You are on page 1of 20

21 ውጤታማና ሳይንሳዊ የአጠናን

ዘዴዎች
አዘጋጅ፦ መምህር አንዋር አወል ሞ.
2014.
•1. የጥናት ዕቅድን መኖር፦ እጃችን የገባ መፅሐፍ
ከማንሳታችን በፊት እናቅድ። ለየትኛው ምን
ያስፈልጋል ግልፅ የሆነ ነገር እንዲኖረንም
ያስችላልና። ከፈተናው በፊት ምን ያህል ቀናት ፣
በገፅ እንደምናጠናው በዝርዝር ማወቅ። ዝርዝር
ዕቅድ ግልፅ ያለው ነገር እንድናውቅ ከማድረጉም
ባሻገር በመሸበርና በመጨነቅ ሊጠፋ ይችል
የነበረውን ጊዜና ጉልበታችንን በሚገባ
2. ተገቢ ማጥኛ ቦታን ማመቻቸት– በዙሪያችን ምቹ ሁኔታን
ስንፈጥር ውጤታም ጥናትን እንካሂዳለን። በቂ ብርሃን ፣ ፍሬሽ
አየር እና ፀጥታ። ከዚህ በተጨማሪ አስተጓጓይ (distractions)
ነገሮችን የሌሉበት አከባቢን መምረጥ ተገቢ ይሆናል።
በምናጠናበት ጊዜ ስልክን off አሊያም flight mode ላይ
ማድረግ።
መቀመጫም ቢሆን እንደየባህሪያችን ልናስብበት ይገባል።
አንዳንዶች ወንበር ላይ ተቀምጠው የሚጠናውን ጠረጴዛ ላይ
ሲያስቀምጡ ፣ ሌሎች ተጋድመው ይገባቸዋል። አንዳንዶቹም
የሚጠናውን ይዘው ዎክ እያደረጉ። ስለሆነም የማጥኛ ቦታና
3. መደበኛ ዕረፍቶችን መውሰድ– የሰው ልጅ አዕምሮ በሚገባ
የሚሰራው ተገቢውን ዕረፍት በየጊዜው መውሰድ ነው። አጥኚዎች
እንዳረጋገጡት በአጫጭር ጊዜዎች ጥናት ማድረግና ዕረፍቶችን
መውሰድ ረዥም ሰዓት ቁጭ ብሎ ያለዕረፍት ከማጥናት ይልቅ
ውጤታማ ነው። ከ2 ሰዓት በላይ ተቀምጦ ማንበብ ፈፅሞ
አይመከርም። አዕምሮአችን ዕንቅልፍ ዕንቅልፍ ሲለው ወይም ንቃት
ባጣንበት ሰዐት ራሳችንን አስገድደን ብናጠና ውጤቱ ድካም ብቻ
ነው። ስለሆነም በየጊዜው ማረፍ ፣ እርምጃ ማድረግ . (walk),
ዓይንን መጨፈን አሊያም ሩቅን በማማተር ዓይንን እና አዕምሮን
ማሳረፍ ይገባል። ዕረፍት ሲባል ታዲያ አዕምሮንም ወደዚያው
ማሰማራት መሆኑን ሳንዘነጋ።
4. አመጋገብን ማስተካከል– good food – good mood
ይላሉ። ስለሆነም ጤናማ ያልሆኑ ምግቦችን ማስወገድ
ይገባል። ፍሬሽና የሚመከሩ ምግቦችን ማዘውተር
ተፈጥሯዊ ካልሆነ ዕንቅልፎነት ፣ ድካምና ሕመምን
ይጠብቀናል። ውሃን አብዝቶ መውሰድም ከድርቀት
(dehydration) ይጠብቀናል። ጥራጥሬ አትክልትና
የወተት ተዋፅዖዎችን መጠቀም የማስታወስ (memory)
ክሕሎታችንን ያሳድግልናል።
5. የመኝታ መደበኛና ቁርጥ ያለ ሰዓትን መያዝ (A
PROPER SLEEP ROUTINE) – ስንተኛ አካላችንም ሆነ
አዕምሮአችን ሙሉ በሙሉ በማረፍ ብርታትና
ጥንካሬያቸውን መልሰው በማግኘት ለነገ ይዘገጃጃሉ።
በቀን የ8 ሰዓት ምቹ ዕንቅልፍ ይመከራል። ብቻ
እንደየሙድና ሰዓታችሁ አጥንታችሁ መደበኛ ሰዓትን
መያዝ ግን ለጤነኛ ጥናት ብቻ ሳይሆን ለጤነኛ
ሕይወትም ወሳኝ ነው። ሚሞሪን ያሻሽላል።
6. አልፎ አልፎ በቡድን ማጥናት– አንዳንዴ ይኼው ባህሪ
የተሻለ ዕውቀት ፣ ሐሳብና መረጃ እንድንገበያይ ይረዳናል።
በመጠያየቅ ጥርጣሬን እንድናስወግድ ከማድረጉም በላይ
ለማስታወስም ፍቱን አካሄድ ነው።
7. አጠር ቅልብጭ ያለ ማስታወሻ ስለመያዝ– ለማስታወስ
ከመጥቀሙም በላይ ማስታወሻዎች ይዘን በመንቀሳቀስ
በየትኛውም ቦታና ሰዓት ለመከለስ ይረዳናል።
8. ያለፉት ዓመታት የፈተና ጥያቄዎችን
