You are on page 1of 4

በመሊው ኢትዮጵያ ሀገር አቀፍ እና ክሌሌ አቀፍ ፈተናዎች እየተቃረቡ ነው። ታዱያ በዚህ ወቅት

ተማሪዎችን እጅግ የሚያስጨንቁ ጉዲዮች እንዳት አዴርገን ሇፈተናው እናጥና? ያጠናነውንስ ሊሇመርሳት ምን
ማዴረግ አሇብን የሚለት ጥያቄዎች ናቸው።
ከዋናው ጥናት በኋሊ ፈተናው ሲቀርብ የክሇሳ ዝግጅት ማዴረግ የተሇመዯ ነው። ነገር ግን ከየት ነው
የሚጀመረው? ቢቢሲ የትምህርት ባሇሙያዎችን፣ የዩኒቨርሲቲ መምህራንን፣ የሥነ ምግብ ተመራማሪዎች፣
ውጤታማ ተማሪዎችን እንዱሁም የሥነ አእምሮ ባሇሙያዎችን አነጋግሮ ይጠቅማለ ያሊቸውን 12 ነጥቦች
አዘጋጅቶሊችኋሌ።
በእነዚህ ምክሮች መሠረት የማስታወስ ችልታችሁንና የትኩረት አቅማችሁን ታዲብራሊችሁ።

1. ቁርስና ጠቃሚ ምግቦች


ሰውነታችን በአግባቡ ሥራውን እንዱሰራ ኃይሌ ያስፈሌገዋሌ፤ አንጎሊችን ዯግሞ ትኩረት እንዱኖረውና
የማስተዋሌ አቅማችን እንዱጨምር በቂ የሆነና ያሌተቆራረጠ የኃይሌ አቅርቦት ይፈሌጋሌ።
ጥናቶች እንዯሚያሳዩት ቁርሳቸውን ተመግበው ወዯፈተና የሚገቡ ተማሪዎች የተሻሇ ውጤት ያስመዘግባለ።
የተመጣጠነ ምግብ ተመግበው ሇፈተና የሚቀርቡት ዯግሞ የበሇጠ የማስታወስና የማስተዋሌ አቅም
ይኖራቸዋሌ።
ስሇዚህ ሁላም ቢሆን ፈተና ያሇባቸው ተማሪዎች እንዯ የገብስ ገንፎ፣ ዲቦ፣ ሩዝና ዴንች ያለ በካርቦሃይዴሬት
የበሇጸጉ ምግቦችን በቁርስ ሰዓት ተመግበው ቢወጡ ይመከራሌ።
እርጎ፣ እንቁሊሌ፣ አሳ፣ ጎመን፣ ቲማቲምና አቮካድ ዓይነት ምግቦችም እጅጉን ጠቃሚ ናቸው።

2. በጠዋት ወዯ ጥናት መግባት


ሁላም ቢሆን ነገሮችን አስቀዴሞ መጀመርን የመሰሇ ነገር የሇም። ሇፈተናም ቢሆን ጥናት በጠዋት ተነስቶ
መጀመር በፈተና ወቅት የተረጋጋ መንፈስ እንዱኖረን ይረዲሌ።
ጠዋት ሊይ ጭንቅሊታችን እረፍት አዴርጎ በአዱስ መንፈስ ሁለንም ነገር ስሇሚጀምር፤ በዚህ ሰዓት ማጥናት
ውጤታማ ያዯርጋሌ። በተሇይ ዯግሞ የክሇሳ ጥናቶችን ሇከሰዓት ማሸጋገር ተገቢ አይዯሇም።
ጠዋት ጥናት የምንጀምርበትና የምናበቃበት ሰዓት ከፈተናው በፊት ባለት ሁሇት ወይም ሦስት ሳምንታት
ውስጥ ተመሳሳይ ሇማዴረግ መሞከርም ውጤታማ ያዯርጋሌ።

