You are on page 1of 4

መዝ.ቁ.

165245

ቀን፡ 27/02/2013

ለፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የካ ምድብ ሦስተኛ የቤተሰብ ችሎት

አዲስ አበባ

አመልካች ……………… ወ/ሮ እመቤት አብርሃም

ተጠሪ ………………. አቶ ታረቀኝ መኩሪያ

ጥቅምት 4 ቀን 2013 ዓ.ም አመልካች ላቀረበችው ክስ የተጠሪ መልስ

1. አመልካች ባቀረበችው ክስ ከ 2000 ዓ.ም ጀምሮ እንደባልና ሚስት አብረን እየኖርን ልጆችና ንብረት አፍርተን ሳለ
ባለመግባባታችን ከቤት ወጥቻለሁ በማለት ዳኝነት ጠይቃለች፡፡
2. የተጠሪ መልስ፡-
2.1. አብረን መኖር የጀመርነው ከየካቲት ወር 2001 ዓ.ም ጀምሮ እንጂ በ 2000 ዓ.ም አይደለም፡፡ ይኸውም ቤተሰቦቿ ቤት
እያለች የመጀመሪያ ልጃችንን አርግዛ የመውለጃ ጊዜዋ በመቃረቡ ቤት ተከራይቼ አብረን መኖር ጀመርን፡፡ የመጀመሪያ
ልጃችን ቢታንያ ታረቀኝ የተወለደችው መጋቢት 23 ቀን 2001 ዓ.ም ለመሆኑ የየካ ክ/ከተማ ጤና ጣቢያ ከልደት ካርዷ
ላይ በፍ/ቤቱ ትዕዛዝ ማረጋገጥ ይችላል፡፡
2.2. አመልካች ባለመግባባታችን ግንኙነታችንን አቋርጫለሁ ባለችው በእኔ በኩል ግንኙነታችንን ከጋብቻ ለይቼ ሳላይ በሙሉ
እምነት ንብረት በስሟ ገዝቻለሁ፡፡ ለምሳሌ፡ የመኖሪያ ቤታችንን በስሟ ገዝቻለሁ፤ በእርሷ የባንክ ሒሳብ ተቀማጭ
ገንዘብ ሳጠራቅም ኖሬያለሁ፡፡ እርሷ ግን በግል ንብረት በማፍራት ዓላማ ላይ ብቻ ስላተኮረች በግራ ቀኛችን ዘመዶች እና
ጎረቤቶቻችን ከአንድ ዓመት በላይ ሳስመክር፣ ሳስወቅስ ኖሬያለሁ፣ ቢሆንም አሁን የልጆቻችንን ሕይወት በሚጎዳ አኳኋን
ኑሮአችንን በመበተኗ ባዝንም በጥያቄዋ ከመስማማት በቀር ሌላ አማራጭ የለኝም፡፡
2.3. አመልካች አራቱም ልጆቻችን ከእርሷ ጋር እንዲያድጉና የሞግዚትነት እና የአሳዳጊነት ሥልጣን በፍ /ቤት
እንዲሠጣት የጠየቀችሁ የህግ አግባብነት የለውም፡፡ እኔም ልጆቼን የማሳደግ እና የመንከባከብ መብት አለኝ፡፡
ሁለቱ ነፍስ ያወቁ ልጆች ከእኔ ጋር፤ ሁለቱ ትንንሾች ከእርሷ ጋር ሆነው በየጊዜው እንዳገኛቸው፤ የትምህርት እና
የአካላቸውን እንዲሁም የሞራላቸውን ሁኔታ እንድከታተል እንዲወሰንልኝ አመልክታለሁ፡፡
2.4. አመልካች በክፋ ልቦና ተነሳስታ የግል ንብረቴን እና የባንክ ሒሳቤን ስታስከብር፤ በስሟ ያፈራነውን የጋራ
ንብረቶች ግን በንብረት ዝርዝር ሳታካትት ደብቃለች፡፡ ይኸውም 1 ኛ. በየካ ክ/ከተማ ወረዳ 11 የቤት ቁ. አዲስ
ስፋቱ በግምት 200 ካ/ሜ ወሰኑ በምሥራቅ - ሐና ወ/ኪዳን፤ በምዕራብ - መንገድ፤ በደቡብ - ታዴዎስ ወ/ኪዳን፤
