You are on page 1of 9

ነመመ ጠቅላላ የውሃ ኮንስትራክሽን ስራ ተቋራጭ ህብረት ሽርክና ማህበር

መመስረቻ ፅሁፍ

አንቀፅ-1

ምስረታ

እኛ ፊርማችን ከዚህ ሰነድ ግርጌ የሚገኝ ማህበርተኞች በዚህ መመስረቻ ጽሁፍ በመተዳደሪያ ደንቡና በ 1952
ዓ.ም በወጣው የኢትዮጵያ ንግድ ህግ መሰረት የሚተዳደር ፀጋዬ እና ታሪኩ ጠቅላላ የውሃ ኮንስትራክሽን ስራ
ተቋራጭ ህብረት ሽርክና ማህበር ነው፡፡

አንቀፅ-2

የማህበሩ አባላት ስም፡ዜግነትና አድራሻ

ተራ ዜግነት አድራሻ
ቁጥ
የአባላት ስም ከተማ ቀበሌ ወረዳ የቤት

ቁጥር

1 NESRI YAYA AHMED ኢትዮጵያዊ ድሬደዋ 02 -- 5983

2 MOHAMMED IDIRIS ኢትዮጵያዊ ድሬደዋ 02 --

3 MAGARSA ABDUMALIK 08

አንቀፅ 3

የማህበሩ ስምና አድራሻ

3.1 የማህበሩ ስም ፀጋዬ እና ታሪኩ ጠቅላላ የውሃ ኮንስትራክሽን ስራ ተቋራጭ ህብረት ሽርክና ማህበር፡፡

3.2 የማህበሩ ዋና መ/ቤት በድሬዳዋ ከተማ ቀበሌ-08 በቤት ቁጥር------------ ሲሆን ወደ ፊት በአገር ውስጥ ባሉ
የክልል ከተሞችና እንዲሁም በውጭ ሀገር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የመክፈት መብቱ የተጠበቀ ነው.

1
አንቀፅ-4

ማህበሩ የተቋቋመባቸው የንግድ ዓላማዎች

4.1.የውሀ ስራዎችን በጥራትና በፍጥነት ማከናወን፡፡

4.2.በሀገራችን የተለያዩ የመስኖ ስራዎችን ማከናወን፡፡

4.3.በገጠሩ የንፁህ ውሀ ፕሮጀክቶችን መስራት፡፡

አንቀፅ-5

የሽርክና የማህበሩ ጠቅላላ ካፒታል

5.1 የማህበሩ ጠቅላላ ገንዘብ ብር 3000.00 (ሁለት ሺ ብር) የእያንዳንዱ አባል መዋጮ ብር 1000.00 (አንድ ሺ
ብር) በየእያንዳንዱ አበላት መዋጮ ድርሻ የተከፋፈለ ነው፡፡

5.2 የማህበሩ አባላት ጠቅላላ መዋጮ በሙሉ በጥሬ ገንዘብ የተከፈለና ገቢ የሆነ ነው።

የአባላት የመዋጮ ድልድል ልክ ከዚህ እንደሚከተለው ነው።

ተራ ቁጥር የአባላት ስም የመዋጮ መጠን የጠቅላላ መዋጮ

1 NESRI YAYA AHMED 1000.00 1000.00

2 MOHAMMED IDIRIS 1000.00 1000.00

3 MSGARSA ABDUMALIK 1000.00 1000.00

ድምር - 3000.00

አንቀፅ-6

የማህበሩ አመራር

ማህበሩ በአንድ ስራ አስኪያጅ ይተዳደራል አቶ/ወ/ሮ ---------------------------የማህበሩ ዋና ስራአስኪያጅ


ሆነው ላልተወሰነ ጊዜ ተመርጠዋል፡፡

2
አንቀፅ-7

የስራ አስኪያጅ ሥልጣንና ተግባር

7.1 በማህበሩ ስም በማንኛውም ባንክ በጋራ ሂሳብ ማንቀሳቀስ፡፡

7.2 የማህበሩን ወኪል ወይም ሰራተኛ ይቀጥራል፣ያሰናብታል ደመወዝ ይከፍላል እንዲሁም፡፡ ሌሎች ከመቅጠር
ከማሰናበት ጋር የተያያዙ ጉዳዮችን ይወስናል።

7.3 የዘርፍ ስራ አስኪያጅ ይሾማል።

7.4 በአባላት ውሳኔ ድርጅቱን በማስያዝ ወይም ሳያሲዝ ብድር ውሎችን ይፈራረማል፡፡

7.5 ማህበሩን በመወከል የኪራይ ውሎች ላይ እና በማንኛውም ውሎች ላይ ይፈርማል።

7.6 በማንኛውም ፍ/ቤት ማህበሩ ከሳሽ፣ተከሳሽ ወይም ጣልቃ ገብ በሚሆንበት ጉዳይ ሁሉ ማህበሩን በመወከል
ይከሳል ይከሰሳል ካስፈለገም በማህበሩ ስም ጠበቃ መወከል ይችላል።

