You are on page 1of 3

ቀን

የቤት ኪራይ ስምምነት ዉል


አከራይ፡- ወ/ሮ
አድራሻ፡-
ተከራይ፡-
አድራሻ፡-

የውሉ ዝርዝር ሁኔታ


እኛ አከራይና ተከራይ እየተባልን ስማችን እና አድራሻችን በዉሉ ላይ የተገለፀው ተዋዋዮች በፍ/ህግ/ቁጥር
1731፣2005 2945 (1) መሰረት ከዚህ የሚከተለውን የቤት ኪራይ ውል ተዋዉለናል፡፡
አንቀጽ አንድ
የውሉ ዓላማ
1. የኪራዩ ልክ በየወሩ 4500( አራት ሺህ አምስት መቶ ) ብር ሆኖ በአጠቃላይ የኪራዩ ዘመን ለሶት
ዓመት ከህዳር 1/03/2005 እስከ ህዳር 1/03/2008 ብቻ ነዉ፡፡
2. የኪራዩ አከፋፈል ዉሉን በፈፀምንበት ቀን የአንድ ዓመት የኪራይ ዋጋ 54,000 (ሀምሳ አራት ሺህ)
በቅድሚያ ተከፍሏል፡፡
3. ተከራይ ይህን ቤት ለህክምና ስራ አገልግሎት ብቻ የሚጠቀም ሲሆን ለተጨማሪ አገልግሎት
ከተፈለገ ቅድሚያ አከራይን በጹሑፍ ማስፈቀድ አለበት፡፡
4. ለዉሉ ምክንያት የሆነዉ ቤት በሻሸመኔ ከተማ በከፍተኛ 02 ቀበሌ 04 የቤት ቁጥር 423 የሆነዉ ቤት
ነዉ፡፡
አንቀጽ ሁለት
የኪራዩ ልክ እና የኪራዩ ዘመን
1. የኪራዩ ልክ በየወሩ 4500.00 ( አራት ሺህ አምስት መቶ ) ብር ሆኖ አጠቃላይ የኪራዩ ዘመን ለሶስት
ዓመት በዚሁ የኪራይ መጠን ብቻ ይቀጥላል፡፡
2. የኪራዩ አከፋፈል ዉሉን በፈፀምንበት ቀን የአንድ ዓመት የኪራይ ዋጋ 54,000 (ሀምሳ አራት ሺህ) ብር
በቅድሚያ ተከፍሏል፡፡
አንቀጽ ሶስት
የመብራት፣ የውሃ የስልክ በተመለከተ
ተከራይ የተጠቀመበትን የውሃና መብራት የስልክ ክፍያ በቢሉ መሰረት ይከፍላል፡፡
አንቀጽ አራት
ስለተከራይ ግዴታዎችና ስለ ውሉ ጊዜ
1. በፍ/ብሔር ሕግ ቁጥር 2968 መሰረት አከራይ ለተከራይ ለ3 ዓመት ቤቱን አከራይቷል፡፡
2. ተከራይ የተከራየዉን ቤት የኪራይ ዉሉ ዘመን ባለቀበት ጊዜ ቅድመ ማስጠንቀቂያ በመስጠት
ቤቱን በነበረበት ሁኔታ ለአከራይ ያስረክባል፡፡
3. ተከራይ የተከራየዉን ቤት በሚለቅበት ሰዓት አሁን ቤቱ ባለበት ሁኔታ ለአከራይ የማስረከብ ግዴታ
አለበት፡፡
4. ተከራይ የተከራየውን ቤት በማናቸውም ሁኔታ ለ3ተኛ ወገን ማስተላለፍ አይችልም፡፡
አንቀጽ አምስት
ስለ ውል ፈቃደኝት
ይህ ውል በተዋዋዮች ፈቃደኝነትና ስምምነት የተፈፀመ በመሆኑ ውሉ ሕጋዊ ነው፡፡
አንቀጽ ስድስት
እንደ ውሉ ስላለመፈፀም
እኛ አከራይና ተከራይ እንደዉሉ ባንፈፅም ወይም ለመፈፀም ፈቃደኛ ባንሆን በሁለቱ ወገኖች በሚመረጥ
ሽማግሌዎች ጉዳያቸዉን በእርቅ እንዲታይ ሽማግሌዎችን የመምረጥ መብት አላቸዉ፡፡ የሽማግሌዎቹም ዉሳኔ
በሁለቱም ወገኖች ላይ አስገዳጅ ይሆናል፡፡
አንቀጽ ሰባት
ስለ መቀጫ/ኪሳራ/
ይህን ውል ያፈረሰ ወይም ለማፍረስ የሞከረ በፍ/ህግ ቁጥር 1889 መሰረት ውል ያፈረሰው ወገን ውል
ላከበረው ወገን 50,000 ብር (ሃምሳ ሺህ)ብር መቀጫ ወይም ኪሳራ ከፍሎ ውሉ የፀና ይሆናል፡፡
አንቀፅ ስምንት
ስለ ምስክሮች
በዉሉ ላይ የተገኙት ምስክሮች
1. አቶ
2. ወ/ሪት
3. አቶ. ስንሆን ዉሉ በተዋዋዮች ወገኞች ሙሉ ፍቃደኝነት ሲፈፀም አይተን
ፈርመናል፡፡
አንቀጽ ዘጠኝ
ዉሉ በተዋዋይ ወገኖች እጅ ስለመሆኑ
ይህ ውል በአከራይና በተከራይ እጅ ይሆናል፡፡ እኛ አከራይና ተከራይ ምስክሮች ይህን ውል አንብበን ተነቦልን
በዉሉ ላይ ፈርናል፡፡
የአከራይ ፊርማ የተከራይ ፊርማ

የምስክሮች ፊርማ
1
2
3

You might also like