You are on page 1of 5

የቅጥር ውል

ይህ የቅጥር ውል (ከዚህ በማስከተል “ውል” በመባል የሚጠቀስ) በ ቀን (“ተፈጻሚ የሚሆንበት ቀን”)


ከዚህ በሚከተሉት ወገኖች መካከል ተፈረመ፡

አሰሪ፡ ሰዐዳ ሁላላ ኮሚፒዉተር አክሰሰሪ ንግድ (“ኤኬ ትሬዲንግ ኃ.የተ.የግል ማኅበር) አድራሻ አዲስ
አበባ፣ ኢትዮጵያ

እና

ሠራተኛ አቶ ሙባረክ ናስር (“ሠራተኛ”) የፖስታ አድራሻ፡-

አሠሪው በሥራ መደቡ ሠራተኛውን ለማሰራት የሚፈልግ በመሆኑ እና ሠራተኛውም ለሚከፈለው ደመወዝ ለአሰሪው
አገልግሎት መስጠት የሚፈልግ በመሆኑ ይህ ዉል ይፈፀማል፣

1. ቅጥር፡- ለመልካም እና ዋጋ ላለው ይዘት፣ ሠራተኛው በኩባንያው ለመስራት ፈቃደኛ ሆኗል፡፡


ሠራተኛውም የሚሰራበት የሥራ መደብ መጠሪያ ከዚህ እንደሚከተለው ይሆናል፡-

የኦፕሬሽን ማናጀር (Operation Manager) እና የሰዉ ሀብት እና የፋይናንስ አስተዳደር

2. የሥራ ቦታ፡- የሥራ ቦታው አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ ይሆናል፡፡

3. የሙከራ ጊዜ፡- ውሉ ከተፈረመበት ቀን ጀምሮ ለ 60 የሥራ ቀናት በሙከራ ጊዜ ላይ ይሆናል፡፡

4. ተግባራት እና ኃላፊነቶች

a) ተግባራት፡- ሠራተኛው በዚህ ስምምነት መሠረት ለመሥራት እና ይህንንም ሲያደርግ የአሰሪውን


ጥቅም መሠረት በማድረግ እንደሚሆን ተስማምቷል፤ ይህንንም በሚፈጽም ወቅት ያለውን
ክህሎት፣ የሥራ ልምድ እና ልዩ ችሎታ ሁሉ በሥራ ላይ ማዋል እንዲሁም በሥራ መደቡ
የሚጠየቀውን ሥራ ሁሉ መፈጸም ሊጠበቅበት ይችላል፡፡ የሥራ መደቡ የሚጠይቀውን ተግባራት
እና ኃላፊነቶችም በሚወጣ ጊዜ ሠራተኛው የኩባንያውን ደንቦች ለማክበር ተስማምቷል፡፡
ሠራተኛው ከዚህ በሚከተለው መልኩ ይሰራል፡-

