Professional Documents
Culture Documents
2222
2222
የመተዳደሪያ ደንብ
ይህ መተዳደሪያ በሰነዱ ግርጌ በተመለከተው ዕለት በፀደቀው የማህበሩ መመስረቻ ጽሁፍ የማይነጣጠል አካል
በመሆን ያገለግላል፡፡
ማህበሩ በኢትዮጵያ ንግድ ሕግ በተመለከተ የህብረት የሽርክና ዓይነት የተደረገ ውል ሲሆን በማህበሩ
መመስረቻ ጹሁፍ በዚህ መተዳደሪያ ደንብ እንዲሁም በንግድ ሕግና አግባብነት ባላቸው የሕግ ድንጋጌዎች
ይተዳደራል፡፡
አንቀጽ አንድ
አንቀጽ ሁለት
የባለመዋጮ ድርሻ
ማህበሩ የባለመዋጮ ዝርዝር የያዘ መዝገብ በዋናው መ/ቤት እንዲገኝ ያደርጋል መዝገቡም በውስጡ
የሚከተሉትን ይይዛል፡፡
ሀ/ የአባላት ስም፣
ለ/የማህበርተኞች መዋጮ፣
ሐ/የመዋጮ ስም መተላለፊየ፣
መ/ ከዚህ በላይ በዝርዝር የተመለከቱት ላይ የተደረገ ማናቸውም ማሻሻያ ወይም ለውጥ፣ ማንኛውም
ማህበርተኛ የህብረት ሽርክና ማህበር መዝገብ ያለክፍያ መመልከት ይችላል፡፡
አንቀጽ ሶስት
መዋጮ ስለማስተላለፍ
1. መዋጮ በማህበርተኞች መካከል ያለምንም ገደብ ሊተላለፍ ይችላል፣ ሆኖም የማህበሩን ድርሻዎች
ለማስተላለፍ ማህበርተኞቹ ሁሉ እንዲስማሙበት ያስፈልጋል፣
2. ከማህበሩ ካፒታል በላይ ያለው ማህበርተኞች ካልፈቀዱ ወይም ሁሉም አባላት ካልወሰኑ በስተቀር
ማንኛውም ማህበርተኛ በስሙ የተመዘገበውን የመዋጮ ድርሻ ለ 3 ኛ ወገን ሊያስተላለፍ አይችልም፣
3. አንድ ማህበርተኛ በሞት ሲለይ በድርሻው የተመዘገበውን ሀብት በህጋዊ ወራሾቹ ወይም እሱ
ለመረጠው 3 ኛ ወገን ሊተላለፍ ይችላል፣ ስራውን ለመቀበል የተለየ ስምምነት ያስፈልጋል፣
4. የማህበርተኛው ወራሾች ድርሻቸውን ለቀሩት የማህበሩ አባል ቅድሚያ በመስጠት ለመሸጥ፣ በስጦታ
ለማስተላለፍ ወይም በአባልነት ለመቀጠል ይችላል፣
5. የድርሻው መተላለፍ በጹሁፍ ሆኖ በአባላቱ መካከል በሚፈፀም ስምምነት እና በኢትዮጵያ ንግድ ሕግ
መሠረት የሚከናወን ይሆናል፡፡
አንቀጽ አራት
የማህበሩ ስራ አስኪያጅ የሚከተሉት ስልጣን ያለው ሲሆን ተግባሩም ከዚህ በታች የተመለከቱት እንዲሆን
ማህበርተኞች ተስማምተዋል፡፡
አንቀጽ አምስት
የስብሰባ ሥነ ሥርዓት
1. የማህበሩ መደበኛ ስብሰባ ቢያንስ በዓመት አንድ ጊዜ በማህበሩ ዋና መስሪያ ቤት ይደረጋል፣
