You are on page 1of 4

ቀን፡-21/01/2016 ዓ.

ለሲዳማ ብ/ክ/መንግስት ጠቅላይ ፍ/ቤት

ይግባኝ ሰሚ ችሎት

ሀዋሳ፣

ይግባኝ ባይ፡- ወ/ሮ ወርቅነሽ ጃልዶ

አድራሻ፡- ሀዋሳ ከተማ ሀይቅ ዳር ክ/ከተማ ጉዱማሌ ቀበሌ

መልስ ሰጪ፡- አቶ ወገኔ ማቴዎስ

አድራሻ፡- ሀዋሳ ከተማ መናኸሪያ ክ/ከተማ ጉዊ ስታዲየም ቀበሌ

በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348 መሠረት የቀረበ የይግባኝ አቤቱታ


ሀ. ጠቅላላ
1. ይግባኙ የቀረበው የሥር የሀዋሳ ከተማ ከ/ፍ/ቤት በመ/ቁ. 34394 በቀን 03/13/2015 ዓ.ም
በዋለው ችሎት በሰጠው ውሳኔ ቅር በመሰኘት በይግባኝ ለማስቀየር የቀረበ አቤቱታ
ነው፡፡
2. ይግባኙ በይርጋ አልታገደም፡፡
3. ለመልስ ሰጪ የሚላከውን መጥሪያ ይግባኝ ባይ አደርሳለሁ፡፡
4. አቤቱታው በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 223 እና 348 መሠረት ተሟልቶ የቀረበ ነው፡፡

ለ. የጉዳዩ አመጣጥ በአጭሩ

የአሁን መልስ ሰጪ በሥር ፍ/ቤት ባቀረበብኝ ክስ የውርስ ሀብት ተጣርቶ ግምቱ ብር 1,200,000
(አንድ ሚሊዮን ሁለት መቶ ሺህ ብር) ከሆነው ድርሻዬ እንዲከፈል በማለት የእናትና የአባቱን
የውርስ ሀብት ነው ያላቸውን በዝርዝር በመጥቀስ ባቀረበው ክስ መነሻነት ይግባኝ ባይ (የሥር
ተጠሪ) በዝርዝር የመከላከያ መልስ እና ማስረጃ ጭምር አቅርቤ ሳለ የሥር ፍ/ቤቱ ማስረጃን
በአግባቡ ሳይመረምር ለመልስ ሰጪ ያደላ ውሳኔ በመወሰኑ በሥር ፍ/ቤት የተፈፀመውን የህግ
አና የማስረጃ ምዘና ስህተት እንዲታረም ያቀረብኩት ይግባኝ ነው፡፡

