You are on page 1of 56

ወርሐዊ መጽሔት | ዕትም ፫ | ፳፻፲፭ ዓ.

የካሮ
ጎሳ
ሶስተኛ ዕትም ሳንኮፋ የአንባብያን ማኀበር - ጎንደር ኢትዮጵያ1

ነሐሴ ፳፻፲፭

ማውጫ
8 ቅንጭብጭብ ጭረት

10 ትዝብት ከእስክንድር ጋር

14 የካሜራ ተዓምር

17 እህት ቤተመጽሐፍ

20 ጥበብና ባሕል

28 ግጥም

34 ተናጋሪ እርሳሶች

37 ደብዳቤ

38 መጽሐፍ ዳሰሳ

40 ተናጋሪ ቀለማት
43 የመንገደኚት መጣጥፍ
49 ቅዳሜን ከሳንኮፋ ጋር
50

20
ጥበብና ጤና

51 የፊልም ዳሰሳ
54 የሳንኮፋ ትውስታዎች
55 ስለ እኛ
2 ጭረት
አምደኞች
ርብቃ ያሬድ
የመጽሐፍ ዳሰሳ

ክንዱ ፈጠነ
ከእስክብድር ጋር(ትዝብት

ሊያ
ቅንጭብጭብ ጭረት

በኃይሉ ዘአዋሽ መልካሳ


እህት ቤተመጽሐፍ

0
ራሔል ስሜነህ
ደብዳቤ

ሶስተኛ ዕትም 3
ነሐሴ ፳፻፲፭

መልዕክተ ጭረት
ተወዳጆች ሆይ
ሰላም ለእናንተ ይሁን፣ ይህ ሦሥተኛ የጭረት ዕትም ነው፡፡
ጭረት ለመጀመሪያ ጊዜ በሰኔ 2015ዓ.ም በሳንኮፋ የአንባብያን ማኅበር ተዘጋጅታ በበይነ መረብ የወጣች
ወርሐዊና ጥበባዊ መጽሔት ናት፡፡
አንባብያን ከመፅሐፍት ቀነጫጭበው ከከተቡት፣ መንገደኞች ከህይወት አጋጣሚዎቻቸው መዝግበው ካሰፈሩትና
ከታዘቡት፣የካሜራ ሌንሶች ካስቀሩት፣ በብሩሽ ከተቀቡና ከተሳሉ አውጣጥታ ይሄን ሦሥተኛ ዕትሟን እንደ ነፍስ
ቅርበቶቻችሁ ዘንቃ ለእናንተ ለአንባቢዎቿ እና የሳንኮፋ ወዳጆች ታበረክታለች፡፡
እናንተም ጫር ጫር በማድረግ አንብቧት፡፡

ሰናይ ጊዜ

ሁሉም ነገር በመጫር(ጠብቆም፣ላልቶም) ይጀምራል!!!


ጭረት

ሳንኮፋ የአንባብያን ማኅበር


እናንብብ፣እንለወጥ፣እናካፍል

4 ጭረት
ተዋወቁን ...
የጭረት አዘጋጆች

ፍናማርያም ኤሊያስ አዲሱ


አዘጋጅ/መንገደኚት አዘጋጅ/ጸሐፊ
ፍና በአካባቢ ጤና የ፩ኛ ዓመት የድህረምረቃ ተማሪ ኤሊሾ በሄልዝ ኢንፎርማቲክስ ፩ኛ ዓመት የድህረምረቃ
ስትሆን ደብዳቤና የሰዎች የህይወት ፍና(መንገድ) ተማሪ ሲሆን ግጥም ለነፍሱ የቀረበለት ሰው ነው።
ትምህርቶች ዓለሟ የሆነላት ሰው ናት:: እንደ ማርያም የበይነ መረብ ውስጥ እንቅስቃሴዎች ሰዎችን አንድም
መንገድ(ፍናማርያም) ሁሉ ሌሎች የህይወት መንገዶች ይገላሉ፣አንድም ያድናሉ ብሎ የሚያምነው እሱ በጥበብ
ማምለጫና ዕረፍት እንደሆኑ የምታምነው እሷ የበዙ ለመታደግ ሲል ጭረትን ፈጥሯል::
መልካም ፍናዎችን ለመፍጠር ጭረት ከትማለች።  @kidan_26
 @Markrylos

እጸህይወት ሚኪያስ
አዘጋጅ/አፍቃሪተ መጽሐፍት አዘጋጅ/ግራፊክስ ዲዛይነር
እጸ የ፪ኛ ዓመት ህክምና ተማሪ ስትሆን ሚኪ የ፬ኛ ዓመት ህክምና ተማሪ ሲሆን የሳፋየር
መጽሐፍትናንባብ የልብ ነገሮቿ የሆኑላት ሰው ናት። ግራፊክስ መስራችና ለንባብ ልዩ ፍቅር ያለው ሰው ነው።
መጽሐፍት የሰዎችን ዕይታዎች ይቀርጻሉ የሚል የግራፊክስ መንደር ከጥበብ ጋር ሲጋመዱ የሰዎችን ልብ
እምነት ያላት እሷ ሰናይ ዕይታዎችን ለመፍጠር ጭረት በበጎ እንደሚዳስሱ የሚያምነው እሱ በተቸረው ጸጋ
መሽጋለች። የሰዎች ልብ ለመድረስ ሲል ጭረት ተገኝቷል።
 @e123etse  @mikyasmaregie
ታዲያ አንቺ ኢትዮጵያ እኛስ ልጆችሽ ምንድን ነን?
አመንኩሽ ማለት የማንችል፣ፍቅራችን የሚያስነውረን
ዕዳችን የሚያስፎክረን፣ግፋችን የሚያስከብረን
ቅንነት የሚያሳፍረን፣ቂማችን የሚያስደስተን
ኸረ ምንድነን??

ሎሬት ጸጋዬ ገ/መድህን


የቴውድሮስ ስንብት ከመቅደላ
ቅንጭብጭብጭረት

“አቻሜ በፍቅረማርቆስ ደስታ”


ሊያ


ብሮነትንም እንዲህ ባለ መልኩ መመልከት ይቻል ዕድሜው ተቀጨ’ ብለን የምናዝን ነን - እኛ ሲዲዎች። ለዚህ ደግሞ

ኖሯል...... ወዲህ የኔ ብቻ ትክክል ወዲያ ዓለም በእኛ ዋናው ምክንያት አፍሪካዊ መሠረታችንን አለመልቀቃችን ነው።

ዙሪያ ብቻ ከሚሉት ተሻግረን ስንመለከት ምናገኛቸው “ኢትዮጵያ በአፈ ታሪክ እየሰማሁ እንዳደግሁት ወርቅ የሆነ ባህል

ህዝቦች ያስገርማሉ፥ ያስተምራሉ፥ ያስተዛዝባሉ ...... አላት፤ በተለይ ባህላዊ መሪዎችዋ ከሌላው የዓለም ክፍል በእጅጉ

”አየሽ አበባ - እኔ ሲዲ ነኝ፤ ከሰሜን ምዕራብ ሕንድ የመጣሁት የተለዩ ናቸው። ለምሳሌ የቦረና መሪ ወይም ገዳሚዎች መካከል

የቅድመ አያቶቼ እትብት የተቀበረባትን ኢትዮጵያን ለማየት ነው። ከፍተኛ የዕድሜ ልዩነት አለ። ታላቁ ግን ታናሹን ያደምጠዋል፤

‘ማንም ሲዲ የዘወትር ፀሎቱ ሐብት ማግኘት አይደለም የሲዲዎች የዕድሜ ልዩነት ከሃላፊነት እንደማያሸሽ፥ እንደማያስንቅ ..... የቦረና

ትልቁ ሃብታችን ፍቅርና መተሳሰብ ነው ....... ለሲዲ ህይወት ዋናው መሪዎች ገና ከጥንት ጀምሮ የገባቸው ናቸው። በቦረና መሪ ‘አባ

መሰረቱ መረዳዳት ነው። ከገነት ተፈጠርሁ ለሚል የጫካ ሰው በጉልበቱ’አይሆንም - ሰላም በጠመንጃ አፈሙዝ ትገኛለች እያሉ

ተጨማሪ ገነት አያሻውም፤ ደስ ብሎን እንኖራለን፥ በሽታ በቀላሉ ለደም መፋሰስ የአለምን ህዝብ የዳረጉት ሩቅ ምስራቆች ከአፍሪካ

እኛን አይደፍርም፥ የአገኘነውን ተካፍለን ከበሮአችንን እየመታን፥ ባህላዊ መሪዎች ሊማሩ ይገባ ነበር ። በአፍሪካ መሪነት ትልቅ ሃላፊነት

በፒኮክ ላባ ተውበን እንደንሳለን...... በሰማንያ ዓመቱ የሞተን ‘ካለ ነው፤ ደስታን፥ ምቾትን..... ይቀንሳል። በቦረና ገዳሚዎች በስልጣን

8 ጭረት
ዘመናቸው ያሻቸውን አይሰሩም፥ የተሻለ አይኖሩም፥ ጎጆአቸውን ጥያቄ ይፈጥራል እንዲያ የሚመካባቸው አለም ባወቃቸው ሲል

አይለቁም.... የግል ሃብት አያከማቹም። ይልቁንስ ስሜታቸው ሚያሞካሻቸው ህዝብና መሪዎችስ ...... ያን ያህል ሰፊ የነበረ ህዝብ

ይታፈናል፥ ፍላጎታቸው ይገደባል...... በአፍሪካ ባህል ህዝብ የመሪዎችን አሁን በጥቂት ባለ ጠባብ አዕምሮ ሀሳቦች ተውጦና ተከፋፍሎ ማየት

ማንነት የሚያሳይ መስታወት ነው..... ስልጣን ግን መስዋዕትነት እንዴት ያማል ........ እኔ ምን ነኝ ምንስ ነበርኩ ብሎ ከመጠየቅ

ነው....... ስልጣን አንገት መድፊያ ነው..... ስልጣን ህሊናንና እውነታውን ለመረዳት ከመሞከር ምን ያግዳል? ዛሬስ እኔ፥ አንተ፥

አቅምን መስጠት ነው...... ስልጣን ሃላፊነትን መወጣት ነው......... አንቺ ....... የቱ መስመር ላይ ነው የምንገኘው? (ኢትዮጵያ በአፍ

የሰለጠንሁ ባዩ ህዝብ መሪዎች ግን በቅድሚያ ቤተ-

መንግስት ያንፃሉ፥ ከህዝቡ ለመለየት፤ በአለባበሳቸው፥

በአኗኗራቸው

‘ሥልጣን ደካማውን
መብለጥ ነው

ኃይለኛ
የስራቸው

ያደርገዋል፤
መጀመርያ።

‘አትንኩኝ፥
“ኢትዮጵያ በአፈ ታሪክ
አትውቀሱኝ.......’ እያሉ ማስፈራራት ይሆናል መለያቸው፤ እየሰማሁ እንዳደግሁት
የራሳቸውን ቡድን ፈጥረው ህዝቡን እንደ አባያ በሬ ያምሱታል

....... የሚሉትን ስሙን እንጂ የሚባለውን አይሰሙም፥ ውሸት


ወርቅ የሆነ ባህል
ዲፕሎማሲያዊ ቋንቋቸው ይሆናል ....... ከዚያ ካለ እነሱ ዓለም አላት፤ በተለይ ባህላዊ
በጭንቅላቷ እንደምትተከል የሚያስቡ ግብዞች ይሆናሉ ......

