You are on page 1of 133

የውይይቱ ርዕስ፡- የኪራይ ሰብሳቢነት ትርጓሜና ፅንሰ ሀሳባዊ ገፅታ

ኪራይ ሰብሳቢነት የሚባለው የንግድ ድርጅቶች በስራ ብቃታቸው ሳይሆን ገንዘብ አቅማቸው በመጠቀም

ፖለቲከኞችን በማግባባት ገበያውን በብቼኝት ለመቆጣጠር የሚያሥችላቸው ህግ እንዲወጣ ሲደረጉና በዚሁ

አግባብ ተጠቃሚ የሆኑ እንደሆነ ነው፡፡ ኪራይ ሰብሳቢነት ከውድድር ውጭ ትርፍ ማግኘት ማለት ነው፡፡

ይህንን ትርፍ ለማግኘት የሚፈልጉ የንግድ ድርጅቶች የንግድ ማህበራት ወይም በልዩ ሁኔታ የመጠቀም

ፍላጎት ያላቸው ቡድኖች ይኖራሉ፡፡

ኪራይ ሰብሳቢነት ቀድሞ በተፈጠረ ሀብት ላይ ምንም አይነት እሴት ሳይጨምሩ የራስን ድርሻ አላግባብ

ማሳደግ ነው፡፡

ይህ ተግባር ደግሞ ውጤታማነትን ይቀንሳል የገቢ አለመመጣጠን ይጨምራል/ይፈጥራል/ በመጨረሻም

ሀገራዊ ውድቀትን ያስከትላል

ኪራይ ሰብሳቢነት የንግድ ተቋማትቨ ወይም ግለሰቦች ለህብረተሰቡ ሀብት ሳይፈጥሩና ምንም አይነት

ጥቕም ሳያስገኙ የገውል ጥቅም ለማግኘት የሚያደርጉት እንቅስቃሴ ነው፡፡

ምሳሌ ንግድ የንግድ ድርጅት የመንግስት አስፈጣሚ አካላትን በማግባባት አግባብነት የሌለው የብድር ድጋፍ

የነፃ ገንዘብ ድጋፍ ከቀረፅ ነፃ ለመሆን እድል ቢያጋኝ ኪራይ ሰብሳቢነት ይባላል፡፡ ምክንያቱም ይህ
ተግባር ከግብር ከፋዩ የሚሰባሰበውን የህብረተሰብ ሀብት ወስዶ ለሆነ ግለሰብ ወይም ተቋም

