You are on page 1of 11

የፍ / መ / ቁ

294783

ቀን

ለፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ ችሎት

አዲስ አበባ

ከሳሽ. አርዲ ኢነርጂ ስልሽን አድራሻ አዲስ አበባ ልደታ ክ/ከተማ ወረዳ 07 ቀበሌ

ተከሳሽ. ደብረብርሃን ዩንቨርስቲ አድራሻ ደ/ብርሃን ቀበሌ 09

ከሳሽ. ጥቅምት 8 ቀን 2014 ዓ.ም በተፃፈ ማመልከቻ ላቀርቡት ክስ ከተከሳሽ የቀረበ መልስ

ከሳሽ ከተከሳሽ ጋር በገባው የኤሌክትሪክ ስራዎች ግንባታ ውል ያለአግባብ በመቋረጡ ምክንያት ግምቱ 748.700 ብር
የሆነ ኪሰራ እንዲሁም ተሰርቶ ለክፍያ የደረሰ እና ያልተፈለ ብር 771594.8 ብር እንዲሁም የዋስትና ገንዘብ ገቢ
እንዲደረግ በማለት ክስ አቅርቧል፡

የመጀመሪያ ደረጃ መቋወሚያ

1.ፍ/ቤቱ ጉዳዩን የማየት ስልጣን የለውም በከሳሽ በተከሳሽ መካከል ያለው የኤሌክትሪክ ስራዎች ግንባታ የተፈፀመው
በደብረብርሃን ከተማ ደብረብርሃን ዩንቨርስቲ ውስጥ በመሆን እና ለሙሉ ምክንያት የሆነው ጉዳዩም የሚፈፀመው በዚሁ
ቦታ በመሆኑ ጉዳዩን የማየት ስልጣን ያለው ይኸው ውሉ በተፈፀመበት እና ለውሉ ምክንያት የሆነው ተግባር
በሚከናወንበት ቦታ ላስቻለው ፍ/ቤት መሆኑን በፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ 24(1)ተገልፆ ይገኛል ስለሆነም ከሳሽ ክስ በዚህ ፍ/ቤት
ማቅረቡ ያለአግባብ በመሆኑ ፍ/ቤቱ በፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ 24(2(ሀ)መሰረት መዝገቡን ዘግቶ እንዲያሰናብተን::

