You are on page 1of 3

መ/ቁ-12742

ቀን-14/05/2016 ዓ.ም

ለዶዮገና ወረዳ ፍ/ቤት

ዶዮገና

ከሳሾች፡-1. አቶ ዝናቡ ሲናሞ አድራሻ ሙራሳ ዌራሞ ቀበሌ

2. ወ/ሮ ጸሐይነሽ ሲናሞ አድራሻ ሙራሳ ዌራሞ ቀበሌ

3. ወ/ሮ በላይነሽ ሲናሞ ሙራሳ ዌራሞ ቀበሌ

ተከሳሾች፡-1. ወ/ሮ ፈለቀች ሲናሞ አድራሻ ሙራሳ ዌራሞ ቀበሌ

2. አቶ ጌታሁን ሲናሞ አድራሻ ሙራሳ ዌራሞ ቀበሌ

በከሳሾች ለቀረበዉ ክስ በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 244 እና 234 መሰረት በ 2 ኛ ተከሳሽ የቀረበ የመጀመሪያ ደረጃ
መቃወሚያና አማራጭ የመከላከያ መልስ ነዉ፡፡

1.የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ፡-

1.1. በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 244 (2.ሀ) መሠረት ፍ/ቤቱ ጉዳዩን ለማየት ሥልጣን የሌለዉ ስለመሆኑ፡-
ከሳሾች በጥምረት ክስ ካቀረቡብን ተከሳሾች 1 ኛ ተከሳሽ ከሀገር ዉጭ ማለትም ደቡብ አፍሪካ ነዋሪ ነዉ፡፡
እንዲሁም 1 ኛ ተከሳሽ ደቡብ አፍሪካ ኗሪ ከመሆኑም ባሻገር በአሁኑ ጊዜ የደቡብ አፍሪካ ዜግነት
አለዉ፡፡ ይህን እዉነታ ከሳሾች እራሳቸዉ ከዚህ ቀደም ለ 1 ኛ ተከሳሽ መጥሪያ ለማድረስ ሲሞክሩ
ከሀገር ዉጭ ደቡብ አፍሪካ ያለ መሆኑን የሚገልጽ ማስረጃ አቅርበዋል፡፡
የፌዴራል ፍ/ቤቶች አዋጅ ቁጥር.1234/2013 አንቀጽ 5(1.በ) ሥር እንደተነገገዉ በክርክሩ የዉጭ ሀገር
ዜጋ ያለበት ከሆነ ጉዳዩን የማየት ሥልጣን የሚኖረዉ የፌደራል ፍ/ቤት እንደሆነ በግልጽ ተመልክቷል፡፡
ይህ ሆኖ ሳለ ከሳሾች ጉዳዩን ለዶዮገና ወረዳ ፍ/ቤት ማቅረባቸዉ ተገቢነት የሌለዉ ሲሆን ጉዳዩ በዚህ
ፍ/ቤት ታይቶ ዉሳኔ ቢሰጥም የተከበረዉን ፍ/ቤት ጊዜ ከማባከንና የሥራ ጫና ከመፍጠር ባለፈ
ተፈጻሚነት ያለዉ ዉሳኔ መስጠት የሚቻል አይደለም፡፡ በመሆኑም የተከበረዉ ፍ/ቤት ጉዳዩ ሥልጣን
ላለዉ የፌዴራል ፍ/ቤት እንዲቀርብ መዝገቡን ዘግቶ እንዲያሰናብተኝ አመለክታለሁ፡፡
1.2.በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 244 (2.ሠ) መሠረት ክሱ በይርጋ የታገደ ስለመሆኑ፡-
1.2.1 በፍ/ህ/ቁ.1000 (1) መሠረት ክሱ በ 3 ዓመት ይርጋ ቀሪ ስለመሆኑ፡-
ተከሳሾች ክርክር ያለባቸዉን ያዞታዎች ያለማንም ጣልቃ ገብነት ለረጅም አመታት ስንጠቀም የቆየን
ሲሆን በነዛ ሁሉ አመታት በይዞታዎቹ ላይ ምንም አይነት የመብት ጥያቄ ሳያነሱ ቆይተዉ አቶ ሲናሞ
