You are on page 1of 7

ግምጥ

ግጥም በሀገራችን እጅግ ጥንታዊ የሆነ የስነ ጽሁፍ ዘር ነው፡፡ በአፃፃፍ ከድንባብ ወይም ከዝረው የሚለ፤የው የራሱ የሆነ
ቤት መመቻና መድፊያ ቃል ያለው እንዲሁም በቃሳት አጠቃቀሙ ረገድ የተመረጡ እምቅነትን፣ ክረትና፣ ቁጥብነት፣
ያሳቸውን ቃላት የሚመረጥና የሚጠቀም የብርቱ ስሜት መግለጫ ነው፡፡ ግጥም ምን ያክል ስሜትን ቆንጥሮ የሚይዝና
ሀሳብን አግዝፎ ለመየለየት አቅም አለው፡፡፡

በአጠቃላይ ግጥም ማለት ስተመረጡ ቃላት ቤት እየደፉ ቤት እየጸሀፍ ውበት ባለው ባው መልሱ የሚቀርብ የስነ ጽሁፍ
ዘርፍ ነው፡፡

የግጥም ባህሪያት
ግጥም በአየጠቃላይ የሚከተሉት ባህሪያት አሉት እነሱም

1. ተጨባጭነት
2. እምቅነት
3. ቁጥብነት ሙዚቃዊነት
4. ምናባዊነት
5. ተውኔታዊነት

ተጨባጭነት
ግጥም ዝም ብሎ ያለምንም ምክንያት የሚነጠም ሳይሆን እንደ ተጨባጭ ከሆነ ሀቅ ላይ የሚነሳና እውነትነት ያለው
ሀብት ነው፡፡ አንድ ነገር ወይም ተፈጥሮን ለመግለፅ ከእሱ ጋር የሚመሳሰሉ ወይም የሚቃረኑ የተለያዩ ጉዳዮችን
በማምጣት በሚነፃፃር በማመሳሰል ወይም በማወዳደር በአይን ህሊናችን እንዲሳልና ሀቁን እነድናውቀው የሚያደርገን
ነው፡፡ ተቂቅ የሆኑ ነገሮችን እንድናውቃቸውና እንድናያቸው በማድረግ የበለጠ ተጨባጭነት እንዲሆኑ ያደርጋቸቃል፡፡

ቁጥብነት/ እምቅነት

ስን ግጥም የቁጥብነት ባህሪ ሊኖረው ይገባል ስንል በሌላ አነጋገር ቃላት እምቅነት ይኑራቸው ማለታችን ነው፡፡ በየ ሀረጉ
የተለያዩ ቃላትን ስናሰገባ ሲታይ ትንሽ ሊተነተኑ ግን በጣም ብዙ አላማ እና ሀሳብ የሆኑ መሆን አለባቸው፡፡

ለዚህም ጥሩ ምሳሌ የሚሆነው ብርሀኑ ገበየው እንዳስቀመጠው ግጥም ልክ እንደ ፈንዲካ ነው፡፡
ሙዚቃዊነት

ግጥም ሲነበብ የራሱ የሆኑ የገዙ ዜማ አለው፡፡ ጮህ ብለን ስናነበውም እየተነበበልን ስናደምጠው የሚሰማን ዜማ ኮርኳሪ
ቃላት ጋር ተደማምሮ አንድ ብርቱ ስሜታችንን ይቀስቅሳል ግጥም ከሌሎች የስነ ትኁፍ ዘርፎች የስነጽሁፍ ዘርፎች
የሚለው በሙዚቃነቱ አንዱ መለያው ነው፡፡ በስነቃሎቻችም ሆነ በዘፈኖችን የምናገቻቸው ጨዋታዎች በአብዛኛው
በግጥም ቃላት የተገነቡ ናቸው፡፡

ግጥም የራሱ የሆነ ዜማና ምት በየቃላቱ በየሀገራቱ በየስንኙ አሉት፡፡ ቃላት ሊደረደሩና ስንኞች ሊገጣጠሙ የዜማውና
ከምቱ ጋር የበለጠ ቁርኝት እንዲኖራቸው፡፡ ይደረጋል ስለዚህም ነው ግጥም ከደጢይነት ይልቅ ጮህ ተብሎ ሲነበብ
ሲደመጥ ጆሮን የመያዝ አቅሙ ከፍተኛ ነው፡፡

