸው ከሆነ ግን በሌላ ተመሣሣይ
እንቅስቃሴ እንዲሳተፉ ማድረግ፤
ƒƒ በመጨረሻም የሰውነት ማቀዝቀ እንቅስቃሴ በየቡድናቸው እንዲሰሩ ማበረታታትና በእለቱ ትምህርት እንቅስቃሴያቸውን
አስመልክቶ ደረጃቸውን መግለፅና ለሚቀጥለው ጊዚያት በመለማመድ በእጅ ወደፊትና ወደኋላ መስፈንጠርን
በመለማመድ ማሻሻል እንደሚኖርባቸው ማሳሰብ፤

ክትትልና ግምገማ:-
ƒƒ የአሰራር ቅደም ተከተሉን ተግባራዊ በማድረግ እየተለማመዱ ስለመሆናቸው ምልከታና ግብረመልስ መስጠት፤
ƒƒ በእጅ ወደፊትና ወደኋላ መስፈንጠርንለመስራት ወሳኝ የሆኑ የአሰራር ቅደም ተከተሎችን እንዲያስረዱ የቃል ጥያቄ
በመጠየቅ ማረጋገጥ፤

የጤናና ሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ~ 8ኛ ክፍል ~ የመምህር መምሪያ ~ 47

ምዕራፍ 5 ጅምናስቲክስ

5.3.የመሣሪያ ጅምናስቲክስ (4 ክ/ጊዜ)

5.3.1. በጥንድ አግዳሚ ዘንግ ላይ ሰውነትን ማወዛወዝ (- ክ/ጊዜ)

ማሳሰቢያ:-በጥንድ አግዳሚ ዘንግ ላይ ወደፊትና ወደኋላ መወዛወዝን በአንድ ክፍለጊዜ ለማስተማር አስቸጋሪ ስለሆነ ከላይ
በተገለፀው የክፍለ ጊዜ መጠን በተከታታይ ማስተማር አስፈላጊ ነው::
ዝርዝር ዓላማ:-ተማሪዎች ይህንን ርዕስ ተምረው ካጠናቀቁበኋላ:-
ƒƒ በጥንድ አግዳሚ ዘንግ ላይ ወደፊትና ወደኋላ መወዛወዝን የአሰራር ቅድም ተከተሎችን ይዘረዝራሉ::
ƒƒ በጥንድ አግዳሚ ዘንግ ላይ ወደፊትና ወደኋላ መወዛወዝን በተሻለ ሁኔታ ሰርተው ያሳያሉ::
ƒƒ በጥንድ አግዳሚ ዘንግ ላይወደፊትና ወደኋላ መወዛወዝን በተሻለ ሁኔታ ለመስራት ፍላጎት ይኖራቸዋል::

የመማር-ማስተማር መርጃ መሣሪያዎች እና ሥፍራዎች:-

መርጃ መሣሪያዎች:-ከትምህርቱ ጋር ተያያዥነት ያላቸው ሥዕሎችና ፎቶዎች፤

ƒƒ ጥንድ አግዳሚ ዘንግ

ሥፍራ:-የተግባር ትምህርት የሚሰጥበት ቦታ

የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል:-

ƒƒ የባለፈውን ክፍለ ጊዜ ትምህርት ተማሪዎች እንዲያስታውሱ ማበረታታት፤
ƒƒ የእለቱን ትምህርት ርዕሰና አላማ ለተማሪዎች ማስተዋወቅ፤
ƒƒ ተማሪዎችን ከ4 እስከ 6 ቡድን (ምድብ) በማደራጀት የሰውነት ማሟሟቅያ እንቅስቃሴዎች ከቀላል እንቅስቃሴዎች
በመጀመር ለዋናው የእለቱ ተግባር ቅድመ ዝግጅት እንዲያደርጉ ማበረታታት፤በውስን የሰውነት ማሟሟቂያ ጊዜ
ለእጆች፤ ለትከሻቸው አካባቢ ትኩረት መስጠት እንዳለባቸው ማስገንዘብ፤
ƒƒ በአለው ጥንድ አግዳሚ ዘንግ ቁጥር ተማሪዎችን ማደራጀትና የጥንድ አግዳሚ ዘንግ አያያዝ ቴክኒክን እንዲለማመዱ
ማበረታታት፤
ƒƒ በጥንድ አግዳሚ ዘንግ ላይ በላኛው ክንድ 90 ዲግሪ በማጠፍ አግዳሚውን በመደገፍ ወደፊትና ወደኋላ መወዛወዝን
ለማለማመድ በመማሪያ መፅሀፉ የተጠቀሱትን የመለማመጃ እንቅስቃሴዎችን በቅደም ተከተላቸው እንዲለማመዱ
ማድረግ፤
ƒƒ ተማሪዎች በቅደም ተከተላቸው መሰረት እንቅስቃሴውን እንዲለማመዱና ተገቢውን ድጋፍ ማድረግ
ƒƒ በጥንድ አግዳሚ ዘንግ ላይ የሰውነት ክብደትን በእጅ ላይ በማሳረፍ እግርን ቀጥ አድርጎ ወደፊትና ወደኋላ መወዛወዝን
በመማሪያ መጽሀፉ በተጠቀሰው የመለማመጃ እንቅስቃሴዎች መሰረት በቅደም ተከተላቸው እንዲለማመዱ ማድረግ፤
ƒƒ በጥንድ አግዳሚው ላይ የሰውነት ክብደት በእጅ ላይ በማሳረፍ እግርን ቀጥ አድርጎ ወደፊትና ወደኋላ መወዛወዝን በተሻለ
ሁኔታ የሚሰሩበት ደረጃ ስለሆነ በመማሪያ መጽሀፉ የእንቅስቃሴው አሰራር ቅድም ተከተል መሰረት እንዲለማመዱ
ማበረታታት፤
ƒƒ እንቅስቃሴውን በተሻለ የሰሩትን ተማሪዎች በመምረጥ ወጥተው እንዲሰሩ ማበረታታት፤

የጤናና ሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ~ 8ኛ ክፍል ~ የመምህር መምሪያ ~ 48

ምዕራፍ 5 ጅምናስቲክስ

ƒƒ በጥንድ አግዳሚው ላይ የሰውነት ክብደት በእጅ ላይ በማሳረፍ እግርን ቀጥ አድርጎ ወደፊትና ወደኋላ መወዛወዝን
በብዙ ጊዜ ልምምድ የሚሻሻል መሆኑን በመግለፅ በትርፍ ጊዚያቸው በጥንቃቄ እንዲለማመዱ ማስገንዘብ፤
ƒƒ የአካል ጉዳተኛ ተማሪዎች ክፍል ውስጥ ካሉና የአካል ጉዳታቸው በጥንድ አግዳሚ ዘንግ ላይ ሰውነትን ማወዛወዝ
ለመስራት የሚፈቅድላቸው ከሆነ ልዩ ትኩረት አድርጎ እንዲሳተፉ ማድረግ፤ የማያሳትፋቸው ከሆነ ግን በሌላ ተመሣሣይ
እንቅስቃሴ እንዲሳተፉ ማድረግ፤
ƒƒ በመጨረሻም የሰውነት ማቀዝቀ እንቅስቃሴ በየቡድናቸው እንዲሰሩ ማበረታታትና በእለቱ ትምህርት እንቅስቃሴያቸውን
አስመልክቶ ደረጃቸውን መግለፅና ለሚቀጥለው ጊዚያት በመለማመድ በእጅ ወደፊትና ወደኋላ መስፈንጠርን
በመለማመድ ማሻሻል እንደሚኖርባቸው ማሳሰብ፤

ክትትልና ግምገማ:-
ƒƒ የአሰራር ቅደም ተከተሉን ተግባራዊ በማድረግ እየተለማመዱ ስለመሆናቸው ምልከታና ግብረመልስ መስጠት፤
ƒƒ በጥንድ አግዳሚ ዘንግ ላይ ሰውነትን ማወዛወዝንለመስራት ወሳኝ የሆኑ የአሰራር ቅደም ተከተሎችን እንዲያስረዱ የቃል
ጥያቄ በመጠየቅ ማረጋገጥ፤
ƒƒ ማሳሰቢያ:- በጥንድ አግዳሚ ዘንግ ላይ ሰውነትን ማወዛወዝ የአንድ ክፍለ ጊዜ ትምህርት ብቻ ሳይሆን ለአራት ክፍለጊዜ
ስለሆነ በመማሪያ መጽሐፉ የተጠቀሱትን የመለማመጃ እንቅስቃሴዎች መሰረት በማድርግ ማስተማር ያስፈልጋል::

የምዕራፉ መልመጃ መልስ

1. ሀ 2. ለ 3. ለ 4. መ 5. መ 6. ሀ

የጤናና ሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ~ 8ኛ ክፍል ~ የመምህር መምሪያ ~ 49

ምዕራፍ 6 የኳስ ጨዋታዎች መሠረታዊ ክህሎት

ምዕራፍ

6 የኳስ ጨዋታዎች መሠረታዊ ክህሎት

የክፍለ ጊዜ ብዛት፡ 15

አጠቃላይ ዓላማዎች፡

ተማሪዎች ይህንን ምዕራፍ ከተማሩ በኋላ፦

ƒƒ የቮሊቦል ኳስን የመለጋት እና ልግ የመቀበል ስልትን ይገነዛባሉ።
ƒƒ የቮሊቦልን የመለጋት ክህሎታቸውን ያዳብራሉ።
ƒƒ የእግር ኳስን ወደ ጎል የመምታት ስልትን ይገነዘባሉ።
ƒƒ የእጅ ኳስ የመወርወር ልምምድን ያደንቃሉ።
ƒƒ ለእግር ኳስ ወደ ጎል መምታት፣ ለእጅ ኳስ መወርወር እና በቮሊቦል ልግ ክህሎታቸውን ያዳብራሉ።

መግቢያ
የኳስ ጨዋታዎች መሰረታዊ እና የላቁ ክህሎቶች አሏቸው። ከእነዚህ ውስጥ የቮሊቦልን የመለጋት፣ የእግር ኳስን ወደ ጎል መምታት፣
በቅርጫት ኳስ በዝላይ ወደ ቅርጫት የመወርወር፣ የእጅ ኳስን የመወርወር ክህሎቶች ይገኙበታል። በዚህ ምዕራፍ የእነዚህን
ክህሎቶች የአሰራር ስልቶች እና ጥቅምች እንመለከታለን። በተጨማሪም እነዚህን ክህሎቶች ለማዳበር የሚረዱ ተግባራትን እና ፅንሰ
ሀሳቦችን እንማራለን።

6.1. የቮሊቦል ኳስን ከላይ ወደታች መለጋት (- ክ/ጊዜ)

6.1.1. የቮሊቦል ኳስን ከላይ ወደታች የመለጋት ስልት (2 ክ/ጊዜ)

ዝርዝር ዓላማ:-ተማሪዎች ይህንን ርዕስ ተምረው ካጠናቀቁበኋላ:-
ƒƒ የቮሊቦል ኳስን ከላይ ወደታች የመለጋት ስልትን በትክክል ይዘረዝራሉ።
ƒƒ የቮሊቦል ኳስን ከላይ ወደታች ለመለጋት ተነሳሽነት ያሳያሉ።
ƒƒ የቮሊቦል ኳስን ከላይ ወደታች መለጋትን በትክክል በተግባር ሰርተው ያሳያሉ።

የመማር-ማስተማር መርጃ መሣሪያዎች እና ሥፍራዎች:-

መርጃ መሣሪያዎች:-የቮሊቦል ኳስ
ሥፍራ:-የተግባር ትምህርት የሚሰጥበት ቦታ
የጤናና ሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ~ 8ኛ ክፍል ~ የመምህር መምሪያ ~ 50
ምዕራፍ 6 የኳስ ጨዋታዎች መሠረታዊ ክህሎት

የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል:-

ƒƒ የክፍሉ ተማሪዎች በረድፍ እንደቆሙ የእለቱን ትምህርት ርዕሰና አላማ ለተማሪዎች ማስተዋወቅ፤
ƒƒ ተማሪዎችን ከ4 እስከ 6 ቡድን (ምድብ) በማደራጀት የሰውነት ማሟሟቅያ እንቅስቃሴዎች ከቀላል እንቅስቃሴዎች
በመጀመር ለዋናው የእለቱ ተግባር ቅድመ ዝግጅት እንዲያደርጉ ማበረታታት፤
ƒƒ በአሉት የኳሶች ቁጥር ልክ በማደራጀት ሁሉም ከመሞከራቸው አስቀድሞ መጀመሪያ መሥራትና ለሌሎች ማሣየት
የሚፈልጉ ተማሪዎች ካሉ ቅድሚያ መሥጠትና እንዲያሣዩ ማድረግ፤ ሌሎችም በሚገባ እንዲመለከቱ ማድረግ፤
ƒƒ ይህ እንቅስቃሴ እንዴት እንደሚሠራ በመማሪያ መፅሀፉ በተጠቀሰው የመለጋት ስልት መሰረት ማስረዳት፤ ሠርቶም
ማሳየት
ƒƒ በቀረቡት ኳሶች ቁጥር የክፍሉን ተማሪዎች በቡድን መክፈልና በመካከላቸው በቂ ቦታ እንዲኖር በማድረግ ግራና ቀኝ
ባለው ሜዳ በረድፍ አሰልፎ ለአንድ ቡድን አንድ ኳስ መስጠት፤
ƒƒ በመማሪያ መፅሀፉ በተጠቀሰው የተግባር ልምምድ መሰረት ተግባራዊ እንዲያደርጉ ክትትልና ድጋፍ ማድረግ፤
ƒƒ በእንቅስቃሴያቸው የተሻሉ ሆነው ኳስ ከላይ ወደታች መለጋትን የሰሩ ተማሪዎች ለሌሎች ከላይ በተገለፀው ቅደም
ተከተል መሰረት እንዲሰሩ ማበረታታት፤
ƒƒ የአካል ጉዳተኛ ተማሪዎች ክፍል ውስጥ ካሉና የአካል ጉዳታቸው ካስ መለጋትን ለመስራት የሚፈቅድላቸው ከሆነ ልዩ
ትኩረት አድርጎ እንዲሳተፉ ማድረግ፤ የማያሳትፋቸው ከሆነ ግን በሌላ ተመሣሣይ እንቅስቃሴ እንዲሳተፉ ማድረግ፤
ƒƒ በመጨረሻም የሰውነት ማቀዝቀ¹ እንቅስቃሴ በየቡድናቸው እንዲሰሩ ማበረታታትና በእለቱ ትምህርት እንቅስቃሴያቸውን
አስመልክቶ ደረጃቸውን መግለፅና ለሚቀጥለው ጊዚያት በመለማመድ ኳስ ከላይ ወደታች ልግን በመለማመድ ማሻሻል
እንደሚኖርባቸው ማሳሰብ፤

ክትትልና ግምገማ:-
ƒƒ የአሰራር ቅደም ተከተሉን ተግባራዊ በማድረግ እየተለማመዱ ስለመሆናቸው ምልከታና ግብረመልስ መስጠት፤
ƒƒ የቮሊቦል ኳስን ከላይ ወደታች መለጋትን ተግባራዊ ለማድረግ ወሳኝ የሆኑ የአሰራር ቅደም ተከተሎችን እንዲያስረዱ
የቃል ጥያቄ በመጠየቅ ማረጋገጥ፤
ƒƒ ማሳሰቢያ-6.1.2.በቮሊቦል ኳስን ከላይ ወደታች የመለጋት ልምምድ በመማሪያ መፅሀፉ በተቀመጠው ቅደም ተከተል
መሰረት ለአንድክፍለ ጊዜ ትምህርት ከላይ በተገለፀው እቅድ መሰረት ተግባራዊ ማድረግ ይቻላል።

6.1.3. በክንድ ልግን የመቀበል ስልት (1 ክ/ጊዜ)

ዝርዝር ዓላማ:-ተማሪዎች ይህንን ርዕስ ተምረው ካጠናቀቁበኋላ:-
ƒƒ በክንድ ልግን የመቀበል ስልትን በትክክል ይዘረዝራሉ።
ƒƒ በክንድ ልግን የመቀበል ክህሎትን ለማዳበር ተነሳሽነት ያሳያሉ።
ƒƒ በክንድ ልግን የመቀበልን በተግባር ሰርተው ያሳያሉ።

የመማር-ማስተማር መርጃ መሣሪያዎች እና ሥፍራዎች:-

መርጃ መሣሪያዎች:- የቮሊቦል ኳስ

ሥፍራ:-የተግባር ትምህርት የሚሰጥበት ቦታ

የጤናና ሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ~ 8ኛ ክፍል ~ የመምህር መምሪያ ~ 51

ምዕራፍ 6 የኳስ ጨዋታዎች መሠረታዊ ክህሎት

የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል:-

ƒƒ የባለፈውን ክፍለ ጊዜ ትምህርት ተማሪዎች እንዲያስታውሱ ማበረታታት፤
ƒƒ የክፍሉ ተማሪዎች በረድፍ እንደቆሙ የእለቱን ትምህርት ርዕሰና አላማ ለተማሪዎች ማስተዋወቅ፤
ƒƒ ተማሪዎችን ከ4 እስከ 6 ቡድን (ምድብ) በማደራጀት የሰውነት ማሟሟቅያ እንቅስቃሴዎች ከቀላል እንቅስቃሴዎች
በመጀመር ለዋናው የእለቱ ተግባር ቅድመ ዝግጅት እንዲያደርጉ ማበረታታት፤
ƒƒ በአሉት የኳሶች ቁጥር ልክ በማደራጀት ሁሉም ከመሞከራቸው አስቀድሞ መጀመሪያ መሥራትና ለሌሎች ማሣየት
የሚፈልጉ ተማሪዎች ካሉ ቅድሚያ መሥጠትና እንዲያሣዩ ማድረግ፤ ሌሎችም በሚገባ እንዲመለከቱ ማድረግ፤
ƒƒ ይህ እንቅስቃሴ እንዴት እንደሚሠራ በመማሪያ መፅሀፉ በተጠቀሰው በክንድ ልግን የመቀበል ስልትን መሰረት
ማስረዳት፤ ሠርቶም ማሳየት፤
ƒƒ በቀረቡት ኳሶች ቁጥር የክፍሉን ተማሪዎች በቡድን መክፈልና በመካከላቸው በቂ ቦታ እንዲኖር በማድረግ ግራና ቀኝ
ባለው ሜዳ በረድፍ አሰልፎ ለአንድ ቡድን አንድ ኳስ መስጠት፤
ƒƒ በመማሪያ መፅሀፉ በተጠቀሰው የተግባር ልምምድ መሰረት ተግባራዊ እንዲያደርጉ ክትትልና ድጋፍ ማድረግ፤
ƒƒ በእንቅስቃሴያቸው የተሻሉ ሆነው በክንድ ልግን የመቀበል በተሻለ ሁኔታ የሰሩ ተማሪዎች ለሌሎች ከላይ በተገለፀው
ቅደም ተከተል መሰረት እንዲሰሩ ማበረታታት፤
ƒƒ የአካል ጉዳተኛ ተማሪዎች ክፍል ውስጥ ካሉና የአካል ጉዳታቸው በክንድ ልግን የመቀበል ለመስራት የሚፈቅድላቸው
ከሆነ ልዩ ትኩረት አድርጎ እንዲሳተፉ ማድረግ፤ የማያሳትፋቸው ከሆነ ግን በሌላ ተመሣሣይ እንቅስቃሴ እንዲሳተፉ
ማድረግ፤
ƒƒ በመጨረሻም የሰውነት ማቀዝቀ¹ እንቅስቃሴ በየቡድናቸው እንዲሰሩ ማበረታታትና በእለቱ ትምህርት እንቅስቃሴያቸውን
አስመልክቶ ደረጃቸውን መግለፅና ለሚቀጥለው ጊዚያት በመለማመድ በክንድ ልግን መቀበልን በመለማመድ ማሻሻል
እንደሚኖርባቸው ማሳሰብ፤

ክትትልና ግምገማ:-
ƒƒ የአሰራር ቅደም ተከተሉን ተግባራዊ በማድረግ እየተለማመዱ ስለመሆናቸው ምልከታና ግብረመልስ መስጠት፤
ƒƒ በክንድ ልግን ለመቀበል እና ተግባራዊ ለማድረግ ወሳኝ የሆኑ የአሰራር ቅደም ተከተሎችን እንዲያስረዱ የቃል ጥያቄ
በመጠየቅ ማረጋገጥ፤

6.1.4. በቮሊቦል ጨዋታ ከላይ ወደታች መለጋት እና መቀበል (1 ክ/ጊዜ)

ዝርዝር ዓላማ:-ተማሪዎች ይህንን ርዕስ ተምረው ካጠናቀቁበኋላ:-
ƒƒ በቮሊቦል ጨዋታ ከላይ ወደታች መለጋት እና በክንድ ልግን የመቀበል ስልቶችን በሚገባ ይገነዘባሉ
ƒƒ በቮሊቦል ጨዋታ ከላይ ወደታች መለጋት እና በክንድ ልግን የመቀበል ክህሎታቸውን ያሻሽላሉ
ƒƒ በቮሊቦል ጨዋታ ከላይ ወደታች መለጋት እና በክንድ ልግን የመቀበል እንቅስቃሴ አወንታዊ አመለካከት ያዳብራሉ

የመማር-ማስተማር መርጃ መሣሪያዎች እና ሥፍራዎች:-

መርጃ መሣሪያዎች:- የቮሊቦል ኳስ

ሥፍራ:-የተግባር ትምህርት የሚሰጥበት ቦታ

የጤናና ሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ~ 8ኛ ክፍል ~ የመምህር መምሪያ ~ 52

ምዕራፍ 6 የኳስ ጨዋታዎች መሠረታዊ ክህሎት

የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል:-

ƒƒ የባለፈውን ክፍለ ጊዜ ትምህርት ተማሪዎች እንዲያስታውሱ ማበረታታት፤
ƒƒ የክፍሉ ተማሪዎች በረድፍ እንደቆሙ የእለቱን ትምህርት ርዕሰና አላማ ለተማሪዎች ማስተዋወቅ፤
ƒƒ ተማሪዎችን ከ4 እስከ 6 ቡድን (ምድብ) በማደራጀት የሰውነት ማሟሟቂያ እንቅስቃሴዎች ከቀላል እንቅስቃሴዎች
በመጀመር ለዋናው የእለቱ ተግባር ቅድመ ዝግጅት እንዲያደርጉ ማበረታታት፤
ƒƒ በመማሪያ መፅሀፉ በተገለፀው መሰረት በጨዋታ ከላይ ወደታች መለጋት እና መቀበልን ሶስት ለሶስት፤ አራት ለአራት
እና አምስት ለአምስት እንዲጫዎቱ ማመቻቸት፤
ƒƒ በመጨረሻም የሰውነት ማቀዝቀ¹ እንቅስቃሴ በየቡድናቸው እንዲሰሩ ማበረታታትና በእለቱ ትምህርት እንቅስቃሴያቸውን
አስመልክቶ ደረጃቸውን መግለፅና ለሚቀጥለው ጊዚያት በመለማመድ በክንድ ልግን መቀበልን በመለማመድ ማሻሻል
እንደሚኖርባቸው ማሳሰብ፤

ክትትልና ግምገማ:-
ƒƒ ከአሁን በፊት የተማሩትን የቮሊቦል ክህሎትን በመጠቀም ጨዋታውን መጫዎታቸውን ምልከታና ግብረመልስ መስጠት፤
ƒƒ ከላይ ወደታች መለጋትናና በክንድ ልግን ለመቀበል እና ተግባራዊ ለማድረግ ወሳኝ የሆኑ የአሰራር ቅደም ተከተሎችን
እንዲያስረዱ የቃል ጥያቄ በመጠየቅ ማረጋገጥ፤
ƒƒ በጨዋታው ምን ያህል እንደረኩና የተማሩትን ተግባራዊ ስለማድረጋቸው ግብረመልስ መቀበል፤

6.2. የእግር ኳስን ወደጎል መምታት (- ክ/ጊዜ)

6.2.1. የእግር ኳስን ወደጎል የመምታት ስልት (1 ክ/ጊዜ)

ዝርዝር ዓላማ:-ተማሪዎች ይህንን ርዕስ ከተማሩ በኋላ፦
ƒƒ ኳስን ወደጎል የመምታት ስልት በትክክል ይዘረዝራሉ፤
ƒƒ በእግር ኳስ ጨዋታ ኳስን ወደጎልለመምታት ፍላጎት ይኖራቸዋል፤
ƒƒ ከሶስት ሙከራ ቢያንስ አንዱን ኳስ በሚጠበቀው ደረጃ አክርረው ይመታሉ፤

የመማር-ማስተማር መርጃ መሣሪያዎች እና ሥፍራዎች:-

መርጃ መሣሪያዎች:- የእግር ኳስ

ሥፍራ:-የተግባር ትምህርት የሚሰጥበት ቦታ

የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል:-

ƒƒ ቁልፍ ክንውኖች ላይ ማስተካከያ በማድረግ በዚሁ ምዕራፍ በንዑስ ርዕስ 6.1.1 (የቮሊቦል ኳስን ከላይ ወደታች የመለጋት
ስልት)የተገለፀውን የመማር ማስተማር ሂደት ይከተሉ፤

