You are on page 1of 4

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት

THE FEDERAL DEMOCRATIC REPUBLIC OF ETHIOPIA FEDERAL FIRST


INSTANCE COURT

የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ኮ/መ/ቁ 298270 ቅጣት

ልደታ ምድብ 5 ኛ ገቢዎችና ጉምሩክ ወንጀል ችሎት ሚያዚያ 26 ቀን 2014 ዓ.ም

ገጽ-17

ዳኛ- ሮባ ቀጨም

ከሳሽ - የፌ/ዐ/ህግ-

ተከሳሽ- 1 ዳንኤል ወልዴ ገ/ስላሴ

2) አዘዘው አይቸ ተሰማ

መዝገቡ የተቀጠረው ተከሳሾች ላይ ቅጣት ለመወሰን ነው፣ ተመርምሮ ተከታዩ ቅጣት ተወስኗል፡፡

ቅጣት

የወንጀል ቅጣት አላማ ወንጀል አድራጊዎች ተቀጥተው ሌላ ወንጀል ከመፈፀም እንዲቆጠቡ እና


እንዲታረሙ ማድረግ እንዲሁም ሌሎች ሰዎች ወንጀል አድርገው ከሚቀጡት ሰዎች እንዲማሩ እና
ወንጀል ከመፈፀም እንዲጠነቀቁ ማስተማር እንደሆነ በ 1996 የወንጀል ህግ አንቀፅ 1 ላይ ተደንግጓል፡፡
የወንጀል ቅጣት ሲወሰን የወጥነት፣ ተገማችነት እና ተመዛዛኝነት መርሆዎችን ታሳቢ ያደረገ የወንጀል
አድራጊውን ግላዊ የአደገኛነት መጠን፣ ያለፈ የሕይወት ታሪኩን እና ወንጀል ለመስራት ያነሳሱትን
ምክንያቶች፣ የግል ኑሮውን ሁኔታ፣ የትምህርት ደረጃውን እንዲሁም የወንጀሉን ከባድነትና የአፈጻጸሙን
ሁኔታዎች ከግንዛቤ ያስገባ መሆን እንዳለበት ከ 1996 ዓ.ም የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 88 (2) እና
ከተሸሻለው የቅጣት አወሳሰን መመሪያ ቁጥር 2/2006 ድንጋጌዎች መረዳት ይቻላል፡፡ የወንጀል ህጉን እና
የቅጣት አወሰሳሰን መመሪያውን መሰረት በማድረግም በተከሳሽ ላይ ተከታዩ ቅጣት ተወስኗል፡፡

ተከሳሾች ጥፋተኛ የተባሉበት 1 ኛ ተከሳሽ የታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 983/2008 አንቀጽ 131/1/(ለ)
፤ 2 ኛ ተከሳሽ በአንቀጽ 128(1) እና 131(1)(ለ) በመተላለፍ ሲሆን ድንጋጌው ከሁለት ዓመት በማያንስ እና
ከአምስት ዓመት በማይበልጥ ጽኑ እስራት የሚያስቀጣ ነው፡፡ ለድንጋጌዎቹ በቅጣት አወሳሰን መመሪያው
ደረጃ እና እርከን ያልወጣለት በመሆኑ የወንጀል ደረጃውን የሚወጣው በቅጣት አወሳሰን መመሪያ ቁጥር
2/2006 አንቀፅ 19 መሰረት ፍርድ ቤት ይሆናል፡፡ ዐ/ህግ ከወንጀል አፈፃፀሙ አንፃር ደረጃው ቀላል ተብሎ
ቢመደብ ተቃውሞ እንደሌለው የገለጸ ሲሆን ፍ/ቤቱም የወንጀል አፈፃፀሙ ውስብስብ ባለመሆኑ
ደረጃውን በቀላል የወንጀል ደረጃ እንዲመደብ ወስኗል፡፡

ኮ/መ/ቁ 298270 ቅጣት

1|Page
የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት

THE FEDERAL DEMOCRATIC REPUBLIC OF ETHIOPIA FEDERAL FIRST


INSTANCE COURT

ሚያዚያ 26 ቀን 2014 ዓ.ም

ገጽ-18

ፍርድ ቤቱ ባወጣ ደረጃ መሰረት ቀላል የወንጀል ደረጃ የሚባለው እርከን ውስጥ የተቀመጠ የእስራት
ቅጣት መጠን ከ 2 ዓመት እስከ 2 ዓመት ከ 9 ወር የሚያስቀጣ ሲሆን ፍ/ቤቱ በዚህ ፍቅድ ስልጣን ውስጥ
መነሻ ቅጣቱ 2 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲሆን ወስኗል፡፡ ይህም መነሻ ቅጣት በቅጣት አወሳሰን መመሪያው
አባሪ አንድ መሰረት የእስራት ቅጣቱ እርከን 10 ላይ ያርፋል፡፡