ፍ/ቤቱ የመጀመሪያደረጃ መቃወሚያውን የሚያልፈው ከሆነ በዋናው ፍሬ ጉዳይ መልሴን እንደሚከተለው አቀርባለሁ፡፡

1. ከሳሽ በቀን 30/2/2013 ዓ.ም በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ባወጣው ግልፅ ጨረታ መረት ጨረታው ለመወዳደር
ከቀረቡ ተጫራቶች መካከል ከሳሽ በጨረታ ቁጥር DBU 11/2013 በቀን 15/2/2013 ዓ.ም በወጣው
ማስታወቂያ መሰረት ተወዳድሮ አሸናፊ በመሆኑ በአጠቃላይ ብር 5,147,153.90 የውል ማስከበሪያ 10% ብር
514,715.39 በማቅረብ በአንድ ወር ጊዜ ዉሰጥ ስራዉን ለማጠናቀቅ በመስማማት ዉል የገባ መሆኑ ይታወቃል
በዚህም መሰረት ከሳሽ ወደ ስራ ገብቶ ስራው እየሰራ እና የሰራው አፈፃፀም እየተገመገመ በማጠይቀው የክፍያ
ጥያቄ (Payment request) መሰረት ክፍያ ሲፈፀምለት የቆየ ሲሆን በቁጥር AESL58-2013 ጥር
26/2013 ዓ.ም ከሳሽ በጠየቀዉ መሰረት በቁጥር DBU/2777/3/2021 በቀን 03/06/2013 የመጀመሪያ ዙር
581,927,50(አምስት መቶ ሰማንያ አንድ ሺህ ዘጠኝ መቶ ሀያ ሰባት ከ 50/100) ብር ከዚህም
የመያዥ(retention)5% 26,451,25(ሀያ ስድስት ሺህ አራት መቶ አምሳ አንድ ከ 25/100) ብር ተቀናሽ
ተደርጐ ክፍያ የተፈፀመ ስሆን ለ 2 ኛ ጊዜ በቁጥር AES 120-2013 በቀን መጋቢት 6/2013 ዓ.ም ባቀረበው
የክፍያ ጥያቄ (Payment request)መሰረት በቁጥር DBU-PO/2866/3/2021 በቀን 09/07/2013 ዓ.ም
931,611.99)(ዘጠኝ መቶ ሰላሳ አንድ ሺህ ስድስት መቶአስራ አንድከ 99/100) ሳንቲም መያዥ
(retention)68,797.25(ስልሳ ስምንት ሺህ ሰባት መቶ ዘጠና ሰባት ከ 25/100) ተቀናሽ በማድረግ ክፍያ
ተፈፅሟል፡፡ ከዚህ በኃላ ግን ከሳሽ ምንም አይነት ያቀረበው የክፍያ ጥያቄ የለም እንዲሁም ከሳሽ የስራ ርክክብ
ያላደረገ በመሆኑ የሰራው ስራ ምን ያህል እንደሆነ እና ምን ያህል የቀረ ስራ እንዳለ ከተከሳሽ ጋር
ባልተማመኑበት ሁኔታ ለክፍያ የደረሰ እና ላልተከፈለ ክፍያ 771,594 እንዲሁም ያልተሰራና ቀሪ ስራ
2,862,019.61 ሲል ያቀረበው በማስረጃ ያልተደገፈ እና አግባብነት የሌለው ጥያቄ ስልሆነ ክሱ ዉድቅ
እንዲሆንልኝ፡፡
2. ከሳሽ ለሰራተኛ የወጣ የቀን ክፍያ 127,116 በማለት ላቀረበው ጥያቄ የሰራተኛ ደመወዝ መክፈል በከሳሽና
በቀጠሯቸው ሰራተኞች መካከል ባለው ዉል የመፈፀም ስሆን ተከሳሽ ከከሳሽ ጋር በገባው ውልም ይህንን ለመክፈል
የተዋዋሉበት ሁኔታ የለም ከዚህ ጋር ተያይዞ ያቀረበዉ ማስረጃም በትክክል ስራተኞቹ የከሳሽ ተቀጣሪ ሰራተኞች
ናቸዉ ለማለት የተሟላ የስራ ዉል አላቀረቡም ስለዚህ ተከሳሽ የሚክፍለበት ምክንያት የለዉም ተብሎ
እንዲወሰንልኝ እጠይቃለሁ፡፡
እቃ ለማጓጓዝ የወጣ በማለት 154,260(መቶ ሀምሳአራት ሺህ ሁለት መቶ ስልሳ) ብር ከሳሽ ያቀረበውን
በተመለከተ በከሳሽና ተከሳሽ መካከል ባለው የኤሌክትሪክ ሳይት ግንባታ ዉል ከሳሽ እነዚህ ነገሮች ባላሟላበት
ሁኔታ ይፈፀማል ለማለት አይቻልም በመሆኑም ከሳሽ እና ተከሳሽ በውላቸው ላይ የመጓጓዣ ወጭ በተመለከተ
ተከሳሽ እንዲከፈል በዉሉ ላይ ባልተገለፀበት ሁኔታ ይህንን መጠየቁ አግባብነት የሌለዉ ስለሆነ ተከሳሽየመክፈል
ሀላፊነት የለበትም ተብሎ እንዲወሰንልኝ፡፡
ዲስትሪቡሽን ቦርድ የኮንክሪት ስራዎች 67,110(ስልሳ ሰባት ሺህ አንድ መቶአስር) ብር እንዲሁም የ 12 መኪና
አሸዋ 102,600(አንድመቶ ሁለት ሺህ ስድስት መቶ)በማለት ላቀረብዉ ተከሳሽ እነዚህን ንብረቶች
ያልተረከባቸዉ እና የማያዉቃቸዉ ንብረቶች ናቸዉ ከሳሽም ያቀረበዉ ማስረጃ የለም ስለዚህ ክሱ ዉድቅ
እንዲደረግልኝ፡፡
