You are on page 1of 12

ኩል ኢንዱስትሪያል ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር

Kul INDUSTRIAL PRIVATE LIMITED COMPANY


የመመስረቻ ፅሑፍ

አንቀፅ አንድ

ምስረታ

በሰነዱ ግርጌ ፊርማችንን ባሰፈርነው መካከል በኢትዮጲያ ንግድ ህግ በዚህ የመመስረቻ ፅሁፍና ተያይዞ በሚገኘው
የመተዳደሪያ ደንብ ስምምነቶች የሚገዛና አላማው ከዚህ በታች በአንቀፅ 4 ስር የተጠቀሱትን የንግድ ስራ
ተግባራት ማከናወን የሆነ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ለመመስረት ስምምነት ተደርጓል፡፡

አንቀፅ 2

የአባላቱ ስም ፣ ዜግነትና አድራሻ

ተ. ስም ዜግነት አድራሻ
ቁ ከተማ ክ/ከተማ ወረዳ የቤ.ቁ የመታወቂያ
ቁጥር
1 አቶ ነቢዩ ክንፈ ክብረት ኢትዮጲያዊ አዳማ ደምበላ ኤሬቻ 268 Ep4571982
ቀበሌ
2 አቶ ዘውዱ ንጋቴ ታረቀኝ ኢትጵያዊ

3 ኢትዮጲያዊ
አንቀፅ 3

የማህበሩ ስምና ዋና መ/ቤት

1. የማህበሩ ስም Ÿ<M ኢንዱስትሪያል ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበርነው፤


2. አባላቱ ወደፊት በሌሎች የኢትዮጲያ ከተሞችም ሆነ ከኢትዮጲያ ውጪ ቅርንጫፍ ለመክፈት
መብታችው እንደተጠበቀ ሆኖ የተመዘገበው የማህበሩ ዋና መስሪያ ቤት በ አዲስ አበባ ከተማ ፣ ልደታ
ክ/ከተማ ፣ ወረዳ 4 የቤ.ቁ አዲስ ውስጥ ነው፤

አንቀፅ አራት

የማህበሩ የንግድ ስራ ዓላማዎች

1. የኮምፒውተር ሃርድዌር እና ሶፍትዌር እንዲሁም መለዋወጫዎችን ማስመጣትና መሸጥ፤


2. የኮምፒውተር መገጣጠሚያ ፋብሪካ መመስረት እና ማስተዳደር፤
3. የጅምላና ችርቻሮ ንግድ ስራዎችን መስራት፤
4. ማናቸውም የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን ማቅረብና መሸጥ፤
5. ማናቸውንም ዓይነት የማስታወቂያ እና ህትመት ስራዎችን እንዲሁም የመልቲ ሚድያ/ብሮድካስ አገልግሎት/ ዘርፍ ላይ
መሰማራት፤
6. የማዕድን ፍለጋ ፣ቁፋሮ እና ማምረት ስራ መስራት፤
7. የተለያዩ አልባሳትን መግዛትና መሸጥ እንዲሁም መፈብረክ፤
8. የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ዘርፍ ውስጥ መሰማራት፤
9. የተለያዩ ሃገር ዓቀፍ እና ዓለም አቀፍ የገቢ ማሰባሰቢያ ቴሌቶን ዝግጅቶችን ማከናወን፤
10. የተለያዩ ዘመናዊ የህትመት መሳሪያዎችንና ዲጂታል የቴክኖሎጂ ማሽኖችን ማስመጣት እና በጅምላ እና
በችርቻሮ ማከፋፈል/መሸጥ፤
11. ማናቸውንም ዓይነት የጅምላና የኮሚሽን ሽያጭ ስራዎችን መስራት፤
12. በሶፍትዌርና ሃርድዌር ፈጠራ እና አገልግሎት ዘርፍ መሰማራት፤
13. በአስጎብኝነት እና በመኪና ኪራይ አገልግሎት ዘርፍ መሰማራት፤
14. የአስመጭነትና ላኪነት ስራ ዘርፍ፤
15. አዳዲስና ያገለገሉ ተሸከርካሪዎችን ወደሃገር ውስጥ በማስገባት መሸጥ፤
16. የሪል ስቴት ግንባታ ሰራ ላይ መሰማራት፤
17. የቤትና የቢሮ ዕቃዎች መፈብረክ፤
18. የእንጨት፤የብረት፤እና የሲሚንቶ፤ የጂፕሰም ወጤቶችንና ኢንዱስትሪዎችን ማቋቋምና መሸጥ፤
19. ሌሎች ተያያዥነት ያላቸውን የንግድ ስራዎች መስራት፤

አንቀፅ 5

የማህበሩ ካፒታል

የማህበሩ ካፒታል ብር 5,000,000.00 (አምስት ሚሊዬን ብር) ሲሆን ይኄው ገንዘብ በጠቅላላ በጥሬ ገንዘብ
የተከፈለ መሆኑን በአንድነት እና በነጠላ አረጋግጠዋል፡፡ ካፒታሉ እያንዳንዳቸው ብር 1,000 (አንድ ሺህ) ዋጋ
ያላቸው 5000 (አምስት ሺህ) አክሲዮኖች ተከፍሏል፡፡

በመስራች አባላት የተያዘው የአክሲዮን መጠን የሚከተለው ነው፡፡

ተ.ቁ ስም የአክሲዮን የአንዱ በጥሬ ገንዘብ ጠቅላላ መዋጮ


ብዛት ዋጋ
1. አቶ ነቢዩ ክንፈ ክብረት
1
2. አቶ ዘውዱ ንጋቴ ታረቀኝ

3.