ሐ. የይግባኝ ቅሬታ ዝርዝር ነጥቦች

1. የሥር ፍ/ቤት በደቡብ ክልል ወላይታ ሶዶ ያለውን ቤት በተመለከተ ሲወሰን መሠረታዊ


የማስረጃ ምዘና ስህተት የተፈፀመበት ስለመሆኑ፣
የመልስ ሰጪ እናት በቀን 19/08/2003 ዓ.ም ከሞቱ በኋላ ይግባኝ ባይ ከመልስ ሰጪ አባት
ጋር ጋብቻ በመፈፀም አንድ ሴት ልጅ ወልጄ ንብረት አፍርተናል፡፡ ከእነዚህ ንብረቶች
አንዱ ሟች ባለቤቴ በሶዶ ከተማ በምሪት ባገኘው ቦታ ላይ ከማዘጋጃ ቤቱ በቀን
17/07/2004 ዓ.ም ማለትም የመልስ ሰጪ እናት ከሞቱ ከአንድ ዓመት በኋላ የግንባታ
ፈቃድ ባለቤቴ ስለመውሰዱና በ 2005 ዓ.ም ጋብቻ ከፈፀምን በኋላ ቤቱን በጋራ ገንዘብ
ስለመገንባታችን በሰነድ እና በሰው ማስረጃ አረጋግጬ ያቀረብኩ ቢሆንም የሥር
ፍ/ቤቱ መልስ ሰጪ በተሻለ ሁኔታ አስረድቷል በማለት በመወሰኑ መሠረታዊ የማስረጃ
ምዘና ስህተት የተፈፀመበት ነው፡፡ የመልስ ሰጪ እናት በሚያዝያ 2003 ዓ.ም ከሞቱ
በኋላ ሟች ባለቤቴ በ 2004 ዓ.ም መጋቢት ወር በምሪት ባገኘው መሬት ግንባታ
ለመጀመር ከማዘጋጃ ቤቱ የግንባታ ፈቃድ ስለመውሰዱ ህጋዊ የሰነድ ማስረጃ ቀርቧል፡፡
ፈቃድ የሚወሰደው ግንባታ ለመጀመር እንጂ ቀደም ሲል ለተገገነባ አይደለም፡፡ የመልስ
ሰጪ እናት ከሞቱ በኋላ እኔና የመልስ ሰጪ አባት የገነባነዉን ግንባታ የመልስ ሰጪ እናት
በህይወት እያለች ገንብታለች ተብሎ በሰዉ ማስረጃ ብቻ የተመሰከረዉን ከሰነድ
ማስረጃ በማስበለጥ የተወሰነዉ ውሳኔ ከህግና ከሞራል ተቃራኒ የሆነ ውሳኔ በመሆኑ
ሊታረም የሚገባው ነው፡፡
የሥር ፍ/ቤቱ ሶዶ በሚገኘው ቤት ይግባኝ ባይ ከሟች ባለቤቴ ጋር የሰራነው ስለመሆኑ
የቀረበውን የሰነድና የሰው ማስረጃ ውደቅ ያደረገበት አግባብ የተሳሳተ ከመሆኑ
በተጨማሪ ቤቱን የማስፋፊያ ግንባታ ማለትም ሰርቪስ ቤቶችን ከሟች ባለቤቴ ጋር
ስለመገንባታችን በበቂ ሁኔታ በማስረጃ የተረጋገጠ ቢሆንም ይህንን ነጥብ ከግንዛቤ
ሳያስገባ ለመልስ ሰጪ በማድላት መወሰኑ ሊታረም የሚገባው ነው፡፡
2. የሥር ፍ/ቤት የመልስ ሰጪ እና የምስክሮችን ቃል በሰነድ ማስረጃ ሳያረጋግጥ ያለፈበት
አግባብ የማስረጃ ምዘና ስህተት የተፈፀመበት ስለመሆኑ፣
መልስ ሰጪ እና ምስክሮቹ በወላይታ ሶዶ አራዳ ክ/ከተማ የሚገኘውን ቤት ግንባታ
በተመለከተ ታህሳስ 19 ቀን 2003 ዓ.ም የግንባታ ፈቃድ ወጥቶ እንደነበረ ሲመሰክሩ
የግንባታ ፈቃዱ በተጠቀሱት ዕለት ስለመውጣቱ የሚያስረዳ የሰነድ ማስረጃ አያይዘው
አላቀረቡም፡፡ የግንባታ ፈቃድ የሚረጋገጠው በሰነድ ማስረጃ እንጂ በሰው የምስክርነት
ቃል አይደለም፡፡ ይግባኝ ባይ ግን ፈቃዱ የወጣበትን ትክክለኛ ጊዜ በሰነድ ማስረጃ
አረጋግጫለሁ፡፡ ፈቃድ የወጣው የመልስ ሰጪ እናት ካረፈች ከ 1 ዓመት በኋላ ስለመሆኑ
በሚገባ ተረጋግጦ ሳለ የሥር ፍ/ቤቱ ንብረቱ የመልስ ሰጪ እናት እና አባት ነው በማለት
የይግባኝ ባይን በሰነድ የተረጋገጠ ማስረጃ በማለፍ መወሰኑ እና የመልስ ሰጪ እና
ምስክሮች የግንባታ ፈቃድ በ 2003 ዓ.ም ስለመውጣቱ በቃል ያስረዱትን በሰነድ
እንዲያረጋግጡ ሊያደርግ ሲገባው ይህንን ሳያረጋግጥ በማለፍ በደፈናው የመልስ ሰጪ
ማስረጃ በተሻለ ሁኔታ አስረድቷል የሚል መደምደሚያ ላይ በመድረስ የይግባኝ ባይን
መብት እና ሞራል በእጅጉ የሚጎዳ ከህግ ተቃራኒ የሆነ ውሳኔ መወሰኑ ሊታረም
የሚገባው ነው፡፡
