You are on page 1of 30

በእቴጌ መነን የልጃገረዶች አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ

ትምህርት ቤት የማለፊያ ነጥብ ማምጣት ባልቻሉ


ተማሪዎች ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ የሚያሳድሩ ጉዳዮች
እና መፍትሄዎቻቸው


ሀብታሙ ዱጉማ
ውበቱ በዛብህ
ገነነ ተስፋዬ
1. መግቢያ
1.1. የጥናቱ አነሳሽ ምክንያት (STATEMENT OF THE
PROBLEM)
 ትምህርት ቤቱ አዲስ በመሆኑ በትምህርት ቤቱ አጠቃላይ
ማህበረሰብ ችግር መከሰቱ አይቀሬ ነው፡፡
 ከሁሉም ችግሮች ተማሪዎች ላይ የሚደርሱ ችግሮች ስሱ
(sensitive) በመሆናቸው ቅድሚያ ሊሰጣቸው ይገባል፡፡
 በተማሪዎች ላይ ካጋጠሙ ችግሮች ውስጥ የት/ቤቱን ማለፊያ
ነጥብ ማምጣት ያልቻሉ ተማሪዎች መኖራቸው አንዱ ነው፡፡
 በ2014 ዓ.ም በመጀመሪያው መንፈቀ ዓመት 38 (9.41%)
ተማሪዎች የማለፊያ ነጥብ ማምጣት አልቻሉም፡፡
የቀጠለ…
በክፍል ደረጃ ደግሞ ከ9ኛ ክፍል 21 ተማሪዎች
(17.4%)፣ ከ10ኛ ክፍል 1 ተማሪ (2.3%)፣ ከ11ኛ ክፍል
8 ተማሪዎች (4.42%)፣ ከ12ኛ ክፍል 8 ተማሪዎች
(13.8%) የማለፊያ ነጥቡን ማስመዝገብ አልቻሉም፡፡
እነዚህ ተማሪዎች የማለፊያ ነጥብ እንዳያመጡ
እንቅፋት የሆኑባቸውን ጉዳዮች በመለየት መፍትሔ
ለመስጠት በማሰብ ይህ ጥናት ተከናውኗል፡፡
1.2. የጥናቱ ዓላማዎች (OBJECTIVES OF THE STUDY)
ይህ ጥናት የሚከተሉትን ሁለት ዓላማዎች አሳክቷል፡፡
ተማሪዎቹ የማለፊያ ነጥብ እንዳያመጡ ያደረጓቸውን
ጉዳዮች መለየት፤
በተማሪዎቹ ውጤት ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ላሳደሩ ጉዳዮች
መፍትሔ መስጠት፡፡
1.3. የጥናቱ አስፈላጊነት (IMPORTANCE OF THE
STUDY)
ይህ ጥናት በመከናወኑ በዋናነት ተማሪዎች፣ መምህራን፣ ርእሳነ
መምህራን እና አጥኝዎች ተጠቃሚዎች ናቸው፡፡
 ተማሪዎች ችግሮቻቸው እንዲፈቱላቸውና የማለፊያ ነጥቡን
አንዲያስመዘግቡ እድል ይፈጥርላቸዋል፡፡
 መምህራን ያሉባቸውን ችግሮች በመለየት ችግሮቹ እንዲቀረፉና
ተማሪዎቻቸውን ውጤታማ እንዲያደርጉ እድል
ይፈጥርላቸዋል፡፡
 ርዕሳነ መምህራን ተማሪዎቹ ያጠማቸውን ችግር በመገንዘብ
መፍትሄ እንዲሰጡ አጋጣሚ ይፈጠርላቸዋል፡፡
 አጥኝዎች ለሚሰሯቸው ጥናቶች በመነሻ ሀሳብነትና በመረጃ
ምንጭነት ያገለግላቸዋል፡፡
1.4. የጥናቱ ወሰን (SCOPE OF THE STUDY)
ይህ ጥናት ከማጥኛ ስፍራ፣ ከተጠኝዎችና ከጥናቱ ርእሰ ጉዳይ
አንጻር የራሱ ወሰን አለው፡፡
ከማጥኛ ስፍራ አንጻር በእቴጌ መነን የልጃገረዶች አዳሪ 2ኛ ደረጃ
ት/ቤት ላይ የተወሰነ ሲሆን ውጤቱ የሌላ ት/ቤቶችን ውጤት
ላይወክል ይችላል፡፡
ከተጠኚዎች አንጻር በት/ቤቱ በሚገኙ በ2014 የመጀመሪያው
መንፈቀ ዓመት የማለፊያ ነጥብ ያላመጡ ተማሪዎች ላይ ብቻ
የተገደበ ሲሆን ከዚህ ውጭ ያሉት ተማሪዎች በጥናቱ
አልተዳሰሱም፡፡
ከጥናቱ ርዕሰ ጉዳይ አንጻር በተማሪዎቹ ውጤት ላይ እንቅፋት
የሆኑ ጉዳዮች ላይ ብቻ ያተኮረ ጥናት ነው፡፡
1.5. የጥናቱ ውስንነት (LIMITATION OF THE STUDY)
ይህ ጥናት ከጽሑፍ መጠይቅ አሞላልና ከጊዜ እጥረት አንጻር
ውስንነት ነበረበት፡፡
የተወሰኑ ተማሪዎች የጽሑፍ መጠይቁን በሚገባ
ባለመሙላታቸው ከመረጃ ትንተና ውጭ ተደርገዋል፡፡
የጊዜ እጥረት በማጋጠሙ ምክንያት ቃለ መጠይቅን
መጠቀም አልተቻለም፡፡
ሆኖም ግን የቃለ መጠይቅ ጥያቄዎች በጽሑፍ
መጠይቁ ተካትተው ክፍተቱ ተሞልቷል፡፡
2. የአጠናን ዘዴ (RESEARCH METHOD)
2.1. የጥናቱ ንድፍ እና ዘዴ (DESIGN OF THE STUDY)
 ይህ ጥናት ከጥናቱ ንድፍ አንጻር መሰረታዊ የጥናት ንድፍን
(basic research design) በመከተል ተከናውኗል፡፡
 ይህም የሆነበት ምክንያት ያጋጠሙ ችግሮችን በመቃኘት
የመፍትሄ ሀሳብ ማቅረብ ላይ ያተኮረ ጥናት በመሆኑ ነው፡፡
 ከጥናት ዘዴ አንጻር ቅይጥ የጥናት ዘዴን (mixed research
method) ተከትሎ የተከናወነ ሲሆን ይህም የሆነበት
አይነታዊና መጠናዊ መረጃዎች (quantitative and
qualitative data) ስለተሰበሰቡ ነው፡፡
2.2. የናሙናዎች አመራረጥ (Sampling method)

