You are on page 1of 54

በአማ ራ ው ሃ ስራዎች ኮንሰትራክሽን ድርጅትና በመ ሠረታዊ ሠራተኛ ማ ኅበ ሩ መ ካካል ለ 7 ኛ ጊዜ የተደረገ

ኅብረት ስም ም ነት

ታህሳስ 1/2012 ዓ.ም

ክፍል አንድ (1)


መ ግ ቢ ያ፡
ይህ የኅብ ረ ት ስም ምነት በአ ሠ ሪ ና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 መሠረት "አሠሪ" እየተባለ በሚ ጠ ራ
ው የአ ማ ራ የውሃ ሥራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት እና "የሠራተኛ ማኅበ ር " ተብሎ በሚ ጠ ራው የአ ማ ራ የውሃ
ሥራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት የሠራተኛ ማኅበር መካከል የተደረገ 7 ኛ ዙር የኅብ ረ ት ስም ም ነት ዛሬ ታህሳስ 1
ቀን 2012 ዓ.ም ተፈረመ፡፡

አንቀጽ አንድ (1)


የኅብረት ስም ም ነቱ ዓላማ
1.1. የድርጅቱንና የሠራተኛውን ደህንነትና ህልውና ለማ ስ ጠ በ ቅ ፣ ለማጠናከርና ለማሳደግ እንዲሁም ድርጅቱ
የተቋቋመ በ ት ን ዓላማ ግቡን እንዲመታ ለማድረግ፣

1|Page
1.2. አገሪቱ ከምትከተለው የኢኮኖሚ ፖሊሲ አንፃር በነፃ ገበያው ብቁ ተወዳዳሪ በመሆን የሠራተኛው ን የሥራ
ዋስትና በዘላቂነት እንዲከበር ማ ስቻል፡፡

1.3. የድርጅቱና የሠራተኛው መብቶችና ግዴታዎች እንዲታወቁ ለማድረግና እንዲሁም የሠራተኛ አስተዳደር
ተግባራት ለመፈፀም የሚ ጠ ቅሙ ደንቦችና መ መ ሪያዎችን ለማ ው ጣ ት፣

1.4. ሠራተኛው የድርጅቱን ሀብትና ንብረት እንደራ ሱ ንብረት ተገንዝቦ ተገቢውን እንክብካቤና ጥበቃ እንዲያደርግ
ለማ ድረግ፣

1.5. በሠራተኛው መካከል የሥራ ፍላጎት እንዲዳብር ለማድረግና እንዲሁም በድርጅቱና በሠራ ተ ኛ ማ ኅበ ሩ መ
ካከል የሥ ራ ግንኙነትን ለማ ጠ ናከር የድርጅቱ ሥ ራ በተሟ ላ ሁኔታ እየተከናወነ ም ርታማ ነቱ ከፍ እንዲል
አመ ቺ ሁኔታዎችን ለመ ፍ ጠ ር ነው፣

አንቀጽ ሁለት (2)

ትርጉም

የቃሉ አግባብ ሌላ ትርጉም ካልተሰጠው በስተቀር በዚህ የህብ ረ ት ስምምነት ውስጥ፡-

2.1. "አዋጅ" ማለት የአ ሠ ሪ ና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 ማለት ነው፡፡

2.2. "ድርጅት" ማ ለት የአማ ራ ው ሃ ሥ ራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት ነው፡፡

2.3. "ማ ኅበ ር " ማ ለት በአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 አንቀጽ 113 ንዑስ አንቀጽ 2.ሀ መ
ሠረት የተቋቋመ የአማ ራ ውሃ ሥ ራዎ ች ኮንስትራክሽን ድርጅት መ ሠረታዊ የሠራተኞች ማ ኅበ ር ነው፡፡

2.4. "ሠራተኛ" ማ ለት በአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 አንቀጽ 2 ንዑስ አንቀጽ 3 ላይ
የተሰጠውን ትርጉም ይይዛል፡፡

2.5. "የትርፍ ሰዓት ሥራ" ማለት በአዋጁና በዚህ የኀብረት ስምምነት ከተወሰነው መደበኛ የሥራ ሰዓት በላይ የሚሠራ
ሥራ የትርፍ ሰዓት ሥራ ነው፡፡

2.6. "የሥራ” ወይም "የደንብ ልብስ" ማለት አንድ ሠራተኛ ሥራውን በሚያከናውንበት ጊዜ እንደ ሥራው ፀባይ
ለሥራው ማከናወኛ ወይም ለሠራተኛው ደህንነትና ንጽህና እንዲያገለግል የሚሰጥ የተወሰነ ልብስ ጫማ ወይንም
ሌላ የመገልገያ መሣሪያ ነው፡፡

2.7. "የአደጋ መከላከያ መሣሪያ" ማለት የድርጅቱን ንብረትና ሠራተኛውን ከአደጋ ለመከላከል የሚሰጥ፣ የሚተከል
ወይም የሚቀመጥ የመከላከያ መሣሪያ ነው፡፡

2.8. “የስራ መሪ” ማለት በአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 አንቀጽ 10 እንደተደነገገው በሕግ ወይም
እንደ ድርጅቱ የስራ ፀባይ በአሰሪው የተሰጠ የውክልና ስልጣን መሰረት የስራ አመራር ፖሊሲዎችን የማውጣትና

2|Page
የማስፈጸም ወይም ሰራተኛን የመቅጠር፣ የማዛወር፣ የማገድ፣ የማሰናበት፣ የመመደብ ተግባሮችን የመወሰን
ስልጣን ያለውግለሰብ ሲሆን፣ እነዚህን የስራ አመራር ጉዳዮዎች አስመልክቶ የአሰሪውን ጥቅም ለመጠበቅ አሰሪው
ሊወስደው ስለሚገባው እርምጃ በማንም ሳይመራ የራሱን የውሳኔ ሀሳብ የሚያቀርብ የህግ አገልግሎት ሀላፊውን
ይጨምራል፤

2.9. "ቅሬታ" ማለት በዚህ ስምምነት ወይም የሕግ ትርጉም ወይም አፈፃፀም ችግር ምክንያት በድርጅቱና
በሠራተኛው ወይም በድርጅቱና በማኅበሩ መካከል በሚፈጠረው አለመግባባት ጉዳይ ለሚመለከተው አካል
የሚቀርብ አቤቱታ ማለት ነው፡፡

2.10. "የሠራተኛ ተጠሪ" ማለት የማኅበሩ የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴና በቅሬታ አቀራረብ ሥነ-ሥርዓት ውስጥ
ለተጠቀሰው በማንኛውንም ደረጃ ሠራተኛውን በመወከል ጉዳዩን ለመከታተል ወይም ከሠራተኛው ጋር
ለመመካከር እንዲችሉ ይኸ ኮሚቴ የሚወክለው ሠራተኛ ወይም ሌላ ሕጋዊ ውክልና ያለው ነው፡፡

2.11. "ደመወዝ" ማለት በአዋጅ ቁጥር 1156/2011 አንቀጽ 53 ንዑስ አንቀጽ 1 የተመለከተው ትርጉም ይኖረዋል፡፡

2.12."የአየር ፀባይ አበል" ማለት አንድ ሠራተኛ የተመደበበትና ለመስክ ስራ የሄደበት የሥራ ቦታ የአየር ፀባይ አስቸጋሪ
በመሆኑ ምክንያት በመንግሥት ተለይተው በሚታወቁ ሥፍራዎች ከሚከፈለው የቀን ውሎ አበል ተመን ላይ
በተጨማሪ የሚከፈል ነው፡፡

2.13."ውሎ አበል" ማለት አንድ ሠራተኛ ለሥራ ጉዳይ ከምድብ የሥራ ቦታው የውሎ አበል በሚያስከፍል ሌላ ቦታ ስራ
እንዲሰራ ታዝዞ በሚሰራበት ወቅት ወይም ከስራ ባህሪው አኳያ ታይቶ በልዩ ሁኔታ በሚወሰነው መሰረት
በእየለቱ ለቁርስ፣ ለምሣ፣ ለእራትና ለመኝታ የሚከፈለው ክፍያ ነው፡፡
2.14.“ቤተሰብ” ማለት የሰራተኛው ህጋዊ ባል/ሚስት፣ ልጅ፣ እናት /አባት፣ ወንድምና እህት፣ አክስት አጎት፣ አያት፣
እንዲሁም እስከ ተመሳሳይ ደረጃ የጋብቻ ዝምድና ማለት ነው፡፡

2.15."የደረጃ ዕድገት" ማለት አንድን ሠራተኛ ከነበረበት የሥራ ደረጃና ደመወዝ ወደ ተሻለ የሥራ ደረጃና ደመወዝ ከፍ
አድርጎ በውድድር መመደብ ማለት ነው፡፡

2.16. የሥራ መደብ" ማለት አዋጅ ቁጥር 1156/2011 አንቀጽ 9 እና 10 በተገለጸው መሠረት በተደረገ የሥራ ውል
ሠራተኛ የተቀጠረበት፣ የተመደበበት ወይም የሚቀጠርበት የሥራ መደብ ነው፡፡

2.17."የዓመት ዕረፍት ፈቃድ" ማለት አንድ ሠራተኛ በዓመት ውስጥ የተወሰነ ቀናት ከምድብ ሥራው ቀሪ ለመሆን
የሚያስችለውና ከደመወዝ ጋር ለዕረፍት የሚሰጥ ፈቃድ ነው፡፡

2.18."ተዋዋዮች" ማለት በዚህ የኅብረት ስምምነት ላይ የተደራደሩትን የድርጅቱና የማኅበሩ ተወካዮች ማለት ነው፡፡

2.19."የዲስፕሊን ቅጣት" ማለት አንድ ሠራተኛ የኅብረት ስምምነቱን የአዋጁንና የድርጅቱን ደንብና መመሪያ
በመተላለፉ ለፈጸመው ጥፋት የሚወሰድበት ቅጣት ነው፡፡

3|Page
2.20."የኅብረት ውይይት" ማለት በድርጅቱና በማኅበሩ ተወካዮች መካከል የጋራ ስምምነት ላይ ለመድረስ የሚደረግ
ውይይት ነው፡፡

2.21.“የአስተዳደር ኮሚቴዎች" ማለት ለቅጥር፣ የዝውውር፣ ለደረጃ ዕድገት፣ ለትምህርት፣ ለዲስፕሊንና ለሥራ
ክንውን ግምገማ መታየት ያለባቸውን አስተዳደር ነክ ጉዳዮችን ተመልክተው የውሳኔ ሀሣብ ለማቅረብ
ከድርጅቱና ከሠራተኛው ወገን ተመርጠው የሚሠሩ የተለያዩ ኮሚቴዎች ናቸው፡፡

2.22.“ዝውውር" ማለት ከአንድ የስራ መደብ ወደ ሌላ ይሰሩበታል ተብሎ በሚታመንበት የስራ መደብ ወይም ከአንድ
የሥራ ቦታ ወደ ሌላ የሥራ ቦታ ተመሳሳይ የደመወዝ ደረጃ ከፍታ ባላቸው እንዲሁም ተመሳሳይ የት/ት
ዝግጅትና የስራ ልምድ በሚጠይቁ የሥራ መደቦች ላይ የሚፈፀም ጊዜያዊ ወይም ቋሚ ዝውውር ነው፡፡

2.23."ትምህርት" ማለት ለድርጅቱ የሥራ ዕድገት በማሰብና ሠራተኛው ችሎታውንና ዕውቀቱን በማሻሻል የተሟላና
የተሻለ አገልግሎት ለመስጠት እንዲችል ሲባል በሀገር ውስጥም ሆነ ከሀገር ውጭ የሚሰጥ ነው፡፡

2.24."የግል ልዩ ክሊኒክ" ማለት ከጤና ጥበቃ ሚኒስተር ወይም ቢሮ በተሰጠ ፈቃድ ልዩ የህክምና አገልግሎት የሚሰጥ
የጤና ድርጅት ነው፡፡

አንቀጽ ሦስት (3)

በኅብረት ስምምነቱና አግባብ ባላቸው ሕጐች መካከል ያለው ግንኙነት

3.1. ስምምነቱ በአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 እንዲሁም አግባብነት ባላቸው መመሪያዎች

በድርጅቱ ተጨባጭ ሁኔታዎች ላይ የተመሠረተ እንደመሆኑ በተዋዋዮች ላይ እንደ ሕግ ተፈፃሚ ይሆናል፡፡

3.2. ህብረት ስምምነቱ መንግስት ካወጣቸው ሕጐች፣ አዋጆች፣ ደንቦችና መመሪያዎች እንዲሁም ወደፊት

ከሚወጡት ሕጎች፣ አዋጆች፣ ደንቦችና መመሪያዎች ጋር በሚጣጣም ሁኔታ እየተተረጎመ ተግባራዊ ይሆናል፡፡

3.3. በዚህ የኅብረት ስምምነት ያልተጠቃለሉ ጉዳዮች በአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 እና

አሠሪና ሠራተኛን በተመለከተ የሚወጡ የመንግስት ሕጎችና ደንቦች እንዲሁም በድርጅቱ የሚወጡ

መመሪያዎች የሚሸፈኑ ይሆናሉ፡፡

አንቀጽ አራት (4)

4|Page
የኅብረት ስምምነቱ ወሰን

4.1. ይህ የኅብረት ስምምነት በድርጅቱ ሰራተኞች ላይ ተፈፃነት ያለው ሲሆን የስራ መሪዎችንና በቀን ሂሳብ ተከፋይ

የሆኑ ሰራተኞችን አይመለከትም፡፡

4.2. በዚህ የኅብረት ስምምነት ውስጥ በተባዕት ፆታ የተጠቀሰው ሁሉ አንስታይ ፆታንም ይመለከታል፡፡

4.3. የዚህ የኅብረት ስምምነት ተፈፃሚነት ወሰን ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 አንቀጽ 134 መሠረት

ተፈፃሚ ይሆናል፡፡

ክፍል ሁለት
የድርጅቱ፣ የሠራተኛ ማኀበሩና የሠራተኛው መብትና ግዴታዎች

አንቀጽ አምስት (5)


የድርጅቱ መብትና ግዴታዎች

5.1. የድርጅቱ መብቶች

ድርጅቱ ይህንን የኀብረት ስምምነትና አዋጅ ቁጥር በ 1156/2011 ላይ የተደነገጉትን ሳይቃረን፡-

5.1.1. በሥራ ውል መሠረት የሠራተኛውን የሥራ እንቅስቃሴና ክንውን የመምራት፣ የማስተዳደርና የመቆጣጠር፣

5.1.2. የድርጅቱን የሥራ ፕሮግራም በማዘጋጀት የአሠራር ስልቶችን፣ መመሪያዎችን፣ ደንቦችን የማቀድና
የመፈፀም፣ የማስፈፀም፣

5.1.3. ሠራተኛን የመቅጠር፣ በሥራ ደረጃ የማሣደግ፣ ከሥራ ደረጃ ዝቅ የማድረግ፣ የማዛወር፣ የዲስፕሊን እርምጃ
የመውሰድ፣ የማገድ፣ የማሰናበት፣

5.1.4. የሥራ ደረጃዎችን ለማውጣት፣ ለማሻሻል፣ ለመለወጥ፣ ለመሠረዝ እንዲሁም የደመወዝ ተመን ወይም ሌላ
ክፍያ ለመወሰን መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

5|Page
5.2. የድርጅቱ ግዴታዎች

5.2.1 ስለ አሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ የወጡትን አዋጆች፣ ደንቦችና መመሪያዎችን ይህንን የኀብረት ስምምነትና
በሁለቱም ወገኖች ስምምነት ወደፊት የሚወጡትን ማሻሻያዎች ያከብራል፣ ተግባራዊም ያደርጋል፡፡

5.2.2 በአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 አንቀጽ 12 እና 92 የተጠቀሱትን ግዴታዎች በሙሉ
ያከብራል ይፈጽማል፡፡

5.2.3 በሠራተኛውና በድርጅቱ መሀል የተለየ ስምምነት ካልተደረገ ወይም ከአቅም በላይ የሆነ ችግር ካልተፈጠረ
በስተቀር ለሥራ የሚያስፈልጉትን መሣሪያዎችና ሥራው በሚጠይቀው ቦታና ጊዜ ያቀርባል፡፡

5.2.4 ድርጅቱ እያንዳንዱ ሠራተኛ የሚሠራውን ሥራና የኃላፊነቱንም ወሰን የሚያሳይ የሥራ መመሪያ ዝርዝርና
የሥራ መደቡን ሁኔታ አዘጋጅቶ ለሠራተኛው ይሰጣል አፈጻጸሙንም ይከታተላል ከሥራ መደቡ ጋር ግንኙነት
የሌለው ተመሳሳይ ያልሆኑ ሥራ ላይ መድቦ ማሠራት አይችልም፡፡ ሆኖም ሠራተኛው ከተስማማ መድቦ
ሊያሰራው ይችላል፡፡ በተጨማሪም በአስተዳደር ኮሚቴዎች እንዲሳተፍ ሊያደርግ ይችላል፡፡

5.2.5 ድርጅቱ የሠራተኛውን ደመወዝና ሌሎች ጥቅማጥቅሞች ለሠራተኛው ወይም ለሕጋዊ ወኪሉ የክፍያ ቀን
ልዩነት ሣያደርግ በወቅቱ ይከፍላል፡፡

5.2.6 ለእያንዳንዱ ሠራተኛ የሥራ አፈፃፀም መመዘኛ፣ የተቀጠረበትን ቀን፣ የደመወዙን ልክ፣ የደረጃና የደመወዝ
ዕድገት፣ በየጊዜው የወሰዳቸውን የፈቃዶች ልክ፣ የጤንነቱን፣ የትምህርቱን፣ የተሣትፎ፣ የምስጋና፣
የዲስፕሊን እርምጃዎችንና የመሳሰሉትን ሁኔታዎች መዝግቦ ይይዛል፡፡

5.2.7 ድርጅቱ ከሠራተኛው የሚሰበሰበው የማኅበሩን ወርሃዊ መዋጮ ከሠራተኛው ደመወዝ በመቀነስ በማኅበሩ
ስም በተከፈተ የባንክ ሂሳብ ገቢ ያደርጋል፣ ማኅበሩም ገቢ ለተደረገለት ገንዘብ ሕጋዊ ደረሰኝ ይሰጣል፡፡
እንዲሁም ከድርጅቱ ጋር በመነጋገር ማህበሩ ለሚሰጣቸው ማህበራዊ አገልግሎቶች እንደ አስፈላጊነቱ
ከሠራተኛው ደመወዝ እየቆረጠ ለማህበሩ ገቢ ያደርጋል፡፡

5.2.8 ድርጅቱ ለማኅበሩ አገልግሎት የሚውል ቢሮና አስፈላጊ የሆኑ ቋሚ የጽ/ቤት ዕቃዎችን ያሟላል፡፡

5.2.9 ከሠራተኛ ማኅበሩ ጋር በመተባበር ሠራተኞች ድርጅቱ የሚመራባቸውን ህጎች የኀብረት ስምምነቱን
አንቀፆች ትርጉምና አፈፃፀም በሚገባ እንዲረዱ አስፈላጊውን ሁሉ ያደርጋል፡፡

5.2.10 የሠራተኛውን ጤንነት፣ ደህንነትና ሞራሉን ለመጠበቅ በየሥራ አካባቢ ተገቢውን ጥንቃቄ ያደርጋል፣
ከማኅበሩ ጋር በመመካከርም አስፈላጊ የሆኑ የመፍትሄ እርምጃዎችን ይወስዳል፡፡

6|Page
5.2.11 በድርጅቱ ውስጥ አስተዳደር እንዳይዛባ የስራ ጊዜ በክርክር እንዳይባክን፣ የአስተዳደር ፍትሕ እንዲሰፍን፣
ሠራተኛው መላ ኃይሉን፣ ችሎታውን እና ሙያውን በሥራ ላይ እንዲያውል የሚችለውን ሁሉ ያደርጋል፣

5.2.12 የሥራው ፀባይ በሚጠይቀው መሠረት ለሠራተኛው የአደጋ መከላከያ መሣሪያዎችንና የሥራ ወይም የደንብ
ልብስ ይሰጣል፤

5.2.13 ለሥራ አስፈላጊ የሆኑ በአንድ የበጀት ዓመት የሚሰጠው የሥራ ወይም የደንብ ልብሶች ቁጥር ከአንድ በላይ
ከሆነ፡-

ሀ/ የመጀመሪያ የበጀት ዓመት በገባ በ 3 ኛው ወር ማለትም በመስከረም ወር ላይ፣

ለ/ ሁለተኛውን ደግሞ በበጀት ዓመቱ አጋማሽ የመጀመሪያው ወር ማለትም በጥር ወር ላይ ለሠራተኛው


አድሎ ያጠናቅቃል፤

5.2.14 አዳዲስ የሥራ ቦታዎች ሲከፈቱ ለሠራተኛው ደህንነት አስፈላጊና መሠረታዊ የሆኑ እንደ ጤና፣ የአደጋ
መከላከያ እና እንደአስፈላጊነቱ የካምፕ አገልግሎት እየታየ በቅድሚያ እንዲሟሉ ድርጅቱ ዝግጅትና ጥረት
ያደርጋል፤

5.2.15 ድርጅቱ የዓመቱን የሥራ አፈፃፀም ሪፖርትና የሥራ መግለጫዎችና የተለያዩ ሠነዶችን እንዲሁም
የሚቀጥለውን የበጀት ዘመን የሥራ ዕቅድ ለማኀበሩ እንዲደርሰው ያደርጋል፣ እንዲሁም ለማኀበሩ ሥራ
አስፈላጊ የሆኑ ሰነዶችን ማኀበሩ ሲጠይቅ ይሰጣል፤

5.2.16 የድርጅቱ አቅም ሲፈቅድ ሠራተኞችን በሀገር ውስጥና በውጭ የትምህርት ተቋማት የድርጅቱን የወደፊት
ዕቅድና የሥልጠና ፍላጎት መሠረት በማድረግ የሥራ አመራር ቦርድ ሲፈቅድ እንዲሠለጥኑ ያደርጋል፤

5.2.17 በዚህ የኅብረት ስምምነት መሠረት የሠራተኛውን የደረጃ ዕድገትና የደመወዝ ጭማሪ በየጊዜው እየተከታተለ
ይጠብቃል፤ይፈጽማል፤

5.2.18 ለሠራተኛው የሚገባውን ሕጋዊ መብቶችና ጥቅሞች ሁሉ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ የመጫን ወይም
የመግታት አሠራር አያደርግም አይፈጽምም፤

5.2.19 ለእያንዳንዱ ሠራተኛ ውጤት ተኮር የዕቅድ አፈፃፀም ምዘና በአንቀጽ 32.2 እንዲሁም በአንቀጽ 32.3 መሠረት
መፈፀሙን ያረጋግጣል፡፡

5.2.20 ሠራተኛው በዓመት ሁለት ጊዜ የግል ማህደሩን ለማየት በጽሁፍ ሲጠይቅ ለሰው ኃይል አስተዳደርና ሀላፊ
ወይም እርሱ የሚወክለው ባለሙያ ባለበት እንዲያይ ድርጅቱ ይፈቅዳል፡፡

7|Page
5.2.21 በማንኛውም ምክንያት የሥራ ውሉ ለተቋረጠበት ሠራተኛ የርክክብ ማስረጃ ሲያቀርብ ድርጅቱ ሥራውን፣
ሙያውን፣ የሠራበት ዘመን፣ ደመወዙን የተደረገውን ሕጋዊ ተቀናናሽ ገልፆ ፎቶግራፍ ያለበት የምስክር ወረቀት
ይሰጣል፡፡

5.2.22 ድርጅቱ ለሠራተኛው አገልግሎት የሚውል የመዝናኛ ክበብ፣ የስፖርት ቦታዎች፣ የትራንስፖርት አገልግሎትና
የመሣሰሉትን ከማኀበሩ ጋር በመመካከር አመቺና አማካይ በሆኑ ቦታዎች ያቋቁማል፡፡

5.2.23 በማንኛውም ሠራተኛ ላይ በዚህ የኀብረት ስምምነት የሥነ ምግባር ደንብ በዝርዝርና በግልጽ ከተደነገጉት
የቅጣት ደንቦች በላይ ድርጅቱ ቅጣት አይወስንም፤

5.2.24 አንድ ሠራተኛ በአንድ የሥራ መደብ ወይም ቦታ ሲመደብ ወይም ሲዛወር ለተመደበበት ሥራ አስፈላጊ
የሆኑትን የሥራ መሣሪያዎች፣ ተንቀሳቃሽ ንብረቶች፣ ገንዘብ፣ ሰነዶች እና የቢሮ ዕቃዎች በድርጅቱ ደንብ
መሠረት በመተማመኛ ሰነድ ያስረክበዋል፤

5.2.25 ድርጅቱ ለድርጅቱ ሰራተኞች በመግቢያና በመውጫ ሰአት የትራንስፖርት አገልግሎት ያመቻቻል፡፡ ሰርቪስ
መኪናውም ሰራተኞችን የሚያሳፍርበት ቦታ በድርጅቱ ይወሰናል፡፡ ነገር ግን በስራ ግዳጅ እና በተለያዩ
ምክንያቶች ድርጅቱ የትራንስፖርት አገልግሎት ማቅረብ ካልቻለ ሰራተኛው በራሱ ትራንስፖርት ሥራ
መግባት ይኖርበታል፡፡ ነገር ግን ድርጅቱ ቀድሞ ለሠራተኛው ማሳዎቅ አለበት፡፡

