You are on page 1of 17

1.3.

ተግባራዊ ንድፈ ሃሳብ/ፈለግ (Functional


Theory/Approach)
 የተግባራዊ ንድፈ ሀሳብ አቀንቃኞች ማንኛውም የፎክሎር
ቅንጣት እና ባህል ማህበራዊ ፋይዳ አለው የሚል አቋም
አላቸው፡፡

 የፎክሎር ቅርፅ ወይም ልማዳዊ ድርጊት አንድ ባህላዊ ፣ ማህበራዊ


ወይም ሥነ ልቦናዊ ተግባር ሳይኖረው ፎክሎር ሊሆን አይችልም
፤የሚል ጠንካራ አቋም ይዞ የተነሳ ነው፡፡

 ንድፈ ሃሳቡ/ፈለጉ ማንኛውም ፎክሎር ጥቅም ሊኖረው ይገባል


የሚል አመለካከት ያለው ነው ፡፡
…የቀጠለ
 የተግባራዊ ፈለግ አቀንቃኝ እንደሆኑ የሚነገርላቸው Bronislaw
Malinowski (1884 -1942)፤ ባህላዊ ተቋማት የአንድን ማህበረሰብ
ቁሳዊ እና ስነልቡናዊ ፍላጎቶች የሚያሟሉ መሳሪያዎች ናቸው ብለው
ያምናሉ።

 የተግባራዊ ፈለግ ተከታይ ምሁራን (Emil Durkheim, Radcliffe-


Brown)፤ የሰው ልጅ መሰረታዊ ፍላጎቶች ናቸው በማለት ምግብን፣
መዋለድን፣ አካላዊ ምቾትንና ደህንነትን፣ መዝናናትን፣ እንቅስቃሴንና
እድገትን ይዘረዝራሉ (Malinowski,1944:67)።

 ተቋማት የግለሰቦችን ስነልቡናዊ እርካታ ለማሟላት የሚኖራቸው ሚና


እና እነዚህን ፍላጎቶች ለማርካት የባህላዊ-ማህበራዊ ማዕቀፎች እንዴት
እንደሚሰሩ መመርመር ላይ ትኩረት ይሰጣሉ።
…የቀጠለ
 የዚህ ፈለግ ዐቢይ ትኩረት ማህበራዊ፣ ፖለቲካዊ፣ ባህላዊ ድርጅቶችና
ተቋማት አሁን ባሉበት ሁኔታ ተጠናክረው እንዲቀጥሉ የቻሉበትን
ሁኔታ ትኩረት በመስጠት ያጠናሉ (Malinowski,1944:69)።

 ተግባራዊ ፈለግ የሚተችበት ማዕከላዊ ጉዳይ በአሁኑ ወቅት


በአገልግሎት ላይ ያሉ የባህል ባህሪያትን በመግለፅ ላይ ብቻ የተወሰነ
ነው።

 ስለሆነም ተግባራዊ የማይሆን የፎክሎር ቅንጣትን እንዴትና ለምን ጠፋ


በማለት አይመረምርም፤ በዚህ ሂደት ታሪክን ይጎርዳል በማለት
የመስኩ ምሁራን ይተቻሉ።
…የቀጠለ
 William Basco (የMalinowski) እሳቤ ግምት ውስጥ በማስገባት፤)
የፎክሎር ተግባራትን በአራት ይከፍላቸዋል፤
 
1ኛ.ማስመለጥ (Escap) ፤
2ኛ. ማረጋገጥ (Validation) ፤
3ኛ.ማስተማር (Education) ፤
4ኛ.ማህበራዊ ቁጥጥር (Social Control) ናቸው።

 የፎክሎር ምሁራን ተግባራዊ ፈለግን ሲጠቀሙ ከዘመኑና ከማህበረሰቡ


አኗኗር ስርዓት ጋር በማጣጣም፤ ወቅታዊ ሂደቱንና ተግባሩን በመለየት
እና በመፈተሽ ሊሰሩ እንደሚገባ የስነሰብ ምሁራን ይመክራሉ።
1.4. መዋቅራዊ ንድፈ ሃሳብ (Structuralism)
 መዋቅራዊ ቲወሪ የነገሮችን አገነባብ ወይም አወቃቀር የሚመረምር
ንድፈ ሃሳብ ነው:: ንድፈ ሃሰቡ በስፋት አገልግሎት ላይ የዋለው በቃላዊ
ጥበቦች (በስነቃሎች) ላይ ነው፡፡

