You are on page 1of 4

ቀን / / 2015

መ/ቁ420/15

ፌዴራል ለጠቅላይ ፍ/ቤት


አዲስ አበባ

በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 320-327 (3) መሰረት በስር ለፌደራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን


አስተዳዳር ፍ/ቤት የተፈፀመ ከባድ ዲሲፒሊን የቅጣት ውሳኔ መሰረታዊ የህግ
ስህተት የተፈፀመበት በመሆኑ በዚህ ጠቅላይ ፍርድ ቤት እንዲታረምልኝ የቀረበ
የይግባኝ ቅሬታ ነው ፡፡

ይግባኝ ባይ-፤- ግዛዉ ሀ/ስላሴ


አድራሻ ሐረረ ቀበሌ 01 የቤት ቁጥር 1020
የሰራ መደብ የማ/ዋ/ አቅ/ምዝ/ባለሙያ
መልስ ሰጪ -የግል ደርጅቶቸ ሰራተኞች ማህበራዊ ዋሰትና አስተዳደር ምስራቅ
ሪ/ ጽ/ቤት
አደራሻ- ድሬደዋ ከተማ

በስር ለፌደራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን አስተዳዳር ፍ/ቤት ፍርድ ቤት በመ.ቁ


............. በሆነው ላይ በቀን ........................ ዓ.ም በዋለው ችሎት የተሰጠው
ውሳኔ ላይ በተሰጠው የከባድ የዲሊፒሊን ቅጣት ዉሳኔ ከይግባኝ ባይ የቀረበ
ይግባኝ ቅሬታ አቤቱታ ነዉ፡፡