ጠቅላላ ድምር

አንቀፅ 6

የባለ አክሲዮኖች ኃላፊነት

ባለ አክሲዮኖች ለማህበሩ ግዴታዎች ኃላፊ የሚሆኑበት በማህበሩ ውስጥ ባላቸው የአክሲዮን ድርሻ መጠን
የተወሰነ ነው፡፡

አንቀፅ 7

የትርፋና ኪሳራ ክፍፍል


አባላቱ በተለየ ሁኔታ ካልተስማሙ በስተቀር ከጠቅላላው ዓመታዊ ትርፍ ህጋዊ የመጠባበቂያ ገንዘብ እና ሌሎች
ጠቅላላ ወጪዎች ከተቀነሰ በኃላ ቀሪው በአባላቱ መካከል እንደአክሲዮን ይዞታቸው ይከፋፈላል፡፡ ኪሳራም ካለ
በተመሳሳይ ሁኔታ በአባላቱ መካከል ይከፋፈላል፡፡ ሆኖም በማንኛውም ሁኔታ አባላቱ በማህበሩ ውስጥ ካለው
የአክሲዮን ካፒታል በላይ ተጠያቂ ሊሆኑ አይችሉም፡፡

አንቀፅ 8

የስራ አመራር

1.የማህበሩ አስተዳደር አካላት የሚከተሉት ናቸው

ሀ. የባለ አክሲዮኖች ጠቅላላ ጉባኤ

ለ. ዋና ሥራ አስኪያጅ

ሐ. ዋና ኦዲተር

2. ማህበሩ በዋና ስራ አስኪያጅ እንደ አስፈላጊነቱ የሚሾሙ የዘርፍ ሥራ አስኪያጅ ሊኖሩት ይችላል፡፡

3. የማህበሩ ስራ አመራር ከአባለቱ መካከል ወይም ከውጭ በአባላቱ በሚመረጥ የስልጣን ዘመኑ ላልተወሰነ ጊዜ
አንድ ዋና ስራ አስኪያጅ ይመራል፡፡ በዚህም መሰረት አቶ ነቢዩ ክንፈ ክብረት የመኖሪያ አድራሻቸው ኦሮሚያ
ክልል አዳማ ከተማ ኢሬቻ ቀበሌ የቤት ቁጥር 268 የሆኑ ከማህበሩ አባላት ውስጥ የማህበሩ ዋና ስራ አስኪያጅ ሆነው
ተሹመዋል፡፡