በሰሜን - አቶ ገላልቻ የሆነና ሦስት ክፍል መኖሪያ ቤታችንን ከነማዕድ ቤቱ 2 ኛ. ተቀማጭ ገንዘባችንን
የምናጠራቅምባቸውን የሒሳብ ቁ. 013200403553 አዋሽ ባንክ እና የሒሳብ ቁ. 310501065043 የኢትዮጵያ
ንግድ ባንክ በስሟ የሚንቀሳቀሰውን ሆነ ብላ ደብቃለች፡፡
2.5. በስሟ የተገዛውን መኖሪያ ቤታችንን በተመለከተ ያየር ካርታ መሸጥ ስለማይፈቀድ የሽያጭ ውሉ ሕጋዊነት
እንዳያጣብን በማለት መሬቱን ፈርሶ ከነበረው ማዕድ ቤት ጋር በ 1992 ዓ.ም እንደተገዛ ተደርጎ ይፃፍ እንጂ
በትክክል ግዢ ፈፅመን ገንዘብ የተከፈለው እና ርክክብ የተደረገው በ 2007 ዓ.ም ህዳር ወር ነው፡፡
2.6. አመልካች ከእርሷ ጋር መኖር ከመጀመራችን በፊት ዕጣ ወጥቶልኝ የቅድሚያ ክፍያዎችንም አጠናቅቄ
ያገኘሁትን የግል የኮንዶሚኒየም ቤቴን በጋራ ንብረት ዝርዝር ውስጥ ማካተቷም የማይገባትን ጥቅም ለማግኘት
በማሰብ ነው፡፡
3. ተጠሪ ለተከበረው ፍ/ቤት የማቀርበው የፍትህ ጥያቄ፡-
3.1. አመልካች የጋራ ነው ብላ ያቀረበችው የኮንዶሚኒየም ቤት አብረን መኖር ከመጀመራችን በፊት በ 2000 ዓ.ም
መጨረሻ በዕጣ ደርሶኝ በ 2001 ዓ.ም ኅዳር ወር የቅድሚያ ክፍያ ፈፅሜ የተረከብኩ ሲሆን፤ በየጊዜው የሚከፈለውንም
ክፍያ ከኪራዩ በተገኘ አላባ ያጠናቀቅሁ ነው ፡፡ ስለዚህ የግል ቤቴ መሆኑ በሰነድ እና በሰው ማስረጃ ተጣርቶ ከጋራ ንብረት
ዝርዝር ውስጥ እንዲወጣ እና የግል ቤቱ ነው ተብሎ እንዲወሰንልኝ፤
3.2. የመኖሪያ ቤታችንም አብረን መኖር ከጀመርን በኋላ በ 2007 ዓ.ም አመልካች ሦስተኛዋን ልጃችንን ዕድላዊት ታረቀኝን
ለመውለድ ወደ ጤና ተቋም ከመግባቷ በፊት የቤቱን ጠቅላላ ዋጋ ብር 130,000.00 (አንድ መቶ ሰላሳ ሺህ) ከተጠቀሱት
የአዋሽ እና የኢትዮ. ንግድ ባንክ ከአመልካች የባንክ ሂሳብ ወጪ አድርጋ ለሻጭ አቶ ታዴዎስ ወ/ኪዳን ከፍላ ወደ ጤና
ጣቢያ የሄደች ለመሆኑ ተጣርቶ የጋራ ንብረት ውስጥ እንዲካተትልኝ፤
3.3. አመልካች በስሟ ካሉት የባንክ ሒሳብ ቁጥሮች የሚንቀሳቀስ ገንዘብ የጋራ መሆኑ እንዲወሰንልኝና ግንኙነታችን
ከተቋረጠ እና በመሐላችን ቅሬታ ከተካረረ ከአንድ ዓመት ወዲህ ገንዘብ በማሸሽ መልክ ያወጣችው ካለ የባንክ
ስቴትመንት በፍ.ብ.ሥ.ሥ ሕግ ቁ. 145 መሠረት በትዕዛዝ ቀርቦ ከተጣራ በኋላ ድርሻዬን እንድትከፍለኝ
እንዲወሰንልኝ፤
3.4. ሁለቱ የመጀመሪያ ልጆቻችን ከእኔ ጋር እንዲኖሩ ይህ የማይሆንበት ምክንያት ካለ ደግሞ በማናቸውም
ጊዜ ሁሉንም ልጆቼን ለማየት እና ለማግኘት እኔም ሆንኩ እነርሱ ሲፈልጉ ለማንሸራሸር እና የሚፈልጉትን ነገር
እንዳደርግላቸው ለመውሰድ እንድችል እንዲወሰንልኝ በታላቅ ትህትና አመለክታለሁ፡፡