3. የሥር ፍ/ቤቱ የቤት ኪራይ ገንዘብን በተመለከተ የወሰነዉ ዉሳኔ ሊታረም የሚገባዉ
ስለመሆኑ፣
የሥር ፍ/ቤት በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሂሰብ ቁጥር 1000311649322 በሆነው ያለው
ገንዘብ የኪራይ ገቢ ስለሆነ ለመልስ ሰጪ እና ለይግባኝ ባይ ልጅ ሊከፋፈል ይገባል
በማለት የወሰነው ውሳኔ ቀደም ሲል ከላይ በዘረዘርኩት መልኩ በተሳሳተ መደምደሚያ
መነሻነት ቤቱ ለይግባኝ ባይ አይገባም በማለት የኪራይ ገንዘቡ አይገባሽም የሚል ውሳኔ
መወሰኑ የህግ እና የማስረጃ ምዘና ስህተት በመሆኑ ሊታረም የሚገባው ነው፡፡
የኪራይ ገንዘቡ ይግባኝ ባይና ሟች ባለቤቴ ከሰራነው ቤት የሚገኝ ገንዘብ እንጂ የመልስ
ሰጪ እናት ሳትሰራ ሰርታለች ተብሎ ለመልስ ሰጪ የሚወሰን አይደለም፡፡ ይግባኝ ባይ
ከሟች ባለቤቴ ጋር በጋራ ሰርተን የጋራ ገንዘባችንን አፍስሰን ሰርተን ካከራየነው ቤት
የተገኘውን ገንዘብ ፍ/ቤቱ የቀረበውን የሰነድ እና የሰው ምስክሮች በአግባቡ
ሳይመረምር ለመልስ ሰጪ መወሰኑ ተገቢ ባለመሆኑ ሊታረም ይገባል፡፡
4. የሥር ፍ/ቤት ለቀብር ማስፈፀሚያ ወጣ ስለተባለው ገንዘብ የወሰነው ውሳኔ ሊታረም
የሚገባው ስለመሆኑ፣
መልስ ሰጪ በሥር ፍ/ቤት ባቀረበው የክስ አቤቱታ ለቀብር ማስፈፀሚያ እና ለሀውልት
ማሰሪያ ብር 82,000 (ሰማኒያ ሁለት ሺህ ብር) ወጪ ስለመደረጉና ይህ ገንዘብ ከውርስ
ሀብቱ እንዲቀነስለት ያቀረበ ሲሆን በሰነድ ማስረጃ ግን ያቀረበው ለሀውልት ማሰሪያ
ለእጅ ከፈልኩ ያለውን 52,000 (ሀምሳ ሁለት ሺህ ብር) ብቻ ነው፡፡ ከዚህ ውጪ ምንም
አይነት የተረጋገጠ ወጪ በሌለበትና በሰነድም ባልቀረበበት ሁኔታ እንዲሁም ለእጅ
አወጣሁ ያለውን ብርም እጅግ የተጋነነ እና የወቅቱን ገበያ ዋጋ ከግምት ውስጥ ያላስገባ
ሆኖ ሳለ ፍ/ቤቱ ተቀብሎ በሰነድ ያልተረጋገጠና አቤቱታ ላይ ብቻ የቀረበውን 82,000
(ሰማኒያ ሁለት ሺህ ብር) ከጠቅላላ የውርስ ሀብት ላይ እንዲቀነስ የወሰነው ውሳኔ
የማስረጃ ምዘና ስህተት የተፈፀመበት በመሆኑ ታርሞ በሰነድ የቀረበው 52,000 (ሀምሳ
ሁለት ሺህ ብር) ብቻ ከጠቅላላ ውርስ ሀብት ላይ እንዲቀነስ ሊወሰን ይገባል፡፡
የምጠይቀው ዳኝነት
የተከበረው ይግባኝ ሰሚ ችሎት ከላይ ያቀረብኩትን አቤቱታ በመቀበል
1. የሥር ፍ/ቤት በወላይታ ሶዶ ከተማ ስለሚገኘው ቤት የወሰነውን ውሳኔ በመሻር
ቤቱ የይግባኝ ባይና የሟች ባለቤቴ የጋራ ሀብት ነው በማለት እንዲወስንና
የሚስትነት ድርሻዬ 50% ደግሞ የሟች ወራሾች በሆኑት መልስ ሰጪ እና ልጄ ህፃን
ዲቦራ ማቴዎስ እኩል እንዲካፈሉ እንዲወሰን፣
2. የሥር ፍ/ቤት የቤት ኪራይ ገንዘብን በተመለከተ የወሰነውን ውሳኔ ተሽሮ
የሚስትነት ድርሻዬ 50% ተጠብቆ እንዲወሰንልኝ፣
3. መልስ ሰጪ ለቀብር ማስፈፀሚያ አወጣሁ ያለውና በሰነድ የተረጋገጠው 52,000
(ሀምሳ ሁለት ሺህ ብር) ብቻ በመሆኑ የሥር ፍ/ቤቱ በዚህ ረገድ የሰጠው ውሳኔ
ታርሞ እንዲወሰንልኝ፣
4. በክሱ ምክንያት ያወጣሁትን ወጪ እና ኪሳራ ለጠበቃ የከፈልኩትን ጭምር
የመጠየቅ መብቴ ተጠብቆ እንዲወሰንልኝ ስል በማክበር አመለክታለሁ፡፡

አቤቱታው በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 92 መሠረት በእውነት የቀረበ ነው፡፡

ይግባኝ ባይ

You might also like