You are on page 1of 52

ወርሃዊ የባህልና የሥነ-ጥበብ መፅሔት

TAZA
ቅፅ 1 ቁጥር 1 መስከረም 2010 ዋጋ 20 ብር

ፖለቲካዊ ባህላችንን ለማረቅ


ከደቂቀ እስጢፋኖስ እስከ ዘመነ ቴዎድሮስ
ousman
ቴአትር፣ ስእልና ተመልካች
የመንግስቱ ለማ ኑዛዜ
4 ፖለቲካዊ ባህላችንን ለማረቅ-
ከደቂቀ እስጢፋኖስ
እስከ ዘመነ ቴዎድሮስ

10
(ከሱልጣን አባዋሪ)

የአሐድ ሐአ’ም ቀብር

16
(ትርጉም ፦መኩሪያ መካሻ)

የቅዱስ ያሬድ ታሪክና የግዕዝ ሥነ


ጽሑፍ ከጌታቸው ኃይሌ (ፕሮፌሰር)

22 ዕውቀትና ልምድ -
ለተተኪው ትውልድ -
1 (ከመንግስቱ ለማ)

28 ቴአትር፣ ስእልና ተመልካች፣


(ታደሰ መስፍን)

32 ሙዚቃ ሙዚቀኛና ተመልካች-

36
ድሮ (ተስፋዬ ገ/ማርያም)

የቅኔ ብራና

38
ከፍትጉ - ለቀኝ ጌታ ዮፍታሄ ንጉሤ

ከኦሎምፒክ ትዝታዎች

40
ቆይታ ከሙዚቃ ባለሙያው አበበ
መለሰ ጋር

ቅፅ-1፣ቁጥር 1 መስከረም 2010 ዓ.ም ገፅ 1


ታዛ መፅሔት
‹‹ታሪኩን፣ ምንጩንና ባህሉን የማያውቅ
ሕዝብ ሥር እንደሌለው ዛፍ ነው››
ደብረ ያሬድ አሳታሚ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ማርከስ ጋርቬይ
በንግድ አዋጅ ቁጥር 980/2008 ዓ.ም
መሰረት ተመዝግቦ በየወሩ የሚታተም
በስነ-ጥበብ፣ ባህልና ትውፊት፣ ታሪክና
ቅርስ እንዲሁም ማህበራዊ ጉዳዮች ላይ
የሚያተኩር መፅሔት በ2009 ዓ.ም
ቀዳሚ ቃል
ተቋቋመ።
ለማረቅ ተቀራርቦ መነጋገርን የመሰለ
ውድ አንባቢያን፣ መፍትሄ የለም። ‘ይህን እንዳናደርግ
ማኔጂንግ ኤዲተሮች፡- የሚያግደን ምንድን ነው?’ የሚለውን
እንኳን ከዘመነ ማቴዎስ ወደ ዘመነ ጥያቄ ለመመለስ ከኋላ ጀምሮ ያለውን
መኩሪያ መካሻ ማርቆስ በሰላም አሸጋገራችሁ! እነሆ ታሪካችንን የሚቃኝ ጽሑፍም አለን።
“ታዛ” የተሰኘች ወርሃዊ የሥነ ጥበብና ሌሎች በርከት ያሉ ርዕሰ ጉዳዮችም
ዓለማየሁ ገ/ሕይወት የባህል መጽሔታችንን የአዲስ ዓመት ይዳሰሳሉ። አንጋፋው ደራሲ ልምዱን
ዋና አዘጋጅ፡-
ስጦታ አድርገን አቅርበንላችኋል። ለተተኪው ያካፍላል። የታዋቂውን ዜማ
“ታዛ” ጥላ፣ የቤት ጥግ፣ መጠለያ፣ ፈጣሪ የአበበ መለሰን ሕይዎት የሚቃኝ
መሰረት እሸቱ ማረፊያ እንዲል፤ መጽሔታችንም ቃለ-መጠይቅም ተሰናድቷል፡፡ የአዲስ
በሰከነ አእምሮ አረፍ ብለን፣ ጊዜ ወስደን ዓመት ዋዜማ ላይ ነንና የጥንቱን የዘመን
አዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወረዳ 6 የምንነጋገርባት፣ የምንወያይባት መለወጫ የሙዚቃ ድግስና ውድድር
እንድትሆን ምኞታችን ነው። ሥነ እያስታወሰ፣ የዚያን ዘመን ትውልድ
የቤት ቁጥር 540
ጥበብና ባህል ደግሞ ራሳችንን በትዝታ ወደኋላ የሚወስድ ለወጣቱ
Meshetu61@gmail.com በውል የምናይባቸው፣ አንድነታችንን ደግሞ ትምህርታዊና አዝናኝ የሚሆን
የምናፀናባቸው፣ የማንነታችን ጽሑፍም ይዘናል።
ስ.ቁ:- 0925427696 መግለጫዎች ናቸው። እኛ የታዛ
አዘጋጆች በተለይ በዚህ የሉላዊነት “ሁሉን ቢናገሩት ሆድ ባዶ ይቀራል”
ዘመን ወጣቶቻችን መሠረታቸውን እንደሚባለው እንዳይሆንብን ቀሪዎቹንም
ሳይለቁ ወደፊት እንዲራመዱ የማድረግ ሥራዎች ወደ ውስጥ ስትዘልቁ
ዓምደኞች፡-
ሃላፊነት አለብን ብለን እናምናለን። መርምሯቸው። እባካችሁ ፃፉልን፣ ሃሳብ
ጌታቸው ኃይሌ (ፕሮፌሰር) ማንነቱን፣ ምንጩን ወይም መነሻውን አስተያየታችሁን ላኩልን። የሃገራችንን
የማያውቅ ሰው መድረሻውን ሊያውቅ ሥነ ጥበብና ባህል በጋራ እንወቅ፣
አቦነህ አሻግሬ (ረ/ፕሮፌሰር) አይችልምና። እንጠብቅ፣ እናበልፅግ፣ እናስተዋውቅ።
በቀለ መኮንን (ረ/ፕሮፌሰር) ወጣት ጸሐፍትንም እናበረታታለን፡፡
በዚህ እትም ስለቅዱስ ያሬድ በዚህ አጋጣሚ ጽሑፍ ያበረከቱልንን፣
ታሪክና ስለ ግዕዝ ሥነጽሑፍ የመስኩ አስተያየት የሰጡንንና በርቱ ያሉንን
ታደሰ መስፍን (ረ/ፕሮፌሰር)
ሊቅ ያዘጋጁትን ጥናታዊ ጽሑፍ ሁሉ ከልብ እናመሰግናለን።
መስፍን መሰለ ታነባላችሁ። የፖለቲካ ባህላችንን
መልካም ንባብ!
ዕቁባይ በርሀ

ፊደል እሸቱ

ተስፋዬ ገ/ማርያም

ሱልጣን አባዋሪ

እክንድር ኃይሉ

የዝግጅት ክፍሉ አድራሻ

ፒያሳ ቸርችል ጎዳና ከካቴድራል ት/ቤት


ፊት ለፊት ካንትሪ ታዎር 7ኛ ፎቅ

ስ.ቁ:- +251 18296194

ፋክስ:- +251 11266736

Email: debreyaredpublisher@
gmail.com

ግራፊክስ ዲዛይነር

ዕንቁዬ ይዘንጋው ተኩስ ቃላትን፣ በብዕር ቃታ…


ዜና እረፍት ታዛ

ያጣነው የሁላችን አባት


የሁላችን አባት የሆኑት ተስፋዬ ሳህሉ ሀምሌ ከሁሉም የትወና
24፣2009 ዓ.ም ”ደህና ሁኑ ልጆች” ብለው እስከ ህይወት ተሰፋዬን ልዩ
ወዲያኛው አሸለቡ። ተስፋዬ ሳህሉ የሙያ ሀብት ባለቤት የሚያደርጋቸው ሴት
ነበሩ። ከተረት አጫዋችነት አንስቶ የአስማት ትርኢት ተዋንያን በሌሉበት ዘመን
አቅራቢ፣ተዋናይ፣የሙዚቃ ተጫዋችና ደራሲ ናቸው። ሻሽ በማሰርና ፂማቸውን
በዕውቁ የኦቴሎ ቴአትር ኢያጎን ሆነው የሰሩ የመድረክ ሙልጭ አድርገው
አድባር ነበሩ። ከመድረክ አልፈው ወደ ጦር ሜዳ በመላጨት ለአራት ዓመታት
ዘምተዋል። በ1944 ዓ.ም በኮርያ አገር በ50 አለቃነት እንደ ሴት ሆነው በየመድረኩ
ማዕረግ ክራር ይዘው ሠራዊቱ ለድል እንዲበቃ እያዝናኑ ታዳሚያቸውን አስደስተዋል።
ሀገራቸውን በአለም መድረክ አስተዋውቀዋል። ሰኔ 20 ‘የአርበኛው ሚስት’ ለዚህ
ቀን 1915 ዓ.ም በባሌ ክፍለ-ሀገር ከዱ ተወለዱ። በ1957 ተጠቃሽ ሲሆን፤አፋጀሽኝ
ዓ.ም የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ሲቋቋም ጀምሮ የልጆች ጊዜ ፣የደም ድምፅ፣ ጎንደሬው
ፕሮግራም በማዘጋጀት ከኢቴቪ እስከ ተለያዩበት 1998 ገብረ ማርያም፣መቀነቷን
ዓ.ም ድረስ ለ41 ዓመታት ልጆችን በተረትና በጨዋታ ከፍታ፣አርበኞችና ኢትዮጵያ የተሰኙት ቴአትሮች
ሲኮተኩቱ ኖረዋል። ይገኙበታል።

አባባ ተስፋዬ (ተስፋዬ ሳህሉ) ከግማሽ ምዕተ-ዓመት ከአጼ ኃይለ-ሥላሴ እጅ ሦስት ጊዜ የወርቅ ሰአት
በላይ ወገናቸውንና አገራቸውን በትጋት ሲያገለግሉ ተሸላሚ ሲሆኑ፤ የኢትዮጵያ የስነ-ጥበባትና የመገናኛ
ኖረዋል። ጌታቸው ደባልቄ “ተስፋዬ ብዙ ሰው ነው” ብሏል። ብዙሃን ሽልማት ድርጅት በ1991 ዓ.ም በተዋናይነት
በመድረክ ላይ ሁሉን ለውጦ ሲታይ እጅግ የሚያስደንቅ የህይወት ዘመን ተሸላሚ ሲያደርጋቸው ከዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ
ችሎታ ነበረው” ያለው ደግሞ ፕሮፌሰር ተሰፋዬ ገሠሠ ደግሞ ሀምሌ 22፣ 2009 ዓ.ም የክብር ዶክትሬት ዲግሪ
ነው። እንደተቀዳጁ ይታወሳል።

አቶ ሃብተስላሴ ታፈሰ አረፉ


ሃገራቸው ተመልሰው በውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር የፕሬስና
ማስታወቂያ መምሪያ ሃላፊ ሆነው አገልግለዋል፡፡

ሆኖም ለቱሪዝም ምንም ትኩረት አለመሰጠቱና መስኩ


ገና በጮርቃው መሆኑ ስላሳሰባቸው አፄ ኃይለ ሥላሴ ዘን
ድቀርበው አንድ ተቋም ሊመሠረት እንደሚገባ ያሳሰስባሉ፡፡
ንጉሠ ነገሥቱም በሃሳቡ ተስማምተው የማደራጀቱን ተግባር
ራሳቸው አቶ ሃብተ ስላሴ ማከናወን እንዳለባቸው ያምናሉ፡፡
ስለዚህም ከውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር በጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽ/ቤት
ፎቶ በአንተነህ አክሊሉ
ስር ወዳለ ቢሮ እንዲዛወሩ ሆነ፡፡ በዚህም መሠረት የቱሪዝምን
ኢንዱስትሪ ከመወጠንና ከማሳደግ በተጨማሪ የኢትዮጵያ
የኢትዮጵያ ቱሪዝም አባት በመባል የሚታወቁት አቶ ሃብተ የቱሪስት ንግድ ሥራ ድርጅትን አቋቁመዋል፡፡
ስላሴ ታፈሰ በዘጠና አንድ ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት
ተለዩ፡፡ የቀብራቸው ሥነ ሥርዓትም ወዳጅ ዘመዶቻቸውና አቶ ሃብተ ስላሴ በምርጥ ፎቶግራፎቻቸው፣ ታሪካዊውን
በርካታ አድናቂዎቻቸው በተገኙበት ነሃሴ 7 ቀን 2009 ዓ.ም የኢትዮጵያ የጉዞ መስመር (The Historic Route)
በቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን ተፈጽሟል። ከአባታቸው በማስተዋወቃቸው፣ ከሁሉም በላይ ደግሞ የአሥራ ሶሥት
ከፊታውራሪ ታፈሰ ሃብተ ሚካኤልና ከእናታቸው ከወይዘሮ ወር ፀሐይ (Thirteen Months of Sunshine) የሚለውን
ሙላቷ በላይነህ በ1918 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ከተማ ታዋቂ የቱሪዝም መፈክር በመፍጠራቸው ይታወቃሉ፡፡ ለዚህም
የተወለዱት አቶ ሃብተ ስላሴ የአንደኛና ሁለተኛ ደረጃ በርካታ ሽልማቶችን አግኝተዋል፡፡ ደርግ ወደ ስልጣን ሲመጣ
ትምህርታቸውን በአቴንስ ግሪክና በግብፅ አሌክሳንድሪያ አቶ ሃብተ ስላሴን ያሰራቸው ሲሆን ከሰባት ዓመታት በኋላ
ተከታትለዋል፡፡ የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን ደግሞ በአሜሪካው ሲፈታቸው በቱሪዝም ዘርፍ አማካሪነት መድቧቸዋል፡፡ እስከ
የሚኒሶታ ግዛት፣ ኖርዝ ፊልድ ውስጥ በሚገኘው የካርልተን ሕይወታቸው ፍፃሜ ለኢትዮጵያ የቱሪዝም ዕድገት የደከሙት
ኮሌጅ በዓለማቀፍ ግንኙነት መስክ ተቀብለዋል፡፡ ከዚያ ወደ አቶ ሃብተ ስላሴ ከወይዘሮ ሙሉመቤት መስፍን ጋር ትዳር
መስርተው ሁለት ወንዶችና አንዲት ሴት ልጆችን አፍርተዋል፡፡
ቅፅ-1፣ቁጥር 1 መስከረም 2010 ዓ.ም ገፅ 3
ታዛ

ፖለቲካዊ ባህላችንን ለማረቅ- ከደቂቀ


(ከሱልጣን አባዋሪ)

በዛሬ ዘመን አንዱ ከሌላው ጋር ተጋግዞ የሚኖርበት ደረጃ


ላይ ደርሰናል፡፡ እንደ ሀገር ወይም እንደ መንደርተኛ ዝቅ ብለን
ካሰብን የራስን ጎጆ ለብቻ ቀይሶ መኖር ቢቻልም ተመራጭ ግን
አይሆንም፡፡ የወደፊቱን መፃኢ ዘመን የሚተነብዩ እንደ ፍራንሲስ
ፉኩያማ ያሉ ጠበብት (Futurologists) የታሪክን መጠናቀቅ
(መጨረሻ) ቢያቀነቅኑም የዓለም መጨረሻነት በበርሊን ግንብ
ወይም በሶቪየት ህብረት መፈራረስ አላበቃም፡፡ የመጻኢ
ዘመን ተንባዮቹ የነሱ ዓለም በዲሞክራሲና በካፒታሊዝም ድል
ባለቤትነት ላይ ብቻ እንደቆመ ሰብከዋል፡፡ አልፎ ተርፎም
የካፒታሊዝም ድርጎ ተጠቃሚዎች የሆኑ የትላልቅ ኮርፖሬሽኖች
ሥራ አስፈጻሚዎች የኩባንያቸውን ባህላዊ እሴቶች አጋነው
አውርተዋል፡፡ ያወራሉም፡፡ ለምሳሌ ያህል የኮካ ኮላ ኩባንያ
ሥራ አስፈጻሚዎችና አሻሻ ጮች ስለ ኮካኮላ ዓለማቀፋዊ
አዲስ ባህል ፈጣሪነት ደረታቸውን ነፍተው አውርተዋል፡፡
አንድ አይነት ይዘት፣መልክና ቁመና ያለው ሸቀጣቸው
በሁሉም ሀገር በሽሚያ ስለሚሸጥ ነው እንዲያ ያሉት፡፡
ቻይናዎች እንኳ ኮካን ‹በጠርሙስ የታሸገው ኢምፔሪያሊዝም›
አቡነ እስጢፋኖስ
እንዳላሉና ጥምብ እርኩሱን እንዳላወጡት ዛሬ ከዓለም
ህዝብ ሁሉ ልቀው ኮካን በብዛት የሚገሽሩት እነሱ ሆነዋል፡፡

በሌላ መልኩ የሚዲያ ልሂቃን፣ በእያንዳንዱ ሰው ቤት ጎጆ ለመሆኑ ፖለቲካዊ ባህል ምንድን ነው?
ላይ የተጠመደውን የሳተላይት ሳህን በማሰብ ዓለማችን ወደ
ዓለማቀፋዊ መንደርነት (Global village) እየተለወጠች መሆኗን ‹ፖለቲካዊ ባህል› የተባለው የእውቀት ዘርፍ ተለይቶ
ነግረውናል፡፡ ዛሬ ዓለም በቶማስ ፍሬድማን ቋንቋ እየተዋሃደች ለምርምር የበቃው በ1950ዎቹ በጋብሬል አመንድ (Gabriel Al-
በመምጣቷ የራስን የግል ግድግዳ አልፎ ማየት ተጀምሯል፡፡ mond) እና ሲድኒ ቬርባ (Sidney Verba) ነው፡፡ አሜሪካውያን
እግርኳስን የፈጠሩት ወግ አጥባቂዎቹ እንግሊዛውያን እንኳ የፖለቲካ ሊቆች ናቸው፡፡ የፖለቲካ ባህል በአንድ ማህበረሰብ
አድማሳቸውን አስፍተው የስፔንን እግርኳስ ውድድር ውስጥ ወይም በግለሰብ የተያዘ ሰፊ ትርጉም ያለው የፖለቲካ
በጀርመን ቢራ እያወራረዱ መመልከታቸውን ቀጥለዋል፡፡ ባህርይን ሊገልፅ የሚችል ማእቀፍ ነው፡፡ አንድ ማህበረሰብ
ይህ ማለት እንኳንስ ለፖለቲካ፣ ለኳስም የአመለካከት ታሪካዊ በሆኑ የተለያዩ መልኮች፣ በባህላዊ ተግባራትና በሰብአዊ
አድማስን ማስፋት ይጠይቃል ለማለት ነው፡፡ ዳሩ፣ ባህላዊ ማህበራት ጉባኤዎች ይገለጻል፡፡ የፖለቲካ ባህል ከዲሞክራሲያዊና
ግድግዳዎች እየፈራረሱ ቢሆንም በአንድ በኩል፣ ውህድ የሆነ ከፖለቲካዊ ተቋማት ጋር ከተሳሰረ ልዕለ ሃሳብ፣ አመለካከቶችና
ባህላዊ ጥምረትን የሚደግፉ፤ በሌላ በኩል፣ ይህን ጥምረት ባህርያት ባለፈ ሊታይ የሚችል ነው፡፡ የፖለቲካ ባህል
የሚቃወሙና በመንደር አመለካከት የታጠሩ ሞልተዋል፡፡ የሚጎለብተው በመነጋገርና በመተማመን፤ በማሳመን፤ ባህላዊ
እነዚህን መንደርተኞች አቅልሎ መመልከትም አይገባም፡፡ የጋራ መግባባትን በመፍጠርና ብዝሃነትን በመቀበል ነው፡፡
ይህ ፖለቲካዊ ባህል በለውጥ ውስጥ የሚዳብርና ለለውጥም
በተለይ በሀገራችን የሚታየውን የፖለቲካ ባህል (Po- እንቅፋት ያልሆነ ነው፡፡ የፖለቲካ ባህል ከፖለቲካዊ ርዕዮተዓለም
litical culture) ቅርጽ-አልባነትና አለመበልጸግ ከስር የሰፋ ሲሆን፣ የተለያየ የፖለቲካ ርዕዮት የሚከተሉ ወገኖች
መሰረቱ በማጥናት ተገቢውን የፈውስ መንገድ መጠቆም በአንድ የፖለቲካ ባህል ውስጥ ራሳቸውን ሊያገኙ ይችላሉ፡፡
ያስፈልጋል፡፡ ይህ ሃላፊነት ደግሞ በተለይ የወደቀው በኢትዮጵያ ይህም ማለት ኢህአዴግ፣ ሰማያዊ ፓርቲ፣ አረና፣ ኢዴፓ ወይም
ምሁራን ላይ ቢሆንም፣ የሀገሩን መልካምነት የሚፈልግ ሁሉም የዲያስፖራዎቹ ተቃዋሚዎች ፖለቲካዊ አመለካከታቸውንና
ዜጋ እንዲነጋገርበት ያስፈልጋል፡፡ የግድም ይላል፡፡ በዚህ መስክ ርዕዮተዓለማቸውን እንደያዙ በፖለቲካዊ ባህል ምህዳር ውስጥ
እኛ የሀገሪቱ ዜጎች በግልጽ ተነጋግረናል ማለት አይቻልም፡፡ ሊከራከሩ፣ ሊፋተጉና የተሻለ ሀሳብ ሊያመነጩልን ይችላሉ፡፡
ይህም በሌላ አገላለጽ ልዩነትንና ሽንፈትን በጸጋ እስከ መቀበል

ቅፅ-1፣ቁጥር 1 መስከረም 2010 ዓ.ም ገፅ 4


ታዛ

እስጢፋኖስ እስከ ዘመነ ቴዎድሮስ

ዳግማዊ አፄ ቴዎድሮስ

ይደርሳል፡፡ በአንድ ወቅት አቶ መለስ ዜናዊ


‹መላጣየን እስካልነካ ድረስ ልንለያይና
ልንከራከር እንችላለን› ያሉትን ያስታውሷል፡፡
በአጠቃላይ መልኩ ፖለቲካዊ ባህል
የሚገለጸው ሰዎች ለፖለቲካዊ ባህርያቸው
ትርጉም ሲሰጡትና ትርጉሙንም ሆነ
ልዩነቱን እሰዬው ብለው ሲቀበሉት ነው፡፡

በመሰረቱ ፖለቲካዊ ባህል፣ የፖለቲካ


ሥርዓቱና የፖለቲካ ሥርዓቱ አባላት
ውጤት እንጂ ሌላ ሊሆን አይችልም፡፡
ስለዚህ የባህሪያት፣ የእምነቶችና ፖለቲካዊ
አስተሳሰቦች ቅንጅት ነው፡፡ በመንግሥትና
በዜጎች ግንኙነት ይገለጻል፡፡ ለዚህም ነው
በፖለቲካ ሥርዓቱ ውስጥ የዜጎችን
የተለያዩ ፖለቲካዊ ባህሪያት የሚያስተሳስረው፡፡
ነፍጠኛው ከብዕረኛው፤ ግራ ቀደሙ ከቀኝ
መንገደኛው፤ ለዘብተኛው ከአክራሪው ጋር
አብረው ተቻችለው እንዲኖሩ ያስችላል፡፡
ሦስት መሰረታዊ አስተሳሰቦች እዚህ ላይ
ያስፈልጉናል፡፡ እነሱም ልዩነትን ማክበር፤
መግባባትና በመጨረሻም የአንድ ሀገር
ዜጋ መሆን ወይም ውህድነት (Homo-
geneity) ናቸው፡፡ እኛ ኢትዮጵያውያን
ዝንተ አለማችንን የሰለጠነ የፖለቲካ
ባህል ኖሮን አያውቅም፡፡ በመተራረድ፣
በመበቃቀል፣ በመመቀኛኘት እናምናለን፡፡
ወንድም ለወንድሙ ጠላቱ ሁኖ ኖሯል፣
ቆይቷል፡፡ ዳግማዊ ኢያሱ በ1775 ዓ.ም.

ቅፅ-1፣ቁጥር 1 መስከረም 2010 ዓ.ም ገፅ 5


ታዛ

በቅርብ ዘመዱ ተመርዞ ነው የሞተው፡፡ ብዙዎቹን ንጉሳውያን እስጢፋኖስ፡- ለምንድን ነው የማልልህ? አንድ ሰው
የእግዜር በሽታ አይደለም የገደላቸው፡፡ ያልዳበረ ፖለቲካዊ ባህል አይደለህም እንዴ? በብሉይም፣ በሐዲስም የተፃፈው
(Parochial Culture) በመስፈኑ የተከተልነው መንገድ ራስን እንደዚሁ ነው፡፡ አንድን ሰው እንዳንድ ያናግሩታል፣ እንደ
የመግደል ባህል ሁኖ ቆይቷል፡፡ ያሳዝናል፡፡ አሁን ያለውም ብዙዎች አይደለም፡፡ እንኳን ሰውን እግዚአብሔርንም ‘አንተ
ትውልድ አዲስ ፖለቲካዊ ባህል ገና አልገነባም፡፡ እስቲ የፖለቲካ አትጣለኝ ጌታ ሆይ፣ አምላኬ አንተ ከኔ አትራቅ፣ የመዳኔ
ባህላችንን ለመዳሰስ ታሪካችንን ወደ ኋላ ተመልሰን እንመልከት፡፡ አምላክ ጌታ ሆይ’ እያልን እንደዚህ ነው የምንጠራው፡፡
ትናንትን መመልከት ወደፊት ለመንደርደር ይጠቅማልና፡፡
ይህ ከላይ የቀረበው ምሳሌ የሃሳብ ልዩነትን አለመቀበልና
‹ፅኑ ነብይ ሲነሳ ፅኑ ንጉሥ ያስነሳል›-እስጢፋኖስ አለመቻቻል መሪዎችን ወደ ከፋ እርምጃ እንደወሰዳቸው ያሳያል፡
፡ ታሪክ እንዳሳየው እስጢፋኖስ በ1437 አካበቢ ለፍርድ ቀረበ፤
ዘርአ ያዕቆብንና ደቂቀ እስጢፋኖሶችን እንውሰድ፡፡ ምስጋና በችሎቱ ላይ በተደጋጋሚ በድፍረት ተ ከ ራ ከ ረ ፡ ፡ በ ዚ ህ ም
ለፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ ይሁንና ጥንታዊውን የፖለቲካ ምክንያት በአደባባይ የተቀመጡት መነኩሴዎች ‘ሞት ይገባዋል፤
ባህላችንን ጨካኝነትና ቅርጽ አልባነት በደቂቀ እስጢፋኖስ ምክንያቱም ሰንበት ሻሪ ነው፤ ለንጉሱ አይታዘዝም፤ ለክብሩም
መፅሀፋቸው ፍንትው አድርገው አሳይተውናል፡፡ የዛሬው አይሰግድም’ ብለው ቢተቹም ንጉሡ ግ ን እን ዲ ገ ረ ፍ ብቻ
ትውልድ ከዚያ መከራና እልቂት ትምህርት መውሰድ አለበት፡፡ ት እ ዛ ዝ ሰጠ፡፡ እንግዲህ ይህ የመነኩሴዎች አቋም ከአድርባይ
የምሁርነት ጠባይ
የፕሮፌሰር ጌታቸውን “ደቂቀ ያ ለ ፈ
እስጢፋኖስ” መጽሀፍ ያነበቡት አይደለም፡፡ ይህን
ፕሮፌሰር መስፍን ወልደ ማርያም በአንድ ወቅት አቶ መለስ ዜናዊ ክፉ ባህርይ
ዛሬም
ደግሞ
ድረስ
ደግሞ፣ በንጉስ ዘርአ ያዕቆብ
የምንታዘበው ነው፡፡
የተፈጸመው ይህ ቀረህ የማይባል
ግፍ አጥንታቸው ድረስ ዘልቆ
‹መላጣየን እስካልነካ ድረስ
እንደተሰማቸው ሲገልጹ “ከግዕዝ ግፉ በዚህ
ወደ ዐማርኛ የተተረጎመው የደቂቀ ልንለያይና ልንከራከር እንችላለን› አያበቃም፤
እስጢፋኖስ ሰቆቃ ያስደነግጣል፣ እንቀጥል፡፡
ያሳዝናል፣ ያስቆጣል፣ የማናውቀው
ራሳችንን እርቃናችንን ያሳየናል”
ያሉትን ያስታውሷል፡፡
እስጢፋኖስን እጅና
ሲሉ አምርረው ገልጸዋል፡፡ እግሩን አስረው 46
ጊዜ ገረፉት፡፡ የዚህ
ፕሮፌሰር ጌታቸው እንዳቀረቡት የደቂቀ እስጢፋኖሶች ዜና ትግራይ በደረሰ ጊዜ፣ በየገዳማቱና በየአድባራቱ የነበሩ
ሥርአታቸው ሌሎች አድባራት ትተውታል የሚሉት የድህነት፣ መነኮሳት፣ ከባድ ጥቃት አደረሱባቸው፡፡ እስጢፋኖስና አንዳንድ
የስግደት፣ የጸሎት፣ የዝምተኝነት ኑሮ ሲሆን፣ ዕምነታቸው ለአብ፣ ተከታዮቹም እንደገና ወደ ንጉሱ ችሎት ተጠሩ፤ እዚያም
ለወልድ፣ ለመስቀል፣ ለንጉስ አንሰግድም፣ እራስን የሚያስጎነብስ የቅጣትና የእስር ፍርድ ተፈረደባቸው:: በእስር ላይ እያሉም
እጅ አንነሳም፣ ከቤተ ክርስቲያን መጻህፍት ውጭ የሆኑትን ከስቃዩ ብዛት አባ እስጢፋኖስ እ.ኤ.አ በ1444 ሞተ፡፡ መሪው
አንቀበልም ነው፡፡ ንጉሱ ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያምና ከሞተ በኋላ በደቂቀ እስጢፋኖሶች ላይ የሚደረገው ክትትል፣
ለክቡር መስቀል ስለማይሰግዱ ነው ሰይፌን የመዘዝኩባቸው ወከባና እንግልት ለተወሰኑ አመታት ጋብ ይላል፡፡ ሆኖም
ይላል፡፡ በተቃራኒው [እስጢፋኖሶች] እንደሚሉት ደግሞ ይሄ ከ1454 (እ.ኤ.አ) አካበቢ ጀምሮ ንጉሡ እነሱን ለማጥፋት ያቀደ
ሰበብ ነው፣ ንጉሱ የሚያሳድዳቸው ለሱ ስላልሰገዱለት ነው፡፡ ዘመቻ አውጆ ለብዙ ዓመታት ተንቀሳቀሰ። ብዙዎቹ የሰው
ልጅ ይችለዋል ተብሎ የማይገመት ሥቃይ ተቀበሉ፤ በልዩ
ንጉሥ፡- ለምንድነው በስግደት ራስክን ዝቅ ልዩ አሰቃቂ መንገድ ተጨፈጨፉ፡፡ የበቀል ፖለቲካችን ማለቂያ
የማታደርገው? የለውም፤ ይህ ሁኔታ የበቀል ፖለቲካችን እርሾ ሳይሆን ይቀራል?

እስጢፋኖስ፡- ሕጉ የሚያዘን ለእግዚአብሔር እንድንሰግድ እንጂ የእስጢፋኖሶች ግፍና ስቃይ በዚህ አላበቃም፣ ዘርአ ያዕቆብን
በውስጡ አንተ እንደምትለው እንድንሰግድ ትእዛዝ የለበትም፡፡ የተካው በእደማሪያምም ቀጠለበት፡፡ ያባቱን ፖሊሲ ገፋበት፡፡ ዞር
ለማንኛውም ከኛ ስግደት አትፈልግ፣ ጸሎትና ቡራኬ ይበቃሃል፡፡ ብሎ ‘አባቴ ምን አጥፍቶ ነበር?’ የማለት ጥያቄ አላቀረበም፡፡
ጨካኙን የመንግስቱን አቋም ለማሻሻል እንኳ አልጣረም፡፡ ልጅ
ከአባቱ መሻል ሲኖርበት የባሰ ፖሊሲውን ቀጠለበት፡፡ አባ
ንጉሥ፡- ለምንድን ነው ሁሌ አንተ የምትለኝ?
እስጢፋኖስ ‹ፅኑ ነብይ ሲነሳ ፅኑ ንጉሥ ያስነሳል› ያለው ተፈጸመ፡

ቅፅ-1፣ቁጥር 1 መስከረም 2010 ዓ.ም ገፅ 6


ታዛ

፡ ንጉሡም ሆነ መንግሥቱ የሚፈልጉት በተገዢዎች ዘንድ ይኖሩ ስለ ነበር ምንም ልዩ ሙያ የሌላቸው መሆኑን አስረዱ፡፡
መወደድን ሳይሆን መፈራትን ነውና መፈራት የገዢዎች ሁነኛ ዘዴ ቴዎድሮስም ዝም ብሎ ካዳመጣቸው በኋላ ‘የቀረውን ዘራፊ ሁላ
መሆኑን እንረዳለን፡፡ ዘርአ ያዕቆብ ፍፁማዊ ስልጣንን በመፍጠር አሰባስባችሁ ትመጣላችሁ፣ የሚሆናችሁ ሥራ ይሰጣችኋል’
የኢትዮጵያን የፖለቲካ ባህል ለዘለቄታው አዛንፎት አልፏል፡፡ ብሎ አሰናበታቸው፡፡ ወንበዴዎቹ ከሄዱ በኋላ የቴዎድሮስ
አማካሪዎች በበኩላቸው ንጉሥ እንዴት ከወንበዴዎች ጋር
ወደ ዘመነ መሳፍንት ደግሞ እንምጣና የመሳፍንቱን የፖለቲካ ይደራደራል ብለው ሳቁ፣ አሽሟጠጡ፡፡ ሽፍቶቹ ከሩቅ ሀገር
ባህል እንመልከት፡፡ የሚከተለው የሚገልጸው ይመስለኛል፡- ወቅቱ ያሉት ሁላ ተጠራርተው ተሰብስበው እንደ ተነገራቸው
ከጎንደር ነገሥታት የመጨረሻው ከሆነው ከተክለጊዮርጊስ ዘመነ ተመልሰው ሲመጡ ንጉሱ ዘቦቹን አዝዞ አንድም ሰው
መንግሥት ፍጻሜ ከ1784 ጀምሮ እስከ 1855 የሚዘልቅ ሲሆን ሳይቀር እንዲገደሉ አደረገ፡፡ ትውፊቱ እንደሚለው ከዚያን
የንጉሰ ነገሥቱ ሥልጣን ተንኮታኩቶ መሳፍንትና ባላባቶች ጊዜ አንስቶ በቴዎድሮስ ግቢ ሳቅና ጨዋታ ቀረ፡፡ በእርግጥ
የየራሳቸውን የአገዛዝ ጎጆ የቀለሱበትን ጊዜ ያመለክታል፡፡ ይህ ከላይ የቀረበው ድርጊት ለህዝቡ ሰላማዊ እፎይታን
የሰጠ ቢሆንም በአጠቃላይ በፖለቲካ ባህሉ ውስጥ መሰረታዊ
ይህን አሳዛኝ የሀገር መበታተን አደጋ የሚታደግ አንድ ፖለቲካዊ ለውጥ ማምጣቱን ይጠቁማል፡፡ ‹ሳቅና ጨዋታ በቴዎድሮስ
ኃይል በዳግማዊ ቴዎድሮስ ዕውን ሆነ፡፡ የያኔው ደጃዝማች ግቢ ቀረ!› የሚለው አባባል የስርአቱ የፖለቲካ አስተሳሰብ
ካሳ በቋራ ወረዳ በሻርጌ መንደር በፍርሃትና በማንበርከክ ላይ የተመሠረተ መሆኑን ያሳያል፡፡
በ1818 ተወለደ፡፡ በኋላም
በሽፍትነት ራሱን አደራጅቶ ለቴዎድሮስ የመጨረሻ
ከቆየ በኋላ ፈርጣማ ኃይል ‹ፅኑ ነብይ ሲነሳ ፅኑ ንጉሥ ውድቀትና ሞት የቅርብ
ሆኖ ወጣ፡፡ በኋላ ላይ አደገኛ ምክንያት ሆኖ የሚወሰደው
ኃይል የሚሆንበትን ሸዋን
ያስነሳል›- እስጢፋኖስ የእንግሊዞች መምጣት ነው
ማንበርከክ ያስፈልገው ነበር፡፡ ቢባልም በሀገሪቱ ውስጥ
ሸዋን ካንበረከከ በኋላ ሦስት መሰረታዊ አስተሳሰቦች እዚህ የነበረው የኃይል አሰላለፍ
ታላላቆቹን የኢትዮጵያ ግዛቶች ወሳኝ ሚና እንደነበረው
ላይ ያስፈልጉናል፡፡ እነሱም ልዩነትን መካድ አይቻልም፡፡ ቴዎድሮስ
አንድ አድርጎ በሥልጣኑ
ስር አዋለ፡፡ እያንዳንዱ ማክበር፤ መግባባትና በመጨረሻም በእንግሊዞች የተሸነፈው
ባላባትም የንጉሠ-ነገሥቱን የአንድ ሀገር ዜጋ መሆን ወይም ከትግሬው በዝብዝ ካሳ፣
ከላስቴው ዋግሹም ጎበዜና
መሪነት በግዴታው ተቀበለ፡፡
ውህድነት (Homogeneity) ናቸው፡፡
ይህ በግዴታ የመጣው እንደ ሳህለ ማሪያም
የፖለቲካ ሂደት የማታ ካሉት ህጋዊ ባላጋራዎቹ
ማታ ተቀናቃኝ መፍጠሩ ጋር ታግሎ የማሸነፍ
የግድ ነውና ከፖለቲካ መረጋጋት ይልቅ የፖለቲካ ሽኩቻው ፖለቲካዊ ብቃት ስላልነበረው ነው፡፡
ቀጠለ፡፡ ባርተኒስኪና ማንቴል-ኒየችኮ እንዳሰፈሩት ከ1855-
1857 ባለው ጊዜ 17 የግድያ ሙከራዎች በቴዎድሮስ ላይ እነዚህ ከላይ በጥቂቱም ቢሆን የቀረቡት ማሳያዎች በኢትዮጵያ
ተደርገዋል፡፡ ይህ የሚያሳየው ከፖለቲካ መቻቻል ይልቅ ውስጥ ፖለቲካዊ ባህላችን ያልዳበረና በዛሬውም ዘመን
ስልጣንን ለመንጠቅ የፖለቲካ መሪን በመግደል (political as- ጠንክሮ እንዳይወጣ የራሳቸውን አፍራሽ ሚና መጫወታቸውን
sassination) ራስን ስልጣን ላይ ማቆናጠጥ ነው፡፡ ሁኔታው ይመሰክራሉ፡፡ የፖለቲካ ባህል ሊዳብርና የጋራ ሊሆን
በኢትዮጵያ የፖለቲካ ህይወት ውስጥ የተዛነፈ (formless- የሚችለው የተለያዩ ፖለቲካዊ እምነቶቻችንን የሚያስተናግድና
ness) የፖለቲካ ባህል ቀድሞውኑ እንግዳ እንዳልነበር ያሳያል፡፡ በእኩልነት ላይ የተመሰረተ መፈቃቀድ ሲኖር፣ ነጻ የኢኮኖሚ
አስተሳሰብ በሁሉም ክልሎች ሲፈጠር፣ ለህግ የበላይነት በጋራ
ቴዎድሮስ ለዘብተኛ የፖለቲካ አቋም በመውሰድ ‹ገበሬ መቆም ሲቻልና መልካም የሆኑ የዜጎች ግንኙነቶች ዳብረው
ይረስ፣ ነጋዴ ይነግድ፣ እያንዳንዱ ሰው በየስራው ይሠማራ› ህብራዊነት ሲደምቅ መሆኑን መገንዘብ ያስፈልጋል፡፡ ጭራና
በማለት የሀገሪቱ ሕዝብ በሙሉ ሥራ እንዲሰራ የሚያደርግ ከአስተሳሰብ ተራ የወጡ የዘውጌነት ፍላጎቶችን ብቻ ይዞ ገመድ
አዋጅ በማውጣትም ይታወቃል፡፡ ከዚህ አዋጅ ጋር በወቅቱ ከመጓተት በመለስ በኢትዮጵያዊ (ኢትዮጵያዊ አይደለንም
የተፈጸመ አንድ አጋጣሚ የፖለቲካ አካሄዱን እንዴት እንደለወጠ የሚሉትን ጨምሮ) አጀንዳ ላይ መከራከር ይኖርብናል፡፡
ስለሚያሳይ ቢጠቀስ መልካም ይመስለኛል፡፡ እንዲህ ነው፣ ጥቂት (ይቀጥላል)...
ሰዎች ወደ ንጉሱ ግቢ መጥተው የሀገሪቱ ነዋሪዎች ሁሉ
በሥራ እንዲሰማሩ የሚለውን ንጉሣዊ መመሪያ ለመከተል
ይከብደናል ሲሉ ተናገሩ፡፡ እስከ ዛሬ ድረስ በዝርፊያና በቅሚያ

ቅፅ-1፣ቁጥር 1 መስከረም 2010 ዓ.ም ገፅ 7


ታዛ ፊልም

NYFA students dancing for an original film


በኢትዮጵያ የሲኒማ ትምህርት (በቀለ መኮንን)

አስፈላጊነትና ተግዳሮቱ
የሲኒማ ነገር በኢትዮጵያ መታወቅ የጀመረው ምናልባትም
ከሰይጣን ቤት ታሪክ ጋር ታጣምሮ አለያም የኢጣሊያን ወረራ
ታክኮ እንደሆነ ተደጋግሞ ሲነገር እናውቃለን። ወደዚህ ወደ ቅርቡ
ዘመን ስንመጣ ደግሞ ስመ- ገናን ከሆኑት ከነ “ጉማ” እና “ሂሩት፣
አባቷ ማነው?” ጋር ኢትዮጵያውያን የሲኒማ ባለሙያዎች
ታሪክም አብሮ መነሳት መጀመሩ የሚዘነጋ አይደለም።
የሆነው ሆኖ ባለፉት ሁለት አሰርት ውስጥ ከዚህ ቀደም በሀገሪቱ
ታሪክ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ ሲኒማን የመጻፍ፣ የመቅረጽ፣
የማቀናበር፣ የማሰራጨትና ለበርካታ ተመልካች የማሳየት ሙያዊ
እንቅስቃሴ ተስፋፍቶ ተመልክተናል። ሲኒማ ሊሆኑ የሚችሉ
ሞልተው የተረፉ ታሪኮች ቀድሞም የነበሩ ቢሆንም በስፋት በሲኒማ
የመጠበብና በቢዝነስ/በኢንዱስትሪ ደረጃ የማደራጀት ድፍረቱና
ሙከራው ግን ፈጽሞ አዲስ እርምጃ ነው ማለት ይቻላል።

በዚህ አጭር የስርጭት ዕድሜው እስከዛሬ ተቀርጸው ለተመልካች


የቀረቡትን የሲኒማ ስራዎች እንኳ ስንመለከት ወደፊት
የኢትዮጵያ ሊባል የሚበቃ የሲኒማ አሻራና የሲኒማ አምባ
መፈጠሩ እንደማይቀር የሚያመላክት ተስፋ አብሮት ይታያል።
በዚያው መጠን የጀማሪነት ህመሙን የሚያባብሱ እንከኖች ዛሬም
ከዓመታት በኋላ ገና አልተላቀቁትም። የሲኒማን ሃያል ጥበባዊ
ቋንቋ ከዘመነኛው ማህበራዊ ጥያቄ ጋር አገናዝቦ አቅም ያለው
ኪነ-ጥበብ የመፍጠር ተግባር የሲኒማው ባህል ስር ባልሰደደበት
ሀገር እንዲሁ በአቦ ሰጡኝ የሚሳካ የዋዛ የቤት ስራ አይደለም። Filmmaking at Northern Film School
ብዙ የሙከራ ዓመታት ብቻቸውን ሊፈቱት ያለመቻላቸው
ምስጢርም የዚሁ ብርቱ የቤት ስራ ማመላከቻ ምስክር ነው። ነው እንግዲህ ዛሬ ጠንካራ መልስ ከሲኒማ ሰሪው የሚጠብቀው።

በደረስንበት ሃያ አንደኛ ምዕታመት ላይ እንደየትኛውም ከዚህ ጥያቄና መልስ ጀርባ ደግሞ የተሰደሩትን እነዚህን ማህበራዊ፣
የስነ-ጥበብ ዘርፍ ሲኒማን በዘልማድና በዝግ ሞቅታ ደጋግሞ ስነ-ውበታዊና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ለማገናዘብ ባንድ ወይም በሌላ
የማምረት ጉዳይ ብቻውን ምኑንም ማንንም ወዴትም ዘዴ አቅም ያለው ሲኒማ ሰሪ ካልተፈጠረ የሲኒማ የሙከራ
ሊያሳድግ ከቶ ዓይቻለውም። ዛሬ የጥበባትን ታሪክ ጨምሮ ወይም የየዋህነት ዘመን ወደ ብስለት ሊሸጋገር አይችልም።
መላው የአፍሪቃ ታሪክ እንደገና በአፍሪቃውያን ተፈትኖ አውቀንም ሆነ ሳናውቅ (ደረጃውን የጠበቀ) የምንላቸው
እየተጻፈ ያለበት ወቅት ላይ ደርሰናል። ከዚያም አልፎ ኪነ-ጥበባትም የሚገኙት ይህንኑ ማሟላት ሲችሉ ብቻ ነው።
የአፍሪቃውያን ፍልስፍናዎች፣ እምነቶችና አመለካከቶች ሁሉ
መሰማትና ቀልብ መግዛት የጀመሩበት ዘመን ተፈጥሯል። በሌላ በኩል የነዚህን ጥያቄዎች መልስ በሙሉ ካንድ ምንጭ
በቀላሉ መቅዳት ይቻላል ማለትም ዘበት ነው። ምንጮቹ የትየለሌ
ዓለም ከደረሰበት ቴክኖሎጂ ጋር የኛ በሆነ ጥበብ የተጠመቁ ናቸው። አንዳንዴ ማስታወስ አንዳንዴም ከየት እንደተገኙ ማወቅ
ድምጾቻችን እንዴት ሆነው ሲኒማ ይሆናሉ? የሚለው ጥያቄ እስኪቸግር። ነገር ግን ወደ ምንጮቹ የሚያደርስ ኋላም ምንጭ