የጤናና ሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ~ 8ኛ ክፍል ~ የመምህር መምሪያ ~ 53

ምዕራፍ 6 የኳስ ጨዋታዎች መሠረታዊ ክህሎት

6.2.2. የእግር ኳስን ወደጎል የመምታት ልምምድ (1 ክ/ጊዜ)

ዝርዝር ዓላማ:-ተማሪዎች ይህንን ርዕስ ከተማሩ በኋላ፦
ƒƒ ኳስን ወደጎል የመምታት ስልት በትክክል ይዘረዝራሉ፤
ƒƒ በእግር ኳስ ጨዋታ ኳስን ወደጎልለመምታት ፍላጎት ይኖራቸዋል፤
ƒƒ ከሶስት ሙከራ ቢያንስ አንዱን ኳስ በሚጠበቀው ደረጃ አክርረው ይመታሉ፤

የመማር-ማስተማር መርጃ መሣሪያዎች እና ሥፍራዎች:-

መርጃ መሣሪያዎች:- የእግር ኳስ

ሥፍራ:-የተግባር ትምህርት የሚሰጥበት ቦታ

የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል:-

ƒƒ የባለፈውን ክፍለ ጊዜ ትምህርት ተማሪዎች እንዲያስታውሱ ማበረታታት፤
ƒƒ የክፍሉ ተማሪዎች በረድፍ እንደቆሙ የእለቱን ትምህርት ርዕሰና አላማ ለተማሪዎች ማስተዋወቅ፤
ƒƒ ተማሪዎችን ከ4 እስከ 6 ቡድን (ምድብ) በማደራጀት የሰውነት ማሟሟቅያ እንቅስቃሴዎች ከቀላል እንቅስቃሴዎች
በመጀመር ለዋናው የእለቱ ተግባር ቅድመ ዝግጅት እንዲያደርጉ ማበረታታት፤
ƒƒ በአሉት የኳሶች ቁጥር ልክ በማደራጀት ሁሉም ከመሞከራቸው አስቀድሞ መጀመሪያ መሥራትና ለሌሎች ማሣየት
የሚፈልጉ ተማሪዎች ካሉ ቅድሚያ መሥጠትና እንዲያሣዩ ማድረግ፤ ሌሎችም በሚገባ እንዲመለከቱ ማድረግ፤
ƒƒ ይህ እንቅስቃሴ እንዴት እንደሚሠራ በመማሪያ መፅሀፉ በተጠቀሰው ከተለያዮ ርቀቶች የእግር ኳስን አክርሮ የመምታት
ልምምድ መሆኑን ማስረዳት፤ ሠርቶም ማሳየት፤
ƒƒ በቀረቡት ኳሶች ቁጥር የክፍሉን ተማሪዎች በቡድን መክፈልና በመካከላቸው በቂ ቦታ እንዲኖር በማድረግ ግራና ቀኝ
ባለው ሜዳ በረድፍ አሰልፎ ለአንድ ቡድን አንድ ኳስ መስጠት፤
ƒƒ በመማሪያ መፅሀፉ በተጠቀሰው የተግባር ልምምድ መሰረት ከተለያዮ ርቀቶች ተግባራዊ እንዲያደርጉ ክትትልና ድጋፍ
ማድረግ፤
ƒƒ በእንቅስቃሴያቸው የተሻሉ ሆነው የእግር ኳስን ወደጎል መምታትን የሰሩ ተማሪዎች ለሌሎች ከላይ በተገለፀው ቅደም
ተከተል መሰረት እንዲሰሩ ማበረታታት፤
ƒƒ የአካል ጉዳተኛ ተማሪዎች ክፍል ውስጥ ካሉና የአካል ጉዳታቸው በክንድ ልግን የመቀበል ለመስራት የሚፈቅድላቸው
ከሆነ ልዩ ትኩረት አድርጎ እንዲሳተፉ ማድረግ፤ የማያሳትፋቸው ከሆነ ግን በሌላ ተመሣሣይ እንቅስቃሴ እንዲሳተፉ
ማድረግ፤
ƒƒ በመጨረሻም የሰውነት ማቀዝቀ¹ እንቅስቃሴ በየቡድናቸው እንዲሰሩ ማበረታታትና በእለቱ ትምህርት እንቅስቃሴያቸውን
አስመልክቶ ደረጃቸውን መግለፅና ለሚቀጥለው ጊዚያት በመለማመድ የእግር ኳስን ወደጎል መምታትንበመለማመድ
ማሻሻል እንደሚኖርባቸው ማሳሰብ፤

ክትትልና ግምገማ:-
ƒƒ የአሰራር ቅደም ተከተሉን ተግባራዊ በማድረግ እየተለማመዱ ስለመሆናቸው ምልከታና ግብረመልስ መስጠት፤

የጤናና ሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ~ 8ኛ ክፍል ~ የመምህር መምሪያ ~ 54

ምዕራፍ 6 የኳስ ጨዋታዎች መሠረታዊ ክህሎት

ƒƒ የእግር ኳስን ወደጎል መምታትን ተግባራዊ ለማድረግ ወሳኝ የሆኑ የአሰራር ቅደም ተከተሎችን እንዲያስረዱ የቃል ጥያቄ
በመጠየቅ ማረጋገጥ፤

6.2.3. በእግር ኳስ ጨዋታ ውስጥ ኳስን አክርሮ መምታት (2 ክ/ጊዜ)

ዝርዝር ዓላማ:-ተማሪዎች ይህንን ርዕስ ተምረው ካጠናቀቁበኋላ:-
ƒƒ በእግር ኳስ ጨዋታ ውስጥ ኳስን ወደጎል መምታት ስልቶችን በሚገባ ይገነዘባሉ
ƒƒ በእግር ኳስ ጨዋታ ውስጥ ኳስን ወደጎል መምታት ክህሎታቸውን ያሻሽላሉ
ƒƒ በእግር ኳስ ጨዋታ ውስጥ ኳስን ወደጎል መምታት እንቅስቃሴ አወንታዊ አመለካከት ያዳብራሉ

የመማር-ማስተማር መርጃ መሣሪያዎች እና ሥፍራዎች:-

መርጃ መሣሪያዎች:- የእግር ኳስ

ሥፍራ:-የተግባር ትምህርት የሚሰጥበት ቦታ

የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል:-

ƒƒ የባለፈውን ክፍለ ጊዜ ትምህርት ተማሪዎች እንዲያስታውሱ ማበረታታት፤
ƒƒ የክፍሉ ተማሪዎች በረድፍ እንደቆሙ የእለቱን ትምህርት ርዕሰና አላማ ለተማሪዎች ማስተዋወቅ፤
ƒƒ ተማሪዎችን ከ4 እስከ 6 ቡድን (ምድብ) በማደራጀት የሰውነት ማሟሟቅያ እንቅስቃሴዎች ከቀላል እንቅስቃሴዎች
በመጀመር ለዋናው የእለቱ ተግባር ቅድመ ዝግጅት እንዲያደርጉ ማበረታታት፤
ƒƒ በመማሪያ መፅሀፉ በተገለፀው መሰረትበእግር ኳስ ጨዋታ ውስጥ ኳስን ወደጎል መምታት ሶስት ለሶስት፤ አራት ለአራት፤
አምስት ለአምስትእና ስድስት ለስድስት እንዲጫዎቱ ማመቻቸት፤
ƒƒ በመጨረሻም የሰውነት ማቀዝቀ¹ እንቅስቃሴ በየቡድናቸው እንዲሰሩ ማበረታታትና በእለቱ ትምህርት እንቅስቃሴያቸውን
አስመልክቶ ደረጃቸውን መግለፅና ለሚቀጥለው ጊዚያት በመለማመድ በክንድ ልግን መቀበልን በመለማመድ ማሻሻል
እንደሚኖርባቸው ማሳሰብ፤

ክትትልና ግምገማ:-
ƒƒ ከአሁን በፊት የተማሩትን የእግር ኳስ ክህሎትን በመጠቀም ጨዋታውን መጫዎታቸውን ምልከታና ግብረመልስ
መስጠት፤
ƒƒ በእግር ኳስ ጨዋታ ውስጥ ኳስን ወደጎል መምታትን ተግባራዊ ለማድረግ ወሳኝ የሆኑ የአሰራር ቅደም ተከተሎችን
እንዲያስረዱ የቃል ጥያቄ በመጠየቅ ማረጋገጥ፤
ƒƒ በጨዋታው ምን ያህል እንደረኩና የተማሩትን ተግባራዊ ስለማድረጋቸው ግብረመልስ መቀበል፤

የጤናና ሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ~ 8ኛ ክፍል ~ የመምህር መምሪያ ~ 55

ምዕራፍ 6 የኳስ ጨዋታዎች መሠረታዊ ክህሎት

6.3. በዝላይ ኳስንወደ ቅርጫት መወርወር (- ክ/ጊዜ)

6.3.1. በዝላይ ወደ ቅርጫት የመወርወር ስልት (1 ክ/ጊዜ)

ዝርዝር ዓላማ:-ተማሪዎች ይህንን ርዕስ ከተማሩ በኋላ፦
ƒƒ ኳስን በዝላይወደ ቅርጫት የመወርወር ስልት ይገነዘባሉ፤
ƒƒ ኳስን በዝላይ ወደ ቅርጫት በመወርወር ይዝናናሉ፤
ƒƒ ከሶስት ሙከራ ቢያንስ አንዱን ኳስ በዝላይ ቅርጫት ያስቆጥራሉ፤

የመማር-ማስተማር መርጃ መሣሪያዎች እና ሥፍራዎች:-

መርጃ መሣሪያዎች:- የቅርጫት ኳስ

ሥፍራ:-የተግባር ትምህርት የሚሰጥበት ቦታ

የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል:-

ƒƒ የባለፈውን ክፍለ ጊዜ ትምህርት ተማሪዎች እንዲያስታውሱ ማበረታታት፤
ƒƒ የክፍሉ ተማሪዎች በረድፍ እንደቆሙ የእለቱን ትምህርት ርዕሰና አላማ ለተማሪዎች ማስተዋወቅ፤
ƒƒ ተማሪዎችን ከ4 እስከ 6 ቡድን (ምድብ) በማደራጀት የሰውነት ማሟሟቂያ እንቅስቃሴዎች ከቀላል እንቅስቃሴዎች
በመጀመር ለዋናው የእለቱ ተግባር ቅድመ ዝግጅት እንዲያደርጉ ማበረታታት፤
ƒƒ በአሉት የኳሶች ቁጥር ልክ በማደራጀት ሁሉም ከመሞከራቸው አስቀድሞ መጀመሪያ መሥራትና ለሌሎች ማሣየት
የሚፈልጉ ተማሪዎች ካሉ ቅድሚያ መሥጠትና እንዲያሣዩ ማድረግ፤ ሌሎችም በሚገባ እንዲመለከቱ ማድረግ፤
ƒƒ ይህ እንቅስቃሴ እንዴት እንደሚሠራ በመማሪያ መፅሀፉ በተጠቀሰው በዝላይ ኳስን ወደ ቅርጫት መወርወር ስልትን
መሰረት ማስረዳት፤ ሠርቶም ማሳየት፤
ƒƒ በቀረቡት ኳሶች ቁጥር የክፍሉን ተማሪዎች በቡድን መክፈልና ያለቅርጫት ኳስ ቦርድ ከጓደኛቸው ፊት ለፊት
በተገለፀላቸው ስልት መሰረት እንዲለማመዱ ማበረታታት፤
ƒƒ በመማሪያ መፅሀፉ በተጠቀሰው የተግባር ልምምድ መሰረት ተግባራዊ እንዲያደርጉ ክትትልና ድጋፍ ማድረግ፤
ƒƒ በእንቅስቃሴያቸው የተሻሉ ሆነው በዝላይ ኳስንወደ ቅርጫት መወርወር በተሻለ ሁኔታ የሰሩ ተማሪዎች ለሌሎች ከላይ
በተገለፀው ቅደም ተከተል መሰረት እንዲሰሩ ማበረታታት፤
ƒƒ የአካል ጉዳተኛ ተማሪዎች ክፍል ውስጥ ካሉና የአካል ጉዳታቸው ኳስን በዝላይ ወደ ቅርጫት በመወርወር ለመስራት
የሚፈቅድላቸው ከሆነ ልዩ ትኩረት አድርጎ እንዲሳተፉ ማድረግ፤ የማያሳትፋቸው ከሆነ ግን በሌላ ተመሣሣይ
እንቅስቃሴ እንዲሳተፉ ማድረግ፤
ƒƒ በመጨረሻም የሰውነት ማቀዝቀ¹ እንቅስቃሴ በየቡድናቸው እንዲሰሩ ማበረታታትና በእለቱ ትምህርት እንቅስቃሴያቸውን
አስመልክቶ ደረጃቸውን መግለፅና ለሚቀጥለው ጊዚያት በመለማመድ በክንድ ልግን መቀበልን በመለማመድ ማሻሻል
እንደሚኖርባቸው ማሳሰብ፤