 የማጥኛ ስፍራው የተመረጠው በአመቺ የንሞና ዘዴ (convenience


sampling) ሲሆን ይህም የተደረገው አጥኝዎቹ ከት/ቤቱ ችግር
ፈቺ አካላት የሚካተቱ በመሆናቸው ነው፡፡
 ተጠኚዎቹ ተማሪዎች የተመረጡት የተለያዩ መስፈርቶችን
መሰረት በማድረግ ነው፡፡
 በት/ቤቱ ከሚገኙ ተማሪዎች ውስጥ የማለፊያ ነጥብ
ማስመዝገብ ያልቻሉ ተማሪዎች በዓላማ ተኮር የንሞና ዘዴ
(purposive sampling) ተመርጠዋል፡፡
 ይህ የሆነበት ምክንያትም ከሁሉም ችግሮች የተማሪዎች
ውጤት ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ በመሆኑ ነው፡፡
የቀጠለ…
 የተማሪዎች የክፍል ደረጃ እና ምድብ (grade level and section)
በጠቅላይ የንሞና ዘዴ (comprehensive sampling method)
ተመርጠዋል፡፡
 ይህም የተደረገበት ምክንያት በሁሉም የክፍል ደረጃዎች የማለፊያ
ነጥብ ያላመጡ ተማሪዎች በመኖራቸው ነው፡፡
 በዚህም መሰረት በት/ቤቱ የሚገኙት ሁሉም የክፍል ደረጃዎች እና
ምድቦች በጥናቱ ተካትተዋል፡፡
 በአራቱም የክፍል ደረጃዎች የሚገኙት የማለፊያ ነጥብ ማምጣት
ያልቻሉ 38 ተማሪዎች በጠቅላይ የንሞና ዘዴ (comprehensive
sampling method) ተመርጠዋል፡፡
 ከመምህራን ውስጥ ደግሞ ቀላል የዕጣ ንሞናን በመጠቀም 11
መምህራን ተመርጠዋል፡፡
2.3. የመረጃ መሰብሰቢያ ዘዴ (DATA COLLECTING METHOD)

