Professional Documents
Culture Documents
መግቢያ
‹‹ሇምን መግበያ አስፈሇገ›› ካሊችሁ መሌሴ ‹‹ጥያቄ አታብዙ›› ብቻ ነው! እንዯውም በቀጥታ
ወዯታሪኩ ሌግባ.....
ሰማይ ቤት ነው ...ፀሃይ በዯቡብ በኩሌ የሚያምር ‹‹ፒንክ›› ብርሃኗን ረጭታሇች .....
(አሊያችሁትም አሊየሁትም የፈሇኩትን ብናገር እንዲትነተርኩኝ!!) እዚህ ሞቱ ብሇን
አይናችን እሰኪጠፋ ያሇቀስንሊቸው ሁለ ዘና ብሇው በቀን አስራ ሶስት ጊዜ እየበለ
እንዯየምርጫቸው እየሇበሱ በቅንጦት ይኖራለ!! ዴሮ የሞተ ዘንዴሮ የሞተ የሇም ! ማንም
ሲሞት በቃ ይቀሊቀሊሌ.. እዛ ጥግ ሊይ ቅዯስት አርሴማን የመሰሇች ቆኝጆ ብርሃን የመሳሰለ
ወንዴና ሴት አሳሊፊወች አጅበዋት በፍቅር ሇቁርስ የተሰሇፉትን ሙታን ትመሇከታሇች
....ቁርስ የሚታዯሇው ስም እየተጠራ ነው ...ቆንጆዋ ሴት ፈገግ ብሊ ተናገረች ‹‹ አዱስ
የመጣችሁ እንኳን ዯህና መጣችሁ ይሄ የእግዚአብሄር መንግስት ነው... አሁን በዚህኛው
አሇም አቆጣጠር ከዘሊሇሙ አስር ቢሉየን ...ሶስት መቶ ሚሉየን ዘጠና ሁሇት ሽ አራት
መቶ ሰባኛው ሰአት ነው ....የዛሬው ቁርስ ክሮቶ ፐረሰኪ ነው ›› ስትሌ ሁለም
አጨበጨቡ፡፡ በሰማይ ቤት እጅግ ተወዲጅ የሆነና ፓስታ የሚመስሌ ምግብ ነው!! ብዙ ጊዜ
ይሄ ምግብ የሚዘጋጀው እንግዲ(አዱስ ሟች) ሲመጣ መሆኑን ሁለም ስሇሚያውቁ ማን
መጥቶ ይሆን በማሇት ዞር ዞር እያለ ተመሇከቱ፡፡ በእርግጥም አንዴ አዱስ እንግዲ
መሃሊቸው ነበር ‹‹ የምዴራዊት ኢዮጲያን ሇ21 አመት የመሩ አቶ መሇስ ዜናዊ ›› አሇ
አንዴ ግዙፍ ሰውነት ያሇው መሌአክ....ሁለም ‹‹እንኳዋን ዯህና መጣህ ›› እያለ ሞቅ ያሇ
አቀባበሌ አዯረጉ ሇእንግዲው...ሇአቶ መሇስ!!
በዚህ ሁኔታ ቅዴሚያ እንግዲው ቁርስ አንስቶ በግዙፉ መሇአክ እየተመራ ኢትዮጲያዊያን
ወዲለበት ታሊቅ መናፈሻ የሚመስሌ ቦታ ሄዯ... ንጉስ ሃይሇስሊሴን ገና እንዲያቸው ነበር
ያወቃቸው ምንም አሌተቀየሩም ያኔ ዊንጌት በትምህርት ጥሩ ውጠየት አምጥቶ የሸሇሙት
ጊዜ እንዲያቸው!! ከጎናቸው ታሊቁ ሚኒሉክ ሇጣይቱ ‹‹ አፈር ስሆን እችን›› እያለ ጉርሻ
ዘርግተው በፍቅር ይስቃለ ...ትንሽ ራቅ ብል ኮስተር ያሇ ሰው ሹርባው ትከሻው ሊይ
ዘንፈሌ ብል በዝምታ ቁርሱን ይበሊሌ! ዝምታው ያስፍራሌ ...መሇስ በግርምት ይህን ሰው
አየው ሇራሱ ‹‹ቴውዴሮስ ››ብል አንሾካሾከ፡፡ ላሊ ባሇሹርባ ሰው ዯግሞ ከቴዴሮስ ጎን
ተቀምጧሌ ...ይኋንስ ነበር ....መሇስ ራመዴ ብል ይኋንስ አጠገብ የነበረ ክፍት ቦታ ሊይ
ተቀመጠና ወዯዩሃንስ እያየ ‹‹ከመይ›› አሇ!! ዴንገት ሁለም በሳቅ ፈነደ!! ቴውዴሮስ
ሳይቀሩ እግራቸውን አንስተው ሳቁ!! ሚኒሉክ ሳህናቸውን በግራ እጃቸው ይዘው በቀኛቸው
አይበለባ እንባቸውን እየጠራረጉ ‹‹ እመብርሃንን የትግሬ ሰው እንዯሆነ ገምቸ ነበር›› ሲለ
ሳቁ የበሇጠ ሞቀ!! ‹‹ወዲጀ›› አለ ሚኒሉክ ‹‹...እዚህ ምዴራዊ ቋንቋ የሇም ትንሽ ስትቆይ
ውስጥህ በአንዴ ቋንቋ ይሞሊሌ ...እሱም የፍቅር ቋንቋ እንሇዋሇን!! ›› መሇስ ወዯይኋንስ
ተመሇከተ እራሱን በመነቅነቅ የሚኒሉክን ቃሌ እውነት መሆኑን አረጋገጠሇት፡፡
ሲፈራ ሲቸር ‹‹ እዚህ አሇም ሊይ የብሄሮች እኩሌነት የሇም ማሇት ነው እንዳት አንዴ
ቋንቋ ብቻ ላልች ሊይ ይጫናሌ››ሲሌ ኮስተር ብል ጠየቀ...›› ቴውዴሮስ በአትኩሮት
ሲመሇከተው ከቆየ በኋሊ ‹‹ፍቅር የማንም አይዯሇም ...ፍቅር ዯግሞ የሁለም ነው ስሇዚህ
ፊዯሌ ሳትቀርፅ ... ቃሌ ሳትቀሊቅሌ ዴንበርም ሳታበጅሇት የምትግባባበት ቋንቋ ካሇህ
ስሇምን ላሊ ቋንቋ ትፈሌጋሇህ›› አሇና ሰሃኑን ሇአሳሊፊው አቀበሇው፡፡ምግቡ እምብዛም
አሌተበሊሇትም!!
መሇስ ቴውዴሮስን በግርምት እያየው ‹‹ ቋዋንቋ እኮ መግባቢያ ብቻ ሳይሆን ማንነትም
ጭምር ነው.....›› አሇ፡፡‹‹ ማን እንዯሆንክ ሇሚያውቅህ አሇም ማንነትህን ማሳወቂያ እንቶ
ፈንቶ ምን ያዯርጋሌ›› ቴውዴሮስ መሇሰ!! መሇስ ‹እነዚህ ሰወች የዯርግ ርዝራዥ መሰለኝ›
አሇና ከአፉ ሊይ መሇሰው!! እሌህ ቢጤ ግን ሽው አሇበት፡፡.ዴንገት አንዴ ወጣት እያፏጨ
መጣና ተቀሊቀሊቸው‹‹ሀይ ጋይስ... ዯግሞ እች መሊጣ ማናት ›› አሇ ወዯመሇስ እየጠቆመ፡፡
ሃይሇስሊሴ ባይናቸው ሲገሇምጡት ዝም አሇ ወጣቱ !! ‹‹ ሌጅ እያሱ ይባሊሌ›› ብሇው
ሇመሇስ አስተዋወቁት! ሌጅ እያሱ ሳቅ ብል ወዯመሇስ እያየ ‹‹ እንዳት መጣህ; እንዯሱ
እራስህን አጥፍተህ ....›› ወዯቴውዴሮስ እያሳየ...‹‹ ወይስ እነዯሸባው በካሌቾ ብሇው
አባረሩሽ...ሂሂሂሂ›› ሃይሇስሊሴ ተበሳጩ!!