2. የማህበሩ አባላት በስብሰባ እንዲገኙ በየአድራሻቸው ጥሪ ይደረግላቸዋል፣
3. እያንዳንዱ አባል በማናቸውም የማህበሩ ስብሰባዎች ላይ መሳተፍ ይችላል፣
4. በማህበሩ የሚደረጉ ማንኛውም ስብሰባዎች የሚካሄዱት የማህበሩ አባላት ከግማሽ በላይ (50+1%)
ሲገኙ ይሆናል፣
5. አባላት በማህበሩ ውስጥ ባላቸው የመዋጮ መጠን ድምጽ የመስጠት መብት አላቸው፣
6. አባላት በማህበሩ ስብሰባ ላይ በመገኘት ወይም የውሳኔ ሀሳባቸውን በጽሁፍ መስጠት ይችላሉ፣
7. ከማህበሩ ዋና ገንዘብ ግማሽ በላይ ባላቸው ማህበርተኞሀት የድምጽ ብልጫ ያገኘ ውሳኔ የማህበሩ
ውሳኔ ይሆናል፣
8. ጉባኤው ያካሄዳቸው ውይይቶች ያሳለፋቸው ውሳኔዎች ሁሉ በቃለ ጉባኤ ተይዘው በዕለቱ በተገኙት
አባላት ከተፈረሙ በኋላ በቃ ጉባኤ መያዣ መዝገብ እንዲቀመጡ ይደረጋል፡፡
አንቀጽ ስድስት
ስለ ማህበር ሂሳቦችና በጀት ዓመት
1. ማህበሩ የተሟላ የሂሳብ አያያዝ ስርዓት እና ተገቢው የሂሳብ መዛግብት ይኖሩታል፣
2. የማህበሩ የበጀት ዓመት ከሐምሌ 1 ቀን እስከ ሰኔ 30 ቀን ድረስ ሲሆን የመጀመሪያ በጀመት ዓመት
ማህበሩ በተቋቋመበት ቀን ጀምሮ ይሆናል፡፡
አንቀጽ ሰባት
ስለመጠባበቂያ ገንዘብ
ከማህበሩ የተጣራ ትርፍ ላይ 20 ፐርሰንት ተቀናሽ እያደረገ የካፒታሉን መዋጮ 10 በመቶ (10%)
እስከሚደርስ ድረስ በመጠባበቂያ ሂሳብ ይያዛል፣ እንደአስፈላጊነቱም በስምምነት መወሰን ይቻላል፡፡
አንቀጽ ስምንት
ተቆጣጣሪ ኦዲተር
ኦዲተር ከዚህ የሚከተሉትን ተግባሮች ያከናውናል፡፡
1. ኦዲተሩ በንግድ ህግና በዚህ መተዳደሪያ ደንብ የተገለፁት ስልጣንና ኃላፊነት ይኖሩታል፣
2. የማህበሩን መዛግብትና ሰነዶች መመርመር፣
3. የማህበሩን ንብረት የሂሳብ መመሠኛ ትርፍና ኪሳራ የሚያሳይ ሰነድ መኖሩን ያረጋግጣል፣
4. ስራ አስኪያጅ የሚያቀርበው ሪፖርት ትክክል መሆኑን ያረጋግጣል፣
5. ለስራው አስፈላጊ የሆኑ መዛግብት ሰነዶች ቃለ ጉባኤ ሌላም መረጃ ያያል፣ይመረምራል፣
6. በዓመታዊ በማናቸውም ጠቅላላ ጉባኤ ስብሰባ መገኘት፣
7. በሕግ የተገለፁትን ሌሎች ግዴታዎች መፈፀም፡፡
አንቀጽ ዘጠኝ
የማህበሩ መፍረስና ሂሳብ ማጣራት
1. ማህበሩ በንግድ ሕግ በተደነገገው ወይም በማህበሩ ጠቅላላ ጉባኤ በአንድ ድምጽ ከተስማሙ ሊፈርስ
