You are on page 1of 3

የድሮ የስምንተኛ ክፍል የአማርኛ መማሪያ መጽሐፍ ላይ ''ሽልንጌን'' የሚል ምንባብ ትዝ ይለኛል።አንድ የባቡር

መንገደኛ የአንዲትን ፍራፍሬ በመሸጥ የምትተዳደር ምስኪን ሽልንግ ይዞ በመሄዱ ''ሽልንጌን ሽልንጌን

ሽልንጌን………..'' እያለች ስትጮህ………….

ዛሬ ታዲያ ይህን የልጅነት ትምህርት ቤት ትዝታ ወደ ህሊናዬ ያመጣው ባለፈው ''አካፋን አካፋ እንላለን''

በሚል የፃፍኩበት የጉድ ገንፎ ስለሆነውና ራሱን የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር ዘብ እያለ የሚጠራው
ድርጅት ነው።በዚህ አጋጣሚ መረጃ በመስጠት የተባበሩኝን ወጣቶች ከወዲሁ ላመሰግን እወዳለሁ።

ማክሰኞ ኤፕሪል 16, 2013 ዓ.ም. ከነዚህ ወጣቶች ጋር የስልክ ቀጠሮ ነበረኝ። እንዲህ ሲሉ የተፈፀመውን

ነገር ጀመሩልኝ ''ኤፕሪል 13, 2013 ከመድረሱ በፊት ልዑል ቀስቅስ በተወካዩ ፀጋዬ ራስታ አማካኝነት

ቁጥራቸው ከ 25-30 ከሚጠጉ የመኖሪያ ፈቃድ ከሚጠባበቁ ስደተኞች ላይ ሃምሳ፥ሃምሳ ዩሮ አምጡና ነግደን

ስናተርፍ እንመልስላችኋለን በማለት ብር አሰባሰቡ። የተባለው ቀን ደረሰና በተጣለብን ግዳጅ መሠረት


ወደተባለው ሥፍራ ስንሄድ የተዘጋጀው አዳራሽ ባህር የሚያክል ሲሆን ታዳሚው ግን በባህሩ መካከል እንዳለች

ትንሽ አሣ መስሎ ሲታየን የ 50 ዩሮአችን ጉዳይ 'ውሃ የበላው ተዝካር' የሚባለው አይነት እንደሆነ

ተረዳን።በጣም አስገራሚው ነገር ደግሞ ምግቡን ከበላነው መካከል አንዳንዶቻችን መጠነኛ ህመም ሲያጋጥመን

አንዳንዶቹ ግን በሆስፒታል አልጋ እስከመያዝ ደርሰዋል።'' ሲሉ የተፈፀመውን ታሪክ በአጭሩ አስቀመጡልኝ።

1
በማግስቱ ወደ ዋሽንግተን በረራ የነበረኝ ቢሆንም ህሊናዬ ሊያርፍልኝ ባለመቻሉ በቂ የሚባል እንቅልፍ እንኳን
በቅጡ መተኛት ተሳነኝ። በዚህም ጀርመናዊው ባለቤቴ ምን እንዳጋጠመኝ ሁለት ጊዜ ጠየቀኝ በእርግጥ ይህ
ምን ተብሎ ይነገራል በሚል ምንም እንዳልተፈጠረ ለማስመሰል ብዙ ጣርኩ።

ረቡዕ ኤፕሪል 17, 2013 ዓ.ም. ከፍራንክፈርት ኤርፖርት ወደ ዋሽንግተኑ የዳለስ ኤርፖርት ባደረኩት ጉዞ

ይህንኑ ጉዳይ እያሰብኩ ነበር። ወጣቶቻችን መሰደድ ሳያንሳቸው ለምን በገዛ ''ወገናቸው'' ይህ ግፍ

ይፈፀምባቸዋል?ወጣቶቻችንን መርዳት ሲገባ ለምን በደካማ ጎናቸው መጠቀም አስፈለገ? እንዲያው መርዳት

ባይቻል እንኳን አለመጉዳት አይቻልም ነበር ወይ?ህግ ባለበት፥ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት በሰፈነበት ሀገር ሌላ

አካል ያላደረሰባቸውን ''የኛ ወገን'' የሚሉት ግለሰቦች እንዴት እንዲህ አይነት ተግባር ይፈፅማሉ?ይህ ነገርስ

እስከመቼ ይቀጥላል?እኛስ የግል ኑሯችን ስለተመቻቸ ብቻ ሌሎች ወገኖቻችን የግፈኞች ሰለባ ሲሆኑ እስከመቼ

ሰምተን ዝም እንላለን?ምን ቢደረግ ነው የስደተኛ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን የፍርድ ቤት 'ኬዝ' ሳይበላሽ

ይህንን ግለሰብ መነጠልና እርቃኑን ማስቀረት ብሎም ለፍርድ ማቅረብ የሚቻለው?(በዚህ አጋጣሚ በጎግል ድረ

ገጽ ላይ ''Stop Abusing Ethiopian Refugees Sex Assault, Racketeering in Germany

by Mr. Leul Keskis's Group'' ብላችሁ ብትገቡ ከዚህ በፊት በኢንተርኔት በነ ልዑል ቀስቅስ ላይ
የተደረገውን የድምፅ ማሰባሰቢያ ፎርም ታገኛላችሁ።)

በግሌ በቅድሚያ እንዲህ መደረግ እንዳለበት ይታየኛል።የመጀመሪያው ጉዳይ እነዚህ ስደተኞች በየትኛውም
መስፈርት የፍርድ ቤት ጉዳያቸው መበላሸት የለበትም፤በመሆኑም የምንወስደው ማንኛውም እርምጃ የነሱን

