Professional Documents
Culture Documents
የንባብ ክህልት
የቅዴመ ግቢ ጉባኤ ተማሪዎች መርሏግብር ማሰሌጠኛ ማንዋሌ
0
ሚያዝያ 2010 ዓ.ም
ማዉጫ
1
ምዕራፌ አንዴ
አንብቦ መረዲት
የአንብቦ መረዲትን ዝርዝር ሃሳቦችን ሇማንሳት ከመሞከራችን በፉት በቅዴሚያ ንባብ ማሇት ምን
ማሇት ነው? የሚሇውን ጥያቄ መሌሰን ሇማሇፌ እንሞክር፡፡ ምናሌባት ንባብ ማሇት ምን ማሇት ነው? የሚሇውን
ጥያቄ ቀሊሌና ማንም ሰው ሉመሌሰው የሚችሇው ዓይነት ጥያቄ አዴርጎ የሚገምት ሰው ሉኖር ይችሌ
ይሆናሌ፡፡እንዱህ አዴርጎ የሚገምት ሰው ግምቱ የተሳሳተ ነው፡፡
ንባብ ማሇት ምን ማሇት ነው? ወይም ንባብ ምንዴን ነው? የሚሇውን ጥያቄ በቀሊለ መመሇስ አይቻሌም፡፡
ንባብ በራሱ ውስብስብ ሂዯት ነው፡፡ ረቂቅ የሆነ አእምሮታዊ ሂዯት በውስጡ የመጠቃሇለ ሁኔታ ነው ሂዯቱን
ውስብስብ ያሰኘው፡፡ ሇዚህም ሳይሆን አይቀርም እነ አሌዯርሰን /1984፣1/ ንባብ ምንዴንነው? የሚሇውን ጥያቄ
በቀሊለ ሇመመሇስ መሞከር ሞኝነት ወይም የዋህነት ነው ሲለ የሚገሌፁት፡፡
የንባብን ምንነት በተመሇከተ በቀሊለ ምሊሽ ሇመስጠት ስሇሚያዲግትም የተሇያዩ ምሁራን ንባብ ምንዴንነው?
የሚሇውን መሰረታዊ ጥያቄ በተሇያየ መንገዴ ሲበይኑት ይታያሌ፡፡ ሁለንም ብያኔዎች መዲሰስ አይሞከርም
አጠር ባሇ መንገዴ የተቀመጠውን ብያኔ በማስፇር የንባብ ምንነት ሇመግሇጽ እንሞክራሇን፡፡ ንባብ ከዚህ
የሚከተለትን ነጥች ያጠቃሌሊሌ፡፡
ሀ. መረዲት፣መገንዘብ፣ትርጉም፣ስሜት ወዘተ…
ሇ. መነጠሌ፣መሇየት፣መቁጠር/ሇሆሄያት/
የሚለትን በአንክሮ ስናስተውሌ እውነትም ንባብ ከእይታ ባሻገር በርካታ ውስብስብ አእምሮአዊ
ተግባራትን ያቀፇ መሆኑን እንመሇከታሇን፡፡ ሂዯቱም ሆሄያትን ከመሇየት አንስቶ፣አገጣጥሞ ማንበብና
መገንዘብን የሚያጠቃሌሌ ሰፉ ሂዯት ነው፡፡ ሰፉ ሂዯት በመሆኑም እንዯ ህፃን የት/ቤትን ዯጃፌ ከረገጥንበት ጊዜ
አንስቶ እስከ እዴሜያችን መጨረሻ ዴረስ የምናዲብረውና የምናሳዴገው መሰረታዊ ክሂሌ ነው፡፡ ንባብ
በየዯረጃው እያዯገና እየዲበረ የሚመጣ ነው፡፡ ከዚህ ቀጥሇን የአንብቦ መረዲትን ምንነት ሇመመሌከት
እንሞክራሇን፡፡
2
የአንብቦ መረዲት ምንነት
