You are on page 1of 3

19/06/2012 ዓ/ም

ለኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን

ለቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ

አዲስ አበባ

ጉዳዩ፡- የደመወዝ ቅጣት እንዲነሳልኝ ስለመጠየቅ

ቀደም ሲል በቀን 02/08/2011 ዓ/ም በቁጥረ አ-13/23/11 በተፃፈ ደብዳቤ መሠረት በ 01/08/2011 ዓ/ም በተደረገ
አጠቃላይ የሠራተኞች ስብሰባ እኔ በስብሰባው ላይ ባልተገኘሁበት መመረጤንና የዲስፕሊን ኮሚቴ አባል ሆኜ
ማገልገል እንደሚገባኝ የተገለጸልኝ መሆኑ ይታወቃል ፡፡

እኔም በወቅቱ በኮሚቴነት ማገልገል የማልችልባቸውን ምክንያቶች ማለትም፡-

1 ኛ. ከዚህ በፊት በዕድገት ኮሚቴ፣በሠራተኛ ማህበር ገ/ያዥነት፣በቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ አባልነትና

በሠማቾች የህ/ሥ/ማ/ገ/ያዥነት

ለበርካታ ዓመታት ያገለገልኩ መሆኔን

2 ኛ. ሥራዬ የፈረቃ መሪ እና በተለይ የራዳር ሥራን ደርቤ የምሠራበመሆኑ ኮሚቴው በሚፈልገኝ

ጊዜ ሁሉ ለመገኘት አመቺ ያለመሆኑን

3 ኛ. መኖሪያዬም ከከተማ ከከተተማ ውጭ ቂሊንጦ ኮንድሚኒየም በመሆኑ ተመላልሶ

ለመሥራት ያለውን አደገኛነትና

4 ኛ. በቤተሰብ የግል ችግርም ስላለብን ይህንን ሁሉ ተጨባጭ ምክንያቶች በተለያዩ ጊዚያት

ከድጋፍ ሰጪ እና ከሰው ሀብት አስተዳደር ለተፃፉልኝ ደብዳቤዎች ሁሉ ከላይ

የዘረዘርኳቸውን ተጨባጭና አሳማኝ ምክንያቶችን በመግለጽ መልስ የሰጠሁ

ቢሆንም በቀን 06/12/2011 ዓ/ም በቁጥር 1194/4/12 ከሰው ሃብት ሥራ አመራር

በተፃፈልኝ ደብዳቤ ከዲስፕሊን ኮሚቴ ሰብሳቢ ጋር በመነጋገር ወደ ኮሚቴው ሥራ

መግባት እንዳለብኝ ና ደብዳቤው መልስ እንደማያስፈልገው ስለተገለጸልኝ እኔም

እኔም ችግሬን ካልተረዱኝ ምንም ማድረግ ስለማልችል የኮሚቴውን ሰብሳቢ አቶ ሠራዊት

ታደሰን በግል ስልካቸው ደውዬ እስካሁን ያልተሳተፍኩበትን ዝርዝር ሁኔታ በመግለጽ

በቀጣይ ከኮሚቴው ጋር አብሮ ለመሥራት የኮሚቴውን የመገናኛ ፕሮግራም ስጠይቃቸው

ኮሚቴው ቋሚ ፕሮግራም እንደሌለውና ኬዞች ሲኖሩ ብቻ ከአንድ ቀን በፊት በመቀጣጠር

እንደሚገናኙ ተነገረኝ ከዚያም ስልካችንን ተለዋውጠን እንዳለን በቀን 28/12/2011


ዓ/ም በቁጥር 1194/1/12 የተጻፈ የክስ ቻርጅ ደብዳቤ ደረሰኝ ከዚያም እምቢተኛ

አለመሆኔንና ከላይ እንደገለጽኩት ከኮሚቴው ሰብሳቢ ጋር ተማምነን ባለሁበት ሰዓት

መሆኑን ገልጬ እንደነበር እየገለጽኩ በአሁኑ ሰዓት ደግሞ በቀን 12/06/2012 ዓ/ም