‘ ከዙፋናቸው ግርጌ ያለው ሰው ሳይሆን ሲረግጡት የሚንቆሻቆሽ


መሪዎችዋ ከሌላው
ድርቆሽ ይመስላቸዋል ...... አበባ! ጊኒ፥ ማሊ፥ ሴኔጋል፥........ ኬንያ፥ የዓለም ክፍል በእጅጉ
ኢትዮጵያ ያሉት የባህል መሪዎች ከሰለጠንሁ ባዩ አንፃር ልዩነታቸውን

በርቀት መጠን መለካት ትልቅ ስህተት ይፈጥራል...... በጥቅሉ አይገናኙም


የተለዩ ናቸው።
ማለት ይቀላል። የሚያሳዝነው ግን ይህ ደግ የአፍሪካ ባህል ከዕለት ወደ

ዕለት እየቀጨጨ ያኛው እየደለበ የመምጣቱ ምስጢር ነው........... ምላሳችን ላይ ነው ወይስ ልባችን ነፍሳችን ውስጥ ያለችው? .......

አቻሜ ላይ የምናገኝው ከሩቅ የአያቶቹን ሀገር ለማየት የመጣው ዛሬም ትልቅ ነበርን ትልቅም እንሆናለን እያልን እንፎክራለን ወይስ

ፒር ነገሃርሻ ንግግር ትንቢት ነው እንዴ ብዬ እያሰብኩ ነበር ትልቅ የሚያስብለን ስራ፥ ምግባር፥ ባህል፥ አኗኗር እንዲኖረን

ዘመናዊ ብሎ የሚገልጣቸው ሩቅ ይመስሉ የነበሩ መሪዎች እንጥራለን?) .......ራሳችንን እንጠይቅ.......... ሠላም ያገናኘን!

አሁን በቤታችን እያየናቸው ነው። እኛ በዚህ ጊዜ ዘር፥ ቀለም ፥

ብሄር በሚሉ አረሞች ስንታነቅ እርሱ በአፍሪካዊነት፥ በአንድነት

ማጭድ ከስራቸው ይነቅላቸዋል። የሃይማኖት ቁርሾ የሞላው

ልባችንን በመግባባት፥ በአንድነት ጦር ያደማማቸዋል። .......

ግን ግን ኢትዮጵያ ብሎ የሚኮራባት ድንቅ ሀገር እውን ዛሬም አለች?

ሶስተኛ ዕትም 9
...በሩን በርግጀው ዘው ብየ ዶርም ስገባ እስክንድር ከአልጋው ላይ ያረገው ሰው የታደለ ነው።...ስጦታ እኮ ነው እናንተው...”እያልኩ

ቁጭ ብሎ መፀሀፍ ያነባል።ቀና ብሎ አይቶኝ መልሶ አቀረቀረ።ግራ እያሰብኩ ቁሜ ቀረው።

ገባኝ።ፊቱን፣አቀማመጡን፣ሁለ ነገሩን...አጢኜ አየሁት።ፍጹም “ምንድን ነው?”አለኝ

ሰላማዊ የሆነ ሁኔታ ውስጥ እንዳለ ጥርጥር የለውም።”ይሄ ሰው ግን “አንተን ልጠይቅህ እንጅ ምንድነው?” አልኩት መልሸ።

ከሰው አልተፈጠረም ይሆን?! እንግዳ ነገር ነው።ምን አይነት ህሊና “ምኑ?” አለኝ

ቢኖረው ነው እንዲህ ከተማዋ በተኩስ እየተናጠች፤ተማሪው ሁሉ “በዚህ ስአት ሰላማዊ ሆነህ እንድትቀመጥ ያረገህ?” አልኩት

መሄጃው ጠቦት በጭንቅ እየተጉላላ፤መግቢያ መውጫው ጭንቅ መፅሀፉን እያሳየኝ ፈገግ አለ።”አንተ ግን አይጨንቅህም በቃ?”አልኩት

በሆነበት ጊዜ እንዲህ ያለምንም መረበሽ በሰላም ቁጭ ከማለት አልፎ እየተቀመጥኩ።

ሞት ደጁን በሚያንኳኳበት ጊዜ መፅሀፍ የሚያነበው?....ዛሬስ አንተን “እ...ምን መሰለህ በእንዲህ አይነት ሁኔታ ውስጥ ጭንቀት

10 ጭረት
የሚፈጥረው ነገር የለም።እኔ ደግሞ ከመጨነቅ ይልቅ ለምሳሌ አንድ ሰው ምሳውን በልቶ የተረፈውን ከጎኑ ምሳ ላጣው ወገኑ

ማሰብን እመርጣለሁ።ለምሳሌ አሁን ጦርነት ምንድን ከመስጠት ይልቅ ለእራቴ ብሎ ካስቀመጠ በጊዜው ከሚያስፈልገው

ነው?ጦርነት እንዲፈጠር መሰረታዊ መንስኤው ውጭ የሆነ ተጨማሪ የፍላጎት ሀሳብ በመሰረታዊ ፍላጎቱ በኩል

ምንድን ነው?ሰዎች መጠፋፋትን እንደምርጫ ለምን አስታኮ በመግባቱ ያችን ለመንጠቅ ይመጣል በሚል ፍርሀት ምሳ

ይወስዳሉ?ምናም እያልኩ ሳስብ ነው የቆየሁት።”አለኝ ያጣውን ሰው መከላከያ የሚሆን ሰውየውን እስከመግደል የሚያደርስ

እሽ ፈላስፋው እስክንድር “እና ምንድነው አልክ?” በክፋት የታመመ ሀሳበሰን ያስባል።አጥር ያጥራል መሳሪያ ያነግታል።

አልኩት ምሳ ያጣውም በበኩሉ በሚፈጠርበት የምግብ ፍላጎት የተነሳ

“እ ....ምን መሰለህ...”መፅሀፉን አጥፎ ከመቀመጫው ምግብ ተርፎት ባስቀመጠው ሰው ላይ የሚያነሳሳ በክፋት የታመመ

እየተስተካከለ “እ...ምን መሰለህ ...አዎ...ጦርነት የክፋት ሀሳብ ያስባል።በእነዚህ በሁለቱ ሰዎች ፍላጎት ውስጥ ሾልኮ የገባው

ውጤት ነው ወይም ክፋት ጫፍ ሲረግጥ ነው።ክፋት ክፋት(ከወገን ይልቅ ለነገ ማለት እና የእርሱ ያልሆነን ነገር መፈለግ)

ደግሞ የሰው ልጅ በመወለድ ወይም በደም ያገኘው የሁለቱ ሰዎች ሀሳብ በሽታ በመሆን በስራ ሲገለጥ የምታየው ነገር

ነገር አልያም ተፈጥሯዊ በህሪ አይደለም።እንደዛ ጦርነት ይባላል።

ቢሆን ኖሮ ከመሰረቱ የማንተዋዎቅ ሰዎች በሆነ ክፋት ወደ አንድ ሰው ውስጥ በፍላጎቱ በኩል ገብቶ የራሱን ጤነኛ

ምክንያት ተገናኝተን አብረን መኖር ባልቻልንም ሀሳብ በመምሰል አስተሳሰቡን በማሳመም ሂደት ውስጥ ከራሱ ጋር

ነበር።ምክንያቱም በመወለድ የሚገኝ ባህሪ ሊገራ ያጣላዋል።ከዛም እራሱን የማይወድ እንዲሆን ያደርገዋል።ይህም

የሚችል ነገር ስላልሆነ።ስለሆነም ጥያቄያችንን የሰው በሁለት መንገድ ሊገለጥ ይችላል።አንደኛውና ዋናው ፍላጎቱን ብቻ

ልጅ ታዲያ ክፋትን ከምን አገኘው?ወደሚል ከፍ እንዲወድ በማድረግ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ እራሱን እንዲጠላ እና

ማድረግ ይኖርብናል።” ሰውነትን እንዲንቅ በማድረግ ነው።....”

