You are on page 1of 4

በፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት

ልደታ ምድብ ------- ወንጀል ችሎት

አ/ አ

የፍ/ቤት መ/ቁ………

የዐ/ህግ መ/ቁ. 0278/2015

የፌ/ፖ/ወ/ም/ቢሮ ወ/መ/ቁ.699/13

ከሳሽ ………….. ፌዴራል ዐቃቤ ህግ

ተከሳሽ …………..1 ኛ/ ፈረሀን ሀሰን ሀስዬ

ዕድሜ፡- 31

ስራ፡- ጫት ነጋዴ

አድራሻ፡- አዲስ አበባ፣ ቦሌ ክ/ከተማ፣ ወረዳ 11፣ ስልሳ ስድስት ሰፈር፣ የቤት ቁጥር …

2 ኛ/ ካሚል አህመድ አብዱላሂ

ዕድሜ፡- 23

ስራ፡- ንግድ

አድራሻ፡- ድሬደዋ ከተማ፣ ቀበሌ 08፣ የቤት ቁጥር 4180

1 ኛ ክስ በሁለቱም ተከሳሾች ላይ

ወንጀሉ

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. የወንጀል ህግ አንቀጽ 32/1/ሀ እና የጉምሩክ አዋጅ ቁጥር 859/06(እንደተሻሻለዉ) ፣ አንቀጽ


168/2’ን በመተላለፍ፣

የወንጀሉ ዝርዝር

ተከሳሾቹ የኮንትሮባንድ ዕቃ መሆኑን እያወቁ ወይም ማወቅ ሲገባቸዉ የሻንሲ ቁጥሩ NZE121-0186656፣
የሞተር ቁጥሩ ደግሞ 1NZ-A626099 እና ቀረጥና ታክስ መጠኑ ደግሞ ብር 5,065,329.02(አምስት ሚሊየን
ስልሳ አምስት ሺህ ሶስት መቶ ሀያ ዘጠኝ ከ 02/100) የሆነ አንድ ኮሮላ ተሽከርካሪ ላይ ቁጥሩ ኮድ 03-
A51094 አ/አ የሆነ እና የሻንሲ ቁጥሩ AHTCB3CD102119678 ለሆነ በቀን 09/02/2010 ዓ.ም ቻይና ሪል
ዊይ ቁ.3 ኢንጅኔሪንግ ግሩፕ ኃላ.የተ.የግ.ማህበር ለተባለዉ ባለንብረት እንዲሁም የሻንሺ ቁጥሩ
JAAKP34G787P15302 ለሆነ በቀን 21/09/2006 ዓ.ም ዘካሪያስ ብርሀኑ ለተባለዉ ባለንብረት የተሰጠዉን
የሰሌዳ ቁጥር በመገልገል በ 2 ኛ ተከሳሽ ካሚል አህመድ አብዱላሂ ስም ሀሰተኛ ሊብሬ በማዘጋጀት
የኮንትሮባንድ ተሽካርካሪዉ ላይ በመለጠፍ 1 ኛ ተከሳሽ ፈረሀን ሀሰን ሀስዮ ተሽከርካሪዉን በመኖሪያ ግቢ
ዉስጥ አቁሞ ባለበት ሁኔታ በቀን 29/06/2013 ዓ.ም ከቀኑ በግምት 06፡00 ሰዓት ሲሆን በአዲስ አበባ ከተማ
አስተዳደር፣ ቦሌ ክፍለ ከተማ፣ ወረዳ 01፣ ልዩ ስሙ ቦሌ ሚካኤል ተብሎ በሚጠራ አከባቢ በሚገኘዉ መኖሪያ
ቤት ግቢ ዉስጥ በተደረገዉ ብርበራ የተያዘ በመሆኑ በፈፀሙት የኮንትሮባንድ ዕቃን ይዘዉ መገኘት ወንጀል
ተከሰዋል፡፡