 በትልመ ጥናቱ (Proposal) ታቅደው የነበሩት የመረጃ


መሰብሰቢያ ዘዴዎች የጽሑፍ መጠይቅ እና ቃለ መጠይቅ ሲሆኑ
በጥናት ሂደቱ ባጋጠመው የጊዜ እጥረት የጽሑፍ መጠይቅ ብቻ
በመረጃ መሰብሰቢያነት አገልግሏል፡፡
 በዚህም መሰረት ለቃለ መጠይቅ ተዘጋጅተው የነበሩት
ጥያቄዎች በጽሑፍ መጠይቅ ተካትተው በተማሪዎችና
በመምህራን የተሞሉ ሁለት መጠይቆች በመረጃ
መሰብሰቢያነት አገልግለዋል፡፡
 ሁለቱም የጽሑፍ መጠይቆች ሁለት ክፍሎች ሲኖሯቸው
የመጀመሪያው ዝግ ጥያቄዎችን፣ ሁለተኛው ደግሞ ክፍት
ጥያቄዎችን ይዘዋል፡፡
2.4. የመረጃ መተንተኛ ዘዴ
 ከጽሑፍ መጠይቁ ዝግ ጥያቄዎች መጠናዊ መረጃዎች
(quantitative data)፣ ከክፍት ጥያቄዎች ደግሞ አይነታዊ
መረጃዎች (qualitative data) ተሰብስበዋል፡፡
 መጠናዊ መረጃዎቹ ገላጭ ስታቲስቲክስን (discripitve
statistics) በመጠቀም የተተነተኑ ሲሆን መቶኛን የሚያሳይ
ሰንጠረዥ በአጋዥነት አገልግሏል፡፡
 እንዲሁም ከክፍት ጥያቄዎች የተገኙት አይነታዊ መረጃዎች
ገለጻን በመጠቀም ተተንትነዋል፡፡
 በሁለቱም የመረጃ መተንተኛ ዘዴዎች የተተነተኑት
መረጃዎችም ገለጻና ትረካን በመጠቀም ተብራርተዋል፡፡
የቀጠለ…
የመረጃ ትንተናው የተከናወነው በሁለት ክፍሎች
ሲሆን በመጀመሪያው ክፍል ከተማሪዎች የተገኙ
መረጃዎች፣ እንዲሁም በሁለተኛው ክፍል
ከመምህራን የተገኙ መረጃዎች ተተንትነዋል፡፡
በተማሪዎቹ የጽሑፍ መጠይቅ ውስጥ 30 መጠይቆች
ሲኖሩ 23ቱ ዝግ፣ 7ቱ ደግሞ ክፍት ጥያቄዎች ናቸው፡፡
እነዚህ 30 መጠይቆችም ዝቅተኛ ውጤት
ለማምጣት እንቅፋት ሊሆኑ የሚችሉ አራት
ጉዳዮችን የተመለከቱ ናቸው፡፡
የቀጠለ…
አራቱ ጉዳዮችም፡-
-የትምህርት ቤቱን አሰራር፣ መመሪያና ደንብ የተመለከቱ፣
-መምህራንን የተመለከቱ፣
-ተማሪዎችን የተመለከቱ እና
-ወላጆችን የተመለከቱ ናቸው፡፡
በመምህራኑ የተሞላው የጽሑፍ መጠይቅ ደግሞ 21
መጠይቆች አሉት፡፡
ከ21ዱ መጠይቆች ውስጥ 19ኙ ዝግ ጥያቄዎች
ሲሆኑ ቀሪዎቹ 2 መጠይቆች ደግሞ ክፍት ናቸው፡፡
3. የጥናቱ ውጤት እና አስተያየት
ይህ ጥናት ቀደም ሲል በተገለጸው መንገድ ከተከናወነ በኋላ
ከጥናቱ የተገኘውን ውጤት መሰረት በማድረግ
መደምደሚያና አስተያየት ተሰጥቷል፡፡ የጥናቱ
መደምደሚያና አስተያየት ቀጥሎ ያሉት ናቸው፡፡
3.1. የጥናቱ ውጤት
