You are on page 1of 4

በፌ/ፖ/ኮ/ወ/ም/ቢሮ የፎረንሲክ ምርመራ ዘርፍ

ለአካላዊ ፎረንሲክ ላብራቶሪ ምርመራ ዳይሬክቶሬት

አዲስ አበባ

ጉዳዩ፡- የሰነድ ምርመራ እንዲደረግ ስለመጠየቅ ይሆናል፡፡

የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 2-06951 ኦ.ሮ የሻንሲ ቁጥሩ JTDBW23E560102557 የሞተር ቁጥር 3843157-2NZ የሆነ
አውቶሞቢል ያሲን አብዲ በተባለ ግለሰብ አማካኝነት በቱሪስት መልክ ወደ አገር ከገባ በኋላ ቀረጥ ተከፍሎበት በህጋዊ
መንገድ ወደ አገር የገባ ለማስመሰል ሃሰተኛ የመንግስት ሰነዶች ተዘጋጅቶለት ሊብሬ እና ታርጋ አውጥቶ በመንቀሳቀስ
ላይ እንዳለ በቀን 21/01/2012 ዓ\ም ደምስ በለው መኮንን ከተባለ ተጠርጣሪ ጋር በቁጥጥር ስር ሊውል ችሏል፡፡

በመሆኑም በተፈጸመው ሃሰተኛ የመንግስንት ሰነዶችን ማዘጋጀትና መገልገል ወንጀል ክስ ጉዳይ በማጣራት ሂደት ውስጥ
ምርመራውን በሰነድ ማስረጃዎች ማስደገፍ እንድንችል ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ተመርማሪ ሰነዶች ትክክለኛነት
እንዲጣራልን እንጠይቃለን፡፡

ሀ‚ ተመርማሪ

በዲክላራሲዮን ቁጥር C-1043 በ 04/10/2018 ዲክላራሲዮን ጀርባ ላይ የታተሙት የማህተም ህትመቶች፡-

1. አዲስ አበባ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት፣ የተሽከርካሪ መለዋወጫና ጎማ እቃ አወጣጥ ዩኒት፣ ፍተሻ ተከናውኗል፣
የፍተሻ ኦፊሰር፣ ስም፣ ፊርማ፣ ቀን፣ ሰዓት፣ ኮድ ቁጥር 4 የሚል ባለ 6 ማእዘን የማህተም ህትመት

2. አ.አ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት፣ ሪከርድ ሥራ አመራር ቡድን፣ የጉምሩክ ሥነ ሥርዓት ተጠናቋል፣ ስም፣ ፊርማ፣
ቀን፣ መለያ ቁጥር 1 የሚል ባለ 4 ማእዘን የማህተም ህትመት

3. አዲስ አበባ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት፣ የተሽከርካሪ መለዋወጫና ጎማ እቃ አወጣጥ ዩኒት፣ ሠነድ ተረጋግጦ
ተሰቷል፣ የሰነድ ምርመራ ኦፊሰር፣ ስም፣ ፊርማ፣ ቀን፣ ሰዓት፣ ኮድ ቁጥር 2 የሚል ባለ 5 ማእዘን የማህም ህትመት

ለ‚ ማመሳከሪያ፡-

1. አዲስ አበባ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ፣ የተሽከርካሪ መለዋወጫና ጎማ እቃ አወጣጥ ዩኒት፣ ፍተሻ ተከናውኗል፣
የፍተሻ ኦፊሰር፣ ስም፣ ፊርማ፣ ቀን፣ ሰዓት፣ ኮድ ቁጥር 4 ባለ 6 ማእዘን የማህተም ህትመት

2 አ.አ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት፣ ሪከርድ ሥራ አመራር ቡድን፣ የጉምሩክ ሥነ-ሥርዓት ተጠናቋል፣ ስም፣ ፊርማ፣
ቀን፣ ሰዓት፣ኮድ ቁጥር 1 ባለ 4 ማእዘን የማህተም ህትመት