ምናባዊነት

በስነ ግጥም የሚነገረው ሀሳብ ምናባዊነት የጎላ ነው፡፡ ይህ ምናባዊ ሀሳብ በአንባቢ ላይ በመከለት በአጋጣሚውና
በተደራሹ መካከል ተግባቦት እንዲፈጠር ያደርጋል፡፡

የአማርኛ የምጣኔ አይነቶች


ምጣኔ ማለት ስንኞች ውስጥ የምናገኛቸው ቀለሞች ቁጥር ማለት ነው፡፡
አንዳንዱ ግጥም ከ 3-5 ቀለሞ ሊኖረው ሌላው ደግሞ እስከ 18 እና ከዛ በላይ ሊኖረው ይችላል
ቀለም የተገባቢ ድምጾች ቅንጅት ነው፡፡

የግጥም ሙያዊ ቃላት


1. ስንኝ ማለት የግጥም አንድ መስመር ማት ነው፡፡
ለምሳሌ መቅደላ አፋፍ ላይ ጩኸት በረከተ 1 ኛ ስንኝ
የሌቱን እናውቅም ወንድ አንድ ሰው ሞተ 2 ኛ ስንኝ
2. ሀረግ ማለት የግጥም እኩሌታ /ግማሽ ማለት ነው፡፡
አስረጅ ከላይ በተመለከተው ምሳሌ ሰረት
መቅሳ አፋፍ ለላይ ጩኸት በረከተ
3. ሆሄ በግጥም ውስጥ ተፅፎ የሚገኝ ማንኛውም ፊደል ሆሄ ይባላል
4. መነሻ ሀረግ በአንድ ስንኝ ውስጥ የመጀመሪያው ሀረግ መነሻ ሀረግ
5. መድረሻ ሀረግ በአንድ ስንኝ ውስጥ መጨረሻ የሚገኝ ሀረግ
6. መቅደላ አፋፍ ላይ ጩኸት በረከተ
7. ቤት በግጥም ውስጥ በመጨረሻ ቃላት ላይ የሚገኝ የግጥሙ ማሳረጊያ ፊደላት ቤት ቃላት
8. ቤት መምቻ፡- የግጥሙ አንድ መስመር በተሳካ ሁኔታ ሲያልቅ ቤት መምቻ ይባላል፡፡
9. ቤት መድፊያ፡- የግጥም ቀጣይ መስመር (ስንኝ) በተሳካ ሁኔታ ሊያልቅ
ምሳሌ ሚኒልክ ተለወልዶ ባያነሳ ጋሻ
ግብሩ እንቁላል ነበር ይሄን ጊዜ ሀበሻ
ቤት መምቻ ቃል ጋሻ
ቤት መድፊያ ቃል ሀበሻ

ቤት መድፊያ እና መምቻ ሆህያት ሁለቱም ስንኝ የተመሳሰለ ካልሆ ግጥሙ አልተለናንም ማለት ነው፡፡

ቀለም በግጥም ውስጥ ተረግጠው (ጠብቀው) የሚበቡ ሆሂያት ቀለም ይባልሉ፡፡


ምሳሌ

አንጓወይም አርኬነ፡- የግጥም አንድ አንቀፅ አንጓ/አርኬ/ ይባላል ይህም ማለት በአንድ ግጥም ውስጥ በአንድ ጉዳይ ላይ ብቻ
ትኩነት አድርጎ የሚወራ እና የስንኞች ስብስብ ነው፡፡