በጥናቱ ውጤት መሰረት በአራቱ ጉዳዮች ላይ የሚከተሉት
ድምዳሜዎች ላይ ተደርሷል፡፡
3.1.1. የት/ቤቱን አሰራር በተመለከተ የተደረሰባቸው
ድምዳሜዎች
የቀጠለ…
 በትምህርት ቤቱ የሚተገበረው የፈተና ፕሮግራም
ለአብዛኛዎቹ ተማሪዎች ምቹ ሲሆን ከ35% በላይ ለሆኑት
ተማሪዎች የሚመች አይደለም፡፡
 የመኝታ ክፍሎች ነባራዊ ሁኔታ ለአብዛኛዎቹ ተማሪዎች
ለማጥናት አመቺ ሲሆን 40% ለሚሆኑት ተማሪዎች ግን
አመች እንዳልሆነ የተማሪዎቹ ምላሽ ያመለክታል፡፡
 የቤተ መጻሕፍቱ አጠቃላይ ነባራዊ ሁኔታና የመጻሕፍት
እጥረት በተማሪዎቹ ውጤት ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ እንዳለው
ከ30% በላይ የሚሆኑት ተማሪዎች ገልጸዋል፡፡
የቀጠለ…
3.1.2. መምህራንን በተመለከተ የተደረሰባቸው ድምዳሜዎች
 የመምህራኑ የትምህርት አቀራረብ ለአብዛኛዎቹ ተማሪዎች
ምቹ ቢሆንም 40% አካባቢ ለሚሆኑት ተማሪዎች ምቹ
እንዳልሆነ የተማሪዎቹ ምላሽ ያመለክታል፡፡
 አብዛኛዎቹ ተማሪዎች ለሚጠይቋቸው ጥያቄዎች
መምህሮቻቸው በምሳሌዎች የተደገፈ በቂ ማብራሪያ
እንደሚሰጣቸው ሲገልጹ ከ20% በላይ የሆኑት ተማሪዎች ግን
በዚህ ሀሳብ አይስማሙም፡፡
 መምህራን የተማሪዎችን የትምህርት አቀባበል ደረጃ መሰረት
ባደረገ መልኩ ትምህርቱን እንደማያቀርቡ ከ70% በላይ
የሚሆኑት ተማሪዎች ገልጸዋል፡፡
የቀጠለ…
 የመምህራኑ ፈተና አወጣጥ ከ60% በላይ ለሚሆኑት ተማሪዎች
አስቸጋሪ እንደሆነና ጥያቄዎቹም ለተማሪዎቹ የሚከብዱ እንደሆኑ
የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡
 ተማሪዎች የሚከብዷቸውን የትምህርት ይዘቶች በመምረጥ
የማጠናከሪያ ትምህርት አይሰጡም፡፡
 መምህራን የሚሰጡት የማጠናከሪያ ትምህርት በተማሪዎቹ ውጤት
ላይ አዎንታዊ ለውጥ እንዳላመጣ ከመምህራን የተገኙ መረጃዎች
ያመለክታሉ፡፡
 አንዳንድ መምህራን ከፈተና በፊት በቂ ክለሳ እንደማያደርጉ፣
ትምህርታዊ ያልሆኑ ምክሮችን እንደማይሰጡ፣ ተማሪዎቹ
ለሚጠየቋቸው ጥያቄዎች በቂ መልስና ማብራሪያ እንደማይሰጡና
የክፍልና የቤት ስራ ከሰጡ በኋላ እንደማይከታተሉ ከተማሪዎቹ
የተገኙት መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡
3.1.3. ተማሪዎችን በተመለከተ የተደረሱ ድምዳሜዎች