ስለመሥራት– ያቀድነው አሊያም
መጠናት ያለብንን አጥንተን ስናበቃ
ያለፉት ዓመት ፈተናዎች መሥራት የግድ
ይላል። ይሄም የፈተናው አዘገጃጀት
እንድናይ ከማስቻሉም በላይ ምን ያክል
ዝግጅት እንዳደርግንም ለማየት
9. ክለሳ ማድረግ– እንደየ አጠናናችን ሊለያይ ቢችልም
ከፈተናው ሣምንት በፊትም ሆነ ሦስት ቀናት በፊት አንድን
የትምህርት ዓይነት ክለሳ ማድረግ ግና አይቀሬ ጉዳይ ነው።
ያልተነካ ርዕሰ ጉዳይ ገና ማንበብህ ከሆነ ሦስቱም R የሚባሉት
ማወቅ የግድ ይላል። በ24 ሰዓት ውስጥ Recap (ጠቅለል
አድርጎ ማየት) , Review (ክለሳ) እና Reinforce (ማጠናከር)።
ሳይንስ እንዲያ ማድረግ ያልቻሉ ሰዎች አዲስ ካገኙት መረጃ
ውስጥ 80% ያህሉን ያጡታል ይላል።
10. ራሱ የፈተናውን ቀን ማሳመር – በቂ ዕንቅልፍ ወስዶ
ለፈተናው መቅረብ ፤ ያንን ቀን በጧቱ መንቃት ፣ ቀለል
ያለ ምግብ መውሰድ ፣ አስፈላጊውን ማቴርያል መያዝ ፣
ቀደም ብሎ በመገኘት የመጨረሻዋ ሰዓት ውክቢያን
ማስወገድ (last-minute races). ሰዓት አክባሪ ፣ አዎንታና
በራሱ ከሚተማመን ሰው ጋር ወደ መፈተኛን ማምራት።
11. ቻርትና ዳያግራም (ስዕላዊ ነገሮችን) ስለመጠቀም
በክለሳ ወቅት በጣም ጠቃሚ ነገሮቹ እነሱ ናቸው።
12. መልሶችንህ ለሌሎች አብራራ
ወላጆችም ሆኑ ታናናሾች በፈተና ሰሞን አብሻቂ
ከሚሆኑብን ይልቅ እንደ ዕድል (advantage)
መጠቀምን መልመድ። መጀመርያ በማብራራት
ጥያቄዎቻቸውን አስተናግድ። ምናልባትም
የማታወቀው ፣ አሊያም ችላ ስላልከው ነገር
ሊያነሱብህ ይችላሉ።
13.አትሸምድዱ
ሌቱን ሙሉ ስትሸመድዱ ብታድሩ የባሰ ጭንቀት ውስጥ
ይከታችሁ እንደሆነ እንጂ ጠብታ ፋይዳ የለውም።
ስለሆነም ነገሮችን በየፈርጁ አያይዞ ማጥናት (ለምሳሌ
cause & Effect) አሊያም ተመሳሳይ ዘዴ መጠቀም።
ፈታኞቹም ተጨናቂ ሰው ናቸውና 80% የሚሆነው ጥያቄ
የሚመጣው ዋና ዋና ከሚባሉት ውስጥ ነው። ዓላማውም
መጣልን ሳይሆን መመዘንን። (ያውራ ዶሮው ጉዳይ)
ከመሸምደድ ይልቅ ክለሳላይ በርቱ።
14. ድሕረ ፈተናን ያለመገምገም 
ፈተና ካለቀ በኋላ በስሕተቶችህ መናደድ
ለቀጣዩ ያለህን ተነሳሽነት ከመዝጋቱም
በላይ ‘ቀድሞ ነበር እንጂ...’ ዓይነት
ሊያስተርትብህ ይችላልና ድሕረ ፈተና
ቼክ ከማድረግ ታቀብ። ፋይዳውም
ዝቅተኛ ነውና።
15. ጮክ ብሎ ለራስ ስለማጫወት
ቦታውና ጊዜው ከፈቀደ ለራስ
መተረክ በሚመስል መልኩ
እያጫወቱ ማጥናት ይመከራል።
በተለይም ዋና ዋና ነጥቦችን።
16. ተመሳሳይ መረጃን በተለያየ መንገድ ስለመማር
Willis, J. የተባለ የስነአዕምሮ ባለሙያ በ2008 ባወጣው ጥናቱ
መንገዶቹ ሲለያዩት የሚያነቃቁት የአዕምሮ ክፍልም ይለያያል
ይላል። ብዙ የአዕምሮ ክፍላችን በነካካንበት ቁጥር ደግሞ አንድ
ነገር የግዱን ይገባናል። ስለሆነም ስለ አንድ ርዕሰ ጉዳይ
Read the class notes
Read the textbook
Watch a  video
Teach someone what you’ve learned
17. በአንዴ አንድ ሳብጄክት ከማጥናት ይልቅ
በዛ ማድረጉ ይመከራል
ትኩረትህ ለመሰብሰብ ይረዳ ዘንድ እዚህም
እዚያም ማጥናት የተሻለ ውጤታማ ነው ይላል
(Rohrer, D. 2012).