ወቅታዊ ጉዳይ ከግምት ያስገባ ሊሆን ይገባል። (ለምሳሌ ባለቤቴ የህግ ባለሙያ ነው ነገር ግን ይህን ጉዳይ

ማለትም ''ልጆቹን ገንዘብ አለአግባብ አምጡ መባላቸው ሳያንስ የተበከለ ምግብ እንዲመገቡ በማድረግና
መንግስትን ለልጆቹ ህክምና ያለአግባብ እንዲያወጣ በማድረግ እንዲሁም ካገኘው ገቢ ላይ ለመንግስት ታክስ ገቢ
ባለማድረግ ወንጀል'' እንዳለ ወደፍርድ ቤት እንውሰደው ቢባል ነገሮች እስኪጣሩ በሚል የብዙ ስደተኛ
ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ጉዳይ በእንጥልጥል ይቆያል ነገር ግን ይህ እንዲሆን ማናችንም መፍቀድ
የለብንም።ይህ ማለት ግን የሰው እና የሰነድ ማስረጃዎችን፣የሀኪም ቤት ማስረጃዎችን በማሰባሰብ ስራ አንሰራም

ማለት አይደለም)።በመሆኑም ያናገርኳቸው ወጣቶች እንደነገሩኝ ከሆነ ጀርመን ውስጥ ያሉት ድርጅቶች ኦነግን

ጨምሮ ማለት ነው ከዋናው ፓርቲ ስር ''የድጋፍ ሰጪ ኮሚቴ'' የሚባል ነገር ያላቸው በመሆኑና የዚህም የድጋፍ
ሰጪ ኮሚቴ ዋና አጀንዳ ስደተኛ ዜጎቻችን የፖለቲካ ተሳትፎ እንዲያደርጉ በዚያውም የፍርድ ቤት
ጉዳይቸውንም እንዲያግዝ ታስቦ የተዘጋጀ በመሆኑ ንቅዘት የማይታይባቸው ድርጅቶች ካሉ በዛ ውስጥ
የሚሳተፉበት ዕድል ቢመቻች አልያም የተሻለ ሃሳብ ያላቸው ሰዎች በጉዳዩ ላይ ቢያስቡበት እና ለመፍትሔ
የቻሉትን ያህል አስተዋጽዖ ሊያደርጉ ይገባል ባይ ነኝ።በዚህ አጋጣሚ ይህንን ጉዳይ ጫፍ ለማድረስ የገንዘብም
ይሁን የሃሳብ ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ ነኝ።ሁለት ነገሮች መፈፀም ይኖርባቸዋል የሚል እምነት አለኝ፦

1 ኛ. ስደተኛ ወገኖቻችን ወረቀት ለማግኘት ሲሉ አላስፈላጊ እንግልት፣የገንዘብና የፆታ ብዝበዛ


እንዳይደረግባቸው መከላከል።ለዚህም ሲባል በዚህ ተግባር ላይ የተጠመዱትን መቶ አለቃ ልዑል ቀስቅስን

2
የመሳሰሉትን ጭንጋፍ ፖለቲከኞችን ማጋለጥ እና ብቻቸውን ማስቀረት እንዲሁም ለፍርድ የሚቀርቡበትን

መረጃዎችና ማስረጃዎች ማሰባሰብ፤በሌላ በኩል የነዚህ ጭንጋፍ ፖለቲከኞች መደበቂያ የሆኑ ፍሬ-አልባ

ድርጅቶችን ለማፍረስ የገቢ ምንጫቸውን ማድረቅ፣እንዲሁም እስኪፈርሱ ድረስ መታገል ብሎም የሚያደርጉትን
የሀሰት ፕሮፓጋንዳ ይፋ ማውጣት እና ማጋለጥ።

2 ኛ. እውነተኛ የፖለቲካ አጀንዳ የሌላቸውን እና በስደተኞች እግር ስር እንደ ቀትር እባብ እየተሽሎከሎኩ
ኢትዮጵያ የመኖሪያ ፈቃድ ያላገኙ ስደተኞች ብቻ ሀገር የሆነች ያህል የፖለቲካቸው ማጠንጠኛ በስደተኛ ካምፕ

/'ሃይም'/ በሚኖሩ ዜጎች ላይ ያደረጉትን ፍሬ-አልባ ድርጅቶች ማጋለጥ እንዲሁም እንዲፈርሱ ብርቱ ጥረት
ማድረግ፤ ጎን ለጎን ደግሞ ሀገራዊ ራዕይ ያላቸውና በጀርመን የምንገኝ ኢትዮጵያውያንን /ባለኝ መረጃ መሠረት

ኢትዮጵያውያንና በትውልድ ኢትዮጵያዊ የሆኑ ዜጎች ቁጥር 33,976 ይደርሳል/ ጭምር ተደራሽ ያደረገ

እንቅስቃሴ የሚያደርጉትን የፖለቲካ ድርጅቶች እና የሲቪክ ማህበራትን መርዳት፤ በሚያደርጉት እንቅስቃሴ ላይ


እነዚህን ከሰላሣ ሺህ በላይ የሆኑ ዜጎችን ለማካተት የሚጥሩትን ድርጅቶች ማገዝ ይገባል ባይ ነኝ።

ሠላማዊት አሰፋ

ኖርዝ ካሮላይና (ኤፕሪል 19, 2013)

You might also like