ክትትልና ግምገማ:-
ƒƒ የአሰራር ቅደም ተከተሉን ተግባራዊ በማድረግ እየተለማመዱ ስለመሆናቸው ምልከታና ግብረመልስ መስጠት፤

የጤናና ሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ~ 8ኛ ክፍል ~ የመምህር መምሪያ ~ 56

ምዕራፍ 6 የኳስ ጨዋታዎች መሠረታዊ ክህሎት

ƒƒ በዝላይ ኳስን ወደ ቅርጫት መወርወርን ተግባራዊ ለማድረግ ወሳኝ የሆኑ የአሰራር ቅደም ተከተሎችን እንዲያስረዱ
የቃል ጥያቄ በመጠየቅ ማረጋገጥ፤

6.3.2. በዝላይ ወደ ቅርጫት የመወርወር ልምምድ (1 ክ/ጊዜ)

ዝርዝር ዓላማ:-ተማሪዎች ይህንን ርዕስ ከተማሩ በኋላ፦
ƒƒ ኳስን በዝላይ ወደ ቅርጫት የመወርወር ስልትን ይተነትናሉ፤
ƒƒ ኳስን በዝላይ ወደ ቅርጫት የመወርወርን እንቅስቃሴ ይወዳሉ፤
ƒƒ ከሁለት ሙከራ ቢያንስ አንዱን ኳስ በዝላይ ቅርጫት ያስቆጥራሉ፤

የመማር-ማስተማር መርጃ መሣሪያዎች እና ሥፍራዎች:-

መርጃ መሣሪያዎች:- የቅርጫት ኳስ

ሥፍራ:-የተግባር ትምህርት የሚሰጥበት ቦታ

የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል:-

ƒƒ ቁልፍ ክንውኖች ላይ ማስተካከያ በማድረግ በዚሁ ምዕራፍ በንዑስ ርዕስ 6.2.2. በእግር ኳስ ጨዋታ ውስጥ ኳስን አክርሮ
መምታት ጨዋታ ልምምድ የተገለፀውን የመማር ማስተማር ሂደት ይከተሉ፤ በልምምዱ ጊዜ ከ5 ሜትር፤ ከ7 ሜትር
እና ከ8 ሜትር ርቀት ዘሎ ኳስን በመወርወር ቅርጫት ማስቆጠር ላይ ትኩረት አድርጎ መስራት፤

6.3.3. በቅርጫትኳስ ጨዋታ ውስጥ በዝላይ የመወርወር

(2 ክ/ጊዜ)
ልምምድ
ዝርዝር ዓላማ:-ተማሪዎች ይህንን ርዕስ ከተማሩ በኋላ፦
ƒƒ ኳስን በዝላይ ወደ ቅርጫት የመወርወር ስልትን ያብራራሉ፤
ƒƒ ኳስን በዝላይ ወደ ቅርጫት በመወርወር ይዝናናሉ፤
ƒƒ በቅርጫት ኳስ ጨዋታ ይደሰታሉ፤
ƒƒ ኳስን በዝላይ ወደ ቅርጫት ለመወርወር አወንታዊ አመለካከት ያዳብራሉ፤
ƒƒ ከሶስት በዝላይ ወደ ቅርጫት የመወርወር ሙከራ ቢያንስ አንዱን ቅርጫት ያስቆጥራሉ፤

የመማር-ማስተማር መርጃ መሣሪያዎች እና ሥፍራዎች:-

መርጃ መሣሪያዎች:- የቅርጫት ኳስ

ሥፍራ:-የተግባር ትምህርት የሚሰጥበት ቦታ

የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል:-

ƒƒ ቁልፍ ክንውኖች ላይ ማስተካከያ በማድረግ በዚሁ ምዕራፍ በንዑስ ርዕስ 6.2.3. በእግር ኳስ ጨዋታ ውስጥ ኳስን አክርሮ
መምታት ጨዋታ የተገለፀውን የመማር ማስተማር ሂደት ይከተሉ፤በልምምዱ ጊዜ ሦስት ለሶስት፤አራት ለአራት እና
አምስት ለአምስት ጨዋታ በማድረግ ማከናወን፤

የጤናና ሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ~ 8ኛ ክፍል ~ የመምህር መምሪያ ~ 57

ምዕራፍ 6 የኳስ ጨዋታዎች መሠረታዊ ክህሎት

6.4 የእጅ ኳስን በመስፈንጠር ወደ ግብ መወርወር (- ክ/ጊዜ)

6.4.1. በእጅ ኳስ በመስፈንጠር ወደ ግብ የመወርወር ስልት (1 ክ/ጊዜ)

ዝርዝር ዓላማ:-ተማሪዎች ይህንን ርዕስ ከተማሩ በኋላ፦
ƒƒ ኳስን በመስፈንጠር ወደግብየመወርወር ስልት በሚገባ ይዘረዝራሉ፤
ƒƒ በእጅ ኳስ ጨዋታ ኳስን በመስፈንጠር ወደግብለመወርወር ፍላጎት ያሳያሉ፤
ƒƒ ከሶስት ሙከራ ቢያንስ አንዱን ኳስ በመስፈንጠር በትክክል ያስቆጥራሉ፤

የመማር-ማስተማር መርጃ መሣሪያዎች እና ሥፍራዎች:-

መርጃ መሣሪያዎች:- የእጅ ኳስ

ሥፍራ:-የተግባር ትምህርት የሚሰጥበት ቦታ

የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል:-

ƒƒ የባለፈውን ክፍለ ጊዜ ትምህርት ተማሪዎች እንዲያስታውሱ ማበረታታት፤
ƒƒ የክፍሉ ተማሪዎች በረድፍ እንደቆሙ የእለቱን ትምህርት ርዕሰና አላማ ለተማሪዎች ማስተዋወቅ፤
ƒƒ ተማሪዎችን ከ4 እስከ 6 ቡድን (ምድብ) በማደራጀት የሰውነት ማሟሟቂያ እንቅስቃሴዎች ከቀላል እንቅስቃሴዎች
በመጀመር ለዋናው የእለቱ ተግባር ቅድመ ዝግጅት እንዲያደርጉ ማበረታታት፤
ƒƒ በአሉት የኳሶች ቁጥር ልክ በማደራጀት ሁሉም ተማሪዎች ከመሞከራቸው አስቀድሞ መጀመሪያ መሥራትና ለሌሎች
ማሣየት የሚፈልጉ ተማሪዎች ካሉ ቅድሚያ መሥጠትና እንዲያሣዩ ማድረግ፤ ሌሎችም በሚገባ እንዲመለከቱ ማድረግ፤
ƒƒ ይህ እንቅስቃሴ እንዴት እንደሚሠራ በመማሪያ መፅሀፉ በተጠቀሰው ኳስን በመስፈንጠር ወደግብ የመወርወር ስልት
መሰረት ማስረዳት፤ ሠርቶም ማሳየት፤
ƒƒ በቀረቡት ኳሶች ቁጥር የክፍሉን ተማሪዎች በቡድን መክፈልና ባለው የእጅ ኳስ ግብ በመጠቀም ከላይ በተገለፀው ስልት
መሰረት እንዲለማመዱ ማበረታታት፤
ƒƒ በመማሪያ መፅሀፉ በተጠቀሰው የተግባር ልምምድ መሰረት ተግባራዊ እንዲያደርጉ ክትትልና ድጋፍ ማድረግ፤
ƒƒ በእንቅስቃሴያቸው የተሻሉ ሆነው ኳስን በመስፈንጠር ወደግብ የመወርወር በተሻለ ሁኔታ የሰሩ ተማሪዎች ለሌሎች
ከላይ በተገለፀው ቅደም ተከተል መሰረት እንዲሰሩ ማበረታታት፤
ƒƒ የአካል ጉዳተኛ ተማሪዎች ክፍል ውስጥ ካሉና የአካል ጉዳታቸው ኳስን በመስፈንጠር ወደግብ መወርወርን ለመስራት
የሚፈቅድላቸው ከሆነ ልዩ ትኩረት አድርጎ እንዲሳተፉ ማድረግ፤ የማያሳትፋቸው ከሆነ ግን በሌላ ተመሣሣይ
እንቅስቃሴ እንዲሳተፉ ማድረግ፤
ƒƒ በመጨረሻም የሰውነት ማቀዝቀ¹ እንቅስቃሴ በየቡድናቸው እንዲሰሩ ማበረታታትና በእለቱ ትምህርት እንቅስቃሴያቸውን
አስመልክቶ ደረጃቸውን መግለፅና ለሚቀጥለው ጊዚያት በመለማመድ በክንድ ልግን መቀበልን በመለማመድ ማሻሻል
እንደሚኖርባቸው ማሳሰብ፤

ክትትልና ግምገማ:-
ƒƒ የአሰራር ቅደም ተከተሉን ተግባራዊ በማድረግ እየተለማመዱ ስለመሆናቸው ምልከታና ግብረመልስ መስጠት፤

የጤናና ሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ~ 8ኛ ክፍል ~ የመምህር መምሪያ ~ 58

ምዕራፍ 6 የኳስ ጨዋታዎች መሠረታዊ ክህሎት

ƒƒ ኳስን በመስፈንጠር ወደግብ መወርወርን ተግባራዊ ለማድረግ ወሳኝ የሆኑ የአሰራር ቅደም ተከተሎችን እንዲያስረዱ
የቃል ጥያቄ በመጠየቅ ማረጋገጥ፤

6.4.2. በእጅ ኳስ ጨዋታ ውስጥ ኳስን በመስፈንጠር ወደ ግብ

(2 ክ/ጊዜ)
የመወርወር ልምምድ
ዝርዝር ዓላማ:-ተማሪዎች ይህንን ርዕስ ከተማሩ በኋላ፦
ƒƒ ኳስን በመስፈንጠር ወደጎል መወርወር ስልትን በሚገባ ያብራራሉ፤
ƒƒ በእጅ ኳስ ጨዋታ ይዝናናሉ፤
ƒƒ ኳስን በመስፈንጠር ወደጎል ለመወርወር አወንታዊ አመለካከት ያዳብራሉ፤
ƒƒ ከሁለት በመስፈንጠር ወደጎል የመወርወር ሙከራ ቢያንስ አንዱን ጎል ያስቆጥራሉ፤

የመማር-ማስተማር መርጃ መሣሪያዎች እና ሥፍራዎች:-

መርጃ መሣሪያዎች:- የእጅ ኳስ

ሥፍራ:-የተግባር ትምህርት የሚሰጥበት ቦታ

የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል:-

ƒƒ የባለፈውን ክፍለ ጊዜ ትምህርት ተማሪዎች እንዲያስታውሱ ማበረታታት፤
ƒƒ የክፍሉ ተማሪዎች በረድፍ እንደቆሙ የእለቱን ትምህርት ርዕሰና አላማ ለተማሪዎች ማስተዋወቅ፤
ƒƒ ተማሪዎችን ከ4 እስከ 6 ቡድን (ምድብ) በማደራጀት የሰውነት ማሟሟቂያ እንቅስቃሴዎች ከቀላል እንቅስቃሴዎች
በመጀመር ለዋናው የእለቱ ተግባር ቅድመ ዝግጅት እንዲያደርጉ ማበረታታት፤
ƒƒ በመማሪያ መፅሀፉ በተገለፀው መሰረትበእጅ ኳስ ጨዋታ ውስጥ ኳስን በመስፈንጠር ወደ ግብ የመወርወር ልምምድ
ሁለት ለሁለት፤ ሦስት ለሦስት እና አራት ለአራትእንዲጫዎቱ ማመቻቸት፤
ƒƒ በመጨረሻም የሰውነት ማቀዝቀ¹ እንቅስቃሴ በየቡድናቸው እንዲሰሩ ማበረታታትና በእለቱ ትምህርት እንቅስቃሴያቸውን
አስመልክቶ ደረጃቸውን መግለፅና ለሚቀጥለው ጊዚያት በመለማመድ በእጅ ኳስ ጨዋታ ውስጥ ኳስን በመስፈንጠር
ወደ ግብ መወርወርን በመለማመድ ማሻሻል እንደሚኖርባቸው ማሳሰብ፤