☐በሙሉ ሰዓት ☐ በትርፍ ሰዓት


b) ኃላፊነቶች

 የሁሉም ፕሮጀክት ስራዎችን ያቅዳል፤ከግብ እስኪደርሱ ይከታተላል በመጨረሻም ስራ ላይ

በማዋል ይመራል

 ፕሮጀክቶችን የሚሰሩ ድርጅቶችን ገምግሞ የተሻለ ድርጅት በመምረጥ ዉል እንዲዋዋል

ያደርጋል

 ፕሮጀክቶቹ ዉስጥ የሚሰሩ ሠራተኞች መመሪያ ይሰጣል፤ ይቆጣጠራል፤ ሪፖርት ይቀበላል፤

 የሁሉንም የስራ ክፍል ስራዎችን መመሪያ ይሰጣል፤ ይቆጣጠራል፤ ሪፖርት ይቀበላል

 ከባለሙያተኞች ጋር መልካም ግንኙነት ይፈጥራል

 ከሁሉም ክፍል ሚቀርቡለትን ጥያቄዎችን በተሰጠው ስልጣን መሰረት ይፈጽማ


 ከሁሉም ክፍል የሚመጡና ከሱ ውጪ ለሚሆኑ ጉዳዩች ለዋና ስራ አስኪያጁ ያቀርባል

 አስፈላጊ የሆኑ ውሎችን ከሚመለከተው አካል ጋር በመሆን ይዋዋላል

 ሌሎች በዋና ስራ አስኪጁ የሚሰጡ ተግባራትን ያከናውናል

 ከሁሉም ሠራተኞች ሚቀርቡለትን ጥያቄዎችን በተሰጠው ስልጣን መሰረት ይፈጽማል

 ከሁሉም ሠራተኞች የሚመጡና ከሱ ውጪ ለሚሆኑ ጉዳዩች ለዋና ስራ አስኪያጁ ያቀርባል

 አስፈላጊ የሆኑ ውሎችን ዋና ስራ አስኪያጁን በመወከል አንደ አስፈላጊነቱ ከሚመለከተው

አካል ጋር በመሆን ይዋዋላል

 ለዋና ስራ አስኪያጅ በየሳምንቱ ሪፖርት ያቀርባል

 ባለሙያ በሚያንስበት ዘርፍ ላይ አዘዋውሮ ያሰራል

 አስፈላጊ ክፍያዎችን ወቅቱን ጠብቆ መከፈላቸዉን ይከታተላል ያስፈጽማል

 እንደ አስፈላጊነቱ የሰው ሃይል እንዲሟላ ያደርጋል

 ሌሎች በዋና ስራ አስኪጁ የሚሰጡ ተግባራትን ያከናውናል

5. የሥራ ሰዓታት፡- ሠራተኛው ተከታትለዉ ከሚያሰሩት ፕሮጀክት እና የሰራተኛ ክትትል አንጻር እና


አብዛኛዉ ሰአት ቢሮ ላይቀመጡ የሚችል በመሆኑ እና ካሉበት ሆነዉ በኮምፒዩተር ስራዎችን የሚሰሩ
በመሆኑ በሳምንት አንደ አስፈላጊነቱ ቅዳሜ እና አሁድን ጨምሮ ቢበዛ ለ 20 ሰአታት እንዲሁም
በቀን ደግሞ ቢበዛ ለ 4 ሰዓታት ከ 5፡00 እስከ 10፡00 ይሰራል፤ በዚህም መካከል የ 1 ሰዓታት የምሣ
እረፍት ይኖረዋል፡፡

6. የቅጥር ጊዜ አሠሪው ሠራተኛውን ከዚህ በሚከተለው አኳኋን ለመቅጠር ተስማምቷል፡-

a) በፈቃደኝነት፡- ይህም ማለት ይህ ስምምነት በአሰሪው ወይም በሰራተኛው በማንኛውም ጊዜ


ሊቋረጥ ይችላል፡፡ ውሉ ከተቋረጠ በኋላ አንዱ ወገን ለሌላው ምንም ዓይነት ኃላፊነት
አይኖርበትም፡፡

b) ሠራተኛው በኩል ስለሚሆን የውል መቋረጥ፡- ሠራተኛው የ 30 ቀናት ቅድመ ማስጠንቀቂያ


በመስጠት ይህንን ውል ሊያቋርጥ ይችላል፡፡

c) በአሰሪው በኩል ስለሚሆነ ውል ማቋረጥ፤ አሰሪው ቢያንስ የ 30 ቀናት ቅድመ ማስጠንቀቂያ


በመስጠት ይህንን ስምምነት ሊያቋርጥ ይችላል፡፡

7. የሠራተኛው፣ ክፍያ፣ መብት እና ጥቅማ ጠቅሞች፡- በቅጥር ጊዜ ውስጥ፣ ሠራተኛው በአሰሪው


የተቀመጡትን ጥቅማ ጥቅሞች የማግኘት መብት ይኖረዋል፡፡
 ለሠራተኛው አግባብነት ባላቸው ሕግጋት ወይም ደንቦች መሠረት ተገቢው ቅናሽ
የሚደረግበት ያልተጣራ ደመወዝ 30000 ብር (ሰላሳ ሺህ ብር) በኢትዮጵያ ብር
ይከፍላል፡፡ ሠራተኛው በድርጅቱ ውስጥ በሥራው ከቀጠለ የደመወዝ ጭማሪ
ሊደረግ ይችላል፡፡

 የ 11 ወራት አገልግሎት ከሰጠ በኋላ ሠራተኛው የ 14 የሥራ ቀናት ፈቃድ የማግኘት መብት
አለው፡፡ ክፍያ የሚከፈልበት የዓመት ፈቃድ ቀናት ብዛት ለእያንዳንዱ የአገልግሎት ዓመት
በአንድ ቀን ይጨምራል፡፡

 አንድ ሠራተኛ ይፋዊ የሕክምና ማስረጃ ሲያቀርብ የ 10 ቀናት የሕመም ፈቃድ ከደመወዝ
ጋር የማግኘት መብት ይኖረዋል፡፡

 ሠራተኛው በሥራ አፈጻጸም ምዘና ላይ ተመስርቶ ዓመታዊ የደመወዝ ዕድገት ያገኛል፡፡

 ማንኛውም ከ 6 ወራት በላይ ለሆነ ጊዜ በኩባንያው ያገለገለ ሠራተኛ ኩባንያው


የሚያዘጋጀውን ዓመታዊ ሎቶሪ ጉርሻ የማግኘት መብት ይኖረዋል፡፡

8. የኩባንያው ደንብ እና መመሪያ

 ያለ በቂ ምክንያት እና ሳይፈቀድ ከሥራ መቅረት የተከለከለ ነው፡፡

 ተገቢው ማሳወቂያ ሳይሰጥ ከሥራ መቅረት የተከከለ ነው፡፡

 በምሣ ዕረፍት ጊዜ ካልሆነ በቀር በሥራ ሰዓታት የግል ስልክ ማነጋገር የተከለከለ ነው፡፡

 ማንኛውም ሠራተኛ በኩባንያው ጉዳዮች ላይ ታማኝ እንዲሆን ይጠበቅበታል፡፡

 በሥራ ሰዓታት ማንኛውም ችግር ያጋጠመ እንደሆነ፣ ለጉዳዩ ወዲያውኑ ተገቢውን ትኩረት
በመስጠት በቀጣይ ሰላሳ ደቂቃዎች ጊዜ ውስጥ መፍትሔ መስጠት ይገባል፡፡ ሆኖም ግን
ሁኔታው ለዋናው ሥራ አስኪያጅ መገለጽ አለበት፡፡