3 አዲስ አበባ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት፣ የተሽከርካሪ መለዋወጫና ጎማ እቃ አወጣጥ ዩኒት፣ ሠነድ ተረጋግጦ ተለቋል፣
የሠነድ ምርመራ ኦፊሰር፣ ስም፣ ፊርማ፣ ቀን፣ ሰዓት፣ ኮድ ቁጥር ባለ 5 ማእዘን የማህተም ህትመት

የሚፈለገው ውጤት
1 ኛ) በፊደል ሀ ተራ ቁጥር 1 ላይ የተገለፀው ባለ 6 ማእዘን የማህም ህትመት በፊደል ለ ተራ ቁጥር 1 ላይ ከተገለፀው
ባለ 6 ማእዘን የማህተም ህትመት ጋር ተመሳሳይ መሆኑ አለመሆኑ

2 ኛ) በፊደል ሀ ተራ ቁጥር 2 ላይ የተገለፀው ባለ 4 ማእዘን የማህም ህትመት በፊደል ለ ተራ ቁጥር 2 ላይ ከተገለፀው


ባለ 4 ማእዘን የማህተም ህትመት ጋር ተመሳሳይ መሆኑ አለመሆኑ

3 ኛ) በፊደል ሀ ተራ ቁጥር 3 ላይ የተገለፀው ባለ 5 ማእዘን የማህም ህትመት በፊደል ለ ተራ ቁጥር 3 ላይ ከተገለፀው


ባለ 5 ማእዘን የማህተም ህትመት ጋር ተመሳሳይ መሆኑ አለመሆኑ በሰነድ ምርመራ ተረጋግጦ ውጤቱ እንዲገለጽልን
ተመርማሪ 1 ገጽ ሰነድ ማመሳከሪያ 6 ገጽ በድምሩ 7 ገጽ በዚህ መሸኛ ደብዳቤ በአቶ ተስፋዬ ሙሉጌታ አማካኝነት
የላክን መሆኑን እየገለጽን ውጤቱን ባመጡት መርማሪ እጅ እንዲላክልን እናሳስባለን፡፡

ከሠላምታ ጋር

በፌ/ፖ/ኮ/ወ/ም/ቢሮ የፎረንሲክ ምርመራ ዘርፍ

ለአካላዊ ፎረንሲክ ላብራቶሪ ምርመራ ዳይሬክቶሬት

አዲስ አበባ

ጉዳዩ፡- የሰነድ ምርመራ እንዲደረግ ስለመጠየቅ ይሆናል፡፡

የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 3-37988 ኦ.ሮ የሻንሲ ቁጥሩ JTDZE32V5C5209406 የሞተር ቁጥር 2AZB526458 የሆነ
RAV 4 መኪና ታጁዲን አብደላ በተባለ ግለሰብ አማካኝነት በቱሪስት መልክ ወደ አገር ከገባ በኋላ ቀረጥ ተከፍሎበት
በህጋዊ መንገድ ወደ አገር የገባ ለማስመሰል ሃሰተኛ የመንግስት ሰነዶች ተዘጋጅቶለት ሊብሬ እና ታርጋ አውጥቶ
በመንቀሳቀስ ላይ እንዳለ ታምራት ደስታ ከተባለ ተጠርጣሪ ጋር በቁጥጥር ስር በመዋሉ ምርመራን በክፍላችን
በማጣራት ላይ እንገኛለን፡፡

በመሆኑም በተፈጸመው ሃሰተኛ የመንግስት ሰነዶችን ማዘጋጀትና መገልገል ወንጀል ክስ ጉዳይ በማጣራት ሂደት ውስጥ
ምርመራውን በሰነድ ማስረጃዎች ማስደገፍ እንድንችል ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ተመርማሪ ሰነዶች ትክክለኛነት
እንዲጣራልን ፡-