ቅፅ-1፣ቁጥር 1 መስከረም 2010 ዓ.ም ገፅ 8


ፊልም ታዛ

የሚያደርግ ራሱ የዕውቀት ጉባዔ ነው። ዕውቀት ወይም በዘመናዊ እንደሚታወቀው ከምንም የተጀመረው ይህ የትምህርት
ቀላል አጠራሩ መረጃ በርከት ያሉ ምንጮች እንዳሉት አይካድም። ክፍል በአሳማኝ ዓላማው የተነሳ በዪኒቨርሲቲው ማኔጅመንት
ይሁንና ሀገራችንን በመሰለ መደበኛ የሲኒማ ዕውቀት ባደባባይና እየተደረገለት የነበረው አስተዳደራዊ ድጋፍ ለስኬቱ አንዱ ድጋፍ
በቀላሉ በማይገኝበት ስፍራ ከመደበኛ የዕውቀት ጉባኤ ባጭሩ ነበር። ይሁን እንጂ በሁለት እግሩ ለማቆም በሚደረግ ቀጣይ
ከትምህርት ቤት የተሻለ ምንጭ ማግኘት ብዙም የማይሞከር ትንንቅ ትምህርት ቤቱ ብቻውን መቅረቱ (በተለይ ላለፉት
ነው። ከዚህኛው ሓያሲ፣ ከዚያኛው ሙዚየም፣ ወይም ሶስት ዓመታት ምንም መሳሪያ ለመግዛት ያለመቻሉ ወይም
ከዚህኛው መጽሀፍ አንዳፍታ አመጣዋለሁ የሚባልለት አገራዊ ያለመፈለጉ) አጀማመሩ ላይ የነበረውን ፍጥነት እንዲያጣ አድርጎ
አቅም ላይ ባለመድረሳችን አሁንም መደበኛ የትምህርት ገበታ ወደፊትም ለመራመድ እግር ከወርች ያሰረው ችግር ሆኗል።
ለሲኒማ መዘርጋቱ አማራጭ የሌለው የመፍትሄ አሳብ ነው።
ኮሌጁን በማቋቋም ወቅት ከሶስቱም ትምህርት ቤቶች
እስካለፈው 2007 ዓ.ም. ድረስ በኢትዮጵያ ውስጥ ሲኒማን ዲሬክተሮቹ ወደአውሮፓና አሜሪካ ዘልቀው ልምድ ይዘው
ለማስተማር የተቋቋመ አንዳችም መደበኛ ከፍተኛ የህዝብ ትምህርት መመለሳቸው ኋላ ላይ ለተቋቋመው ለዚህ የሲኒማ ትምህርት
ቤት አልነበረም። ከላይ እንደጠቃቀስኩት የዚሁ ትምህርት ቤት ክፍል ከፍተኛ አስተዋጽዖ ሊያበረክት ችሏል። ለምሳሌ
(መደበኛ ትምህርት) ጉባዔ ያለመኖር ነው የኢትዮጵያን ሲኒማ በኒው ዮርክ የኮሎምቢያ ዩኒቨርሲቲ የፊልም ትምህርት ቤት
የብስለት ዘመን አላቃርብ ብሎ ያቆየው ዋነኛው ምክንያት። የተስተዋለው ተማሪዎችን ከተለያየ የዕውቀት ምንጭ መውሰድ
ወይም የተለያየ ትምህርት የገበዩ ተማሪዎችን መቀበል ሊናገሩ
በዘጠናዎቹ መጀመሪያ ወደ ኢትዮጵያ ብቅ ይል የነበረው ያሰቡት ወይም ሊተርኩ የሚችሉት ታሪክ እስካላቸው ድረስ
ትልቁ የሲኒማ ምሁር ፕሮፌሰር ተሾመ ወ/ገብርኤል ምን ያህል ዘርፈ-ብዙ ጥቅም እንዳለው ለመረዳት ተችሏል።
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ንግግር ካደረገ በኋላ ከዩኒቨርሲቲው ኋላም በተግባራዊ ሙከራ ጥቅሙንም ለመጋራት ተችሏል።
ሀላፊዎች ጋር ስለ ሲኒማ ትምህርት ቤት መቋቋም ብዙ ብዙ
ውይይት አድርገው እንደነበር አስታውሳለሁ። ከዚያም በኋላ ያም ሆነ ይህ የትልልቆቹ ጥያቄዎች መልስ መገኛ የሆነ ጉባዔ
ዩኒቨርሲቲው በውጭ ሀገር ከሚኖሩ ታዋቂ ኢትዮጵያውያን ለመፍጠር ግን ገና ብዙ መሟላት የሚገባቸው መዋቅሮች፣
የሲኒማ ባለሙያዎችና መምህራን ጋርም እንዲሁ ትምህርት ቁሳቁሶች፣ ባለሙያዎችና ዕውቀቶች አሉ። ባሁኑ ወቅት ከመላው
ቤቱን የማቋቋም ተደጋጋሚ ሙከራዎች አድርጎ እንደነበር ዓለም በባለሙያዎቹ ፍላጎትና በተቋማችንም ጥያቄ እየተጋበዙ
አውቃለሁ። በዘጠናዎቹ ኢጋማሽ ግድምም በተለይ ጥልቅ ልምዶቻቸውንና ዕውቀቶቻቸውን እያካፈሉ የሚመለሱ
በጋዜጠኝነት ትምህርት ቤት በኩል የተደረገ ብርቱ ጥረት ዓለማቀፍ ባለሙያዎች አስተዋጽዖ በቀላሉ የሚታይ አይደለም።
እንዲሁ ዳር ያለመድረሱ አይዘነጋም። ለረዥም ዓመታት በነዚሁ ባለሙያዎች አማካይነት ኢትዮጵያውያን ባለሙያዎች
የሲኒማ ኮርሶችን በመምዘዝ ከተውኔት ትምህርቶች ጋር ይሰጥ በዓለማቀፍ መድረክ ሊያገኙ የሚችሉበትን የውጭም ሆነ
የነበረው በዪኒቨርሲቲው የቴአትር ትምህርት ክፍል ነበር። የውስጥ የቤት ስራ ለመስራት ዕቅዱ አለ። ሌላውና ዋናው
ነገር በመስኩ ላይ ያለው የሲኒማ ማህበረሰብ ከትምህርት
በሁለት ሺህ ዓ.ም. መጀመሪያ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ቤቱ ጋር የሚሰራበትን መንገድ ማመቻቸት ነው። በመተባበር
አካዳሚክ ክፍሎች እንደገና ሲዋቀሩ የስነ-ጥበብ፣ የሙዚቃና የተሻለ ማደግ ስለሚቻልም ስለሚሻልም። ለዚህም አስቀድሞ
የቴአትር ትምህርት ቤቶች ባንድ ኮሌጅ ስር ተደራጅተው መድረኩን የተመቻቸ ማድረግ ይጠበቃል። የዩኒቨርሲቲውም ሆነ
እንዲሰሩ መደረጉ የሲኒማን የትምህርት ገበታ የመዘርጋትን የመንግስት ድጋፍ በዚህ በኩል ተወዳዳሪ የሌለው ነው። አያሌ
አስፈላጊነት እንደገና ቀሰቀሰው። በዚህ አጋጣሚ የሲኒማ እውቅ ተቋማት ከታላቅነት ጣሪያ የደረሱት ብዙዎቹ እንዲሁ
ትምህርት ክፍልን ለማቋቋም የተደረጉ ሙከራዎች ሁሉ ከምንም ወይም በጣም ከትንሽ ተነስተው ነው። ተሰጥዖና ዝንባሌ
ከመክሸፍ ያለፈ የውጤት ታሪክ ስላልነበራቸው ማንም ተመልሶ ያንንም አድናቂና ገዢ እስካለ ድረስ። የደረስንበት ዘመን በተለይ
በዚያ ውስጥ የመዳከር ሃላፊነትን መውሰድ የፈለገ አልነበረም። በሲኒማ ጥበብ፣ የሚተርከው ላለው ኢትዮጵያዊን ለመሰለ
ባለታሪክ አያሌ የማደግና የመስፋፋት ዕድሎች ፈጥሮለታል።
በዚያ መካከል የስነ-ጥበብ ትምህርት ቤት አዲስ አበባ ውስጥ ዓለም የደረሰበትን ቴክኖሎጂ ለመጠቀም ሌሎች ያለፉበትን
አይቢስ ይባል ከነበረ የካናዳ ግብረ-ሰናይ ድርጅት ጋር ስምምነት ሂደት ማለፍ ሳይጠበቅበት ከቁንጮው መሳፈር የሚችልበት
ይፈራረማል። ይህም የአኒሜሽን ክፍለ-ትምህርት ለማቋቋም ዘመን ነው። ተሰጥዖ ደረጃውን ከጠበቀ ዕውቀት ጋር ተዳምሮ
ያለመ ሲሆን በስምምነቱ መሰረት የትምህርት ቤቱ የጊዜው የራስን አሻራ በባለቤቱ ድምጽ ለዓለም ለማሰማት ከዓለም ፊት
ሃላፊ የካናዳን ተቋማት ከጎበኘ በኋላ የስምምነት ፍላጎቱ ወደ እኛም የምንለው አለን ለማለት ሲኒማን የሚያክል መሳሪያ ብዙ
ሲኒማ ትምህርት ደረጃ እንዲሸጋገር ምክንያት ሆነ። ምንም አይገኝም። በዘመኑ ደረጃ ተዘጋጅቶ ለመገኘት የሁሉም በተለይም
እንኳ ስምምነቱ እየተጓተተ ጉዳዩን አሰልቺ ቢያደርገውም የመንግስት ድርሻ አሁንም ገና ብዙ ሃላፊነት ያለበት ነው።
በመጨረሻ ባንድ ጊዜ አምስት ወጣቶችን ለቴክኒካዊ ስልጠና
ወደ ካናዳ ኪቤክ ለመላክ ተችሎ ነበር። የስምምነቱ ወደ ሲኒማ
ደረጃ ማደግ መንስኤውም በኮሌጁ ስር ለሲኒማ ዋነኛ ግብአቶች
የሚባሉት የድምጽ፣ የምስልና የንቅናቄ ትምህርት ቤቶችና ከዚህኛው ሓያሲ፣ ከዚያኛው
ዲሲፕሊኖች በሙሉ ባንድ ስፍራ የመገኘታቸው አጋጣሚ
ነበር። ይሁንና አላቋርጥ ያለው የሲኒማ ፈተና በዚህኛውም ሙዚየም፣ ወይም ከዚህኛው
ዙር አልተላቀቀም ነበር። ይህም ወደ ውጭ ተልከው የነበሩት
አምስቱም ወጣቶች በሙሉ እዚያው የመቅረታቸው ዜና ነበር። መጽሀፍ አንዳፍታ አመጣዋለሁ
የስነ_ጥበብ ትምህርት ቤት ግን በሲኒማ ትምህርት ታሪክ ውስጥ
ካልተሳካላቸው ተራ ላለመግባት ቆርጦ ስለነበር በአሜሪካን
የሚባልለት አገራዊ አቅም ላይ
አገር ከሚገኙ ኢትዮጵያውያን የሲኒማ ባለሙያዎችና ሀገርም ባለመድረሳችን አሁንም መደበኛ
ውስጥ ካሉ ጥቂት ልምድ ያላቸው ባለሙያዎች ጋር በመሆን
አዲስ የአካዳሚክ ቅድመ-ዝግጅት ላይ በመስራት የትምህርት የትምህርት ገበታ ለሲኒማ
መርሀ-ግብሩን በዩኒቨርሲቲው እንዲጸድቅ አደረገ። ባገር
ውስጥ ይመጥናሉ ብሎ ከመረጣቸው ለጊዜው ጥቂት የሲኒማ መዘርጋቱ አማራጭ የሌለው
ባለሙያዎችና ከውጭ ሀገር ከቀጠራቸው ሁለት ባለሙያዎች
ጋር አጠናክሮ የመጀመሪያውን የመንግስት ከፍተኛ የሲኒማ የመፍትሄ አሳብ ነው።
ትምህርት ቤት በመስከረም ወር 2007 ዓ.ም. ሊከፍት ችሏል።

ቅፅ-1፣ቁጥር 1 መስከረም 2010 ዓ.ም ገፅ 9


ታዛ አጭር ልብወለድ

አሐድ ሐአ’ም

የአሐድ ሐአ’ም ቀብር


እጅግ የታወቀና የተከበረ ሰው መሆን እ ኔ ና ሞልቻድስኪ ብቻ ነን ስለዚህ ታሪክ
አለበት አልኩኝ። የምናውቀው። የታሪኩን መጨረሻ ለማየት
በይበልጥ የጓጓሁት ደግሞ እኔ ነኝ።
ሁሉም ጉዳይ እጅግ ቢያስደንቀኝም፤
ደግሞም በጥቂቱ ሳያሳስበኝ አልቀረም። ሽማግሌውን ሞልቻድስኪን
ውስጠ‐ ምስጢሩን መመርመር ያዝኩ። አልወደውም፤ ደግሞም እፈራዋለሁ።
ወላጆቼ ከፓሪስ ከሚመጣው የሩሲያኛ ከሱቅ አንድ ከረሜላ የሰጠኝ እንደሆን
ፐስሌዲኒይ ኖቬስት ጋዜጣ በቀር ሌላ ከጉንጭ ላይ ሙዳ ስጋ ቆርሶ የመውሰድ
አያነቡም። ጋዜጣው ስለ አሐድ ሐአ’ም ያህል ይቆናጠጣል። ሁሌም ድርጊቱ
አንዲት ቃል እንኳ አስነብቦ አያውቅም። እንዲህ ነው። ከቃላት በቀር ምንም ነገር
መኩሪያ መካሻ
ዳሩ ግን እነሱም ቢሆኑ ወሬ የሚሰሙት በዋዛ አሳልፎ አይሰጥም። ጠንካራ ጎኑ
ከሽማግሌው ሞልቻድስኪ ነው። መለፍለፍ ነው፤ አንድ ነገር ከጠየቅኩት
(በቤንጃሚን ታሙዝ) እሱ ከዋርሶ የሚመጣውን ሔይንት
ሁሌም መልስ ይሰጠኛል። እናቴ ሁሌም
ስራ ብዙ በመሆኗ አባቴም ከስራው በቀር
ትርጉም:- መኩሪያ መካሻ የተሰኘ ጋዜጣ ያገኛል። በዚያ ጋዜጣ ላይ በሌላ ነገር ውስጥ ጥልቅ ስለማይል


ደግሞ የአሐድ ሐአ’ም ታሪክ፣ የፖሊስ ዝርዝር መልስ የሚሰጠኝ ሞልቻድስኪ
ሐድ ሐአ’ም የሞተው ገና የሰባት እና ጋሪዎቹ እንዲሁም ሌሎች ታሪኮች ነው። ሆኖም የእሱ ነገር ስሜት ሰጥቶኝ
ዓመት ልጅ እያለሁ ነው። ስለ ነበሩበት። ሰፈሩ ሁሉ በዚህ መንገድ ነው አያውቅም። እንዲያውም አባቴ ነገሩ
አሐድ ሐአ’ም ምንም የማውቀው ስለ ታሪኩ የሚያውቀው እና በኋላም እርባና ቢስ ነው ብሎ ስላጣጣለብኝ እንጂ
ነገር ባይኖረኝም፤ ስለ እሱ ወሬውን የሚጠርቀው። በእነዚያ ጊዚያት ስለ ሁሉም ጉዳይ ማለትም ስለ አሐድ
የሰማሁት ከባለ ግሮሰሪው ሞልቻድስኪ ነበር። እንኖር የነበረው ኤፒሲ በተሰኘውና ሐአ’ምና ስለ ፖሊስ ከእሱ አስቀድሜ
አሐድ ሐአ’ም በሚኖርበት ሰፈር ፈረሶች፣ በእንግሊዝ-ፍልስጤም ዳርቻ መንደር ማወቅ እችል ነበር። ስለዚህ ሌላ ምርጫ
ጋሪዎችና አውቶብሶች እንዳያልፉ ታግደዋል፤ ነው። ይህም አረቦች የሚኖሩበትን ስለሌለኝ ወደ ሞልቻድስኪ ሄጄ በሔይንት
ምክንያቱም ድምፃቸውን መቋቋም የሚችል የማንሺየህ መንደር በሚያዋስነው ጋዜጣ ስለተፃፈው ነገር እጠይቀዋለሁ።
አልነበረምና። ምንም አይነት ትራፊክ በቤቱ ስፍራ ሲሆን አረቦቹ ስለ አሐድ ሐአ’ም
ደጃፍ እንዲያልፍ አይፈቅዱም-ፖሊሶቹ። ይህ ሰምተው አያውቁም። በመጀመሪያ ሰሞን ሁሉንም
ሁኔታ እጅግ ስላስደመመኝ አሐድ ሐአ’ም ማን
ነገር በዝርዝር ፃፉ። አሐድ ሐአ’ም
እንደሆነ መረጃ መሰብሰብ ገባሁ። በከተማው ከአካባቢው መንደርተኛ

ቅፅ-1፣ቁጥር 1 መስከረም 2010 ዓ.ም ገፅ 10


አጭር ልብወለድ ታዛ

ቤንጃሚን ታሙዝ

መታመሙን፣ መልካም ሁኔታ ላይ እንዳልሆነ፣ ግን ደግሞ፤ ፍሬም የለውም። ደግሞም ቀብሩ የት እንደሆነና
ፍፁማዊ ፀጥታን እንደፈለገና ፖሊስም በዚሁ የተነሳ ክብካቤ ጆሮው ላይ የሚያርፍ የመነፅር እዚያም መገኘት እንዳለብኝ
እንደሚያደርግለት ሃተታ አቀረቡ። ስለዚህ ጉዳይ እንኳን መደገፊያም አልነበረውም። በ ማ ሰ ብ ሞልቻድስኪን
አስቀድሜ ነግሬያችኋለሁ። በኋላ ደግሞ የጤናው ሁኔታ ይበልጥ እንዲህ አይነቱን መነጽር ቀደም ጠ የ ኩ ት ። ሞልቻድስኪ
መታወኩን እና ዕውነታውን ሁሉ ዘክዝከው ማውጣታቸውን ሲል አውቃለሁ። አባቴም ጋዜጣውን ተ መ ል ክ ቶ
ቀጠሉ። ያለው ይህን መሰል መነጽር ማ ክ ሰ ኞ በ ዘ ጠ ኝ ሰዓት
ነውና። ሌንሶቹ በጥብቅ አስከሬኑ ከቤቱ እንደሚወጣና
አሐድ ሐአ’ም እውነተኛ ስሙ አሐድ ሐአ’ም ሳይሆን አቶ ተጣጣፊ ስፕሪንግ የተያያዙ እንደሚቀበር ነገረኝ። ሲነግረኝ
ጂንስበርግ መሆኑም ታወቀ። በሩሲያ ውስጥ ሕገ-ወጥ ጉዳዮችን በመሆናቸው እና አፍንጫ ያ ዕለት ሰኞ እና ባለቀ ረፋድ
አንስቶ ስለሚጽፍ እንዳይያዘ እና ራሱን ለመሰወር ሲል አሐድ ላይ ግጥም ስለሚሉ ቀይ ሰዓት ነበር።
ሐአ’ም ነኝ አለ። በመጨረሻም ወደ እንግሊዝ ለመሰደድ ምልክት ያትማሉ። ለዚህ ነው
ተገደደ። እዚያም ማለፊያ ገቢ የሚያስገኝለትን የሻይ ንግድ ከአፍንጫ ላይ የማይወድቁት። በዚያው ዕለት ምሽት ስለ
በመነገድ ቆየ። ከዚያም ወደ ፍልስጥኤም በመምጣት ሔርዚሊያ የሚደሉ ባይሆንም መስህብነት ጉዳዩ ለወላጆቼ ነግሬ ቀብር
ጅምናዚየም አጠገብ ቤት ተሰጠው። ወላጆቼ የመጀመሪያ ደረጃ አላቸው። ዳሩ እንዳይወድቁና ላይ መገኘት እንዳለብኝም
ትምህርቴን በመልካም ሁኔታ ካጠናቀቀሁ ወደ ሔርዚሊያ እንዳይሰበሩ ጥንቃቄ ማድረግ ገለጽኩላቸው። አባቴ “እንቶ-
ጅምናዚየም እንደሚያስገቡኝ አበክረው ይነግሩኝ ነበር። ለዚህም ያስፈልጋል። ፈንቶ አታውራ” ብሎ ሲቆጣኝ፣
ነው ስለ አሐድ ሐአ’ም ከመስማቴ በፊት ስሙን የማውቀው። እናቴ ደግሞ “መጀመሪያ የቤት
ደግሞም አሐድ ሐአ’ም በሔርዚሊያ ጂምናዚየም አጠገብ ይኖር አሐድ ሐአ’ም ግን -ሥራህን በሰራህ” አለቺኝ።
ነበር የሚለውን ወሬ ስሰማ አዲስ ዜና ያልሆነብኝ። በእነዚህ ችግሮች የተጨነቀ በዚህ ሁኔታ ውስጥ ሆኜ
አይመስልም። ከፎቶ ግራፉ በነጋታው ከቀኑ ስምንት ሰዓት
በመጨረሻም ከእነ ፎቶው ስለመሞቱ ጽፈው አወጡ። እንደምመለከተው ሌላ ተኩል ሲሆን ከአሐድ ሐአ’ም
ሽማግሌው ሞልቻድስኪ ፎቶውን እንድመለከት ስላደረገኝ የሚያስጨንቀው ነገር አለ። መኖሪያ ቤት ፊት ለፊት
በሕይወቴ የምደመምበትን አንድ ነገር አገኘሁ። ሁሌም ስለ ፊቱ የተጨነቀና የተጠበበ ካለው የጽሕፈት እቃ መደብር
ፀሐፊዎች አስባለሁ። በተለይ ደግሞ ሕገ ወጥ ነገሮች የሚጽፉትን ነው። ሞልቻድስኪ እንደነገረኝ እና ከግሮሰሪው አጠገብ ቆሜ
ፀጉራቸው ብዙ፣ ጺመ ቁጥቋጦዎች እና አይነ ፈጣጦች አድርጌ ከሆነ ስለ አገራችን የወደፊት ጠበቅሁ። ምንም ቢሆን ሁለት
እገምታለሁ። ብዙ መፃፍ ምናልባትም አይንን ይጎለጉላል። ዳሩ ዕድል የሚጨነቅ እና ሰዓት ያህል ከመዘግየት ግማሽ
ግን አሐድ ሐአ’ምን እንዴት ልግለፅላችሁ? ፊቱ ባለሦስት ለሁሉም ችግሮች መፍትሄ ሰዓት ቀድሞ መገኘት ይሻላል።
ማዕዘን ነው። ከወደላይ ግንባረ ሰፊና መላጣ፤ ከወደታች አገጨ ለመስጠት የሚኳትን ጸሓፊ በትዕግሥት ብጠብቅም በዚያ
ጠባብ እና ሹል ነው። ፎቶውን ከተመለከትኩ በኋላ ግን የነበረኝን ነበር። ለዚህም ነው እንዲህ ስፍራ የተገኘሁት እኔ ብቻ
አስተሳሰብ ለወጥኩ። ከሁሉም በላይ የጸሐፊዎቹ አዕምሮ ነው ዕውቅ የሆነውና ፖሊሶችም መሆኔ ደግሞ ደነቀኝ። ከብዙ
ዋናውና አስፈላጊው ነገር። ለዚህም ነው ጭንቅሎ ራስ እና ለእሱ ያላቸው እይታ እንዲያ ሰዓታት በኋላ በትሩምፔልዩር
ሾጣጣ የፊት ገጽ የያዘው። እንደ ማንኛውም የእሱ ዘመን የሆነው። ጎዳና ወደሚገኘው የመቃብር
ሰዎች መነጽር ያደረገ ሲሆን፣ የእሱ መነጽር ግን ወርቃማ ስፍራ ለመሄድ ወሰንኩ።

ቅፅ-1፣ቁጥር 1 መስከረም 2010 ዓ.ም ገፅ 11


ታዛ አጭር ልብወለድ

ሥፍራው ፀጥ ያለና ሰላማዊ ሲሆን የተወሰኑ ሴቶች በብዙ የሰፈሩ ትላልቅ ሰዎች ለመጀመሪያ ጊዜ ስለተመለከቱት
መቃብሮች ላይ ሲያነቡ ተመለከትኩ። ሆኖም ግን አሐድ ስሙን ጠየቁት። እሱም የእኔን ስም በመጠየቁ ስሜ ኤልያኪም
ሐአ’ም መቃብር ላይ ማንም አያለቅስም። መጠየቅ ደግሞ ተገቢ መሆኑን ነገርኩት። እሱም በተራው ስሙ ቪክተር መሆኑን
አልነበረም፤ ደግሞም ከማላውቀው ሰው ጋር አልነጋገርም። ተናገረ። በመጀመሪያ የቁጩ መስሎኝ ነበር። በኋላ ግን
ስለዚህ ወደ አሌንባይ ጎዳና ተመልሼ ለመጓዝ ወሰንኩ። የቀብሩ አመንኩት። በደንብ መተዋወቅም ጀመርን።
ሥነ‐ስርአት በዚያ ጎዳና ላይ ሊካሄድ ይችላል ብዬ ተስፋ
በማድረግ ለቀስተኞቹን ልደርስባቸው ወደዛው አቀናሁ። አንድ ዕድሜዬን ጠየቀኝ፤ ሰባት መሆኑን ነገርኩት። የእሱ ዕድሜ
ነገር ሳይከሰት አይቀርም መሰል መንገዱ ተዘጋግቷል። ሃያ ሦስት መሆኑን ነገረኝ። ከዚያ በጌዩላ የመጀመሪያ ደረጃ
ትምህርት ቤት ተማሪ እንደነበርኩ ስነግረው፤ እሱ ትምህርቱን
ወደ ኸርዚሊያ ጂምናዚየም ለመመለስ ስወስን የውሻ ድካም ጨርሶ በእብራይስጥ፣ በአረብኛና በፈረንሳይኛ ቋንቋዎች
ተሰምቶኝ ነበር። ስለዚህ ከጄኡላ ጎዳና በተጓዳኝ ወዳለው እንደሚሰራ አብራራልኝ። በመጀመሪያ እዚህም ላይ የዋሸኝ
ወደ አለንባይ ጎዳና አግዳሚ ወንበር ላይ እረፍት ለማድረግ መስሎኝ ነበር። ‘እንዴት ይህን ሁሉ ቋንቋ ያውቃል በሚል?’
ተቀመጥኩ። ከዚያ ሆኜ በድንጋይ የተገነባውንና አባቴ ፂሙንና ዳሩ ግን እንዳልዋሸኝ እርግጠኛ ነኝ።
ፀጉሩን የሚያስተካክልበትን ህንፃ እመለከታለሁ። ፀጉር
አስተካካዩ እንደ ወላጆቼ ሁሉ ወደ ኤሬትዝ እስራኤል የመጣው ቀስ እያልን ነበር የምናዘግመው። ምክንያቱም በዚያ አሸዋማ
በጀልባ ነው። መሬት ላይ በበረባሶ ጫማ በፍጥነት መጓዝ አስቸጋሪ ነው።
በተለይ እኔን አሸዋው አስቸግሮኝ ስለነበር አንድ ቀልድ ነገረኝ።
ለቀስተኞቹ በፒንስኬር ጎዳና አድርገው ወደ መቃብሩ በቀልዱም እንዲህ ባለ በረሃ ውሰጥ የእስራኤል ልጆች ለአርባ
ሲያልፉ ጠብቄ እነሱን ለማጀብ ነበር እዚያ መጠበቄ። አላማዬ አመታት ከምስር (ግብፅ) አገር ወደዚህ እንደተጓዙ። “እንዳንተ
እንደዚያ ቢሆንም ዕንቅልፍ ጣለኝ። በረባሶ ጫማ አድርገው ቢሆን ኖሮ ግን ሰማኒያ ዓመት
ይፈጅባቸው ነበር” አለኝ። ከዚያ ሁለታችንም ተያይዘን ሳቅን።
ምን ያህል ጊዜ እንደተኛሁ ባላውቅም አንድ ድንገተኛ እጅ ታሪኩን ካወቅሁ በኋላ በሚያስቅ መልኩ መልሼ መተረኩን
ትከሻዬ ላይ አረፈ። ከዚያም በጨዋነትና በለዘበ ድምፅ “አንተ አልቻልኩበትም። በትምህርት ቤት በኩል ሳልፍ የተማርኩበትን
ልጅ በል ተነስ! አንተ ልጅ!” አለኝ። ትምህርት ቤት አሳየሁት። እሱም በተራው ስለትምህርት
ወዳድነቴ ሲጠይቀኝ እንደነገሩ መሆኔን ነገርኩት።
በ መ ጀ መ ሪ ያ ጊ ዜ ው ድንግዝግዝ ያለና አየሩም ትንሽ
ቀዝቀዝ የሚል ስሜት ተሰማኝ። በዝግታ ፊት ለፊቴ የቆመው ከዚያ ለምን በእንቅልፍ እንደወደቅሁ ጠየቀኝ። እኔም
ሰው ማን እንደሆን ለመለየት ቻልኩ። እንደ ሞልቻድስኪ ስለ አሐድ ሐአ’ም ጉዳይ አንስቼ የቀድሞ ስሙ ጂንስበርግ
ሽማግሌም ያልሆነ፤ እንደኔም ገና ጨቅላ ልጅ ያልነበረ ስለመሆኑ፣ በእንግሊዝ ስለነበረው የሻይ ንግድና ስለሁሉም
በመሀል የዕድሜ ክልል የሚገመት-እንበልና አሥራ ስድስት የማውቀውን ያህል ነግሬው በቀብሩ ሽኝት ለመገኘት ስለመፈለጌ
ዓመት የሚሆነው ሰው ነበር። ከእንቅልፌ እንደ ነቃሁ መገመት ተረኩለት።
ባልችልም በኋላ ግን ሃያ ሦስት ዓመቱ እንደሆነ ተገንዝቤያለሁ።
በዚያን ጊዜ ቪክቶር በአግራሞት “ምን?!” ሲል ጮኸ።
“አዳምጥ” አለኝ። ቀጥሎም “እዚህ አካባቢ ነው የምኖረው፤ “በዚያ አግዳሚ ላይ አሥራ ሁለት ቀናት ተኛህ ማለት ነው?”
ከብዙ ሰዓታት በፊት አግዳሚ ወንበር ላይ ተቀምጠህ አለኝ። እንዲህ አይነቱ ጥያቄ መቼም እብድ ያደርጋል። በዚያ
ተመልክቼሀለሁ። አግዳሚ ላይ አሥራ ሁለት ቀናት መተኛቴ ወላጆቼም በእነዚያ
ቀናት ሁሉ በእኔ ላይ ስለደረሰው አለማወቃቸው ከአዕምሮ
አሁን መሽቷል። እዚህ ተጋድመህ ብትቀር ቤተሰቦችህ
በላይ ነው። ለግማሽ ቀን እንኳን በቤት ካልታየሁ እንዴት
ሊጨነቁ ይችላሉ ብዬ አስባለሁ። ስለዚህ ተነስና ወደ ቤትህ
እንደሚያደርጋቸው አውቃለሁ። በዚህ ጊዜ ስለሆነው ነገር
ላድርስህ። የት ነው የምትኖረው?”
ምንም ላውቅ አልችልም። “አሥራ ሁለት ቀን ስትል ምን
ተነስቼ ቆምኩ። ጉልበቴ እንደዛለ ተሰማኝ። እንደምንም ማለትህ ነው?” አልኩት ቪክቶርን። ቪክቶርም በተራው
ብዬ ቆምኩና ተመለከትኩት። መልካም ወጣት ነው። ንግግሩም “የገረመኝኮ ከአሥራ ሁለት ቀናት በፊት የአሐድ ሐአ’ምን
ያማረ። እንዳይጨነቅ እና በራሴ መሄድ እንደምችል ነገርኩት። ቀብር በመስኮቴ በኩል በዓይኔ በብረቱ መመልከቴ ነው”።
ዕውነታው ግን የጌዩላን ጎዳና ሙሉ ርዝመት፣ በሐይራኮን
“ታዲያ ቀብሩ ዛሬ ስለመሆኑ እንዴት አሰብኩ?” መልሼ
ጎዳና አድርጎ በሀሰን ቤክ መስጊድ በኩል ማለፍ እንዲህ ቀላል
ጠየኩት።
አይደለም። እኔ ስለምፈራ ሳይሆን በዚያ ጨለማ ምን መሆን
እንደሚቻል ስለማይታወቅ ነው። ብቻዬን ለቆኝ እንደማይሄድ “ዛሬ መሆኑን ማን ነገረህ?” አለኝ ቪክቶር።
ተስፋ ያደረኩ ሲሆን እሱም ብቻዬን አለቀቀኝም። የተመላለስነው
ቃል መልካም ቢሆንም ትእዛዛዊም ጭምር ስለነበር የሚለኝን “ባለ ግሮሰሪው ሞልቻድስኪ ነው የነገረኝ” አልኩት።
ተቀበልኩት። እናም እጄን ሰጥቼው አብሬው በጌዩላ ጎዳና መጓዝ
ጀመርን። “ይህን ፍሬ ከርስኪ ወሬ ከየት አመጣው?” ሲል በጥያቄ
አፋጠጠኝ።

ቅፅ-1፣ቁጥር 1 መስከረም 2010 ዓ.ም ገፅ 12


አጭር ልብወለድ ታዛ

“ከጋዜጣው አግኝቶ ነው” አልኩት። “አሐድ ሐአ’ምን ይበልጣሉን?” ብዬ ስጠይው “አዎን


በትክክል” የሚል ፈርጣማ መልስ ሰጠኝ። በአባባሉ ብደነቅም
“ከየትኛው ጋዜጣ?” ሲል ጠየቀኝ። በሃሳቡ ግን አልተስማማሁም። ድንገት ቤታችን መቃረባችንንና
ከሞልቻድስኪ ግሮሰሪ መድረሳችንን ተመለከትኩ። ማልቀስ
“ከሔይንት ጋዜጣ” መለስኩለት። ዳሩ ግን ወላጆቼ
ዳዳኝ። ሁኔታው ግራ ፈትል ቢሆንብኝም ጨለማ በመሆኑ ግን
የሚያነቡት “ፓስለድኒይ ኖቪስት” የተባለውን ጋዜጣ
ተደሰትኩ።
ቢሆንም እነሱ ግን ምንም ነገር አላሉኝም። እሱ ግን ከዋርሶ
የሚመጣውንና መቶ በመቶ እርግጠኛ የሆነ ጋዜጣ እንደነበረው እራሴን ለመቆጣጠር እየታገልኩ ግሮሰሪውን አሳየሁት።
አስረዳሁት። በዚህ ጊዜ እንደ እብድ ሳቀ። ከውጭ የሚመጡት እርሱም “ነገ ጠዋት ለባለ ግሮሰሪው የእብራይስጥ ጋዜጣ
ጋዜጦች በፖስታ ቤት ስለሚገቡ አንዳንድ ጊዜ እስከ ሁለት ማንበብ እንዲጀምር ንገረው አለኝ” ፈርጠም ብሎ “ንገረው”
ሳምንት ድረስ እንደሚፈጅባቸውና እኔ የተመለከትኩት የአሐድ አለኝ ቪክቶር አሁንም። “እብራይስጣዊ-እብራይስጥኛ ይናገር”።
ሐአ’ም ፎቶግራፍ ያለበት ጋዜጣም ሁለት ሳምንት ያህል የቆየ
መሆኑን ዘርዝሮ አስረዳኝ። በትክክል ላገናዘበው ደግሞ ሁለት አብሮኝ ደረጃውን ወጥቶ በሩን ራሱ አንኳኳ። ወደ ቤት
ሳምንት እና አሥራ ሁለት ቀናት ብዙም ልዩነት የላቸውም። ዘለቅን። ስለ ሁኔታው ከማስረዳቱ በፊት አባቴ ቶሎ ብሎ
ቪክቶር በሁኔታው ቢስቅም እኔ ግን ወይ ፍንክች! አለመሳቄን ሲዳብሰኝ እናቴ ጩኸቷን አቅልጣ አቀፈቺኝ። ቪክቶርም
ሲመለከት ደግሞ “አትጨነቅ፣ ደግሞም አትዘን ኤልየኪም። ወዲያው ደህና ሁኑ ብሎ ተሰናበተ።
ይህ ስህተት ባይከሰት ኖሮ መች እንዲህ ወዳጅ እንሆን ነበር?”
ሲል አፅናናኝ። ከእናቴ ዕቅፍ እንደተላቀቅሁ ወደ ባልኮኒው ወጥቼ ቪክቶር
ቤታችንን ለቆ ወደቀኝ መታጠፉን ተመለከትኩ። ባለ በሌለ
እሱ ያለውን ሁሉ በጥሞና ባዳምጥም ምንም መልስ ጉልበቴም “ቪክቶር መልካም ሰው ነህ፣ እወድሃለሁ!” ስል
አልሰጠሁም። እንዲያውም ከበፊቱ ይልቅ አሁን ደስተኛ ነኝ። ጮኽኩ። ወዲያው ደግሞ ማን እንዲህ እንዳለው እንዳያውቅ
ከዚያም የባህሩን ሞገድ ድምፅ ስለመስማቴ ጠየቀኝና ወደ ባህሩ በባልኮኒው መከለያ ስር ተደበቅሁ። እዚያው እንዳጎነበስኩ
የመቃረባችን ምልክት መሆኑን ተናግሮ ወደ ሐይአርኮን ጎዳና አገጬ በመመታቱ ከንፈሬ ተሰንጥቆ መድማቱ ታወቀኝ።
እንደምንታጠፍ ገለፀልኝ። እኔ ግን ባህሩ ሩቅ በሆነና ለረጅም
ጊዜ አብረን እንድንጓዝ መፈለጌን ነገርኩት። ቪክቶር በበኩሉ ጊዜ በሁኔታው ወላጆቼ ተደናገጡ። ወዲያው በቁስል ማድረቂያ
በሰዓት ሳይሆን በወዳጅነት እንደሚወሰንና መላው ሕይወታችን አዮዲን እና ሌላም ተጨማሪ የህክምና እርዳታ እያደረጉልኝ
ከፊት ለፊታችን በመሆኑ ስለ ጊዜ መጨነቅ እንደማይኖርብን በመሀሉ ጭልጥ ያለ እንቅልፍ ወሰደኝ። እንዲያው ስለደከመኝ
ነገረኝ። ሳይሆን ብቻዬን መሆን ስለፈለኩ። ማለትም ከቪክቶር ጋር
ዳግም የመገናኘት ምኞት ጣለኝ።
በወቅቱ የተረዳሁት ስለመሆኔ አላውቅም፤ አሁን ግን እሱ
ያለኝ ነገር ገብቶኛል። አብረን እንደተጓዝን “አዳምጥ፣ አንድ በዚያ ምሽት ስለ ቪክቶር ማለም አልቻልኩም። በሌላ
መዝሙር እዘምርልሃለሁ” ብሎኝ ነበር። እናም “ሁሉም ጊዜ ግን አድርጌዋለሁ። እስከ ዛሬም ድረስ እንዲያ ነው።
ጀልባዎች የሰንበትን ብርሃን ያበራሉ” የሚለውን መዝሙር ***
እስከመጨረሻው ዘመረልኝ። በተራዬ የምችለውን መዝሙር
ማስታወሻ ፦ አሐድ ሐአ’ም በብዕር ስሙ (Nom-de-
እንድዘምርለት ቢጠይቀኝም፤ እኔ ለመዘመር አፈርኩ። እሱ ግን
plume) የታወቀ የእብራይስጥ ደራሲ አሸር ሒርች ጂንስበርግ
በተጨማሪ “ኦ ምሽቱ፣ ኦ ምሽቱ፣ ኦ አባት አገር” የሚለውን
ዘመረልኝ። ከዚያም ገጣሚያን በዓለም ያሉ ታላቅ ሰዎች ናቸው ሲሆን ከ1856-1927) የኖረ ነው።
አለኝ።

እሱ ከዋርሶ የሚመጣውን ሔይንት የተሰኘ ጋዜጣ


ያገኛል። በዚያ ጋዜጣ ላይ ደግሞ የአሐድ ሐአ’ም ታሪክ፣
የፖሊስ እና ጋሪዎቹ እንዲሁም ሌሎች ታሪኮች ነበሩበት።
ሰፈሩ ሁሉ በዚህ መንገድ ነው ስለ ታሪኩ የሚያውቀው
እና በኋላም ወሬውን የሚጠርቀው።

ቅፅ-1፣ቁጥር 1 መስከረም 2010 ዓ.ም ገፅ 13


ታዛ

ገፅ 14
ታዛ

ቅፅ-1፣ቁጥር 1 መስከረም 2010 ዓ.ም ገፅ 15


ታዛ ደብረ-ያሬድ



የቅዱስ ያሬድ ታሪክና


ከጌታቸው ኃይሌ (ፕሮፌሰር)
የግዕዝ ሥነ ጽሑፍ

ወናሁ፡ ይኬልሑ፡ ኲሎሙ፡ ደቂቁ፡ ውስተ፡ ቤተ፡ ታሪካችን ለቅዱስ ያሬድና ለድርሰቶቹ እንዳደረገው የነሱን
ክርስቲያን፡ በማኅሌተ፡ ሱራፌል፡ በከመ፡ መሀሮሙ፡ ስምና ድርሰት መዝግቦልን አላገኘንም። ስሙ ያልታወቀ
ውእቱ፡ ሰሚዖ፡ እምኔሆሙ። ኢትዮጵያዊ የደረሰው የምንለው እንኳን የዚያን ዘመን ድርሰት
የለንም። መኖሩን እስክናውቅ ድረስ፥ ቅዱስ ያሬድን ብቸኛ
እነሆ (የያሬድ) ተማሪዎች ሁሉ (የኢትዮጵያ ካህናት) የግዕዝ ሥነጽሑፍ መሥራች አድርገን መቁጠር ይኖርብናል።
ከሱራፌል ሰምቶ እንዳስተማራቸው እቤተ ክርስቲያን
በእነሱ ማህሌት ይዘምራሉ (ድርሳን ዘያሬድ ገጽ 15)፡፡ ቀሲስ ያሬድን ብቸኛ የግዕዝ ሥነጽሑፍ መሥራች አድርጎ
ለማየት በቂ ምክንያት አለን። እንዲያውም የግዕዝ ሥነጽሑፍ
የያሬድን ቃል የተማረ ሰው ፍሬው [አራት ሺህ] መሥራች ከማለት ይልቅ የኢትዮጵያ ሥነጽሑፍ መሥራች
ልንለው ይገባል። ልዩነቱ ምንድነው? ልዩነቱ፥ “አንድን ድርሰት
ነው፡፡ ኩነኔም የለበትም፡፡ ብሔራዊ የሚያደርገው የድርሰቱ ቋንቋ ነው፥ ወይስ የደራሲው
ዜግነት፥ ወይስ የድርሰቱ ርእስ ነው” ከሚሉት ዓለም አቀፋዊ
(ታሪክ ዘያሬድ) ጥያቄዎች ጋር የተያያዘ ነው። በነዚህ ጥያቄዎች ምክንያት የግዕዝን
ሥነጽሑፍ ከሁለት ልንከፍለው እንችላለን። አንዱ ክፍል ከባሕር
ማዶ ተጽፈው ወደግዕዝ የተተረጎሙትን መጻሕፍት ይይዛል።
ለምሳሌ ያህል፥ በአክሱም ዘመነ መንግሥት ከግሪክኛ ወደግዕዝ
ቅዱስ ያሬድን ከመስኬ ከግዕዝ ሥነጽሑፍ ጋር የተተረጎሙት ወንጌላቱ፥ የአባ ጳኵሚስ ሥርዓተ መነኮሳት፥
ያያያዝኩት የግዕዝ ሥነጽሑፍ መሥራች ስለሆነ መጽሐፈ ቄርሎስ የግዕዝ ሥነጽሑፍ አካላት ናቸው። የግዕዝ
ነው። በቅዱስ ያሬድ ዘመን የግዕዝ ሥነጽሑፍ ሥነጽሑፍ አካላት ያደረጋቸው በግዕዝ ቋንቋ መገኘታቸው ብቻ
የዳበረ እንደነበረ የደረሰው ድጓ እየመሰከረ ሳለ፥ እንጂ፥ በደራሲዎቹ ዜግነት አይደለም። ሆኖም የግዕዝ ሥነጽሑፍ
እንዴት መሥራች እንለዋለን? ራሱም ቅዱስ ያሬድ ታሪክ በተነገረ ቁጥር ሲጠሩ ይኖራሉ። ሁለተኛው ክፍል በቀጥታ
እውቀቱን ያገኘው የግዕዝ ሥነጽሑፍ ሊቅና መምህር በግዕዝ የተደረሱትን ድርሰቶች ያጠቃልላል። የቅዱስ ያሬድ፥ የአባ
የነበረው የአባ ጌዴዎን ተማሪ ሆኖ አይደለምን? ጊዮርጊስ ዘጋስጫ፥ የርቱዐ ሃይማኖት፥ የአፄ ዘርአ ያዕቆብ፥ የአርከ
ቅዱስ ያሬድን የግዕዝ ሥነጽሑፍ መሥራች ሥሉስ፥ የአባ ባሕርይ ድርሰቶች ከዚህ ክፍል የሚገቡ ናቸው።
ከማድረግ ይልቅ “የግዕዝን ሥነጽሑፍ ያዳበረ ሊቅ” በድንጋይ ላይ ተጽፈው ከተገኙት ጽሑፎች በቀር የቅዱስ ያሬድን
ማለት አይሻልምን? የሚሉ ትምህርታዊ ጥያቄዎች ድርሰቶች የሚቀድም ኢትዮጵያዊ ድርሰት እስካሁን አልተገኘም።
ቢነሱ የተገባ ነው። ሆኖም፥ ሌሎች ደራስያን ካሉ፥
ቅዱስ ያሬድ ስሙ ሲጠራ የሚኖረው ለቤተ ክርስቲያን