አቃቤ ህግ ተከሳሾች ላይ ያቀረበ የቅጣት መክበጃ በለመኖሩ መነሻ እርከን ላይ ለውጥ አይፈጠርም፡፡ የቅጣት
ማቅለያን በተመለከተ ተከሳሾች የወንጀል ሪከርድ የሌላቸው መሆኑን፤1 ኛ ተከሳሽ በበጎ አድራጎት/ልማት ስራ
ውስጥ የሚሳተፍ መሆኑን ፤ተከሳሾች የቤተሰብ ሐላፊ መሆናቸውን፤ 1 ኛ ተከሳሽ ብድር በመውሰድ ለ 30
ሰራተኞች የስራ እድል የፈጠረላቸው መሆኑን፤ 1 ኛ ተከሳሽ ለመከላከያ ሰራዊት ድጋፍ ማድረጉን በመግለጽ
እንዲሁም 1 ኛ እና 2 ኛ ተከሳሾች ህመምተኛ የሆኑ አባት እና እናት ያለው ሲሆን በየቀኑ ክትትል የሚያስፈልጋቸው
መሆኑን እና 2 ኛ ተከሳሽ መልካም ፀባይ ያለ በመሆኑን በመግለጽ 1 ኛ ተከሳሽ እንደ 7 የቅጣት ማቅከለያ
እንዲሁም 2 ኛ ተከሳሽ እንደ 4 የቅጣት ማቅለያ የቀረቡ ሲሆን ይህን በተመለከተ አቃቤ ህግ አስታየት እንዲሰጥበት
ተጠይቀው 1 ኛ ተከሳሽን በተመለከተ 1 ኛ እና 7 ኛ ተራ ቁጥር ላይ የተጠቀሱት ፤ እንዲሁም 2 ኛ እና 3 ኛ ተራ
ቁጥር ላይ የተጠቀሱ እና በተራ ቁጥር 4 ኛ እና 6 ኛ ላይ የተጠቀሱት ማቅለያ ምክንያቶች ተጣምረው መያዝ
አለበት ያለ ሲሆን 2 ኛ ተከሳሽን በተመለከተ ማቅለያዎቹ የተደጋገሙ በመሆኑ እንደ ሁለት የቅጣት ማቅለያ ብቻ
ልያዝለት ይገባል በማለት አስታየት ሰጥቷል፡፡

ፍርድ ቤቱም ተከሳሾች ሪከርድ የሌለባቸው በመሆኑ በወ/ህ/ቁ.82(1)(ሀ) ለሁለቱም ተከሳሾች እንደ አንድ የቅጣት
ማቅለያ ተቀብሏል፡፡ በሌላ በኩል ተከሳሾች የቤተሰብ አስተዳዳሪ መሆኑን በማስረጃ ያረጋገጡ በመሆኑ ለሁለቱም
ተከሳሾች እንደ አንድ የቅጣት ማቅለያ በወ/ህ/ቁ.86 መሰረት ፍርድ ቤቱ ተቀብሏል፡፡ በሌላ በኩል 1 ኛ እና 2 ኛ
ተከሳሾች የወንጀል ሪከርድ አለመኖራቸው እና መልካም ጸባይ መኖራቸውን ነጣጥለው ለየብቻ ያቀረቡ ሲሆን አንድ
ሰው የወንጀል ሪከርድ አለመኖሩ እና መልካም ጸባይ መኖሩ ተጠቃለው የተከሳሾች ባህሪ የሚያሳይ በመሆኑ በዚህ
ረገድ ተከሳሾች ተነጣጥለው እንድያዝላቸው ያቀረቡት አስታት ተቀባይነት የለሁም በማለት ፍርድ ቤቱ አልፏል፡፡
በሌላ በኩል 1 ኛ እኛ 2 ኛ ተከሳሾች ታማሚ የሆኑ እናት እና አባት መኖራቸውን እና ደካማ መሆናቸው እንዲሁም
1 ኛ ተከሳሽ ከ 30 በላይ ሰራተኞች ማስተዳደሩ ተከሳሾች ሐላፊነት ያላቸው በመሆኑ እንደ አንድ የቅጣት መቅለያ
ይያዛል እንጂ ተነጣጥለው የሚያዝበት አግባብ አይኖርም፡፡

ኮ/መ/ቁ 298270 ቅጣት

ሚያዚያ 26 ቀን 2014 ዓ.ም

ገጽ-19

2|Page
የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት

THE FEDERAL DEMOCRATIC REPUBLIC OF ETHIOPIA FEDERAL FIRST


INSTANCE COURT

ከዚህም በተጨማሪም 1 ኛ ተከሳሽ ለበጎ አድራጎት ድርጂት ድጋፍ ማድረጉ እና ለመከላከያ ሰራዊት ድጋፍ ማድረጉ
የ 1 ኛ ተከሳሽን በጎ አድራጎት ስራን የሚያሳይ በመሆኑ ተጠቃለው እንደ አንድ የቅጣት ማቅለያ በወ/ህ/ቁ.86
መሰረት ፍርድ ቤቱ ተቀብሏል፡፡