ክትትልና ግምገማ:-
ƒƒ ከአሁን በፊት የተማሩትን በእጅ ኳስ ጨዋታ ውስጥ ኳስን በመስፈንጠር ወደ ግብ የመወርወር ጨዋታውን
መጫዎታቸውን ምልከታና ግብረመልስ መስጠት፤
ƒƒ በእጅ ኳስ ጨዋታ ውስጥ ኳስን በመስፈንጠር ወደ ግብ የመወርወር ተግባራዊ ለማድረግ ወሳኝ የሆኑ የአሰራር ቅደም
ተከተሎችን እንዲያስረዱ የቃል ጥያቄ በመጠየቅ ማረጋገጥ፤
ƒƒ በጨዋታው ምን ያህል እንደረኩና የተማሩትን ተግባራዊ ስለማድረጋቸው ግብረመልስ መቀበል፤

የጤናና ሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ~ 8ኛ ክፍል ~ የመምህር መምሪያ ~ 59

ምዕራፍ 7 የኢትዮጵያና የአለም ባህላዊ ጨዋታዎች

ምዕራፍ

7 የኢትዮጵያና የአለም ባህላዊ ጨዋታዎች

የክፍለ ጊዜ ብዛት፡ 11

አጠቃላይ ዓላማዎች፡

ተማሪዎች ይህንን ምዕራፍ ከተማራችሁ በኋላ፡-

ƒƒ ዋና ዋና የኢትዮጵያ ባህላዊ ጨዋታዎችን ይተነትናሉ::
ƒƒ የተወሰኑ የአለም ሀገራትን ባህላዊ ጨዋታዎችን ያደንቃሉ::
ƒƒ ባህላዊ ጨዋታዎች ለጤናማ የአኗኗር ዘይቤ የሚያበረክቱትን አስተዋጾ ያደንቃሉ::
ƒƒ የተወሰኑ የኢትዮጵያ ባህላዊ ጨዋታዎችን ክህሎት ያዳብራሉ::

መግቢያ
በዚህ ምዕራፍ የኢትዮጵያ ባህላዊ ስፖርት ጨዋታች ምን እንደሆኑና በኢትዮጵያ ባህል ስፖርት ፌድሬሽን የተካተቱትን የባህል
ስፖርቶች 7ኛ ክፍል ያልተማራችሁት ላይ ትኩረት በማድርግ የሚቀርብ እና የተወሰኑ የአለም ሀገራትን ባህላዊ ጨዋታዎችን በመጠኑ
ለመዳሰስ ተሞክሯል።

7.1 የኢትዮጵያ ባሕላዊ ጨዋታዎች (1 ክ/ጊዜ)

ዝርዝር ዓላማ:-ተማሪዎች ይህንን ርዕስ ተምረው ካጠናቀቁበኋላ:-
ƒƒ የባህል ስፖርት ምንነትን በሚገባ ያብራራሉ።
ƒƒ የኢትዮጵያ ባህል ስፖርት ፈረድሬሽን ህግና ደንብ ከወጣላቸው ባህላዊ ጨዋታዎች መካከል ቢያንስ አራቱን ይዘረዝራሉ።
ƒƒ በአካባቢያቸው የሚዘወተሩ ባህላዊ ጨዋታዎችን ለመጫዎት ፍለጎት ይኖራቸዋል።

መሠረታዊ ጽንሰ-ሀሳብ (ለመምህሩ/ሯ የመነሻ ሀሳብ):-

ƒƒ በመማሪያ መጽሀፉ ለመነሻ የተጠቀሰው ሀሳብ እንዳለ ሆኖ ከተለያዮ የመረጃ ምንጮች ሀሳብን በመፈለግ ማዳበር
ይቻላል።

የመማር-ማስተማር መርጃ መሣሪያዎች እና ሥፍራዎች:-

መርጃ መሣሪያዎች:-ስለባህላዊ ጨዋታ የሚገልጹ ፖስተሮች፤ ስዕሎች፤ ቻርቶች፤ ፊልሞች ፎቶዎችና ጽሁፎች
ሥፍራ:-የንድፈ ሀሳብ ትምህርት በሚሰጥበት ክፍል ውስጥ፣
የጤናና ሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ~ 8ኛ ክፍል ~ የመምህር መምሪያ ~ 60
ምዕራፍ 7 የኢትዮጵያና የአለም ባህላዊ ጨዋታዎች

የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል:-

ƒƒ የዕለቱን ትምህርት ርዕስና አላማዎቹን ማስተዋወቅ፤
ƒƒ ተማሪዎችን በጥንድ በጥንድ በማደራጀት በመማሪያ መጽሐፉ የተሰጡትን ተግባራት ማለትም ባህላዊ ስፖርታዊ
ጨዋታዎች ምን ማለት እንደሆነና በኢትዮጲያ የባህል ስፖርት ፌድሬሽን ህግና ደንብ ወጥቶላቸው በህዝብ የሚዘወተሩ
ባህላዊ ስፖርታዊ ጨዋታዎችን እንድዘረዝሩ ማበረታታት፤
ƒƒ ተማሪዎች የተወያዮበትን እንዲያንፀባርቁ እድል መስጠት፤
ƒƒ ተማሪዎች ከአንፀባረቁት ሀሳብ በመነሳት ባህላዊ ስፖርታዊ ጨዋታዎች ምንነትን በሰፊው ማብራራትና በየኢትዮጵያ
ባህል ስፖርት ፈረድሬሽን ህግና ደንብ ከወጣላቸው ባህላዊ ጨዋታዎች መካከል የተወሰኑትን በ7ኛ ክፍል እንደተማሩትና
በዚህ ክፍል ያሉትንም በመዘርዘር ማስረዳት፤
ƒƒ ተማሪዎችየተማሩትን ትምህርት መረዳታቸውን ለማረጋገጥ የቃል ጥያቄ በመጠየቅ ማረጋገጥ።
ƒƒ ተማሪዎችን በትንንሽ ቡድኖች በማደራጀት በአካባቢያቸው የሚያውቋቸውን ባህላዊ ጨዋታዎች እንዲዘረዝሩና ህግና
ደንብ ወጥቶላቸው በዚህ ክፍል ደረጃ እንዲማሩት ከተጠቀሱት ጋር ያላቸውን ግንኙነት እንዲያብራሩ ማበረታታት
ƒƒ ተማሪዎች የተወያዮበትን ተራ በተራ እንዲያቀርቡ ማበረታታትና ተማሪዎች ከገለጹት አንጻር የተዘረዘሩትን ባህላዊ
ጨዋታዎች ከአሁን በፊት በተማሩት የክፍል ደረጃ እንደተማሩና የተወሰኑትን በወጣላቸው ህግና ደንብ መሰረት
እንዲለማመዱ በሰፊው ማብራራት፣
ƒƒ ከተሰጠው ማብራሪያ በመነሳት ተማሪዎች ያልገባቸውን እንዲጠይቁ እድል መስጠት፣
ƒƒ የተጠየቁትን ጥያቄ በተማሪዎችና በመምህሩ/ሯ መመለስ፣ ስለትግል ባህላዊ ጨዋታ የቤት ስራ መስጠት

ክትትልና ግምገማ:-
ƒƒ የእለቱን ትምህርት ዝርዝር አላማዎች በትክክል መተግበሩን በጥያቄና መልስ፣ በሚያቀርቡት ውይይት እንዲሁም
ጓደኞቻቸው በሚያስተካክሏቸው ሀሳብ መሰረት መገምገም ይቻላል።

7.1.1. የትግል ባህላዊ ስፖርት ጨዋታ (2 ክ/ጊዜ)

ዝርዝር ዓላማ:-ተማሪዎች ይህንን ርዕስ ተምረው ካጠናቀቁበኋላ:-
ƒƒ የትግል ባህላዊ ጨዋታ ምንነትን በትክክል ይገልፃሉ።
ƒƒ ከትግል ባህላዊ ጨዋታ ህጎች መካከል ቢያንስ አራቱን ያብራራሉ።
ƒƒ የትግል ባህላዊ ጨዋታ በተለያየ አተጋገል ዓይነቶች ለመለማመድ ይነሳሳሉ።

መሠረታዊ ጽንሰ-ሀሳብ (ለመምህሩ/ሯ የመነሻ ሀሳብ):-

ƒƒ በዚህ ክፍል ደረጃ እንዲማሩ የሚፈለገው መሰረታዊና ዋናዋና ህጎችን ስለሆነ በመማሪያ መፅሀፉ የተጠቀሱትን መጠቀም
ተገቢ ነው። ይህ እንዳለ ሆኖ ሰፊ የፅንሰ ሀሳብና የተግባር እውቀት እንዲኖረን ከተፈለገ የኢትዮጵያ የባህል ስፖርት
ፌድሬሽን ያዘጋጀውን ማንዋል እንደማጣቀሻ መጠቀም ያስፈልገል።

የመማር-ማስተማር መርጃ መሣሪያዎች እና ሥፍራዎች:-

መርጃ መሣሪያዎች:- ስለትግል የባህል ጨዋታ የሚገልጹ ፖስተሮች፤ ስዕሎች፤ ቻርቶች፤ ፊልሞች ፎቶዎችና ጽሁፎች
ሥፍራ:-የንድፈ ሀሳብ ትምህርት በሚሰጥበት ክፍል ውስጥ፣
የጤናና ሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ~ 8ኛ ክፍል ~ የመምህር መምሪያ ~ 61
ምዕራፍ 7 የኢትዮጵያና የአለም ባህላዊ ጨዋታዎች

የመማር ማስተማር ቅደም ተከተክ:-

ƒƒ የዕለቱን ትምህርት ርዕስና አላማዎቹን ማስተዋወቅ፣
ƒƒ በኢትዮጵያ የባህል ስፖርት ፌድሬሽን ሕግና ደንብ ወጥቶላቸ በስፖርት መልክ የሚዘወተሩት ባህላዊ ስፖርታዊ
ጨዋታዎችን በየግላቸው አዕምሮአቸውን በማሰላሰል ሀሣባቸውን እንዲገልፁ ማበረታታት፤
ƒƒ የክፍሉን ተማሪዎች እንደ ቁጥራቸው በቡድን በማደራጀት ስለትግል ባህላዊ ስፖርት በአካባቢው ስላለው የትግል
ጨዋታ ልምድ እና ተጨማሪ መረጃዎችን እንዲያመጡ የቤት ስራ በተሰጣቸው መሰረት ያገኙትን መረጃ ከጓደኞቻቸው
ጋር እንዲወያዮበት ማድረግ
ƒƒ የተወያዮበትን ሀሳብ ከየቡድኑ ተወካይ በመውጣት ለክፍሉ ተማሪዎች እንዲያንፀባርቁ ማበረታታት፤
ƒƒ ተማሪዎች ከገለጹት አንጻር ስለትግል ጨዋታ መቼ እንደተጀመረና ሌሎችንም ሀሳቦች በማንሳት ማብራሪያ መስጠት፣
ƒƒ የክፍሉን ተማሪዎች ጥንድ ጥንድ በማደራጀትበትግል ባህላዊ ስፖርት ጨዋታ ዋናዋና ሕጎች በተመለከተ በመማሪያ
መጽሐፉ የተቀመጠውን ተግባር ሀሳብ እንዲለዋወጡና ከዚያም የደረሱበትን ድምዳሜ ለክፍሉ ተማሪዎች እንዲያንጸባርቁ
እድል መስጠት፤
ƒƒ በቀረቡት ሀሳብ ላይ በመመሥረት የትግል ጨዋታ በእነሱ ደረጃ ማወቅ ያለባቸውን ዋናዋና ህግ በአጭሩ ማስረዳት፤
ƒƒ ከተሰጠው ማብራሪያ በመነሳት ተማሪዎች ያልገባቸውን እንዲጠይቁ እድል መስጠት፣
ƒƒ የተጠየቁትን ጥያቄ በተማሪዎችና በመምህሩ/ሯ መመለስ፣ ለሚቀጥለው ክፍለ ጊዜ የትግልን ውድድር በተግባር
እንደሚማሩ እና የሚጠበቅባቸውን ዝግጅት መግለፅ፤

ክትትልና ግምገማ:-
ƒƒ የእለቱን ትምህርት ዝርዝር አላማዎች በትክክል መተግበሩን በጥያቄና መልስ፣ በሚያቀርቡት ውይይት እንዲሁም
ጓደኞቻቸው በሚያስተካክሏቸው ሀሳብ መሰረት መገምገም ይቻላል።