“እሺ ከፍ አደረግነው እንበል ከምን አገኘው ልትል “በቃ ...በቃ...ወንድሜ ማብራሪያው ይበቃል። ይልቅ ላወራኸው

ነው ደግሞ?” መልሱን ለመስማት ወደሱ አልጋ ሁሉ መፍትሔው ምንድነው አልክ?” አልኩት አቋርጨ።በእኔ ቤት

እየተጠጠጋሁ ጠየኩት። ያለመፍትሄ ትርጉም አልባ ከንቱ ሀሳብ ነው ለማለት ነበር።እሱ ግን

“ እኔ እንደሚመስለኝ ክፋት ልክ እንደቫይረስ አይነት ጠባይ ያለው “መፍትሔውማ ሁሉም ሰው ይህን ተረድቶ እራሱን የሚወድ ሰው

ከውጭ ወደ ውስጥ የሚገባ የሀሳብ በሽታ ነው።የመግቢያ መንገዱ ሲሆን ብቻ ነው።”አለኝ

ደግሞ ፍላጎት የሚባል ቀዳዳ ነው።በዚህ ፍላጎት በሚባል ቀዳዳ በኩል “ስትል?”አልኩት

ተደባልቆ በመግባት ሀሳብን በሽተኛ ካረገው በኋላ በአካል ሲገለጥ “ስልማ እራሱን የሚወድ ሰው ጤነኛ አስተሳሰብ ያለው ሰው

እናየዋለን።ሰው እራሱን በዙሪያው ካለው ነገር ሁሉ ጋር አግባብቶ ነውና ዙሪያውን በሚከተለው ሰላም፣ፍቅርና መልካምነት

ለመኖር ይችል ዘንድ የህዋስ በሮች አሉት።እነዚህ የሚሰማቸው ይታወቃል።ህልውናውንም ሆነ የሚወዳቸውን ሰዎች ህልውና

ህዋሳት(sensery organs) በሚያስተላልፉት መልእክት ምክንያት ከእርሱ በሚወጣ ነገር ማጣት አይፈልግምና በራሱ ላይ እንዲሆንበት

የሚወለድ ፍላጎት የክፋት መግቢያም በመሆን ያገለግላል። የማይሻውን ነገር በማንም ላይ አያደርግም።እያንዳንዱን ሀሳቡን

ሶስተኛ ዕትም 11
በራሱና በሚወዳቸው ሰዎች ላይ ቢተገበር ሊሠማው የሚችለውን ነገር ፍላጎቶቹ ጋር እየተዳበሉ የሚመጡትን አላስፈላጊ ፍላጎቶች ተረድቶ

በማሰብ የታመመ ሀሳቦቹን በተግሳፅ እያከመ እንዳይገለጥ በማድረግ ቆርጦ እንዲጥላቸው መቀስ ሆነው በሚያገለግሉት ህጎች ውስጥ ሲኖር

መልካምነትን በራሱና በዙሪያው ባሉት ሁሉ ላይ ያፈሳል።ስለራሱ ነው።” አለኝ

የሚገደው ነውና ስለሌሎች እኔ ግን በዚህ ስአት እንዲህ

እንዲገደው የሚያደርገውን ጦርነት የክፋት ውጤት ነው ወይም በማውራቱ እያናደደኝ ሰለነበር

ተፈጥሮውንም ይጠብቃል። ክፋት ጫፍ ሲረግጥ ነው።ክፋት ደግሞ ከልቤ ሁኜ ካለመስማቴም በላይ

እግዜሩም ሰውን ሲፈጥረው ፍላጎት የሰው ልጅ በመወለድ ወይም በደም “እንደው አፈር ስሆን አሁን

እንዲኖረው አድርጎ ይሁን እንጅ ያገኘው ነገር አልያም ተፈጥሯዊ በህሪ የምትለው ዲስኩር ታዲያ ከዚህ

ከፍላጎቱ ጋር ተደባልቆ በመግባት አይደለም።እንደዛ ቢሆን ኖሮ ከመሰረቱ ጦርነት ጋር ምን ያገናኘዋል?ምንስ

የአስተሳሰብ በሽታ የሚሆን የክፋት የማንተዋዎቅ ሰዎች በሆነ ምክንያት አረጋግቶ የሚያስቀምጥ ነገር

ትል አብሮ ሊገባ እንደሚችል ተገናኝተን አብረን መኖር ባልቻልንም ነበር።` አለው?”አልኩት በሀይለ ቃል።

የሚያውቅ ነውና ቀድሞ የእያንዳንዱ “ከገባህ የዚህ ጦርነት መንስኤው

ፍላጎት ማበጠሪያ የሚሆኑ የትእዛዝ የታመመ የፍላጎት ሀሳብ

ወንፊቶችን አስቀምጧል።ማንም አስሩን ትዕዛዛት ቢያከብር ነው።መፍትሔውም እርሱን ቆርጦ መጣል ነው።እያለኩህ ነው።”አለኝ

የክፋት በሽታ ወደውስጡ አይገባም።ወንጀልም በአለም አይኖርም ገርመም አርጎ እያየኝ “እዳያ ወሬኛ ነገሮች እንዳንተ ሀሳብ ቀላል

ነበር።ምክንያቱም የሰው ልጅን ፍላጎት ከአምልኮት እስከ እረፍት መስለውሀል?” ብዬ ጥየው ወጣሁ።

አጠቃለው የሚመዝኑ ሚዛኖች ናቸው።ህግና ስርዓት ሁሉ ከእነሱ

አይወጣም።እንዳጠቃላይ የሰው ልጅ ሰላም የሚሆነው ከመሰረታዊ

12 ጭረት
ታሪኩን እንዳይፅፍ፣ ትውልድ እጁ ታስሮ፣
በትላንቱ ሾተል ዛሬው ተሸንቁሮ፣
ባልኖረው ተካሶ፣ ባልሰራው ተዋቅሶ፣
ለፀብ መዶለቻ፣ ያያቱን ስም ጠቅሶ፣
ላለፈው ሲናከስ ለመጪው ሳይተጋ፣
በምን ስሌት ይሆን፣ ትዉልዷ ጨልሞ ሀገር የምትነጋ?

በረከት በላይነህ
ይነጋል!

ሶስተኛ ዕትም
13
ጭረት 13
PHOTOGRAPHY

by

Mahlet
Seyoum

14 ጭረት
ሶስተኛ ዕትም 15

ፎቶግራፊ ለኔ ከቀን ተቀን ኑሮዬ አውጥቶ
ሰላም የሚሰጠኝ፣ የሚያድሰኝ፣ የምረጋጋበት፣
የሚያስደስተኝ፣ አዳዲስ ነገሮችን ለመስራት
የሚያነሳሳኝ (Creative) የሚያደርገኝ፣ ከዛም
አልፎ የሕብረተሰቡን ባህል፣ ወግና የአኗኗር ዘይቤ
ለሌላው ማሕበረሰብ ክፍል የማሳይበት ነው።

ማህሌት ስዩም
Enviromentalist

16 ጭረት
እህትቤተመጽሐፍ

አዕኗቅ
ይወለዱ
ዘንድ
የተወለደች
ዕንቁ
ሶስተኛ ዕትም 17
በኃይሉዘአዋሽመልካሳ

በፍቅረማርቆስ ደስታ ‹‹ጃጋማ ኬሎ የበጋው መብረቅ›› በሎሬት ለክብሯ ራሳቸውን የገበሩ ወጣቶች ከብበዋታልና በተራው እርሱ

ጸጋዬ ገብረመድኅን ‹‹እሳት ወይ አበባ›› ሥራዎች ውስጥ በገናናነት ገበረላት፣ ማለለላት እንጂ፡፡

የተከተበለት ታላቁ ወንዛችን ‹‹አዋሽ›› በሚያልፍበት አካባቢ ስሙን የንባብን ጥም ለተጠሙ ሁሉ ለማርካት ስንቅን ሰንቃ ተነስታለችና