በቁጥር 1194/4/12 በተፃፈ ደብዳቤ የአሥራ ስድስት ቀን ደመወዝ የተቀጣሁ መሆኔን

እየገለጽኩ ውሳኔው በገንዘብም በሞራልም በጣም የሚጎዳኝና በተለይበአሁኑ ሰዓት አዲስ

የሠራተኛ ምደባ በሚከናወንበት ሠዓት መሆኑ ደግሞ እጅግ የከፋ ያደርገዋል፡፡ የግል

ማህደሬም ከተቀጠርኩበት ረጅም አመታት ጀምሮ ምንም ዓይነት ቅጣት ያልተቀጣሁና

ይልቁንም የምስጋና ደብዳቤዎች እንዳሉኝ ማየት ይቻላል፡፡

ስለዚህ ሁኔታውን በመገናዘብ የተቀጣሁት ቅጣት እንዲነሳልኝ በትህትና እጠይቃለሁ፡፡

ከሰላምታ ጋር!!

ንጉሤ አጥሌ

ግልባጭ፡-
 ለኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር
 ለኤር ናቪጌሽን ም/ዋና ዳይሬክተር
 ለመገናኛ፣ናቪጌሽንና ቅኝት ዳይሬክተር
19/06/2012 ዓ/ም

ለኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን

ለሰው ሀብት ሥራ አመራር

አዲስ አበባ

ጉዳዩ፡- የደመወዝ ቅጣት እንዲነሳልኝ ስለመጠየቅ

በቀን 12/06/2012 ዓ/ ም በቁጥር 1194/4/12 በተፃፈ ደብዳቤ መሠረት እንደሚታወቀው ቀደም ሲል


የዲስፕሊን ኮሚቴነት ተመድቤ እንደነበርና በኮሚቴነት ሳልቀጥል ምክንያቶቼን ሳስረዳም ተቀባይነት ባለማግኘቴ
ሥራውን ለመቀጠል ከኮሚቴው ሰብሳቢ ጋር ተወያይተን ኬዞች ሲኖሩ እንደሚነገረኝ ስልክ ተለዋውጠን እንደነበር
ባለፈውም ለክሱ ቻርጅ በመለስኩት ደብዳቤ ላይ የገለጽኩ መሆኔን እያስታወስኩ ምንም ጥሪ ሳይደረግልኝ ይህ የ 16
ቀናት የደመወዝ ቅጣት ሲደርሰኝ በጣም ነው ያዘንኩት፡፡

ምክንያቱም መጀመሪያውንም ሥራዬ የፈረቃ መሪና በተለይ በፈረቃዬ ብቸኛ የራዳር ባለሙያ በመሆኔ
ምክንያት ሥራውን ጥዬ ወደ ኮሚቴ ሥራ መሄድ የማልችል መሆኔን ጭምር በተደጋገሚ ገለጬ ነበር ይሁንና
ለመሥራትም ፈቃደኛነቴን ብገልጽም እንደጥፋተኛ መቆጠሬ በተለይ በአሁኑ ሰዓት አዲስ የሰራተኛ ምደባ
በሚከናወንበት ሰዓት በህይወት ዘመኔ ከተቀጠርኩበት ጊዜ ጀምሮ ምንም ዓይነት ቅጣት ተቀጥቼ የማላውቅ መሆኔን
መህደሬም ያሳያል የቅርብም ሆነ የበላይ አለቆቼ የሚመሰክሩት ጉዳይ ነው፡፡

የተጣለብኝ ቅጣት እኔንም ሆነ ቤተሰቤን በገንዘብም ሆነ በሞራል እጅግ በጣም የሚጎዳ ስለሆነ ቅጠቱ
እንዲነሳልኝ ሳመለክት ለሚደረግልኝ መልካም አስተያት በቅድሚያ አመሰግናሁ፡፡

ከሰላምታ ጋር!!

ንጉሤ አጥሌ

ግልባጭ፡-
 ለኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር
 ለኤር ናቪጌሽን ም/ዋና ዳይሬክተር
 ለመገናኛ፣ናቪጌሽንና ቅኝት ዳይሬክተር
 ለድጋፍ ሰጪ አገልግሎት ደይሬክቶሬት

You might also like