አንቀፅ 9

የዋና ስራ አስኪያጅ ስልጣንና ተግባር

1. የዘርፍ ሥራ አስኪያጆችን ይሾማል ፣ ይሽራል፣ ተግባራቸውን ዘርዝሮ ይሰጣል፣ ይቆጣጠራል፤


2. ጠቅላላው ጉባኤ ሲፈቅድ በአስፈላጊው ቦታ ሁሉ ማህበሩን በመወከል ይፈርማል፤
3. ለማህበሩ ቴክኒካዊና አስተዳደራዊ ተግባሮች ኃላፊ ነው፤
4. የጠቅላላ ጉባዔ ውሳኔዎችን ሥራ ላይ ያውላል፤
5. ጠቅላላው ጉባኤ ሲፈቅድ ለማህበሩ የሚከፈል ገንዘብ መቀበል፣ የማህበሩን ዕዳዎች መክፈል፣ ማናቸውም የሀዋላ
ወረቀት፤ የተስፋ ሰነድ፣ የባንክ ሰነድ ማዘጋጀትና በጀርባ ላይ መፈረም፣ ማደስና መክፈል እንዲሁም ማናቸውንም
ሰነዶች ማፅደቅና ከጀርባው መፈረም፤
6. በባንክ ወይም በባንኮች በድርጅቱ ስም ሂሳብ ወይም ሂሳቦች ይከፍታል፣ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ በጥቅሉ እስከ ብር
50,000.00 (ሀምሳ ሺ ብር) ገንዘብ ቼክ በመፈረም ጭምር በተናጠል ፊርማ ለድርጅቱ ዓላማ ብቻ ለሚውል ወጪ
ያንቀሳቅሳል፣ ከብር 50,001.00 (ሀምሳ ሺ አንድ ብር) እስከ ብር 100,000.00 (አንድ መቶ ሺ ብር) የገንዘብ መጠን
የያዙ ቼኮችን እንደአስፈላጊነቱ ጠቅላላ ጉባዔው ከመረጠው ሰው ጋር አሊያም ከፋይናንስ ክፍል ኃላፊው ጋር
በጣምራ በመፈረም የማህበሩን ሂሳብ ያንቀሳቅሳል፣ የማህበሩ ከፍተኛ ባለአክሲዮን ለማህበሩ ዋና ስራ አስኪያጅ እና
ለፋይናንስ ኃላፊው የማህበሩን ሂሳብ አስመልክቶ የተሰጡ ስልጣኖች ጨምሮ የማህበሩን የባንክ ሂሳብ ያለገደብ
የማንቀሳቀስ፤የማህበሩን የሚንቀሳቀስና የማይንቀሳቀስ ንብረት በዋስትና የማስያዝ፤ የካፒታል ዕቃ ዱቤ ግዢ
የመፈፀም፤ ኪራይ ውል የመፈፀምና መፈራረም፤ ከማንኛውም ባንክና ሌሎች የገንዘብ ተቋማት ገንዘብ የመበደር፤
የማህበሩ የሚንቀሳቀስና የማይንቀሳቀስ ንብረት የመሸጥ፤ የመለወጥ፤ ለሶስተኛ ወገን ስም የማዞር፤ ካፒታል
የማሳደግ እንዲሁም በማናቸውም መንግስታዊ እና መንግስታዊ ባልሆኑ ተቋማት ዘንድ ቀርበው ጉዳዮችን
ተከታትለው የማስፈፀም ስልጣን ይኖራቸዋል፤
7. የማህበሩን ወኪል ወይም ሠራተኛ ይቀጥራል፣ ያሰናብታል፣
8. የማህበሩ ጠቅላላ ጉባኤ ሲፈቅድ የሠራተኞችን እና የወኪሎችን ደመወዝ ፣ ጉርሻ እና ሌሎች ተያያዥነት
ያላቸውን ክፍያዎች ይወስናል፤
9. የማህበሩ ጠቅላላ ጉባኤ በሚሰጠው ውሳኔ መሰረት የማህበሩን የሚንቀሳቀስና የማይንቀሳቀስ ንብረት የመሸጥ ፤
የመለወጥ ፤ የማከራየት እንዲሁም እነዚህን ንብረቶች በዋስትና በማስያዝ ከባንክ እና ከሌሎች የብድር ተቋማት
በማህበሩ ስም መበደር ይችላል፤
10. የማህበሩ ጠቅላላ ጉባኤ በሚሰጠው ውሳኔ መሰረት ለማህበሩ ንግድ በመልካም ሁኔታ መካሄድ የሚጠቅሙ ግዢዎች
ሽያጭና የእነዚህም ማዘዣዎች ይወስናል፤
11. የማህበሩ ጠቅላላ ጉባኤ በሚሰጠው ውሳኔ መሰረት ከማህበሩ ንግድ ጋር የተያያዙ ማናቸውንም የንግድ ልውውጥ
በተመለከተ ከሶስተኛ ወገኖች ጋር ውል ይዋዋላል፤
12. በማናቸውም ፍርድ ቤት ማህበሩ ከሳሽ ፣ ተከሳሽ ወይም ጣልቃ ገብ በሚሆንበት ጉዳይ ሁሉ ማህበሩን በመወከል
አስፈላጊውን ይፈፅማል አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ለሶስተኛ ወገን ውክልና ይሰጣል እንደአስፈለጋኒቱ ይሽራል፤
13. ማህበርተኞች ሊቀበሉትና ሊያፀድቁት እንዲችሉ የሂሳብ ወጪና የገቢ መዝገብ በደንብ እንዲያዝ አስፈላጊውን
እርምጃ ይወስዳል፡፡ የማህበሩ ዓላማ ግቡን እንዲመታ አስፈላጊ መስሎ በታየው ጊዜ ከላይ ከተገለፁት ተግባራት
መሃል ማናቸውንም በሌላ ሶስተኛ ሰው እንዲፈፀም በማህበሩ ስም ውክልና ይሰጣል ይሽራል፤
14. ማህበሩን በተገቢው ሁኔታ ለማስተዳደር አላማዎቹንና ተግባሩን ለማስፈፀም ኃላፊ ይሆናል፤
15. የማህበሩን አጠቃላይ የሥራ እንቅስቃሴ ያደራጃል፣ ያስተባብራል፣ አቅጣጫ የማሳየት የመምራትና የመቆጣጠር
ስራ ይሰራል፤
16. በማህበሩ ስም ከሌሎች 3 ኛ ወገኖች ጋር ማናቸውንም ህጋዊ ውሎች መደራደርና መፈረም፤ ማህበሩ ያደረጋቸውን
ውሎችና ስምምነቶች የመፈፀም እና የማስፈፀም፤
17. በማህበሩ መመስረቻ ፅሁፍ ፣ መተዳደሪያ ደንብ ፣ በየጊዜው ጉባኤው በሚያስተላልፋቸው ውሳኔዎች እና በህግ በተሰጠው
ሥልጣን ተግባሩን ጠቅላላ ጉባሄው ሲፈቅድ በከፊልም ሆነ በጠቅላላው ለሌላ 3 ኛ ወገን በውክልና ማስተላለፍ
ይችላል፤ እንዲሁም የጉሙሩክ አስተላላፊና የህግ ባለሙያዎችንና ጠበቆችን በማህበሩ ሥም ለመወከል ሥልጣን
ይሰጣል ይሽራል፤
18. የማህበሩን መመሪያዎች ፣ የውስጥ ደንቦች በማርቀቅ ለጠቅላላ ጉባኤ በማሳወቅ እና እንዲጸድቅ በማድረግ ተግባራዊ
ማድረግ ይኖርበታል፤
19. ዋና ስራ አስኪያጁ በህግ ፣ በማህበሩ መተዳደሪያ ደንብ ፣ በተለያየ ጊዜ ስልጣናቸውን በሚመለከት በሚወጡ
የማሻሻያ ውሳኔዎች እና በሥራ አስኪያጁ በሚወሰኑ እንዲሁም በዝርዝር መመሪያ ከተሰጣቸው የስልጣን ክልል
ውጪ በስልጣናቸው ለሚፈፅሙት ጥፋት በንግድ ህጉ አንቀፅ 530 መሰረት ለማህበሩ እና ለ 3 ኛ ወገኖች ኃላፊነት
አለባቸው፤