5.2.26 ከሥራ ጋር ግንኙነት ባለው በሠራተኛ ላይ ለሚደርስ በሐኪም ለተረጋገጠ አደጋ የመድን ዋስትና ይገባል
እንዲሁም በአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 አንቀጽ 98 መሠረት በሥራ ምክንያት
ለሚመጡ በሽታዎች የመድን ዋስትና ይገባል፡፡

5.2.27 ሠራተኛ ሲቀጠር፣ ሲመደብ፣ የደረጃ ዕድገት ሲያገኝ የዲስፕሊን እርምጃ ሲወሰድበት የሥራ ምስጋናና
የተሣትፎ ደብዳቤ ሲሰጠው ለትምህርት ሲሄድ፣ ሲዛወር፣ ሲሰናበትና ሲሞት ድርጅቱ ለማኅበሩ ያሣውቃል፤

5.2.28 አዳዲስ የሥራ መደቦች ሲከፈቱ ድርጅቱ ለማኅበሩ ያሣውቃል፤እንዲሁም ሠራተኛውን የሚመለከቱ
መመሪያዎች ሲዘጋጁ የመኅበሩ ተወካዮች እንዲሳተፉ ይደረጋል፡፡

5.2.29 ይህ የኅብረት ስምምነት ድርድር ተፈፅሞ በሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ከፀደቀ በኋላ በሦስት ወር ጊዜ
ውስጥ ድርጅቱ የስምምነቱን ኮፒ በማተሚያ ቤት አሳትሞ ለእያንዳንዱ ነባርና አዲስ ተቀጣሪ ሠራተኛ
እንዲደርስ ያደርጋል፡፡

5.2.30 ድርጅቱ በሠራተኛው ሕይወትና ጤንነት ላይ አደጋ ሊያስከትል በሚችል ሥራ ላይ አያሰማራም፤

5.2.31 ድርጅቱ የበጀት አመቱን ሂሳብ በመዝጋት በውጪ ኦዲተሮች አስመርምሮ ውጤቱን ለማህበሩ
የሚያሳውቀው ከሐምሌ 1 ቀን ጀምሮ ባለው 6/ስድስት/ ወር ጊዜ ውስጥ ይሆናል፡፡

8|Page
5.2.32 የሠራተኛውን የቢኤስሲ እቅድና የአፈጻጸም ውጤት በወቅቱ ሞልቶ በማያቀርብ የቅርብ የስራ መሪ ላይ
አስተዳደራዊ እርምጃ የመውሰድ ግዴታ አለበት፡፡

አንቀጽ ስድስት (6)


ማኅበሩን ስለማወቅ፣ የማኅበሩ መብትና ገዴታዎች

6.1. የማኅበሩ መብት፣

6.1.1. በዚህ የኅብረት ስምምነት ውስጥ ስለተመለከቱትም ሆነ ወይም ከስምምነቱ ውጪ ሊያጋጥሙ ስለሚችሉ
ማናቸውም የሥራ ሁኔታዎች ሠራተኛውን ወክሎ ከድርጅቱ ጋር የሚነጋገር ማኅበሩ መሆኑን ድርጅቱ
ያውቃል፤

6.1.2. በዚህ የኅብረት ስምምነት መሠረት በሚቋቋሙ ኮሚቴዎች ውስጥ ሠራተኛውን የሚወክሉ አባላት
ተጠሪነታቸው ለማኀበሩ መሆኑንና አባላቱን በመሰየም አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ውክልናቸውን የመሰረዝና
በሌሎች አባላት የመተካት መብት የማኀበሩ ነው፤

6.1.3. ማንኛውንም የሥራ ሁኔታዎች በተመለከተ የድርጅቱን ሠራተኞች በመወከል የኅብረት ስምምነት
መደራደር፤

6.1.4. በየጊዜው በሚደረገው የድርጅቱና የማኅበሩ የጋራ ስብሰባ ላይ ማኅበሩ ችግር ያለባቸውን የሥራ ሁኔታዎችና
አፈፃፀሞች የማቅረብ፣ እንዲስተካከሉ የመጠየቅና በጋራ መፍትሄዎችን በመፈለግ ተግባራዊ የማድረግ፤

6.1.5. አስፈላጊ በሆነበት ጊዜ ማኅበሩ በሕጋዊ መንገድ ጠቅላላ ጉባኤ የመጥራት ወይም የመሰብሰብ መብት ያለው
መሆኑንና ስብሰባም ሲጠራ በቅድሚያ ድርጅቱን አሳውቆና አስፈቅዶ ነው፤

6.1.6. በኅብረት ስምምነቱ ያልተጠቀሱ ነገር ግን ሠራተኛውን የሚመለከቱ ጉዳዮች ቢኖሩ ወይም ቢከሠቱ ማኅበሩ
ለድርጅቱ በጽሁፍ የማሳወቅ፤

6.1.7. ማኅበሩ በድርጅቱ የሥራ ዕቅድ አወጣጥ እና የአፈጻጸም ግምገማ ላይ ይሣተፋል፣ ለተግባራዊነቱና ለአፈፃፀሙ
የበኩሉን ድርሻ ያበረክታል፤
6.1.8. ማኅበሩ ከቅጥር በስተቀር የማህበሩ አባል ላልሆኑ የድርጅቱ ሠራተኞች በማነኛውም ጉዳይ ላይ ቀርቦ ከድርጅቱ
ጋር አይደራደርም፡፡

9|Page
6.2. የሠራተኛ ማኅበሩ ግዴታዎች

6.2.1. ሠራተኞች የሚጠቀሙባቸውን የምርት መሣሪያዎችና ንብረቶች በቁጠባና በእንክብካቤ እንዲያዙ


የድርጅቱን የሥራ ውጤት በብዛትም ሆነ በጥራት እንዲያዳብርና ምዝበራና ብክነትን እንዲወገዱ ማኅበሩ
ያስተምራል፣ ያበረታታል፣ ያግዛል፤

6.2.2 የድርጅቱ ምርታማነት ከፍ እያለ እንዲሄድ የሠራተኛው የፈጠራ ችሎታ እንዲዳብር ያነቃቃል፣ ያበረታታል፣
ይከታተላል እንዲሁም በተለያዩ የሥራ ደረጃ ላይ የሚገኙ ሠራተኞች የተመደቡበትን ተግባርና ኃላፊነት
በጥራትና በታማኝነት እንዲወጡ ያግዛል፤

6.2.3. ማኅበሩ ሠራተኛውን የኅብረት ስምምነት አንቀፆች ትርጉምና አፈፃፀም፣ በመንግስትና በድርጅቱ የሚወጡ
ሕጎችን፣ ደንቦችንና መመሪያዎችን በሚገባ እንዲረዳና ጠንካራ የሥራ ዲሲፕሊን እንዲኖረው አስፈላጊውን
ሁሉ ያደርጋል፤ እንዲሁም ለኢንዱስትሪ ሰላም መስፈን ሲባል በቅን መንፈስ ለችግሮች መፍትሄ የመሻት
ግዴታ አለበት፡፡

አንቀጽ ሰባት (7)


የሠራተኛው መብትና ግዴታ
7.1. የሠራተኛው ግዴታ

7.1.1. በሥራ ውሉ ላይ የተመለከተውንና የተመደበበትን የሥራ መደብ ተግባርና ኃላፊነት ሥራ እራሱ የመሥራት፤

7.1.2. ይህን የኅብረት ስምምነት፣ አዋጁንና የድርጅቱን መመሪዎች በማይቃረን በሥራ ውሉና በሥራ ደንቡ
መሠረት በድርጅቱ የሚሰጠውን ትዕዛዝ ይፈጽማል፤

7.1.3. ለተመደበበት ሥራ በቅን መንፈስ ዕውቀቱንና ችሎታውን ያበረክታል፣ የድርጅቱን የሥራ ውጤት ለማሣደግ
በሚደረገው ጥረት ሙሉ የሥራ ኃይሉን በተግባር ያውላል፤

7.1.4. ማንኛውም ሠራተኛ በተመደበበት ሥራ ኃላፊነት በተሰጠው የሥልጣን ክልል ይኸን የኅብረት ስምምነት እና
አግባብ ያላቸው አዋጆችና መመሪያዎችን ተግባራዊ ያደርጋል፤

7.1.5. ሠራተኛው ከድርጅቱ በኃላፈነት የተረከባቸውን ሠነዶች ዕቃዎችና መሣሪያዎችን ወይም ሌሎች
ንብረቶችን ይንከባከባል፣ ይጠብቃል፣ ሥራው ሲፈፀም መመለስ የሚገባውን መልሶ ለድርጅቱ ያስረክባል፣
ከአቅም በላይ መሆኑ ካልተረጋገጠ በስተቀር በንብረቱ ላይ ላደረሰው ጉዳትም ሆነ ጉድለት በሕግ ወይም
በማስረጃ ሲረጋገጥ ተጠያቂ ይሆናል፤

10 | P a g e
7.1.6. ለሥራ ብቁ በሆነ የአዕምሮና የአካል አቋም ማለትም ከስካርና ጫትን ጨምሮ ከአደገኛ ዕፅ ሱስ ነጻ ሆኖ ዘወትር
በሥራ ሰዓት በሥራ ላይ ይገኛል፤
7.1.7. በሠራተኛው ላይ ፍርሃት፣ ጭንቀትና የመንፈስ መሸበርን የሚያሣድሩ፣ የሥራ መንፈስና ምርታማነትን
የሚፃረሩ ድርጊቶችን በሠራተኛው ውስጥ አያስፋፋም፤

7.1.8. በራሱ ሕይወትና ጤንነት ላይ አደጋን በሚያስከትል አኳኋን በሥራ ቦታ በሕይወትና በንብረት ላይ አደጋ ሲደርስ
ወይም አስጊ ሁኔታ ሲፈጠር አደጋውን ለመከላከል ተገቢውን እርዳታ ያደርጋል፤

7.1.9. እራሱንም ሆነ ሌሎች የሥራ ጓደኞቹን ለአደጋ የሚያጋልጥ እንዲሁም የድርጅቱን ጥቅም የሚነካ ወይም የሚጎዳ
ማናቸውንም ተግባር በማወቅም ሆነ በቸልተኝነት አይፈጽምም፤

7.1.10. ከድርጅቱ በሰነድ የወሰደውን ገንዘብ በሕጋዊ መንገድ የተጠቀመበትን በሕጋዊ የወጪ ማስረጃዎች በድርጅቱ
ያወራርዳል፣ በሥራው ያልተጠቀመበትንም ገንዘብ በድርጅቱ የፋይናንስ መመሪያ መሠረት ተመላሽ ያደርጋል፤

7.1.11. የሥራ ውሉ ተቋርጦ ከድርጅቱ ሲሰናበት በእጁ የሚገኘውን የድርጅቱን ንብረት ወይም ገንዘብ በሙሉ ያስረክባል
ወይም ገቢ ያደርጋል እንዲሁም ዕዳ ካለበት ድርጅቱ ለሰራተኛው የሚከፍለው ገንዘብ ካለ ዕዳውን ሙሉ
ለሙሉ ቀንሶ ማስቀረት ይችላል፡፡

7.1.12. ሠራተኛው በኦዲት የተረጋገጠበት ዕዳ ሲኖርበትና ከደመወዙ መቆረጥ ሲኖርበት ድርጅቱ በየወሩ ከሰራተኛው
ደመወዙ ላይ 1/3 ኛ እየቆረጠ ያስቀራል፡፡ ሠራተኛውም የመክፈል ግዴታ አለበት፡፡

7.1.13. ከድርጅቱ ካልተፈቀደለት በስተቀር የድርጅቱን ገንዘብ፣ ሰነድና ንብረት ለግል ጥቅሙ አያውልም፣ ሌላም ለግሉ
እንዲጠቀምበት አሳልፎ አይሰጥም፤

7.1.14 በሥራው ምክንያት የማይገባውን ጥቅም ለማግኘት አይሞክርም፣ ማማለጃ ወይም ጉቦ አይሰጥም ወይም
አይቀበልም፡፡

7.1.15. ማንኛውም ሠራተኛ የትርፍ ሰዓት ሥራ እንዲሠራ አይገደድም፣ ሆኖም ድርጅቱ አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው
ሠራተኛውን በአሠሪና ሠራተኛ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 አንቀጽ 67 ንዑስ አንቀጽ 1 መሠረት ድርጅቱ
ሲያዝዘው ይሠራል፤

7.1.16. በመረጃ የሚደገፍ ከአቅም በላይ የሆነ ችግር ካልገጠመው በስተቀር ሠራተኛው አስቀድሞ ፈቃድ ሳያገኝ
ከመደበኛ ሥራው አይቀርም፤

7.1.17.የአዋጅ ቁጥር 1156/2011 አንቀጽ 13/2፣ 93 እና 94 ድንጋጌዎችን የኅብረት ስምምነትን የሥራ ደንብንና
በሕግ መሠረት የሚተላለፉ መመሪያዎችንና ትዕዛዞችን የማክበር ግዴታ አለበት፡፡

11 | P a g e
7.2. የሠራተኛው መብት፡-

7.2.1. የሠራተኛ ማኅበሩ አባል የመሆን፣ የማኅበሩን መዋጮ የመክፈል፣ በማኅበሩ አመራር የመምረጥና
የመመረጥ እንዲሁም በማኅበሩ የመወከልና በማኅበሩ ሲታዘዝም ማኅበሩን የመወከል፤

7.2.2. አግባብ ባለው ፍ/ቤት ዘንድ በድርጅቱ ላይ ቅሬታ የማቅረብ፣ ድርጅቱን የመክሰስና ለመብቱ የመከራከር፤

7.2.3. የሠራተኛው መብት፣ በመንግሥት፣ በፍርድ ቤት ትዕዛዝ ወይም በዚህ ኅብረት ስምምነት በሌላ አኳኋን
የሚከለከልበት ምክንያት እስከሌለ ድረስ ማናቸውም ሠራተኛ በዚህ ስምምነት ውስጥ የተጠቀሱትን
መብቶችና ጥቅሞች በሙሉ የማግኘት፤

7.2.4. የራሱን መብት የሚቃረን ድርጊት ባጋጠመ ጊዜ በቅሬታ አቀራረብ ሥነ-ሥርዓት መሠረት
ለሚመለከተው የሥራ ኃላፊ ጉዳዩን የማቅረብና የመከራከር፤

7.2.5. ሠራተኞች ሲያገቡ፣ ሕጋዊ ልጆቻቸውን ሲድሩ የድርጅቱን የመዝናኛ አዳራሽ በነፃ ይጠቀማሉ፤ ሆኖም
ስለሌሎች ጉዳዮች ድርጅቱና ማኅበሩ በጋራ በሚያወጡት መመሪያ መሠረት ይፈጸማል፤

7.2.6. ከቤተሰቦቻቸው ተለይተው በየሥራ ቦታው የሚገኙ ሠራተኞች ከባድ አደጋና አስጊ ሕመም
ሲያጋጥማቸው ለቤተሰቦቻቸው በድርጅቱ ያሉትን የመገናኛ ዘዴዎች ተጠቅመው ያሳውቃሉ፤

አንቀጽ ስምንት (8)


ማህበሩ በድርጅቱ አስተዳደር ጉዳዮች ላይ ወክሎ ተካፋይ ስለመሆን

8.1. በዚህ የኅብረት ስምምነት በድርጅቱ አስተዳደርና በሠራተኛው መካከል የሰመረ ግንኙነት እንዲኖር ለማድረግ
የሠራተኛው ዕውቀትና ችሎታ ተገቢውን ሥፍራ አግኝቶ ዓላማው በይበልጥ ውጤታማ እንዲሆንና
የሠራተኛው ደህንነት እንዲጠበቅ ማኀበሩ በድርጅቱ አስተዳደር ውስጥ ከዚህ በታች በተመለከቱት ኮሚቴዎች
ውስጥ ይሣተፋል፤

ሀ/ የትምህርትና ሥልጠና ኮሚቴ


ለ/ የቅጥርና የደረጃ ዕድገት ኮሚቴ
ሐ/ የዲሲፕሊን ኮሚቴ
መ/ የሙያና ደህንነት ኮሚቴ
ሠ/ የስፖርት ኮሚቴ

8.2. እንደአስፈላጊነቱ ሌሎች ሠራተኛው እንዲሣተፍባቸው በሚያስፈልጉ ኮሚቴዎች ውስጥ ይሣተፋል፤

8.3. ከላይ የተመለከቱት ኮሚቴዎች በኅብረት ስምምነቱና በድርጅቱ አስተዳደራዊ ደንብና መመሪያ መሠረት
ሥራቸውን ያከናውናሉ፤

12 | P a g e
8.4. በአንቀጽ 8.1 ለተጠቀሱት ለእያንዳንዱ ኮሚቴ ማኅበሩን የሚወክሉት ቢያንስ 2 (ሁለት) አባላት ይኖሩታል፤
ድርጅቱን የሚወክሉ ብዛት ግን በድርጅቱ አስተዳደር ደንብና መመሪያ መሠረት የሚፈፀም ሆኖ ከማኅበሩ
ተወካዮች ቢያንስ በአንድ መብለጥ አለበት፤

8.5. የድርጅቱ የሥራ ውጤት ከፍተኛ ዕድገት እንዲያገኝና ዕድገቱም ቀጣይነት እንዲኖረው ለማድረግ በዓመታዊ
ዕቅድ ውይይት ላይ እንዲሁም በየሩብ ዓመቱ በሚካሄድ የዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ ስብሰባ ላይ ከማኅበሩ
አመራር አባላት እንዲሣተፉ ያደርጋል፤

8.6. በድርጅቱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ወይም በድርጅቱ ደንብና መመሪያ ውሳኔዎችን እንዲወስኑ የስልጣን ውክልና
የተሰጠው አካል የአንድን ኮሚቴ የውሣኔ ሀሣብ በሙሉ ወይም በከፈል ካልተስማማበት ምክንያቱን በመግለጽ
በ 10 ቀናት ጊዜ ውስጥ ኮሚቴው ጉዳዩን እንደገና አይቶና መርምሮ በድጋሚ የውሣኔ ሀሣብ እንዲያቀርብ
ሊያዝዝ ይችላል፤ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ወይም የስልጣን ውክልና የተሰጠው አካል የመጨረሻ ውሳኔ ይሰጣል፡፡
በመጨረሻም የዋና ሥራ አስፈጻማው ውሣኔ ቅር የተሰኘ ወገን ጉዳዩን አግባብ ላለው የሕግ አካል ቅሬታውን
ሊያቀርብ ይችላል፡፡

ክፍል ሦስት
ቅጥር፣ ምደባ፣ የደረጃ ዕድገት፣ ዝውውር፣ ትምህርትና ሥልጠና
አንቀጽ ዘጠኝ (9)
ቅጥር

9.1. በድርጅቱ ውስጥ የሠራተኛ ቅጥር የሚፈጸመው በዚህ የኀብረት ስምምነት፡ በአዋጅ ቁጥር 1156/2011 እና
፣በሰው ሃብት አስተዳደር መመሪያ መሠረት ከድርጅቱና ከማኀበሩ ተወጣጥተው በሚቋቋመው የቅጥርና የደረጃ
ዕድገት ኮሚቴ አማካኝነት ይሆናል፤ ከዚህ ውጭ የሚደረግ የአዲስ ሠራተኛ ቅጥር ሕጋዊ እውቅና አይኖረውም፤

9.2. አንድን ከተሿሚና ከሥራ መሪ ውጭ ያለ ክፍት የሥራ መደብ ከድርጅቱ ሠራተኞች ውስጥ በዝውውርና በደረጃ
ዕድገት መሙላት ሳይቻል ሲቀር የውጭ ተወዳዳሪዎች በማስታወቂያ ሊጠሩ ይችላሉ፤

9.3. አዲስ ቅጥር ሰራተኛ የቅጥር ፎርማሊቲ ከማሟላቱ በፊት በድርጅቱ የጤናና ሌሎች ማስረጃዎች እንዲያቀርብ
ሲታዘዝ ለምርመራው እና ለሌሎች ወጭዎች የሚያወጣው ወጭ በራሱ ይሸፈናል፡፡

9.4. የሠራተኛ ቅጥር የሚፈጸመው በግልጽ ውድድር ሲሆን ለተጠየቀው ቦታ ተፈላጊውን መስፈርትና በቅጥርና
የደረጃ ዕድገት ኮሚቴ የሚሰጠውን መመዘኛ አሟልቶ ሲገኝ ቅጥሩ ይከናወናል፤ የአዲስ ተቀጣሪ ሠራተኛ
የሙከራ ጊዜው ከ 60 ተከታታይ ቀናት የማይበልጥ ይሆናል፤

9.5 በማጭበርበር፣ በስርቆትና በሌሎች የሙስና ጉዳዩች በዲስኘሊን የተባረረ ሰራተኛ በድጋሚ በድርጅቱ መቀጠር
አይችልም፡፡ ሆኖም በሌሎች የዲስኘሊን ጉዳዩች የሥራ ውላቸው የተቋረጠ ሠራተኞች እስከ ሁለት አመት ድረስ
በድርጅቱ መቀጠር አይችሉም፡፡

13 | P a g e
9.6 ላልተወሰነ ጊዜ የስራ መደብ ላይ በሚወጣ ክፍት የሥራ መደብ ላይ ድርጅቱ ከዚህ በፊት ከፕሮጀክት ፕሮጀክት
እያዛወረ ሲያሰራቸው የነበሩ የኮንትራት ቅጥር ሰራተኞች ስራ ላይ እያሉ ላልተወሰነ ጊዜ የስራ መደብ ላይ
ከያዙት የስራ መደብ ከፍ ያለ ደረጃ ወደ አለው የስራ መደብ በደረጃ እድገት መወዳደር ይችላሉ፡፡ በዚሁ የስራ
መደብ ላይ ተወዳድሮ ካላለፈ በድጋሚ መወዳደር የሚችለው ውጤቱ ከታወቀበት ቀን ጀምሮ ከ 3 ወር በኋላ ነው፡፡
9.7 በተራ ቁጥር 9.6 የተገለፀው ቢኖርም ይህ የህብረት ስምምነት ከፀደቀ በኋላ በድርጅቱ ውስጥ የሚቀጠሩ የተወሰነ
ጊዜ/ስራ ሠራተኞች ባልተወሰነ ጊዜ የስራ መደቦች ላይ በደረጃ እድገትም ሆነ በዝውውር መሳተፍ አይችሉም፡፡
9.8. ይህ የህብረት ስምምነት ከፀደቀ በኋላ በተወሰነ ጊዜ/ስራ የስራ መደቦች ላይ በሚወጣ የደረጃ እድገት ውድድር ላይ
የሚሳተፉት ይህ የኅብረት ስምምነት ከመጽደቁ በፊት በድርጅቱ የተቀጠሩ የፕሮጀክት የተወሰነ ጊዜ/ስራ
ሠራተኞች ብቻ ናቸው፡፡ ሆኖም የደረጃ እድገት ያደገ ሠራተኛ የቀድሞ ውሉ ተቋርጦ በአዲስ ላደገበት የስራ
መደብ የሙከራ ጊዜ ሳያስፈልገው በአዲስ ውል መያዝ ይጠበቅበታል፡፡

አንቀጽ አስር (10)


የሠራተኛ ምደባ

10.1. ሠራተኛ ሲቀጠር እንደ ሥራውና እንደ ቅጥር ውሉ ሁኔታ በሙያውና በችሎታው መሠረት እንዲመደብ
ይደረጋል፣

10.2. በማንኛውም ክፍት በሆነ የስራ መደብ ላይ ወይም በፈቃድ፣ በህመም፤ በማንኛውም ምክንያት ለጊዜው ቀሪ
በሆኑ የባለሙያና የስራ መሪ የሥራ መደቦች ላይ ከ 30 ቀን በላይ ከመደበኛ ስራው ጋር ደርቦ በውክልና ከሰራ
ሰራተኛው በውክልና በሚሰራበት ስራ መደብ መነሻ ደመወዝና በሚከፈለው ደመወዝ መካከል ልዩነት ካለ
የልዩነቱን 50% (ሀምሳ በመቶ) እና ከቤት አበል በስተቀር ለስራ መደቡ የተፈቀደ ጥቅማጥቅም ካለ
ይከፈለዋል፡፡ ውክልናውም በዘርፉ በኩል ቀርቦ በሰው ሃይል በኩል ይሆናል፡፡ ሆኖም አንድን ሠራተኛ በባለሙያ
መደብ ላይ ከ 6 ወር በላይ ወክሎ ማሰራት አይቻልም፡፡

10.3 ከተራ ቁጥር 10.1-10.2 የተጠቀሰው ቢኖርም በተወሰነ ጊዜ/ስራ የስራ መደብ ላይ ያልተወሰነ ጊዜ/ስራ
ሠራተኛን ወይም ባልተወሰነ ጊዜ/ስራ የስራ መደብ ላይ የተወሰነ ጊዜ/ስራ ሠራተኛ ወክሎ ማሰራት
አይቻልም፡፡

አንቀጽ አሥራ አንድ (11)


የደረጃ ዕድገት

11.1. በድርጅቱ ቋሚ ክፍት የሥራ ቦታ በሚኖርበት ጊዜ ለቦታው ብቁ የሚሆኑ ሠራተኞች ለደረጃ ዕድገት
እንዲወዳደሩ የውድድር ማስታወቂያ በድርጅቱ ማስታወቂያ መለጠፊያና በሌሎች ግልጽ በሆኑ ቦታዎች

14 | P a g e
እንዲለጠፉ ይደረጋል፤ ማስታወቂያውም ለ 5/አምስት/ ተከታታይ የሥራ ቀናት ቅዳሜን ጨምሮ ተለጥፎ
እንዲቆይ ይደረጋል፡፡