የይግባኙ ምክንያት ባጭሩ


መልስ ሰጪ መ/ቤት መጋቢት 28 ቀነ 2015 ዓ.ም ባቀረበዉ የመከላከያ መልስ
በህገወጥ መንገድ የጡረታ አበል እንዲወሰንላቸዉ የተደረጉት አቶ ወንድማገኝ
ላሽተዉ ቢተዉ የጡረታ መብት እንዲከበርላቸዉ ጥያቄ ያቀረበዉ ድርጅት በግብር
ከፋይ መለያ ቁጥር 0044926402 ተመዝግቦ በሚታወቀዉ ለአለም ሆቴል ሲሆን
ይግባኝ ባይ በግብር ከፋይ መለያ ቁጥር 002117949 እና በደርጅት ምዝገባ
መለያ ቁጥር 0611000725 ተመዝግቦ በሚታወቀዉ መስከርም አልጋ ቤት ጋር
በማገናኘት ጉዳዩን በማወሳሰብ የጡረታ መለያ ቁጥር ተሻሽሎ የመስጠት ብቻ
አንደሆነ በማስመሰል የዲሲፒሊን ክሱን ጭብጥ ቀይረዉ ያቀረቡት መንገድ
አግባብ አይደለም ከዚህ ሌላ ቀደም ሲል በይግባኝ ባይና በመልስ ሰጪ መ/ቤት
የቀረቡት ሰነዶች በሙሉ የተፈረሙትና ማህተማቸዉ የሚናገረዉ ለአለመ ሆቴል
ሆኖ ሳለ ከመስከረም አልጋ ቤት ጋር መያያዙ ተገቢ አይደላም በተጨማሪም
ይግባኝ ባይ አቶ ወንድማገኝ ላሽተዉ የሰሩት በግብር ከፋይ መለያ ቁጥር
0002117949 እና በድርጅት ምዝገባ ቁጥር 0611000725 ተመዝግቦ በሚገኘዉ
መስከረም አልጋ ቤት ነዉ ቢልም በተቋሙ የሥራ ማንዋል መሠረት ግለሰቡ
አንደሌሎች ሠራተኞች ስሙ በጡ3 ላይ የድርጅት ምዝገባ ላይ ያልተመዘገበ
ከመሆኑም በላይ ለግለሰቡ የአበል መጠየቂያ ቅጽ ጡ2 ሞልቶ ያቀረበዉ በግብር
ከፋይ መለያ ቁጥር 0044926402 እና በድርጅት ምዝገባ ቁጥር 0611001162
ተመዝግቦ ባለዉ ሆኖ ሳለ የጡረታ ሽፋን ዉስጥ ያልነበረን ግለሰብ ለመጥቅም
በሚመስል መልኩ የጡረታ መለያ ቁጥር በመስጠት አለአግባብ የጡረታ አበል
እንዲወሰንላቸዉ ማስተላለፋቸዉን ከቀረበዉ ሰነዶች መረዳት ይቻላል፡፡የሚለዉን
የመልስ ሰጪ የመከላከያ መልስ መሠረት አድርጎ ለአለም ሆቴል በሚለዉ
የድርጅቱ ጠቅላላ መጠሪያ ስም መረጃዎች በመምጣታቸዉ ብቻ የድርጅቶቹን
የግበር ከፋይ መለያ ቁጥር ፈርሞ የላከዉ ባለቤት ስምና የሁለቱ ድርጀቶች
የማህተም ልዩነት ሳይታይ ለተወስነብኝ ከባድ የዲሲፒሊን ቅጣት ይግባኝ
ለማለት ነዉ፡፡
በመጀመሪያ አቶ ወንድማገኝ ላሽተዉ ቢተዉ የጠረታ መብት አንዲከበርላቸዉ
ጥያቄ ያቀርበዉ በግብር ከፋይ መለያ ቁጥር 0044926402 ተመዝግቦ ባለዉ
ለአለም ሆቴል ነዉ ለሚለዉ የጠረታ መጠየቂያ ቅጽ ጡ2 ላይ የአሰሪዉ
መስራቤት የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር በሚለዉ ቦታ ላይ የተመዘገበዉ ጠቅላላ
መጠሪያዉ ለአለመ ሆቴል ተብሎ በሚጠራዉ ድርጅት በግብር ከፋይ መለያ
ቁጥር 0002117949 ተመዝግቦ ከሚገኘዉ የመስከረም አልጋ ቤት መሆኑ
እንዲሁም በንግድ ፍቃዱ ባለቤት መስከረም በላይነህ ስም ፊራማና ክብ ማህተሙ
ከላይ በአማርኛ ከስር በእንግሊዘኛ ለአለም ሆቴሌ ሐረር የሚል ስያሜና የቤት
ስልክ ቁጥር ባለዉ ማህተም ተመቶ የመጣ እንጂ በግብር ከፋይ መለያ ቁጥር
0044926402 ተመዘግቦ ከሚገኘዉ ለአለም ሆቴል በንግድ ፍቃዱ ባለቤት ደስታ
አርአያ ስም ፊርማና ክብ ማህተሙ ከላይ ለአለም ሆቴል ከስር ደስታ አርአያ
ባርና ሬስቶራንት በሚል ስያሜና የሞባይል ስልክ ቁጥር ባለዉ ማህተመ ተመቶ
ያልመጣ ለመሆኑ ከዚሀ ይግባኝ ጋር ያቀረብኩትን የጡረታ መጠየቂያ ጡ2 ቅጽ
መረጃን አይቶ ማረጋገጥ ይቻላል፡፡
- በይግባኝ ባይና በመልስ ሰጪ መ/ቤት ቀደም ሲል የቀረቡት ሰነዶች በሙሉ
የተፈረሙትና ማህተማቸዉ የሚናገረዉ ለአለመ ሆቴል ነዉ ለሚለዉ በግብር
ከፋይ መለያ ቁጥር 0044926402 ተመዝግቦ የሚገኘዉ ለአለም ሆቴል የንግድ
ፍቃዱ ባለቤት ስም ደስታ አርአያ ሀጎስ ሲሆን ክብ ማህተሙ ከላይ ለአለም
ሆቴል ከስር ደስታ አርአያ ባርና ሬስቶራንት የሚል ስያሜና የሞባይል ቁጥር
የያዘ ሲሆን ጠቅላላ መጠሪያዉ ለአለም ሆቴል ተብሎ በሚጠራዉ ድርጅት
በግብር ከፋይ መለያ ቁጥር 0002117949 ተመዝግቦ የሚገኘዉ መስከረም አልጋ
ቤት የንግድ ፍቃዱ ባለቤት ስም መስከረም በላይነህ ሲሆን ክብ ማህተሙ
ከላይ በአማርኛ ከሰር በእንግሊዘኛ ለአለም ሆቴል ሐረር የሚል ስያሜና
