You are on page 1of 49

እስልምና እና ሳይንስ

ዝግጅት፡ አደም ጉዬ

ስልክ ቁጥር፡ 0911312866


ማውጫ

ማውጫ .................................................................................................................................. 1
መቅድም ................................................................................................................................. 3
ምእራፍ አንድ.......................................................................................................................... 5
1.እስላማዊ የአምልኮ ተግባራት፤ድንጋጌዎችና ክልከላዎች በሳይንስ መነጽር ...................................... 5
1.1 ሰላት(ስግደት) እና ሳይንስ ............................................................................................................. 5
1.1.1 ሰላት ጭንቀትን በማስወገድ አእምሮን ዘና እንደሚያደርግ በሳይንሳዊ ግኝት መረጋገጡ 5
1.1.2 በግንባር መሬት መንካት (ሱጁድ) የሚያከትለው አስገራሚ ሳይንሳዊ ጠቀሜታው............ 6
1.1.3 ሰላት የደም ግፊት ችግርን ይቀርፋል................................................................................... 8
1.2 እስላማዊ ፆምና ሳይንስ ................................................................................................................. 9
1.2.1 ፆምና ሳይንሳዊ ጠቀሜታው ................................................................................................. 9
1.2.2 የአያመል ቢድ ፆም እና ሳይንስ.......................................................................................... 12
1.3 ኢስላማዊ የእንስሳ አስተራረድ ዘዴ በሳይንስ ሲቃኝ .................................................................. 13
1.4 በተፋታች እና ባሏ በሞተባት ሴት ............................................................................................. 16
1.5 ፂምን ማሰደግ/ማስረዘም በሳይንስ እይታ ................................................................................. 18
1.6 የአሳማ ስጋና ሳይንሳዊ እይታው ................................................................................................ 19
ምእራፍ ሁለት....................................................................................................................... 21
ቅዱስ ቁርኣንና ሳይንስ ............................................................................................................ 21
2.1. ስነ-ፅንስ እና ስነ-አካል ................................................................................................................. 21
2.1.1 የፅንስ ፆታ ........................................................................................................................... 21
2.1.2 የሰው ልጅ ከጥቂት የዘር ፈሳሽ ጠብታ ስለመፈጠሩ ......................................................... 22
2.1.3 የሰው ልጅ አንጎል በቁርኣንና በሳይንስ ............................................................................... 23
2.2 እንስሳት ....................................................................................................................................... 24
2.2.1 ንብ በቁርኣንና በሳይንስ ....................................................................................................... 24
2.2.2 ሸረሪት በቁርኣንና በሳይንስ.................................................................................................. 27
2.2.3 ጉንዳን በቁርኣንና በሳይንስ .................................................................................................. 29
2.2.4 የከብቶች ወተት አመራረት በቁርኣንና በሳይንስ ................................................................. 31
2.3 ስነ -ምድር ................................................................................................................................... 32
2.3.1 የዓለምችን ዝቅተኛ ስፍራ ................................................................................................... 32

1
2.3.2 ብረት(Iron) በቁርኣንና በሳይነስ .......................................................................................... 33
2.4 ውቅያኖግራፊ (የውሃ አካላት ጥናት) ......................................................................................... 34
2.4.1 ሁለት ባህሮች መካከል ያለው ገርዶ................................................................................... 34
2.4.2 ጨለማና መእበል በጥልቅ ውቅያኖስ/ባህር ውስጥ............................................................. 36
2.5 ስነ- ፈለክና ቁርኣን ...................................................................................................................... 37
2.5.1 የፀሐይ መሽከርከር .............................................................................................................. 37
2.5.2 የፀሐይ መጥፋት ................................................................................................................. 38
2.6 ከብናኝ (አቶም) በታች ቁስ አካል ስለመኖሩ በቁርኣንና ሳይንስ ................................................. 38
2.7 የአፅናፉ አለም (Universe) አመጣጥና ህይወት......................................................................... 39
ምእራፍ ሶስት ........................................................................................................................ 41
የነቢዩ(ሰ፡ዐ፡ወ) ንግግሮች እና ተግባራት በሳይንስ እይታ ............................................................... 41
3.1 የጀርባ አጥንት (የጅራት ጎመድ) ................................................................................................ 41
3.2 ዝምብ የሚጠጣ ነገር ውስጥ ቢገባ ............................................................................................. 42
3.3 አልፎ አልፎ በባዶ እግር መሄድ ................................................................................................ 43
3.4 የነቢዩ (ሰ፡ዐ፡ወ) ወረርሺኝ መከላከያ መንገድ ............................................................................. 43
3.5 ወተት ከተጠጣ በኃላ አፍን በውሃ መጉመጥመጥ .................................................................... 45
ዋቢ መጽሐፍት ..................................................................................................................... 46

2
መቅድም
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩህሩህ በጣም አዛኘ በሆነው

ምስጋና የተባለ በአጠቃላይ ለዓለማቱ ጌታ ለአላህ ይገባው። የአላህ እዝነት፣በረከቱ፣እንዲሁም


ሰላሙ እርሱ ለዓለም እዝነት አድርጎ በላካቸውና የነብያት መደምድሚያ በሆኑት በነቢያችን
ሙሐመድ (ሰ፣ዐ፣ወ) በንፁሓን ቤተሰቦቻቸው፣ በባልደረቦቻቸው እና የእነርሱን መንገድ እስከ
ዕለተ ትንሳኤ በተከተሉት ለይ ሁሉ ይስፈን።

አምላካችን አላህ ሰዎች በእርሱ እንዲያምኑ ዘንድ የተለያዩ መልክተኞችን በታዓምራቱ


አስድግፎ ልኳል። ነቢዩላህ ኢብራሂም(ዐ፡ሰ) በአላህ ታዓምር ከሚነድ ፍም እሳት ሲድኑ፣ነቢዩ
ሙሳ (ዐ፣ሰ) ደግሞ በአላህ ታግዘው በአንዲት ብትራቸው ተዋቂ ደጋሚዎችን ለአላህ ወድቀው
እንዲሰግዱ ከማድረጋቸውም ባሻግር አምባገነኑን፤አምላክ ነኝባዩን፤ጨካኙንና አሳዳጁን የግብፁን
ፈርኦን ማንበረከክ ችለዋል። በተጨማሪ ኢሳ (ኢየሱስ) (ዐ፣ሰ) ሙታንን ከሞት እንዲያስነሱ እና
የማይድኑ በሽታዎችን በመዳበስ ብቻ እንዲፈውሱ በታላቅ ታዓምር ከአላህ ዘንድ ተልኳል፡፡
ነቢዩላህ ሳሊህን (ዐ፡ሰ) አላህ ህዝቦቸን ያሳምንበት ዘንድ ግመል ድንጋይን ሰብራ እንድትወጣ
አደረገለት። አላህ ሰዎች ቅኑን መንገድ እንዲከተሉ ዘንድ ነቢያችን ሙሐመድን (ሰ፡ዐ፡ወ)
በርካታ ታዓምራት ላካቸው፡፡ ከነዚህም መካከል የጨረቃ መሰንጠቅ፣ውሃ ከጣታቸው መሃል
መፍሰስና ሌሎችም የተረጋገጡ በርካታ ታዓምራት አሉ።

እነዚህ ታዓምራት ለተመለከቱት ትውልዶች በቂ የሆነ ማረጋገጫ ናቸው። ከነቢዩ (ሰ፣ዐ፣ወ)


በፊት የተላኩት መልእክተኞች መልእክታቸው ግዜያዊ ስለነበርና የተላኩትም ለህዝቦቻቸው ብቻ
ስለነበር ግዜያዊ ታዓምራት በቂ ናቸው። ሆኖም ግን የነበዩ ሙሐመድ (ሰ፣ዐ፣ወ) መልእክት
በዘመኑ ለነበሩት ህዝቦች ብቻ የታሰበ አልነበረም፡፡ ነበዩ ሙሐመድ (ሰ፡ዐ፡ወ) ይዘው የመጡት
መልእክት ለመላው የሰው ዘር ሲሆን እስከ ዕለተ ትንሳኤ ድረስ የሚቆይ ነው፡፡ አላህ በ21ኛው
የቁርኣን ምእራፍ ውስጥ ለዓለማት እዝነት አድርገን እንጂ አላክንህም በማለት ነቢዩ ሙሐመድ
(ሰ፡ዐ፡ወ) እስከ ዕለተ ትንሳኤ ድረስ ላሉ ለዓለም ህዝብ ሁሉ መላካቸውን ይነግረናል።
በተጨማሪም እያንዱ ከኔ በፊት ያለው ነቢይ ለራሱ ህዝብ ብቻ የተላከ ሲሆን እኔ ግን
የተላኩት ለዓለም ህዝብ ነው በማለት ነቢዩ (ሰ፡ዐ፡ወ) ተናግረዋል። ስለዚህ ነቢዩ
ሙሐመድ(ሰ፡ዐ፡ወ) ከፈጣሪ የተላኩ እውነተኛ ነቢይና መልእክተኛ መሆናቸው እስኪረጋገጥ
ድረስ የሳቸው (ሰ፡ዐ፡ወ) መልእክት እስከ ዕለተ ትንሳዔ ድረስ የጊዜ ፈተናን በሚቋቋም መልኩ
እንዲሁም በሁሉም ቦታና በሁሉም ሰው አዕምሮ ይገባ ዘንድ በታላቅ ታዓምር መደገፍ
ነበረበት፡፡

ከነቢዩ(ሰ፡ዐ፡ወ) በፊት የነበሩት መልእክተኞች ሲሞቱ የተሰጣቸው ታዓምርም ወዲያው


ይቆማል፡፡ ነገር ግን የነቢዩ (ሰ፡ዐ፡ወ) ታዓምር በሳቸው ሞት አላበቃም፡፡ ይልቁንም እስከ ዕለተ
ትንሳኤ ድረስ በሰው አዕምሮ እየተዳሰሰ ይኖራል፡፡ በየጊዜው ከሚወጡ ሳይንሳዊ ግኝቶችና
የምርምር ውጤቶች መካከል የቅዱስ ቁርኣንን ታዓምር ወይም የነቢዩን ታዓምር የሚያሳዩ
እልፍ አዕላፍ ናቸው፡፡

3
የእስልምና ነገር የጎን ውጋት፤የልብ ፍልጠት የሆነባቸው ሰዎች እስልምናን በተለይም
የእስልምናን የአምልኮ ተግባራት፤ድንጋጌዎች፤ክልከላዎችንና ሌሎችንም ውሃ በማይቋጥር
ስሁት ሙግታቸው ሊያጠለሹ ይሞክራሉ፡፡እውነታው ግን በርካታ ሳይንሳዊ ግኝቶችና
ምርምሮች ከእስልምና የአምልኮ ተግባራት፤ድንጋጌዎች፤ክልከላዎች ጋር ይስማማሉ እንዲሁም
ያበረታታሉ፡፡

ስለዚህ በእስልምና ዙሪያ ብዥታ ያለበት ይህን መጽሐፍ በማንበብ እውነታው ለይ ለመድረስ
የሚያስችለውን የጊዜ ርቀት በጣም ሊያጠብ የችላል፡፡ ሳይደርቅ በእርጥቡ፤ ሳይቃጠል በቅጠል
እንዲሉ ሞት ሳይቀድመን እውነታውን በገለልተኝነት በመረዳት ትክክለኛውን መንገድ እንያዝ፡፡

ልብ ያለው ልብ ይበል!!!

4
ምእራፍ አንድ
1. እስላማዊ የአምልኮ ተግባራት፤ድንጋጌዎችና ክልከላዎች በሳይንስ መነጽር
1.1 ሰላት(ስግደት) እና ሳይንስ

በእስልምና በየቀኑ የሚደረግ ፀሎት በአረብኛ ቋንቋ ሰላት ተብሎ የሚጠራ ሲሆን በአይነቱ
ለየት ያለ አምልኮ ነው። ጸሎት ሲባል አጠቃላይ ልመናን የሚያመለክት ቢሆንም ሰላት ግን
አምላካችን አላህን ለመገዛት የሚደረግ የጸሎት ዓይነት ሆኖ ንግግርንና አካላዊ እንቅስቃሴን
አንድ ለይ ያጣመረ የአምልኮ ተግባር ነው። ይህ የአምልኮ ተግባር በሁሉም ሙስሊሞች ለይ
ግዴታ ሲሆን በእስልምና ሁለተኛ የእምነት ምሶሶ ውስጥ ይመደባል። በቅዱስ ቁርኣን ምእራፍ
4 አንቀጽ 103 እንደተገለጸው ማንኛውም ሙስሊም አምስቱን እለታዊ ሰላት (ስግደት) ወቅቱን
ጠብቆ መፈጸም አለበት።

ሶላትንም በፈጸማችሁ ጊዜ ቆማችሁም ተቀምጣችሁም በጎኖቻችሁም ላይ ተጋድማችሁ አላህን


አውሱ፡፡ በረጋችሁም ጊዜ ሶላትን (አሟልታችሁ) ስገዱ፡፡ ሶላት በምእምናን ላይ በጊዜያት
የተወሰነች ግዴታ ናትና (4:103) ፡፡
በጥንቃቄ የተከናወነ ሰላት በርካታ መንፈሰዊ ጥቅሞች ያሉት ሲሆን ከመንፈሳዊ ጥቅሙም
ባሻገር ሰላት ውስጥ የሚደረጉ አከላዊ እንቅስቃሴዎችና ተመስጦ ለጤንነታችን ጭምር ጉልህ
አስተዋጽኦ እንዳላቸው የዘመኑ ሳይንሳዊ ግኝቶት ያትታሉ። የተወሰኑትን እንካቹ ብለናል።

1.1.1 ሰላት ጭንቀትን በማስወገድ አእምሮን ዘና እንደሚያደርግ በሳይንሳዊ


ግኝት መረጋገጡ

ሰላት የሚከናወነው አካላዊ እንቅስቃሴዎችን በማድረግ ሲሆን ይህም መቆምን፣ መቀመጥን፣


ማጎንበስን(ሩኩእ ማድረግን) እና በግንባር መሬት መንካትን (ሱጁድ ማድረግን) ያጠቃልላል።
ከአካላዊ እንቅስቃሴ በተጨማሪ እንደ አስፈላጊነቱ የተወሰኑ የቁርኣን ክፍሎችም ይነበባሉ
እንዲሁም የተለያዩ ውዳሴዎችና ጸሎት እንደ አስፈላጊነቱ ይባላሉ። ሰላት ማለት በተመስጦና
በማሰላሰል የሚከናወን የአምልኮ ተግባር ነው። ሳይንሳዊ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ሰላት ውስጥ
ያለው የተመስጦና የማሰላሰል ሂደት የራስ ሰር ነርቭ ስርኣትና (Automatic nervous
system)ማእከላዊ የነርብ ስርኣት (Central nervous system) ለይ አዎንታዊ ተፅእኖ
ያሳድራል።

በ 2014 በማሌዢያ አገር ሰላት ሚያስከትለውን ተጽእኖ ለማወቅ የተደረገ ሳይንሳዊ ምርምር
ነበር፡፡የጥናቱን ግብ ለማሳካት ሲባል 30 ሙስሊም ወጣቶች ለናሙናነት የተወሰዱ ሲሆን
ኤሌከትሮኢንስፓሎግረም (Electroencephalogram) EEG የሚባል የአንጎል እንቅስቃሴ
መለኪያ መሳሪያ የጥናቱን ውጤት ለማወቅ ጥቅም ለይ ውሏል፡፡ ለንጽጽር ያመች ዘንድ
ለናሙና የተመረጡ 30 ዎቹም ሙስሊም ወጣቶች ከሰላት በፊት፣ በሰላት ውስጥና ከሰላት

5
በኃላ በኮምፒወተር ለይ የተመሰረተ የመረጃ ማግኛ ስርኣት ለይ በመመርኮዝ የEEG ምርምራ
ተደረገላቸው። የተገኘውም ውጤት የሚያስደንቅ ነበር።

የተገኘውም ውጤት እንደሚያሳየው በሰላት ወቅት ወይም ደግሞ ሰላት በሚከናወንበት ወቅት
የተመዘገበው የኤሌክትሮይንስፋሎግራፊ (EEG) አንጻራዊ ኃይል (Relative power)
በመካከለኛውና በኃለኛው የአንጎል ክፍል ለይ ከሰላት በፊትና በኃላ ካለው ጋር ሲነፃፀር ከፍተኛ
ነው፡፡ ይህ ማለት ደግሞ በሰላት ውስጥ አእምሮዋችን በጭንቀት መወገድ ምክንያት ዘና
እንደሚል ያሳያል፡፡[1]

1.1.2 በግንባር መሬት መንካት (ሱጁድ) የሚያከትለው አስገራሚ ሳይንሳዊ


ጠቀሜታው

በሰላት ውስጥ በግንባር መሬት መንካት (ሱጁድ ማድረግ) ልዩ ቦታን ይዟል፡፡ ምንም እንኳን
የሰላት ዋና አላማ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ለማድረግ ባይሆንም ለሰው አካል ዘርፈ ብዙ
የህክምና ጠቀሜታዎች እንዳለው ተረጋግጦዋል፡፡ ነቢዩ (ሰ፡ዐ፡ወ) ኢብኑ ማጃህ በዘገቡት ሀዲስ
ውስጥ ሰላትን አዘውተሮ የሚሰግድ ሰው በተለይም በመስጊድ ዉስጥ የሚሰግድ ሰው ብዙ
ከማያውቋቸው በሽታ እንደሚጠበቅ ተናግሮዋል፡፡ በሰላት ወቅት ግንባርን መሬት ማስነካት
(ሱጁድ ማድረግ) ከእስልምና ፀሎት ጋር ብቻ ተቆራኛ ነው፡፡ ነቢዩ (ሰ፡ዐ፡ወ) እንዳወሱት
ሙስሊሙ ሰጋጅ ለፈጣሪው በጣም ቅርብ የሚሆነው በዚህ ወቅት ነው፡፡ ኢማሙ ቡኻሪ አቡ
ሁረይራን ጠቅሰው እንደዘገቡት የአላህ መልክተኛ እንዲህ ብለዋል ‘’አንድ ባሪያ ለጌታው በጣም
ቅርብ የሚሆነው በሰላት ውስጥ ግንባሩን መሬት በሚያስነካበት ጊዜ ነው፤ ስለዚህ በዚህ ወቀት
ዱኣ ማድረግን አብዙ’’፡፡እራሳቸው ነቢዩ(ሰ፡ዐ፡ወ) ሱጁድን ያስረዝሙ እንደነበር ተገልጾዋል፡፡[2]
ሳይንቲስቶች እንዳረጋገጡት አሁን ባለንበት ዘመን የሰው ልጅ ከምንም ግዜ በባሰ ሁኔታ
ለኤሌክትሪክ ጨረሮች የተጋለጠ ነው። የዚህ ምክንያት ደግሞ ከሞባይል፤ ከቴሌቪዥን፤
ማይክሮዌቭ እንዲሁም የምንጠቀምባቸው የኤሌክትሮ ማግኔት መሳሪያዎች የሚወጡ
ኤሌክትሮ ማግኔት ጨረሮች አማካኝነት ነው። እነዚህ ጨረሮች በሰው ጤና ለይ በተለይ
በማዕከላዊ ነርቭ ስርዓቶች (Central Nerveous Systems) ለይ ከፍተኛ ጉዳት ያደርሳሉ። አንድ
ሰው እነዚህን ጨረሮች እሰካላስወገደ ድረስ ለራስ ምታት፤ለአንገት ህመም፤ለጡንቻ መወዛወዝና
ለመሳሰሉት ጤና ጠንቆች መጋለጡ አይቀሬ የሆነ ሀቅ ነው፡፡

የጨረሮችን ጉዳት ለማሰቀረት ከመሬት ጋር ንኪኪ መፍጠር እንዳለብን የዘርፉ ተመራማሪዎች


አበክረው ይገልፃሉ፡፡ በተለይም ግንባራችንን ከመሬት ጋር ማነካካት ይበልጥ ተመራጭ እንደሆነ
ተገልፆዋል ምክንያቱም ምድር እነዚህ ኤሌክትሮ ማግኔቲክ ጨረሮች የመሳብ ችሎታ ስላላት
ነው፡፡ የሰው ልጅን የማሰቢያ አቅም የሚቆጣጠረው ወይም የሚወስነው የፊተኛው የአንጎል
ክፍል (ግንባር)ነው፡፡ ስለሆነም በግንባራችን መሬት በምንነካበት ወቅት ከተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ
መሳሪያዎች ወደ ሰውነታችን የገቡትን ተጨማሪ ጨረሮች ከአዕምሮዋችንና ከማዕከላዊ ነርቭ
ስርዓቶች (Central Nerveous Systems) ወደ መሬት ሰለሚሰራጩ ሰላማችንን እናገኛለን፡፡
ሙስሊሞች በቀን አምሰት ጊዜ ሰላትን ሲያከናውኑ ግንባራቻውን ለ34 ጊዜ ከመሬት ጋር
ያነካካሉ (ሱጁድ ያደርጋሉ)፡፡የተለያዩ ግዴታ ያልሆኑትን ወይም ትርፍ ሰላትን በምናከናውንበት

6
ወቅት ደግሞ ከመሬት ጋር ያለን ንኪኪ እየጨመረ ይሄዳል ማለት ነው፡፡ ስለዚህ ሰላትን
አዘውትረው የሚያከናውኑ ሰዎች የአዕምሮ ደስታና መዝናናትን እንደሚጎናፀፉ ምንም ጥርጥር
የለውም፡፡[3] ሱብሃነላህ! ሁሌም ከአላህ ትእዛዝ በስተጀርባ ትልቅ ጥበብ አለ፡፡

አንተ ለጉዳይ ከቤትህ ወጣ ብለህ ደክሞህ ወደ ቤት ልትመለስ ትችላለክ፡፡ ነገር ግን በድካም


የዛለውን ሰውነትህን አልጋ ለይ ከማሳረፍህ በፊት ትጥበት አድርገህ ወደ ሰላት አምርተህ
ከዚያም ሱጁድ ስታደርግ ያንን ሁሉ ድካምን ጨምሮ ከተለያዩ ኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎች ወደ
ጭንቅላትህ ብሎም ወደ ሰውነትህ የገቡ ኤሌክትሮ ማግኔቲክ ጨረሮች ይወገዱና ሰላምህን
ተገኛለህ።

ከዚህም በተጨማሪ ሱጁድ ማድረግ የደም ዝውውርን እንዲጨምር ያደርጋል፣የአንገታችንንም


ጡንቻ ጠንካራ ያደርጋል። ሱጁድ ስንወርድ (በግንባራችን መሬት ስንነካ) አንጎላችን ወይም
ጭንቅላታችን ከልባችን በታች የሚሆንበት አጋጣሚ ይፈጠራል፡፡በእለት ተዕለት እንቀስቃሴያችን
ውስጥ ይህን አጋጣሚ (ጭንቅላት ከልብ በታች የሚሆንበት አጋጣሚ) ማግኘት እጅግ አዳጋች
ነው፡፡ ምክንያቱም በአብዛኛው እንቅስቃሴያችን ውስጥ ጭንቅላት ሁሌም ከልብ በለይ ነው
የሚሆነው፡፡ ስንተኛ ወይም ጋደም ስንል እንኳን ጭንቅላት ከልብ በለይ ነው፡፡ ምናልባትም
ጭንቅላት ከልብ በታች ሊሆን ከሚችልባቻው በጣም ጥቂት እንቅስቃሴዎች መካካል አንዱ
ሰላት ነው ብንል ከሀቁ ቅንጣት ታክል ዝንፍ አንልም፡፡ በሱጁድ ወቅት በግንባራችን መሬት
መንካታችን ደም ከልብ ወደ ጭንቅላትና አንጎል በሙሉ ሀይል እንዲመጣ ያደርጋል፡፡
በአንጎላችን ውስጥ የደም አቅረቦት በማጨመሩ ምክንያት ደግሞ አንጎላችን ተጨማሪ ምግብን
ያገኛል፡፡ ይህ ደግሞ ትውስታን ከመጨመሩም ባሻገር የማየት፤የመስማትና የማተኮር
አቅማችንን ከፍ ያደርጋል፡፡ በሥነ-ልቦናም ጠንካራ እንድንሆን ያደርገናል፡፡ አዘውትሮው ሰላትን
የሚያከናውኑ ሰዎች የበለጠ ጠንካራ ሀይል ይኖራቸዋል እንዲሁም በኑሯቸው ውስጥ
የሚገጥማቸውንን ችግሮች በተሻለ መንገድ መቋቋም ይችላሉ፡፡ እነዚህ ሰዎች
ለጭንቅላት፤ለሥነ- ልቦናችግሮች እና የግንዛቤ ተግባራት (cognitive functions) ተጋላጭ
አይደሉም፡፡[2]

በሱጁድ ወቅት ግንባራችን ከመሬት ጋር ንኪኪ ስለሚፈጥር የአንገት ጡንቻዎች ከወትሮ


የተሻለ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ያደርጋሉ፡፡ ግንባር መሬት ሲነካ ሁሉም ሸክም አንገት ለይ
ስለሚያርፍ የአንገት ጡንቻዎች እየጠነከሩ ይሄዳሉ፡፡ ጠንካራ የአንገት ጡንቻዎች ማለት ደግሞ
የአንገት አከርካሪ አጥንት የተጠበቀ ይሆናል ማለት ነው፡፡ይህ ደግሞ በጭንቅላታችን ለይ
አዎንታዊ ተፅእኖ ያሳድራል ምክንያቱም ጭንቅላታችን በአከርካሪ አጥንት ለይ ስለ ተደገፈ
ነው፡፡ ስለዚህ አዘውትረው ሰላትን የሚያከውኑ ሰዎች በተለመዱ የአንገት ህመሞች እምብዛም
አይጠቁም ምክንያቱም በቀን አምስት ጊዜ ሰላት ሲያከናውኑ ግንባራቸውን 34 ጊዜ ከመሬት
ጋር በማነካካት የአንገት ጡንቻዎቻቸውን ስለሚያጠነክሩ ነው፡፡[2]

በሰላት ክንውን ጊዜ የሚደረገው ሱጁድ (በግንባር መሬት መንካት) በሰውነት ውስጥ ባሉ አካል
ክፍሎችና ጡንቻዎች ለይም የራሱ የሆነ ተጽእኖ አለው፡፡ ሱጁድ ማድረግ ለሴቶች መህፀን
በሽታ ጥሩ ሕክምና ነው ተብሎዋል፡፡ ለወንዶችም ጥሩ የሆነ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ነው፡፡
ከሱጁድ በምንነሳበት ወቅት (ግንባራችንን ከመሬት ቀና ስናደርግ) ጡንቻዎቻችን በንቃት

7
ይንቀሳቀሳሉ እንዲሁም ከወንድ ዘር ፍሬ ጋር የተዛማዱ ጡንቻዎችም ይጠነክራሉ፡፡ በሰላት
ወቅት ግንባራችንን መሬት ስናስነካና (ሱጁድ ስናደርግ) ከመሬት ቀና ስናደርግ (ከሱጁድ ስንነሳ)
የሚደረጋው እንቅስቃሴ የጀርባ ጡንቻዎችን መዘርጋትና መኮማተር ስለሚያስከትል
ጡንቻዎቹን ጠንካራ እንዲሆኑ ያደጋቸዋል፡፡ይህ ደግሞ የጀርባ ህመምን ያስወግዳል፡፡ ለዚህም
ነው አዘውትረው ሰላትን የሚያከናውኑ ሰዎች የጀርባ ህመም ብዙም የማይሰማቸው፡፡[2]