2 ኛ ክስ በሁለቱም ተከሳሾች ላይ

ወንጀሉ

በ 1996 ዓ.ም የወጣዉን ኢ.ፌ.ዲ.ሪ ወንጀል ህግ አንቀጽ 32/1/ሀ እና 378’ን በመተላለፍ፣

ዝርዝር

ተከሳሾቹ ከላይ በ 1 ኛ ክስ ዉስጥ የተመለከተዉ እና ቀረጥና ታክስ መጠኑ ብር 5,065,329.02(አምስት


ሚሊየን ስልሳ አምስት ሺህ ሶስት መቶ ሀያ ዘጠኝ ከ 02/100) የሆነን የኮንትሮባንድ ተሽከርካሪ ህጋዊ
ለማስመሰል በማሰብ ከላይ በ 1 ኛ ክስ ዉስጥ በተገለፀዉ ሁኔታ የሌላ ተሽከርካሪን ሰሌዳ ቁጥር ኮድ 03-
A51094 አ/አ በመገልገል በ 2 ኛ ተከሳሽ ካሚል አህመድ አብዱላሂ ስም ሀሰተኛ ሊብሬ በማዘጋጀት
የኮንትሮባንድ ተሽካርካሪዉ ላይ በመለጠፍ 1 ኛ ተከሳሽ ፈረሀን ሀሰን ሀስዮ ተሽከርካሪዉን በመኖሪያ ግቢ
ዉስጥ አቁሞ ባለበት ሁኔታ በቀን 29/06/2013 ዓ.ም ከቀኑ በግምት 06፡00 ሰዓት ሲሆን በአዲስ አበባ ከተማ
አስተዳደር፣ ቦሌ ክፍለ ከተማ፣ ወረዳ 01፣ ልዩ ስሙ ቦሌ ሚካኤል ተብሎ በሚጠራ አከባቢ በሚገኘዉ መኖሪያ
ቤት ግቢ ዉስጥ በተደረገዉ ብርበራ የተያዘ በመሆኑ በፈፀሙት ሀሰተኛ ሰነድ መገልገል ወንጀል ተከሰዋል፡፡

የማስረጃዎች ዝርዝር

ሀ/ የሰዉ ምስክሮች፡-

1. ም/ኢ/ር ሀይሉ ሀ/ማሪያም ወንዱ አድራሻ፡- አዲስ አበባ፣ ኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከ፣ ወ/11፣ የቤ.ቁ. 636

2. ወ/ሮ እሌኒ ጌታሁን በላይነህ አድራሻ፡- አዲስ አበባ፣ ቦሌ ክ/ከ፣ ወ/01፣ የቤ.ቁ. 5097.

3. አቶ ሄኖክ ሽብሩ ሳበ አድራሻ፡- አዲስ አበባ፣ ቦሌ ክ/ከ፣ ወ/01፣ የቤ.ቁ. 2354.

4. ለ/ የሰነድ ማስረጃዎች፡-

1. የሻንሲ ቁጥሩ NZE121-0186656፣ የሞተር ቁጥሩ ደግሞ 1NZ-A626099 የሆነ ተሽከርካሪ ላይ


በ 2 ኛ ተከሳሽ ስም የተዘጋጀ ሊብሬ ኮፒዉን ኮፒዉን 01-ገጽ፡፡
2. በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ትራንስፖርት ሚኒስቴር የትራንስፖርት ባለስልጣን በቁጥር 02/ኮዘ/373/13 በቀን
07/07/2013 ዓ.ም በሰጠዉ መረጃ የሻንሲ ቁጥር NZE121-0186656 ትክክለኛ የፋብሪካዉ ህጋዊ
ቁጥር መሆኑን ያረጋገጠበት ደብዳቤ ኮፒዉን 01-ገጽ፡፡

3. በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ትራንስፖርት ሚኒስቴር የትራንስፖርት ባለስልጣን በቁጥር 17/መ 7 መ/120/13 በቀን


02/07/2013 ዓ.ም በሰጠዉ መረጃ የሻንሲ ቁጥሩ NZE121-0186656 የሆነ ተሽከርካሪ በባለስልጣን
መስሪያ ቤታቸዉ መረጃ ቋት ዉስጥ ያልተመዘገበ መሆኑን ያረጋገጠበት ደብዳቤ ኮፒዉን 01-ገጽ፡፡

4. በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ትራንስፖርት ሚኒስቴር የትራንስፖርት ባለስልጣን በቁጥር 163/የሠምምስ/13 በቀን