ከሳሽ/variation works/ ለተጨማሪ ስራዎች ክፍያ 138,165,78(መቶ ሰላሳ ስምንት ሺህ አንድ መቶ
ስልሳ አምሰት ብር ከ 78/100)በማለት ላቀረበው የክፍያ ጥያቄ እነዚህን ስራዎች ስለመስራቱ የቀረበ ማስረጃ
የለም ምን አይነት ስራዎችን በመቀነስ ወይም በመጨመር ስለመስራቱ የሚያመልክት የከሳሽ እና የተከሳሽ
ስምምነት የሚያመለክት ማስረጃ አላቀረበም በመሆኑም ከሳሽ ይህን ክፍያ ሊከፈል የሚችልበት የህግ አግባብ
የለም ተብሎ እንዲወሰንልኝ፡፡
የመጋዘን አገልግሎት ኪራይ የ 3 ወር 12,000(አስራ ሁለት ሺህ ብር) የጥበቃ ወጭ 3000 በድምሩ 9000
በማለት ለቀረበው ጥያቄ ተከሳሽ ከሳሽ በተቻለ መጠን ስራውን እንዲያጠናቅቅ የሚያቀርባቸውን የውል
ማራዘሚያዎች በመቀበል ለሰራቸው ስራዎች ደግሞ ክፍያ በመክፈል በተቻለ መጠን ከሳሽ ስራውን ሰርቶ እና
ጨርሶ እንዲያስረክበው ለማድረግ ቢሞክርም ከሳሽ በራሱ ምክንያት ስራውን ለመስራት ባለመፈለጉ
በተሰጠውም ማስጠንቀቂያ መሰረት ወደ ስራው ገብቶ በመስራት እና የገጠመውን ችግር ለተከሳሽ በማሳወቅ
ለስራው መጠናቀቅ ምንም አስተዋፅኦ ስያደርግ እነዚህን ክፍያዎች ተከሳሽ ይከፈለን ማለቱ ተከሳሽን
አላስፈላጊ ወጭ በመጠየቅ ያለአግባብ ለመበልፀግ ያለው ሀሳብ የሚያሳይ በመሆኑ ጥያቄው ውድቅ
እዲደረግልኝ፡፡
ለ 72 ቀን ያልጋ ወጪ ለ 4 ሰዎች 43,200 (አርባ ሶስት ሺህ ሁለት መቶ) ሰዎች በማለት ላቀረበው ጥያቄ
ከሳሽ ከሰራተኞች ጋር ባለው የስራ ውል ሊከፈላቸው የሚችለውን የአበል ጥያቄ ተከሳሽን በምንም አግባብ
ሊጠይቁ የሚችልበት ሁኔታ የለም በመሆኑም ፍርድቤቱ ጥያቄውን ውድቅ እንዲያደርግልን፡፡
ከሳሽ በተጨማሪ ሪቴንሽን (መያዣ) ክፍያ 95,248 (ዘጠና አምስት ሺህ ሁለት መቶ አርባ ስምንት) ብር
እንዲከፈለኝ በማለት ጥያቄ አቅርበዋል በመሰረቱ የሬቴንሽን (የማያዣ) ክፍያ ስራው ከተጠናቀቀ በኃላ
የሚከፈል ክፍያ ሲሆን ከሳሽ እና ተከሳሽ በገቡት በአጠቃላይ የዉል ሁኔታ አንቀፅ 88.7 መሰረት ስራው
ርክክብ እና ችግር ማስወገጃ ግዜ ተብሎ የተቀመጠው 12 ወር መሆኑ ያመለክታል በመሆኑም ከሳሽ ስራውን
ጨርሶ ባላስረከበበት እና ለሰራው ስራ ችግር ማስወገጃ ተብሎ በማያዣነት የተያዘውን ብር ይከፈለኝ ብሎ
ጥያቄ ማቅረቡ አግባብነት የሌለው መሆኑ ጥያቄው ውድቅ እንዲደረግልን እንጠይቃለሁ፡፡
3. ከሳሽ በተከሳሽ ግቢ ወስጥ በሚሰሩ ግንባታ ስራዎች ምክንያት በማድረግ ስራ ተስተጓጉሎብኛል በማለት ላቀረበው
ክስ በተመለከተ በግቢው ውስጥ የሚሰሩ ስራዎች ስራውን በውሉ ላይ በተጠቀሰው ቀን መሰረት ለማጠናቀቅ
ስላልቻልኩ ብሎ ከሳሽ በቁጥር AESL135-2013 በቀን መጋቢት 29 ቀን 2013 ባቀረበው የውል ይራዘምልኝ
ጥያቄ ተከሳሸ ጥያቄውን ተቀብሎ በቁጥር ደ.ብ.ዩ.ቢ.ል/337/1-01/7 በቀን 12/08/2013 ዓ.ም ውል ያራዘመ
ሲሆን ከሳሽም በተራዘመው ውል መሰረት ስራውን ማጠናቀቅ አልቻለም፡ እንዲሁም ከሳሽ በድጋሚ ይህን
ምክንያት አድርጐ ውል እንዲራዘምለትም የጠየቀው ጥያቄ የለም ይህ በሆነበት ሁኔታ የራሱን የስራ ድክመት
በመሸፈን እና ስራውን ያላጠናቀቀው በተከሳሽ ምክኒያት ነው ለማለት ያቀረበው ክስ ከእውነት የራቀ እና
በማስረጃ ያልተደገፈ ስለሆነ ምክኒያቱን ውድቅ እንዲያደረግልኝ፡፡
4. የቅድመ ክፍያ በተመለከተ ከሳሽ ላቀረበው ጥያቄ በከሳሽና በተከሳሽ መካከል ባለው ልዩ የውል ሁኔታዎች SCC
አንቀፅ 60.1,60.2 መሰረት የቅድመ ክፍያ እንደሌለ ተስማምተው ውሉን አፅድቀዋል፡፡ይህ በሆነበት ሁኔታ ከሳሽ
በውሉ ውስጥ ስምምነት ላይ ያላሰፈሩትንና ያልተስማሙበትን ቅድመ ክፍያ መጠየቁ አግባብነት የለውም
ይህንንም እንደውል ለመፈፀም ያልቻለበት ምክንያት አድርጐ ማቅረቡ አግባብነት የሌለው በመሆኑ ጥያቄው
ውድቅ እንዲደረግልኝ ስል እጠይቃለሁ፡፡

