You are on page 1of 3

ቀን፡________________________________

የስራ ቅጥር ስምምነት ውል

ውል ሰጪ፡-

አድራሻ፡- አ.አ ክ/ከተማ ወረዳ የቤት ቁጥር

ውል ተቀባይ፡-

አድራሻ፡- አ.አ ክ/ከተማ ወረዳ የቤት ቁጥር

ውል ሰጪ እና ውል ተቀባይ በፍ/ብ/ሕ/ቁ 1731/2005 መሰረት ከዚህ የሚከተለውን የስራ ቅጥር ስምምነት ውል ተዋውለናል፡፡

አንቀጽ አንድ

የስራ አይነትና ቦታ

1,አሰሪ_____________________________የሚገኘው የስራ ቦታ ላይ__________________________________የስራ ዘርፍ ውል


ተቀባይ________________________________ የሆኑትን በሰራተኛነት ለመቅጠር በመስማማታቸው የተደረገ የስራ ውል ነው።

አንቀጽ ሁለት

የደሞዝ መጠን

1, እኔ አሰሪ ሰራተኛን በ__________________________________ ሰራተኛነት እንዲሰሩ በወር ብር. (____________ )


ቀጥሬያቸውለው፡፡ ሰራተኛውም ለተቀጠሩበት የ_____________ ስራ ስራቸውን ባላቸው ሙያ በሚገባ የሚወጡ እና የሚሰሩ መሆኑን
ተስማምተን ቀጥሬአቸዋለሁ ፡፡

2, እኔም ዉል ተቀባይ. ______________________________ስራ ሙያ የተቀጠርኩ ሲሆን በወር ብር / ብር/ለከፍሉኝ ተስማምቼ ተቀጥሬአለሁ።


እኔም ዉል ተቀባይ ለተቀጠርኩበት_____________________ስራ ስራዉን ባለኝ ሙያ በሚገባ የምወጣ እና የምሰራ መሆኑን ተስማምቼ
ተቀጥሬአለሁ፡፡

አንቀጽ ሶስት

የአከፋፈሉ ሁኔታ

1, በ_________________ስራ ዘርፍ ተሰማርተው ሲሰሩ ውል ተቀባይ ደመወዝ የሚቀበሉት በኢትዮጵያ ወር አቆጣጠር ወር በገባ
በመጀመሪያው ቀን ተከፋይ ይሆናሉ።

2, በዚህ የስራ ውል ላይ የተደረሰው የአጠቃላይ ደመወዝ መጠን ላይ ተፈጻሚነት የሚኖራቸው የግብር ግዴታዎች በአሰሪ ተከፋይ
ይሆናሉ

አንቀጽ አራት

የቅጥር ጊዜ

1, የዚህ ውል የቅጥር ጊዜ ከስምምነቱ ቀን ጀምሮ የሚቆይ ይሆናል። በአመት መጨረሻም በወገኖቹ ስምምነት የሚታደስ ይሆናል።

2, የሥራው ጊዜ ውስጥ የመጀመሪያው ሦስት ወር ለሠራተኛው የሙከራ ጊዜ ይሆናል።

3, በሙከራ ጊዜ ውስጥ አሰሪው የሰራተኛው የሙያ ብቃትና ችሎታ ለተመደበበት የስራ መደብ የማይመጥን ሆኖ ካገኘው ያለማስጠንቀቂያ እና
የአገልግሎት ካሳ ክፍያ መክፈል ሳይጠብቅበት የስራ ውሉን ማቋረጥ ይችላል።
አንቀጽ አምስት

የአሰሪ ግዴታዎች

1, ለስራ አስፈላጊ የሆኑ ቁሳቁሶችን እና መሳሪያዎችን በድርጅቱ ወጪ ማቅረብ

2, በየወሩ ለሰራተኛው የሚከፈል ደመወዝ በማዘጋጀት መክፈል

3, በአሰሪና ሰራተኛው አዋጅ ላይ የሰራተኛ እረፍት ጊዜ ማለትም አመታዊ ፈቃድ የመጀመሪያ አመቱን ሲያጠናቅቅ 16 የእረፍት ቀናት ይኖሩታል።
እንዲሁም እንደአስፈላጊነቱ የህመም እረፍት፤ ልዩ ልዩ ሁኔታዎች እና የወሊድ ፈቃድ የመሳሰሉት በህግ ባላቸው አግባብነት መሰረት የማክበር ግዴታ
አለበት።