በሰላት ወቅት የሚደረገው ሱጁድ ዋናው አላማ አምልኮ ነው እንጂ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ
ለማድረግ አይደለም፡፡ ሆኖም ግን በርካታ ሳይንሳዊ ጥቅሞች እንዳሉት ከለይ በተብራራው
የሱጁድ ጥቅሞች ለይ አይተናል፡፡ ስለዚህ አንድ ሙሰሊም በሰላት ውስጥ ሱጁድ አድርጎ
(ግንባሩን ከመሬት ጋር አገናኘቶ) ሳይነሳ ረጀም ጊዜ በቆየ ቁጥር በርካታ መንፈሳዊና ሳይንሳዊ
ጥቅሞችን እንደሚሸምት እሙንና ቅቡል ነው፡፡ ነቢዩ (ሰ፡ዐ፡ወ) የሱጁድን ጥቅም ብታውቁ ኖሮ
አስከ የውሙል ቂያማ ወይም እለተ ትንሳኤ ድረስ ከሱ አትነሱም ብለው ነበር፡፡ ሱጁድ ምን
ያህል ጥቅም ቢኖረው ነው ነቢዩ (ሰ፡ዐ፡ወ) ይህን የተናገሩት፡፡ኢማሙ ቡኻሪ እናታችን ዓኢሻን
(ረ፡ዐ) ጠቅሰው እንደዘገቡት እራሳቸው ረሱል (ሰ፡ዐ፡ወ) አንድ ሰው 50 የቁርኣን አንቀጾችን
የሚቀራውን ያህል ሱጁድን ያስረዝሙ እንደ ነበር ተገልጾዋል፡፡ በሌላ ዘገባ ነቢዩ (ሰ፡ዐ፡ወ)
ከእርሶ ጋር በጀነት ውስጥ ጎሮቤት መሆን እፈልጋለው ላላቸው አንድ ወጣት ሱጁድ ማድረግን
አብዛ ብለው ነው የመከሩት፡፡ ስለዚህ ይህ የሰላት ዋናው ክፍል ወይም ቁንጮ የሆነው ሱጁድ
(በግንባር መሬት መንካት) የሁለቱ ዓለም (ምድረዊና ሰማያዊ ዓለም)ስኬት መክፈቻ ቁልፍ ነው
ቢባል ማጋነን አይሆንም፡፡ ሰላት ስንሰግድ በፍጥነት ጎንበስ ቀና የምንል ሰዎች ምድራዊም
ሰማያዊም ጥቅም እንዳያመልጠን ይህን ጉዳይ በደምብ ልናጤን ይገባል፡፡

1.1.3 ሰላት የደም ግፊት ችግርን ይቀርፋል

በሰውነታችን ውስጥ ከቁጥጥር ውጭ ወይም ደግሞ ባልተስተካከለ የደም ፍሰትና ዝውውር


ምክንያት የደም ግፊት ችግር ሊኖርብን ይችላል። ይህ ችግር የሚከሰተው ወደ አንድ የተወሰነ
የሰውነት ክፍል በሚፈሰው ደም በጣም ብዙ ከሆነ ወይም ደግሞ ወደ አንድ የተወሰነ ክፍል
በሚፈሰው ደም በጣም ዝቅተኛ ከሆነ ነው። ታዲያ እንዲ አይነት ተያያዥ ችግር ላለባቸው
ሰዎች ሰላት ጥሩ መፍትሄ ይዞ ብቅ ብሎዋል።በሰላት ውስጥ ያለው አኳኃን የደም ፍሰትን
በማስተካከል ረገድ ከፍተኛ ሚና ይጫወታል። በሰላት ክንውን ግዜ የሚደረጉ አካላዊ
እንቅስቃሴዎች (መቆም፣መጎንበስ(ሩኩእ)፣በግንባር መሬት መንካት (ሱጁድ)ና መቀመጥ) በልብ
ምትና በደም ግፊት ለይ ያላቸውን ተፅእኖ አስመልክቶ ጥናት ተደርጎዋል። የጥናቱ ውጤት
እንደሚያሳየው ከሆነ በሰላት ውስት መቆም የልብ ምትን የሚጨምር ሲሆን ሱጁድ ማድረግ
ደግሞ የልብ ምትን ይቀንሳል፡፡በተጨማሪም ሰላት በሚከናወንበት ወቅት ሲያስቶሊክ (systolic)
የደም ግፊት (የላይኛው ልኬት)ና ዲያስቶሊክ (Dystolic) የደም ግፊት (የታችኛው ልኬት)
ከፍተኛ መቀነስ አሳይቶዋል። ስለዚህ በቀን አምስት ግዜ በመደበኛነት ሰላትን የሚያከናውኑ
ሰዎች ጤናማ የሆነ የደም ዝውውር ይኖራቸዋል፣ የተስተካከለ የልብ ምት ይኖራቸዋል፣
የሰውነት ስብንም መቀነስ ይችላሉ፡፡ [4]

8
1.2 እስላማዊ ፆምና ሳይንስ
1.2.1 ፆምና ሳይንሳዊ ጠቀሜታው

ፆም ከአምስቱ የእስልምና ምሰሶዎች መካከል አንዱ ነው፡፡ ታማሚዎች፤ነፍሰጡር ሴቶች፤የወር


አበባ ለይ ያሉ ሴቶች፤በጉዞ ለይ ያሉ፤ትንንሽ ህፃናትና አረጋውያን ሲቀሩ በሁሉም ሙስሊሞች
ለይ በየዓመቱ የረመዳንን ወር ምንም ሳያጓድሉ መፆም ግዴታ ነው፡፡ ቅዱስ ቁርኣን በምእራፍ
ሁለት አንቀፅ 183 ለይ ጾም በሙስሊሞች ለይ የተደነገገ የአምልኮ ተግባራት መካከል አንዱ
እንደሆነ እንደሚከተለው ይገልፃል፡፡

እናንተ ያመናችሁ ሆይ ጾም በነዚያ ከናንተ በፊት በነበሩት (ሕዝቦች) ላይ እንደ ተጻፈ


በናንተም ላይ ተጻፈ (ተደነባ) ልትጠነቀቁ ይከጀላልና፡፡ (2፡183)
በዚህ የተከበረ የቁርኣን አንቀፅ ውስጥ አምለካችን አላህ ፆም እንደነገገና ለሁሉም ሰው ልጆች
የተለመደና የተቋቋመ ስርኣት እንዳደረገ ይነግረናል፡፡በእስልምና የረመዳንን ወር መፆም
እያንዳንዱ ሙስሊም ለይ ግዴታ ሲሆን ከረመዳን በተጨማሪ ሌሎች ግዴታ ያልሆኑ ወይም
ደግሞ በፍቃደኝነት የሚፆሙ በብዛት አሉ፡፡አንድ ሙስሊም አማኝ ራሱን ለፈጣሪ አስገዝቶ
እንዲሁም ክልከላዎችን ጠብቆ በመፆሙ ምክንያት ከፈጣሪ ዘንድ ይህ ነው ተብሎ የማይገመት
ላቅ ያለ ምንዳ ያገኛል፡፡

ሙስሊም ያልሆኑ ወገኖቻችን የሙስሊሞችን ፆም ሲያጥላሉና ሲያብጠለጥሉ ማየት የተለመደ


ነው፡፡እውነታው ግን የሙስሊሞች ፆም ከመንፈሳዊ ጥቅሙ ባሻገር ለጤና ጭምር እጅግ
ጠቃሚ ስለመሆኑ በሳይንሳዊ ግኝት ያመለክታሉ፡፡

ምግብን አብዝታን ስንመገብ ሰውነታችን ውስት ሄዶ ይከማቻል፡፡ይህ ደግሞ ልዩ ልዩ ችግሮችን


ያሰከትልብናል፡፡ወደ መርዝነትም ተቀይሮ በህብረ ህዋሳት ውስጥ ይከማቻል፡፡የዚህ ሁሉውጤት
የተለያዩ በሽታዎችን እና የጤና እክሎችን ማስከተሉ ነው፡፡ ስለዚህ ያለ አግባብ ምግብን
ከመጠን በለይ መመገብ በጤና ለይ አደጋ ማስከተሉ የማይካድ ሀቅ ሆኖ እናገኛለን፡፡ አንድ
የሳይንስ ሊቅ እንዳሉት አንድ አይነት ምግብን ብቻ በተከታታይ መውሰድ የሰውነታችን
ሜታቦሊዝም ለይ ከፍተኛ ጫና ያሳድራል፡፡ ይህ ፀረ - ጤና የሆነውን አመጋገብ ማስወገድ
የምግብ መፍጫ ሆርሞኖችን እና ኢንሱሊንን እንዲቀንስ በማድረግ ጤናችንን የተጠበቀ
ያደርጋል፡፡ ለምሳሌ በየሁለት ቀን ኣንዴ የሚመገቡ የላብራቶሪ አይጦች በየቀኑ ከሚመገቡ
አይጦች በለይ ረዘም ላለ ጊዜ በህይወት እንደሚቆዩ ተረጋግጧል፡፡[5]

በአውሮፓ ከህዳሴ ዘመን በኃላ የሳይንስ ሊቃውንቶች ሰዎች ምግብን ከመጠን በለይ
እንዳይመገቡ ጥሪ እያደረጉ ይገኛሉ፤ ይልቁንም ከመጠን ያለፈ የምግብ ክምችትን ለመቀነስ
ፆምን ይመክራሉ፡፡ ሆዳምነት ከተንሰራፋ ከወረርሺኝ ወይም ጦርነት የበለጠ ለሞት የሚዳርግ
በሽታ እንደሆነ አፅንኦት ሰጥተው ይናገራሉ፡፡ ስለሆነም ሰውነታችን የሚያስፈልገውን ብቻ
መብላት አለብን፡፡ ሁሉን ቻይና አዋቂ የሆነው አምላካችን አላህ የሰውን ነፍስ ለማፅዳትና
ምግብን ከመጠን በለይ በመመገብ ምክንያት ለሚከሰቱት በሽታዎችና ህመሞች ህክምና ይሆን

9
ዘንድ ፆምን ደንግጓል፡፡ አምላካችን አላህ በቅዱስ ቁርኣን ምእራፍ ሁለት አንቀፅ 184 ለይ
እንዲህ ይላል፡፡[5]

‹‹ ---- መፆማችሁ ለናንተ የበለጠ ነው፤የምታውቁ ብትሆኑ (ትመርጡታላቹ) ----›› (2፡184)

በዚህ አንቀፅ ውስጥ የፆምን ጥቅም ብታውቁ ኖሮ እንደውም ትመርጡታላችሁ እያለን ነው፡፡
የሙስሊሞች ፆም ሳይንሳዊ ጥቅሞች አሁን ባለንበት ዘመን በስፋት እየታወቁ መጥቶዋል፡፡
ከጥቅሞቹ መካከል የተወሰኑት ቀንጨብ ተደርገው እንደሚከተለው ይቀርባሉ፡፡

1. በጾም እና በሰውነት በሽታ የመከላከል ስርዓት መካከል ቁርኝት አለ፡፡ የሰውነት በሽታ
የመከላከል ስርዓት ሰውነቶችን ከብዙ ቫይረሶች እና ከጎጂ ባክቴሪያዎች የሚጠብቅ
የወታደሮች ቡድን ነው፡ በፆም ወቅት የሰውነታችን በሽታ መከላከል አቅሙ እየጨመረ
እንደሚሄድ ሀኪሞች ይናገራሉ። ሳይንሳዊ እውነታዎች እንደሚጠቁሙት ፆምን
ማዘውተር ሊምፍቶድ (lymphocytes) የሚባሉ የነጭ ደም ሴል አይነቶችን በ10 እጥፍ
እንዲጨምሩ ያደርጋል፡፡ እነዚህ ሴሎች ሰውነትን ከሚያጠቁ ጥቃቅን ነፍሳት እና ከውጭ
አካላት የሚከላከሉ የደም ሴሎች ናቸው፡፡ በተጨማሪም በፆም ወቅት ሰውነትን ከተለያዩ
ጥቃት የሚጠብቁ ሴሎች መጠናቸው ብቻ ሳይሆን የጥራት ደረጃቸውም
ይጨምራል፡፡ሰውነትን የሚወር ማንኛንውም ህዋሰትንና እንግዳ አካላትን የሚፋለሙት
የተለያዩ የፀረ እነግዳ አካላት ዓይነቶችም በፆም ወቅት ይጨምራሉ፡፡በሁሉም በሽታዎች
ላይ የሰውነት መቋቋም እየጨመረ በሄደ መጠን ሐኪሞች ጾም በሽታ የመከላከል
ስርዓታችንን እንደሚያነቃ ያረጋግጣሉ፡፡ስለሆነም ጾም ሰውነት ራሱን እንዲከላከል
የሚረዳ ውጤታማ መሳሪያ ነው፡፡[6]

2. በፆምና ከመጠን ያለፈን ውፍረት ለመከላከል በሚደረግ ህክምና መካከል ዝምድና አለ።
ምክንያቱም ውፍረትን ለመከላከል ፆም ሁነኛ የሆነ መፍትሄ ነው። የቅርብ ግዜ
ሳይንቲስቶች ፆም ስብን ለማስወገድ፤ቅባቶችን ለሟሟት እና ሆርሞኖችን ለማደራጀት
እንደሚረዳ ይናገራሉ። ከመጠን በለይ ውፍረት ከአመጋገባችን ችግር፣ከስነ ልቦና እና
ማህበራዊ ጫናዎች ሊመጣ ይችላል። በፆም ምክንያት የሚመጣው የአዕምሮና ስነ ልቦና
መረጋጋት እነዚህ ሁሉ ችግሮች ሊቀረፉ ይችላሉ። በተጨማሪም ፆም ውፍረትን
ተከትሎ የሚመጡትን የደም ግፊት፣ የልብ ህመምንና የመሳሰሉትን በሽታዎች በማከም
ረገድ ትልቅ ሚና ይጫወታል፡፡[6]
3. ፆም በሰውነት ውስጥ ለተከማቹ መርዞች ፈውስ እንደሆነ ሳይንቲስቶች ያረጋግጣሉ
ምክንያቱም የሰውነት ሴሎችን ከነዚህ መርዞች ለማፅዳት ስለሚረዳ ነው።ከልብ ወለድ
የማይናገሩት ነቢዩ ሙሐመድ (ሰ፣ዐ፣ወ) ሙስሊም በዘገቡት ሀዲስ ውስጥ ፆም መከላከያ
ነው ብለዋል። ይህ የነቢዩ ንግግር ፆም የብዙ ነገሮች መከላከያ እንደሆነ ይነግረናል ።[7]
ፆም በሰውነት ሴሎች ውስጥ የተከማቹትን መርዛማ ንጥረ- ነገሮች እንዲሁም ደግሞ
በህብረ ህዋሳት መካከል የሚገኙትን መርዛማ ንጥረ ነግሮች ለማስወገድ ይረዳል።እነዚህ
መርዛማ ንጥረ ነገሮች በብዛት የሚመጡት ከታሸጉ ምግቦች፣ ከመድሃኒትና ከተበከለ
አየር ነው።[6]

10
4. የህክምና ባለሙያዎች ከረጅም ህይወት ጀርባ ፆም አንዱ ምክንያት እንደሆነ ይናገራሉ።
ብዙ ሙስሊም ያልሆኑ ሊቃውንቶች ስለ ፆም ልዩ ልዩ ጥቅሞች መፅሐፍን የፃፉ ሲሆን
ብዙ ጊዜ በፆም የሚያሳልፉ ሰዎች ከማይፆሙት አንፃር የበለጠ ረጅም እድሜ አላቸው
የሚል ድምዳሜ ለይ ደርሰዋል፡፡[8]
5. ፆም የወንዶችንም ሆነ የሴቶችን የመራባት ችሎታን ከፍ ያደርጋል። መፆም ብዙን ጊዜ
ተፈጥሮኣዊ የግብረ ስጋ ግንኙነት ፍላጎታችንን ይቀንሳል። ይህ ደግሞ የስነ-ልቦናና
የባህሪ መዛባትን ይከላከላል። የነቢዩ መሐመድ (ሰ፣ዐ፣ወ) ንግግር ለዚህ ማረጋገጫ ነው።
ነቢዩ (ሰ፣ዐ፣ወ) እንዲህ ብለው ነበር ‹‹‹ ወጣቶች ሆይ ከናንተ ማግባት የሚችል ሰው
ጣጣውን ከቻለ ያግባ፣ ማግባት የማይችል ከሆነ ደግሞ ስጋዊ ፍላጎቱን መግታት ይችል
ዘንድ ይፁም ›››።በፆም ወቅት ስሜትን የሚቀሰቅሰው ቴስቴስትሮን የተባለ የወንዱ
ሆርሞን መጠኑ ለብዙ ቀናት ይቀንሳል። ከዚያ በኃላ ከፍተኛ ጭማሪ ያሳያል። በሌላ
አገላለፅ በተከታታይ ቀናት ስንፆም ስጋዊ ፍላጎታችን ይቀንሳል። ስናፈጥር (ፆሙን
ስንፈታ) ስጋዊ ፍላጎታችን ከበፊቱ የበለጠ ስለሚነቃቃ የመራባት አቅምን እንዲጨምር
ያደርጋል፡፡[6]
6. በፆም ወቅት በፆም ወቅት የደከሙና ያረጁ ሴሎች ይሞታሉ። አዳዲስ ሴሎች ደግሞ
መፅደቅ ይጀምራሉ።[6]

ብዙ ሰዎች ፆም በጤናቸው ለይ አሉታዊ ተፅእኖ ያሳድራል ብለው ያስባሉ፡፡ ሰውነታቸው ልክ


እንደ ሰው ሰራሽ ማሽን በነዳጅ ብቻ የሚሰራ አድርገው ይቆጥራሉ። በየቀኑ ሶስት ጊዜ መመገብ
አለመቻል ከፍተኛ አደጋ የሚያስከትል ወይም ጎጂ እንደ ሆነ ያስባሉ። ይህ ደግሞ በረመዳን
ፆም ለሊቱን ከፍተኛ መጠን ያለውን ምግብና መጠጥ እንዲወስዱ ያደርጋቸዋል። ቀኑን ደግሞ
በእንቅልፍ ያሳልፋሉ። ይህ የተሳሳተ አካሄድ ስራ እንዲቆምያደርጋል፤ምርትና ምርታማነትን
ይቀንሳል፣የምግብና የመጠጥ ፍጆታን ደግሞ ይጨምራል። ይህ አካሄድ የተሳሳት መሆኑን
በርካታ ወሳኝ ማስረጃዎችን ማስቀመጥ ይቻላል።[6]

ሳይንሳዊ ግኝቶች እስላማዊ ጾም በጣም ቀላል መሆኑን የሚያመለክቱ ሲሆን በፆም ወቅት
ሰውነት ለአሉታዊ ተፅእኖ የማይጋለጥ መሆኑን ጭምር አበክረው ያስረዳሉ።በተቃራኒው ግን
ሰውነት ያለ ጾም ሊያገኙ የማይችሉ ብዙ ጥቅሞችን በፆም ወቅት ያገኛል፡፡ ኢስላማዊ ጾም
ሰውነታችን ላይ በጣም ቀላል ነው። ይህንን በማረጋገጥም ሁሉን ቻይ የሆነው አላህ በቅዱስ
ቁርኣን ምእራፍ ሁለት አንቀፅ 185 ለይ እንዲህ ይላል፡፡

(እንድትጾሙ የተጻፈባችሁ) ያ በርሱ ውስጥ ለሰዎች መሪ ከቅን መንገድና (እውነትን ከውሸት)


ከሚለዩም ገላጮች (አንቀጾች) ሲኾን ቁርኣን የተወረደበት የረመዳን ወር ነው፡፡ ከእናንተም
ወሩን ያገኘ ሰው ይጹመው፡፡ በሽተኛ ወይም በጉዞ ላይ የኾነም ሰው ከሌሎች ቀኖች ቁጥሮችን
(በልኩ) መጾም አለበት፡፡ አላህ በእናንተ ገሩን (ነገር) ይሻል፡፡ በእናንተም ችግሩን አይሻም
(2:285) ፡፡
አላህ በዓመት ውስጥ ለጥቂት ቀናት ብቻ መፆምን ያዘዘው፡፡በተጨማሪም ይህንን አጭር የፆም
ወቅት በህመምተኛ ወይም በመንገድ ተጓዥ ላይ አላዘዘም። በዚህ ፆም ውስጥ ሰው በቀን
ውስጥ ለተወሰነ ጊዜ ማለትም ከማለዳ እስከ ፀሐይ መግቢያ ድረስ ከምግብና ከመጠጥ

11
ይርቃል። ማታ ደግሞ የመብላትና የመጠጣት ነፃነት አለው። ስለሆነም ጾም የሚያደርገው
አንድ ሰው ምግብና መጠጥ የሚበላበትን ጊዜ መለወጥ እንጂ ሌላ አይደለም። ይህ ደግሞ ጉዳት
አያመጣም። ስለዚህ እስላማዊ ፆም ቀለል ያለ ለሰው ልጅ በሚመች መልኩ በፈጣሪ የተደነገገ
ፆም ነው፡፡ በርካታ ሳይንሳዊ ጥቀሞች እንዳሉትም ሙስሊም ባልሆኑ ሊቃውንት ጭምር
ተረጋግጧል፡፡[6]
1.2.2 የአያመል ቢድ ፆም እና ሳይንስ

በአረቢኛ አያመል ቢድ ቀናት የሚባሉት የጨረቃ ወር 13ኛው፤14ኛው እና 15ኛው ቀናት


ናቸው፡፡ በእናዚህ ሶስቱ ቀናት ጨረቃ ሙሉ (Full moon) ሆና በመውጣት አከባቢውን በደማቅ
ብርሃን ታለብሳለች፡፡ ይህ ብርሃን ከሌላው ጊዜ የበለጠ ደማቅና በተለይም በበረሃማ አከባቢ ነጣ
ብሎ ይታያል፡፡በዚህም ምክንያት እናዚህ ሶስቱ ቀናት ነጮቹ ቀናት (the white days) በመባል
ይታወቃሉ፡፡

ግዴታ ከሆነው ከረመዳን ፆም ውጪ ነቢዩ (ሰ፡ዐ፡ወ) ተጨማሪ ቀናትን መፆም ያዘወትሩ


እንደነበር በበርካታ ሀዲሶች ተገልፆዋል፡፡ ከነዚህ ቀናት ማከከል አንዱ የአያመል ቢድ ቀናት
ወይም ነጮቹ ቀናት ናቸው፡፡ ኒሳኢና ቲርሚዚ በዘገቡት ሰሂህ ሀዲስ ውስጥ አቡ ዘር (ረ፡ዐ)
የአላሀ መልእክተኛ (ሰ፡ዐ፡ወ) በወር ሶስት ቀናትን ማለትም የጨረቃ ወር 13ኛው፤14ኛው እና
15ኛው ቀናትን እንድንፆም ያዙን ነበር በማለት ተናግሮዋል፡፡

ጨረቃ ለፀሐይ በጣም ቅርብ የሆነች የተፈጥሮ ሳታላይት ናት፡፡ ዘመናዊ ስነ ፈለክ ከመምጣቱ
ከረጅም ጊዜ በፊት በበርካታ ጥንታዊ የጥበብ ባለሙያዎችና አፈታሪኮች ስለ ጨረቃ ብዙ ነገር
ተብሎዋል፡፡ የጥንት ሰዎች ጨረቃ በምድር ለይ የሚያሳድረውን ተጽእኖ መገንዘብ ጀምረው
ነበር፡፡ ሆኖም ግን የጨረቃ ሩቅ ክፍል ለረጅም ክፍለ ዘመናት ለጥናት ተደራሽ አልነበረም፡፡
ባለፈው ምዕተ ዓመት ውስጥ ግን የስነ ፈለክና የኮስሞቲክሰ ፈጣን እድገት ተከትሎ በርካታ
በጨረቃ ዙሪያ መረጃዎች እየወጡ ይገኛሉ፡፡

እንደ ዘመኑ የስነ ፈለክ ሳይንስ የጨረቃ ዑደት በሰዎች እለት ተዕለት እንቅስቃሴ፤በሰዎች
ባህሪና ጤና ለይ ተፅእኖ ያሳድራል፡፡ በተለይም ጨረቃ ሙሉ (full moon) ሆና በመውጣት
አከባቢውን በደማቅ ብርሃን ስታለብስ ሰዎች በደምብ መተኛት አይችሉም፤ጭንቀትና
ተጋላጭነት በስፋት ይስተዋላል፡፡እንዲሁም በሙሉ ጨረቃ (full moon) ወቅት ሰዎች የችኮላ
ድርጊቶችን ይፈጽማሉ፤አደጋዎች እና ወንጀሎች በብዛት ይከሰታሉ፡፡ በሽታዎችን በተመለከተ
ደግሞ ጨረቃ ሙሉ ሆና በምትወጣበት ቀናት ይባባሳሉ፡፡ በተጨማሪ ሰዎች አሉታዊ
አመለካከቶችን ያመነጫሉ፡፡

በአሜሪካ የስነ-ልቦና ባለሙያ የሆኑት ዶ/ር ሊበር‹‹ በጨረቃ ዑደትና በሰው ልጆች ለይ ወንጀል
ዝንባሌዎችና ስሜታዊነት መካከል ጠንካራ ግንኙነት አለ ብሎዋል፡፡ ዶ/ር ሊበር በሆስፒታሎች
እና በፖሊስ ጣቢያዎች ውስጥ የተለያዩ የስታቲስቲክስ መረጃዎችን ከሰበሰበ በኃላ የመንገድ
አደጋዎችና ወንጀሎች ከጨረቃ ዑደት ጋር የተቆራኙ መሆኑን ደርሶበታል፡፡የሱ ሳይንሳዊ
ጥናቶች ፍቺና ከባድ የሆነ ውዝግብ ጨረቃ ሙሉ በምትሆንበት ቀናት ውስጥ በብዛት
እንደሚከሰቱ ያረጋግጣሉ፡፡[9]

12
ጨረቃ ሙሉ ስትሆንና በሰዎች ለይ የጨረቃ ውጤት ከፍተኛ ደረጃ ለይ በሚደርስበት ወቅት
ለሚከሰቱት ዘርፈ-ብዙ ችግሮች እስልምና ፍቱን የሆነ ነቢያ መድሃኒት አዘጋጅቶዋል፡፡ ይህም
ጨረቃ ሙሉ የምትሆንበትን ሶስቱን ቀናት ማለትም በጨረቃ አቆጣጠር 13ኛ፤14ኛ እና 15ኛ
ቀናትን በፆም ማሳለፍ ነው፡፡ እነዚህን ሶሰቱን ነጭ ቀናት መፆም የወንጀል ድርጊቶችን፤የባህሪ
መዛባትን እና በሽታዎችን ለመከላከል እጅግ በጣም ጠቃሚ ነው፡፡[9]

የዘመኑ የስነ ፈለክ ሳይንስ ጨረቃ ሙሉ ሆና በምትወጣበት ቀናት ምድር ለይ ከወትሮው


የበለጠ የተለያዩ የወንጀል ድርጊቶች፤በሽታዎችና የስነ-ልቦና ችግሮች እንደሚከሰት ያሳያል፡፡
ከዚህም በተጨማሪ በነዚህ ቀናት ስሜታችን በከፍተኛ ሁኔታ ስለሚቀሰቀስ ለወሲብ ያለን
ፍላጎት በጣም ከፍ ይላል፡፡ የሚገርመው ነገር ነቢያችን (ሰ፡ዐ፡ወ) ጨረቃ ሙሉ በምትሆንበት
በነዚህ ቀናት ነው እንድንፆም የመከሩን፡፡ ይህ አንዴት ሊሆን ይችላል? ሳይንስ ዛሬ ለይ ጨረቃ
ሙሉ በምትሆንባቸው ቀናት ምድር ለይ ትልቅ ችግር ይፈጠራል ብሎ ይናገራል፡፡ ለዓለማት
እዝነት የተላኩት ነቢዩ (ሰ፡ዐ፡ወ) ደግሞ ጨረቃ ሙሉ በምትሆንባቸው ቀናት ማለትም በጨረቃ
አቆጣጠር 13ኛ፤14ኛ እና 15ኛ ቀናትን ፁሙ በማለት ሳይንስ ይከሰታል ላለው ችግሮች ዘመን
የማይሽረውን መፍትሄ አስቀምጦውልናል፡፡ እነዚህን ቀናት እንድንፆም ለነቢዩ (ሰ፡ዐ፡ወ) ማን
ነገራቸው? ቅዱስ ቁርኣን ምእራፍ 53 ከአንቀፅ 3 እስከ 4 ደረስ ለዚህ ጥያቄ መልስ አለው፡፡
 ነቢያችሁ (ሙሐመድ) አልተሳሳተም፤ አልጠመመምም፡፡ (53፡2)
 ከልብ ወለድም አይናገርም፡፡ (53:3)
 እርሱ (ንግግሩ) የሚወርድ ራእይ እንጅ ሌላ አይደለም፡፡ (53:4)
1.3 ኢስላማዊ የእንስሳ አስተራረድ ዘዴ በሳይንስ ሲቃኝ
እስላማዊ የእንስሳ አስተራረድ በዘመናዊ በሳይንስ ይደገፋል ወይስ አይደገፍም የሚለውን
ከማየታችን በፊት ለምግብንነት ያልተፈቀዱ ምን ምን እንደሆኑ ከቅዱስ ቁርኣን እንይ። ቅዱስ
ቁርኣን በምእራፍ ሁለት አንቀፅ 173 ለይ ለምግብነት ያልተፈቀዱ ነገሮችን ሲገልፅ እንዲህ
ይላል።