ሚኒሉክ መሇስ ነገሩ እንዲሌተዋጠሇት ገብቷቸው... ወዯጀመሩት ወሬ ተመሇሱና ‹‹
ሰማህ...መስቀሌ በፈረንጅ አፍ ጥራው በአበሻ ሌሳን ሰይመው ቅዴስናውን አትቀንሰውም!!
ያው መስቀሌ ነው ፣ መስቀለ ሊይ ስሇሁለ የሞተው በቋንቋ መከፋፈሌን ሽሮ ፍቅር
ይለት ቋንቋ አብስሯሌና መስቀለ በምንም ቋንቋ ቢጠራ ሁለ ይግባባበታሌ ሁለ
ያከብረዋሌ!! አገርም እንዱሁ ነው!! ባንዱራው ቋንቋው ‹‹ብሄር›› ያሌከው ሁለ ቅደስ
መስቀሌ ነው መስቀለ ሊይ የአገር ፍቅር ይለት እውነት ከላሇ ከንቱ ነው!! ፍቅር ነው
ማንነት !
መሇስ ቁርሱን መብሊት ጀመረ...በውስጡ ‹‹ እነዚህ ሰወች የሚሇቁኝ አይነት አይዯለም››
እያሇ ማሰብ ጀምሮ ነበር!!
‹‹ ያ ባሇጌ የት ሂድ ነው አንተ የነገስከው›› ሲለ ሃይሇስሊሴ ዴንገት ጠየቁ....
‹‹ማን›› አሇ መሇስ
‹‹ እኛን የዯፈረን ያ መንግስቱ የሚባሌ ወሮ በሊ›› አለ ቆጣ ብሇው!!
‹‹ እሱ የተከበረውን የኢትዮጲያ ህዝብ 17 አመት ሙለ ሲያሰቃይ ሲያስርና ሲገዴሌ ይሄ
ግፍ እንዱቆም በሰሊም ብንጠይቀው እንቢ ስሊሇ ሇህዝብ መብት መከበር ስንሌ ጫካ ገብተን
ዴራሹን አጠፋነው ... እኛ ኢትዮጲያን ስንቆጣጠር ግፍና ጭፍጨፋው ቆመ›› ከማሇቱ
ከአጠገባቸው የተቀመጡ በርከት ያለ ወጣቶች በሳቅ አውካኩ፡፡ መሇስ ዞር ብል አይቷቸው
...ሲያበቃ እነማን ናቸው ብል ይኋንስን ጠየቀው ይኋንስ በረጅሙ ተነፈሰና ‹‹ በምዴር
አቆጣጠር 1997 በአንዴ ሊይ የመጡ ናቸው ›› አሇው ባጭሩ!! ‹‹ እዚህም ጩኧት አሇቻ››
ሲሌ አሰበ መሇስ!! ከዛ በኋሊ ዝምታ ነገሰ፡፡ የሌጅ እያሱ ፉጨት ብቻ ነበር የሚሰማው .....
ይቀጥሊሌ....
ክፍሌ ሁሇት
*********************************************
**********************************************************************
******************************************************************
*****************************************************
መሇስ ፣ስብሃት፣ በአለ ግርማ እና ሌጅ እያሱ በአቶ መሇስ አጀንዲ ሊይ ሇመነጋገር አንዱት
ጨሇምሇም ያሇች ጥግ ሊይ ተቀምጠዋሌ ... ይሄ ሁኔታ አቶ መሇስን የመጀመሪያውን
የህወሃት ጉባኤ አስታወሳቸው ውስጣቸው በትግሌ እና በአቢዮት ስሜት ተሞሊ፡፡ በዛ ሊይ
የገዘዋትን ጫት ሲጀምሩ በቃ ነገሩ ሁለ ተገሊሇጠሊቸው .... ሰማይ ቤት በአቢዮታዊ
ዳሞክራሲ መርህ መመራት አሇበት ሲለ አሰቡ! ከሰማይ ቤት ማምሇጥ ብቻ ሳይሆን
መሊውን ጭቁኑን የሰማይ ቤት ህዝብ ከዚህ የአፈና ስርአት ነፃ ማውጣት አማራቸው
.....እናም የእሇቱን አጀንዲ ዯራሲ ስብሃት ከፈቱት....
‹‹ በአለ እንዱሁም እያሱ ወንዴማችን መሇስ አንዱት ሃሳብ ተከስታሇታሇች እናንተ ጋር
እንመካከርባት ብሇን ነው.....››አለ
‹‹ ምን ችግር አሇው እንነጋገርበታ .... ›› አሇ በአለ በእርጋታ
ስብሃት ከገነት ስሇማምሇጥ መሇስ ያወረዋቸውን በዝርዝር ከተናፈሩ በኋሊ ‹‹ የሚጨመር
ካሇ መሇስ ተናገር››
‹‹ ሁለንም ነገር በሚገባ ገሌፀኸዋሌ ....አሁን ዯግሞ ምን አሰብኩ ብቻችንን ከምናመሌጥ
ሇምን እዚህ ያሇውን ስርአት አንቀይረውም ››
በአለ ከትከት ብል ሳቀና ‹‹ወይ መመሳሰሌ !›› አሇ
‹‹ ማን ጋር ?›› አለ አቶ መሇስ ይሄን ሃሳብ ቀዴሞኝ ያሰበ ይኖር ይሆን ብሇው
‹‹ ሳጥናኤሌ ጋር ነዋ!! ....እሱም ወዯምዴር ከመወርወሩ በፊት ሌክ እንዲንተ ነበር ያሰበው
ሃሃሃሃሃሃሃሃ››በአለ ሳቁን ማቆም አሌቻሇም!!
‹‹ ሳጥናኤሌ ..... ሰይጣኑ? ›› አቶ መሇስ በግርምት ጠየቁ
‹‹ ታዱያስ...እሱ ነበር የእግዜር መንግስት ሊይ አብዮት ያስነሳው ከዛ በኋሊ ዯግሞ ይሄው
አንተ ተነሳህ ሃሃሃሃሃ ››
‹‹መቸ ›› አቶ መሇስ ጠየቁ በጉጉት
‹‹ የዛሬ ብዙ ሚሉየን አመት አካባቢ›› ካሇ በኋሊ የሳጥናኤሌን አመፅ ይተርክሊቸው
ጀመረ......