5. የጥሬ እቃ አቅርቦትንም በተመለከተ ተከሳሽ የከሳሽን የውል ማራዘሚያ ምክንያቶች ውድቅ ሳያደረግ እየተቀበለ
ውሉን እያራዘመ የቆየ መሆኑን ካቀርብናቸው ማስረጃዎች መረዳት ይቻላል በመሆኑም ከሳሽ በድጋሚ የጥሬ እቃ
አቅርቦት አለ እና ውል ይራዘምንል ብሎ ቢያመለክት ተከሳሽ ጥያቄውን ላይቀበልበት የሚችልበት ምክንያት አልነበረም
ሆኖም ግን ከሳሽ እነዚህን ምክንያቶች አላግባብ በማቅረብ ውሉ የተቆረጠው በተከሳሽ ጥፋት መሆኑን ለማመለክት
ያቀረበው መክንያት በመሆኑ ፍርድቤቱ ጥያቄውን ውድቅ እንዲያደርግልኝ እጠይቃለሁ፡፡

6. ከሳሽ ውሉ በተከሳሽ ጥፋትና ከአቅሜ በላይ በሆነ ችግር ውሉ ለማጠናቀቅ አልቻልኩም ይበል እንጂ የተከሳሽ ጥፋት
ምን እንደሆነ ያቀረበው በቂ ማስረጃ የለም እንዲሁም ካቅሚ በላይ በሆነ መክንያት ውሉን አልፈፀምኩም ይበል እንጂ
ከአቅም በላይ (force majour) ብሎ የገለፀው ወይም ያቀረበው ማስረጃ የለም ተከሳሽ ውሉን ማቋረጡ ተከሳሽ
ስራዉን በውሉ መሰረት አለመስራት ሆኖ እያለ ከሳሽ ውሉ ያላአግባብ ተቆርጦብኛል ማለቱ አግባብነት የለውም
በመሆኑም ከሳሽ ለውል ማስከበርያነት ከአባይ ባንክ በ 514,744.39 (አምስት መቶ አስራ አራት ሺህ ሰባት መቶ አርባ
አራት ብር ከ 39/100) ለተከሳሽ ገቢ የመይሆንበት ምክንያት የለም የውል ማስከበሪያ ስምምነቱም ያለምንም
መክንያት ተከሳሽ በጠየቀ ግዚ ገቢ እንደሚደረግ ይገልፃል በመሆኑም በተደጋጋሚ ገንዘቡ ገቢ እንዲደረግ የጠየቅንበት
ሁኔታ ስላለ ፍ/ቤቱ የከሳሽን ጥያቄ ውድቅ በማድረግ ውል ማስከበሪያ ገንዘቡ ወደ ተከሳሽ ገቢ እንዲሆን እንዲወሰንልን
እንጠይቃለን፡፡
በአጠቃላይ ተከሳሽ ዉሉን ያፈረሰዉ ከሳሽ እንደገባዉ ዉል ስራዉን ባለማክናዎኑ በመሆኑ በህጉ እና በዉሉ መሰረት
ትክክል ነዉ ተብሎ ስራዉ በከሳሽ ምክኒያት የተቋረጠ በመሆኑ ተከሳሽ 1,519,000(አንድ ሚሊዮን አምስት መቶ አስራ
ዘጠኝ ሺህ )መክፈል የለበትም በማለት ክሱን ዉድቅ አድርጎ በክሱ ምክኒያት ላወጣነዉ ወጭ ዝርዝር የማቅረብ መብት
ተጠብቆልን በነፃ እንዲያሰናብተን አመለክታለሁ፡፡

ያቀረብኩት መልስ እዉነት ስለመሆኑ በፍ/ብ/ሕ/ቁ 92 መሰረት አረጋግጣለሁ

ፀደይ እሸቱ

ተከሳሽ ነ

የኮ/መ/ቁ 298233

ቀን መጋቢት 29/2014 ዓ.ም

ለፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት

ልደታ ምድብ ችሎት 1 ኛ ኮንስትራክሽን ችሎት

አዲስ አበባ

ከሳሽ፡-ደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ አድራሻ…. ደ/ብርሃን 09 ቀበሌ

ተከሳሾች፡-1 ኛ አርዲ ኢነርጅ ሶሉሽንስ አድራሻ… ልደታ ክ/ከተማ ወረዳ 07

2 ኛ አባይ ባንክ አ.ማ አድራሻ…. አዲስ አበባ


ከ ከሳሽ የቀረበ የክርክር ማቆሚያ (የፍርድ አስተያየት)