በናንተ ላይ እርም ያደረገው በክትንና ደምን፣ የእሪያ ሥጋንም፣ በእርሱም (ማረድ) ከአላህ ስም
ሌላ የተነሳበትን ነገር ብቻ ነው፡፡ሽፍታና ወሰን አላፊ ሳይኾን (ለመብላት) የተገደደ ሰውም በርሱ
ላይ ኃጢኣት የለበትም፡፡ (2፡173)
ይህ የቁርኣን አንቀጽ የሞተን ነገር (በክትን) መመገብ፣ደምን ለምግብነት ማዋል እንዲሁም
ደግሞ የእሪያን ስጋ መመገብ በእስልምና ክልክል መሆኑን ይነግረናል። እዚህ አንቀጽ ውስጥ
ደም ክልክል የሆነበትን ምክንያት በሳይንሳዊ ማስረጃ ጭምር አስደግፈን ለማብራራት
እንሞክራለን። ደምን መብላት ስለመከልከሉ ማብራራት የእስልምና አስተራረድ ዘዴ ለምን
ተመራጭ እንደሆነ ለማስረዳት ያግዛል፡፡

13
ደምን መጠጣት ወይም ለምግብነት ማዋል በእስልምና ክልክል ስለመሆኑ ቁርኣን 2:173
ያብራራል። በተጨማሪም ቁርኣን 16፡115 እና ቁርኣን 6፡145 ለይም ደምን ለምግብነት ማዋል
እርም መሆኑን ተገልጾዋል፡፡ሳይንሳዊ እውነታዎችም ይህንን ክልከላ የሚያጠናክሩ ናቸው።

ከደም ተግባራት መካከል አንዱ አልሚ ንጥረ ነገሮችን ወደ ተለያዩ ሰውነታችን ክፍሎች
መውሰድና ቆሻሻ ነገሮችንና መርዛማና ንጥረ ነገሮችን ደግሞ ከህብረ ከሰውነታችን ክፍል ሰብስቦ
እንዲወገዱ ማድረግ ነው። እነዚህ ቆሻሻ ምርቶችና መርዛማ ንጥረ ነገሮች ለሰውነት ጎጂ ናቸው
እናም በኩላሊት በኩል ይወገዳሉ። ቆሻሻና ጎጂ ነገሮች በሽንት በኩልም ከሰውነታችን ተጣርተው
ወደ ውጪ ይወጣሉ። ይህ አንዱ ቆሻሻ ማስወገጃ መንገድ ነው። ደም የተላያዩ በሽታ አምጪ
የሆኑ ቆሻሻ ነገሮችን ይዞ ይዘዋወራል።ለዚህም ነው ደምን መመገብ ለጤና በጣም ጎጂ ነው
የተባለው። የሚበላ ስጋ ውስጥ ብዙ ደም ካለበት አደጋ ሊያስከትል ይችላል ምክንያቱም ደሙ
በያዘው ቆሻሻና መርዛማ ንጥረ ነገሮች አማካኝነት በሽታ ለይ ልንወድቅ ስለምንችል ነው።
ስለዚህ ስጋቸው ለመብል የተፈቀዱ እንስሳት በሚታረዱበት ወቅት ደሙ ከታረደው እንስሳ
ሙሉ በሙሉ ወደ ውጪ መፍሰስ አለበት ወይም አብዛኛው ደም መፍሰሱን ማረጋገጥ ማቻል
አለበብን፡፡ ምክንያቱም ደምንና በደም የተጨማለቀውን ስጋ መመገብ ለጤና በጣም ጎጂ ነው፡፡
[10]

ሙስሊም ያልሆኑ ሰዎች በእስልምና የእንስሳ አስተራረድ ዘዴ ለይ ከፍተኛ ትችት ይሰነዝራሉ።


የሙስሊሞች እንስሳ አስተራረድ ጭካኔ የተሞላበትና እንስሳውን አሰቃይቶ የሚገድል ነው
ብለው ያስባሉ። ይህ አስተሳሰብ ከእውነታው የራቀ ነው፡፡ እስልምና በሰውም ሆነ በእንስሳ ለይ
የጭካኔ በትርን ከማሳረፍ ጥንቃቄ ያደርጋል።

ነቢዩ መሐመድ (ሰ፡ዐ፡ወ) እንዲህ ብለዋል፡፡‹‹‹ በእውነት አላህ በሁሉም ነገር ማስተካከልን
አዟል። ስትገድሉ አስተካክላችሁ ግደሉ፣ ስታርዱ አስተካክላችሁ እረዱ፣ እያንዳንዳቹ ቢላውን
በደንብ ይሳል፣ የሚያርደውን እንስሳ አያሰቃየው›››፡፡ ስለዚህ ሌላው ቀርቶ እንስሳትን ስናርድ
እንኳማሰቃየት የለብንም። ከማረዳችን በፊትም እህልና ውሃ በመስጠት መንከባከብ አለብን።
[10]

የዘመኑ ሳይንሳዊ እውነታ እንደሚያመለክተው ከሆነ ምርጡና የእንስሳትን ስቃይ የሚቀንሰው


የእንስሳ አስተራረድ ዘዴ ማለት የሙስሊሞች አካሄድ ነው፡፡በእስልምና ስጋው ለመብል
የተፈቀደ እንስሳ በሚታረድበት ወቅት የእንስሳው መተንፈሻው ቱቦ (Trachea) እና የደም
ጅማቱ (Jagular vein) ነው ከፊት ለፊት በኩል መቆረጥ ያለበት። በኃላ በኩል ወይም ደግሞ
በአንገቱ ጀርባ መቆረጥ የለበትም። በተጨማሪም የእንስሳው አንገት ሙሉ በሙሉ መቆረጥ
ወይም መሰበር የለበትም። የአከርካሪው አጥንትም (Spinal Cord) በፍፁም መቆረጥ ያሌለበት
ሲሆን ደሙ ፈሶ እስኪያልቅ ድረስ ሌሎች ተመሳሳይ ድርጊቶች መደረግ የለባቸውም፡፡[11]
ይህ የእስልምና አስተራረድ ዘዴ የራሱ የሆነ ሳይንሳዊ እንደምታ አዝሏል፡፡

በእስልምና ለእርድ የቀረበ እንስሳ በሚታረድበት ወቅት መተንፈሻው ቱቦውና የደም ጅማቱ
ከፊት ለፊቱ መቆረጡ ደሙ ሙሉ በሙሉ ወደ ውጭ እንዲፈስ ያደርጋል። ከዚህም ባሻጋር

14
የታረደው እንስሳ ሙሉ በሙሉ ራሱን ስለሚስት ህመም ወይም ስቃይ አይሰማውም።ሁለት
አንኳር የሆኑ ቁምነገሮችን ከዚህ መውሰድ እንችላለን።

አንደኛ፣ሰዎች የእስልምና የእንስሳ አስተራረድ ጭካኔ የተሞላበት ነው ብለው እንደሚያስቡት


አይደለም። ምክንያቱም እንስሳው ከፊት ለፊቱ በኩል የመተንፈሻው ቱቦውና የደም ጅማቱ
አንድ ለይ በደምብ በተሳለ ቢላ ሲቆረጥ ወዲያው ራሱን ከመሳቱ የተነሳ ህመም ወይም ስቃይ
እንደማይሰማው በሳይንሳዊ ጥናት ተረጋግጦዋል፡፡

ሀለተኛ፣ለእርድ የቀረበው እንስሳ የመተንፈሻው ቱቦና የደም ጅማቱ በሚቆረጥበት ወቅት ደሙ


ሙሉ በሙሉ ነው ወደ ውጪ የሚፈሰው።ደም በሽታ አምጪ የሆኑ ጀርሞች የሚያድጉባቸው
በጣም ለም ከሆኑ ቦታዎች አንዱ ሲሆን ለሰው አካል ጎጂ የሆኑ ነገሮችን በውስጡ ይዞዋል።
ስለዚህ የታረደው እንስሳ ከሞተ በኃላ ደሙ በስጋው ውስጥ ከቆየ በውስጡ ካሉት ጎጂ ንጥረ
ነገሮች በተጨመሪ ለበሽታ አምጪ ጀርሞች መራቢያ ምቹ ይሆናል። ስለዚህ ደምንና በደም
የተነከረውን ስጋ መመገብ አደጋ ስላለው ደሙ ወደ ውጭ መፍሰሱ ስጋውን ንፁህና ጤናማ
ያደርጋል፡፡ [12] ነገር ግን ለእርድ የቀረበው እንስሳ አንገቱ ሙሉ ለሙሉ ተቆርጦ የሚነሳ
ከሆነ ደሙ ከእንስሳ ወደ ውጭ መፍሰሱን ያቆማል። በተጨማሪም የእንስሳው አከርካሪው
አጥንት (Spinal cord) የሚቆረጥ ከሆነ ፕሪኦን (Prion) የሚባል በሽታ ስለሚቀሰቅስ የስጋውን
ጥራት አደጋ ውስጥ ይከተዋል። [13]

ሳይንሳዊ እውነታ እንደሚያሳየው በኢስላማዊ የእንስሳ አስተራረድመሰረት የእንስሳው መተንፈሻ


ቱቦና የደም ጅማቱ አንድ ለይ ሲቆረጥ አንጎል ደም መቀበልን ያቆማል፡፡ነገር ግን የሰውን
አስተሳሰብንና ስሜቶችን የሚቆጣጠረው ሴሬብረም (Cerebrum) የሚባል የአንጎል ክፍል
በህይወት አለ። የእንስሳው አንገት ከኃላው ስላልተቆረጠ አሁንም ከእንስሳቱ የሰውነት ክፍሎች
ጋር የተቆራኘ ነው። ስለሆነም የነርቭ ስርዓቱ ወደ ሴሬብሬም (የአንጎል ፊተኛው ክፍል) ደም
ይላክ ዘንድ ወደ ልብ መልእክት ይልካል። ልብ ደግሞ መልእክቱን ተቀብሎ ደምን ወደ አንጎል
ሲገፋ የታረደው እንስሳ እንቅስቃሴ ያደርጋል ወይም ይፈራገጣል። ይህ የእንስሳው መፈራገጥ
በህመም ወይም በስቃይ ምክንያት ሳይሆን ደምን ወደ አንጎል የመግፋት እንቅስቃሴ ነው። ነገር
ግን ከልብ ወደ አንጎል የተላከው ደም የደም መተላለፊያው ቱቦ (የደም ጅማቱ) በመቆረጡ
ምክንያት አቅጣጫውን ስቶ በጠቅላላ ወደ ውጭ መፍሰስ ይጀምራል። ይህ አካሄድ ደሙ
በጠቅላላ ወደ ውጭ ፈሶ እንኪያልቅ ድረስ ይቀጥላል። እንስሳት በዚህ እስላማዊ ዘዴ
መታረዳቸው ደም ሙሉ በሙሉ ወደ ውጪ ስለሚፈስ ስጋው ጤናማና ጥራቱ ከየትኛው
የእንስሳ አስተራረድ ዘዴ የበለጠ የተጠበቀ ይሆናል። በተጨማሪም ኢስላማዊ የእንስሳ
አስተራረድ ዘዴ እንስሳዎችን ያሰቃየል የሚለው ሀሳብ ከንቱና ውሃ የማይቋጥር ገለባ ክስ ሆኖ
ተገኝቶዋል።በጥቅሉ ሳይንስ ከእስልምና የእንስሳ አስተራረድ ዘዴን ይደግፋል፡፡ [12]

በጀርመን አገር በሃኖቨር ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ባልሆኑ ጀርመናዊ ፕሮፌሰር እና በሙስሊም


ግብፃዊ ዶክተር አንድ የተካሄደ ሳይንሳዊ ጥናት ነበር። ጥናቱ የእስልምናን የእንስሳ አስተራረድ
ዘዴ ከምእራቡ አለም የእንስሳ አስተራረድ ዘዴ ጋር ለማነፃፀር የተደረገ ጥናት ነበር። ሰዎች
እስላማዊ እርስ ለእንስሳት ሰብዓዊነትም ጭምር የሚጠነቀቅ መሆኑን ጀርመናዊው ፕሮፌሰር
ሹልትዝ እና ግብፃዊው ዶ/ር ሀዚም በጀርመን ሀኖቨር ዩኒቨርሲቲ ኤሌክትሮኤንስፋሎግራም

15
(Electroencephalogram) ወይም (EEG) መሳሪያ በመጠቀም በጋራ በደረጉት ሳይንሳዊ
ምርመራ አረጋግጠዋል። ከምርምሩ የተገኘው ውጤትም እንደሚከተለው ነው። [12]

 እንስሳው በእስላማዊ አስተራረድ ዘዴ ከመታረዱ በፊት ያተመዘገው የEEG ምርመራ


ውጤትና ታርዶ ሶስት ሰከንድ ከቆየ በኃላ ያለው የEEG መሳሪያ ምርመራ ዉጤት
ተመሳሳይ ነው። ምክንያቱም በእስላማዊ እርድ መሰረት የእንስሳው የደም ጅማቱና
የመተንፈሻ ቱቦው ከተቆረጠ በኃላ ስቃይ ወይም የህመም ስሜት ስለማይሰማው ነው።
ለሚቀጥለው ሶስት ሰከንድ ደግሞ EEG እንስሳው ሙሉ በሙሉ ራሱን እንደሳተ
ዘግበዋል። ይህም የሆነው ደሙ ሙሉ በሙሉ ከእንስሳው ፈሶ በማለቁ ነው። ከ12
ሰከንድ በኃላ ደግሞ EEG የምርመራ መሳሪያ ዜሮ ውጤትን አሳየ። ይህ የሚያሳየው
ደግሞ በእስላማዊ እርድ መሰረት የተረደው እንስሳ በጭራሽ የህመም ስሜት
እንደማይታይበት ነው። ከተወሰኑ ሰከነዶች በኃላ የአንጎል መለኪያው (EEG) ዜሮ
ውጤት ቢያሳይም የልብ ምት ግን አሁንም አላቆመም፡፡ ይህ ደግሞ ከፍተኛ የሆነ ደም
ከታረደው እንስሳ ወደ ውጪ እንዲፈስ እገዛ ያደርጋል፡፡ በመጨረሻም ንፁህና ከደም
ጋር ንኪኪ ያሌለው ስጋ ይገኛል፡፡

 በምእራቡ ዓለም እንስሳው ለእርድ ሲቀርብ በመጀመሪያ ጭንቅላቱ ለዚሁ ዓላማ ተብሎ
በተዘጋጀ ማደንዘዣ መሳሪያ ይመታና ራሱን እንዲስት ይደረጋል።እንስሳው ራሱን ስቶ
ከወደቀ በኃላ ይታረዳል። በዚህ አይነት ዘዴ የታረደ እንስሳ ህመም እንደሚሰማው
የEEG ምርመራ ውጤት አሳይቷል። በተጨማሪም በምእራቡ ዓለም እንስሳ አስተራረድ
ዘዴ የታረደው እንስሳ በእስልምና መንገድ ከታረደው እንስሳ ጋር ሲነፃፀር የልብ ምቱ
ወዲያው ነውየቆመው፡፡ ይህ ደግሞ ደም ሙሉ በሙሉ ከእንስሳው ሰውነት እንዳይወጣና
ከስጋው ጋር ንኪኪ እንዲፈጥር ስለሚያደርግ የስጋውን ጥራት ይቀንሳል። ስለዚህ
በእስላማዊ መንገድ የታረደው እንስሳ ከምእራባዊያን እንስሳ አስተራረድ ዘዴ ጋር
ሲነፃፀር አንደኛ፣ የታረደው እንስሳ ህመም ወይም ከባድ ስቃይ አይሰማውም ሁለተኛ፣
ደሙ በጠቅላላ ወደ ውጪ ስለሚፈስ የስጋው ጥራት አስተማማኝኛ ከበሽታ አምጪ
ጀርሞችና ቆሻሻ ነገሮች የፀዳ ይሆናል፡፡
1.4 በተፋታች እና ባሏ በሞተባት ሴት

በእስልምና ውስጥ አንድ ባሏ የፈታት ሴት ሌላ ባል ከማግባቷ በፊት ቢያንስ ሶስት ወሮችን


ወይም ሶስት የወር አበባ ወቅቶችን መቆየት እንዳለባት ቅዱስ ቁርኣን በምእራፍ ሁለት አንቀጽ
228 ለይ ይገልፃል።

የተፈቱ ሴቶችም ነፍሶቻቸውን (ከማግባት) ሦስትን ቁርእ ይጠብቁ፡፡ በአላህና በመጨረሻውም


ቀን የሚያምኑ ቢኾኑ አላህ በማሕፀኖቻቸው ውስጥ የፈጠረውን ሊደብቁ ለነርሱ
አይፈቀድላቸውም፡፡ ባሎቻቸውም በዚህ ውስጥ እርቅን ቢፈልጉ በመማለሳቸው ተገቢዎች
ናቸው፡፡ ለእነርሱም (ለሴቶች) የዚያ በእነርሱ ላይ ያለባቸው (ግዳጅ) ብጤ በመልካም
አኑዋኑዋር (በባሎቻቸው ላይ መብት) አላቸው፡፡ ለወንዶችም (ጣጣቸውን ስለሚሸከሙ) በእነሱ
ላይ ብልጫ አላቸው፡፡ አላህም አሸናፊ ጥበበኛ ነው (2:228) ።

16
አንድ ቁርእ ማለት አንድ የወር አበባ ወቅት ማለት ሲሆን ሶስት ቁርእ ማለት ደግሞ ሶስት
የወር አበባ ወቅት ማለት ነው። ስለዚህ አንዲት የተፈታች ሴት ሌላ ባል ከማግባትዋ በፊት
ሶስት ቁርእ መጠበቅ አለባት ማለት ሶስት የወር አበባ ወቅቶችን ወይም በግምት ሶስት ወር
መቆየት አለባት ማለት ነው።

ገለሞታ (ባሏ የሞተባት ሴት) ደግሞ ሌላ ባል ከማግባቷ በፊት 4 ወር ከ10 ቀን መጠበቅ


እንዳለባት ቅዱስ ቁርኣን በምእራፍ ሁለት አንቀፅ 234 ለይ እንደሚከተለው ይናገራል።

እነዚያም ከናንተ ውስጥ የሚሞቱና ሚስቶችን የሚተዉ (ሚስቶቻቸው) በነፍሶቻቸው አራት


ወሮች ከዐስር (ቀናት ከጋብቻ) ይታገሱ፡፡ ጊዜያቸውንም በጨረሱ ጊዜ በነፍሶቻቸው በታወቀ
ሕግ በሠሩት ነገር በእናንተ ላይ ኃጢአት የለባችሁም፡፡ አላህም በምትሠሩት ሁሉ ውስጥ ዐዋቂ
ነው፡፡ (2:234)
ስለዚህ በእስልምና የተፈታች ሴት ሌላ ባል ከማግባቷ በፊት ሶስት ወር መቆየት ያለባት ሲሆን
እርጉዝ ከሆነች ደግሞ እስክወልድ ድረስ መጠበቅ አለባት።ባሏ የሞተባት ሴት ደግሞ ሌላ
ወንድ ከማግባቷ በፊት 4 ወር ከ10 ቀን መጠበቅ አለባት። ይህን በተመለከተ ሳይንስ አንዳች
ያለው ነገር ይኖር ይሆን? የዚህ እስላማዊ ድንጋጌዎች ሳይንሳዊ እንደምታቸው ምንድነው?

በባሏ የተፈተች ሴት ሌላ ወንድ ሳታገባ በፊት 3 የወር አበባ ወይም 3 ወር መጠበቅ ግዴታ
ይሆንባታል ምናልባትም አርግዛም ከሆነ እስክትወልድ መጠበቅ ይኖርባታል የሚለው
የእስልምና አስተምህሮ ከዘመኑ ሳይንሳዊ ግኝት ጋር ሙሉ ለሙሉ ተስማምቶ እናገኛለን።
ሳይንስ እንደሚነግረን ከሆነ የወንዱ ዘር ፍሬ 62% ፕሮቲን ያሉት ሲሆን እሱም እንደ ጣት
አሻራችን ከሰው ወደ ሰው ይለያያል። ይህ ነገር ደግሞ የእያንዳንዱን ሰው ኮድ ለመለየት
ይጠቅመናል ልክ ኮምፒውተር ውስጥ አንድን ነገር ለመለየት ኮድ እንድምንጠቀመው ማለት
ነው። አንዲት ሴት ከባሏ ጋር ተፋታ ወዲያውኑ ሌላ ካገበች ልክ ኮምፒዩተራችን ውስጥ ሌላ
ቨይረስ ገብቶ እንደሚያጠቃ ሁሉ የሷንም መህፀን በሌላ ቨይረስ እንዲጋለጥ ያደርጋታል። ይህ
ደግሞ አደገኛ ስለሆነ ላልተመጣጠነና ለተለያዩ በሽታ ያጋልጣታል። ይህ ሳይንስ ያረጋገጠው
ሀቅ ነው። ሳይንሳዊ እውነታዎች እንደሚያሳዩት ከፍቺ በኋላ ያለው የመጀመሪያ ወር አበባ
ከ32-35%፣የሁለተኛው ወር አበባ ከ67-72%፣እንዲሁም የ3ኛ ወር አበባ 99.9% የቀድሞ ባሏን
ዘር ፍሬ ከማህፀኗ ጠራርጎ ያስወጣል። ይህ አካሄድ የሴቷን መህፀን ከ3 ወር በኃላ ንፁህና
ጤናማ አድርጎ ያዘጋጃል። [14] [15]

ባሏ የሞተባት ሴት ይህን ኮድ (የባሏን ዘር ፍሬ) ለማስወገድ ተጨማሪ ጊዜ ያስፈልጋታል፡፡


ምክንያቱም ሀዘኑ ኮዱ ከማሕፀኗ ቶሎ እንዳይወጣ ስለሚያደርግ ነው፡፡ ለዚህም ነው ባሏ
የሞተባት ሴት አግብታ ከተፋታች የበለጠ ብዙ ጊዜ የምትቆየው፡ ፡[14] [15]

ብዙን ግዜ ከተለያዩ ወንዶች ጋር አንሶላ ሚጋፈፉ ሴቶች በማሕፀናቸው ውስጥ የተለያየ


የወንድ ዘር ፍሬ ስለሚቀላቀል በበሽታ የመጋለጥ እድላቸው በጣም ከፍተኛ ነው። በዚህም
ምክንያት የዘመኑ የፅንስ ሐኪሞች ሙስሊም ሴቶች ከሌሎች ሴቶች አንፃር በጣም ንፁህ ሴቶች
ናቸው ብለዋል። ከአላህ ትእዛዝ ወይም ድንጋጌ በስተጀርባ ትልቅ ጥበብ እንዳለ ከዚህ መረዳት
እንችላለን፡፡

17
የፅንስ ሀኪሞች በአሜሪካ የሚኖሩ የአፍሪካ ሙስሊም ሴቶች ለይ ጥናት አድርገው ነበር።
የጥናቱ ውጤት እንደሚያሳየው ሁሉም ሙስሊም ሴቶች የባሎቻቸውን ኮድ (የባሎቻቸውን ዘር
ፍሬ) ብቻ ነው በውስጣቸው የያዙት። በተቃራኒው ደግሞ ሙስሊም ያልሆኑ ሴቶች ለይ
የተደረገው ምርመራ ከሁለት እስከ ሶስት የሚደርሱ የተለያዩ የወንዶች ኮድ ሴቶች
እንደተሸከሙ ተረጋግጠዋል። ይህ ደግሞ ለተለያዩ በሽታ እንዲጋለጡ ያደርጋቸዋል። ከዚህም
በመነሳት ሴቶችን በንፅህና መያዝ የሚችለው ብቸኛው ሀይማኖት እስልምና መሆኑን
ተመራማሪዎች መገንዘብ ችለዋል [14] [15]::

1.5 ፂምን ማሰደግ/ማስረዘም በሳይንስ እይታ

ቅዱስ ቁርኣን በምእራፍ 3 አንቀፅ 31 ለይ እንዲህ ይላል።

በላቸው፡- «አላህን የምትወዱ እንደኾናችሁ ተከተሉኝ፤ አላህ ይወዳችኋልና፡፡ ኀጢኣቶቻችሁንም


ለናንተ ይምራልና፡፡ አላህም መሓሪ አዛኝ ነው፡፡» (3:31)
ይህ አንቀፅ አላህን እንወዳለን ብለን የምናስብ ከሆነ ነቢዩ መሐመድን (ሰ፣ዐ፣ወ) መከተል
እንዳለብን ይነግረናል። ነቢዩን መከተል ማለት እሳቸው አድርጉ ያሉትን ማድረግ፤ፈለጋቸውን
መከተል እንዲሁም ከከለከሉን ነገር ደግሞ መከልከል ማለት ነው።

ነቢዩ ከዘዙን መካከል አንዱ ፂማችንን እንድናሳድግ ነው። ኢማሙ ሙስሊም አቡሁረይራን
ጠቅሰው በዘገቡት ሀዲስ ውስጥ የአላህ መልእክተኛ (ሰ፣ዐ፣ወ) የሚከተለውን ተናግረዋል። ‹‹‹
ፂማቹን አሳድጉ ከዞራስትሪይንስ (እሳት አምላኪዎች) አትመሳሰሉ።››› አብዛኛውን ግዜ ፂም
ማሳደግ እንደ ሙስሊሞች መለያ ተደርጎ ይታሰባል። ምክንያቱም አብዛኛው ሙስሊሞች
ፂማቸውን ያሳድጋሉ ይንከባከባሉ። ለመንደርደሪያ ይሆን ዘንድ አንድ ምሳሌ ብቻ ተጠቀምን
እንጂ ነቢዩ (ሰ፣ዐ፣ወ) በበርካታ ንግግራቸው ፂምን ማሳደግ እንዳለብን ተናግሯል። በዚህም
ምክንያት ብዙሃኑ ሙስሊም ሊቃውንቶች ፂምን ማሳደግ እንጂ መቆረጥ ክልክል ነው ብለዋል።
በአሁን ግዜ ፂምን ማሳደግ እንደዋነኛ የሙስሊሞች መለያ ተደርጎ ይታያል። ምክንያቱም
ሙስሊሞች ናቸው በብዛት ፂማቸውን የሚያሳድጉትና የሚንከባከቡት። ይህን በማድረጋቸው
የአላህንና መልክተኛውን ውዴታ ያተርፋሉ። ትልቅ ምንዳንም ያገኛሉ። ይህ ነቢዩ (ሰ፣ዐ፣ወ)
ያዘዙት ተግባርና ሙስሊሞች አጥብቀው የያዙት ፂምን የማሳደግ ፈለግ (ሱና) በሳይንሳዊ
እይታ ሲቃኝ ምን ይመስላል? ፂም ማሳደግን ሳይንስ ያበረታታል ወይስ ያወግዛል? ምክንያቱስ
ምንድነው? በዚህ አምድ ይህንንናና የመሳሰሉትን ይዳሰሳሉ፡፡

ፂምን ማሳደግ የተለያዩ ሳይንሳዊ ጥቅሞች አሉት።ፂምን ከተለያዩ ጎጂ ኬሚካሎች ይከላከላል።


ፂም በሴሎች ለይ ጉዳት ሊያስከትሉ የሚችሉ መጨማደድን እና መጥፎ ቆዳ እንዲኖረን
ሊያደርጉ ከሚችሉ ብክለቶች ሁሉ ይከላከላል። ፂም መኖሩ ወንዶችን ወጣት ያደርጋቸዋል።
የሰውነት ቆዳችን የተፈጥሮውን እርጥበት ከመጠበቁም ባሻገር የቆዳችንን መጨማደድ
ይቀንሳል:: [16]

18
የፂም መኖር የወንዶችን ፊት ከካንሰር ይከላከላል። ቤዝል-ሴል ካንሲኖማስ (Basal-cell
carcinomas) የሚባል ከሁሉም የካንሰር አይነቶች የበለጠ ታዋቂ ካንሰር አለ። በዚህ ካንሰር
ከሚያዙት 5 ሰዎች መካከል 4ቱ ወንዶች ሲሆኑ ካንሰሩ የሚያጠቃው የወንዶችን ፊት፣
ጭንቅላትና አንገት ነው። በአሜሪካ በደቡብ ቂዊስላንድ ዩንቨርስቲ በተደረገው ሳይንሳዊ ምርምር
የፂም መኖር የዚህ ካንሰር አምጪ የሆነውንና ከፀሐይ የሚመነጨውን አልትራ ቫዮሌት ጨረር
(ultra violet rays) እስከ 95 በመቶ ድረስ ይከላከላል፡፡[17] [18] ይህ በጣም ትልቅ ጥቅም
ነው። ስለሆነም ፂም ወንዶችን የሚያጠቃውን ካንሰር ይከላከላል ማለት ነው። ህይወታችንን
ሊያሳጣ የሚችል ገዳይ በሽታን በፂማችን ከመከላከል የበለጠ ምን የተሻለ ነገር ይኖራል?