11.2. ለደረጃ ዕድገቱ በወጣው ማስታወቂያ ላይ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟላ ላልተወሰነ ጊዜ ሠራተኛ
ሁሉ ለውድድሩ መመዝገብ ይችላል፤

11.3. አንድ የድርጅቱ ሰራተኛ በደረጃ ዕድገት ለመወዳደር በድርጅቱ ከተቀጠረ ወይም በደረጃ እድገት ተወዳድሮ ያለፈ

በድጋሜ ለመወዳደር ከሆነ ዘጠኝ ወር የሞላው ሆኖ አማካኝ የሥራ አፈጻጸም ውጤቱም 60% እና በላይ መሆን

ይኖርበታል፡፡

11.4 በአንድ የስራ መደብ ላይ በደረጃ እድገት የተመደበ ሰራተኛ ከ 3 ወር በፊት ቢለቅ ወይም አንድ ዓይነትና ተመሳሳይ

የሥራ ደረጃ ያለው ተጨማሪ የስራ መደብ ቢከፈት እና ቦታው በሰው ኃይል እንዲመዋላ በዘርፉና በኮርፖሬት

የሰው ሃብት ስራ አመራር ከታመነበት የደረጃ ዕድገት ማስታወቂያ ማውጣት ሳያስፈልግ ቀደም ሲል በስራ መደቡ

ላይ ተወዳድረው ከነበሩት ሰራተኞች መካከል የማለፊያ ነጥብና በላይ ካመጡት ውስጥ በውጤታቸው ቅደም

ተከተል መሰረት የደረጃ ዕድገቱ ይሰጣል፡፡

11.5 በተራ ቁጥር 11.4 የተመለከተው የሚተገበረው በቀጥታ የተወዳደረበት የስራ መደብ ከሆነ በሠራተኛው ማመልከቻ፣

አንድ ዓይነትና ተመሳሳይ የስራ መደቦች ሲከፈቱ ግን የዘርፍ ኃላፊው በሚያቀርበው የሰው ሃይል ይሟላልኝ

ጥያቄ መሰረት ብቻ ይሆናል፡፡

11.6 ለደረጃ እድገት የሚወዳደር ሰራተኛ የቅርብ ጊዜ ተከታታይ የ 2 ጊዜ የስራ አፈፃፀም ምዘና አማካኝ ውጤት

ከ 60% በታች መሆን የለበትም፡፡ የ 2 ጊዜ ከሌለ በደረጃ እድገት ኮሚቴው ውሳኔ የአንድ ጊዜ ከበቂ ምክንያት ጋር

ሊያዝ ይችላል፡፡

11.7 ለደረጃ እድገት ለመወዳደር ለሠራተኛው የሚያዘው የቅርብ ጊዜ የስራ አፈጻፀም ውጤት የሚያዘው ከግል ማህደሩ

ጋር ተያይዞ የሚገኘው ብቻ ይሆናል፡፡

11.8 በደረጃ እድገት ውድድር ጊዜ የማወዳደሪያ መስፈርት የስራ አፈፃፀም ውጤት 30%፣ የማህደር ጥራት ከ 10%፣

እና የተግባርና/ ወይም የፅሁፍ ፈተና ከ 60% ተይዞ አሸናፊው ቢያንስ በተሰጠው ፈተና እና በጠቅላላ ድምር

50% ውጤት ማምጣት አለበት፡፡ በተሰጠው ፈተና እኩል ነጥብ ያገኙ ተወዳዳሪዎች ቅድሚያ ለሴት ይሰጣል

አንድ አይነት ፆታ ካላቸው የተሻለ የትምህርት ደረጃ ላለው በዚህም እኩል ከሆኑ በአገልግሎት ጊዜ እንዲለዩ

ይደረጋል፡፡ ዝርዝር አፈጻፀሙ በድርጅቱ በሰው ሃብት ስራ አመራር መመሪያ መሠረት ይሆናል፡፡

15 | P a g e
11.9 ለአንድ ክፍት የሥራ ቦታ የሚፈለጉትን መሥፈርት አሟልቶ ለደረጃ ዕድገት ያመለከተ ብቸኛ ተወዳዳሪ

በተሰጠው ፈተና ውጤቱ 50 ፐርሰንት እና በላይ ማግኘት ይኖርበታል፡፡

11.10 አንድ ሠራተኛ ዕድገት ካገኘ ከዘጠኝ ወር በላይ ከሆነው በሌላ ዕድገት ሊወዳደር ይችላል፤ ዕድገት ያገኘ ሠራተኛ
የሙከራ ጊዜ አይኖረውም፤

11.11 አዲስ ሠራተኛ ያልተወሰነ ጊዜ ተቀጥሮ ዘጠኝ ወር በድርጅቱ ውስጥ ከሠራ ለደረጃ ዕድገት በሚወጣው
የውስጥ ማስታወቂያ ተፈላጊ መስፈርቶችን እስካሟላ ድረስ ለደረጃ ዕድገት ሊወዳደር ይችላል፤

11.12. የደረጃ ዕድገት አሰጣጥ የሚፈጸመው የቅጥርና የደረጃ ዕድገት ኮሚቴ በሚያቀርበው ውሳኔ ሃሳብና በሰው ኃይል
አስተዳደር መመሪያው ላይ የማጽደቅ ስልጣን በተሰጠው አካል ሲፀድቅ ነው፡፡

11.13. በማንኛውም በድርጅቱ ውስጥ በሚሰጠው የደረጃ ዕድገት ላይ ቅሬታና ቅዋሜ ያለው ሠራተኛ ደረጃውን
ጠብቆ ለማንኛውም ቅሬታ ተመልካች አካል ሕጋዊ በሆነ መንገድ ቅሬታውንና ተቃውሞውን በወቅቱ
ማሰማት ወይም ማቅረብ ይችላል፡፡

11.14. በዚህ የኅብረት ስምምነት ስለ ቅጥርና ደረጃ ዕድገት የተገለፁትን በማያፈርስና በማይቃወም ሁኔታ ሌሎች
ያልተጠቀሱ ዝርዝር የቅጥርና የደረጃ ዕድገት አፈፃፀም በድርጅቱ የሰው ሃብት አስተዳደር መመሪያ መሠረት
የሚፈፀሙ ይሆናሉ፤

11.15. ስለደረጃ እድገት አሰጣጥ በዚህ አንቀጽ ንዑስ ቁጥር 11.6፣ 11.8 እና 11.9 የተገለፀው እንደተጠበቀ ሆኖ
የተመረጠው ሠራተኛ በሥነ ምግባሩ ብቁ አይደለም ብሎ የደረጃ ዕድገት ኮሚቴው ወይም አጽዳቂው
በሚያምንበት ጊዜ ጉዳዩን እንደ አስፈላጊነቱ ለዋና ሥራ አስፈጻሚ አቅርቦ የመጨረሻ ውሳኔ ይሰጣል፡፡
እንዲሁም ለሙስና ተጋላጭ በሆኑ የሥራ መደቦች ግዥ፣ ኮንትራት አስተዳደር፣ በንብረት ሠራተኛነት፣
በገንዘብ ያዥ እና የኦዲት የስራ መደቦች ላይ የደረጃ ዕድገትም ሆነ ቅጥር የሚፈፀመው በሚቀጠረው
ወይም በሚያድገው ሰራተኛ በአጽዳቂው ኃላፊ በሥነ ምግባሩ ሲታመንበት ብቻ ይሆናል፡፡

11.16 በአንድ የስራ መደብ ላይ ተወዳድሮ ከማለፊያ ነጥብ በታች ያመጣ (የወደቀ) ተወዳዳሪ በዚሁ የስራ መደብ ላይ
በድጋሚ መወዳደር የሚችለው ውጤቱ ከታወቀ ከ 3 ወር በኋላ ነው፡፡

11.17 አንድ ሰራተኛ ዕድገት አግኝቶ በራሱ አነሳሽነት ዕድገቱን ከሰረዘ በሌላ መደብ ላይ በዕድገት ለመወዳደር 9 ወራት
የመጠበቅ ግዴታ አለበት፡፡

አንቀጽ አሥራ ሁለት (12)

16 | P a g e
ዝውውር

12.1. ድርጅቱ በማንኛውም ጊዜ የሠራተኛ ዝውውር የሚያደርገው ሥራና ሠራተኛን ለማገናኘት የድርጅቱን ሥራ
ለማሣደግና ምርታማነትን ከፍ ለማድረግ ባለው ዓላማ ወይም ሠራተኛው በሚያቀርበው የዝውውር ጥያቄ
መሠረት ድርጅቱ ሲስማማ ብቻ ይሆናል፤

12.2. ዝውውሩ የሚከናወነው ሠራተኛው ተመድቦ ከሚሠራበት አካባቢ ወደ ሌላ የሥራ አካባቢ ወይም ቦታ ከሆነ
የሚያገኘውን ጥቅምና የሥራ ደረጃ በመጥቀስ እንዲዛወር ከተወሰነበት ቀን 15 ቀናት አስቀድሞ ሠራተኛው
እንዲያውቀው ያደርጋል፤

12.3. ድርጅቱ አንድን ሠራተኛ ሲያዛውረው ሠራተኛው በጊዜያዊ የጤና መታወክ ምክንያት ቅርብ የሐኪም ክትትል
እንደሚያስፈልገው ከታመነበትና ከሆስፒታል ለዚሁ ማረጋገጫ ሲያቀርብ እንዲሁም በሚዛወርበት አካባቢ
ሕክምናውን ሊያገኝ እንደማይችል ሲረጋገጥ ችግሩ እስኪቃለል ድረስ ዝውውሩ እንዲዘገይ ይደረጋል፤

12.4. አንድ ሠራተኛ ካለበት የሥራ ቦታ ወደ ሌላ የሥራ ቦታ በድርጅቱ ፍላጎት በቋሚነት ሲዛወር ለራሱና አብሮት
ለሚሄደው ቤተሰብ እንዲሁም ለእቃ ማንሻ የሚሆን የትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅቱ ይሰጠዋል፡፡ ሆኖም
በራሳቸው ጠያቂነትና ፍላጐት የሚዛወሩ ሠራተኞች የውሎ አበልና የትራንስፖርት ወጪ አይከፈላቸውም፤

12.5. ነፍሰጡር የሆነች ሠራተኛ የምትሠራው ሥራ ለጤናዋ አመቺ አለመሆኑ በሐኪም ሲረጋገጥ ድርጅቱ
ደመወዝና ደረጃ ሳይቀንስ ወደ ሌላ አመቺ ሥራ ክፍል ወይም ሥራ ቦታ እስክትወልድ ድረስ አዛውሮ
ያሠራታል፤

12.6 ከአንድ የስራ መደብ ወደ ሌላ የስራ መደብ በራሱ ጠያቂነት በዝውውር የተመደበ ሰራተኛ ወደ ሌላ የስራ መደብ
በዝውውር ለመወዳደር ቢያንስ ስድስት ወር መጠበቅ ይኖርበታል፡፡

12.7. አንድ ሰራተኛ ከአንድ የስራ መደብ ወደ ሌላ የስራ መደብ ለመዛወር በመጀመሪያ በተዛወረበት ወይም
በተቀጠረበት ወይም ባደገበት የስራ መደብ ላይ ቢያንስ 6 ወራት የማገልገል ግዴታ አለበት፡፡

አንቀጽ አሥራ ሶስት (13)

ትምህርትና ሥልጠና

13.1. ሠራተኛው በሙያው፣ በዕውቀቱና በችሎታው ተሻሽሎ ለተመደበበት ሥራ ብቁ ሆኖ እንዲገኝ ድርጅቱ


አስፈላጊውን እገዛ ያደርግለታል፡፡

17 | P a g e
13.2. በሀገር ውስጥ ሴሚናር ወይም የሙያ ማሻሻያ ኮርስ ሲኖርና ሠራተኞች እንዲሣተፉ ሲደረግ በሥራ ላይ እንዳለ
ተቆጥሮ ደመወዝ ይከፈለዋል፡፡ ሴሚናሩ የሚካሄድበት ወይም ኮርሱ የሚሰጥበት ቦታ ሠራተኛው ከሚሠራበት
ቦታ ውጭ በመሆኑ ለትራንስፖርት፣ ለምግብና ለመኝታ ተጨማሪ ወጪ የሚያስከትልበት ሆኖ ከተገኘ ባለው
ደንብና መመሪያ መሠረት ይከፈላል፡፡ ሆኖም የትራንስፖርት፣ የምግብና የመኝታ አገልግሎት ሥልጠናው
ካዘጋጀው አካል ከተሰጠው ድርጅቱ የሚከፍለው ሌላ ወጪ አይኖርም፤

13.3. በየትኛውም የሥራ መደብ ላይ ያለ የድርጅቱ ሰራተኛ ለሚከታተለው የማታ/የተልኮ ትምህርት


የሚያስፈልገው ወጭ ከትምህርት ቤቱ በሚሰጠው ማለፊያ ውጤት እና የክፍያ ደረሰኝ መሠረት
ለመጀመሪያና ለሁለተኛ ደረጃ ሙሉ ክፍያ ድርጅቱ ይከፍላል፡፡ ከክፍል ክፍል ላልተዛወረ ሠራተኛ ድርጅቱ
ወጭውን አይሸፍንም፡፡

13.4. የኮሌጅ ዲፕሎማ ወይም የቴክኒክና ሙያ ዲፕሎማ ከሌቭል 1 እስከ ሌቭል አምስት ተፈቅዶለት ለሚማር
ሠራተኛ የሚማረው የትምህርት አይነት ከሚሰራበት የሥራ መደብ ተፈላጊ ችሎታ መስፈርት ላይ የተጠቀሰ
መሆኑ እየተረጋገጠ ከትምህርት ቤቱ በሚሰጠው ማለፊያ ውጤት እና የክፍያ ደረሰኝ መሠረት 100%
የትምህርት ወጭ ይሸፈናል፡፡ ሆኖም ከ 12/10 በላይ የትምህርት ዝግጅትና ደረጃ በማይጠይቁ የስራ መደቦች
ላይ እየሰሩ ላሉ ሰራተኞች የሚማሩት የትምህርት ዓይነት በድርጅቱ የትምህርት ዝግጅት ተፈላጊ ችሎታ
መስፈርት መመሪያ ውስጥ የተካተተ እስከሆነ ድረስ በድርጅቱ እንዲማሩ እስከተፈቀደ ድረስ እስከ ኮሌጅ
ዲፕሎማ መማር ይችላሉ፡፡ ሆኖም ድጋሚ ለሚወሰዱ ኮርሶች ድርጅቱ ወጭ አይሸፍንም፡፡

13.5 በድርጅቱ ተፈቅዶለት የመጀመሪያ ዲግሪ ለሚማር ሠራተኛ የሚማረው የትምህርት አይነት ከሚሰራበት
የሥራ መደብ ተፈላጊ ችሎታ መስፈርት ላይ የተጠቀሰ መሆኑ እየተረጋገጠ ከትምህርት ቤቱ በሚሰጠው
ማለፊያ ውጤት እና የክፍያ ደረሰኝ መሠረት 100% የትምህርት ወጭ ይሸፈናል፡፡ ሆኖም ድጋሚ ለሚወሰዱ
ኮርሶች ድርጅቱ ወጭ አይሸፍንም፡፡

13.6 ድርጅቱ የትምህርት ክፍያ ለማወራረድ ለመጀመሪያው ዓመት ሰራተኛው ያለፈበትን የፈተና ውጤት
እንዲያቀርብ ሳይገደድ በገባው ውል መሰረት ሂሳቡ ይወራረዳል፤ ነገር ግን የሚቀጥለው የትምህርት ደረጃ
ክፍያ ለመፈፀም ሰራተኛው ቅድሚያ ለተከፈለለተ ያለፈበትን ውጤት ማያያዝ ይኖርበታል፡፡

13.7 የትምህርት ዕድል አግኝቶ ትምህርቱን ያጠናቀቀ ሰራተኛ ግዴታውን ሳይጨርስ ሌላ ትምህርት መጀመር
አይችልም ፡፡

13.8 በድርጅቱ የትምህርት ዕድል የተሰጠው ሠራተኛ በራሱ ተነሳሽነት ወይም ዝቅተኛ ውጤት በማምጣት ሆነ በሌላ
ምክንያት ትምህርቱን ቢያቋርጥ ሌላ የትምህርት ዕድል ለማግኘት ቢያንስ 2/ሁለት/ ዓመት መጠበቅ
ይኖርበታል፡፡

13.9 ድርጅቱ የትምህርት ወጪ የሚሸፈነው ላልተወሰነ ጊዜ ቅጥር ሠራተኞችና ይህ የህብረት ስምምነት ከመጽደቁ
በፊት በድርጅቱ ለተቀጠሩ የተወሰነ ጊዜ/ስራ ሠራተኞችን ብቻ ነው፡፡

18 | P a g e
13.10 ከ 12/10 ክፍል በላይ የሚማሩ ወጭ የሚሸፈንላቸው ሰራተኞች በድርጅቱ የስልጠና መመሪያ መሰረት
በቅድሚያ ውል ሲፈጽሙና የስልጠና ዋስትና ሲያሟሉ ብቻ ነው፡፡

13.11 በልዩ ሁኔታ ካልተፈቀደ በስተቀር አንድ ሠራተኛ ለመማር የሚፈቀድለት ተመሳሳይ የትምህርት ደረጃ የሌለው
ሲሆን ብቻ ነው፡፡ ለምሳሌ ዲፕሎማ ያለው ለሌላ ዲፕሎማ ወይም የመጀመሪያ ዲግሪ ያለው ለሌላ
የመጀመሪያ ዲግሪ ለመማር አይፈቀድለትም፡

13.12 በዚህ አንቀጽ ተራ ቁጥር 13.4 እና 13.5 ላይ የተጠቀሰውን ክፍያ ድርጅቱ የሚከፍለው ከ 12/10 ኛ ክፍል በላይ
ለሚሰጥ ትምህርት ወይም የሙያ ማሻሻያ ትምህርት ወይም የተልዕኮ ትምህርት ሠራተኛው ለመከታተል
ከፈለገ ከሚሠራው ሥራ ጋር በቀጥታ ግንኙነት ያለው ለመሆኑ ለማረጋገጥ ትምህርቱን የሚከታተልበት ተቋም
በትምህርት ሚ/ር ተቀባይነት ያለው ለመሆኑ ተጣርቶ ከድርጅቱ በቅድሚያ ስምምነት ማግኘት አለበት፤

13.13 በክልሉ መንግስት አማካኝነት ወይም በድርጅቱ የውጭ ሀገር ትምህርት ሠራተኛው እንዲከታተል ድርጅቱ
ሲያደርግ ትምህርቱን ጨርሶ እስኪመለስ ደመወዝና ከሥልጠናው ጋር ተያያዥነት ያላቸውን ክፍያዎች
የሚፈፅመው በድርጅቱ የትምህርትና ሥልጠና መመሪያ መሠረት ይሆናል፡፡

13.14 በውጭ ሀገር ወይም በሀገር ውስጥ ትምህርቱን የሚከታተል ሠራተኛ ለትምህርት ከመሄዱ በፊት በዚሁ ጉዳይ
በድርጅቱ በሥራ ላይ በዋለው መመሪያ መሠረት ውል በማድረግ ትምህርቱን አጠናቆ ሲመለስ ድርጅቱን
ማገልገል ይኖርበታል፤

13.15. በክልሉ መንግሥት አማካኝነት ወይም በድርጅቱ የሀገር ውስጥ ትምህርት ሠራተኛው እንዲከታተል
ሲያደርግ ትምህርቱን ለማጠናቀቅ ለሚሰጠው የጊዜ ገደብ ብቻ በድርጅቱ የትምህርት/ስልጠና መመሪያ
መሠረት ድርጅቱ የሠራተኛውን ደመወዝ ብቻ ይከፍላል፡፡

13.16 አዲስ ተቀጣሪ ሠራተኛ በድርጅቱ የትምህርት እድል ለማግኘት ቢያንስ 2 ዓመት ማገልገል አለበት፡፡ ሆኖም
ሁለተኛ ዲግሪና ከዚያ በላይ ለተጨማሪ ለሚደረግ ውድድር ቅድሚያ በድርጅቱ ዲግሪና ከዚያ በላይ
በድርጅቱ ወጭ የትምህርት ላላገኙት ይሠጣል፡፡

13.17 በድርጅቱ ወይም በሠራተኛው በራሱ ወጭ ከስራ ውጭ ሆኖ በመደበኛ የትምህር ጊዜ በድርጅቱ ተፈቅዶለት
የሚማር ሠራተኛ ከደመወዙ ውጭ ያለ የደንብ ልብስም ሆነ ሌሎች ጥቅማጥቅሞች ሊከፈለው
አይችልም፡፡
13.18 በዚህ አንቀጽ በተወመጠው መሠረት ድርጅቱ ለሠራተኞች የትምህርት ወጭ የሚሸፍነው ይህ የኅብተረት
ስምምነት ከፀደቀ በኋላ እንዲማሩ በድርጅቱ ለሚፈቀድላቸው ሠራተኞች ብቻ ሲሆን ከዚህ ኅብረት
ስምምነት ድርድር በፊት በትምህርት ላይ የሚገኙ ሠራተኞች የትምህርት ወጭ የሚሸፈነው አስቀድሞ
በያዙት የውል ስምምነት አማካኝነት ይሆናል፡፡

19 | P a g e
ክፍል አራት
ልዩ ልዩ ጥቅሞችና አገልግሎቶች
አንቀጽ አሥራ አራት (14)
የሥራ ሰዓት

14.1. የማንኛውም ሠራተኛ መደበኛ የሥራ ሰዓት በቀን ከ 8 ሰዓት በሣምንት ከ 48 ሰዓት መብለጥ የለበትም፤

14.2. የሥራ መግቢያና መውጫ ሰዓት ከሰኞ እስከ ሐሙስ


ጧት ከ 2፡30-6፡30
ከሰዓት ከ 7፡30-11፡30 ይሆናል፡፡
አርብ ጧት ከ 2፡30-5፡30
ከሰዓት ከ 7፡30-11፡30
ቅዳሜ ጧት 2፡30-5፡30 ብቻ ይሆናል፡፡

14.3. ሆኖም ድርጅቱ ካመነበት "ቅዳሜ ከሰዓት መግቢያ 8፡00 ሰዓት መውጫ 11፡00 ሰዓት ይሆናል፡፡ ይህም ማለት
በድርጅቱ ዋና መ/ቤትና በቅ/ጽ/ቤቶች ሥራ ኖሮት ማንኛውንም የድርጅቱን ሠራተኛ ሥራ እንዲገባ
ሲያደርግ ብቻ ነው፡፡ በዚህም መሠረት የሰራተኛ የቅርብ ሀላፊ ሠራተኞችን በግል፣ በከፊልና ሙሉ በሙሉ
ሥራ ካለው እንዲገቡ ማድረግ ይችላል፡፡ የሚገቡ ሠራተኞችንም የቅርብ ኃላፊው አስቀድሞ መንገር
ይገባዋል፡፡

14.4. ድርጅቱ ለሠራተኞች የሻይ እረፍት የሚሆን ከመደበኛ የሥራ ሰዓት የሚቆጠር በቀን 30 ደቂቃ እረፍት
ይሰጣል፡፡ ይኸውም አስራ አምስት ደቂቃ ጧት ከ 4፡15-4፡30 አስራ አምስት ደቂቃ ከሰዓት 9፡30-9፡45 ይሆናል፡፡
ሆኖም ኘሮጀክቶች በራሳቸው ኘሮግራም መሠረት ሰዓቱን ሊያመቻቹ ይችላሉ፡፡

14.5. የድርጅቱ ሠራተኞች የሣምንት ዕረፍት ቀን በአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 አንቀጽ 69
ተ.ቁ.1 መሠረት ይሆናል፤

14.6. የሣምንት የዕረፍት ጊዜ ለድርጅቱ ሠራተኞች በሙሉ በአንድ ላይና በአንድ ጊዜ ይሰጣል፤ ይሁን እንጂ በሥራ

ፀባያቸው ምክንያት በፈረቃ ወይም በሽፍት የሚሠሩ ሠራተኞች የሥራ ሰዓት በአዋጅ ቁጥር 1156/2011

አንቀጽ 64 መሠረት መደበኛ የሥራ ሰዓቶችን አማካይ በማድረግ የሚደለደል ሲሆን የዕረፍት ጊዜያቸውም

በሚወጣው የሥራ ፕሮግራም ድልድል መሠረት ይሆናል፡፡

14.7. በሥራ ምክንያት መስክ ላይ ውሎ አበል እየተከፈላቸው የሚሠሩ ሠራተኞች በሣምንት ከ 48 ሰዓት ሳይበልጥ

ቅዳሜ ሙሉ ቀን እንደመደበኛ የሥራ ሰዓት ተቆጥሮ እንዲሠሩ ይደረጋል፤

20 | P a g e
አንቀጽ አሥራ አምስት (15)