አንቀፅ 10
የማህበሩ የስራ ዘመን

አባላቱ በተለየ ሁኔታ ለመወሰን ያለው መብት እንደተጠበቀ ሆኖ ማህበሩ የተቋቋመው ላልተወሰነ ጊዜ ነው፡፡

አዲስ አበባ ሚያዚያ 5 ቀን 2012 ዓ.ም

የመስራች አባላት ስም ፊርማ

1. አቶ ነቢዩ ክንፈ ክብረት ----------------------


2. አቶ ዘውዱ ንጋቴ ታረቀኝ ---------------------
3. ----------------------

ኩል ኢንዱስትሪያል ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር


Kul INDUSTRIAL PRIVATE LIMITED COMPANY
መተዳደሪያ ደንብ

አንቀፅ 1

ጠቅላላ

1. የስም ዝርዝራችን፤ አድራሻችንና ዜግነታችን ከዚህ ጋር በተያያዘው የመመስረቻ ፅሁፍ ውስጥ የተመለከተው
የመስራች አባላት እፎይታ ኢንዱስትሪያል ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበርይህንን መተዳደሪያ ደንብ አፅድቀናል፤
2. የቃሉ አግባብ ሌላ ትርጉም የሚሰጠው ካልሆነ በቀር በዚህ መተዳደሪያ ደንብ የተጠቀሱ ቃላት እና ሀረጎች
በኢትዮጵያ የንግድ ህግ የተሰጣቸውን ትርጓሜ ይኖራቸዋል፤
3. በዚህ መተዳደሪያ ደንብ እና በማህበሩ መመስረቻ ፅሁፍ መካከል አለመጣጣም ከተፈጠረ በመመስረቻ ፅሁፉ
የተመለከተው ተፈፃሚ ይሆናል፤
4. በዚህ መተዳደሪያ ደንብ ባልተሸፈኑ ጉዳዮች ላይ የኢትዮጵያ የንግድ ህግ እና አግባብነት ያላቸው ሌሎች ህጎች
ተፈፃሚ ይሆናሉ፤
5. ይህ መተዳደሪያ ደንብ የማህበሩ መመስረቻ ፅሁፍ አካል ተደርጎ የሚቆጠር እና የማህበራቱን ስራዎች ለመምራት
በማህበርተኞች የተዘጋጀ ነው፡፡
አንቀፅ 2

ስለ የማህበሩ ዋና ገንዘብ (ካፒታል) እና ስለማህበሩ አክሲዮን ድርሻ መዝገብ

1. የማህበሩ ዋና ገንዘብ ብር 5,000,000.00 (አምስት ሚሊዬን ብር) ነው፤


2. ይኸው ገንዘብ እያንዳንዳቸው ብር 1,000 (አንድ ሺ ብር) በሚያወጡ 5000/አምስት ሺህ/ አክሲዮኖች
ተከፋፍሎ በአባላቱ በጥሬ ገንዘብ ሙሉ በሙሉ ተከፍሏል፤
3. ማህበሩ የማህበርተኞቹን ስምና አድራሻ፤ የማህበርተኞቹን መዋጮ ድርሻ፤ የአክሲዮን ዝውውር ሁኔታና
የሚደረጉ የደንብ ማሻሻያ የሚመዘገብበት መዝገብ ይይዛል፤
4. በሂሳብ ዓመት መጨረሻ የማህበርተኞቹን ዝርዝርና የመዋጮአቸውን መጠን የያዘ ዝርዝር ለንግድ ቢሮ ይልካል፤
5. የማህበሩ አባላት የማህበሩን ካፒታል አንዴ ወይም ከዚህ በላይ ለሆነ ጊዜ ማሳደግ ይችላል፤
6. የእያንዳንዱ ማህበርተኛ ኃላፊነት በያዘው አክሲዮን ዋጋ መጠን ብቻ ይሆናል፤
7. የማህበሩ አክሲዮኖች የማይከፋፈሉ ናቸው፤
አንቀፅ 3
ስለ አክስዮን እና አክሲዮኖቹን ስለማስተላለፍ
1. የማህበሩ አክሲዮኖች ስም የተመዘገቡ ተራ እና አንድ አይነት ዋጋ ያላቸው ይሆናሉ፤
2. የማህበሩ አክሲዮኖች በማህበርተኞች መካከል ያለ ገደብ ሊተላለፍ ይችላሉ፡፡ ይሁን እንጂ ለ 3 ኛ ወገን
ሊተላለፍ የሚችለው በማህርተኞች ጠቅላላ ጉባኤ 3/4 ኛ አብላጫ ድምፅ ውሳኔ መሰረት ይሆናል፤
3. አክሲዮኖች ከማህበሩ ውጪ ላለ ሰው ማስተላለፍ የሚቻለው በቅድሚያ ቢያንስ ከማህበሩ ካፒታል 75% (ሰባ
አምስት በመቶ) የያዙትን አባል ስምምነት ማግኝት ሲቻል ነው፡፡ የአባላቱ ስምምነት ካልተገኘና አክሲዮን
ማስተላለፍ የፈለገ አባል በሀሳቡ ከፀና ለሽያጭ የቀረበውን አክሲዮን የመግዛት ቅድሚያ የሚሰጠው ከአባላቱ
መካከል ቀደምት ለሆነው ይሆናል፤
4. ከአንድ በላይ ቀደምትነት ያላቸው ሰዎች አክሲዮን ለመግዛት ያላቸውን የቅድሚያ መብት ለመጠቀም የፈለጉ
እንደሆነ ከመካከላቸው በጨረታ አሸናፊ ለሚሆነው አባል ይሸጣል ይህም የአክሲዮን ማስተላለፍ በፅሁፍ መሆን
ያለበት ሲሆን በመዝገብ ካልተመዘገበ ዋጋ አይኖረውም፤
5. ማህበሩ በዋና ፅህፈት ቤቱ የማህበርተኞችን ስም እና የአክሲዮን ብዛት እንዲሁም የአክሲዮን ዝውውሮችን እና
ሌሎች ለውጦችን መመዝገቢያ የአክሲዮን መዝገብ ማዘጋጀት አለበት፡፡በፅሁፍ ካልተደረገ እና በማህበሩ
የአክሲዮን መዝገብ ያልተመዘገቡ የአክሲዮን ዝርዝሮች በማህበሩም ሆነ በ 3 ኛ ወገኖች ላይ መቃወሚያ ሊሆኑ
አይችሉም፤
6. እያንዳንዱ አክሲዮን ከተጣራ ዓመታዊ ትርፍ ላይ ትርፍ የማግኘት መብት እንዲሁም የማህበሩን ኪሳራ
የመጋራት ግዴታ ያስከትላል፤
7. ማንኛውም ማህበርተኛ በማህበሩ ስብሰባዎች የመገኘት እና ባለው አክሲዮን ልክ ድምፅ የመስጠት የመምረጥ
እና የመመረጥ እንዲሁም የማህበሩን ውሳኔዎች የመቃወም እና የማህበሩን ሰነዶች የመመልከት እና የማግኘት
መብት አለው፤
8. ማህበሩ በእያንዳንዱ ማህበርተኛ ስም የአክሲዮን ብዛት እንዲሁም በማህበሩ ካፒታል በመዋጮነት ያስገባውን
የገንዘብ መጠን የሚያሳይ በማህበሩ ማህተም የተረጋገጠ እና በዋናው ስራ አስኪያጅ የተፈረመ የአክሲዮን
የምስክር ወረቀት ለማህበርተኞች ይሰጣል፡፡
አንቀፅ 4
ካፒታል ስለመጨመር
ማህበርተኞች ሙሉ ለሙሉ እስከተሟሉ ድረስ የማህበሩ ካፒታል መቼውም ቢሆን መጨመር ይችላል፡፡ ይህም
የሚሆነው አክሲዮኖችን በመጨመርና አባላት ባላቸው ድርሻ አክሲዮን መጠን ተመጣጣኝ አክሲዮኖችን እንዲገዛ
በማድረግ ወይም አክሲዮኖችን ወደ ውጪ በመሸጥ ወይም በዓመቱ የሚገኝውን ትርፍ ወደ ካፒታል በማዞር ሊሆን
ይችላል፡፡ ይሁን እንጂ አንድ አባል ያለፍላጎቱ አክሲዮን እንዲገዛ አይገደድም፡፡
አንቀፅ 5
የማህበሩ የሥራ አመራር
1. የማህበሩ ጠቅላላ ጉባዔ በማናቸውም ጉዳይ የወሳኝነት ስልጣን ያለው የማህበሩ የበላይ አካል ነው፤
2. የማህበሩ ሥራ አስኪያጅ በመመስረቻ ፅሁፉ እና በንግድ ህጉ በተሰጣቸው ስልጣን መሰረት የማህበሩን ስራ
ይመራሉ ፤ያስተዳድራሉ፤ ይፈፀማሉ፤ ያስፈፅማሉ፤