የዕፅዋት ሐኪሞች ባከናወኑት ሳይንሳዊ ምርምር ፂም የጉሮሮ በሽታዎችን እንደሚከላከል


አረጋግጠዋል፡፡ይህንን የፂም ጥቅም እንዳንድ የምእራባዊያን ዶክርተሮች ችምር ያውቁታል።
ሀኪሞች እንደሚናገሩት ፂም የምናሳድግ ከሆነ ወደፊት በጉሮሮ በሽታ የመያዝ እድላችን
ይቀንሳል። [16]

1.6 የአሳማ ስጋና ሳይንሳዊ እይታው

እስልምና አካላዊ፣መንፈሳዊ እና ስሜታዊ ደህንነትን ከግምት ውስጥ ያስገባ ሀይማኖት ነው። አምላካችን
አላህ ለዓላማ ነው የፈጠረን እናም የማንረጋጋበትና የማንተማመንበት ዓለም ለይ አልተወንም። በዚህ
ዓለምና በመጪው ዓለም የስኬት ባለቤት እንድሆን ዘንድ የመመሪያ መጽሐፍን፤ቁርኣን፤የነቢያት እና
መልእክተኞችን ምሳሌ ሰጠን። አንድ ሙስሊም አምላኩን በማምለክና ሕጎቹን ወይም ደንቦቹን ተግባራዊ
በማድረግ ህይወቱን ያሳልፋል ወይም ማሳለፍ ይጠበቅበታል። ከነዚህ ህጎች አንዱ የአሳማ ስጋ ወይም
የአሳማ ስጋ ምርቶችን ከመመገብ ሙሉ ለሙሉ መታቀብ ነው።

እስልምና መንፈሳዊ፤ስሜታዊና አካላዊ ጤንነትን እርስ በእርስ መገናኘትን የሚገነዘብ አጠቃላይ


ሃይማኖት ነው፡፡አንድ ሰው የሚበላውና የሚጠጣው በአጠቃላይ ጤና እና ደህንነት ላይ ቀጥተኛ ተጽዕኖ
አለው። አምላካችን አላህ የአሳማን ስጋ መመገብን እርም አድርጓል።ይህን አስመልክቶ ቅዱስ ቁርኣን
በምእራፍ ሁለት አንቀጽ 173 ለይ እንዲህ ይላል።

በናንተ ላይ እርም ያደረገው በክትንና ደምን፣ የእሪያ ሥጋንም፣ በእርሱም (ማረድ) ከአላህ ስም ሌላ
የተነሳበትን ነገር ብቻ ነው፡፡ሽፍታና ወሰን አላፊ ሳይኾን (ለመብላት) የተገደደ ሰውም በርሱ ላይ
ኃጢኣት የለበትም አላህ መሓሪ አዛኝ ነውና፡፡ (2:173)

አንድ አንድ ግዜ አላህ ነገሮችን ለምን እንዳዘዘ ወይም እንደከለከለ በጭራሽ ማወቅ ወይም መረዳት
ሊከብደን እንችላለን። ምክንያቱም አላህ ስላዘዘን ብቻ ከዛ ነገር እንታቀባለን። ይህ የመጀመሪያ ምክንያት
ሲሆን ለምን አላህ እንደከለከለን ለማወቅ ጥረትአድርገን ብንደርስበት ይህ እንደ ሁለተኛ ምክንያት
ይቆጠራል። ስለዚህ የአላህ ትእዛዝ እስከሆነ ድረስ ያለምንም ምርመራ ወይም ጥናት የአሳማን ስጋ
ከመመገብ እንቆጠባለን። ቅዱስ ቁርኣን በምእራፍ 33 አንቀጽ 36 አላህና የአላህ መልክተኛ በወሰኑት
ነገር ለይ ምንም አማራጭ እንዳሌለን ግልፅ አድርጎ ይነግረናል።

19
አላህና መልክተኛውም ነገርን በፈረዱ ጊዜ ለምእምናንና ለምእምናት ከነገራቸው ለእነርሱ ምርጫ
ሊኖራቸው አይገባም! የአላህንና የመልክተኛውንም ትእዛዝ የጣሰ ሰው ግልጽ የሆነን መሳሳት በእርግጥ
ተሳሳተ፡፡ (33:36)

አንድ ሙስሊም አማኝ አላህ እጅግ ጥበበኛና እጅግ ፍትሃዊ መሆኑን ይረዳል።ስለሆነም የእርሱ ህጎች
አካላዊ፣ስሜታዊ ወይም መንፈሳዊ ጥቅም እንዲኖራቸው ተደርገው የተቀየሱ ናቸው። ፈጣሪ ለፍጥረኑ
የተሻለውን መንገድ ያውቃል። መልካም በሆኑት ነገሮች እንድንደሰት የፈቀደልን ሲሆን በተቃራኒው
ደግሞ በእምነታችን፣በጤንነታችንና በስነ ምግባር ግን ለይ ጉዳት ሊያስከትሉ ከሚችሉ ነገሮች ደግሞ
ይከለክለናል። በዚህም ምክንያት ሙስሊሞች የተከለከሉትን ነገሮች መብላት የሚያስከትለውን አደጋ
ጠንቅቀው ስለሚያውቁ ይከለከላሉ። ከፍተኛ ወጪ የሚጠይቅ ቢሆንም እንኳ የተፈቀደን ምግብን
ለማግኘት ከፍተኛ ጥረት ያደርጋሉ።

አንድ ሙስሊም አማኝ ባለማወቅ ወይም በስህተት የአሳማን ስጋ ከበላ በሱ ለይ ምንም ኃጢያት
የለበትም። አላህ በስህተት ወይም በመርሳት በምናደርገው ነገር አይቀጠንም። ሆኖም ግን እያወቀ
የአሳማን ስጋ ወይም የአሳማ ምርቶች የሆኑ ምግቦችና መጠጥ ወይም ደግሞ መድሃኒቶችን መጠቀም
አይፈቀድለትም። ጥርጣሬ ካደረበት የሚያቁትን ሰዎች መጠየቅ ጥረት ማድረግ አለበት።

በአሁን ጊዜ የአሳማ ስጋንና የአሳማ ስጋ ምርቶችን መጠቀም ጤናችን ለይ ጉዳት ሊያመጣ እንደሚችል
ሳይንሳዊ ግኝቶች በሰፊው ያትታሉ። ከዓመታት በፊት በሜክሲኮና በሰሜን አሜሪካ የተከሰተው የአሳማ
ጉንፋን ምክንያት አሳማ ሰው ለይ ጉዳት የሚያደርሱ ጥገኛ ነፍሳትን (parasites) እንደሚይዙ
ታውቆዋል፡፡

የቫይረስ አጥኚዎች (ቫይሮሎጂስቶች) አሳማ ለኢንፍሉዌንዛ ተስማሚ የመራቢያ ቦታ መሆኑን ከረጅም


ጊዜ ጀምሮ ያውቃሉ። የበሽታ መከላከያ ባለሙያ የሆኑት ዶ/ር ግራሃም በርጌስ እንደሚገልጹት
በተለምዶ በዶሮ ውስጥና በሰው ልጆች ውስጥ የሚያድጉ ቫይረሶች በአሳማ ውስጥ ጭምር ይራባሉ።
ስለዚህ አሳማ ለተለያዩ ለበሽታ አምጪ ቫይረሶች ዋነኛ የመራቢያ ቦታ ነው ቢባል ማጋነን አይሆንም።

እሳማዎች የገኙትን ሁሉ የሚበሉ (omnivorous) እንስሳ ናቸው። እፅዋትንም እንስሳትንም ይበላሉ።


የሞቱ ነፍሳትን፣ትሎችን፣የዛፍ ቅርፊትን፣የበሰበሱ ሬሳዎችን፣ቆሻሻዎችንና ሌሎችንም ነገሮች
ይመገባሉ። አሳማዎች በጣም ጥቂት የላብ እጢዎች ስላላቸው ከሰውነታቸው መርዛማ ነገሮችን ሙሉ
በሙሉ ማስወገድ አይችሉም። አዳዲስ የጥናት ግኝቶች እንደሚያመለክቱት አሳማን ማርባት ለተለያዩ
በሽታ አምጪ ባክቴሪያና ኢንፌክሺኖች መስፋፋት ምክንያት ነው።

አሳማዎች ብዙውን ጊዜ የሚኖሩት በአነስተኛ ክፍተቶች ውስጥ ሲሆን ፀረ-ባክቴሪያ መድሃኒትን


የሚቋቋሙ አደገኛ ባክቴሪያዎችን ይሸከማሉ። ይህ መድሃኒት ተከላካይ ባክቴሪያ በአሜሪካ ትልቅ ጉዳት
ያመጣ ሲሆን የቅርብ ጊዜ ምርመራዎች እንደሚያመለክቱት በአሜሪካ 49% የሚሆኑ አሳማዎችና 45%
የሆኑ የአሳማ ሰራተኞች ይህን አደገኛ ባክቴክሪያ በመያዛቸው ምክንያት በየአመቱ ለ18,000 ሰው ሞት
ተጠያቂ ሆኖዋል፡፡[19]

ሙስሊሞች አላህ ስለከለከላቸው የአሳማን ስጋ ከመብላት ይታቀባሉ። በአሳማ አካልና አኗኗር ዙሪያ
በተደረገውም ሳይንሳዊ ጥናት አሳማ እርኩስ በመሆኑ ምክንያት ስጋውን መመገብ የጤና ችግርን
እንደሚያስከትል ተረጋግጠዋል።

20
ምእራፍ ሁለት
ቅዱስ ቁርኣንና ሳይንስ
2.1. ስነ-ፅንስ እና ስነ-አካል
2.1.1 የፅንስ ፆታ

እስከ ቅርብ ግዜ ድረስ የፅንስ ፆታ የሚወሰነው በእናት ሴሎች ነው ተብሎ ይታሰብ ነበር። ይህ
ማለት የፅንስ ፆታ መወሰኛ ውስጥ ጉልህ ሚና የምትጫወተው ሴት ናት ተብሎ ይታሰብ
ነበር፡፡[20] በህንድ አገር ወላጆች ከሴት ልጅ ይልቅ ወንድ ልጅ እንዲኖራቸው ይፈልጋሉ፡፡
በዚህም የተነሳ በርካታ ጥንዶች ወንድ ልጅ ለማግኘት ሲሉ መውለዳቸውን ይቀጥላሉ፡፡
ያልተፈለጉ ሴት ልጆች ሲወለዱ እናት የወቀሳ ውርጂብኝ ታስተናግዳላች ምክንያቱም ሴት
የፅንስን ፆታ የመወሰን ጉልህ ድርሻ አላት ተብላ ስለሚታሰብ ነው።[21] የወንዱና የሴቷ
ሴሎች በአንድነት የፅንስን ፆታ ይወስናሉ የሚሉም ሰዎችም አሉ።[20] ቅዱስ ቁርኣን ግን
የፅንስን ፆታ መወሰኛ አስመልከቶ ለየት ዘገባ በምእራፍ 53 ከአንቀጽ 45 እስከ 46 ለይ
አስፍሯል።

እርሱም ሁለቱን ዓይነቶች ወንድንና ሴትን ፈጠረ (53:45)

ከፍትወት ጠብታ (በማህጸን ውስጥ) በምትፈሰስ ጊዜ (53:46)


ሁለቱ የቁርኣን አንቀፆች ወንድና ሴትን ከፍትወት ጠብታ (Drop of Semen) መፈጠራቸውን
ያሳያሉ፡፡ በሌላ አገላለፅ የፅንስ ፆታ (ማለትም ወንድነትና ሴትነት) የሚወሰነው በወንዱ የዘር
ፈሳሽ ጠብታ መሆኑን ቅዱስ ቁርኣን ምእራፍ 53 ከአንቀፅ 45 እስከ 46 ለይ በማያሻማ
አገላለፅ አስፍሮታል። ስለዚህ በእናት መህፀን ውስጥ የሚፈጠረውን ሽል ፆታውን በመወሰን
ረገድ ዋናውን ሚና የሚጫወተው የወንዱ የዘር ፈሳሽ እንጂ የሴት እንቁላል አይደለም፡፡ ይህ
አስገራሚና የጥንቱን ኃላ ቀር አስተሳሰብ የሻረ የቁርኣን ገላፃ በ20ኛው ክፍለ ዘመን በዘመናዊ
ሳይንስም ጭምር ተረጋግጧል።

በ20ኛው ክፍለ ዘመን ከሳይንስና ቴክኖሎጂ እድገት ጋር ተያይዞ ጄኔቲክስ (Genetics) እና


ሞልክዩላር ባዮሎጂ (Molecular biology) የሚባሉ አዳዲስ የትምህርት መስኮች ከዓለም ጋር
ተዋወቁ። በዚህም ምክንያት የበፊቶቹ ፅንሰ ሀሳቦች ውድቅ ሆኑና ከቁርኣን ገለፃ ጋር
የሚስማሙ ግንችቶች ብቅአሉ። አዲሱና በሳይንስ ሊቃውንት ተፈትሾ የተረጋገጠው የሳይንስና
ቴክኖሎጂ ግንኝት እንደሚከተለው ይቀርባል፡፡

የሚወለደው ህፃን ፆታ ማለትም ሴት ይሁን ወንድ የሚመሰረተው ባለ 23 ጥንድ ክሮሞዞም


(Chromosomes) ከሆኑ የእናትን ባህሪ ከሚይዘው እንቁላልና ባለ 23 ጥንድ ክሮሞዞም
(Chromosomes) የአባትን ባህሪ ከሚይዘው የወንድ ዘር ሆኖ ሴቷ XX በሚል ሲገለፅ የወንዱ
ደግሞ በXY ይገለፃል፡፡ በመጀመሪ ደረጃ ፆታ የሚለየው ልክ እንደተፀነሰ ሲሆን የሴቷን እቁላል

21
የሚያፀንሰው በወንዴ ዘር ፈሳሽ ውስጥ ባለው ክሮሞዞም (Chromosomes) በሚባል ኬሚካል
ይወሰናል፡፡ ከለይ እንደተገለፀው የወንዴው XY ሲሆን የሴቷ XX ተብሎ ሊገለጽ በሚችል ነው
ዘር የተሰራው፡፡ የወንዴው ዘርና የሴቷ ዘር ሲገናኙ በመጀመሪያ ደረጃ ህዋሶቹ ይለያያሉ XY
የነበረው የወንዴው ዘር X እና Y ይሆናል XX የነበረው የሴቷ ዘር X እና Y ይሆናል፡፡ Y
ተባእታይ (masculine) ባህሪ ሲኖረው X ደግሞ እንስታይ (feminine) ባህሪ ይኖረዋል። ይህ
ማለት የወንዴው ዘር X እና Yን በውስጡ የያዘ ሲሆን የሴቷ ደግሞ Xን ብቻ ነው በውስጡ
የያዘው፡፡ በዚህም መሰረት ፅንስ የሚፈጠረው X ከሚባለው የወንዴ ዘር ከሆነ ከሴቷ X ብቻ
ስለሚመታ ‹‹ XX ›› ይሆናል ማለት ነው፡፡ ይህ ማለት ህፃኗ ሴት ሆና ተወለዳላች ማለት
ነው፡፡ ነገር ግን ከወንዴው Y ከመጣ ከሴት X ብቻ ስለሚመጣ ‹‹ XY ›› ይሆናል ማለትም
የፅንሱ ፆታ ወንድ የሆናል፡፡ ስለዚህ የወንድ ዘር ፍሬ የፅንሱን ፆታ የሚወስን ሲሆን የሴቷ
በዚህ ረገድ ምንም ድርሻ የለውም። [20] [21] ይህ ሳይንሳዊ መረጃ ወንድና ሴትን
ከፍትወት ጠብታ(ከወንዱ ዘር ፍሬ) ፈጠረ ከሚለው የቁረኣን አንቀፅ ጋር በትክክል ገጥሞ
እናገኛለን፡፡ ዛሬ ለይ በ20ኛው ክፍለ ዘመን ሳይንስ የደረሰበትን የፅንስ ፆታ መረጃ ከ1400
ለነቢዩ ሙሐመድ (ሰ፣ዐ፣ወ) በቅዱስ ቁርኣን ውስጥ ማን ነገራቸው?

በተለምዶ በህንድ አገር ውስጥ አማት የልጅ ልጇ ወንድ እንዲሆንላት ጥልቅ የሆነ ፍለጐት
አላት እናም የተወለደው ልጅ የምትፈለገውን አይነት ፆታ ከሌለው ምክንያቷ ምራቷ /የልጇ
ሚስት/ነች በማለት ትወቅሳለች፡፡ የሚወለደው ፆታን በተመለከተ ወሳኙ የወንድ የዘር ፈሳሽ
እንጂ የሴት እንቁላል አለመሆኑን ቢያውቁና መውቀስ አለብን ብለው የሚያምኑ ከሆነ
ምራታቸውን ሳይሆን እራሱ ልጃቸውን ተጠያቂ ማድረግ ነበረባቸው ምክንያቱም በቁርአንም
ይሁን በሳይንስ ለሚወለደው ህፃን ፆታ ወሳኙ የወንድ የዘር ፈሳሽ እንጂ የሴቷ አይደለም፡፡
በነገራችን ላይ አንድ ሙስሉም የወንድ የዘር ፈሳሽ ለፆታው ማንነት ትልቁን ሚና ቢጫወትም
ባልየው (ወንድ) የፈለገውን ጾታ ሳይሆን አላህ (ሱ.ወ) የወሰነው እንደሚሆን ሊያምን
ይገባል፡፡[21]

2.1.2 የሰው ልጅ ከጥቂት የዘር ፈሳሽ ጠብታ ስለመፈጠሩ

በግንኙነት ወቅት ወንድ ወደ 250 ሚሊየን የሚጠጋ ዘር ፍሬ ነው የሚያፈሰው። የወንዱ ዘር


ፍሬ ወደ ሴቷ እንቁላል ጋር እስኪደርሱ ድረስ አድካሚ ጉዞ ያደርጋሉ። ሆኖም ግን ወደ
መህፀን ከሚደረገው አድካሚ ጉዞ በኋላ ከሴቷ እንቁላል ጋር ሊደርሱ የሚችሉት ወደ አንድ ሺ
የሚጠጉት የዘር ፍሬዎች ብቻ ናቸው። የተቀሩት አብዛኛዎቹ በመንገድ ለይ ሞተው የሚቀሩ
ናቸው። በመጨረሻዎቹ የአምስት ደቂቃ ሩጫ በኃላ ከአንድ ሺው መካከል ከሴቷ እንቁላል ጋር
የሚወሀደው አንድ የዘር ፍሬ ብቻ ነው። ይህ የሚነግረን በማህፀን ውስጥ ፅንሱ (የሰው ልጅ)
የሚፈጠረው በግንኙነት ወቅት በሚፈሰው በሁሉም የዘር ፍሬ ሳይሆን በጥቂቱ ብቻ እንደሆነ
ነው። ይህን እውነታ ዓለም ባልሰለጠነበት ወቅት ቅዱስ ቁርኣን ከሳይንስ ቀድሞ አስፍሮዋል።
ቁርኣን በምእራፍ 75 ከአንቀጽ 36 እስከ 37 ለይ እንዲህ ይላል።

ሰው ስድ ኾኖ መትተውን ይጠረጥራልን? (75፡36)

22
የሚፈሰስ ከኾነ የፍትወት ጠብታ አልነበረምን? (75:37)
እዚጋ የተፈለገው ‹‹ ከፍትወት ጠብታ›› (From a drop of semen) የሚል ነው። ፅንሱ
የሚፈጠረው ከጠብታው ወይም ከጥቂት ዘር ፈሳሽ እንደሆነ ያሳያል። [20]

2.1.3 የሰው ልጅ አንጎል በቁርኣንና በሳይንስ

ለብዙ ክፍለ ዘመናት የሰው አንጎል የፊተኛው ክፍል ከአይን አጠገብ ስለሆነ ብቻ የዓይናችንን
ሁኔታ ይቆጣጠራል ተብሎ ይታሰብ ነበር። ሆኖም ግን ይህ አሰተሳሰብ ከእውነታው ጋር አብሮ
ሊሄድ አልቻለም፡፡ እንደውም የዘመኑ ሳይንስ የደረሰበት እውነታ ከጥንቱ ሀሳብ ጋር የሚቃረን
ሆኖ ተገኝቶዋል። ዛሬ ለይ የፊተኛው የአንጎል ክፍል ዓይናችንን ሳይሆን ንግግራችንን
እንደሚቆጣጠር ታውቆዋል።የዓይናችንን ዕይታ የሚቆጣጠረው የአንጎል ክፍል ደግሞ
የአንጎላችን የጀርባው ክፍል ነው። ቅዱስ ቁርኣን ምእራፍ 96 ከአንቀጽ 15 እስከ 16 እንዲህ
ይላል። [22]

ይተው ባይከለከል አናቱን ይዘን እንጎትተዋለን (96:15) ፡፡

ውሸታም ስሕተተኛ የኾነችውን አናቱን (96:16) ፡፡


ሁለቱ አንቀጾች የሚገኙት ነቢዩ ሙሐመድ (ሰ፣ዐ፣ወ) ለይ ከወረደው የመጀመሪያ ምእራፍ
ውስጥ ነው። እነዚህ ሀለቱ አንቀፆች ማለትም (96:15) እና (96:16) የወረዱት መካ ውስጥ
አንድ አቡጃህል የሚባል የሙስሊሞች ቀንደኛ ጠላት ነቢዩ (ሰ፣ዐ፣ወ) ለይ ጥቃት ለማድረስ
ሙከራ በማድረጉ ነው። በዚህ ምክንያት አምላካችን አላህ ሰውየው (አቡጃህል) ከድርጊቱ
ባይከለከል ውሸታምና ስህተተኛ የሆነችውን አናቱን ይዘን እንጎትተዋለን በማለት አንቀጾቹን
አወረደ።

አናት ማለት የአንጎላችን የፊተኛው ክፍል (Frontal part of brain, forelock) ነው። ቁርኣን
96፡16 ለይ ‹‹‹ ውሸታም ስሕተተኛ የኾነችውን አናቱን ››› ሲል አናት ከውሸትና ስህተት ጋር
እንዴት ተገናኙ ብለን ጥያቄ ልናስነሳ እንችላለን፡፡

አንጎል የተለያዩ ክፍሎች ያሉት ሲሆን ከዚህም መካከል አንዱ ግንባር ወይም አናት የሚባለው
የአንጎል የፊተኛው ክፍል ነው፡፡ ይህ የአንጎል የፊተኛው ክፍል ግባችንን ለማሳካት የምናስበውን
ሀሳብ ወይም ድርጊቶችን ይወስናል እንዲሁም ይቆጣጠራል፡፡እቅድ፣ችግርን መፍታትና
የእውቀት ሂደቶች በጠቅላላ በዚህ የአንጎል ከፍል ቁጥጥር ስር ናቸው፡፡ በተጨማሪ የውሸት
ንግግርን ጨምሮ ሁሉም የማታለያ ሂደቶች በዚህ የአንጎል ከፍል ውስጥ የሚወሰኑ ናቸው፡፡
ከለይ የተገለፁት የቁርኣን አንቀፆችም ልክ እንደ ዘመናዊ ሳይንስ አናት (ግንባር) ወይም
የአንጎል የፊተኛው ክፍል (frontal part of brain) ውሸትንና ሀጢያትን እንደሚቆጣጠር
ይናገራሉ፡፡[23]

23
ለአንድ ሰው የውሸት ንግግርና ሀጢያት ትልቁን ሚና የሚጫወተው አናት ወይም ደግሞ
ግንባር የሚባል የአንጎል የፊተኛው ክፍል ነው። Essentials of Anatomy and Physiology
የሚባል በርካታ የቅርብ ሳይንሳዊ ጥናትን ያካተተ መፅሐፍ ለይ እንደተመለከተው የፊተኛው
የአንጎላችን ክፍል ለተነሳሽነትና ለጠበኝነት መንስኤ ከሆነ በእርግጥም ውሸትንና ኃጢያትን
ያስከትላል ምክንያቱም አነዚህ ውጤቶች በቀላሉ የተነሻሽነትና የጠበኝነት ውጤቶች ናቸው።
ሳይንስ የፊተኛው የአንጎል ክፍል (አናት) ለውሸትና ኃጢያት መንስኤ መሆኑን ከዛሬ 60
ዓመት በፊት ቢነግረንም ቅዱስ ቁርኣን ግን 1400 ዓመት በፊት ሁሉንም ቀድሞ አለም
ባልሰለጠነበት ወቅት ግንባር/አናት/ የፊተኛው የአንጎል ክፍል ለውሸት ንግግርና ለኃጢያት
መንስኤ ቦታ መሆኑን ተናግሮዋል።[24]

2.2 እንስሳት
2.2.1 ንብ በቁርኣንና በሳይንስ

የማር ንብ ከሌሎች እንስሳት በተሻለ በቅዱስ ቁርኣን ውስጥ ተጠቅሶዋል። በቅዱስ ቁርኣን
ውስጥ ከተጠቀሱት ነፍሳቶች አሉ ሆኖም ግን የንብን ያህል ላቅ ያለ ሚና አይጫወቱም።
በቁርኣን ውስጥ በሁለት ተከታታይ አንቀጾች ውስጥ የተጠቀሰው ብቻኛው እንስሳ ንብ ነው።
የቁርኣን 16ኛው ምእራፍ በስሙ የንብ ምእራፍ ተብሎ ነው የተሰየመው። እዚህ ጋር አንድ
አስደናቂ ነገር መመልከት እንችላለን። በሳይንስ በጥብቅ እንደተረጋገጠው በሁሉም የንብ
ዝርያዎች ውስጥ ወንድ ንብ 16 ነጠላ ክሮሞዞም (Chromosomes) ሲኖሮው ሴቷ ንብ ደግሞ
16 ጥንድ ክሮሞዞም (Chromosomes) አላት። በተጨማሪም ንግስቷ ንብ እንቁላሉን ሰብራ
የምትወጣው በ16 ቀናተ ውስጥ ነው። በዚሁ የንብ ምእራፍ ውስጥ ‹‹ ንብ››የሚል ቃል
በብቸኝነት የተጠቀሰው በ68ኛው አንቀፅ ውስጥ (16:68) ነው። በዚህ አንቀፅ ውስጥ
ከመጀመሪያው ፊደል ጀምሮ ንብ የሚል ቃል እስካለበት ድረስ 16 ፊደላት አሉ። ይህ ብቻ
አይደለም ‹‹ንብ›› የሚል ቃል ያለበት ብቸኛው አንቀፅ (16:68) ከ16 የተላያዩ የአረብኛ ፊደሎች
ነው የተገነባው።[25] ከለይ የተብራራውን ጠቅለል ስናደርገው ይህን ይመስላል።

የንብ ምእራፍ መረጃ

 የቅዱስ ቁርኣን የንብ ምእራፍ ቁጥር 16 ነው፡፡


 ‹‹ንብ›› የሚል ቃል ያለበት ብቸኛው አንቀፅ (16:68) የተገነባው ከ16 የተለያዩ ፊደላት
ነው፡፡
 ‹‹ንብ›› የሚል ቃል ያለበት ብቸኛው አንቀፅ ማለትም ቁርኣን (16:68) 16 ቃላት
አሉት፡፡[26]
 ‹‹ንብ›› የሚል ቃል ያለበት ብቸኛው አንቀፅ ወይም ቁርኣን (16:68) ውስጥ
ከመጀመሪያው ፊደል ጀምሮ ንብ አስከሚለው ቃልን ጨምሮ አጠቃላይ 16 የአረብኛ
ፊደላት አሉ፡፡
ሳይንሳዊ መረጃ

 በሁሉም የንብ ዝርያ ውስጥ የወንድ ንብ ክሮሞዞም (Chromosome) ብዛት 16 ነው፡፡


 በሁሉም የንብ ዝርያዎች ውስጥ የሴት ንብ ክሮሞዞም ብዛት 16 ጥንድ ነው፡፡

24
 ንግስቷ ንብ እንቁላል ሰብራ ንብ ሆና የምትወጣው 16 ቀን ውስጥ ነው።

የሳይንሱ መረጃ ከቁርኣኑ ጋር እንዴት ሊመሳሰል ቻለ? ይህ ሁሉ መመሳሰል በዘፈቀደ ነው?