ይዘው ቅጣያን ከሚጨምሩት መካከል ነው ከተማችን፡፡ ከዚህ ወጀብ ቢያይል አውሎው ቢከፋ ‹‹ወይ ፍንክች…›› እርሷ መች

ከሚፈስ ወንዝ አጠገብ በአንዲት ደገኛ ቀን ሰናይ ምክር ተመከረ እንዲህ በቀላሉ ትበገርና አነሳሷ ለይስሙላ ስላይደለ ዶፍ

ይህ ምክር እንደ ሌላው ግዑዝ አካል ወንዙ ይዞት እንዲሄድ ሰባቱ እየወረደባት ዶፉን እንደመልካም ገበሬ ትልሟን የምታቀናበት

ወጣቶች አልፈቀዱለትም እንደልማዱ ግብርም አልተገበረለትም አድርጋው ቆየች እንጂ፡፡

ላለፉት ዘጠኝ ዓመታት ትውልድ እየተቀያየረ ከቀየው ተሻግሮ እንደቀልድ ያይደለ ትንቢት በሚመስል በአብላጫ ድምጽ ያገኘችው

በአየሩ ላይ ሃሳቧን እየሸጠች ስትናኝ ከረመች፤ በሃሳብ ልዕልና ያመኑ ስሟ የዋዛ አለመሆኑን ለማሳየት ብዙ አልፈጀባትም ጥንካሬዋ

18 ጭረት
የሠራች ተስፋን ሰንቃ ተስፋን የምታከፋፍለዋ እመቤት። <<አዋሽ መልካሳ የነገው

ተስፋ ቤተ-መጻሕፍት>>

ውጥኗ ብዙ ቢሆንም በወጣኒነት ሳትሸማቀቅ ንባብ ባሕል ይሆን ዘንድ ከከተማ

አስተዳደር እስከ ኢፌድሪ ሲቪክ ማኅበራት ባለሥልጣን ሕጋዊ ፈቃድ አግኝታ

<<ዛሬም በንባብ፣ ለንባብ፣ ስለንባብ እንተጋለን!>> ስትል ለአፍታ ሳትሸማቀቅ ጉዞዋን

ባልሳተ የበጎነት ተግባር ተጠምዳ መኖርን መምረጥ ባሕሏ ያደረገችም ናት። የበአቷን

ማነስ ያዩ ከሩቅ አይተው ሲጠጓት እንደ ደርባባ እመቤት ስትሰፋባቸው፣ እርሷ ዓለም

የሚጠብባት ሰፊ መሆኗን አምነው የሚሳሱላት በፍቅር እንዲወድቁላት የሚያደርግ

ስስቷ ለሁሌም ተናፋቂ ይሆንባቸዋል። ከልብ ቀርበው ከመአዷ በረከት የቀመሱ

ከአዋሽ ሲወጡም ባሉበት ከንባብ መአድ አለመራቃቸው እና ባሉበት እርሷን መሰል

ሌላ ውድ ለማግኘት እና ለማቋቋም መከጀላቸው የበረታ ናፍቆቷ መገለጫ ነው።

ስለዝናዋ የሰሙ እና መጥተው የጎበኙ ደራስያን፣ጋዜጠኞች እና ንባብ ላይ የሚሠሩ

ተቋማት ስስታቸውን ባገኙት አጋጣሚ ሲገልጹ ማየት ለእርሷ የሰርክ ተግባር

ስለሚሆንባት እምብዛም ሳትደነቅ ትኩረቷን አያሳሳባትም ለእርሷ ፍላጎቷ ከዚህ

ያይላልና፤ በየከተማ መሰል እህቶች እንዲወለዱላት አይ በዛ እኔ ብቻ ልድመቅ ለኔ

ብቻ ይሰጠኝን ከሃሳቧ ጓዳ አሽቀንጥራ የጣለች ናትና ለእህቶቿ መጸነስ የምትጓጓ፣

በውልደታቸው ጊዜ ለወላጆቻቸው አራስጥየቃ የምትኳትን ናት። ቀና ብላ ታላላቆቿን

በንቀት የማትገላምጥ የማንጓጠጥ ጠባይ የሌላት ከሁሉ ለመማራ በምታደርገው

ጥንቃቄ ታናናሾቿን የማትደፈጥጥም፤ ለእርሷ የንባብ ድግስ ካለ የድንኳን ሰባሪነት

ሳይሰማት ለመታደም የምትገሰግስ የጥሟን ነዲድ የምታረሰርስ ትጉህ ናት።

ከከተማው ነዋሪ ለመነሻ የሰበሰበችውን ጥቂት መጻሕፍት በጠባብ የኪራይ ቤት


በስሟ ተጀመረ ስሟ ግብሯን ይገልጥ ዘንድ
የጀመረችውን በመጻሕፍት ክምችቷ አብዝታ ከኪራይ ቤት ባትወጣም ቦታ
ተሽቀዳደመ ቀልድ የመሰለው መሰባሰብ የምር
ለማግኘት ዘወትር ደጅ የምትጠና ናት። ከአዳማ ታነብባለች እስከ ንባብ ለሕይወት
ሲሆን ዓመት አልፈጀበትም ስሟ ያማለላቸው
የመመጻሕፍት ዐውደርዕይ በመሳተፏ ከመጻሕፍት በዘለለ ስሟን የመሸጥ በርካታ
እንደ ኮረዳ ይጎመዧት ገቡ አንዳንዱ ሊዋደቁላ
እድሎችን ተጠቅማ አሳክታለች።
አንዳንዱ ሊጥሏት ከጀሉ እርሷ ተቋቁማ በፍቅር
ንባብ ይሰፋ ዘንድ ምኞቷ ውጥኗ ነው ሁሌም ቃሏ <<ዛሬም በንባብ፣ ለንባብ፣
ለቀረባት ሀዘኗን እና ደስታዋን እያጋራች
ስለንባብ እንተጋለን!>> ነው።
ዓመታትን ኖረች ትኖራለችም።

ይህቺ የአዋሽ መልካሳዋ ንግሥት ናት በትንሽ


v
ዓመት እድሜዋ የትልቅ ዓመታት ሥራዎችን

ሶስተኛ ዕትም 19
ባህልናጥበብ

የካሮ
ጎሳ
ቅኝት - በእጸሕይወት

20 ጭረት
ሶስተኛ ዕትም 21
22 ጭረት
የካሮ ጎሳ የገፅ ቅብን
ከሚያዘወትሩ ጎሳዎች
ውስጥ ተጠቃሽ ነው።
ካሮን የምናገኘው
በደቡብ ኢትዮጵያ
በታችኛው የኦሞ ወንዝ
ዙሪያ ነው። ሙርሲ ፣
ባና፣ ባሻዳ የካሮ ጎሳ
ጎረቤት ብሄረሰቦች
ወይም ጎሳዎች ናቸዉ ።

ሶስተኛ ዕትም 23
24 ጭረት

ዓለም ዙሪያ ያሉ ህዝቦች የተለያዩ አይነት የባህል ።እነዚህ ምልክቶች አብዛኛውን ጊዜ ተፈጥሮን በማስተዋል የተወሰዱ

ልብሶችን ፣ ንቅሳቶችን ፣ጌጣጌጦችን፣ የገፅ ቅብ ናቸው ። የወፎችን የላባ አደራደር ፣ የሜዳ አህያን ቀለማት እና

እና የመሳሰሉትን ራሳቸውን ለመግለፅ አና ለውበት መስመሮች የመሳሰሉትን በመከተል የገፅ ቅብ ይሠራሉ ። ይህን

ይጠቀሙባቸዋል ። በዚህ ዕትማችን ላይ የምናነሳው የገፅ ቅብ የሚሠሩት በመኖሪያቸው አቅራቢያ የሚገኝን የበሃ

የካሮ ጎሳ የገፅ ቅብን ከሚያዘወትሩ ጎሳዎች ውስጥ ተጠቃሽ ነው። ካሮን ድንጋይ ከውሀ ጋር በማደባለቅ ነዉ ። ይህን የገፅ ቅብ ወንዶቹም

የምናገኘው በደቡብ ኢትዮጵያ በታችኛው የኦሞ ወንዝ ዙሪያ ነው። ሆነ ሴቶቹ ያዘወትሩታል። ከዘወትር መዋቢያነት በተጨማሪም

ሙርሲ ፣ ባና፣ ባሻዳ የካሮ ጎሳ ጎረቤት ብሄረሰቦች ወይም ጎሳዎች ናቸዉ ። በጋብቻ እና ሌሎች ስነስርዓቶች ላይም ይጠቀሙበታል ። የካሮ

በካሮ ጎሳ የሚኖሩ ህዘቦች ለገፅ ቅብ የተለያዩ ምልክቶችን ይጠቀማሉ ሴቶች ደግሞ በገፅ ቅብ ብቻ ሳይሆን የተለያየ ቅርፅ ያላቸው

ሶስተኛ ዕትም 25
26 ጭረት
ጠባሳዎች ሰውነታቸው ላይ በማሳረፍ እንደ መዋቢያ ይጠቀማሉ ። ness) እንደሆነ ፅሁፎች ያሳያሉ ። በአሁኑ ሰዓት የግልግል ጊቤ

የካሮ ጎሳ በኢትዮጵያ ምናልባትም በመላው አፍሪካ ካሉ ጎሳዎች ግድብ በኦሞ ወንዝ የውሀ መጠን እና ሙላት ላይ በሚያሳድረው

በህዝብ ቁጥር በጣም አነስተኛው እንደሆነ ይታሰባል ። በህዝብ ተፅዕኖ ምክንያት የሚጠቀሙበትን ውሃ መቀዳት ከባድ እየሆነ

ቁጥር ከ1000 እስከ 2000 እንደሆኑ የሚነገርላቸው የካሮ ህዘቦች መጥቷል ። ከዚህም በተጨማሪ ጎረቤት ሆነው ከሚኖሩ ከሙርሲ

የቁጥራቸው መመናመን ዋናው ምክንያት በ19ኛው ክፍለ ዘመን ብሄረሰብ ጋር ያሉ ግጭቶች ለበለጠ መመናመን ያጋልጣቸዋል ።

መጨረሻ አካባቢ የተከሰተ የገንዲ በሽታ (sleeping sick-

ሶስተኛ ዕትም 27
ግጥም እውነትም ያማል
ከሰው መሸሽ ሰላምን ፍለጋ
ደግሞ መገረፍ በብቸኝነት አለንጋ

እቤቱም ቀጋ ውጩም ቀጋ
ከቶ ማጣት አልጋ በሰላም የረጋ
ለብቻ መጣላት ከዕልፍ ሰው መንጋ

የህፃኑን ልቅሶ... የህፃኑን ፈገግታ


የዘመድን ወሬም... የባዕድን ሰላምታ
የህዝብን ጨዋታ... የህዝብን እሪታ
ባንድ አርጎ መጥላት እንደ እኩይ ጫጫታ
ማንንም አለመሻት...
ብቻ መሆንንም መጥላት
ደህና ነህ ወይ ሲልህ....ምናገባህ ብለህ
ሆ ብሎ ሲሄድም...ከንቱ ጥያቄህ
ከንቱ ማሰብህ
አሁን ከልብ ቢሆን እንደ ቀላል እንዲህ
ምን እንኳን ብሰድብህ
መች ትሄድ ነበረ ምናምን ሲያስብልህ

ሰውን አስገፍቶህ ሰውን ሲያስናፍቅህ


ከጎንደር ሳትሄድ ግድርድር ሲያረግህ
ሰውም ሳይረዳ ይሁና ሲልልህ
ብ....ቻ...ህ...ን ሲተውህ
ትታመማለህ

እውነት ያማል

አይዞን..ከዛሬ..ነገ ይሻላል ሲሉ
በቁራ ተስፋክ ተስፋን ሲቀጥሉ
ትናንትን ያደሩ ዛሬንም የዋሉ
ድክም ብቸው ድንገት ዝም ሲሉ
የላዪን ባታቅም እነሱ ሲዝሉ
ወይኔ ሳትል
ይሁናና...መቼስ ሰው አይድሉ
ይደክማሉ ተስፋን ይቆርጣሉ

እኔ ግን...
ከቶ ተስፋ አልቆርጥም የላዩ እያለ
ብለህ ሳትጨርስ ውስጥ እንዲ ካለ

28 ጭረት
" እሱስ አምላክ ቢሆን ሰውንም አይድለ ... "
አው...
ሊደክመው ይችላል የየለቱ ለቅሶክ
ደግሞ ምታለቅሰው አንተ ብቻ አይድለህ
አንተስ ብቻ ብትሆን ተስፋ እንዳይቆርጥብህ
...ለመሆኑ ማነክ ..who are you ሲልክ
.............ያማል

እውነት ያማል
ቁስልህን ሸፍነህ ያልዳነውን ሁላ
ላመል አለባብሰህ ደግፈህ በዱላ

አንከስ...ራመድ እያልክ ስትሄድ በተስፋ


አን የዞረባት መጥታ ተክለፍልፋ
ለራሷ ደንቅፏት ካንተ ብትደፋ
ዱላህን አስጥላ ብትከትህ ካዳፋ

ከበላይህ ሁናም ብትልህ ይቅርታ


መካሻ ይመስል ለግሳክ ፈገግታ
ልብህን አቅልጣ እግርህን ብትፈታ

ለራሷም ተነስታ አንተን ብታነሳ


እንሂድ ብትልህ ዱላህን አስትታ

ልሂድ አልሂድ ሳትል


" እመን ትድናለህ ምናምን...እንዳሉ "
ማመኑ ይሻላል ከመወላወሉ !
በማለት..
ምስኪኗ ዱላህን...ሳታመሰግናት
ከአዳፋው እንኳ...ነፃ ሳታወጣት
ትተሀት ብትሄድ...ሴቲቷን አምነሃት

ከዛ ግን

ትንሽ እንደተጓዝክ ዞር ብላ ባንዴ


ልብህ ስትል ያኔ ልስመኝ ነው እንዴ
ወይኔ ጉዴ
Thanks ስለሸኘኸኝ ውዴ
እና
እዚጋ በመሆን ባሌን ጠብቃለው
በነገራችን ላይ ሄዋን እባላለው
ስትልህ.....ድሮም...
ሄዋን ማሳሳት እንጂ ምን ታቃለች ሌላ
ብለህ ሳትጨርስ... እግር ተንገዳግዳ
....አንጣ ስትል ዱላ
ሶስተኛ ዕትም 29
ዱላ... የለም ሳትል በፊት ስትወድቅ ወደኃላ
ከአየር ላይ ሁነህም
እርም ሄዋን ከእንግዲህ በኃላ....