አንብቦ መረዲት ማሇት ከአንዴ አሀዴ ውስጥ ተፇሊጊውን መረጃ በብቃት ማሰባሰብ መቻሌ ማሇት ነው፡፡
በዚህ ዓይነቱ ሂዯት ውስጥ አንባቢው የማይፇሇገውን መረጃ እያንጉዋሇሇ በመተው የሚፇሌገውን ዓይነት ብቻ
ሉመርጥ ይችሊሌ፡፡ ከዚህም በቀር የአንደን አሀዴ መሰረታዊ ሀሳብ ከመረዲትም ባሻገር የአሀደን ዝርዝር
በብቃት የሚገነዘብበትም ሁኔታ የሚጠቃሇሇው እዚህ ውስጥ ነው፡፡ ይኸው የተነበበውን ይዘት ምክንያት
የመረዲት፣የመገንዘብ ትርጉምና ስሜት የማፇሊሇግ ባህርይ ይታይበታሌ፡፡
አንብቦ መረዲት ሁሌጊዜም አንዴ ዓይነት ነው ማሇት አይዯሇም፡፡ አንብበን ሇመረዲት በምናዯርገው
ጥረት የተሇያየ የአነባበብ መንገዴ እንከተሊሇን፡፡ እንዯሚነበበው አሀዴ አይነትና እንዯሚነብበት ዓሊማ የተሇያዩ
የአነባበብ መንገድችን መከተሌ ሉዲብር የሚገባው፣ትኩረትም ሉዯረግበት የሚገባ መሰረታዊ ጉዲይ ነው፡፡
በስፊት የሚታወቁትና አዘውትሮም ተግባር ሊይ የሚዉለት የንባብ መንገድች ከዚህ የሚከተለት ናቸው፡፡
3
እነዚህ ከፌ ሲሌ የተጠቀሱት የአነባበብ መንገድች ተዯጋጋፉ መሆናቸውን ማስተዋሌ ያስፇሌጋሌ፡፡ አንዴ
አንባቢ እነዚህን የአነባበብ አይነቶች ጥቅም ሊይ ሉያውሊቸው ይችሊሌ፡፡ከዚህ ውጪ በሆነ መንገዴ አንደ
ከላሊው ጋር የማይዛመዴ ወይም ፌፁም ራሱን የቻሇ ተዯርጎ መታየት የሇበትም፡፡ አንደን የአነባብ መንገዴም
ከላሊው ጋር እያቀናጀን እንጠቀማሇን፡፡
በጽሐፌ ውስጥ በግሌጽ ከሰፇሩና ካሌሰፊሩ መረጃዎችና ፌንጭዎች ወይም ከቀዯመ እውቀት በመነሳት ወይም
ሁሇቱን በቅንጅት በመጠቀም የቃሊትና የሏረጋት ትርጉም ማወቅ ያስፇሌጋሌ፡፡
ምሳላ፡ በሊ = ተመገበ
ሄዯ = ተጓዘ
ከሊይ የቀረበውን ቃሌ (በሊ) የሚሇው ከአገባቡ አንፃር የተሇያየ ትርጉም ሉኖረው ችሎሌ፡፡ ስሇዚህ ላልችንም
ቃሊት እንዯየ አገባባቸው የትርጉም ሇውጥ ስሇሚያመጡ በምንነብ ሠዓት በአግባቡ መገንዘብ ያስፇሌጋሌ፡፡
4
ሏ/ የፇሉጣዊ አነጋገሮችን ፌቺ ከአገባባቸው መረዲት
በቃሊት ምርጫ ሂዯት ግብ መቺ ቃሌ ሇመጠቀም የዘይቤ አጠቃቀምን በወጉ መረዲት ያሻሌ፡፡ ዘይቤ በንግግር
ወይም በጽሐፌ የሚተሊሇፌ ሃሳብ እና ስሜት ምጥቀትና ጥሌቀት ባሇው መንገዴ ሇመግሇጽ የምንጠቀምበት