ቅፅ-1፣ቁጥር 1 መስከረም 2010 ዓ.ም ገፅ 16


ደብረ-ያሬድ ታዛ





?
ባበረከተው ሥነጽሑፍና ማኅሌት ብቻ ሳይሆን እስካሁን ሥነ ጽሑፍነታቸው፣ በርናልድ ቭላ ያሳተማቸው የጾመ
የምናውቀው ታሪኩ እንደሚያሳየን ለቤተ ክርስቲያን ድጓና የምዕራፍ መጻሕፍት የሚደነቁ እንጂ፣ የሚነቀፉ
ልጆች የጽናት አርአያ በመሆን ጭምርም ነው። አይደሉም፡፡ ሌላ ምን አለን? አፄ ኃይለሥላሴ በሊቀ
ሥልጣናት ሀብተ ማርያም ወርቅነህ ሰብሳቢነት ያቋቋሙት
ኮሚቴ አንድ ሰው በእጁ የቀዳውን ድጓ፣ መጽሐፈ ድጓ፣
ያሬድ ማን ነው? ቅዱስ ያሬድ የደረሰው የሚል ርዕስ ሰጥቶ ፎቶግራፍ
አስነስቶ ያሳተመው መጽሐፍ ከደብዛዛነቱ የተነሳ ለጥናት
ቅዱስ ያሬድ ታላቅ የኢትዮጵያ የታሪክ ሰው
የተመቸ እንዳይደለ ያየው ሁሉ የሚመሰክረው ነው፡፡
ሆኖ ሳለ፣ ሊቃውንታችን ትምህርቱን ዓመታት እያሳለፉ፣
መምህራን እያፈራረቁ፣ በቅናት፣ በጥንቃቄና በኩራት የዘመኑ የምርምር ስልት ምርኮኛ መሆን የሚያስከትለው
ሲማሩ፣ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ሰውየው ማን እንደሆነ ሦስተኛው ግዴታ አንድን ነገር ያለ ማስረጃ እንደ ጽድቅ የመናገር
ለማወቅና እኛንም ለማሳወቅ የሚገባውን ምርምር ነፃነት ማጣት ነው፡፡
ሲያደርጉ አልታዩም፡፡ ስለዚህ ራሱን ቅዱስ ያሬድንና እሱ
ደረሳቸው የሚባሉትን በሚገባ ለይተን ሳናውቅ እንኖራለን፡፡
የቅዱስ ያሬድ ታሪክ፤
እውነተኛውን መልስ የማግኛው መንገድ የዘመኑ
የምርምር ስልት ስለሆነ፣ የስልቱ ምርኮኛ ያልሆነ ሰው ካለ ስለ ቅዱስ ያሬድ ታሪክ ያገኘሁትን ሁሉ ሳቀርብ፣
በዚያ መንገድ ስንጓዝ የማነሳቸው ጥያቄዎች ግር ሊሉት ድንገት የአንዱ ምንጭ ከሌላው ሳይስማማ ብታገኙት፣
ይችላሉ፡፡ እውነቱን ለማወቅ የሚደረገው የመጀመሪያው እውነተኛው ታሪክ የቱ እንደሆነ የሚታወቅበት ጊዜ
ውሳኔ ጥያቄ አለመፍራት ነው፡፡ ምርኮኛነት የሚያስከትለው እስከሚመጣበት ጊዜ ድረስ፣ ቀደም ብዬ ስለ ምርምርና
ሁለተኛው ነገር አንድን የምርምር ውጤት ለመቀበል ጥርጣሬ የተናገርኩትንና ‹‹መጻሕፍትሰ፡ ለእመ፡ ቦን፡
ወሳኙ ተመራማሪው ውጤቱን ያገኘው ትክክለኛውን አብትረ፡ እምተዛበጣ፡ በበይናቲሆን፡›› (መጻህፍት እኮ ዱላ
መንገድ ይዞ መሄዱ እንጂ፣ የተመራማሪው ማንነት ወይም ቢኖራቸው እርስ በራሳቸው በተደባደቡ ነበር) የሚሉትን
ዜግነት አለመሆኑን እንደ ሃይማኖት አጥብቆ መያዝ ነው፡ ሊቃውንት አፄ ዘርአ ያዕቆብ የተቆጣቸውን እያስታወስን
፡ ለምሳሌ፣ አውጉስ ዲልማን በላቲን የጻፈውን የግዕዝ መቀጠል ይኖርብናል፡፡ ቅዱስ ያሬድ የነበረበት ዘመን ሩቅ
መዝገበ ቃላት የራሳቸውን ዕውቀት አክለውበት በአማርኛ ስለሆነ፣ መሠረቱን ያለቀቁ ጥሩ ጥሩ ልብ ወለድ ታሪኮች
ያቀረቡልንን አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌን ኢትዮጵያዊ ሊሆኑም ይችላሉ፡፡ የሥነ ጽሑፍና የቋንቋ ተመራማሪ
ስለሆኑ አድንቆ፣ አውጉስ ዲልማንን ኢትዮጵያዊ እንዲህ ያሉ ድርሰቶች ሲያገኝ በታላቅ አክብሮት ያቅፋቸዋል
ስላልሆነ፣ ‹‹እሱ ማን ሆነና ነው እኛን ኢትዮጵያውያንን እንጂ፣ እውነተኛ ታሪክ ካልሆናችሁ ብሎ አይቀየማቸውም፡፡
ሊያስተምረን የሚቃጣው?›› ማለት አይቻልም፡፡ እንደ

ቅፅ-1፣ቁጥር 1 መስከረም 2010 ዓ.ም ገፅ 17


ታዛ ደብረ-ያሬድ
እንግዲህ ከመግቢያው ላይ ‹‹እስካሁን
የምናውቀው ታሪክ›› ባልኩበት ምክንያት
ልጀምር፡፡ የመንፈሳዊ አባቶቻችን ታሪክ
በጽሑፍ የቆየልን በገድል፣ በድርሳን፣
በስንክሳር ተዝካር ሲሆን የአንዳንዶቹ
ተአምራታቸውን ይጨምራል፡፡ ሁሉም
የገድል ክፍሎች ናቸው፡፡ በጠቅላላ አነጋገር
ገድል፣ ቀደም ብዬ እንደተናገርኩት፣ ጻድቁ
መምህር ሲያርፍ እንደ አባቱ አድርጎ
የሚያየውና የሚያደንቀው፣ መንፈስ
ቅዱስ ለሥራው የጠራው ደቀ መዝሙሩ
የሚጽፍለት የህይወት ታሪክ ነው፡፡ ድርሳን
ደግሞ በጻድቁ በዓል ዕለት ጻድቁን ለመዘከር
በገድሉ ላይ ተመስርቶ የሚሰጥ መንፈሳዊ
ትምህርት ነው፡፡ የኔም የዛሬ ጽሁፍ
መንፈሳዊ ብቻ ቢሆን ኖሮ፣ ቁጥሩ ከዚያው
ይሆን ነበር፡፡ የስንክሳሩ ተዝካር የተዘጋጀው
በመሠረቱ ድርሳን ከሌለ የበዓሉ ዕለት
እንደ ድርሳን ሆኖ እንዲያገለግል ነው፡፡
ገድልና የስንክሳር ተዝካር ነባር ሲሆኑ፣
ድርሳን አንድ የተጠራ ሰው በየትኛውም
በዓል ገድሉን መሠረት አድርጎ የሚሰጠው
ዕለታዊ ትምህርት ነው፡፡ እንደ ቅኔ ብዛት
አይኑረው እንጂ፣ እንደ ቅኔ ማለት
ነው፡፡ ግን ከጥቂቶቹ በቀር ድርሳኖች ሁሉ
ከትውልድ ወደ ትውልድ አይተላለፉም፡፡ አፄ ኃይለ ሥላሴ በሊቀ ሥልጣናት ሀብተ ለይቼ አልተቸውም፤ ሙሉውን ለማንበብ
ማርያም ወርቅነህ ሰብሳቢነት ያቋቋሙት ለሚፈልግ ባጅ በእንግሊዝኛ በ1928
የተላለፉትም ቢሆኑ አሁን እንደገድሉና ኮሚቴ “አምስቱ ፀዋትወ ዜማዎች” በሚል ዓመተ እግዚእ (ዓ.እ.) ባሳተመው ውስጥ
እንደስንክሳሩ ተዝካር ነባር ሆነዋል፡፡ ርዕስ በ1960 እና በ1965 ዓ.ም. ባሳተመው ይገኛል፡፡ በኢጣሊያዊው ጉይዲ የተጀመረው
ድርሳናት የገድልን ያህል የተሟሉ መጽሐፍ መግቢያ ላይ “(የያሬድ) የስንክሳሩ የግዕዙና የኢጣሊያንኛ
አለመሆናቸው በግምት የሚደረስበት የህይወት ታሪኩ መጽሐፍ ስለሚነግረን” ትርጉሙ ህትመት አሁን በፈረንሳዊው
ነው፣ ሆኖም የታሪክ ምንጮች ናቸው፡፡ የሚል አነጋገር ይገኛል፡፡ ኮሚቴው በኮሊን ከፈረንሳዊኛ ትርጉሙ ጋር በብዙ
ቅዱስ ያሬድም ድርሳን፣ አጭር (የሶስት ‹‹የህይወት ታሪኩ መጽሐፍ›› የሚለው ቅጽ ተፈጽሟል፡፡ የያሬድ የስንክሳሩ
ገጽ) ገድል፣ የሠራቸው ሶስት ተአምራት ገድሉን ይሁን አይሁን፣ መጽሐፉም የት ተዝካር ምንጮቹ ሁሉ በሚስማሙበት
እና የስንክሳር ተዝካር ተጽፎለታል፣ እንደሚገኝ አይናገርም፡፡ እንደምገምተው በግንቦት አሥራ አንድ ስር ይገኛል፡፡
ሁሉም እውጪ አገር ታትመዋል፡፡ ቅዱስ ያሬድን የሚያውቁት ከስንክሳሩ
ተዝካርና በየመጽሐፈ ድጓው ባዶ ገጽ ላይ ድርሳኑ፣ ቁንጽሉ ገድል፣ ሦስቱ ተአምራት
እንዳጋጣሚ ብዙ መጻሕፍት ለማገላበጥ ከተጻፈው እንጂ ከገድሉ አይመስልም፡፡ ባንድነት ተቀድተው ባሁኑ ጊዜ ከሦስት
ዕድል ባገኝም፣ ከአጭሩ ገድል ሌላ “ገድለ ቦታ እንደሚገኙ ይታወቃል፤ እነዚህም (1)
ያሬድ” የሚል የተሟላ መጽሐፍ እስካሁን ከ ጻ ድ ቃ ን ውስጥ ገድል ፓሪስ፣ በአስራ ዘጠነኛው ምዕተ ዓመት
አላየሁም፤ ያየም ሰው አላውቅም። ሊቀ ያልተጻፈላቸው አባቶችና እናቶች ተቀድቶ ቢብሎዎቴክ ናሲዮናል በሚባለው
ካህናት ጥዑመ ልሳን ካሣ፣ “ያሬድና ዜማው” አሉ፣ ያሬድ ከነሱ አንዱ ይሆን እንዴ? ቤተ መጻሕፍት ውስጥ d’Abbadie
በሚል ርዕስ በደረሱት መጽሐፍ ውስጥ አይደለም፣ ገድል ነበረው፡፡ ግን እንደ 227 በሚል ቁጥር የተቀመጠው፣ (2)
አንድ “የቅዱስ ያሬድ ታሪክና የዜማው አፄ ዘርአ ያዕቆብ ያለ ለእምነቱ ቀናተኛ ለንደን፣ በአስራ ሰባተኛው ምዕተ ዓመት
ምልክቶች” እና ሦስት “ገድለ ያሬድ” ባለሥልጣን ያጠፋው ይመስለኛል፡፡ ተቀድቶ በእንግሊዝ ቤተ መጻሕፍት
የሚባሉ የታተሙና ያልታተሙ መጻሕፍት እንዲያውም አፄ ዘርአ ያዕቆብ ሳይሆን (ብሪቲሽ ላይብረሪ) Or. 12860 በሚል
ይጠቅሳሉ፡፡ እነዚህን ምንጮች ስላላየኋቸው አይቀርም ገድሉን ጨቁኖ ሌላ ቁንጽል ገድል ቁጥር የተመዘገበው፣ (3) ደብረ ሐይቅ
አልተቻቸውም፡፡ ሆኖም ሊቀ ካህናት ጥዑመ የጻፈለት፡፡ ማስረጃዬን አቅርቤ እስክጨርስ እስጢፋኖስ (አምባሰል) በአስራ ስድስተኛው
ልሳን ከነዚህ ምንጮች የሚጠቅሷቸው ሁሉ እንደምትታገሱኝ አምናለሁ፡፡ የጥንቱ ምዕተ ዓመት የተቀዳውና EMML
እውጪ አገር ታትመዋል ካልኋቸውና ወደ ገድል ስላልተገኘ ዛሬ ዓለም እንደ ገድል 1844, 179b-189a በሚል መታወቂያ
ኋላ ከምጠቅሰው በብዙ የድጓ እጅ ጽሑፎች አድርጎ የተቀበለው ድርሳኑንና ከድርሳኑ ማይክሮፊልም የተነሳው ናቸው፡፡
ውስጥ ከሚገኘው አጭር ታሪክ ውጪ የበለጠ ትምህርት የሌለውን ቁንጽሉን
አይደሉም፡፡ ከነዚያ ውጪ የሆኑት ጥቂቶቹ ገድል ነው፡፡ ስለዚህ የጥንቱ ገድል በእጃችን ኮንቲ ሮሲኒ የሚባል ዕውቅ
ነገሮች ደግሞ ከገድሉ ሳይሆን ከሊቃውንቱ እስኪገባና ዕውቀታችንን እስኪያሟላልን ኢጣሊያዊ የፓሪሱን ቅጂ በአንድነት
ጠይቀው ያገኟቸው ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ድረስ ከድርሳኑ፣ ከስንክሳሩና ከሌላም ‹‹ድርሳን ወገድል ዘያሬድ›› በሚል ርዕስ
ምክንያቱም የታተመው ድርሳን/ገድል ያገኘነውን ታሪክ መወያያ እናደርጋለን፡፡ ለህትመት ያዘጋጀው መጀመሪያ ሊጵጺያ
‹‹መጽሐፈ ገድሉ እንዳለው›› የሚለውን ላይ በ19ዐ4 ዓ.እ.፣ እንደገና ደግሞ
ጥቅስ መልሰው ‹‹መጽሐፈ ገድሉ እንዳለው›› ሉቨን ላይ በ1961 ዓ.እ.፣ ታትሟል፡
ብለው ይቀዱታል እንጂ ጥቅሱ እውነትም አንደኛ ምንጭ፣ ‹‹ድርሳን ፡ ርዕሰ ደብር አብርሃምም በአንድ
‹‹መጽሐፈ ገድሉ ውስጥ ይኑር አይኑር ድርሰቱ ውስጥ ጠቅሶታል፡፡ የታተመው
ወገድል ዘያሬድ›› የፓሪሱ ቅጂ እንዳጋጣሚ ከሁሉም
እንዳረጋገጡ መጽሐፋቸው አያሳይም፡፡
ብልሹው ነው፡፡ ድርሳን ሆኖ ሳለ
ከላይ እንደገለጽኩት የቅዱስ ያሬድን ታሪክ ‹‹ድርሳን ወገድል ዘያሬድ›› የሚል ርዕስ
ሶስት ገድሎች የሚሏቸውንም የምናውቀው (1) ከድርሳኑና ‹‹ከገድሉ››፣
ሦስት ያደረጓቸው እርስ በራሳቸው (2) ከስንክሳሩ ተዝካርና (3) በየመጽሐፈ የሰጠውም ደራሲው ሳይሆን የኋላ ሰው
የሚያለያዩዋቸው ምን ምን እንደሆኑ ድጓው ሊቃውንቱ ከጻፏቸው ማስታወሻዎች ያከለው መሆን አለበት፡፡ ይኸንን ጥርጣሬ
አልጻፉም፡፡ እንደሚመስለኝ ያንድ ነው፡፡ የስንክሳሩ ተዝካር ከድርሳኑና የሚያጠናክሩ የማያወላውሉ ማስረጃዎች
ገድል ሦስት ቅጂዎች ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ከአጭሩ ገድል የተለየ ስላይደለ ከእነሱ በራሱ በድርሳኑ ውስጥ አሉ፡፡ ለምሳሌ
ገድል ሆኖ ‹‹በከመ፡ ይቤ፡ መጽሐፈ፡

ቅፅ-1፣ቁጥር 1 መስከረም 2010 ዓ.ም ገፅ 18


ደብረ-ያሬድ ታዛ
ገድሉ›› (መጽሐፈ ገድሉ እንዳለው) በዓላት ማህሌት ደረሰላቸው፡፡›› በመላእክት ጨምረውበታል፡፡ ስለዚህ ይኸ ‹‹ቃለ
እያለ ገድሉን ይጠቅሰዋል፡፡ ሁለተኛም በዲያቆናት ተልእኮ በየመአርጎቹ በገበዘ እግዚአብሔር በአስማት ይገኛል፣ ያሬድም
የታተመው ቅጂ እንጂ ሌሎቹ ሁለቱ አክሱም ቤተ ክርስቲያን (እያገለገለ) ኖረ፡፡ ቃለ እግዚአብሔር አልተማረም›› ብለው
ቅጂዎች እንዲህ ያለ ርዕስ የላቸውም፡፡ የጻፉት የሚታመን አይደለም፡፡ ታላቅ ካህን
ቅዱስ ያሬድ እንደዚህ ብዙ ዓመታት የሆነው መገረፍን በመሸከም፣ በትዕግስት፣
ከኢትዮጵያ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ከኖረ በኋላ፣ ሚስት አጭተውለት በሠርግ በምሕላ፣ በፀሎት ነው፡፡ ቅዱስ ያሬድ ወደ
የእጅ ጽሑፎች በህይወትና በማይክሮፊልም በሕግ አጋብተውት በአገልግሎቱ ቀጠለ፡፡ ሰማይ ተመስጦ የሱራፌልን ማህሌት
ቢወጡም ሌሎቹ መጻሕፍት ብዙ ቅጂ በዚያን ጊዜ ሚስቱን የሚደልላት አንድ ሰምቶ ተማረ፣ ከነሱም ጥሩ ማህሌት
ሲኖራቸው ድርሳኑ ያለው በነዚህ በሦስት ሰው ነበረ፡፡ ያሬድም ከሀዘንና ከልብ ትካዜ ወሰደና የተማረውን ማህሌት ተረድቶ ወደ
ቅጂዎች ብቻ ነው፡፡ የለንደኑን መጽሐፍ ላይ ወደቀ፡፡ አንድ ቀን ወስፈንጥሩን ደግኖ ምድር ወረደ፡፡ ገበዘ አክሱም ከምትባለው
ካታሎግ ያደረገው ፕሮፌሰር ስትሬልሲን በደፈጣ ሊገድለው ከመንገድ ሲጠብቀው ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በሦስት ሰዓት
እንደሚለው በለንደኑና ኮንቲ ሮሲኒ እግዚአብሔር የልቡን ዐውቆ ከኤዶም ገነት ላይ ገብቶ ከፍ ባለ ዜማ ‹‹ሃሌ ሉያ
ባሳተመው በፓሪሱ ቅጂ መካከል ብዙ በሥላሴ ምሳሌ ሦስት ወፎች ላከለት፡፡ ያሬድ ለአብ፣ ሃሌ ሉያ ለወልድ፣ ሃሌ ሉያ
ልዩነት አለ፡፡ የሚታመን አባባል ነው፡ ካለበት ቦታ አየር ላይ ቆመው፤ ከሦስቱ ለመንፈስ ቅዱስ፣፡፡ ቀዳሚሃ ለጽዮን ሰማየ
፡‹‹EMML›› በማይክሮፊልም ተነስተው ወፎች አንዲቷ በሰው ቋንቋ አነጋገረችው፤ ሳረረ፤ ወበዳግም አርአዮ ለሙሴ ዘከመ
ቅጂያቸው አዲስ አበባ በቤተ ክህነት፣ ‹‹ይኸን ሰው ለምን ትገድለዋለህ? ከትዳር ይገብር ግብራ ለደብተራ፡፡›› ብሎ ጮኸ፡
በቤተ መጻሕፍት ወመዘክር፣ በአዲስ ይልቅ ክህነት አትሻልምን? ጌታችን ሹሙ ፡ ይህችን ማህሌት ‹‹አርያም›› አላት፡፡
አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ እኔ በምሰራበት የቅዱስ በወንጌል፣ ‘ደግ ሊቅ ሆይ፤ ምን ጥሩ ነገር
ዮሐንስ ዩኒቨርሲቲም (ኮሌጅቪል - ብሠራ የዘለዓለም ሕይወት አገኛለሁ? ብሎ የጻድቁ ካሌብ ልጅ ንጉሥ ገብረ መስቀል
ሚኒሶታ፣ አሜሪካ) የተከማቹት መጻሕፍት በጠየቀው ጊዜ ጌታ ኢየሱስ ‘ትእዛዞቹን ይኸን ጣፋጭና ከፍ ያለ ዜማ የሰማ ጊዜ
የሚታወቁበት የEthiopian Manuscript የምትጠብቅ ከሆነ ነፍስ አትግደል’ ጫማውን አላደረገም ነበር፤ ንግሥቲቱም
Microfilm Library ምህጻረ ቃል ነው፡፡ ብሎታል፡፡ (ማቴ 19፣ 18፣ ማር 1ዐ፣ ገረዶቿን ትታ ያንን ጣፋጭ ድምጽ
ክምችቱ ትልቅ ሆኖ ሳለ የድርሰቱ ቅጂ 19፣ ሉቃ 18፣2ዐ) አንተስ (ይኸን ክፉ ለመስማት አብረው ሮጡ፡፡ ጳጳሱም፣
ይኸው EMML 1844, ff. 179b-189a ነገር) እንዴት በልብህ አሰብከው? ክህነት ካህናቱም፣ የቤተመንግሥቱ ታላላቅ
ውስጥ ያለው ብቻ ነው፡፡ ሆኖም በዕድሜ አትሻልምን? ከመንግሥትና በምድር ላይ ሰዎችም መጡ፡፡ በቃናው ጣዕም ውስጥ
ከሁሉም ቀደምትነት ያለው ስለሆነ ካለው ሁሉ አትበልጥምን? ያሬድ ሆይ አጥንት የሚያርስ፣ ልብ የሚያስደስት አዲስ
ዕድሜው ከሁሉም የበለጠ ያስከብረዋል፡፡ አንተ ብፁዕ ነህ፡፡ የተሸከመችህም ማህፀን ነገር ስላገኙበት የዱር አራዊት፣ ከብቶች፣
ብፅዕት ናት›› አለችው፡፡ ያሬድ ይኸን የሰማይ ወፎች ተሰብስበው ሲሰሙት ዋሉ።
ቅዱስ ያሬድ ትውልዱ አክሱም ሰምቶ ወደ ሰማይ ቀና ቢል ሦስቱን
ሆኖ፤ የኖረው በንጉሥ ገብረ መስቀል ወፎች አየ፡፡ ‹‹ከየት ነው የመጣችሁት? በስድስት ሰዓት ላይ በመሰንቆ ድምጽ
ዘመን ነው፡፡ የአክሱም ጽዮን አለቃና እንደ ሰው የምትናገሩት ከኤዶም ገነት በሶስት ሰዓት ጀምሮ እንዲሁ እስከ
መምህር አባ ጌዴዎን ዘመዱ ነበረ፡፡ ነው እንዴ?›› ብሎ ጠየቃቸው፡፡ አንዷ ዘጠኝ ሰዓት ድረስ ሲዘምር ዋለ። ካህን
የአባጌዴዎን ተማሪ ሆኖ ዳዊት ለመድገም ወፍ ‹‹ማህሌት ከሃያ አራቱ ካህናተ ያሬድ ሰይጣንን ተጋድሎ አሸነፈው፡፡ …
ብዙ ቢሞክር አልሆንልህ አለው፡፡ በዚህ ሰማይ እንደምትቀበል ልንነግርህ ከኤዶም አንድ ቀን ከኢትዮጵያ ንጉሥ ካሌብ ልጅ
ጊዜ አንድ ልጅ ትምህርት አልገባህ ሲለው ገነት ወደ አንተ ተልከናል›› አለችው፡፡ ከንጉሥ ገብረ መስቀል እግር ማሳረፊያ
አስተማሪዎቻችን የሚያደርጉትን ሁሉ በታች ሳለ ከማህሌቱ የዜማ ጣዕም የተነሳ
መምህሩ አደረገለት --- ‹‹ወዘበጦ ብዙኃ›› ይኸን ሲናገሩ ያሬድ ተመሰጠ፡፡ እነዚያም ሳያውቅ (ሹል) ብረት ያላት ዘንጉን
(ለምን አይገባህም ብሎ ብዙ ደበደበው፡፡) ወፎች ወደ ኤዶም ገነት ተመለሱ፤ ከዓይኑ በያሬድ እግር ሰፌዱ ላይ ተከላት፡፡ ካህኑ
ግርፋቱ ስለጎዳው መታገስ ተስኖት ተሰወሩ፡፡ ቅዱስ ያሬድ እዚያው እንደቆመ ያሬድ የማህሌቱ ቃል እስኪያልቅ ድረስ
ከወላጆቹ ቤት ወጥቶ ጠፋ፡፡ እብነ ለሀኪም ከኋላቸው ኢየሩሳሌም (ሰማያዊት) ገባ፡፡ ታገሠ፤ ምክንያቱም (ማህሌቱ) ከሰማይ
(ቀዳማዊ ምኒልክ) ወደ ተቀበረበት ዱር እዚያም የሰማይና የምድር ፈጣሪን ስብሐት እንጂ ከምድር አልነበረችም፡፡ መጽሐፈ
ሄዶ ከአንድ ዛፍ ስር ከፀሓይ ተጠልሎ ሲያቀርቡለት፣ ሲያመሰግኑት፣ ቅዱስ ገድሉ እንደሚለው የተማራት ከሃያ አራቱ
ቁጭ አለ፡፡ ከዚያ ቁጭ እንዳለ አንድ ትል ቅዱስ ሲሉት የዕንዚራ ድምፅ፣ የአርጋኖን ካህናተ ሰማይ ነው፡፡
ከዛፉ ላይ ሊወጣ ሲሞክር በተደጋጋሚ ድምፅ፣ የመሰንቆ ድምፅ ሰማ፡፡ ታላቁን
ግማሽ መንገድ እየሄደ ሲወድቅ ቆይቶ ንጉሥ በቅዱስ መንበሩ ዙሪያ ጧት ማታ ቅዱስ ያሬድ ከሃያ አራቱ ካህናተ ሰማይ
ከብዙ መከራ በኋላ ከጫፍ ደርሶ በስብሐታት፣ በማህሌት፣ በቅኔ፣ ከፍ የተቀበለውን ቃለ እግዚአብሔርና ዜማ
ሊበላት የፈለጋትን ቅጠል ሲበላ አየና ባለ ዜማ ስብሐት ያቀርቡለታል፡፡ ያሬድ ከአሰማና ለሌሎች ካስተማረ በኋላ ንጉሥ
‹‹እንዴት ግርፋትን አትታገስም፣ ይኸን ሲሰማ ካለበት ወደ ላይ ከፍ ሊልና ገብረ መስቀል እንዲፈቅድለት ለምኖ
ሕመምንስ ለምን አትሸከምም? ትዕግስት ወደነሱ ሊገባ ፈለገ፤ ግን አልተቻለውም፡ ሲፈቅድለት በምንኩስና አክሱምን ጥሎ
ብታበዛ እኮ እግዚአብሔር (ትምህርቱን) ፡ እነዚያ ወፎች መጡና ከእነሱ አንዷ መነነ፡፡
ይገልጽልህ ነበረ›› ሲል ራሱን ገሰጸው፡፡ ‹‹የሰማኸው አልገባህምን?›› አለችው፡፡
‹‹አልገባኝም›› አላት፡፡ ‹‹እንዲገባህ አድርጌ ከገበዘ አክሱም ቤተ ክርስቲያን ገብቶ
ይኸንን ብሎ አለቀሰና ወደ እኔ እነግርሃለሁ፤ የእግዚአብሔርን በዜማ፣ ‹‹ቅድስት
መምህሩ ወደ አባ ጌዴዎን ተመልሶ፣ አዲሱን ስሙን ጥራ፣ እሱም ኢየሱስ
‹‹አባ ሆይ ይቅር በለኝና እንደበፊቱ ክርስቶስ ነው፡፡ (የኢየሱስ ክርስቶስን ወብፅዕት፣ ስብሐት ወቡርክት፣ ክብር
አስተምረኝ፡፡›› አለው፡፡ መምህሩም ስም ሲጠራ) ከሃያ አራቱ ካህናተ ሰማይ በልዕልት፣ አንቀጸ ብርሃን›› እያለ
እንዳልክ ብሎ ተቀበለው፡፡ እግዚአብሔር በየዜማው ዓይነት ማህሌት ተቀብሎ፣ እስከመጨረሻው ዘምሮ ወጥቶ ሄደ፡፡
ልቡን አብርቶለት ያንኑ ዕለት ዳዊት ‹‹ጐሥዓ ልብየ ቃለ ሠናየ›› አለና በሦስት
ደገመ፤ ከመዝሙረ ዳዊት ጋር አብረው ሰዓት ላይ ወደቀድሞው ሁኔታ ተመለሰ፡፡ ካህናቱ እያዘኑና እያለቀሱ፣ እሱም
የሚቀዱትንም መኃልየ መኃልይንና ውዳሴ እያለቀሰ ሸኙት፡፡ ወደ ሰሜን ዱር፣ ወደ
ማርያምን፣ የሰማንያ አሐዱን መጻሕፍት አንዳንድ ሰዎች ‹‹ቃለ እግዚአብሔር ጸለምት ሄዶ እዚያ በብዙ ትጋት በጾምና
ትርጉም፣ ሌሎችንም ተምሮ ጨረሰ፡፡ ለያሬድ በአስማት ተገልጾለት ታላቅ ካህን በጸሎት በስብሐተ እግዚአብሔር ተጠምዶ፣
‹‹መጽሐፈ ገድሉ እንዳለው ማህሌቱን ሆነ፡፡ ቃለ እግዚአብሔር በአስማት የሚገኝ የእግዚአብሔርን ማህሌት ከሱራፌል
(ዜማውን ማለት ነው) የተቀበለው ከሃያ ለመሆኑ፣ እነሆ በያሬድ መጽሐፈ ገድል እንደተማረው ለጸለምትና ለሰሜን ሰዎች
አራቱ ካህናተ ሰማይ ነው፡፡ … በየወራቱ ውስጥ አስማት አለ›› ይላሉ፡፡ የያሬድ ቋንቋቸው ሌላ ለሆነው ለአገው ሰዎች
እንዲዘመርበት ዓመቱን በአራቱ ክፍለ መጽሐፈ ገድል ጥራት ያለው ነው፣ ሁሉ ሲያስተምር ኖረ፡፡ የአክሱም ጽዮን
ዓመት፣ ማለት በክረምት፣ በበጋ፣ በመጸው፣ ግን ሐሰተኞች ከሰማንያ አሐዱ የሕግ ካህናትም ወንድሙ ጭምር እዚያው
በፀደይ ከፍሎ በውስጣቸው ለሚከበሩ መጻሕፍት ውስጥ ያላገኙትን አስማት አለበት ድረስ መጥተው ጎብኝተውታል፡፡

ቅፅ-1፣ቁጥር 1 መስከረም 2010 ዓ.ም ገፅ 19


ታዛ ደብረ-ያሬድ

ቅዱስ ያሬድ ገድሉን ፈጽሞ በምድረ ሰሜን አረፈ፡፡ በክንፎቹ ሲያጨበጭብና ለመሰሎቹ (ለአዕዋፍ ዘር) ሲለምን
አስከሬኑ ለማንም ሳይታወቅና ሳይገለጥ እስካሁን (ድርሳኑ አይቶ፣ ከአየው ሁሉ በጣም አደነቀና፣ ‹‹ከክብሩ ዘንድ የጠራኝ
እስከተጻፈበት ዘመን) በምሥራቅ ሰሜን አለ፡፡›› እግዚአብሔር የተባረከ ይሁን›› አለ፡፡ ደግሞ ከመላእክት ሰፈር
ወሰደው፡፡ እዚያ ሁሉም በየቃላቸው ግማሾቹ ሆ ይላሉ፣
እዚህ ዋና ምንጭ ውስጥ ሁለት ነገሮች የሉም፤ (ሀ) ግማሾቹ ይዘምራሉ፣ ግማሾቹ እልልታ ያሰማሉ፣ ግማሾቹ
የእናት አባቱ ስም፣ (ለ) ድጓ የሚለው የድርሰቱ ስም፣ ይቀድሳሉ፣ ግማሾቹ ያጨበጭባሉ፣ ግማሾቹ ይጨፍራሉ፡፡
ምንጮቹ ሁሉ ለድርሰቱ የሚሰጡት ስም የተለያየ ነው፡፡
ምስጋና የሚገባው መድኃኒታችን ኢየሱስ ይኸንን ሁሉ ባሳየው
ጊዜ የማስተዋል መንፈስ ከፈጣሪ ዘንድ ተልኮለት ወደ አርያም
ሁለተኛ ምንጭ፣ (ወደ ላይኛው ሰማይ) መለሰው፡፡ ከዚያ በኋላ በሰማያውያን
ካህናት ዘንድ እንዳየው፣ ‹‹ሃሌ ሉያ ለአብ፣ ሃሌ ሉያ ለወልድ፣
በዚህ ርዕስ ስር የማቀርበው ታሪክ በብዙ የEMML ክምችት ሃሌ ሉያ ለመንፈስ ቅዱስ፡፡ ቀዳሚሃ ለጽዮን ሰማየ ሣረረ፡
ውስጥ በግዕዝ ተቀድቶ ይገኛል፡፡ ከላይ ለጠቀስኩት “አምስቱ ፡ ወዘተ.›› በማለት ጀመረ፡፡ ስለዚህ ‹‹አርያም›› አሉት፡፡
ጸዋትወ ዜማዎች” መግቢያ የጻፉለት ሰዎች፣ ‹‹(የያሬድ) ከዚያ ‹‹ዋይ ዜማ ዘሰማዕኩ በሰማይ›› (አለ)፡፡ ከዚያ በኋላ
የህይወት ታሪኩ መጽሐፍ ስለሚነግረን›› የሚሉት ይኸንን ከምድር ወረደና ከምኩራብ ቆሞ ‹‹ቅድስት ወብፅዕት ወዘተ.››
በብዛት የሚገኘውን ቅጂ አግኝተው ለመሆኑ ጥቅሳቸው አለ፡፡ ከዚያ በጻድቁ ንጉሥ በገብረ መስቀል ዘመን ማለት
ያሳያል፡፡ አስፈላጊ ሆኖ ስላላገኘሁት ነው እንጂ፣ ቢፈለግ በነገሠ በአሥራ አራት ዓመት ወደ ከተማ ሄዶ ብዙዎቹን
በአውሮፓ ቤተ መጻሕፍት ውስጥም ይገኝ ይመስለኛል፡፡ ድርሰቶች በቅደም ተከተል ሁሉንም ተናገረ፡፡ የብሉይና
የሐዲስ መጻሕፍትን ሁሉ ቃኛቸው፡፡ የትግሬ ሊቃውንት
ላሁኑ ግን በEMML, 4540,ff.1a-2b ያለውን ታሪክ ስህተት ሳይበት
ሳዊራ፣ መንክራ፣ እስክንድር፣ በስድር (ድርሰቱን) ተቀበሉት፡፡
የተቻለውን ያህል ከሌሎቹ የEMML ምንጮች ጋር እያስተያየሁና
በአራት ዓመት ከአምስት ወር ብዙ ድርሰቶች ደረሰ፡፡ ከዚያ
እያረምኩ ወደ አማርኛ ተርጉሜ ሳቀርበው እንዲህ ይላል፡፡
በጽሙና (በዝምታ) አሥራ ሦስት ዓመት ከሰባት ወር ኖሮ፣
‹‹በስመ፡ አብ፡ ወወልድ፡ ወመንፈስ፡ ቅዱስ፤ አሐዱ አምላክ፡፡ ግንቦት አሥራ አንድ ቀን በሠላሳ ዘጠኝ ዓመቱ በሰላም
ይኸ የቅዱስ ያሬድ ታሪክ በእግዚአብሔር አብ ፈቃድ፣ በወልድ አረፈ፡፡ በእግዚአብሔር ውዴታ በአባቶቹ መቃብር ተቀበረ፡፡
ውዴታ፣ በመንፈስ ቅዱስ ሥራ የሆነ ነው፡፡ ይህ ዝናው በዓለም (እግዚአብሔር) ምስጋና ለዘለዓለም ይድረሰው አሜን፡፡››
ሁሉ የተሰማ ቅዱስ ያሬድ አባቱ ከቤተ መንግሥት እናቱ
ከቤተ ክህነት ነበሩ፡፡ በመጀመሪያው ወር በአምስተኛው ቀን ሦስተኛ ምንጭ፣
ተወለደ፡፡ በጥሩ አስተዳደግ አሳደጉት፡፡ የአባቱ ስም ገማልኤል፣
የናቱ ስም ታውልያ ነበር፡፡ ሁለቱም የተመረጡና ቅኖች ይኸ ምንጭ ከላይ ያነሳሁት ፕሮፌሰር ደላማተር
ነበሩ፡፡ በተወለደ በአሥራ ሁለት ዓመቱ የቤተ ክርስቲያን ፎቶግራፍ ካነሳቸው እጅ ጽሑፎች አንዱ ሲሆን የእጅ ጽሑፉ
መጻሕፍትን እንዲያስተምረው ስሙ ይስሐቅ ከሚባል ከአንድ ባለቤት ኤሊዛ ትባላለች፡፡ የኤሊዛንና የሌሎችን ከሁለት መቶ
ብልህ፣ ደግ፣ እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰው ዘንድ ወሰዱት፡፡ የሚበልጡ እጅ ጽሕፈቶችና ክታቦች ፎቶግራፍ አንስቶ
ሰባት ዓመት ሲጠብቅ ቆዬ፡፡ ከዚያ ከትግሬ አኩስም በባባ ልኮልኛል። ከኢትዮጵያ ‹‹ከተወሰዱት እጅ ጽሕፈቶች ውስጥ
ቀበሌ ስሙ ዳጊ በሚባል ቦታ ሲማር ሰባት ዓመት ቆዬ፡፡ አንዳንዶቹ ኢትዮጵያ ውስጥ ሌላ ቅጂ እንዳላቸው እንኳን
ከዚያ ቆሞ ሲፀልይ እንቅልፍ ወሰደው፡፡ ከሰማይ ሦስት ወፎች አላውቅም›› ማለቴ ይታወሳል፡፡ ይህ በEliza Codex 8 ውስጥ
መጥተው ሊቀ ካህናት ኢየሱስ ክርስቶስ ወዳለበት አመጠቁት፡፡ አገኘሁት የምለው የያሬድ ታሪክ አንዱ ሊሆን ይችላል፡፡
ሦስት ጊዜ ሰገደለት፡፡ ከዚያ የምህረት መልአክ ሰዳክያል ወስዶ በEMML እጅ ጽሑፎች ውስጥ አላየሁትም፡፡ ያሬድን የሚያህል
መንበሮችን፣ ክብሮችንና ክፍሎቹን (ኤፌ1፣21፣3፣1ዐ፣6፣12፣ ታላቅ የታሪክ ሰው ታሪክ በሺ የሚቆጠሩት የእጅ ጽሑፎች
ቈላ 1፣16) አሳየው፡፡ ሰዳክያል ከዚያ ወስዶ አራቱ እንስሳት ክምችት ውስጥ ካልተገኘ ከሌላ ቦታ መገኘቱ ያጠራጥራል፡፡
ካሉበት አደረሰው፡፡ የሰው መልክ ያለው (ገጸ ብእሲ) ቆሞ ታሪኩ የተጻፈው በአማርኛ ነው፡፡ ግን ዓረፍተ ነገሮቹን ረጋ
ሲያመሰግንና ለመሰሎቹ (ለሰው ልጆች) ሲለምን አይቶ ተገረመ፣ ብሎ ለመረመራቸው ጥንት የተደረሰው በግዕዝ ሆኖ አንድ
አደነቀም፡፡ ደግሞ የበሬ መልክ ያለው (ገጸ ላህም) ሲያገሳና ሰው ወደ አማርኛ ቃል በቃል የተረጐመው ይመስላል፡፡ እነሆ፤
ሲናገር ለመሰሎቹ (ለከብት ዘር) ሲለምን፣ ራሱን ሲያወዛውዝ
አይቶ ተገረመ፣ አደነቀም፡፡ ደግሞ የአንበሳ መልክ ያለው “(ያሬድ) አባቱ ገማልያል ይባላል፣ ወላጆቹ በትውልድ
(ገጸ አንበሳ) ከማሰሪያው እንደተፈታ እምቦሳ ጥጃ ሲቦርቅና ከአሮንና ከሌዊ ቤት ነበሩ፡፡ እናቱ ታውልያ የኢትዮጵያ
ለመሰሎቹ (ለአራዊት ዘር) ሲለምን አይቶ ተገረመ፣ አደነቀም፡ ጳጰስ የነበረው የአባ ሰላማ እኅት ናት፡፡ ከመወለዱ በፊት
፡ ደግሞ የንስር መልክ ያለው (ገጸ ንስር) በእግሮቹ ሲረግጥ የኢትዮጵያ መብራት እንደሚሆን ቅዱስ ሚካኤል ለአባቱና
ለእናቱ በህልማቸው ትንቢት ተናግሮላቸው ነበር፡፡ …

ያሬድ በተወለደ በሰባት ዓመቱ ለጌታ አደረ፡፡ ያጼ ገብረ


መስቀል ቢትወደድ ዥን አስራሪ ዜና ገብርኤል ይሏል
(ይባላል) ያደረለት ጌታ፡፡ ‹‹ጋሻ ቢያሲዙኅ አትችል፣ ጦር
ሾተል ቢያሸክሙህ ላትችል፣ ምን ትሆነኝ?›› ብሎ መለሰው፡
፡ ከዚያ ወዲያ እማራለሁ መጽሐፍ ብሎ እቤተ እግዚአብሔር
ገባ፡፡ ዓመት ሙሉ መምህሩ ሳያውቀው ተቀመጠ፡፡ ከዚያ
ወዲያ አወቁትና ‹‹ምነው ምን ትሻለህ?›› ብለው ጠየቁት፡፡
እርሱም ሲል ‹‹እማራለሁ መጽሐፍ ብየ መጥቻለሁ፣ አቤቱ››
ብሎ መለሰለዎ፡፡ ‹‹ንገሩት›› አሉና አዘዙ፡፡ ሀ ሁ ሂ ማለት
አውኮት አምስት ዓመት ተቀመጠ፡፡ ‹‹ፊደሉስ ታልገባኝ›› ብሎ
ሲሄድ እዛፍ ስር አረፈ፡፡ እጥላ ተቀምጦ ሳለ ትል የዚያን
ዛፍ ቅጸል እበላለሁ እያለ ሲወጣ ሲወርድ በሰባተኛው ወጥቶ
በላው፡፡ ያን አየና ተመልሶ ሰባት ዓመት ልምላ ብሎ እዚያው
ገባ (ተመለሰ)፡፡ ከዚያ ወዲያ አልገባህ ቢለው ተነስቶ ሲሄድ
ቀድሞ ያደረለት ጌታ እመንገድ አገኜው፡፡ ‹‹እኔ ቤት ቀድሞ
የነበርህ አይደለህም?›› ብሎ ጠየቀው፡፡ ‹‹አወን ነኝ እንጅ››
ብሎ መለሰለትና ሁለቱም ዝናም መጣ ‹‹አጫውተኝ›› አለውና