ምናምን ያልከው ቃል
ከፊትህ ሲደቀን...እውነት ያማል

እውነት ያማል

መድሃኒት ፍለጋ ዓለምን ስትዞር


የምን እንደው እንኳ እማይታወቅ ዶክተር
ንገረኝ በማለት ህመምህን ሳታስቀር

ሁሉንም ስነግረው የምድን ቢመስልህ


መላ ህመምህን ትዘረዝራለህ

ገና ሳጨርስ ግን....ገባኝ

ሁለመናህን ስትነካው ሁሉንም ካመመህ


ሌላ ምንም አይደል...በሽተኛ ናት ጣትህ

ብሎ የእውር ድንብር ምርመራም ሳያረግ


ይቆረጥ ጣቱ!...ለማለት ብዕሩን ሲያውረገርግ

ኧረግ ኧረግ ኧረ ጣቴ ደና ናት ስትል


ከየት መጣ የማይባል ወደል
" ይሄ ቅንጭላቱም ደና አይድል "
ዳይ ወደ አማኑኤል !
ሲልህ...

ኧረግ ኧረግ ቅንጭላቴስ...


ልትል ታስብና...

ሌላ መቶ ይሄማ...
ሳይኖርበት አይቀርም እንትን
....ዳይ ወደ ሰይጣን !
እንዳይልህ በመፍራት ትለዋለው አሜን

አሜን ወደ አማኑኤል ።
ቢሆንም ግን ያማል ።

።።።።።እውነት ያማል።።።።።።

በዳዊት አለምዘውድ
ያመመኝ ለት
30 ጭረት
የ'ጊዜ'ፍርሃት

ብቻውን ፣ላያኖር
ወይ፥ብቻውን ላይገድለኝ
"ፈሪ ጊዜ"በየጊዜው...
እያነሳ፡መልሶ የሚጥለኝ
'ከበረርኩ የምቀድመው'
መስሎት ነው መሰለኝ!።
(ደበበ፡ችላበለው)
02/04/15

ሶስተኛ ዕትም 31
ይሄን ጠይማም መልክ
------
ከእናቴ ወርሼ
ይሄን ጠይማም መልክ፣
እንዴት ሌላ ልምሰል በመጠየም ምትክ፣
ስፀነስ ጀምሮ ከሷ ተጣብቄ፣
ስወለድ ጀምሮ ዘጠኝ ወር ጠብቄ፣
ካደኩም ጀምሮ እራሴን አውቄ፣
እሪ! መች ቀረልኝ ዳዴ መንፋቀቄ።
የ'ናቴ ጠረኗ ና! ይለኛል ባንዴ፣
ጮርቃ ልጅነቴ፣
አልሄደም ተጉዞ አላለፈም እንዴ!፣
እንዳለፈው ዘመን እንደ ጨቅላነቴ፣
የእናቴን ጡት መጥባት ያምረኛል አንዳንዴ።
ጥቅምት 15-2-2015
- ቢኒ የደሜ ልጅ

32 ጭረት
Ruffled Room, Ruffled Mind
If you ever look for me
I’m in my room deep asleep
Walking around my bed
Be careful of your steps
Not that you would wake me though
Cause I’m up in heaven in peace
But the papers you’re stepping on
Are my broken heart pieces
Sit by the fire place on the rocking chair
And read what I wrote you
Read the agony it bear
Then you will know, I’m gone forever
With a hollow body
A shattered soul, a reaped out heart
But, My darling
Sit by the fireplace
I don’t want you to get cold
Sit by the rocking chair
It’ll soothe your sad soul
And Keep at by my ghost . . .

By Skyblue

ሶስተኛ ዕትም 33
ሄኖክከፋለ
ተናጋሪ
እርሳሶች

34 ጭረት
ሰዓሊ - ሄኖክ ከፋለ
5ኛ ዓመት ሕክምና ተማሪ

ሶስተኛ ዕትም 35
ለጤዛ ተዋድቀን
(በወቀቱ ስዩም)

"እድሚያችን ሰባ ነው ቢበዛም ሰማንያ"


ይህም ኑሮ ሆኖ ጠዋት ማታ ፍልሚያ
አንዱ ካንዱ ጥዋ: ጥቃት የቀመሰ
በየደጃፉ ላይ ምሽግ እየማሰ
ጦር እንደ ቄጤማ እየነሰነሰ
መንደሩን ሸንሽኖ ባጋም እሾህ ቅጥር
ወገን እያስለየ ባሰለፈን ቁጥር
ጤናችን ሲሸረፍ
ቀናችን ሲዘረፍ
የት ሸሽተን እንትረፍ
የትገብተን እንረፍ?
በዶፍ ዝናብ አገር ለጤዛ ተዋድቀን
ሰላም እንደራበን ደስታ እንደናፈቀን
ትግላችን ሰልፋችን ያከትማል አንድቀን:

36 ጭረት
ደብዳቤ
ራሄልስሜነህ

ጥቅምት 7,2015

ከእለታት የሆነ ቀን...ጦርነት እና ሞት...መፈናቀል እና ስደት..ቂም እና ጥላቻ...ከነዚህ ሁሉ


ምንላቀቅበት ጊዜ ይሆናል።እንደው እንዲሁ ለምዶብን ቅር ቅር ይለን ይሆን?ልምድ እኮ
ከሃጢያት ይከፋል ደም የለመደ መሬትስ ምን ያበቅል ይሆን?ምን ይውጠን ይሆን ብየ ሳስብ
አብዝቶ ይጨንቀኛል!ነጋችን ያስፈራኛል(ከቶ ከዛሬ የሚብስ ነገስ እንዴት ያለ ይሆን?)ምኑን ከምኑ
እንደምታደርጊው የሚያስጨንቅ ዘመን።አይንሽ እያየ ነገሮች እየተባባሱ...ሁኔታዎች ከድጥ ወደ
ማጡ እየሄዱ ስታይ. ..ከቶ ከዚህ የከፋ ምን ሊመጣ የሚል ደፋር ያለ እንዳይመስልሽ...ሁሉም ቤቱን
ዘግቶ የባሰ አታምጣ ከማለት ዉጭ...አይሽ ደመነፍስሽ ነገሮች ከዚህ ሊከፉ እንደሚችሉ ፍንትው
አርጎ ያሳይሻል።ብቻ ምን አለፋሽ...የዘሬን ያንዘርዝረኝ በሚባልባት ሃገር መኖሩ በራሱ ያንዘረዝራል!
# ፍቅር እና ጦርነት...ያንድ ሳንቲም ሁለት ገፅታዎች ናቸው ቢባል እውነት አለው።በተቃርኖ በተሞላች
አለም ውስጥ ሁለቱ ጎን ለጎን ቢሄዱ የሚደንቅ አደለም።ከእለታት በማላስታውሰው ቀን...እርሱን
ባየሁበት ቅፅበት ምኞቶቼን ሁሉ ሸክፎ ቢይዝ ተመኘሁ።የመውደድን ሳይሆን የመወደድን ሃላፊነት
ልሰጠው...እንዲሁ ድንገት ብንን ትይና ምኞቶችሽን አንድ ሰው ላይ ማየት ያሰኝሻል (ችግር እኮ
ነው መቼም) እኔም ፈርዶብኝ አርሱም ጥሎበት ይሄው ደሞ ዛሬ እርሱ የምፈልገው አይነት ሰው
ቢሆን ምናለበት ብየ ድርቅ ብያለው...የኔ መውደድ እንግዲህ እንዲህ ያለ ነው ቀልቤ ያረፈበት ሰው
ላይ መውደዴን መፈለግ...ምኞቴን መመኘት...ብቻ እንዲህ ያለው ስሜት ለኔም ብዙ አይገባኝ።
.......ደሞ ደሞ ያስደነገጠኝ ጥይምናህ መስሎህ ነው?አደለም ያስደነገጠኝ የገዛ
ሃሳቤ ነው...ምኞቶቼን እዚህ ሰው ጋ ባኖራቸውስ የሚለው ሃሳቤ ነው...እንዴ ያስባለኝ!

ያንቺው ብሩህ

ሶስተኛ ዕትም 37
38
ጭረት
BOOK REVIEW
When Breath Becomes Air - Rebecca Yared
“I don’t think I ever spent a minute of any day won- year more for everything he imagined to his life to be

dering why I did this work, or whether it was worth a reality. It goes on to show the difficult decisions he

it. The call to protect life—and not merely life but an- has to make, not as a doctor, but as a patient, a husband

other’s identity; it is perhaps not too much to say an- and eventually a father. Paul and his wife’s reaction

other’s soul—was obvious in its sacredness.”Paul Ka- to their dreams being crushed so suddenly is record-

lanithi; When Breath Becomes Air ed. The book, even though not

This is a book about an outstanding “...even if I’m dy- written particularly in a sad tone,

doctor of Indian descent in the US ing, until I actu- allows the reader to look at experi-

and his final chapter of life on earth. ally die, I am still ences and evaluate emotional val-

The author talks about his parents, living.” ues that are not quite expressible.

family, childhood and how he chose And paul says”...As a doctor, I

his career path. His interest in writing and philosophy had had some sense of what patients with life-chang-

had contributed to his overall compass of life, building ing illnesses faced—and it was exactly these mo-

his principle and shaping every path he goes though. ments I had wanted to explore with them. Shouldn’t

He shares his experience as a doctor, the kinds of terminal illness, then, be the perfect gift to that young

patients he treated and saved...and lost. The book is man who had wanted to understand death? What bet-

filled with cases and real hospital experiences, not ter way to understand it than to live it? But I’d had

only of himself but also some of his teachers and col- no idea how hard it would be, how much terrain I

leagues. Different types of people are described in the would have to explore, map, settle. I’d always imag-

setting of a hospital in different scenarios; a lot of us ined the doctor’s work as something like connecting

would find ourselves as one of the personelle in Stan- two pieces of railroad track, allowing a smooth jour-

ford University Hospital, which is where the author ney for the patient. I hadn’t expected the prospect

was doing his residency, attending in one of the most of facing my own mortality to be so disorienting,

demanding specialties of medicine, neurosurgery. so dislocating. I thought back to my younger self,

The book can be summed up as being a man’s search who might’ve wanted to “forge in the smithy of my

for what makes life meaningful and the mean being soul the uncreated conscience of my race”; looking

forced to answer it himself as he is urged by death at into my own soul, I found the tools too brittle, the

the peak of his career, just as he starts to hope for a fire too weak, to forge even my own conscience.”