 በተማሪዎች መካከል እርስ በእርስ ከመረዳዳት ይልቅ አሉታዊ


ፉክክር እንደሚታይ ከ60% በላይ የሚሆኑት ተማሪዎች ገልጸዋል፡፡
 ቀድሞ በነበሩባቸው ትምህርት ቤቶች ጥሩ የትምህርት መሰረት
አለመኖራቸው ለተማሪዎች ውጤት ዝቅ ማለት አንዱ
ምክንያት እንደሆነ የተገኙት መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡
 ከተጠየቁት ተማሪዎች ውስጥ 25% የሚሆኑት በትምህርት ቤቱ
በመማራቸው ደስተኞች አለመሆናቸውን ገልጸዋል፡፡
 ከተጠየቁት ተማሪዎች ውስጥ ከ53% በላይ የሚሆኑት
ከወላጆቻቸው ጋር ተለይተው መማራቸው በውጤታቸው ላይ
አሉታዊ ተጽዕኖ እንዳሳደረባቸው ገልጸዋል፡፡
የቀጠለ…
 አብዛኛዎቹ ተማሪዎች በፕሮግራም የማጥናት ልምድ
እንደሌላቸው፣ በፈተና ወቅት እንደሚጨነቁ፣ የቋንቋ
ውስንነት ችግር እንዳለባቸው፣ በፈተና ሰአት
እንደሚቸኩሉና ለፈተና በሚገባ እንደማይዘጋጁ መረጃዎቹ
ያመለክታሉ፡፡
 ከመምህራን የተሰበሰቡት መረጃዎች እንደሚያመለክቱት
መምህራን የማጠናከሪያ ትምህርት ለመስጠት
ተማሪዎቻቸውን ሲጠሩ አብዛኛዎቹ ተማሪዎች አይገኙም፡፡