አንቀፅ 6

ስለ ሥራ አስኪያጅ የሥራ ዋጋ

የሥራ አስኪያጅ የሥራ ዋጋ የሚወሰነው በማህበርተኞቹ ጠቅላላ ጉባዔ ስብሳባ ይሆናል፡፡ ይህም ሲሆን የስራ ዋጋቸው
በደመወዝ ወይም በትርፍ ተካፋይ ወይም ሁለቱንም በማግኘት እንዲሆን ለማድረግ ይቻላል፡፤

አንቀፅ 7

የሥራ አስኪያጅ ኃላፊነት

የማህበሩ ስራ አስኪያጅ ከስልጣን ገደባቸው ውጪ በንግድ ህጉ የተሰጡትን ድንጋጌዎች ወይም በማህበሩ የመመስረቻ
ፅሁፍና በዚህ የመተዳደሪያ ደንብ የተመለከቱትን በመጣስ በስልጣናቸው የሚፈፅሟቸውን ጥፋቶች በማህበሩና በሶስተኛ
ወገኞች ፊት በራሳቸው ኃላፊ ይሆናሉ፡፡

አንቀፅ 8

ሥራ አስኪያጅ ስለመሻር

የማህበሩ ሥራ አስኪያጅ ሊሻሩ የሚችሉት በንግድ ህጉ ቁጥር 527/መ መሰረት ይሆናል፡፡

አንቀፅ 9

ያለስብሰባ ስለሚተላለፉ ውሳኔዎች

1. ጉባዔ እንዲሰበሰብ ህግ ወይም የማህበሩ መተዳደርያ ደንብ በማያስገድድበት ጊዜ ዋናው ሥራ አስኪያጅ ድምፅ
ሊሰጥበት የተፈለገውን ጉዳይ ለእያንዳንዱ አባል በፅሁፍ በመላክ/ኢሜይል/ በማድረግ በጉዳዩ ላይ አባላት
በፅሁፍ ድምፅ እንዲሰጡበት መጠየቅ አለበት፤
2. አባላቱም በፅሁፍ/በኢሜይል/ ምላሽ መስጠታቸውን እንዳረጋገጠ ወዲያውኑ የእያንዳንዱን የውሳኔ ሃሳብ
በመቀበል ተግባራዊ ያደርጋል፤ ውሳኔያቸውን ልዩነት ያለ እንደሆነ በአብላጫው አባላት ውሳኔ መሰረት
እንዲፈፀም ይደረጋል፡፡
አንቀፅ 10
ስብሰባ
1. የማህበሩ የሂሳብ ዓመት ከተዘጋ አራት ወር ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ የማህበሩ ጠቅላላ ጉባዔ መጠራት አለበት፡፡
2. ዋናው ሥራ አስኪያጅ ዓመታዊ የማህበርተኞች ስብሰባ ከመደረጉ በፊት ለ 20/ሃያ/ ቀን ባላነሰ ጊዜ አስቀድሞ
ለአባላት በአደራ ደብዳቤ የስብሰባውን ጥሪ ማሳወቅ ለውሳኔ ወይም ለውይይት ያቀረበውን ሃሳብ/አጀንዳ/ ምን
እንደሆነ በግልፅ ማስረዳት/ማሳወቅ አለበት፤
3. አዲተሩ ወይም በዋናው ገንዘብ ከግማሽ በላይ የሚወክሉ ማህበርተኞች በማናቸውም ጊዜ የማህበሩ ጠቅላላ
ጉባዔ እንዲሰበሰብ ሊያደርጉ ይችላሉ፤