ስፖርት፣ መዝናኛና ቤተ-መፃሕፍት

15.1. ሠራተኛው በስፖርት እንቅስቃሴ የአካል ጥንካሬና የአእምሮ ተሃድሶ እንዲያገኝ ማኅበሩ በሚያደርገው ጥረት

የድርጅቱ አቅም በፈቀደ መጠን የገንዘብ፣ የሞራልና ሌሎች አስፈላጊ የሆኑ የቁሳቁሶች ድጋፍ ያደርጋል፤

በአግባቡ በሥራ ላይ መዋሉን ይቆጣጠራል፡፡ ማኅበሩም የስፖርቱን እንቅስቃሴ በበላይነት ያስተዳድራል፡፡

15.2. ሠራተኛው በዕረፍት ጊዜው የሚዝናናበትን የሠራተኞች መዝናኛ ክበብ ማኅበሩ ያስተዳድረዋል፤

ይቆጣጠረዋል፤ ገቢውንም በአግባቡ ለማኅበሩና ለሠራተኛው ግልጋሎት እንዲሁም ለመዝናኛ ክበቡ መሻሻል

እንዲውል ያደርጋል፤

15.3. ድርጅቱ ለሠራተኛው መዝናኛ ክበብ መሻሻል /ጥገናና የውስጥ ማቴሪያሎች ወዘተ.. /ያሟላል፤

15.4. የድርጅቱ ሠራተኞች የሳይንስና ቴክኖሎጂ ዕውቀታቸውን ለማስፋት በተለይም የኮንስትራክሽን ክፍለ

ኢኮኖሚ የሥራ እንቅስቃሴና የፈጠራ ችሎታቸውን ለማሳደግ የሚረዳ ቤተ-መፃሕፍት ከማኅበሩ ጋር

በመተባበር ደረጃ በደረጃ ያቋቁማል፣ ያደራጃል፡

አንቀጽ አሥራ ስድስት (16)

የካምፕ አገልግሎት

16.1. የሥራው ሁኔታ አስገድዶ ካምፕ መሥራት ሲያስፈልግ ድንኳኖችንና ማንኛውንም የመኝታ፣ የመዝናኛ

ማቴሪያሎችን እንዲሁም የምግብ ቁሳቁሶች ድርጅቱ ያዘጋጃል፡፡

16.2. በአንቀጽ 16.1 ዝርዝር አፈፃፀም አካቶ ድርጅቱ የካምፕ አስተዳደር መመሪያ እንዲዘጋጅ ያደርጋል፡፡

አንቀጽ አሥራ ሰባት (17)

21 | P a g e
ትራንስፖርት

17.1. በሥራ ቦታ የተፈጠረ ችግርን ለመፍታት ወይም በድርጅቱና በማኀበሩ ታምኖበት አስፈላጊ የሆነ የሥራ

ቅስቀሳ ለማድረግ ከድርጅቱና ከማኀበሩ የተውጣጡ ሰዎች ሲንቀሳቀሱ የውሎ አበልና የትራንስፖርት

አገልግሎት ድርጅቱ ይችላል፤

17.2. ሠራተኛው ሲሞት የቀብሩ ሥነ-ሥርዓት በሚፈፀምበት ቦታ ለሚገኙ የድርጅቱ ሠራተኞች የትራንስፖርት

አገልግሎት ይሰጣል፤ ይኸም የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጠው ቀብሩ በድርጅቱ ዋና ጽ/ቤት ወይም

በቅ/ጽ/ቤቶች በሚገኝበት ቦታ ሲፈጸም ሲሆንና እንደ ሁኔታው እየታየ ለሥራ ባልተሠማሩ ተሽከርካሪዎች

በመጠቀም ይሆናል፤

17.3. ሠራተኛው በሥራ ላይ ለሚደርስበት አደጋ ወይም ከሥራው ጋር ግንኙነት ባለው ሕመም ወይም በማንኛውም

ህመም ወይም አደጋ ሲሞት ድርጅቱ አስከሬኑን የቀብሩ ሥነ-ሥርዓት ወደሚፈፀምበት ቦታ ያደርሰዋል፤

17.4. ሠራተኛው በሥራ ምክንያት በደረሰበት ጉዳት ወይም ከሥራው ጋር ግንኙነት ባለው ሕመም የሞተ እንደሆነ
በአዋጅ 1156/2011 አንቀጽ 110.1.ለ መሠረት ለሟች ሠራተኞች ጥገኞች ክፍያ ይፈፀማል፡፡

አንቀጽ አሥራ ስምንት (18)


የህክምና አገልግሎት

18.1. ድርጅቱ በየአካባቢው በተለያዩ የጥገናና የኮንስትራክሽን እንዲሁም በመሳሰሉት ሥራዎች ላይ ተሰማርተው
የመቆረጥ፣ የመቀጥቀጥ፣ የመወጋት የመፈንከት እና ሌሎች በሥራ ላይ ለሚፈጠሩ አደጋዎች የመጀመሪያ
እርዳታ እንዲያገኙ ያደርጋል፣ በሜጋ ኘሮጀክቶች ላይ አነስተኛ ህክምና ለማድረግ የሚያስችል ክሊኒክ
ያቋቁማል፤

18.2. የህክምና አገልግሎት

ሀ/ ማንኛውም ያልተወሰነ ጊዜ እና ፕሮጀክቱ እስኪጠናቀቅ የስራ ውል ያለው ሰራተኛ ከስራው ጋር ግንኙነት


በሌለው ህመም ምክንያት ለሚያወጣው የህክምና ወጭ ከመንግስት የህክምና ተቋማት 100% ይሸፍናል፡፡

22 | P a g e
ለ/ ህጋዊ ሰውነት ካላቸው የግል የህክምና ተቋማት 85% ይወራረድላቸዋል፡፡ ህጋዊ ሰውነት ካላቸው ሲባል ግን
መካከለኛ እና ከዚህ በታች ያሉትን የህክምና ተቋማት አያካትትም፡፡ ሆኖም ከመካከለኛ ክሊኒክ በላይ
አለመኖሩ ከተረጋገጠ ከመካከለኛ ተቋማት የሚመጡ ህክምና ማስረጃዎች ተቀባይነት ያገኛሉ፡፡

ሐ/ ሠራተኛው በህብረት ስምምነቱ፣ በተፈቀዱ የህክምና ተቋማት በሀኪም እንዲተኛ ሲታዘዝ በመንግስት
100% እንዲሁም በግል የሁለተኛ ማዕረግ አልጋ ሂሳብ ተመን እንዲያቀርብ ተደርጎ የተመኑ 85% ወጭ
ይሸፈንለታል፡፡

መ/ በመንግስት የህክምና ተቋማት ወይም ህጋዊ በሆነ ከፍተኛ የግል የህክምና ተቋማት ትዕዛዝ መሰረት
ሠራተኛው ከሚሰራበት ቦታ ወደ ሌላ ቦታ ሄዶ እንዲታከም ሲደረግ ሪፈር የተደረገበትን ማስረጃ አቅርቦ
ደርሶ መልስ የየብስ ትራንስፖርት ወጭ እንዲሁም የመሄጃና የመመለሻ ውሎ አበል ለአንድ ጊዜ ብቻ
ይሸፈንለታል፡፡ በተጨማሪም ተከታታይ ቀጠሮ የሚሠጠው ከሆነ በሚያመጣው ማስረጃ መሰረት የደርሶ
መልስ የየብስ ትራንስፖርት ብቻ ይሸፈንለታል፡፡

ሠ/ በሰራተኛው ላይ የደረሰው ህመም ለህይዎቱ አስጊ መሆኑ በሀኪም ሲረጋገጥ፡ ድርጅቱ የሰራተኛውን ሂወት
ለማትረፍ ሲባል በሀገር ውስጥ የአየር ትራንስፖርት አስፈላጊ መሆኑ ከታመነበት ድርጅቱ ወጭውን
ይሸፍናል፡፡
ረ/ ሠራተኛው በህክምና ተቋማት መታከሙን ከሚያመጣው ደረሰኝ በተጨማሪ በተቋሙ ማወቂያ ኮፒ ላይ
የህክምና ተቋሙ ማህተም ያረፈበትን መረጃ ማቅረብ አለበት፡፡
ሰ/ ክሊኒክ በተቋቋመባቸው ፕሮጅክቶች የሚሠሩ ሠራተኞች ወደ ውጭ ወተው ለመታከም ከክሊኒኩ ሪፈር
ማፃፍ ይጠበቅባቸዋል፡፡
ቀ/ እንድ ሠራተኛ ለእረፍት ወይም በስራ ምክንያት ካልሆነ በስተቀር ሌላ ቦታ ሄዶ ታክሞ የሚያመጣው ህክምና
ደረሰኝም ሆነ የህመም እረፍት ተቀባይነት የለውም፡፡
ሸ/ ለኩላሊት እጥበት ድርጅቱ ለአንድ ጊዜ ብቻ እስከ 20,000 /ሃያ ሽ ብር/ ብር ወጭ የሚሸፍን ሲሆን
ከተጠቀሰው የገንዘብ መጠን ከአንድ ጊዜ በላይ ግን ድርጅቱ አይሸፍንም፣
በ/ በአንቀጽ 18.2 /ለ/ መሠረት ድርጅቱ የተሻሉ ናቸው ከሚላቸው የህክምና ተቋማት የዱቤ ህክምና ውል ይዞ
ሊያሳክም ይችላል፡፡

18.3. ድርጅቱ ከዚህ በታች ለተመለከቱት ሕክምና ወጪ አይሸፍንም፤

18.3.1. ለአባለዘር በሽታ


18.3.2. ሴት ሠራተኛ በራሷ ፈቃድ ሆን ብላ በምታደርገው ውርጃ ለሚመጣ ሕመም
18.3.3. በመጠጥ፣ በሐሺሽ ወዘተ.. ምክንያት በሚደርሱ በሽታዎች፤
18.3.4. ከስራ ላይ አደጋ ውጪ ጥርስ ለማስሞላት፣ ለማስተካከል፣
18.3.5 ለሰውነት ውበት ሲባል ለሚደረግ የፕላስቲክ ሰርጀሪ፣

23 | P a g e
18.4. ከስራው ጋር ግንኙነት በሌለው ህመም ሰራተኛው የዓይን መነፀር እንዲገዛ በሀኪም ሲታዘዝ እና ማረጋገጫ
ሲያቀርብ መነፀሩ የተገዛበትን ዋጋ ከብር 1000 /አንድ ሺ ብር/ ያልበለጠ፣ የጆሮ ማዳመጫ ከብር
5000 /አምስት ሺ ብር/ ያልበለጠ ለአንድ ጊዜ ብቻ ድርጅቱ ይሸፍናል፡፡

18.5. በሥራ ምክንያት ስለሚመጣ በሽታ በአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 አንቀጽ 98 ላይ
በሠፈረው መሠረት ይፈፀማል፡፡
18.6 ከላይ የተጠቀሱት የህክምና ወጭዎች የሚሸፈነው ለሀገር ውስጥ ህክምና ብቻ ነው፡፡ የውጭ ሀገር ህክመና
አያካትትም፡፡

18.7. የድርጅቱ ሰራተኛ ከስራው ጋር ባልተገናኘ ሁኔታ በህመም ቢሞት ለቀብር ስነ-ስርአት ማስፈፀሚያ የሚውል
ከድርጅቱ 4000.00 ብር እና ለቤተሰቦቹ ማቋቋሚያ የሚሆን የ 3 ወር ደመወዝ ከሰራተኛ ማህበሩ 4000.00
ብር ለቤተሰቦቹ ይሰጣል፡፡

አንቀጽ አሥራ ዘጠኝ (19)


አበል
19.1. የድርጅቱ ባልደረባ ከምድብ የሥራ ቦታው ወደ ሌላ የሥራ ቦታ ሥራ እንዲያከናውን ሲታዘዝ በሚሄድበት ቦታ
ለሚያጋጥመው የምግብና የመኝታ ወጪ ለመሸፈን ውሎ አበል ይከፍለዋል፤ አከፋፈሉም የድርጅቱ ስራ
አመራር በሚወስነው መሠረት ወይም በድርጅቱ መመሪያ መሰረት ተፈጻሚ ይሆናል፡፡

19.2. የበረሀ አበል ክፍያ አፈፃፀም መንግስት ባወጣው መመሪያ መሠረት ይፈፀማል፡

19.3 ለገንዘብ ያዥ፡ ለተንቀሳቃሽ ገንዘብ ያዥ፤ እቃ ግምጃ ቤት ሰራተኛ /ከደረጃ 1 እስከ 4/፤ ለግዥ ሰራተኞች
ደረጃ 1፣ በምንዛሬ /በአሰጣጥ ስህተት/ ገንዘብ ወይም ንብረት ሊጐድልባቸው ስለሚችል ለመጠባበቂያ ይረዳ
ዘንድ በየወሩ ታሳቢ ሆኖ የሚከፈል ብር 200 ድርጅቱ ይከፍላል፡፡ ክፍያው የሚፈፀምበት ጊዜ በመመሪያ
ይወሰናል፡፡ ሆኖም ለፕሮጀክት ሠራተኞች የሚከፈለው በበጀት ዓመቱ ለሠሩባቸው ወራቶች ብቻ ይሆናል፡፡

19.4. ይህ የኀብረት ስምምነት ከፀናበት ጊዜ ጀምሮ በአንቀፅ 19.3 የተጠቀሱት የስራ መደቦች ላይ የሚሰሩ
ሰራተኞች በወር የተተመነው የማካካሻ ገንዘብ ተጠራቅሞ በበጀት ዓመቱ መጨረሻ ላይ የሠራተኛው ሂሣብ
ተመርምሮ ከገንዘብ ጉድለት ነፃ ሆኖ ሲገኝ ብቻ ይከፈለዋል፡፡

19.5. በበጀት ዓመቱ መጨረሻ ላይ የሠራተኛው ሂሣብ ተመርምሮ ያጐደለው ገንዘብ ከማካካሻ ገንዘብ ያነሰ ከሆነ
ዕዳው ተቀንሶ ቀሪው ገንዘብ ለሠራተኛው ይከፈለዋል፤ ይሁን እንጂ ያጎደለው ገንዘብ ከማካካሻ ገንዘብ በላይ
ከሆነ የጉድለቱን ልዩነት በሚሰጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ ሠራተኛው አሟልቶ እንዲከፍል ይደረጋል፡፡

19. 6. ከበጀት ዓመቱ መጨረሻ በፊት ሠራተኛው በልዩ ልዩ ምክንያት በ 19.3 ላይ የተዘረዘሩትን የሥራ በደቦች ሲለቅ
ሂሣቡ ተመርምሮ በዚህ ኀብረት ስምምነት አንቀጽ 19.5 መሠረት ተፈፃሚ ይሆናል፡፡

24 | P a g e
19.7. የውሎ አበል እየተከፈላቸው ኘሮጀክት ላይ ለሚሰሩ የፕሮጀክት ሰራተኞች ለሥራ ጉዳይ ዋናው ጽ/ቤት (ባሕር
ዳር) ወይም ቅ/ጽ/ቤት (ኮምቦልቻ) ለሥራ በሚመጡበት ጊዜ የውሎ አበል አይከፍልም፡፡

19.8 የወተት አበል


ብሉ ፕሪነት፤ ማባዣ፤ ብየዳ፤ የአካል ቅጥቀጣ ባለሙያ፣ አውቶ ኤሌክትሪሽያን ከረዳት እስከ አስተባባሪ፣ ላይበራሪያን፣
ሀንድ ድሪል ኦፕሬተር ሰራተኞች፤ ክሬሸር ኦፕሬተር፤ የሲሚንቶ እና ጎማ እቃ ግምጃ ቤት ሰራተኞች፣ የስሜንቶ እና የጎማ
ረዳት እቃ ግ/ቤት ሰራተኛች፤ ሲኔር ማሽኒስት/ማሽኒስት/ረዳት ማሽኒስት፣ የራድያተር ባለሙያ፣ የመለዋወጫ ሳልቫጅ
ስቶር ሰራተኛ/ የመኪና ባትሪ የሚይዙ ከሆኑ ብቻ/፣ የሂሳብ ሰነድ ያዥ፤ በሰው ሀይል ስር ያሉ መዛግብት ሰራተኞች፣
የንብረት ክፍል የህትመትና ሰነድ ያዥ ሰራተኞች ስራ ላይ ባይሆኑም ሳይቆራረጥ በቀን አንድ ሊትር ወተት ይሰጠዋል፡፡
ሠራተኛው የስራ መደቡን ከለቀቀበት ቀን ጀምሮ ክፍያው ይቋረጣል፡፡

አንቀጽ ሃያ (20)
የትርፍ ሰዓት ሥራ

20.1. ድርጅቱ በአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 አንቀጽ 67 መሠረትና እንዲሁም በዚህ የህብረት
ስምምነት በድርጅቱ የሥራ ፀባይና የሥራ ሁኔታ አስገዳጅነት የትርፍ ሰዓት ሥራ ለማሠራት ይችላል፡፡
20.2 በተራ ቁጥር 20.1 የተገለፀው ቢኖርም ትርፍ ስዓት ስራ በቀን ከ 4 ስዓት፣ በሳምንት ከ 12 ሥዓት መብለጥ
የለበትም፡፡

20.3 የትርፍ ሰዓት ሥራ አከፋፈል በአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁ.1156/2011 አንቀጽ 68 መሠረት ይፈጸማል፤

20.4 የትርፍ ሰዓት ክፍያ ከሚቀጥለው ወር ደመወዝ ጋር ተዳምሮ ይከፈላል፤

20.5. በአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 አንቀጽ 64 እንዲሁም በዚህ የኀብረት ስምምነት አንቀጽ
14.6 መሠረት የሣምንት የሥራ ሰዓትን ወይም መደበኛ የሥራ ሰዓቶችን በማደላደል የሚሠሩ የሥራ ሰዓቶች
የትርፍ ሰዓት ሥራ እንደሆኑ አይቆጠርም፤

አንቀጽ ሃያ አንድ (21)


የሕዝብ በዓላት

21.1. በአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 አንቀጽ 73 መሠረት በሕዝብ በዓላት ቀን ሠራተኛው
ደመወዝ እየተከፈለው ያርፋል፡፡

አንቀጽ ሃያ ሁለት (22.)


የደመወዝ ጭማሪ

25 | P a g e
22.1. ድርጅቱ በአንድ የበጀት ዓመት ጊዜ ውስጥ ከሚያገኘው ያልተጣራ ትርፍ ላይ የትርፍ ገቢ ግብር ተቀንሶ
ከሚገኘው የተጣራ ትርፍ ላይ ሕጋዊ መጠባበቂያ 5% በመቀነስ ለሠራተኞች ላልተወሰነ ጊዜ እና ፕሮጀክት
እስከሚጠናቀቅ ድረስ የስራ ውል ላላቸው ለተወሰነ ጊዜ ሠራተኞች ብቻ የደመወዝ እርከን ጭማሪ ወይም
የደመወዝ እርከን ጭማሪ እና ቦነሰ ይሰጣል፡፡
22.2 በአንቀጽ 22.1 መሠረት የሚሰጠው የደመወዝ ጭማሪ ወይም ቦነስ ወይም የደመወዝ ጭማሪና ቦነስ አፈፃፀም
እንደሚከተለው ይሆናል፡፡

22.2.1. በበጀት አመቱ ውስጥ የሚገኝ የተጣራ ትርፍ ከድርጅቱ ካፒታል ጋር ተነፃፅሮ እና ድርጅቱ የፊዚካል እቅዱን
80% ካጠናቀቀ በቀረበው ስሌት ማለትም ድርጅቱ በበጀት አመቱ ከተገኘው የተጣራ ትርፍ ጋር በማነፃፃር
ትርፉ ከካፒታሉ፡-
ሀ/ ከ 0.03 በላይ እስከ 0.05 ድረስ ከሆነ የ 1 ወር ደመወዝ ቦነስ፣
ለ/ ከ 0.05 በላይ እስከ 0.1 ድረስ ከሆነ የ 1.5 ወር ደመወዝ ቦነስ እና የአንድ (1) እርከን የደመወዝ
ጭማሪ፣
ሐ/ ከ 0.1 በላይ ከሆነ የ 2 ወር ደመወዝ ቦነስ እና የአንድ (1) እርከን የደመወዝ ጭማሪ ይደረጋል፡፡

22.2.2 በበጀት ዓመቱ ውስጥ የሚገኝ የተጣራ ትርፍ ከድርጅቱ ካፒታል ጋር ተነፃጽሮና ድርጅቱ የፊዚካል ዕቅዱን 90%
ካጠናቀቀ በቀረበው ስሌት ማለትም ድርጅቱ በበጀት ዓመቱ ከተገኘው የተጣራ ትርፍ ጋር በማነፃፀር ትርፉ
ከካፒታሉ፡-
ሀ/ ከ 0.05 በላይ እስከ 0.07 ድረስ ከሆነ የአንድ ተኩል (1.5) ወር ደመወዝ ቦነስ እና የአንድ (1) እርከን
የደመወዝ ጭማሪ፣
ለ/ ከ 0.07 በላይ እስከ 0.13 ድረስ ከሆነ የሁለት (2) ወር ደመወዝ ቦነስ እና የአንድ (1) እርከን የደመወዝ
ጭማሪ፣
ሐ/ ከ 0.13 በላይ ከሆነ የሁለት ተኩል (2.5) ወር ደመወዝ ቦነስ እና የሁለት (2)እርከን የደመወዝ
ጭማሪ ይደረጋል፡፡

22.3. በአንቀጽ 22.2 መሠረት ድርጅቱ እና ሠራተኛ ማህበሩ የተስማሙበት የደመወዝ ጭማሪና የቦነስ ክፍያ ስምምነት
የህብረት ስምምነቱ ማለቂያ ድረስ የፀና ይሆናል፡፡

22.4. አንድ ሠራተኛ ሙሉ በጀት ዓመቱን ካልራ የሚያገኘው ቦነስ በሰራበት ልክ እየተሰላ ይሆናል፡፡ የእርክን ጭማሬ
ለማግኘት ግን ቢያንስ የበጀት ዓመቱን ¾ ኛ ጊዜ ወይም ዘጠኝ ወር ያገለገለ መሆን አለበት፤

22.5. ሰራተኛ ቦነስ በሚከፈልበት በጀት ዓመት የሁለት ጊዜ ተከታታይ የስራ አፈፃፀም ውጤት ከ 60 በመቶ በታች ካገኘ
ቦነስም ሆነ የደመወዝ ጭማሪ አያገኝም፡፡ በበጀት ዓመቱ በሁለት ተከታታይ የሥራ አፈጻጸም ምዘና ውጤት
60 ከመቶ እና በላይ ያመጡ ሠራተኞች የቦነስ አከፋፈልም በሥራ አፈጻጸም ምዘና ውጤታቸው መሰረት
ይሆናል፡፡ አከፋፈሉም የሁለት ጊዜ የሥራ አፈጻጸም ውጤታቸው 60 ከመቶ እና በላይ ሆኖ አማካይ የሥራ
አፈጻጸም ውጤታቸው፡-

26 | P a g e
 80-100% ከሆነ የተፈቀደውን የቦነስ መጠን 100% ይሆናል፡፡
 70-79.99% ከሆነ የተፈቀደውን የቦነስ መጠን 90% ይሆናል፡፡
 60-69.99% ከሆነ የተፈቀደውን የቦነስ መጠን 80% ይሆናል፡፡

22.6. የጉርሻ /ቦነስ/ አፈፃፀምን በተመለከተ ተጨማሪ አፈጻጸም ደንብ/መመሪያ ማውጣት ሲያስፈልግ ድርጅቱና
ሠራተኛ ማኀበሩ በጋራ በሚያወጡት የአፈጻጸም ደንብ/ስምምነት መሠረት ተፈጻሚ ይሆናል፡፡

22.7. ቦነስ በሚፈፀምበት ጊዜ የስራ ውላቸው በተለያየ ምክንያት ተቋርጦ ለተሰናበቱ ሰራተኞች የቦነስ ክፍያ
ድርጅቱ ይፈጽማል፡፡ ነገር ግን የእርከን ጭማሪ አያገኙም፡፡ ይህ ተፈጻሚ የሚሆነው ክፍያው በተጀመረ በ 3
ወር ጊዜ ውስጥ ጥያቄው ከቀረበ ብቻ ነው ፡፡

22.8. የድርጅቱ ትርፍና ኪሣራ የሚመሰረተው የድርጅቱ የበጀት ዓመት ሂሳብ በውጪ ኦዲተሮች ተመርምሮ
መግለጫ ከተሰጠበት በኋላ ነው፡፡

22.9 ድርጅቱ የበጀት አመቱን ሂሣብ ዘግቶ በውጪ ኦዲተሮች አስመርምሮ ትርፍና ኪሣራውን ማወቅ ያለበት
ከሐምሌ 1/አንድ/ ቀን ጀምሮ ባለው 6/ስድስት/ ወር ጊዜ ውስጥ ይሆናል፡፡

22.10 የደመወዝ ጭማሪው ተግባራዊ የሚሆነው ትርፍ በተገኘበት አመት መጨረሻ ወር ቀጥሎ ባለው በአዲሱ
የበጀት አመት የመጀመሪያ ወር ሐምሌ 1 ጀምሮ ነው፡፡

22.11 መንግስት በማናቸውም ጊዜ የሚያደርገው የደመወዝ ልዩ ማሻሻያ ሲኖር የሥራ አመራር ቦርድ ተጠይቆ
ሲፈቀድ በድርጅቱ ሠራተኞች ደመወዝ ላይ እየተጨመረ ሊከፈል ይችላል፡፡

22.12 ትርፍ በተመዘገበበት ወይም ቦነስ በሚከፈልበት በጀት ዓመት በመደበኛ ትምህርት ላይ ላለ ሠራተኛ ቦነስም
ሆነ የደመወዝ እርከን ጭማሪ አይከፈለውም፡፡

22.13 በተራ ቁጥር 22.7 የተገለፀው ቢኖርም ቦነስ በሚገኝበት በጀት ዓመት በዲሲፕሊን የስራ ውሉ የተቋረጠ
ሰራተኛ ቦነስም ሆነ እርከን ጭማሪ አይከፈለውም፡፡

