You are on page 1of 3

yÄNx@L :Y¬ãC

Daniel kibret’s Views


www.danielkibret.com

የሕይወት ታሪኬ

አዘጋጅ(
አዘጋጅ ፊታውራሪ አመዴ ለማ መጋቢት 1913 ( 2001 ዓም

ኅትመት፡(
ኅትመት 2003 ዓም

ዋጋ(
ዋጋ 60 ብር

ፊታውራሪ አመዴ ለማ ኢትዮጵያ ካፈራቻቸው ታላላቅ ሰዎች አንዱ ናቸው፡፡ በኢትዮጵያ የንግድ እንቅ
ስቃሴ፣ ፖለቲካዊ ጉዞ፣ የሕግ አወጣጥ፣ ማኅበራዊ ኑሮ፣ ሽምግልና እና ቅርስ ላይ የራሳቸውን አሻራ
መተው የቻሉ ሰው ናቸው፡፡

በጥንቱ የወሎ ጠቅላይ ግዛት በወረሂመኑ አውራጃ በአሊ ቤት ወረዳ መጋቢት 30 ቀን 1913
የተወለዱት ፊታውራሪ አመዴ በ88 ዓመት ጉዟቸው የኢትዮጵያን ዘመናዊ ታሪክ ያስቃኙናል፡፡ ስለ
ባህላችን፣ ታሪካችን፣ ሃይማኖታችን እና ኢኮኖሚያችን፣ ብሎም ስለ ዘመናዊው የፖለቲካ ጉዟችን
የሚነግሩን የማናውቃቸው ነገሮች አሉ፡፡

ፊታውራሪ አመዴ ሁለገብ ሰው በመሆናቸው የክርስትናን ባህል ከክርስቲያኖቹ በላይ ሲተርኩት እናያለን፡፡
በተለይም ደግሞ በአካባቢያቸው የነበሩ ዛሬ ግን በመጥፋት ላይ የሚገኙትን ባህላዊ ጨዋታዎች ሲተርኩ

dkibret@gmail.com
yÄNx@L :Y¬ãC
Daniel kibret’s Views
www.danielkibret.com
እኛንም የጨዋታው አካል አድርገው ነው፡፡ በዚያ ዘመን የነበረውን የንግድ አሠራር፣ የሂሳብ አያያዝ፣
የብድር መንገድ፣ የመጀመርያዎቹ ኩባንያዎች እና አክስዮኖች እንዴት እንደተቋቋሙ ይተርኩልናል፡፡

የኢትዮጵያውያን የኀዘን ልብስ ጥቁር የሆነው ከጣልያን ወረራ በኋላ ነው ብለው ይከራከራከሉ
ፊታውራሪ፡፡ ለዚህም ባህላዊ ማስረጃ አምጥተው ባህላቸን ምን እንደነበር ይነግሩናል፡፡ አንብቡት፡፡

በጣልያን ዘመን የነበረውን አስጨናቂ ሁኔታ በልጅ አእምሯቸው የታዘቡትን ሲነግሩን እየተሰቀቅን እንድ
ናነብ ያደርጉናል፡፡ የዚያን ዘመን የፓርላማ እንዴት ይሠራ እንደነበር ከራሳቸው ከንጉሡ ጋር ያደርጉት
የነበረውን ክርክር፣ ከውጭ ይመጣ በነበረው ብድር ላይ ከንጉሡ ጋር በመለያየታቸው ፓርላማው እንዴት
ውድቅ አድርጎባቸው እንደነበር ይነግሩናል፡፡

ፊታውራሪ አመዴ ሴተኛ አዳሪነት በመተዳደርያነት እንዴት በጣልያን ጊዜ እንደ ተጀመረ ራሳቸው ያትን
ይነግሩናል፡፡ ጣልያን ካምፕ ሠርቶ ለወታደሮቹ የሚሆኑ ወጣት ሴቶችን በሴተኛ አዳሪነት እንዴት
ያሠማራ እንደ ነበር ነግረውናል፡፡ እንዲያውም የሴቶቹ ፎቶ በር ላይ ተለጥፎ እንዴት ይመረጡ እንደ
ነበር ያዩትን ይመሰክራሉ፡፡