7.7 በማህበሩ ስም ከማህበሩ አባላት ወይም ከውጪ ለሌላ 3 ኛ ወገን ውክልና መስጠት መሻር ይችላል ።

7.8 ለማህበሩ ስራ የሚሆን ቤቶችን ይከራያል፡፡

7.9 የማህበሩን ስራ በበላይነት ይመራል ይቆጣጠራል።

አንቀጽ-8

የማህበሩን ኦዲተር

10.1 ማህበሩ በንግድ ህግ መሰረት የሂሳብ መዛግብቶችን ይይዛል፡፡

10.2 የማህበሩ ኦዲተሮች በማህበሩ አባላት ስምምነት ሊመረጡ ይችላሉ፡፡

10.3 ማህበሩ በንግድ ህግ መሰረት በየበጀት ዓመቱ በኦዲተሮች የሂሳብ ምርመራ ያደርጋል፡፡

3
አንቀጽ 9

ስለትርፍ አከፋፈል

9.1 አመታዊ የተጣራ ትርፍ እያንዳንዱ ባለድርሻ አባል ከዓመቱ ትርፍ 80% ይከፋፈላል፡፡ ቀሪው በማህበሩ ሂሳብ
ተቀማጭ ይሆናል፡፡

9.2 ትርፉ ህግና የመተዳደሪያ ደንቡ በሚፈቅደው መሰረት ለማህበርተኞች ይከፋፈላል፡፡

አንቀጽ-10

የአባላት ኃላፊነት

ድርጅቱ ኪሳራ ቢደርስበትና ቢፈርስ የአባላቱ የጋራ ኪሳራ ይሆናል፡፡

የማህበሩየቆይታ ጊዜ

ማህበሩ የተቋቋመው ላልተወሰነ ጊዜ ነው።

ተራ ቁጥር የአባላት ስም ፊርማ

1 NESRI YAYA AMMED

2 MAGARSA ABDUMAKIK

3 MOHAMMED IDIRIS

4
ነመመ ጠቅላላ የውሃ ኮንስትራክሽን ስራ ተቋራጭ ህብረት ሽርክና ማህበር

መተዳደሪያ ደንብ

ይህ መተዳደሪያ ደንብ በኢትዮጵያ ንግድ ህግ መሰረት ፀጋዬ እና ታሪኩ ጠቅላላ የውሃ ኮንስትራክሽን ስራ ተቋራጭ
ህብረት ሽርክና ማህበር ነው ፡፡

የመመስረቻ ጽሁፍ አካል ነው፡፡

አንቀፅ አንድ

የአባላት መብቶች

እያንዳንዱ አባል

1.1 በአባላት ስብሰባዎች ሁሉ የመሳተፍ፡፡


1.2 በስብሳዎች ሁሉ ድምጽ የመስጠት፡፡
1.3 በሸርክና ማህበሩ የሚገኝን የንብረት ቆጠራና የሂሳብ ሚዛን ሰነድን እና የኦዲተሮች ሪፖርት የመመርመር ቅጂ
መውሰድ፡፡
1.4 በሕግ በመመስረቻ ጽሁፍ በዚሁ የመተዳደሪያ ደንብ በተሰጠው ሌሎች መብቶች የመጠቀም መብት አለው፡፡

አንቀጽ ሁለት

ስለካፒታል

 የሽርክና ማህበሩ ጠቅላላ ካፒታል ብር 3000.00(ሁለት ሺ ብር) ሲሆን ይህም በ 3 አባላት የተከፈለ ሆኖ
የእያንዳንዱ ድርሻ 1000.00 ብር (አንድ ሺ ብር) ነው፡፡
 የማህበሩ ጠቅላላ ካፒታል በማህበሩ መመስረቻ ፁሁፍ አንቀጽ 5 ስር በተገለፀው መሰረት በሙሉ በጥሬ
ገንዘብ ተከፍሏል፡፡

አንቀፅ ሶስት

የሽርክና ማህበሩ አመራር አካላት

የስራ አመራር አካላት የሚከተሉት ይሆናሉ

ሀ. ጠቅላላ ጉባኤ
ለ. ዋና ስራ አስኪያጅ
ሐ. ም/ስራአስኪያጅ

5
አንቀጽ አራት

የማህበርተኛ ጠቅላላ ጉባኤ

የሽርክና ማህበሩ ጠቅላላ ስብሰባ የማህበሩ የመጨረሻ የስልጣን አካል ነው ስለሆነም የሽርክና ማህበሩ ጠቅላላ
ጉባኤ የማህበሩ ከፍተኛ የአስተዳደር አካል ሆኖ ማህበሩን በሚመለከቱ ጉዳዮች ሁሉ የመወሰን ስልጣን አለው፡፡