22.14 የሥራ ውል ጊዜያቸው ከአንድ ወር በላይ ክፍተት ሳይኖረው ከተወሰነ ጊዜ ቅጥር (ኮንትራት) ወደ ቋሚ
የተዛወሩ ወይም ከውጭ ተወዳዳሪዎች ጋር ተወዳድረው በማለፋቸው የተወሰነ ጊዜ ቅጥር ውላቸው ተቋርጦ
ላልተወሰነ ጊዜ የተቀጠሩ (ቋሚ) የሆኑ ወይም የተሻለ የደመወዝ ደረጃ ባለው የሥራ መደብ ላይ ከውጭ
ተወዳዳሪዎች ጋር ተወዳድረው በማለፋቸው በአዲስ ቅጥር ውል የተቀጠሩ ሠራተኞች ካሉ በደንቡና
በመመሪያው ላይ የሰፈሩትን መስፈርቶች እስካሟሉ ድረስ እንደማንኛውም ሠራተኛ የተፈቀደውን ቦነስም
ሆነ የደመወዝ ዕርከን ጭማሪ ያገኛሉ፡፡

27 | P a g e
22.15 በበጀት አመቱ ለረጅም ጊዜ በሕመም ፈቃድ ላይ ያሳለፋ ካሉ ጉዳዩ ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት የተፈጠረ
መሆኑን በማየት የስራ ውላቸው ለተቋረጠ ቦነስ ብቻ በሥራ ላይ ያሉ ካሉ ደግሞ የተፈቀደውን ቦነስም ሆነ
የደመወዝ ዕርከን ጭማሪ ያገኛሉ፡፡

አንቀጽ ሃያ ሦስት (23)


ቅድሚያ ደመወዝ

23.1. በድርጅቱ ላልተወሰነ ጊዜ የተቀጠረ ወይም ፕሮጀክት እስከሚጠነቀቅ ውል ላላቸው ለተወሰነ ጊዜ ቅጥር
ሠራተኛ አስቸኳይና የማይታለፍ ችግር ሲያጋጥመው 1/3 በላይ የሆነ ተቆራጭ የሌለበት መሆኑን አረጋግጦ
ከአንድ ወር ደመወዝ የማይበልጥ በአንድ የበጀት ዓመት ውስጥ ተከፍሎ የሚያልቅ የደመወዝ ቅድሚያ ክፍያ
በየዓመቱ ለአንድ ጊዜ ብቻ ሊሠጥ ይችላል፡፡

23.2. ሠራተኛው የወሰደውን የደመወዝ ብድሩን ለድርጅቱ በየወሩ ከደመወዙ ላይ 1/3 እየተቆረጠ ገቢ ይደረጋል፡፡
የሠራተኛው የሥራ ውል የሚቋረጥ ከሆነ ያለበትን ቀሪ ዕዳ ከሚከፈለው ገንዘብ ላይ ሙሉ ለሙሉ ቆርጦ
ያስቀራል፡፡

አንቀጽ ሀያ አራት (24)


ፈቃድ

"ፈቃድ" ማለት ሠራተኛው ከመደበኛ የሥራ ጊዜ ከደመወዝ ጋር ወይም ያለደመወዝ ከሥራ ቀሪ መሆን እንዲችል
የተፈቀደለት ጊዜ ማለት ነው፡፡

24.1. የዓመት ዕረፍት ፈቃድ

24.1.1. አንድ አመት ያገለገለ ሰራተኛ 18 የስራ ቀን የዓመት ዕረፍት ያገኛል፡፡

24.1.2. ከአንድ ዓመት በላይ ያገለገለ ሠራተኛ በ 18 ቀናት ላይ ለእያንዳንዱ ተጨማሪ ሁለት ዓመት የአገልግሎት
ዘመን 1/አንድ/ቀን እየታከለበት የዓመት ፈቃዱን ያገኛል፤

24.1.3. ምንም እንኳ ሠራተኛው የዓመት ፈቃድ መውሰድ መብቱ የተጠበቀ ቢሆንም በአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ
አዋጅ ቁጥር 1156/2011 አንቀጽ 79 ንዑስ አንቀጽ 2 እና 3 መሠረት የድርጅቱ የሥራ ሁኔታ ሲያስገድደው
የዓመት ፈቃድ ማስተላለፍ ይቻላል፤

24.1.4. የዓመት ዕረፍት ፈቃድ ሠራተኛው ሲጠይቅና ድርጅቱም ሲስማማ ለሁለት ዓመታት ሊተላለፍ ይችላል፤

28 | P a g e
24.1.5. የዓመት ዕረፍት ፈቃድ በገንዘብ ተለውጦ አይሰጥም፣

24.1.6. በዚህ አንቀጽ በተራ ቁጥር 24.1.5 የተገለፀው ቢኖርም የዓመት ዕረፍት ፈቃዱን አቋርጦ ሥራ እንዲገባ
በድርጅቱ ለሚጠራ ሠራተኛ የዓመት ዕረፍት ፈቃድ በአሰሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 1156/2011
አንቀጽ 80 ንዑስ አንቀጽ 2 መሠረት በገንዘብ ተለውጦ ይሰጠዋል፡፡

24.1.7. ማንኛውም የድርጅቱ ሠራተኛ የዓመት ፈቃድ ወስዶ ሳይጨርስ ቢታመምና በመካከሉም ከሐኪም
የሕመም ፈቃድ ካቀረበ የሕመም ፈቃድ ጊዜው ከዓመት ፈቃድ አይታሰብም፤

24.1.8. አንድን ሰራተኛ በሥራው ባህሪ ምክንያት ለተወሰነ ጊዜ የሚሰራው ስራ ከሌለው ድርጅቱ አስቀድሞ የ 10
ቀን ማስጠንቀቂያ በመስጠት የአመት ፈቃድ ሰጥቶ ማስወጣት ይችላል፡፡

24.1.9. የሙከራ ጊዜውን የጨረሰ ሠራተኛ ዓመት ሳይሞላው የሥራ ውሉ ሲቋረጥ በድርጅቱ ብቻ የሠራበት ጊዜ
ተተምኖ የሚገባውን የዕረፍት ጊዜ በገንዘብ ተለውጦ ይከፈለዋል፤

24.1.10. ሠራተኛው ሲለቅ ወይም ሲሰናበት ያልተጠቀመበት በህጋዊ መንገድ የተላለፈለት ቀሪ የዓመት እረፍት ቀናት
ካለው እስከ ሁለት በጀት ዓመት ወደ ኋላ ሄዶ በገንዘብ ታስቦ ይሠጠዋል፡፡

24.1.11. አንድ ሠራተኛ ያገለገለበት ጊዜ ከአንድ ዓመት በታች ከሆነ በአገልግሎት ዘመኑ ልክ ተመጣጣኝ የሆነ
ዕረፍት በዚያው በአገለገለበት ዘመን ይሰጠዋል፤

24.1.12. አንድ ሠራተኛ የዓመት ዕረፍት ፈቃድ ሳይከፋፈል ይሰጠዋል፤ ይሁን እንጂ ሠራተኛው ተከፋፍሎ
እንዲሰጠው ሲጠይቅና ድርጅቱም ሲስማማ ተከፋፍሎ ሊወስድ ይችላል፤

24.1.13 በመደበኛ/ በቀን/ ወይም በክረምት ፕሮግራም ከስራ ውጭ ሆነው እንዲማሩ የተፈቀደላቸው ሠራተኞች
በትምህርት ቆይታ ላይ እያሉ የዓመት እረፍት ፈቃድ አይታሰብላቸውም፡፡

24.1.14 ድርጅቱ ፈቅዶ ትምህርት ላይ ያለ ሰራተኛ ት/ቤት ከመግባቱ በፊት ያለው የአመት ዕረፍት ቀናት የሚቃጠል
ከሆነ ወደ ገንዘብ ተቀይሮ ይከፈለዋል፡፡

24.1.15 በየበጀት ዓመቱ በድርጅቱ የሥራ ባህሪ ምክንያት በክረምት/በአየር ፀባይ ችግር ምክንያት ፕሮጀክት ሲዘጋ
የፕሮጀክት ሰራተኞች (የተሽከርካሪ ኦፕሬተሮችን ጨምሮ) በዋናው መ/ቤት ወይም ሌላ በክረምት ወቅት
ባልተዘጋ ፕሮጀክት ላይ ለሥራ እስካልተፈለጉ ድረስ ያልተጠቀሙበትን የዓመት ፈቃድ ቀናት እንዲወስዱ
ይደረጋል፡፡ ሠራተኞች የዓመት ፈቃዳቸውን ጨርሰውም ፕሮጀክቱ ካልተከፈተ ወይም ድርጅቱ ሥራ መስጠት
ካልተቻለ ልዩ ፈቃድ ወስደው እንዲቆዩ ሊደረግ ይችላል፡፡

24.1.16. የድርጅቱ ወንድ ሰራተኛ ህጋዊ የጋብቻ (የክብር መዝገብ ሹም፤ የባሀል፤ የሀይማኖት) ከፋይሉ ጋር ከተያያዘና
ባለቤቱ ስለመውለዷ ማረጋገጫ ሲያቀርብ የ 5/አምስት/ተከታታይ ቀናት ፈቃድ ከደመወዝ ጋር ይሰጣል፡፡

29 | P a g e
24.2. የሕመም ፈቃድ

24.2.1. አንድ ሠራተኛ የሙከራ ጊዜውን ከጨረሰ በኋላ በሥራ ላይ በሚደርሰው ጉዳት ሳይሆን በሌላ ሕመም
ምክንያት ሥራ ለመሥራት ካልቻለ በዚህ አንቀጽ መሠረት የሕመም ፈቃድ ያገኛል፤

24.2.2. ማንኛውም ሠራተኛ በሕመም ምክንያት ከሥራ ሲቀር አሠሪው ስለ ሁኔታው ሊያውቅ የሚችል ወይም
ሠራተኛው ለማስታወቅ የማይችል ካልሆነ በቀር በማግስቱ ለአሠሪው ያሳውቃል፤

24.2.3. ማንኛውም ሠራተኛ የሕመም ፈቃድ የሚያገኘው በመንግስት በታወቀ የሕክምና ድርጅቶች ማለትም
ከሆስፒታል፣ ከጤና ጣቢያና ክሊኒክ ወይም ከግል ከፍተኛ ክሊኒክ ወይም ከግል ልዩ የህክምና ክሊኒክ ወይም
ከግል ሆስፒታል ተገቢ የሆነ የሕክምና የምስክር ወረቀት ሲያቀርብ ነው፤

24.2.4. ለህመም ፈቃድ የደመወዝ ክፍያ አፈፃፀም


ሀ/ ለመጀመሪያ ሁለት (2) ወር ከሙሉ ደመወዝ ጋር
ለ/ ለሚቀጥሉት ሁለት (2) የደመወዙን 75% ደመወዝ ጋር
ሐ/ ለሚቀጥሉት አራት (4) ወራት የደመወዙን 50%
መ/ ለሚቀጥሉት ሁለት (2) ወራት የደመወዙን 25%
ሰ/ ለሚቀጥሉት ሁለት (2) ወራት ያለ ደመወዝ
ረ/ ከዚህ በኋላ የማይሻለው ከሆነ የሥራ ውሉ ይቋረጣል፡፡

24.2.5. የኤች.አይ.ቪ/ኤድስ ህሙማን የሆኑ ሠራተኞች በሀኪም የተረጋገጠና ይህንኑ ማስረጃ ላቀረቡ ሰራተኞች
ሀ. ለመጀመሪያ ስምንት (8) ወራት ሙሉ ደመወዝና ለቀሪዎች
ለ. ለሚቀጥሉት አራት (4) ወራት ደግሞ 75% ደመወዝ
ሐ. ለሚቀጥሉት ስድስት (6) ወራት 50% ደመወዝ
እንዲከፈላቸው ይደረጋል፡፡
መ. ለሚቀጥሉት ስድስት (6) ወራት ያለ ደመወዝ
ሠ. ከዚህ በኋላ የማይሻለው ከሆነ የሥራ ውሉ ሊቋረጥ ይችላል፡፡

24.3. የወሊድ ፈቃድ

24.3.1. ነፍሰ ጡር የሆነች ሠራተኛ ከርግዝናዋ ጋር የተያያዘ ምርመራ ለማድረግ አሠሪው ከደመወዝ ጋር ፈቃድ
ይሰጣል፤ ሆኖም ሠራተኛዋ ከምርመራው በኋላ የሐኪም ማስረጃ ማቅረብ አለባት፤
24.3.2. ነፍሰጡር የሆነች ሠራተኛ ከመውለዷ በፊት ሐኪም እንድታርፍ ካዘዘ ከደመወዝ ጋር ዕረፍት ይሰጣታል፤

24.3.3. ነፍሰ ጡር የሆነች ሰራተኛ እወልዳለሁ ብላ ከገመተችበት ወይም ከወሊድ በፊት የቅድመ ወሊድ ፈቃድ
ሳትወጣ ስራ ላይ ካሳለፈች ይህ የቅድመ መወሊድ ፈቃድ ከወለደች በኋላ እንድትጠቀምበት ይደረጋል፡፡

30 | P a g e
24.3.4. ሠራተኛዋ ከመውለዷ በፊት የወሰደችው የ 30 ቀናት ፈቃድ ሲያልቅ ካልወለደች እስከምትወልድበት ቀን
ድረስ በአንቀጽ 24.3.2 መሠረት ዕረፍት ልታገኝ ትችላለች፡፡ የ 30 ቀን ፈቃዷ ሳያልቅ ከወለደች በአንቀጽ
24.3.3 መሠረት የምትወስደው የወሊድ ፈቃድ ይጀምራል፡፡
24.3.5 ሠራተኛዋ ከመውለዷ በፊት የወሰደችው 30 የስራ ቀናት የቅድመ ወሊድ ፈቃድ ሳያልቅ ካልወለደች
እስከምትወልድበት ቀን ድረስ በዚህ አንቀፅ 24.3.1 መሰረት እረፍት ልታገኝ ትችላለች፣
24.3.6 የ 30 የስራ ቀናት የቅድመ ወሊድ ፈቃዷ ሳያልቅ ከወለደች የ 90 ቀን የስራ ቀናት የድህረ ወሊድ ፈቃዷ
ይጀምራል፡፡
24.3.7 ድርጅቱ እንደ አስፈላጊነቱ በዋናው መ/ቤትና በቅ/ጽ/ቤት የህፃናት ማቆያ ሊያቋቁም ይችላል፡፡

24.4. የሐዘን ፈቃድ

24.4.1. የሐዘን ፈቃድ ለሠራተኛው የሚሰጠው በአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 አንቀጽ
81.1/ለ/ መሠረት ይሆናል፤ በተጨማሪም ከሠራተኛው ቤት አስከሬን ሲወጣ ነው፤

24.4.2. ሠራተኛው ሲሞት ከየክፍሉ የተውጣጡ ሠራተኞች በቀብሩ ሥነ-ሥርዓት ላይ እንዲገኙ ይደረጋል፡፡ በቀብር
ስነ-ስርዓቱ ለመገኘት ለሄዱት ሠራተኞች ብቻ የቀብሩ ሥነ-ሥርዓት እስኪፈፀም ድረስ ለቀብሩ ቀን ብቻ
ከደመወዝ ጋር ፈቃድ ይሰጣቸዋል፡፡
24.4.3 የድርጅቱ ዋና መ/ቤት በሚገኝበት ባህርዳር ላይና የቅ/ጽ/ቤቶች በሚገኙበት ከተማ ላይ የሠራተኛው ቤተሠብ
ሞቶ የቀብር ስነ ስርዓት በነዚሁ ከተሞች የሚፈፀም ከሆነ ሠራተኛው የሚሠራበት የስራ ሂደት ሠራተኞች
ብቻ በቀብር ስነ ስርዓቱ ላይ እንዲገኙ ቀብሩ እከሚፈጸምበት ጊዜ ብቻ ደመወዝ የሚከፈልበት ፈቃድ
ይሠጣቸዋል፡፡ ተሸከርካሪ ካለም ይመቻችላቸዋል፡፡ ሌሎች ሠራተኞች ማስተዛዘን ከፈለጉ ተሸከርካሪ
ከ 10፡30 ጀምሮ ተመቻችቶላቸው እንዲሄዱ ይፈቀድላቸዋል፡፡

24.5. ልዩ ልዩ ፈቃድ

24.5.1. ሠራተኛው ሕጋዊ ጋብቻ በሚፈፀምበት ጊዜ 4/አራት/ የስራ ቀናት ደመወዝ የሚከፈልበት የጋብቻ ፈቃድ
ይሰጣል፡፡

24.5.2. ሠራተኛው ከፖሊስ ጣቢያ፣ ከፍ/ቤት፣ ከሕዝባውያን ድርጅቶች ወይም ሕጋዊ ሥልጣን ባለው ሌላ አካል
ለምስክርነት ወይም ክርክር ሲኖርበት መጥሪያ በደረሰው ጊዜ በሚያቀርበው መረጃ መሠረት ፈቃዱ
ከደመወዝ ጋር ይሰጠዋል፡፡

24.5.3. በዚህ ኀብረት ስምምነት አንቀጽ 24.4.1 ላይ በተጠቀሰው ሐዘን ምክንያት ከሥራ ቦታው ውጪ የሚሄድ
ከሆነ ለጉዞ ደርሶ መልስ እንደቦታው ርቀት ከ 4 ቀናት ያልበለጠ ደመወዝ የሚከፈልበት ፈቃድ ይሰጠዋል፤

24.5.4. ሠራተኛው ከሥራው ጋር ግንኙነት በሌለው ሕመም ምክንያት ወደ ሌላ የሕክምና ቦታ ሄዶ እንዲታከም


በሐኪም ሲታዘዝ ሐኪሙ ካዘዘው ቀን ማግስት ጀምሮ ለደርሶ መልስ እንደቦታው ርቀት ከ 4 ቀናት

31 | P a g e
ያልበለጠ ደመወዝ የሚከፈልበት ፈቃድ ይሰጠዋል፤ በሚያቀርበውም የሕክምና ማስረጃ መሠረት
የሕመም ፈቃድ ክፍያ በዚሁ ኀብረት ስምምነት አንቀጽ 24.2.5 መሠረት ይፈፀማል፤

24.5.5. ማንኛውም ሠራተኛ ደመወዝ ከሚከፈልባቸው ፈቃዶች ሌላ ድርጅቱ ሲያምንበት ሠራተኛው


ለሚያጋጥመው ከአቅም በላይ ለሆነ ችግር በዓመት ደመወዝ የማይከፈልበት እስከ 30/ሠላሳ/ ቀናት ፈቃድ
ይሰጠዋል፤

24.6. የትምህርት ፈተና ፈቃድ


ሠራተኛው በትርፍ ጊዜው በሚከታተለው ትምህርት ፈተና የሚሰጠው በሥራ ሰዓት ከሆነ ሠራተኛው
በሚያቀርበው ማስረጃ መሠረት ለፈተናው ቀን ብቻ ድርጅቱ ከደመወዝ ጋር ፈቃድ ይሰጠዋል፤

24.7. ልዩ ፈቃድ
ማንኛውም ሠራተኛ /በድንገት/ ለሚያጋጥመው ችግር ወይም ሁኔታ ዓመት ፈቃዱን ከጨረሰ ደመወዝ
የሚከፈልበት በተከታታይ ከሁለት ቀን ያልበለጠ በዓመት ውስጥ ከሦስት ቀናት ያልበለጠ ልዩ ፈቃድ ድርጅቱ
ሲያምንበት ይሰጠዋል፤

24.8. ለማኀበር ሥራ የሚሰጥ ፈቃድ

የሠራተኞች ማኀበር መሪዎች የሥራ ክርክር ለማቅረብ የኀብረት ስምምነት ለመደራደር በማኀበር ስብሰባ ለመገኘት
በሴሚናሮችና በሥልጠና ለመካፈል እንዲችሉ ማኀበሩ ተካፋይ የሚሆኑትን ሠራተኞች ዝርዝር ለድርጅቱ
ሲያስታውቅ ድርጅቱ ደመወዝ የሚከፈልበት ፈቃድ ይሰጣል፤

አንቀጽ ሃያ አምስት (25)


የሥራ ልብስ
25.1. የሚታደሉ የሥራ ልብስ ጨርቆች ዓይነት፣ የጫማ ሞዴሎችና የንጽህና መስጫ እቃዎች

25.1.1. ይህ ህብረት ስምምነት ከፀደቀ በኋላ የሚቀርቡ የስራ ልብሶች በአገር ውስጥ ፋብሪካዎች የሚመረቱ ሆነው
ተሰፍተው የሚቀርቡ ብቻ ይሆናሉ፡፡ የሁሉም ጨርቆች ቀለምም አንድ አይነት ይሆናል፡፡
25.1.2 ለ 3/4 ኛ ካፖርት 70% ጥጥ እና 30% የሌሎች ጨርቆች ውህድ ያለው 1 ኛ ደረጃ ጨርቅ ሲሆን በጀርባው ላይ
የድርጅቱ አርማ ያለበት ሰፍቶ ከሚያቀርብ ፋብሪካ ተገዝቶ የሚቀርብ ይሆናል፡፡
25.1.3 የሚቀርበው ቱታ ከጀርባው ላይ የድርጅቱ አርማ ወይም ሎጎ የታተመበት ሙሉ ወይም ሜዞ ሲሆን የጨርቁ
አይነት ደግሞ 65% ጥጥ 35% የሌሎች ጨርቆች ውህድ ያለው 1 ኛ ደረጃ ጨርቅ ይሆናል፡፡ ግዥውም ሠፍቶ
ከሚያቀርብ ፋብሪካ ይፈፀማል፡፡

32 | P a g e
25.1.4 የወንዶች ኮትና ሱሪ 65% ጥጥና 35% የሌሎች ጨርቆች ውህድ ያለው 1 ኛ ደረጃ ጭርቅ ሲሆን ግዥው ደግሞ
ባህር ዳር ላይና ኮምቦልቻ ላይ ሰፍተው ማቅረብ ከሚችሉ ከተሻሉ ድርጅቶች ይሆናል፡፡
25.1.5 የሴቶች ሙሉና ጉርድ ቀሚስ 65% ጥጥና 35% የሌሎች ጨርቆች ውህድ ያለው 1 ኛ ደረጃ ጭርቅ ሲሆን
ግዥው ደግሞ ባህር ዳር ላይና ኮምቦልቻ ላይ ሰፍተው ማቅረብ ከሚችሉ ከተሻሉ ድርጅቶች ይሆናል፡፡
25.1.6 ሸሚዝ 65% ጥጥና 35% የሌሎች ጨርቆች ውህድ ያለው 1 ኛ ደረጃ ጭርቅ ሲሆን ግዥውም ሠፍቶ ማቅረብ
ከሚችል ፋብሪካ ይፈፀማል፡፡
25.1.7 የሴቶች የውስጥ ልብስ ጥራቱን የጠበቀ ቦብሊን ይሆናል፣
25.1.8 ለጥበቃ አገልግሎት የሚሠጠው ካፖርት ገበር ያለው ሆኖ የሱፍ ወይም የጥጥ ወይም የሴንቴቲክ ወይም የጥጥና
የሴንቴቲክ ውህድ ያለው ይሆናል፡፡
25.1.9 ለጥበቃ ሠራተኞች የሚሠጠው የዝናብ ልብስ ከሴንቴቲክ ወይም ከጥጥና ከሴንቴቲክ የተሰራ ይሆናል፡፡
25.1.10 አጭር ቆዳ ጫማና ሴፍቲ ጫማ ከአገር ውስጥ ፋብሪካዎች በቀጥታ የሚገዛ ሲሆን ጥራቱም ከጥቅማጥቅም፣
ከሠራተኛ ማህበሩ፣ ከኦፕሬተር፣ ከጥገና እና ከጥበቃ በተውጣጣ ኮሚቴ ይመረጣል፣ ተገዝቶ ሲመጣም
አረጋግጦ ገቢ እንዲሆን ይደረጋል፡፡
25.1.11 ለሁሉም ላልተወሰነ ጊዜና የተወሰነ ጊዜ/ስራ ቅጥር ሠራተኞች በወር ሁለት እያንዳንዱ 250 ግራም የልብስ
ሳሙና እና አንድ ትልቅ ሶፍት እንዲያገኙ ስርጭቱም በዋናው መ/ቤትና በቅ/ጽ/ቤቱ በጥቅል ግዥ ተገዝቶ
በንብረት ክፍል በኩል አሰራሩን ተጠብቆ የሚሰራጭ ይሆናል፡፡
25.1.12 ለሠራተኞች የሚሠጠው የደንብ ልብስና የንጽህና መስጫ እቃዎች መጠን በሚቀጥለው ሠንጠረዥ መሠረት
ይሆናል፡፡

ለስራ የሚያስፈልጉ የደንብ ልብስ ዓይነትና ብዛት

በዓመት የሚሰጠው የደንብ ልብስ


ተ/ቁ የደንብ ልብስ የሚያገኙ የስራ መደቦች ዝርዝር

ዓይነት መለኪያ ብዛት ምርመራ


ኮትና ሱሪ ቁጥር 1
አውቶሞቢል/የቀላል ተሽከርካሪ/ሚኒባስ / የዋና ሥራ ስራ ሙሉ ቱታ ቁጥር 1
1 አስፈጻሚ/ የምክትል ዋና ሥራ ስራ አስፈጻሚ/ የሰራተኛ ሰርቪስ
ኦፕሬተር ደ-1/2 ኦፕሬተር አጭር ቆ ዳ ጫማ ጥንድ 2