1. ከሳሽ 1 ኛ ተከሳሽ በገባው ኤሌክትሪክ ግንባታ ውል መሰረት ስራዉን ጨርሶ ባለማጠናቀቁ ምክኒያት
የማቋረጫ ክፍያ እንዲክፍል ክስ አቅርበን ምስክሮቻችንን አሰምተናል፡ በዚህም ከሳሽ ለዉሉ መቋረጥ
ምክኒያት የሆነዉ 1 ኛ ተከሳሽ በገባዉ ውል መሰረት ስራዉን አጠናቀቆ ባለመጨረሱ በተለይም በተማሪዎች
ማደሪያ (ተማሪዎች አገልግሎት )ህንፃ ላይ የሚዘረጋዉን 3*240/120 የሆነ ኬብል እና MDB-AUD
የተባለዉን ቦረድ አቅርቦ ከጄኔተሮች ጋር አግናኝቶ ባለማጠናቀቁ ምክኒያት መሆኑን ይህም የዉሉን 50%
የሚሆነዉን ስራ መሆኑን ያቀረብናቸዉ ምስክሮች መስክረዋል፡፡ የ 1 ኛተከሳሽ 1 ኛ ምስክር እና የድርጅቱ ሃላፊ
የሆኑት በሰጡት የምስክረነት ቃልም ይህ ወደ ተማሪዎች ማደሪያ የሚዘረጋዉ የኤሌክትሪክ መስመር
መዘርጋት ስራ ያለመስራቱን በምስክርነት ቃሉ አረጋግጠጧል በተጨመማሪም እነዚህን ለስራዉ አስፈላጊ የሆኑ
እቃዎችን ስራዉ በሚሰራበት አካባቢም ያላቀረበ መሆኑን ሶስቱም የከሳሽ ምስክሮች ያስረዱ ሲሆን
በተመሳሳይ የተከሳሽ 1 ኛ ምስክርም ይሄንኑ አረጋግጠዋል ፡፡ይህ ለተማሪዎች አገልግሎት ህንፃ የሚሰራዉ
የኤሌትሪክ ግንባታ 1 ኛተከሳሽ በከሳሽ ግቢ ዉስጥ በሚሰራ የተፋሰስ ስራ ምክኒያት ተስተጓጉሎበኛል ከሚለዉ
የኤሌትሪክ መስመር ዝረጋታ ጋር የማይገናን ስራ መሆኑን ሁሉም የከሳሽ ምስክሮች በተመሳሳይ የመሰከሩ
ሲሆን የተከሳሽ 1 ኛ ምስክርም ይሄንኑ ሳይክድ በተመሳሳይ ምስክርነቱን ሰጥቷል፡፡
2. ተከሳሽ በውሉ መሰረት ስራየን እንዳልሰራ ያደረገኝ በከሳሽ ግቢ ዉስጥ በሚሰራ የተፋሰስ ስራ ምክኒያት ነዉ
በሚል ላቀረበዉ ምክኒያት የከሳሽ ምስክሮች በሰጡት ቃል የተፋሰስ ስራዉን ምክኒያት በማድረግ ውሉ
እንዲራዘም በጠየቀዉ መሰረት እስከ ሚያዚያ 10 ድረስ 2013 ዓም ድረስ በራሱ በተከሳሽ ጠያቂት
የተራዘመለት መሆኑን እና ይህን ከተፋሰስ ስራዉ ጋር የሚያገናኘዉን ስራ የኤሌትሪክ መስመሩን በቱቦ
(ፒቢሲ)ዉስጥ አሳልፎ እንዲሰራዉ ተስማምተዉ በዛ መልኩ ሰርቶ ስራዉም ያለቀ ስራ ተደርጎ የተረከቡት
መሆኑን እና ይህም የሆነዉ የመጨረሻዉ የዉል የተራዘመበት ጊዜ ከማለቁ በፊት እንደሆነ በተመሳሳይ
አስረድተዋል ከዚህ በኋላም ተከሳሽ የተፋሰስ ግንባታዉ ስራዉን ለማጠናቀቅ እንቅፋት እንደሆነበት ለከሳሽ
ያሳወቀበት ሁኔታ የለም ለዚህም ያቀረበዉ የጽሁፍ ማስረጃ የለም፤ ተጨማሪ ውል እንዲራዘምለት
ያቀረበዉም ጥያቁ የለም ውል እንዲራዘምለት መጠየቅ ያለበት ተከሳሽ መሆኑን እና ይህንንም ያላደረገ
መሆኑን 1 ኛ የተከሳሽ ምስክር እና የድርጅቱ ሃላፊ የሆኑት በሰጡት የምስክርነት ቃል ይህንኑ አረጋግጠዋል
3. የ 1 ኛተከሳሽ ምስክሮች በተፋሰስ ግንባታ ስራዉ ምክኒያት እንደዉሉ ስራችንን ሰርተን መጨረስ አልቻልንም
የሚለዉን ለማስረዳት የቀረቡ ቢሆንም የኤሌትሪክ ግንባታዉ እና የተፋሰስ ስራዉ የሚገናኙት አንድ አቋራች
ቦታ ላይ መሆኑን ይሄዉም 1 ኛ የተከሳሽ ምስክር 10 ሜትር የሚሆን እርዝመት አለዉ ብሎ ሲመሰክር 2 ኛ እና
ሶስተኛ ምስክሮች ደግሞ ርዝመቱ 5 ሜትር እና 6 ሜትር ነዉ በማለት በተለያ መንገድ መስክረዋል፡
በተጨማሪም የመጨረሻዉን የውል ማራዘሚያ ጠይቀን ማራዘሚያዉ ዝግይቶ ነዉ የደረሰን በማለት 1 ኛ
የተከሳሽ ምስክር ቃሉን የሰጠ ሲሆን 2 ኛ ምስክር ደግሞ የውል ማራዘሚያዉ ሳይደረሰን ማስጠንቀቂያ
ተሰጥቶናል በማለት በተለየ መንገድ ምስክረቱን ሰጥቷል ፡በእንዲሁም የተከሳሽ 1 ኛ ምስክር የኤሌትሪክ
መስመሩን በፒቢሲ ዉስጥ በማሳለፍ የተፋሰስ ስራዉን አቋርጦ እንዲያልፍ ከከሳሽ ጋር የተስማሙ መሆኑን
ሲመሰክሩ 2 ኛ የተከሳሽ ምስክር ግን ከከሳሽ ጋር ምንም አይነት ስምምነት ሳኖር የኤሌትሪክ መስመሩ
እንዳይጎዳ በማሰብ በፒቢሲ ዉስጥ አሳልፈን ዘርግተነዋል ሲሉ በተለየ መንገድ ምስክሯል፡በተጨማሪም
መስመሩ በተፋሰሱ ላይ የተዘረጋዉ የዉሉ ዘመን ካለቀ በኋላ ነዉ በማለት የሰጡት የምስክርነት ቃል ተከሳሽ
ምንም ጥቅም የማያገኝበትን ስራ ለአንድ የመንግስት ተቋም በነጻ ይስራል ተብሎ ሊታመን ማይችል እና
ተቀባይነት የሌለዉ ምስክረነት ቃል መሆኑን መረዳት ይቻላል፡፡ከዚህ በተጨማሪ የተከሳሽ ምስክሮች ተጨማሪ
ስራ ሰርተናል በማለት ለሰጡት የምስክረነት ቃል ከዋናዉ ዉል በመጨመር ምን አይነት ሰራ ለመስራት ከከሳሽ
ጋር እንደተስማሙ የማሳይ ምንም አይነት መረጃ አላቀረቡም፡፡
በአጠቃለይ ከሳሽ እንዳቀረብነዉ ክስ እና እንዳሲያዝነዉ ጭብጥ ምስክሮቻችን በበቂ ሁኔታ ያስረዱልን
ሲሆን በተከሳሽ በኩል የቀረቡት ምስክሮች በተለይም 1 ኛ እና 2 ኛ ምስክሮች መካከል በተለያየ መንገድ
ቃላቸዉን ከመስጠታቸዉ በተጨማሪ በ ተንቀሳቃሽ ምስል እና በፎቶ አስደግፈዉ ያቀረቡትን ቀን ወር እና
አመተ ምህረት የማይገልፅ ማስረጃ ነዉ፡ አንዲሁም የ 1 ኛተከሳሽ 1 ኛምስክር እና የድርጅቱ ሃላፊ በተለያ ጊዜ
ከ ከሳሽ ጋር ስራዉን በተመለከተ ስለመያደርገዉ ዉይይትም ምንም የማዉቁት ነገር እነደሌለ የመሰከሩ በመሆኑ
እንዲሁም 1 ኛተከሳሽ ምንም አይነት የጽኁፍ ማስረጃ ስላላቀረበ ክሱን አስተባብሏል ለማለት አያስችልም ፡፡
በመሆኑ የተከበረዉ ፍ/ቤት ከሳሽ ባቀረብነዉ ክስ እና ማሰረጃ መሰረት ዉሳኔ እንዲወስንልኝ ስንል
እንጠይቃለን፡፡