ሶስተኛ ዕትም 39
Paintings
by ብርሀነ ትንሳኤ

40 ጭረት
ሶስተኛ ዕትም 41
42 ጭረት
ፍናማርያም

የመንገደኚትመጣጥፍ
“I know why a caged bird sings” • አሻግሬ እብዱና ውሸት ታንቃ ትሙት
ህይወት ውሰጥ ተነግሮን ከምንረዳው ይልቅ ኖረናቸው አሻግሬ ድሮ ድሮ እጅግ ያተረፈ ነጋዴ ነበር ይላሉ የኋላ
የሰረፁን ነገሮች ይበረታሉ፡፡ አንዳንዴ ሰዎችን ከመረዳት የኋላ ከሚያምናቸው የሽርክ ጓደኞቹ ተከድቶ ከከሰረ አንስቶ
ርቀን የምንገኘው፣ህመማቸው የማይሰማን በራሳችን በሰፈራችን መንገድ ላይ “ውሸት ታንቃ ትሙት” ብሎ በመጮህ
የህይወት መስመር ውስጥ ከህመም ጋር ስላልተዋወቅን ነው፡፡ ሌላ አሻግሬን ይዞ ተከሰተ፡፡ አምኗቸው የከዱትን፣እውነቱን
አሊያም እንደዚህ መኖር(ጠብቆ) አለበት ብለን ካስቀመጥነው በሀሰት ገልብጠው የጣሉትን በግሉ ሸንጎ ለመፋረድ ሲል፣
የራሳችን ልክነትን ካዘነፉ ከመረዳት እንርቃለን፡፡ በእርግጥም ለዚህ ሰው እምነትን ማጉደል፣ሀሰትን መንገር
ህመም ሆኖበታል ውሸት ታንቃ ትሙትለት፡፡
እግሬ ሽሬን ከረገጠበት ቀን አንስቶ በተለይም አያቴን ይዤ • እማማ ኡኡ
የስነ-አዕምሮ ህክምና ከመጣንበት ቀን ጀምሮ በሀሣቤ የሰፈራችን ትላልቅ ሰዎች የሊበን እናት ይሏቸው ነበር እኛ
የምጥለው የማነሳው፣ስለህይወት ለመረዳት ከራሴ ጋር ደግሞ እማማ ኡኡ፡፡ የሊበን እናት እማማ ኡኡ የተባሉት ኡኡ
የምነዛነዘው በዝቷል፡፡ በስንት ስንክሣሮች በተከበበች ዓለም ብሎ የሚጮህ ሰው ከሰሙ ድንጋይ ይዘው በማሯሯጣቸው
ጋር እየተላተሙ፣ጭነቷን መሸከም ከከበዳቸው ሰዎች፣ጥሰው ነው፡፡ እማማ ያቺን ቃል አምርረው የጠሏት የአንድ ልጃቸውን
ወጥተው አዕምሮና ሀሳባቸው ታፍኖ ከሰመጡ፣ ወደ ልክነት ሊበን መርዶ ከሰሙት ቀን ጀምሮ ነው፣ምናልባት ሲያረዷቸው
ለመውጣትና ለመተንፈስ ከሚነገዳገዱና ከሚፍጨረጨሩ የሰሟት የመጀመሪያ ቃል ሆና ኡኡ ሲባል የልጃቸውን
ሰዎች ጋር ለአያቴ ስል መሰንበት ኑባሬዬ ከሆነ በኋላ ህመም አለመመለስ እየደጋገመች ስለምትነግራቸው ነው፡፡
ሰርፆኛል፤ህመም ገብቶኛል፡፡ ታዲያ ግቢውን ከረገጥኩበት አንዳንዴ ሰዎች ሊሉን የፈለጉትን ነገር ሊነግሩን ባሰቡ ሰዓት
የመጀመሪያዋ ሰዓት አንስቶ ልጅ እያለን ሰፈራችን ውስጥ አንረዳቸውም፤እንተላለፋለን፡፡ ስንኖር፣፣ስናጣ፣ስንወድቅና
ስለሚታወቁት አዕምሮአቸውን የታመሙ ሰዎች ታሪክ ስንሰበር ህመሙን እናውቀዋለን፡፡ አያቴ ከመጣሁ ጀምሮ
ማውጠንጠን ጀምሬ ነበር፡፡ ብዙ ቃላት አላወራችም ብቻ በየመሀሉ ደረቷን እየደቃች
ሶስተኛ ዕትም 43
ከምሕላ ጸሎቶች አንዱን ትደጋግማለች፡፡ የሚከበበው የአያቴ መሪጌታ ወልዳይ ቤት ባዶ ነበር፣አክስቴ
አንቲ ማርያም አክሱም ጽላተ ሙሴ አብረኸት የለችም፣ዘርዓ ዳዊትና ክብሮም የሉም፣አባ
ተዓረቅና እንዶ መሬት ከይመሴ ክብረቅዱሳንና እማሆይ ሣህለማርያም የሉም፣ ምንምና ማንም
ሕራይ በልናዶ መሬት ከይመሴ የለም ምስኪኗ አያቴ ዕንበባ(አደዬ) ብቻ፣ ቤት ማለት ጣራና
ከሁለት ዓመታት በኋላ ሽሬ ስመለስ ለወትሮ በሰዎች ግድግዳ ብቻ ነው እንዴ አይመስለኝም አያቱን ከተኛችበት
44 ጭረት
ለቤተሰቡ ባወጣው ቀጭን ትዕዛዝ
መሰረት ከልጅ እስከ የልጅልጅ የአብነት
ትምህርት የመማር ግዴታ ነበረብን፡፡
ለእኔም የመጀመሪያ የግዕዝ ቃላቶችን በቃሌ
ያስጠናኝ አያቴ ነበር፣ አቡነ ሳልል የሰዓታት
መግቢያ ላይ ያለችዋን ነበር የህይወት ስንቅ
ናት እያለ ያሸመደደኝ፣ በእግዚአብሔር
ታምኛለሁ፣ብወድቅም በእርሱ እነሳለሁ
የምትለዋን
ሠለስተ አስማተ ነሢእየ እትመረጎዝ
እመኒ ወደቁ እትነሣእ
ወእመኒ ሖርኩ ውስተ ጽልመት
እግዚአብሔር ያበርህ ሊተ
ታዲያ ይሄ ሰው ከዜማው ና ከአቋቋሙ፣
ከመቋሚያና ጽናጽሉ ውጪ ጠመንጃ
የጨበጡ እጆች እንዳልነበሩት ተረድተውለት
ይሆን ? አላውቅም፡፡
• አክስቴ አብረኸት
ለሁላችን አምባሻና ህብስት እየጋገረች ከሻይ
ጋር የምትሰጠን፣በኢትዮ ኤርትራ ጦርነት
ሄዶ በቀረው ባሏ ሁሌ የምታለቅስ ናት ፡፡
ምናልባት ለእርሷስ ባሏን የነጠቃትን ጦርነት
አምርራ ትጠላ እንደነበር ያውቁላት ይሆን?
እንጃ
• ዘርዓዳዊት
የአክስቴ አብረኸት የመጀመሪያ ልጅ
ነው ወንድሜ ዘርዓ፣ ልጅ እያለሁ
አያቴ ወንጌለ ዮሐንስን እንዲያስቀጽለኝ
ነግረውት፣በምገድፋቸው ቃላት
እየተናደደ፣ወይቤላና ወይቤሎ ማለት
ከብዶኝ በ አይደለም ቨ በይ እያለ እስከ
ምዕራፍ አራት እየተነዛነዝን ገብተን
ወአውስአ ኢየሱስ ወይቤላ እንዳልኩ
መሳሳቴ ገብቶኝ የተለመደው ቁጣውን
ስጠብቅ እያነበብሽ ያለውን ተረድተሸዋል
ግን ብሎኝ ከተቀመጠበት በሀሳብ ሲጓዝ
እኔም ምን ይሆን ብዬ መሳቱን ትቼ ወንጌለ
ዮሐንስ ምዕራፍ አራትን ከላይ እስከታች
አልጋ ላይ በራስጌዋ በኩል ተቀምጬ ስለቤተሰባችን ማሰብ ስደጋግም፣ አይ ዘርዓ … እሺ የሱንስ በዛች
ጀመርኩ፡፡እውነት ግን እነዚህን ሰዎች ሀቅ አልነበራቸውም ምዕራፍ የተፃፈውን ሣምራዊ አይሁዳዊ የማያስብል አንድ
ጦርነትን ይፈልጉ ነበር የሆነ የዘላላም መጠጥን ሊጠጣ የወደደ፣እንኳን ሰው
• መሪጌታ ወልዳይ ማጥፋት ይቅርና ቃላትና ዜማ ስሰብር የሚቆጣ ወንድሜ
አያቴ መሪጌታ ወልዳይ የአቋቋም መምህር ሲሆን እሱ
ሶስተኛ ዕትም 45
እንደነበር ገብቷቸው ይሆን? እንጃ አላውቅም፡፡ የአያቴ ዕንበባ ታናሽ እህት ነበሩ እማሆይ፣ቁጣቸውና የአቡነ
• አባ ክብረቅዱሳን አረጋዊ ዝክራቸው አይረሳኝም፣ አይ እማሆይ ሁሉም ነገር
በአያቴ ደብር አብረው የሚያገለግሉ መነኩሴናየቅዳሴ መሰተር እና ትክክል መሆን አለበት የሚሏት ነገር፣ ምስለ
መምህር ናቸው፣አባ ክብረ ቅዱሳን(የኔታዬ)፡፡ እንደሌሎቹ ሥዕላቱን የሚቀቡት ሽቶ ሲያልቅባቸው የሚያዝኑት ሀዘን አንድ
የቤተሰባችን ሴቶች የቅኔ ትምህርትን ትቼ ለነፍሴ የሆነ ሰው ሲገዛላቸው እየፈነደቁ ቀድመው ሥዕለ ማርያምን
የቀረበውን ዜማ ለመቀፀል በማሰቤ ነበር አያቴ በደስታ የሚቀቧት ነገር፣ ጠንቅቀው የተማሩ ቢሆኑም የሚደጋግሟት
ከእርሳቸው ስር እንድማር ሲወስደኝ በቅርበት ያወኳቸው፡፡ አንድ ጸሎታቸው የሆነው ይትቀደስ ስምከ፣የሆነ ቀን የአቡነ
በደብረአባይናዋልድባ ናፍቆታቸው እኛም የማናቀውን ደብር አረጋዊ ዝክር ደርሶባቸው እንዳስለመዱት እኔና ረዊና የበሶ
አስናፍቀውናል፣ስለተቀደሰው የምንኩስና ህይወት ሲነግሩን ዱቄት ስለአቡነአረጋዊ እያልን ጠይቀን ከበረከት እንድንካፈል
ዜማውና ካስባሉን በኋላ በሚነግሩን የነፍስ ትምህርቶች ለመጀመሪያ ጊዜ ሲልኩን እንዴት በየሰው ቤት እንሄዳለን
ስንት የጨለማ ቀናቶቼን ወጥቼባቸዋለሁ፡፡እና የኔታዬ ብለን ስንነጫነጭ በቁጣ እንኳን እናንተ ይቺ እናት ብለው
ከቅዳሴ ጸሎት ሀበነ ንኅበር(አንድ መሆንን ስጠን) የምትለዋን ሥዕለማርያማቸውን እያመለከቱ በየሰው ቤት ሀሜት ሳትፈራ
እንደሚወዷት በቅዳሴያቸው ለአንድነት እንጂ ለጠብ ዜማ እንጀራ ለምናለች ብለው ሲያበሩን ከንቱነታችንን አምነን በሶ
እንደሌላቸው ተሰምቶላቸው ይሆን? አላውቅም፡፡ ሰብስበን ስንመጣ የመረቁን ምርቃትና ለቁጣቸው የነገሩን
• እማሆይ ሣህለማርያም የአንድ ሊቅ ቅኔ
ማርያም ድንግል ዘኢትፈርሀ ሐሜተ
ፍርፈራተ ሕብስተ ሰአለት በፍና እንዘ ትፀውር ሕብስተ
“የኖሩባቸው ቤቶች የተመላለሱባቸው
እማሆይስ ታዲያ ከዝክራቸውና በደስታ ቅዱሳኖቻቸውን
ከሚቀቡት ሽቶ በቀር ሌላ ሀቅ እንዳልነበራቸው ታውቆላቸው
የሽሬ ጎዳናዎች የዋህነታቸውና
ይሆን እንጃ አላውቅም፡፡ ሀቃቸው ይነግሩላቸው ይሆን?
• ክብሮም
አንዳንዴ ሰዎች ሰርግና ሞት አንድ ነው ሲሉ ፍቅርም አንድ አላውቅም፣አላውቅም፣አላውቅም”
እንደሆነ ማን በነገራቸው እላለሁ፡፡ ክብሮም የመጀመሪያም
የመጨረሻም ፍቅሬ ነበር ፡፡ ለእርሱ ደብዳቤ መፃፍ ሰበብ አላውቅም፣አላውቅም፣አላውቅም
ትግርኛ መጻፍ የተለማመድኩበት፣ከደብዳቤ ፍቅር ተጣብቄ Mahmoud darwish እንዳለ “I don’t know who sold
የቀረሁበት ክብሮም፣ አዲስአበባ ስመለስ ሌላ ነገር እንደሌለ our homeland, but I saw who paid the price”
ሁሉ ክረምት እስኪደርስ ስሙን ዘርዓ እንዳስጠናኝ የከፈለውን አውቃለሁ፣ለምን ሰዎች ሰላምን አብዝተው
ወንጌለ ዮሐንስ የምደጋግምለት ክብሮም፣አያቶቼ ጋር አስሬ እንደሚፈልጓት አውቃለሁ፣ለምን ስለሁሉም ባሰብኩ ጊዜ
በመደወልና ዘርዓን ፈልጌው ነው እያልኩ ጥያቄዬን ትቼ እንደ ሚፋጅ እሳት ውሃ በጉንጮቼ ላይ እንደሚወርድ
ስለእርሱ ቀን ውሎ ወንድሜን የምነዘንዝለት አውቃለሁ፡፡ አያቴም ለምን ያንን ዜማ እንደምትደጋግመው
ክብሮም፡፡ የሆነ ጊዜ ከስድስተኛው ጽጌ አሁን አውቃለሁ:: ጦርነት እንደ ሙሽራ ለሁሉም በየተራ
ማኅሌት አዳር በኋላ የትላልቆቹን አቋቋምና ይድረሰው ተብሎ የሚዜምለት አይደለም፣ይበቃል፡፡
እሱ ከበሮውን ይዞ እንዴት ሲያጅባቸው ጉንጮቼን እጆች ሲዳብሷቸው ከሄድኩበት ብንን አልኩ አያቴ
እንደነበር ከዜማው ጋር ለእኔና ዘርዓ እያሳየ ነበረች ጓለይ ጓለይ እያለች አብራ እያነባች የምጠርግልኝ
ተመየጢ ተመየጢ ወኢትጎንድዪ ብሎ ቀስ ብላ እጆቼን ይዛ “ማርያም ታውቃለች “ አለችኝ ፣እንባ
ሳናስበው ተንሸራቶ ሲወድቅ እኔና ዘርዓ ባረገዙ አይኖቼ እያየኋት እጆቿን አጥብቄ አንገቴን እየነቀነኩ
ልባችን እስኪፈርስ የሳቅነው ተመልሶ አዎ ማርያም ታውቃለች አልኳት፡፡ እጆቿን ወደደረቷ መልሳ
እግሩን እያመላከተ ስለተፈጠረው የቴክኒክ እየደቃች በድጋሚ ማዜም ጀመረች
ስህተት ይቅርታ ብሎ በቀደመው ሀይሉ
ተመየጢ ብሎ ሲጀምር ዘርዓ ተቀላቅሎት አንቲ ማርያም አክሱም ጽላተ ሙሴ
ተመየጢ እያልን ያመሸንበት፡፡ ክብሮም ተዓረቅና እንዶ መሬት ከይመሴ
ናተይ፤እሱንስ ተመየጢ(ተመለሺ) እያለ ሕራይ በልናዶ መሬት ከይመሴ
እንዳትዘገይ የሚለማመናት፣ማኅሌቷን ቀጥ
ብሎ የሚቆምላት ፣ልጅነቱን ለውዳሴዋ ዶክተር ማያ አንጄሎ ለግልታሪኳና ለጥቁሮች ጭቆና
የሰጠላት ርኅርኂት እመቤት እንዳለችው ለማመልከት “I know why a caged bird sings” እንዳለች
ይረዱ ይሆን ከወንዞች ማዶ ይሄንን እያሰበች ሁሉ እኔም የታሰረች፣የተዘጋባት ወፍ ለምን እንደምትዘምር
የምትፅፍ፣ወደፊት ስለእርሱና እሷ ስታስብ አውቃለሁ፡፡ አያቴን ተቀላቅዬ ማዜም ጀመርኩ፡፡ አንቺ
የነበረ፣ክረምት አልፎ ልታየው የምትናፍቅ የሙሴ ጽላቱ የምትባይ ማርያም፣መሬት ሳይመሽ ታረቂን፣
አንዲት ሴት እንዳለችው ይገባቸው ይሆን እሺ በይን፣ተለመኚን፡፡
እንጃ
ስለሁሉም አሰብኩ አብርሃና ክራሩ፣ንግስቲና ተጻፈ በፍናማርያም
የኪሮስ አለማየሁ (ኣንጉዐይ ፍስስ) ዘፈኖች፣ ነሐሴ 16 2015 ዓም
እነቅሳነትን፣ረዊናን ፣ አነ ደሊናና ሸዊትን፣
የኖሩባቸው ቤቶች የተመላለሱባቸው
የሽሬ ጎዳናዎች የዋህነታቸውና
ሀቃቸው ይነግሩላቸው ይሆን?