ምት እና ምጣኔ
ምት ለስነ ግጥም አይቀሬ ዋነኛ ባህሪ መሆኑን

ክሌንዝ ብሩክስ እና የበር ቴን ዋረን በቀዳሚነት የጠቀሱት ተፈጥሮአዊና በእለት እለት እንቅስቃሴአችን ይብጡኑ ደግሞ
በውስጣችን የሚገኝ በመሆኑ ነው፡፡ ምት በእርግጥ የሕይወት መሰረታዊ ባህሪ ነው፡፡ በራሳችን ሰውነት ውስጥ
በተደጋጋሚነት የሚኖርና በውልም የምናውቃው ሲሆን በልብ አመረታታችን በአተነፋፈአችንና በአረማመዳችን ላይ
ይታያል ስለነባራዊ አለም ያለን ግንዛቤ ከወቅቶች ከቀንና ሌሊት እንዲሁም ከብርሀንና ከጨለማ መፈራረቅ ጋር የተያያዘ
መሆኑ ቡዙ ጊዜ ይጠቀሳል ምት ከብዙ አይነት መሰረታዊ ሂደቶች ጋር ከመቆራኘቱ በተጨማሪ ከራራ ስሜቶችን
መቅለጫ ሲሆን ይታያል፡፡

የአንድ ግጥም የተስተካከለ ነው፡፡ ሲባል አንዱን ሀረግ ለማለት ወይም ለማንበብ የሚፈጀው ጊዜ ተከትሎት
የሚመጣውን ለማለት ወይም ለማንበብ ከሚወሰደው ጊዜ ጋር እኩል ነው፡፡ ማለት ነው፡፡ ይህ እኩልነት ወጥም የጠበቀ
ተመጣጣኝነነት ከጉልህ ለእዝነ ህሊና መስማት ይኖርበታል፡፡ አንዱ ሀረግ ተብሎ ከትንሽ እረፍት ወይም ቆይታ በኋላ
ተከታዩ ሲቀጥል የሚፈጠረው የአንባብ ተከታይ ምት የሐበቀ ከሆነ ዜማውም ሙዚቃዊ ቃና ጠብቆ ይጎዛል፡፡ ይህ ደግሞ
በመፈንታው የግጥሙን ስሜት ነኪነትና ኪናዊ ከመችነት ያስገኛል፡፡ ግጥሙ አጭርም ይሁን ረጅም ይህንን መንገድ
ተከትሎ መሄድ ይኖርበታል ከዚህ ውጪ ማለትም ከምማኔው ከጠበቀ ምቱና ከሙዚቃዊ ቃናው ከአነገጠ የስነግጥመነቱ
ዋነኛ ባህሪ ቀሪ ማለት ነው፡፡
አንበሳ ነው ጀግና ቀጣው አስበርጋጊ
የነፃነት አርማ የድል ፋና ወጊ ይህ ግጥም ሁለት ስንኞችና አራት ሀረጎች አሉት እያንዳንዱ ስንኝ ሁለት ሁለት ሀረጎች
ይዟል፡፡
በዚህ ግጥም ያሉትን ሀረጎች ለማንበብ ዪፈጅበት የጊዜ መጠን እኩል ነው፡፡ የዚህ ግጥም ቀለማት
አንበሳ ነው ጀግና ቀጣው አስበርጋጊ