ኦርታቦ ከሞቱ ከ 24 ዓመት በኋላ እንዲሁም እናታችን ወ/ሮ ሙሉነሽ ደባልቄ ከሞቱ 10 ዓመት በኋላ
ይህን ክስ አቅርበዋል፡፡
ከሳሾች ከመሠረቱም የመዉረስ መብት የላቸዉም እንጂ መብት ቢኖራቸዉ እንኳን ክርክር የተነሳባቸዉ
ይዞታዎቸ በተከሳሶች መያዛቸዉን ካወቁ በ 3 ዓመት ካለፈ በኋላ ስለወራሽነት የሚቀርብ ክስ
ተቀባይነት የሌለዉ መሆኑ በፍ/ህ/ቁ.1000 (1) ሥር ተደንግጓል፡፡
በመሆኑም ከሳሾች በቅርቡ በ 2016 ዓ.ም ያገኙት የወራሽነት ማስረጃ በህጉ መሠረት ተቀባይነት
የሌለዉ ሲሆን ተከሳሾች ይዞታወቹን ለበርካታ አመታት ያለከሳሾች ተሳትፎና ጣልቃ ገብነት
እየተጠቀምን ቆይተን አሁን ላይ ያቀረቡት ክስ ጉዳዩ በይርጋ ቀሪ ስለሆነ ተቀባይነት የሌለዉ ነዉ
በማለት የተከበረዉ ፍ./ቤት 2 ኛ ተከሳሽን በነጻ ሊያሰናብተኝ ይገባል፡፡
1.2.2 በፍ/ህ/ቁ 1000(2) መሠረት ክሱ በ 15 ይርጋ ቀሪ ስለመሆኑ፡-
ፍርድ ቤቱ የ 3 ዓመቱን ይርጋ አያልፈዉም እንጂ የሚያልፍ ከሆነ፤የእናትና አባታችን ልጅ ከሆነችዉ
ከ 3 ኛ ተራ ከሳሽ ባስተቀር ሌሎች ከሳሾች የአባተችን አቶ ሲናሞ ኦርታቦ ልጆች እንጂ የእናታችን
የወ/ሮ ሙሉነሽ ደባልቄ ልጆች አይደሉም፡፡
የክርክሩ ይዞታዎች ደግሞ ከእናታችን ወ/ሮ ሙሉነሽ ደባልቄ ቤተሰብ በኩል በዉርስ የመጡ ናቸዉ
እንጂ አቶ ሲናሞ ኦርታቦ እና ወ/ሮ ሙሉነሽ ደባልቄ በጋራ ያፈሯቸዉ ይዞታዎች አይደሉም፡፡
በመሆኑም ከ 3 ኛ ተራ ከሳሽ ባስተቀር ሌሎቹ ከሳሾች በፍ/ህጋችን ቁ.849(2) መሠረት ምንም አይነት
የዉርስ ጥያቄ የማቅረብ መብት እንኳን የላቸዉም፡፡ ከሳሾች መብት አለን የሚሉም ከሆነ ከአባታችን
ከአቶ ስናሞ ኦርታቦ እና ከእናታቸዉ ወ/ሮ አረሴ ስናሞ በኩል ስለሆነ አቶ ስናሞ ኦርታቦ ከሞቱ በ 15
ዓመት ዉስጥ ክስ ማቅረብ ነበረባቸዉ፡፡
ከሳሾች ከአቶ ሲናሞ ኦርታቦን በኩል የሚኖራቸዉን የዉርስ ጥያቄ ሳያቀርቡ 24 ዓመታት አልፈዋል፡፡
ስለዚህ በፍ/ህ/ቁ 1000(2) መሠረት ከ 3 ኛ ተራ ከሳሽ ባስተቀር ሌሎች ከሳሾች የዉርስ ጥያቄ
በማናቸዉም አስተያየት ማቅረብ አይችሉም፡፡
ስለዚህም የተከበረዉ ፍ/ቤት የከሳሾችን ክስ ዉድቅ በማድረግ ወደ ዋናዉ ክርክር መግባት ሳያስፈልግ
መዝገቡን ዘግቶ እንዲያሰናብተኝ አመለክታለሁ፡፡
ፍርድ ቤቱ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ነጥቦቹን አያልፋቸዉም እንጂ የሚያልፋቸዉ ከሆነ
በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 234 መሰረት አማራጭ የመከላከያ መልሴን ከዚህ ቀጥሎ አቀርባለሁ፡፡