ሶስተኛ ዕትም 47
በየጥሻው ተወትፈን እንደተምች ስንረፈረፍ
ቅኔ በበቀቀን ሲዘረፍ
አቀርቅረን ስናንቋርር፣ቅሪታችንን ስናንቃርር
እንደቀላጤ አክንባሎ
ቁልቁል ባፍጢም ተተክለን
በእርኩስ አመዳይ ተበክለን
እንዲህ የትም ስንቀር እያየህ ዝም ካልክማ
እውነት እውነት... ከመንበርህ የለህማ!

አያ ሙሌ
እውነት ከመንበርህ የለህማ

48 ጭረት
ቅዳሜን ከሳንኮፋ ጋር
መታደል ወይስ መታገል
ሳምሪ፡ የሞከርነው ካልተሳካ እንታገላለን ወይስ አልታደልነውም ብለን እንተዋለን?
ያብስራ፡ ለምን የታደልነው ነገር ላይ ሰርተን አንኖርም ለምን እንታገላለን እንዴ?
ሮቤል፡ መታደል ካልን ሁሉም ነገር አስቀድሞ ተወስኗል፤መታገል ካልን ግን freewill እና survival ነው፡፡
ሳሚ፡ በታደልነው ላይ ስንታገል ነው፤መርጠን መታገል አለብን፡፡ መታገል የማንችላቸው ነገሮች አሉ፤
ተፈጥሮ፣ቦታም ይገድበናል፡፡
ቢንያም፡ ፅንፍ ነገሮች አይደሉም፡፡ በመታገል ውስጥ የሚሰጡ እድሎች አሉ፡፡
ቤዛኵሉ፡ ሁለቱም አስፈላጊ ናቸው፡፡ መታገል ካልቻለ ሰው መኖር አይችልም ግን ደግሞ ሁሉም ይቻላል
ማለት አይደለም፡፡ በመታገል ውስጥ የሚሰጡ ስጦታዎች(መታደሎች) እና መጀመሪያም የነበሩን መታደሎች
አሉ፡፡
ምህረት፡ መታደል አንድ አማራጭ ነው፡፡ በመታገላችን ውስጥም መታደላችንን እናመጣዋለን፡፡
ዳዊት፡ ታግለን የማንለውጣቸው ነገሮች የሉም፡፡
ብሩክታዊት፡ የህይወት ጣዕሟ ራሱ ከትግል የመጣ ነው፡፡
ኤዶም፡ መታገላችን አይቀሬ ነው ግን የሚመጣውን ውጤት ቅድሚያ መዝነን መታገል አለብን፡፡ እናም
ከhard work ,smart work እመርጣለሁ ፤ እርግጥ በ hard work የማይመጣ ነገር የለም ግን ጊዜያችንን
እያፈሰስን ያለንበትን ነገር ማወቅ አለብን፡፡