*****************************************************************
ሳጥናኤሌ ሇዴፍን ሰማያዊ ግዛት የእግዜር ወኪሌ የግዜር ጋራጅና አራጅ ሁኖ ተመርጦ
ነበር ! ውበቱ ወንዲወንዴነቱ ግረማ ሞገሱ ...ባጠቃሊይ ሙለ ሁኖ የተፈጠረ ...ማንም
‹የማይሳፈጠው› ታሊቅ መሇአክ ነበር !! እግዜርን ፊት ሇፊት ማየት የተፈቀዯሇት ብቸኛ
መሇአክ !! እንግዱህ እግዚአብሔር ከፀሃይ 7 ሽ እጅ የዯመቀ ስሇነበር እሱን ቀጥ ብል
ማየት የማይታሰብ ነው ወሊ መሇአክት ወሊ ላሊው ፍጥረት ፈጣሪን ፊት ሇፊት አየሁት
የሚሌ አሌነበረም ፡፡ ሳጥናኤሌ ግን አይቶታሌ ፡፡የእግዜር ኪሩብ ነበር .....እግዜር በችልቱ
ሲቀመጥ ሚሉን ቢሉየን ትሪሉየን ከዋትሪሉየን መሇአክት በግንባሩ መሬት ሊይ ተዯፍቶ
ቅደስ ...ቅደስ... እያሇ ይሰግዲሌ ....
ሳጥናኤሌ ፊቱን ወዯሰጋጁ መሇአክት ጀርባውን ሇእግዚአብሔር አዴርጎ ከምዴር ጥግ
እስከጥግ የሚዯርስ ክንፉን ዘርገቶ ይቆማሌ፡፡ የፈጣሪ ሃያሌ ብርሃን እንዯጥቁር መነፀር
ከፊቱ በቆመው ሳጥናኤሌ ክንፍ ውስጥ ያሌፍና ሃይለ ተቀንሶ ብርሃኑም ተሇሳሌሶ
ሇላልቹ ይታያሌ እንዱህ እየሆነ ብዙ ሚሉየን አመት እንዯተቆጠረ አንዴ ቀን ሳጥናኤሌ
ክፉ ሃሳብ ሽው አሇበት ... መሇአክቱ ሇኔ ነው ወይስ ከሀዋሊየ ሇቆመው ፈጣሪ የሚሰግደት
ሲሌ አሰበ!! ‹‹ አይ ሇኔ ነው ....ባይሆንም ሇኔ መሆን አሇበት ››አሇና በሌቡ ያሰበውን ጩሆ
ተናገረው ‹‹ አዋጅ አዋጅ ....ከዛሬ ጀምሮ የምትሰግደት ሇኔ ሇታሊቁ ሳጥናኤሌ መሆኑን
አውቃችሁ ስግዯታችሁን አጠናክራችሁ ቀጥለ››
ሲሌ በታሊቅ ዴምፅ አንባረቀ ፡፡ እግዚአብሄርም እስቲ ጉደን ሌየው ብል ዝም!! ግማሹ
መሇአከክ ሇሳጥኛኤሌ በግንባሩ ተዯፋ ሚካኤሌ ግን ‹‹ ምናሌክ አንተ ›› ሲሌ በቁጣ ጮኸ!!
‹‹ ምንስ ብሌ ምን ያገባሃሌ ዝም ብሇህ ስገዴ ›› ሲሌ ሳጥናኤሌ በትእቢት ተናገረ ‹‹ ‹‹እኮ
ሊማን ነው የምሰግዯው›› አሇ ሚካኤሌ ዯሙ ፈሌቶ
‹‹ ሇኔ ሇታሊቁ ሳጥናኤሌ ነዋ››አሇ ሳጥናኤሌ ከዛ በፊት ባሌታየ ወዯፊትም በማይታይ
ትእቢት
‹‹አሊዯርገውም ...ሇታሇቁ ፈጣሪ ብቻ ነው የምሰግዯው ››
‹‹ ከእኔ በሊይ ታሊቅ የሇም››
‹‹ እንዱህ ነኝና ሚካኤሌ ›› ብል እሳት ሇብሶ እሳት ጎርሶ የእሳት ሰይፉን መዥረጥ
ሲያዯርገው ሳጥናኤሌም አስፈሪ ሰይፉን መዘዘ እሌፍ አእሊፍ መሊእክት ሇሁሇት ተከፈለ
፡፡ግማሹ ከሚካኤሌ ግማሹ ከሳጥናኤሌ ..... ያሁለ የእሳት ሰይፉን እያንቦገቦገ ተፋጠጠ .....
እግዜር ጉደን አያሇሁ ብል ዝም!!!!!!
እነአብርሃ እነማቱሳሊ
ጠጡ ካቲካሊ .....
እነሰይጦ እነሚኪ ተማዘዙ ሻሙሊ....
ሇማንም ምንም አሊለም ጉደ እስኪሇይ ዝም ዝምምም!!
በዛ በኩሌ እነገብረኤሌ እነፋናኤሌ የግዜር ጦር ....በዚህ በኩሌ እነኩሽካኩ እነማናኩ
የሳጥናኤሌ ጦር ......
ተጀጀመረ !!
የሚካኤሌና የሳጥናኤሌ ሰይፍ ሲጋጭ ፀኃይ ተፈነካከተች ፣ኮከቦች ረገፉ፣ ዘጠኝ ትናንሽ
አሇማት ተፈጠሩ ፣ ሰማይ ቤት ተዯረማመሰ ፣ ምዴረ መሇአክ ተጠዛጠዘ...ዴለ
ወዯሳጥናኤሌ አዯሊ ከእሌፉ እሩብ እሌፍ በሰይፍ አሇቀ .... ሳጥናኤሌ አሁን ሜርኩሪ
የምንሊትን ፕሊኔት አንስቶ ሚካኤሌ ሊይ ወረወረበት ሇትንሽ ሳተው ....ሚካኤሌ በተራው
ማርስን አንስቶ እንዯአሇል ወዯሳጥናኤሌ ወረወረበት ...የቀራቸው ፕሊኔት የሇም
ተወራወሩ!! የሚካኤሌ ጦር ተዲከመ ከዛ ሁለ መሇአክ ጥቂት ቀሩ ...የሳጥናኤሌ ጦር ግን
የመፋሇም ወኔው እየጨመረ ጭራሽ እነሚካኤሌን መክበብ ጀመረ ..... በመጨረሻ ሚካኤሌ
ጦሩን ሉያይ ዞር ባሇበት ቅፅበት የሳጥናኤሌ ክንዴ አረፈበትና ወዯቀ!! ሳጥናኤሌ በፍፁም
ትእቢት ሚካኤሌን ቁሌቁሌ እያየ ሰይፉን ከፍፍፍፍፍ አዯረገና በሚካኤሌ ሌብ ትክክሌ
ቁሌቁሌ ሉሰካበት ሲያነጣጥር ሚካኤሌ የቀኝ ክንፉን ሇመነሳት ዘረጋ..... በዚች ቅፅበት
ሚካኤሌ ክንፉ ሊይ በዯማቅ ቀይ ቀሇም የተፃፈው የፈጣሪ ስም የሳጥናኤሌን ሰይፍ እጁ
ሊይ አሟሟው ....አይኑ ጨሇማ ጉሌበቱ ቄጤማ ሆነበት ...... ነገር ተገሇባበጠ በቃ!!
ሳጥናኤሌ የፊጥኝ ተጠፍሮ ቁሌቁሌ ወዯጨሇማ ተጣሇ ግብረአበሮቹ በምዴር እንዯትቢያ
ተበተኑ እነጅኒ እነ መተት እነቡዲ .......›› አሇና በአለ ግርማ ትረካውን ጨረሰ !!