አንቀፅ 11

ጠቅላላ ጉባዔና ምልዓተ ጉባዔ

1. ሥራ አስኪያጅ ወይም የማህበሩ ካፒታል ከእኩሌታው በላይ የያዙ አባላት በማንኛውም ጊዜ የሁለት ሳምንት
የማስታወቂያ ጊዜ በመስጠት የጠቅላላ ጉባኤ ስብሰባ እንዲጠራ ሊያደርጉ ይችላሉ፤
2. ጠቅላላ ጉባኤ ባለ አክሲዮኖች ሁሉ የሚሳተፉባቸው ሆነው መደበኛ ወይም ድንገተኛ ሊሆኑ ይችላሉ፤
3. ዋናው ሥራ አስኪያጅ ዓመታዊ የማህበርተኞች ስብሰባ ከመደረጉ በፊት 10 ቀን ባላነሰ ጊዜ አስቀድሞ ለአባላት
በአደራ ደብዳቤ የስብሰባውን ጥሪ ማሳወቅና ለውሳኔ ወይም ለውይይት የቀረበው ሀሳብ ምን እንደሆነ በግልፅ
መረዳት አለበት፤
4. በዚህ መተዳደሪያ ደንብ ፣ መመስረቻ ፅሁፍና በኢትዮጵያ ንግድ ህግ ቁጥር ተለይተው የተደነገጉት እንደተጠበቀ
ሆነው ከጠቅላላ የማህበሩ ካፒታል 2/3 ኛ አክሲዮን የያዙ አባላት ሲገኙ ምልዓተ ጉባዔ ይሆናል፤
5. እያንዳንዱ ባለ አክሲዮን በአክሲዮን መጠኑ ድምፁ የመስጠት መብት አለው፤
6. አግባብነት ባላቸው የንግድ ህግ ድንጋጌዎች በመመስረቻ ፅሁፍና በዚህ መተዳደሪያ ደንብ ሆነ በንግድ ህጉ
ተለይተው የተደነገጉት እንደተጠበቁ ሆነው ማንኛውም ከማህበሩ ጋር በተያያዙ ጉዳዮች ከእኩሌታው በላይ
ድምፅ/50+1/ ውሳኔዎች መሰረት ተፈፃሚ ይሆናሉ፤
7. በስብሰባዎች ወቅት የሚደረጉ ጉዳዩች ውይይቶችና ውሳኔዎች በቃለ ጉባዔ ተይዘው በአባላት መፈረም
አለባቸው፤

አንቀፅ 12

ስለጠቅላላ ጉባዔ ስልጣን

1. የማህበሩን ስትራቴጂ ዕቅዶች፤ህጎች፤ፖሊሲና የስራ ዕቅድ ማመንጨት ፣ ማፅደቅና በአግባቡ ስራ ላይ መዋሉን


መቆጣጠር፤
2. የዓመቱን የሥራ ዕቅድና በጀት ማፅደቅ፤
3. የማህበሩን የስራ አፈፃፀም በሚመለከት ለዋና ስራ አስኪያጅ መመሪያ መስጠት፤
4. ማህበሩን ማስፋፋት ወይም ማፍረስ፤ ማሻሻያ ማድረግ፤ አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኝው ውሳኔ መስጠት፤
5. ስለዓመታዊ ትርፍ ክፍፍል ውሳኔ መስጠት፤
6. በሥራ አስኪያጅ እና ኦዲተሮች የሚቀርቡ ሪፖርቶችና ጉዳዮችን መርምሮ የመጨረሻ ውሳኔ መስጠትና ሌሎች
በህግ ፣ በጠቅላላ ጉባኤ የተፈቀዱና የተተው ጉዳዮች ላይ ውሳኔ መስጠትና ማከናወን ናቸው፡፡

አንቀፅ 13

የኦዲተሮች ስልጣንና ተግባር

1. የኦዲተሮች ተጠሪነት ለጠቅላላ ጉባዔው ነው፤


2. የማህበሩ ሂሳብና የሂሳብ መዛግብት በህግ በሚጠየቀው መሰረት በአግባቡ መመዝገባቸውንና መያዛቸውን
ማረጋገጥ፤
3. የማህበሩን ንብረት፤የሂሳብ ማመዛዘኛ ትርፍ ኪሳራውንም የሚያሳዩትን መዛግብት ትከክለኛነት ማረጋገጥ፤
4. የማህበሩ ገቢና ወጪ በትክክል መመዝገቡን የመቆጣጠር፤
5. ስራውን ለማከናወን አስፈላጊ ነው ብሎ የሚያምንበትን የማህበሩን ማናቸውም መዝገብ፤ሰነዶች፤ቃለ
ጉባዔያት እና ሌሎች መረጃዎችን ማየት እና መመርመር፤
6. የማህበሩ ከፍተኛ አመራሮች የሰጡት ሪፖርት የማህበሩን ትክክለኛ ገፅታ የሚያሳይ መሆኑን ማረጋገጥ፤
7. በየአመቱ መጨረሻ የማህበሩን አጠቃላይ የፋይናንስ እንቅስቃሴ በሚመለከተት መግለጫ በማዘጋጀት
ለጠቅላላው ጉባዔ ሪፖርት ማድረግ፤
8. ሌሎች ግዴታዎችንም መፈፀም፡፡

አንቀፅ 14

የባለአክሲዮን እንደራሴ

1. ማንኛውም ባለአክሲዮን በማህበሩ ጉዳይ ላይ የሚወክለውን አንድ እንደራሴ/ወኪል/ ለመሾም ይችላል፤


2. ባለአክሲዮኑ በህግ የሰውነት መብት የተሰጠው ማህበር ከሆነ እንደራሴው/ወኪሉ/ በባለአክሲዮኑ በመመስረቻ
ፅሁፉ የተሾመ ሥራ አስኪያጅ ይሆናል፤
3. እንደራሴነቱ ስልጣን በግልፅ ካልታደሰ በቀር እንደራሴው ለባለአክሲዮኑ የተሰጡት ስልጣንና ተግባሮች
ይኖሩታል፤