ሸሚዝ ቁጥር 2
ኮትና ሱሪ ቁጥር 1
መለስተኛ ካርጎ ትራክ (Isuzu) /፣ ውሀ ቦቴ/ነዳጅ ቦቴ/ካርጎ ትራክ
(ትልቅ) /ዳም ትራክ/ትራክ ማውንትድ ሚክሰር /ሎቤድ/ሀይቤድ/ ሙሉ ቱታ ቁጥር 1
ኦፕሬተር፣ የተሸከርካሪ የንድፈ ሀሳብና የተግባር አሰልጣኝ፣ረዳት
2 አጭር ቆዳ ጫማ ጥንድ 1
ሀይቬድ/ ሎቤድ/ትራክ ማውንትድ ሚክሰር/ኮንክሪት ፓምፕ/ ባችንግ
ፕላንት/ኦፕሬተር፣ረዳት ባችንግ ፕላንት ደ.1/2 ኦፕሬተር ፣ረዳት ሴፍቲ ጫማ ጥንድ 1
ኮንክሬት ፓምፕ አፕሬተር/፣የቀላል ማሽነሪ የተግባር አሰልጣኝ
ሸሚዝ ቁጥር 2
3 ግሬደር/ዶዘር/ኤክስካቬተር/ሎደር/ባክሁ ሎደር/ ሮለር ትልቁና ኮትና ሱሪ ቁጥር 1
ትንሹ/ክሬሸር ደ.1/2/ ዋገን ድሪል/ ዳምፐር/ ቡም ክሬን/ ካርጎ ክሬን
/ሀንድ ድሪል/ፎርክ ሊፍት/ ትራክተር ኦፕሬተር፣ ደረጃ-1 እና ረዳት ሙሉ ቱታ ቁጥር 1
ደ-1/ግሬደር/ዶዘር/ኤክስካቬተር/ኦፕሬተር፣ የትልቅ/የትንሽ ክሬሸር ሴፍቲ ጫማ ጥንድ 2
ረዳት ደ.1/2/፣ረዳት ዋገን ድሪል ደ.1/2፣ ረዳት ሸሚዝ ቁጥር 2

33 | P a g e
ለስራ የሚያስፈልጉ የደንብ ልብስ ዓይነትና ብዛት

በዓመት የሚሰጠው የደንብ ልብስ


ተ/ቁ የደንብ ልብስ የሚያገኙ የስራ መደቦች ዝርዝር

ዓይነት መለኪያ ብዛት ምርመራ

ቡምክሬን፣የግሬደር/የዶዘር /የኤክስካቫተር/ የሎደር የተግባር


አሰልጣኝ

ሙሉ ቀሚስ ቁጥር 2

ውስጥ ልብስ ቁጥር 2


ጽዳት፣ ተላላኪና ጽዳት ሰራተኛ፣ተላላኪ፤የክሊኒክ ካርድና ጽዳት
4 ሽርጥ (ለጽዳት ፣
ሰራተኛ (ሴት)
ተላላኪና ጽዳት ቁጥር 2
ሰራተኛ ብቻ)
አጭር ቆዳ ጫማ ጥንድ 2
ኮትና ሱሪ ቁጥር 2
ሸሚዝ (ለተላላኪ ብቻ) ቁጥር 2

5 ጽዳት፣ ተላላኪና ጽዳት ሰራተኛ፣ተላላኪ (ወንድ) ሽርጥ (ለጽዳት ፣


ተላላኪና ጽዳት ቁጥር 2
ሰራተኛ ብቻ)
አጭር ቆዳ ጫማ ጥንድ 2
ኮትና ሱሪ ቁጥር 1
ሙሉ ቱታ ቁጥር 1
ሸሚዝ ቁጥር 2

አጭር ቦት የቆዳ
ጥንድ 1
6 አትክልተኛና የግቢ ውበት ሠራተኛ/ወንድ/ሴት ጫማ/ለወንድ

አጭር ቆዳ ጫማ/ለሴት ጥንድ 1

የላስቲክ ቦት ጫማ ጥንድ 1
የዝናብ ልብስ ቁጥር 1
ኮትና ሱሪ ቁጥር 2

ጥበቃ ሰራተኛ፣ የጥበቃ ሽፍት መሪ፤ የጥበቃ ተቆጣጣሪ/ /ወንድ/ ሸሚዝ ቁጥር 2
7
እና ፖስተኛ ወ/ሴ አጭር ቆዳ ጫማ ጥንድ 2
ካልስ (ፖስተኛን ጥንድ 2

34 | P a g e
ለስራ የሚያስፈልጉ የደንብ ልብስ ዓይነትና ብዛት

በዓመት የሚሰጠው የደንብ ልብስ


ተ/ቁ የደንብ ልብስ የሚያገኙ የስራ መደቦች ዝርዝር

ዓይነት መለኪያ ብዛት ምርመራ


አይመለከትም)
በየ 3
የዝናብ ልብስ ቁጥር 1
ዓመቱ
ካፖርት (ፖስተኛን በየ 3
ቁጥር 1
አይመለከትም) ዓመቱ
ብርድ ልብስ (ለጥበቃ
በየ 5
ብቻ) ቁጥር 1
ዓመቱ

ጉርድ ቀሚስ ቁጥር 1


ውስጥ ልብስ ቁጥር 1
አንድ ወጥ ሸሚዝና ሱሪ በቁጥር 1
ሸሚዝ ቁጥር 1
አጭር ቆዳ ጫማ ጥንድ 2
8 ጥበቃ ሰራተኛ፣ የጥበቃ ሽፍት መሪ፤ የጥበቃ ተቆጣጣሪ/ሴት
ካልስ ጥንድ 2
በየ 3
የዝናብ ልብስ ቁጥር 1
ዓመቱ
ብርድ ልብስ በየ 5
ቁጥር 1
ዓመቱ
አጭር ቆዳ ጫማ ጥንድ 2
የሰራተኛ ማህደር አስተዳደር ባለሙያ፤የመረጃ ዴስክና ስልክ
ኦፕሬተር፤የኮምፒውተር አካል ጥገናና ድጋፍ ከፍተኛ
ባለሙያ፤የኔትዎርክ ማስተዳደር ከፍተኛ ባለሙያ ግንባታ
9 ቤተመጽሀፍትና ሬጅስትራል ባለሙያ፤የሲስተም ልማትና 3/4 ኛ ካፖርት ቁጥር 1
አስተዳደር ከፍተኛ ባለሙያ፤የፕሮጀክት አይሲቲ ባለሙ፣የአይሲቲ
የስራ ሂደት ሀላፊ፣መሳሪያ ጥገና/የመሳሪያ ኤሌክትሪክ፣ቦዲና ብየዳ
ጥገና ንዑስ የስራ ሂደት ዳታ ኢንኮደር፣የሂሳብ ሠነድ ያዥ፣
3/4 ኛ ካፖርት ቁጥር 1
10 ቀያሽ ከደረጃ-1 እሰከ ደረጃ-5 ፣የቅየሳ ቡድን አስተባባሪ
ሴፍቲ ጫማ ጥንድ 2

ሙሉ ቱታ 1

ሚኒ ቱታ 1
ዕቃ ግ/ቤት ሰራተኛ ደረጃ 3 (ነዳጅ፣ ዘይትና ቅባት)፤ጀነሬተር
11
ኦፕሬተርና የተሸከርካሪ ፓርኪንግ ተቆጣጣሪ
ሴፍቲ ጫማ/
ለፓርኪንግ ተቆጣጣሪ ጥንድ 1
ጉርድ ቆዳ ጫማ/

35 | P a g e
ለስራ የሚያስፈልጉ የደንብ ልብስ ዓይነትና ብዛት

በዓመት የሚሰጠው የደንብ ልብስ


ተ/ቁ የደንብ ልብስ የሚያገኙ የስራ መደቦች ዝርዝር

ዓይነት መለኪያ ብዛት ምርመራ


የክሊኒክ ሀላፊ፤ ክሊኒካል ነርስ፣ የህክምና ላቦራቶሪ ቴክኒሻን፤
12 ነጭ ጋዋን ቁጥር 1
ፋርማሲስት፣

ረዳት ዕቃ ግ/ቤት ሰራተኛ፣ዕቃ ግምጃ ቤት ሰራተኛ ከደ.1 እሰከ ደ-4፤


ስቶክ ክለርክ ፣የሰነድ ህትመት፣ ስርጭትና ቁጥጥር ባለሙያ፤ንብረት
ምዝገባና ቁጥጥር ባለሙያ፣የሽያጭና ንብረት ማስወገድ ባለሙያ 3/4 ኛ ካፖርት ቁጥር 1
፣የቢሮ ቋሚ እቃዎች አስተዳደርና ክትትል ባለሙያ ፣ የተሸከርካሪ፣
ማሽነሪና ኢኪዩፕመንት አስተዳደርና ክትትል ከፍተኛ ኦፊሰር ፣
የተሸከርካሪ፣ ማሽነሪና ኢኪዩፕመንት ግባዓት አስተዳደርና ክትትል
ከፍተኛ ኦፊሰር፣ የኮንስትራክሽን ግባዓት አስተዳደርና ክትትል
ከፍተኛ ባለሙያ፣የቢሮ አገልግሎት የሚውሉ እቃዎች ቡድን
13 አስተባባሪ፣የተሸከርካሪ ማሸነሪና ኢኪዩፕመንት አስተዳደር ንዑስ
የስራ ሂደት ሀላፊ ፣የኮንስትራክሽን ግባዓቶች አስተዳደር ንዑስ
የስራ ሂደት ሀላፊ፣ ንብረት አስተዳደር የስራ ሂደት ሀላፊ ፣ጠቅላላ
አገልግሎት አስተባባሪ፣የመሳሪያ ቱልስ ሠራተኛ፣ የኢንሹራንስና
አደጋ ክትትል ባለሙያ፣ የጥገና ማቴሪያል አቅርቦትና ክትትል
ባለሙያ፤የኢንሹራንስና የውጭ ጥገና ክትትል ባለሙያ ፤የጥገና አጭር ቆዳ ጫማ ጥንድ 1
ጥያቄ አረጋጋጭና ክትትል ባለሙያ፣ የጥገና እቅድ መረጃ ዝግጅትና
ተንታኝ ባለሙያ፣የመሳሪያ ጥገና እቅድና የጥራት ክትትል ቡድን
አስተባባሪ፣የማሽነሪ የንድፈ ሀሳብ አሰልጣኝ

15 CAD ቴክኒሻን ፤ድራፍት ፐርሰን (የንድፍ ባለሙያ) ፣ኳንቲቲ


ሰርቨየር፣ የውሃ ፕሮጀክት መሀንዲስ ሱፐርቫይዘር ከደ.2 እሰከ ደ-4፣
ኤሌክትሮ ሜካኒካል/ ኤሌክትሪካል መሀንዲሰ‹ የቢሮ ኤሌክትሪካል
መሀንዲስ፤የውሃ ፕሮጀክት ጨረታ ሰነድ ዝግጅትና ዲዛይን ግምገማ 3/4 ኛ ካፖርት ቁጥር 1
መሀንዲስ ደ.3 እና ደ-4፣ህንጻና ሌሎች ሲቪል ስራዎች ሱፐርቫይዘር
መሀንዲስ ደ. 3 እና ደ-4፣የክትትል፣ ክፍያ ዝግጅትና የክሌም
ጉዳዮች መሀንዲስ ደ-3 እና ደ-4፣ዲዛይንና ማቴሪያል አረጋጋጭ
መሀንዲስ፣የውሃ ፕሮጀክት ውል እና የሱፐርቪዥን ሰነዶች አዘጋጅ
መሀንዲስ ደ-4፣የህንጻና ሌሎች ሲቪል ሥራዎች ውልና ሴፍቲ ጫማ ጥንድ 1
የሱፐርቪዥን ሰነዶች አዘጋጅ መሀንዲስ ደ-4፣የውል አዋጭነት
ግምገማና የዋጋ ትንተና መሀንዲስ ደ-4፣ ጀማሪ
መሀንዲስ፣መሀንዲስ ከደ.2፣ እሰከ ደ-4፣ሳይት ወይም ቢሮ መሀንዲስ
ከደ-1 እሰከ ደ-4 ፣ጅኦሎጅስት፣የኢንሹራንስ፣ ፈቃድና ቦሎ
ባለሙያ፣የኢኩፕመንት ሥርጭትና ክትትል ኦፊሰር፤የኢኩፕምንት
አስተዳደርና ጥገና ባለሙያ፤ከፍተኛ የመሳሪያ ሁኔታ ክትትልና
ትንተና ኦፊሰር፣ መሳሪያ አስተዳደርና ስምሪት ባለሙያ፣የግባት
አቅርቦትና አጠቃቀም ክትትል ኦፊሰር ፣የከባድ /የቀላል ተሽከርካሪ/
የከባድና ቀላል ማሽነሪ/ ስምሪትና ክትትል ባለሙያ ወይም

36 | P a g e
ለስራ የሚያስፈልጉ የደንብ ልብስ ዓይነትና ብዛት

በዓመት የሚሰጠው የደንብ ልብስ


ተ/ቁ የደንብ ልብስ የሚያገኙ የስራ መደቦች ዝርዝር

ዓይነት መለኪያ ብዛት ምርመራ

አስተባባሪ፤የመሳሪያ አጠቃቀም /የመሳሪያ አጠቃቀምና ስምሪት/


መሳሪያ ጥገና ንዑስ የስራ ሂደት ኃላፊ፣

3/4 ኛ ካፖርት ቁጥር 1


መሳሪያ አስተዳደርና ጥገና /መሳሪያ አጠቃቀም ቡድን
አስተባባሪ፤መሣሪያ ጥገና/መሣሪያ
አስተዳደር/ /ማንፋክቸሪንግ/መሳሪያ አስተዳደርና ጥገና/ኤልክትሮ
መካኒካልና የቀላል ኢኩፕመንቶች አስተዳደርና ጥገና የስራ ሂደት
ሀላፊ፤ የፕሮጀክት ክትትል ሀላፊ፣የውሃ ወይም የህንጻና ሌሎች
ሲቪል ስራዎች ዋና መሀንዲስ፣የጨረታ ሰነድ ዝግጅት፣ ዲዛይን
ግምገማና ሱፐርቪዥን የስራ ሂደት ኃላፊ፣ኮንትራት አስተዳደር /
የኮንስትራክሽን ኦፕሬሽን ዋና የስራ ሂደት ሀላፊ፣የኮንስትራክሽን
15
/መሣሪያ አስተዳደርና ጥገና ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ፣የዋና ሥራ
አስፈጻሚ አማካሪ፣ዋና ሥራ አስፈጻሚ፣የክትትል፣ ክፍያ ዝግጅትና
የክሌም ጉዳዮች /የውል አዋጭነት ግምገማና የዋጋ ትንተና/ውሃ
ኮንስትራክሽን /ህንጻና ሌሎች ሲቪል ስራዎች ኮንስትራክሽን/የሥራ
ሂደት ሀላፊ፣የኮንስትራክሽን ዘርፍ ዋና ምህንድስና
አስተባባሪ፣ኮንስትራክሽን ኦፕሬሽን /የኮንትራት አስተዳደር ቡድን
አስተባባሪ ፣ፕሮጀክት ሥራ አስኪያጅ፣ሳኒተሪ መሀንዲስ ደ-1
፣ኦዶቪዥዋል ባለሙያ፣ ኮንስትራክሽ ላቦራቶሪ ቴክኒሻን
ሴፍቲ ጫማ ጥንድ 1

ሙሉ ቱታ ቁጥር 1
ቧንቧ ሠራተኛ ፎርማን፣ጀማሪ ቧንቧ ሠራተኛ፣ቧንቧ ሠራተኛ
16
ከደ.1-ደ.5፣ጀመሪ ፎርማን፤ ኮንስትራክሽን ፎርማን ከደ.1-ደ.5፤
ሚኒ ቱታ ቁጥር 1
ሴፍቲ ጫማ ጥንድ 2
17 ረዳት መካኒክ ደ.1/2፣መካኒክ ከደ.1-ደ.4፣ረዳት በያጅ 1/2፣በያጅ ሚኒ ቱታ ቁጥር 1
ከደ.1- ደ.4፣ ረዳት የአካል ቅጥቀጣና እድሳት ባለሙያ 1/2 ፣ የአካል ሙሉ ቱታ ቁጥር 1

37 | P a g e
ለስራ የሚያስፈልጉ የደንብ ልብስ ዓይነትና ብዛት

በዓመት የሚሰጠው የደንብ ልብስ


ተ/ቁ የደንብ ልብስ የሚያገኙ የስራ መደቦች ዝርዝር

ዓይነት መለኪያ ብዛት ምርመራ

ሴፍቲ ጫማ ጥንድ 2

ቅጥቀጣና እድሳት ባለሙያ ከደ-1-ደ.4፣የኤሌክትሮ መካኒካል


ባለሙያ ከደ.2-ደ.4፣የሸራ ሪቬት ባለሙያ፣የኢንጀክስን ፓምፕ
ከፍተኛ ባለሙያ/ቴክኒሽያን፣የሆዝ መጭመቂያ
ባለሙያ፣የግሪስ፣የጎሚስታና ዕጥበት ባለሙያና ተቆጣጣሪ፣እጥበትና
ግሪስ ሰራተኛ፣የጎማ ጥገና ባለሙያ፣የራዲያተር ጥገና
ባለሙያ/ከፍተኛ ባለሙያ፣ጀኔራል መካኒክ፣ረዳት ማሽኒስት- 200 ግራም ኦሞ ቁጥር 2 በወር
1/2፣ማሽኒስት፣ሲኔር ማሽኒስት፣ስቴሽነሪ ሚክሰር ኦፕሬተር፣የቀላል
ኢኩፕመንት አስተዳደርና ጥገና /ኤሌክትሮ መካኒካል/ተሸከርካሪ
ሙሉ ቱታ ቁጥር 1
ሁለገብ የቢሮ ጥገናና አገልግሎት ኦፊሰር፣ የመሳሪያ መካኒካል ጥገና
18 3/4 ኛ ካፖርት ቁጥር 1
/የመሳሪያ ኤሌክትሪክ፣ቦዲና ብየዳ ጥገና ንዑስ የስራ ሂደት ሀላፊ
ሴፍቲ ጫማ ጥንድ 2
3/4 ኛ ካፖርት ቁጥር 1
19 ማባዣናፎቶኮፒባለሙያ
ጉርድ ቆዳ ጫማ ቁጥር 1

የመሳሪያ ረዳት ኤሌክትሪሻን ደ-1/2፤የመሳሪያ ኤሌክትሪሻን ከደ.1- ሙሉ ቱታ ቁጥር 1


ደ.4፣ሁለገብ የቢሮ ጥገናና አገልግሎት ኦፊሰር፣የመሳሪያ 3/4 ኛ ካፖርት ቁጥር 1
20
ኤሌክትሪካል ጥገና ቡድን አስተባባሪ፣ የመሳሪያ መካኒካል ጥገና
/የመሳሪያ ኤሌክትሪክ፣ቦዲና ብየዳ ጥገና ንዑስ የስራ ሂደት ሀላፊ ሴፍቲ ጫማ ጥንድ 2

200 ግራም ኦሞ ቁጥር 2 በወር

25.2 የሥራ ልብሶች አሰጣጥና አጠቃቀም ሁኔታ

38 | P a g e
5.2.1 ድርጅቱ በአንድ የበጀት ዘመን የሚሰጠው የሥራ ወይም የደንብ ልብስ በቁጥር ከአንድ በላይ ከሆነ
በዚህ ኀብረት ስምምነት አንቀጽ 5.2.13 "ሀ" እና "ለ" በተገለፀው መሠረት ያድላል፤ ይሁን እንጂ የሚሰጠው
የሥራ ልብስ በቁጥር 1/አንድ/ ከሆነ በዚህ ኅብረት ስምምነት አንቀጽ 5.2.13 "ሀ" በተጠቀሰው ጊዜ ይሰጣል፤

5.2.2 ማንኛውም ሠራተኛ የሚሰጠውን የሥራ ወይም የደንብ ልብሶች በጥንቃቄ በመያዝ በሥራ ቦታና
ሰዓት ዘወትር የመልበስ ግዴታ አለበት፡፡

5.2.3 የደንብ ልብስ ተሰጥቶት ያልለበሰ ሰራተኛ በህብረት ስምምነቱ በተቀመጠው የቅጣት ደረጃ መሰረት
ይቀጣል ፡፡

5.2.4 የደንብ ልብስም ሆነ የንጽህና መስጫ እቃዎች ተገዝተውለት በ 6 ወር ውስጥ ያለወሰደ ሰራተኛ
የሚያቀርበው የይሰጠኝ ጥያቄ ተቀባይነት የለውም፡

5.2.5 የአደጋ መከላከያ የሙያና ደህንነት ባለሙያ እያጠና በሚያቀርበው መሰረት በድርጅቱ የሚቀርብ
ይሆናል፡፡

አንቀጽ ሀያ ስድስት (26)


የአገልግሎት ክፍያና የጉዳት ካሣ ክፍያ
26.1. የሥራ ስንብት ክፍያ በአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 አንቀጽ 39፣ 40 እና 41 መሠረት
ይፈጸማል፤

26.2. ማንኛውም ሠራተኛ በሥራ ላይ እያለ ጉዳት ሲደርስበት የጉዳት ክፍያውን በተመለከተ በአሠሪና ሠራተኛ
ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 አንቀጽ 109 ላይ በሰፈረው መሠረት ይፈጸማል፤

26.3. በሥራ ምክንያት ስለሚመጣ በሽታ በአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 አንቀጽ 98 ላይ
በሰፈረው መሠረት ይፈጸማል፤

26.4. በሥራ ላይ የሚደርስ አደጋ በአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 አንቀጽ 97 ላይ በሰፈረው
መሠረት ይፈጸማል፤

26.5. የአካል ጉዳት መጠን ደረጃዎችና ስለ አካል ጉዳት መጠን አወሳሰን በአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር
1156/2011 በአንቀጽ 99፣ 100፣ 101፣ 102 በሠፈረው መሠረት ይፈፀማል፤

አንቀጽ ሃያ ሰባት (27)


ጡረታ
27.1. አግባብ ያለው የመንግስት የጡረታ ሕግ በድርጅቱ ውስጥ ተፈፃሚ ይሆናል፤

ክፍል አምስት
የሥነ-ሥርዓት ደንቦችና አፈፃፀማቸው
አንቀጽ ሃያ ስምንት (28)

39 | P a g e
የቅጣት ደንብ

28.1. በድርጅቱና በማኀበሩ የሚወከሉ እኩል አባሎች /ሰብሳቢውን ሳይጨምር/ የሚገኙበት የዲስፕሊን ኮሚቴ
በድርጅቱ ዋና መ/ቤት ወይም በሥሩ ባሉ ቅ/ጽ/ቤቶች ይቋቋማል፤ ሰብሳቢው በድርጅቱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ
ወይም በቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ ይወከላል፤

28.2. ማንኛውም የዲሲፕሊን ጉዳዩች በድርጅቱ ወይም በቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቱ በተቋቋመው የዲስፕሊን ኮሚቴ
አማካኝነት ይታያሉ፡፡ ሆኖም ከሥራ ላይ በመቅረትና ማርፈድ ምክንያት የሚወሰድ የዲስፕሊን እርምጃ
ከደመወዝ ቅጣት እስከ ሥራ ውል ማቋረጥ (ስንብት) ድረስ ያለው በሰው ኃይል ሥራ አመራር ኦፊሰሮች በኩል
አስተያየት እየቀረበ በሰው ኃይል አስተዳደር ኃላፊ የሚወሰን ይሆናል፡፡

28.3. የሰራተኛው የቅርብ ሀላፊ እስከ ጽሁፍ ማስጠንቀቂያ ድረስ ያሉትን የዲስፕሊን እርምጃዎች ለዲስፕሊን
ኮሚቴ ማቅረብ ሳያስፈልግ በራሱ ቀጥታ ሊወስድ ይችላል፡፡

28.4. የዲስፕሊን ኮሚቴ ያጣራቸውን ጉዳዮች ለድርጅቱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ወይም ለቅ/ጽ/ቤት ኃላፊው የውሳኔ
ሀሳብ ያቀርባል፡፡ የድርጅቱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ወይም የቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ የቀረበለትን የውሳኔ ሀሳብ ከህግ
አንጻር መርምሮ ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል ሊቀበለው ወይም ሊሽረው ይችላል፡፡ በመጨረሻም የራሱን
ውሳኔ ያስቀምጣል፡፡

28.5. የዲሲፕሊን ቅጣት ወይም አፈፃጸም በሰራተኛው ማህደር ውስጥ በሪከርድነት ተይዞ በሰራተኛው ላይ ሊጠቀስ ወይም የደረጃ
እድገት ሊያሳግድ ወይም ነጥብ ለማስቀነስ የሚቻለው ከዚህ በታች በተመለከተው ሰንጠረዥ መሰረት ይሆናል፡፡

ለደረጃ እድገት ቅጣቱን


ለማህደር
ታግደው ከጨረሱ በኋላ
ጥራት
ተ.ቁ የተወሰደው የዲስኘሊን እርምጃ የሚቆዩበት ነጥብ እተቀነሰ
የሚስጥ ነጥብ
ጊዜ/የቅጣት ጊዜ የሚወዳደሩበት
ከ 10%
ጊዜ
ከደረጃና ደመወዝ ዝቅ ማድረግ (ከባድ) 1 ዓመት ከስድስት ------ ------
1
ወር
ከአንድ ወር በላይ እስከ ሦስት ወር 9 ወር -------- ---------
2 የደመወዝ ቅጣት (ከባድ)

እስከ አንድ ወር የደመወዝ ቅጣት 6 ወር


3
(ቀላል)
የፅሁፍ ማስጠንቀቂያ ቅጣት (ቀላል) ---- 3 ወር 9
4

5 ምንም የቅጣት ሪከርድ የሌለበት ---- ----- 10

40 | P a g e
28.6. የቅጣት ዘመኑን የጨረሰ ሠራተኛ ገደቡ ካለቀበት ጊዜ ጀምሮ የደረጃ ዕድገት የመወዳደር መብቱ
ይጠብቅለታል፡፡ በዕድገት አግባብ ካልሆነ በስተቀር ዝቅ ከማለቱ በፊት ወደ ነበረበት የሥራ መደብ ቀጥታ
መመደብ አይችልም፡፡ እንዲሁም ከማርፈድና ከስራ መቅረት ጋር በተያያዘ የሚሠጥ ቅጣት ለማነኛውም
ውድድር ውጤት አያስቀንስም፡፡