4.1 የማህበሩ የሂሳብ ሚዘን ትርፍ ኪሳራ መግለጫ ይመረምራል፡፡ የዋና ስራ አስኪያጅንና የኦዲተሮችን ሪፖርት
ማጽደቅ፡፡

4.2 ዋና ስራአስኪያጅና ም/ስራአስያጅን መሾም፡፡

4.3 የትርፍ ወይም ኪሳራን አከፋፈልና ድልድል መወሰን፡፡

4.4 የማህበሩን መመስረቻና መተዳደሪያ ደንብ ማሻሻል በሚቀርቡ ጉዳዮች ላይ መወሰን፡፡

አንቀጽ አምስት

ስለ ስብሰባ

5.1 የማህበሩ መደበኛ ስብሰባ በየአንዳንዱ የበጀት አመት ሶስት ወራት በማህበሩ ጽ/ቤት ወይም የማህበሩ ዋና
ስራአስኪያጅ በሚወስኑት የስብሰባ ቦታ ይደረጋል ሆኖም የማህበሩ ዋና ስራ አስኪያጅ ወይም ም/ስራ አስኪያጅ
ወይም በኦዲተሮች ጥያቄ በማንኛውም ጊዜ የአባላት ስብሰባ ሊጠራ ይችላል፡፡ የአባላት ስብሰባ ጥሪ በዋና ስራ
አስኪያጅ አማካኝነት ከስብሰባው አስራ አምስት ቀን በፊት ለሽርክና ማህበሩ አባላት በደብዳቤ እንዲደርሳቸው
መደረግ ይኖርበታል፡፡

አንቀጽ ስድስት

የማህበርተኞች የድምጽ ብልጫና ምልዓተ ጉባኤ

6.1 የማህበሩ አባላት ከግማሽ በላይ ከተገኙ ስብሰባው ሊካሄድ ይችላል፡፡

6.2 ከማህበሩ አባላት ከግማሽ በላይ ወይም በ 3/4 ማህበርተኞች ድምጽ ብልጫ ያገኘ ውሳኔ ተግባራዊ
ሊሆንይችላል፡፡

6
አንቀጽ ሰባት

የዋና ስራ አስኪያጅ ስልጣንና ተግባር

7.1 ዋና ስራአስኪያጅ በመመስረቻ ጽሁፍና በዘህ መተዳደሪያ ደንብ ከተሰጠው ስልጣ ውጪ በመስራት
በሚያደርሰው ጥፋት በህግ ፊት በግሉ ተጠያቂ ነው፡፡

7.2 ዋና ስራአስኪያጁ በሆነ ምክንያት ለጊዜው ስራቸውን መስራት ባይችሉ ከአባላቱ ጋር በመነጋገር
ም/ስራአስኪያጁንወኪል ማድረግ ይችላል፡፡

አንቀጽ ስምንት

ኦዲተር

8.1 የማህበሩ ኦዲተሮች የማህበሩን የሂሳብ ሰነዶች መዛግብት ይመረምራሉ፡፡ ከስራአስኪያጁ አስፈላጊ ማብራሪያ
መጠየቅ ይችላሉ፡፡እንዲሁም የማህበሩን የሂሳብ መዝገብና ሰነዶች በመመርመር የሂሳብ ሪፖርትና ከሪፖርቱ በመነሳት
በማህበሩ የወደፊት እንቅስቃሴ ላይ አስፈላጊውን ሪፖርት ያቀርባሉ፡፡

8.2 የኦዲተሮችን ክፍያ እና /ወይም አበል በሽርክና ማህበሩ ጠቅላላ ስብሰባ ይወሰናል፡፡

አንቀጽ ዘጠኝ

የዋና ስራአስኪያጅ ክፍያ

9.1 የዋና ስራአስኪያጅ ልዩልዩ አበሎች ወይም ጥቅም በሽርክና ማህበሩ ውሳኔ ወደ ፊት ይወሰናል፡፡

አንቀጽ አስር

ስለሽርክና ማህበሩ መተላለፍ

10.1 በማህበርተኞች መካከል የስራ ድርሻ ዝውውር ማድረግ ገደብ አይኖርበትም፡፡

10.2 የስራ ድርሻ ዝውውሩ በጽሁፍ ካልሆነና በቃለጉባኤ ካልተያዘ ህጋዊነት አይኖረውም፡፡

10.3 ከሽርክና ማህበሩ አባላት ውጪ የስራ ዝውውር ለማድረግ ጠቅላላ አባላት ማጽደቅ አለባቸው ሆኖም
በቅድሚያ ከማህበሩ ጋር ያለውን እዳም ሆነ ጥቅም ማጣራት ይኖርባቸዋል፡፡