አንቀፅ 15

ስለማህበሩ ሂሳቦች

1. ማህበሩ ሂሳቡን የንግድ ህጉ በሚደነግገው ተቀባይነት ባለው ዘመናዊ የሂሳብ አያያዝ ስነ ስርዓትና ደንብ ይይዛል፤
2. በሂሳቡ አመት መጨረሻ የማህበሩን ንብረቶች የሚያሳይ ሚዛን በዋናው ስራ አስኪያጅ ይዘጋጃል፡፡ ይህም ሚዛን
እንዲፀድቅና እንዲመረመር ለኦዲተሮችና ለማህበርተኞች ይተላለፋል፤
3. የማህበሩ ዓመታዊ ሁኔታ የሂሳብ ሚዛን የትርፍና ኪሳራ ሁኔታ የንብረት ቆጠራዎችና የዋና ስራ አስኪያጅ
ወይም የኦዲት ሪፖርት የሚያሳዩ ሰነዶች በየጊዜው ለአባላት ይላካሉ፤
4. በንግድ ህጉ አንቀፅ 539 እንደተደነገገው ከተጣለው ትርፍ ላይ በየአመቱ መጠባበቂያ የሚሆን ቢያንስ 5
(አምሰት በመቶ) እየተቀነሰ ይቀመጣል፤ ይሄው መጠባበቂያ ከማህበሩ ዋና ገንዘብ አንድ አስረኛ እጅ ሲደርስ
ግዴታ መሆኑ ይቀራል፤
5. በትርፍ ክፍፍል መመስረቻ ፅሁፍ አንቀፅ 6 እና በንግድ ህጉ አንቀፅ 539 መሰረት በየዓመቱ መጨረሻ የመንግስት
ግብር ክፍያዎች ፣ ህጋዊ መጠባበቂያና አግባብነት ያላቸው ማንኛቸውም ወጪዎችና ብድሮች ህጋዊ
መጠባበቂያና ብድሮች ከተቀነሱ በኃላ ያገኘው ንፁህ ትርፍ በአባላት አክሲዮን ድርሻ መጠን ይከፋፈላል፤
6. የማህበሩ አባላት በሙሉ ስምምነት እስከተገኘ ድረስ ለአንድ ለማህበሩ ጉዳይ ማስፈፀሚያ የሚውል ከትርፍ
ክፍፍል በመቀነስ ተጨማሪ ልዩ የመጠባበቀያ ገንዘብ ማስቀመጥ ይችላል፤

አንቀፅ 16

የማህበሩ ዓርማ እና ማህተም

ማህበሩ ዓርማና ማህተም ይኖሩታል፡፡ ይህም የሚውለው ለማህበሩ ስራና ጥቅም ብቻ ነው፡፡

አንቀፅ 17

የሂሳብ ዓመት

1. የማህበሩ የሂሳብ ዓመት በኢትዮጲያ አቆጣጠር ከ ሐምሌ 1 ቀን እስከ ሰኔ 30 ድረስ ሲሆን የመጀመሪያው
የበጀት አመት ማህበሩ ህጋዊ ሆኖ ከተቋቋመበት ቀን ጀምሮ እስከ ሰኔ 30 ያለው ይሆናል፤
2. የማህበሩ ሂሳብ የሚዘጋው ቢያንስ በአመት አንድ ጊዜ ይሆናል፤

አንቀፅ 18
ስለትርፍ አደላደልና አከፋፈል
1. የማህበሩ ዕዳዎች ወጪዎች ከተቀነሱ እንዲሁም የመጠባበቂያ ገንዘብ ከተነሳ በኃላ ከትርፉ ቀሪ የሆነው ገንዘብ
ለባለአክስዮኖች እንዲከፋፈል ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባዔው ውሳኔ ይሰጥበታል፤
2. ትርፉም የሚከፋፈለው ባለአክስዮኖች በከፈሉት ገንዘብ መጠን በውል በተጠቀሰው የቀደምትነት መብት
መሠረት ነው፤
3. የትርፍ ድርሻዎቹ የሚከፈሉበት ቀን የአከፋፈሉ ሁኔታ በዓመታዊው ጠቅላላ ጉባዔ የሚወሰኑ ናቸው፡፡

አንቀፅ 19

ስለወራሾች

1. አንድ ማህበርተኛ ሲሞት በሟቹ እግር ወራሾች ተተክተው አባል ይሆናሉ፤


2. የማህበሩ አባል ከወራሾቹ ውስጥ አንድ ወይም የተወሰኑትን ለይቶ የድርሻውን ተጠቃሚ እንዲሆኑ መሰየም
ይችላል፡፡ ሆኖም ወራሾቹ በአባልነት መቀጠል የማይፈልጉ ከሆነ በማህበሩ የወቅቱ የሂሳብ ዓመት የሚገኘው
የንብረት ዝርዝር የሂሳብ መዝገብ መሰረት የድርሻቸው ይከፈላቸውና ይሰናበታሉ፡፡ ቀሪ አባላት በሚስማሙበት
መልክ የወጪውን አባል ድርሻ አክሲዮን ለራሳቸው ድርሻ በመግዛት ወደ ውጪ በመሸጥ የማህበሩን ስራ
ማንቀሳቀስ ይቀጥላሉ፡፡

አንቀፅ 20

ስለ ማህበሩ መፍረስ

1. ማህበሩ በንግድ ህግ ቁጥር 217፣218፣511፣542 እና 543 በተደነገገው መሰረት በቂ በሆኑ ምክንያቶች ብቻ


በፍርድ ቤት ሊፈርስ ይችላል፤
2. ከማህበሩ አባላት አንዱ ወገን የማህበሩ መፍረስ ቢጠየቅ ቀሪዎቹ የጠያቂውን አክሲዮን ድርሻ በሂሳብ መዝገቡ
መሰረት ዋጋ በመክፈል የማህበሩን ስራ በመካከላቸው (በመተካት) ይቀጥላሉ እንጂ ማህበሩ በአባል ጥያቄ
አይፈስርም፤