 በተጨማሪም ንድፈ ሃሳቡ የአንድን ፎክሎር ምንነት ለመገንዘብ


ፎክሎሩ በዠነር መከፈል አለበት የሚል እሳቤ አለው (Sims.and
stephens፣2005) ፡፡

 መዋቅራዊ ንድፈ ሃሳብ የፎክሎሩን ቅርፅ ለመግለፅ ጥሩ አቅም ያለው


ቢሆንም ሌሎች፤ የፎክሎር ገፅታዎችን ለምሳሌ የፎክሎሩን አካባቢያዊ
ስያሜ ክዋኔ አውድ የሰዎችን የእርስ በእርስ ግንኙነት የማሳየት አቅሙ
ደካማ ነው፡፡
…የቀጠለ
 ንድፈ ሃሳቡ ነገሮች እንዴት ጥቅም ይሰጣሉ ፤ከሚለው ይልቅ ነገሮች
ምንድን ናቸው በሚለው ላይ ትኩረት ያደርጋል፡፡ ንድፈ ሃሳቡ ምንም
እንኳን የዠነር እውቀታችንን ቢያሰፋም ፎክሎርን በዠነር መክፈል
የስራ ግብ ሊሆን አይገባም፡፡

 ፎክሎር የማህበረሰብ ዕውቀት (ጥበብ) ነው (ዳን ቤን ሞስ)፤ ከሚለው


የሙያው ምንነት ብያኔ አንፃር ፎክሎሩን ህይወት አልባና ከሰው
የተገነጠለ ደረቅ ጉዳይ ስለሚያርገው ንድፈ ሃሳቡን ጎደሎ ያደርገዋል፡፡

 ስለሆነም ንድፈ ሃሳቡ ቅርፅን ከማሳየት ጠንካራ አቅሙ የተነሳ ለመረጃ


መተንተኛነት ሲውል ደካማጎኖቹን ለመሸፈን ሌሎች ንድፈ ሃሳቦችን
መጠቀም ያስፈልጋል፡፡
1.5. ትዕምርትና ትርጉም (Symbolic and Interpretative)
 የትዕምርትና ትርጉም ንድፈ ሃሳብ ማህበራዊና ባህላዊ ውክልናዎች
ያላቸውን ትርጉም፣ ልዩ ዋጋ፣ ውክልና፣ መልዕክት እና የሚፈጥሩትን
ስነልቦናዊ ለውጦች የምናጠናበት እንደሆነ (Danesi, 2004, 3)
ይገልጻሉ፡፡

 ነገረ-ትዕምርት (“Semiotics” ወይም “semiology”) ትዕምርቶች


በህዝቦች አኗኗር ውስጥ ያላቸውን ህይወት የሚያጠና ሳይንስ ነው
(Danesi, 2004, 3)፡፡

 ባህላዊ ቁሶችን፣ ድርጊቶችን እና ክስተቶችን ከአጠቃላይ ሁነታቸው


ያለፉ አካባቢያዊና ባህላዊ ስምምነት እንዳላቸው ትዕምርቶች፣
ፍቺዎችን በመፈከር ያጠናል (Danesi, 2004; Woodward, 2007)፡፡
…የቀጠለ
 በነገረ- ትዕምርት የጥናት ዘርፍ ሁለት አይነት የትዕምርቶች ፍቺዎችን
ማጥኛ ንድፎች አሉ፤ አንደኛው የFerdinand de Saussure
የጥንድዮሽ (didactic) ንድፍ ሲሆን፣ ሁለተኛው ደግሞ Charles S.
Peirce የሦስትዮሽ (triadic) ንድፍ ነው፡፡

 በPearce የነገረ-ትዕምርት ንድፈ ሀሳብ መሠረት የትዕምርቶች ዓለም


የተገነባው በቁስአካል፣ በአዕምሮ እና በባህል መሀል በሚካሄድ የእርስ
በእርስ መስተጋብር ውስጥ ነው፡፡

 ቁስ አካል አያሌ ትዕምርቶች የሚመነጩበት ተጨባጩ ዓለም ሲሆን፣


የሰው ልጅ ውጪያዊውን ዓለም ከውስጣዊው ጋር የሚያገናኝበትን
ችሎታ የሚያጎናፅፈው አዕምሮ ነው፡፡
…የቀጠለ
 ባህል ደግሞ ትዕምርቶችን በማላመድና በማቆየት ለተግባራዊ ፋይዳዎች
እንዲውሉና ወደ ተለያዩ አቅጣጫዎች እንዲሰራጩ የሚያደርግ ስርዓት ነው
(Danesi, 2004: 18) ፡፡