ሀሳብ ከሀሳብ የሚፋጭበት፣ሀሳብ ከሀሳብ የሚፋተግበት፣ሀሳብ ከሀሳብ የሚጋመድበት፣


ቃላት በቀጭን የሚፈተሉበት፣እይታ እንደ ጥጥ የሚባዘትበት፣የዕብለት እርቃን
የሚገለጥበት፣እውነት ጥሩ በፍታ የምትደርብበት ዕለት።
ይምጡ፣ይታደሙ፣ይናገሩ፣ያዳምጡ፣ ይደመሙ።
ዘወትር ቅዳሜ ከምሽቱ 1:30 ጀምሮ ከሳንኮፋ አንባብያን ማኀበር

ሶስተኛ ዕትም 49
ጥበብና ጤና
በተስፋዬ ብርሃኑ(ዶ/ር)

እንደ መባቻ መደምደሚያ እንዲሆነን ከጥበብ ውጤቶች መካከል ለአብነትም መዚቃ በዕጽዋት ዕድገት
ላይ የነበረውን በምርምር የተደገፈ በጎ ተጽዕኖ እንመልከት። ለጥናት እና ምርምር ያመች ዘንድ ተመሳሳይ
ዕጽዋት በተለያየ ቦታ ተተከሉ። ለአንደኛው ኩትኳቶ፣ ውሃ እና ፀሐይ ብርሃን ሳይጓደል ክብካቤ ይደረግለት
ነበር። ለሌላኛው አትክልት ደግሞ ለመጀመሪያው ከሚሰጠው ክብካቤ ባሻገር ሙዚቃ በየዕለቱ ይከፈትለት
ነበር(በየትኛው ጆሮ ሊሰማ?! እንጃ በእርግጥ ቦታኒስት አይደለሁም።) በጥናቱ ማጠቃለያ ወቅት የተገኘው
ውጤት በየቀኑ ሙዚቃ የሚከፈትለት ዕፅ ሙዚቃ ከማይከፈትለት ዕፅ የተሻለ ዕድገት ማሳየቱን ጠቁሟል።
ታድያ ስሜቱ ይህ ነው የማይባል፣ መከፋት መደሰት የሌለበት፣ ራበኝ ጠማኝ የማያውቅ፣ በረደኝ ሞቀኝ
ምኑም ያልሆነ፣ ማኅበራዊ ኑሮ የማይገደው ተክል ያን ያክል በሙዚቃ ተጽዕኖ ሥር ከወደቀ ስሜቱ ዕለት
ዕለት የሚዋዥቅበት፣ ማልቀስ መሳቅ ማግኘት መጣት ሚፈራረቁበት፣ ማኅበራዊ ሕይወት ሚያስተሳስረው
የሰው ልጅ ጥበባዊ በሆኑ ነገሮች ማለትም ሙዚቃ፣ ስዕል፣ ቴአትር፣ ፊልም፣ ድራማ፣ ልብወለድ፣ ግጥም፣
ሥነ-ቃል እና ሌሎችም ጥበባዊ ሥራዎች እንዴት ተጽእኖ አይፈጥሩበት?! ጤና ጥበብንና አካላዊ ቅርጽን፤
ጤና ጥበብንና አእምሮአዊ ውጤትን፤ ጤና ጥበብንና ማኅበራዊ መስተጋብርን ማሰናሰያ ሰንሰለት ነውና።
ጥበብም እንዲሁ።
              ጤና ለጥበብ፥ ጥበብ ለጤና

ዋቢዎች
1. https://ajph.aphapublications.org/doi/abs/10.2105/AJPH.2008.156497
2. Ottawa Charter for Health Promotion. Geneva, WHO, 1986.
3. https://www.emerald.com/insight/content/doi/10.1108/09654280510617169/full/html
4. https://applications.emro.who.int/dsaf/EMRPUB_2012_EN_1362.pdf

50 ጭረት
የፊልም
ዳሰሳ
Freedom Writers
(2007)
“But even an ordinary
secretary or a house-
wife or a teenager can,
within their own small
ways,turn on a small
light in a dark room”

“Don’t let the action of a few determine the way የምንፈጥራቸው ብርሃኖች፣የነፍስ ዕረፍቶችና የኑሮ
you feel about the entire group” ጥራት(Quality of life) በዋነኝነት ልናስብላቸው


- Miss Erin Gruwell ቢገቡም እናልፋቸዋልን፡፡ አክመን የላክናቸው ሰዎች
ለተኛ ዓመት የግቢ ተማሪ ሳለሁ ከአንድ በተመሳሳይ በሽታ ታመው ሌላውንም ጨምረው
ገጠር አካባቢ በሚገኙ የተለያዩ አንደኛ ሲመጡ አይተናል፣ ለብዙ ጊዜያት በመንገዳችን
ደረጃ ትምህርት ቤቶች እና በመንደር ለልመናቸው ሳንቲም የወረወርንላቸው እዛው
ውስጥ የሚገኙ ቤቶች ውስጥ ስለ “Neglected ጎዳና ላይ ከአምስት አስር አመታት በኋላ ስንመለስ
Tropical Disease” ባስተማርን በቀጣዮቹ ቀናት መኖራቸውን እንታዘባለን፡፡ እንደዚህ ለመኖር
በባዶ እግራቸው ት/ቤት የሚመጡ ፣በተለየ መልኩ እንዳልተፈጠርን ይልቁንም የራሳቸንንና የሌሎችን
Scabies የሚጨምርበት ፣የውሃና ሳሙና አለመኖርን ኑሮ ለማብራት እንደተፈጠርን ባሰብኩ ሰዓት በ6ኛ
መመልከታችን እያስተማሩ መመለሱ ብቻ ዋጋ ቢስ ክፍል አዕምሮዬ የተመለከትኩት ፊልም ትዝ ይለኛል።
መሆኑ የገባን ግን ምንም ማድረግ አልቻልንም ነበር፡፡ ፊልሙ በእውነተኛ ታሪክ ላይ ተመርኩዞ የተሰራ
አንዳንዴ የተሰጠንን ሥራ ብቻ አከናውኖ ሲሆን በፊልሙ ውስጥ ለዋና ገፀ ባሀሪዋ እንደ አባት
መመለስ ብቻ ሳይሆን በየደረስንባቸው ቦታዎች ሆኖ የሚሰራው ሰው እንዲህ ሲላት እናደምጣለን:

52 ጭረት
“But no matter what, You have to remem- ፍራንክ አይነት የየግል ታሪኮቻቸው የሰፈረበት የነፃነት
ber, it’s just a job” ብዕረኞች ማስታወሻ(Freedom Writers Diary)
ውድሮው ዊልሰን ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት (Woodrow በሚል ለማሳተም ይበቃሉ፡፡
wilson high school) ውስጥ የክፍል 203የሥነ- በፊልሙ ውስጥ በተማሪዎቹ ተጋብዛ የተገኘችው
ጽሑፍ አስተማሪ እና የክፍል ሀላፊ የሆነችው ልጁ የእነአና ፍራንክ ወዳጅ የተናገረችው ሀሳብ አዲስ
መምህርት ኤረን ግሩዌል (Erin Gruwell) ግን አበባ ፒያሳ ላይ ካለው የአጤ ምኒልክ ሀውልት ስር
አባቷ ያላትን ሳታደምጥ ከተማሪዎቿ የተዘበራረቀ ከተፃፈው ሀሳብ ጋር ይመሳሰልብኛል፡፡
ህይወትና ባህሪ፣ ከት/ቤቱ መምህራንና አስተዳደር “But even an ordinary secretary or a house-
እንዲሁም ከግል ህይወቷ ጋር በመታገል የልጆቹን wife or a teenager can, within their own
ህይወት ለመቀየር በገዛ መንገዷ ስትጥር ያሳየናል፣ small ways,turn on a small light in a dark
የነፃነት ብዕረኞች ወይም Freedom Writers room”
ፊልም፡፡ ሀውልቱ ሥር ደግሞ እንዲህ ይላል፡ “ከታላቅ ወይም
ሁሉም ተማሪዎች የየራሳቸው የከበደ የህይወት ከታናሽ መወለድ ሙያ አይደለም ራስን ለታላቅ
ስንክሳሮች እንዳሏቸው ለአንድ ጉዳይ ብላ ታሪክ መውለድ እንጂ..!
በሰጠቻቸው የየግል ሀሳብና ስሜት ማስፈሪያቸው እንደ ኤረን ያሉ ሰዎችን ያብዛልን
ላይ ከተረዳች በኋላ በመካከላቸው ያለውን የዘር
መጠላላት፣ የግድየለሽነት ስሜት እንዲሁም ንባብን
የመጥላት አባዜ በናዚ ጭፍጨፋ ከተፈጠሩት
ታሪኮች እንዲረዱ እና የየግል ችግሮች ከምንም
ነገር እንደማያግዳቸውና በማንም ላይ
እንደማያሰለጥናቸው በማሳየት የተማሪዎቿን
ልብ በመመለስ አያልፉትም የተባሉበትን ሁለተኛ
ደረጃ ትምህርት እንዲያልፉና በመካከላቸው
ፍቅር እንዲኖር ትደግፋቸዋለቸ፡፡
ከዚህም ጋር ተያይዞ ባነበቡት የአና
ማስታወሻ(Anne Frank, The Diary of a
young girl) አማካኝነት አና ፍራንክና ቤተሰቦቿን
ያስጠጋችውን ሚፕ ጊስ የተባለችዋን ሴት(Miep
Gies) በመጥራትና ለራሳቸውም እንደ አና

ሶስተኛ ዕትም 53
ሳንኮፋ
ትውስታ

During Gondar Book festival sankofa mem-


ber(Eyob Mesfin) with Dr Dessalegn(now the
former UoG president) and Gondar city officials

54 ጭረት
When will we meet? She said
- A year after the war ends.
- When will the war end?
— When we meet.”
----------
Mahmoud Darwish
Palestinian poet

ጭረት
ቀጣይ እትም
በቅርቡ ይጠብቁ

You might also like