You are on page 1of 3

የቤት ኪራይ ውል ስምምነት

ይህ የቤት ኪራይ ውል ስምምነት የተደረገው በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በደብረ ዘይት ከተማ በወረዳ 01
ቀበሌ……..በአኢትዮጵያ ካቶሊካውያን ምእመናን ቤተክርስቲያን ስም ተመዝግቦ የሚገኘው በም/ቤቱ ተወካይ በአቶ
ኃይሌ ሸዋና (ከአሁን በኋላ አከራይ ተብሎ ይጠራል) በ……………………………………….(ከአሁን በኋላ ተከራይ
ተብሎ ይጠራል) መካከል ተደረገ ነው፡፡

አንቀፅ 1፡-የኪራይ መጠን

የቦታው ስፋት 3000 ሜ.ካ. ሲሆን ቤቱ በ…….ሜ.ካ. ላይ አርፏል፡፡በመሆኑም አከራይ ቤቱን በየወሩ በ
ብር……………………………….(…………………………………………………………….) ቫትን
ጨምሮ ለተከራይ ለማከራይት ተስማምቷል፡፡ተከራይ ደግሞ ከላይ በተጠቀሰው የብር መጠንና ቫት በየወሩ
ለመክፈል ተስማምቷል፡፡

አንቀፅ 2፡-የአከራይ ግዴታዎች

2.1. ቤቱ እጅርናም ሆነ ከተከራይ ጋር በማይገናኝ ነገር አደጋ ቢደርስበት

ኃላፊነቱ የአከራይ ነው፤በደረሰው ችግርምክንያት አከራይ ቤቱን መጠገን እንዲችል ተከራይ

ሁኔታዎችን ያመቻቻል፡፡

2.2 አከራይ ወይም ወኪሉ ከ 48 ሰዓታት በፊት በስልክ ወይም በሌላ በተመቸው መንገድ አሳውቆ

ማየትና መጐብኘት ይችላል፡፡

2.3. አከራይ ዓመታዊ የመሬትና የህንፃ ግብር ይከፍላል፡፡

አንቀፅ 3፡- የተከራይ ግዴታዎች

3.1. ተከራይ ቤቱን ሲለቅ ቤቱን፣ግቢውንና አጥሩን ሲከራይ በነበረበት ሁኔታ ማስረከብ አለበት፡፡

3.2. ተከራይ በገባው ውል መሠረት የቤቱን በሮች፣መስኮቶች፣ሽንት ቤቶች፣የውሃ ቧንቧዎች ግቢውንና

አጥሩን በአግባቡ መጠቀም አለበት፡፡

3.3. ተከራይ በገባው ውል መሠረት በቤቱም ሆነ በግቢው ላይ ያለ አከራይ ዕውቅና ምንም ዓይነት

ለውጥ ማድረግ አይችልም፡፡

3.4. ተከራይ የሚሰራው ሥራ የሚገልፅ ምልክት ከአከራይ ጋር በመነጋገር በውጭ በር ላይ

መለጠፍ ይችላል፡፡

3.5. ተከራይ የጥበቃ ሠራተኞች ደመወዝ ፣የውሃና መብራት ፍጆታዎችና ተዛማጅነት ያላቸውን

ወጪዎች ይሸፍናል፡፡
3.6. ተከራይ ቤቱንና ግቢውን ያለአከራይ የጽሑፍ ስምምነት ሶስተኛ ወገን ማስተላፍም ሆነ

ማከራየት አይችልም፡፡

3.7. ተከራይ በማንኛውም ጊዜ ከኪራይ ውሉ ላይ በተቀመጠው መሠረት ስምምነቱን ሲያፈርስ

ቤቱን፣ግቢውንና አጥሩን በነበረው ሁኔታ ማስረከብ ይኖርበታል፤የራሱ የሁኑ ዕቃዎች

ካሉም በሙሉ ይዞ ማውጣት ይኖርበታል፡፡

3.8. ተከራይ የቤቱን ኪራይ በተስማማው ውል መሠረት ወቅቱን ጠብቆ መክፈል አለበት፡፡

አንቀፅ 4፡-የውል ስምምነቱ የሚያበቃበትና የሚታደስበት ጊዜ፡-

አከራይና ተከራይ ከ…………ቀን 2012 ዓም..አስከ……………ቀን 2013 ዓ.ም. እንዲቆይ

ተስማምተዋል፡፡የውል ጊዜው ሲያልቅ አዲስ የውል ስምምነት ያደርጋሉ፡፡

አንቀፅ 5፡አጠቃላይ፡

5.1. ተከራይ በማንኛውም ጊዜ አካባቢውን የሚረብሽ ሥራ መሥራት የለበትም፡፡