ሀ‚ ተመርማሪ

በዲክላራሲዮን ቁጥር C-992 በ 18/04/2012 ዲክላራሲዮን ጀርባ ላይ የታተሙት የማህተም ህትመቶች፡-

1. አ.አ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት፣ ሪከርድ ሥራ አመራር ቡድን፣ የጉምሩክ ሥነ ሥርዓት ተጠናቋል፣ ስም፣ ፊርማ፣
ቀን፣ መለያ ቁጥር 1 የሚል ባለ 4 ማእዘን የማህተም ህትመት

2. አዲስ አበባ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት፣ የተሽከርካሪ መለዋወጫና ጎማ እቃ አወጣጥ ዩኒት፣ ሠነድ ተረጋግጦ
ተሰቷል፣ የሰነድ ምርመራ ኦፊሰር፣ ስም፣ ፊርማ፣ ቀን፣ ሰዓት፣ ኮድ ቁጥር 2 የሚል ባለ 5 ማእዘን የማህም ህትመት

ለ‚ ማመሳከሪያ፡-

1. አ.አ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት፣ ሪከርድ ሥራ አመራር ቡድን፣ የጉምሩክ ሥነ-ሥርዓት ተጠናቋል፣ ስም፣ ፊርማ፣
ቀን፣ ሰዓት፣ኮድ ቁጥር 1 ባለ 4 ማእዘን የማህተም ህትመት በንጹህ ወረቀት ላይ 10 ቦታ የታተመ

2. አዲስ አበባ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት፣ የተሽከርካሪ መለዋወጫና ጎማ እቃ አወጣጥ ዩኒት፣ ሠነድ ተረጋግጦ
ተለቋል፣ የሠነድ ምርመራ ኦፊሰር፣ ስም፣ ፊርማ፣ ቀን፣ ሰዓት፣ ኮድ ቁጥር-- ባለ 5 ማእዘን የማህተም ህትመት በንጹህ
ወረቀት ላይ 10 ቦታ የታተመ ኮድ ቁጥሩ 2 ቢሆንም በአገልግሎት ብዛት የኮድ ቁጥሩ የለቀቀ መሆኑን እንዲሁም
በተመሳሳይ ስም ከዚህ በፊት ታትሞ የተወገደ ማህተም የሌለ መሆኑን የሚልጽ ከአ .አ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅርንጫፍ
ጽ/ቤት የተጻፈ 02 ገጽ ደብዳቤ

የሚፈለገው ውጤት

1 ኛ) በፊደል ሀ ተራ ቁጥር 1 ላይ የተገለፀው ባለ 4 ማእዘን የማህም ህትመት በፊደል ለ ተራ ቁጥር 1 ላይ ከተገለፀው


ባለ 4 ማእዘን የማህተም ህትመት ጋር ተመሳሳይ መሆኑ አለመሆኑ

2 ኛ) በፊደል ሀ ተራ ቁጥር 2 ላይ የተገለፀው ባለ 5 ማእዘን የማህም ህትመት በፊደል ለ ተራ ቁጥር 2 ላይ ከተገለፀው


ባለ 5 ማእዘን የማህተም ህትመት ጋር ተመሳሳይ መሆኑ አለመሆኑ በሰነድ ምርመራ ተረጋግጦ ውጤቱ እንዲገለጽልን
ተመርማሪ 01 ገጽ፣ ሰነድ ማመሳከሪያ 04 ገጽ፣ ከአ.አ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የተጻፈ ደብዳቤ 02 ገጽ
ደብዳቤ በድምሩ 7 ገጽ በዚህ መሸኛ ደብዳቤ በረ/ኢ/ር ቶማስ ዮናስ አማካኝነት የላክን መሆኑን እየገለጽን ውጤቱን
ባመጡት መርማሪ እጅ እንዲላክልን እናሳስባለን፡፡

ከሠላምታ ጋር

You might also like