አቶ መሇስ በጥሞና ሲያዲምጡ ቆዩና ‹‹ በጣም ጥሩ ሳጥናኤሌ የተሸነፈበትን ምክንያት
ስንገመግም
1. ሳጥናኤሌ ህዝባዊ አሌነበረም ሰራዊቱም የተሳሳተ መነሻ ይዞ ነበር የተዋጋው
2.ሳጥናኤሌ በቂ እና አሳማኝ ቅስቀሳ አሊዯረገም ! ቅስቀሳው ቢዯረግ ኖሮ በቀሊለ የቀሩትን
መሊእክት ከጎኑ ማሰሇፍ ይችሌ ነበር
3. ባጠቃሊይ የዚህ ጦርነት ጥሩ ጎን ቢሸነፍም ወዯምዴር ተወርውሯሌ ፡፡ እኛም
የምንፈሌገው ተወርውረንም ይሁን በክብር ተሸኝተን ወዯምዴር መመሇስ ነው ስሇዚህ በዚህ
ጦርነት ተሸናፊ የሇም››
‹‹ አሇቻ ወኔ ›› አለ ስብሃት!!
(ይቀጥሊሌ)
April 1, 2013
April 3, 2013
*****************************************************************************
April 5, 2013
ባሇፈው ወጋችን በክፍሌ አስራ አንዴ ግማሽ አቶ መሇስ ሁኔታውና አጋጣሚው ፕ/ር
አስራት ቤት አዴርቸው በእንግዴነት በሄደበት ቤት ሞቅ ያሇ ክርክር ገጥሟቸው እንዯነበር
አይተናሌ ፡፡ ....
‹‹ የምትሄዴበት መኪና ከውጭ ወዯውስጥ ባያሳይም ህዝብህ ያይሃሌ ያውቀሃሌ!! አንተ
ግን ከውስጥ ወዯውጭ ህዝብህን እያየኸውም አታውቀውም .....አመፁን ተወው ትግለን
ተወው ዝም ብል የሰራሃውን ብትስራ እንዯባእዴ ዲር ቁሞ የሚያይህ ህዝብ እኮ ስታሌፍ
ስታገዴም ርግማኑን ያሌጎመጉማሌ!! ‹እየውሌህ የእግዚአብሄር እጣ ፋንታ ህዝቡ ነው›
ይሊሌ የክርስቲያኖች መፅሃፍ ቅደስ በየትኛውም እምነት ህዝብ የባሇስሌጣን ሳይሆን
የፈጣሪ ሃብት ነው! ህዝብ ብረት አንስቶ ባይፋሇምህ ከተማ ወጥቶ ባሇስሌጣን ባይሳዯብ
ይህ ህዝብ የቲም አይዯሇም ባሇቤት አሇው! ባሇቤቱ የተነሳ ቀን ባሇስሌጣኖችህን እንዲሳማ
አመዴ ያስሌሳቸዋሌ ...በህዝብ ገንዘብና ሃብት የሚሞሊቀቁትን ሁለ .... ›› እያለ ፕ/ር
አስራት መሇስን ሲሞግቱት ነበር ያቆምነው ....ወጋችንን እንቀጥሌ....
***************************************************************************
ፕሮፌሰር አስራት ጥሌቅ በሆነ ዝምታ ውስጥ ቆዩእና በትህትና ‹‹ ይቅርታ እንግዱህ
ወንዴሜ ከወግና ከባህሊችን አፈንግጨ እንግዲየን በመነትረኬ ›› አለ አቶ መሇስን ቅሬታ
ባዘሇ ፈገግታ እየተመሇከቱ
‹‹ ግዴ የሇም ፕ/ር ..ሃሳብዎትን በግሌፅ በመናገረወ ተዯስቻሇሁ ፤በቀጣይ ሇምናካሂዯው
የሌማት ስራ ግብአት ይሆነናሌ›› አለ አቶ መሇስ
‹‹ ሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃ እንዳ ሃሃሃሃሃሃሃሃሃ ይቅርታ ..በቀጣይ
ነው ያሌከው ? ሃሃሃሃሃ...አንተ ሰው መሞትህን እስካሁን አሊመንክም ማሇት ነው?
....ሃሃሃ ሇዘሊሇም ከዚህ ውሌፍት ማሇት የሇም አቶ መሇስ ! አሇቀ! ተከተተ! ቀጣይ
የሚባሌ ታሪክ የሇም...›› ፕ/ር ሳቃቸውን ማቆም አሌቻለም!!
አቶ መሇስ ወዯ ፕ/ር አስራት ጠጋ አለና ‹‹ ፕ/ር! እኔና እርሰዎ የተሇያየ አመሇካከት፣
የተሇያየ እሳቤና ባህሪ እንዲሇን ግሌፅ ፤ነው ግን ...በአንዴ ነገር የምንስማማ ይመስሇኛሌ
.....እሱም ሊመንበት ነገር ወዯኋሊ አንሌም!! ምዴርም ሊይ እያሇን ሁሇታችንም እግራችንን
ከተከሌንበት የአመሇካከት ዴንበር ሊይ መነቃነቅ አቅቶን ነው የሆነው ሁለ የሆነው!!
...ገሊጋይ አጥተን ሁለም ዴንጋይ የሚያቀብሌ ...››
‹‹ እስቲ ወዯነጥብህ.... አቶ መሇስ ››
‹‹ .... ሌነግረወት እኮ ነው .... ከዛ በፊት ግን ሌጠይቀወት፣ አንዴ እዴሌ ተሰጥቶዎት
ወዯኢትዮጲያ ቢሄደ ምን ያዯርጋለ ?››
‹‹ አሁን ኢትዮጲያ ሊይ ገዡ ማነው? ››
‹‹ኢህዳግ ››
‹‹እንግዱያውስ መሄዴ አሌፈሌግም !!››
‹‹እሽ ላሊ መንግስት ነው እንበሌ›› አለ አቶ መሇስ ሉያማትቡ እየቃጣቸው
‹‹ ጥሩ.... አንተም ወዯምዴር ትመሇሳሇህ ወይስ ብቻየን ነው የምንሄዯው? ››
‹‹ ማሇት....በቃ ..እኔም እርሰዎም ምዴር ሊይ ብንመሇስ.....››
‹‹ ጥሩ ....ሁሇታችንም ብንመሇስና... ኢትዮጲያ "ፍትሃዊ በሆነ መንግስት" እየተዲዯረች
ብትጠብቀን ማሇት ነው?››
‹‹ትክክሌ!! ›› አለ አቶ መሇስ ሇመሌሱ ጓጉተው
‹‹ እንዯዛ ቢሆንማ ...›› አለ ፕ/ር.. ፊታቸው በዯስታ በርቶ አይኖቻቸውን ጨፍነው ሁሇት
እጆቻቸውን ወዯሰማይ ዘርግተው ‹‹እንዯዛ ቢሆን....የመጀመሪያ ስራየ እርሰወን ፍርዴ ቤት
መገተር ነበር!! ...ያው ፍርዴ ቤቱ ሇሰሩት ግፍና በዯሌ ሞት ስሇሚፈርዴብዎ እርሰወ እኔን
ሸኝተው ይመሇሳለ!! እኔ አገሬ ሊይ ቀሪ እዴሜን የናፈቀኝን ነፃነት እያጣጣምኩ...ሁለም
በስራው ሌክ የሚጠቀምባት ... አገሬን ...እንዯጧት ፀሃይ እየሞኳት ...ወጣቶቿ ጥሇዋት
የማይፈረጥጡባትን አገሬን ... ጥጋበኛና ጉቦኛ አስመሳይና ዘረኛ ባሇስሌጣናት
የማይፈነጩባትን አገሬን እያያሁ ....እውር ፍርዴ ቤት አካሇጎዯል ዱሞክራሲ እጁ የሰሇሇ
ህገ-መንግስት ‹ኮማ› ውስጥ የገባ የምርጫ ቦርዴ ሳይሆን የፍትህ ክንደ ግፈኞችን
የሚዯቁስ፣ እውነት ሳትወጣ መድሻው ጠረንጴዛ የማይዯቃ ፍርዴ ቤት ያሇባት አገሬን
...‹ህዝብ ብሎሌ› የተባሇሇት ሳይሆን ህዝብ በትክክሌ ይሁን ያሇው ህገ መንግስት ያሇባት
አገሬን ...በአንዴ አይኑ የባሇስሌጣን ቁጣ በላሊኛው አይኑ የወንጀሇኛ መቅጫ ህግ እያየ
የማይፈርዴ ዲኛ ያሇባት አገሬን እያየሁ... በቃህ እስካሇኝ እኖር ነበር!!›› አለና ግን ምን
ያዯርጋሌ ....ብሇው ዝም አለ...