3. ምን ሊይ ትኩረት ማዴረግ እንዲሇባችሁ ወስኑ


በመጀመሪያ ፈተናው የጽሁፍ ነው ወይስ የተግባር? ወይስ ቃሇመጠይቅ ነው የሚሇውን መሇየት ወሳኝ ነው።
ሁለም ዓይነት ፈተናዎች የራሳቸው የሆነ የተሇያየ አይነት አቀራረብ አሊቸው። በምሳላ አስዯግፎ ማብራሪያ
መስጠት የሚጠይቅ ዓይነት ፈተና ከሆነ ከዚህ በፊት የተሠሩ ፈተናዎችን እያመሳከሩ ጥቂት ቦታዎች ሊይ
በትኩረት መዘጋጀት።
ምናሌባት ፈተናው ምርጫ አሌያም አጭር መሌስ የሚፈሌግ ዓይነት ከሆነ ቀሇሌ ያሇና አጠቃሊይ መረጃዎችን
ሇመያዝ መሞከር።

4. እቅዴ ማዘጋጀት
ምናሌባት ነገሮችን ቦታ ቦታ ሇማስያዝና እቅዴ ሇማውጣት የምናጠፋው ጊዜ የባከነ መስል ሉሰማን ይችሊሌ።
ነገር ግን እውነታው በተቃራኒው ነው። ምክንያቱም ምን ማጥናት እንዲሇባችሁና መቼ ማጥናት እንዲሇባችሁ
እቅዲችሁ ይነግራችኋሌ።
ከዚህ በተጨማሪም ምን ያክሌ እንዯተጓዛችሁ ሇመመዝገብና ሇመከታተሌ ይረዲሌ።
የትኞቹን ማስታወሻ ዯብተሮች መቼ መመሌከት እንዲሇባችሁ፣ የትኞቹን መጻህፍት ሇተጨማሪ ማብራሪያ
እንዯምትጠቀሙ እንዱሁም የፈተና ጥያቄዎችን መቼ መሇማመዴ እንዲሇባችሁ በእቅዴ ውስጥ ማስገባት
ውጤታማ ያዯርጋሌ።
እዚህ ጋር መርሳት የላሇብን ሇእረፍትና አካሊዊ እንቅስቃሴም ቦታ መስጠት እንዲሇብን ነው።

5. ከፋፍል ማጥናት
የክሇሳ ጥናትን ከፋፍል ማካሄዴን የመሰሇ ነገር የሇም። አንዴ የትምህርት ዓይነት ሊይ 10 ሰዓት ሙለ
ከማሳሇፍ በየቀኑ አንዴ ሰዓት በማጥናት በ10 ቀን መጨረስ ይበሌጥ ውጤታማ ያዯርጋሌ።
ያጠናነውን ነገር ሇማስታወስና በቀሊለ ሇመሸምዯዴ ጭንቅሊታችን ጊዜ ይፈሌጋሌ። ከፋፍል ማጥናት ዯግሞ
ሇዚህ ፍቱን መዴሃኒት ነው። ከፋፍል ማጥናት እጅግ ውጤታማው መንገዴ እንዯሆነም በመሊው ዓሇም
የተሰሩ የተሇያዩ ጥናቶች ያሇመክታለ።

6. ራሳችሁን ቶል ቶል ፈትኑ
የሥነ አዕምሮ ጥናት ባሇሙያዎች እንዯሚለት የማስታወስ ችልታን ሇማዲበርና በራስ መተማመናችንን
ሇመጨመር ራስን መፈተን ውጤታማ ያዯርጋሌ።
ከዚህ በተጨማሪ እየተዘጋጀንበት ያሇነውን ጉዲይ በዯንብ እንዴናውቀው ከማዴረጉ በተጨማሪ የረሳናቸው
አሌያም የዘሇሌናቸው ርዕሶችን ሇመሇየት ይረዲናሌ።
7. መምህር መሆን
ከባደን የክሇሳና ራሳችሁን የመፈተን ሥራውን ካከናወናችሁ በኋሊ ጓዯኞቻችሁን ሰብሰብ አዴርጋችሁ
በጭንቅሊታችሁ የሚመጣውን ነገር በሙለ ንገሯቸው። ራሳችሁን በመምህር ቦታ አዴርጋችሁ
እውቀታችሁን ሇማካፈሌ ሞክሩ።
ምን ያህሌ እንዯምታስታውሱ ሇማወቅ ከመርዲቱ በተጨማሪ ጓዯኞቻችሁንም ትጠቅሟቸዋሊችሁ።