28.7. የዲሲፕሊን እርምጃ ከመወሰዱ በፊት የጥፋቱ ሁኔታና ክብደት በሚገባ መመርመር ይገባዋል፤ እንዲሁም
የዲሲፕሊን እርምጃ የሚወሰደው ሠራተኛውን ከጥፋቱ ለማረም ሥራው እንዳይበደል ለመቆጣጠርና ሌሎች
ሠራተኞች ተመሣሣይ ጥፋት እንዳይፈጽሙ ትምህርታዊ እንዲሆን ነው፤

28.8. ከቃል ማስጠንቀቂያ በስተቀር በአንድ ሠራተኛ ላይ የሥነ-ሥርዓት እርምጃ በሚወሰድበት ወቅት የጥፋቱን
ዝርዝር ሁኔታ በጽሁፍ እንዲያውቀው ይደረጋል፤ ይህንንም ሠራተኛው ፈርሞ እንዲወስድ ድርጅቱ ያደርጋል፤
ፈርሞ ለመቀበል ፈቃደኛ ካልሆነ ወይም አስፈርሞ ለመስጠት ባይቻል በድርጅቱ የውስጥ ማስታወቂያ ሰሌዳ
በሚሰራበት ፕሮጀክት የውስጥ ማስታዎቂያ ቢያንስ ለአምስት ቀን ተለጥፎ እንዲቆይ ይደረጋል፤ በዚህም
ሠራተኛው ደብዳቤውን እንዳወቀ ወይም እንደተቀበለው ይቆጠራል፤

28.9. በማንኛውም ሁኔታ የሚወሰድ የሥነ-ሥርዓት እርምጃ በግልባጭ ማህበሩ እንዲያውቀው ይደረጋል፤

28.10. ሠራተኛው በሚወስደው የሥነ-ሥርዓት እርምጃ ላይ ቅር የተሰኘ ከሆነ በቅሬታ አቀራረብ የሥነ-ሥርዓት
መሠረት ጉዳዩን በይግባኝ ለሚመለከተው አካል ያቀርባል፤

28.11. ጥፋቱ ከሥራ የሚያሰናብት ከሆነ ድርጅቱ ሠራተኛውን ወዲያውኑ ሥራ እንዲያቆም በማድረግ በአንድ ወር
ጊዜ ውስጥ ጉዳዩን አጣርቶ ውሳኔ እንዲያገኝ ያደርጋል፤ ሥራ እንዲያቆምም የሚደረገው በድርጅቱ ንብረት
ላይ ጉዳት የሚያደርስ፣ በባልደረቦቹ ላይ አደጋ የሚያስከትል ወይም የድርጅቱ ሥራ እንዳይሠራ የሚያደርግ
መሆኑ ሲረጋገጥና ወይም ተመሣሣይ ጥፋት ሲፈጽም ነው፤

28.12. እገዳው የሚፀናው ደብዳቤውን ፈርሞ ከተቀበለበት ቀን ወይም የእገዳው ውሣኔ በማስታወቂያ ሠሌዳ
ከተለጠፈ ማግስት ጀምሮ ይሆናል፤

28.13. የድርጅቱ ዋና ስራ አስፈጻሚ ሠራተኛውን በማገድና የታገደበትን ምክንያት በመግለጽ የዲሲፕሊን ክስ


እንዲመሰርት ለህግ፣ ስነምግባርና መልካም አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ያሳውቃል፡፡ የለህግ፣ ስነምግባርና
መልካም አስተዳደር ዳይሬክቶሬትም መረጃዎችን አደራጅቶ ክስ ይመሰርታል፤ የዲሲፕሊን ኮሚቴውም
ጉዳዩን አጣርቶ የመጨረሻ ውሣኔ እንዲሰጥበት ለዋና ሥራ አስፈጻሚ የመጨረሻ የውሳኔ ሃሳብ ያቀርባል፤

28.14. ለውሣኔ መዘግየት ሠራተኛው እራሱ ምክንያት ካልሆነ በስተቀር ከ 30/ሰላሳ/ ቀናት በላይ ከሥራ አግዶ
ማቆየት አይቻልም፤ በዚህ የጊዜ ገደብ ውስጥ ውሣኔ ካላገኘ ደመወዝ እየተከፈለው ውሣኔውን ይጠባበቃል፤

28.15. በሠራተኛው ምክንያት በሁለት ወር ጊዜ ውስጥ ውሣኔ መስጠት ካልተቻለም ይህም በማስረጃ ሲረጋገጥ
ድርጅቱ ደመወዝ ሳይከፈለው ከሥራ ሊያሰናብተው ይችላል፤

28.16. የዲሲፕሊን እርምጃ የሚወሰደው ሠራተኛን ከጥፋቱ ለማረምና ለማስተካከል በመሆኑ አንድ ሠራተኛ
በአንድ ጊዜ የተለያዩ ጥፋቶች ቢፈጽም ሊቀጣ የሚችለው በፈፀመው ከፍተኛ ጥፋት ብቻ ይሆናል፤

41 | P a g e
28.17. በአዋጁና በህብረት ስምምነቱ ያለማስጠንቀቂያና በማስጠንቀቂያ ከሥራ ከሚያሰናብቱ ጥፋቶች በስተቀር
በአንድ ሠራተኛ ላይ ዲሲፕሊን እርምጃ ሲወሰድ የሚወሰደው ቅጣት ስለጥፋትና ቅጣት ዓይነቶች
በሚያመለክተው ሠንጠረዥ መሠረት ነው፤

28.18. ለጥፋትና ቅጣት ዓይነቶች በሚያመለክተው ሠንጠረዥ ላይ ከተዘረዘሩት የጥፋት ዓይነቶች ውጪ


የሚያጋጥሙ ሌሎች ጥፋቶች ቢፈጸሙ የጥፋቶቹ ከባድነትና ቀላልነት ዓይነታቸውና ይዘታቸው
እየተፈተሸና እየታየ ከሠንጠረዡ ውስጥ በተዘረዘሩት ቅጣት ዓይነቶች ውስጥ ተመጣጣኝ ወይም ሊዛመድ
ወይም ተቀራራቢ ይሆናል ተብለው በሚገመቱት የቅጣት ዓይነቶች መጠቀም ይቻላል፤

28.19. አንድ ሠረተኛ በዲሲፕሊን ለከሰስ የሚችለው ዘርፉ የሰራተኛውን ጥፋት በተመለከተ በጽሁፍ ክስ
እንዲመሰረት ለዋናው መ/ቤት ለኮርፖሬት ስራ አስኬያጅ ወይም ለቅ/ጽ/ቤት ለሰው ሃብት አስተዳደር የስራ
ሂት ሲያቀርብ ክሱ ህግ፣ ስነ ምግባር እና መልካም አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ወይም አስተባባሪ በኩል
እንዲመሰረት ይደረጋል፡፡

28.20. አንድ ሠራተኛ በፈጸመው ጥፋት የተነሣ በዚህ ኀብረት ስምምነት መሠረት የሚወሰዱ የዲሲፕሊን እርምጃ
በወንጀል ወይም በፍትሐብሔር ከመከሰስ አያግደውም፤

አንቀጽ ሃያ ጠዘኝ (29)


የሥራ ውል ስለማቋረጥ

29.1. የሥራ ውል የሚቋረጠው በአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 አንቀጽ 24፣ 25፣ 26 ወይም
በዚህ ኀብረት ስምምነት አንቀጽ 29.2 እና 29.3 መሠረት ወይም በአንቀጽ 30 በተገለጸው የዲሲፕሊን
ጉድለት ለስንብት የሚያበቃ ጥፋት መፈፀም ይሆናል፤

29.2. የሥራ ውል በማስጠንቀቂያ ስለማቋረጥ

29.2.1. የሥራ ውል በአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 አንቀጽ 28 መሠረት በማስጠንቀቂያ ሊቋረጥ
ይችላል፤

29.2.2 በንብረት እና ገንዘብ ላይ የተመደበ ሰራተኛ ገንዘብ ወይም ንብረት ማጉደሉ በኦዲት ከተረጋገጠ ቀን ጀምሮ
በዲሲፕሊን ኮሚቴ ታይቶ ውሉ ሊቋረጥ ይችላል፡፡

29.3.የሥራ ውል ያለማስጠንቀቂያ ስለማቋረጥ

ሥራ ውል በአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 አንቀጽ 27 እና 32 መሠረት ያለማስጠንቀቂያ የሥራ
ውል ሊቋረጥ ይችላል፤ በተጨማሪም በዚህ ኀብረት ስምምነት መሠረት የሚከተሉት ሁኔታዎች በአንደኛ ደረጃ ከሥራ
የሚያሰናብቱ ይሆናሉ፤

42 | P a g e
29.3.1 ያለበቂ ምክንያት ሠራተኛው የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ እየተሰጠው በ 6 ወር ውስጥ በጠቅላላው ለስምንት ጊዜ
የስራ ስዓት ካላከበረ ወይም በተመሳሳይ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ እየተሰጠው በ 6 ወር ውስጥ ለአምስት ቀናት
ከስራ ከቀረ፡፡

29.3.2 የድርጅቱን ንብረት፣ ገንዘብ ሰነድ በማጭበርበርም ሆነ በቀጥታ ሰርቆ ያጠፋ፣ የሰረዘ ወይም የደለዘ፣
በተጭበረበሩ ሰነዶችና በሐሰት የምስክር ወረቀት ተቀጥሮ ወይም ሆን ብሎ የተጭበረበረ የሐሰት ሰነድ
ወይም የምስክር ወረቀት እንዲሰጥ ያደረገ ወይም ከላይ በተጠቀሱት የማጭበርበር ተግባራት ሆን ብሎ
የተባበረ፤

29.3.3 በተጭበረበሩ ሰነዶችና በሐሰት የምስክር ወረቀቶች ተቀጥሮ ወይም እድገት አግኝቶ ቢገኝ ወይም ሆን ብሎ
የተጭበረበረ የሐሰት ሰነድ ወይም የምስክር ወረቀት እንዲሰጥ ያደረገ ወይም ከላይ ከተጠቀሱት
የማጭበርበር ተግባራት ሆን ብሎ የተባበረ፤
29.3.4 በሥራና በሠራተኛ ወይም በድርጅቱ ንብረት ላይ አደጋ ሊያስከትል የሚችል ድርጊት ሆን ብሎ የፈፀመ፤

29.3.5 ሆን ብሎ ወይም በቸልተኝነት የኤሌክትሪክ፣ የውሃ፣ የስልክና የሬዲዮ መገናኛ መስመሮች እንዳይሠሩ አድርጎ
በሥራ፣ በሠራተኛና በድርጅቱ ንብረት ላይ ከባድ ጉዳት ያደረሰ፤

29.3.6 ማንኛውም ሠራተኛ ለባለጉዳዩ ወይም ለሌላ ሠራተኛ የማይገባውን ልዩ ጥቅም ለማግኘት ወይም
ለማስገኘት አስቦ ከባለጉዳዩ ወይም ከሠራተኛው መማለጃ ጉቦ መቀበሉ በማስረጃ የተረጋገጠበት፤

29.3.7. አስመስሎ የፈረመ፣ የድርጅቱን ማኀተም ለግሉ ወይም ለሌላ ወገን ጥቅም ያዋለ፤

29.3.8 በሥራ ላይ ድብደባ ወይም ግድያ የፈፀመ ወይም ለመፈፀም የሞከረ፤

29.3.9 በድርጅቱ በሥራ ቦታ ዝሙት የፈፀመ፤

29.3.10 በማንኛውም ሁኔታ በድርጅቱ ላይ የተቃጣውን ከባድ አደጋ እያወቀ ወይም ማወቅ ሲገባው ሆን ብሎ
ወይም በቸልተኝነት ለድርጅቱ ካላሣወቀ ወይም የተቻለውን ያህል አደጋውን ለመከላከል /ለመመከት/
ጥረት ያላደረገ፤

29.3.11 ከማኅደር ውስጥ የሚገኝ ማስረጃዎችን ሆን ብሎ ወይም በቸልተኝነት ያጠፋና በድርጅቱ ወይም
በሠራተኛው ላይ ከፍተኛ ጉዳት ያደረሰ፤

29.3.12 በድርጅቱ ወይም በሠራተኛው ላይ ሆን ብሎ በሙያ ሥራው ጉዳትና አደጋ እንዲደርስ ያደረገ፤

29.3.13 እምነት ማጉደሉ በማስረጃ የተረጋገጠበት፤

29.3.14 በሥራ ፀባዩ የተሰጠውን የጦር መሣሪያ ለማይመለከተው ሰው ያዋሰ፤ ያስታጠቀ ወይም ወንጀል
እንዲሠራበት ያደረገና የጥበቃ አባል ሆኖ ለጥፋት፣ ለሌብነት ወይም ለጉዳት የተባበረና ያመቻቸ መሆኑ
በማስረጃ የተረጋገጠበት፤

29.3.15 በወንጀል ጥፋተኛ ሆኖ መገኘትና በጥፋቱም ምክንያት ለሥራ ብቁ ሆኖ አለመገኘት፤

29.3.16 የሥራ ውል ያለማስጠንቀቂያ ስለማቋረጥ የተጠቀሱት ተግባራዊ የሚሆኑት በእያንዳንዱ አንቀጽ


የተገለፁት ጥፋቶች በማስረጃ ሲረጋገጡ ነው፤

43 | P a g e
29.3.17 የሠራተኛው የሥራ ዕቅድ አፈፃፀም ውጤት ለመጀመሪያ ጊዜ ዝቅተኛ ሆኖ ሲገኝ የድክመቱ ምክንያት
እየተጣራ ምክር፣ ስልጠናና የሥራ ላይ ልምምድ እንዲሠጠው ሊደረግ ይገባል፡፡ የዕቅድ አፈፃፀም ምዘና
ውጤቱ ለ 2 ኛ ጊዜ ዝቅተኛ ከሆነ ከደረጃ ዝቅ እንዲል ወይም ከሥራ እንዲሠናበት ይደረጋል፤

29.3.18 ዋስትና ለሚጠይቁ የስራ መደቦች ሰራተኛው የመጀመሪያ ዋሱ ዋስትናውን እንዲያወርድ ከጠየቀበት ቀን
አንስቶ ባሉት ተከታታይ 30 ቀን ጊዜ ውስጥ ተተኪ ዋስ ካላቀረበ ድርጅቱ የስራ ውሉን ያቋርጣል፡፡
29.3.19 የድርጅቱን ማህተም አስመስሎ የተጠቀመ ወይም የድርጅቱን ማህተም በሀሰት ለግል ጥቅም ወይም ለሌላ
ወገን ጥቅም ያዋለ እና ለጥበቃ የተሰጠውን የጦር መሳሪያ ለወንጀል ተግባር እንዲውል ማድረግ ወይም ለሌላ
ሰው አሳልፎ መስጠት ያለማስጠንቀቂያ የስራ ውል የሚቋረጥ ይሆናል፡፡
29.3.20 በአዋጅ ቁጥር 1156/2011 በአንቀጽ 14/2/ የተመለከቱ ህገወጥ ድርጊቶችን መፈጸም፡፡
29.3.21 በሠራተኛው ላይ ከሠላሳ ቀናት ለሚበልጥ ጊዜ የእስራት ፍርድ ተወስኖበት ከስራ ሲቀር የስራ ውሉ
ይቋረጣል፡፡

አንቀጽ ሠላሣ (30)


የሥራ ውል ያለማስጠንቀቂያ ወይም በማስጠንቀቂያ ከሚያቋርጡ የዲስፕሊን ጥፋቶች በስተቀር ሌሎች ጥፋቶች
ከዚህ በታች በተገለፀው ሰንጠረዥ መሰረት ተፈፃሚ ይሆናሉ፡፡
የጥፋት ዓይነትና የቅጣት ሰንጠረዥ
የሥነ ሥርዓት እርምጃ አወሳሰድ የቅጣት ደረጃ
ተ.ቁ የጥፋት ዓይነት
1 2 3 4
30.1 ሥራን በመበደል የተመደበበትን የ 5 ቀን ደመወዝና የ 10 ቀን የ 15 ቀን ስንብት
ሥራ በቸልተኝነት ወይም ሆን ብሎ የጽሁፍ ደመወዝና ደመወዝና
በልግመኝነት በወቅቱ አለመሥራት ማስጠንቀቂያ የጽሁፍ የጽሁፍ
ማስጠንቀቂያ ማስጠንቀቂያ
30.2 ሌሎች ሠራተኞች እና ሀላፊዎች የ 10 ቀን ደመወዝና የ 15 ቀን የ 30 ቀን ስንብት
ሥራ እንዳይሠሩ ማነሳሳት ወይም የጽሁፍ ደመወዝና ደመወዝና
የሐሰት ወሬ በመንዛት ሥራ ማስጠንቀቂያ የጽሁፍ የጽሁፍ
ማስፈታት ወይም ስም ማጥፋት ማስጠንቀቂያ ማስጠንቀቂያ
30.3 የተመደበበትን ሥራ እንዲሠራ የ 10 ቀን ደመወዝና የ 15 ቀን የ 30 ቀን ስንብት
የተሰጠውን ትዕዛዝ አለመቀበል የጽሁፍ ደመወዝና ደመወዝና
ማስጠንቀቂያ የጽሁፍ የጽሁፍ
ማስጠንቀቂያ ማስጠንቀቂያ
30.4 ከድርጅቱ ሥራ ጋር በተያያዘ ሁኔታ የ 10 ቀን ደመወዝና የ 15 ቀን የ 30 ቀን ስንብት
ሆን ብሎ በሠራተኞች ላይ በደል የጽሁፍ ደመወዝና ደመወዝና
ወይም በግል ንብረታቸው ላይ ማስጠንቀቂያ የጽሁፍ የጽሁፍ
ጉዳት ያደረሰ ወይም በቸልተኝነት ማስጠንቀቂያ ማስጠንቀቂያ
ይህ እንዲደርስ ያደረገ
30.5 የድርጅቱን ከባድ ወይም ቀላል የ 15 ቀን ደመወዝና የ 30 ቀን ስንብት
ተሸከርካሪ ወይም ማሽነሪ በራሱ የጽሁፍ ደመወዝና
ጥፋት በተሽከርካው ወይም ማስጠንቀቂያ የጽሁፍ

44 | P a g e
የሥነ ሥርዓት እርምጃ አወሳሰድ የቅጣት ደረጃ
ተ.ቁ የጥፋት ዓይነት
1 2 3 4
በማሽነሪው ላይ ጉዳት ያደረሰ ማስጠንቀቂያ
30.6 የድርጅቱን ተሽከርካሪ በራሱ የ 10 ቀን ደመወዝና የ 15 ቀን ስንብት
ጥፋት ላልተፈቀደ ተግባር ማዋል የጽሁፍ ደመወዝና
ወይም ከድርጅቱ ቅጥር ግቢ ውጭ ማስጠንቀቂያ የጽሁፍ
ካለ ድርጅቱ ፈቃድ ማሳደር ማስጠንቀቂያ

30.7 የድርጅቱን ተሽከርካሪ በራሱ ጥፋት የ 10 ቀን ደመወዝና የ 15 ቀን ስንብት


ያለ ህጋዊ መንጃ ፈቃድና ያለ የጽሁፍ ደመወዝና
ድርጅቱ ፈቃድ የድርጅቱን ማስጠንቀቂያ የጽሁፍ
ተሽከርካሪ መንዳት እንዲነዳ
ማስጠንቀቂያ
አሣልፎ መስጠት
30.8 በሥልጣን ወይም በተሰጠው የሥራ የ 10 ቀን ደመወዝና የ 15 ቀን የ 30 ቀን ስንብት
ኃላፊነት ያለ አግባብ መጠቀም የጽሁፍ ደመወዝና ደመወዝና
ማስጠንቀቂያ የጽሁፍ የጽሁፍ
ማስጠንቀቂያ ማስጠንቀቂያ
30.9 ከሥራ ጋር በተያያዘ ሁኔታ የ 5 ቀን ደመወዝና የ 10 ቀን ስንብት
ግለሰቦችን ተጠያቂ ላለማድረግ የጽሁፍ ደመወዝና የፅሁፍ
ወይም ለመጥቀም በማሰብ በሐሰት ማስጠንቀቂያ ማስጠንቀቂያ
የቃል ወይም የፅሁፍ ማስረጃ
በማቅረብ /በመስጠት/ በድርጅቱ
በደል እንዲደርስ ማድረግ
30.10 በመደበኛ የሥራ ሰዓት መግቢያና በስድስት ወር ውስጥ በስድስት ወር በስድስት ወር በስድስት
መውጫ ሰዓት ያለበቂ ምክንያት ከአንድ እስከ ሦስት ውስጥ ከአራት ውስጥ ወር
ዘግይቶ መግባትና ቀድሞ መውጣት ጊዜ የ 2 ቀን እስከ አምስት ከስድስት እስከ ውስጥ
ደመወዝና የጽሁፍ ጊዜ የ 5 ቀን ሰባት ጊዜ ስምንት
ማስጠንቀቂያ ደመወዝና የ 10 ቀን ና በላይ
የጽሁፍ ደመወዝና ጊዜ
ማስጠንቀቂያ የጽሁፍ ስንብት
ማስጠንቀቂያ
30.11 የቢሮ ሥነ ሥርዓት አጉድሎ የ 3 ቀን ደመወዝና የ 5 ቀን የ 10 ቀን ስንብት
መገኘት፣ መተኛት ቢሮ ውስጥ የጽሁፍ ደመወዝና ደመወዝና
መነገድና የመሣሠሉትም መፈፀም ማስጠንቀቂያ የጽሁፍ የጽሁፍ
ማስጠንቀቂያ ማስጠንቀቂያ
30.12 ያለ በቂ ምክንያት ወይም በስድስት ወር ውስጥ በስድስት ወር በስድስት ወር
ሳያስፈቅዱ ከስራ መቅረት አንድ ቀን የቀረ ውስጥ ከሁለት ውስጥ አምስት
የአንድ ቀን እስከ አራት ቀን ቀን እና በላይ
ደመወዝና የጽሁፍ የቀረ የቀረበትን የቀረ ስንብት
ማስጠንቀቂያ ቀን ደመወዝና
ድጋሜ የጽሁፍ
ማስጠንቀቂያ

45 | P a g e
የሥነ ሥርዓት እርምጃ አወሳሰድ የቅጣት ደረጃ
ተ.ቁ የጥፋት ዓይነት
1 2 3 4
30.13 በሥራ ላይ የድርጅቱ ሠራተኛ ስም የ 5 ቀን ደመወዝና የ 10 ቀን የ 15 ቀን ስንብት
በሐሰት ማጥፋት ወይም መሳደብ የጽሁፍ ደመወዝና ደመወዝና
ወይም መዛት ማስጠንቀቂያ የጽሁፍ የጽሁፍ
ማስጠንቀቂያ ማስጠንቀቂያ
30.14 በመጠጥ ሀይል ወይም በአደንዛዥ የፅሑፍ ከ 15 ቀን እስከ ከደረጃና
እጽ ተመርዞ ስራ መግባትና ቢሮ ማስጠንቀቂያ የ 10 1 ወር ደመወዝ ከደመወዝ ዝቅ
ወይም ካምኘ መረበሽ ቀን ደመወዝ ቅጣት ማድረግ እስከ
ስንብት
30.15 ውሣኔ ያልተሰጠበት የድርጅቱን የፅሑፍ የ 1 ወር ደመወዝ ከደረጃና
ሚስጥር ማባከን ማስጠንቀቂያ እና ከደመወዝ ዝቅ
15 ቀን ደመወዝ ማድረግ እስከ
ቅጣት ስንብት
30.16 ብልሽት እንዳለውና በተሽከርካሪው እስከ 15 ቀን ከደረጃና ከስራ
ወይም በመሣሪያው ላይ ጉዳት ደመወዝ ቅጣት ከደመወዝ ዝቅ ማሠናበት
እንደሚደርስ እየታወቀ የፅሑፍ ማድረግ
ተሽከርካሪንና መሣሪያን ማስጠንቀቂያ
ማንቀሳቀስ ወይም
እንዲያንቀሣቅሱ መፍቀድ

30.17 ከአቅም በላይ ባልሆነ ምክንያት እስከ 1 ወር ደመወዝ ከደረጃና ከስራ


ወይም በጥንቃቄ ጉድለት ቅጣት እና ከደመወዝ ዝቅ ማሠናበት
በማንኛውም የድርጅቱ ንብረት የደረሰውን ጉዳት ማድረግ
ላይ አደጋ ማድረስ ማስከፈል
30.18 በኃላፊነት ተመድቦ ሠርቶ የፅሑፍ የ 1 ወር ደመወዝ ከደረጃና
ባለማሠራት ስራውን የጓተተ ማስጠንቀቂያ ከደመወዝ ዝቅ
የሚጠበቅበትን ቁጥጥር ያላደረገና ማድረግ እስከ
መመሪያ ያልሠጠ ስንብት
30.19 በስራ ሰዓት በምድብ ስራ ቦታ የጽሁፍ የ 15 ቀን የ 1 ወር ከደረጃ
ስራውን ትቶ በግቢው ውስጥ ቢሮ ማስጠንቀቂያ ደመወዝ ደመወዝ ቅጣት ዝቅ
ለቢሮ ያለአግባብ መዘዋወር ማድረግ