አቶ መሇስ ስሇአቢዮታቸው እያሰቡ ‹‹ በቃ ይሄው ነው ምኞትዎ ?...››አለ
‹‹ ላሊ ላሊ .....አዎ!! ...ሁሌጊዜ እሁዴ እሁዴ የእርሰወን ባሇስሌጣናት ቃሉቲ እስር ቤት
እየሄዴኩ እጠይቃቸው ነበር፡፡ ሁለም መታጎራቸው ስሇማይቀር ....››
‹‹ ፕ/ር ሰማይ ቤት አስዯስቶዎታሌ››
‹‹ በሚገባ! ማንም ሲገፋ አሊይም ...ማንም ሲራብ አሊይም ...ማንም ሲታሰር አሊይም...››
‹‹ ፕ/ር ሁሊችንም እኮ እስረኛ ነን እንዯውም የዘሊሇም ይሄ እንዳት አይታይዎትም››
‹‹ሃሃሃሃሃሃሃሃ››
‹‹ምን አሳቀዎት››
‹‹ እስር ያስጠሊሌ አይዯሌ ››
‹‹ በጣም››
‹‹ ይሄንን ስታስፈፅም ነው የኖርከው !! በቂ ባሌሆነ ምክንያት ስታስር ከኖርክ አንተንም
ያሰረህ በቂ ምክንያት ያሇው አይመስሌህም››
‹‹ እኔ ማንንም ካሇበቂ ምክንያት አሊሰርኩም የማሰርም ስሌጣን አሌነበረኝም ...የአገርን
ሰሊም የአገርን ዯህንነት የማስጠበቅ ህዝባዊ ሃሊፊነት ነበረብኝ ፡፡ ህገ መንግስቱን የጣሰ
ማንም ሰው ከየትም ይምጣ የትኛውም የትምህርት ዯረጃ ይኑረው በሃገሪቱ ህግ ይዲኛሌ››
‹‹ ..የትኛውም ስሌጣን ቢኖረውስ››
‹‹እባክዎ ፕ/ር አያሊግጡ እያወራን ያሇነው ስሇሃገር መሰሇኝ››
‹‹አአአአ ስሇሃገር ሳይሆን ስሇኢትዮጲያ ነው››
‹‹ኢትዮጲያ አገር አይዯሇችም እንዳ››
‹‹ አገር ማሇት ምዴሯ ሊይ የተወሇደ ሁለ ንብረት ናት ካሌን ኢትዮጲያ አገር ሇመሆን
ህዝብ የቀራታሌ››
‹‹ህዝቡ የት ሄዯ ያውም በቋንቋ በባህሌ በታሪክ ሃብታም የሆነ ህዝብ ያሊት አገር መሆኗን
ማንም ይመሰክራሌ››
‹‹ ሌክነህ ማንም ይመሰክራሌ ህዝቡ ራሱ ግን አይመሰክርም..ህዝቡ የሇም እኮ ሸፍቷሌ
አረብ አገር የሚለት ጫካ ሴቱ ዘምቷሌ፣ ወንደ....››
‹‹ የሰው ሌጅ የፈሇገበት አገር ሂድ የመስራትም ሆነ የመኖር ሰበአዊ መብቱ ሉከበር
ይገባሌ ››
‹‹መብትን ተጠቅሞ በምርጫ መሄዴ ላሊ በዴህነት ካሌቾ ተጠሌዞ አገርን ጥል መሄዴ
ላሊ››
‹‹ፕ/ር... ሇምን ሁለን ነገር ያጨሊሌሙታሌ... ሇምን እኛ ሊይ ሲዯርስ ላሊ አገር ሂድ
መስራት ብርቅና ዴንቅ ይሆናሌ . ስንትና ስንት ህዝብ ካንደ አገር ወዯላሊው እየሄዯ ይኖር
የሇም እንዳ...በብዙ ሽ የሚቆጠሩ ቻይናውያን በመሊው አሇም አገራቺንን ጨምሮ
ተሰራጭተው እየሰሩ አይዯሇም እንዳ...››
‹‹አቶ መሇስ ! ስሇመሄዴ አይዯሇም የማወራህ ... ሳይፈሌጉ ስሇመሄዴ ነው ...!! ዯግሞስ
ከላሊው አሇም ወዯአገራቺንም ሆነ ወዯ ላሊ ገር የሚሄደ ዜጎች እንዯኛ ተዋርዯውና ሰበአዊ
ክብራቸው ተረግጦ ነው እንዳ የሚኖሩት....በታሪክ ከውጭ አገር ወዯ ኢትዮጲያ ሂድ
የተዋረዯ ሰው ያውቃለ....የነብዩን መሌእክተኞች ተቀብሊ አርዲና ጋርዲ ያኖረች አገር
ሌጆችዋ ከፎቅ እየተወረወሩ እንዯላባና ቀማኛ እየተሳዯደ ነው ዛሬ .....