ቁጥር

ቀን

ለሰሜን ሸዋ ከፍተኛ ፍ/ቤት

ደብረብርሀን

ከሳሽ…..ደብረብርሀን ዩኒቨርሲቲ አድራሻ ደብረብርሀን ቀበሌ 09

ተከሳሾች …..1 ኛ አስካል ባየህ እዉነቱ አድራሻ ደብረብርሀን 09 ቀበሌ

2 ኛ መሬም ሷሊህ ኡመር አድራሻ ደብረብርሀን 06 ቀበሌ

የክሱ ርእስ፡- በዉሉ መሰረት ባለመፈጸሙ ምክኒያት የቀረበ ክስ ነዉ

ሀ.ፍ/ቤቱ ጉዳዩን የማየት ስልጣን አለዉ

ለ.ከሳሽ እና ተከሳሽ በህግ ያልተገደበ መብት አለን

ሐ.ከሳሽ ክሱን የሚያቀርበዉ በነገረ ፈጁ አማካኝነት ነዉ

መ.ክሱ የቀረበዉ በ 133,440 (አንድ መቶ ሰላሳ ሶስት ሺህ አራት መቶ አርባ አራት )ብር

ግምት ነዉ

ሠ.ክሱ በፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ 222 እና 223 መሰረት የቀረበ ነዉ

የክሱ ዝርዝር

1. በከሳሽ እና በ 1 ኛተከሳሽ መካከል በቀን 11/01/2010 ዓ.ም የትምህርት ዉል ስምምነት የተደረገ ሲሆን በዉሉ
መሰረት 1 ኛ ተከሳሽ ለሁለተኛ (ማስተርስ) ዲግሪ በጅኦቴክኒካል ትምህርት በባህርዳር ዪኒቨርሲቲ ለሁለት
ዓመት ለመማር ዉል የገባች መሆኑ የታወቃል፡፡
2. ሆኖም 1 ኛተከሳሽ ለተቋሙ ሳታሳዉቅ እና ምንም አይነት ምክኒያት ሳታቀርብ የዉሉን አንቀጽ 2.4
በመተላለፍ ትምህረቷን ያቋረጠች ሲሆን ከሰዉ ሀብት አስተዳደርና ልማት ዳይሮክቶሬት በቁጥር/Ref.No
9644/33-01/25 በቀን 21/06/2011 በወጣ የመጀመሪያ ማስታወቂያ 1 ኛ ተከሳሽ ትምህረት ላይ ስለመሆኗ
የሚገልጽ ህጋዊ ማስረጃ ይዘዉ እንዲቀርቡ የተጠየቁ ቢሆንም ባለማቅረባቸዉ በድጋሜ በቁጥር/Ref.No
9826/33-01/07 በቀን 04/07/2011 ለሁለተኛ ጊዜ ማስታወቂያ የወጣ ቢሆንም ያሉበትን ሁኔታ የሚገልጽ
ማስረጃ ለያቀርቡ ባለመቻላቸዉ በቁጥር Ref.No 10362/33-01/10/በቀን 07/08/2011 ዓ.ም በተፃፈ
ደብዳቤ ከስራ እንዲሰናበቱ ተደርገዋል፡፡
3. በመሆኑም የዉሉ አንቀፅ 2.9 መሰረት 1 ኛ ተከሳሽ በዉሉ መሰረት ሳይፈጽሙ ቢቀሩ ለመክፈል ከተስማሙት
ዉስጥ የትምህርት ዉል ፈፅመዉ ከሄዱበት 11/01/2010 ጅምሮ ከስራ እስከተሰናበቱበት ህዳር ወር 2011
ዓ.ም ድረስ በከሳሽ ተቀቋም የተከፈላቸዉ የ 14(አስራ አራት )ወር ደመዎዝ 14 × 8310 ብር
=116,340(አንድ መቶ አስራ ስድስት ሺህ ሶስት መቶ አርባ ብር) 12 ወር ከ 20 ቀን ለቤት አበል የተከፈለ፡
12 ወር ከ 20 ቀን × 700 ብር=8,866 ለትራንስፖረት የተከፈለ 12 ወር ከ 20 ቀን × 150 ብር = 1,900
ለትምህርት ቁሳቁስ የተከፈለ 12 ወር ከ 20 ቀን × 500=6,333 ጥቅማጥቅም ብር 133,439(አንድ መቶ
ሰላሳ ሶስት ሺህ አራት መቶ አርባ ብር ) እንዲሁ በዉሉ አንቀፅ 2.9.7 መሰረት እንደዉሉ ባለመፈጸማቸዉ
ቅጣት 10,000(አስር ሺህ ብር ) ተጨምሮ አጠቃላይ 143,439 (አንድ መቶ አርባ ሶስት ሺ አራት መቶ ሰላሳ
ዘጠኝ )ብር እንዲከፍሉ እንዲወሰንልን