ንጉሥ ኃይለ ሥላሴን እና የወሎን ሕዝብ ምን እንዳቀያየማቸው፣ በዚህም ምክንያት አልጋ ወራሹ በሕዝቡ
ላይ ይፈጽሙት ስለነበረው በደል፣ ያም በጊዜው ባለ መስተካከሉ በማይጨው ጦርነት የተከሰተውን
አሳዛኝ ነገር ፊታውራሪ እንደ ፊልም ያቀርቡታል፡፡

በእንግሊዝ ስላደረጉት ታሪካዊ ጉብኝ በዚያውም እንዴት ከደጃዝማች ዘውዴ ገብረ ሥላሴ ጋር እንደ
ተገናኙ ይነግሩናል፡፡ ለሀገራቸው ቅን አሳቢ የነበሩት ፊታውራሪ አመዴ ደጃዝማች ዘውዴ ወደ ሀገራቸው
እንዲገቡ ከላይ እስከ ታች የደከሙትን ድካም ያወጉናል፡፡

ፊታውራሪ አመዴ የአኩስም ሐውልት እንዲመለስ ከአርባ ዓመታት በላይ ያደረጉትን ተጋድሎም ተርከ
ውታል፡፡ የታሠሩትን የቅንጅት መሪዎች ለማስፈታት እንዴት እንደ ታገሉ ይተርኩትና የተፈቱት የቅንጅት
መሪዎች ያስፈቱን ፈረንጆች ናቸው በማለታቸው ማዘናቸውንም ነግረውናል፡፡ አያይዘውም «የፈረንጅ
አስታራቂ እና የእህል አረቂ እራስ ከማዞር በስተቀር ዋጋ የለውም» ብለው ይመክራሉ፡፡

ፊታውራሪ አመዴ በገንዘብ እጥረት የተቸገሩ የአንድ ቤተ ክርስቲያን ካህናትን ችግር ለመፍታት በቤተ
ክርስቲያን ተገኝተው ያደረጉትን ንግግር አስፍረውልናል፡፡ በእርሳቸው ቅስቀሳ ቤተ ክርስቲያኑን ከመዘጋት
እንዴት እንደታደጉት ሲነግሩን ምናለ የርሳቸውን ዓይነት ሺዎች ቢፈጠሩ እንላለን፡፡

በመጨረሻም በየመንግሥታቱ የመንግሥታቱን ፖሊሲዎች በመተቸት ያደረጓቸውን ንግግሮች አስቀም


ጠዋቸዋል፡፡

dkibret@gmail.com
yÄNx@L :Y¬ãC
Daniel kibret’s Views
www.danielkibret.com
መጽሐፉን ፊታውራሪ ቢጽፉትም የታተመው ካረፉ በኋላ ነውና የአሟሟታቸውን ሁኔታ፣ የቀብራቸውንም ሥነ
ሥርዓት ቤተሰቦቻቸው ቢያካትቱልን መልካም ነበር፡፡ የፊታውራሪ አሟሟት እና አቀባበር ለክብራቸው
የማይመጥን እንደነበረ የታወቀ ነው፡፡ ኢትዮጵያ ለታላላቅ ሰዎቿ ያላትን ክብር የሚያሳይም ነው፡፡

መጽሐፉን ሳነብ አንዳንድ ጊዜ እያዘንኩ፣ አንዳንድ ጊዜ ደግሞ ብቻዬን እንደ ዕብድ እየሳቅኩ ነበር፡፡
በተለይም ለፓርላማ ሲወዳደሩ ያደረጉትን ክርክር በሳቅ ነው የጨረስኩት፡፡

በሉ እናንተም መጽሐፉን ግዙና እዘኑ፣ ሳቁም፡፡

መልካም ንባብ፡፡

dkibret@gmail.com

You might also like