7.1.1.2. የትግል ባህላዊ ስፖርት ጨዋታ ልምምድ

ƒƒ የባለፈውን ክፍለ ጊዜ ትምህርት ተማሪዎች እንዲያስታውሱ ማበረታታት፤
ƒƒ የእለቱን ትምህርት ርዕሰና አላማ ለተማሪዎች ማስተዋወቅ፤
ƒƒ ተማሪዎችን ከ4 እስከ 6 ቡድን (ምድብ) በማደራጀት የሰውነት ማሟሟቅያ እንቅስቃሴዎች ከቀላል እንቅስቃሴዎች
በመጀመር ለዋናው የእለቱ ተግባር ቅድመ ዝግጅት እንዲያደርጉ ማበረታታት፤
ƒƒ የትግል ውድድር እድሚያቸው ከ18 ዓመት በላይ ያሉ የሚወዳደሩት ባህላዊ ጨዋታ መሆኑን በመግለፅ በእነሱ ደረጃ
በሰፈራቸው እንደሚጫወቱ በማሰብ በክብደታቸው ተማሪዎችን ማደራጀት
ƒƒ ጉዳት በማያደርስ ፍራሽ ላይ ፍላጎት ያላቸው ተማሪዎች በሚያውቁት የአተጋገል አይነት እንዲታገሉ ማድረግና ሌሎች
ተማሪዎችም እንዲከታተሉ ማድረግ
ƒƒ ሁሉም ተማሪዎች ተራ በተራ እንዲሳተፉ ማድረግና በመካከል የትግል ውድድር ዋና ዋና ህጎች ማስጨበጥ
ƒƒ የአካል ጉዳተኛ ተማሪዎች ክፍል ውስጥ ካሉና የአካል ጉዳታቸው የትግል ጨዋታን መጫዎት የሚፈቅድላቸው ከሆነ
ልዩ ትኩረት አድርጎ እንዲሳተፉ ማድረግ፤ የማያሳትፋቸው ከሆነ ግን በሌላ ተመሣሣይ እንቅስቃሴ እንዲሳተፉ ማድረግ፤
ƒƒ በመጨረሻም የሰውነት ማቀዝቀ እንቅስቃሴ በየቡድናቸው እንዲሰሩ ማበረታታትና በእለቱ ትምህርት እንቅስቃሴያቸውን
አስመልክቶ ባህልን እንዴት ማጎልበት እንዳለባቸው ግንዛቤ በመስጠት ደረጃቸውን መግለፅና ማበረታት፤

የጤናና ሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ~ 8ኛ ክፍል ~ የመምህር መምሪያ ~ 62

ምዕራፍ 7 የኢትዮጵያና የአለም ባህላዊ ጨዋታዎች

ክትትልና ግምገማ:-
ƒƒ የእለቱን ትምህርት ዝርዝር አላማዎች በትክክል መተግበሩን በጥያቄና መልስ፣ በምልከታ፣ በሚያቀርቡት ሀሳብ እንዲሁም
ጓደኞቻቸው በሚያስተካክሏቸው ሀሳብ መሰረት መገምገም ይቻላል።

7.1.2. የኩርቦ ባህላዊ ስፖርት ጨዋታ 2 ክ/ጊዜ)

ማሳሰቢያ:- ይህ ክፍለ ጊዜ ለ7.1.2፣ ለ7.1.2.1 እና ለ7.1.2.2 ለአሉት ንዑስ ርዕሶች የተመደበ ነው።
ዝርዝር ዓላማ:-ተማሪዎች ይህንን ርዕስ ተምረው ካጠናቀቁበኋላ:-
ƒƒ የኩርቦ ባህላዊ ስፖርት ጨዋታ ከሌሎች ባህላዊ ጨዋታ ልዮ ከሚያደርገው መካከል ቢያንስ ሁለቱን ይዘረዝራሉ።
ƒƒ የኩርቦ ባህላዊ ጨዋታ ህጎች መካከል የተወሰኑትን ይዘረዝራሉ።
ƒƒ ውስን በሆነ ክልል በመቆምና በመንቀሳቀስ መሬት ላይ የሚሽከረከርን የኮርቦ ቀለበት በዘንግ መሀሏን ወግቶ ማቆምን
ይለማመዳሉ።
ƒƒ የኩርቦ ባህላዊ ጨዋታ መጫዎት ከፍተኛ ፍላጎት ይኖራቸዋል።

መሠረታዊ ጽንሰ-ሀሳብ (ለመምህሩ/ሯ የመነሻ ሀሳብ):-

የኩርቦ ባህላዊ ስፖርት ዋና ዋና ህጎች:-
ƒƒ የኩርቦ የመወደሪያ ቦታ የተስተካከለ ሆኖ የኩርቦዋን ቀለበት ያለምንም ችግር የሚያንከባልልና የሚወረውረው ዘንግ
መሬት ወግቶ መቆም የሚያስችል መሆን አለበት፣
ƒƒ የዘንግ መወርወሪያ ቦታ ለወንድ 10በ10 ሜትር ሲሆን ለሴት 7 ሜትር ርዝመት እና 10 ሜትር ወርድ እንዲኖረው
ያስፈልጋል።
ƒƒ የኩርቦው የማሽከርከሪያ ክልል ርዝመቱ 10 ሜትር ወርዱ 1.25 ሜትር ለሁለቱም ፆታዎች ነው።
ƒƒ የኩርቦ ዘንግ ከተለያየ እንጨት ዓይነቶች የኩርቦዋን ቀለበት ወግቶ መቆም እንዲችል በጫፉ ላይ 30 ሴ.ሜ ርዝመት
ያለው ቀለል ያለ ሹል ብረት በመግጠም የሚዘጋጅ ነው።
ƒƒ የኩርቦ ቀለበት ከማይሰብር ልዩ ሐረግ፣ ከፕላስቲክ ቱቦ፣ ከብረት ለመስራት ከሚያስችሉ ነገሮች በክብ ቅርፅ የሚዘጋጅ
መሆን አለበት። ክብ ስፋቱ 30 ሳ.ሜ ውፍረቱ 7 ሴ.ሜ ለሁለቱም ፆታዎች
ƒƒ የኩርቦ ባህላዊ ውድድር ዳኞች አንድ ዋና ዳኛ እና አንድ ነጥብ መዝጋቢ ዳኛ ናቸው።

የመማር-ማስተማር መርጃ መሣሪያዎች እና ሥፍራዎች:-

መርጃ መሣሪያዎች:- ስለኮርቦ የባህል ጨዋታ የሚገልጹ ፖስተሮች፤ ስዕሎች፤ ቻርቶች፤ ፊልሞች ፎቶዎችና ጽሁፎች
ሥፍራ:-የንድፈ ሀሳብ ትምህርት በሚሰጥበት ክፍል ውስጥ፣

የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል:-

ƒƒ የዕለቱን ትምህርት ርዕስና አላማዎቹን ማስተዋወቅ
ƒƒ የክፍሉን ተማሪዎች እንደ ቁጥራቸው በቡድን በማደራጀት ስለኩርቦ ባህላዊ ስፖርት በአካባቢው ስላለው የጨዋታ
ልምድ እና ተጨማሪ መረጃዎችን እንዲያመጡ የቤት ስራ በተሰጣቸው መሰረት ያገኙትን መረጃ ከጓደኞቻቸው ጋር
እንዲወያዮበት ማድረግ

የጤናና ሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ~ 8ኛ ክፍል ~ የመምህር መምሪያ ~ 63

ምዕራፍ 7 የኢትዮጵያና የአለም ባህላዊ ጨዋታዎች

ƒƒ በኢትዮጵያ የባህል ስፖርት ፌድሬሽን ሕግና ደንብ ወጥቶላቸ በስፖርት መልክ ከሚዘወተሩ ባህላዊ ስፖርታዊ
ጨዋታዎች መካከል አንዱ የኩርቦ ባህላዊ ጨዋታ መሆኑን በመግለፅ ስለኮርቦ ጨዋታ ታሪክ፤ የትኛውን የአካል ብቃት
እንደሚያዳብር እና የጨዋታ አይነቶችን በቡድን በመሆን ሀሳባቸውን እንዲለዋወጡ ማበረታታት፤
ƒƒ የተወያዮበትን ሀሳብ ከየቡድኑ ተወካይ በመውጣት ለክፍሉ ተማሪዎች እንዲያንፀባርቁ ማበረታታት፤
ƒƒ ተማሪዎች ከገለጹት አንጻር ስለኩርቦ ጨዋታ ታሪክ ምን እንደሚያዳብር እና የጨዋታ ዓይነቶችን በመዘርዘር ማብራሪያ
መስጠት፣
ƒƒ የክፍሉን ተማሪዎች ጥንድ ጥንድ በማደራጀትየኩርቦ ባህላዊ ስፖርት ጨዋታ ዋናዋና ሕጎች በተመለከተ በመማሪያ
መጽሐፉ የተቀመጠውን ተግባር ሀሳብ እንዲለዋወጡና ከዚያም የደረሱበትን ድምዳሜ ለክፍሉ ተማሪዎች እንዲያንጸባርቁ
እድል መስጠት፤
ƒƒ በቀረቡት ሀሳብ ላይ በመመሥረት የኩርቦ ጨዋታ በእነሱ ደረጃ ማወቅ ያለባቸውን ዋናዋና ህግ በአጭሩ ማስረዳት፤
ƒƒ ከተሰጠው ማብራሪያ በመነሳት ተማሪዎች ያልገባቸውን እንዲጠይቁ እድል መስጠት፣
ƒƒ የተጠየቁትን ጥያቄ በተማሪዎችና በመምህሩ/ሯ መመለስ፣ ለሚቀጥለው ክፍለ ጊዜ የኩርቦ መጫዎቻ ዘንግና ቀለበት
አዘጋጅተው እንዲመጡና በተግባር እንደሚማሩ መግለፅ፤

ክትትልና ግምገማ:-
ƒƒ የእለቱን ትምህርት ዝርዝር አላማዎች በትክክል መተግበሩን በጥያቄና መልስ፣ በሚያቀርቡት ውይይት እንዲሁም
ጓደኞቻቸው በሚያስተካክሏቸው ሀሳብ መሰረት መገምገም ይቻላል።

7.1.2.3. የኩርቦ ባህላዊ ጨዋታ ልምምድ

ƒƒ የባለፈውን ክፍለ ጊዜ ትምህርት ተማሪዎች እንዲያስታውሱ ማበረታታት፤
ƒƒ የእለቱን ትምህርት ርዕሰና አላማ ለተማሪዎች ማስተዋወቅ፤
ƒƒ ተማሪዎችን ከ4 እስከ 6 ቡድን (ምድብ) በማደራጀት የሰውነት ማሟሟቅያ እንቅስቃሴዎች ከቀላል እንቅስቃሴዎች
በመጀመር ለዋናው የእለቱ ተግባር ቅድመ ዝግጅት እንዲያደርጉ ማበረታታት፤
ƒƒ ለኮርቦ ባህላዊ ጨዋታ በአዘጋጁት ዘንግና የኮርቦ ቀለበት ቁጥር መሰረት ጥንድ ጥንድ ሆነው እንዲደራጁ ማድረግ
ƒƒ የኩርቦ የጨዋታ ቦታ በርዝመቱም ሆነ በስፋቱ ለሁለቱም ፆታ አመጣጥኖ በማዘጋጀት ቀለበት በማሽከርክር በዘንጉ
ወግቶ ማቆም ወይም ማሾለክን እንዲለማመዱ ማበረታታት
ƒƒ ሁሉም ተማሪዎች ተራ በተራ እንዲሳተፉ ማድረግና በመካከል የኮርቦ ጨዋታ ህግን እንዲገነዘቡት ማድረግ
ƒƒ ይህ ልምምድ በአንድ ቀን ብቻ ተሰርቶ የሚተው ሳይሆን ተማሪዎች በትርፍ ጊዚያቸው እንዲለማመዱት ያስፈልጋል
ƒƒ የአካል ጉዳተኛ ተማሪዎች ክፍል ውስጥ ካሉና የአካል ጉዳታቸው የኮርቦ ጨዋታን መጫዎት የሚፈቅድላቸው ከሆነ ልዩ
ትኩረት አድርጎ እንዲሳተፉ ማድረግ፤ የማያሳትፋቸው ከሆነ ግን በሌላ ተመሣሣይ እንቅስቃሴ እንዲሳተፉ ማድረግ፤
ƒƒ በመጨረሻም የሰውነት ማቀዝቀ እንቅስቃሴ በየቡድናቸው እንዲሰሩ ማበረታታትና በእለቱ ትምህርት እንቅስቃሴያቸውን
አስመልክቶ የኮርቦ ጨዋታ ኢላማን የሚያለማምድ የባህል ጨዋታ ስለሆን በትርፍ ጊዚያቸው መለማመድ እንዳለባቸው
ግንዛቤ በመስጠት ደረጃቸውን መግለፅና ማበረታት