ይችላል፡፡ ሆኖም በአንድ ማህበርተኛ አቤቱታ ማህበሩ እንዲፈርስ በሕግ በተጠየቀ ጊዜ በስሙ
የተመዘገበው ድርሻ ባለው የደብተር ዋና /Book Value/ መሠረት ለሌላው አባል በግዢ እንዲተላለፍ
ይደረጋል
2. ድርሻዎች ሁሉ በአንድ ማህበርተኛ እጅ የገቡ እንደሆነ ይፈርሳል
3. ማህበሩ የሚፈርስ ሲሆን ጠቅላላ ጉባኤው ሂሳብ የሚጣራበትን ሁኔታ ይወስናል አንድ ወይም ከአንድ
የበለጡ ሂሳብ አጣሪዎች ይሾማሉ ስልጣናቸውንም ይወስናሉ፡፡
አንቀጽ አስር
ስለትርፍ አከፋፈል
የዓመቱ የተጣራ ትርፍ በተረጋገጡ ተከፋዮችና በመተዳደሪያ ደንብ መሠት ለመጠባበቂየ የሚያስፈልገውን
ገንዘብ ተወስኖ ከተቀነሰ በኋላ ቀሪው ገንዘብ በዓመቱ መጨረሻ ላይ ለእያንዳንዱ አባል ባለው ድርሻ መጠን
ይከፋፈላል፡፡
አንቀጽ አስራ አንድ
ግልግል
ማህበርተኞች በመካከላቸው ወይም ከማህበሩ ጋር የሚፈጠሩ አለመግባባቶች በስምምነት ይጨረሳሉ፡፡
ለመጨረስ ካልቻሉ በቅድሚያ ጉዳያቸውን በግልግል ዳኝነት /እንዲጨርሱ ይደረጋል፡፡ የግልግል ዳኞች ብዛት 3
ሆነው ሰብሳቢ በ 2 ቱ ወገኖች ስምምነት ይመረጣል፡፡ ካልተስማሙ በፍ/ቤት ወይም በኢትዮጵያ ንግድ ምክር
ቤት ይመረጣሉ፡፡
መመስረቻ ጹሁፍ
እኛ ስማችን፣ ዜግነታችንና አድራሻችን ከዚህ በታች የተጠቀሰው በ 1952 ዓ.ም በወጣው የኢትዮጵያ ንግድ
ሕግ ዋቅጅራ ሙሉጌታ እና ጓደኞቻቸው የኮንስትራክሽን ስራ ህብረት ሽርክና ማህበር በዚህ የመመስረቻ
ጹሁፍ መተዳደሪያ ደንብ መሠረት ተስማምተን አቋቁመናል፡፡
አንቀጽ አንድ
የአባላት ሙሉ ስም ፣ ዜግነት እና አድራሻ
አንቀጽ ሁለት
የማህበሩ ስም
ዋቅጅራ ሙሉጊታ እና ጓደኞቻቸው የኮንስትራክሽን ስራ ህብረት ሽርክና ማህበር
አንቀጽ ሶስት
የማህበሩ አድራሻ
የማህበሩ አድራሻ ከተማ አዲስ አበባ ክ/ከተማ ን/ስ/ላ/ክ/ከተማ ወረዳ 09 የቤት ቁጥር 113/1884/ ነው ፡፡
ከማህበሩ አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶችን በሀገር ውስጥም ሆነ ከሀገር ውጭ ሊያቋቁም
ይችላል፡፡
አንቀጽ አራት
የማህበሩ ዓላማዎች
ማህበሩ የሚከተሉት ዓላማዎች ይኖሩታል፡-
ለህብረተሰቡ ጥራት ያለው የኮንስትራክሽን ስራ መስራት፣
ማንኛውንም የኮንስትራክሽን ስራ በታቀደለት በጀት እና ጊዜ አጠናቆ ማስረከብ፣