እንዴት ከ1400 ዓመት በፊት አለም ባልሰለጠነበት ግዜ በአረቢያ ምድረበዳ የኖረ የማያነብ
የማይፅፍ ሰው (አለይሂሰላቱ ወሰላም) የንብ ምእራፍን ከዘመኑ የንብ እውነታ ጋር እንዲሄድ
ወይም እንዲዛመድ አድርጎ ሊያቀናብር ይችላል? ይህ ሁሉንም ነገር ከሚያውቀው ከፈጣሪ
አላህ ውጪ በማንም ሊቀናበር አይችልም።

ንቦች በሶስት ይከፈላሉ እነሱም ወንዱ ንብ፣ሰረተኛ ንብና ንግስቷ ንብ ናቸው። ወንዱ ንብ 16
ነጠላ ክሮሞሶም ሲኖረው ሴቷ ንብ ደግሞ 16 ጥንድ ክሮሞሶም ይኖራታል። ወንዱ ንብ ስራው
ከንግስቷ ጋር ግንኙነት ከማድረግ ውጭ ሌላ ስራ የለውም። በጥንት ዘመን በተለይም
በሼኪስፒር ዘመን ሰራተኛ ንቦች ወንድ ንቦች ሲሆኑ የሚተዳደሩት ደግሞ በወንዱ ንጉስ ንብ
ነው ተብሎ ይታሰብ ነበር፡፡ ሆኖም ግን ከዚህ በፊት የነበሩ መላምቶች እውነት እንዳልሆኑ
ታወቁ፡፡ ከ300 ዓመታት በፊት በንቦች ለይ በተደረገው ዘመናዊ ምርመራ ትክክለኛው መረጃ
ይፋ ሆነ፡፡ በዚህም መሰረት ሰራተኛ ንቦች ሁሉም ሴት ንቦች ሲሆኑ ስራቸው ደግሞ ቀፎ
ማዘጋጀት፤ የአበባ ዱቄትን መሰብሰብና በሱም ማርን መስራት ነው። ንቦች የሚተዳደሩት
በንጉስ ንብ ሳይሆን በንግሰቷ ንብ እንደሆነም ጭምር በዘመናዊ ሳይንስ ተደረሰበት፡፡ ስለዚህ
ሁሉም ሰራተኛ ንቦች ሴት ንቦች ናቸው ማለት ነው። ይህ ዓለም በቅርቡ የደረሰበት መረጃ
መሆኑ ምንም ጥርጥር የለውም። ከ1400 ዓመት በፊት ወንዱ ንብ እና ሴቷ ንብ ተለይተው
በማይታወቁበት ጊዜ በቅዱስ ቁርኣን በሚያስደምም ሁኔታ ልክ እንደ ዘመኑ ሳይንስ ሰረተኛ ንብ
ሴት ንብ እንደሆነች ተገልጾዋል፡፡[21]

ጌታህም ወደ ንብ እንዲህ ሲል አስታወቀ «ከተራራዎች፣ ከዛፍም፣ (ሰዎች) ከሚሠሩትም (ቀፎ)


ቤቶችን ያዢ (16:68) ፡፡

«ከዚያም ከፍሬዎች ሁሉ ብይ፡፡ የጌታሽንም መንገዶች (ላንቺ) የተገሩ ሲኾኑ ግቢ፡፡» ከሆዶችዋ
መልኮቹ የተለያዩ መጠጥ ይወጣል፡፡ በእርሱ ውስጥ ለሰዎች መድኃኒት አለበት፡፡ በዚህ ውስጥ
ለሚያስተነትኑ ሕዝቦች በእርግጥ ተዓምር አልለበት (16:69) ፡፡
(ቁርኣን 16: 68-69) ያዢ፣ብዪ፣ግቢ፣የሚሉ ቃሎችን እናገኛለን።እነዚህ ቃሎች ከሴቷ ንብ ጋር
ነው የሚሄዱት። በሌላ አገላለፅ (ቁርኣን 16፡68 - 69) ስለ ንብ በሚተርክበት ግዜ የሴትን ፆታ
(feminine gender) ነው የተጠቀመው። ያዢ፣ ብዪ፣ ግቢ ተብለው የተጠቀሱ ግሶች የሴትን
ፆታ አመልካች ናቸው። ስለዚህ ከተራራዎች፤ከዛፎችም፤ሰዎች ከሚሰሩትም ቤትን ወይም ቀፎን
ይዛ አበባዎችን በመሰብሰብ ማርን የምትሰራው ሰረተኛዋ ሴት ንብ ናት፡፡ ቁርኣን ውስጥ
የተጠቀሱት የሴቷ ንብ ስራዎች የሚከተለት ናቸው።
1. ቀፎ መገንባት (16:68)

25
2. አበባን መሰብሰብ (16:69)
3. ማር ማዘጋጀት (16:69) [27]
የማር ንብ አካል በሶስት ይከፈላል እነሱም ራስ፣ደረትና ሆድ ናቸው። ቁርኣን (16:69) ውስጥ
‹‹‹ሆዶችዋ››› የሚል ቃል እናገኛለን። ‹‹‹ሆዶችዋ››› ተብሎ የተተረጎመው የአረቢኛ ቃል
‹‹‹ቡጡኒሃ››› የሚል ሲሆን ከቃሉ መጨረሻ ለይ የመጣችው ‹‹‹ሃ›››ነጠላ ሴት ንብን (singular
female bee) የምታመለክት ናት። የብዙ ሴት ንቦችን ሆድ ለማመልከት ቢሆን ኖሮ ቁርኣን
16:69 በ ‹‹‹ሃ››› ፊደል ፋንታ‹‹‹ሁነ››› የሚለውን ቅጥያ ይጠቀምና ‹‹‹ ቡጡኒሁነ››› የሚል
ቃል ይኖረው ነበር። ‹‹‹ ቡጡኒሁነ ›››ማለት ‹‹‹ ሆዳቸው ›››እንደማለት ሲሆን ‹‹‹ የብዙ ሴት
ንቦችን ››› ሆድ ያመለክታል። ቁርኣን 16:69 ግን ሆድን ለመግለፅ የተጠቀመው የአረቢኛ ቃል
‹‹‹ቡጡኒሃ››› የሚል ሲሆን ትርጉሙም ሆዶችዋ ወይም ደግሞ ‹‹‹ የሴቷ ንብ ብዙ ሆድ ›››፡፡
በሌላ አገላለፅ ቅዱስ ቁርኣን ማር የምታዘጋጀው ሴቷ ንብ ከአንድ በለይ ሆድ አላት እያለን
ነው። ይህ እንዴት ሊሆን ይችላል? ይህ የገሀዱን አለም እውነታ ይፃረራል ወይስ አይፃረርም?
በጭራሽ አይፃረርም ምክንያቱም ማር የምታዘጋጀው ሴቷ ንብ የምትበለውን ምግብ
ከምትፈጭበት ሆድ በተጨማሪ ሌላ ማር የምታዘጋጅበት ሆድ እንዳላት ፀሓይ የሞቀው
እውነት ነው። [27]

የማር መድሃኒትነት

በቅዱስ ቁርኣን ውስጥ ‹‹‹መድሃኒት››› ወይም ደግሞ በአረብኛ ‹‹‹‹ (ሺፋኡን) ››››
የሚለው ቃል አገልግሎት ለይ የዋለው ለሁለት ነገሮች ሲሆን እሱም ለቁርኣንና ማር ነው።
[28] ማር ለምግብም ሆነ ለመድሃኒትናት ካለው ጥቅም አንፃር ‹‹ፈሳሽ ወርቅ›› ተብሎ እስከ
መጠራትም ደርሶዋል፡፡ በዘመናዊ ሳይንስ ማር ለበረካታ ጤና እክሎች ፍቱን መድሃኒት
እንደሆነ ቢታወቅም ከብዙ ዓመታት በፊት በቅዱስ ቁርኣን ከንብ ሆድ የሚወጣው ማር ለሰው
ልጅ መድሀኒት እንደሆነ ተገልጾዋል፡፡

«ከዚያም ከፍሬዎች ሁሉ ብይ፡፡ የጌታሽንም መንገዶች (ላንቺ) የተገሩ ሲኾኑ ግቢ፡፡» ከሆዶችዋ
መልኮቹ የተለያዩ መጠጥ ይወጣል፡፡ በእርሱ ውስጥ ለሰዎች መድኃኒት አለበት፡፡ በዚህ ውስጥ
ለሚያስተነትኑ ሕዝቦች በእርግጥ ተዓምር አልለበት (16:69) ፡፡
ማር ከስኳር የበለጠ ጣፋጭ ሲሆን ለየት ያለ የኬሚካል ባህሪዎች አሉት፡፡ ማር ልዩ ጣእም
ስላለው አንዳንድ ሰዎች ከስኳርና ከሌሎች ጣፋጮች የበለጠ ይመርጡታል፡፡ ከፍተኛ የሆነ
የስኳር ክምችት ስላለው ባክቴሪያዎችን የመግደል አቅም አለው፡፡ የእርጥበት መጠኑ በጣም
ዝቅተኛ ስለሆነ ማንኛውም ዓይነት ፍጡር በውስጡ ሊራባ አይችልም፡፡ የተፈጥሮ የሆነ ጥሬ
ማር የእርጥበት መጠኑ በጣም ዝቅተኛ የሚባል ሲሆን ከ14% እስከ 18% ድረስ ነው፡፡
ስለሆነም ማንኛውም ዓይነት ፍጡር በውስጡ ሊራባ አይችልም፡፡ ተፈጥሯዊ የአየር ወለድ

26
እርሾዎችም (Natural Air Born Yeasts) የማር እርጥበት መጠኑ በጣም ዝቅተኛ ስለሆነ በውስጡ
ንቁ መሆን አይችሉም፡፡

ማር ከሎሚ ጋር ተቀላቅሎ ለጉንፋን ህመም ማስታገሻነት ይውላል፡፡ ማር የጉሮሮ መቆጣትን


ከመቀነሱም በለይ በአፍ ውስጥ የሚገኙትን ባክቴሪያዎች አድገው ችግር እንዳያስከትሉ
ይከላከላል፡፡

ማር ለሆድ ህመምና ችግሮች ጥቅም ለይ ይዉላል፡፡ሳይንሳዊ ግኝቶች እንደሚጠቀሙት ማር


ለጨጓራ ወይም ለጨጓራ ቁስለት ህክምና ጥቅም ለይ ሲውል ውጤታማነቱ ከፍተኛ ነው፡፡ማር
ፀረ-ባክቴሪያ፤ፀረ-ቨይረስ እና ፀረ-ፈንገስ ባህሪ በውስጡ ስላለው ለተለያዩ ቁስሎችና ኢንፌክሺኖች
ህክመና ውጤታማ እንደሆነ ተረጋግጧል፡፡

ማር በተለያዩ ስኳሮችና ማእድናት የበለፀገ ነው፡፡ማር ፀረ-ሙቀት አማቂ (Anti-oxidant) ስለሆነ


ደማችን በተሸለ ሁኔታ እንዲዘዋወርና እንደ አንጎል ላሉ የሰውነት ክፍሎች ኦክሲጂን እንዲደርስ
ያግዛል፡፡ የካሎሪ መጠኑ ዝቅተኛ ስለሆነ የስኳር ህመምተኞችና የልብ ህሙማን እንዲሁም
ከመጠን በለይ ክብደት ያላቸው ሰዎች እንደማጣፈጫነት ሊጠቀሙት የችላሉ፡፡ [29]

2.2.2 ሸረሪት በቁርኣንና በሳይንስ

እንደ ሌሎች ቋንቋዎች ሁሉ የአረቢኛ ቋንቋ ቃላት ‹‹ሴት›› እና ‹‹ተባእታይ›› ቅጥያ አሉት።
በእነዚህ ቅጥያዎች በመታገዝ በአንድ ዐረፍተ ነገር ውስጥ አንድ ግስ (verb) የሴት ወይም
የወንድ አመልካች መሆኑን በቀላሉ እንረዳለን። በአረቢኛ በአንድ ግስ (verb) መጨረሻ ለይ
‹‹ት›› ተብሎ የሚነበብ የአረቢኛ ፊደል ከታከለበት ያለጥርጥር ያቃል ሴትን ይጠቁማል ማለት
ነው። [30]

በቅዱስ ቁርኣን ውስጥ ‹‹የሸረሪት ምእራፍ›› ተብሎ የሚጠራ ምእራፍ ያለ ሲሆን የሚገኘው
በ29ኛው ምእራፍ ለይ ነው። በዚህ የሸረሪት ምእራፍ ወይም ደግሞ በ29ኛው ምእራፍ አንቀፅ
41 ለይ አምላካችን አላህ እንዲህ ይላል።

የእነዚያ ከአላህ ሌላ ረዳቶችን (ጣዖታትን) የያዙ ሰዎች ምሳሌ ቤትን እንደ ሠራች ሸረሪት ብጤ
ነው፡፡ ከቤቶችም ሁሉ በጣም ደካማው የሸረሪት ቤት ነው፡፡ ቢያውቁ ኖሮ (አማልክት አድርገው
አይግገዟቸውም ነበር) (21:41)።
በአንቀፅ ውስጥ ‹‹ሸረሪት›› ተብሎ የተተረጎመው የአረቢኛው ቃል ‹‹አንከቡት›› የሚባል ቃል
ነው፡፡ በዚህ አንቀፅ ውስጥ አላህ ከሱ ውጭ ሌላ ረዳቶችን የሚይዙ ሰዎችን ከሸረሪት ቤት ጋር
አነፃፅረዋቸዋል። ልክ እንደ ሌሎቹ ነፍሳት ሸረሪትም ሴቴና ወንዴ ተብለው ለሁለት ይከፈላሉ፡፡
ነገር ግን የሸረሪት ቤት ወይም ድርን የሚሰራው ወንዱ ሸረሪት ነው ወይስ ሴቷ ሸረሪት ናት?
ወይስ ሁለቱም ናቸው? ስለዚህ ጉዳይ ቅዱስ ቁርኣን ምን ይለናል? ከለይ በተገለፀው አንቀፅ
ውስጥ በአረብኛው ትርጉሙ ለይ ‹‹ኢተከዘት›› የሚል ግስ የምናገኝ ሲሆን ቃሉ ‹‹አንድን ነገር

27
መስራትን›› ያመለክታል። በዚህ የአረቢኛ ግስ መጨረሻ ለይ ‹‹ት›› የሚል ቅጥያ ያለበት ሲሆን
የሴት ፆታን ጠቋሚ ነው። ስለዚህ ከለይ የተብራራው የቁርኣን አንቀፅ ቤትን ወይም ድርን
የምትሰራው ሴት ሸረሪት ናት ብሎ እየነገረን ነው። ባጭሩ ከ1400 ዓመታት በፊት ቅዱስ
ቁረኣን የሸረሪትን ድር የምትሰራው ሴት ሸረሪት እንደ ሆነች በምእረፍ 21 አንቀፅ 41 ለይ
ገልጾዋል፡፡ በዚህ ረገድ በዘመናዊ ሳይንስ ምን ተብሎዋል?

እንደ ጎርጎርሳዊያኑ ዘመን አቆጣጠር በ1984 ኮስሞስ (Kosmos) የተባለ በዓለም ለይ ታዋቂ
የጀርመን የሳይንስ መጽሔት ስለ ሸረሪት አንድ አንድ አስገራሚ ነገር አስነብቦ ነበር። መጽሔቱ
ለይ ከሰፈሩት ፅሁፎች መካከል የሚከተሉትን መስመሮች ሲያነቡ በቁርኣን ሳይንሳዊ ታዓምር
እንደሚደመሙ ተስፋ አደርጋለሁ።

‹‹ የሸረሪት ድርን መስራትና ምግብን ማደን በሴት ሸረሪት ብቻ የተወሰነ ነው። የእስልምናው
ነብይ ተደብቆበት የነበረውን የዋሻ መግቢያ የሚሸፍን ድር የተሰራው በሴት ሸረሪት ነው። ስለ
ወንድ ሸረሪት ህይወት ብዙ መረጃ የለንም። እኛ የምናውቀው የሸረሪት ድርን መስራት
የሚችሉት ሴት ሸረሪቶች ብቻ መሆናቸውን ነው›› የሚል ፅሁፍ ተጠቃሹ መፅሔት አስነብቦ
ነበር። [30]

ስለ ሸረሪት ሌላ አንድ ትኩረትን የሚስብ ጉዳይ አለ ይህም ከተለይ የተብራራው የቁርኣን


አንቀፅ ወይም ቁርአን 29:41 ‹‹ ከቤቶች ሁሉ ደካማው ቤት የሸረሪት ቤት ነው ›› ይላል።
አንቀጹ ውስጥ ‹‹ (አውሀነ) ›› የሚል የአረቢኛ ቃል የምናገኝ ሲሆን ትርጉሙም ‹‹በጣም
ደካማ (the weakest) ››ማለት ነው። ይህ እንዴት ሊሆን ቻለ? ይህን ጥያቄ ከመመለሳችን
በፊት ሳይንስ በሸረሪት ህይወት ዙሪያ ምን እንደሚል እንይ። [31]

በ20ኛው እና በ21ኛው ክፍለ ዘመን የተፈጥሮ እና የዱር እንስሳት ጥናት መስፋፋትን ተከትሎ
የተፈጥሮ ተመራማሪዎች እና የሳይንስ ሊቃውንት በሸረሪቶች ሕይወት ላይ የሚያጠነጥኑ
በእውነት የተንፀባረቁ አስገራሚ፣ የልታሰቡና ከመደበኛ አካሄድ ውጭ የሆኑትን ምልከታዎች
ይፋ አድርገዋል። በዓለማችን ለይ ከ45,000 በለይ የሸረሪት ዝርያዎች ያሉ ሲሆን በሸረሪት ቤት
ውስጥ መገዳደል እንዲሁም እርስ በርስ መበላላት የተለመደ ነው። ከግብረስጋ ግንኙነት በኋላ
ወንድ ሸረሪቶች በሚስቶቻቸው ይገደሉና ለምግብነት ይውላሉ።ሴት ሸረሪቶች ባሎቻቸውን ብቻ
ሳይሆን ማግባት ማይፈልጉትንም ወንድ ሸረሪቶችንም ጭምር ከመግደል ወደኋላ አይመለሱም።
ይህ በሸረሪት ቤት ውስጥ ፍጥጫና አለመረጋጋት እንዳለ ያሳየናል። [31]

ወንድ ሸረሪቶች ከግብረ ስጋ ግንኙነት በኋላ በሚስቶቻቸው ስለሚገደሉ ህፃናቶች በእናታቸው


ስር ብቻ ነው የሚያድጉት። ሌላ አስገራሚ ነገርም አለ። የምግብ እጥረት ሲፈጠር እናት
ሸረሪት ልጃን የልተፈለፈሉትን የራሷን እንቁላል ትመግባቸዋለች። ይህ ማለት ህፃን ሸረሪቶች
ከረሃብ ለማምለጥ ሲሉ ታናሽ ወንድሞቻቸውና እህቶቻቸውን ጭምር ገድለው ይበላሉ። ረሃብ
ሲጠናባቸው በሸሪሪት ድር ውስጥ ከባድ ፍልሚያ ይካሄድና አንዳንዴ እናት ልጆችዋን ጭምር
ገድላ መብላት ትጀምራልች። አንዳንድ ግዜ ደግሞ እናት ተስፋ ስትቆርጥ ራሷን መስዋእት
ታደርግና በገዛ ልጆችዋ ትበላለች። በዚህም ምክንያት በሸረሪት ቤት ውስጥ ከ100ዎቹ መካከል
በጣም ጥቂት ብቻ ነው የሚተርፉት።ስለዚህ የሸረሪት ቤተሰብ ከሌሎች ፍጥረታት ቤተሰብ ጋር
ሲነፃፀር በጭካኔ፣በመገዳደል የተሞላ እና ብትንትኑ የወጣ እጅግ በጣም ደካማ ቤተሰብ ነው።

28
ቅዱስ ቁርኣን ከ1400 ዓመት በፊት ስለ ሸረሪት ማንም ምንም በማያውቅበት ግዜ ከዘመኑ
ሳይንስ ቀድሞ ከቤቶች ሁሉ ደካማው ቤት የሸረሪት ቤት ነው በማለት ተናግሮዋል። [31]

2.2.3 ጉንዳን በቁርኣንና በሳይንስ

ተፈጥሮ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸውን ፍጥረታት በውስጧ ይዛ ትገኛለች፡፡ ግዙፍ ከሆኑት እንስሳት
እስከ ትንንሾቹ ነፍሳት ምድርን መኖሪያቸው አድርገው የተለያዩ የህይወት ዑደትን
ያሳልፋሉ፡፡ከነዚህ ነፍሳት ጉንዳን አንዱ ነው፡፡ በዓለም ለይ በርከታ ጉንዳን ዝርያዎች እንዳሉ
ይነገራል፡፡ በአንድ የጉንዳን ስብስብ ውስጥ ሶስት ዓይነት ጉንዳኖች አሉ፡፡ሰራተኛ፤ንግስትና
አውራ (ወንድ) ጉንዳን በመባል ይታወቃሉ፡፡እያንዳንዱ የጉንዳን ዓይነት የራሱ የሆነ ተግባሮች
አሉት፡፡ በውስጣቸው ያለውን አደረጃጀት መሰረት ያደረገ የስራ ክፍፍል ያላቸው ከመሆኑም
በለይ፤ በአንድ የጉንዳን ስብስብ ውስጥ መሰራት ካለበት ምንም ሳይሰራ አይቀርም፡፡

የቅዱስ ቁርኣን 27ኛው ምእራፍ ‹‹የጉንዳን ምእራፍ››ይባላል።በዚህ ምእራፍ ውስጥ አላህ ነቢዩ
ሱለይማንን (ዐ፣ሰ) የወፍ ቋንቋ እንዳስተማረው ይነግረናል።የጉንዳንንም ንግግር በመስማቱም
እየሳቀ ጥርሱን ፈገግ እንዳደረገ ጭምር ያወሳል። በዚህ አምድ ትኩረታችን ስለ ምእራፍ 27
(የጉንዳን ምእራፍ) አንቀፅ 18 ለይ ነው፡፡

በጉንዳንም ሸለቆ በመጡ ጊዜ አንዲት ጉንዳን «እናንተ ጉንዳኖች ሆይ! ወደ መኖሪያዎቻችሁ


ግቡ፡፡ ሱለይማንና ሰራዊቱ እነርሱ የማያውቁ ሲኾኑ አይሰባብሩዋችሁ» አለች (27:18)
ይህ አንቀፅ እንዲት ጉንዳን ሱለይማንና ሰራዊቱ አንዳይሰባብሩዋችሁ ወደ መኖሪያቹ ግቡ ብላ
ለሌሎች ጉንዳኖች መልእከት እንዳስተላለፈች ይነግረናል፡፡ ተጠቃሹ እንቀፅ ጉንዳንን በተመለከት
ሁለት መረጃዎችን በውስጡ አዝሎዋል፡፡ የመጀመሪያ ጉንዳኖች እርሰ በርሳቸው እንደሚነጋገሩ
የሚያሳይ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ የማስጠንቀቂያ መልእክት ያስተላለፈችው ጉንዳን ፆታዋ
ሴት ነው ምክንያቱም ‹‹አለች›› የሚለው ግስ የሴትን ፆታ አመልካች በመሆኑ ነው፡፡ ለመሆኑ
ሳይንስ በጉንዳኖች አኗኗር ዙሪያ፤ስለ ፆታቸውና ስለ ተግባቦታቸው ምን ይላል? በሳይንሱ ዓለም
ስለ ጉንዳን አኗኗርና ህይወት ዑደታቸው የቅርብ ጊዜ መረጃዎች ምን ይላሉ?