ቅፅ-1፣ቁጥር 1 መስከረም 2010 ዓ.ም ገፅ 20


ደብረ-ያሬድ ታዛ

ቀሲስ ያሬድን ብቸኛ የግዕዝ ሥነ ጽሑፍ መሥራች አድርጎ ለማየት በቂ ምክንያት


አለን። እንዲያውም የግዕዝ ሥነ ጽሑፍ መሥራች ከማለት ይልቅ የኢትዮጵያ
ሥነ ጽሑፍ መሥራች ልንለው ይገባል።

ሁለቱ እጥላ እሾላ ስር አረፉ፡፡ ጭፍራው እዋሻ ገባ፡፡ ሁለቱ በዕዝል፣ በግዕዝና በአራራይ ሁሉንም አዚሟቸዋል፡፡ የርሱም
ሲጫወቱ እንቅልፍ መጣባቼውና ተኙ፡፡ ሁለቱም እልም አዩ፣ ድርሰት ብዙ ነው፡፡ ከሰማንያ አሐዱ መጻሕፍት ቢያተርፍ
መኰንኑ ለያሬድ ሲያይለት እኮረብታ ላይ ሆኖ (ፋና) ሲያበራ እንጂ አይጐድልም፡፡ ለኛም የመጣልን ያንዱ ዘመን ብቻ ነው፡፡
አየለት፡፡ ያሬድም ለመኮንኑ ሲያይለት ጥቁርና ነጭ ከቦት አየ፤ የሦስቱ ዘመናት ባህረ ተከዚ ተሰውሯል ይባላል፡፡ ሦስት
ከነጩም ጥቁሩ በልጦ አየ፡፡ ሁለቱም አንድ ጊዜ ነቁና ሁለቱም ዓመት ከሦስት ወር እየዞረ ጮኸ፡፡ አራት ዓመት ተቀምጦ
ህልማቼውን ተነጋገሩ፡፡ መኰንኑ ለያሬድ ሲለው ‹‹የጀመርከው አስተማረ ይባላል፡፡ ባፄ ገብረ መስቀል ዘመን ነው መጮኹም
ነገር ይቀናሀል፤ ታስተምራለህ፤ ፋና ማብራት ማስተማር ማስተማሩም፡፡ የያሬድን ቃል የተማረ ሰው ፍሬው አራት ሺህ
ነው፤ እኮረብታም ላይ መሆንህ አኵስም ጽዮን ናት፡፡ እኔ ነው፤ ኩነኔም የለበትም፡፡ የሱም መሰወር የግንቦት ሐና ለት
ነጭና ጥቁር ከቦ ከነጩ ጥቁሩ በልጦ ያልኸኝ ምንድነው?›› ነው፡፡ ሁሉ እንዳይጣፍ ይበዛል ብለን ነው ይህ ይበቃል ብለን፡፡”
ብሎ ጠየቀው፤ ያሬድም ለመኰንኑ ሲል ‹‹ዘመነዎ ቀርቧል
ለመዊት›› ብሎ ነገረውና ‹‹እንሂድ እቤቴ›› ብሎ ይዞት ሄደ፡፡ እነዚህ ሁለቱ ምንጮች የያሬድ አባት ገማልያል/
አንድ ልጅ ነበረችው ‹‹ንሳ ቤቴን ልጄን ያውልህ›› አለና መነነ፡፡ ገማልኤል፣ እናቱ ታውልያ እንደሆነ በመስማማት ይናገራሉ፡፡
ሁለቱም ምንጮች ልክ ሊሆኑም ላይሆኑም ይችላሉ፤ ከጥንቱ
ያሬድም ቤቱን ሲጠብቅ አሥር ዓመት ተቀመጠ፡፡ ድንግል ሁኖ፡፡ ገድል የወሰዱትም ነገር ይኖራቸዋል፤ ግን በየትኛውም እጅ
በመቶ ሃምሳ አስጠምዶ ሲያሳርስ ዘር ቢያልቅበት አስመጣለሁ ጽሑፍ ውስጥ የአባቱ ስም ይስሐቅ፣ የናቱ ስም ክርስቲና ነበር
ብሎ እቤት ወጣ፡፡ በር ተዘግቶ አዳራሽ ተከፍቶ አገኜ፡፡ ጠጅ የሚል አላየሁም፡፡ ምንጮቹ ይስሐቅን የመምህሩ ስም ነው
ተዘንብሎ ሥጋ ሲዘለዘል አየ፡፡ ‹‹እቴ ላንች ብዬም አይደል የሚያደርጉት፡፡ ይስሐቅን የአባቱ ስም ማድረግን ያስፋፋው ከላይ
መቀመጤ፤ የወዳጅን እሬሳ ሳያገላብጡ አይቀብሩምና ተዛሬ ነግ የጠቀስኩት መጽሐፈ ድጓ፣ ቅዱስ ያሬድ የደረሰው የተባለው
ቢመጡ ብዬ መጠበቄ ስለዚህ ነበር›› (አላት)፡፡ እርሷም ስትል መጽሐፍ ያለው የያሬድ ታሪክ ይመስለኛል፡፡ ታውልያን
‹‹ጠባቂ ቢያጡ ጋሻ ጦር ሰጡ›› ብላ መለሰችለት፡፡ እርሱም አንዳንድ የEMML ምንጮች ሊቀ መዘምራን ሞገስ እንደጻፈውም
‹‹እንዳሻሽ›› ብሎ ተዋትና መንኖ ሲሄድ እመንገድ ዝናም ታውክልያ ይሏታል፡፡ ስንክሳሩ ውስጥ ቅዱስ ያሬድ በሚዘከርበት
መጣበት፡፡ እዋሻ ገብቶ ተጠለለ፣ እንቅልፍ መጣበት፡፡ በህልሙ ዕለት (ግንቦት አሥራ አንድ ቀን) ታውክልያ የምትባል
መልአከ እግዚአብሔር መጥቶ ‹‹ሰማንያ አሐዱ መጻሕፍት ጻድቅት ትዘከራለች፤ አጋጣሚ ሊሆንም ላይሆንም ይችላል፡፡
እነግርሃለሁ›› አለው፡፡ ተነስቶ አባ ዘኪዎስ የሚባሉ ባህታዊ
ነበሩና እርስዎ ዘንድ ሄደና ‹‹ዛሬ በህልሜ ብዙ መጻሕፍት (ይቀጥላል)...
እነግርኃለሁ ብሎ አለኝ፡፡ ከቤተ እግዚአብሔር ገብቼ ሰባት ዓመት
ሙሉ ፊደል ተስኖኝ ወጣሁ፤ ምን ላድርግ?››አለዎ፡፡ ‹‹መልካም
አሳይቶሃል፤ ቀኖና ያዝ፣ መልካም አሳይቶሃል ልጄ›› አሉት፡፡
ከዚያ ወዲያ ሂዶ ተከዜ ተሚሉ ባህር ገብቶ ሰባት ሱባዔ ፀለየ፡፡
መላእክት እየመጡ ‹‹ምን ትሻለህ?›› አሉት፡፡ እርሱም ሲል
‹‹ሀብቴ ቢሰወረኝ ፈጣሬየን እለምናለሁ›› አላቸው፡፡ በአንድ
ሱባዔ ጠየቁት፣ በሁለተኛው፣ በሦስተኛውም ሱባዔ እየመጡ
ይጐበኙት ነበር መላእክት፡፡ ቅዱስ ሚካኤል ጠባቂው ነበር፤
ቅዱስ ገብርኤልም አልተለየውም፣ ከነሠራዊታቸው ሁል ጊዜ
የስባሔያቼውን ድምጽ እየሰማ ያመሰግን ነበር ሥሉስ ቅዱስን
ሰባት ሰማያት ተገለፀለትና እነጽሮተ ሰማይ ድረስ፡፡ በሰባተኛው
ሱባዔ ቅዱስ ሚካኤል ታቅፎ አወጣና እሥላሴ ፊት አደረሰው፡፡
‹‹ወነፍሐ መንፈሰ፡ ህይወት፡ ውስተ፡ ገጹ፡ ለአዳም፡›› እንዳለ
በኦሪት፡፡ ሥሉስ ቅዱስ እፍ አሉት ይሏል (ይባላል)፡፡ ያ መንፈስ
ቅዱስ አሰከረውና መጮኸ ዠመረ በዜማ፡፡ ‹‹በማን?›› ቢሉ
በዕዝል ይሏል (ይባላል)፡፡ ‹‹ምራ ብሎ ጀመረ›› ቢሉ ‹‹ቅድስት፡
ወብፅዕት›› ብሎ ጀመረ፤ ድርሰቱም የሱ ነው ይሏል (ይባላል)፡፡

ማህሌት ሦስት ነው ሦስቱም በዕዝል ይጀምራል፡፡ ሦስቱ


እነማናቸው ቢሉ ስብሐተ ነግህ፣ ክስተት፣ መወድስ፣ ይሏል
(ይባላል)፡፡ ማህሌት እሊህ ናቸው፡፡ የቀረውሳ ቢሉ መስተዛውዓ
ካህናት (የካህናት መጫወቻ ናቸው) ይሏል (ይባላል)፡፡ አራራይ
ዜማ አስከትሏል፡፡ አርያምን አስከትሏል፡፡ ቀዳሚ ብሎ
አራተኛው እሦስተኛው ሰማይ ሆኖ ጮኸው ይሏል (ይባላል)፡፡
ጠፈር ይባላል፤ ማህደረ መላእክት ነው፡፡ ሠራዊተ ሚካኤል
ወገብርኤል ተከትለው ሲሸኙት ይሏል (ይባላል) “እስከ፡ ይበጽህ፡
ደብረ፡ አኵስም፡ ወሶበ፡ አብፅሕዎ፡ ወተመይጡ፡ መንገለ፡
ሰማይ፡ ሀገሮሙ፡ እንዘ፡ ይብሉ፡ እግዚአብሔር፤ ይዕቀብከ፤
ወእግዚአብሔር፤ ይክድንከ፡ በየማነ፤ እዴሁ፡፡ ወዘንተ፡
ብሂሎሙ፤ ዓርጉ፡ ውስተ፤ ሰማይ” እንዳለ፡፡ ያሬድም እደጀ
ብርሃን ቁሞ ‹‹ቀዳሚ(ሃ) ለጽዮን ሰማየ ሣረረ›› ብሎ ጮኸ፡፡
እቤተ መቅደስ ገብቶ ‹‹ወይ፤ ዜማ፡ ዘሰማዕኩ፤ በሰማይ›› ብሎ
ጮኸ፡፡ ከዚያ ወዲያ ሰማንያ አሐዱ መጻሕፍትን አዜማቸው፡፡
41 ብሉያት፣ 35 ሐዲሳት አራት ከፍሎ አዚሟቸዋል፤

ቅፅ-1፣ቁጥር 1 መስከረም 2010 ዓ.ም ገፅ 21


ታዛ

የመንግስቱ ለማ ኑዛዜ   
ዕውቀትና ልምድ - ይህ የፀሐፌ ተውኔትና ባለቅኔ

ለተተኪው ትውልድ-1 መንግስቱ ለማ ስራ ለመጀመሪያ


ጊዜ ለንባብ የበቃው በ1980 ዓ.ም.
በየካቲት መፅሔት ነበር። እነሆ
ከ30 ዓመታት በኋላ ከቤተሰቦቻቸው
ጋር ተመካክረን ዳግም ለህትመት
እንዲበቃ የፈለግንበት ምክንያት
መልዕክታቸው ለአዲሱ ትውልድ
እንዲደርስ በማሰብ ነው። ይህንን
ጉዳይ ያጫወትነው አንጋፋ የቴያትር
ባለሙያና የባለቅኔው ወዳጅ አቶ
ተስፋዬ ገሠሠ ሃሳባችንን ከደገፈ
በኋላ “በነገራችን ላይ እሱ ፅሁፍ
ኑዛዜው እንደሆነ ታውቃላችሁ?”
ከመንግስቱ ለማ አለን። እውነትም ሃብት ንብረት
ከዕለታት አንድ ቀን በአዲስ አበባ ከተማ ከገዳም ሠፈር በስተማዶ
ሳይሆን የእውቀት ሃብት
ጠጉሩ በሽበት ጥጥ የመሰለ፣ መላጣው የሚያንጸባርቅ አንጋፋ የሚወረስበት ኑዛዜ! አንጋፋው ዘንድ
ደራሲ ሪዙን አንዠርጐ፣ መነጽሩን ከጐራዳ አፍንጫው ሰክቶ፣
ምክር ፈልጎ የሄደው ወጣትም
በአሮጌ ሶፋ ላይ ተኮፍሶ የግእዝ ቅኔ መጽሐፍ ይመለከት ነበር፡፡
ከፊቱ አነስተኛ ጠረጴዛ አለች፡፡ እኮ “ምንድነው ችግሩ? በርጋታ
ንገረኝ፤ በጥሞና አዳምጬ በተቻለኝ
ሰዓቱ ረፋድ ቢሆንም ወራቱ ክረምት ስለሆነ በአሮጌ ሱፍ ኮትና
ሱሪ ላይ በደረበው ወፍራም ጋቢ ተጀቡኖ አንጋፋው በጭቃ እረዳሃለሁ። የገንዘብ ችግር እንደሆነ
ቤት ሳሎኑ ውስጥ ተዝናንቶ ተቀምጧል፡፡ ሳሎኒቱ በፈረንጅ ግን ራሴም ያለሁበት ስለሆነ ወደ
ቋንቋ በተጻፉ መጻሕፍት ታጭቃለች፡፡
ሌላ ሰው ብትሄድ ይሻላል›› የሚል
የውጭው ቆርቆሮ በር ተደጋግሞ ይቆረቆራል፡፡ አንጋፋው መልስ ነው የሚያገኘው።
ደራሲ ግን በግእዝ ቅኔ ተመስጦ ኳኳታውን ልብም አላለው፡፡

ገረዲቱ ትገባና እንግዳ መምጣቱን ታስታውቃለች፡፡ አያይዛም


እንግዳው ከተለመዱት ጠጉረ ሸበቶና ራሰ መላጣ ወዳጆቹ ለየት ‹‹አልችልም ጋሼ፣ ተነሥተው መጽሐፍ እያነበቡ ናቸው
ያለ አፍለኛ ወጣት መሆኑን ታክላለች፡፡ ራሷም ወጣት ነች፣ ብዬዋለሁ፡፡ መቼም ዋሺ አትሉኝም ዛሬ በሰንበት ያውም
መልከ ቀናና ባላገር አደግ ግን ቀልጣፋ፡፡ በገብሬል ምድር፡፡››

‹‹የሉም በይ - ወጥተዋል በይ›› ይላል አንጋፋው፡፡ ‹‹ዛሬ አንጋፋው ለመቆጣት ይከጅላል፤ ግን አይቆጣም፤ ዕድሜ
እንግዳ አልቀበልም፤ ሥራ ይዣለሁ፡፡›› አቀዝቅዞ ፈላስፋ አድርጐት፡፡ ቢሆንም የተለመደውን ምክርና
ተግሳጹን ለታማኝ ገረዱ ከመለገሥ አልተቆጠበም፡፡
‹‹የለም ጋሼ፣ ይህን አስቀድመው ከጧቱ ስላልነገሩኝ አሉ
ብዬዋለሁ›› ትላለች፡፡ ‹‹ስንትዬ ልንገርሽ ወርቂቱ? ከገረድ ሥራ አንዱና ዋነኛው
ውሸት ነው ብዬሻለሁ፡፡ ጌቶቹ በቤት እያሉ “የለሁም በይ” ካሉ፡
‹‹እንግዲያማ ተኝተዋል ገና አልተነሱም በይዋ!›› ለእንግዳው “የሉም” ብለሽ መንገር ነው፤ ሳይተኙ “እንቅልፍ

ቅፅ-1፣ቁጥር 1 መስከረም 2010 ዓ.ም ገፅ 22


ታዛ

ቭላድሚር ማያኮቭስኪ ቤርቶልት ብሬሽት ሎፔ ደ ቬጋ

ወስዶኛል” ካሉም ይህንኑ ማሳወቅ ነው፡፡›› ‹‹ዕውነትም አሁን ሳስበው ፍቅር ነው፤ ፍቅር መሆን አለበት!
ፍቅር ባይሆን ኖሮ እንዲህ ግራ አያጋባኝም ነበር…›› በሐሳብ
ልትናገር ስትል እጁን አነሳና አገዳት፡፡ ‹‹ውሸት ኃጢአት ነው ተመስጦ ጥቂት አሰላሰለ፡፡ ‹‹አዎ ፍቅር ነው፤ የግጥም፣ የሥነ
ልትይኝ አይደለም እንደልማድሽ? መሆኑን አላጣሁትም፡፡ ግጥም፣ የቅኔ ፍቅር፡፡ አዎንና! ሕይወቴ ቅኔ ነው!››
በኃጢአቱ ግን ኃላፊው እኔ ጌቶቹ እንጂ አንቺ ገረዲቱ
አይደለሽም፡፡›› የአርእስተ ችግሩ በድንገት መለወጥ በረጅም ዕድሜው ብዙ
ነገር ያየና የሰማ ነውና አንጋፋውን አልገረመውም፡፡ ሆኖም
የጣደችው ቡና እንዳይገነፍልባት ወደ ማድቤቷ ለመመለስ ሁኔታውን ለማጣራት ፈልጓል፡፡
ቸኩላለች፡፡
‹‹ የቅኔ ፍቅር ስትል፣ የማንበብ ነው የመጻፍ?››
‹‹ታዲያ አሁን ልጁን ምን ልበለው?››
‹‹የመጻፍ ነው እንጂ! አዎ፣ ጌታዬ የያዘኝ የደራሲነት ፍቅር
‹‹አሉ ካልሽው ወዲያ ምን ይደረጋል? አስገቢው›› ነው፤ የቅኔ ደራሲነት፡፡ እርስዎ ዘንድ የመጣሁትም በዚሁ
ምክንያት ነው፡፡ የታወቁ አንጋፋ ደራሲ እንደመሆንዎ መጠን፣
ገረድ ትወጣለች፡፡ ወዲያው ደፈር ብሎ በልበ ሙሉነት ወጣቱ
እኔም በበኩሌ ባለ ተስፋ ወጣት ደራሲ እንደ መሆኔ ከእርስዎ
ይገባል፡፡ በአለባበሱ ሽትር ነው፤ ያበጠ ዘመናዊ የሸራ ቦርሳ
አንዳንድ ጠቃሚ ነገር ለመቅሰም እገደዳለሁ፡፡››
አንግቷል፡፡
‹‹የግጥም ነው የቅኔ ደራሲ ነኝ የምትለኝ?›› አለ አንጋፋ፡፡
‹‹ያለ ቀጠሮ በመምጣቴ ጌታዬን ይቅርታ እጠይቃለሁ፡፡ ጉዳዩ
አላስቆም፣ አላስቀምጥ፣ አላስተኛ ስላለኝ ነው በሰንበት ምድር ‹‹አንዳንድ ሰዎች ቅኔን ግጥም ይሉታል፡፡ እኔ ግን ሁሉንም
እርስዎን ለማስቸገር መድፈሬ፡፡ በከፍተኛ ችግር ላይ ነው ቅኔ ነው የምለው፡፡ ይገርምዎታል፤ ገና በሃያ ሦስት ዓመት
የምገኘው፡፡›› እድሜዬ ይህን ሁሉ ግጥም ጽፌአለሁ፡፡ ጽሑፉን በዚህ ቦርሳ
አጭቄ አምጥቼዋለሁ፡፡›› ቦርሳውን ከትከሻው አውርዶ እጭኑ
‹‹ዐረፍ በል - ወንበሩን ሳብ አርገው፤ ምንድነው ችግሩ?
ላይ አደላድሎ ያስቀምጠዋል::
በርጋታ ንገረኝ፤ በጥሞና አዳምጬ በተቻለኝ እረዳሃለሁ፡፡
የገንዘብ ችግር እንደሆነ ግን ራሴም ያለሁበት ስለሆነ ወደ ሌላ አንጋፋው እንደ መደንገጥ ብሎ መነጽሩን ሲያወልቅ፤ ዓይኖቹ
ሰው ብትሄድ ይሻላል፡፡›› ፈጠው ይቁለጨለጫሉ፡፡

ይህ የመጨረሻው ዐረፍተ ነገር ወጣቱን ያስገርመዋል፡፡ ‹‹እስቲ ድገመው ስንት ግጥም አልከኝ? ከጆሮዬ ነው
‹‹ገንዘብ? ገንዘብ አሉኝ? የምን ገንዘብ ጌታዬ! ችግሬ የገንዘብ መሰል…››
መሰብሰብ ቢሆን ኖሮ፣ እኔም እንደጓደኞቼ ትልቅ ሥራ ይዤ
ወፍራም ደሞዝ መግመጥ አያቅተኝም ነበር፡፡ ችግሬ ሌላ ነው፤ ‹‹ከአንድ ሺ ግጥም በላይ ጽፌአለሁ፤ ጽሑፎቹንም
ለየት ያለ ነው የኔ ችግሬ›› አለ የችግሩን ባሕርይ በኅሊና ይዣቸዋለሁ፡፡›› ቦርሳውን ቸብ ቸብ አደረገ፡፡ ‹‹ግጥሞቹን
ለመተንተን እየታገለ ቁጭ ሲል፡፡ አንብበውልኝ ስለያንዳንዱ ቅኔ ሚዛናዊ አስተያየትዎን እንዲሰጡኝ
ለመጠየቅ ነው የመጣሁት፡፡ እኔ ራሴ ሁሉንም እወዳቸዋለሁ፤
‹‹ገንዘብ ካልሆነ፡ ዐውቀዋለሁ ፍቅር ነው›› ችግሬም ይኸው ነው፡፡ አሁን በቅርብ ከማሳትመው የግጥም
መጽሐፍ የትኞቹን አስገብቼ የትኞቹን ላስወጣ? ሁሉንም
‹‹ፍቅር አሉ?!›› ወጣቱ በመደነቁ እንደ መሳቅ ቃጣ፡፡

ቅፅ-1፣ቁጥር 1 መስከረም 2010 ዓ.ም ገፅ 23


ታዛ

እንዳላሳትም የገንዘብ አቅም ያልኩዎት፡፡ እሺ ነው እምቢ?›› አለ ወጣቱ እንደግልፍታ መሳይ


ያጥረኛል፡፡›› እየቃጣው፡፡ የአንጋፋው ዝምታ አላማረውም፡፡ ‹‹ያነቡልኛል
አያነቡልኝም?››
‹‹አንድ ሺ ቅኔ በሃያ
ሦስት ዓመት ዕድሜ ታላቅ ‹‹የኔን ችግር ደግሞ ልንገርህ፣ ከአንድ ሺህ በላይ ግጥም
ብርታት ነው፤ አርበኝነት›› በጥንቃቄ ለማንበብና ስለያንዳንዱ አስተያየት ለመስጠት ጊዜውም
አለ በደራሲነት ዘመኑ ጉልበቱም ያጥረኛል፡፡››
ሙሉ አምስት መቶ እንኳ
ግጥም ያልጻፈው አንጋፋ ‹‹ገባኝ፤ ያንተ ግጥም አይረባም ለማለት ነው የሚያስቡት፡፡
ራሱን ወዝወዝ እያደረገ:: አሳብዎን እንዲህ በግልጥ ይንገሩኝና ወደ ሌላ ልሂድ፡፡ እርስዎ
ዘንድ የመጣሁት፣ ወጣት ደራሲያንን የሚያበረታቱ አንጋፋ
‹‹ግጥሞቹን ሊያነቡልኝ ደራሲ ናቸው የሚያሰኝ ዝናዎን ሰምቼ ነበር፡፡››
ይህ የመጨረሻው ዐረፍተ
ፈቃድዎ ከሆነ አሁኑኑ
ከነቦርሳው ላስረክብዎት›› ‹‹ረጋ በልና እንወያይ፤ በተቻለኝ አንተንም ለማበረታታት
ነገር ወጣቱን ዝግጁ ነኝ፡፡ አሥር ግጥም መርጠህ … እጅግ በጣም ጥሩ
አለ ወጣቱ ከማግባቢያና
ያስገርመዋል፡፡ ናቸው የምትላቸውን አሥር ግጥሞች ብታመጣልኝ እነሱን
ከማባበያ ደረቅ ፈገግታ ጋር
‹‹እሺ ይበሉና ያስደስቱኝ አነብልሃለሁ፡፡››
‹‹ገንዘብ? ገንዘብ አሉኝ?
ለዘላለም ባለውለታዎ
የምን ‹‹አሥር?! አሥር ምንድነው ከአንድ ሺ ግጥም?›› አለ ወጣቱ
እሆናለሁ፡፡››
እንደ መቆጣት እየቃጣው::
ገንዘብ ጌታዬ! ችግሬ አንጋፋው ቦርሳውን
‹‹የኔ ገረድ የምታደርገውን ልንገርህ?››
የገንዘብ በመነጽሩ ከቃኘ በኋላ
ዓይኖቹን ከሳሎኗ አሮጌ አንጋፋው እጁን ጸፋ፣ ርእሰ ጉዳዩን በመለወጥ፡፡
መሰብሰብ ቢሆን ኖሮ፣ ምንጣፍ እንደተከለ ቆየ፡፡
ወዲያው ገረዲቱ ከቸች አለች፡፡
እኔም እንደጓደኞቼ ትልቅ ‹‹ አንድ ሺ … አንድ ሺ…
ከአንድ ሺ በላይ…›› ‹‹ጠሩኝ?››
ሥራ ይዤ ወፍራም
በረጅም ዕድሜው እንዲህ ‹‹አዎ፤ አንድ ትልቅ ነገር ልጠይቅሽ ነው፡፡››
ደሞዝ
ያለ ነገር አጋጥሞት
‹‹ቶሎ ይጠይቁ፤ ወጥ ሥራ ይዣለሁ፡፡››
መግመጥ አያቅተኝም አያውቅም፤ ነገሩ መንታ
ነበር፡፡ ሆነበት፡፡ ማመን አቃተው፤ ‹‹ጥያቄውም የወጥን ሙያ የሚጠቅስ ነው፡፡ ወጥሽን ስትሠሪ
ላለማመን አልደፈረም፡፡ የጣእሙን ሁኔታ ለመገመት ስትሺ ምንድነው የምታደርጊ?››
ችግሬ ሌላ ነው፤ ለየት የሰው ነገር ምን ይታወቃል?
ይህ ወጣት ገና ሰው ‹‹ጣእሙን? ለመቅመስ? በማማሰያ ወጡን ጠንቆል አድርጌ፡
ያለ
ያላወቀው የሥነ ድርሰት እመዳፌ ላይ በጥቂቱ አስነክቼ ነዋ ከዚያ የምቀምሰው፡፡ ይኸ
ጉድ ቢሆንስ? ሎፔ ደቬጋ ምን ታምር አለው? ለእንዲህ ያለው ጥያቄ እየጠሩ ሥራ
ነው የኔ ችግሬ››
የተባለው የጥንቱ የስጳንያ ባያስፈቱኝ…›› ውልቅ ብላ ወጣች፡፡
ደራሲ ታሪክ ትዝ አለው፡
‹‹ይኸውልህ፡ የኔ ገረድ የወጧን ጣእም ለማወቅ የምታጣጥመው
፡ ሎፔ ደቬጋ 2 ሺ 200
ቅምሻውን ነው ሙሉውን አይደለም፡፡››
አጫጭርና ረጃጅም
ተውኔቶችን የደረሰ የሥነ ‹‹ቅኔን ከሽሮ ወጥ ጋር ማማሰልዎ ይቅርታ - ማመሳሰልዎ
ድርሰት ጉድ ነበር፡፡ ያሳዝናል›› አለ ወጣቱ ተከዝ እያለ፡፡

‹‹ታዲያስ እሺ ነው ‹‹ስለወጡ አንከራከር፤ ደግሞም ሁል ጊዜ ሽሮ ብቻ


እንቢ?›› አለ ትእግሥቱ እንዳይመስልህ፡፡ ለክርክር አሁን ጊዜው አይደለም፡፡›› አለ
ያለቀበት አፍለኛ፡፡ አንጋፋው ፈገግ እያለ፡፡ ‹‹ጥሩ ጥሩ ናቸው የምትላቸውን አሥር
ግጥሞች መርጠህ ባመቸህ ጊዜ አምጣልኝ ቅምሻውን፡፡ እነዚያን
ከሐሳብ ሰመመን ባነነ
በጥንቃቄ አንብቤ፣ ተንትኜ፣ መዝኜ፣ አመዛዝኜ ስለ ገጣሚነትህ
አንጋፋው ‹‹ምን አልከኝ?››
የሚኖረኝን አስተያየት እነግርሃለሁ፡፡ ክርክር ከዚያ በኋላ ነው፡፡››
‹‹ ቁርጡን ይንገሩኝ ነው

ቅፅ-1፣ቁጥር 1 መስከረም 2010 ዓ.ም ገፅ 24


ታዛ

‹‹እየነገርኩዎ! ግጥሞቼን ሁሉንም እንደ ወለድኳቸው ልጆቼ ከዚያም ከእንጦጦ ማርያም በታች ከአፋፉ በደንጊያ ላይ አረፍ
ነው የማያቸው፡፡ አንዱን ከአንዱ ማበላለጥ አይሆንልኝም፤ ብሎ አዲስ አበባን የዝቅዝቅ ሲመለከት ጥቂት ሰዓት አሳለፈ፡፡
አይቻለኝም፡፡ ችግሬም ይህ ነው፡፡›› አለ ወጣቱ እንደ መጨነቅ የሚያስበው ስለ ከተማዪቱ ሥዕላዊ ውበት፣ ባሻገር ስለሚታየው
እያለ ‹‹እርስዎ ሁሉንም አንድ ባንድ እንዲያነቡልኝ የምለምንዎ ስለ የረር ተራራና ስለ ዝቋላ ጋራ ግርማ ሞገስ ሳይሆን፣
ስለዚሁ ነው፡፡›› ስለዚያች የዘመመች አሮጌ የቆርቆሮ ቤት፣ ስለሚኖርባት አንጋፋ
ደራሲና ያም ስለ ሰነዘረው አስገራሚ ሐሳብ ነበር፡፡
‹‹እንግዲያማ ሺውም ሁሉ ግሩም ድንቅ ናቸው ማለትህ
እንዳይሆን!›› ‹‹የሚገርም እኮ ነው!›› አለ ከራሱ ጥላ ጋር በመወያየት
‹‹አሥር ግጥም ከአንድ ሺ ግጥም? ከሺ አሥር ከመቶ አንድ
‹‹በኔ ዓይን ናቸው፡፡›› መሆኑ ነው፡፡ የቀረው አይረባም ማለታቸው ነው? ታላቁ
ደራሲ፡፡ ድፍረታቸው ነው የሚገርመኝ፤ በሕይወታቸው ሙሉ
‹‹ዓይን ቅንድቡን የማያየው በጣም ቅርቡ ስለሆነ ነው፡፡›› አለ
አምስት መቶ ግጥም እንኳን ሳይጽፉ!...››
አንጋፋው እንደ መፈላሰፍ እየቃጣው፡፡
ይህ ካፉ እንደ ወጣ እንደ ድንጋጤ ያለ እንግዳ ነገር ተሰማውና
ወጣቱ በደራሲ ወኔ ግንፍል ይልና ብድግ ይላል ‹‹እርስዎ
በድንገት ዝም አለ፡፡ ዝም ያለው ሌላ ሰው ባጠገቡ ሲናገር የሰማ
ጋ በመምጣቴ ተሳስቻለሁ፤ እርስዎም እንደ ሌሎቹ ነዎት፡፡
ስለመሰለው ነው፡፡ ከጐኑ-ከጐኑም ቀርቦ ከውስጡ፣ ከልቡ::
አንጋፋ የምትባሉት እንደዚሁ ናችሁ፤ አዲስ ኃይል፣ ትኩስ
መንትያ ወንድሙ ይመስለዋል፤ እኅቶች እንጂ ወንድም እንኳ
የድርሰት ጉልበት ሲያጋጥማችሁ፣ በአናቱ ላይ ቀዝቃዛ ውሃ
ባይኖረው፡፡
መቸለስ ብቻ ነው የሚቀናችሁ፡፡ መቅናት ይቀናችኋል፡፡››
አቶ መንታዬ ጥያቄ ነበር የሚደረድረው፡፡ ‹‹ምን ይታወቃል?
ከወጣ በኋላ፣ እንደ ገና መለስ አለና ‹‹ወርቅ ጊዜዎን በማባከኔ
አንጋፋው መቶ በመቶ ተሳስተዋል ባንልስ፤ ስሕተታቸው ሃምሳ
ወፍራም ይቅርታ እጠይቃለሁ፡፡›› አለ በምጸት፡፡ ከዚያ
በመቶ ቢሆንስ? ከቀረው ሃምሳ በመቶ ግማሹ እንኳ ትክክል
ተመንጥቆ ሄደ ያበጠ ቦርሳውን አንግቶ፡፡
ሆኖ ቢገኝስ? በእኛስ ወገን በራስ ሥራ፣ በራስ ድርሰት፣
አንጋፋው ራሱን ወዘወዘና የግእዝ ቅኔ መጽሐፉን ማንበብ ውበትና ጥራት ያለው መተማመን መቶ በመቶ መሆኑ ስሕተት
ቀጠለ፡፡ ቢሆንስ? ዕውነቱ ከሃምሳ በመቶ ያነሰ ቢሆንስ? የሚያሳስብ
ሒሳብ ይሉሃል እንዲህ ያለ ነው!››
ግን ወጣቱ እንደ ሄደ አይቀርም፡፡
ወጣቱ ደራሲ እንደ መባነን አለና ብድግ አለ፤ ‹‹ይህ የምሰማው
በሳምንቱ በዚያው ሰዓትና ቦታ አንጋፋና ወጣት በቀደመ የስካር ነው የእብደት?!... ሳይመሽ በጊዜ እቤቴ ሄጄ ቶሎ ብዬ
ሁኔታቸው ተቀምጠው እንደ መፋጠጥ ብለዋል፡፡ በትንሹ ልተኛ፡፡ የዛሬው ነገር አላማረኝም፡፡ የኔው ነው ጥፋቱ፡፡ ሜታ
ጠረጴዛ ላይ አንድ ወፍራም የፈረንጅ መፅሐፍ ተዘርግቷል፡፡ ቢራ ላይ ባሮንስ ጂን መደረብ ጂኒ ነው የሚያመጣው፡፡ ጂኑን
ነገር የሚጀምር አንጋፋው ነው፡፡ አስቀድሜ ቢራውን ማስከተል ነበር- ‘ለማሳደጃ’ የሚሻለኝ፡፡
ለወደፊት ይህን ማስታወስ አለብኝ…››
‹‹ተመልሰህ የምትመጣ አልመሰለኝም ነበር፡፡ ምን ሌላ ጉዳይ
አመጣህ? ተቆጥተህ ነበር የሄድከው፡፡›› ዕውነትም ወጣቱ የእንጦጦን ጠመዝማዛ ቁልቁለት በፈጣን እርምጃ
ባለፈው እሑድ ተቆጥቶ ከሄደ በኋላ የሚመለስ አይመስልም ተያያዘው፡፡ እዋናው አስፋልት እንኳ ከገባም በኋላ መንገዱን
ነበር:: ግን ከዚያ ወዲህ በሳምንቱ ውስጥ ያልታሰበ ነገር በእግሩ ነው የፈጨው፡፡ እቤት ደርሶ አልጋው ላይ እረብ
አጋጥሞታል፡፡ እስኪልና እንቅልፍ እልም አርጐ እስኪወስደው ድረስ፡፡

በአንጋፋው ደራሲ ቤት የተዋለበትን ‹‹ግፍ›› ለማረሳሻ በየቀኑ ታናናሽ እኅቶቹን ለራት እንዳይቀሰቅሱት አዞ ስለነበር፡ እነርሱም
ወደ አንድ የሚያውቃት ግሮሰሪ ጐራ እያለ ከሜታ ቢራው መጠጣቱንና መበሳጨቱን አይተው ትእዛዙን ያለልማዳቸው
ደጋግሞ ተጐንጭቷል፡፡ ሜታውን አምስቱን ቀን ያለማሠለስ አከበሩለት፡፡
ቢጠጣም ብስጭቱን ለማስወገድ ባለመቻሉ በስድስተኛው ቀን
ቅዳሜ በአናቱ ባሮን ጂን ደራርቦበታል:: ግን ሜታውም ባሮኑም አቶ መንታዬ ግን ልዩ እንግዳ ፍጥረት አልነበረም፤ የወጣቱ
አእምሮውን ሊያደነዝዘው አልቻለም፡፡ የቢራ ማኅበርተኞቹ ውስጣዊ ባሕርይ ገጽታ የሕገ ኅሊናው ነጸብራቅ ነበር እንጂ፡፡
ጨዋታና ቀልድም አልጣመው፡፡
የመንደር ዶሮ ደጋግሞ እስኪጮኽ ድረስ ሌሊቱ በሰላም እንቅልፍ
ከግሮሰሪዋ ወጣና በአውቶቡስ ተሳፍሮ የበላይ ዘለቀን ጐዳና አለፈ፡፡ ዶሮው የመጨረሻ ጩኸቱን ሲያዜም ነው ወጣቱ ደራሲ
አቀበቱን ይዞ ተጓዘ፡፡ እጐጃም በር ኬላ ሲደርስ ወደ ቀኝ ብንን ብሎ የራስጌውን መብራት ያበራው፡፡ አንዳንዴ ኃይለኛ
ታጠፈና የእግር መንገዱን በእንጦጦ ጋራ ላይ ቀጠለ፤ ዝግ ችግር ላጋጠመው ሰው በእንቅልፍ ልቡ ውስጠ ኅሊናው ችግሩን
ብሎ በመራመድ እያሰበ በራጉኤል ጐን አለፈ፡፡ ተንትኖ፣ አንጥሮ፣ አበጥሮ፣ መፍትሔውን ሲነጋጋ ብልጭ
ያደርግለታል፡፡ በብልጭታው የተስፋ ጭላንጭል ይታየዋል፡፡

ቅፅ-1፣ቁጥር 1 መስከረም 2010 ዓ.ም ገፅ 25


ታዛ

ይህ ጭላንጭል ነበር ወጣቱን ከእንቅልፉ ቀስቅሶ ግጥሞቹን የመጀመሪያ ጥያቄ ማንሳት ብቻ ነው፡፡›› ጥቂት ሲያስብ ቆየና
ሁሉ ከታጨቁበት ቦርሳ አልጋው ላይ እንዲዘረግፍና በውል ‹‹ሌላ ጥያቄ ልጠይቅ፣ አሁንም አትቀየም እንደሆን››
እንዲቃኛቸው ያስገደደው፡፡
‹‹ይጠይቁ፣ አልቀየምም፡፡››
ከቅኝቱ ኋላ ረፈድ ሲል ወደ አንጋፋው ቤት አዘገመ፡፡ መጠነኛ
ፋይል ጠቅልሎ ጨብጧል፤ የሸራ ቦርሳውን እቤት ትቶታል፡፡ ‹‹ጥያቄው ይህ ነው፤ እያንዳንዱን ግጥም ስንት ጊዜ ነው
የምትጽፈው?››
‹‹እኮ ምን ሌላ ጉዳይ አመጣህ?›› አለ አንጋፋው በድጋሚ፡፡
‹‹ስንት ጊዜ? አንድ ጊዜ ነዋ፡፡ እኔ አንድ ግጥም አንድ ጊዜ
በወጣቱ ገጽ ላይ ከዚህ ቀደም ያልተከሰተ አይናፋርነት መሳይ ነው የምጽፈው፡፡ መሠረዝ መደለዝ የሚባል ነገር አልወድም፡፡
ይታይ ነበር፡፡ ‹‹መርጠህ አምጣ ያሉኝን አሥር ቅኔ … ግጥም በንጹሕ ወረቀት ላይ ገና ሲወጠን ጀምሮ ቁልጭ ብሎ ሲሠፍር
ማለቴ ነው አምጥቻለሁ፡፡ ግን አስቀድሜ ላስጠንቅቅዎት:: ነው ግጥም ደስ የሚለኝ፡፡››
ያመጣሁት ከሌሎቹ ግጥሞቼ ይልቅ ደስ ከሚሉኝ ጥቂቶቹን
ነው፤ ይበልጣሉ የምላቸውን አይደለም፡፡ ማበላለጥ አሁንም አንጋፋው የመጣበትን ሳቅ ገታ፡፡ ‹‹አንደኛ ረቂቅ፣ ሁለተኛ
አልተቻለኝም፡፡›› ረቂቅ፣ ሦስተኛ ረቂቅ የለህማ?››

‹‹ዋናው ነገር መምረጥ መቻል ነው፡፡ የምርጫህ መነሻ ፍቅር ‹‹በፍፁም! አንድን ግጥም የምጽፈው አንዴ ብቻ ነው፤
ሆነ ውዴታ ወይም ግዴታ እምብዛም ልዩነት የለው፡፡ መምረጡ የድርሰቱ መንፈስ እንዳነሣሣኝ ነው የማነጉደው፡፡ ሐሳብ
ላይ ነው ቁም ነገሩ›› አቶ አንጋፋ በድንገት ነቃ ፈገግ አለ፤ የሚመጣልኝ እንደ ማእበል ስለሆነ፤ ቆም ብሎ ለማሰላሰያ፣
ዓይኖቹ ቁልጭልጭ አሉ፡፡ ‹‹የታል ያመጣኸው? ... ስጠኝና ለመሰረዣ፣ ለመደለዣ ፈጽሞ ጊዜ አይሰጠኝም፡፡ ስጨርስ ነው
ልመልከትልህ፡፡›› የሚያሳርፈኝ፡፡››

ወጣት ከወንበር ብድግ ብሎ አሥሩን ግጥሞች ከተጠቀለሉበት ‹‹እንደ ማእበል ›› አልክ? … እንደ ማእበል ደሴ!››
ፋይል አውጥቶ በሁለት እጁ ላንጋፋው አስረክቦ ተቀመጠ፡፡
‹‹የሰው ስም ነው ማእበል ደሴ?››
አንጋፋው በችኮላ ግጥሞቹን እየዘረጋጋ ይመለካከት ጀመር፡፡
“የታላቅ ባለቅኔ መጠሪያ ነው፡፡ ‘ማእበል’ የሙገሳ ነው እንደ
አልፎ አልፎ አርእስታቸውን በለሆሳስ ለራሱ ያነባል፤ አልፎ
ፈረስ ስም ያለ፤ ‘ደሴ’ የቁልምጫ ስም፤ ደስታ ነው የራሳቸው
አልፎ ግንባሩን ይቋጥራል፤ ይወጥራል፤ ፊቱን ያኮማትራል፤
ስም፡፡›› ተከዝ አለ አንጋፋ ራሱን ደፋ አርጐ::
አልፎ አልፎም ሸበቶ መላጣ ራሱን ይደባብሳል፡፡ ከገለባበጠና
ካነበበ በኋላ ግጥሞቹን ሰበሰበና ጠረጴዛዋ ላይ በቁመታቸው ‹‹ሰምቼውም አላውቅ፡፡››
እየመታታ አስተካከለና ገጾቹን ቆጠረ፡፡ ለጥቆ ከቀኝ እጅ ወደ
ግራ፣ ከግራ ወደ ቀኝ፣ እያዘዋወረ እንደ ቅቤ አሎሎ በማንከብከብ ‹‹እንዳልሰማህ ዐውቃለሁ፡፡ ስሙ ወደ ግእዝ ቅኔ የሚስበን
የወረቀት ሚዛናቸውን የሚገምት ይመስል ነበር፡፡ ስለሆነ፣ ለጊዜው እንለፈው፡፡

ይህ ሁሉ ሲከናወን ወጣቱ ደራሲ ትእግስት በተሞላ ትዝብት አነጋገሩ ወጣቱን ይከነክነዋል:: ‹‹እንዝለለው የሚሉት
ይመለከታል፡፡ ቆይቶ አንጋፋው ተናገረ፡፡ ‹‹አንዳንድ ጥያቄ ምሥጢሩን ብነግረው አይገባውም ብለው አይደለም?››
ብጠይቅ ትቀየማለህ?››
‹‹አይገባህም አይደለም፤ እንድነግርህ አትፈቅድ ይሆናል ነው፤
‹‹ይጠይቁ ምን አስቀየመኝ? የማፍርበት ነገር የለም፡፡›› አለ ሳትወድ በግድ ብነግርህ ትቀየም ይሆናል ነው አስተሳሰቤ፡፡
ወጣቱ እንደመከንከን እየጀመረው፡፡ ›› እንደ መቸኮል አለ፡፡ ‹‹ለሁሉም አሁን የያዝነው ያንተን
ግጥሞች ጉዳይ ነው፤ የግእዝ ቅኔን አይደለም፡፡ ወደ ሥራችን
‹‹ግጥሞችህ የተጻፉበት ወረቀት ሳሳ ያለ ነው፤ የአሥሩ ግጥም እንመለስ… የት ላይ ነበርን? እምን ላይ ነበርን?››
ጠቅላላው ጽሑፍ ቢመዘን ስንት ግራም የሚሆን ይመስልሃል?››
‹‹አንዱን ቅኔ ስንት ጊዜ ትጽፈዋለህ? ብለውኝ፤ መልሱን
‹‹ሥጋ ወይንም ስኳር አይደለ፤ ግጥም እንዴት በኪሎ ሰጥቻለሁ፡፡ ሌላ ጥያቄ ካለዎ ይጠይቁ፡፡››
ይመዘናል?›› አለ ወጣቱ ደራሲ በምጸት፡፡
‹‹እግረ መንገዴን የሽማግሌ ምክር ብሰነዝር፤ ትቆጣለህ?
‹‹አይምሰልህ፤ አንዳንዱ ዓይነት ግጥም ይመዘናል፤ የሚከነዳም ሐቁን ንገረኝ፡፡››
ሞልቷል፡፡››
ወጣቱ አመናታ፡፡ ግን ቢያመናታም ወዲያውኑ ነው መልሱን
‹‹ግጥሞችህ አለቅጥ ረዘሙ ለማለት ፈልገው ነው መሰል?›› የሰጠው፡፡ ‹‹በስራው የማይተማመን ነው የሚቆጣ፡፡ እኔ
ደሞ ተራዬን ልጠይቅዎት፤ ምክርዎን ባልቀበለው ይቆጣሉ፣
‹‹ትንተናውን ለሌላ ጊዜ እናቆየው፡፡ አሁን የያዝኩት አንዳንድ
ይቀየማሉ?››

ቅፅ-1፣ቁጥር 1 መስከረም 2010 ዓ.ም ገፅ 26


ታዛ

‹‹እንዴት ብዬ? ለምን ብዬ? እንዲያውም ከልብ ያልመነጨና የሚገልጹት ሐሳብም ይህን ያህል ጥልቀት አልነበረው፡፡ በስሜት
ከልብ የማይገባ ምክርን ሁሉ ፈጽመህ አትቀበል ነው የምልህ፡፡›› ደረጃ ደግሞ ከመጠን በላይ ተጋነዋል፡፡ አብዛኞቹ የተጻፉበት
በወጣቱ ፊት ላይ ፈገግታ መሳይ ተከሠተ፤ ‹‹እንዲህ ከሆነ ቋንቋ ‹‹ጋራጋንቲ›› የሚባለው ኮረኮንች ዓይነት በመሆኑ ጆሮን
አመልዎ የምንግባባ ይመስለኛል፡፡›› ሆነ ምላስን የሚያነቅፍ ነበር፡፡ አንዳንዶቹ ከሚገልጹት ሐሳብ
መወሳሰብና አጉል መራቀቅ የተነሳ የተማረ አንባቢ እንኳን
‹‹ማን ያውቃል? ምን ይታወቃል? እያደር ሁሉም ይታያል፡፡
የሚረዳቸው አልነበሩም፡፡ ያልተሰረዙ፣ ያልተደለዙ በመጀመሪያ
አምጣ ያልኩህን አምጥተሃል፤ የበኩልህን ፈጽመሃል፡፡ እኔ
ረቂቅ ብቻ የተፈጸሙ እንደ መሆናቸው መጠን ሌላ ሌላም
ደግሞ አሥሩን ግጥሞችህን አንብቤ የበኩሌን እፈጽማለሁ፡፡
ተጨማሪ ጉድለት ነበረባቸው፡፡
ደግሞ…››
ይህን ሁሉ በጥሞና በመገንዘቡ፤ አንጋፋው ከችግር ላይ ወደቀ፡፡
ወጣቱ ያቋርጠዋል፡፡ ‹‹መልሱን ይሰጡኛል?››
የምርመራውንና የምዘናውን ውጤት ለወጣቱ ደራሲ እቅጩን
‹‹በችኮላ አይሆንም፡፡ የዛሬ ሳምንት በዚሁ ዕለት፤ በዚሁ ሰዓት ቢነግረው ወጣቱ ተስፋ እንዳይቆርጥበት ሰጋ፤ ባይነግረው
ተመለስ፡፡ ግምቴንና አስተያየቴን ባጠቃላይም ምዘናዬን ያን ጊዜ መዋሸት ሊሆንበት ሆነ:: ወጣቱ ከስሕተቱ እንዳይማር ማድረግ
እሰጣለሁ፡፡›› ሆነበት፡፡ ምን ይሻላል?