 በPearce የሦስትዮሽ ንድፍ መሠረት የማንኛውም ትዕምርት ፍቺዎች


የሚፈልቁት የትዕምርቱ አካል በሆኑ ሦስት የትዕምርት አላባውያን መሀል
በሚካሄድ ረቂቅ ሂደት አማካኝነትነው፡፡

 አላባውያኑ “እምር/ምልክት”፤ “እማሬ” (Object) እምሩ የሚያመለክተው


ሀሳብ እና ፍካሬ (Interpretation) ናቸው፡፡

 ፍቺ (የሚሰማንን ስሜት፣ በአምሯችን የሚፈጥርብንን ምስል፣ የምናገኘውን


መረጃ፣ ወዘተ.) የሚገልጹ ናቸው (Danesi, 2004):: ተምሳሌቶች የህዝቡን
እንዴትነት በማሳየት፣ በመጠበቅና በማቆየት ከፍተኛ ሚና ይጫወታሉ(Bell,
1997, 61)፡፡
1.6. ክዋኔ ተኮር ንድፈ ሃሳብ (Performance Centered Theory)

 Bauman (1986) ክዋኔ የተግባቦት ወይም ያነጋገር ስልት መሆኑን


ይገልጻሉ፡፡

 ከዋኙ ቃል ግጥሙን በሚያቀርብበት ባህል እና ልማዳዊ ህግ መሰረት


የሚጠበቅበትን ጥበብ እያሟላ፣ ታዳሚው ደግሞ ከቃል ግጥሙ
የሚጠበቀውን ትውፊታዊ ውበት እያገኘ እርስ በእርስ የሚፈጥሩት
ተግባቦት ነው፡፡

 ክዋኔ ታዳሚው የከዋኙን ባህላዊ ክህሎት ገምግሞ የሚመዝንበት እና


ልምድ የሚቀያየሩበት ሲሆን፤ ለክወናው መፍዘዝም ሆነ መድመቅ
የታዳሚው ሚና ወሳኝ ነው፡፡
…የቀጠለ

 ክዋኔያዊ የመረጃ መተንተኛ ዘዴ አንድ ፎክሎር ምን እንደሆነ፣ መቼ ፣


የት፣ በማን፣ እንዴት እንደሚከወንና ከዋኞችን ምን የጋራ ጉዳይ
እንዳሰባሰባቸው፣ በመካከላቸው ያለው ጥበባዊ ተግባቦት ምን
እንደሆነ የሚመረምር የፎክሎር ማጥኛ ዘዴ መሆኑ ይገለጻል (Dan
Ben፣1993)፡፡

 አንድ የፎክሎር ባለሙያ በክዋኔያዊ የመረጃ መተንተኛ ዘዴ መረጃውን


ሊተነትን ሲነሳ፤ ፎክሎሩ ምንድን ነው፣ ፎክሎሩ የሚቀርብበት መንገድ
በምን ስልት ነው፣ ፎክሎሩ የቀረበበት ቦታ፣ጊዜና ሁኔታ ምን
ያመለክታል፣ ከዋኞች እነማን ናቸው፣ ምን አይነት ዝግጅት አድርገዋል፣
ምን አይነት ባህርይ ያሳያሉ፣ ታዳሚው ምን ምላሽ እየሰጠ ነው
የሚሉትን ጥያቄዎችን በጥንቃቄ ማዬት ያሥፈልጋል፡፡
…የቀጠለ

 Kapchan, (1995, 479) ክዋኔ ውበታዊ የሆነ የድርጊት ባህሪ፣ የንግግር


ዘዴ፣ በአካል የሚከወን በጊዜና በቦታ የተገደበ፣ በታወቀ መዋቅር
በከዋኞች የሚቀርብ ከመሆኑም በተጨማሪ በተደጋጋሚ የሚፈፀም፣
በግልና በቡድን የሚዋቀር የማንነት ማሳያ ነው፡፡

 አንድን ክዋኔ ስንመረምር የክዋኔው አገላለፅና ጥበባዊ ተግባቦቱ መቼ?