02/10/2013 ዓ.ም በሰጠዉ መረጃ በሰሌዳ ቁጥር ኮድ 03-A51094 አ/አ በባለንብረት ዘካሪያስ ብርሃኑ
ተመዝግቦ የነበረ እና በቀን 26/06/2010 ዓ.ም ምትክ ሰሌዳ የተሰራ መሆኑን የገለፀበት ደብዳቤ
ከእነአባሪዉ ኮፒዉን 05-ገጽ፡፡

5. የሻንሲ ቁጥሩ NZE121-0186656 የሆነ ተሽከርካሪ በባለስልጣን መስሪያ ቤታቸዉ መረጃ ቋት ዉስጥ
ያልተመዘገበ መሆኑን ያረጋገጠበት ደብዳቤ ኮፒዉን 01-ገጽ፡፡

6. በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአሽከርካሪ ተሽከርካሪ ፈቃድ እና ቁጥጥር ባለስልጣን የየካ ቅ/ጽ/ቤት
በቁጥር …..3182/13 በቀን 07/07/2013 ዓ.ም በሰጠዉ መረጃ በሰሌዳ ቁጥር ኮድ 03-A51094 አ/አ
በባለንብረት 2 ኛ ተከሳሽ ካሚል አህመድ አብዱላሂ ስም የተመዘገበ ተሽከርካሪ የሌለ መሆኑን
ያረጋገጠበት ደብዳቤ ኮፒዉን 01-ገጽ፡፡

7. በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአሽከርካሪ ተሽከርካሪ ፈቃድ እና ቁጥጥር ባለስልጣን የቦሌ ቅ/ጽ/ቤት
በቁጥር …..2660/13 በቀን 06/07/2013 ዓ.ም በሰጠዉ መረጃ በሰሌዳ ቁጥር ኮድ 03-A51094 አ/አ
የተመዘገበዉ በባለንብረት ቻይና ሪል ዌይ ቁ 3 ኢንጅኔሪንግ ግሩፕ ኃላ.የተ.የግ.ማህበር ስም ነዉ እንጂ
በባለንብረት 2 ኛ ተከሳሽ ካሊድ አህመድ አብዱላሂ ስም አለመሆኑን ያረጋገጠበት ደብዳቤ ከእነ
አባሪዉ ኮፒዉን 03-ገጽ፡፡

8. የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ አገልግሎት ድርጅት በነሐሴ 24 ቀን 2013 ዓ.ም


በቁጥር ኮሜመ/ማመ/4156/13 በሰጠዉ ማስረጃ የሻንሲ ቁጥሩ NZE121-0186656 የሆነ ተሽከርካሪ
በድርጅቱ ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መምሪያ ዉስጥ ተመዝግቦ ያልተገኘ መሆኑን ያረጋገጠበት
ደብዳቤ ኮፒዉን 01-ገጽ፡፡

9. በኢፌዲሪ ትራንስፖርት ሚኒስቴር የመድን ፈንድ አስተዳደር ኤጀንሲ በቁጥር ህ.24/2656/13 በቀን
09 ሰኔ 2013 ዓ.ም በፃፈዉ ደብዳቤ 1 ኛ ተከሳሽ አቶ ፈረሀን ሀሰን ሰሌዳ ቁጥር ኮድ 03-A51094 አ/አ
በሆነ ተሽከርካሪ ላይ ያቀረባቸዉ እና ቁጥራቸዉ 1 ኛ/ 1376374 እና 2 ኛ/ 059320 የሆኑ የመድን
ፋንድ ሰርተፊኬቶች በትክክል የተሰጡት የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 03-02212HR ለሆነ ነዉ እንጂ የሰሌዳ
ቁጥሩ ኮድ 03-A51094 አ/አ ለሆነ እንዳልሆነ ያረጋገጠበት ደብዳቤ ኮፒዉን 01-ገጽ፡፡