‹‹ከሰጡኝ በኋላ አንድ ሌላ የሚያደርጉልኝ ነገር አለ፤ ዞሮ ዞሮ በመካያው አንድ ቀን ጥርሱን ነክሶ የምዘናውን ውጤት
ላስቸግርዎትና፡፡ አሁን በቅርቡ በማሳትመው የቅኔ መጽሐፌ ለወጣቱ ማስረዳት ሳያስፈልግ አይቀርም፡፡ ወጣቱ የተሳሳተው
መጀመሪያ ላይ የሚውል አምስት ገጽ ያህል መግቢያ እርስዎ ግጥሙን በፈጠራ ግልቢያ የሽምጥ በመጻፉ ሳይሆን ከጻፈው
የታወቁ አንጋፋ ደራሲ እንደመሆንዎ ቢጽፉልኝ ለገበያው በጣም በኋላ በምዘናዊ ቴሌስኮፕ መነፅር ሳይመረምረው በመቅረቱ
ይረዳኝ ነበር፡፡›› አለ ወጣቱ ሳይለማመጥ ክብሩን ጠብቆ፡፡ ነው፡፡ ይህን ሁሉ አንጋፋው ካወጣና ካወረደ በኋላ ‘ለማንኛውም
ወጣቱ በቀጠሮው እስኪመለስ ድረስ ነገሩን በይደር ማቆየት
‹‹ለሁሉም ጊዜ አለው፤ አትቸኩል፡፡›› አንጋፋው እፊቱ ይሻላል’ በማለት ጉዳዩን ወደ ጐን ገለል አድርጐ የራሱን
የተዘረጋውን መጽሐፍ አነሳ፡፡ ‹‹ይህን መጽሐፍ ታውቀዋለህ? የማንበብና የመጻፍ መደበኛ ስራ ቀጠለ፡፡
የነቤርቶልት ብሬኽትን፣ የነማያኮቭስኪን የሌሎች የሌሎችንም
ቅኔ ያዘለ ነው፡፡››

ወጣቱ ብድግ አለና መጽሐፉን ተመለከተ፤ ‹‹የለም፣


አላውቀውም፡፡ ሳምንት እመጣለሁ፤ እስከዚያው ደኅና ሁኑ፡፡›› ዞሮ ዞሮ በመካያው አንድ
ወጣቱ ከኋላው በሩን ዘጋ፡፡ * * *
ቀን ጥርሱን ነክሶ የምዘናውን
አንጋፋው መነጽሩን አስተካክሎ ሰካና የወጣቱን ግጥም ማንበብ
እንደጀመረ፤ ወርቂቱ ከቸች፡፡
ውጤት ለወጣቱ ማስረዳት
‹‹ሻይና ስኳር አልቋል፡፡›› አለች በተለመደ ቅልጥፍናዋ፡፡

አቶ አንጋፋ እጁን ከደረት ኪሱ ሰደደና ገንዘብ አውጥቶ ሰጣት፤


ሳያስፈልግ አይቀርም፡፡
በጥድፊያ ተቀበለችና ወጣች፤ እርሱ የግጥም ንባቡን ቀጠለ፡፡
ወጣቱ የተሳሳተው ግጥሙን
የወጣቱን ግጥሞች አሥሩንም አንድ ጊዜ ፈጠን ባለ ንባብ
ወጣቸው፡፡ አንጋፋው ቀጥሎ ከሦስት ቦታ መደባቸው፤
በፈጠራ ግልቢያ የሽምጥ
እንደየርዕሰ ጉዳያቸው ተመሳሳይነት ለጥቆ የየመደቡን ግጥሞች
እየለየ በድጋሚ በዝግታ በማሰላሰል አነበበ፡፡ እያነበበ አንዳንድ
ሐሳብ ሲመጣለት በማስታወሻ ደብተሩ ቶሎ ብሎ ያሠፍረው
በመጻፉ ሳይሆን ከጻፈው
ነበር፡፡
በኋላ በምዘናዊ ቴሌስኮፕ
በዚህ ዘዴ አሥሩን ግጥሞች ከመረመረ በኋላ ስለ ሥነ-
ጥበባዊና ኪነ ጥበባዊ ደረጃቸው ያገኘውን ውጤት በልቡ ያወጣ
ያወርድ ጀመር፡፡
መነፅር ሳይመረምረው
የወጣቱ ግጥሞች አለቅጥ ረጃጅም ነበሩ፤ በይዘት ረገድ አለቅጥ በመቅረቱ ነው፡፡
ሰፍተዋል፤ ሲሰፉ ሳስተዋል፤ ቤት መምቻቸው አብዛኛውን ሳድስ
ቀለም ነው፤ እንደ ‹‹ት››፤ እንደ ‹‹ን››፤ እንደ ‹‹ች›› ያለው፡፡

ቅፅ-1፣ቁጥር 1 መስከረም 2010 ዓ.ም ገፅ 27


ታዛ ስነ-ስዕል

ቴአትር፣ ስዕልና
ተመልካች ስእልን ማየት ሆነ መጽሀፍን
ማንበብ በተፈለገው ሰዓትና ቦታ
ማከናወን የሚቻል ሲሆን ቴአትር
ግን መሠረታዊ ባህሪው አቅራቢና
የታዳሚ ውህደት እንደመሆኑ መጠን
በአንድ ቦታ በአንድ ጊዜ ተመልካችን
ሰብስቦ ትርዒት የሚያዩበትንና
የሚነጋገሩበትን መድረክ መፍጠር
ታደሰ መስፍን
ይኖርበታል፡፡

ሁሉም አይነት የጥበብ ዘርፎች ቴአትርና ስእልን


ጨምሮ ውስብስብ የፈጠራ ስራ ውጤቶች ናቸው፡፡
ከሁሉም የቴአትር ፎርሞች የበለጠ የሚዘወተረውና ገናና
በዚህም ሂደት ውስጥ ዋና አላማቸው በአብዛኛው የሰውን የሆነው የስነ-ጽሁፍ ውጤት ድራማ ከመሆኑ የተነሳና አብዛኛውን
ስሜት ለማንፀባረቅ የሚችል ተምሳሌታዊ ቅርጽ /sym- ጊዜ ቴአትር ሲባል ድራማ የሚለው ስለሆነ፣ የመድረክ ገጽ
bolic forms/ መፍጠር፣ መፈለግና ማግኘት ነው፡፡ ሰዓሊውም ስልጠና የሚያተኩረው ይህንኑ የፀሀፌ ተውኔት
ድርሰት ሀሳብ በስእሉ ለመተርጐምና ለማስፋፋት ነው፡፡
ማንም ተመልካች በሸራ ላይ በቀለምና ብሩሽ የተሰራን ሰው ምስል
አይቶ፣ ምስሉ የእውነተኛ ሰው ወካይ መሆኑን ይገነዘባል፡፡ የመድረክ ዲዛይን በጣም ትልቅ ስለሆነ የትርዒቱን ይዘትና
ማለትም ስእሉ እንጂ የጥበቡ መገለጫ፣ እውነተኛ ሰው አይደለም፡፡ ቅርጽ በከፍተኛ ደረጃ የመደገፍ ሀይል አለው:: ከመድረክ ጀርባ
ወደ ታች ከሚወርደው ስእል በተጨማሪ ዲዛይኑ በዚያ ቴአትር
በቴአትር ጥበብ ግን በህይወት የሚንቀሳቀስ ሰው ራሱ /ተዋናዩ/ ላይ ሊታዩ የሚገባቸውን እቃዎችና አልባሳት የመታየትና
ነው የጥበቡ ዋነኛ ማከናወኛና መገለጫ መሳሪያው፡፡ የማጀብ ባህሪ እንዲኖራቸው ማድረግ ብቻ ሳይሆን ተዋንያኑም
እንደልብ ተንቀሳቅሰው እንዲጫወቱ ማስቻል አለበት፡፡ የነዚህ
ሁሉ ቅንጅትና አጠቃላይ ትእይንቶች ናቸው ቴአትርን ሊወክሉ
ስእልም ሆነ ቴአትር ሁለቱም በባህሪያቸው በእይታዊ ጥበብ የሚችሉት፡፡ እንደ ቴአትሩ ይዘት በአንድ ቴአትር ብዙ የመድረክ
ጐራ ውስጥ ስለሚመደቡ ተመልካችን ይፈልጋሉ፡፡ ስእልን ገጽ ትርዒቶች ሊያስፈልጉ ስለሚችሉ እነዚህን ሁሉ ዲዛይን
ማየት ሆነ መጽሀፍን ማንበብ በተፈለገው ሰዓትና ቦታ ማከናወን ማድረግ መስራትና ተሰርተው ካለቁም በኋላ ባህሪያቸውን
የሚቻል ሲሆን ቴአትር ግን መሠረታዊ ባህሪው አቅራቢና ሊያጐላ በሚችል መንገድ መብራት ማግኘታቸውን ማረጋገጥ
የታዳሚ ውህደት እንደመሆኑ መጠን በአንድ ቦታ በአንድ ጊዜ ያስፈልጋል፡፡
ተመልካችን ሰብስቦ ትርዒት የሚያዩበትንና የሚነጋገሩበትን
መድረክ መፍጠር ይኖርበታል፡፡ ብርሀን ዋናው ፎርም ገላጭ ነው:: ብርሀን ከሌለ ጥላ የለም፡፡
ብርሀንና ጥላ ከሌሉ ደግሞ ፎርም አይታይም፡፡ ስለዚህ የመድረክ
ወደ መድረክ ገጽ ዲዛይን በምንሸጋገርበት ጊዜ ዲዛይን አንድ ገጽን ከመብራት ነጥሎ ማሰብ አይቻልም፡፡ የስራ ክፍፍል
የቴአትር ፕሮዳክሽን ቅንጅት አካል ስለሆነ ተግባሩ ቴአትር ጐልቶ በሚታይበት የቴአትር ፕሮዳክሽን ውስጥ ሁሉንም
ውስጥ ያለውን ጭብጥ ወደ አጠቃላይ እይታዊ ገጽታ መቀየር የመድረክ እይታ ዝግጅት በአንድ ሰዓሊ ብቻ ማሰራት ግዴታ
ነው፡፡ ይህም ተግባራዊ የሚሆነው የመድረክ ገጽ፣ ስእል፣ አይደለም፡፡ በአብዛኛው በትላልቅ ቴአትሮች ሊለያዩ ይችላሉ፡፡
አልባሳት፣ ብርሀንና ድምጽ አራቱም በአንድ ላይ ሲቀናጁ ሁሉንም የሚያገናኛቸውና የሚያዋህዳቸው ግን መሠረታዊ
ነው፡፡ ሁሉም ነገር በፍጥነት እየተለዋወጠ በሚገኝበት አለም የዲዛይን ጽንሰ ሀሳብ ነው፡፡ ይኸውም የቴአትር ደራሲውን
ውስጥ የቴአትርና የተመልካች ሁኔታም በዚያው መጠን ሀሳብ ከቴአትር አዘጋጁ ጋር በመተባበር ወደ እይታዊ ቋንቋ
ጊዜ ያመጣውንና የሚያመጣውን እየመሰለ ይጓዛል፡፡ እነዚህ መተርጐምና በተገቢው ሁኔታ መድረክ ላይ በተግባር አጉልቶ
ሁኔታዎች እንደማንኛውም ጠቢብ የመድረክ ገጽ ሰአሊውንም ማሳየት ነው፡፡ በአምፊ ቴአትርና ወደፊት ወደ ተመልካቹ ወጣ
ሳይነካኩት አያልፉም:: ዲዛይነር ከሚሰራቸው የቴአትር ወጣ ባሉ መድረኮች ላይ ከሁሉም ዲዛይኖች በላይ ጐልቶ
ፎርሞች ዋና ዋናዎቹ ድራማ፣ በድምጽና ብርሃን ላይ ትኩረት የሚወጣው የአልባሳቱ ዲዛይን ነው፡፡
የሚያደርገው ኦፔራ ባሌትና ዘመናዊ ዳንስን ያቀፈው ኦዲዮ-
ቪዥዋል ሙዚቃዊ ፎርምና ሁሉንም የሚያቀናጀው የዳንስና ዲዛይነሩ በቴአትር ውስጥ ያሉትን ገጸ-ባህሪያትና
ድራማ ፎርም ይገኙበታል፡፡ ነገር ግን ምንም ዓይነት አቅጣጫ፣ የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ በሚገባ ማወቁ ለሚሰራው ስራ
ቅርጽና ይዘት ቴአትር ቤቶች ቢይዙም ሰዓሊው ሁሉንም ወሳኝነት አለው፡፡ የጨዋታው እንቅስቃሴ ስለሆነ ለቴአትሩ
ፎርሞች ዲዛይን ማድረግ አለበት፡፡ እስትንፋስና ህይወት የሚሰጠው አንዳንድ ጊዜም እራሱ የገጹ
ዝግጅት፣ እራሱ የእንቅስቃሴው አካል ይሆናል፡፡ ዋናውና

ቅፅ-1፣ቁጥር 1 መስከረም 2010 ዓ.ም ገፅ 28


ስነ-ስዕል ታዛ

የቴአትር መድረክ ዲዛይን

የመጀመሪያው የመድረክ ገጽ ዝግጅት ለጨዋታው እንቅስቃሴ አለበት፡፡ ራሱ የቴአትሩ መንፈስ ቀለሙን ይፈጥረዋል፡፡
አስፈላጊና ተስማሚ አካባቢና ቦታ መፍጠር ነው፡፡ ምክንያቱም ከቴአትሩ ሂደት ነው ሰዓሊው የዲዛይኑን መንፈስ
የሚያገኘው፡፡ ስለዚህ እግረ መንገዱን ፎርሙን ያገኛል፡፡
አጠቃላይ የቴአትሩን ዋንኛ ስሜት በመድረኩ ገጽ ማግኘት ፎርሙና ይዘቱ ተገናኙ ማለት ደግሞ የመድረኩ ዲዛይን
ማለት ተመልካቹ ገና መድረኩን ሲያይ መተላለፍ ያለበትን የተዋጣ ሆነ ማለት ነው፡፡
መንፈስ ወዲያው መረዳት ያስችለዋል፡፡ ሞቅ ያለ፣ ደስ የሚል፣
ደብዛዛ፣ ሀዘን የበዛበት፣ አስቂኝ ወዘተ… መሆኑን ይረዳል፡፡ ቴአትር በአንድ ቦታና በአንድ ጊዜ በተመልካችና በተዋንያን
መሀል የሚደረግ ግንኙነት ስለሆነ የጊዜያዊነት ስሜት አለው፡፡
የመድረክ ገጽ ዲዛይን ብቻውን ሊቆም የማይችልና የድራማው ስለዚህ ስዕሉ ቋሚ የሆነ ነገር ቢሆንም ከቴአትሩ ጊዜያዊና
ትርዒት አካል እንደ መሆኑ መጠን ሰዓሊው ማሰብ ያለበት /ቅጽበታዊ/ ተለዋዋጭ ሂደት ጋር አብሮ ለመቀናጀት በቀላሉ
ስለ ስእሉ ብቻ ሳይሆን ስለቴአትር ቴክኖሎጂና ቴክኒክም የሚንቀሳቀስና ቴአትሩ ሲያልቅም መነሳት የሚችል መሆን
ጭምር መሆን አለበት፡፡ ሰዓሊው የዲዛይኑን ንድፍ ቢያወጣና አለበት፡፡ እዚህ ላይ መታወስ ያለበት ለስላሳና ጠንካራ የመድረክ
ሞዴል ቢሰራም የመጨረሻው ስራ ተከናውኖ ቴአትር መድረክ ገጽ ክብደትን የሚሸከሙና የማይሸከሙ የመድረክ ግንባታዎችን
ላይ እስካልወጣ ድረስ የዲዛይኑ ስራ አይገባደድም፡፡ ስለዚህ ግምት ውስጥ በማስገባት ነው፡፡ ቴአትር ሁልጊዜ ከሌሎች ነገሮች
ድራማ ራሱን የቻለ የስሜት መግለጫ ዘርፍ መሆኑን ተገንዝቦ የበለጠ ፎርሞችን ከህይወት በላይ አጉልቶና አጋኖ ስለሚያሳይ
ከቴአትሩ ጋር ሙሉ በሙሉ እራሱን ማዋሀድ መቻል አለበት፡፡ የመድረክ ገጽ ስዕል መጠንም ከተመልካቹ ጋር ያለውን ርቀት
ግምት ውስጥ ያስገባ፣ በጣም የጐላና ትልቅ ነው፡፡ ስለዚህ
ሰዓሊው የሚሰራቸው የመድረክ ገጽ ዲዛይኖች ጥራት ባህሪው እንደሌሎች ስዕሎች አይነት ቢሆንም ከመጠኑ የተነሳ
እንዲኖራቸው ለማድረግ አርቆ አስተዋይ፣ ሀሳብ ቶሎ ማመንጨት ለመስራት በጣም ሰፊ ቦታ የሚጠይቅ ነው፡፡ መሬት ላይ
የሚችል፣ በቴክኒክና በክሂሎት የዳበረ፣ የደራሲውን ስሜትና ተነጥፎ አቀባቡም ወደ ላይና ወደ ታች (vertically)፣ ወደ ጐንና
ሀሳብ የሚረዳና የሚጋራ፣ አጠቃላይ የትርዒቱን ይዘትና ቅርጽ ወደ ጐን (horizontally)፣ በትላልቅ ቡሩሾች ስለሆነ፣ ተሠርቶ
ማገናዘብ የሚችል፣ በቀላሉ ለማግኘትና ለመስራት በሚችሉ ሲያልቅና ሲሰቀል ሊያመጣ የሚችለውን ለውጥና መዛባት
ቁሳቁሶች በመጠቀም የመድረክ ገጽን ማንቀሳቀስና ብርሀን (distortion) ከግምት ውስጥ በማስገባት አስቀድሞ መጠንቀቅ
ሲያርፍባቸው ምን ዓይነት ስሜት ማስተላለፍ መቻላቸውን ያስፈልጋል፡፡ ከዚያም ለመድረስ የመድረኩን መጠንና ቅርጽ
አስቀድሞ ማወቅና አጠቃላይ የቴአትሩን መንፈስ ለመፍጠር በደንብ ማገናዘብ ያስፈልጋል፡፡ በተጨማሪም በተመልካቹ ግራና
ከፍተኛ ሚና መጫወት ሲችል ነው፡፡ ቀኝ ጠርዞች ላይና ሎጂ /ፎቅ/ ላይ የሚቀመጡ ተመልካቾች
መድረኩን እንደ መሀል ተመልካቾች ሙሉ በሙሉ የማየት
የመድረክ ገጽ ዲዛይነሮች የየራሳቸው የአሰራር ዘይቤና እድል ስለሌላቸው ዲዛይነሩ በሚሰራበት ጊዜ በተቻለ መጠን
መንገድ ሊኖራቸው ቢችልም፣ ሀሳብን የማመንጨት ችሎታቸው ዋናውን ሀሳብ ለሁሉም በሚዳረስበት ቦታ ላይ ማስቀመጥ
ያለጥርጥር ይለያያል፡፡ ሀሳብ ሊመነጭ የሚችለው ከቴአትሩ አለበት፡፡
ጽሁፍ ቢሆንም የቴአትሩን ዋና መንፈስ መረዳትና ተረድቶም
ወደ እይታዊ ቋንቋ ለመለወጥ የእያንዳንዱን ሰዓሊ የድርሰት መሰረታዊ የእይታዊ ጥበብ ቋንቋ ፊደሎችና የዲዛይን ወይንም
ችሎታ ይጠይቃል፡፡ ስለዚህ ሰዓሊው ቴአትሩን ማንበብና ‹‹ምን የድርሰት ህጐች ተመሳሳይነትና ተወራራሽነት አላቸው፡፡
አይነት ቴአትር ነው? ደራሲው ምን ማለት ፈልጐ ነው? ዋናው ይኸውም ዲዛይን የሚጀምረው ከተፈጥሮ ነው፡፡ ስለዚህ ነው
ይዘቱ፣ መንፈሱ ምንድን ነው? ቴአትሩ ኮሜዲ፣ ትራጀዲ… ተፈጥሮ የሁሉ ነገር መነሻና መድረሻ የምትሆነው፡፡ ምናልባት
ወዘተ ምንድን ነው?›› የሚሉትን ጥያቄዎች መጠየቅና መመለስ አርቲስቱ ተፈጥሮ ካስቀመጠችለት ሌላ ስሜትን አእምሮንና

ቅፅ-1፣ቁጥር 1 መስከረም 2010 ዓ.ም ገፅ 29


ታዛ ስነ-ስዕል

የካበተ ችሎታን መጨመር ይችላል፡፡ በስሜት መስራት


እንደያንዳንዱ ግለሰብ ይለያያል፡፡ አእምሯዊ ስራውን ግን
ለክቶም፣ ተጠቦም፣ አስቦም፣ አሰላስሎም መስራት ይቻላል፡፡
ስለዚህ የፈጠራ ስራው የተሟላ የሚሆነው እነዚህ ሁለቱ
ማለትም ስሜትና እውቀት ወይም አእምሮ ሲገናኙ ነው፡፡

እነመስመር፣ ፎርም፣ ቀለም፣ ለስላሳነት፣ ሸካራነት ወዘተ…


ለሁሉም የእይታዊ ጥበብ ፊደሎች የመሆናቸውን ያህል እነ
ድግግሞሽ፣ ሚዛናዊነት፣ ልዩነት፣ በአንድነት መጣጣም፣
ማጉላት ወዘተ… እንግዲህ የነዚህ ቋንቋዎች ቅንጅት ድምር
ውጤት ነው ድርሰት የሚሆነው፡፡ እነዚህን መርሆዎች
በመጠቀም ነው ገና መጋረጃው ሲከፈት በተመልካቹ ላይ
የሚፈጥረውን ስሜት ለሁለት ሰዓትና ከዚያም በላይ ሳይደበዝዝ
ማቆየት የሚቻለው፡፡

ቴአትር ውስጥ አንዱ የመድረክ ስዕል አላማ በሁለት


አውታረ መጠን ላይ በሶስት አውታረ መጠን ጥልቀት መፍጠር
ሲሆን አራተኛና ወሳኝ የሆነውን አውታረ መጠን ‹‹ጊዜ››
ወይም እንቅስቃሴ በደንብ እንዲፈጠርና በተገቢው እንዲካሄድ
ዲዛይነሩ የመድረክ ወለሉን አቀማመጥ /floor plan/ አብሮ
ዲዛይን ማድረግ አለበት፡፡

የተሟላ ቴአትር ቤት የቁሳቁሶች፣ የዕቃ ግምጃ ቤት፣ የመድረክ


ገጽ ስራዎች የሚከናወኑበት የመስሪያ ቦታ፣ የእንጨትና የብረት
ስራዎች እየተሰሩ የሚገጣጠሙበትና ለቴአትሩ የሚያስፈልጉ
የአልባሳትና ልዩ ቅንብር ዲዛይን
በተጠባባቂነት የሚገኙ ስራዎችን በጊዜያዊ ማስቀመጫነት
የሚያገለግሉ ቦታዎች አሉት፡፡
የመድረክ ገጽ ዲዛይን ከሰዓሊው፣ ከግለሰቡ የአሰራር ዘይቤ ጋር
ቴአትሩን የመቆጣጠርና የማቀናጀት ዋናውን ኃላፊነት ይዛመዳል፡፡
የሚይዘው የቴአትር አዘጋጁ እንደመሆኑ መጠን የአዘጋጁ
አጠቃላይ አመለካከት በተውኔቱ ይዘትና ቅርጽ እይታዊ የመድረክ ከመድረክ ገጽ ዲዛይን ጐን ለጐን የአልባሳት ዲዛይንም የጐላ
ቅንጅት ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ ስላለው ሰዓሊው ከአዘጋጁ ጋር ድርሻ እያያዘ በመምጣቱ የአልባሳት ዲዛይነር የያንዳንዱን ገጸ
አብሮ መስራት መቻል አለበት፡፡ የአዘጋጆች አይነትም ‹‹እራስህ ባህሪ ውስጣዊ ማንነት በአልባሳቱ እንዲገልጽ የማድረግ ሀላፊነት
እንደ ፈለግህ ስራው› ከሚለው አንስቶ ‹‹እኔ የምፈልገው እንዲህ አለው፡፡ ዘመናዊ የአልባሳት ዲዛይነር አልባሳትን፣ የፀጉር
ነው›› እስከሚለው ይደርሳል፡፡ ከሁሉም ጥሩ ዲዛይን ለማውጣት አሰራር አይነቶችን፣ ዊግን፣ የፊት ገጽታ ቅብና ማስክ ወይም
ግን የሁለቱ፣ የአዘጋጁና ዲዛይነሩ አብሮ መስራት፤ በሁለቱ ጭምብል የመሳሰሉትን ነገሮች በመስራት የገጸ-ባህሪውን የኑሮ
መሀል የግልጽነትና መቻቻል መኖር ዋንኛውን ቦታ ይይዛል፡፡ ሁኔታ፣ በህብረተሰቡ ውስጥ ያለውን የመደብ /ኢኮኖሚያዊ/
የእነሱ ትብብርም የሚጀመረው ከመነጋገርና ከመወያየት ይዞታ በትክክል ማንፀባረቅ መቻል ነው፡፡ በተጨማሪም
ሲሆን ይህም ትብብር የድራማው ባህሪና አጠቃላይ ስሜት የትርዒቱ ታሪክ የተመሰረተበትና የተፈፀመበት ጊዜ፣ ዘመን፣
ምን እንደሚመስል ስለሚረዳ አጠቃላይ ውጤቱ ላይ ከፍተኛ ቦታ፣ ጂኦግራፊያዊ አቀማመጥ፣ የአየር ፀባይ፣ ወቅት /ቀንና
አወንታዊ ተጽዕኖ ይኖረዋል፡፡ ከዳይሬክተሩ ጋር ስለቴአትሩ ማታ/ የመሳሰሉትን ለመግለጽ ከፍተኛ እገዛ ያደርጋል፡፡
መንፈስ ከተወያዩ በኋላ በተሻለ መንገድ የቴአትሩን ይዘት ወደ
እይታዊ ጥበብ ለመቀየር ለመጨረሻ ጊዜ ጽሁፉን ማንበብ ከግሪክ ዘመን ጀምሮ እስከ 19ኛው ክፍለ ዘመን ድረስ
ያሻል፡፡ ይህም ለቴአትሩ በመድረኩ ዝግጅት በኩል ከቴክኒክ አልባሳትን በተመለከተ ተዋንያን እራሳቸው የመሰላቸውን ልብስ
አንፃር ምን መደረግ እንዳለበት ለመወሰንና ወደ ተግባራዊ ይለብሳሉ። አለበለዚያም የመድረክ አስተባባሪው፣ አዘጋጁ ወይም
እንቅስቃሴ ለመሸጋገር ይረዳል፡፡ አልባሽ ሰው፣ ባጠቃላይ ሁሉም የመሰላቸውን ያለብሷቸው
ነበር እንጂ ስለአጠቃላዩ የቴአትር ዝግጅት እይታዊ ውህደት
የመድረክ ዲዛይን ከምንም በላይ ብሔራዊ ቅርጽን ብዙም አይጨነቁም ነበር፤ እውቀቱም አልነበራቸውም፡፡
ያንፀባርቃል፡፡ ለምሳሌ የሮማን፣ የጀርመን፣ የጣሊያን፣
የፈረንሳይ፣ የሩሲያ ወዘተ… የመድረክ ገጽ ስራዎች አቀራረብ በ20ኛው ክፍለ ዘመን የተወሳሰበ የቴአትር መድረክ ዝግጅት
ዘይቤያቸው ይለያያል፡፡ ዋናዎቹ እውነታዊነትና ቴያትራዊነት የአልባሳት ዲዛይን የበለጠ ተቀባይነት እያገኘ መጣ፡፡ አልባሳትን
ናቸው፡፡ እውነታዊነት አብዛኛውን ቦታ የያዘ ሲሆን በዚህ ስልት ዲዛይን የሚያደርግ፣ የሚመርጥና የሚቆጣጠር ከጠቅላላው
የሚሰራ ሰዓሊ አካባቢው እውነትን የተላበሰ ከመሆኑም በላይ ፕሮዳክሽን ጋር መዋሀዱን የሚያረጋግጥ መኖሩ ግድ ሆነ፡፡
የሚሰራው እውነተኛ ቦታ እስከሚመስል ድረስ ማስመሰል እንደመድረክ ገጽ ሰዓሊው ሁሉ የአልባሳት ዲዛይነሩም ከቴአትሩ
አለበት፡፡ ከቴያትራዊነት ስልት የሚጠበቀው ደግሞ የቦታውን አዘጋጅ ጋር በመሆን ገጸ ባህሪያቱ የሚኖሩበትን የቴአትር
ተምሳሌትነት የቴአትሩን ስሜትና ሁኔታ፣ ተፈጥሮን አለም በመፍጠር የደራሲውን ሀሳባዊ እይታ በመጋራትና
ማስመሰልን በመቀነስ በምናባዊና ሀሳባዊ ህይወት መተካት በማገዝ ባህሪያቱ በአልባሳት አማካኝነት ጐልተው እንዲወጡ
ነው፡፡ የልብሱን አይነት፣ ቀለም፣ ሻካራና ልስላሴ፣ ስታይል ላይ
ትኩረት በማድረግ ለአጠቃላዩ የቴአትር ፕሮዳክሽን ማማር
የ20ኛው ክፍለ ዘመን የመድረክ ገጽ ዝግጅት ከተፈጥሯዊው የራሱን ድርሻ ይወጣል፡፡
አቀራረብ ይልቅ ስሜትን (mood) ወደሚያንፀባርቅ ተምሳሌታዊ
ትዕይንት መዛወርና እንቅስቃሴውም ብርሀንና ድምጽን በማጋነን ማስክ ወይም ጭምብል መስራት የቆየ ባህል ያላቸው
ውስጣዊ ስሜት ጐልቶ እንዲወጣ በማድረግ ተመልካችን ህዝቦች ጥበብ ከመሆኑም በላይ ከፍተኛ ምትሀታዊ ሀይል
ይበልጥ የሚያሳትፍ እየሆነ መጥቷል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ እንዳለው ሆኖ ሲታመንበት ቆይቷል፡፡ ማስክ በምዕራቡም ሆነ

ቅፅ-1፣ቁጥር 1 መስከረም 2010 ዓ.ም ገፅ 30


ስነ-ስዕል
ስነ-ስዕል ታዛ

ስእልም ሆነ ቴአትር ሁለቱም


በባህሪያቸው በእይታዊ ጥበብ
ጐራ ውስጥ ስለሚመደቡ
ተመልካችን ይፈልጋሉ፡፡

በምስራቁ አገሮች ቀደም ሲል ጀምሮ የቴአትር አካል እንደነበረ


የተመዘገቡ ብዙ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡ በግሪክ፣ በሮማ፣ በጃፓን፣
በሜክሲኮ፣ በፔሩ፣ በምዕራብና በመካከለኛው አፍሪካ ወዘተ…
በጣም የተለመደ ነበር፡፡

ማስክ የተዋንያኑን ገፅታ በማጉላት ከርቀት እንዲታይ


ሲረዳ ዋና ዋና ስሜቶችን ሐዘን፣ ደስታ፣ ንዴት፣ ጨካኝነት፣
ጀግንነት፣ ደግነት፣ ቀልድ… ወዘተ ለማንጸባረቅ ይረዳል፡፡
ማስክ ለተዋናይ ግርማ ሞገስ በመስጠት ጐልቶ እንዲታይ
ለማድረግ ጉልህ ድርሻ አለው፡፡ በተለይ ማስክ ላይ ብርሀን
ሲበራ ስለሚያንጸባርቅ ብርሃኑ በተቀያየረ ቁጥር የሚሰጠውም
ስሜት ይቀያየራል፡፡ ዛሬ ዛሬ ማስክ ባሰራሩ በጣም የሚመች፣
ጠንካራ፣ ክብደት የሌለው፣ ቀላልና በተፈለገው የተዋናዩ የፊት ገጠር አካባቢ ያለን የተፈጥሮ ትዕይንት የሚወክል የመድረክ ዲዛይን
ቅርፅ ለማንሳት የሚቻል የሚተጣጠፍ እየሆነ መጥቷል፡፡
በቴአትሩ ላይ የሚያስፈልጉ ማስኮችን የሚመርጠውና የይለፍ
በጣም አጓጊ እየሆኑ ነው፡፡ የአርት የቴክኖሎጂ የቅርፃ ቅርፅ፣
ማረጋገጫ የሚሰጠው የአልባሳት ዲዛይነሩ ነው፡፡ በአሁኑ ጊዜ
የሥነ ፅሁፍ፣ የዳንስ፣ የሥነ ሕንፃ ወዘተ… አንዱ ካንዱ
ባደጉ አገሮች የሚገኙ በኮሜርሻል ቴአትር ውስጥ የሚሠሩ
እየተወራረሱና እየተዋሃዱ መሄዳቸው ብቻ ሳይሆን ፈጣን
የአልባሳት ዲዛይነሮች የራሳቸው የዲዛይን ስቱዲዮ ያላቸውና
የሆነው የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ እድገት ሁሉንም ሙያዎች
ለቴአትርና ለሙዚቃዊ ድራማ አልባሳትን ለማቅረብ የተሟላ
እየነካካቸው ስለሆነ ከለውጡም ሆነ ከእድገቱ ተጎጂ ሳይሆን
ድርጅት ያላቸው ናቸው፡፡
ተጠቃሚ ለመሆን መጣጣር የሚያስፈልጋቸው ይመስለኛል -
በመጨረሻም የቴአትር መራቀቅ ብቻ ሣይሆን ኢኮኖሚውም የመድረክ ገፅ ዝግጅትን ጨምሮ፡፡
አላቂና ውድ የሆኑ አሮጌ ቁሳቁሶችን፣ እንደ እንጨት ያሉትንም
በሌሎች ቁሳቁሶች እየቀየራቸው ነው፡፡ በዘመናዊ ቴአትሮች
በኮምፒዩተር የሚታገዙ የብርሀንና የቅንብር ሥርዓቶች

ቅፅ-1፣ቁጥር 1 መስከረም 2010 ዓ.ም ገፅ 31


ታዛ ገፀ-ኅሩያን

ሙዚቃ፣ሙዚቀኛ
እና ተመልካች-
ድሮ

ተስፋዬ ገ/ማርያም
አብሮ የሚያብበው ብዙ ነው፡፡ ሀገር ፍቅሮች አሉ፡፡ የአዲስ
ጊዜው እንዴት ይሮጣል እባካችሁ፡፡ ለዚህች መጣጥፌ አበባ ማዘጋጃ ቤት ተጫዋቾች አሉ፡፡ እነክቡር ዘበኛ፣ ፖሊስና
የማናግረው ሰው ሳውጠነጥን መጀመሪያ የኢትዮጵያ ቴአትር ምድር ጦር ተደብቀው ቆይተው ድንገት ሲቪል ጥበበኛውን
ቤተመዛግብት የሆኑት ጌታቸው ደባልቄ ታሰቡኝ፡፡ ሌላ አንጋፋ ጉድ ሊያደርጉት ይችላሉ፡፡ ከነዚህ ሁሉ የበታች ሆኖ የሚገኝ
ስዳስስ ደግሞ አልጋነሽ ታሪኩ በአይምሮዬ መጣች፡፡ ከሁለቱ ወዮለት፡፡ በጋዜጠኞች፣ በሀያሲዎች እና በአንዳንድ ሀሳብ
ወረድ ያለ አንጋፋ ስፈልግ ደግሞ ራሴን አገኘሁት፡፡ እውነትም ወርዋሪዎች ይተገተጋል፡፡ ልምምዱ ውድድር ማሸነፍ ብቻ
አልጋነሽን ሳወራት ለአንዳንድ ጉዳዮች “ያው አንተም ታውቃለህ” ሳይሆን ከሙጢዎች ለመዳንም ነው፡፡ ላብ ደም ያድናል እንዲሉ
እያለች ዋቢ እያደረገችኝ ነበር፡፡ እርግጥ ነው የዘመን መለወጫ ወታደሮቹ አርቲስቶቹም ላብ ከከፋ ትችት ያድናል ይላሉ፡፡
የሙዚቃ ትርኢት መጣ መጣ ሲባል በብሄራዊ ቴአትር
የነበረውን ሽርጉድ አስታውሰዋለሁ፡፡ ስለዚህም ግምገማ ከባድ የሆነ ሚና ተጎናጽፏል፡፡ ከግምገማ
በኋላ አሰልጣኞች ከከፋቸው፣ “ምነው ልጆች እንዲህ ነበር
ሽርጉዱ ብዙውን ጊዜ በሰኔ አጋማሽ ይጀመራል:: ከዚህ የሰራነው?” ካሉ ወይ ፊታቸውን ካጠቆሩ ልምምዱ በቀን
ጊዜ ጀምሮ እስከ መስከረም መጨረሻ ድረስ የእረፍት ጥያቄ ሳይወሰን በምሽትም ይካሄዳል፡፡
የሚያነሳ ሙዚቀኛ፣ ተወዛዋዥና ድምጻዊ እንደ ጤነኛ
አይታይም፡፡ ቢጠይቅም ሲያምረው ይቀራል’ንጂ የሚፈቅድለት የዘመን መለወጫ የሙዚቃ ድግስ የሚጀምረው በመስከረም
አያገኝም፡፡ የሚተርፈው ነገር ‘ፈቃድ ጠየቀ’ ተብሎ መዘባበቻ አንድ ዋዜማ ነው፡፡ በዚህ ጊዜ ትርኢቱን ብቻ ሳይሆን
መሆን ብቻ ነው፡፡ አርቲስቶቹን ማየትም ያስደስታል፡፡ ሁሉም የክቱን ይለብሳል፡፡
ተመልካቹም ቢሆን በጊዜው ፋሽን ፏ ብሎ ነው የሚመጣው፡፡
ግቢውን አንዳች መንፈስ የወረረው ይመስላል፡፡
በየጥጉ ዜማና ግጥም የሚሞክሩ፣ ሀሳብ የሚለዋወጡ፣ አዳራሾች ተንቆጥቁጠው እንግዶቻቸውን ያስተናግዳሉ፡፡
የሚጨቃጨቁ፣ የሚያንጎራጉሩ፣ ብቻቸውን የሚያወሩ ያ ለወራት የተለፋበት የሙዚቃ ድግስም እነሆ ለህዝቡ ይቀርባል፡
(ማሪያም ታጫውታቸዋለች ይባላል) ይታያሉ፡፡ የግጥም፣ ፡ ጭብጨባው ሊጎርፍ ይችላል፡፡ አድናቂ ተደናቂን በጓሮ በር
የዜማ፣ የአቀናባሪ ለማኝ ሲሯሯጥ ይውላል፡፡ እይልኝ፣ ጠብቆ ያስፈርማል፡፡ አሁን አንድ ነገር ብቻ ይቀራል፡፡ ጋዜጦች
ስማልኝ፣ ሞክርልኝ፣ አርምልኝ ነው የሰኔ ግርግር:: ምን ብለው ጽፈው ይሆን? ጳውሎስ ኞኞ ምን ይለን ይሆን?
ብርሀኑ ዘርይሁንን ሲገባ ያየው አለ? ሙሉጌታ ሉሌስ አብሮት
ሀምሌና ነሀሴ ዋናው ልምምድ ይጦፋል፡፡ ግር ብለው ነበር? … የጨነቀው ዘፋኝ የሚያንሾካሹከው ነው፡፡ ለእኔ የተለየ
የሚገቡ ሙዚቀኞች እና ተወዛዋዦች የሚታዩበት ጊዜ ነው፡ ስሜት ወደ ሰጠኝ ወደ 1958 ዓ.ም. የዘመን መለወጫ የሙዚቃ
፡ ሌሊት ይገባል ምሽት ይወጣል፡፡ የአልባሳት እና የትእይንት ድግስ ድህረ ትርኢት የጋዜጣ ሂስ ልውሰዳችሁ፡፡ ምናልባት
ዲዛይኖች ይዘጋጃሉ፡፡ ስለቀለም፣ ስለቅርጽ፣ ስለሀርመኒ ነው ስለቀደሙት አመታት በጭንቁርም ቢሆን ያሳየን ይሆናል፡፡
ወሬው ሁሉ፡፡ ግዢ ላይ ርብርብ ይጀመራል፡፡ መሰዳደብ፣
መጣላት፣ መካሰስ ይበዛል - በክረምት:: ትላንት ምሽት ዱላ “ከጥቂት አመታት ወዲህ በየአመቱ በተውጣጡ ቡድኖች
ቀረሽ ተሰዳድበው የነበሩ ሙዚቀኞች ዛሬ ጠዋት አፍ ለአፍ የሚቀርበው የሙዚቃ ዝግጅት እንደመጠጡና እርዱ የዘመን
ገጥመው ስለመስከረም የሚያልሙትን ማየት የክረምቱ ወግ መለወጫ በአል አንድ ዋና ክፍል ሆኖ ቆይቶ ነበር፡፡ አዝማሪ
ነበር:: በአገራችን ቀድሞም የነበረ መሆኑ ቢታወቅም፤ የዘመናዊ
ሙዚቃን ስሜት ካራገቡት ምክንያቶች ዋናው የዘመን
ፀጉረ ልውጥ በግቢው ከታየ ለአርቲስቶቹ ከአንዱ የኪነጥበብ መለወጫው የሙዚቃ በአል ነው ሊባል ይችላል፡፡”
ቡድን ተልኮ የመጣ የጥበብ ሌባ ነው፡፡ የሚያንጎራጉር ድምጹን
ይቀንሳል፡፡ ተወዛዋዦች እንቅስቃሴ ይቀይራሉ (የድሮውን በመስከረም ወር የመጀመሪያው የአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ
ነው የምንሰራው ለማለት):: “ማነህ? ማን አስገባህ? ለምን በብርሀኑ ዘርይሁን የሰፈረ ርእሰ አንቀፅ ነው፡፡ እንደኔ እንደኔ
መጣህ? ልምምድ አካባቢ እንዳትደርስ” የሚሉ ጥያቄዎችና ይህ የዘመን መለወጫ የሙዚቃ ትርኢት መጀመሩ ለዘመናዊት
ማስጠንቀቂያዎች ይጎርፉለታል፡፡ አልባሳት ይኮረጃሉ ተብሎ ኢትዮጵያ የሙዚቃ እድገት ገናና የሆነ ቦታ አለው ባይ ነኝ፡፡
የሚፈራው ግምገማ ላይ ነው፡፡ እዚህም ላይ ቢሆን ስጋቱ ይኸው ዛሬም ትላልቆቹ የሙዚቃ ድግሶች የሚጦፉት የዘመን
ከፍ ካለ በናሙና ወይ ደግሞ ቀድሞ በሚታወቅ ልብስ መለወጫን ምክንያት አድርገው ነው፡፡ እና መልካም ውርስ ነው
ያስገመግሙታል፡፡ ይሄ፡፡

ይህ ሁሉ ጭንቀትና ውጥረት በልጦ ለመገኘት ነው፡፡ በ1958 ዓ.ም. የአዲስ አበባ ማዘጋጃ ቴአትር ቤት የመግቢያ
መስከረም ሲገባ እንደአደይ አበባ ከየአካባቢው አደይ አበባ ጋር ዋጋ ጨምሮ ነበር፡፡ 15 ብር አደረገው:: አርቲስቶች አንዳንድ

ቅፅ-1፣ቁጥር 1 መስከረም 2010 ዓ.ም ገፅ 32


ገፀ-ኅሩያን ታዛ

ስሞታ ከሙዚቃዎቻቸው ጋር ቀላቀሉ፡፡ የዘመኑ ፖለቲካም ጥሩ ወምበር እገዛ ነበር፡፡”


በዘፈኖች ውስጥ ገብቶ ነበር:: እኔም የዚህ ዘመን ሀያሲዎች
ትኩረቴን ስለሳቡት ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ የቃረምኩትን በዚህ የመልካም መስተንግዶ እጥረት ላይ ያማረረች ሴት ዝቅ
ላካፍላችሁ፡፡ ከኛው ዘመን ጋር ታነጻጽሩታላችሁ:: ብላ ስለትርኢቱ ደግሞ እንዲህ ብላለች፡፡