ስንብት
በስራ ስዓት ያለ ድርጅቱ ፈቃድ የ 15 ቀን ደመወዝና የአንድ ወር ስንብት
ወረቀት እያዞረ ሌሎች ሠራተኞችን የጽሁፍ ደመወዝና
ማስፈረም፣ ስብሰባ መጥራት፣ ማስጠንቀቂያ የጽሁፍ
አድማ ማነሳሳት ማስጠንቀቂያ

46 | P a g e
የሥነ ሥርዓት እርምጃ አወሳሰድ የቅጣት ደረጃ
ተ.ቁ የጥፋት ዓይነት
1 2 3 4
30.20 በያዘው የጦር መሳሪያ ያለአግባብ የ 1 ወር ደመወዝ ከስራ ማሠናበት -
የሰራ ባልደረቦችንም ሆነ ሌሎች ቅጣት እና የፁሁፍ
ባለጉዳዬችን በስራ ቦታ ማስጠንቀቂያ
ማስፈራራት
30.21 ያልተፈቀደ ድምፅ አልባና ባለ የፅሑፍ የ 1 ወር ደመወዝ ከደረጃ እና
ድምፅ መሳሪያዎች በስራ ቦታና ማስጠንቀቂያ ቅጣት እና ከደመወዝ ዝቅ
በካምኘ ውስጥ ይዞ መገኘት የፁሁፍ ማድረግ እስከ
ማስጠንቀቂያ ስንብት
30.22 ድርጅቱ ምልክት ባደረገበት ወይም ጉዳት ካለ ጉዳቱን ጉዳት ካለ ጉዳቱን ከስራ
በማስታወቂያ እንዲታወቅ ሸፍኖ የ 1 ወር ሸፍኖ ከደረጃና ማሠናበት
በገለፀበት የተከለከለ ቦታ አካባቢ ደመወዝ ቅጣት ደመወዝ ዝቅ
ሲጋራ ማጨስና እሣት ማቀጣጠል ማድረግ
30.23 በቸልተኝነት /ሆን ብሎ/በድርጅቱ የጽሑፍ የ 1 ወር ደመወዝ ከደረጃና
ውስጥ ከሞራል ጋር የሚቃረኑ ማስጠንቀቂያና የ 15 ቅጣት እና ደመወዝ ዝቅ
ወይም አስነዋሪ ተግባራት መፈፀም ቀን ደመወዝ ቅጣት የፁሁፍ ማድረግ እስከ
ወይም እንዲፈፀም ማመቻቸት፣ ማስጠንቀቂያ ስንብት

30.24 አድሏዊ አሠራር መፈፀም ወይም የተፈፀመው ድርጊት የ 1 ወር ደመወዝ ከደረጃና


እንዲፈፀም ማድረግ ፣ ተሽሮ የ 15 ቀን ቅጣት እና ደመወዝ ዝቅ
ደመወዝና የፁሁፍ የፁሁፍ ማድረግ እስከ
ማስጠንቀቂያ ማስጠንቀቂያ ስንብት
30.25 ሆን ብሎ ወይም በቸልተኝነት የደረሠ ጉዳት ካለ የደረሠ ጉዳት ካለ የደረሠ ጉዳት
የድርጅቱን ደንቦችና መመሪያዎች ጉዳቱን መክፈልና ጉዳቱን መክፈልና ካለ ጉዳቱን
አክብሮ በተገቢው መንገድ በስራ የፅሑፍ የ 15 ቀን ደሞዝ መክፈልና እስከ
ላይ ያላዋለ፣ ማስጠንቀቂያ ቅጣት ስንብት

30.26 በሥራ ገበታ ላይ የሌለን ሠራተኛን የጽሁፍ የ 15 ቀን ስንብት


በሰዓት መቆጣጣሪያ ላይ አስመስሎ ማስጠንቀቂያ ደመወዝና
መፈረም የጽሁፍ
ማስጠንቀቂያ
30.27 በድርጅቱ ንብረትም ሆነ የ 10 ቀን ደመወዝና የ 15 ቀን የ 30 ቀን ስንብት
በሠራተኛው ላይ አደጋ ደርሶ የጽሁፍ ደመወዝና ደመወዝና
እርዳታ አለማድረግ ማስጠንቀቂያ የጽሁፍ የጽሁፍ
ማስጠንቀቂያ ማስጠንቀቂያ
30.28 የተሰጠውን የሥራ ልብስና የአደጋ የጽሁፍ የ 5 ቀን የ 10 ቀን ስንብት
መከላከያ በሥራ ላይ ሆኖ ማስጠንቀቂያ ደመወዝና ደመወዝና
አለመልበስ የጽሁፍ የጽሁፍ
ማሰጠንቀቂያ ማስጠንቀቂያ
30.29 ተረኛ ሆኖ በጥበቃ ነጥብ የ 10 ቀን ደመወዝና ስንብት
አለመገኘት ወይም መተኛት የጽሁፍ
ማስጠንቀቂያ

47 | P a g e
የሥነ ሥርዓት እርምጃ አወሳሰድ የቅጣት ደረጃ
ተ.ቁ የጥፋት ዓይነት
1 2 3 4
30.30 ያለ በቂ ምክንያት የተሠጠውን ስራ የ 5 ቀን ደመወዝና የ 10 ቀን የ 15 ቀን ስንብት
ማዘግየት የጽሁፍ ደመወዝና ደመወዝና
ማስጠንቀቂያ የጽሁፍ የጽሁፍ
ማስጠንቀቂያ ማስጠንቀቂያ
30.31 በድርጅቱ የሥራ ክልል ቁማር የ 10 ቀን ደመወዝና የ 20 ቀን ስንብት
መጫወት የጽሁፍ ደመወዝና
ማስጠንቀቂያ የጽሁፍ
ማጠንቀቂያ
30.32 ማስታወቂያዎች ከሰሌዳ ላይ የ 10 ቀን ደመወዝና የ 20 ቀን ስንብት
ማንሳት ወይም መቅደድ የጽሁፍ ደመወዝና
ማስጠንቀቂያ የጽሁፍ
ማጠንቀቂያ
30.33 ከሚመለከተው አካል እና የ 5 ቀን ደመወዝና የ 10 ቀን የ 15 ቀን ስንብት
ከተፈቀደው ቦታ ውጪ ጽሁፎችን፣ የጽሁፍ ደመወዝና ደመወዝና
መልዕክቶችን፣ ሥዕሎችን መለጠፍ ማስጠንቀቂያ የጽሁፍ የጽሁፍ
ማስጠንቀቂያ ማስጠንቀቂያ
30.34 ድርጅቱ ለመግቢያና ለመውጫ የ 5 ቀን ደመወዝ የ 10 ቀን የ 15 ቀን ስንብት
ከወሰነው በር ውጪ መጠቀም ከጽሁፍ ደመወዝና ደመወዝና
ማስጠንቀቂያ የጽሁፍ የጽሁፍ
ማስጠንቀቂያ ማስጠንቀቂያ
30.35 በሰነድ የወሰደውን የድርጅቱን የስራ የ 10 ቀን ደመወዝና የአንድ ወር ስንብት
ማስኬጃ ገንዘብ በፋይናንስ መመሪያ የጽሁፍ ደመወዝና
መሠረት በራሱ ጥፋት በወቅቱ ማስጠንቀቂያ የጽሁፍ
አለማወራረድ ማስጠንቀቂያ

30.36 የትራፊክ ደንብ በመጣስ የ 10 ቀን ደመወዝና የ 15 ቀን የ1 ወር ስንብት


ከተፈቀደው ፍጥነት በላይ የጽሁፍ ደመወዝና ደመወዝና
የድርጅቱን ተሽከርካሪ መንዳት ማስጠንቀቂያ የጽሁፍ የጽሁፍ
ማስጠንቀቂያ ማስጠንቀቂያ
30.37 የሚያሽከረክረው የድርጅቱ በተሽከርካሪው ላይ ስንብት
ተሽከርካሪ ላይ አደጋ ደርሶ ሪፖርት የደረሰውን ጉዳት
ሳያደርግ ቢቀር ዋጋ ከፍሎ የ 10 ቀን
ደመወዝና የጽሁፍ
ማስጠንቀቂያ
30.38 የድርጅቱን ተሽከርካሪዎች የ 10 ቀን ደመወዝና የ 15 ቀን የ1 ወር
መቆጣጠሪያ ሎግ ቡክ በየዕለቱ የጽሁፍ ደመወዝና ደመወዝና
አለመሙላት ወይም በአግባቡ ማስጠንቀቂያ የጽሁፍ የጽሁፍ
አለመያዝ ወይም መጣል ማስጠንቀቂያ ማስጠንቀቂያ

48 | P a g e
የሥነ ሥርዓት እርምጃ አወሳሰድ የቅጣት ደረጃ
ተ.ቁ የጥፋት ዓይነት
1 2 3 4
30.39 እስከ 5000 ብር የገንዘብ ጉድለት የጎደለበትን የጎደለበትን የጎደለበትን ስንብት
የተገኘበት ገ/ያዥ/ተቀባይ ወይም እንዲመልስ ተደርጎ እንዲመልስ እንዲመልስ
ግዥ ኦፊሰር ደረጃ-1 የጽሁፍ ተደርጎ የ 5 ቀን ተደርጎ የ 15
ማስጠንቀቂያ የደመወዝ ቅጣት ቀን የደመወዝ
ቅጣት
30.40 ከ 5001 እስከ 10,000 ብር የገንዘብ የጎደለበትን የጎደለበትን የጎደለበትን ስንብት
ጉድለት የተገኘበት ገ/ያዥ/ተቀባይ እንዲመልስ ተደርጎ እንዲመልስ እንዲመልስ
ወይም ግዥ ኦፊሰር ደረጃ-1 የ 5 ቀን የደመወዝ ተደርጎ የ 10 ቀን ተደርጎ የአንድ
ቅጣት የደመወዝ ቅጣት ወር የደመወዝ
ቅጣት
30.41 ከ 10,001 እስከ 30,000 ብር የጎደለበትን የጎደለበትን ስንብት
የገንዘብ ጉድለት የተገኘበት እንዲመልስ ተደርጎ እንዲመልስ
ገ/ያዥ/ተቀባይ ወይም ግዥ ኦፊሰር የ 15 ቀን የደመወዝ ተደርጎ የአንድ
ደረጃ-1 ቅጣት ወር የደመወዝ
ቅጣት
30.42 ከ 30,001 እስከ 50,000 ብር የጎደለበትን ስንብት
የገንዘብ ጉድለት የተገኘበት እንዲመልስ ተደርጎ
ገ/ያዥ/ተቀባይ ወይም ግዥ ኦፊሰር የአንድ ወር
ደረጃ-1 የደመወዝ ቅጣት
30.43 ከ 50,000 ብር በላይ የገንዘብ ስንበት
ጉድለት የተገኘበት ገ/ያዥ/ተቀባይ
ወይም ግዥ ኦፊሰር ደረጃ-1

30.44 እስከ 10,000 ብር የንብረት ጉድለት የጎደለበትን የጎደለበትን የጎደለበትን ስንብት


የተገኘበት ዕቃ ግምጃ ቤት ሠራተኛ እንዲመልስ ተደርጎ እንዲመልስ እንዲመልስ
የጽሁፍ ተደርጎ የ 5 ቀን ተደርጎ የ 10
ማስጠንቀቂያ የደመወዝ ቅጣት ቀን የደመወዝ
ቅጣት
30.45 ከ 10,001 እስከ 30,000 ብር የጎደለበትን የጎደለበትን የጎደለበትን ስንብት
የንብረት ጉድለት የተገኘበት ዕቃ እንዲመልስ ተደርጎ እንዲመልስ እንዲመልስ
ግምጃ ቤት ሠራተኛ የ 5 ቀን የደመወዝ ተደርጎ የ 10 ቀን ተደርጎ የ 15
ቅጣት የደመወዝ ቅጣት ቀን የደመወዝ
ቅጣት
30.46 ከ 30,001 እስከ 100,000 ብር የጎደለበትን የጎደለበትን ስንብት
የንብረት ጉድለት የተገኘበት ዕቃ እንዲመልስ ተደርጎ እንዲመልስ
ግምጃ ቤት ሠራተኛ የ 15 ቀን የደመወዝ ተደርጎ አንድ ወር
ቅጣት የደመወዝ ቅጣት
30.47 ከ 100,000 ብር በላይ የንብረት
ጉድለት የተገኘበት ዕቃ ግምጃ ቤት
ሠራተኛ ስንበት

49 | P a g e
የሥነ ሥርዓት እርምጃ አወሳሰድ የቅጣት ደረጃ
ተ.ቁ የጥፋት ዓይነት
1 2 3 4
30.48 ቅድሚያ የውሎ አበል ወስዶ የ 5 ቀን ደመወዝ የ 10 ቀን
ስራውን ፈጽሞ ከተመለሰ በኋላ ቅጣት ደመወዝ ቅጣት
ያለበቂ ምክንያት በአስር የስራ
ቀናት ውስጥ ሂሳቡን ያላወራረደ
30.49 ንብረት በሽፒንግ ወስዶ የርክክብ የ 5 ቀን ደመወዝ የ 10 ቀን
ሰነዱን ያለበቂ ምክንያት ቅጣት ደመወዝ ቅጣት
ካስረከበበት ቀን ጀምሮ በ 30 የስራ
ቀናት ውስጥ ያልመለሰ
ማሳሰቢያ. ከላይ በሰንጠረዥ የተዘረዘሩት የቅጣት ደረጃዎች 1/2/3/4 ተብለው የተቀመጡ ቢሆንም እንደ ጥፋቱ ክብደት የጥፋት
ደረጃውን ቅደም ተከተል ሳይጠብቅ ከፍ ወይም ዝቅ ብሎ የቅጣት ውሳኔ ሊተላለፍ ይችላል፡፡

50 | P a g e
አንቀጽ ሠላሣ አንድ (31)
የቅሬታ አቀራረብ ሥነ-ሥርዓት

31.1. ቅሬታ በተነሣ ጊዜ በተቻለ ፍጥነት ውሣኔ ማግኘት እንዳለበት ድርጅቱና ማኀበሩ የሚያምኑ ሲሆን በቅን መንፈስ
ቅሬታውን ለማስወገድ ይጥራሉ፤

31.2. ከሁለቱ ወገኖች ቅሬታ የተሰማው ቅሬታውን ለማስወገድ ውይይት እንዲደረግበት ስብሰባ መጥራት ይችላል፤

31.3. የተፈጠረውን ቅሬታ ሊፈታ የማይችል ከሆነ ወይም ስምምነት ላይ መድረስ ካልተቻለ ቅሬታ ያለበት ወገን ሕጋዊ
በሆነ መንገድ ለማንኛውም ቅሬታ ተመልካች አካል ማቅረብ ይችላል፤

31.4. የወል የሥራ ቅሬታ ሲፈጠር ቅሬታውን በቀጥታ ለድርጅቱ ኃላፊ ያቀርባል፤ ኃላፊው ውሣኔውን በ 10 የሥራ ቀናት
ውስጥ ይገልፃል፡፡ ማኅበሩም ውሣኔውን እንዲያውቀው ያደርጋል፤ ውሣኔው በማኀበሩ ተቀባይነት ካላገኘ አግባብ
ላለው አስማሚ አካል በማቅረብ በአዋጁ መሠረት ሊያስፈጽም ይችላል፤

31.5. ማንኛውም የቅሬታ አቀራረብ በጽሁፍ ይሆናል፤

ክፍል ስድስት
ሠራተኛ ስለመመዘን የሥራ ክንውን ግምገማና
ውድድር የጋራ ውይይትና የስምምነት ጊዜ
አንቀጽ ሰላሳ ሁለት (32)
ሠራተኛ ስለመመዘን

32.1. ማንኛውም የድርጅቱ ሠራተኛ ውጤት ተኮር የዕቅድ አፈፃፀም ምዘና በዓመት ሁለት ጊዜ በቅርብ
ኃላፊው ይሞላለታል፤

32.2. የሠራተኛው ውጤት ተኮር የዕቅድ አፈፃፀም ምዘና የሚካሄደው በቅርብ የሥራ ኃላፊው መሪነት ሆኖ
በቅርብ የሥራ ኃላፊውና በፈፃሚው ሠራተኛ በየወቅቱ ክትትል በተያዙ የዕቅድ አፈፃፀም መረጃዎች ላይ
በመመስረት ይሆናል፤

32.2.1. ውይይት ተካሂዶ በጋራ መግባባት በሚደርስበት የውጤት ምዘና መሠረት ነጥብ ይሰጣል፡፡

32.2.2.በምዘና ውጤት ላይ መግባባት ካልተቻለና ሠራተኛው ቅር ከተሰኘ ቀጥሎ ላለው የስራ መሪ ቅሬታውን
አቅርቦ በሚሰጠው አስተያየት መሠረት ነጥብ ተሰጥቶ እንዲፈራረሙበት ይደረጋል፡፡
32.3 ሠራተኛው በተሰጠው ውጤት ላይም ሆነ በሚሰጠው እቅድ ላይ ልዩነታ ካለው ልዩነቱን አስቀምጦ
የመፈረም ግዴታ አለበት፣ ነገር ግን ቅሬታ ሳያቀርብ ሳይፈርምበት ከቀረ እንደተስማማ ተቆጥሮ
ውጤቱ ይያዛል፡፡

32.4. በአንቀጽ 32.2.2. መሠረት በተሰጠው ውጤት ተኮር የዕቅድ አፈፃፀም ምዘና ነጥብ ላይ ቅሬታ በማንሳት
ለመፈረም ፈቃደኛ ካልሆኑ በቅጹ ላይ የቅርብ የሥራ ኃላፊው የበላይ የሆነው የስራ መሪ መግለጫ ሰጥቶበት
በሚወሰነው መሠረት ተፈፃሚ ይሆናል፤

51 | P a g e
32.5 አንድ ሠራተኛ ቀድሞ ከነበረበት የሥራ ቦታ ወይም መደብ ወደ ሌላ የሥራ መደብና ቦታ ቢዛወርና የሚቆጣጠረው
ኃላፊ አዲስ ከሆነ ሠራተኛው አዲስ በተዛወረበት የሥራ ቦታ ከሁለት ወር በላይ ከሠራ የሥራ አፈፃፀሙን
የሚሞላው አዲስ አለቃው ይሆናል፤ ነገር ግን ከቀድሞው ኃላፊው ጋር አራት ወርና ከዚያም በላይ ከሠራ የሥራ
አፈፃፀሙን የቀድሞው ኃላፊው ይሞላለታል፤

32.6 የሠራተኛው ውጤት ተኮር የዕቅድ አፈፃፀም ምዘና ነጥብ አሰጣጥ በድርጅቱ ውጤት ተኮር የዕቅድ አፈፃፀም ምዘና
መመሪያ መሠረት ይፈፀማል፤

አንቀጽ ሠላሣ ሦስት (33)


የሥራ ክንውን ግምገማና የሥራ ውድድር

33.1. ድርጅቱ በዓመቱ የተከናወኑትን ተግባራት በየስድስት ወሩ እንዲገመገም ያደርጋል፤ ስብሰባው የሚካሄደው የሥራ
እንቅስቃሴውን መጠን በማየት ድርጅቱ በሚያስተላልፈው የጥሪ ፕሮግራም መሠረት ይሆናል፡፡ ስብሰባውም
በድርጅቱ ኃላፊ ወይም ኃላፊው በሚወክሉት ሰው ይመራል፤

33.2. ድርጅቱ በነፃ ገበያው ውስጥ ተወዳድሮ ከፍተኛ የሥራ ውጤትና ቅልጥፍና ማሣደግ ከሠራተኛው የሥራ ዋስትና ጋር
የተያያዘ መሆኑን ድርጅቱና ማኀበሩ ተረድተውታል፤ ይህንንም በሥራ ለመተርጎም እንዲቻል ሠራተኛው
በየተሰማራበት የሥራ መስክ የሥራ ፍላጎት በይበልጥ እንዲዳብር የሥራ ጥራትና ፍጥነት ከፍ እንዲል፤ በአጠቃላይ
የድርጅቱ ሠራተኞች ፍሬያማ የሥራ ውጤት ሲያስገኙ የማበረታቻ ስጦታና የምስክር ወረቀት ሊሰጥ ይችላል፤

አንቀጽ ሠላሣ አራት (34)


የጋራ ውይይት

34.1. በድርጅቱና በሠራተኞች ጉዳይ ላይ ድርጅቱና ሠራተኛ ማኅበሩ የጋራ ውይይት ያደርጋሉ፤

34.2. በተለይ በዚህ ኅብረት ስምምነት ውስጥ ያልተካተቱና ያልተሟሉ ወይም አሻሚ የሆኑ ሁኔታዎች ሲፈጠሩ የማሻሻል
ወይም የመለወጥ ወይም የማብራራት ሁኔታዎችን በማስተካከል በማናቸው ጊዜ ድርጅቱና ማኅበሩ ተፈራርመው
በሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ በማቅረብ አስመዝግበው ሲጸድቅ ሥራ ላይ እንዲውል ይደርጋል፤

አንቀጽ ሠላሣ አምስት (35)


የስምምነት ጊዜ

35.1. ይህ የኅብረት ስምምነት በሁለቱም ወገኖች ጸድቆ ከተፈረመና ለሠራተኛና ማኀበራዊ ጉዳይ ቢሮ ቀርቦ ከተመዘገበና
ከፀደቀ በኋላ ሥራ ላይ ይውላል፤

35.2. ይህ የኅብረት ስምምነት በሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ ቀርቦ ፀድቆ ከተመዘገበበት ወር የመጀመሪያ ቀን አንስቶ
ለ 3/ሶስት/ ዓመት የፀና ይሆናል፡፡

ይህ የኅብረት ስምምነት በሠራተኛ ማኀበሩና በድርጅቱ መካከል ዛሬ ታህሳስ 1 ቀን 2012 ዓ.ም ተፈረመ፡፡

ስለ ድርጅቱ ስለ ሠራተኛ ማኀበሩ

52 | P a g e
__________ __________
ዘመነ ፀሀይ ባህሩ ብርሀን

ዋና ሥራ አስፈጻሚ የማኀበሩ ሊቀመንበር

ይህ የኅብረት ስምምነት ሲፈረም የነበሩ ምስክሮች

1. አቶ ከፍያለው ሙላቴ ....................


2. አቶ ዘላለም ባይለየኝ -----------------
3. አቶ ክንፈ ሚካኤል አያልነህ---------------
4. አዲሱ ጥላሁን……………………………

ታህሳስ 1 ቀን 2012 ዓ.ም

ማውጫ ገጽ
ክፍል አንድ ..............................................................................................................................................1
መ ግ ቢ ያ፡-..............................................................................................................................................2
የኀብረት ስምምነቱ ዓላማ..............................................................................................................................2
ትርጉም……………………………………………………………………………………………2
በኀብረት ስምምነቱና አግባብ ባላቸው ሕጐች መሃል ያለው ግንኙነት.........................................................................5
የኀብረት ስምምነቱ ወሰን..............................................................................................................................5
ክፍል ሁለት..............................................................................................................................................6
የድርጅቱ፣ የሠራተኛ ማኀበሩና የሠራተኛው መብትና ግዴታዎች..............................................................................6
የድርጅቱ መብትና ግዴታዎች.........................................................................................................................6
ማኀበሩን ስለማወቅ፣ የማኀበሩ መብትና ገዴታዎች.............................................................................................10
የሠራተኛው መብትና ግዴታ........................................................................................................................11
በድርጅቱ አስተዳደር የሠራተኛ ተካፋይ ስለመሆን..............................................................................................13
ክፍል ሦስት.............................................................................................................................................14
ቅጥር፣ ምደባ፣ የደረጃ ዕድገት፣ ዝውውር፣ ትምህርትና ሥልጠና.............................................................................14
ትምህርትና ሥልጠና..................................................................................................................................19
ክፍል አራት.............................................................................................................................................21
ልዩ ልዩ ጥቅሞችና አገልግሎቶች....................................................................................................................21

53 | P a g e
ስፖርት፣ መዝናኛና ቤተ-መፃሕፍት................................................................................................................22

የካምፕ አገልግሎት....................................................................................................................................23
ትራንስፖርት...........................................................................................................................................23
የህክምና አገልግሎት..................................................................................................................................24
አበል ….………………………………………………………………………………………….25
የትርፍ ሰዓት ሥራ.....................................................................................................................................26
የሕዝብ በዓላት.........................................................................................................................................27
የደመወዝ ጭማሪ......................................................................................................................................27
ቅድሚያ ደመወዝ......................................................................................................................................29
ፈቃድ ……………………………………………………………………………………………..29
የሥራ ልብስ............................................................................................................................................34
የአገልግሎት ክፍያና የጉዳት ካሣ ክፍያ............................................................................................................41
ክፍል አምስት..........................................................................................................................................42
የሥነ-ሥርዓት ደንቦችና አፈፃፀማቸው.............................................................................................................42
የጥፋት ዓይነትና የቅጣት ሰንጠረዥ................................................................................................................48
የቅሬታ አቀራረብ ሥነ-ሥርዓት.....................................................................................................................55
ክፍል ስድስት...........................................................................................................................................55
ሠራተኛ ስለመመዘን የሥራ ክንውን ግምገማና...................................................................................................55
ውድድር የጋራ ውይይትና የስምምነት ጊዜ.....................................................................................................55
ሠራተኛ ስለመመዘን..................................................................................................................................55
የሥራ ክንውን ግምገማና የሥራ ውድድር........................................................................................................56
የጋራ ውይይት.........................................................................................................................................56
የስምምነት ጊዜ.........................................................................................................................................57

54 | P a g e

You might also like