ስሌት ነው፡፡ በዚህም ዘይቤ ሀሳብን ሇየት ባሇ መንገዴ ሇመግሇጽ ሲታሰብ፣ሆነ ብል ከተሇመዯው የቋንቋ
አጠቃቀም ማፇንገጥ ነው፡፡
የዘይቤ አጠቃቀም ስሌት በቋንቋ አጠቃቀም ሂዯት ሇቃሊት ምርጫ ግብ መችነት የሚዋቀረው ሉተሊሇፌ
ከተፇሇገው አሳብ ወይም ጉዲይ ባህሪ አንፃር በተሇይም ረቂቅ የሆኑ ጉዲዮችን ተጨባጭ በሆነ መንገዴ
ሇመግሇጽ ሲታሰብ ዘይቤያዊ አጠቃቀም መጠቀም ነው ምክንያቱም ዘይቤዎች በነገሮች፣ሁኔታዎች፣ዴርጊቶችና
ባህርያት ወዘተ መካከሌ ያለትን ዝምዴናዎች ወይም ሌዩነቶች በማወዲዯር ሇመግሇጽ ያስችሊሌ፡፡
ዘይቤ የሚታወቁና ረቂቅ ጉዲዮችን ብቻ ሳይሆን ወትሮአዊ የሆኑ ግሌጽ ጉዲዮችንም አግዝፍ ሇስሜት
በማቅረብ የሚባሇው ነገር በአእምሮ ውስጥ እንዯ ስዕሌ እንዱታይ ሇማዴረግ ስሇሚያስችሌ ጠቃሜታው የጎሊ
ነው፡፡ ንግግር አዋቂ ነው የሚናገረው መሬት ጠብ አይሌም አፌ ያስከፌታሌ ወዘተ የሚባሌሊቸው ሰዎች
በአብዛኛው ንግግራቸው ዘይቤያዊ ስሇሆነ ነው፡፡ ባሇቅኔ ሉቅ የጠሇቀ እውቀት አሇው ወዘተ የሚባሌሇትም
ሰው እንዱሁ ሃሳቡን በዘይቤያዊ ስሌት መግሇጽን የሚያዘወትር ሰው ነው፡፡
በአጠቃሊይ ዘይቤ የአዴማጭን ወይም የአንባቢን ስሜት ሇመግዛት ሃሳቡን ግሌጽ፣ጥሌቅና ስሜት ነኪ በሆነ
መሌኩ ሇማስተሊሇፌ መሌዕክትን በተቀባዩ አዕምሮ ውስጥ በስዕሊዊ መንገዴ ሇማቅረብ ፌሬ ነገር በአዕምሮ
በማቆየት ምስሌ ፇጥሮ ትውስታ እንዱኖር ሇማዴረግ ወዘተ የሚያስችሌ የቋንቋ አጠቃቀም ስሌት በመሆኑ
5
አንባቢ የዘይቤ አይነቶችን ጠንቅቆ ካወቀ በጽሐፌ ውስጥ የገባውን ሃሳብ በቀሊለ መረዲት ስሇሚችሌ የዘይቤ
ዓይነቶች ብዙ ቢሆኑም ዋና ዋናዎቹን እንዯሚከተሇው ሇማቅረብ ተሞክሯሌ፡፡
ተሇዋጭ ዘይቤ በቀጥታ ሇውጥ /ባህሪን፣ቁመናን ቅርጽን ዴርጊትን ወዘተ በቀጥታ በመሇወጥ የሚገሌጽበት
ዘይቤ ነው፡፡
ምሳላ
ከሊይ የቀረቡት ተሇዋጭ ዘይቤዎችን ስንመሇከት ሁሇት ነገሮች ከተሇያየ ጎራ ማሇትም ሠናይት
በቀሇ፣ሂሩት፣ከሰው ወገን ሲሆኑ ልሚ ከፌራፌሬ ወገን፣ፌሌጥ ከእንጨት ወገን ንብ ከእንስሳት ወገን በመውሰዴ
የአንደ ባህሪይ ሙለ ሇሙለ በማሌበስ ሲያነፃፅር እናያሇን፡፡
ምሳላ፡- ሂሩት ንብ ናት ስንሌ የንብ ሙለ ባህሪይ ሇሂሩት ተሰጥቷሌ፡፡ ይህ ማሇት ሂሩት ጠንካራ