ምክንያቱም አንድን ሳብጄክት ይዞ መዋል
የመሰላቸትም የማደናገርም (confuse
የማድረግ) ዕድሉም ይሰፋልና ነው።
18. ጭንቀቶቻችሁን ፃፉ፦
ፈተና ላይ እሰራ ይሆን?
ዋና ዋናውን concept አሊያም equation ብረሳስ?
ፈተናው ከጠበቅኩት በላይ ከባድ ቢሆንስ?
የUniversity of Chicago አጥኚዎች ስሜቶቻቸውን
ካልፃፉት ይልቅ የፃፉቱ የትሻለ ውጤት አግኝቷል።
በተለይም ደግሞ ጥሎባቸው ዘወትር ተጨናቂ በሆኑት ላይ
መንገዱ ሰርቷል። አንዴ ካወቋቸው በስሜቶቹ ተጎትተው
እንዳይወሰዱ አሊያም መልስ እንዲያዘጋጁ ይረዳቸዋል
ይላል Psychologist Kitty Klein።
19. እያጠናችሁ ያላችሁት ከዚህ ቀደም ከምታውቁት
ጋራ ማቆራኘት.
Henry Roediger III and Mark A. “Make It Stick:
The Science of Successful Learning” በተባለው ዝነኛ
መፅሐፋቸው በጣም በፍጥነት አንድን ነገር ለመያዝና
ለመረዳት ፍቱን መንገድ ነው ብለውታል። ለምሳሌ
የኤሌክትሪክ ውስጥ ቮልቴጅ ስለመፍሰስ ከውሃ መፍሰስ
ጋራ አገናኝቶ መገንዘብ። አሊያም wbc ጠላትን
እንደሚመክት ወታደር አድርጎ የማሰብ ነገር።
20. ጥናትህን በሚገባ ስትጨርስ ራስህን ስለመሸለም
ሽልማቱ ቀለል ያለና ወጭ የማይጠይቅ ሊሆን ይችላል፦
• ዎክ ማድረግ
• ቀለል ያለ ምግብ ስለመብላት
• Listening to your favorite music
 Stretching
 Playing a musical instrument
 Taking a shower
21. ከሂደቱ ጋራ በፍቅር መውደቅ
ግሬድ ስለመስቀል ፣ ስለመሸለም አድጎ የሆነ ነገር ስለመሆን ሳይሆን እጅ
ላይ ላይ ያለችዋን ጡብ በትክክል ስለማስቀመጥ ማሰብ።
.
Carol Dweck’s እንደሚያመላክተው፦
ጥረት ላይ እንጂ ውጤት ላይ አናተኩር
ፍቅራችን ከሂደት ጋር እንጂ ከስኬት ጋር አይሁን
‘ከባባድ’ የሚባሉቱ ሳብጄክቶች ሳይቀሩ በርትተው ከሰሩባቸውና ጊዜ
ከሰጧቸው ጥሩ ሊሰሯቸው እንደሚችሉ ያውቃሉ።
ስኬት (success)ን የሚለኩት ራሳቸውን አዲስ ነገር ወደ መማር
በመገፋፋት እንጂ straight A’s በማግኘት እንዳልሆነ አውቀው በጥረት
ግን straight A’sም ቢሆን እንደማይቀር ያውቁታል።

You might also like