Professional Documents
Culture Documents
1
1
የብየዳ የአገልግሎት ስራ ውል
አድራሻ፡- አዲስ አበባ ጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 የቤት ቁጥር አዲስ
ውል ተቀባይ፡- አቶ ሰለሞን ዳኜ
ውል ሰጪ ለሃና ማርያም ግቢ የኤሌክትሪክ መስመር ከስዊች ጊር እስከ ትራንስፎርመር የገመድ ዝርጋታና የማገናኘት ስራ
በሚፈለገው ጥራትና በአስቸኳይ ከስር በተመለከተው ሰንጠረዥ እንዲሰራለት ስለፈለገ፤
ውል ተቀባይ ደግሞ፤ የተጠቀሰውን የኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታና የማገናኘት ስራ ጥራቱን በጠበቀ ሁኔታና ከላይ
በተመለከተው ዋጋ እንዲሁም በፍጥነት ለመስራት ስለተስማማ በሁለቱ ተዋዋይ ወገኖች መካከል ይህ የውል ስምምነት
ተፈፅሟል፡፡
አንቀፅ አንድ
የውል ሰጪ ግዴታ
ውል ሰጪ የተጠቀሰው የኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታና የማገናኘት ስራ ውል ሰጪ በሚያቀርብለት እቃ መሰረት ሙሉ
በሙሉ በጥራት መሰራቱ ሲረጋገጥ ከተ.እ.ታ በፊት 82,080.00 ብር (ሰማንያ ሁለት ሺህ ሰማንያ ብር) በተጨማሪ
የተ.እ.ታ 15% = 12,312 ጨመሮ በጠቅላላ 94,392.00 ብር (ዘጠና አራት ሺህ ሶስት መቶ ዘጠና ሁለት ብር) ውል
ሰጪ ሙሉ ክፍያ ለውል ተቀባይ ይከፍላል፡፡
አንቀፅ ሁለት
የውል ተቀባይ ግዴታ
ውል ተቀባይ የተጠቀሰው የኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታና የማገናኘት ስራ በጥራት የመስራትና በተባለው ጊዜ የማስረከብ
ግዴታ አለበት፡፡
አንቀፅ ሶስት
የክፍያ ጥያቄ ስለማቅረብ
ውል ተቀባይ የተጠቀሰው የኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታና የማገናኘት ስራ በጥራት መሰራቱ የሚያረጋገጥ ተገቢ ማስረጃ
አቅርቦ የሰራበትን ገንዘብ እንዲከፈለው ጥያቄ ማቅረብና ውል ሰጪም የኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታና የማገናኘት
ዋጋውን ብር ከ ተ.እ.ታ በፊት 82,080.00 ብር (ሰማንያ ሁለት ሺህ ሰማንያ ብር) በተጨማሪ የተ.እ.ታ 15% = 12,312
ሲጨመር በጠቅላላ 94392.00 ብር (ዘጠና አራት ሺህ ሶስት መቶ ዘጠና ሁለት ብር) ጥያቄ ሲቀርበልት በአንድ ጊዜ
ይከፍላል፡፡
አንቀፅ አራት
አለመግባባትን ስለመፍታት
በዚህ ውል መሰረት በውል ተቀባይና በውል ሰጪ መካከል የሚፈጠሩ አለመግባባቶች ሁሉ አግባብ ባለው የኢትዮጵያ
ሕግ መሰረት ውሳኔ ያገኛል፡፡
አንቀፅ አምስት
ከአቅም በላይ የሆኑ አስገዳጅ ሁኔታዎች
ከአቅም በላይ የሆኑ አስገዳጅ ሁኔታዎች ማለትም የተፈጥሮ አደጋና ጦርነት የመሳሰሉት ቢከሰቱ ውል ሰጪም ሆነ
ውል ተቀባይ የተጠያቂነት ኃላፊነት የለባቸውም፡፡
አንቀፅ ስድስት
የውሉ ተፈፃሚነት
ይህ ውል በሁለቱ ተዋዋይ ወገኖች ከተፈረመበት ቀን ጀምሮ የፀና ይሆናል፡፡
ውል ሰጪ ውል ተቀባይ
ስም ---------------------------------- ስም -------------------------------------
ኃላፊነት ----------------------------- ኃላፊነት --------------------------------
ፊርማ -------------------------------- ፊርማ -----------------------------------
ቀን ----------------------------------- ቀን ---------------------------------------
እማኞች
ስም ፊርማ
1. ---------------------------------------- ------------------------------
2. ---------------------------------------- ------------------------------