Professional Documents
Culture Documents
የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ
በእኔ በአሁኑ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ ሰጪ እና በአሁኑ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ ተቀባይ መካከል ሚያዚያ 25 ቀን 2010
ዓ.ም የትራንሳይክል ሽያጭ ውል ስምምነት የፈጸምን መሆናችን ይታወቃል፡፡ በመሆኑም ንብረትነቱ የአሁኑ የጽሁፍ
ማስጠንቀቂያ ሰጪ የሆነውን ትራንሳይክል ባጃጅ የሰሌዳ ቁጥር 1 - 11947 ኦሮ የሆነውን ለአሁኗ የጽሁፍ
ማስጠንቀቂያ ተቀባይ በብር 90,000 (ዘጠና ሺህ ) ሸጬልዎት ከሽያጩም ገንዘብ ውስጥ በእለቱ የውል ሰነድ
ደረሰኝነት አማካኝነት ብር 80000 (ሰማኒያ ሺህ) ተቀብዬ ቀሪውን ብር 10000 (አስር ሺህ) የባጃጁን ንብረትነት ስም
በእርስዎ በአሁኗ የጽሁፍ ተቀባይዋ እስከ ሰኔ 25 ቀን 2010 ዓ.ም ድረስ ሲዛወር ልቀበልና ላዛውርልዎት መስማማታችን
ይታወቃል፡፡
ይን እንጂ እስከ ዛሬ ቀን ድረስ በስልክና በአካልም ያቀረብኩልዎት ጥሪ አክብረው ስም ለማዛወርና ቀሪውን ብር 10000
(አስር ሺህ) ሊከፍሉኝ ፍቃደኛ ሆነው አልተገኙም፡፡ ስለዚህ ከዛሬ ይህ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ ከደረስዎት ቀን አንስቶ
በሚታሰብ 8 ቀናት ውስጥ ቀርበው ስም እንዲያዛውሩና የሚፈለግብዎትንም ብር 10000 (አስር ሺህ) የማይከፍሉኝ
ከሆነ ጉዳዩን ለሚመለከተው ፍርድ ቤት አቅርቤ የዳኝነት ወጪ ፣ የጠበቃና የቀላጤ ልዩ ልዩ ወጪዎችን ጭምር
በማስከፈል መብቴን በህግ አግባብ ለማስፈፀም የምገደድ መሆኔን አበክሬ እየገለፅኩ ይህንን የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ
የሰጠሁ መሆኔን አሳውቃለሁ፡፡
_________________________