የዘመኑ ሀያሲ ለሙዚቃ ካለው ፍቅር ይጀምራል ትችቱን፡፡ “…. ጨዋታው እንደሌላው ቀን የሞቀ አልነበረም፡፡ ከአሁን
አንድ ሁለቱን እነሆ: አሁን ይሻል ይሆን እያልኩ ስጠባበቅ ቆየሁ፡፡ ሆኖም ምንም
የተለወጠ ነገር አልነበረም፡፡ ብዙነሽ በቀለ ዘፈነች፡፡ …ከዘፈኗ
“ሙዚቃ ከመጠን በላይ እወዳለሁ፡፡ ስለሙዚቃ ያለኝ ፍቅር ይልቅ በልብሷ አደነኳት፡፡ ውብ የሆኑ ልብሶች ለብሳ ነበር፡
ይህ ነው አይባልም፡፡ ስለዚህም የሙዚቃ ድግስ አልፎኝ ፡ ጥላሁን መጣ …ግን የድሮው ጥላሁን አልነበረም፡፡ ፈገግታ
አያውቅም፡፡” ወ/ት ፍስሀ ደምሴ የተባለች ታዳሚ አያሳይም፡፡ ያን ደስ የሚለውን ንቅናቄ አላሳየም… ጓደኛዬን
ጠየኳት፡፡ ምነው እንዲህ ሆነ? አልኳት ኮርቶ ይሆናል አለችኝ፡፡
“እኔ ከሙዚቃ አፍቃሪዎች አንዱ ነኝ፡፡ ሙዚቃንም ከመውደዴ እሱነቱ የታወቀው በምን ሆነና ነው የሚኮራው? አልኩ በሆዴ::
የተነሳ ከዚህ በፊት በአገራችን ሙዚቀኞች የተዘፈኑትን ዘፈኖች
አርእስታቸውን ብቻ በመስማት ዜማቸውን እንዲህ ነው ብዬ አንድ ላጣራው ያልቻልኩት ጉዳይ ገጥሞኛል፡፡ በ1958
ለሚጠይቀኝ ሰው የማጉረምረም ያህል አንጎራጉራለሁ፡፡ ሆኖም ዓ.ም. አንዱ ጎልቶ የታየው ነገር የአርቲስቶች ብሶት ነው፡
ድምጼ ለሰሚ አያስደስትም፡፡” ሌላ ጸሀፊ ፡ ብሶታቸውን ሲገልፁም “ህዝቡ ሙዚቃ አያውቅም” የሚል
ነገር አስተጋብተው ነበር፡፡ ታዲያ እኔ ላጣራው ያልቻልኩት
በዚህ አመት ሙዚቃ አፍቃሪው ከዘፋኞች ጋር የተቀያየመ ይህን ሀሳባቸውን ያስተላለፉት በዘፈን ወይም በንግግር መሆን
ይመስላል፡፡ አንዳንድ ትችቶች ከዱላ የሚተናነሱ አይደሉም፡፡ አለመሆኑን ነው፡፡ በዚህ ሀሳባቸው ግን እውቁ ጋዜጠኛና
የታሪክ ሰው ጳውሎስ ኞኞ “ህዝቡ ሙዚቃ አያውቅም?” በሚል
ብርሀኑ ዘርይሁን በአመቱ መጀመሪያ ላይ “ያልነበረው ርእስ ደብድቧቸው ነበር፡፡ ሌሎችም የሱን ፈለግ ተከትለው
የሙዚቃ በዓል” ብሎ በጻፈው ርእሰ አንቀጽ እንዲህ ይላል:: ወረዱባቸው፡፡ አንዱ እንዲህ አለ፡፡

“በአንድ ምሽት የዓመት ደስታን የምገበይ መስሎኝ ነበር፡፡ “… እነጥላሁን ማንን አይተው ነው ህዝቡ ሙዚቃ አይወድም
ግን በአንድ ምሽት የዓመት በሽታ ገዛሁ” ይህን ያለው አራት የሚሉት? ለመሆኑ እነሱ የሙዚቃ ስሜት አድሮባቸዋል ወይስ
ቤተሰቡን ይዞ በአንዱ ቴአትር ቤት የዘመን መለወጫ ዋዜማን ሳይወዱ ይጮሀሉ? የኛ ዘፋኞች እኮ ሳይወዱ የገፍ ያህል
ምሽት አሳልፎ የተበሳጨ ሰው … ነው” ይላል ብርሀኑ:: ቀጠል ይጮሀሉ? የኛ ዘፋኞች እኮ ለተመለከታቸው ከኋላቸው አለንጋ
አድርጎም “ለዘመን መለወጫ ምሽት በልደት አዳራሽም ሆነ የተያዘባቸው ይመስላል፡፡”
በአዲስ አበባ ከተማ አዳራሽ የተገኘ አብዛኛው የሚስማማበት
እውነት ነው::” ሲል አክሏል፡፡ ዘፋኞች ስለመብታቸውም አንስተው ነበረ መሰለኝ፡፡ ወይ
በሙዚቃ ወይ በዲስኩር፡፡ ብቻ ብዙ ሰዎችን አስቆጥቷል::
ሌላዋ ከሳምንት በፊት የመግቢያ ቲኬት በ15 ብር የገዛች
ተመልካች “15 ብር ከፍሎ ያለ ወምበር” በሚል ርእስ ስር “ሙዚቀኞቻችን መብታችን ተወሰደ ብለው ላጉረመረሙት
እንዲህ ብላለች፡፡ አቶ ጳውሎስ ኞኞ ተገቢውን መልስ ሰጥተዋል፡፡ እንደሌላ አገር
ሙዚቀኞች ባለፔዦዎችና ባለመርቸዲስ ሊሆኑ ፈልገዋል፡፡ እኛ
“ ከምሽቱ አንድ ሰአት ላይ ማዘጋጃ ቤት ደረስኩ ፡፡ አዳራሹ መች ከለከልናቸው?” አሉ ጳውሎስ ኞኞ፡፡ እውነታቸውን ነው
ከአፍ እስከገደፉ ጢቅ ብሏል፡፡ እንኳን መቀመጫ መቆሚያ … ህዝቡ በየጊዜው የሚያሰሙትን አዲስም ሆነ አሮጌ ዜማዎች
መፈናፈኛ የለም፡፡ ያላሰብኩት ያልጠረጠርኩት ጉድ ስለገጠመኝ ለማዳመጥ ወደአዳራሻቸው ሲገባ እየከፈለ ነው፡፡ ሊጫወቱ
ክው ብዬ ቀረሁ፡፡ አንዳንድ ጊዜ አውቶቡስ ላይ እንደሚደረገው ሲመጡም ሆነ ሲጨርሱ እጃቸው እስኪነፈርቅ ያጨበጭባሉ
ሴት ናት እንነሳላት የሚል አልተገኘም፡፡ እንኳን ተነስቶ …”
ተቀመጪ የሚለኝ ዘወር ብሎ የሚመለከተኝ አልተገኘም፡፡
እኔም በነሱ አልፈርድም፡፡ እንደኔው 15 ብር ከፍለው የገቡ በ1958 እና ከዛ በፊት በነበረው አመት ኢትዮጵያ ከሶማሌ
ናቸው…አንድ መልኩን እንጂ ስሙን የማላስታውሰው ሰው ጋር የተጣላችበትና በየጋዜጣው ሱማሌዎችን የሚያሳንስ
አንድ በጣም ያረጀ ወምበር አምጥቶ እዚህች ላይ አረፍ በይ እኛን ደግሞ ከፍ ከፍ የሚያደርግ መጣጥፍና ካርቱን ስእሎች
አለኝ፡፡ ደክሞኝ ነበረና ወንበሯ ተመቻችታ ሳትቀመጥ ዘርፈጥ በየጋዜጣው የሚበዙበት ጊዜ ነበር፡፡ ይኸው አልበገርም
አልኩባት፡፡ ቃ ቃ አለችና ይዛኝ ጉልስስ አለች… በ15 ብር 2 ባይነት ወደመድረኩ ተዛምቶ የእንቁጣጣሽ ዘፈኖች መካከል

ቅፅ-1፣ቁጥር 1 መስከረም 2010 ዓ.ም ገፅ 33


ታዛ
ዘባሪቆም
ፉከራና ቀረርቶ ተሸንቁሮ ነበር፡፡ አንዳንድ ተቺዎች ግን
አልወደዱትም፡፡ አንዱ እንዲህ ከትቧል፡፡

“… ደግሞ የዚህ ሁሉ ጉድ ሲገርመን ፖለቲካ


መፈትፈቱ … ዘራፍ ዘራፍ ሽርጣም ገዳይ …. ሽርጥ
የሚለብስ ስንት ኢትዮጵያዊ አለ፤ በልደት አዳራሽ እንኳ
ከተቀመጡት ስንቱ ያሸረጠ ነው፡፡ ታዲያስ አገዳደሉ
እነዚህን ጨምሮ ነው?”

ይህ ፀሀፊ ሌላም ያልጣመው ነገር ነበር፡፡ ብዙነሽ ፊደል እሸቱ


በዚህ አመት “ከረሜላዬ ነህ” በሚል ዘፈን ነበር መድረክ
የወጣችው:: በዚህ ያኮረፈው ሀያሲ ትችቱን በምፀት
አዋዝቶ ጋዜጣው ላይ አስፍሯል፡፡

“ብዙነሽ…ከረሜላ ነህ እያለች የምትወደውን ሰውዬ


ስታጣጥም ሰነበተች፡፡ በዚህ አኳኋን ከቀጠለ ወንድ ባሜሪካ ቆይታዬ ካፈራኋቸው ወዳጆቼ መካከል ከፊሎቹ
አድናቂ፤ አሞጋሽ ... ሴት ተደናቂ፤ ተሞጋሽ መሆኗ ደባሎቼ (ሩ‘ሜቶቼ) ናቸው። ለዛሬ ስለ ደባል በተነሳ
ሊቀር ነው፡፡ የወንድ መልክና ገላ የሚሞገስበት ዘመን ቁጥር ሁሌም ከማወሳቸው መካከል ተርጓሚው፣
1958 ዓ/ም መጣ፡፡ ለዚህ ይሆን ዘንድሮ የቁንጅና ውድድር
የወደቀው? እንዲህ ከሆነ ለ1959 ዓ/ም የወንዶች ቁንጅና ሰብስቤ፣መንግስትና አሰጌን ልዘክር ወደድኩ።
ውድድር እንዳይወድቅ ከአሁኑ ይታሰብበት፡፡”

1958 ዓ.ም. በሙዚቀኞቻችን በተለይም ደግሞ


ተርጓሚው፡-
በዘፋኞቻችን ላይ ከባድ ትችት የተሰነዘረበት አመት
ይመስለኛል፡፡ ዘፋኞቻችን ለዚህ የተዳረጉት ዝግጅታቸው የመጀመሪያው ደባሌ “ተርጓሚው” በሚል ቅፅል ስሙ
ከወትሮው የተለየ እና የወረደ ሆኖ ሳይሆን “ህዝቡ ሙዚቃ ይታወቃል። እንግሊዝኛ ወይም ሌላ ቋንቋ ሳይሆን ገንዘብ
አያውቅም” ብለው በአደባባይ በመዳፈራቸው ተመልካቹ የመተርጎም ስራ የተጠናወተው ወጣት ነው። የአሜሪካን
ተቆጥቶ ነው፡፡ ምን መልካም ቢሰሩ ህዝብን ማክበር ዶላር ወደ ኢትዮጵያ ብር በኛ በደባሎቹ አባባል ይተረጉማል።
ይገባል፡፡ ለሚናገሩት ነገርም ማስተዋል ያሻል፡፡ አለበለዚያ “ወይ ጉድ አንድ ቡና በ80 ብር የምንጠጣበት አገር?” ይላል
ለህዝብ ቁጣ መጋለጥን ያመጣል፡፡ አንዳንዶቹ ትችቶች አንዱን ቀን። ያንድ ጥብስ ዋጋ ከማወራረጃና ቲፑ ጋር ከፍሎ
እጅግ በከፋ ሁኔታ ስለተጻፉ መድገሙ አልተመቸንም፡፡ ከመጣ ደግሞ “አቤት ዛሬ የበላሁት የ360 ብር እራት!” እያለ
ይሁንና ወደ ደጋፊዎች ደግሞ ላሸጋግራችሁ፡፡ ከዚህ እንቅልፍ ይነሳናል። የምንከፍለውን የቤት ኪራይ በብላክ
የሚለጥቀው በዘንድሮ ቋንቋ “የገባው” የሚባል አይነት
ነው:: ማርኬት ተርጉሞ ሲናገር የማይሸበር ተከራይ አልነበረም።
ከዕለታት ባንዱ ከተርጓሚው ጋር ነዳጅ ለመቅዳት የቆምንበት
“(እነ ጳውሎስ ኞኞ) ጥላሁን “ሙዚቀኞች በርቱ ማህበር ቦታ የሚጠጣ ነገር ለማንሳት ገባን። ሁለት ለስላሳ መጠጦች
እናቋቁም” ብሎ ስለዘፈነ አፈርኩ ብለዋል፡፡ የዜማና የግጥም ይዘን ገንዘብ ተቀባዩ ጋ እንደቆምን ተርጓሚው “Here you go,
ደራሲዎች የደከሙበትን የሙዚቃ አዋቂዎች የቀመሩትን this is 94 Ethiopian birr” (ሂድ እንግዲህ! 94 የኢትዮጵያ
ዜማ አላግባብ በመዝረፍ ሲቸረችሩ የኖሩት ዘራፊዎች ብር!) ሲል በረድፍ በቆሙ ገቢያተኞች ፊት አሸማቀቀኝ። ሻጩ
ግድብ እንዲበጅላቸው በህብረት ማህበር በማቋቋም ህንዳዊ ደግሞ ቀበል አድርጎ “ዳቲስ ጎን ቢ 240 ሩፒ ኢን
ጥቅማችንን እንጠብቅ ብሎ ሙዚቀኞችን መቀስቀሱ ማይ ካንትሪ በዲ” (ወዳጄ፣ በእኔ ሃገር ደግሞ 240 ሩጲ ነው)
የሚያሳፍር መስሎ ከታየዎት አሁንም ደግመው ይፈሩ
እንጂ የታሰበው እንደማይቀር ይመኑ፡፡ ጥሩ ዝና ያላቸው በማለት አፅናንቶ ሸኘኝ። ከልብስና ጫማ እስከ ሹካና ማንኪያ
ሙዚቀኞች በህብረት ማህበር ካቋቋሙ መልካም ጥቅም በብር አስልቶ የሚሸምተው ተርጓሚ የገዛ ደሞዙን ብቻ በዶላር
እንደሚያገኙ የታመነ ነው፡፡ ያሰላል። ተርጓሚውን የማውቀው ዶላር 12 ብር ሳለ ነበር።
ዛሬ ዶላር 23 ብር ሲገባ እሱ የት እንደገባ አላውቅም።
ይህ የሙዚቃ አድናቂና ተቆርቋሪ በጊዜው የነበሩትን
ኦርኬስትራዎች አወዳድሷቸዋል፡፡
ሰብስቤ፡-
“የራስ ባንድ የሙዚቃ ክፍል በብዙ የውጪ ሀገር
ሰዎች የተደነቁ የሙዚቃ ተጫዋቾች የሚገኙበት ክፍል ተርጓሚውን ሳስብ አብሮ ‘ሚታወሰኝ ሌላው ደባሌ ሰብስቤ
ነው፡፡ የክብር ዘበኛ የሙዚቃ ጓዶች በሙዚቃ ቲዎሪ ነው። ቤሳ ቤስቲን የማይጥል፣ ከግሮሰሪ ፌስታል እስከ ወተት
የበለጸጉ በመሆናቸው ያኮሩናል፡፡ የቀዳማዊ ኃይለስላሴ ላስቲክ የሚንከባከብ፣ ከቢራው በላይ ጠርሙሱ የሚያሳሳው
ቴያትር የሙዚቃ ጓድ ለዛ ባለው ጨዋታው የገነነ ስም ቁራሌው ቢጤ! ሰብስቤ እጅ የገባ የወረቀት ሳህንና ኩባያ
ያለው ነው፡፡ የፖሊስ ሠራዊት የሲንፎኒ ኦርኬስትራ ጭምር “ዩዝ ኤንድ ስሮው” መሆኑ ቀርቶ “ዩዝ ኤንድ ሪዩዝ”
በአፍሪካ የመጀመሪያው ነው፡፡ ተነቃናቂው የምድር ጦር
ኦርኬስትራ ቅልጥፍናው የሚያስመሰግነው ነው፡፡” ሆኖ ይቀጥላል። በዚህ መሰረት በማንኛውም አጋጣሚ ወደ
ቤታችን የገባ “ቱጎ ቦክስ” ወደ ቋሚ የቤት ቁስነት ተቀይሮ
ዛሬ ላይ ቆመን 1958ን ስንመለከት ያኔ ተነስቶ በምሳ ዕቃነት ያገለግላል። ቤት አልባ ችግረኛ ከማየት
የነበረው ‘እንተባበርና ለመብታችን እንቁም’ የሚለው በላይ መንገድ ላይ የተጣለ ሶፋ፣ ኮምፒውተርና ቴሌቪዥን
የነጥላሁን ጥያቄ ዛሬም ከጥያቄ በወጉ የዘለለ አይደለም፡፡ አንጀቱን የሚበላው ሰብስቤ ካለው ሁሉ ስስት በፈረንጅ ለማኝ
እኔ በዚያ ዘመን ሙዚቀኞች ስራዎቻቸውን ለህዝብ አይጨክንም። ሽራፊ ሳንቲምም ቢሆን መፅውቶ ከለማኙ
ከማቅረባቸው በፊት ለልምምድ የሚሰጡት ትኩረት ዘመን በላይ ፈጣሪን የሚያመሰግነው ግን ራሱ ነው። ካንድም ሁለቴ
ተሻጋሪ የጥበብ ውጤቶችን ለተከታዮቻቸው እንዲያወርሱ ለፈረንጅ ሳንቲም ሲሰጥ ፎቶ እንዳነሳው ጠይቆኝ ባግራሞት
ምክንያት ሆኗቸዋል እላለሁ፡፡ ለብለብ ያኔ የሚታወቅ
ምግብ አልነበረም፡፡ ደግሞ ብእሩን ስሎ የሚጠብቀው አልፌዋለሁኝ። ከጊዜ በኋላ ግን ይህ ስሜቱ ለሚከተለው
ሀያሲም ዋዛ አልነበረም፡፡ ግጥሜ መነሻ ሆነኝ።

ደህና እንሰንብት::

ቅፅ-1፣ቁጥር 1 መስከረም 2010 ዓ.ም ገፅ 34


ታዛ
ዘባሪቆም

ከደባሎቼ ማስታወሻ
የፈረንጅ ለማኝ መንግስት፡-
ልዩ ፍጥር እንግዳ- ሌላኛው ደባሌ መንግስት ይባላል። መንግስትን አምሮ የሚተች
ቢግ ታይምና ፉል ታይም ተቃዋሚ ነው። ፍሪጅ ውስጥ ያኖረው
ላይኔ ብርቅ ሆኖብኝ ያኔ ልጅ እያለሁ፣ ምግብ ጎድሎ ቢያገኝ እንኳ ከኛ ሩሜቶቹ ቀድሞ መንግስትን
ባለፈበት ሁሉ- የሚጠረጥር ወፈፌ!
እግሬ እስከሚቀጥን ተከትየዋለሁ። ከጥቂት ዓመታት በፊት ደብዛው በጠፋው የማሌዢያ አውሮፕላን
ከኩዮቼ ጋራ ስሙን እየጠራን፣ ላይ “የኢትዮጵያ መንግስት እጅ ያለበት አይመስለኝም” የሚል
አስተያዬት በመስጠቴ በደጋፊነት አግልሎኛል። አንድ ምሽት
ሰላምታ ልንሰጠው በቋንቋው ቢያወራን፣ ቤት ውስጥ የኢቦላ ወሬ ተነሳ። ወረርሽኑ ወደ አገራችን
አይና‘ይኑን ስናየው ዙሪያውን አጅበን፣ እንዳይገባ ሁሉም ስጋቱን ሲገልፅ ቆይቶ የመንግስት ተራ ደረሰ።
እንደተለመደው መንግስት በሽታውን ለመከላከል ምንም ጥረት
በመገረም ይሁን ወይ እየሰደበን፣
አላደረገም ይላል ብለን ስንጠብቅ “ኢቦላ እንዳይገባ አላችሁ?”
ያነሳን ነበረ ፎቶ እየታዘበን። በማለት ጀመረ። “ኢቦላ ኢትዮጵያ ከገባ ሃያ ስንት አመት ሆነው?”
ይሄው ዛሬ አድጌ- ሲል እርስ በርስ ተያይተን ወደየክፍላችን ተበታተን።

በሰማይ አርጌ ባህር ተሸግሬ መጥቼ ከሱ አገር፣


አሁን በቀደም ’ለት-
አሰጌ፡-
ወደ ስራ ስሄድ ያስቆመኝ መብራት ላይ ካስፓልቱ ባሻገር፣ የመጨረሻው ደባሌ አሰጌ ሲሆን ቅጥያ ስሙን የወረሰው ካዛውንቱ
ሴት አዳኝ ፊታውራሪ አሰጌ ነው። ሴቶች ከጠቅላላው የአለም
አንድ ጉስቁል ያለ- ህዝብ የላቀውን ድርሻ ቢይዙም 80 በመቶ ያህሉ በ20% ወንዶች
የኔ ቢጤ ፈረንጅ ኩርምት ብሎ ቆሟል፣ ቁጥጥር ስር መሆናቸው አሳዛኝ እውነት ነው። ምክንያቱን ደግሞ
ሀብት፣ ዝና፣ አካላዊ መስህብ ወዘተ እያሉ መዘርዘር ይቻላል።
“ቤት የሌለኝ ድሀ እርዳኝ” የሚል ትልቅ ካርቱን ተሸክሟል፣
ደባሌ አሰጌ በሀብቱ የከበረ፣ በምግባሩ የታፈረ፣ በሰውነቱ የዳበረና
እኔስ ምኔ ሞኜ፣ በመልኩም ያማረ ሳይሆን ከነዚህ የሄዋን ባለ ፀጎች ተራ ለመሰለፍ
ይሄዋ ተገኜ፣ መብቃቱ ለኔና መላ ሩ‘ሜቱ ጭምር ክብርና ኩራት ነው። እድሜ
ለሱ ቤታችንን የማትወድ ሴት፣ የማያውደው ሽቶ አልነበረም።
“ርሀብተኛ” ብሎ ዘሬን የሚጠራው፣
እጄ ላይ ሲወድቅ ሲማፀን በተራው፣ አሰጌ ከስራ ወደ ቤቱ በመግባት ላይ በነበረበት አንድ ምሽት
የጎረቤት ለቅሶ ለመድረስ ከመጣች አንዲት እንስት ጋር ተገናኘ።
እኮ እኔ ቀብራራው ስንት ያደረገኝን የሰራኝን ሳውቀው፣ እቃዋን ተሸክሞ ቤታችን ድረስ ሲያስገባት ያላትን ለመስማት
“እግዜር ይስጥህ” ብየ ደሞ ልመርቀው? አልታደልኩም። ቤት ከገባች በኋላ እጇን አፏ ላይ ጭና
በዝምታ ቁጭ አለች። በቤቱ ሌላኛው ጥግ ባለውና እንደ አልጋ
“ና ልስጥህ ራሴ፣
በምንጠቀምበት ሶፋ ላይ ተሸፋፍኜ አስገራሚውን ትዕይንት
ከሞላው ከኪሴ፣ በድብቅ ስከታተል “እኔ ምልህ? አለች ልጅት “ለቅሶ ቤቱ ግን
የወገኔን ፋንታ ሁሉን ጨማምሬ፣ ይሄ ነው እንዴ” ስትል ሳቄን ታግዬ አቆምኩት። “well” አለ አሰጌ
ከሴት ጋር ሲያወራ እንደሚያደርገው እንግሊዝኛውን ደብለቅ
ተቀበል ምፅዋቴን ስለምዬ አገሬ፣ እያደረገ “to be honest ለቅሶው next door ነው። እዚያ ጥግ
ስለ ወለላይቱ ስለ አይጠና አንጀቷ፣ የምታይው ወንድም ግን ደርሷል። ብዙ እድሜ የለውም።” አላት
ወደተኛሁበት እያመላከተ። በብስጭት ያመጣችውን ዕቃ መጎተት
ሰው ጥላ ማትበላ ካለ ከማጀቷ፣ ስትጀምር እግሯ ላይ ተወርውሮ ወደቀ፡-
እንካ ተቀበለኝ፣
“በወንድ ልጅ አምላክ በቁም እያሉ መረዳዳት ይሻላል! ላንድ ሳጥን
ስለ አዛኟ በለኝ ስለ ወላዲቱ፣ ውሃና ለስላሳ የግድ መሞት አለብን?” እያለ መማፀን ሲጀምር
በፃድቃን ሰማእታት ባርባራት ታቦቱ፣ ለጎረቤት ለቅሶ የቋጠረችውን እምባ እኛ ቤት በሳቅ ዘራችው።
ተራዳኝ በለኛ- በዚህ ሁኔታ ውሃና ለስላሳው ብቻ ሳይሆን እሷ ጭምር የአሰጌ
ሆና ቆየች።
“ኩርማን የተቸገርኩ የራበኝ የጠማኝ”
በሱ አይደል የሚኖር-
ስሜን እያጠፋ ዘር ማንዘርህ ሲያማኝ፤
“ምን ይመስላል? ለማኝ!”

ቅፅ-1፣ቁጥር 1 መስከረም 2010 ዓ.ም ገፅ 35


ታዛ
የቅኔ ብራና

እናም ወጣት ዮፍታሄ ብሄርተኛ

ዮፍታሄ
ከፍትጉ
ባለቅኔ ስደተኛ
መዝሙሩ ይሰማናል

ለቀኝ ጌታ ዮፍታሄ ንጉሤ ፊደሉ ይጠራናል


ቀለሙ ይታየናል
ኪነቱ ይገፋናል።
የእሱ ፀረ ፋሺስትም ግጥሞች
የቃል የሆሄ ፍሞች
የግጥም ስዕል፣ ገድሎች
የኪነት ትግል ድሎች . . . . . .
የእናት ሃገሩ ዋይታ
የእመ ብሔሩ ሆታ
የወገኑ ግፍ ሰቆቃ
የከተማ - የገጠሩ የወንድ የሴት እንባ ሲቃ
የሰቀቀን፣ የብስጭት፣ የበቀል የጀግንነትም
የአመፃ ስሜት ውልዱ፣
“እመቤቴ ተመለሺው . . . . .
ድንግል ሃገሬ” ጥሪው
የግጥም ቋጥኝ አምዱ
ያው ከብዙው አንዱ።
ከጊዜው ጋር ይቀረፃል፤ በታሪክም ይታደሳል
ትንሳኤው በእጃችን ነው በብዕርም ይፈወሳል
ይወረሳል።
እናም ወጣት ዮፍታሄ - ያ የጠዋት ግጥም ወፍ
ለካስ ሞት ታሪክን ገድሎ የወራሪዎች ጥንብ ሴራ - የፋሺስት አመፅ ሲጦፍ
ትዝታን በጊዜ ጨርቅ፣ በዘመን ሸማው አዝሎ በቅኔ ድምፁ ጩኸት
ፊደልን በጎርፍ አይቦ፣ ቃልን ከስሩ ነቅሎ በግጥሙ ልሳን ዋይታ
ኪነትን በእንድድ ጨምቆ፣ ቅኔን በእሳት ቀቅሎ በብዕሩም ኪነት መዳፍ
የብዕር ደምን ፍሬ፣ ግጥምን ከትቢያ ጥሎ የእናቱን እንባ ጠርጎ - የአንጀት ቁስሏን በመዳሰስ
የሕዝብ ሕይወት ነፀብራቅን መድሃኒቷን ነፃነትን፣
የመደቦችን ፍልሚያ፣ የእድገት ትግልንም ሃቅን በኪነቱ ሲደፈድፍ
የሕብረሰብን መስታዎትን በግጥሞቹ ሲያሰናዳ
ስነ-ጽሁፍ ስነ-ስዕል ቅርጻ ቅርጽን፣ ደም ቀለሙን ሲያንጠፈጥፍ የሠራውን የቅኔውን ጥብቅ
ሃውልቱን
ጥበባትን
አንረሳም - አንዘነጋም
ለካስ ሞት ታሪክን ገድሎ
አለው የታሪክ ዋጋም።
ለካስ ሞት ኪነትን ጥሎ
ዋ! ዮፍታሄ ያ የጠዋት ግጥም ወፍ
አይቻለውም ሊያደርግ ከንቱ
ዋ! ዮፍታሄ ያ የጠዋት ኪነት በራፍ
የዮፍታሄም ስጋ - ሞቱ
ያ የጠዋት ቅኔ ምዕራፍ
እንደዚሁ . . . . . .
ዋ ዮፍታሄ
በቅኔ ሕይወት ጎሑ
ዋ . . . . . .
የኪነት ትንሳኤውም
ጎሕ መጽሔት መስከረም 1969፣ ገጽ 17
ከታሪኩ ጋር ያውም። (ንግድ ማተሚያ ቤት)

ቅፅ-1፣ቁጥር 1 መስከረም 2010 ዓ.ም ገፅ 36


ታዛ
የቅኔ ብራና

ቅኔ መወድስ -አማርኛ
ዘመሪጌታ ዮሐንስ ታምሩ
የቅኔ አዝመራ አረም፣ ፈፅሞ እስኪጠራ፣

ትጉሁ ገበሬ መምህር፣ እያረመና እያጣራ፣

ያበቀለችውን ጎጃም፣ ምስጢረ ሰዋሰው አዝመራ፣

ዳግም እንዳይበቅል አደረገው፣

ያን እየዘረፈ ሁልጊዜ ፉከራ፣

ያደርጋልና ያ ዘራፊ፣

የቅኔ ቤትን ሊዘርፍ፣ ባለቤቱን እንኳ ምንም


ሳይፈራ።

ሰዋሰውሂ ትልቁ አዝመራ፣ ሳይበቅል ቀረ በተራ፣

ባልተለሳለሰ ጭንጫ መሬት፣ ያለ አገባቡ


እየተዘራ፣

ወበእንተዝ ተሀዝን፣ የቅኔ ባለቤት ዋሸራ፣

ያለ አገባቡ በመዘራቱ፣ እየተበራየ በፉገራ።

ቅፅ-1፣ቁጥር 1 መስከረም 2010 ዓ.ም ገፅ 37


የታዛ አሻራ

ከኦሎምፒክ
ትዝታዎች

(ዓለማየሁ ገ/ሕይወት)

“በአገር አቋራጭና በዓለም


ሐምሌ 2004 ዓ.ም. እግር ጥሎኝ ኬንያ ነበርኩ። አንዱን
ቀን ደግሞ ከዋና ከተማዋ ከናይሮቢ 140 ኪሎሜትር ያህል
ርቃ በምትገኘው የናኩሩ ከተማ አዳር አድርጌያለሁ። ከስራ
ሻምፒዮና ደጋግማ ድል የመታችና
ባልደረቦቼ ጋር የሄድንበትን ተግባር አጠናቀን ምሽቱን
በተዘጋጄ የራትና የትውውቅ ፕሮግራም ላይ እየተዝናናን ነው።
በደራርቱ ቱሉ እግር የተተካች
ሥፍራው በዛፎች የተከበበና በጥሩ ሁኔታ የተያዘ በመሆኑ እጅግ
ያምራል። እናም ውጪ ለምለም ሜዳ ላይ በተሰራ ድንኳን ውስጥ ግሩም አትሌት” ይላታል ጥሩዬን።
ሆነን ከመብሉም ከመጠጡም እየወሳሰድን እንጫወታለን። በመሃሉ
ፊኛዬን ላቃልል በምግብ አዳራሹ በኩል ሳልፍ ሰዎች ቴሌቪዥኑ
ሳያስመስልብኝ አልቀረም።
ላይ አፍጥጠው ተመለከትኩ። ትዝ ሲለኝ ዕለቱ በሎንዶኑ ኦሎምፒክ
የሴቶች የአስር ሺህ ሜትር ሩጫ ውድድር የሚከናወንበት ኖሯል። “እሱን አውቃለሁ። አሁን የሚወዳደሩት ግን ሴቶች መሰሉኝ” አለኝ
አመልካች ጣቱን ቴሌቪዥኑ ላይ ቀስሮ።
ውድድሩ ሊጀመር ተቃርቧል። አዘጋጆቹ ተወዳዳሪዎቹን እያስተዋወቁ
ነው። ዋናው ትኩረት ጥሩነሽ ዲባባ ላይ ነበር ማለት ይቻላል። “ኦኦኦኦኦኦኦኦ!” አልኩ ሃሳብህ ገባኝ እንደማለት።
አንደኛው ጋዜጠኛ ሃያ ሁለት አትሌቶች የሚወዳደሩ መሆናቸውን
ከገለፀ በኋላ ዝርዝሩ ክብሯን ለማስጠበቅ የምትሮጠዋን የኦሎምፒክ “ያ! አለዚያማ ‘ጋባስላሴና ኬንሳ ቤኬሌ’ን ልረሳ አልችልም።” ስም
ሪኮርድ ባለቤት ጥሩነሽን እንደሚጨምር ይናገራል። “በአገር አጠራሩ ሳቄን አመጣው። በተለይ የቀነኒሳን ስም ኬንያ ሊለው
አቋራጭና በዓለም ሻምፒዮና ደጋግማ ድል የመታችና በደራርቱ ቱሉ ምንም አልቀረው። እንደገና ትኩረታችንን ወደ ቴሌቪዥኑ አደረግን።
እግር የተተካች ግሩም አትሌት” ይላታል ጥሩዬን። ከአራት ዓመት ከፊት በርካቶች ያሉበት የሯጮች ቡድን ተደራርበው ቀጥለዋል።
በፊት በተከናወነው የቤጂንግ ኦሎምፒክ በአምስትና በአስር ሺህ ቀሪዎቹ ደግሞ በተንተን ብለው ይከተላሉ። ዋና ዋናዎቹ ሯጮች
ለሃገሯ ሁለት ወርቅ በማስገኘት በታሪክ የመጀመሪያዋ ሴት አትሌት ቀድመው የተፈተለኩትን ሶስት ጃፓኖች እየተጠጉ ነው። ጃፓኖቹ
ለመሆን መብቃቷንና የዓመቱ ምርጥ አትሌት መባሏን አትቷል:: አሯሯጮች ሳይሆኑ አይቀሩም። በቡድን ሆነው መሳብ ጀምረው
ለጥቆም በጉዳት ምክንያት ላለፉት ጥቂት ዓመታት ከውድድር ርቃ ነበር። የተሻለ ሰዓት ለማስመዝገብ የታሰበ ይመስላል። የኦሎምፒክ
መቆየቷን ተናግሯል:: የኬንያዎቹ ኪፕየጎና ቼሩዬት ተከታዩን ደረጃ ሪኮርድ ምናልባት ይሻሻል ይሆናል። አዲስ የዓለም ሪኮርድ ይመጣል
ይዘዋል። ወርቅነሽ ኪዳኔንና በላይነሽ ኦልጅራንም እንዲሁ ድንቅ ተብሎ ግን አይጠበቅም። የኦሎምፒክ ውድድር ሃላፊነት የበዛበት፣
ውጤት ያስመዘገቡ ጠንካራ አትሌቶች ሲል ያደንቃቸዋል። በትውልድ ጭንቀትና ስጋት ያየለበት ነው። በዚያው ልክ የመጨረሻው ዙር
ኢትዮጵያዊት የሆነችውንና ለባህሬን የምትሮጠውን ሺታየ እሸቴንም እስኪቀር መጠባበቁ ይበዛል። ጋዜጠኞቹ ስለ ዋና ዋናዎቹ ሯጮች
እንዲሁ ያነሳሷታል:: ሁሉን ነገር ትቼ “ታስከር” የተሰኘውን የኬንያ የቅርብና የሩቅ ድሎች እየጠቃቀሱ በቅብብል ይተርካሉ። በተለይ
ቢራ አዘዝኩና እዚያው ቀረሁ። በአንደኛው ጥግ ወዳሉት ሰዎች በልምዷና በአጨራረስ ፍጥነቷ ጥሩነሽ ከሁሉም የተለየች ከሁሉም
ሄድኩናም “አጠገባችሁ ብቀመጥ ትፈቅዳላችሁን?” አልኳቸው። የላቀች መሆኗን እየደጋገሙ ይናገራሉ።
ሲስማሙልኝ ወንበር ስቤ ተቀመጥኩ።
ያ ወዳጄ በመሃል ጋዜጣ ሲመለከት ቆየና ከት ብሎ ሳቀ። ነገር
ሩጫው ተጀመረ። የመጀመሪያዋን ረድፍ ለመያዝ ያህል ፈጠን ግን የተመኘውን ትኩረት ያገኘ አልመሰለኝም። ዘወር ብሎ ሲያየኝ
ፈጠን ካሉና ሰልፋቸውን ካሳመሩ በኋላ እየተጠባበቁ መሮጥ ሆነ። አይኖቼን ወደያዘው ጋዜጣ ወረወርኳቸው። በዚህን ጊዜ ‘‘ሉክ ኣት
በዚህ ጊዜ አጠገቤ ካሉት አንዱ፦ ዚስ’’ (ተመልከት) አለና ጋዜጣውን ከሁለት አጥፎ አቀበለኝ። ከፊል
ቀልቤን ቴሌቪዥኑ ላይ አድርጌ ጋዜጣውን ለመቃኘት ሞከርኩ::
“አ ዩ ፍሮም ኤቶፕያ?” (ኢትዮጵያዊ ነህን?) አለኝ። ጨዋታ ጉዳዩ በወቅቱ የኬንያ ጠቅላይ ሚኒስትር የነበሩትን ራይላ ኦዲንጋን
እንደመጀመር አይነት መሆኑ ነው። የሚተች “ጭምብሉ ተገልጦ ሲታይ፣ ፍትህን ፍለጋ” የተሰኘ
መፅሃፍ ስለመውጣቱ ነበር። መፅሐፉ አነጋጋሪ ሆኗል:: ለዚህም
“አዎ” ብዬ ዝም አልኩ። ቀጠለናም፦
ምክንያቱ ደራሲው ሚስተር ሚጉና ቀደም ሲል የጠቅላይ ሚኒስትር
“ጥሩ ጥሩ ሴት ሯጮች አሏችሁ” አለኝ አይኑን ቴሌቪዥኑ ላይ ኦዲንጋ ልዩ ረዳት ሆኖ ያገለገለ መሆኑ ነው:: ነቃፊዎቹ ከስራው
እንደተከለ። በመባረሩ ምክንያት የደረሰበትን ብስጭት ለማብረድ ሲል የፈጠራ
ክሶችን አቅርቧል:: ወይንም ነገሮችን ከልክ በላይ አጋንኗል ሲሉ
“በጣም! ወንዶችም ጭምር” አልኩት ሳላስበው። ነገር የመፈለግ ተችተውታል:: ደጋፊዎቹ ደግሞ በስራ አጋጣሚ የታዘባቸውን

ቅፅ-1፣ቁጥር 1 መስከረም 2010 ዓ.ም ገፅ 38


የታዛ አሻራ

ራኒንግ … አም … ዊ አር
ኦልሞስት ኢኳል:: ዘኦንሊ
ቲንግ ዩ ቢች አስ ጉድ ኢስ
ዊስ ዩር ኤር ላይንስ:: ዳትስ
ኤ ፋክት! ዩ ሃቭ ኤ ዎርልድ
ክላስ ኬርዬር::” (በፕሬስ
እንበልጣችኋለን፣ በዴሞክራሲ
እንበልጣችኋለን፣ በረዥም
ርቀት ሩጫ … እንኳ … እኩል
ነን ማለት ይቻላል። በደንብ
አድርጋችሁ የምትበልጡን
በአየር መንገዳችሁ ብቻ ነው።
ይኼ የማይካድ ሃቅ ነው።
በዓለም አቀፍ ደረጃ የተደነቀ
አየር መንገድ ነው ያላችሁ።)

እዚህ ላይ ትንሽ ሞቅ አለኝ::


ሐዲስ ዓለማየሁ በ”ፍቅር እስከ
መቃብር” ኣቸው እንዳሉት
ምስጋና - በእኔ ሁኔታ
ደግሞ አድናቆት - ከየትም
አቅጣጫ ቢመጣ ተመስጋኙን
ወይም ተደናቂውን ማስደሰቱ
አይቀርም::

አሁን ስድስት ኪሎ ሜትሩን


ጨርሰዋል:: ወርቅነሽ እየመራች
ነው:: ከአስራ አምስት ደቂቃ
“ያ! አለዚያማ ‘ጋባስላሴና ኬንሳ ቤኬሌ’ን በላይ ሳይሮጡ አይቀርም:: ከሶስቱ የኬንያ ተወዳዳሪዎች አንዷ
ቼፕክሩይ ውድድሩን አቋርጣ እንደወጣች ጋዜጠኛው ሲናገር አጠገቤ
ልረሳ አልችልም።” ስም አጠራሩ ሳቄን የተቀመጠው ሰው ጠረጴዛውን በቡጢ ነረተው:: ጥቂት የብስጭት
አመጣው። በተለይ የቀነኒሳን ስም ኬንያ ቃላት በኪስዋሂሊ ቋንቋ ሳይናገርም አልቀረም። እኔ ግን ደስ
ብሎኛል። ‘አንድ ዕዳ ቀለለ’ ብያለሁ በሆዴ።
ሊለው ምንም አልቀረው። ጥቂት እንደተጓዙ አራቱ ተነጥለው መምራት ያዙ:: ወርቅነሽ
ከፊት፣ ኪፕየጎና ቼሩየት ከመሃል፣ ጥሩነሽ ከእነሱ በኋላ:: ጋዜጠኛው
የወርቅነሽን ጥንካሬና ውድድሩን የማፍጠን ብቃት በአድናቆት
ግድፈቶችና ቅሌቶች በግልፅና በድፍረት ማቅረቡ ተገቢ ነው ይገልፃል:: እየደጋገመም ስሟን ይጠራል:: አሁን ሁለት ኪሎ ሜትር
ሲሉ አድንቀውታል:: ደራሲው ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአጭር ጊዜ ይቀራቸዋል::
ቢሊዮኔር የሆኑበትንና እህታቸውንና የባለቤታቸውን ወንድም
አምባሳደር፣ ወንድማቸውን ረዳት ሚኒስትር፣ ሁለት እህቶቻቸውንና ሶስት ዙር ያህል ሲቀራቸው ጥሩነሽ ወደፊት ገፋ አደረገች::
ሶስት ልጆቻቸውን ልዩ ረዳት ማድረጋቸውን፣ ሌሎች የአጎትና ራሷን አቅሟን እየለካች እየተዘጋጀች ይመስላል:: ከፊቷ ያለችው
የአክስት ልጆቻቸውንም እንዲሁ በተለያዩ የስልጣን እርከኖች ላይ ኪፕየጎ ብቻ ነች:: ጥሩነሽ ተጠግታታለች:: ሁለት ዙር ቀረ:: የልቤ
ማስቀመጣቸውን፣ ስም እየጠቀሰ ያጋልጣል:: አልፎ ተርፎም “ይህ ምት እንደ ቤተክርስቲያን ደወል ሰው የሚሰማው እስኪመስለኝ
ነው የሚባል ስራ የሌላቸው ልጆቻቸው እጅግ በተንጣለለ ቪላ ውስጥ ድረስ ጨምሯል:: ብዙም ሳይቆይ ጥሩዬ ኪፕየጎን አልፋት
ሲኖሩና የቅንጦት መኪኖችን ሲያሽከረክሩ እያየን ዝም የምንልበት ሄደች:: ቼሩየት ልትከተላት ሞክራ ነበር:: ሆኖም አልቻለችም::
ምክንያት ምንድነው?” ሲል ይጠይቃል:: እንኳን ለወርቁ ለብሩም አልበቃች:: ጥሩዬ ሁሉንም ጣጥላቸው
ስትሄድ ሳላስበው ተፈናጥሬ ከወንበሬ ተነሳሁ:: አንድ ሁለት
በመሃሉ ቀና ብዬ ወደቴሌቪዥኑ ስመለከት ወደ ሶስት ሺህ ሜትር የቢራ ጠርሙሶች ተከትለውኝ ኖሮ ወለሉ ላይ ሲከሰከሱ ጉዳይም
እየተጠጉ፣ ፍጥነታቸውም እየጨመረ ነው። ሌላኛው ጋዜጠኛ አላልኳቸው:: ጋዜጠኛው በመካከላቸው ያለው ልዩነት መስፋቱን፣
በበኩሉ ምስራቅ አፍሪቃውያቱ በመገስገስ ላይ መሆናቸውን አበሰረ:: ስለጥሩነሽ የአጨራረስ ፍጥነት እጅግ አስደናቂነት ሲናገርና ዳግም
“እንደተለመደው ውድድሩ በኢትዮጵያና በኬንያ አትሌቶች መካከል ወደ ታላቅና ገናና ድል እየገሰገሰች መሆኑን ሲያበስር፣ ባለሁበት
ሆኗል” ሲልም አከለ:: በዚህ ጊዜ አጠገቤ የተቀመጠው ሰው ዘወር መዝለል ጀመርኩ:: እሰው ሃገር መሆኔን ሁሉ ረስቻለሁ። አንዳንዶቹ
ብሎ በኩራት አይነት ተመለከተኝ:: እኔም ፅዋየን አነሳሁለትና በተስፋ መቁረጥ አይነት ውድድሩን ትተው እኔን ሲመለከቱኝ ሳይ
ተጎነጨሁ:: ልቤ ከወዲሁ ድው ድው ማለት ጀምሯል:: ወዲያው እንደማፈር አርጎኝ ነበር:: በስተመጨረሻ ሁለተኛና ሶስተኛ የወጡት
ከኦዲንጋ ታሪክ ጋር ወደ ሌላ ገፅ መዞሬን ትቼ “ኢንትረስቲንግ” የኬንያ አትሌቶች ወርቅ ካገኙት ኢትዮጵያውያት ባልተናነሰ ሁኔታ
(የሚገርም ነው!) አልኩና ጋዜጣውን ለባለቤቱ መለስኩለት። ሃሳቤ እየፈነጠዙ መሄዳቸው ያልጣማቸው ነበሩ:: ከነዚህ አንዱ “በፕሬስና
ሙሉ ትኩረቴን ውድድሩ ላይ ለማድረግ ነበር:: ሰውየው ግን:- በዲሞክራሲ እንበልጣችኋለን” ያለኝ ሰው ነበር::
“ጁ ዩ ሃቭ ሰች ኧ ቫይብራንት ሚዲያ ኢን ኤቶፕያ?” (ይህን “ዋት’ስ ኦል ዲስ ዳንስ? ኢት’ስ ጀስት ኧ ሲልቨር!” (እስቲ ይኼን
የመሰለ ጠንካራና ህይወት ያለው ሚዲያ አላችሁን?) አለኝ ጋዜጣውን ሁሉ ፈንጠዝያ ምን ይሉታል? ብር አደለ እንዴ ያገኙት!?) ይላል
እየተቀበለኝ:: ጣቱን ቴሌቪዥኑ ላይ ቀስሮ። ታዲያ ወደ ስራ ባልደረቦቼ ከመሄዴ
በፊት ጨበጥኩትና “እንኳን ደስ ያለህ” አልኩት:: “አንተንም እንዲሁ”
የፕሬስ ነገር ብዙ የባህልና የእምነት ጣጣ ቢኖርበትም ለእኔ አለኝ:: እጁን ከመልቀቄ በፊትም:-
የቋንጃ እከክ መሆኑ አልቀረም:: ስለዚህ ወደሌላ ወደማልሸነፍበት
መስክ ለማምለጥ መሞከር ነበረብኝ:: ሰውየው ግን ፋታ የሚሰጥ “ባት ዊ ቢት ዩ ኢን ዲስታንስ ራኒንግ:: ራይት?” (በረዥም ርቀት
አይነት አልሆነም:: በእርግጥ የራሱ እንከን ባያጣውም የኬንያ ፕሬስ ግን እኛ ነን ‘ምናቀምሳችሁ:: አይመስልህም?) አልኩት::
የደረሰበት ደረጃ ላይ እንዳልደረስን ውስጤ ያውቃል:: መቀበል ግን
አልፈለግኩም:: ከሁሉ በላይ የገረመኝ ደግሞ በሩጫ ውድድር መካከል “የስ ዩ ዱ!” (እውነት ነው!) ሲለኝ ሳቄን መደበቅ አቃተኝ::
እንዲህ አይነት ጨዋታ ማምጣቱ ነው:: ፊቴን ወደቴሌቪዥኑ አዙሬ
ፀጥ አልኩ:: እሱ ግን ቀጠለ:: ክብርና ሞገስ ለድንቅ አትሌቶቻችን!!