8. ከተንቀሳቃሽ ስሌካችሁ ራቅ በለ
ስሌኮች በጣም ብዙ ጥቅም አሊቸው። ነገር ግን በጥናት ወቅት ከጥቅማቸው ይሌቅ ጉዲታቸው ነው
የሚያመዝነው። በተሇይ ዯግሞ ማህበራዊ ሚዱያዎችን የምትጠቀሙ ከሆነ።
ብዙ ጥናቶች እንዲረጋገጡት ብዙ ጊዜያቸውን ስሌካቸው ሊይ የሚያሳሌፉ ተማሪዎች የትምህርት
ውጤታቸው ሁላም ቢሆን ዝቅ ያሇ ነው።

9. ሙዚቃ መቀነስና በጸጥታ ማንበብ


በጸጥታ ውስጥ ሆነው ጥናታቸውን የሚያከናወኑ ተማሪዎች ሙዚቃ እየሰሙ ከሚያጠኑት ጋር ሲወዲዯሩ
በእጅጉ የተሻሇ የማስታወስና የትኩረት አቅም እንዲሇቸው ማረጋገጥ ተችሎሌ።

10. ቋሚ እረፍትና አካሊዊ እንቅስቃሴ


ውጤታማ የክሇሳ ጥናት ማሇት እረፍት አሌባ ጥናት ማሇት አይዯሇም። በጥናታችን መሀሌ መሀሌ ሊይ ጥሩ
አየር ሇማግኘትና ሰውነታችንን ሇማፍታታት ወጣ ብል እንቅስቃሴ ማዴረግ የማስታወስ ችልታችንን በዯንብ
ከፍ ያዯርገዋሌ። ከዚህ በተጨማሪ ሰውነታችን እና ጭንቅሊታችን በእጅጉ የተሳሰሩ በመሆናቸው እንቅስቃሴ
ስናዯርግ የዯም ዝውውራችን ይስተካከሊሌ፤ ይህ ዯግሞ በቂ ኦክስጅን ወዯ ጭንቅሊታችን እንዱሄዴ ይረዲሌ።
አካሊዊ እንቅስቃሴ ማዴረግ ተዘርዝሮ የማያሌቅ ጥቅሞች ያለት ሲሆን ጭንቀትን መከሊከሌና በራስ
መተማመንን መጨመር ከነዚህ መካከሌ ይጠቀሳለ።

11. እንቅሌፍ
ከፈተና በፊት ያሇችውን ምሽት ጥሩ እንቅሌፍ አግኝቶ ማሳሇፍ ተገቢ እንዯሆነ ብዙዎች ይስማማለ። ነገር ግን
ጥሩ እንቅሌፍ ፈተናው ሲቃረብ ብቻ ሳይሆን ከሳምንታት በፊት ገና ዋናው ጥናት ሲዯረግና ክሇሳ
በሚዯረግበት ወቅትም እጅግ ወሳኝ ነው።
በጠዋት ተነስቶ ውጤታማ የክሇሳ ጥናት ካዯረጉ በኋሊ በጊዜ ተኝቶ ጥሩ እንቅሌፍ ማግኘት ሰውነታችንና
ጭንቅሊታችን በዯንብ ተግባብተው እንዱሰሩ ይረዲቸዋሌ። ላሉቱን በሙለ ሇማጥናት ሙከራ አታዴርጉ
ይሊለ የዘርፉ ባሇሙያዎች። ምክንያቱም ራሳችን ሊይ ጫና እያሳዯርን ስሇሆነ።

12. መረጋጋትና በጎ በጎውን ማሰብ


እስካሁን የተዘረዘሩትን ነገሮች ሁለ ተግባራዊ ካዯረጋችሁ ምንም የሚያሳስባችሁ ነገር ሉኖር አይገባም። ዘና
ብሊችሁ ወዯ ፈተና መግባት ብቻ ነው የሚቀራችሁ። ምናሌባት ጥሩ ያሌሆነ አጋጣሚ ቢገጥማችሁ እንኳን
እሱን ረስታችሁ ሇቀጣዩ በጥሩ መንፈስ ሇመዘጋጀት ሞክሩ።
በመጨረሻም በእያንዲንደ ጥሩ የፈተና ጊዜ ሇራሳችሁ ሽሌማት መስጠት አትርሱ።
Source: - BBC Amharic

You might also like