 ከመምህራን የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው


አብዛኛዎቹ ተማሪዎች የመምህራንን ምክር አይተገብሩም፡፡
የቀጠለ…
3.4.1. ወላጆችን በተመለከተ የተደረሱ ድምዳሜዎች
ከተማሪዎቹ የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው ከ78%
በላይ የሚሆኑት ወላጆቻቸው የልጆቻቸውን ውጤት
አይከታተሉም፡፡
አንዳንድ ተማሪዎች ከዘመድ ጋር ስለሚኖሩና
ዘመዶቻቸውም ስለሚያፈራሯቸው ውጤታቸው ዝቅ ሊል
እንደቻለ ከተማሪዎች የተገኙት መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡
3.2. አስተያየት
በጥናቱ የተደረሰባቸውን ድምዳሜዎች መሰረት በማድረግ ለሚመለከታቸው
አካላት የመፍትሄ ሀሳቦች በአጥኝዎቹ ተሰጥተዋል፤ የመፍትሄ ሀሳቦቹ ቀጥሎ
ያሉት ናቸው፡፡
ለት/ቤቱ አስተዳደር የተጠቆሙ የመፍትሄ ሀሳቦች
የወርኃዊና የአጠቃላይ ፈተና ፕሮግሮሞችን የተማሪዎችን
ፍላጎት ባማከለ መንገድ ቢደረግ ተማሪዎቹ ፈተናዎቹን በሚገባ
በመስራት ጥሩ ውጤት ማስመዝገብ ይችላሉ፡፡
የመኝታ ክፍል ስርዓቱ ለተማሪዎች የሚመችና ለማጥናት
የተመቻቸ ቢደረግ መልካም ነው፡፡
ቤተ መጻሕፍቱ ጠቃሚ መጻሕፍትን ቢያሟላና ለጥናትና የግልና
የቡድን ስራዎችን ለመስራች አመቺ ሆኖ ቢዘጋጅ መልካም ነው፡፡
የቀጠለ…
 ቤተ መጻሕፍቱ ባለሙያ ተሟልቶለት የ24 ሰአት አገልግሎት
እንዲሰጥ ቢደረግ የተማሪዎችን ውጤት በማሻሻል ረገድ በጎ
አስተዋጽዖ ይኖረዋል፡፡
 አጠቃላይ የትምህርት ቤቱ ምድረ ግቢ ለተማሪዎች ሳቢና
ማራኪ ቢደረግና ለተማሪዎች ለብቻቸው መዝናኛ ክበብ
ቢዘጋጅላቸው መልካም ነው፡፡
 የተማሪዎችን የየእለት እንቅስቃሴ በመከታተል፣ በመቅረብና
ችግሮቻቸውን በመረዳት ለችግሮቻቸው መፍትሄ ቢሰጡ
መልካም ነው፡፡
 ከቀለም ትምህርቱ ጎን ለጎን ስነ ልቦናዊ ምክር ቢሰጧቸው
ከጭንቀት በመላቀቅ በትምህርታቸው ውጤታማ መሆን
ይችላሉ፡፡
የቀጠለ…
 የተማሪዎችን ውጤትና ስነ ምግባር በተመለከተ ከወላጆች ጋር
ተደጋጋሚ ውይይት ቢደረግ ተማሪዎች የሚያጋጥሟቸውን
ችግሮች ተረድቶ መፍትሄ ለመስጠት ምቹ ሁኔታ ይፈጠራል፡፡
 ከመደበኛው የማስተማር ጎን ለጎን ተማሪዎችን ለማስጠናት
ያመቻቸው ዘንድ መምህራን በትምህርት ቤቱ አካባቢ
የሚኖሩበት ሁኔታ ቢመቻች መልካም ነው፡፡
ለመምህራን የተጠቆሙ የመፍትሄ ሀሳቦች
 የተማሪዎችን ፍላጎት በማጥናት ፍላጎታቸውን ያማከሉ
የትምህርት አቀራረብ ዘዴዎችን ተጠቅመው ትምህርቱን
ቢያቀርቡ ተማሪዎችን ውጤታማ ማድረግ ይቻላል፡፡
የቀጠለ…
 ሁሉም ተማሪዎች ለሚጠይቋቸው ጥያቄዎች በምሳሌዎች
የተደገፈ ማብራሪያ ቢሰጡ ሁሉንም ተማሪዎች ውጤታማ
ማድረግ ይቻላል፡፡