የቤት ስልክ ቁጥር የያዘ መሆኑ እንዲሁም የአቶ ወንድማገኝ ላሽተዉ ቢተዉ
የቅጥር የአገልግሎት ና የሂወት ታሪክ እና የጡረታ መጠየቂያ ጡ2 ቅጽ በግብር
ከፋይ መለያ ቁጥር 0002117949 ተመዝግቦ ካለዉ መስከረም አልጋ ቤት
በግብር ከፋይ መለያ ቁጥሩ በንግድ ፍቃዱ ባለቤት መስከረም በላይነህ ስም
ፊርማና ከብ ማህተሙ ከላይ በአማርኛ ከስር በእንግሊዘኛ ለአለም ሆቴል ሐረር
የሚል ስያሜና የቤት ስልክ ቁጥር ባለዉ ተመቶ የመጣ ለመሆኑ ግልጽ መረጃ
እያለ በግብር ከፋይ መለያ ቁጥር 0044926402 ተመዝግቦ ካለዉ ለአለም ሆቴል
በንግድ ፍቃዱ ባለቤት ደስታ አርአያ ሀጎስ ስም ፊርማና ክብ ማህተሙ ከላይ
ለአለም ሆቴል ከስር ደስታ አርአያ ባርና ሬስቶራንት የሚል ስያሜና የሞባይል
ስልክ ቁጥር ባለዉ ተመቶ የመጣ ነዉ ተብሎ የከባድ የዲሲፒሊን ቅጣት
ያለአግባብ የተወሰነበኝ ሰለሆነ ያቀረብኩት መረጃ በድጋሚ በትክክል
እንዲታይልኝ ነዉ፡፡
- አቶ ወንድማገኝ ላሽተዉ የድርጅት ምዝገባ ጡ3 ቅጽ ላይ አልተመዘገቡም
ለተባለዉ ግለሰቡ አገልግሎት ፈጽመዉ የስራ ዉል ያቋረጡት መስከረም አልጋ
ቤት የተባለዉ ድርጅት በሐረር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በ 8/4/2006ዓ .ም ከመመዝገቡ
በፊት በመሆኑ በምዝገባዉ ወቅት እየሰሩ ካሉት ሰራተኞች ጋር ጡ3 ቅጽ ላይ
ሊመዘገብ ያልቻለዉ ስለሆነም ክቡር ፍ/ቤቱ ቀደም ሲል ያቀረብኩት የመልስ
መልስ በዉሳኔዉ ላይ በመከላከያነት ሳይካተት ከባድ የዲሲፒሊን ቅጣት
ያለአግባብ የተወሰነብኝ ሰለሆነ አያይዤ ያቀረብኩት መረጃ በድጋሚ በትክክል
እንዲታይልኝ ነዉ፡፡
- የአቶ ወንድማገኝ ላሽተዉ የአበል መጠየቂያ ቅጽ ጡ2 ሞልቶ ያቀረበዉ ጠቅላላ
መጠሪያዉ ለአለም ሆቴል ተብሎ በሚጠራዉ ድረጅት በግብር ከፋይ መለያ
ቁጥር 0002117949 እና በድርጅት ምዝገባ ቁጥር 0611000725 ተመዝግቦ
ካለዉ መስከረም አልጋ ቤት መሆኑን በንግድ ፍቃዱ ባለቤት መስከረም በላይነህ
ስም ፊርማና ክብ ማህተሙ ከላይ በአማርኛ ከስር በእንግሊዘኛ ለአለም ሆቴል
ሐረር የሚል ስያሜና የቤት ስልክ ቁጥር ባለዉ ማህተም ተመቶ የመጣ እንጂ
በግብር ከፋይ ቁጥር 0044926402 እና በድርጅት ምዝገባ ቁጥር 0611001162
ተመዝግቦ ካለዉ ለአለም ሆቴል አለመሆኑን በንግድ ፍቃዱ ባለቤት ደስታ
አርአያ ሀጎስ ስም ፊርማና ክብ ማህተሙ ከላይ ለአለም ሆቴል ከስር ደስታ
አርአያ ባርና ሬስቶራነት የሚል ስያሜና የሞባይል ስልክ ቁጥር ባለዉ ማህተም
ተመቶ የመጣ ባለመሆኑ በግል ድርጅት ስራተኞች ጡረታ አዋጅ ቁጥር
715/2003 አንቀጽ 5 ቁጥር 1 ማንኛዉም የገል ድርጅት ወይም የግል ድርጅት
ሰራተኛ የምዝገባ ማስረጃ ተሟልቶ ሲቀርብ የማህበራዊ ዋስትና ቁጥር ይስጠዋል
በሚለዉ ድንጋጌ መስረት የተሰጠ መሆኑ እየታወቀ ከአዋጅ ድንጋጌ ዉጭ
በመልስ ሰጪ በተሰጠ የመቃወሚያ መልስ መልስ መሰረት ያለአግባብ
የተወሰነብኝ ከባድ የዲሲፒሊ ዉሳኔ በክቡር ፍ/ቤቱ በድጋሚ በትክክል
እንዲታይልኝ ነዉ፡፡
የምጠይቀው ዳኝነት
የተወሰነብኝ ከባደ የዲሲፒሊን ቅጣት ተብሎ የተወሰነብኝ ያቀረብኩት መረጃ
በትክክል ታይቶ ዉሳኔዉ እንዲነሳልኝ በአክብሮት ፍትህ እጠይቃለሁ፡፡
የስር ለፌደራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን አስተዳዳር ፍ/ቤት ከባድ የዲሲፒሊን
የቅጣት ውሳኔ ተብሎ የቀረበብኝ ሙሉ በሙሉ እንዲሻርልኝ ፍትህ
እጠይቃለሁ ፡፡
በስር ለፌደራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን አስተዳዳር ፍ/ቤት ፍርድ ቤት በመ.ቁ
............. በሆነው ላይ በቀን ........................ ዓ.ም በዋለው ችሎት የተሰጠው
ውሳኔ ግልባጭ............ (0...) ገፅ ፎቶ ኮፒ ከቅሬታዬ ጋር አቅርቢያለሁ ዋናው
በእጄ ይገኛል ፡፡
ይግባኙ የቀረበዉ በእዉነት መሆኑን በፍ/ሥ/ሥ ቁጥር 92 መሰረት
አረጋግጣለሁ፡፡

ይግባኝ ባይ ፊርማ

You might also like