የአገሬ ቄስ ከትምህርት ቤት ትምህርት ቤት በእግሩ ሲንከራት ስሇእመብርሃን እያሇ በቁራሽ
ርሃቡን እያስታገሰ ያገኘውን ቅስና እየናቅን አገሩ ሊይ መክሇፍት ሲያሳዴዴ የኖረ እዚህ ግባ
የማይባሌ የፈረንጅ ዱያቆን አገራችን ሊይ በክብር የነገስታት አማካሪ ሁኖ ሲንዯሊቀቅ ነው
የኖረው ! ወርቅ ቢያነጥፉሊቸው ዞረው የማያዩ ሴት ሌጆቻችን ‹ሰይጣንም ቢሆን አግብቶ
ከዚች አገር ያውጣን › እያለ አይዯሇም እንዳ....››
‹‹ ይሄ ከግሌ ስነምግባር ጋር የተያያዘ ጉዲይ ነው ... ››
‹‹የቱ ነው ከግሌ ስነምግባር ጋር የተያያዘ ጉዲይ ››
‹‹የሴት እህቶቻችን››
‹‹ ምኑ ሊይ ነው የስነምግባር ችግርነቱ ››
‹‹ ሴትነትን የችግር መፍቻ ቁሌፍ አዴርጎ የመጠቀሙ አመሇካከት ነዋ !!...በየትኛውም
አገዛዝ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ ሇሴቶች መብት ታግሇናሌ!! ሴቶች ሊይ ተጭኖ የኖረው
የባርነት ቀንበር ከባዴ ከመሆኑ ብዛት ምንግስትና ህዝብ ተባብረው እንኳን ባንዳ
ሉያወርደት አሌቻለም፡፡ ሴቶችን ከወንድች ጭቆና ቀርቶ ከራሳቸው ‹‹የአንችሌም›› እሳቤ
ማሊቀቅ ራሱን የቻሇ ከባዴ ስራ ነው!! ከጓዲ ወዯትምህርት ቤት ወዯስራ ብልም ወዯስሌጣን
እና ወዯታሊሊቅ ሃሊፊነቶች ሴቶችን ማምጣት ፈተና ነበር ሇእኛ ፡፡ ቢሆንም ወዯዚህ
እስከመጣሁበት ጊዜ አበረታች የሆኑ ሇውጦች አይተናሌ ....››
‹‹አቶ መሇስ››
‹‹አቤት ፕ/ር...››
‹‹ ሰሇቸኸኝ !!....››
‹‹እንግዱያውስ ሌሂዴ›› ብሇው ከተቀመጡበት ተነሱ አቶ መሇስ
‹‹ ሰሇቸኸኝ እንጅ ሂዴ አሊሌኩም››
‹‹ አይ እኔም እርስዎ ስሇሰሇቹኝ ብሄዴ ይሻሊሌ ብየ ነው›› አለ እሌህ በሚመስሌ
አነጋገር፡፡
‹‹ሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃ....ኖ! ርእስ እንቀይር ማሇት ነበር የእኔ ሃሳብ ሶሪ ስሊስቀየምኩህ ››
‹‹ አሁን መሄዴ አሇብኝ !!! ባይሆን ላሊ ቀን እንገናኛሇን ››
‹‹ ጥሩ ከመሄዴህ በፊት ግን አንዴ ነገር ሌጠይቅህ ይሄ ሰማይ ቤት ነው እውነትን ዯበቅን
አሌዯበቅን ዋጋ የሇውም ...እንዳው ከኢሃዳግ ባሇስሌጣናት በጣም የምትጠሊው እና በጣም
የምትወዯዲቸውን ንገረኝ እስቲ››
አቶ መሇስ ጥያቄው አሳቃቸው ሳቁን እንዯቀሌዴ ጀመሩትና የሆነ የሆነ ነገር ትዝ
እያሊቸው ሰማይ ቤት ከመጡ ጀምሮ ስቀው የማያውቁትን ሳቅ ሳቁ ‹‹ ሃሃሃሃሃሃሃሃ
ሂሂሂሂሂ.....››
(ይቀጥሊሌ)
ባጭሩ ባሇፈው ወጋችን ጠ/ሚንስትር መሇስ ፕ/ር አስራት ጋር የሞቀ ክርክር አዴርገው
እንዯነበር አውስተናሌ፡፡ ቀታዩ እነሆ....
በሰማይ ቤት ነገስታት የሚያርፉበት ቦታ ላሊው ተራ ህዝብ ከሚያርፍበት ቦታ ይሇያሌ፡፡
በሩ ሊይ ክንፉ ከኮተቤ አቃቂ የሚዯርስ መሇአክ ጎርዯዴ ጎርዯዴ እያሇ ይጠብቃሌ !! አቶ
መሇስ በዚህ ግቢ ሇሁሇት ወራት ሲኖሩ እንዯፈሇጉ ሲገቡና ሲወጡ አይተውት ስሇማያውቁ
ዛሬ እንዯጆቢራ ፊታቸው ተገትሮ መንገዴ ሲከሇክሊቸው ግራ ተጋቡ! ቀጥ ብሇው አዩት
ዯራሲወች መንዯር ውሇው .... መሸት እስከሚሌ ዴረስ ዯግሞ ፕ/ር አስራት ጋር ቆይተው
ገና መመሇሳቸው ነበር!‹‹ የምዴራዊው ሙታን ችክችክ ሲገርመኝ መሇአኩ ዯግሞ ምን
ፍጠር ይሇኛሌ›› አለና ሲፈሩ ሲቸሩ ‹‹ጌታየ ችግር አሇ›› አለት አይናገር አይጋገር ዝም!!
‹‹እዚህ ውስጥ ነው የምኖረው መሇስ እባሊሊሁ›› ዝም!!
‹‹ ጠቅሊይ ሚንስትር መሇስ ዜናዊ እኮ ነኝ›› ዝም ! አሌፈውት ሉሄደ ሲለ ክንፉን
ዘርጋው ....እየተዘረጋ እየተዘረጋ.....አይናቸው ማየት እስኪችሇው ዴረስ ተዘርግቶ ጫፉ
አዴማስ ውስጥ ገባ.... አቶ መሇስ ‹‹የባቡር ሃዱዴ በዚህ ፍጥነት ቢዘረጋ ...›› ብሇው
አሰቡና
‹‹ ይቅርታ ይሄን ሁለ ክንፍ የሚያዘረጋ ምን ችግር ችግር ተፈጠረ ›› ሲለ ጠየቁ...ዝም!!
ስብሃት ገ/እግዚያብሔር ትዝ አሎቸው
እነአብርሃም እነማቱሳሊ ጠጡ ካቲካሊ
..........ጠጥተውም ዝም ! ዝምምምምም እንዯመሇአኩ ከንፍ የረዘመ ዝምታ!!
‹‹ ሇምን አታሳሌፈኝም ....›› ዝም!!
‹‹የምዴራዊት ኢትዮጲያ ጠቅሊይ ሚንስትር መሇስ ዜናዊ አስረስ እኮ ነኝ››
‹‹ብትሆንስ?›› አስገምጋሚው የመሇአክ ዴምፅ መሇስን ወዯኋሊ አስፈነጠራቸው
‹‹ እሱማ ብሆንም ዋጋ የሇውም አሌፏሌ›› አለ ነገሩን ሇማረጋጋት
‹‹ ባያሌፍስ?›› መሇአኩ በበሇጠ ዴምፅ አስገመገመ
‹‹ማሇቴ ...ያው...ቆይ ግን ሇምንዴነው እንዲሌገባ የተከሇከሌኩት? ››
‹‹ጠ/ሚንስትር እዚህ አይገባም›› አሇ መሇአኩ ባጭሩ
"እና ምኖች ናቸው የሚገቡት?››
‹‹ነገስታት ብቻ››
‹‹ እኛ አገር የምንተዲዯረው በንጉስ ሳይሆን እንዯእንግሉዝ እንዯ .....በቃ ንጉስ ሌትሇኝ
ትችሊሇህ!! !የንጉሳዊ አገዛዝ በአገራችን ስሇላሇ እንጅ ንጉስ ማሇት ነኝ ያው››
‹‹ አይመሇከተኝም ንጉስ ብቻ ነው እዚህ የሚገባው ››
‹‹ እና አገር መሪ አይገባም ?››
‹‹ይገባሌ! ሚንስትር ሚንስትሮች ጋር ነው ››
‹‹እኔኮ ሚንስትር አይዯሇሁም ሇምን አትረዲኝም ጠቅሊይ ነኝ ....››
‹‹ ጠቅሊይ ምን››
‹‹ሚንስትር››
‹‹ሚንስትሮች ጋር ሂዴ››