“ዊ ቢች ዩ ኢን ፕሬስ፣ ዊ ቢች ዩ ኢን ዴሞክራሲ! ኢን ዲስታንስ

ቅፅ-1፣ቁጥር 1 መስከረም 2010 ዓ.ም ገፅ 39


ታዛ ገፀ-ኅሩያን

ቆይታ ከሙዚቃ ባለ
ሙያው አበበ መለሰ ጋር

ታዛ፡- አቤ በመጀመሪያ ደረጃ በሙያህ መስክ ያበረከትከውን አበበ፡- የተወለድኩትና ያደግኩት ባህር ዳር ውስጥ ነው -
ታላቅ አስተዋፅዖ በውል የተመለከተው የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ጣና ሃይቅ ዳር። ሻለቃ ያየህ ይራድ የሚባሉ የባህር ዳር
የክብር ዱክትርና ማዕረግ ስለሰጠህ እንኳን ደስ ያለህ ለማለት አውራጃ ገዥና የእናቴ ወንድም የጎጃም ክፍለ ሃገር የስልክና
እንወዳለን። የፖስታ ቤት ሹምነትንም ደርበው ይሰሩ ነበር። የሻለቃ ያየህ
ይራድ መኖሪያ የድሮው ራስ ሆቴል ኋላ ግዮን ሆቴል ያለበት
አበበ፡- እንኳን አብሮ ደስ አለን። አካባቢ እንደቤተመንግስት ያለ ነበር ሃይቁ ዳር። እህታቸውም
(የእኔ እናት) ከገጠር መጥታ አብራቸው ትኖር ነበር። አባቴ
ታዛ፡- በእውነቱ ዩኒቨርሲቲው ክብሩን የሰጠህ በሁላችን ስም ደግሞ በአካባቢው በታታሪነቱና በሁለገብነቱ የታወቀ ነበር።
ነው ማለት እንችላለን። ሥራዎችህ በሁላችንም ልብና አእምሮ ስለዚህ“ከዚህ ጎበዝ ጋር እናጋባት” ተባለ። በድሮ ጊዜ ጎበዝና
ውስጥ ያሉ ናቸው። በዚያ ላይ ለቁጥር የሚያታክቱ ሥራዎችን ታታሪ ሰው ሲገኝ ለዝምድና ይፈለግ ነበርና በዚህ አጋጣሚ
ነው ያበረከትከው። እንደውም የጤና እክል ገጥሞህ በነበረበት ነው እናትና አባቴ የተገናኙት። እና እኔም እዚያው ግቢ ውስጥ
ወቅት ዋሺንግተን ዲሲ ውስጥ ለክብርህ በተሰናዳ አንድ ዝግጅት ተወለድኩ። የእኔ ህይወት እንግዲህ እዚያ ነው የሚጀምረው
ሥራዎችህ በአጭር በአጭሩ ሲቀርቡ ከብዛታቸው የተነሳ - ጣና ሃይቅ ዳር። ከዚያ በኋላ ቤት ሰራንና ቀበሌ ሁለት
-ከወጣቶቹ እስከ አንጋፋዎቹ እስከነ አያ ይርጋ ዱባለ ድረስ ወደሚባለው አካባቢ ሄድን። ተጨማሪ ልጆች ተወለዱ።
-የእሱ ያልሆኑትን ማቅረቡ ይቀላል መባሉን እናስታውሳለን። ያደግነውም እዚያው ነው።
በማስከተል የታዛ መጽሔት እንግዳችን እንድትሆን ያቀረብንልህን
ጥያቄ ተቀብለህ ለዚህ ቃለ መጠይቅ ዝግጁ ስለሆንክልን ከልብ ታዛ፡- የሙዚቃው ነገርስ እንዴት ተጀመረ?
እናመሰግንሃለን።
አበበ:- የሚገርምህ የሙዚቃውም ነገር ያኔ ነው የተጀመረው።
አበበ፡- እኔም አመሰግናለሁ። የጠጉር ማበጠሪያውን በወረቀት ሸፍነን ልክ እንደሃርሞኒካ
አድርገን እንነፋ ነበር። ሃይለኛ የሙዚቃ ስሜት ነበረን።
ታዛ፡- እስኪ ልጅነትህን አጋራን። አስተዳደግህ ምን ይመስላል? ሶስተኛ ክፍል ሆነን ክፍል ውስጥ መዝሙር እንዘምር ነበር።
ስራዬ ብለን በደንብ ይዘነው የነበረው ግን አራተኛ ክፍል ከገባን

ቅፅ-1፣ቁጥር 1 መስከረም 2010 ዓ.ም ገፅ 40


ገፀ-ኅሩያን ታዛ

በኋላ ነው። አራታችን ከስካውቶች ፊት አራታችን ከኋላ ሆነን ውሃ የክረምት ትምህርት ያስተምረን ነበር። የራሱን ዘፈን
ታምቡር እየመታን ስንሄድ ስካውቶች ደግሞ ዘንጋቸውን ይዘፍንም ነበር። እሱ ደግሞ የበለጠ ወደ ዓለማየሁ እሸቴ
እያሽከረከሩ በሰልፍ ያልፋሉ። የሕንድ ዘፈን ከሚጫወት ሐጎስ እንድሳብ አደረገኝ። ወርቅ ውሃ የዓለማየሁ ዋና አድናቂ ነበር።
ከበደ የሚባል ጎበዝ ድምፃዊ ጋር ሆነንም እንዘፍን ነበር። ከዚያ አየህ ተገናኘን። ወደሻይ ቤት ይዞኝ ይሄዳል። በራድ ሻይ
አምስተኛ ክፍል ገባን። በዚያን ጊዜ አበራ ማሞና ጥሩነህ ማሞ ይታዘዛል። ያኔ ሙዚቃ እሚሰማው ሻይ ቤት ውስጥ ነው።
የሚያዘጋጁት የዘፈን ምርጫ ፕሮግራም ነበር። እና እህቶቼ አንድ በራድ ሻይ ለሶስትና ላራት አዘህ እየጠጣህ ሙዚቃህን
የዘፈኖቹን ዝርዝር ይመዘግቡ ነበር። ትዝ ይለኛል የነመልካሙ መከስከስ ነው። ሸክላው እየተገለባበጠ ይለቀቃል። ሙዚቃ
ተበጀ፣ የነዓለማየሁ እሸቴ፣ የነሀብታሙ ሺፈራው፣ የነጌታቸው የማጣጣም ፍላጎታችንና ስሜታችን እያደገ ይሄዳል። ስድስተኛ
ካሳ ሥራዎች የሚተላለፉበት ዘመን ነው። ዓለማየሁ እሸቴን ክፍል ስገባ ሙዚቃውን ኮስተር ብዬ መያዝ ጀመርኩ። ሰባተኛ
በጣም እወደው ነበር ከልጅነቴ ጀምሮ። በዚያ ላይ ዘሜ - ክፍል እያለሁ ደግሞ አንድ ነገር ተፈጠረ። ደርግ ከገባ በኋላ
ወንድሜ አለ። ምናልባትም የመጀመሪያው የወጣቶች የተቃውሞ ሰልፍ
የተደረገው ባህርዳር ውስጥ ሳይሆን አይቀርም። ምክንያቱን
ታዛ፡- ዘመነ መለሰ? አላስታውስም። ሰው ሁሉ የሞተበት ነው። ታዲያ ያኔ

አበበ፡- አዎ። እሱ ደግሞ የጥላሁንን ዘፈኖች በጣም ነበር “የእግዜር ያለህ፣ እግዚኦ በሉ
የሚጫወታቸው። ታዲያ ቤት ውስጥ ጉርድ በርሚል አስገብተን
የእግዜር ያለሽ፣ እግዚኦ በሉ
መደብደብ፣ መጫወት ነው። ደግሞ ያን ጊዜ የተለያዩ ዘፋኞች
ይመጡ ነበር። አዝመራችን አልቋል አሉ።
ታዛ፡- ወደ ባህር ዳር? ወይኔ ድሃው፣ ያልታደልኩት
አበበ፡- አዎ፣ እነማንን አስታውሳለሁ መሰለህ … እነ አያሌው አዝመራዬን አስጨረስኩት።”
መስፍን፣ እነ አክሊሉ ስዩም፣ ደግሞ አንድ ጠይም ረዘም ያለ
ነበር ከእነሱ ጋር አስፋው የሚባል… ብዬ ግጥሙንም ዜማውንም ደረስኩና መድረክ ላይ ተጫወትኩት
- እዚያው በትምህርት ቤታችን ግቢ ውስጥ።
ታዛ፡- አስፋው ወ/ማርያም? ከዚያው ከጎንደር ፖሊስ ኦርኬስትራ
ከሆነ … ታዛ፡- የሰዉ አቀባበል እንዴት ነበር?

አበበ፡- አዎ፣ አሰፋ የሚባል ሳክስፎን ተጫዋችም ነበራቸው አበበ፡- ወጣቱ በጣም ወደደው። ጩኸት በጩኸት ሆነ። ያን ጊዜ
… ይመጡና በመኪና ሆነው ከተማውን እየዞሩ ማስታወቂያ ከበሮ (ድራም) መጫወት ጀምሬያለሁ። ድራሙን የምንጫወተው
ያስነግራሉ። እኛ ታዲያ እነሱን እየተከተልን እንሮጣለን። ግን ለሁለት ነው፡፡ እኔ ከበሮውንና ፔዳሉን እመታለሁ። አብዱ
የምሥራቅ በረኛ፣ እነ ወጋየሁ ደግነቱ ያሉበት፣ ቡድን ደግሞ ሰይድ የሚባል ጓደኛዬ ደግሞ ሳህኗን። በዚያ ላይ ሃርሞኒካ
ከሐረር ይመጣል። መቼም የሚያመልጠን የለም። ባንገባም አለን። በድምፅ ማጉያ እንጠቀማለን። ይገርምሃል፣ አንድ ወር
እንኳ በመስኮትና ባጥር ተንጠላጥለንም ቢሆን ለማየት እንኳ አልወሰደብኝም ሌላ ስራ ጀመርኩ።
መሞከራችን አይቀርም። ከአዲስ አበባም እንዲሁ ይመጡ ነበር።
እንግዲህ ድራሙ አለ። ያን ሁሉ ስንሰማ እንቆይና ቤት ስንገባ “አልፈርድም፣ ጊዜው ነው፣ ጊዜው ነው
ያን በርሜል እየደበደብን ሰፈሩን ስንረብሽ ነበር የምንውለው።
በኋላ እኔም እንደህቶቼ በዘፈን ምርጫ ፕሮግራም በየሳምንቱ ተራው ደርሶለት ነው፣
የሚቀርቡትን ዘፈኖች መመዝገብ ያዝኩ። ታዲያ በሳምንቱ
ስጠብቅ የመዘገብኳቸው አይቀሩም። ትዝ የሚለኝ የታምራት እማዬ ተከበብሽ ባረመኖች እጅ
ሞላ (በዜማ) “በናፍቆት አለንጋ ጨክነሽ ልቤን የቀጣሽው፣ እቱ
የምወድሽ ናፍቆቴ የት ነበር ያለሽው”፣ የጌታቸው ካሳ “ትዝታ”፣ ላንቺ እሚያስብ የለም፣ ለራሱ ነው እንጂ።
ዓለማየሁ ስለ እናቱና ስለ እህቱ የዘፈናቸው፣ የጥላሁንም
እረኛውም ክፉ፣ ልሳኑ መራራ
እንዲሁ ነበሩበት። ታዲያ እንዳልኩህ ዘመነ የጥላሁንን
“ስግብግብ ጆሮዬ” ሲዘፍን እኔ እቀበለዋለሁ። አለ አይደል “ጎጂ
ጠቃሚውን እያግበሰበሰ” ሲል እኔ “ስግብግብ ጆሮዬ” እላለሁ።
እኔ የዓለማየሁን ስዘፍን ደግሞ እሱ ያጅበኛል።

ታዛ፡- የዜማው ነገርስ መቼ ተጀመረ?

አበበ፡- አምስተኛ ክፍል ስገባ እንዴት እንደሆነ ሳላውቀው


የዜማ ስሜት ውስጥ ገባሁ።

“በችጋር ተጠብሳ ልጇን ባሳደገች፣

ፈትፍታ ባበላች እናት ባዳ ሆነች።”

የሚል ግጥምና ዜማ ሰራሁ ማለት ነው። ከዚያ ለካ እኔም


ዜማ መስራት እችላለሁ አይነት ነገር ተሰማኝ። ስድስተኛ ክፍል
ስሆን ታዋቂ ዘፋኝ ሆንኩ ከተማው ውስጥ። የምዘፍነው የት
ነው? ትምህርት ቤት። ወርቅ ውሃ አዲስ የሚባል ባህርዳር
ውስጥ ታዋቂ የሆነ ዘፋኝ ነበረ። ለሙሉቀን መለሰ ግጥም
የሚሰጡ እንደ አሥራት አንለይ አይነቶችም ነበሩ። እና ወርቅ

ቅፅ-1፣ቁጥር 1 መስከረም 2010 ዓ.ም ገፅ 41


ታዛ ገፀ-ኅሩያን

ሊያደርግ ፈለገ፣ ሁሉን በየተራ።” በህይወት የሉም። በቃ አንድ ላይ ሆነን ተማሪውን አሳብደነው
ነበር። በዚህ መሃል በስንት ዓ.ም. እንደሆነ አሁን በደንብ
ይኼንም መድረክ ላይ ተጫወትኩት። እንግዲህ ቅኔ መሆኑ አላስታውሰውም እንጂ ለእናት አገር ጥሪ ተብሎ እነ ጥላሁን
ነው። እረኛ ማለት ጠባቂ፣ መሪ ማለት ነው። ከዚያ በኋላ ገሰሰ ወደ ባህር ዳር ይመጣሉ። ከዚያ በፊት የ1966/67ቱን
አንድ ሞዛርት የሚባል የሙዚቃ ባንድ አቋቋምን፣ ዛሬ ብዙዎቹ ድርቅ በተመለከተ፡-
አረብ አገር ናቸው። ያኔ የመን ዜጎቿን ወደ ሃገራቸው
የወሰደች ጊዜ ነው ብዙዎቹ የሄዱ። አንድ ጣሊያናዊም ነበር “ተነሳ ወገኔ ያለህን እርዳቸው
አንቶኒዮ የሚባል። እንግዲህ ሰባተኛና ስምንተኛ ክፍል እያለሁ
ማለት ነው። ዘጠነኛ ክፍል ስገባ ረብሻ ሆኖ ትምህርት ቤት ያለኛ መመኪያ ቀራቢም የላቸው”…
ስለተዘጋ ለእረፍት ደንበጫ ወደምትኖር እህቴ ዘንድ ሄድኩ።
ረዘነ የሚባል አስተማሪ ነበር ከጎረቤት። እና እየጠራ ሻይ የሚል ግጥም ፅፌ ስለነበር በአጋጣሚው ዜማ ሰራሁለት።
ይጋብዘኛል፣ ያቀርበኛል። ያኔ ታዲያ የሸክላ ማጫወቻ ነበረው። ከዚያ እነ ጥላሁን ጨርሰው ከመድረክ ሲወርዱ እኔ ጊታሬን
በተለይ የዓለማየሁ እሸቴን ሥራዎች እንሰማ ነበር። ይህ በዚህ ይዤ ወጣሁ - ብቻዬን። ለመጀመሪያ ጊዜ አሪፍ ማይክሮፎን
እንዳለ ከአዲስ አበባ ሶስት መምህራን ተመድበው ይመጡና አገኘሁ። ዘመናዊ የሆነ ለጊታሩ ለብቻ፣ ለእኔ ለብቻ።
ከእሱ ጋር በደባልነት ይቀመጣሉ። አንደኛው መምህር ደግሞ ስታዲዮሙን ድብልቅልቅ የሚያደርግ። ከዚያ በፊት የስብሰባ
ጊታር ይዞ ነው የመጣው። ያን ጊታር ይዞ ሲጫወት አየዋለሁ። ጥሪ የሚተላለፍበት የቀበሌ ድምፅ ማጉያ ሰው ይዞልኝ ወይም
ጠጋ ብዬ አመታቱን፣ ሁኔታውን እመለከታለሁ። እሱ ሲሄድ ጊታሬ ላይ አጣብቄ ነበር የምሰራው። በቃ ወጥቼ ስዘፍን የልጅ
ደግሞ ተነስቼ እጫወታለሁ። ትዝ ይለኛል “ተው ስማኝ አገሬ” ድምፅ ነው ያለኝ። አሥራ አምስት ዓመቴ ቢሆን ነው። እነ
የሚለውን ዜማ ነው መጀመሪያ የተጫወትኩት። ያለምንም ጥላሁን፣እነብዙነሽና እነ ሻለቃ ኃይሉ ፅጌ (ኋላ ኮሎኔል) ባሉበት
አስተማሪ። ቀጠልኩና አንድ አብዮታዊ ዜማ ተጫወትኩ። ዘፈንኩ። ታዲያ ስዩም ባሩዳ መጣና አሥር ብር ሸለመኝ።
(በዜማ) “ያለምንም ደም፣ እንከኗ ይውደም” የሚለው መሰለኝ። ብዙዬ ደግሞ መጣችና ሌላ አሥር ብር ሸለመችኝ። የሁለቱ
ፎቶግራፍ ለረጅም ጊዜ ባህር ዳር ውስጥ ሙላት ሙዚቃ
ታዛ፡- ከዚያ በፊት በጊታር የተሰሩ ዘፈኖችን ምን ያህል ሰምተህ ቤት ተለጥፎ ነበር። አቯራ ጠግቦ ሁሉ አላነሱትም፡፡ ወደ
ነበር? ትምህርት ቤት ስሄድ አየው ነበር። እና ያን ሰራሁ። ልክ
ከመድረክ እንደወረድኩ እነጥላሁንን ለማየት ወደኋላ ስሄድ
አበበ፡- ለመጀመሪያ ጊዜ ጊታር ሲጫወት የሰማሁት ግርማ ሻለቃ ኃይሉን አገኘኋቸው። “ነይ ወደዚህ፣ ነይ! እኛ ጋ መቀጠር
ምንተስኖት ነው። ቀጥሎ ፀጋዬ መርጊያ። “ቀልዱን ተይ የምትፈልጊ ከሆነ ክረምት ላይ ነይና በሲቪል እንቀጥርሻለን።
ቀልዱን ተይ” በሚለው ዘፈን የሚታወቀው መስፍን አበበ አዲስ አበባ ነይና ክቡር ዘበኛ፣ማይጨው ጦር ሠፈር ብለሽ
ነው። ቀድሞ የተጫወተው ግን ግርማ ምንተስኖት ነው። ከዚያ ጠይቀሽ እንድትመጪ” አሉኝ። “እሺ” አልኩኝ። ጥሌ ዝም ብሎ
በኋላ ነው መስፍን አበበ የሚመጣው - ነፍሱን ይማረውና። ይጉረዘረዛል። እጁን ኪሱ ከቶ አይኑን ወዲያና ወዲህ እየላከ
እና የጋሼ ግርማ ምንተስኖትን ጨዋታዎች መሞከር ያዝኩ። ይንጎማለላል። ተፈጥሮው እኮ እሚገርም ነው። ደሞ ሲፈሩት፤
ወደባህር ዳር ተመልሼ ስሄድ የጊታሩን ቁመት፣ ወርድና ስፋት ማነው የሚቀርበው? ሁሉም እኮ ፀጥ ነው የሚለው።
እንዲሁም ቁልፎቹ የሚያርፉበትን ቦታና የመሳሰሉትን በደንብ
አድርጌ ለክቼ ነበር። ከዚያ አናፂዎች ዘንድ ሄጄ ኮምፐልሳቶ ታዛ፡- ከዚያስ ምን ሆነ?
ጠየቅኳቸውና በነፃ የሰጡኝ ይመስለኛል። ያኔ ገንዘብ ከየት
አግኝቼ እገዛለሁ!? ከዚያ ወስጄ ቀረፅኩት። የጊታሩን ላይና አበበ፡- እንግዲህ ከክቡር ዘበኛዎች ጋር በዚህ ሁኔታ ተለያየን።
ታች በኮምፐልሳቶው ከሰራሁ በኋላ ማጣመሙን ስላልቻልኩ በቃ ልቤ ተነሳስቷል። ወደ አዲስ አበባ ለመሄድ ቆርጫለሁ።
ቆርቆሮ ቀረፅኩና አደረግኩበት። በየመሃሉ ደግሞ እንጨት ሻለቃ ኃይሉም ተስፋ ሰጥተውኛል። ስለዚህ ገንዘብ ያስፈልገኛል
አስገባሁበት። ከታች ደግሞ በሚስማር መታሁት። እንጨቱን አልኩና አባቴ ጋ ሄጄ ብጠይቀው አሥር ብር ሰጠኝ። ያኔ ጥቂት
ስድስት ቦታ በሳሁት። ከዚያ የብስክሌት ፍሬን አለ አይደለም ገንዘብ አልነበረም። ሆኖም ስለማይበቃኝ እህቴ ዘንድ ደምበጫ
እሱን ፈትቼ ስድስቱን ወጥሬ አሰርኩበት። ከዚያ እጫወትበት ሄድኩ። እኔ በተፈጥሮዬ በጣም ግልፅ ስለሆንኩ ሁሉንም
ጀመር። ነገር በዝርዝር አጫወትኳት። እሷ ደግሞ ለታላቅ እህቴ
ደውላ “ኧረ ጠፍቶ ሊሄድ ነው” ብላ ስትነግራት “እንደውም
ታዛ፡- ውጤቱንስ እንዴት አገኘኸው? ባለቤቴ የደብረማርቆስ አውራጃ አስተዳዳሪ ሆኖ ስለተሾመ
እየመጣን ነውና ይጠብቀን” ትላታላች። እኔ የምጠብቀው
አበበ፡- አሪፍ ነበር። ይገርምሃል በዚሁ መንገድ ሶስት ጊታሮችን አዲስ ዓመት እየተቃረበ ስለነበር በዓሉን ውዬ ለመሄድ ነው።
ለጓደኞቼ ሰራሁላቸው። ያን እየያዝኩ ትምህርት ቤት ስሄድ ለካስ “ሃምሳ ብር እሰጠዋለሁ ብላለች ብለሽ እስክንመጣ
አንድ መምህር ያየኛል። ዳዊት ይባላል። በኋላ ግርግር ሲመጣ እንደምንም አቆይው”ብላት ኖሯል። እንዳሉትም መጡ። ጋሼ
ወደ ሻዕቢያ ገባ። እንደው በሕይወት በኖረና ባገኘሁት እንዴት - የእህቴ ባለቤት - አጃቢ አለው፤ የደርግ ባለስልጣን ነው።
ደስ ባለኝ ነበር። እንዴት ነው ደግ የዋለልህን ሰው ዕድል ደርግ ለመጀመሪያ ጊዜ ለፖለቲካ ትምህርት ወደውጪ ሃገር
አጋጥሞህ ብታመሰግነው ደስ ይልሃል አይደል? ስሜቴን አይቶ ከላካቸው ሰልጣኞች አንዱ ነው። ሃንጋሪ ነበር የሄደው። ሁለት
አዲስ ጊታሩን እንድጫወትበት አውጥቶ ሰጠኝ። አሪፍ ጊታር ነው ሶስት ዓመት ቆይቶ ነው የተመለሰው። ፊት መምህር ነው
ነው፣ ድምፁ በጣም ቆንጆ ነው። ከዚያ በኋላማ ምን ልበልህ የነበረው። እኔንም አስተምሮኛል። ያሳደገኝም ነው። ጀምበር
ደብተሮቼን በጀርባዬ ሻጥ አድርጌ ጊታሩን አንግቤ መሄድ ነው። አበበ ይባላል። የባህር ዳር ተማሪ በሙሉ ያውቀዋል። እና
ጊታሩን ውጪ ሰው ጋ አስቀምጬው ወደ ክፍል እገባለሁ፤ ከዚያን ቀን ጀምሮ እስረኛ ሆንኩ።
በእረፍት ሰዓት ወጥቼ እጫወታለሁ። ተማሪዎች ይሰበሰባሉ።
ከዚያ ሳሙኤል ለሚባል ጓደኛዬ ደግሞ ኬፓይፕ የተሰኘች ታዛ፡- እዚያው ደምበጫ?
የሙዚቃ መሳሪያ ወንድሙ አመጣለት።
አበበ፡- አዎ፣ እንደምታውቀው ደምበጫ ትንሽ ከተማ ነች። እና
ታዛ፡- ዋሺንት ነገር ነች? ሻይ ልጠጣም ስሄድ ጠባቂዎቹ ይከተሉኛል። አንድ ቀን ጊታሬን
ወዳስቀመጥኩበት ቤት … የሺጥላ የሚባል ጓደኛም ነበረኝ
አበበ፡- እንደ አኮርዲዮን ያለች ኪቦርድ ያላት ነች፤ ግን ደግሞ እና እሱን ለማግኘት ሹልክ ብዬ እሄዳለሁ። ከዚያ ጠፋ ጠፋ
ትነፋለች። ኬፓይፕ ትባላለች። ሌላው ጓደኛችን አገሬ ጌጡ ተባለና በፍለጋ ተገኘሁ። ከዚያ ወዲያ ጭራሽ ከቤት እንዳትወጣ
ይባላል እሱ ደግሞ የእጅ ድራም ይይዛል። ዛሬ ሁለቱም ተባልኩኝ። በቃ በመኪና ተጭኜ ደብረማርቆስ ቤተመንግስት

ቅፅ-1፣ቁጥር 1 መስከረም 2010 ዓ.ም ገፅ 42


ገፀ-ኅሩያን ታዛ

ገባሁ። “ትምህርትህን ተማር፣ አዲስ አበባ አትሄድም፣ ጊታር እዚህ ሄድኩ ሳይል ጠፍቶ ተረብሸን ነበር። እና ሁለተኛ
ይገዛልሃል” ተባልኩ። እውነትም ጊታር ተገዛልኝ። ቀጥ ብዬ ሴሚስተርን በደንብ አልተከታተልኩም። ያም ተጨምሮ መሰለኝ።
ትምህርቴን መማር ጀመርኩ። ከቤት የምወጣው በመኪና ስለዚህ ወደአዲስ አበባ መምጣት ነበረብኝ። እህቴ ፓስተር ነበር
ነው፣ የምመለሰውም በመኪና ነው። ከዚያ ውጪ መውጣት የምትሠራው። ያልነገርኩህ ማርቆስ እያለሁ ከእስከ የሚባል
የለም። አንድ የረሳሁት ደምበጫ በቆየሁበት ወቅት ከኤፍሬም ጓደኛ ነበረኝ። ታዲያ ከማን ጋር ያስተዋውቀኛል ከፀጋዬ ደቦጭ
ታምሩ ጋር ይሰራ የነበረ ሃይለኛ ባንድ መጥቶ ነበር። ብታይ ጋር። ጊታር እንጫወታለን፣ ስለሙዚቃ እንነጋገራለን። ፀጋዬ
ሳክስፎን አላቸው፣ “የደብረማረቆስ ኪነት ቡድን” ነው መሰለኝ ያኔ ስለነሰላም ስዩም፣ ስለአይቤክሰ ባንድ፣ ስለነጆቫኒ ብዙ ነገር
ስሙ። ካሳ የሚባል ሳክስፎን ተጫዋች ነበራቸው። አኮርዲዮን፣ ያውቅ ነበር። አዲስ አበባ መጥቼም ከፀጋዬ ጋር ተገናኘሁ።
ጊታርና ድራም በብቃት ይጫወታሉ፤ ዘፋኞችም አሏቸው። ያኔ ባጋጣሚ ያንዳችን ቤት ከሌላኛችን ያን ያህል አይርቅም ነበር።
ኤፍሬም ለቋል፣ ወደአዲስ አበባ ሄዷል። እና ትርኢታቸውን እውነቴን ነው የምልህ ለእኔ እዚህ መድረስ ትልቅ ድጋፍ
ላይ ስገባ አንዷን ዘፋኝ ወደድኳት። ጠይም ቆንጆ ነች። የኔ ካደረጉልኝ ሰዎች የመጀመሪያው ዘመነ ነው፤ ሁለተኛው ፀጋዬ
ብትሆን ብለህ የምትመኘው ነገር አለ አይደለም? እሷ ታዋቂ ደቦጭ። ሻይ ቡና እየጋበዘኝ የአዲስ አበባን ሙዚቃ ቤቶች
ነች፣ ትዘፍናለች፣ ትወዛወዛለች። እኔን ማንም አያውቀኝም፣ እያዞረ ያስተዋወቀኝና ከብዙ ወጣቶች ጋር ያግባባኝ ፀጋዬ ነው።
ግን ጊታር እጫወታለሁ ጥሩ ሙያ አለኝ። ከዚያ ተለያየን፣ በዚህ አጋጣሚም በጣም ላመሰግነው እፈልጋለሁ።
እንዳልኩህ ወደ ደብረማርቆስ ሄድን። በትርፍ ጊዜዬ በቤተ
መንግስቱ ጀርባ ሆኜ ጊታሬን እጫወታለሁ። ጊታር የሚጫወት ታዛ፡- የመዝፈኑን ነገር ለምን ተውከው?
መጣ ሲባል ሰምቶ ሳክስፎን ተጫዋቹ ካሳ ይመጣና
ይተዋወቀኛል። በዋናው በር መውጣት ስለማይፈቀድልኝ አበበ፡- እኔ መዝፈን ነበር የምፈልገው። ግን አልተሳካም።
ለጠባቂዎቹ ሳንቲም እየሰጠሁ በጓሮው በኩል መሹለክ ጀመርኩ። ለወንድሜ ለዘመነ መለሰ ግን ብዙ አዳዲስ ዜማዎችን ሰርቼለት
እነካሳ እየመጡ ይወስዱኛል። እዚያ ስሄድ ማንን አገኛለሁ? ነበር። እና ከሴንትራል ሙዚቃ ቤት ጋር ተነጋግሮ ካሴት
ያቺን ልጅ፣ የወደድኳትን። በኋላ ባለቤቴና የሶስት ልጆቼ እናት ሊያወጣ ይመላለሳል። ሙዚቃ ቤቱ ዜማዎቹን ወዷቸዋል።
የሆነችውን ያኔ ነው የተዋወቅኳት። ለረጅም ጊዜ ነው አብረን በአጋጣሚ ኤፍሬም ታምሩም እዚያ ነበር የሚሰራው። ያን
የኖርነው። ከዘጠነኛ ክፍል ጀምሮ እስራኤል እስከሄድኩበት ሰሞን ደግሞ የሙዚቃ ማህበር ተቋቁሞ አዳዲስ ፈጠራ ነው
ጊዜ ድረስ። እንደውም የሆነ ጊዜ ላይ ኤፍሬም የተጫወተውን እንጂ የድሮ ስራዎችን ማቅረብ አይቻልም ተብሏል። በዚህ ጊዜ
“የኔ አደይ አበባ” ለእሷ ነው የሰራሁላት። ከዚያ ቡድን ጋር ነው እንግዲህ እኔ ወደ ሙዚቃው ዓለም ለመግባት ስጣጣር
ድሮ የሰራሁትን “ተነሳ ወገኔ”ን ነው የምጫወተው። እነ “አንቺ የነበረው።ታዲያ ዘፋኞች ሁሉ ምን ይዘው ይቅረቡ? ኤፍሬም
መልካም ወጣት” ያሉበት የመስፍን አበበ ዘፈኖች በዚያ ዓመት አለ። ተሾመ ወልዴም አለ፣ገና ወጣት ድምፃዊ ነበር። ሙሉቀን
ነው የወጡት። የማይሰለቹ ሥራዎች ነበሩ። እናትምህርቴን ነው አንጋፋው ያኔ። ሁሉም አዲስ ዜማ የት ነው የምናገኘው
እየተማርኩ እነሱን እጫወት ነበር። ያኔ የቀረፅኳቸው ዘፈኖቼ የሚሉበት ጊዜ ነው። ከዚያ ኤፍሬም መቸገሩን ሲያይ
አሁን ድረስ አሉ። ከዚያ ጋሼ ተዛወረና ወደ አስበ ተፈሪ የሴንትራል ሙዚቃ ቤት ባለቤት “ይኼ ልጅ እኮ ጥሩ ጥሩ
ሄድን። አመልማል አባተን የተዋወቅኳትም ያን ጊዜ ነው። ዜማዎች አሉት” ይለዋል። ኤፍሬም ዘመነን ሲያገኘው “ማነው
እዚያ ደግሞ ሁለተኛው የመስፍን አበበ ካሴት ወጣ። (በዜማ) ዜማዎቹን የሰጠህ?” ሲል ይጠይቀዋል። “ታላቅ ወንድሜ ነው
“ዘራፍ ዘራፍ፣ እኔ እኔ፣ እኔ ለሃገሬ፣ እሞታለሁ ዛሬ” የሚል የሰጠኝ” ይለዋል። “ታዲያ ለምን አታስተዋውቀኝም?” ሲለው
ከሶማሊያ ወረራ ጋር ተያይዞ የተሰራ ዘፈን ያለበት። ቀጥሎ እሺ ይልና ወደቤት ይዞት ይመጣል። ዘሜ ቤት እንደደረሰ
ደግሞ “ደሴ ላይ ነው ቤቷ”ን አወጣ። እንዲያ እያለ ይቀጥላል። “የቀረፅካቸውን ዜማዎች ያዝና ቶሎ እንሂድ፤ለኤፍሬም ታምሩ
ይህን ሁሉ የማጫውትህ የመስፍን አበበ ዘፈኖች ምን ያህል ትሰጠዋለህ። ፈጠን በል ውጪ እየጠበቀን” ነው ይለኛል።
ተፅዕኖ አሳድረውብኝ እንደነበር ልነግርህ ነው።
ታዛ፡- ምን ተሰማህ?
ታዛ፡- ሌላስ የማን ተፅዕኖ አለብኝ ብለህ ታሰባለህ?
አበበ፡- እኔ በህይወቴ ማግኘት የምፈልገው ሙሉቀንን
አበበ፡- ወደሱ ልመጣልህ ነበር። በዚህ ሁኔታ ላይ እያለሁ ነበር። ለሙሉቀን እሰጠዋለሁ ብዬ ያዘጋጀኋቸው ዜማዎችም
“ሃገሯ ዋርሳ መገራ” የሚለውን የሙሉቀን መለሰ ዘፈን ነበሩኝ። በዚያን ወቅት ሙሉቀንን ወደማምለክ ተጠግቻለሁ።
ሰማሁ። ያን ጊዜ ከመስፍን አበበ ተሸርሽሬ ዘጠና ሳይሆን አርባ እንደነገርኩህ ከልጅነቴ ጀምሮ ሙሉቀን ውስጤ ገብቷል -
አምስት ዲግሪ ዞሬ ወደ ሙሉቀን ሄድኩኝ። “ናኑ ናኑ ነይ”ን ከመስፍን አበበ ጋር። ከዚያ ዜማዎቹን ይዤ ወደ ኤፍሬም
ያወጣ ጊዜ ደግሞ ይበልጥ ተሳብኩ። (በዜማ) “የአባይ ዳሩ ዳሩ ስሄድ መኪናው ውስጥ ቁጭ ብሏል። የደስ ደስ ያለው ጠይም
ያበቅላል ጠንበለል፣ ዋጥ ላርጋትና አላየሁም ልበል” ያለበትም ወጣት ነው። ግባ አለኝና መኪናው ውስጥ ገባሁ። ወደሙዚቃ
ነው። ባመቱ “ላኪልኝ በርሙሌ”ን አስከተለ። ብቻ ምን ልበልህ ቤቱ ይዘውኝ ሄዱ። “እስኪ አሰማን” አለኝና ከፈትኩላቸው።
ቀስ በቀስ ሙሉቀን እያሸነፈ መጣ። በዚህ ወቅት በ1973/74 ያው “ነይልኝ” ነው አንዱ። ሌላው “ወለባ ነይ” ነው። እና አሁን
ብዙ ድርሰቶችን መፃፍ ጀመርኩ። በመስፍን አበበ ስልት የተሰሩ የዘነጋኋቸውን ጨምሮ ወደ ስድስት የሚደርሱ ዜማዎችን
ከሃያ በላይ ዜማዎች ነበሩኝ። የሙሉቀንን ዘፈኖች ስሰማ ደግሞ አሰማኋቸው። ኤፍሬም በጣም ወደዳቸው። ከዚያ “ስንት ነው
ሌሎች ሥራዎችን ቀጠልኩ። ለኤፍሬም የሰጠሁትን “ነይልኝ የምትሸጥልን?” ሲሉኝ “እኔ እንጃ እናንተ የምትሰጡኝን ንገሩኝ”
ነይልኝ” ለምሳሌ በዚያን ወቅት ነው የደረስኩት። ስል፣

ታዛ፡- ከአስበ ተፈሪ በኋላስ ህይወት ወደየት ወሰደችህ? “አርባ አርባ ብር ነው የምንሰጥህ ላንዱ” ይሉኛል (ሳቅ)።
እርግጥ አርባ ብር ብዙ ነው ያኔ! ኮትና ሱሪ በሰማንያ ብር
አበበ፡- ወደ አቦምሳ - አርሲ። በነገርህ ላይ አቦምሳ እያለሁም ማሰፋት ይቻል ነበር። ጫማም በሰላሳ አምስትና ባርባ ብር
እንዲሁ በኪነት ውስጥ እሳተፍ ነበር። ክራር የለመድኩትና ይገኛል። ከዚያ የስድስቱ ዜማዎች ሂሳብ 240 ብር ይሆንና 100
የድራም ችሎታዬን ያሻሻልኩትም አቦምሳ ውስጥ ነው። እዚያ ብር ቀብድ ይሰጠኛል። “በሚቀጥለው ቀን መጥተህ ቀሪውን
ስለቆየሁም ለብዙ የአቦምሳ ልጆች የአካባቢው ተወላጅ ነበር ትወስዳለህ” አሉኝ። ያን ይዤ በረርኩ። በማግስቱ ሄጄ “ቀሪውን
የምመስላቸው። ከዚያ ተመልሼ እንደገና ወደደብረማርቆስ ብር ስጠኝ” ስለው “እንዴ በነፃ አይደለም እንዴ የሰጠኸው?”
ሄድኩ። በጣም ጎበዝ ተማሪ ሆንኩኝ። ከዘጠነኛ ክፍል ጀምሮ ይለኛል። “ለምንድነው በነፃ የምሰጠው?”
አንደኛ፣ ሁለተኛና ሶስተኛ ነበር የምወጣው። አሥራ ሁለተኛ
ክፍል ስፈተን ግን ለከፍተኛ ትምህርት የሚያበቃ ውጤት “በነፃ ብለኸኝ”
ሳላመጣ ቀረሁ። ትንሽ የቤተሰብ ችግር ነበር። ወንድሜ ዘሜ

