You are on page 1of 4

በመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ

እና

በሰቦቃ ሰርቤሳ መካከል የተደረገ

የካቶ ክሬን ጥገና ውል

ህዳር፣ 10/2014

1
የካቶ ክሬን ጥገና ውል
ይህ ውል ከዚህ በኃል “ደንበኛው” ተብሎ በሚጠራው በመከላከያ ኮንስትራክሽን
ኢንተርፕራይዝ አድራሻ ወሎ ሰፈር ብራና ማተሚያ ፊት ለፊት፣
እና
ከዚህ በኃላ “አገልግሎት ሰጪ” ተብሎ በሚጠራው አቶ ሰቦቃ ሰርቤሳ፣ አድራሻ አዲስ
አበባ ወረዳ 03፣ የቤት.ቁጥር 448፣ መካከል በህዳር 10 ቀን 2014 ዓ.ም ተገብቷል።
ደንበኛው የካቶ ክሬን ሞዴል……….መለያ ቁጥር ………. የሆነውን ለማስጠገን
የፈለገ ሲሆን ይህንኑ ሥራም አገልግሎት ሰጪው እንዲያከናውን መርጧል።

አጠቃላይ ሁኔታ፦
አገልግሎት ሰጪ የደንበኛውን ካቶ ክሬን በተገቢው ሁኔታና ሰሪው ፋብሪካ በሚያዘው
መሰረት ጥገናውን በደንበኛው ወርክ ሾፕ ውስጥ ለማከናወን ተስማምቷል።

የአገልግሎት ሰጪ ግዴታዎች፦
1. ጥገናውን የሚያከናውኑ ባለሙያዎችን ከሙሉ የጥገና መሳሪያዎች ጋር ያቀርባል፣
2. በካቶ ክሬን አምራች የተዘጋጀ የጥገና ማንዋል “Service Manual” በመጠቀም፣
ጥገናውን ያከናውናል፣ በማንዋሉ የተሰጡ መስፈርቶችና ልኬቶች “Specification”
መጠበቃቸውን የረጋግጣል፣
3. ጥገናው በሚካሄድበት የደንበኛው ወርክ ሾፕ ውስጥ ያለውን ስነ-ሥርዓትና ደንብ
ሠራተኞች እንዲያከብሩ ያደርጋል።
4. በጥገናው ውቅት የታዩ ጉድለቶች፣ መሰተካከል ያለባቸው የቴክኒክ ሁኔታዎችና
ለወደፊቱ ለክሬኑ ሥራ የሚጠቅሙ ጥቆማዎች ካሉ ለደንበኛው ያሳውቃል።
5. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥሩን ያሳውቃል።

2
የደንበኛው ግዴታዎች
1. የስራ ቦታ ያመቻቻል፣
2. የሚሰሩ የጥገና ስራዎችን ዝርዝር ፈትሾ ያቀርባል፣
3. የመለዋወጫ ዕቃዎችን ያቀርባል፣
4. የጥገና ሥራውን የሚከታተሉ የራሱን ባለሙያዎች ይመድባል፣
5. ሌሎች ለጥገናው የሚያስፈልጉ የጽዳት፣ የማጠቢያ፣ ዕቃ ማንሻ የመሳሰሉትን
ያቀርባል፣
6. ለጥገናው የተመደቡ የአገልግሎት ሰጪ ሠራተኞችን ወደ ወርክሾፕ የሚገቡበትን
ሁኔታ ያመቻቻል፣
7. ጥገናው ተጠናቆ የክሬኑ መስራት ከተረጋገጠ በኃላ ክፍያ ይፈፀማል።

በአገልግሎት ሰጪ የሚሰሩ የጥገና ስራዎች ዝርዝር


1. ካንቢዮ ወርዶ፣ ክሌች ተገጥሞ ካንቢዮ መጫን፣
2. ማስተር ሲሊንደር ሞድፊክ ይደረጋል፣
3. ሃይድሮሊክ ፓንፕ ይቀየራል፣
4. ኮንትሮል ቫልቨ ይቀየራል፣
5. አውቶ ሪገር ፒስተን ሲል ተቀይሮ የገጠማል፣
6. ነዳጅ ሲስተም ይስተካከላል፣
7. ጠቅላላ የሃይድሮሊክ ሲስተም ይስተካከላል፣
የጥገና ዋጋ፦
ለክሬን ጥገና የእጅ ዋጋ ደንበኛው ለአገልግሎት ሰጪ ሁለት ከመቶ ታክስ ቆርጦ ብር
40,000 /አርባ ሺ ብር/ ይከፍላል።
ርክክብ፦
1. አገልግሎት ሰጪ የጥገና ሥራውን በአስር የሥራ ቀናት ውስጥ አከናዉኖ
ለማስረከብ ተስማምቷል።
2. የክሬኑ ጥገና እንደለቀ ደንበኛው አስፈላጊውን ፍተሻ በማካሄድ ጥገናው በትክክል
መከናወኑን በማረጋገጥ ሞተሩን ይረከባል።
3. ደንበኛው የተቀየሩ መለዋወጫዎች አገልገሎት ላይ ያልዋሉ መለዋወጫዎችን
ይረከባል።

3
ዋስትና፦
አገልግሎት ሰጪ ለሠራው ሥራ የአንድ ዓመት ዋስትና ይሰጣል። የሚሰጠው ዋስትና
ከተሠራው ሥራ ጋር ለሚገናኙ የጥገና አገልግሎት ሲሆን በአጠቃቀም ወይም በየወቅቱ
በሚደረጉ የመከለከል ጥገና ማነስ ምክንያት የሚከሰቱ ብልሽቶች በዋስትናው
አይጠቃለሉም።

አለመግባባት፦
በዚህ ውል ምክንያት አለመግባባት ቢፈጠር ሁለቱም ወገኖች በስምምነት ለመፍታት
ይሞክራሉ። መፍታት ካልቻል አንዱ ወገን ጉዳዩን ለሚመለከተው ፍርድ ቤት
ያቀርባል።
አስገዳጅ ሁኔታዎች
ከአቅም በላይ በሆኑ አስገዳጅ ሁኔታዎች ለሚፈጠር ጉዳይ ማናቸውም ወገን ተጠያቂ
አይሆንም።

የዉሉ ተፈፃሚነት፦
ይህ ውል ህዳር 29 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ የፀና ይሆናል።

ስለ ደንበኛው ስለ አገልግሎት ሰጪ
ስም፦ _____________ ስም፦ _______________
ፊርማ፦ _____________ ፊርማ፦ ______________
ቀን፦ _______________ ቀን፦ _______________

ምስክሮች

ስም ፊርማ ቀን
1. __________________ _____________ _________
2. __________________ ______________ _________
3. __________________ _______________ _________
4. __________________ _______________ _________

You might also like