የነፃነት አርማ የድል ፋና ወጊ

ይህ ግጥም በሀረግ 6 ቀለሞች እና በስንኝ 12 ቀለሞች አሉት

የግጥም አይነቶች
የግጥም አይነቶች ለቀለሞች ብዛታቸው አማካኝነት በ 3 ይከፈላል

እነሱም 1. የወል ቤት ግጥም

2. የሰንጎ መገን ግጥም

3. የቡሄ በሉግጥም

የወል ቤት ግጥም

በሀረግ 6 በስንኝ 12 ቀለሞች አሉት

የሰንጎ መገን ግጥም

ይህ ግጥም በአብዛኛው ለፍከራ ለሸልላ እና ለክራር ጨዋታ የሚያገለግል ሲሆን ሀረግ 5 በስንኝ 10 ቀለሞችን ይይዛል፡፡

ቡሄ በሉ

አብዛኛው ጊዜ ለልጆችና ለበአል ጨዋታ የሚያገለግል ሲሆን በሀረግ 4 ስንኝ 8 ቀለሞችን የያዘ ነው፡፡

ግጥም እንዴት ይነበባል


አንድን የስነ ግጥም ስራ ለመረዳት ወይም በውል ለመገንዘብ ትንተናዊ ንባብ አስፈላጊ ነው፡፡ እና ኤድመንድ አልሾልኝ
እዳሉን አንድ ግጥም የተዋጣለት የስነ ጥበብ ስራ ሲሆን ለአንባቢው በአንዳንድ ገጽታዎች ለየት ገጠመኝ ስለ ሚሆን
አንባቢው ግጥሙን ሙሉ በሙሉ ለመረዳት በጥልቀት ተንትኖ ማመን አለበት፡፡ አንድን ግጥም ላይ ላይን ብቻ በማየት
ሙለውን መረዳት አዳጋች ነው፡፡ በአጠቃላይ ቅንብሩ ጠልቆ መማር መርና መስተዋል ከስራ ጠመኝ ጋር በመዛመድ
ውስጠምስጢሩን ፈልፍሎማጤን ያሻል፡፡ የገጣሚውን ሀሳብ በውል ለመገንዘብ ያስፈልጋል፡፡
አንድን ግጥም አንብቦ ለመረዳት ከሁሉ አስቀድሞ የቃሳት ምርጫን መመልከት ያሳል፡፡ የቃላት ደረጃና አውዳዊ አገባብ
የቃላቱን አይነት የቃሳቱን አደረረዳር ስልትነና የሀረረጋቱንና የአ.ነገሮቹን አቅነባበር ማጤን ይገባል፡፡

ስነ ግጥም አስካሁን እንዳተገለፀው የራሱ ቅርጽና ይዘት ያለው ቋንቋን ለየት ባለመልክ የሚጠቀምና ሌሎች ውስጣዊ
ባህሪያትን የተባለ የስነ ጽህብ ዙር ነው፡፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ ስነ ግጥም ሙሉ ደስታ ብሩህ ድባብ ያላቸው አስዊኝ ገጽታዎች ወይም ኮስታራና መራራ ነገሮችን
ሊያቀርብ ይችላል፡፡ ለምሳሌ ተከታዩ ግጥም በሰዎች ዘን ሲፈጠር እንደሚችሉትን ስሜትን እንበል፡፡

ሁለት በራ ሰዎች ሲያልፍ በጎዳና

እቃ መሬት ወድቆ ብልጭ ሲል አዩና

ተሸቀዳድመው ሄደው ከቦታው ሲደርሱ

ተፎካካሩበት ሁለቱም ሊያነሱ

በኋካም ተማተው በጥሩ በጡጫ

አንደኛው ነጠቀንልበቱ ብልጫ

አገላበጠና በመለከት ፈጠውሮ

በቃውን አገኘው መጠፊዎ ሆኖ

እስቲ ሁላችሁም ሁላችሁም በሱ ፍረዱት

እሱ እራሱ በራ ጠጉር የለበት

ሮጠ ተማቶ ቀምቶ ቢያመን

ምን ያደረውግለታል ሚዶለመላጣ
ጥያቄ

አጭር መልስ መልሱ

1. ምት ስነ ግጥም አይቀሬ ዋነኛ ባህሪ በመሆኑን --------------------------እና -------------------- በቀዳሚነት


የሚጠቀሱት ሰዎች ናቸው፡፡
2. የግጥም አይነቶች ጥቅሱ
3. የግጥም ባህሪያት ዘርዝር
4. ግጥም ምን ማለት ነው፡፡
5. የግጥም ሙያዊ ቃላትን ዘርዝር፡፡

የመረጃ ምንጭ

ከሰዋሰው እና ስነፅሁፍ መጽሀፍ

ከስነ ጽሁፍ መጽሀፍ

ማውጫ
ርዕስ ገጽ

ግምጥ.............................................................................................................................................................
የግጥም ባህሪያት...............................................................................................................................................
የአማርኛ የምጣኔ አይነቶች................................................................................................................................
የግጥም ሙያዊ ቃላት........................................................................................................................................
ምት እና ምጣኔ.................................................................................................................................................
የግጥም አይነቶች..............................................................................................................................................
ግጥም እንዴት ይነበባል......................................................................................................................................

You might also like