ሠራተኛ ወይም እንዲንቧ መርዝ የሆነ አሳብ እንዲሊት እንዱሁም መሌከ ጥፈ እንዯሆነች በአንዴ ሃሳብ አጠር
መጠን ባሇ መሌኩ የሂሩት አጠቃሊይ ባህሪይ ተገሌፆሌ፡፡
ተነፃፃሪ ዘይቤ እንዯ ተሇዋጭ ዘይቤ ሁለ ነገሮችን በማወዲዯር በመካሊቸው ያሇውን የጋራ ጉዲይ በመሇየት ጎን
ሇጎን የአንደን ባህሪይ ከላሊው አንፃር የሚገሌጽ ነው፡፡ ከተሇዋጭ ዘይቤ የሚሇየው የማነፃፀሪያ ቃሊትና
ሏረጋትን በመጠቀሙ ነው፡፡
(እንዯ፣ያህሌ፣ይመስሌ፣ከ….ጋር ይወዯዲራሌ ከ….. ይነፃፀራሌ ወዘተ) ተነፃፃሪ ዘይቤ የአንደን ባህሪይ ሇላሊው
በከፉሌ እንጂ ሙለ ሇሙለ አይሰጥም፡፡
ምሳላ
በተራ ቁጥር አንዴ ሊይ ያሇውን ምሳላ ስንመሇከት የአንበሳው ባህሪይ በከፉሌ ከአሇሚቱ ክንዴ ጋር ሲነፃፀር
እናያሇን፡፡ ይህ ማሇት የአንበሳ ክንዴ ብርቱ ነው፡፡ የአስቴርም ክንዴ ብርቱ መሆኑን እንዯ የሚሇው ማነፃፀሪያ
ቃሌ በመውሰዴ ጸሏፉው ሃሳቡን ገሌጧሌ፡፡
ሰውኛ ዘይቤ ሰው ያሌሆኑ ፌጥረታት የሰውን ዴርጊት እንዱፇጽሙ በማዴረግ ሃሳብ የሚገሇጽበት ዘይቤ ነው፡፡
የዘይቤው ዋነኛ መሇያ ዴርጊት መፇፀም ነው፡፡
ምሳላ
ከሊይ የቀረቡትን ምሳላዎች ሰማዩ፣ኢትዮጵያና ምዴር ሰዎች አይዯለም ነገር የሰውን ባህርይ ማሇት መከሌከሌ፣
እሌሌ፣ ማሇት፣ ማህፃን መዝጋት የሚለትን ባህርያት በማሊበስ ፀሏፉው ሃሳቡ ሲገሌጽ እናያሇን፡፡ እንዱህ
አይነቱ አገሊሇጽ ሰውኛ ዘይቤ በመባሌ ይታወቃሌ፡፡
ተምሣላት የውክሌና ዘይቤ ነው፡፡ አንዴ የሆነን ነገር ፀሏፉው (ዯራሲው) ሇሚገሌፀው ሃሳብ በውክሌና
የሚያቆምበት የዘይቤ አይነት ነው፡፡ የተምሳላት ዘይቤያዊ ውክሌና ዓሇም አቀፊዊና ሁሇንተናዊ፣አገራዊ
(ብሔራዊ) እና ግሊዊ ተብል ይከፇሊሌ፡፡ተምሳላቱ በምሌክት ወይም በቃሌ ሉገሇጽ ይችሊሌ፡፡
ምሳላ
መስቀሌ---- ክርስትና
ጨረቃ----- እስሌምና
ርግብ------ የሠሊም ምሌክት
ከሊይ የተጠቀሱት ዓይነት በየትኛውም ሕዝብ ዘንዴ ወጥ ውክሌና ያሊቸው ምሌክቶች ሁሇንተናዊ
(ዓሇም አቀፊዊ) ተምሳላት ይባሊለ፡፡
7
ፌሬ = ሌጅ
አበባ = ወጣትነት
ጨረቃ = ውበት
ተክሌ(ሇጋ) = ህፃንነት
በግ = የፃዴቃን (የዋህ)
ጎጆ = ትዲር