5.2. ተከራይ የተከራየውን ቤትና ግቢ በጥንቃቄ መያዝ ይጠበቅበታል፤በራሱ ስህተት/ግድ የለሽነት

ለተፈጠሩ አደጋዎች/ስህተቶች ለአከራዩ ወዲያውኑ ማሳወቅ ይኖርበታል፡፡

5.3. ተከራይም ሆነ አከራይ አስፈላጊ ባልሆኑ ነገሮች/ጉዳዮች መጨቃጨቅ አይኖርባቸውም፡፡

5.6. ምናልባት ችግሮች ቢከሰቱ ወደ ሕግ ከመሄድ በፊት በውይይት እንዲፈቱ ጥረት ይደረጋል፤ይህ

ሳይሳካ ቢቀር ሁለቱም በመረጡት አስታራቂ ይዳኛሉ፤ በዚህ የማይስማሙ ከሆነ ተጎዳሁ

የሚለው አካል ወደ ፍርድ ቤት የመሄድ መብቱ የተጠበቀ ይሆናል፡፡

አንቀፅ 6፡- ውሉ የሚፈርስበት ሁኔታ

6.1. በማንኛውም ጊዜ ከአቅም በላይ በሆኑ ሁኔታዎች ሲያጋጥሙ ውሉ እንዲቋረጥ ከአከራይም ሆነ

ከተከራይ የ……ወር/ወራት የቅድሚያ ማስጠንቀቂያ ከተሰጠ ውሉ ይቋረጣል፤ ውሉ

እንዲቋረጥ የጠየቀው አከራይ ከሆነ ከተከራይ በቅድሚያ የተቀበለውን ተከራይ

ያልተጠቀመበትን ገንዘብ ይመልሳል፡፡ጥያቄው የቀረበው ከተከራይ ከሆነ ግን የከፈለው

ገንዘብ አይመለስለትም፡፡

6.2. በሕግ ሥራው እንዲቆም/እንዲቋረጥ ሁኔታዎች ከተፈጠሩ ውሉ ይቋረጣል፡፡

6.3 ተከራይ ኪራይ መክፈሉን ከ 30 (ሠላሳ) ቀናት በላይ የሚያዘገይ ከሆነ ውሉ ይቋረጣል፡፡


6.4. ከዚህ ውል ስምምነት ውጪ አከራይ ወይም ተከራይ የሕግ ጥሰት ፈፅሞ ቢገኝ

የ………..ወር/ወራት ማስጠንቀቂ ይሰጣል፤ የውል ሥምምነቱም ይፈርሳል፡፡

አንቀፅ 7፡-የክፍያ ጊዜ

7.1. በውል ስምምነቱ መሠረት ተከራይ በቅድሚያ የ………ወር/ወራት ኪራይ ብር ………………..

(………………………………………………) ይከፍላል፡፡

7.2. ተከራይ በቅድሚያ የከፈለው ኪራይ ሲያልቅ በየወሩ መጀመሪያ ባሉት አምስት ቀናት ውስጥ

በንብ ኢንተርናሽናል ባንክ አ.ማ. በም/ቤቱ የቁጠባ ሒሳብ--ECS-National Council of Laity,

SPS 346 ገቢ ለማድረግ ተስማምቷል፤ የገቢ ደረሰኙ ለም/ቤቱ ዋና ፀሐፊ ለአቶ ኃሌ ሸዋ በግንባር ወይም
አመቺ በሆነ መንገድ ይሰጣል፡፡

ይህ ውል በተዋዋዮች መካከል በፍ/ሕ/ቁ/2945 እና በተከታታዮቹ አንቀፆች መሠረት በሕግ ፊት የፀና ሲሆን


ይህንን ውል ያፈረሰ ውሉን ለጠበቀ ወገን ብር………………መቀጫ ከፍሎ ውሉ የፀና ይሆናል፡፡

አንቀፅ 8፡- አድራሻ

1. የም/ቤቱ ተወካይ/አከራይ፡-

ስም……………………..አድራሻ………………..ስልክ…………………………ፊርማ…………

2. ተከራይ/ሕጋዊ የተከራይ ተወካይ፡-

ስም ………………….አድራሻ…………………ስልክ…………………………ፊርማ………

እኛ ስማችን ቀጥሎ የተዘረዘረው ምስክሮች አከራይና ተከራይ የውል ስምምነቱን ሲፈፅሙ

ማየታችንን በፊርማችን አናረጋግጣለን፡፡

ምስክሮች፡-

1.ስም………………………..አድራሻ…………………… ስልክ………………………. ፊርማ…………

2.ስም…………………………አድራሻ……………………..ስልክ……………………………ፊርማ……

3.ስም…………………………አድራሻ…………………….ስልክ…………………………….ፊርማ…….

You might also like