 ወርኃዊና ማጠቃለያ ፈተናዎችን ሲያዘጋጁ የሁሉንም
ተማሪዎች አቅም ከግምት ውስጥ ቢያስገቡ የፈተና ላይ
ጭንቀትንና የውጤት መቀነስን ማስወገድ ይቻላል፡፡
 ተማሪዎች የሚከብዷቸውን ይዘቶች ከየምዕራፉ በመምረጥ
የማጠናከሪያ ትምህርት ቢሰጡ የተማሪዎቹን ውጤት
ማሳደግ ይቻላል፡፡
 የተማሪዎች ውጤት ዝቅ ያለበትንና የሚሰጡት የማጠናከሪያ
ትምህርት በተማሪዎቹ ውጤት ላይ ለውጥ ማምጣት
ያልቻለበትን ምክንያት የተመለከቱ ጥናቶችን በማከናወን
መፍትሄ ቢሰጡ መልካም ነው፡፡
የቀጠለ…
 ለተማሪዎች የሚሰጧቸውን የክፍልና የቤት ስራዎች
ተማሪዎች በሚገባ መስራታቸውን በመከታተል ተገቢ ግብረ
መልሶችን ቢሰጡ፣ እንዲሁም ከፈተና በፊት ተገቢ ክለሳና
የመለማመጃ ጥያቄዎችን ቢሰጧቸው በፈተና ወቅት
የሚኖርን ጭንቀት ማስቀረትና ውጤታማ ማድረግ ይቻላል፡፡
ለተማሪዎች የተሰጡ አስተያየቶች
 እርስ በእርስ አላስፈላጊ ፉክክር ባያደርጉና በጥናት ወቅት
እርስ በእርሳቸው ቢረዳዱ አንዳቸው ከሌላቸው የተለያዩ
የጥናት ዘዴዎችንና እውቀትን በማግኘት ውጤታማ መሆን
ይችላሉ፡፡
የቀጠለ…
 ራሳቸውን ከት/ቤቱ ነባራዊ ሁኔታ ጋር በማለማመድና ዋና
ትኩረታቸውን ትምህርታቸው ላይ ብቻ በማድረግ ውጤታማ
ለመሆን ጥረት ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፡፡
 ፈተና ከመቃረቡ በፊት የጥናት ፕሮግራም በማዘጋጀት
ቢያጠኑ፣ ያልገባቸውን ከመምህሮቻቸው በመጠየቅ ቢረዱ፣
በፈተና ወቅት ሳይቸኩሉ ተረጋግተው እንዲሁም ከጭንቀት
በጸዳ መንገድ ፈተናዎችን ቢሰሩ አመርቂ ውጤት ማስመዝገብ
ይችላሉ፡፡
 በየጊዜው በመለማመድና ከመምህሮቻቸውና ከጓደኞቻቸው
እርዳታ በመጠየቅ የቋንቋ ችሎታቸውን ለማሳደግ ቢጥሩ በዚህ
ምክንያት ዝቅ ሊል የሚችለው ውጤታቸው መስተካከል
ይችላል፡፡
የቀጠለ…
 መምህራን በሚሰጧቸው የማጠናከሪያ ትምህርት ክፍለ ጊዜዎች
ባለመቅረትና የመምህሮቻቸውን ምክር በመስማት ክፍተቶቻቸውን
ለመሙላት ጥረት ቢያደርጉ ጥሩ ውጤት ማስመዝገብ ይችላሉ፡፡
ለወላጆች የተሰጡ አስተያየቶች
 ልጆቻቸው ያመጡትን ውጤት በየጊዜው በመከታተል ድጋፍና ክትትል
ቢያደርጉ ተማሪዎቹ ጥሩ ውጤት እንዲያመጡ እድል ይፈጠርላቸዋል፡፡
 በየጊዜው ልጆቻቸው ስላጋጠሟቸው ችግሮች በመጠየቅ
ለችግሮቻቸው መፍትሄ ለመስጠት ቢጥሩ መልካም ነው፡፡
የቀጠለ…
ልጆቻቸው ከፍርሀትና ጭንቀት ነጻ ሆነው
ትምህርታቸውን እንዲማሩና ሙሉ ትኩረታቸውን
በትምህርታቸው ላይ ብቻ እንዲያደርጉ ያላሰለሰ
ምክር ቢሰጡ በውጤታቸው ላይ አዎንታዊ ለውጥ
ይገኛል፡፡
የልጆቻቸውን አጠቃላይ እንቅስቃሴ በተመለከተ
ከመምህሮቻቸውና ከአስተዳደሮች በመጠየቅ
የሚታዩትን ችግሮች ለመፍታት ቢጥሩ መልካም
ነው፡፡
እናመሰግናለን!

You might also like