10.4 ከማህበርተኞች መካከል ከሽርክና ማህበሩ የመሰረዝ ጥያቄ ሲቀርብ በጠቅላላ ጉባኤው መጽደቅ አለበት ሆኖም
በበጀት አመቱ መጨረሻ ላይ በኦዲተር ተመርምሮ በማህበሩ ከታወቀ በኃላ በአባሉ ላይ የሚፈለግ ማንኛውንም
እዳዎች በማቀናነስ የሚቀረውን ድርሻ ተሰጥቶት ይሰረዛል፡፡

7
አንቀጽ አስራ አንድ

ስለ ወራሾች

11.1 አንድ ማህበርተኛ ሲሞት ህጋዊ ወራሾች ባለቤት ይሆናሉ ወይም መሀበርተኛው ማግኘት የሚገባውን ጥቅም
ማግኘት ይችላሉ፡፡

11.2 አንድ በሞት የተለየ የሽርክና ማህበሩ አባል ህጋዊ ወራሾች በማህበሩ ውስጥ በመግባት መብታቸው
እንደተጠበቀ ሆኖ በዚህ መጠቀም ካልፈለጉ ማህበሩ ከሟች ላይየሚፈለግ ማንኛውንም እዳዎች ቀንሶ የሚቀረውን
ድርሻ ይከፍላል፡፡

አንቀጽ 12

ስለማህበሩ ሂሳብና መጠባበቂያ ገንዘብ

12.1 ማህበሩ የተሟላ ሂሳብ መዝገብ ይኖረዋል፡፡

12.2 ለማህበሩ መጠባበቂያ ገንዘብ ተቀማጭ የሚደረገው ከተጣራው ትርፍ ላይ ቢያንስ 20% (ሀያ ፐርሰንት)
እየተቀነሰ ይቀመጣል ይሀውም የማህበሩን ካፒታል 3/4 ሲደርስ ግዴታ መሆኑ ይቀራል፡፡

አንቀጽ 13

ማሻሻል

13.1 ይህ መተዳደሪያ ደንብ የመመስረቻ ጽሁፍ በሽርክና ማህበሩ በሙሉ አባላት ስምምነት ሊሻሻል ወይም
ሊለወጥ ይችላል፡፡

አንቀጽ አስራ አራት

አለመግባባት

141 ማህበሩ በሚንቀሳቀስበትም ሆነ በሚፈርስበት ጊዜ በሽርክና ማህበሩ አባላት መካከል ማህበሩን አስመልክቶ
የሚፈጠረውን አለመግባባት በስምምነት እንዲያልቅ ይደረጋል፡፡

14.2 በሽርክና ማህበሩ መካከል የተፈጠረው አለመግባባት በስምምነት መጨረስ ካልተቻለ በኢትዮጵያ ህግ ስልጣን
በተሰጠው ፍ/ቤት በሚሰጠው ውሳኔ መፍትሄ ያገኛል፡፡

8
አንቀጽ አስራ አምስት

የማህበሩ የሂሳብ ዓመት

15.1 የማህበሩ የበጀት ዘመን በየዓመቱ ከሀምሌ/ 1 እስከ ሰኔ/ 30 ቀን ድረስ ይሆናል፡፡የመጀመሪያው የሂሳብ ዓመት
ግን ማህበሩ በንግድ መዝገብ ከተመዘገበበት ጊዜ ጀምሮ እስከሚቀጥለው ሰኔ ሰላሳ ቀን ድረስ ነው፡፡

አንቀጽ አስራ ስድስት

ስለማህበሩ መፍረስ

16.1 ማህበሩ በንግድ ህግ ቁጥር 217 እና 218 መሰረት ወይም በጠቅላላ ማህበርተኞች ፍላጎት ሊፈርስ ይችላል

ማህበርተኞች ይህንን የሽርክና ማህበር መተዳደሪያ ደንብ ከዛሬ------ቀን-----------ዓ.ም በሰነዶች ማረጋገጫና


ምዝገባ ጽ/ቤት ድሬደዋ ቅርንጫፍ ቀርበን ፈርመናል፡፡

ተራ ቁጥር የአባላት ስም ፊርማ

1 NESRI YAYA AHMED

2 MAGARSA ABDUMALIK

3 MOHAMMED IDIRIS

You might also like