ያቀረብኩት መልስ እውነት መሆኑን በፍ.ብ.ሥ.ሥ ሕግ ቁ. 92 መሠረት አረጋግጣለሁ፡፡

ተጠሪ

ታረቀኝ መኩሪያ

መዝ.ቁ. 165245
ቀን፡ 27/02/2013

ለፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የካ ምድብ የቤተሰብ ችሎት

አዲስ አበባ

አመልካች ……………… ወ/ሮ እመቤት አብርሃም


ተጠሪ ………………. አቶ ታረቀኝ መኩሪያ

በፍ.ብ.ሥ.ሥ ሕግ ቁ. 223 መሠረት የቀረበ የማስረጃ ዝርዝር


1. የሰነድ ማስረጃ ፡-
1.1. የኮንዶሙኒየም ቤት ከአመልካች ጋር ከመኖራችን ከየካቲት 2001 ዓ.ም በፊት ያገኘሁት የግል ቤቴ መሆኑን የሚያስረዳልኝ
በ 11/03/2001 ዓ.ም የተፃፈ የቅድመ ክፍያ ቅፅ አንድ ገፅ ፎቶ ኮፒ አቅርቤአለሁ፡፡ ዋናው በእጄ ይገኛል፡፡
1.2. ዕጣው የወጣልኝ ከቅድመ ክፍያው በፊት በ 2000 ዓ.ም መጨረሻ አካባቢ ለመሆኑ ከቂርቆስ ክ/ከተማ የቤቶች ልማት
ኤጀንሲ በፍ.ብ.ሥ.ሥ ሕግ ቁ. 145 መሠረት በፍ/ቤቱ ትዕዛዝ መሠረት እንዲረጋገጥ እጠይቃለሁ፡፡
1.3. የመኖሪያ ቤታችን የግዢ ሙሉ ሒሳብ ብር 130,000.00 (አንድ መቶ ሰላሳ ሺህ) ከአመልካች የባንክ ሒሳብ ቁ.
013200403553 አዋሽ ባንክ እና የሒሳብ ቁ. 310501065043 የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ወጪ ተደርጎ ኅዳር 15
ቀን 2007 ዓ.ም መከፈሉን የሚያሳይ የባንክ ስቴትመንት በፍ.ብ.ሥ.ሥ ሕግ ቁ. 145 መሠረት በፍ/ቤት ትዕዛዝ
ቀርቦ እንዲታይልኝ እጠይቃለሁ፡፡
2. የሰው ምስክሮች ፡-
2.1. የኮንዶሚኒየም ቤቱ ዕጣ የደረሰኝ እና ቅድመ ክፍያ የፈፀምኩት አብረን መኖር ከመጀመራችን በፊት ተጠሪ ከቤተሰቤ ጋር
ሳለሁ ለመሆኑ የሚያስረዱልኝ ምስክሮች
1. አቶ ዮሐንስ ጆርጅ ……………. አድራሻ፡ አዲስ አበባ
2. አቶ ሽመልስ ገርባ ……………. አድራሻ፡ አዲስ አበባ
3. አቶ ዘላለም መኩሪያ ……………. አድራሻ፡ አዲስ አበባ
2.2. በየካ ክ/ከተማ ወረዳ 11 ያለው መኖሪያ ቤታችን ከአቶ ታዴዎስ ወ/ኪዳን በ 2007 ዓ.ም ያየር ካርታ ተገዝቶ የሠራነው
መሆኑን የሚያስረዱልኝ ምስክሮች
1. አቶ ጋሻው ተሰማ ……………. አድራሻ፡ አዲስ አበባ 4. አቶ ሽመልስ ገርባ ……………. አድራሻ፡ አዲስ አበባ
2. አቶ ግዛው ገ/ማርያም ……. አድራሻ፡ አዲስ አበባ 5. አቶ ታዴዎስ ወ/ኪዳን ……………. አድራሻ፡ አዲስ አበባ
3. አቶ ደነቀው አብርሃም ……... አድራሻ፡ አዲስ አበባ
6. አቶ እሸቱ ወርቁ ……………. አድራሻ፡አዲስ አበባ፤ ሲሆኑ
ጭብጡ ካልተለወጠ የማቀርበው ማስረጃ ይኸው መሆኑን በፍ.ብ.ሥ.ሥ ሕግ ቁ. 92 መሠረት አረጋግጣለሁ፡፡

ተጠሪ

ታረቀኝ መኩሪያ

መዝ.ቁ. 165245
ቀን፡ 03/03/2013

ለፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የካ ምድብ የቤተሰብ ችሎት

አዲስ አበባ

አመልካች ……………… ወ/ሮ እመቤት አብርሃም

ተጠሪ ………………. አቶ ታረቀኝ መኩሪያ


በፍ.ብ.ሥ.ሥ ሕግ ቁ. 205 እና 154 መሠረት የቀረበ አቤቱታ

በ 20/02/2013 ዓ.ም ተጠሪ ባቀረብኩት የእግድ አቤቱታ መሠረት የተከበረው ፍ/ቤት በአዋሽ ባንክ እና በኢት/ንግድ ባንክ
ጠቅሼ ባቀረብኳቸው የሒሳብ ቁጥሮች ያለው ሒሳብ ተከብሮ እንዲቆይ አዝዞልኝ ነበር፡፡

ይሁን እንጂ የኢት/ንግድ ባንክ የሂሳብ ቁ.310501065043 የሆነ የለም ብሎ ባንኩ ስለመሰለኝ እርግጠኛ የሆነ የሒሳብ
ቁጥር ባላገኝም እንኳ በአመልካች ስም በንግድ ባንኩ ተቀማጭ ገንዘብ እንዳለን እርግጠኛ ስለሆንኩ በባንኩ ውስጥ በስሟ ደብተር
ተከፍቶ የተቀመጠ ሒሳብ እንዲታገድ ተብሎ እንዲታዘዝልኝ በትህትና አመለክታለሁ፡፡

አቤቱታዬ እውነት መሆኑን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁ. 92 መሠረት አረጋግጣለሁ፡፡

አመልካች

ታረቀኝ መኩሪያ

You might also like