በጉንዳኖች ለይ በተደረገው ሳይንሳዊ ጥናት ጉንዳኖች እርስ በርስ ለመግባባት የሚያስችላቸው


በጣም የተወሳሰበ ማህበራዊ አደረጃጀት እንደነበራቸው ተረጋግጠዋል። የ21ኛው ከፍለ ዘመን
ሳይንሳዊ ግኝት ጉንዳኖች እርስ በርስ መግባባት የሚችሉበት የግንኙነት መረብ እንዳላቸው
አሳይቶዋል፡፡በብሔራዊ ጂኦግራፊ መጽሔት (National Geographic Magazine) ውስጥ
የታተመ አንድ ፅሁፍ የሚከተውን አስነብቧል፡፡ [32]

‹‹‹ጉንዳን በጭንቅላቷ ለይ በዙ የስሜት ህወሳትን ይዛለች፡፡ ይህን የስሜት ህዋሳት በመጠቀም


በውስጡ ሚሊዮን እና ከዛ በለይ ሰራተኛ ጉንደኖችን ለያዘው የጉንዳን ስብስብ የኬሚካልና
የምስል መልእክቶችን ታስተላልፋለች፡፡ ሁሉም ሰራተኛ ጉንዳኖች ሴት ጉንዳኖች ናቸው፡፡
አንጎሏ ግማሽ ሚሊዮን የሚደርሱ የነርቭ ሴሎችን በውስጡ ይዞዋል፡፡ አንቴናዎች እንደ
አፍንጫና ጣት ጠቃሚ ያገለግላሉ፡፡›››

29
እኛ ባናስተውልም እንኳ ጉንዳኖች በጣም በተለየ መልኩ በስሜት ህዋሶቻቸው መግባብትና
መነጋገር የችላሉ፡፡ ጉንዳኖች ጎጆቻቸውን ለመገንባትም ሆነ ለእርስ በርስ ጠብ ለመፍጠር ይህን
የስሜት ህዋሶቻተውን ይጠቀማሉ፡፡ ጉንዳኖች በአስደናቂ የግንኙነት ስርኣታቸው የሰው ልጅ
አንዳነዴ ተነጋግሮ መፍታት የማይችላውን ጉዳዮች በተሻለ መልኩ ይፈታሉ ያከናውናሉ፡፡

ጉንዳኖቸ በሚያመነጩት ፌሮሞን (Pheromone) በሚባል ኬሚካልና በአንቴናዎቻቸው


ይግባባሉ፡፡ አንድ ጉንዳን ፌሮሞን (Pheromone) የሚባለውን ኬሚካል ሲያመነጭ ሌሎች
ጉንዳኖች ኬሚካሉን በማሽተት ብቻ የተፈለገውን መልእክት ይረዳሉ፡፡ የሚያመነጩት ኬሚካል
ከመልእከት ወደ መልእክት ይለያያል፡፡ ጉንዳኖች ከተወለዱ ጀምሮ ነው ያለ ማንም አስተማሪ
ይህን አስገራሚ የመግባቢያ ዘዴ የሚጠቀሙት፡፡ ጉንዳኖች በአንቴናቸውም ጭምር ይግባባሉ፡፡
አንቴናቸውን በመጠቀም እርስ በርስ ይነካካሉ በዚህም ብዙ መልእከቶችን ይለዋወጣሉ፡፡በብዛት
ይህን የሚጠቀሙት ለሰላምታ፤ለእራት ግብዣ፤ለማህበራዊ ስብሰባዎችና ለመሳሰሉት ጉዳዮች
ነው፡፡

በድምፅ መግባባት ጉንዳኖች በተደጋጋሚ የሚጠቀሙበት ሌላ የእርስ በርስ መግባቢያ ዘዴ


ነው፡፡ሁለት ዓይነት ድምጾችን ይጠቀማሉ፡፡ አንደኛው አንድን ነገር በመምታት የሚመጣ ድምፅ
ወይም ደግሞ መሬትን በመምታት የሚመጣ ድምፅ ሲሆን ሌላኛው ደግሞ የተወሰኑ የሰውነት
ክፍሎችን እርስ በርስ በማጋጨት የሚፈጠር ድምፅ ነው፡፡ የሰውነት ክፍሎችን በመምታት
የሚፈጠረው ድምፅ ብዙውን ጊዜ ጥቅም ለይ የሚውለው የዛፍ ጎጆ ላላቸው የጉንዳን ስብስቦች
ነው፡፡ አናጢ ጉንዳኖች ደግሞ ‹‹ከበሮን በመጫወት›› በሚመጣው ድምፅ ይግባባሉ፡፡ እንዲሁም
ወደ ጎጆዋቸው እየደረሰ ያለውን አደጋ ለመከላከልና ለሌሎች ጉንዳኖች ለማሳወቅ ከበሮን
በመምታት መልእክት ያስተላልፋሉ፡፡[32]

ጉንዳኖች እርስ በርሳቸው ተነጋግረው መግባባት እንደሚችሉ ዓለም በቅርብ ግዜ ቢደርስበትም


ቅዱስ ቁርኣን ከማንም ቀድሞ ሰዎች ጉንዳኖች እርስ በርሳቸው ይነጋገራሉ እንዲሁም ይግባባሉ
ብሎ መቼም በማያስቡበት ወቅት በምእራፍ 27 አንቀፅ 18 ለይ ጉንዳኖች በነቢዩ ሱለይማን
(ዐ፣ሰ) ዘመን እርስ በርሳቸው እንደተነጋገሩ ይገልፃል።

ምእራፍ 27 አንቀፅ 18 በደምብ አስተውለን ካየነው ሌላ አንድ አስደናቂ ነገር በውስጡ


ይዞዋል። ይህም ሱሌይማንና ሰራዊቱ እንዳይሰባብራቹ ወደ መኖሪያችሁ ግቡ ብላ ለሌሎች
ጉንዳኖች መልእክት ያስተላለፈችው ሴት ጉንዳን ናት። ተጠቃሹ አንቀፅ ውስጥ ‹‹አለች›› የሚል
ቃል እናገኛለን።ይህ ቃል ደግሞ ‹‹የሴት ፆታን›› አመልካች ነው። ‹‹አለች››ተብሎ የተተረጎመው
የአረቢኛ ቃል ‹‹ቃለት›› የሚል ነው። በአረቢኛ በአንድ ግስ (Verb) መጨረሻ ለይ ‹‹ት›› ተብሎ
የሚነበብ የአረቢኛ ፊደል ከታከለበት ያለጥርጥር ያቃል የሴት ፆታን ይጠቁማል ማለት ነው።
በዚህም መሰረት ‹‹ቃለት›› በሚለው ግስ ውስጥ መጨረሻ ለይ ያለችው ‹‹ት›› ፊደል የሴት
ፆታን ታመለክታለች። ስለዚህ ሴቷ ጉንዳን ናት መልእክት ያስተላለፈችው።

በዓለማችን ወደ 10,000 የሚጠጉ የጉንዳን ዝርያዎች አሉ።የጉንዳኖች ማህበረብ የሚተዳደሩት


በንግስቷ ጉንዳን ሲሆን ዋና ስራው በሺዎቹ የሚቆጠሩ እንቁላሎችን በመጣል ትውልድን
ማስቀጠል መቻል ነው። ሰራተኞቹ ጉንዳኖች (በተለምዶ በሰዎች የሚታዩ ጉንዳኖች) ክንፍ

30
አልባ የሆኑ ሁሉም ሴቶች ናቸው። በሌላ አገላለፅ ሰራተኞቹ ጉንዳኖች ሁሉም ክንፍ አልባ
የሆኑ ሴት ጉንዳኖች ናቸው። እነዚህ ጉንዳኖች አይራቡም ይልቁንም የንግስቷን ዘር
ይንከባከባሉ፣መጠለያ ይሰራሉ፣እንደ ወታደር የጉንዳንን ማህበረስ ከጥቃት ይከላከላሉ እንዲሁም
ሌሎች በርካታ ተግባራትን ይከላከላሉ። የወንዶች ጉንዳኖች አንድ የስራ ድርሻ ብቻ ነው
ያላቸው ይህም ከንግስቷ ጋር ግብረ ስጋ ግንኙነት መፈፀም ብቻ ነው። ግንኙነት ከፈፀሙ በኋላ
ብዙም ሳይቆዩ ሊሞቱ ይችላሉ፡፡[33] ወንዶች ጉንዳኖችና ንግስቷ ጉንዳን ክንፍ አላቸው።
የመራቢያ ጊዜያቸው ሲደርስ አየር ለይ በመብረር ግንኙነት ይፈፅማሉ፡፡ [34]

የቅዱስ ቁርኣን ምእራፍ 27 አንቀፅ 18 ለይ ያለውን ካየነው ከጉንዳኖች ባህሪና አኗናር ጋር


የገጠመ ሆኖ እናገኛለን። ወንዱ ጉንዳን ከንግስቷ ጋር ግብረ ስጋ ግንኙነት ከመፈፀም ውጪ
ሌላ ስራ የለውም፡፡ ሁሉም ሰራተኞች ሴት ጉንዳኖች ናቸው።እነኚህ ጉንዳኖች ደግሞ ክንፍ
የላቸውም። ስለዚህ መብረር አይችሉም። ከስራቸው መካከል አንዱ ማህበረሰባቸውን ከአደጋ
መጠበቅ ነው። አደጋ ሲይንዣብብ አደጋ መኖሩን አውቀው ሌሎች ራሳቸውን እንዲከላከሉ
በተለያዩ መግባቢያ መንገዶች የማስጠንቀቂያ መልእክት ያስተላልፋሉ፡፡ ቁርኣን (27:18) ለይም
የጉንዳንን ስብስብ ከጥቃት ለመከላከል በማሰብ ሱሌይማን እንዳይሰባብራችሁ ወደ
መኖሪያዎቻችሁ ግቡ የሚል መልእክት የተላለፈው በሴት ጉንዳን ነው፡፡ ምክንቱም በቁርኣኑ
ውስጥ ‹‹አለች›› የሚለው የአማርኛ ግስ ሴት ጉንዳንን የሚጠቁም ነው፡፡

2.2.4 የከብቶች ወተት አመራረት በቁርኣንና በሳይንስ

ብዙውን ግዜ ፍየሎች፣ በጎችና ላሞች ሳር ሲግጡ እናያለን። እነዚህ ከብቶች በሚግጡት ሳርና
ከነሱ ከሚገኘው ወተት መካከል ያለው ትስስር ለማናችንም ግልፅ ያልሆነ ጉዳይ ነበር።
አምላካችን አላህ ሳር እንዲመገቡ ያደርጋቸዋል። ይህ የሚመገቡት ሳር የተለያዩ ሂደቶችን ካለፈ
በኋላ ከአልሚ ምግቦች መካከል አንዱ የሆነውን ወተት እንዲገኝ ምክንያት ሆኗል። [27]

በጥንት ግዜ ሰዎች ከጡት ጫፎች አጠገብ ካለው ነጭ ስብ ውስጥ ወተት እንደሚመረት ያስቡ
ነበር።ዛሬ ለይ ግን ይህ አመለካከት ተቀባይነት ሊያገኝ አልቻለም። ወተት የሚመረተው በወተት
እጢ ውስጥ ሲሆን ለማምረቻ የሚሆኑ ንጥረ ነገሮች የሚወሰዱት ደግሞ ከደም ፍሰት ነው።
የደም ዝረቱ ደግሞ አስፈላጊውን ንጥረ ነገር የሚያገኘው ከተፈጨው ምግብ (ፈርስ) ነው። ይህ
ማለት ከብቶች የሚግጡት ሳር/ቅጠል ከተፈጨ በኃላ ወይም ፈርስ ከሆነ በኃላ አስፈላጊ ንጥረ
ነገሮች በደም አማካኝነት ወደ ወተት እጢ ይጓዛሉ። ከዚያም በእጢው ውስጥ ነው እንግዲህ
ወተት የሚቀነባበረው። ይህ ተፈጥሯዊ የሆነ የወተት ማቀነባበሪያ ሂደት ነው። [35]

ይህ የ20ኛው ወይም 21ኛው ክፍለ ዘመን የከብቶች ወተት አመራረት ግኝት ከ1400 ዓመታት
በፊት የሰው ልጅ ወተትን ከመጠጣት ውጭ እንዴት እንደሚገኝ በማያውቅበት ግዜ ቅዱስ
ቁርኣን ስለ አመራረቱ ምእራፍ 16 አንቀጽ 66 ለይ እንደሚከተለው ገልጾታል።

ለናንተም በግመል፣ በከብት፣ በፍየል በእርግጥ መገምገሚያ አልላችሁ፡፡ በሆዶቹ ውስጥ ካለው
ከፈርስና ከደም መካከል ጥሩ ወተትን ለጠጪዎች ተዋጭ ሲሆን እናጠጣችኋለን፡፡ (16:66)

31
ከለይ የተገለፀው አንቀጽ በሆድ ውስጥ በፈርስ (የተፈጨ ምግብ)ና ደም ጥሩና የሚጠጣ ወተት
እንደሚገኝ ወይም እንደሚመረት ይነግረናል። ይህ ማለት የተፈጨው ምግብ (ፈርስ)ና የደም
ግንኙነት ለወተት አመራረት ምክንያት ሆኗል። ፈርስ (የተፈጨ) ምግብና ደም ለወተት
አመራረት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያበረክታሉ፡፡ ይህን አስገራሚ መረጃ ለነቢዩ መሐመድ (ሰ፣ዐ፣ወ)
ማነው የነገራቸው? ዊሊያም ሀርቬይ (William Harvey) ነቢዩ ሙሐመድ (ሰ፣ዐ፣ወ) ከሞቱ
1000 ዓመት በኃላ ነው የደም ስርጭትን ያገኘው። በነቢዩ ግዜ ደም ከተፈጨ ምግብ
የሚገኘውን ንጥረ ነገር ተሸክሞ ለወተት ማምረቻ ወደ ወተት እጢዎች እንደሚያጓጉዝ ማንም
የሚያውቅ አልነበረም። [27]

አምላካችን አላህ ከብቶች ከሚግጡትን ሳርና ከሚጠጡት ውሃ በራሱ ጥበብና አካሄድ ወተትን
የመሰለ ጣፋጭ ነገር ለሰው ልጅ አስገኘ። በምድር ለይ ሳር + ውሃ = ወተት የሚሰጥ ፋብሪካ
ይኖራልን? በጭራሽ ለዚህም ነው ቁርኣን (16:66) ለናንተ በግመል፣በከብት፣ በፍየል በእርግጥ
ትልቅ መገምገሚያ (ትምህርት) አለላችሁ ያለን። የአላህን ጥበብና ሀይል እንዲሁም ለሰው
ልጆች የዋለውን ትልቅ ውለታ እንገነዘባለን።
2.3 ስነ -ምድር
2.3.1 የዓለምችን ዝቅተኛ ስፍራ

ሙት ባህር (dead sea) ይባላል። ይህ ስፍራ በመካከለኛው ምስራቅ በእስራኤልና ዮርዳኖስ


ማካከል የሚገኝ ሲሆን አለማችን ለይ ካሉት እጅግ በጣም ልዩ ቦታዎች አንዱ ነው። ሙት
ባህር ስያሜውን ያገኘው በቅርቡ ሲሆን የቀድሞ ስሙ ጨው ባህር ይባላል። ሙት ባህር
ወይም ጨው ባህር የተባለበት ምክንያት ከሌሎች የባህር አካላት በተለየ መልኩ በውስጡ
ምንም ህይወት ያለው ነገር ባለመኖሩ ነው። [36]

ይህ ባህር አስደናቂ ነገሩ በአለማችን ከሉት ውሃ እና ባህር አካላት በተቃራኒው ማንሳፈፍ


እንጂ ማስመጥ አያውቅም። እዚህ ባህር ውስጥ ከገባክ መስመጥ አትችልም። እድሉን አግኝተህ
ይህን አስገራሚ ባህር ለመጎብኘት ከበቃህ ዋና መቻል አይጠበቅበህም ምክንያቱም ሙት ባህር
ላይ እንኳንስ መዋኘት ተኝተህ ጋዜጣ ማንበብ ትችላለህና፡፡ [36]

ይህ የሙት ባህር ስፍራ ሌላ አስደናቂ ነገር አለው። ይህ ስፍራ ከባህር ወለል በታች እስከ 412
ጫማ (430 ሜትር) ርቀት ሲኖረው በዚህም ምክንያት የምድራችን ዝቅተኛ ስፍራ
ሆኗል።[37] ይህ ሊታወቅ የቻለው በዘመናዊ ሳይንስና ቴክኖሎጂ በተደረገው ጥናትና ምርመራ
ነው። ኢትዮጵያን ጨምሮ ሌሎች ሀገራት ለይም ዝቅተኛ የሚባሉ ቦታዎች ቢገኙም ሙት
ባህርን የሚስተካከል ግን በጭራሽ አይገኝም። ይህ አስገራሚ ስፍራ ከ1400 ዓመት በፊት
በቅዱስ ቁርኣን ተከትቦ መገኘቱ የበለጠ እንድንገረም ያደርገናል። ቅዱስ ቁርኣን በምእራፍ 30
ከአንቀጽ 1 አስከ 3 ለይ የሚከተለውን እናገኛለን።

አ.ለ.መ (አሊፍ ላም ሚም)፡፡(30፡1)

32
ሩም ተሸነፈች፡፡(30፡2)

በጣም ቅርብ በሆነችው ምድር፡፡እነርሱም ከመሸነፋቸው በኋላ በእርግጥ ያሸንፋሉ፡፡ (30፡3)


ከታሪኩ ስንነሳ ከለይ ያሉት የተከበሩት አንቀጾች የወረዱበት የራሳቸው የሆነ ምክንያት
አላቸው። ነቢዩ ሙሐመድ (ሰ:ዐ:ወ) እና ባልደረቦቻቸው መካ በነበሩበት ወቅት የወቅቱ ሃያላን
የነበሩት ፐርሺያ(እሳት አምላኪዎች)ና ሮም (የመጽሀፉ ባለቤቶች) መካከል በሙት ባህር (dead
sea) አጠገብ ከባድ ጦርነት ይካሄድና በመካ ሙሽሪኮች የሚደገፉት ፐርሺያኖች በርካታ የሮም
ግዛቶችን በመማረክ ያሸንፋሉ። ሙስሊሞች ለሮም ቀረቤታ ስላላቸው እነሱ በመሸነፋቸው ተከፉ
ተሸበሩም።ወዲያው ሙስሊሞችን የሚያስደስትና ሀዘናቸውን የሚጠግን የቁርኣን አንቀጽ ወረደ።
የቀርኣን አንቀጾቹ ሮም በፐርሺያ ብትሸነፍም በጥቂት ዓመታት ተመልሳ እንደምታሸንፍ
ከዚያም ሙስሊሞች እንደሚደሰቱ የሚተነብይ ነበር።በመጨራሻም የቁርኣኑ ትንቢት
ተፈፃሚነት አገኘ።

ለዛሬው ርእሳችን ወሳኝ የሆነው የ30ኛው ምእራፍ 3ኛው አንቀጽ ነው። ይህ አንቀጽ
ሮማውያኖች ከማሸነፋቸው በፊት በጣም ቅርብ በሆነችው ምድር እንደተሸነፉ ይነግረናል።
በጣም ቅርብ በሆነችው ተብሎ የተተረጎመው የአረቢኛ ቃል ‹‹ (አድነል አርድ) ››
የሚል ሲሆን ሌላው ትርጉሙ ደግሞ ‹‹በጣም ዝቅተኛ ምድር›› ማለት ነው። ሁለቱም
ትርጉሞች ያስኬዳሉ። ስለዚህ ሮም በፐርሺያ የተሸነፈችበት ቦታ በጣም ዝቅተኛ በሆነው ምድር
ለይ ነው። በጣም ዝቅተኛ የሆነው ምደር (the lowest place of the earth) ደግሞ ፐርሺያኖችና
ሮማውያኖች የተዋጉበት ሙት ባህር ተብሎ የሚጠራ ስፍራ ነው፡፡[20]

ስለዚህ ሙት ባህርና አከባቢው ልክ ዘመኑ ሳይንስ በቅዱስ ቁርኣን ውስጥ ዝቅተኛ ምድር
ተብሎዋል፡፡ይህ የቁርኣንን ታዓምር ፍንተው አድርጎ የሚገልፅ ነው ምክንያቱም በ7ኛው ከፍለ
ዘመን ሳታላይቶች እና ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎች በወቅቱ ባለመገኘታቸው እንዲህ አይነቱን
እውነታ ማንም ሊያውቅ ወይም ሊገምተው አይችልም፡፡ ስለሆነም የዚህ መረጃ ምንጩ ከፈጣሪ
ሌላ ከየትም ሊሆን አይችልም፡፡
2.3.2 ብረት(Iron) በቁርኣንና በሳይነስ

በቅዱስ ቁርኣን ውስጥ ከተጠቀሱ ንጥረ ነገሮች አንዱ ብረት (iron) ነው። በስሙ የተሰየ
ምእራፍም አለ። የቀርኣን 57ኛው ምእራፍ የብረት ምእራፍ ወይም ደግሞ በአረቢኛ ‹‹ሱረቱል
ሀዲድ›› ይባላል። በዚሁ ምእራፍ አንቀፅ 27 ለይ አላህ እንዲህ ይላል

‹‹‹-------ብረትንም በውስጡ ብርቱ ኀይልና ለሰዎችም መጠቃቀሚያዎች ያልሉበት ሲኾን


አወረድን------››› (57:25)፡፡
በዚህ አንቀፅ ውስጥ አላህ ብረት ለሰዎች መጠቃሚያ ይሆን ዘንድ አወረድን ይላል። በአንቀፁ
ውስጥ ‹‹አወረድን›› ተብሎ የተተረጎመው የአረቢኛ ቃል ‹‹አንዘልና›› የሚል ሲሆን ቃሉ ብረት
(iron) ከሰማይ መውረዱን ይነግረናል። እንዴት ከመሬት የሚወጣው የብረት ማእድን ከሰማይ
ሊወርድ ይችላል? ዘመናዊ የስነ ፈለክ ግኝቶችም ይህንን የቁርኣኑን መረጃ የሚያጠናክሩ
ናቸው።

33
ዘመናዊ የስነ ፈለክ ግኝቶች ብረት ጠፈር ውስጥ ካሉ ግዙፍ ከዋክብት የመጣ መሆኑን
ገልፀዋል። በምድር ለይ ያለው ብረት ብቻ ሳይሆን በፀሓይ ስርኣት (solar system) ውስጥ
የሚገኘውም ብረት ከጠፈር ውጭ ካሉ ግዙፍ ከዋክብት ነው የመጣው። ምክንያቱም በፀሓይ
ውስጥ ያለው የሙቀት መጠን ብረትን ለመፍጠር በቂ ስላልሆነ ነው። የፀሓይ የውጪው ክፍል
6,000 ዲግሪ የሙቀት መጠን ሲኖረው የውስጡ ዋናው ከፍል የሙቀት መጠኑ ደግሞ
በግምት 20 ሚሊዮን ዲግሪ ይሆናል። ብረት ደግሞ ሊመረት የሚችለው የሙቀት መጠናቸው
መቶ ሚሊዮን የሆኑ ከፀሓይ እጅግ በጣም ትላልቅ በሆኑ ኮከቦች ብቻ ነው። የተመረተው
የብረት መጠን ከተወሰነው በለይ ከፍ ሲል ኮከቡ ማስተናገድ ስለማይችል ትልቅ የሆነ ፍንዳታ
ይፈጠራል። የፍንዳታው ስም ኖቫ (Nova) ወይም ሱፐር ኖቫ (Super nova) ይባላል። በዚህ
ታላቅ ፍንዳታ ምክንያት ብረት ከጠፈር ወደ ምድር ይወርዳል። ቅዱስ ቁርኣን በ7ኛው ክፍለ
ዘመን ማንም ሊያስብ የማይችለውን ሀቅ አስፍሮታል። ይህን መረጃ ለነቢዩ መሐመድ
(ሰ፣ዐ፣ወ) ማን ነገራቸው? [38]

2.4 ውቅያኖግራፊ (የውሃ አካላት ጥናት)


2.4.1 ሁለት ባህሮች መካከል ያለው ገርዶ

በዘመናዊ ሳይንስ ሁለት የተለያዩ ባህሮች የሚገናኙበትን ቦታና በሁለቱም መካከሌ ማገጃ
ወይም ግርዶ እንዳለ ተደርሶበታል። ይህ ማገጃ ወይም ሁለቱን ባህሮችን ይከፍላል፡፡ እያንዳንዱ
ባህር የራሱ የሆነ የሙቀት፣የጨዋማነትና የውፍረት መጠን አለው። ለምሳሌ የሜዲትራኒያን
ባህር ውሃ በጣሪቅ (Gibraltar) ተራራ አማካኝነት ወደ አትላንቲክ ውቅያኖስ ይገባል ይህም
በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ ኪሎ ሜትሮችን በመጓዝ ነው፡፡ በአትላንቲክ ውቅያኖስ ውስጥ ወደ
አንድ ሺህ ሜትር ጥልቀት ከነ ሙቀቱ፤ጨዋማነቱና ከአነስተኛ ውፍረቱ ጋር ይጓዛል፡፡
የሜዲትራኒያን ባህር ጨዋማነቱ ከ36% በለይ ሲሆን የሙቀት መጠኑ ደግሞ 11.5 ዲግሪ
ሴንትግሬድ ነው፡፡ አትላንቲክ ውቅያኖስን ስናይ ደግሞ ጨዋማነቱ ከ36% በታቸ፤የሙቀት
መጠኑ ደግሞ 10.0 ዲግሪ ሴንትግሬድ ሆኖ እናገኛለን፡፡ በመካከላቸው ማገጃ በመኖሩ ምክንያት
ሁለቱ የውሃ አካላት በሚገናኙበት ወቅት ይህንን የሙቀትና ጨዋማነት መጠናቸውን ሳይለቁ
ነው፡፡

የሰው ልጅ እንዲ አይነት አስገራሚና ውስብስብ የሆኑ ነገሮች አሉ ብሎ በማያስብበት ጊዜ


ቅዱስ ቁርኣን ተገናኝተው የማይደባለቁ የውሃ አካላት እንዳሉ እንደሚከተለው አስፍሯል።

ሁለቱን ባሕሮች የሚገናኙ ሲኾኑ ለቀቃቸው፡፡ (55:19)

(እንዳይዋሐዱ) በመካከላቸው ጋራጅ አልለ፡፡ (አንዱ ባንዱ ላይ) ወሰን አያልፉም፡፡ (55:20)

34
ነገር ግን ቅዱስ ቁርኣን በጣፋጭና ጨዋማ ውሃ መካከል ያለውን መለያ ሲናገር ከመለያው
የሚከለክለውን ግርዶሽ መኖሩን መግለጹ ነው፡፡ይህንንም በማስመልከት ምእራፍ 25 አንቀፅ 53
እንዲህ ይላል፡፡

እርሱም ያ ሁለቱን ባሕሮች አጎራብቶ የለቀቀ ነው፡፡ ይህ ጥምን የሚቆርጥ ጣፋጭ ነው፡፡
ይህም የሚመረግግ ጨው ነው፡፡ በመካከላቸውም (ከመቀላቀል) መለያንና የተከለለን ክልል
ያደረገ ነው፡፡ (25፡53)
ምናልባት አንድ ሰው ጥያቄ ልጠይቅ ይችላል፡ አላህ በቁርአን ውስጥ በጣፊጭና ጨዋማ
መካከሌ ያለውን መለያ ሲናገር ለምን ግርዶሽን ገለጸ ነገር ግን በሁለቱ ባህሮች ያለውን መለያ
ሲናገር አልጠቀሰውም?
ዘመናዊ ሳይንስ የወንዞችን መፍሰሻ ቦታ መርምሮ በማግኘት ጣፋጭና ጨዋማ ውሃ
የሚገናኙበትን ቦታ አውቋል፡፡ ሁኔታው ከሁለቱ ባህሮች የመገናኛ ቦታ በጥቂቱም ቢሆን
ይለያል፡፡ ከወንዞች ፌሳሽ ጣፊጭ ውሃ ከጨዋማ ውሃ የሚለይበት መንስኤ ዝቅተኛ አካባቢ
(pycnocline) ለይ መሆኑ ተጠንቷል፡፡በደንሲቲውና በአቋራጭነቱ የሚለይና በሁለቱ
መስመሮች መካከሌ መለያ ያለው ነው፡፡ ይህ መለያ ክልል ከጣፋጭና ከጨዋማ ውሃ የሆነ
የተለያየ የጨዋማነት ደረጃ አለው፡፡
እነዚህ መረጃዎች አሁን ቢሆን እንጂ ከዚህ በፊት አይታወቁም ነበር፡፡የሙቀት፣የጣፋጭና
የጨዋማነት መለኪያ እንዲሁም የደንሲቲንና ኦክሲጅን የሚሟማበትን ደረጃ ለይቶ የሚያሳዩ
መሳሪያዎችንና ዘመናዊ መመሪያዎችን በመጠቀም ነው፡፡
የሰው ልጅ ዓይን በሁለቱ ባህሮች መካከል ያለውን መገናኛ መስመር ለይቶ ማወቅ አይችልም፡፡
ይልቁንም ሁለቱ ባህሮች እንደ አንድ ባህር ሆኖ ይታዩናል፡፡ እንዱሁም የሰው ልጅ ዓይን
በወንዞች የሚፈሰውን የውሃ ክፍፍል ሶስት አይነት እንደሆነ ለይቶ ማወቅ አይችልም፤ይህም
ጣፊጭ ውሃ፤ጨዋማና መክፈያ(መለያ ክልል) ነው።