ከማን ጋር? እና እንዴት ተከወነ የሚሉት ጥያቄዎች ይፈጠሩብናል፡፡
ስለሆነም ከቴክስቱ ፣ ከቴክስቱ ይዘትና ከአውዱ አንፃር የክንዋኔውን
ምንነትና የሚያስገኘውን ማህበራዊ ፋይዳ መመርመር ያስፈልጋል፡፡
…የቀጠለ
 ከክዋኔ ንድፈ ሃሳብ ጋር ተያይዘው ከሚነሱ ጉዳዮች ውስጥ አውድ፣ ከዋኝና
ታዳሚ ተጠቃሾች ናቸው፡፡

 አውድ በፎክሎር ጥናት ውስጥ ከክዋኔ ጋር ተያይዞ የሚነሳ ዋና ጉዳይ ነው፡፡


አንድን ክዋኔ ስንመረምር አውድን ማእከል ያደረገ መሆን አለበት፡፡ ይህም
በሰዎች መካከል ያለ ግንኙነትና ባህላዊ ስምምነቶች ለመረዳት ያስችላል
(Finnegan, 1992, 88)፡፡

 አውድ ተኮር ምርምር ሲካሄድ ክዋኔው ከመጀመሩ በፊት ምን እናውቃለን?


ክክዋኔው በኋላስ ምን አዲስ ነገር ተገኘ? ክዋኔው በሚከወንበት ወቅት
የሚታዩ አካባቢያዊ ገለፃና በክዋኔ ጊዜ በተሳታፊዎችና በከዋኙ መሀል ያሉ
ግንኙነቶች ምን ይመስላሉ? የሚሉትን ነጥቦች ማስተዋል አለብን
(Finnegan, 1992, 88)፡፡
…የቀጠለ
 (Bauman, 1983, 367) አውዳዊ ትንታኔን ስናደርግ ከግምት ውስጥ
መግባት ያለባቸው ጉዳዮች ብለው ያስቀመጠቸው ስድስት ነጥቦች
አሉ፡፡ እነሱም፡-
1. የፍቺ አውድ (የሚከወነው ዋና ጉዳይ ምንድን ነው)፣
2. ተቀማዊ አውድ (የት ይከወናል)፣
3. ተግባቦታዊ አውድ (ከሌላ የፎክሎር አይነት ጋር እንዴት
ይዛመዳል)፣
4. ማህበራዊ መሰረት (ምን አይነት ሰዎችን አካቷል)፣
5. ግለሰባዊ አውድ (ከግለሰቡ ኑሮ ጋር እንዴት ይስማማሉ)፣
6. ሁኔታዊ አውድ (ማህበረሰቡ በምን አይነት ሁኔታ ውስጥ ነው
የሚጠቀምባቸው) የሚሉ ናቸው፡፡
…የቀጠለ
 ከዋኝ፡- ከዋኝ ያደጉበትን ማህበረሰብ ባህል፣ወግና ልማድ በማንፀባረቅ
በአቀራረቡ ክዋኔው ላይ ነፍስ ይዘሩበታል፡፡

 የክዋኔን ዋና ቦታ የሚይዘው ከዋኙ ነው፤ ምክንያቱም የከዋኙ ሚና


የሌሎችንም ቀልብ የመሳብ ሃይል ስላለው ነው፡፡ ስለዚህ ቀዳሚው
ከዋኙ ሲሆን ካልዓዩ ደግሞ ታዳሚዎች ናቸው፡፡

 ታዳሚ፡- ከአውድና ከከዋኝ በመቀጠል ክዋኔ ሲነሳ ተያይዞ የሚመጣው


ጉዳይ ታዳሚ ነው፡፡ አንድ ክዋኔ ሲከወን በአጋጣሚ ወይም ደግሞ ሆን
ተብሎ የሚገኙ ሰዎች ታዳሚዎች ይባላሉ፡፡

 አንድ ክዋኔ በሚከወን ጊዜ ክዋኔው ለሚካሄድበት መቼት የተሳታፊዎቹ


ባህሪያትና ምላሽ ትኩረት መስጠት ያሻል፡፡
…የቀጠለ
 የፎክሎር ጥናት ተመራማሪ ታዳሚዎቹ በክዋኔው ተሳታፊ
መሆናቸውን፣ ተሳትፎአቸው እንዴት እንደነበርና ወደ ክዋኔው
ከመግባታቸው በፊት ከነበራቸው ሁኔታ እንዴት ሊነጠሉና በክዋኔው
ሊመሰጡ እንደቻሉ መመርመር አለበት፡፡
አመሰግናለሁ!!!

You might also like