4. 2 ኛ ተከሳሽ 1 ኛተከሳሽ በዉሉ 2.1 እስከ 2.8 የተዘረዘሩትን ሳይፈጽም ቢቀር ዋስ በመሆን በአንድነት እና
በነጠላ ሀላፊነት እንዳለባቸዉ በዉሉ አንቀፅ ቁጥር 5.1 መ በገቡት የዋስትና ግዴታ መሰረት ብር 133,440
(አንድ መቶ ሰላሳ ሶስት ሺህ አራት መቶ አርባ ብር) እንዲከፍሉ ፍ/ቤቱ እንዲወስንልን ቀረበ ክስ ነዉ፡፡

የምንጠይቀዉ ዳኝነት

1. 1 ኛ ተከሳሽ የትምህርት ስልጠና ዉል ገብተዉ ለትምህርት የተላኩ ቢሆንም ከሳሽ ተቋምን ሳያሳዉቁ
ትምህርታቸዉን በማቋረጣቸዉ ከሳሽ ያለአግባብ ለ ተከሳሽ የከፈለዉን 133,440 (አንድ መቶ ሰላሳ ሶስት
ሺህ አራት መቶ አርባ ) ብር ከእነ ህጋዊ ወለዱ ታስቦ እንዲከፍሉ እንዲወሰንልን
2. 2 ኛ ተከሳሽ በዉሉ አንቀፅ በገቡት የማይነጣጠል ዋስትና ግዴታ መሰረት 133,440 (ሁለት መቶ ስልሳ ዘጠኝ
ሺህ ስምነት መቶ አርባ ብር) ከነህጋዊ ወለዱ እንዲከፍሉ እንዲወሰንልን
3. ለዚህ ክስ ላወጣነዉ ወጭ እና ኪሳራ እንዲወስንልን ፍ/ቤቱን እንጠይቃለን፡፡

ያቀረብነዉ ክስ እዉነት ስለመሆኑ በፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁጥር 92 መሰረት እናረጋግጣለን፡፡


ቀን

ለሰሜን ሸዋ ከፍተኛ ፍ/ቤት

ደብረብርሀን

ከሳሽ…..ደብረብርሀን ዩኒቨርሲቲ አድራሻ ደብረብርሀን ቀበሌ 09

ተከሳሾች …..1 ኛ አስካል ባየህ እዉነቱ አድራሻ ደብረብርሀን 09 ቀበሌ

2 ኛ መሬም ሷሊህ ኡመር አድራሻ ደብረብርሀን 06 ቀበሌ

በፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁጥር 223 መሰረት የቀረበ የማስረጃ ዝርዝር

የጽሁፍ ማስረጃ

1. 1 ኛ ተከሳሽ በከሳሽ ተቋም የተቀጠሩ መሆኑን የሚገልጽ በቁጥር Ref1817/16-01/12 በቀን


24/01/2008 ዓ.ም የተጻፈ ደብዳቤ፡፡
2. 1 ኛ ተከሳሽ ለድህረ ምረቃ ትምህረት እድል የሰጣቸዉ በመሆኑ የትምህተት ዉል እንዲዋዋሉ ለህግ
ክፍሉ በቁጥር Ref.No 2107/20-01/25 በቀን 08/02/2009 የተፃፈ ደብዳቤ
3. ከሳሽ ተቋም ዉል ሰጭ 1 ኛተከሳሽ ዉል ተቀባይ በመሆን እና 2 ኛ ተከሳሽ የ 1 ኛ ተከሳሽ ዋስ
በመሆን በቀን 08/02/2009 ዓ.ም የተፈጸመ ትምህርት ስልጠና ዉል፡፡
4. 2 ኛ ተከሳሽ ለ 1 ኛ ተከሳሽ ዋስ ለመሆን ከዩኒቭረሲቲዉ ሰዉ ሀብት አመራር ደጋፊ የስራ ሂደት
በቁጥር Ref.No 2113/20-01/14 በቀን 08/02/2009 ዓ.ም ያጻፉት ደብዳቤ
5. 1 ኛ ተከሳሽ የትምህርት ጊዜአቸዉን አጠናቀዉ ወደስራ ባለመመለሳቸዉ በቁጥር Ref.No 9643/33-
01/25 በቀን 21/06/2011 ዓ.ም ያመረጃቸዉን ይዘወ እንዲቀርቡ የመጀመሪያ ማስታወቂያ የወጣበት
ደብዳቤ 1 ገጽ ኮፒ
6. 1 ኛ ለዩኒርስቲዉ የሰዉ ሃብት አስተዳደር እና ልማት ዳይሮክቶሬትያሉበትን ሁኔታ እንዲያሳዉቁ
የሚጠይቅ 2 ኛ ጊዜ በቁጥር Ref.No 9826/33-01/07 በቀን 04/07/2011 ዓ.ም የወጣ ማስታወቂያ
7. 1 ኛ ተከሳሽ በመጀመረያም ሆነ በሁለተኛ ማሰታወቂያ ልቀረ በመሆኑ በቁጥር Ref.No10360/33-
01/10 በቀን 07/08/2011 ዓ.ም ከመንግስት ስራ የተሰናበቱ መሆኑን የሚገልፅ ደብዳቤ 1 ገጽ ኮፒ
8. 1 ኛ ተከሳሽ በገቡት የዉል ግዴታ መሰረት ባለመፈጸማቸዉ ክስ እንዲመሰረትባቸዉ ለህግ አገልግሎት
ክፍል በቁጥር Ref.No100405/33/01/25 በቀን 09/08/2011 ዓ.ም የተፃፈ ደብዳቤ 1 ገጽኮፒ

የሰዉ ማስረጃ

1.

2.

3.