ቅፅ-1፣ቁጥር 1 መስከረም 2010 ዓ.ም ገፅ 43


ታዛ ገፀ-ኅሩያን

“ኧረ እኔ በነፃ አላልኩም”። ከዚያ “ኤፍሬምን አነጋግረው የመጀመሪያዬ ስለነበር ግን ደንግጫለሁ። እንደውም ኋላ ላይ
ከፈለግክ” ሲለኝ ቀጥ ብዬ ወደ ኤፍሬም ቤት። ፒያሳ ጎንደር ዜማዎችን በልበሙሉነት በምሰራበት ጊዜ “ምነው ዛሬ ከሙሉቀን
ሆስቴል ነበር የሚኖረው ያኔ። ስደርስ ውጪ ቁጭ ብሎ ጋር በሰራሁ ኖሮ” ብያለሁ። ምክንያቱም ያኔ የፍርሃት ስሜት
አገኘሁትና፤ ነበረብኝ። በህይወቴ ውስጥ ትልቅ እርካታ ያገኘሁበት ከሙሉቀን
ጋር የሰራሁበት ወቅት ነው። ባህላዊ ዜማዎችን ሲጫወት
“ምን ብዬ ነው በነፃ የምሰጣችሁ?” ስለው “አይ ይሄማ እንዴት እንደሚያሻሽላቸው ታያለህ። የነባህሩ ቀኜን ስራዎች
አይሆንም፣ ከኔም ሂሳብ ቢሆን ተቆርጦ ይሰጥሃል” አለኝ። ያዳምጣል። የእንግሊዝኛ ሙዚቃዎችን ይሰማል። ሙሉቀን እኮ
ከዚያ አነጋገረልኝ መሰል ተከፈለኝ። በቃ ከዚያ በኋላ ጠፋሁ። በጣም የተለየ ሰው ነው። ብዙም ተምሬበታለሁ። አሁን ለምሳሌ
በመላ በሰበብ መነሻው ህዝባዊ ነው። እኔ ደግሞ በማይነር
ታዛ፡- ለምን? የነበረውን ሜጄር አድርጌ ሰራሁት።ይህን እውቀት ያገኘሁት
ከማነው? ከሙሉቀን። ይህን ለሙከራ ያህል ሰራሁት እንጂ
አበበ፡- በነፃ የሚለው ነገር ትንሽ አናዶኝ ነበር። በወሩ ነው እግዚአብሔር ይመስገን ዜማ እንደሁ ይፈሳል። ከዚያ የተሻሉ
እንደዚህ የሙዚቃ ቤቱ ባለቤት አቶ መኮንን መስፍን ቤቴ ድረስ ስንት ስራዎች ተሰሩ!?
ይመጣና “እንዲያው አቶ አበበ፤ ለሌሎችም ዜማ ብታዘጋጅላቸው?
ብዙ የያዝኳቸው ዘፋኞችም አሉ”ይለኛል። ባለፈው “ከሙሉቀን ታዛ፡- ጊታሩን ካዋሰህ መምህር ሌላ በልጅነትህ የሙዚቃ
ጋር መስራት ስለምፈልግ አገናኘኝ” ብዬው ነበር። ሙሉቀን ስሜትህን ተረድቶ ያገዘህ ወይም ያበረታታህ አለ? የሙዚቃ
ከእሱ ጋር ነበር የሚሰራው። “ምንም ችግር የለም፣ ብቻ አንተ አስተማሪ፣ተቋምም ሊሆን ይችላል።
ና” ብሎኛል። እንግዲህ ከፀጋዬ ጋር ሆነን መርካቶን ሳንረግጥ
አንውልም። እናም ሴንትራል ሙዚቃ ቤት ጎራ እንላለን። አበበ፡- ሮሃ ባንዶች ለእኔ ትምህርት ቤቶቼ ናቸው - በተለይ
ሙዚቃ ይወጣል፣ እንሰማለን። በራድ ሻይ ያስመጣልናል ዳዊት ይፍሩ። እዚያ ቤት ውስጥ ሪትምና ሳውንድ ምን
አቶ መኮንን፣ እንጠጣለን። አንዳንድ ቀንም ምሳ ይጋብዘናል። መሆን እንዳለበት በሚገባ ተምሬያለሁ። እና አሁን የትም
ከዚያ አንድ ቀን “ለሙሉቀን ዜማ እንድታዘጋጅለት” ሲለኝ ቦታ ሄጄ ቀረፃ ላይ ጥሩ የሆነና ያልሆነ ድምፅን በቀላሉ ነው
“እሱን አይደል እንዴ የምፈልገው፣ በጣም ነው ደስ የሚለኝ” የምለየው። በሮሃ ባንድ ተቃኝቼ ነው ያደግኩት። ከነሱ ጋር
አልኩት። ከዚያ በፊት ሙሉቀንን ሰፈር መጥቶ ፓስተር እህቴ አስራ ሰባት ዓመት ነው የሰራሁት። የነሱ ሳውንድ ደግሞ
ቤት አካባቢ ማለት ነው በሩቁ አይቼዋለሁ። ዙሪያሽ የምትባል እስካሁን አልተገኘም። እንደሮሃ ባንድ አይነት ሳውንድ በጣም
ጎረቤታችን አለች። ሙሉቀንን በጣም እንደምወደው ስለምታውቅ ታይት የሆነ ለዚያውም በዚያ በሞተ ዕቃ በዴክ እየተቀረፀ።
“አቤ አቤ” ትለኛለች “ምንድነው” ስላት “ሙሉቀን መለሰ እዚህ ዛሬ በኮምፒውተርም በምንም ተቀርፆ ደረጃውን የጠበቀ ድምፅ
ማሞ ጋራዥ መኪና እያሰራ ነው” ትለኛለች። ሮጨ ስደርስ አትሰማም። በዚያ ዘመን ግን እነ ጆቫኒ ስራውን በስነስርዓት
ልክ መኪናውን ሲያንቀሳቅስ፣ ከኋላ እየሮጥኩ ስከተለው በጎን ነበር የሚያከናውኑት። ዳዊት በመስማት ጆቫኒ በመስራት፣
በኩል አየሁት። ነጭ ነው የሚመስለው፣ ጠጉሩን ወደኋላ በማቃናት። ጆቫኒን የሚያህል ቤዝ ጊታር ተጫዋች ዳዊት
አስተኝቶታል። በቃ ሳልደርስበት ስለቀረሁ አለቀስኩ። እንግዲህ ዘንድ ሄዶ ቆሞ ቅኝቱን ሲያስተካክል ስታይ፣ በነዚህ ሁለት
ያ ሁሉ አልፎ አሁን ላገኘው ነው። አንዱን ቀን አቶ መኮንን ግዙፍ ባለሙያዎች መካከል የነበረውን መከባበር መቼም
ወደ ሙሉቀን ሊወስደኝ ሰምንት ሰዓት ላይ ቀጠረኝ። እኔ ልነግርህ አልችልም። አብሬያቸው በሰራሁባቸው ዓመታት ምን
በስንት የሄድኩ ይመስልሃል? አራት ሰዓት። አይነት የስራ ሰዎች መሆናቸውን ተረድቻለሁ። ሰው እንዴት
ዓመቱን ሙሉ ያለማቋረጥ ዜማና ግጥም ይሰራል? ዓመቱን
ታዛ፡- የመጓጓት ነው? ሙሉ ያለማቋረጥ ቅንብር (አሬንጅመንት) ይሰራል? ያ ሁሉ
ዜማና ግጥም ሲሰራ የቅንብሩ ስራ የነሱ ነው። አስራ ስንት
አበበ፡- ታዲያስ! አቶ መኮንን ራሱ ገርሞት “ምነው በጊዜ ዓመት። ያን ሁሉ ዘመን ተከባብረን ተቻችለን ነው። መኮራረፍ
መጣህ?” ሲለኝ “አይ ግድየለም” ብዬ ቁጭ አልኩ። ከዚያ ወጥቶ የለ ምን የለ። ይኼ ባንዳንዱ ባንድ የምትሰማው አይነት
የሆነ ቦታ ሄዶ ሲዘገይ ‘አይ ይሄ ሰውዬ በዚያው ሊቀር ነው ጭቅጭቅ ጨርሶ የለም። ጀማሪዎች ናቸው ብለው አይንቁንም።
እንዴ’ እያልኩ እጨነቃለሁ። ከአንድና ከሁለት ሰዓት በላይ “አበበ ሃሳብ አለህ እዚህ ጋ?” ይሉኛል። “እዚች ጋ እንዲህ
ቆይቶ ይመጣል። ሰዓቱ ሲደርስ ተያይዘን ወደ ግዮን ሆቴል ብትሆንልን” ስል “እስኪ በለው” ነው። መደጋገፍ ነበረ። ይሄ
ሄድን። ስንደርስ ሙዚቃ ይሰማናል። ሮሃዎች ከሙሉቀን ጋር ታዲያ ስለቅንብር ብዙ እንዳውቅ ረዳኝ። “ሙዚቃ” የሚለውን
እየተለማመዱ ነበር። የሙሉቀንን ድምፅ ስሰማ ሰውነቴ ነው ስራዬን ለምሳሌ ውስጡንም ውጩንም ሁሉን ነገር ጨርሼ
የሚርደው። ሙዚቃው ሲያልቅ ጠጉሩን ወደኋላ እያበጠረ እንድወስድላቸው አስችሎኛል። በነገራችን ላይ ግጥሙንም፣
መጣና መኪናው ውስጥ ገብቶ ከኋላ ተቀመጠ። ዜማውንም፣ ቅንብሩንም በአንድ ሌሊት ነው የሰራሁት። አራት
ዘፋኞች ናቸው፣ አራት ቨርስ አለው፣ አራት የተለያዬ ሪትም
“እንደምነህ? ደህና ነህ? ከየት ነው የመጣኸው?” ሲለኝ “ከጎጃም አለው። “መተባበር ቢኖር”ም ግማሹ ግጥም የኔ ነው። ግማሹን
ባህርዳር፣ እናቴ ደግሞ ከብቸና ናት” አልኩት። ሙሉቀን የብቸና ደግሞ ይልምሽ (ይልማ ገብረአብ) ነው የሰራው። ሙዚቃውን
ልጅ መሆኑን ስለማውቅ ሆን ብዬ ነው። “ኧረ ባክህ፣ ብቸና እኮ እኔ ነኝ የሠራሁት።
የእኔ አገር ነው” አለኝ። ከዚያ ወደቤቱ ሄድን። ቤቱ ያምራል።
ከዚያ “ዘፈኖችህን ይዘሃል?” ሲለኝ “አይ ጊታር አልያዝኩም”። ታዛ፡- በዜማ ፈጠራስ ረገድ?
“በቃ ነገ ጠዋት እንድትመጣ። ቤቱ ይጠፋብሃል?” አበበ፡- ዜማ የእግዚአብሔር ስጦታ ነው። ማንም ያሰለጠነኝ
የለም። ግን ዝንባሌዬን አይተው የደገፉኝ አሉ። የአምስተኛ ክፍል
“አይ አይጠፋብኝም”
አስተማሪዬ፣ እህቶቼ ደግፈውኛል። ዘሜም አብሮ በመስራት
አነቃቅቶኛል። ፀጋዬ ደቦጭ ብዙ ነገር አድርጎልኛል። ከይልምሽ
“በቃ ለገሃር ስትደርስ በዚህ ስልክ ደውልልኝ” አለና ሃምሳ
ጋር መገናኘታችን ብዙ እንድሰራ አድርጎኛል። ሙሉቀን መለሰ
ብር ሰጠኝ። በሚቀጥለው ቀን ጊታሬን ይዤ ስሄድ ሃምሳ
አስተምሮኛል።ትምህርት ቤቴ ነው በለው። እሱን ከሚያህል
ሳንቲም ነው ለታክሲ የከፈልኩት። ከዚያ እኔ ቁጭ ብዬ በጊታር
ግዙፍ ዘፋኝ ጎን ሆኖ መስራቱ ራሱ የሚሰጥህ ብርታት
እዘፍንለታለሁ፣ እሱ እየተንጎራደደ ይከተለኛል። አብሮኝ
ቀላል አይደለም። በሌላ በኩል ኢትዮጵያ ውስጥ አንድ ሰሞን
ያዜማል። በመሃል ደግሞ “ቆይ ቆይ እንዲህ አትለውም?”
የባዕድ ዘፈኖችን ነበር የምንሰማው። ከውጪ የመጡ ዘፈኖች
ይለኛል በዜማ፣ ያራቅቀዋል። እና አብሮኝ ይላል። ይህን ሁሉም
ከስልት (style) አንፃር ተፅዕኖ ያደርጉ ነበር። ቡጊ፣ ማሪንጌ፣
ይቀርፀዋል።መቼም እኮ ከሙሉቀን ጋር መስራት ያስደስታል።

ቅፅ-1፣ቁጥር 1 መስከረም 2010 ዓ.ም ገፅ 44


ገፀ-ኅሩያን ታዛ

ቻቻ፣ ትዊስት፣ ምናምን ነበር። የውጩን ሙዚቃ ማወቅ የሙዚቃ ትርኢታቸውን በሚገባ ይመለከታሉ ይላል። አንተ
ጥሩ ነው። የሚጠቅመንን መውሰድም ክፉ አይደለም። ዋናው ይሄን እንዴት ታየዋለህ?
እኛስ የት አለን? ያኛው የማነው? የእኛ የእኛ ነው። ለዓለምም
የሰጠን ነን። ቅዱስ ያሬድ ኖታ የፃፈውና ያንን ሁሉ ድርሰት አበበ፡- ይኸውልህ፣ የጋናን ሙዚቃ ስንት ቀን ይመለከቱታል?
የደረሰው ከክርስቶስ ልደት በኋላ በአምስት መቶ ዓመት ገደማ ነው ጥያቄው። አንድ ቀን ሁለት ቀን ሊያዩት ይችላሉ።
ነው። እነ ሞዛርት እኮ ኋላ ነው የመጡት። እኛ እኮ ከሁሉም እንጂ እንደአሜሪካ ሙዚቃ ይደመጣሉ ማለት አይደለም።
ቀድመን ኖታ የፃፍን ነን። ከዚያም በላይ እንደውቅያኖስ የሰፋ የማዶና የዘር ሃረግ ከጣሊያን እንደሆነ ይነገራል። አዘውትራ
የሙዚቃ ኖታ ነው ያለን። ብዙ አላዋቂዎች ግን ‘የኢትዮጵያ የምትዘፍነውና የታወቀችው ግን በእንግሊዝኛ ሥራዎቿ ነው።
ሙዚቃ ባለ አምስት ቅኝት ስለሆነ ጠባብ ነው፣ የፈረንጆች የኛው አቤል ኢትዮጵያን አስጠራ እንጂ ታዋቂ የሆነው የነሱን
ግን ሰፊ ነው’ ይላሉ። የትግርኛ ሙዚቃ ባለ ሰባት ቅኝት ነው ሙዚቃ ስለተጫወተ ነው። የኛን ሙዚቃ ቢጫወት ማን
እንደውጪዎቹ። አንቺሆዬ ለኔ፣ ባቲ፣ አምባሰል፣ ትዝታ፣ ይሰማዋል? አየህ የነሱ የነሱ ነው፣ የኛ የኛ ነው። የነሱ ሙዚቃ
ትዝታ ማይነር … እንደ ኢትዮጵያ የተንበሸበሸ በዓለም ላይ ለምን ተሰሚ ሆነ? ካልን ጉልበት ስላላቸው፣ ወሳኝና ተፅዕኖ
የለም እኮ ነው የምልህ። በጣም ሃብታሞች ነን። አንዳንዶቹ ፈጣሪ ስለሆኑ ነው። እንጂ የነሱ ተነጥሎ ዓለማቀፍ ነው ሊባል
ደግሞ ሙዚቃችን ሌሎቹ የደረሱበት ዓለማቀፍ ደረጃ እንዲደርስ አይችልም። በኖታ ተመርተን፣ህጉን ተከትለን እስከሄድን ድረስ
ምንትሴ ቅብጥርሴ ይላሉ። የፈለግክ ብትሰራ ማን ይሰማልሃል? እኛ የምንጫወተውም፣ ጋናዎች የሚጫወቱትም፣ አሜሪካኖች
በመሠረቱ የእያንዳንዱ ሃገር ዘፈን ለየራሱ ኢንተርናሽናል የሚጫወቱትም፣ ጣሊያኖች የሚጫወቱትም ሙዚቃ ዓለማቀፍ
ነው። ለአሜሪካውያን የአሜሪካ ዘፈን የራሳቸው ነው። ማነው ነው። ነገር ግን የማንም አገር ሙዚቃ አሜሪካ ሄዶ አንደኛ
ኢንተርናሽናል አድርጎ የሰጣቸው። እንደዛ የሚባል ነገር የለም። ሊሆን አይችልም። የውጪ ሙዚቃዎችን መስማት የለብንም?
ኖታ ብለው ያመጡት ጣሊያኖች ናቸው “ዶ ሬ ሚ ፋ ሶ ላ ሲ እንሰማለን። እኔ ለምሳሌ የጥቁር አሜሪካውያንና የህንዶችን
ዶ” ብለው የሰጡን። መስማት ደስ ይለኛል። ያገራችንን ሙዚቃ ዝቅ ስናደርግ ግን
በጣም ይሰማኛል። እርግጥ ብዙ መስራት ያለብን ነገሮች አሉ።
ታዛ፡- ምናልባት እዚህ ላይ የሚነሳው ነገር፣ ለምሳሌ ጋሽ ኖታዎችን በትክክል ማወቅ ያስፈልጋል። አሁን አንዱ “ዘፋኝ ነኝ”
ተስፋዬ ለማ የሚለው ሙዚቃችን በየትም ሃገር እንዲደመጥ ብሎ ብድግ ይላል። ስለሙዚቃ ግን ምንም አያውቅም። በሌላው
በትምህርት ላይ መመስረት አለበት ነው። ኖታ ማንበብ የሚችሉ፣ ዓለም ከልጅነታቸው ጀምሮ ፒያኖ ላይ ነው የሚቀመጡት።
የሙዚቃን ቋንቋ የሚረዱ ሙያተኞች ሊኖሩን ይገባል። ይህ ሙዚቃንም በትክክል እየሰሙ ነው የሚያድጉት። ታዲያ
ሲሆን ነው በነሱ መደበኛ መድረክ (Mainstream) ገብተን ሲያድጉም ሆነ ሙዚቀኛ ሲሆኑ አውቀውት ነው የሚሰሩት።
ልንደመጥ የምንችለው ነው። እዚህ ላይ የጋናን ሙዚቀኞች እኛ አገር ውስጥ ይህ ይጎድላል። ወደሙዚቃው ዓለም የሚመጡ
በምሳሌነት ያመጣል። ቋንቋቸውን የማይሰሙ አሜሪካውያን ሁሉ መሠረታዊ የሆኑትን እውቀቶች ማወቅ ይኖርባቸዋል።

ቅፅ-1፣ቁጥር 1 መስከረም 2010 ዓ.ም ገፅ 45


ታዛ ገፀ-ኅሩያን

የሙዚቃን ቋንቋ ሳያውቁ እኮ ዘፋኝ መሆን ያስቸግራል።ስለዚህ ተዘጋጅቶልሃል” አሉት።


አስፈላጊው ነገር ሃገራችን ውስጥ የሚበቅሉ ዘፋኞችን
በህፃንነታቸው ሙዚቃ ላይ ማስቀመጥ ነው። ሲያድጉ የትም “እኔ ከመጀመሪያው ጀምሮ ከነሱ ጋር ነው የምሰራው። አሁንም
ሃገር ሄደው ሲዘፍኑ በልበሙሉነት ይሆናል፣ አይሳሳቱም። ከነሱ ጋር እየሰራሁ ነው።”

ታዛ፡- በሙዚቃ ሥራህ በጣም የተደሰትክበትን ቀን “በኋላ ችግር ቢፈጠርብህ እነዚህን ልጆች አምነህ…”
ታስታውሳለህ?
“በነሱ ላይ እምነት አለኝ። ሁሌም ከነሱ ጋር ነው የኖርኩት።
አበበ፡- የሚገርምህ ነገር እንደዛ ብዬ አስቤ አላውቅም። ሥራዬን አሁንም ከነሱ ጋር ነው መስራት የምፈልገው።”
ስጨርስ ይሳካ ይሆን? እንዳሰብኩት ሆኖ ይወጣ ይሆን? እያልኩ
“ሰርታችኋል ታዲያ?”
ነው የምጨነቀው።
“አዎ ሰርተናል” ይላል ይልምሽ።
ታዛ፡- የተከፋህበትንስ ቀን?
“ከሰራችሁ ሳምፕሉን (ናሙናውን) ቀርፃችሁ አምጡ ዛሬውኑ።”
አበበ፡- በሙዚቃ ምክንያት?
“ዛሬማ አይቻልም” አለ ኤፍሬም፣ ደፈራቸው። “ደክሞኛል፣
ታዛ፡- አዎ፣ በሙዚቃ ስራህ ምክንያት። ተመልሼ መምጣት አልችልም። ነገ ወይም ከነገ ወዲያ ይዘን
እንመጣለን።”
አበበ፡- እኔ ፈጠራ ውስጥ ስሆን ዝም ብዬ እመሰጣለሁ።
እንደውም አንዳንዱን ነገር ሰዎች ኋላ ሲነግሩኝ ነው እንጂ “ነገ አይደለም፣ ነገ ጠዋት!”
የምናገረውን አላውቀውም። ምንጊዜም የተሻለ ስራ ይዞ
የመውጣት ፍላጎት ነበረኝ። አንዳንዴ እልህ ውስጥ ገብተህ አየህ አዲስ ሰርተን እንዳናመጣ ነው። እሺ አልንና ተያይዘን
ለማሸነፍ የምትሰራበት አጋጣሚ ይኖራል። አንድ ታሪክ ሄድን። ቶሎ ብለን ምሳችንን በላንና ተቀመጥንበት።
ልንገርህ። ፊት የተከፋሁበት ኋላ ደግሞ በውጤቱ የተደሰትኩበት አልሰራነውምኮ፣ ይልማ ነው በድፍረት የተናገረው። እኔ ቤት
ነገር ነው። የተያያዘ ጉዳይ ነው። “የብሩህ ተስፋ እሸት” የተሰኘ ሆነን ጊታራችን ያዝንና አልነው በቃ።
ካሴት ለማውጣት በሙዚቃ ማህበር አማካይነት ጥረት ይደረግ
ነበር። ኮሎኔል መንግስቱ ሃይለማርያም የሰፈራውን አካባቢ “እመጣለሁኝ ሙናናዬ
ሄደው ጎብኝተው ነበር። የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችም ለሰፋሪዎች
ጎጆ ሊሰሩ የዘመቱበት ወቅት ነው። ሮሃ ባንድ እዚያው ፍቅር ነው ጎዳናዬ”
ድረስ ሄዶ ትርኢት ሁሉ አቅርቧል። እና በዚያን ወቅት እኛ
ብዙ ችግር ነበረብን። አንደኛ ገና ወጣቶች ነን። እነሱ የቆዩ ባንድ ሌሊት አጠናቀቅንና አይናችን በርበሬ መስሎ ይዘን
ናቸው። በዚያ ላይ ባለስልጣኖችም አሉባቸው። ያኔ የመንግስት ሄድን። ከዚያ ሲያዩን ሳቁ በቃ።
ሰራተኛ ወይም ፖለቲከኛ ካልሆንክ ተቀባይነትህ እምብዛም
“አይ ቁጭ ብላችሁ ስትሰሩ አድራችሁ ነው የመጣችሁት።
ነው። እና የመንግስት ሰራተኞች የሆኑ፣ ከነሱ ጋር የሚሰሩ
ምንም ለውጥ አታመጡም።”
አንዳንድ ከውጪ ሃገር ተምረው የመጡ ነበሩ። ታዲያ ከነሱ
ጋር ካልሰራችሁ እያሉ ተፅዕኖ የሚያደርጉብን ነበሩ። ከኛ ሁለት ዜማዎችን ነው ይዘን የሄድነው። አንድ ዝግ ያለም ነበር
አምስት ከነዚያ አምስት አድርገን ካሴት አብረን እንድናወጣ አሁን የማላስታውሰው። ቀሪ እኔ ጋር ስላልነበረኝ እንዴት
እያሉ ስራችንን ያጓትቱብን ነበር። በኋላ ነጋዴው ዞር በሉ ይቆጨኛል መሰለህ። ሙዚቃ ማህበር ውስጥ ነው የነበረው።
ማለት ጀመረ። ታዲያ “የብሩህ ተስፋ እሸት” በሚሰራበት ጊዜ ይሄኔ ተዘርፏል። ከዚያ ጎዳናዬን ሲሰሙት ተደነቁ። በተለይ
እናንተን አልጠራናችሁም ተብለን ተከለከልን። እንደውም አንድ አቶ ፋንታሁን አንተአለኸኝ።
ጊዜ የኩኩ ሰብስቤን ካሴት ከኤሌክትራ ሙዚቃ ቤት ጋር
ልንሰራ ስንሄድ “እኛ እዚህ ሌላ ስራ እየሰራን እናንተ የነጋዴ “ለነገሩ ደህና ሰርታችኋል፤ ዘፈናችሁ ጥሩ ነው። አስር አለቃ
ስራ ይዛችሁ ትመጣላችሁ?” ብለው አባረሩን። በሚቀጥለው እገዳውን አንሳላቸው ለማንኛውም። ነገ ጠዋት ጭቃ ሲያቦኩ
ቀን ስንሄድ ደግሞ “ታግዳችኋል” አሉን። “ለምን መጥታችሁ እናገኛቸው የለ!” አየህ እንደጠላት ነው የሚያዩን እኛን። ከዚያ
አልተሳተፋችሁም?” በዚያን ጊዜ ከአንድ መቶ ሃያ በላይ ለኤፍሬም ነገርነውና ሄደን ተኛን፣ እሱም ተኛ። በማግስቱ እኔ
ዜማዎች በተለያዩ ባለሙያዎች ተዘጋጅተው ነበር። ለኤፍሬም፣ ቤት ተገናኘንና በሁለት ቀን ውስጥ ቅንብሩን ሰራን። በማግስቱ
ለማህሙድ፣ ለሂሩት፣ ለብዙነሽ … ሁሉ ተዘጋጅቷል። ታዲያ ነው እንደዚህ ቀረፃው ይደረግ ነበር። ልክ እኛ ስንገባ ታምራት
ስንሄድ “እናንተ የአብዮቱ ስራ ሲሰራ፣የአገሪቱ ትልቅ ስራ ሞላ “ፍቅሬ ሆይ ልንገርሽ” የሚለውን ስራውን እየተጫወተ
ሲሰራ የት ነበራችሁ?” ነበር። ብዙዬ ነበረች፣ እነ ፀሐዬ ዮሐንስ፣ ወንድሙ ቶላ ነበሩ።
ይልማ ጎበዝ ነው።“እኛ እኮ ሰርተናል” ይላቸዋል። “የኛ ተራ መቼ ነው?”አላቸው ኤፍሬም። ሲናገር እኮ ያኮረፈ
ነው የሚመስለው። እኔ ያኔ የሆነ ቀይ ጃፖኒ ነገር ለብሻለሁ።
“ለማን?” እና ብዙዬ “ይሄ አረቡ ልጅ ማነው?” ትላለች። “የዘመነ መለሰ
ወንድም እኮ ነው” ይሏታል። “ውይ በሞትኩት! የዘሙዬ ወንድም
“ለኤፍሬም”
ነው እንዴ?” አለች ብለው ነገሩኝ። ቀጥሎ አመልማል ገባችና
“መቼ የሰራችሁት ነው? አምጡት ኤፍሬምን!” “ገዳም ገደምዳማዬ” የሚለው ዘፈን ተቀረፀ። ከዚያ የኛ ተራ
ደርሶ ይጀመር ሲባል “እኛ ሙዚቃውን ጨርሰን መጥተናል”
ስንሄድ ኤፍሬም ባጋጣሚ ለስራ ሐረር ይሁን ጅጅጋ ሄዶ አልናቸው። ከዚያ ኤፍሬም “አስጠናቸው” አለኝ። ማይክሮፎን
ቆይቶ ገና መምጣቱ ነው። ነገርነውና እሺ ብሎ ተያይዘን ጋ ሄድኩና ዳዊትን ሳነጋግረው፣ “እስኪ ኤፍሬም ዝፈነው”
ሄድን። ይወደናል፣ በቃ ጓደኞች ሆነን የለም? ከዚያ በር ላይ አለው፣ ዘፈነው። ቅኝቱን ምኑን አስተካከሉና “አበበ ሙዚቃውን
ስንደርስ “አሁን ምንድነው የምላቸው” አለን። “አይ ችግር የለም አስጠናን” አለኝ። አንዴ ወጣሁላቸውና ያዙት። አንዴ ከያዙ
እኛ አብረን እንናገራለን” አለው ይልማ። ስንገባ “ኤፍሬም! አይለቁም። ፈቃደና ዮናስ እኮ የሚደንቁ ናቸው። ኤፍሬም
እኛኮ እዚህ መቶ ሃያ ምናምን ዜማዎች አሉን። ምርጥ ዜማ እየተጫወተ ደግሞ ተለማመድነው። ኤፍሬም ይዘፍናል፣ እኔ
አንድ ማይክሮፎን ይዤ ሙዚቃውን እላለሁ።

ቅፅ-1፣ቁጥር 1 መስከረም 2010 ዓ.ም ገፅ 46


ገፀ-ኅሩያን ታዛ

አንደኛው ዙር አልቆ ሁለተኛው ዙር ላይ ኤፍሬም ይግባ ጠይቆኝ እኔም ድምፁን ሰምቼው ፈቃደኛ ሆኜ ነበር። በዚያን
ተባለ። ገባና አንደኛው ዙር ተቀረፀ። ሁለተኛው ዙር ሊቀረፅ ጊዜ ከሰራናቸው ካሴቶች አንድም እንኳ የወደቀ አልነበረም። የነ
ሲል ረዘመ ተባለ። እና አስቆሙት የሙዚቃ ማህበሩ ሰዎች። ኤፍሬም ታምሩ፣ አመልማል አባተ፣ ራሄል ዮሐንስ፣ አረጋኸኝ
ኤፍሬም አይሆንም አለ። በኋላ እኛ ነን ለምነነው “ግድየለህም ወራሽ፣ ቴዎድሮሰ ታደሰና የመሳሰሉት። በወቅቱ ወረፋ ስለነበረ
እንደጣፈጠ ይለቅ” ብለነው እሺ ብሎ የተቀረፀው። የተወሰነ “ከሶስት ወር በኋላ እንደዚህ ኑ” እላቸዋለሁ። ሆኖም አሳታሚው
ክፍሉንም ቆረጡት። ካሴቱ ሲወጣ ደግሞ በ “ቢ” በኩል ሙዚቃ ቤት ትዕግስት ስላጣ የሆነ ቦታ ወሰደው። ስራው
አደረጉት። ቦታ አልሰጡትም። ብዙውን ጊዜ ጥሩ ጥሩ ስራዎች ግን እንደጠበቀው አልሆነለትም። ምናልባት ያቺን አጋጣሚ
በ “ኤ” በኩል ነው የሚወጡት። ከዚያ ሲለቀቅ ነጥሮ ወጣ። ተጠቅሞባት ቢሆን ኖሮ ዛሬ ወይ እንደኤፍሬም ወይ እንደ
ሰዉ በጣም ወደደው። እንደውም ካሴቱን ብድግ አደረገው አረጋኸኝ የሚታይ ይሆን ነበር። ከዚያ በኋላ ወደ ሐረርጌ ሄጄ
ማለት ትችላለህ። እኔና ይልምሽ ፍሎሪዳ የሚባል ቡናቤት ቢራ ለሁለተኛ ጊዜ ተገናኘን። እንደገናም አዲስ አበባ ስንገናኝ በጣም
ልንጠጣ ስንሄድ ማንን እናያለን አቶ ፋንታሁንን፣ የሙዚቃ ተቀራረብን። የረሳሁት በሁለት ሺህ ይመስለኛል በሬዲዮ ቀርቦ
ማህበሩን ፀሐፊ። “አይ ሌላ ቦታ እንሂድ” ብለን ልንመለስ ስንል ሲዘፍን መኪና ውስጥ ሆኜ ሰማሁት። ድምፁ መቼም ልዩ
“ኑ ኑ ልጆቼ” ብሎ እኔንና ይልምሽን በግራና በቀኝ ይዞ “ቁጭ ነው። የኬነዲንም ጥሩ አድርጎ ይጫወታቸዋል። እና ከእሱ
በሉ ልጆቼ፣ ከጉድ አወጣችሁን” አለን። ለካስ የፖለቲካ ጉዳይ ጋር ዜማዎችን መርጠን መስራት ጀመርን። እስካሁን ወደ
ኖሯል። ባይሳካ ኖሮ ብዙ ጣጣ ሊያመጣባቸው ይችል ነበር። አስራ ሁለት የሚደርሱ ሙዚቃዎችን ቀርፀናል። አንድ ሁለት
ይቀሩናል። የመጣሁትም ለዚሁ ነው።
ታዛ፡- ለኢትዮጵያ ሙዚቃ እድገት እንቅፋቶች ናቸው
የምትላቸው ነገሮች አሉ? ሁለተኛ ጥሩ ድምፅ ያለው ልጅ አለኝ። ሙሴ አበበ ይባላል።
እና የሱን ስራዎች ከኤልያስ መልካ ጋር ሆነን እየሰራን ነው።
አበበ፡- ሙዚቃ መቼም የፈጠራና የተሰጥኦ ጉዳይ ነው። የሱ ታላቅም አለች። የሚገርም ድምፅ ያላት። ኤዶም ትባላለች።
ጥበብ ከላይ ነው የምትመጣው። ስሜትህ ሲነካ የምትፈጥረው ግን አልሰራችበትም። ትምህርቱ የላትም።
እንጂ እንደሌላ ማናቸውም አይነት ስራ ‘እስቲ ልስራ ብለህ’
የምትቀመጥበት አይደለም። ጥበብ ስትመጣ ቃላቱንም፣ የዜማ ታዛ፡- ተከታዩ ጥያቄ የልጆችህን ዝንባሌ የሚመለከት ነበር።
ፍሰቱንም ይዛልህ ነው የምትመጣው። እንቅፋቱ ሙያተኛው ለመሆኑ የሙሴን ችሎታ እንዴት አወቅከው? በቤት ወይም
ሙያውን አለመያዙ ነው። ትክክለኛው ባለሙያ በትክክለኛ በትምህርት ቤት አካባቢ ያንጎራጉር ነበር?
ቦታው ላይ አይደለም። ከሙያው በላይ የገንዘቡ ፍቅር ነው
ጎልቶ የሚታየው። ዝና ፍለጋው ነው ደምቆ የሚታየው። አበበ፡- እኔ ውጪ እያለሁ በሸገር ሬዲዮ ከመዓዛ ብሩ ጋር አየር
እንዲህ አይነት ሰዎችም ሆኑ ሥራዎቻቸው ደግሞ እድሜ ላይ ሆኖ ሲዘፍን ነው የሰማሁት። በጣም ተገረምኩኝ። ከዚያ
አይኖራቸውም። የአንድ ሰሞን ሆይ ሆይታ ነው። በድርሰት እስራኤል መጥቶ ከእኔ ጋር ሲገናኝ ማሻሻል ጀመረ ራሱን።
ስራ ላይ ትክክለኛ ባለሙያዎች አለመሰለፋቸው፣ ተገቢው ዜማ ባለፈው ዓመት አብረን መጥተን ነበር። የተወሰኑ ዜማዎችን
ለተገቢው ዘፋኝ አለመሰጠቱ፣ ትክክለኛ ባለሙያዎች የሚሰሩበት መርጠን ስቱዲዮ ውስጥ ገብተን ሰራነው። አሁን ደግሞ አንድ
ምቹ ሁኔታ አለመኖሩ፣ እነዚህን ልጠቅስልህ እችላለሁ። አሁን ሁለት ዜማዎችን ከኤልያስ መልካ ጋር ለመስራት እቅድ አለኝ።
ከነኤልያስ መልካ ጋር የጀመርነው ስራ ውጤታማ ከሆነ የተሻለ ከተሳካ ደግሞ ሌላ ከእስራኤል ሃገር የመጣች እህታችን አለች።
ሁኔታ ይፈጠራል ብዬ አምናለሁ። አሁን ያሉ ደራሲያን የእኛን እዚያ ነው ተወልዳ ያደገችው፤ አማርኛ ብዙ አትችልም። እና
ዘመን አይነት ስራዎች የማይፈጥሩበት ምክንያት የለም። ግጥሙን አማርኛ አድርጌ ሰርቼላታለሁ። የእሷንም ስራዎች
ይህን በእርግጠኛነት ነው የምነግርህ። ለምን ደራሲ ተጠቃሚ ከጃኖ ባንድ ጋር ለመስራት ፕሮግራም ይዘናል። ሌላው
የሚሆንበት ስርዓት ካለ ፈጠራን ያነሳሳል። ሁሉም በፈጠራ ሥራዎቼ እየተዘረፉ ነው ያሉት። ይሄን ሳላሰምርበት ማለፍ
ስራው በአግባቡ ተጠቃሚ ይሆናል። በሙሉ ነፃነት የሚሰራ አልፈልግም። አሁን ለእንዳለ ካዘጋጄናቸው ስራዎች እንኳ
ሰው ውጤታማ ይሆናል። የሌሎችን ስራ እየቦጫጨቁ መውሰድ ሁለቱ ተወስደውብናል። በጣም የምንጠብቃቸውን ስራዎች
ይቆማል። ወስደው ሰርተውብናል። የሚገርመው አትስሩ እያልኳቸው እኮ
ነው። በራስህ ሃብት ንብረት አለማዘዝ፣ በቤትህ በርህን መቆለፍ
ታዛ፡- ኢንተርኔትና ማህበራዊ ሚዲያው የተስፋፋበት ዘመን አለመቻል በጣም ያሳዝናል። ማንም የደከምኩባቸውን ንብረቶቼን
ነው። ይህ ደግሞ አዎንታዊም አሉታዊም ገፅታዎች አሉት መንካት አይችልም። ግን እየተነኩ ነው፣ ህግ እንደሌለበት ሃገር
ተብሎ ይታመናል። አንተ ምን ታስባለህ? ሙዚቃ መጫወቻ እየሆነ ነው። እንደፈለጉ እያነሱ እንደፈለጉ
የሚወስዱብህ ከሆን በጣም ነው የሚዘገንነው። አንዳንድ ሰዎች
አበበ፡- እኔ በሁለት መንገድ ነው የማየው። በመጀመሪያ ደረጃ እነሱን ደግፈው ሲናገሩ “ምናለበት ቢዘፍነው” ሲሉ እሰማለሁ።
በአሁኑ ወቅት ቴክኖሎጂው ፈቅዶ በቀረፃ ወቅት እንደድሮው እኔ ግን የዘራፊዎቹ ተባባሪዎች አድርጌ ነው የማያቸው። ይሄን
የሚባክን ጊዜ የለም። ስራ ያቀላጥፋል። አንዳንድ የሚያሳንፍ ጊዜ ልጃቸውን ሰርቀው ቢወስዱባቸው እንዴት እንደሚሰማቸው
ነገር ቢኖረውም። ማህበራዊ ሚዲያው በጣም በአጭር ጊዜ የገባቸው አልመሰለኝም። ፈጠራምኮ አምጠህ የምትወልደው ነገር
ውስጥ ሙዚቃን በየትኛውም የዓለም ክፍል ማዳረስ በማስቻሉ ነው። አንዳንዶቹማ ዘርፈውህም፣ አትስሩ እያልካቸውም ስምህን
በብዙ ሚሊዮን ህዝብ እንዲደመጥ ምቹ ሁኔታ ፈጥሯል።
ኢትዮጵያም ውስጥ እንዲሁ ነው። ጉዳቱ ምንድነው መቆጣጠር
አለመቻሉ ነው። የፈጠራ ባለመብቶች ተጠቃሚ እንዳይሆኑ
እያደረገ ነው። ፊት ሲዲ ነበር፣ ከዛ ፍሎፒ መጣ አሁን ደግሞ
በፍላሽ ሆኗል። ይሄ እንግዲህ በመላው ዓለም የሚታይ ነው።
ባይሆን እዚያ ኦርጂናል ያልሆኑ ሥራዎችን አትግዙ ሲባል
የሚያዳምጠው ስለሚበዛ፣ አቅምም ስላላቸው ችግሩ ጎልቶ
የሚታየው በአፍሪቃና በመሳሰሉት ገና በማደግ ላይ ያሉ
አካባቢዎች ነው።

ታዛ፡- አሁን ምን እየሰራህ ነው?

አበበ፡- ይህ አጠገቤ የምታየው ወንድሜ እንዳለ አባተ ይባላል።


ጥሩ ድምፃዊ ነው። በ1978 ዓም አካባቢ ከእኔ ጋር ለመስራት

ቅፅ-1፣ቁጥር 1 መስከረም 2010 ዓ.ም ገፅ 47


ታዛ ገፀ-ኅሩያን
ጭምር አስወጥተው ይወስዱታል። እና እነሱን ለመፋረድም አበበ፡- አብሮኝ የነበረ ግን ተከተለኝ የምለው ትልቁ ሞገስ ተካ
ጭምር ነው የመጣሁት። ሆኖም ባለማወቅ የሰሩትን፣ ቢያንስ ነው። ሌሎችም አሉ። ሁለት ስላልከኝ ነው እንጂ እነ አበበ
ማንነቴን ያልደበቁትን በይቅርታ ላልፋቸው እችላለሁ። ብርሃኔ አሉ፣ ካሁኑ ዘመን ደግሞ ቴዲ አፍሮን እወድለታለሁ፣
በማንአለብኝነት፣ አይሆንም እያልኳቸው የወሰዱትንና ስሜን አደንቀዋለሁ። አማኑኤል ይልማን በተለይ። እንደዚህ ብዙ ስራ
ሳይቀር የካዱትን ግን እፋረዳቸዋለሁ። በማን ስም? በሞቱት መስራቱን አላውቅም ነበር። ብዙ ብዙ የማደንቃቸውን ስራዎች
በነተስፋዬ ለሜሳ፣ በነተዘራ ኃይለሚካኤል፣ በነተመስገን ተካና ለካስ የሰራቸው እሱ ነው። በቅርብ ጊዜ ነው ያወቅኩት።
በሌሎቹም ስም። እነሱ ሞተዋል። ልጆቻቸው መክሰስ ይችላሉ። እንደውም በዚህ አጋጣሚ አማኑኤልን ይቅርታ መጠየቅ
ነገር ግን አቅም ስለሌላቸው ወይም ስለማያውቁት ይሆናል እፈልጋለሁ። “ለትንሿ እንስጋ” እና “ሳታመኻኝ ብላኝ” የሚሉትን
በችግርና ዝናብ በሚያፈስ ቤት እየኖሩ ዝም ያሉት። ዘራፊዎቹ ጎሳዬ ተስፋዬ የተጫወታቸውንና የመሳሰሉትን ምርጥ ስራዎች
ግን ብዙ ብር እያፈሱበት ነው። እኔም እኮ ሞቼ ቢሆን ኖሮ የሠራ ነው፡፡
የልጆቼ እጣ ተመሳሳይ ይሆን ነበር።
ታዛ፡- ሙዚቀኛ ባልሆን ኖሮ ምን እሆን ነበር? ብለህ አስበህ
ከቅጂ መብት (ኮፒ ራይት) ጋር በተያያዘ ሌላ ልናነሳው ታውቃለህ?
የሚገባ ጉዳይ ያን ጊዜ እኛ ከሙዚቃ አሳታሚዎቹ ጋር ውል
የተፈራረምነው ለስድስት ወር ተባብለን ነው። እነሱ ግን እስከዛሬ አበበ፡- ሙዚቀኛ ባልሆን ምናልባት የምርምር ስራ ውስጥ
ድረስ እያተሙ ይሸጣሉ። ለዚህ ማስረጃው አለ። በአዲሱ ህግ የምገባ ይመስለኛል፡፡ ዝም ብዬ ሳስበው አስትሮኖሚ ይስበኛል፣
ደግሞ ለአምስት ዓመት ነው የሚፈቀድላቸው። ከአምስት ሁለተኛው የስነልቦና (Psychology) መስክ ነው።
ዓመት በኋላ ወደኛ መመለስ አለባቸው። ያን እያደረጉ ግን
አይደለም። ጭራሽ አሁን ደግሞ በባለመብትነት ገብተው የእኛን ታዛ፡- የመጨረሻ ጥያቄ፣ከምግብ የምትወደውን እስኪ በደረጃ
ገንዘብ እንደገና ለመውሰድ ይፈልጋሉ። እና ‘አመንጪዎች ነን አስቀምጥልን?
እንዲህ ነን’ እያሉ በተለያዬ መንገድ ለመውሰድ ይሞክራሉ።
ይሄንም እየተቃወምን ነው ያለነው። በርካታ ሙዚቀኞችም አበበ፡- አንደኛ ደረጃ እንጀራ በሽሮ ነው። ሽሮው ግን ትንሽ
ከኛ ጋር ናቸው። አንጋፋዎቹን እነ ማህሙድን፣ ዓለማየሁ ጨው የገባበት፣ የተንደከደከ፣ ቅመም የሌለበት፣ሽንኩርት
እሸቴን፣ ባህታ ገ/ሕይወትን ጨምሮ። ከተከታዮቹ ደግሞ እነ ያልገባበት ነው። ይሄ ምን ያስታውሰኛል መሰለህ ገጠር ዘመቻ
ነዋይ፣ ሃይልዬ፣ ማዲንጎ፣ ከአቀናባሪዎችም እነ ዳዊት ይፍሩ፣ ጣቢያ እያለሁ ትንሽ ቅባዕ ኑግ የገባበት የባላገር ሽሮ። ምስርም
ኤልያስ መልካ፣ ካሙዙ፣ ከደራስያን እኔ፣ አበበ ብርሃኔ፣ ሞገስ እወዳለሁ። ቀጥሎ ክትፎ፣ ግን በሳምንት አንድ ቀን ነው። ስጋ
ተካ፣ ፀጋዬ ደቦጭ፣ ይልማ ገ/አብ፣ እነሱ እነሱ ያሉበት ነው። ደግሞ ቅባትና ሽንኩርት ያልገባበት ግንፍልፍል ብሎ የወጣ።
ሕዝቡም ከጎናችን እንደሚቆም እርግጠኛ ነኝ።
ታዛ፡- አቤ፣ በጣም ነው የምናመሰግነው። ጥሩ ጊዜ ነው
ታዛ፡- በሺዎች የሚቆጠሩ ሥራዎች እንዳሉህ ነው የሚነገረው። ያሳለፍነው፡፡ እግዜር ይስጥልን።
ከነዚህ ውስጥ አምስት ምረጥልኝ ብልህ የትኞቹን ትመርጣለህ?
አበበ፡- እኔም ደስ ብሎኛል፣ አመሰግናለሁ።
አበበ፡- ትልቁና ዋናው “ኢትዮጵያ” ነው።

ታዛ፡- ጥላሁን የተጫወተው?

አበበ፡- አዎ፣ቴዲ ማክ ነው ሙዚቃውን ያቀናበረው፣ ዜማውን


እኔ ነኝ የሰራሁት።

ታዛ፡- ግጥሙ የዓለምፀሐይ ነው አይደል?

አበበ፡- ትክክል! ግጥሙ የዓለምፀሐይ ወዳጆ ነው። እንደ ዜማ የእግዚአብሔር ስጦታ


ኢትዮጵያ ሕዝብ መዝሙር በየሄድክበት ቦታ ሁሉ የምትሰማው
ነው። ሁሉም ሃገሩን እያስታወሰ የሚያለቅስበት ነው። ነው። ማንም ያሰለጠነኝ
ሁለተኛው “መተባበር ቢኖር”፣ ቀጥሎ “ሙዚቃ” ነው። ከዚያ
“ሰላም” ማህሙድ የተጫወተው ነው። ይህም የሚያስደምመኝ የለም። ግን ዝንባሌዬን
ሥራ ነው። ሌላው ምንጊዜም የምወደው ዘፈን “አካሌ” ነው።
ኤፍሬም ታምሩ የተጫወተው። ይልምሽ ነው ግጥሙን ቆንጆ
አድርጎ የሰራው። እንግዲህ አብዛኞቹ ሃገርን የተመለከቱ
አይተው የደገፉኝ አሉ።
ስለሆኑና ስሜት ስለሚሰጡኝ ነው። ከፍቅር “አካሌ” በጣም
ይመስጠኛል።

ታዛ፡- እስኪ ከምታደንቃቸው የዜማ ባለሙያዎች ከቀደሙህ እኔ ፈጠራ ውስጥ ስሆን


አንድ ከተከተሉህ ደግሞ አንድ ንገረኝ?
ዝም ብዬ እመሰጣለሁ።
አበበ፡- ተስፋዬ ለሜሳ ምንም የማልጠራጠርበትና የማደንቀው
የዜማ ባለሙያ ነው። ሁለተኛው ነዋይ ደበበ ነው። ከተከተሉኝ እንደውም አንዳንዱን
ሳይሆን አብሮኝ ነው የጀመረው። የነዋይን ድርሰቶች ምንጊዜም
ሳደንቃቸው ነው የምኖር። ነገር ሰዎች ኋላ ሲነግሩኝ
ታዛ፡- ጥሩ ነው ጥያቄዬን አስተካከልክልኝ። ተስፋዬ ለሜሳ
ከቀደሙህ፣ ነዋይ ደበበ ካንተ ዘመነኞች፣ አንድ ከተከተሉህ ነው እንጂ የምናገረውን
ብለን ወደ ሶስት እናሳድገዋ።
አላውቀውም።
ቅፅ-1፣ቁጥር 1 መስከረም 2010 ዓ.ም ገፅ 48

You might also like