You are on page 1of 3

ቀን፡ 30/12/2014 ዓ.

የመኪና ኪራይ ውል ስምምነት

አከራይ - ሀቢብ መሀመድ ከድር /ዜግነት ኢትዮጵያዊ

አድራሻ - አ.አ ክ/ከተማ አዲስ ወረዳ - 01 የቤት.ቁ - 293 ስልክ.ቁ 0911425784

ተከራይ - ሎፍቲሀብ ትሬንዲግ ኃ/የተ/የግ/ማ

አድራሻ - አ.አ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ወረዳ 02 የቤት.ቁ አዲስ ስልክ.ቁ 0920761200

አንቀጽ 1

ጠቅላላ

እኔ አከራይ አቶ ሀቢብ መሀመድ ከድር በስሜ ተመዝግቦ የሚገኝ የ2005 ሞዴል ሰሌዳ ቁጥሩ AA-02-
C08862 እና የቻሲስ ቁጥሩ NZE120-3090700 የሆነ መኪና ለ 1ወር ማለትም 30/12/2014 ዓ.ም እስከ
30/01/2015 ዓ.ም ድረስ ተከራይ ድርጅት አንዲጠቀሙበት አከራይቻለው፡፡

አንቀጽ

ኪራይ አከፋፈሉን

1. ተከራይ ለተከራየው መኪና ለአከራይ በቀን ብር 1,100 (አንድ ሽህ አንድ መቶ ብር ከ) በጠቅላላው


በወር 33,000 (ሰላሳ ሶስት ሽህ ብር) ለመክፈል ተስማምተዋል፡፡ የስራ ቀን እሁድ ጨምሮ ስለሆነ
ያልሰራበት ቀን እንደማይታሰብ እናሳውቃለን፡፡
2. ቅድመ ክፍያ ብር 33,000 (ሰላሳ ሽህ ብር) መውሰዳቸው እናሳውቃለን፡፡

የአከራይ ግዴታ
1. መኪናውን ከላይ በተጠቀሰው ቀን ለመንገድ አገልግሎት ብቁ አድርጎ ያስረክባል፡፡
2. የመኪናው ሹፌር ጤናማና የወቅቱ ግብር የተገበረበት መንጃ ፍቃድ ያለው እንዲሁም የተከራዩን
መመሪያ ተከትሎ የሚሰራ መሆን አለበት፡፡
3. የኪራይ መኪናው ከተከራይ ቁጥጥር ውጭ በሆነ ምክንያት ቢበላሽ ባፋጣኝ ተሰርቶ ለአገልግሎት
እንዲበቃ ያደርጋል፡፡
4. የኪራይ መኪና በዚህ ስምምነት ከተመለከተው የኪራይ ማብቂያ ቀን በፊት እንዲመለስለት ቢፈልግ
ቢያንስ የሁለት ሳምንት ግዜ ማስጠንቀቂያ ለተከራይ መስጠት ይኖርበታል፡፡
5. አከራይ ተከራይ በተስማሙበት ቦታ መኪናው ደህንነት በተጠበቀበት መልኩ ያሳድሩታል፡፡
6. መኪናው በወርሃዊ ጥገና ወይም በድንገተኛ ብልሽት ምክንያት በገራዥ ውስጥ የሚቆም ቢሆን
ጥገናውን አጠናቆ እስኪመጣ ድረስ ለሚቆይባቸው ቀናት ኪራይ አይከፈለውም፡፡ (በሌላ ተመሳሳይ
መኪና ይተካሉ)፡፡
7. አከራይ ሙሉ በሙሉ የጉዳት ኢንሹራንስ፤ ለሶስተኛ ወገን ኢንሹራንስ አንዲሁም/ማንኛውንም
ተያያዥ የሆኑ የመድን ሽፋኖች በውል ሰጪ/በአከራይ/የሚሸፈን ይሆናል፡፡

የተከራይ ግዴታ

1. የተከራየውን መኪና ደህንነት መጠበቅና በጥንቃቄ መያዝ አለበት፡፡


2. የተከራየውን መኪና ለሶስተኛ ወገን በኪራይ ወይም በሌላ ሁኔታ አሳልፎ አይሰጥም፡፡
3. የኪራይ መኪናውን በዚህ ስምምነት ከተመለከተው ቀን በፊት ለመመለስ ቢፈልግ ቢያንስ የሁለት
ሳምንት ግዜ ማስጠንቀቂያ ለአከራይ መስጠት ይኖርበታል፡፡
4. ተከራይ መኪናው የሚያድርበትን ቦታ ማዘጋጀት እና መጠበቅ፡፡
5. የነዳጅ ወጪን ተከራይ ይከፍላል፡፡

ይህንን ስምምነት ለመቀየር ወይም ለማሻሻል የሚቻለው ሁለት ተወያይ ወገኖች በጽሁፍ ሲስማሙ ብቻ ነው።
ይህም ውል በፍ/ብ/ሕ/ቁ.1731/2005/1679 በሚያዘው መሰረት በህግ ፊት የጸና ነው፡፡

አከራይ ተከራይ
ስም፦አቶ ሀቢብ መሀመድ ከድር ስም ____________________

ፊርማ ___________ ፊርማ ___________

የምስክሮች ስምና ፊርማ

1. __________________
2. __________________
3. __________________

You might also like