Professional Documents
Culture Documents
ትላንት ወድያና ትላንት ቆቦ ውስጥ የተከሰተው ከሰውነት የራቀ እጅግ አሰቃቂ፣ ነውረኛና አብሮ የመኖር ተስፋን የሚያጨልም
የዕብደት ተግባር ሁለት ንፁሐን የትግራይ ተወላጆች በትግራዋይነታቸው ተገድለዋል፣ በደርዘኖች የሚቆጠሩ የተጋሩ መኖርያ
ቤቶች፣ የንግድ ሱቆች ተዘርፈዋል፣ ተቃጥለዋል።
ቪ ኦ ኤ ላይ ቀርበው ወልዲያ ላይ ስለተፈፀመው ተጋሩ ተጋሩ በመሆናቸው ብቻ መኖርያ ቤቶቻቸው፣ የንግድ ሱቆቻቸው
በእሳት እንዲጋዩ፣ እንዲዘረፉ ስለሆኑበት ሁኔታ የተጠየቁ የወልዲያ ኗሪ የትግራይ ተወላጆች እንደሚገልፁት ወልዲያ ጠበብ
ያለች ከተማ እንደመሆኗ አብዛኛው ሕዝብ የጠበቀ ማሕበራዊ ግንኙነት ያለው መሆኑንና እርስበርሱ በቅርበት እንደሚተዋወቅ
ይገልፁና ወልዲያ ላይ የተከሰተው ችግር ድንገት የተከሰተ ሳይሆን ብዙ ዝግጅት የተደረገበት መሆኑን፤ ብጥብጡን ሲመሩት
ሲያስተባብሩ የነበሩ የተመረጡ የተጋሩ ንብረቶች እንዲቃጠሉ ሲያስተባብሩ የነበሩ ሰዎች በብዛት የወልዲያ ኗሪዎች
አልነበሩም።
በብአዴን ካምፕ ውስጥ እጅግ ቤተኛ የሆነው ኢሳት ሰሞኑን በብአዴን ውስጥ ሁለት አንጃዎች እንደተፈጠሩና አንደኛው
በጎንደሮች የሚመራና ሸዋዎችን የሚያቅፍ መሆኑን፤ ሁለተኛው የወሎዎች መሆኑን ገልፆ ነበር(ጎጃሞች ከየትኛው አንጃ ጋር
እንደወገኑ አልታወቀም)።
በዚያ ላይ ሰሞኑን ጎንደር አካባቢ በአማራ ፖሊስ የተያዘ በርካታ የጦር መሳርያ አለ፤ መቸም የአማራ ክልል ፖሊስ የጦር
መሳርያዎችን ከቁጥጥር ማስገባት የተለመደ ዜና አይደለም።ወልዲያ ላይ ለምን? ለምን አሁን?
ጎንደርና በአንዳንድ የጎጃም አካባቢዎች ተከስቶ የነበረው ፖለቲካዊ ቀውስ አንፃራዊ መረጋጋት ባሳየበት በዚህ ወቅት ለምን
ወልዲያ ላይ አዲስ እሳት መለኮስ አስፈለገ?"የወልዲያው እሳት የለኮሰው ማን ነው"? የለሚው ጥያቄ ለመመለስ ሶስቱ ከዚሁ
እሳት የየራሳቸው "ትርፍ ለማጋበስ" የሚፈልጉ አካላት እየያቸው፦1: "ተጋድሎ" ና ቅቡልነት (Martyrdom and
legitimacy) : ባለፉ ሁለት ሶስት ዓመታት በነበረው አስጨንቆና እጅ ጠምዝዞ የበላይነት ለማግኘት በተደረገው ተጋድሎኖ
በተከፈለው "መስዋእትነት" የወሎ ተሳትፎ ምንም ነበር የሚል ስሜት አለ። በተለይም የጎንደር ልሒቃን "የበለጠ መስዋእት
የከፈልነዉ እኛ ሆነን እያለ እንደምን ወሎዎች በብአዴን ስልጣን ጠቅለው ያዙ" የሚል ስሜት አለ። ወልዲያ ውስጥ ግርግር
በማስነሳት የተጋሩ ንብረት እንዲወድም፣ አካል እንዲጎድል ማድረግ "እኛም በተጋድሎው አለንበት" የሚል መልዕክት
ያስተላልፋል፤ በዎሎው ቡድን ላይ የሚነሳው የ Legitimacy በከፊል እንዲመልስ እምነት ተጥሎበታል።