በአጠቃሊይ አንዴ አንባቢ የዘይቤ ዓይነቶች ጠንቅቆ ማወቁ ዯራሲው የፃፇውን ሀሳብ በቀሊለ የመረዲት
አቅሙ ከፌተኛ ነው፡፡
8
በዘመናችን ግዝፌ ችግራችን የኤዴስ በሽታ ይመስሇኛሌ፡፡ ወዘተ በማሇት ሰዎች ከእራሳቸው ስሜት
በመነሳት የሚገሌፁት ሃሳብ ነገር ግን ሁለንም ማኀበረሰብ ሉያስማማ የማይችሌ ነገር አስተያየት ይባሊሌ፡፡
ስሇዚህ አንባቢው በሚያነብበት ጊዜ እውነታን ከአስተያየት የማይሇይ ከሆነ አስተሳሰቡ በተሳሳተ መንገዴ
ሉሆን ስሇሚችሌ ጥንቃቄ ማዴረግ ያስፇሌጋሌ፡፡
9
የንባብ ጠቀሜታ
ንባብ በጣም ብዙ የሆነ ጠቀሜታዎች ቢኖሩትም የተወሰኑትን ሇማየት እንሞክራሇን፡፡
1. የማናዉቃቸው ነገሮች እናውቃሇን፡፡ ዮሏ 21÷25
2. ያሇንን እውቀት የበሇጠ እናሰፊበታሇን ዮሏ 5÷4 ዮሏ 5÷39
3. ወቅታዊ መረጃዎችን ሁለ ጊዜ በማግኘት በዘመኑ ከተቀየሩ አስተሳሰቦች ጋር አብረን መራመዴ እንችሊሇን፡፡
4. ሕይወታችንን ከአዯጋ እንጠብቃሇን፡፡ ሇምሳላ መዴኃኒቶች ጊዜያቸው ያሇፇባቸው እንዲንጠቀም እንዱሁ
መመሪያዎችን በማክበር አዯጋ ሉያመጡብን ከሚችለ ነገሮች እራሳችንን እንጠብቃሇን፡፡ 2ጢሞ 3÷16
5. ሇመዝናናት
6. እውነታን ከአስተያት ሇመሇየት
7. ሇመጽናናት ወዘተ ጠቀሜታ አሇው
10
በመጽሏፌ ያሇውን ትንቢት ሁለ ማንም ሇገዛ ሇራሱ ሉተረጉም አሌተፇቀዯም፣ትንቢት ከቶ በሰው ፇቃዴ
አሌመጣምና፣ዲሩ ግን በእግዚአብሔር ተሌከው ቅደሳን ሰዎች በመንፇስ ቅደስ ተነዴተው ተናገሩ፡፡
2ጴጥ 1÷20
ፉሌጶስም ሮጠ የነቢዩን የኢሳይስን መጽሏፌ ሲያነብ ሰማና በእውኑ የምታነበውን ታስተውሇዋሇህን አሇው፡፡
እርሱም የሚመራኝ ሳይኖር ይህ እንዳት ይቻሇኛሌ? አሇው፡፡ያነበው የነበረ የመጽሏፌ ክፌሌ ይህ ነበር፡፡
‹‹እንዯ በግ ወዯ መታረዴ ተነዲ የበግ ጠቦትም በሸሊቹ ፉት ዝም እንዯሚሌ እንዱሁ አፌን አሌከፇተም
በውርዯቱ ፌርደ ተወገዯ ሕይወቱ ከምዴር ተወግዲሇችና ትውሌደንስ ማን ይናገራሌ?››
ግ.ሏዋ 8÷31 ት.ኢሳ 53÷7
ኢየሱስም ያዯረገው ብዙ ላሊ ነገር ዯግሞ አሇ፡፡ሁለ በእያንዲንደ ቢፃፌ ሇተፃፈት መፃሕፌት ዓሇም ሇራሱ
ባሌበቃቸው ፡፡
ዮሏ 21÷25
መፃሕፌትንና የእግዚአብሔርን ኃይሌ አታውቁምና የምትስቱ አይዯሇምን?