‹‹ንጉስና አገር መሪ ምን አሇያየው 21 አመት አገር መርቻሇሁ››
‹‹እኔም 21 አመት አገር መርቻሇሁ›› አሇ መሇአኩ 21 አመት አገር መምራት ብርቅ ነው
እነዳ በሚሌ ዴምፅ
መሇስ በጣም ተገርመው ‹‹የት ነው አንተ አገር የመረሃው ዯግሞ... እኔ በታሪክም
በአካሌም ሰምቸም አይቸም አሊውቅም እንዲንት አይነት ...ማሇት....›› አለ ክንፉን እያዩ
‹‹ ክንፌ ገርሞህ ነው ሃሃሃሃ! ምዴር ሊይ አገር መሪ የነበራችሁ ሁለ በአይን ስሇማይታይ
እንጅ አንዲንድቻችሁ ጭራ አንዲንድቻችሁ ቀንዴ አሊችሁ በጣም አሌፎ አሌፎ ክንፍ ቢጤ
ያሊቸውም ነበሩ›› አሇ ቀሌዴ በሚመስሌ አነጋገር
‹‹ ቆይ አንተ 21 አመት የመረሃው የትኛውን አገር ነው ›› አለ መሇስ
‹‹ኢትዮጲያን››
‹‹ አ....ኢትዮጰያ...ኢትጲያ ምዴር ሊይ ያሇችውን ኢትዮጲያ....››
‹‹ አወ››
‹‹ ትቀሌዲሇህ››
‹‹አሌቀሇዴኩም›› የተቆጣ መሰሇ መሇአኩ
‹‹እና ኢትዮጲያን ከመቸ እስከመቸ መራሃት ....››
‹‹ ከ 1983 እስከ 2004››
‹‹ይሄ ጊዜ እኮ እኔ ኢትዮጲያን የመራሁበት ነው››
‹‹ አይግረምህ! ዴፍን አፍሪካ እንዯመሪወቿ ግፍና በዯሌ ቢሆን ኖሮ እስካሁን አትኖርም
ነበር፤ አንዴ ገዠ ስሌጣን ሲይዝ አንዴ ሃያሌ መሇአክ ህዝቡን ሇመጠበቅ ይመዯባሌ
ምክንያቱም ህዝቡ ንብረትነቱ የታሊቁ ፈጣሪ እንጅ የመሪው አይዯሇም ፡፡››
አቶ መሇስ በመሇአኩ ንግግር ተበሳጩ ‹‹...ተው እንጅ እና ነገስታቱ ህዝቡ፣ ሳር ቅጠለ
፣የምትተነፍሱት አየር ሳይቀር የኛ ነው ሲለ የት ነበራችሁ ... ህዝቡ የሚያመሌከውን
አምሊክ ሳይቀር ነገስታቱ ሲመርጡሇት የት ነበራችሁ ...ዯርግ ያንን ሁለ ህዝብ ሲያርዯው
የት ነበራችሁ ....›› አለና አፈጠጡበት....
‹‹ ምነው አቆምክ....›› አሇ መሇአኩ በትዝብት ፈገግ ብል
‹‹ ...ሂትሇር ያንን ሁለ አይሁዴ ....››
‹‹ቆይ ቆይ ...ከዯርግ ቀጥል ሂትሇር ነበር ኢትዮጲያ ሊይ ገዥ የነበረው? ....ስሇራስህ
ተናገር››
‹‹ እኔ ምን አዯረኩ...? ››
‹‹ቅዴም ያሌካቸው ነገስታትም እኛ ምን አዯረግን ነው የሚለት....ሂትሇር እራሱ እንዯዛ
ነው የሚሇው ....››
‹‹ያው 21 አመት ገዛሁ ካሌክ በእኔ የስሌጣን ዘመን ..... ያየኸውን ስህተት ተናገር ...በእኔ
ጊዜ ነው የሃይማኖት ነፃነት የተከበረው ....በእኔ ጊዜ ነው ሃይማኖትና መንግስት ተሇያይቶ
የየራሱን ጉዲይ ካሇማንም ጣሌቃ ገብነት ሲያከናውን የነበረው ሇምን እንዲሊየ ትሆናሇህ....››
መሇአኩ ፈገግ አሇና ‹‹ ...ባአንተ ጊዜ ነው ሞራሌ እና ስነ ምግባር የሂወት መንገዴ መሆኑ
ቀርቶ አንዴ የትምህርት አይነት ብቻ የሆነው ....ባንተ ጊዜ ነው ፖሇቲካ የሚተነፍስ
እየታነቀ ዴራሹ ሲጠፋ መገናኛ ብዙሃኑ ሁለ ስሇዘሙት እናስተምር ብሇው ዝሙት ህዝብ
ውስጥ የዘሩት...ባንተ ጊዜ ነው የወሲብ አብዮት ፈንዴቶ ሴት ወንደ በአሰቃቂ ጥሌፍሌፎሽ
ውስጥ የወዯቀው .......ትውሌዴ በዝሙት የተጥሇቀሇቀው ... ባንተ ጊዜ ነው ግብረሰድም
ያቆጠቆጠው... ››
አቶ መሇስ በውስጣቸው ‹‹ ይሄ መሇአክ የግንቦት ሰባት አባሌ ነው እንዳ ›› ብሇው አሰቡ
‹‹ እና አሁን በሩን ትሇቅሌኛሇህ ወይስ ሌሇስ ››
‹‹ተመሇስ››
‹‹ እስካሁን እዚህ ስኖር ሇምን አሌተከሇከሌኩም››
‹‹ ነገስታቱ አሌከሇከለህም ነበር ››
‹‹እና አሁን ከሇከለ ››
‹‹ አወ እንዲይመጣብን አለ››
መሇስ ቱግ አለ እሌሃቸው ውስጣቸው ተንተገተገ ‹‹ ስማ!... ገዯሌ ግቡ በሊቸው ... ይሄ
ተንኮሌና ክፋታችሁ ነው አገራችንን ወዯኋሊ ያስቀራት ብሎችኋሌ በሊቸው .. ፈሪ ቦቅቧቃ
ናችሁ በሊቸው ወሊ አዴዋ ወሊ መቅዯሊ ትሊሊችሁ እንጅ እውነት ፊት ሇሴከንዴ መቆም
የማትችለ የተንኮሌ አባቶች ናችሁ በሊቸው ..›› አለ በብስጭት እየተወራጩ
‹‹እኔ ነገር አመሊሊሽ አይዯሇሁም››
‹‹ እሽ አንዳ ፍቀዴሌኝና እራሴ ነግሪያቸው ሌመሇስ››
‹‹ ጥፋ ከዚህ›› መሇአኩ ዴፍን ሰማይ ቤትን የሚያናጋ በሚመስሌ ዴምፅ አንባረቀ፡፡
አቶ መሇስ ቁጣቸው እንዯዝንብ መንጋ ግርርር ብል ከሊያቸው ሊይ ሲሄዴ ታወቃቸው ፡፡
‹‹እንዲሌክ›› አለ በማይሰማ ዴምፅ ዙረው መንገዲቸውን ቀጠለ!! ሇረዥም ሰአት መናገርም
ማሰብም ተኗቸው እግሮቻቸውን ተከትሇው ከተጓዙ በኋሊ ዴምፃቸውን ቀንሰው
‹‹ ምን ያስዯነፋዋሌ ታዯያ ፈጣሪ የሰጠውን ስሌጣን በስርአት አይጠቀምም...አምባ ገነን..››
አለና ወዯኋሊቸው ዞር ብሇው ተገሊመጡ ወዱያው ቀጥ ብሇው ሲያዩ ዙረያውን በንፁህ
ውሃ የተከበበ ዯሴት ከሩቁ ተመሇከቱ ዲሩ ሊይ አረፍ አለና በትካዜ ዯሴቱን እያዩ ውሃ
በሆነ ሙታን ህዝብ ውሃ በሆነ አሇም ውሃ በሆነ መሇአክ ውሃ በሆነ ፕሮፌሰር የተከበብኩ
ዯሴት ነኝ›› አለ!! የማያውቅት ስሜት ወዯዯሴቷእንዱሄደ ገፋፋቸው፡፡ ግን መንገዴ
የሇውም ዙሪያውን ውሃ ነበር!! ከተቀመጡበት ተነስተው ሲንጎራዯደ ሁሇት ሰወች
ከሀዋሊቸው መጥተው በቀጥታ ወዯውሃው ሄደ ምንም እንዲሌተፈጠረ ሁለ እየሳቁ
ወዯውሃው ገቡ ! ውሃውን ያት አይመስሌም...አቶ መሇስ ሉጮሁ ብሇው ተውትና
የሚገርመውን ተአምር ማየት ጀመሩ ሰወቹ በውሃው ሊይ እየተራመደ ወዯዯሴቱ ይገሰግሱ
ጀመረ ...