በአጠቃላይ ለ 1 ኛ ተከሳሽ ሶስት(3) የቅጣት ማቅለያ እንዲሁም ለ 2 ኛ ተከሳሽ ሁለት(2) የቅጣት ማቅለያ
የተያዘላቸው በመሆኑ ከእስራት ቅጣት መነሻ እርከን 10 ላይ 1 ኛ ተከሳሽን በተመለከተ ወደ እርከን 7 የሚመለስ
ሲሆን እርከን 7 ስር ያለው የቅጣት መጠን ከ 1 አመት እስከ 1 አመት ከ 6 ወር ሲሆን 2 ኛ ተከሳሽን በተመለከተ ወደ
እርከን 8 የሚመለስ ሲሆን እርከን 6 ስር ያለው የቅጣት መጠን ከ 1 አመት ከ 2 ወር እስከ 1 አመት ከ 8 ወር
እስራት ቅጣት ነው፡፡

ፍርድ ቤቱ በተያዘው እርከን ስር ተከሳሾች ከእንደዚህ መሰል ድርጊታቸው እንድታረሙና ለሌሎችም


ማስጠንቀቂያ ይሆን ዘንድ 1 ኛ ተከሳሽ በ 1 ዓመት ፅኑ እና 2 ኛ ተከሳሽ በ 1 አመት ከ 2 ወር ጽኑ እስራት እንዲቀጡ
በወ/መ/ስ/ስ/ህ/ቁ.149(5) መሰረት ወስኗል፡፡

በሌላ በኩል ተከሳሾች ቅጣቱ እንዲገደብላቸው የጠየቁ ሲሆን የገደብ ጥያቄን በተመለከተ ቅጣት መገደብ የፍርድ
ቤቶች ስልጣን ሲሆን አንድ ተከሳሽ የወንጀል ክስ አምነው ባይቀበሉም እንኳን ፍርድ ቤቶች የቅጣት አፈጻጸምን
ሲወስኑ ተከሳሾች ክሱን አምነው አለመቀበላቸው እንደ ተጠበቀ ሆኖ ቅጣት እንዲገደብላቸው የሚያስችሉ
አስገዳጅ ሁኔታዎች መኖሩ እና አለመኖሩን መመርመር የግድ አስፈላጊ ነው፡፡ በሌላ አገላለጽ ቅጣት ተከሳሾች ላይ
ከተጣለ በኃላ የወንጀል ህጉን አላማ ልያሳካ የምችለው ቅጣቱ ሲፈጸም ነው ወይንስ ተገድቦ ሲቆይ ነው የሚለውን
ጥያቄ መመለስ የግድ አስፈላጊ ነው፡፡

ወደ ጉዳዩ ሲንመለስ ተከሳሾች የወንጀል ድርጊቱን አምነው ያልተቀበሉ ቢሆንም ተከሳሾች በእስር እንዳይቀጡ
የሚያደርግጋቸው አሳማኝ እና አስገዳጅ መስረጃዎች መቅረቡን እና አለመቅሩቡን ሲንመለከት ተከሳሾች እናት እና
አባታቸው ታማሚ መሆናቸውን እና ክትትል የሚያስፈልጋቸው መሆኑን ነው እንጂ ከህክምና ተቋም በማስረጃ
አስደግፈው ያቀረቡት ማስረጃ የሌለ በመሆኑ እንዲሁም 1 ኛ ተከሳሽ 30 ሰራተኞችን የሚያስተዳድሩ መሆናቸውን
ይግለጽ እንጂ እውነትም 1 ኛ ተከሳሽ ይህን ሁሉ ሰራተኞችን የሚያስተዳድር መሆኑን የሚያሳይ ስም ዝርዝር እና
ሰራተኞች በየወሩ የሚፈርሙት ፐይሮል እንደማስረጃነት ያላቀረበ በመሆኑ ቅጣቱ እንዲገደብ

ኮ/መ/ቁ 298270 ቅጣት

ሚያዚያ 26 ቀን 2014 ዓ.ም

ገጽ-20

ያያደርገው ምክንያት ባለመኖሩ ገደብ ተከሳሾችን ያስተምራል ተብሎ ስለማይገመት ፍርድ ቤቱ የገደብ ጥያቄውን
አልተቀበለም፡፡

3|Page
የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት

THE FEDERAL DEMOCRATIC REPUBLIC OF ETHIOPIA FEDERAL FIRST


INSTANCE COURT

ትዕዛዝ
1. 1 ኛ ተከሳሽ ላይ የተወሰነውን የ 1 አመት ጽኑ እስራት 2 ኛ ተከሳሽ ላይ የተወሰነውን የ 1 አመት
ከ 2 ወር ጽኑ እስራት ተከሳሾች በፖሊስ ጣቢያ የታሰሩት ካለ በማሰብ በውሳኔ መሰረት
እንዲያስፈጽም ታዟል፡፡ይጻፍ፡፡
2. መዝገቡ የመጨረሻ ውሳኔ ስላገኜ ተከሳሾች ያስያዙት የዋስትና ገንዘብ ማንነታቸው ተረጋግጦ
ለተከሳሾች እንዲመለስ ታዟል፡፡ ይጻፍ፡፡
3. ተከሳሾችን ላይ የተሰጠውን ውሳኔን በተመለከተ ይግባኝ መብት ነው፡
4. መዝገቡ ስለተዘጋ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ፡፡

4|Page

You might also like