የጤናና ሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ~ 8ኛ ክፍል ~ የመምህር መምሪያ ~ 64

ምዕራፍ 7 የኢትዮጵያና የአለም ባህላዊ ጨዋታዎች

ክትትልና ግምገማ:-
ƒƒ የእለቱን ትምህርት ዝርዝር አላማዎች በትክክል መተግበሩን በጥያቄና መልስ፣ በምልከታ፣ በሚያቀርቡት ሀሳብ እንዲሁም
ጓደኞቻቸው በሚያስተካክሏቸው ሀሳብ መሰረት መገምገም ይቻላል።

7.1.3. የቡብ የባህላዊ ስፖርት ጨዋታ 2 ክ/ጊዜ)

ዝርዝር ዓላማ:-ተማሪዎች ይህንን ርዕስ ተምረው ካጠናቀቁበኋላ:-
ƒƒ የቡብ ባህላዊ ጨዋታ በየትኛው አከባቢ በይበልጥ ይዘወተር እንደነበር ይገልፃሉ።
ƒƒ ከቡብ ባህላዊ ጨዋታ ህጎች መካከል ቢያንስ አራቱን ይዘረዝራሉ።
ƒƒ የቡብ ባህላዊ ጨዋታን ለመጫዎት ተነሳሽነት ያሳያሉ።
ƒƒ የቡብ ባህላዊ ጨዋታን በተወሰነ ደረጃ ጨዋታውን ይለማመዳሉ።

መሠረታዊ ጽንሰ-ሀሳብ (ለመምህሩ/ሯ የመነሻ ሀሳብ):-

የቡብ ባህላዊ ጨዋታ ዋና ዋና ህጎች:-
ƒƒ የመጫዎቻ ቦርድና ጠጠር በአካባቢው ከሚገኙ ነገሮች ሊዘጋጁ ይችላሉ።
ƒƒ የመጫዎቻ ቦርድ መጠንና ይዘት:-
ªªየቦርድ ርዝመትና ወርዱ በተመሳሳይ 40 በ40 ሳ.ሜ ነው።
ªªቦርዱ ወይም ሳንቃው በውስጡ 4 ካሬዎች ወደጎን 4 ካሬዎች ወደታች በድምሩ በ16 ካሬዎች የተከፋፈለ ነው።
ªªየቦርዱ ከፍታ ከ8 እስከ 10 ሳ.ሜ ሲሆን የሚቀባው የቀለም ዓይነት ነጭ ሲሆን መስመሮቹ ደግሞ ጥቁር ቀለም መሆን
አለባቸው።
ªªየቡብ መጫዎቻ ቦርድ 24 የጠጠር ማስቀመጫ እና አንድ የጨዋታ መጀመሪያ ጣቢያ በድምሩ 25 ጣቢያዎች አሉት።
ªªበቡብ መጫዎቻ ቦርድ መካከል ላይ የሚገኘው የዳይመንድ ቅርፅ ያለው ጣቢያ ወይም ስፍራ ውድድሩን ለመጀመር
የሚኬድበት ጣቢያ ነው።
ƒƒ ውድድሩን የሚመሩት ዳኞች አንድ ዋና ዳኛና አንድ ነጥብ መዝጋቢ ናቸው።

የመማር-ማስተማር መርጃ መሣሪያዎች እና ሥፍራዎች:-

መርጃ መሣሪያዎች:- ስለቡብ የባህል ጨዋታ የሚገልጹ ፖስተሮች፤ ስዕሎች፤ ቻርቶች፤ ፊልሞች ፎቶዎችና ጽሁፎች
ሥፍራ:-የንድፈ ሀሳብ ትምህርት በሚሰጥበት ክፍል ውስጥ፣
የመማር ማስተማር ቅደም ተከተክ:-
ƒƒ የዕለቱን ትምህርት ርዕስና አላማዎቹን ማስተዋወቅ
ƒƒ የክፍሉን ተማሪዎች እንደ ቁጥራቸው በቡድን በማደራጀት ስለቡብ ባህላዊ ስፖርት በአካባቢው ስላለው የጨዋታ
ልምድ እና ተጨማሪ መረጃዎችን እንዲያመጡ የቤት ስራ በተሰጣቸው መሰረት ያገኙትን መረጃ ከጓደኞቻቸው ጋር
እንዲወያዮበት ማድረግ

የጤናና ሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ~ 8ኛ ክፍል ~ የመምህር መምሪያ ~ 65

ምዕራፍ 7 የኢትዮጵያና የአለም ባህላዊ ጨዋታዎች

ƒƒ በኢትዮåያ የባህል ስፖርት ፌድሬሽን ሕግና ደንብ ወጥቶላቸ በስፖርት መልክ ከሚዘወተሩ ባህላዊ ስፖርታዊ ጨዋታዎች
መካከል አንዱ የቡብ ባህላዊ ጨዋታ መሆኑን በመግለፅ ስለቡብ ጨዋታ ታሪክ፤ የሚሰጠውን ጥቅምር እና የመጫወቻ
ቦርድና ጠጠር ከምን ሊዘጋጁ እንደሚችሉ በቡድን በመሆን ሀሳባቸውን እንዲለዋወጡ ማበረታታት
ƒƒ የተወያዮበትን ሀሳብ ከየቡድኑ ተወካይ በመውጣት ለክፍሉ ተማሪዎች እንዲያንፀባርቁ ማበረታታት፤
ƒƒ ተማሪዎች ከገለጹት አንጻር ስለቡብ ጨዋታ ታሪክ የሚሰጠውን ጥቅምና የመጫወቻ ቦርድ ከምን እንዲሚዘጋጅ
በመዘርዘር ማብራሪያ መስጠት፣
ƒƒ የክፍሉን ተማሪዎች ጥንድ ጥንድ በማደራጀት የቡብ ባህላዊ ስፖርት ጨዋታ ዋናዋና ሕጎች በተመለከተ በመማሪያ
መጽሐፉ የተቀመጠውን ተግባር ሀሳብ እንዲለዋወጡና ከዚያም የደረሱበትን ድምዳሜ ለክፍሉ ተማሪዎች እንዲያንጸባርቁ
እድል መስጠት፤
ƒƒ በቀረቡት ሀሳብ ላይ በመመስረት የቡብ ጨዋታ በእነሱ ደረጃ ማወቅ ያለባቸውን ዋናዋና ህግ በአጭሩ ማስረዳት፤
ƒƒ ከተሰጠው ማብራሪያ በመነሳት ተማሪዎች ያልገባቸውን እንዲጠይቁ እድል መስጠት፣
ƒƒ የተጠየቁትን ጥያቄ በተማሪዎችና በመምህሩ/ሯ መመለስ፣ ለሚቀጥለው ክፍለ ጊዜ የቡብ መጫዎቻ ቦርድና ጠጠር
አዘጋጅተው እንዲመጡና በተግባር እንደሚማሩ መግለፅ

ክትትልና ግምገማ:-
ƒƒ የእለቱን ትምህርት ዝርዝር አላማዎች በትክክል መተግበሩን በጥያቄና መልስ፣ በሚያቀርቡት ውይይት እንዲሁም
ጓደኞቻቸው በሚያስተካክሏቸው ሀሳብ መሰረት መገምገም ይቻላል።

7.1.3.2. የቡብ ባህላዊ ጨዋታ ልምምድ

ƒƒ የባለፈውን ክፍለ ጊዜ ትምህርት ተማሪዎች እንዲያስታውሱ ማበረታታት፤
ƒƒ የእለቱን ትምህርት ርዕሰና አላማ ለተማሪዎች ማስተዋወቅ፤
ƒƒ ለቡብ ባህላዊ ጨዋታ በአዘጋጁት ቦርድና ጠጠር መሰረት ጥንድ ጥንድ ሆነው እንዲደራጁ ማድረግ
ƒƒ የቡብ ባህላዊ ጨዋታን የሚችሉ ተማሪዎች ካሉ ካልሆነም ይህን ጨዋታ የሚችል ባለሙያ በመጋበዝ የአጨዋወቱን
ሁኔታ በተግበርና በገለጻ ማስተማር
ƒƒ በተመለከቱት መሰረት ሁሉም ተማሪዎች ተራ በተራ እንዲሳተፉ ማድረግና በመካከል የቡብ ጨዋታ ህግን እንዲገነዘቡት
ማድረግ
ƒƒ ይህ ልምምድ በአንድ ቀን ብቻ ተሰርቶ የሚተው ሳይሆን ተማሪዎች በትርፍ ጊዚያቸው እንዲለማመዱት ያስፈልጋል
ƒƒ ስለቀስት ባህላዊ ጨዋታ በአካባቢያችሁ ከሚገኙ ታላላቅ ሰዎችን ጠይይቀው እንዲመጡ የቤት ስራ መስጠት

ክትትልና ግምገማ:-
ƒƒ የእለቱን ትምህርት ዝርዝር አላማዎች በትክክል መተግበሩን በጥያቄና መልስ፣ በምልከታ፣ በሚያቀርቡት ሀሳብ እንዲሁም
ጓደኞቻቸው ጋር በሚያደርጉት ልምምድ መገምገም ይቻላል።

የጤናና ሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ~ 8ኛ ክፍል ~ የመምህር መምሪያ ~ 66

ምዕራፍ 7 የኢትዮጵያና የአለም ባህላዊ ጨዋታዎች

7.1.4 የቀስት ባህላዊ ጨዋታ 2 ክ/ጊዜ)

ማሳሰቢያ:- ይህ ክፍለ ጊዜ ለ7.1.4፣ ለ7.1.4.1 እና ለ7.1.4. 2 ለአሉት ንዑስ ርዕሶች የተመደበ ነው።
ዝርዝር ዓላማ:-ተማሪዎች ይህንን ርዕስ ተምረው ካጠናቀቁበኋላ:-
ƒƒ የቀስት ባህላዊ ጨዋታ ምን ምን ብቃቶችን እንደሚያዳብ ያብራራሉ
ƒƒ ከቀስት ባህላዊ ጨዋታ ክጎች መካከል ቢያንስ ሦስቱን ይዘረዝራሉ
ƒƒ በቀስት ባህላዊ ጨዋታ የተሻለ የተጫወቱትን ተማሪዎች ያደንቃሉ
ƒƒ በቀስት ባግላዊ ጨዋታ ህጉ በሚፈቅደው መሰረት ጨዋታውን ይለማመዳሉ

መሠረታዊ ጽንሰ-ሀሳብ (ለመምህሩ/ሯ የመነሻ ሀሳብ):-

ƒƒ በዚህ ክፍል ደረጃ እንዲማሩ የሚፈለገው መሰረታዊና ዋናዋና ነጥቦችን ስለሆነ በመማሪያ መፅሀፉ የተጠቀሱትን
መጠቀም ተገቢ ነው። ይህ እንዳለ ሆኖ ሰፊ የፅንሰ ሀሳብና የተግባር እውቀት እንዲኖረን ከተፈለገ የኢትዮåያ የባህል
ስፖርት ፌድሬሽን ያዘጋጀውን ማንዋል እንደማጣቀሻ መጠቀም ያስፈልገል።
ƒƒ የቀስት ባህላዊ ጨዋታ የማነጣጠር፣ የማለም፣ የእይታና ትክክለኛነትን፣ በራስ
ƒƒ መተማመንንና የመገመት ብቃት የሚለካበትና ተጋጣሚ ቡድኖች ሁለት ሁለት
ƒƒ ተወዳዳሪዎችን በማሰለፍ የአጨዋወት ህግና ደንብ በሚፈቅደው መሠረት ለውድድር
ƒƒ በተዘጋጀው ቀስት በተወሰነ ርቀት ላይ የተዘጋጀውን የመወዳደሪያ ቦርድ ለውድድር
ƒƒ በተከለለ ቦታ ላይ በመሆን ቀስቱን አስፈንጥሮ አስፈላጊው ቦታ ላይ በመውጋት ከተጋጣሚ ቡድንየነጥብ ብልጫ
በማምጣት አሸናፊ ለመሆን የሚደረግ ባህላዊ ጫዋታ ነው።

የመማር-ማስተማር መርጃ መሣሪያዎች እና ሥፍራዎች:-

መርጃ መሣሪያዎች:- ስለቀስት የባህል ጨዋታ የሚገልጹ ፖስተሮች፤ ስዕሎች፤ ቻርቶች፤ ፊልሞች ፎቶዎችና ጽሁፎች
ሥፍራ:-የንድፈ ሀሳብ ትምህርት በሚሰጥበት ክፍል ውስጥ፣