 በሥራ ቦታ የግል ንጽሕናን መጠበቅ ግዴታ ነው፡፡

 ማንኛውም ሠራተኛ የኩባንያውን መገልገያዎች በአግባቡ መጠቀም ይኖርበታል፡፡

 ሠራተኞች የኩባንያውን ምሥጢራዊ ጉዳዮች እና ሰነዶች በአገባቡ መያዝ አለበት፡፡

 ማንኛውም ሠራተኛ የኩባንያውን ደንቦች እና መመሪያዎች የጣሰ እንደሆነ ተገቢ የሆነ


እርምጃ ይወሰዳል፣ ሠራተኛውም ማስጠንቀቂያ ደብዳቤ ይሰጠዋል፡፡ ሠራተኛውም
ስህተቱን ያላረመ እንደሆነ፣ የኢት. ብር 1000-2000 ቅጣት ይጣልበታል፡፡ ሁኔታው እየተባባሰ
ከሄደ ደግሞ እንደ መጨረሻ አማራጭ ኩባንያው የሠራተኛውን የቅጥር ውል ያቋርጣል፡፡

 ሠራተኞች የቅጥር ውላቸው በሚያበቃ ጊዜ ለሥራ የተሰጧቸውን መሣሪያዎች እና


መገልገያዎች ተመላሽ ማድረግ አለባቸው፡፡

 ሠራተኞች የኩባንያውን ደንቦች እና መመሪያዎች እንዲያከብሩ ይጠበቅባቸዋል፡፡


 በድርጅቱ ዉስጥ ማንኛዉም የስነምግባር ጥሰት በሚያስተዉሉ ጊዜ ችግሩን ለዋና አለቃ
የማሳወቅ ግዴታ አለበት፡፡ ሆንም ይሄን ያደርጉ መገኘት በድርጅቱ የሚያስይቅ ይሆናል፡፡

9. የሠአሰሪዎች ግዴታ

 አንድ አሰሪ ከሥራ ውሉ ጋር የሥራ መዘርዝር መስጠት አለበት

 ኩባንያው ለሥራ የሚያስፈልጉ ማቴሪያሎች እና መገልገያዎች ማቅረብ አለባቸው፡፡

 ኩባንያው በውሉ ጊዜያት በእያንዳንዱ ወር መጨረሻ ስምምነት የተደረገበትን ደመወዝ


መክፈል አለበት፡፡

 ኩባንያው በቅጥር ጊዜ ማብቂያ ለሠራተኛው የሥራ ልምድ ማስረጃ የመስጠት ግዴታ


አለበት፡፡

 ሠራተኛው ለሥራ ለሚያደርገው ጉዞ የሚያወጣውን ወጪ ሁሉ ኩባንያው መሸፈን አለበት፡፡

10. ውል ስለማቋረጥ፡- ውሉ ከዚህ ከሚከተሉት ሁኔታዎች በአንዱ ይቋረጣል፡-

 ሠራተኛው ለ 10 ወይም ከዚያ በላይ ለሆኑ ጊዜያት ሳያሳውቅ የቀረ እንደሆነ ውሉ


ይቋረጣል፡፡ ነገር ግን ሠራተኛው ለመቅረቱ ምክንያት የሆነውን ወይም የጤና የምሥክር
ወረቀት ማቅረብ የቻለ እንደሆነ ቀናቱ ከዓመታዊ ፈቃድ እና የሕመም ፈቃድ ላይ
እንዲቀነሱ በማድረግ በሚገባ ይታያል፡፡

 ሁለቱ ወገኖች ውሉን ለማቋረጥ የተስማሙ እንደሆነ ውሉ ያቋረጣል፡፡

 የሥራ መደቡ አላስፈላጊ በመሆኑ ምክንያት ኩባንያው ሠራተኞችን የሚቀንስ ከሆነ ውሉ


ይቋረጣል፡፡

 ከሁለቱ ወገኖች ማናቸውም የአንድ ወር ማስጠንቀቂያ የሰጠ እንደሆነ ውሉ ይቋረጣል፡፡

 ሠራተኞች ከዚህ ዓለም በሞት ሲለዩ ውሉ ይቋረጣል፡፡

 ሠራተኞች ሥራቸውን መሥራት ያልቻሉ እንደሆነ፣ ይህ ውል ይቋረጣል፡፡

 ሠራተኞች የሥነ ምግባር ጉድለት ያለባቸው እንደሆነ ይህ ውል ይቋረጣል፡፡

አሠሪ ሠራተኛ

ስም ፡- ስም፡-
ቀን፡- ቀን፡-

ፊርማ፡- ፊርማ፡-

ዋስ፡-

ስም ፡-

ቀን፡-

ፊርማ፡-

You might also like