ጥቁር ባሕር ከአውሮፓና እስያ አሕጉራት መካከል የሚገኝ ትልቅ ባህር ነው። ይህ ባህር
በተለያዩ የዓለማችን ክፍል ጎብኝዎች በየአመቱ ይጎበኛል። ሳይንቲስቶች አንድ አስገራሚና
ያልተጠበቀ ነገር በጥቁር ባህር ውስጥ አግኝተዋል። ይህም ራሱን ያቻለ ከባህሩ ጋር
የማይቀላቀል ወንዝ ጥቁር ባህር ውስጥ ይገኛል። የወንዙ ጥልቀት 40 ሜትር ነው። ይህ
ጥቁር ባህር ውስጥ ያለው ለየት ያለ ወንዝ መልኩ ሰማያዊ ሲሆን ከሌላ ውሃ ጋር
አይቀላቀልም። ይህ ማለት ጥቁር ባህር ውስጥ የማይደባለቁ ሁለት የውሃ አካላት የራሳቸውን
ፀባይ ይዘው አትንካኝ አልነካህም ተባብለው አብረው ይኖራሉ አንዱ የባህሩ ውሃ ሲሆን
ሁለተኛው የወንዝ ውሃ ነው። ይህ እንዴት ሊሆን ይችላል? የጥቁር ባህር ውሃ ውስጥ ሌላ
ሰማያዊ መልክ ያለው የወንዝ ውሃ አለ። የሚገርመው ሁለቱ የውሃ አካላት አለመቀላቀላቸው
ነው። [39]

35
2.4.2 ጨለማና መእበል በጥልቅ ውቅያኖስ/ባህር ውስጥ

ቅዱስ ቁርኣን ጥልቅ የሆነ ትርጉምን ለማስተላለፍ ምሳሎዎችን ይጠቀማል። በምእራፍ 24


አንቀጽ 40 ለይ ስለ ከሃዲዎች ሁኔታ ሲገልፅ እንዲህ ይላል።

ወይም (መጥፎ ሥራዎቻቸውን) ከበላዩ ደመና ያለበት ማዕበል በሚሸፈነው ጥልቅ ባህር ውስጥ
እንዳሉ ጨለማዎች ነው፡፡ (እነዚያ) ከፊላቸው ከከፊሉ በላይ ድርብርብ የኾኑ ጨለማዎች
ናቸው፡፡ (በዚህች) የተሞከረ (ሰው) እጁን ባወጣ ጊዜ ሊያያት አይቀርብም፡፡ አላህም ለእርሱ
ብርሃንን ያላደረገለት ሰው ለእርሱ ምንም ብርሃን የለውም፡፡ (24:40)
ይህ አንቀፅ የከሓዲዎችን መጥፎ ስራ ምሳሌን የሚገልፅ ነው፡፡ጥልቅ ባህር ውስጥ ጨለማዎች
እንዳሉና በውስጣዊ ማእበሎች እንደተሸፈኑ ያሳያል፡፡ አንቀፁ ሁለት አንኳር ነጥቦችን በውስጡ
ይዞዋል፡፡እነሱም የጥልቅ ባህር ጨለማዎችና የጥልቅ ባህር ውስጣዊ መእበሎች ናቸው፡፡

ማእበሎች የሚከሰቱት በለይኛው የውሃ ክፍል ለይ ብቻ እንደሆነ ተደርጎ ይታሰብ ነበር።


ሆኖም ግን ከለይኛው የባህር ውሃ ለይ ብቻ ሳይሆን ጥልቅ ባህር (deap oceans) ውስጥም
ውስጣዊ ማእበሎች (internal waves) እንደሚገኙ ሳይንቲስቶች ደርሰውበታል። እነዚህ ውስጣዊ
ማእበሎች ለሰው ዓይን የማይታዩና በልዩ መሳሪያና ባለሙያ ብቻ ሊታዩ የሚችሉ ናቸው።
ቅዱስ ቁርኣን የሚገልፀው በውቅያኖስ ውስጥ ስላለው ውስጣዊ ሞገዶች ብቻ ሳይሆን በጥልቅ
ውቅያኖስ ውስጥ ስላለው ጥልቅ ጨለማም ጭምር ነው። አንድ ሰው እስከ 70 ሜትር ወደ
ውስጥ ጠልቆ ሊገባ ይችላል ምክንያቱም እስከ 70 ሜትር ድረስ በቂ ብርሃን ሊያገኝ ይችላል።
ነገር ግን ከ100 ሜትር ያህል ከሄደ ሙሉ ለሙሉ ጨለማ ስለሚሆን ምንም ነገር ማየት
አይችልም። [40]

ቅዱስ ቁርኣን ጥልቅ ባህር ውስጥ ስላለው ጨለማ ከዘመኑ ሳይንሳዊ ግኝት ጋር በሚስማማ
መልኩ ገልፆታል።ቁርኣን ከ1400 ዓመት በፊት የገለፀውን የጥልቅ ባህር ውስጥ ጨለማ ዓለም
ከ ከ1930 በኋላ ነው የደረሰበት። በተጨሪም የሰው ልጅ የባህር መእበል የሚገኘው የለይኛው
የውቅያኖስ ወይም ደግሞ የባህር ክፍል ለይ ነው ብሎ በሚያስብበት ወቅት ቅዱስ ቁርኣን
ከባህር ወለል በታች ጥልቅ ባህር ውስጥም ጭምር መእበል እንደለ ገልፆታል። ዓለም ልክ እንደ
ቁርኣኑ ገለፃ ጥልቅ ባህር በሞገዶች/መእበል የተሞላ መሆኑን የተገነዘበው ከ1930 በኋላ ነው።
ይህ እውነታ በ20ኛው ክፍለ ዘመን በሰላሳዎቹ ውስጥ ሰርጓች መርከቦች ከተፈጠሩ በኋላ ነው
የታወቀው። [41]

ከለይ የተጠቀሱትን መራጃዎች ለማግኘት ሶስት ክፍለ ዘመናትን የፈጀ እልህ አስጨራሽና
ከፍተኛ ምርምሮች ተደርጎዋል። በመቶዎች የሚቆጠሩ ተመራማሪዎችና መርማሪዎችም
ተሳትፈውበታል። ታዲያ ሳይንሳዊ ምርምሮች በሌሉበት ወይም ባልተጀመረበት እና ዓለም
በአፈታሪክ በተሞላች ወቅት ስለ ጥልቅ ባህር ሚስጢሮች ለነቢዩ (ሰ፡ዐ፡ወ) ማን አሳወቀ፡፡
እንኳን ባህር ቀርቶ የመጠጥ ውሃ ለማግኘት አዳጋች በሆነው በአረቢያ ምድረበዳ የኖረና
በህይወት ዘመኑ አንድም ቀን በባህር ተጉዞ የማያውቅ ሰው (ሰ፡ዐ፡ወ) እነዚህን ከባባድ የጥልቅ
የባህርና ውቅያኖስ ትክክለኛ ሚስጥሮች አገኘ? ያገኘውን መረጃ እውነት ስለመሆኑ እንዴት
እረግጠኛ ሆነ? እዚህ ጋር ልብ ያለው ልብ ማለት ይችላል፡፡[41]

36
2.5 ስነ- ፈለክና ቁርኣን
2.5.1 የፀሐይ መሽከርከር

ለረጅም ግዜ አውሮፓውያን ፈላስፎች እና ሳይንቲስቶች ምድር በአፅናፉ ዓለም መካከል ለይ


ሆኖ ፀሓይን ጨምሮ ሌሎች አካላቶች በዙሪያዋ ይሽከረከራሉ ብለው ያስቡ ነበር። ይህ
አስተሳሰብ ከክስቶስ በፊት በሁለተኛው መቶ ዘመን ከቶለሚ (Ptolemy) ዘመን ጀምሮ
ተንሰራፍቶ የቆየ ነበር። እንደ ጎርጎርሳውያኑ ዘመን አቆጣጠር በ1512 ኒኮላስ ካፖርኒከስ
ሄሊዮሴንትሪክ (Heliocentric) የሚባል ንድፈ ሀሳብ በማምጣት ፀሐይ መካከል ለይ ሆና
የማትቀሳቀስ ስትሆን ፕላኔቶች ደግሞ በዙሪያዋ እንደሚሽከረከሩ ይፋ አደረገ። ይህ አዲሱ
ንድፈ ሀሳብ የቀድሞውን ፀሓይ ትሽከረከራለች የሚለው ሀሳብ ውድቅ ያደረገ ነበር።

በ1609 ጀርመናዊው ሳይንቲሰት ዩሓኑስ ኬፕለር (Yohannus Keppler) ‹‹Astonomia


Nova›› በሚል ርእስ ባሳተመው መጽሐፍ ውስጥ ፕላኔቶች በፀሓይ ዙሪያ ብቻ ሳይሆን
በራሳቸው ዛቢያም ጭምር በተለያየ ፍጥነት እንደሚሽከረከሩ ገለፀ። በዚህም አዲስ እውቀት
ምክንያት አውሮፓውያን ሳይንቲስቶች ፀሓይና አጨፋሪዎቿን (sun and solar system)
ጨምሮ የለሊትና ቀን ሁኔታን በትክክል ማብራሪያ መስጠት ችለዋል።

ከነዚህ ሁሉ ግኝት በኋላ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ፀሓይ ልክ እንደ ምድር ሁሉ በራሷ ዛቢያ
አትሽከረከርም የሚል ንድፈ ሀሳብ በሰፊው ተቀባይነት አግኘቶ ነበር።በትምህርት ቤት
በጂኦግራፊ መማሪያ መጽሐፍ ውስጥም እስከ ቅርብ ግዜ ድረስ ይህ ሀሳብ ተካቶ ነበር። እንደ
ኒኮላስ ካፖርኒከስና ዩሓኑስ ኬፕሌር ንድፈ ሀሳብ ፀሐይ የማትቀሳቀስ ወይም የማትሽከረከር
አካል ተደርጋ ብትታይም እንደ ቅዱስ ቁርኣን ግን ፀሓይ የራሷን ሚዛን ጠብቃ ትሽከረከራለች።
ቅዱስ ቁርኣን በምእራፍ 21 አንቀፅ 33 ለይ እንዲህ ይላል።

እርሱም ሌሊትንና ቀንን፣ ፀሐይንና ጨረቃንም የፈጠረ ነው፡፡ ሁሉም በፈለካቸው ውስጥ
ይዋኛሉ። (21:33)
በዚህ የቁርኣን አንቀፅ ውስጥ ‹‹ይዋኛሉ›› ተብሎ የተተረጎመው የአረቢኛ ቃል ‹‹የስበሁን››
የሚል ሲሆን ከማንኛውም ተንቀሳቃሽ አካል የሚመጣውን የመንቀሳቀስ ሀይል ያሳያል። ይህን
‹‹የስበሁን›› ወይም ‹‹ይዋኛሉ›› የሚለውን ቃል እንደ ፀሐይ ላለው ሰማያዊ አካል
ከተጠቀምንበት ‹‹ ፀሓይ በጠፈር ውስጥ ትሽከረከራለች ››የሚለውን ሀሳብ ያሲዛል። ስለዚህ
ቅዱስ ቁርኣን ከ1400 ዓመት የስነ ፈለክ ሳይንስ በማይታወቅበት ወቅት ፀሐይም ጨረቃም
በፈላካቻው ውስጥ እንደሚሽከረከሩ ተናግሮዋል። በዘመኑ ጥልቅ የስነ-ፈለክ ምርምር ውጤት
መሰረት ዓለም በአሁን ሰዓት ልክ እንደ ቅዱስ ቁርኣኑ ገለፃ ፀሓይ ተንቀሳቃሽ አካል ወይም
ደግሞ በራሳ ዛቢያ ለይ የምትሽከረከር መሆኑዋን አምኖ ተቀብሎዋል። የትምህርት ቤት
መማሪያ መጽሐፍትም ይህን ቁርኣኑን እውነታ በማከተት በአዲስ መልክ ብቅ ካሉ ዓመታት
ተቆጥረዋል።

37
በዘመናዊ መሳሪያ በመታገዝ የፀሐይን እሽክርክሪት ለመመልከት ተችለዋል። ፀሐይ በራሷ ዛቢያ
ለመሽከርከር በግምት 25 ቀናት የሚፋጅባት ሲሆን በወተታማው መንገድ (milk way) አንድ
ዙር ተሽከርክራ ለማጠናቀቅ 200 ሚሊዮን ዓመት ይፈጅባታል። [21]

2.5.2 የፀሐይ መጥፋት

ላለፉት አምስት ቢሊዮን ዓመታት ፀሐይ ብርሃን የምታመነጨው በለይኛው ክፍሏ ለይ


በሚካሄዱ የኬሚካል ሂደቶች አማካኝነት ነው። ወደፊት ፀሐይ ብርሃን መስጠት አቁማ ሙሉ
ለሙሉ የምትጠፋበት ግዜ ይመጣል። ታዲያ በዚህ ወቅት ምድር ለይ ያለ ህይወት ሁሉ
ያከትምለታል። ይህን ሳይንስ በቅርብ ግዜ የደረሰበት አስገራሚ መረጃ ቅዱስ ቁርኣን ከማንም
ቀድሞ ፀሐይ ቋሚ እንዳልሆነችና ወደፊት እንደምትጠፋ በምእራፍ 36 አንቀጽ 38 ለይ
አስፍሯል። [21]

ፀሐይም ለእርሷ ወደ ሆነው መርጊያ ትሮጣለች፡፡ ይህ የአሸናፊው የዐዋቂው አምላክ ውሳኔ ነው


፡፡ (36:38)
በዚህ አንቀፅ ውስጥ ‹‹መርጊያ›› ተብሎ የተተረጎመው የአረቢኛ ቃል ‹‹ሙስተቀር›› የሚል
ሲሆን የተወሰነ ግዜ ወይም ቦታ ማለት ነው። አንቀፁ ውስጥ ፀሐይ ወደ ተወሰነላት አቅጣጫ
ትሮጣለች ሲል ፀሐይ እስከተወሰነላት ግዜ ብቻ ነው የምትቆየውማለቱ ነው። ይህ ደግሞ ፀሐይ
ወደፊት እንደምትጠፋ ያሳያል። [21]

ቅዱስ ቁርኣን ምእራፍ 35 እንቀፅ 13 ለይም ፀሐይ እስከተወሰነላት ግዜ ብቻ እንደምትሮጥ


(እንደምትኖር) ይገልፃል።

ሌሊትን በቀን ውስጥ ያስገባል፡፡ ቀንንም በሌሊት ውሰጥ ያስገባል፤ ፀሐይንና ጨረቃንም ገራ፡፡
ሁሉም እተወሰነ ጊዜ ድረስ ይሮጣሉ፡፡ ይህ ጌታችሁ አላህ ነው፡፡ ንግሥናው የእርሱ ብቻ ነው፡፡
እነዚያም ከእርሱ ሌላ የምትግገዟቸው የተምር ፍሬ ሽፋን እንኳ አይኖራቸውም፡፡ (35:13)

2.6 ከብናኝ (አቶም) በታች ቁስ አካል ስለመኖሩ በቁርኣንና ሳይንስ


ነቢዩ ሙሐመድ (ሰ፡ዐ፡ወ) ከመላካቸው ከብዙ ዓመት በፊት አቶሚዝም የሚባል በግሪካዊ
ፈላስፋ ዲሞክሪተስ የተመሰረተው ፅንሰ-ሀሳብ ይታወቅ ነበር። ዲሞክሪተስና ከሱ በኋላ የመጡ
ፈላስፋዎች ቁስ አካል (matter) በጣም ትናንሽ የሆኑ፤የማይበሰብሱና የማይከፋፈሉ አቶም
የተባሉ ነገሮችን በውስጣቸው ይዞዋል ብለው ያምኑ ነበር።አረቦችም ጭምር በዚህ ሀሳብ ያምኑ
ነበር። በአረቦች ዘንድ ትንሹ ቅንጣት ‹‹ዘረህ›› ይባላል። አይከፋፈልም እንዲሁም በስብሶ ሊጠፋ
አይችልም ተብሎ የሚታሰበው ከሁሉም ትንሹ ቅንጣት (አቶም) አሁን ለይ ሊካፈፈል
እንደሚችል በዘመናዊ ሳይንስ የተረጋገጠ ሀቅ ሆኖዋል፡፡

38
ብናኝ ወይም አቶም ከተከፋፈለ ከአቶም (ብናኝ) በታች የሆነ ሌላ ቁስ አካል አለ ማለት
ነው።ይህ አዲስና የቅርብ ግዜ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ግኝት የሆነው ሀሳብ በቅዱስ ቁርኣን ውስጥ
ከ1400 ዓመታት በፊት መጠቀሱ ቁርኣን ከዘመናዊ ሳይንስ ጋር ከመስማማትም አልፎ
የቀደማቸው መሆኑን ያሳያል።

እነዚያ የካዱትም «ሰዓቲቱ አትመጣብንም» አሉ፡፡ በላቸው «አይደለም፤ ሩቁን ሁሉ ዐዋቂ


በኾነው ጌታዬ እምላለሁ፡፡ በእርግጥ ትመጣባችኋለች፡፡ የብናኝ ክብደት ያክል እንኳ በሰማያትና
በምድር ውስጥ ከእርሱ አይርቅም፡፡ ከዚህ ያነሰም ኾነ የበለጠ የለም በግልጹ መጽሐፍ ውስጥ
የተመዘገበ ቢኾን እንጅ፡፡» (34:3)
ይህ የቁርኣን አንቀፅ ከብኛኝ ወይም ቅንጣት ወይም ደግሞ አቶም ያነሰ ቁስ አካል እንዳለ
ይነግረናል። በዘመናዊ ሳይንስ ብኛኝ (አቶም) እንደሚከፋፈል ተረጋግጦዋል። ብናኝ ሲከፋፈል
ደግሞ ከብኛኝ በታች የሆነ ቁስ አካል እናገኛለን ማለት ነው። [42]

2.7 የአፅናፉ አለም (Universe) አመጣጥና ህይወት


አፅናፉ አለም እንዴት ተፈጠረ ከምንስ ተገኘ የሚለው ጉዳይ ሳንቲስቶችን በጣም ከሚያሳስባቸውና
ከተወያዩባቸው ጉዳዮች መካከል አንዱ ነው። በታሪክ ውስጥ ይህን ጉዳይ በተመለከተ ብዙ ንድፈ
ሀሳቦች ቀርበዋል። እያንዳንዱ ፅንሰ-ሀሳብ በሳይንሱ ዓለም ውስጥ በየጊዜው ይሻሻልና በፊት የነበሩ
ሀሳቦች ስህተት ነው ተብለው ይወገዳሉ።

ስለ አፅናፉ አለም አፈጣጠር ዛሬ ለይ በሰፊው ተቀባይነት ያለውና ሳይንቲስቶች የተስማሙበት


ፅንሰ-ሀሳብ አቢይ ፍንዳታ ወይም ቢግ ባንግ ቲዎሪ (big bang theory) የሚባል ነው።ይህ
ፅንሰ-ሀሳብ ሳይንቲስቶች ስለ የአፅናፉ አለም ብዙ ጥያቄዎችን እንዲመልሱ አስችሏቸዋል፡፡
እንደ ቢግ-ባንግ ፅንሰ-ሀሳብ አሁን ያለው አፅናፉ ዓለም ከ13.7 ቢሊዮን ዓመታት በፊት
የመጣው በጣም ሀይለኛና ሞቀታማ ከሆነ ቦታ ነው። ይህን ፅንሰ ሀሳብ ለመጀመሪያ ጊዜ
ያመነጩት ሩሲያዊ የኮስሞሎጂ ባለሙያና የሒሳብ ሊቅ አሌክሳንደር ፍሪድማንና ቤልጄሚያዊ
የፊዚክስ ሊቅ ጆርጅ ለማይትሬ ናቸው። አፅናፉ ዓለም ማነሻ እንዳለው የሚያሳየው የቢግ- ባንግ
ፍንዳታ ንድፈ ሀሳብ በተለያዩ ሳይንስ ሊቃውንት በተለይ በፊዚክስ ሊቃውንት ዘንድ ሰፊ
ተቀባይነትን አግኝቶዋል። በአብይ ፍንዳታ (big bang theory) ፅንሰ ሀሳብ መሰረት አፅናፉ
ዓለም (universe) ተስፋፍቶ የአሁኑን ቅርፅ ከመያዙ በፊት መጀመሪያ በጣም ሀይለኛና ሞቃት
በሆነ ሁኔታ ውስጥ ነበር ማለትም እፅናፉ ዓለም አንድ ቁራጭ አካል ነበረች። ቢግ ባንግ (big
bang) ወይም አብይ ፍንዳታ ተብሎ በሚጠራው ትልቅ ፍንዳታ ምክንያት ይህ ቁራጭ አካል
ወደ ተለያዩ አካሎች ተከፋፈለና አፅናፉ ዓለም አሁን ያለውን ቅርፅ ያዘ።

ይህ በ19ኛው ክፍለ ዘመን በሳይንስ ሊቃውንት የተገኘው አዲስ ግኝት ከ1400 ዓመታት በፊት
በቅዱስ ቁርኣን ተጠቅሶ እናገኛለን። ቅዱስ ቁርኣን በምእራፍ 21 አንቀፅ 30 ለይ እንዲህ
ይላል።

39
እነዚያም የካዱት ሰማያትና ምድር የተጣበቁ የነበሩና የለያየናቸው መኾናችንን አያውቁምን
ሕያው የኾነንም ነገር ሁሉ ከውሃ ፈጠርን፡፡ አያምኑምን (21:30)
የቁርኣኑአንቀፅ መጀመሪያ ለይ ምድርና ሰማይ የተጣበቁና አንድ እንደነበሩ ከዚያም ተለያይተው
የአሁኑን ቅርፅ እንደያዙ ነው የሚነግረን። አንቀፁ ውስጥ የተጣበቁ ተብሎ የተተረጎመው
የአረቢኛ ቃል ‹‹ (ረትቀን) ››የሚል ሲሆን የተዋሀደ፣ የተጣጣመ ወይም ደግሞ የማይነጠል
ማለት ነው።ማለትም ይህ ቃል በአረቢኛ ሁለት በአንድ ለይ የተጣመሩ ነግሮችን ለመግለፅ
ጥቅም ለይ ይውላል።

የቁርኣኑ አንቀፅ ከቢግ ባንግ ፅንሰ-ሀሳብ ጋር የገጠመ ሆኖ እናገኛለን። ሳይንሱ እንደሚነግረን


አፅናፉ ዓለም መጀመሪያ አንድ ንጥረ ነገር ወይም ቁራጭ አካል ብቻ ነበር። ሰማይና ምድርም
በአንድ አይነት የተጠላለፉ የማይነጣጠሉ አንድ ንጥረ ነገር ብቻ ነበሩ። ከዚያም ይህ ንጥረ ነገር
በትልቅ ፍንዳታ ምክንያት ወደ ተለያየ ቁርጥራጭ አካል ተከፋፈለ ወይም ተለያየ። ይህ ማለት
መጀመሪያ ሰማይና ምድር አንደ ለይ በአንድ ንጥረ ነገር ብቻ ነበሩ። ከዚያም ተለያዩና የአሁኑን
ቅርፅ ያዙ።

ዓለም ሰማይና ምድርን ጨምሮ አፅናፉ-አለም መጀመሪያ አንድ አካል እንደነበሩ በኃላ ለይ
ደግሞ እንደተለያዩ በቅርብ ጊዜ የደረሰበት ቢሆንም ቅዱስ ቁርኣንም ይህን እውነታ ከ1400
በፊት አስፍሮታል፡፡ የሚያስገርመው ነገር ቅዱስ ቁርኣን ከሳይንሱ ጋር መስማማቱ ብቻ
ሳይሆን ሳይንሱን በ1400 ዓመታት ቀድሞ መገኘቱ ነው፡፡ ይህን መረጃ ከ1400 ዓመታት በፊት
አለም ባልሰለጠነበት ወቅት በመሃይማን ህዝቦች መካከል በምድረ በዳ የኖረ የማያነብ የማይፅፍ
ሰው (ሰ፡ዐ፡ወ) እንዴት ሊያገኝ ይችላል? ስለዚህ የዚህ መረጃ ምንጩ ከፈጣሪ ውጪ ማንም
ሊሆን አንደማይችል እሙንና ቀቡል ነው፡፡ [43]

ከለይ የተብራራው የቁርኣን አንቀፅ አንድ ሌላ እውነታ በውስጡ አቅፎ ይዞዋል። ይህም አላህ
ህያው የሆነውን ነገር ሁሉ ከውሃ ፈጠርን ይላል። በሳይንስ ሴል (Cell) የህያዋን ፍጥረታት
(ህይወት ያላቸው ፍጡራን) ሁሉ መሰረታዊና መነሻ ክፍል ነው፡፡ ሳይቶፕላዝም (cytoplasm)
የሚባል የሴል መሰረታዊ ንጥረ ነገር ደግሞ 80 በመቶ ውሃ ነው፡፡ የተለያዩ ዘመናዊ
ምርምሮችም አብዛኛዎቹ ፍጥረታት ከ50 እስከ 90 በመቶ ድረስ ውሃ እንደሚይዙ ያሳያሉ፡፡
አስቡት እስኪ ከ1400 ዓመታት በፊት የውሃ እጦት ባለበት የአረቢያ ምድረበዳ የሚኖር
የማያነብ የማይፅፍ እንዲሁም ከአገሩ ወጥቶ የማያውቅ ሰው (አለይሂሰላቱ ወሰላም) እንዴት
እንዴት ልክ ዘመኑ ሳይንስ ህያው ፍጡር ሁሉ የተገኘው ከውሃ ብሎ ሊናገር ይችላል?
በተጨማሪም ቅዱስ ቁርኣን ምእራፍ 24 አንቀፅ 45 ለይም ተንቀሳቃሽ ፍጡር ሁሉ ከውሃ
እንደተፈጠረ ይነግረናል።

አላህም ተንቀሳቃሽን ሁሉ ከውሃ ፈጠረ፡፡ ከእነሱም በሆዱ ላይ የሚኼድ አልለ፡፡ ከእነሱም


በሁለት እግሮች ላይ የሚኼድ አልለ፡፡ አላህ የሚሻውን ሁሉ ይፈጥራል፡፡ አላህ በነገሩ ሁሉ
ላይ ቻይ ነውና (24:45) ። [21]
40
ምእራፍ ሶስት
የነቢዩ(ሰ፡ዐ፡ወ) ንግግሮች እና ተግባራት በሳይንስ እይታ
3.1 የጀርባ አጥንት (የጅራት ጎመድ)

ሙስሊም አቡሁራይራን ጠቅሰው በዘገቡት ሀዲስ ውስጥ ነቢዩ (ሰ፡ዐ፡ወ) እንዲህ ብለዋል፣
የአደም ልጅ ከሞተ በኋላ ምድር ማንኛውንም የሰውነት ክፍሉን ቁርጥም አድርጋ ትበላለች
አንዲት አጥንት ብቻ ስትቀር። የሰው ልጅ ከዚች አጥንት ነው የተፈጠረው እንዲሁም በፍርዱ
ቀንም ከርሷ ነው ኢንዲበቅል የሚደረገው።

ይች ከጀርባ አጥንታችን የታችኛው ክፍል ከዳሌያችን መጋጠሚያ አከባቢ የምትገኝ ትንሽዬ


አጥንት ስትሆን በተለምዶ ጅራት ጎመድ ተብላ ትጠራለች። በአረብኛ ‹‹አጅቡ አዝዘነብ››
የምትታወቅ በጣም ትንሽ የሆነችና የሰናፍጭ ፍሬ የምታክል አጥንት ናት። ይች ትንሽዬ
አጥንት የሰው ልጅ ሲፈጠር ገና በማህፀን ውስጥ እያለ የሰውነቱ መሰረት የሚጣልባት ስትሆን
ከሞተ በኋላ እንዲሁም ስጋውና ሌላው አጥንቱ ከበሰበሰ በኋላ ሁሉ ትኖራለች። ከዚህ ጥንጥዬ
የአጥንት ፍላጭ ነው በፍርድ ቀን የሰው ልጅ ከሙታን ዓለም ስጋ በቅሎበት በአፀድ ነፍስ
የሚቀሰቀሰው። ነቢዩ (ሰ፡ዐ፡ወ) እንዳረጋገጡት አላህ ከሰማይ ውሃ የመሰለ ፈሳሽ ያወርድና
ሙታን ልክ እንደ ዕፅዋት ሁሉ ከየመቃብሮቻቸው ይበቅላሉ።