ማር 12÷24
ምዕራፌ ሁሇት
ቅዴመ ዝግጅት
አፌአዊ ውስጣዊ
መጽሏፌ ቅደስን ማንበብ ማሇት ከእግዚአብሔር ጋር መነጋገር ስሇሆነ ፇሪሃ እግዚአብሔር ሉኖር
ይገባሌ፡፡
ሏ/ በማስተዋሌ ማንበብ
መ/ መምህራንን መጠየቅ
ማን?
ምን?
ምን ይናገራሌ?
የዴርጊቶቹ ቅዯም ተከተሌ ምንዴን ናቸው?
የተጠቀሱት ሰዎች ጠባይ ምን ይመስሊሌ?
12
ጸሏፉው (ተናጋሪው) ስሇነዚህ ሰዎች ቀዯም ሲሌ ምን ብሎሌ?
በተጠቀሱት ሰዎች ሊይ ምን ዯረሰ?
ከተገሇጹት ዴርጊቶች በኋሊና በፉት የተከናወኑ ምንዴን ናቸው?
መቼ?
የት?
ሇምን?
እንዳት?
ምሣላ፡-
13
ስም አሇመግሇጥ
አርቆ መናገር
ዲጊመ ቃሌ
አጉሌቶ ማቅረብ
ባሇጠጋ ወዯ እግዚአብሔር መንግሥት ከሚገባ፤ግመሌ በመርፋ ቀዲዲ ቢገባ ይቀሊሌ፡፡ ማቴ. 19 ÷24
ምሳላ መንግሥተ ሰማያት ሇሌጁ ሰርግ ያዯረገ ንጉሥን ተመስሊሇች፡፡ ማቴ. 22÷1
14
ምሳላ፡-
የመጸሕፌት ትርጓሜ
ምሥጢራዊ ትርጓሜ
ነጠሊ ትርጓሜ ምሳላያዊ ትርጓሜ
15
ነጠሊ ትርጓሜ፡-
ዘይቤውን ወይም ንባቡን ወስድ ያሇምንም ሏተታ መተርጎም (ከቋንቋ ወዯ ቋንቋ መመሇስ)
ምሳላያዊ ትርጓሜ፡-
ምሳላ፡- የእመቤታችን ዘሊሇማዊ ዴንግሌና ‹‹እህቴ ሙሽራ የተቆሇፇ ገነት የተዘጋ ምንጭ የታተመ ፇሳሽ ናት››
መ. 4÷12
ምሥጢራዊ ትርጓሜ፡-
ምሥጢራዊ ትርጉም፡-
ሀ. ሇአብነት
ሇ. ትንቢቱን ሇመፇጸም
‹‹አምሊኬ አምሊኬ ሇምን ተውኸኝ›› መዝ. 21÷1 (አምሊኪየ አምሊኪየ ይሌ የነበረ ሥጋን እንዯተዋሏዯ
ሇመጠየቅ ነው፡፡)
ሏ. ሇአቅርቦተ ሰይጣን
16