አሁን እንደምናየው በነዚሁ "የአማራ ህዝብ ወኪሎች ነን" የሚሉ ልሂቃን ዘንድ "ተጋድሎ" ማለት አንድን ተራ ሚስኪን
ትግራዋይን መግደል ነው፤ "ትክክለኛ (legitimate) ወኪል" ለመሆንም የግድ አንድን ከምኑም የሌለበት ረዳት-አልባ
ትግራዋይ መግደል ወይም ለዐመታት ለፍቶ ያፈራውን ሀብት ንብረቱን መዝረፍ ወይም በእሳት ማንደድ ያልተፃፈ "መስፈርት"
መሆኑ እውነት ነዉ።2: የወሎው ቡድን የችግሮች አያያዝና አፈታት ደካማነት ማሳየት፤ ቡድኑን ከማሕበራዊ መሠረቱ ጋር
ማለያየት፤ የወልዲያ የብጥብጥ ችቦ የተለኮሰው የወልዲያ-መቀለ እግር ኳስ ቡድኖች ጨዋታ አስታኮ እንደሆነ የሚታወስ
ነው። በጊዜው ይህንን ብጥብጥ ለማስነሳት በጎንደር በር በኩል በርካታ ደርዘን መኪኖች የተለያዩ ባነሮችና ሌሎች ነገሮች የያዙ
ወጣቶች እንደገቡና የብጥብጡና የውድመቱ ዋነኛ ተዋናዮች እንደነበሩ የሚታወስ ነው። ወልዲያ ላይ ብጥብጥ በማስነሳት
ፖሊስ እርምጃ እንዲወስድ ቢሆን የወሎው ቡድን እንደሚከስርበት ግምት ተይዞ ነበር። የወሎው ቡድን በበኩሉ ይህንን ነገር
"ባላየ" ለማለፍ የመረጠበት ምክንያት ትርፉን በማስላት ነው።
3: ሶስተኛ ቡድን ደግሞ አለ- በትግራይ ሕዝብ ጥቅምና ሕልውና ፈፅሞ የማይተኛ፤ የፖለቲካ ርዕዮተ-ዐለሙ፣ ታሪኩና
የቀደመም የአሁንም መሰባሰብያው "ፀረ-ትግራዋይነት" የሆነ፤ የጠቅላይ አግላይነትና ተስፋፊነት ባህሪያት የነገሱበት ቡድን።
ይህ በዋነኝነት ውጪ በሚኖሩ ሐይሎች የሚዘወር ሲሆን ይህ ቡድን በምዕራብ ትግራይ በኩል ሞክሮ የከሸፈበት ሙከራ
በደቡብ ትግራይ በኩል ለመሞከር ነው፤ ለዚሁ ቡድን ወልዲያ መሸጋገርያ መሆኗ ነው።
የሚያሳዝነው ግን የሶስቱ ቡድኖች የትግል ስልት ሚስኪን ትግራዋይን መግደል፤ የንሐፁን ተጋሩ ንብረት መዝረፍና በእሳት
ማንደድ መሆኑ ነው።
ከላይ ያልኩትን ልድገመው፦ "የአማራ ህዝብ ወኪሎች ነን" በሚሉ ልሂቃን ዘንድ "ተጋድሎ" ማለት አንድን ተራ ሚስኪን
ትግራዋይን መግደል ነው፤ "የአማራ ህዝብ ትክክለኛ (legitimate)ና ተቆርቋሪ ወኪል" ለመሆንም የግድ አንድን ከምኑም
የሌለበት ረዳት-አልባ ትግራዋይ መግደል ወይም ለዐመታት ለፍቶ ያፈራውን ሀብት ንብረቱን መዝረፍ ወይም በእሳት ማንደድ
ያልተፃፈ "መስፈርት" መሆኑ እውነት ነዉ።
Jan 30 · Sent from Messenger
Kidane Berhe
ደም ! ሂወት!ንብረትን ትግራዋይ በቃ ሓታቲ ዘይብሉ ደም ከልቢ ኮይኑ ክተርፍ! ሎምስ እንታይ ኢን ከ እንገብሮ!
እንተተአሰሩ ይፈትሑ ይባሃሉ ንሕና ሞይትና እንቀሪ እኮ ኮይና! ብስሩ እኮ አብኩሉ ቦታ ምኳኑ እዩ እቲ ጊዳይ ክፉእ ዝገብሮ!
Jan 30
https://amharic.voanews.com/a/4263018.html