የመማር ማስተማር ቅደም ተከተክ:-

ƒƒ የዕለቱን ትምህርት ርዕስና አላማዎቹን ማስተዋወቅ
ƒƒ የክፍሉን ተማሪዎች እንደ ቁጥራቸው በቡድን በማደራጀት ስለቀስት ባህላዊ ስፖርት በአካባቢው ስላለው የጨዋታ
ልምድ እና ተጨማሪ መረጃዎችን እንዲያመጡ የቤት ስራ በተሰጣቸው መሰረት ያገኙትን መረጃ ከጓደኞቻቸው ጋር
እንዲወያዮበት ማድረግ
ƒƒ በኢትዮåያ የባህል ስፖርት ፌድሬሽን ሕግና ደንብ ወጥቶላቸ በስፖርት መልክ ከሚዘወተሩ ባህላዊ ስፖርታዊ
ጨዋታዎች መካከል አንዱ የቀስት ባህላዊ ጨዋታ መሆኑን በመግለፅ ስለቀስት ጨዋታ ታሪክ፤ የሚሰጠውን ጥቅምር
እና የመጫወቻመሳሪያዎቹ ከምን ሊዘጋጁ እነደሚችሉ በቡድን በመሆን ሀሳባቸውን እንዲለዋወጡ ማበረታታት
ƒƒ የተወያዮበትን ሀሳብ ከየቡድኑ ተወካይ በመውጣትለክፍሉ ተማሪዎች እንዲያንፀባርቁ ማበረታታት፤
ƒƒ ተማሪዎች ከገለጹት አንጻር ስለቀስትባህላዊ ጨዋታ ታሪክ፤ የሚሰጠውን ጥቅምና የመጫወቻ መሳሪያዎች ከምን
እንዲሚዘጋጅ በመዘርዘር ማብራሪያ መስጠት፣

የጤናና ሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ~ 8ኛ ክፍል ~ የመምህር መምሪያ ~ 67

ምዕራፍ 7 የኢትዮጵያና የአለም ባህላዊ ጨዋታዎች

ƒƒ የክፍሉን ተማሪዎች ጥንድ ጥንድ በማደራጀት የቀስት ባህላዊ ስፖርት ጨዋታ ዋናዋና ሕጎች በተመለከተ በመማሪያ
መጽሐፉ የተቀመጠውን ተግባር ሀሳብ እንዲለዋወጡና ከዚያም የደረሱበትን ድምዳሜ ለክፍሉ ተማሪዎች እንዲያንጸባርቁ
እድል መስጠት፤
ƒƒ በቀረቡት ሀሳብ ላይ በመመስረት የቀስትባህላዊ ጨዋታ በእነሱ ደረጃ ማወቅ ያለባቸውን ዋናዋና ህግ በአጭሩ ማስረዳት፤
ƒƒ ከተሰጠው ማብራሪያ በመነሳት ተማሪዎች ያልገባቸውን እንዲጠይቁ እድል መስጠት፣
ƒƒ የተጠየቁትን ጥያቄ በተማሪዎችና በመምህሩ/ሯ መመለስ፣ ለሚቀጥለው ክፍለ ጊዜ የቀስት መጫዎቻ መሳሪያዎችን
አዘጋጅተው እንዲመጡና በተግባር እንደሚማሩ መግለፅ፤

ክትትልና ግምገማ:-
ƒƒ የእለቱን ትምህርት ዝርዝር አላማዎች በትክክል መተግበሩን በጥያቄና መልስ፣ በሚያቀርቡት ውይይት እንዲሁም
ጓደኞቻቸው በሚያስተካክሏቸው ሀሳብ መሰረት መገምገም ይቻላል።

7.1.4.3. የቀስት ባህላዊ ጨዋታ ልምምድ

ƒƒ የባለፈውን ክፍለ ጊዜ ትምህርት ተማሪዎች እንዲያስታውሱ ማበረታታት፤
ƒƒ የእለቱን ትምህርት ርዕሰና አላማ ለተማሪዎች ማስተዋወቅ፤
ƒƒ ለቀስት መጫዎቻ የሚሆነውን ሜዳ ቀድሞ በማዘጋጀት ስለሜዳው አሰራር፤የቀስት ባህላዊ ጨዋታ መሣሪያዎች በባለሙያ
ገለፃ ማድረግ እና ተማሪዎች ከሚያውቁት የቀስት ጨዋታ ጋር ያለውን ሁኔታ እንዲያገናዝቡ ማበረታታት፤
ƒƒ የቀስት ባህላዊ ጨዋታን የሚችሉ ተማሪዎች ካሉ ካልሆነም ይህን ጨዋታ የሚችል የተጋበዘው ባለሙያ የአጨዋወቱን
ሁኔታ በተግባርና በገለጻ ማስተማር፤
ƒƒ በተመለከቱት መሰረት ለኢላማ የሚሆን ከካርቶን የሚቀመጥበትን ርቀቱንበመመጠን ሁሉም ተማሪዎች ተራ በተራ
እንዲሳተፉ ማድረግ፤
ƒƒ ይህ ልምምድ በአንድ ቀን ብቻ ተሰርቶ የሚተው ሳይሆን ተማሪዎች በትርፍ ጊዚያቸው እንዲለማመዱት ያስፈልጋል።

ክትትልና ግምገማ:-
ƒƒ የእለቱን ትምህርት ዝርዝር አላማዎች በትክክል መተግበሩን በጥያቄና መልስ፣ በምልከታ፣ በሚያቀርቡት ሀሳብ እንዲሁም
ጓደኞቻቸው ጋር በሚያደርጉት ልምምድ መገምገም ይቻላል።

7.2 የተወሰኑ የአለም ሀገራት ባህላዊ ጨዋታዎች 2 ክ/ጊዜ)

7.2.1. የድራጎንእባብጨዋታ 1 ክ/ጊዜ)

ዝርዝር ዓላማ:-ተማሪዎች ይህንን ርዕስ ተምረው ካጠናቀቁበኋላ:-
ƒƒ የተወሰኑ የአለም ሀገራት ባህላዊ ጨዋታዎች መካከል ቢያንስ ሦስቱን ይዘረዝራሉ።
ƒƒ ከአለም ሀገራት ባህላዊ ጨዋታዎች መካከል የድራጎንእባብጨዋታይጫዎታሉ።
ƒƒ የአለም ሀገራት ባህላዊ ጨዋታዎችን ያደንቃሉ።

የመማር-ማስተማር መርጃ መሣሪያዎች እና ሥፍራዎች:-

የጤናና ሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ~ 8ኛ ክፍል ~ የመምህር መምሪያ ~ 68

ምዕራፍ 7 የኢትዮጵያና የአለም ባህላዊ ጨዋታዎች

መርጃ መሣሪያዎች:- የአለም ሀገራት ባህላዊ ጨዋታዎችን የሚገልጹ ፖስተሮች፤ ስዕሎች፤ ፊልሞች፤ ፎቶዎችና ጽሁፎች
ሥፍራ:-የንድፈ ሀሳብ ትምህርት በሚሰጥበት ክፍል ውስጥ፣

የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል:-

ƒƒ የባለፈውን ክፍለ ጊዜ ትምህርት ተማሪዎች እንዲያስታውሱ ማበረታታት፤
ƒƒ የክፍሉ ተማሪዎች በረድፍ እንደቆሙ የእለቱን ትምህርት ርዕሰና አላማ ለተማሪዎች ማስተዋወቅ፤
ƒƒ ተማሪዎችን ከ4 እስከ 6 ቡድን (ምድብ) በማደራጀት የሰውነት ማሟሟቂያ እንቅስቃሴዎች ከቀላል እንቅስቃሴዎች
በመጀመር ለዋናው የእለቱ ተግባር ቅድመ ዝግጅት እንዲያደርጉ ማበረታታት፤
ƒƒ በመማሪያ መፅሀፉ በተገለፀው መሰረትየድራጎንእባብጨዋታበየቡድናቸው እንዲጫዎቱ ክትትልና ድጋፍ ማድረግ፤
ƒƒ የጨዋታው ህግና ደንብ በሚጋ እንዲገባቸው መጀመሪያ አንድ ቡድን ሰርቶ እንዲያሳይ ማበረታታት፤
ƒƒ በመጨረሻም የሰውነት ማቀዝቀ¹ እንቅስቃሴ በየቡድናቸው እንዲሰሩ ማበረታታትና በእለቱ ትምህርት እንቅስቃሴያቸውን
አስመልክቶ ብዙ ጊዜ አሸናፊ የሆነውን መሪ ወይም የሆነችውን መሪ በማበረታታት ለሚቀጥለው ክፍለ ጊዜ የሌሎች
አለም ሀገራትን ጨዋታ የቻሉትን ያህል ጠይቀው እንዲመጡ ማሳሰብ፤

ክትትልና ግምገማ:-
ƒƒ የእለቱን ትምህርት ዝርዝር አላማዎች በትክክል መተግበሩን በጥያቄና መልስ፤ በምልከታ እንዲሁም ከጓደኞቻቸው ጋር
ሲጫዎቱና እንቅስቃሴውን ለመስራት በሚያሳዮት ፍላጎት መሰረት መገምገም ይቻላል::
ƒƒ በጨዋታው ምን ያህል እንደረኩና የተማሩትን ተግባራዊ ስለማድረጋቸው ግብረመልስ መቀበል፤

7.2.2. የአፍሪካ ልጃገረዶች ባሕላዊ ጨዋታ (ስቶኪንግ) 1 ክ/ጊዜ)

ƒƒ ጨዋታውየመግባባት እና የመተባበር ከህሎትጋር ያለውን ግንኙነት በትክክል ያበራራሉ።
ƒƒ ልዩ የቅርጫት ኳስ ጨዋታ ሲጫዎቱ ራሳቸውን በማወቅና በአግባቡ ለመተባበር ተነሳሽነት ያሳያሉ።
ƒƒ ልዩ የቅርጫት ኳስ ጨዋታ እንቅስቃሴን በትክክል ይሰራሉ።

የመማር-ማስተማር መርጃ መሣሪያዎች እና ሥፍራዎች:-

መርጃ መሣሪያዎች:- ገመድ፣

ሥፍራ:- የተግባር ትምህርት የሚሰጥበት የስፖርት ሜዳ፣

የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል:-

ƒƒ የባለፈውን ትምህርት በጥያቄና መልስ መከለስ፣
ƒƒ የእለቱን ትምህርት ርዕሰና አላማ ለተማሪዎች ማስተዋወቅ፣
ƒƒ ተማሪዎችን በአራት ወይም በስድስት ምድብ በማደራጀት የሰውነት ማሟሟቂያ እንቅስቃሴዎች ከቀላል እንቅስቃሴዎች
በመጀመር ለዋናው የእለቱ ተግባር ቅድመ ዝግጅት እንዲያደርጉ ማበረታታት፣
ƒƒ ተማሪዎች ከእለቱ ተግባር ወይም ትምህርት ጋር ተቀራራቢነት ያለው የሰውነት ማሟሟቂያ እንቅስቃሴ እንዲሰሩ
ማበረታታትና ተማሪዎች እንቅስቃሴዎችን ሲሰሩ በመከታተል ማስተካከያ መስጠት፣
ƒƒ በመማሪያ መፅሀፉ በተገለፀው መሰረት የጨዋታው ህግና አጨዋወት መሰረት ተግባራዊ ማድረግ፣

የጤናና ሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ~ 8ኛ ክፍል ~ የመምህር መምሪያ ~ 69

ምዕራፍ 7 የኢትዮጵያና የአለም ባህላዊ ጨዋታዎች

ƒƒ ጨዋታውን በመደጋገም እንዲጫዎቱ እድል መስጠት፣

ƒƒ በመቀጠልም የሰውነት ማቀዝቀዣ እና ማሳሳቢያ እንቅስቃሴ እንዲያደርጉ ማድረግ፣
ƒƒ የእለቱ ትምህርት ምን ያህል እንዳዝናናቸውና እንደሳባቸው እንዲሁም ለምን ጥቅም እንደሆነ እንዲገልጹ ማድረግና
ማጠናቀቅ፣

ክትትልና ግምገማ:-
ƒƒ የእለቱን ትምህርት ዝርዝር አላማዎች በትክክል መተግበሩን በጥያቄና መልስ፤ በምልከታ እንዲሁም ከጓደኞቻቸው ጋር
ሲጫዎቱና እንቅስቃሴውን ለመስራት በሚያሳዮት ፍላጎት መሰረት መገምገም ይቻላል::
ƒƒ በጨዋታው ምን ያህል እንደረኩና የተማሩትን ተግባራዊ ስለማድረጋቸው ግብረመልስ መቀበል፤

የጤናና ሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ~ 8ኛ ክፍል ~ የመምህር መምሪያ ~ 70

You might also like