አቶ መሇስ ነገሩን ማመን አሌቻለም መሞከር እንዲሇባቸው ወስነው ወዯውሃው ተጠጉና
ቀኝ እግራቸውን አስቀዴመው ውሃውን ረገጥ አዯረጉት እንዯመሬት ጠንካራ ነው
ዯጋግመው ሞከሩና አንዴ እግራቸውን አስከተለ ቀስ በቀስ በዴፍረት በውሃው ሊይ
መራመዴ ጀመሩ.... ከዛ ሶምሶማ .....በመጨረሻም እንዯእብዴ እየሳቁ እሩጫ ጀመሩ፡፡
በውሃ ሊይ መሮጥ እጅግ በጣም የሚያዝናና ነበር ሃሳባቸውን ሃዘናቸውን አስረሳቸው፡፡
‹የኢትዮጰያ ህዝብ ይህንን ቢያይ ምን ይሊሌ › ሲለ አሰቡ መጀመረያ የኢሃዳግ
ባሇስሌጣናት .... ሃሳቡ አዝናናቸው አባደሊ ገመዲ ‹ እሳቸው የጀመሩትን...› ብል ቢሸፍቱ
ሃይቅ ውስጥ ሲዘፈዘፍ ታያቸው ....ሳሞራ ታንክ ይዠ ካሌተሸገርኩ ማሇቱ አይቀርም
...ስዩም መስፍን ረጋ ብል ፊቱን በውሃ ውስጥ እያየ ሲያዘግም አዱሱ ሇገሰ ጣናን እንዳት
የእግር መንገዴ ማዴረግ ይቻሊሌ ብል ሉጠይቅ ይችሊሌ፡፡
በረከት ስምኦን ሇቪኦኤ እንግሉዝኛው ክፍሌ ‹‹ሇህዝብ ጥቅም እንኳን በውሃ ሊይ በእሳት
ውስጥ አሌፈን ነው የመጣነው ምኑ ነው የሚያስዯንቀው ›› ሲሌም ታያቸው ...
.‹‹.አቶ ኃይሇማሪያም ዯሳሇኝ ምን ይሌ ይሆን › ›አለና ሩጫቸውን አቁመው ማሰብ
ጀመሩ.... ምናሌባት‹‹ የኢትዮጲያ ህዝብ ሆይ የተከበራችሁ ሴቶች ፣የተከበራችሁ ወንድች
...የተከበራችሁ ተማሪወች ፣ የተከበራችሁ ....የጎዲና ተዲዲሪወች....የምታመሌኩትን ዛሬ
ምረጡ እኔና ፓርቲየ ግራ ገብቶናሌ ክርስቶስም በውሃ ሊይ ተራምዯዋሌ መሇስም
ተራምዯዋሌ...ክርስቶስም ተከተለኝ ብሇዋሌ መሇስም ተከተለኝ ብሇዋሌ .....ያም ስሇኛ
ተሰውቷሌ ይሄም ስሇኛ .......››
ተቀዋሚወችም ዝም አይለም! ብርሃኑ ነጋ ‹‹በውሃ ሊይ መራመዴ ስሇቻሌን ብቻ ትርፍ
በላሇው ጉዞ እግራችን እስኪቀጥን መዲከር የሇብንም›› ማሇቱ አይቀርም ፡፡ አቶ ቡሌቻ
‹‹ይሄ ክርስቶስን መጋፋት ነው እንኳን አምሊክን ተጋፍተን እንዯውም የተገፋን ነን ››
እያለ አባታዊ ምክራቸውን ይሰጣለ በየነ ጴጥሮስ ‹‹ ጥያቀው እንዳት ወዯዯሴቱ ሄዴን
ሳይሆን ዯሴቱ ሊይ ምን አሇ የሚሇው ይመስሇኛሌ ተረጋግተን ብናየው መሌካም ነው››
ሌዯቱ አያላው ‹‹ኢዳፓ የሚያምነው መራመዴ ጥሩ ቢሆንም ይሄ የሚራመደበት ውሃ
እርስወ እንዱራመደበት ተብል ጠጣር ሲሆን በውስጡ ይኖሩ የነበሩ በርካታ አሶች
ማሇቃቸው ተገቢ አይዯሇም ብል ነው...››
ምክትሌ ጠቅሊይ ሚንስትር ዯመቀ መኮነን ‹‹ታሊቁ ጠቅሊይ ሚንስትራችን በአፍሪካ
የመጀመሪያ በአሇም ሁሇተኛ የሆነውን የውሃ ሊይ ጉዞ በማዴረጋቸው መሊው የአማራ
ህዝብ የተሰማውን ኩራት እየገሇፀ ይህ ጉዟቸው እንዲይቋረጥ የአማራ ብሄራዊ ክሌሊዊ
መንግስት የጣና ሃይቅን ሇክቡር ጠ/ሚንስትር መሇስ በስጦታነት አበርቷሌ!!››
አርቲስት ሰራዊት ፍቅሬ ‹‹ ውሃን እንዯምንጣፍ ረግጦ ከሌማት ወዯሌማት አገርን ያሻገረ
...በግርማ ሞገሱ ባህር ያሸበረ ...በየብስ በባህር ያሰበበት የሚዯርስ መሇስ!!!›› እያሇ በኢቲቪ
ሞቅ ሲያዯርገው ታያቸው ይሄን ይሄን እያሰቡ ዯሴቱ መግቢያ ሊይ ሲዯርሱ የአረብ አገራት
ነገስታት ሲሞቱ የሚገቡበት ዯሴት መሆኑን በሩ ሊይ በተሇጠፈው ፅሁፍ አወቁ
.....ወዯውስጥ ሲገቡ ታሊሊቅ ቤተመንግስት የሚመሳስለ ቤቶች ዯሴቱን
ሞሌተውታሌ...ወዯአንደ ጠጋ ብሇው ሲመሇከቱ በሩ ሊይ ማን እንዯሚኖርበት የሚገሌፅ
ፅሁፍ ተሇጥፎበታሌ፡፡ አንዴ አምስት ቤቶችን እንዲሇፉ ያዩት ፅሁፍ አስቆማቸው ‹‹
ኮሮኔሌ መአመር ጋዲፊ የምዴራዊት ሉቢያ ንጉስ የነበሩ››
ይሊሌ ፡፡ መሇስ በሩ ሊይ ቁመው አሰቡ ‹‹ይሄ ነውጠኛ ሰውየ ስሇአብዮቱ ባማክረው ዯስታ
ነው የሚፈነዴቀው ...ስሇዚህ ...›› ብሇው ወዯውስጥ መግባት ጀመሩ!!
(ይቀጥሊሌ)