10. ቡና ኢንሹራንስ አ.ማ. በቀን መጋቢት 02/2013 ዓ.ም በቁጥር ቡኢአማ/ወሰብ/0004/2013 በፃፈዉ
ደብዳቤ ሰሌዳ ቁጥር ኮድ 03-A51094 አ/አ ለሆነ ተሽከርካሪ የሶስተኛ ወገን ሽፋን የሰጠ መሆኑን
በማረጋገጥ አሁን በኮንትሮባንድ የተያዘዉ ተሽከርካሪ ዉስጥ የተገኘዉ የሶስተኛ ወገን ምስክር ወረቀት
ተሽከርካሪዉን ህጋዊ ለማስመሰል የተጭበረበረ የመድን ፈንድ የተጠቀሙ መሆናቸዉን የሚያረጋግጥ
ደብዳቤ ኮፒዉን 01-ገጽ፡፡
11. በኢፌዲሪ ጉምሩክ ኮሚሽን የአዲስ አበባ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት በሞዴል 270፣ በደረሰኝ ቁጥር
CCAAK 003821 በቀን 27/11/2013 ዓ.ም የሻንሲ ቁጥሩ NZE121-0186656 የሆነ ተሽከርካሪ ገቢ
ያደረገበት ሰነድ ኮፒዉን 01-ገጽ፡፡

12. በኢፌዲሪ ጉምሩክ ኮሚሽን የአዲስ አበባ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት በቁጥር 4.1.8/0210/13
በመጋቢት 09 ቀን 27/11/2013 ዓ.ም በፃፈዉ ደብዳቤ የሻንሲ ቁጥሩ NZE121-0186656 የሆነ እና
የሞተር ቁጥሩ 1NZ-A626099 የሆነ እና ለክሱ ምክንያት የሆነዉ ተሽከርካሪ በጉምሩክ የመረጃ
ክምችት ዉስጥ ተመዝግቦ ያልተገኘ መሆኑን በመግለጽ ተሽከርካሪዉ በኮንትሮባንድ መንገድ ወደ አገር
ዉስጥ የገባ መሆኑን ያረጋገጠበት ደብዳቤ ኮፒዉን 01-ገጽ፡፡

13. በኢፌዲሪ ጉምሩክ ኮሚሽን የአዲስ አበባ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት በሞዴል 270፣ በደረሰኝ ቁጥር
CCAAK 003821 በቀን 27/11/2013 ዓ.ም የሻንሲ ቁጥሩ NZE121-0186656 የሆነ ተሽከርካሪ ገቢ
ያደረገበት ሰነድ ኮፒዉን 01-ገጽ፡፡

14. በኢፌዲሪ ጉምሩክ ኮሚሽን የአዲስ አበባ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት በቁጥር 4.1.8/0210/13 በቀን
21/12/2013 ዓ.ም በፃፈዉ ደብዳቤ የሻንሲ ቁጥሩ NZE121-0186656 የሆነ፣የሞተር ቁጥሩ 1NZ-
A626099 የሆነ እና ለክሱ ምክንያት የሆነዉ ተሽከርካሪ በጉምሩክ የመረጃ ክምችት ዉስጥ ተመዝግቦ
ያልተገኘ መሆኑን በመግለጽ ተሽከርካሪዉ በኮንትሮባንድ መንገድ ወደ አገር ዉስጥ የገባ መሆኑን
ያረጋገጠበት ደብዳቤ ኮፒዉን 01-ገጽ፡፡

15. በኢፌዲሪ ጉምሩክ ኮሚሽን የአዲስ አበባ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት በቁጥር 4.4.3/አ 54/192 በቀን
21/12/2013 ዓ.ም በፃፈዉ ደብዳቤ ለክሱ ምክንያት የሆነዉ ተሽከርካሪ ቀረጥና ታክስ ብር
5,065,329.02(አምስት ሚሊየን ስልሳ አምስት ሺህ ሶስት መቶ ሀያ ዘጠኝ ከ 02/100) መሆኑን
የገለፀበት ደብዳቤ ከእነባሪዉ ኮፒዉን 03-ገጽ፡፡

ማስታወሻ፡-

 1 ኛ ተከሳሽ ከቀን 29/06/2013-16/07/2013 ዓ.ም በእስር ላይ ከቆየ በኃላ በቀን 23/10/2014 ዓ.ም
በፍ/ቤት ዋስትና ተለቋል፡፡

 2 ኛ ተከሳሽ እጁ አልተያዘም፡፡

 ክሱ በመደበኛ ስነ-ስርዓት የቀረበ ነዉ፡፡

You might also like