1. ከሳሾች ክስ ያቀረቡባቸዉን ይዞታዎች የመዉረስ መብት የሌላቸዉ ስለመሆኑ፡-

ከሳሾች የአባታችን አቶ ስናሞ ኦርታቦ ልጆች መሆናቸዉ የታወቀ ቢሆንም ከሳሾች ከ 3 ኛ ከሳሽ
ባስተቀር የእናታችን ወ/ሮ ሙሉነሽ ደባልቄ ልጆች አይደለም፡፡
ክርክር ያለባቸዉ ይዞታዎች ከሳሾች እንደሚሉት አባታችን አቶ ስናሞ ኦርታቦና እናታችን ሙሉነሽ
ደባልቄ በጋራ ያፈሯቸዉ ሳይሆን እናታችን ወ/ሮ ሙሉነሽ ከአባታቸዉ ደባልቄ በዉርስ ያገኙት ነዉ፡፡
በፍ/ህ/ቁ/849 መሠረት ከአባት መስመር የመጣዉን ለአባት ወገን ከእናት በኩል የመጣዉን ደግሞ ለእናት
ወገን ማዉረስ ግዴታ እንደሆነ ተደንግጓል፡፡ በዚሁ አንቀጽ ንዑስ ቁ.2 ከእናት ወገን የመጣን
የማይንቀሳቅስ ንብረት የአባት ወገን ለሆኑ ሰዎች በዉርስ መስጠት አይቻልም በሚል በግልጽ ተደንግጎ
ይገኛል፡፡
ስለሆነም በዚህ ጉዳይ ከሳሾች የአባት ወገን ሲሆኑ ይዞታዎቹ ደግሞ ከእናት ወገን የመጡ ስለሆኑ
ከሳሾች ምንም አይነት የመዉረስ መብት አይኖራቸዉም፡፡
እኛ ተከሳሾች በፍ/ህ/ቁ 842 መሠረት ከእናታችን በኩል ተወላጆችና የመጀመሪያ ደረጃ ወራሾች እያለን
ይዞታዎቹ ወደ ሌለኛዉ ወገን ማለትም ወደ አባታችን መስመር የሚተላለፉበት የህግ አግባብ የለም፡፡
ስለዚህ ይህ የዉርስ ህግ መርሆ በመጣረስ የማይገባ ጥቅም ሊገኝበት የቀረበ ክስ ስለሆነ ዉድቅ ሊሆን
ይገባል፡፡
2. ከሳሾች እራሱን የቻለ የዉርስ ይዞታ ያላቸዉ ስለመሆኑ፡-
ከሳሾች ክርክር ያለባቸዉ ይዞታዎች ባሉበት በዚያዉ አካባቢ አባታችን አቶ ስናሞ ኦርታቦና
የእናታቸዉን ወ/ሮ አረሴ ስናሞ የነበረዉን ይዞታ በዉርስ ይዘዉ እየተጠቀሙበት ኖረዋል፡፡
ከሳሾች እራሱን የቻለ ለዘመናት ሲጠቀሙ የኖሩበት በቂ ይዞታ እያላቸዉ በጭራሽ የማይመለከታቸዉ
ተከሳሾች ህጋዊ ወራሽ የሆንበትን ያልአግባብ ለመበልጸግ ከማሰብ የመጣ ካሆነ ባስተቀር ህጋዊ
መሠረት የሌለዉ ክስ ነዉ፡፡
3. ከሳሾች ክርክር ያለባቸዉን ይዞታዎች የማይጠቀሙ ስለመሆኑ፡-
እኔ 2 ኛ ተከሳሽ ከ 1 ኛ ተራ ተከሳሽ ጋር በስምምነት ይዞታዎቹንን ያለማንም ጣልቃ ገብነት በእጃችን
አድርገን ስንጠቀም የነበረ ሲሆን፣ በጋዛ ፈቃዳችን ተስማምተን ይዞታዉን በ 1 ኛ ተራ ተከሳሽ ስም
ህጋዊ የይዞታ ማረጋገጫ ደብተር አስወጥተን፣ሌሎች ህጋዊ መጠይቆች እያሟላን እንዲሁም ግብር
በ 1 ኛ ተራ ተከሳሽ ስም እየገበርን ወላጅ እንታችን ወ.ሮ ሙሉነሽ ደባልቄ ከሞቱበት ከ 2006 ጀምሮ
ይዞታዎቹ በእኔ በ 2 ኛ ተራ ተከሳሽና 1 ኛ ተከሳሽ እጅ ቆይተዋል፡፡
ከሳሾች ከመሰረቱ የወራሽነት መብታቸዉ ይዞታዎቹ ከእናታችን ወገን በዉርስ የመጣ በመሆኑ በህግ
የተገደበ ነዉ፡፡ ከዚህም ባለፈ ደግሞ ከሳሾች ክርክር ያለባቸዉን ይዞታዎች ተጠቅመዉ የማያዉቁ፣1 ኛ
ከሳሽ አባታችን ከከሳሾች እናት ወ/ሮ አረሴ ስናሞ ጋር ያፈሩትን ሌላ ይዞታ ለዘመናት ሲጠቀም የቆየ
ሲሆን፣2 ኛ እና 3 ኛ ተራ ከሳሾች ሀዲያ ዞን በትዳር ሄደዉ ለዘመና የቆዩ ቤተሰብና ንብረት አፍርተዉ
ሲኖሩ የነበሩ ናቸዉ፡፡ ስለዚህም ከሳሶች በደ/ብ/ብ/ህ/ክ/ የመሬት አስተዳደርና አጠቃቀም አዋጅ
ቁ.110/99 መሠረት ይዞታዉን የማይጠቀሙና የቤተሰብ አባል ስላልሆኑ የወራሽነት መብት የሌላቸዉ
ስለሆን ክሱ ወድቅ ሊደረግ ይገባል፡፡
ፍ/ቤቱን የምጠይቀዉ ዳኝነት፡-
1.ከሳሾች ክስ ያቀቡባቸዉን ይዞታዎች የሚወርሱበት የህግ አግባብ የሌለ በመሆኑ የተከበረዉ ፍ/ቤት
ከሳሾች የመዉረስ መብት የላቸዉም ተብሎ እንዲወሰንልኝ እጠይቃለሀ፡፡
2.የዉርስ ይዞታዎቹ ሊካፈሉ አይገባም ተብሎ እንዲወሰን እጠይቃለሁ፡፡
3.ከሳሾች ያላግባብ ያወጣነዉን ወጪና ኪሳራ የመጠየቅ መብታችን ተከብሮ እንዲወሰንልን
አመለክታለሁ፡፡
ዮሀንስ ጳዉሎስ(ጠበቃ)

You might also like