ነቢዩ (ሰ፡ዐ፡ወ) ከብዙ መቶ ዓመታት በፊት የተነበዩት ይህ ሳይንሳዊ ሀቅ ገና አሁን በቅርቡ


ነው የተረጋገጠው። ዶ/ር መሐመድ አሊ ኤልባር የተባሉ የፅንስ ጥናት ጠቢብ (embryologist)
ጥልቅ በሆነ ፍተሻቸው እንዳረጋገጡት የሰው አካል የተፈጠረው በጣም ለስላሳና ቀጭን ከሆነ
ክር (ፀጉር) መሰል ቁስ (strand) ነው።

ፅንሱ በእናቱ በማህፀን ውስጥ 15ኛውን ቀን ሲይዝ የማህፀን ግድግዳዎች ለይ ይጣበቃል። ይህ


ለስላሳና ቀጭን ቁስ (strand) በሚገባ ከተደላደለ በኋላ የሰው ልጅ አካላት በፅንሱ ውስጥ
መሰረት እየያዙ ይመጣሉ። በተለይም የነርቭ አውታሮቹ (nervous system) የመጀመሪያዎቹ
የጀርባ አጥንት መዋቅሮችና ሌሎችም የአካል ክፍሎች እየዳበሩ መሄድ ይጀምራል። ምክንያቱም
ለዚህ ፀጉር መሳይ ቁስ (strand) አላህ ችሎታን ስለሚሰጠው ህዋሳቶች የየራሳቸውን ባህሪ
እየያዙ እንዲራቡና ወደ ህብረ ህዋስ (tissue) እንዲያድጉ ስለሚያደርግ ነው።እንዲሁም
የተለያዩ ውስጣዊ አካላት (organs) ከህብረ ህዋሶች ጋር ትብብር አድርገው ሰው የተባለውን
የዳበረና በልዩ ቅንብር የተዘጋጀ ፍጡር እንዲገኝ ያደርጋሉ። በጥናት እንደተደረሰበት ይህ ፀጉር
(ክር) መሳይ ቁስ (Strand) ሰው ከሞተ በኋላ የሚበሰብስ ሲሆን ከውስጡ ግን አንድ ትንሽ
አጥንት ብቻ ሳትበሰብስ ትቀራለች። ይች ናት እንግዲህ ‹‹ዐጅቡ አዝዘነብ (የጅራት ጎመድ)››
ተብላ በሀዲስ የተጠቀሰችው።

የቻይናውያን የሳይንቲስቶች ቡድን በቤተ ሙከራቸው ባደረጉት ፍተሻ ይችን ጥንጥዬ አጥንት
ሙሉ በሙሉ ለማጥፋት እንደማይቻል አረጋግጠዋል። እነዚህ ሰዎች ይችን አጥንት በሀይለኛ
አሲድ ዉስጥ ዘፍዝፈው በማቆየት ድራሿን ሊያጠፏት ሞክረዋል ግን አልሆነም። እንዲሁም
በማቃጠል፣ በመደብደብ ( በመውቀጥ)ና ለከፍተኛ ጨረር እንድትጋለጥ በማድረግ ከምድረገፅ

41
ሊያስወግዷት ያላደረጉት ሙከራ የለም ይሁን እንጂ ሁሉም ልፋታቸው ከንቱ ነበር
የሆነባቸው። ይህ የሚያሳየን የነቢዩ (ሰ፡ዐ፡ወ) ሀዲስ ወይም ንግግር በእውነት የተሞላ ብቻ
ሳይሆን ሳይንሳዊ ፍተሻዎችን ሁሉ በብዙ ዘመናት የቀደመ መሆኑን ጭምር ነው።[44]

3.2 ዝምብ የሚጠጣ ነገር ውስጥ ቢገባ

ዝንቦች በምድር ላይ በጣም የተለመዱ ከአከባቢያችን በብዛት የማይጠፉ ነፍሳት ናቸው።


ሳይንሳዊ እውነታዎች እንዳረጋገጡት በዓለማችን ወደ 87,000 የሚጠጉ የዝምብ ዝርያዎች
አሉ።ዝምቦች በአንድ ጎናቸው (ክንፍ) በሽታ አምጪ ጀርሞችን ይዘው ይጓዛሉ። እነዚህ
ጀርሞች በሰው ለይ ጉዳት የሚያስከትሉ ሲሆን ዝምቧንም ጭምር የሚጎዱ ናቸው። ስለዚህ
አንድ ዝምብ ራሳን ከጀርሞች እንድትከላከል በአንድ ክንፏ መርከሻ መድሃኒት ታጥቃለች። ይህ
ባይሆን ኖሮ አንድም ዝምብ ምድር ለይ አይቀርም ነበር። ይህን ሁሉ እውነታ ዓለም በቅርቡ
የደረሰበት፡፡[45]

ከ1400 ዓመታት በፊት የማይፅፉ የማያነቡ ውዱ ነቢይ የሚከተለውን ማለታቸውን ኢማሙ


ቡኻሪና አቡ ሁረይራን ጠቅሰው ዘግቦዋል።

‹‹አንድ ዝንብ በአንዳችሁ መጠጥ ውስጥ ቢገባ ሙሉ በሙሉ በፈሳሹ ውስጥ መጥለቅ አለበት
ከዚያም ያስወግዱት ፣ ምክንያቱም አንዱ ክንፉ በሽታ አለው ሌላኛው ደግሞ ፈውስ አለው "።
ስለ ዝምብና በህሪዋ ማንም ምንም በማያውቅበት ጊዜ ረሱል ሰ፡ዐ፡ወ ዝምብ በአንድ ክንፏ በሽታ
በሌላ ክንፏ መድሃኒት አላት›› በማለት ተናግረዋል።
የሚገርመው በግብፅና በሳዑዲ አረቢያ የሚገኙ የሙስሊም ተመራማሪዎች ቡድን በውሃ፤በማር
እና በተለያዩ ጭማቂዎች ኮንቴይነሮች ላይ በአንድ ወቅት ጥናት አካሂደው ነበር፡፡ ኮንቴኔሮቹ
ውስጥ ዝምቦች እንዲገቡ ተደረጉ። በአጉሊ መነጽር በተደረገው ምርመራ ዝምቦች ሙሉ
ለሙሉ የጠለቁባቸው ፈሳሾች ከባክቴሪያና ቨይረስ ነፃ ስለሆኑ ለመጠጥ መዋል እንደሚችሉ
ተረጋግጥዋል። ታዲያ ነቢዩ (ሰ፡ዐ፣ወ) ያሉት ይህንኑ አይደል። በአንዳችሁ መጠጥ ውስጥ
ዝምብ ቢገባ ሙሉ ለሙሉ ወደ ውስጥ አጥልቃቹ አውጡትና ጠጡ ነው ያሉት። ነቢዩ
(ሰ፡ዐ፡ወ) ይህን ሁሉ መረጃ እንዴት እውቁ? ቅዱስ ቁርኣን ምእራፍ 53 ከአንቀፅ 3 እስከ 4
ደረስ ለዚህ ጥያቄ መልስ አለው፡፡

ከልብ ወለድም አይናገርም፡፡ (53:3)

እርሱ (ንግግሩ) የሚወርድ ራእይ እንጅ ሌላ አይደለም፡፡ (53:4)


ስለዚህ አንድ ነገር ይናገሩ እንጂ እውነት ስለመሆኑ ምንም ጥርጥር የለውም። ከለይ
የተብራራውን ሀዲስ ባትተገብረው አያስቀጠህም። ተግባራዊ ብታደርገው ደግሞ ምንዳ
ታገኝበታለህ። ጉዞ ለይ ሆነክ ውሃ ጥም በጣም አሰቃየክ እንበል። በስንት መከራ የገኘከውን
ውሃ ልክ ልትጠጣ ስትል በድንገት ዝምብ ገባበት። ዝምብ የምትውልበትን ቦታ ስታስብ
ውሃውን መድፋት አሰኘክ። ግን ደግሞ ሌላ ማግኘት አትችልም። ዝምቧን እንዳለ ውሃ ውስጥ

42
ነክረክ ብታወጣነ ውሃውን ብትጠጣ ያለምንም የጎንዮሽ ጉዳት ጥምህን ታረካለህ አጅርም
ታገኝበታለክ። በአንድ ድንጋይ ሁለት ወፍ ማለት እንደዚህ ነው፡፡ የዱንያንም የአኺራንም
ጥቅም ሸመትክ።

3.3 አልፎ አልፎ በባዶ እግር መሄድ

ከመሬት ጋር ንኪኪ ባለ ማድረጋችን ወይም በመቀነሳችን ምክንያት ሰውነታችን ውስጥ


ፖዘቲቭ ቻርጅ (Positive charges) ከጊዜ ወደ ጊዜ ይጠራቀማሉ፡፡ ለዚህ መንስኤነት ግንባር
ቀደም ተጠቃሹ ደግሞ የምንመገበው ምግብ ነው፡፡ በሰውነታችን ውስጥ የተመገብነውን ምግብ
ወደ ሀይል ለመለወጥ በሚደረገው ሂደት ውስጥ ‹‹free radicals (ፍሪ ራዲካልስ)›› የሚባሉ
ኬሚካሎች ይመነጫሉ። እነዚህ ውህዶች ባክቴሪያዎችን እና ቫይረሶችን ጨምሮ በሰውነት
ውስጥ የማይፈለጉ ነገሮችን የማጥቃት እና የማጥፋት ችሎታ ያላቸው በመሆናቸው ቢያንስ
በከፊል አስፈላጊ ሆነው ይታያሉ። ነገር ግን በሰውነታችን ውስጥ free radicals የሚባሉ
ኬሚካሎች በጣም ከበዙ ስር የሰደደ እንደ ስኳር፣የልብ ህመም፣ደም ግፊትና የመሳሰሉ
በሽታዎችን ያስከትላሉ።

ለዚህ ሁሉ መፍትሄ ከሆኑ ነገሮች አንዱ ከመሬት ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ማድረግ ነው፡፡ ይህ
ማለት የሰውነት ቆዳችንን ከአፈርን/መሬት/ ከምድር ጋር ንክኪ እንዲኖረው ማድረግ አለብን።
በተለይ አልፎ አልፎም ቢሆን በባዶ እግር መሬት/አፈር ለይ መሄድ ሁነኛ የሆነ መፍትሄ
ነው።ምክንያቱም የመሬት ገፅ ኔጋቲቭ ቻርጅ ስላለው ነው።ሰውነታችን የሚያመነጨው ‹‹free
radicals›› የሚባሉ ኬሚካሎች ፖዘቲቭ ቻርጅ (Positive charges) ስላላቸው ኔጋቲቭ ቻርጅ
(Negative charges) ካለው የምድር ገፅ ጋር ንክኪ ስፈጥሩ ይጠፋሉ ወይም ደግሞ ይቀንሳሉ።
ሰላምችንም ይመለሳል። ጤናችን በእጃችን ነው ያለው።

ነቢዩ (ሰ፡ዐ፡ወ) አልፎ አልፎ ባዶ እግራቸውን ይሄዱ ነበር ሌሎችንም ያዙ ነበር የሚለውን
ስንሰማ ነገሩ የጤና ጉዳይ ብቻ ሳይሆን የነቢዩ(ሰ፡ዐ፡ወ) ሱና (ፈለግ) ጭምር መሆኑን
እንገነዘባለን። ይህን የመሰለ ለዘመናችን እጅግ አስፈላጊ የሆነ ነገር ጭራሽ የተረሳ ሱና
ሆኖዋል። [46] [47]

ከነቢዩ (ሰ፡ዐ፡ወ) ባልደረቦች መካከል አንድ ሰው ግብፅ ውስጥ ወደ ነበረው ፈዳላህ ኢብኑ
ዑበይድ (ረዲየላሁ ዐንሁ) ተጓዘ፡፡ ከአጭር ውይይት በኋላ ባልደረባው ፈዳልህ ኢብኑ ዑበይድን
‹ለምን በአንተ ላይ ጫማ አላየሁም?› ብሎ ጠየቀው፡፡ ፈዳላህም ነቢዩ (ሰ፡ዐ፡ወ) አንዳንድ ጊዜ
በባዶ እግር እንድንሄድ አዘውናል ብሎ መለሰ ((ኢማም አቡ ዳውድ በሂዲስ ቁጥር 3629 ለይ
ዘግቦዋል። ሼይኩል አልባኒ አል ሲልሲላ አሰሂሃ ቁጥር 502 ለይሰሂህ ብሎውታል። እራሳቸው
ረሱል አልፎ አልፎ ባዶ እግራቸውን ይሄዱ እንደነበር ተዘግቦዋል።

3.4 የነቢዩ (ሰ፡ዐ፡ወ) ወረርሺኝ መከላከያ መንገድ

ነቢዩ ሙሐመድ (ሰ፡ዐ፡ወ) ወረርሺኝ በሚነሳበት ጊዜ ማድረግ ያላብንን ስኬታማ የሆነ አካሄድ
ጠቁመውን አልፏል። ቡኻሪና ሙስሊም እንደ ዘገቡት ነቢዩ (ሰ፡ዐ፡ወ) እንዲህ ብለዋል።

43
‹‹በአንድ ምድር ለይ ወረርሺኝ ከሰማችሁ ወደሱ አትግቡ፣ ወረርሺኑ የተከሰተ ቦታን ደግሞ
አይተው፡፡ በተጨማሪም ኢማሙ አህመድ በዘገቡት ሀዲስ ውስጥም የሚከተለውን ብለዋል።
‹‹ወረርሺን ከላበት ቦታ የሚሸሽ ሰው በአላህ መንገድ ለይ ከመታገል እንደሚሸሽ ሰው ነው።
ትእግስት አድርጎ ባለበት ቦታ የሚቆይ ሰው ደግሞ የሰማእታትን ምንዳ ያገኛል።
ሁለቱ ከለይ የተገለፁት የነቢዩ (ሰ፡ዐ፡ወ) ንግግሮች ወረርሺኝ በሚከሰትበት ግዜ ለመቆጣጠርና
እንደይስፋፋ ለማድረግ ማድረግ ካለብን ነገሮች አንዱ ወረርሺኝ ወደ ተነሳበት ቦታ አለመጓዝ
ሲሆን እኛ ያለንበት ስፍራ ወረርሺኙ ከተከሰተ ደግሞ ለሌሎች አከባቢ እንዳይሰራጭ ለማድረግ
ያለንበት ስፍራ ለቀን መሄድ እንዳሌለብን ይመክሩናል። ይህ አካሄድ ወረርሺኝ በሚከሰትበት
ወቅት እንቅስቃሴን መግታት እንዳለብን ያሳያል።

ዘመናዊ ሳይንስ ረቂቅ ተህዋሲያን (micro organisms) የሚባዙበትን መንገዶችና የሚያስከትሉትን


በሽታዎች ደርሰውበታል። የሳይንስ ሊቃውንት እንዳረጋገጡት በወረርሺኙ ቦታ ለይ ምንም ምልክት
የሌለባቸው ጤናማ ሰዎች ቀድሞውኑ ረቂቅ ተህዋሲያን (micro organisms) ስለተሸከሙ ወደ ሌላ
ቦታ በሚዘዋወሩበት ወቅት በሽታ ሊያስተላልፉ ይችላሉ። ስለዚህ ጤናማ ሰዎች ቢሆኑም እንኳ
ወረርሺኑ የተከሰተበትን ቦታ ለቀው ወደ ሌላ አከባቢ መሄድ የለባቸውም።

በነቢዩ (ሰ፡ዐ፡ወ) ጊዜ እንዲሁም ከሱ በፊትም ሆነ በኋላ ማይክሮብስ (microbes) የሚባሉ


በሽታ አምጪ ረቂቅ ተህዋሲያን እስከተገኙበት ጊዜ ድረስ ሰዎች ወረርሺኞች የሚከሰቱት
በአጋንንት፣በአጋንንትና በከዋክት ምክንያት ነው ብሎ ያስቡ ነበር፡፡ በዚህም ምክንያት
ለወረርሺኙ ፈውስ ለማግኘት ወደ ጥንቆላና አስማት ያመሩ ያመራሉ።

ዓለማችን በዚህ ሁኔታ ለይ ባለችበት ሰዓት ነው ነቢዩ (ሰ፡ዐ፡ወ) የተለያዩ በሽታዎችንና


መቅሰፍትን ለመከላከል ያስችል ዘንድ ኳረንታይን የሚባል ለዘመናችን ትልቅ መሰረት የሆነ
ስርዓት ያቋቋሙት። ነቢዩ (ሰ፡ዐ፡ወ) ባልደረቦቻቸውን ‹‹ወረርሺኑ ካለበት ቦታ ለቃችሁ
አትውጡ እንዲሁም ወደ ወረርሺኙ ክልልም ጉብኝት አታድርጉ›› ከማለት አልፈው ትእዛዛቸው
በትክክል ስለመከናወኑም ጭምር ያረጋግጡ ነበር።

አንድጤናማ የሆነ ሰው ከሁለት መቶ ዓመታት በፊት ወረርሺን ያለበትን ቦታ ለቆ እንዳይሄድና


እዛው እንዲቆይ ቢጠየቅ ኖሮ ጥያቄውን ከምንም ሳይቆጥር ለመኖር ካለው ፍላጎት አንፃር ወደ
ሌላ ቦታ ይሸሽ ነበር። የነቢዩን (ሰ፡ዐ፡ወ) ትእዛዝ በማክበር በወርረሺኝ ግዜ ሸሽተው የማይሄዱት
ሙስሊሞች ብቻ ናቸው። ነገር ግን ጤናማ ሆነው የሚታዩ ሰዎችም ጀርም ተሸካሚዎች ሊሆኑ
እንደሚችሉና ወደ ሌላ ቦታ መሄዳቸው በሽታውን እንደሚያስፋፋ በዘመናዊ ሳይንስ
እስከሚረጋገጥ ድረስ ሙስሊሞች ያልሆኑ ሰዎች ከወረርሺኙ ቦታ ለቆ የማይሄዱትን ጤናማ
የሆኑ ሙስሊሞችን ቢያዩ ይሳለቁባቸው ነበር። [48]

በአሁን ሰዓት ወረረሺኝን ለመከላከል የተለያዩ አገሮች የሚከተሉት ኳረንታይን የሚባል ዘዴ


መሰረት የተጣለው በነቢዩ ሙሐመድ (ሰ፡ዐ፡ወ) ነው፡፡ ወረርሺን ካለበት ቦታ አትግቡ እንዲሁም
ወረርሺኝ የተከሰተበትን ቦታ ለቃችሁ አትሂዱ በማለት እንቅስቃሴ እንዲገታ ለተከታዮቻቸው
ትእዛዝ አስተላልፈው ነበር፡፡ ይህን የነቢዩ (ሰ፡ዐ፡ወ) ፈለግ ዓለማችን ለይ በቀጥታም ሆነ
በተዘዋዋሪ ተግባራዊ እየተደረገ ይገኛል፡፡

44
3.5 ወተት ከተጠጣ በኃላ አፍን በውሃ መጉመጥመጥ
እንደሚታወቀው ጠንካራ አጥንቶችን በመገንባት ረገድ ካልሺየም (Calcium) የሚባል ንጥረ ነገር
በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ወተትና የወተት ተዋፅኦዎች በዚህ ንጥረ ነገር በጣም የበለፀጉ ናቸው፡፡
አንድ ኩባያ ወተት 300 ሚሊግራም ካልሺየም በውስጡ ይዞዋል፡፡ ወተት ጥርስንና የጥርስ
አጥንቶችንም ጭምር ጤንነታቸውን ይጠብቃል፡፡ ስለዚህ ወተት ለጥርስ ጥሩ ስለመሆኑ ምንም
አያጠያይቅም፡፡

በወትተ ውስጥ የሚገኘው ካልሺየም ህፃናት ጠንካራ የመጀመሪያ እና ቋሚ ጥርስ እንዲዳብሩ


ይረዳል፡፡ ወተት ከካልሺየም ውጪ የስኳር ምንጭም ነው፡፡ ቢሆንም ግን ወተትን መጠጣት
እንድናቆም አያደርገንም፡፡በወተት ውስጥ ያለው ስኳር ላክቶስ (Lactose) የሚባል ሲሆን በትንሹ
በጥርሶቻችን ለይ ጉዳት ያደርሳል፡፡

ወተት ውስጥ ያለው ካልሲየም የሚባል ንጥረ ነገር ለአጥንት ጥንካሬ እንዲሁም ደግሞ ለጥርስ
ጤንነት በጣም ጠቃሚ ቢሆንምወተት ጠጥተን ስንነሳ አፋችንን በውሃ ማለቅለቅ/መጉመጥመጥ
ወይም ደግሞ ጥርሳችንን መፋቅ እንዳለብን የጥርስ ሀኪሞች ይመክራሉ። ምክንያቱም ወተት
ውስጥ ያለው ላክቶስ (Lactose) የሚባል የስኳር አይነት ጥርሳችን ለይ ለረጅም ግዜ ከቆየ
ጥርሳችንን በግዜ ሂደት የመቦርቦር አቅም ስላለው ነው።

እኛ የምናስበው ወተት ለህፃናት ጥሩ እንደሆነ ብቻ ነው። ስለሆነም አብዛኛውን ጊዜ ልጆቻችንን


ማታ ለይ ወተት ጠጥተው በዛው እንዲተኙ እናደርጋቸዋለን፡፡ ስንቶቻችን ነን ወተት
አጠጥተናቸው በዛው የምናስተኛቸው። ወተት በተደጋጋሚ ለረጅም ግዜ የምንጠቀም ከሆንን
አፋችንን በውሃ መጉመጥመጥ ወይም ደግሞ ጥርሳችንን ብንፍቅ ይመከራል። [49]

ታዲያ ታለቁ ነቢይ (ሰ፡ዐ፡ወ) ያደረጉት ይህንኑ አይደል፡፡ ቡኻሪ እና ሙስሊም ኢብኒ አባስን
ጠቅሰው እንደዘገቡት ‹‹ነቢዩ (ሰ፡ዐ፡ወ) ወተት ጠጡና አፋቸው በውሃ ተጉመጠመጡ። ከዚያም
ስብ አለው አሉ››። ይህ ሳይንሳዊ ጥቅም ያዘለ የነቢዩ (ሰ፡ዐ፡ወ) ሱና (ፈለግ) አሁን ለይ እስከ
መረሳት ጭምር የደረሰ ነው፡፡

45
ዋቢ መጽሐፍት
[1] Doufesh H, Ibrahim F., Ismail NA., Ahmad WA (2014). Effect of Muslim prayer (salat) on
α Electroencephalography and its relatiohsip with Automatic Nervous System Activity. The
Journa of Alternative and Complimentary mediine, Volume 20, number 7, Pp. 558 – 562

[2] Medical Benefits of Prayer. 06/07/2010. www.islamweb.net

[3] Amazing Benefits of Prostration in Islam and New Science on “Earthing’’. The Deen show
Greatings of Peace.

[4] Doufesh H, Ibrahim F., Ismail NA., Ahmad WA. Assessment of heart rates and blood
pressure in different salat positions. Journal of Physical Therapy Science, from internate benefit
of Islamic prayer

[5] Islamweb.net (2012). Fasting is a Scientific Miracle - I. Retrived from


https://www.islamweb.net/en/ramadan/article/179041/

[6] Islamweb.net (2012). Fasting is a Scientific Miracle - II. Retrived from


https://www.islamweb.net/en/ramadan/article/179043/

[7] Abduldaem Al-kaheel (n.d). Secrets of Fasting-2. www.kaheel7.com/eng


[8] Abduldaem Al-kaheel (n.d). Secrets of Fasting-1. www.kaheel7.com/eng
[9] Islamway.net (2012). The Scientific Signs in Fasting the White Days.
[10] Dr. Ghulam Mustafa Khan (1982). AL- Dhabh. Slaying Animals for Food the Islamic
Law. Islamic Medical Association London and TaHa Publishers Ltd, London.
[11] Requirements of Animal Slaughtering, in accordance with the provision of Islamic Sharia.
[12] Islamweb.net (2010).The Miracle of Slaughtering in Islam. Retrived from
https://www.islamweb.net/en/article/161841/the-miracle-of-slaughtering-in-islam

[13] Hajimohammadi, B. Ehrampoush, M.H. and Hajimohammadi, B. (2014). Theories about


effects of Islamic Slaughter Laws on Meat Hygiene. Health scope, 3(1).
[14] AraweeloNews network (2020). Muslim woman is the cleanest on earth.
https://www.arawelonews.com
[14] Saalamedia (2018). Muslim woman is the cleanest on earth.

[16) Dr Gohar Mushtaq (n.d). Scientific and Islamic reasons for growing beard.
[17] Abduldaem Al-kaheel (n.d). Benefits of Beards. www.kaheel7.com/eng
[18] Fetters, K.Alesia (2013).5 lesser known benefits of having a beard
[19] Stacey, Aisha (2011). Why Pork is Forbidden in Islam: Obeying the Law of God.
www.IslamReligion.com

46
[20] Abu Subhan (n.d). Linguistic, Historic, Futuristic, and Scientific Miracle of the Quran.
http://www.hasbunallah.com.au
[21] Dr. Zakir Naik. The Qur’aan and Modern Science. Compatible or Incompatible? Islamic
Research foundation.
[22] Brain functions. https://www.miracles-of-quran.com
[23] Curley, Allison (2013). The Truth about Lies. The Science of Deception. BrainFacts.org
[24]
[25] Binimad Al-Ateeqi (2017). Quran Mathemathical Miracles.An Undeniable Miraculous
Code.
[26] Honey Bees. https://www.miracles-of-quran.com
[27] Taslaman, Caner (2006). The Quran. Unchallengeable Miracle. Citlembic publications
[28] Dr.Tauseef Ahmad Khan (2020).Honey: A cure for man kind? www.alhahkam.org

[29] Islamweb.net (2014).The miracle of honey as alternative medicine. www.islamweb.net

[30] Beki, Niyazi (n.d). A Miracle of the Quran. Retrived from


https://questionsonislam.com
[31] IslamReligion.com (2018). The Quran on Spider Webs. Retrived from www.
IslamReligion.com

[32] Harun Yahya (2000). The Miracle in the Ant. Published by Vural Yayincilik, Istanbul,
Turkey.

[33] Ants. Nationalgeographic.com May 10, 2011)

[34] Lupo, Lisa Jo (2019). Why ants have wings only sometimes during the year?

[35] Milk. https://www.miracles-of-quran.com

[36] Dead Sea - Wikipedia. Retrived from https://en.m.wikipedia.org/wiki/dead-sea

[37] Dead Sea. https://www.miracles-of-quran.com

[38] A.O (2007).The Miracle of Quran. www.IslamReligion.com)

[39] I.A. Ibrahim (2012). እስልምናን ለመገንዘብ አጭር ስዕላዊ ማስረጃ. www.alukah.net

[40] IslamHouse.com (2014). Some of Scientific Miracles in Brief

[41] AL-Shaykh. Abdul-Majeed AZeez AL-Zindani (2009). Interna Waves and ‘’Quran on
Oceanography. quranand science.com

47
[42] Dr. Garry Miller (1992). The Amazing Quran. Abul-Qasim Publishing house (AQPH)

[43] The splitting Asunder of the Earth and the Skies. Retrived from
https://questionsonislam.com

[44] Zaghlul El-Naggar (2004). Treasures in Sunnah. A scientific Approach. Al-Falah


Fpundation

[45] Abduldaem Al-Kaheel (n.d). New facts: the flies have a cure. www.kaheel7.com/eng

[46] Wells, Katie (2019). Earthing and Grounding: Legit or Hype? (How to and When not to).
Retrived from https://wellnessmama.com/5600/earthing-grounding/

[47] Isaac Elias, Kick of your shoes: Surprising MD-Approved Benefits of Walking Barefoot.
Mindbodygreen.com.

[48] Website manager (2012). Quarantine: A Prophetic Discovery.quranandscience.com


[49] PLD (n.d). How milk affect your teeth? Retrived from
https://www.pomptonlakesdentstry.com

48

You might also like