አንቀፅ 21

ያለመግባባትን ስለመፍታት

1. ማህበሩ ህልውና ባለው ጊዜም ሆነ በሚፈርስ ጊዜ በማህበርተኞቹ መካከል አለመግባባት ቢፈጠር በተቻለ
መጠን በመግባባትና በስምምነት እንዲያልቅ ከፍተኛ ጥረት ይደረጋል፡፡ በስምምነት ወይም በጠቅላላ ጉባዔ
መፍትሄ ካላገኝ በፍ/ብሄር ህግ ቁጥር 3325 እና ተከታዮቹ በተደነገገው መሰረት በኢትዮጲያ ውስጥ በግልግል
ጉባዔ ይታያል፤
2. ጉዳዩ በግልግል አካል የሚታይ ሲሆን እያንዳንዱ ወገን አንዳንድ ገላጋይ ዳኛ ይመርጣል ፣ ገላጋይ ዳኞቹም በጋራ
የራሳቸውን ሰብሳቢ ይመርጣል፣ በሰብሳቢው ምርጫ ስምምነት ተፈጥሮ አንደኛው ወገን ገላጋይ ዳኛ መርጦ
ለሌላኛው ባሳወቀ እና ማስታወቂያ መድረሱ በተረጋገጠ በ 20 ቀናት ውስጥ ሌላኛው ወገን መርጦ ካላሳወቀ
አንደኛው ወገን መርጦ ባቀረበው ገላጋይ ዳኛ ብቻ ጉዳዩ ታይቶ ውሳኔ ያገኛል፤
3. በማንኛውም ሁኔታ የግልግል ዳኞች ቁጥር ሰብሳቢውን ጨምሮ ከሶስት አይበልጥም፤
4. የግልግል ዳኞች በተከራካሪው ወገኖች የቀረበላቸውን ማንኛውም ጉዳይ በማህበሩ የመመስረቻ ፅሁፍ ፣
የመተዳደሪያ ደንብና አግባብነት ካለው ህግ አኳያ በመመርመር ዳኞች ውሳኔ ይግባኝ የሌለው እና በተከራካሪ
ወገኖች ላይ የፀናና ተፈፃሚነት ያለው ይሆናል፡፡
5. ሆኖም ግን በግልግል ዳኞች ጉዳዩን መፍታት ያልተቻለ እንደሆነ ብቻ የዳኝነት ስልጣን ባለው በሀገሪቱ ፍርድ
ቤት ጉዳዩ እንዲታይ ይደረጋል፤

አንቀፅ 22

ልዩ ልዩ

1. ማንኛውም በመመስረቻ ፅሁፍና በመተዳደሪያ ደንቡ በግልፅ ያልተቀመጠ ጉዳይ ቢኖር በኢትዮጲያ ንግድ ህግና
በሌሎች አግባብነት ባላቸው ህጎች መሰረት ተፈፃሚ ይሆናል፤
2. የመመስረቻ ፅሁፉንም ሆነ የመተዳደሪያ ደንቡን ለማሻሻል በንግድ ህጉ ቁጥር 536(2) መሰረት ከማህበሩ ካፒታል
75 (ሰባ አምስት በመቶ) የያዙ ባለአክሲዮኖች ስምምነት ማግኘት ያስፈልጋል፤

አንቀፅ 23

ተፈፃሚነት

1. ይህ መተዳደሪያ ደንብ እና የመመስረቻ ፅሁፍ ስልጣን ባለው አካል ፊት ከፀደቀበት ጊዜ ጀምሮ የፀና ይሆናል፤
2. ይህን መተዳደሪያ ደንብ አንብበንና አፅድቀን ዛሬ ሚያዚያ 5 ቀን 2012 ዓ.ም ተፈራርመናል፡፡

ስም ፊርማ

1. --------------------- ----------------------
2. --------------------- ---------------------
3. --------------------- ----------------------

የባለአክስዮኖች ቃለ ጉባዔ ቁጥር 1

የስብሰባው ቀን፡- መጋቢት 28 ቀን 2012 ዓ.ም

የስብሰባው ሰዓት፡- 8፡00-9፡00


የስብሰባው ቦታ፡- ልደታ

የስብሰባው አጀንዳ፡-

1. ለሚቋቋመው ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር አማራጭ ስሞችን ስለማፅደቅ ይሆናል

በስብሰባው የተሰጡ አስተያየቶችና የውሳኔ ሃሳቦች

የስብሰባው መሪ የሆኑት አቶ ነቢዩ ክንፈ ስለድርጅቱ ምዝገባ ሂደትና መሰል ጉዳዮች በዝርዝር ካስረዱ በኃላ
ለድርጅቱ ስያሜ የሚሆኑ አማራጭ ስሞችን እንዲሰየሙ በሰጡት ሃሳብና አስተያየት መነሻ የሚከተሉት
ስያሜዎች በቅደም ተከተላቸው መሰረት የድርጅቱ የምዝገባ ስሞች እንዲሆኑ በስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡

1 ኛ አማራጭ ስም፡- ኩል ኢንዱስትሪያል ኃላ/የተ/የግ/ማር

2 ኛ. አማራጭ ስም፡- ደንበላ ኢንዱስትሪያል ኃላ/የተ/የግ/ማር

3 ኛ. አማራጭ ስም፡- አልፋ ኢንዱስትሪያል ኃላ/የተ/የግ/ማር

ሌላ አጀንዳ ባለመኖሩ ስብሰባው በዚሁ ተጠናቋል፡፡

You might also like