Professional Documents
Culture Documents
የኮንትራቱ ዓይነት፤ በኛንጋቶም ወረዳ በካኩታ ቀበሌ የሚገነባው የእንስሳት ህክምና ክሊኒክ እና በሾንኮራ ቀበሌ የሚገነባው የዓሳ
መጋዘን ግንባታና ተያያዥ ሥራዎች ግንባታ ጠቅላላ የእጅ ዋጋ ብር 180,916.22 (አንድ መቶ ሰማኒያ ሺህ ዘጠኝ መቶ አሥራ
ስድስት ብር ከሀያ ሁለት ሳንቲም ብቻ) ሲሆን፤ ሁሉ ጸንቶ የሚቆየው ከዛሬው ዕለት ጀምሮ ለአንድ ወር ከ 10 ቀን ሲሆን አስፈላጊ
ሆኖ ሲገኝ በሁለቱ ተዋዋዮች ስምምነት የሚራዘም ይሆናል፡፡ይህ ውል በህግ ፊት የጸና ነው፡፡
Y^¨< ¯Ã’ƒ ´`´` SKŸ=Á w³ƒ
1. የእንስሳት ክሊኒክ ግንባታ ጥቅል ___1___
2. የደረቅ ሽንት ቤት ግንባታ ጥቅል ___1___
3. የቆሻሻ ማቃጠያ ግንባታ ጥቅል ___1___
4. የእንስሳት መከተቢያ ጥቅል ___1___
5. የቅጥር ግቢ አጥር ሥራ ጥቅል ___1___
6. የዓሳ ምርት መጋዘን ግንባታ ሥራ ጥቅል ___1___
1. ውል ተቀባዩ የፕሮጀክቱን ግንባታ ሥራ በንድፍ (በዲሮዊንጉ)ና በሥራ ዝርዝሩ በተቀመጠው ስፔስፊኬሽን መሠረት
የመሥራትና ግልጽ ያልሆነ ነገር በሚያጋጥም ጊዜ የሳይት መሐንዲሱንም ሆነ ሌላ የሚመለከተውን አካል የማማከር
ግዴታ አለበት፡፡
2. የሚሠራው ሥራ የእጅ ዋጋን ብቻ የሚያስከፍል ከሆነ ውል ሰጪ አስፈላጊውን የሰው ኃይልና የእጅ መሣሪያዎችን
የማቅረብ ግዴታ የለበትም፡፡
3. የሚሰራው ሥራ የእጅ ዋጋን ብቻ የሚያጠቃልል ከሆነ ውል ተቀባዩ አስፈላጊውን የሰው ሀይል ያቀርባል፡፡
5. በውሉ መሠረት ተሠርተው ለተጠናቀቁ ሥራዎች በትክክል መሠራታቸው በውል ሰጪ ሲረጋገጥ ክፍያ መጠየቅ
ይቻላል፡፡ ሆኖም ግን የክፍያው ጥያቄ ቢንያንስ ከሶስት ቀናት በፊት መታወቅ አለበት፡፡
6. ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት ወይም በበሽታ ካልሆነ በቀር በምንም ዓይነት ሁኔታ ሥራውን ማቋረጥ ወይም
ማዘግየት አይቻልም፡፡
7. ውሉን ለማቋረጥ ውል ተቀባይ ሲፈልግ በቂ ምክንያት በማቅረብ ውሉን ከሚያቋርጥበት አንድ ሣምንት ቀደም ብሎ
ማሣወቅ አለበት፡፡
8. ካለምንም ማስጠንቀቂያ ውሉን ቢያቋርጥ ወይም ሥራውን አቁሞ ከ 3 ቀን በላይ ከጠፋ የሠራቸው ሥራዎች ክፍያ
ሙሉ ለውል ሰጪ ገቢ ይሆናል፡፡
9. ውል ተቀባይ ለሠራው የሥራ መጠን ከሚከፈለው የክፍያ መጠን ለመልም ሥራ ዋስትና 10% በመያዣነት ይዞ
ሥራው ሲጠቃለል ውል ሰጪ ለውል ተቀባይ ይከፍላል፡፡
ማጠቃለያ፡-
ውል ሰጪና ውል ተቀባይ ከዚህ በላይ የተዘረዘሩትን ሃሳቦች በሙሉ አውቀንና አምነንበት ተስማምተን በዛሬው ቀን ተፈራርመናል፡፡
የውል ሰጪ ህጋዊ ተወካይ ስምና ፊርማ የውል ተቀባይ ስምና ፊርማ
ማሳሰቢያ፡- ይህ ውል በ 3 ኮፒ ተዘጋጅቶ አንድ ለውል ተቀባይ አንድ ለአስተዳደርና ፋይናንስ አንድ ለምሕንድስና አገልግሎት ክፍል
ይሰጣል፡፡
ምስክሮች (ስምና ፊርማ)
1. ………………………………………………. ቀን………………………….
2. ……………………………………………….ቀን………………………….
3. ……………………………………………….ቀን………………………….