ማንኛውንም ፕሮጀክት በተመሳሳይ ተነሳሽነትና ቆራጥነት ሰርቶ የደንበኞችን እርካታ በጠበቀ መልኩ
ማጠናቀቅ፣
የአካባቢውን፣ የማህበረሰቡንና የሰራተኞቹን ጤና እና ምቾች በጠበቀ መልኩ ስራን ሰርቶ ማጠናቀቅ፣
ጥራታቸውን የጠበቁ የኮንስትራክሽን ምርትና ውጤቶችን ማቅረብ፣
ማህበሩን ወደ ላቀ ደረጃ ማሸጋገር፡፡
አንቀጽ አምስት
ካፒታል
የማህበሩ ካፒታል ብር 125,000 / አንድ መቶ ሃያ አምስት ሺህ ብር / ሲሆን በእያንዳንዳቸው የማህበሩ አባላት
ብር 25,000 / ሃያ አምስት ሺህ ብር/ ተከፍሏል፡፡
አንቀጽ ስድስት
ስለትርፍና ኪሳራ አከፋፈል
አስፈላጊ የመንግስት ግብር ከተከፈለ በኋላ የተጣራውን ትርፍ ወይም ኪሳራ አባላት ባዋጡት ድርሻ መሠረት
ይከፋፈላል፡፡
አንቀጽ ሰባት
የማህበሩ አስተዳደር
ማህበሩ በአንድ ወይም በብዙዎች ማህበርተኞች በሆኑ ወይም ባልሆኑ ሥራ አስኪያጅ ይተዳደራል፡፡ በዚህም
መሠረት አቶ ዋቅጅራ በርሲሳ ጨፌ የማህበሩ ሥራ አስኪያጅ፣ አቶ ሙሉጌታ በዛ ዋቅጅራ የማህበሩ ምክትል
ሥራ አስኪያጅ እና አቶ ብሩክ ንጉሴ ጋዲሳ የማህበሩ ሒሳብ ሹም ሆነው እንዲሰሩ ተሹመዋል፡፡
አንቀጽ ስምንት
የስራ አስኪያጅ ሥልጣንና ተግባር
1. በማህበሩ ስም ማንኛውንም ህጋዊ ሥራዎች ያከናውናል፣የንግድ ስራውን ይመራል፣ ያስተዳድራል፣
2. በማህበሩ ስም በሚደረጉ ስምምነቶች ላይ ይፈርማል፣
3. የንግድ ሥራዎችን ይቆጣጠራል ያስተዳድራል ፣
4. የማህበሩን ሠራተኞች ይቀጥራል ያሰናብታል፣ ደሞዝ ይከፍላል፣
5. በማህበሩ ስም ከማህበሩ ሂሳብ ሹም ጋር በመሆን የባንክ ሂሳብ ይከፍታል፣ ገንዘብ ወጪ ገቢ ያደርጋል
ያንቀሳቅሳል፣
6. ማህበሩ ሲከስም ሆነ ሲከሰስ ይከራከራል ካልሆነ የህግ ጠበቃ ይወክላል፣
7. እንደ አስፈላጊነቱ ከማህበሩ አባላት ሥልጣኑን ለ 3 ኛ ወገን ይወክላል፣
8. በንግድ ህግ እና በማህበሩ ደንብ መሠረት ይፈፀማል ያስፈፅማል፣
9. የቤት ኪራይ ውል በማህበሩ ስም ይዋዋላል፣ የኪራይ ውል ያፈርሳል፡፡
አንቀጽ ዘጠኝ
የማህበሩ ዕድሜ
ማህበሩ የተቋቋመው ላልተወሰነ ጊዜ ነው፡፡ ይህ መመስረቻ ጽሁፍ በመስራች አባላት ቃይቶና ተነቦ በአዲስ
አበባ ከተማ ተፈረመ፡፡
አንቀፅ አስር
ኦዲተር
ከአባላት የተመረጠ 1 ኦዲተር ይኖረዋል፡፡