አንቀጽ ስድስት

የሰራተኛ ግዴታዎች

1, ሰራተኛው የስራ መግቢያና መውጫ ሰዓትአክብሮ የመስራት፤ ከአሰሪው ፈቃድ ካልተሰጠው በቀር ምንጊዜም በስራ ቦታ ላይ መገኘት;

2, ከአሰሪው በሚሰጠው ትእዛዝ መሰረት በድርጅቱ ቅርንጫፎች እየተዘዋወረ መስራት፤

3, የሚሰራባቸውን ንብረቶች እና ለሰራተኛው የተሰጡ መገልገያዎችን በአግባቡና በጥንቃቄ በመያዝ እና ብልሽት ወይም ጉድለት ሲያጋጥም ወዲያውኑ
ለአሰሪው ወይም ለቅርብ አለቃው የማሳወቅ

4, የበላይ አመራር ሳይፈቅድለት የድርጅት ንብረት ወይም ገንዘብ ያለመውሰድ፤ በድርጅቱ ንብረትና ገንዘብ ሆን ብሎም ሆነ በቸልተኝነት ጉዳት
ከማድረስ መቆጠብ፤ እንዲሁም የድርጅት ሚስጢር የመጠበቅ ግዴታ አለበት

5, ከድርጅቱ ጋር ተወዳዳሪ ከሆኑ ድርጅቶች ጋር በሚኖረው የስራ ግንኙነት፤ ድርጅቱን በማይጎዳ መልኩ መከናወን የሚኖርበት ሲሆን፤ የ ድርጅቱን
ጥቅም ከሚያሳጡ ወይም ጉዳት ከሚያስከትሉ ግንኙነቶች መቆጠብ ይኖርበታል

6, በዚህ ዝርዝር ውስጥ ያልተካተቱሙያው የሚጠይቃቸውን መልካም ተግባራትን ማከናወን፤ የበላይ አመራር ትዕዛዝን መቀበል እና ሌሎች በአሰሪና
ሰራተኛ አዋጁ ላይ የተጠቀሱ ግዴታዎችን ማክበር ይኖርበታል።

አንቀጽ ሰባት

የውሉ አካል የሆኑ ሰነዶች

ድርጅቱ የሚያወጣቸውን ህጎች የአሰራር መመሪያዎች፤ ማንዋሎችና ሌሎች ሰራተኛው ፈርሞ የሚቀበላቸውንሰነዶች የሚያስቀምጡን መመሪያ
በመተላለፍ ለሚፈጽመው ጥፋት ወይም ጉዳት ሀላፊነት ይወስዳል።

አንቀጽ ስምንት

የስራ ውል ስለሚቋረጥባቸው ሁኔታዎች

ይህ የስራ ውል በሚከተሉት ሁኔታዎች ይቋረጣል።

1, በተዋዋዮቹ የጋራ የጽሁፍ ስምምነት

2, ሰራተኛው የአንድ ወር ቅድመ ማስጠንቀቂያ ለድርጅቱ በመስጠት

3, ሰራተኛው በዚህ ውል አንቀጽ አምስት እና በአሰሪ እና ሰራተኛ ጉዳይ አዋጅ የተቀመጡ ግዴታዎች በሚተላለፍ ጊዜ አሰሪው ያለ ማስጠንቀቂያ
ሰራተኛውን ማሰናበት ይችላል።

4, የኩባንያው የስራ ሁኔታ በሚቀንስበት/ በሚቀዘቅዝበት ጊዜ የአንድ ወር ቅድመ ማስጠንቀቂያ ለሰራተኛው በመስጠት ሊቋረጥ ይችላል።

ይህንን የቅጥር ስምምነት ውል በፍ/ብ/ሕ/ቁ 1889/1890 በፍ/ብ/ሕ/ቁ 1731/2005 መሰረት በህግ ፊት የጸና ነው፡፡

ተዋዋይ ወገኖች
1, ውል ሰጪ/ አሰሪ
አድራሻ

2, ውል ተቀባይ/ ሰራተኛ
አድራሻ

ይህንን ውል ስንዋዋል የነበሩ እማኞች

1. አቶ. /ዜግነት ኢትዮጵያዊ/

አድራሻ፡- አድራሻ፡- አ.አ ክ/ከተማ ወረዳ የቤት ቁጥር

2. አቶ. /ዜግነት ኢትዮጵያዊ/

አድራሻ፡- አድራሻ፡- አ.አ ክ/ከተማ ወረዳ የቤት ቁጥር

You might also like