ለአ/ብ/ክ/መ/ጠ/ፍ/ቤት
ድብረብርሃን

ቀን ነሀሴ /2014 ዓ.ም

ለአ/ብ/ክ/መ ጠቅላይ ፍ/ቤት

ደብረብርሃን ምድብ ችሎት

ደብረብርሃን

የፍርድ ባለመብት… ደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ አድራሻ ደብረብርሃን 09 ቀበሌ

የፍርድ ባለእዳ… አባስ ኮንስትራክሽን ድርጅት አድራሻ አ/አ ልደታ ክ/ከተማ ወረዳ 07

በፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ. 378 መሰረት እንደ ዉሳኔዉ እንዲፈጸም የቀረበ የአፈፃፀም ክስ ነዉ፡፡

1. የአፈፃጸም ክስ የቀረበበት ፍርድ የሰጠዉ የሰሜን ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ምድብ /መ/ቁ. 298233
ሚያዚያ 11 ቀን 2014 ዓ.ም ነዉ፡፡
2. እስካሁን በዉሳኔዉ መሰረት የተፈጸመ ነገር የለም፡፡

የአቤቱታው ዝርዝር

በፍርድ ባለመብት ደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ እና በፍርድ ባእዳዎች አባስ ኮንስትራክሽን ድርጅት መነበረዉ
የግንባታ ውል ክስ ኢነርጅ ሶሉሽንስ 2 ኛ አባይ ባንክ አክሲዎን ማህበር መካከል በፌዴራል የመ/ደ/ፍ/ቤት 1 ኛ
ኮንስትራክሽን ችሎት በኮ/መ/ቁ/298233 በነበረዉ የኤሌትሪክ ግንባታ ውል ክስ ክርክር ፍ/ቤቱ ሚያዚያ 11 ቀን
2014 ዓ.ም በሰጠዉ ውሳኔ 1 ኛ የፍርድ ባለእዳ ለውሉ መቋረጥ ጥፋተኛ በመሆኑ የውል ማቋረጫ ክፍያ ብር
351,765.06(ሶስት መቶ ሀምሳ አንድ ሺህ ሰባት መቶ ስልሳ አምሰት ከዜሮ ስድስት ሳንቲም ) እንዲሁም 2 ኛ
የፍርድ ባለእዳ የመልካም ስራ አፈጻጸም ዋስትና ብር 514,715.39(አምስት መቶ አስራ አራት ሺህ ሰባት መቶ
አስራ አምስት ከሰላሳ ዘጠኝ ሳንቲም) እንዲከፍሉ ወስኗል፡፡የፍርድ ባለእዳዎች እሰካሁን በዉሳኔዉ መሰረት
የተወሰነባቸዉን ገንዘብ ገቢ ያላደረጉ በመሆኑ በህግ አግባብ እንዲከፍሉ እንዲደረግልን ስንል አቤቱታችንን
እናቀርባለን፡፡

የምንጠይቀዉ ዳኝነት

1. 1 ኛ የፍርድ በለእዳ በውሳኔዉ መሰረት ብር 351,765.06(ሶስት መቶ ሀምሳ አንድ ሺህ ሰባት


መቶ ስልሳ አምስት ከዜሮ ስድስት ሳንቲም) እንዲከፍል እንደረግልን፡፡
2. 2 ኛ የፍርድ ባለእዳ በውሳኔው መሰረት 514,715.39(አምስት መቶ አስራ አራት ሺህ ሰባት መቶ
አስራ አምስት ከሰላሳ ዘጠኝ ሳንቲም)እንዲከፍል እንዲደረግልን ስንል እንጠይቃለን፡፡

ያቀረብነዉ አቤቱታ እዉነት ስለመሆኑ በፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ 92 መሰረት እናረጋግጣለን፡፡

ስለ ፍርድ ባለመብት መ/ቤት

ፀደይ እሸቱ

ነገረ-ፈጅ
ለአ/ብ/ክ/መ/ጠ/ፍ/ቤት

ደብረብርሀን

የአፈፃፀም ከሳሽ፡-ደብረብርሃን ዩኒቭረሲቲ አድራሻ ደብረብረኀን

የአፈፃፀም ተከሳሽ፡- ማስተር ኮንስትራክሽን ድርጅት አድራሻ አዲስ አበባ

በፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ. 378 መሰረት አንደ ስምምነት ዉሉ እንዲፈጸም የቀረበ የአፈፃፀም ክስ ነዉ፡፡

1. የአፈፃጸም ክስ የቀረበበት ፍርድ የሰጠዉ የፌዴራል የመጀመሪያ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ 1 ኛ


ኮንስትራክሽን ችሎት በኮ/መ/ቁ. 298233 ሚያዚያ 11 ቀን 2014 ዓ.ም ነዉ፡፡
2. እስካሁን በዉሳኔዉ መሰረት የተፈጸመ ነገር የለም፡፡

የአቤቱታው ዝርዝር

በፍርድ ባለመብት ደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ እና በፍርድ ባእዳዎች 1 ኛ አርዲ ኢነርጅ ሶሉሽንስ 2 ኛ አባይ
ባንክ አክሲዎን ማህበር መካከል በፌዴራል የመ/ደ/ፍ/ቤት 1 ኛ ኮንስትራክሽን ችሎት በኮ/መ/ቁ/298233 በነበረዉ
የኤሌትሪክ ግንባታ ውል ክስ ክርክር ፍ/ቤቱ ሚያዚያ 11 ቀን 2014 ዓ.ም በሰጠዉ ውሳኔ 1 ኛ የፍርድ ባለእዳ
ለውሉ መቋረጥ

You might also like