ወይም ለሌላ አካል መስጠትና የህብረተሰቡን ጥቅም ማሳጣት በመሆኑ ነው፡፡


የውይይቱ ርዕስ፡- ወደ ክላስተር ማዕከላት የሚገቡ ኢንተርፕራይዞችን ውጤት ይፋ ማድረግና ቅሬታ ማስተናገድ

1. ፕሮጀክቶች በወረዳ ን/ኢ/ገ/ልማት ከሚገኙ ኢንዱስትሪ ልማት ባለሙያዎች ከተገመገሙ

በኋላ ለኢንዱስትሪ ዘርፍ ማኔጅመንት ቀርቦ በኃላፊው ይሁንታ ያገኘ ፕሮጀክት

በየደረጃው ለሚገኙ ከንቲባ ወይም ዋና አስተዳዳሪ ተልዕኮ እንዲፀድቅ ይደረጋል

2. በሁለቱ የበላይ ኃላፊዎች ደረጃውን ጠብቆ የፀደቀ ፕሮጀክት ውጤቱ ከፀደቀበት ቀን

ጀምሮ በማስታዋቂያ ቦርድ ለተከታታየይ ቀን መለጠፍ አለበት

3. ማስታወቂያው በለተለጠፈ ሰባት ቀናት ውስጥ ቅሬታ ያለው ፕሮጀክት ቅሬታውን

ቀጥሎ ላለው ንግድ/ኢን/ገ/ል/መምሪያ ወይም ቢሮ ቅሬታው በቀረበ በአምስት ቀን ውስጥ

ቅሬታውን አይቶ ውሳኔ መስጠት አለበት

4. በውሳኔው ቅር የተሰኙ አካል ቅሬታውን ለክልል ንግድ ኢንዱስትሪና ገበያ ልማት ቢሮ

ወይም ቢሮው የወሰነው ከሆነ ለክልሉ ቅሬታ ለሚ ያቀርባል ቅሬታ የቀበውን ቅሬታ

ለደረሰው በ 10 ቀን ውስጥ የመጨረሻ ውሳኔ ይሰጣል

5. በዚህ አንቀፅ ንዑስ አንቀፅ 1 እስከ ንዑስ እስከ ንዑስ አንቀፅ 3 በተገፀው መሰረት

ቅሬታውን የሚያዩት አስቀድሞ ውሳኔ ያልተሳተፉ ባለሙያዎች ናቸው


6. ቅሬታውን የሚገመግም ባለሙያ በመጀመሪያ ግምገማ የተሳተፉ መሆን የለበትም

በዚህም ቅደም ተከተል መሰረት የክልሉ ንድና ኢንዱስትሪ ገበያ ልማት ኃላፊ የሚሰጠው

ውሳኔ የመጨረሻ ይሆናል፡፡


የውይይቱ ርዕስ፡- በሁለገብ ኢንዱስትሪ ፓርክ የሚገቡ ፕሮጀክቶች መሟላትያለባቸው ቅድመ ሁኔታ

መመልመያበመስፈርትናየመሬት መጠን አወሳሰን፣

1. በሁለገብ የኢንዱስትሪ ፓርክ ሚገቡ ፕሮጀክቶች ያለቀለት የኢንዱስትሪ ምርት የሚያመርቱ

የመካከለኛና ከፍተኛ የአምራች ኢንዱስትሪዎች ናቸው፡፡

2. በሁለገብ ኢንዱስትሪ ፓርክ ሚገቡ አምራች ኢንዱስትሪ ፕሮጀክቶች አግባብ ባለው ህግ የሚጠየቁ

የአካባቢ ደህንነትን ከመጠበቅ አኳያ ማህበራዊና ተፈጥሯዊ ደህንነትን በብናኝ፣በንዝረት፣በመጥፎ

ሽታ፣በሀይለኛ ድምፅ፣በዝቃጭ በፈሳሽ ጭስና በሌሎች ማንኛውም ብክለት የሚያጋልጥ ሁኔታ ተፅዕኖ

ግምገማ ያለፉና ተፅዕኖውን መከላከል የሚያስችል ቴክኖሎጅ ካላሟሉ በኢንዱስትሪ ፓርኩ ውስጥ

እንዲገቡ አይፈቀድም፡፡

3. መስፈርቱን ያሟሉ የኢንዱስትሪ ፕሮጀክቶች በፓርኩ ውስጥ ለሚወስዱት ቦታ በሊዝ አዋጅ

የተቀመጡ መነሻ የሊዝ ክፍያ እጀና በፓርኮች ኮርፖሬሽን መመሪያ ቁጥር 5 እና 4/2009 መሰረት የሸድ

ኪራይ መከፈል የሚችሉ መሆኑ አለባቸው፡፡

4. በሁለገብ ኢንዱስትሪ ፓርክ የሚገቡ ፕሮጀክቶችና የፕሮጀክቱ ፕሮፖዛልና የኢንቨስትመንት ካፒታል

አቅርበው በእጩነት ከተመዘገቡ ለፕሮጀክቱ በጠቅላላ ከሚያስፈልግ ወጪ በቅድሚያ 30 በመቶ የባንክ

አካውንት ያላቸው መሆኑን ከባንክ ማቅረብ አለባቸው፡፡

5. የወጭ ንግድና ለማበረታታት ሲባል የሚያመርቱት ምርት ውስጥ በሁለገብ ኢንዱስትሪ ፓርክ 40 በመቶ

እና ከዚያ በላ ተቀባይነት ያለው ውጭ ምርት ቨወደ ውጭ የሚልኩ ኢንዱስትሪዎች ትኩረት

የውሰጣቸዋል፡፡

6. ወደ ሁለገብ ኢንዱስትሪ መፓርክ የሚገቡ ፕሮጀክቶች በአራቱ ንዑስ ዘርፎች ከይሆናል፡፡


1. በጨርቃጨርቅ ቆዳና አልባሳት ንዑስ ዘርፎች

2. በእንጨትና ብረታ ብረት ንዑስ ዘርች

3. በአግሮ ፕሮሰሲንግ የምግብና ፋርማሲዮሎቲካል ንዑስ ዘረፍች

4. በኮንስትራክሽንና ግብዓት ኬሚካል ንዑስ ዘርፎች ጠጠርና መሰል ምርቶች ውጭ ያሉትን

ማለት ነው፡፡
የውይይቱ ርዕስ፡- የአክስዮን ማህበር ህግ

ስለ ድንገተኛ ጉባኤ

ሰነዶችን የማወቅ መብት

1. ድንገተኛ ጉባኤ ከመደረጉ በፊት ባሉት ውስጥ ማንኛውም ባለ አክስዮን በማህበሩ ዋና መ/ቤት ለውሳኔ

የሚቀርቡ ጽሁፎች ቢኖሩም ተቆጣጣሪ ሪፖርቶች ራሱ ለማወቅ ወይም ግልባጩን የመውሰድ መብት

አለው፡፡

2. እነዚሁም ጹሁፎች በዚሁ ጊዜ ውስጥ በጹሁፍ ጥያቄ ለሚደረግ ባለ አክስዮን ሁሉ በራሱ ኪሳራ

ይላኩለታል፡፡

ስልጣን

በህግ የተወሰኑ ተቃራኒ ነገር ከሌላ በቀር ድንገተኛ የሆኑ ጉባኤዎች ብቻ የማህበሩን መስረቻ ጹሁፍ

ወይም የማህበሩን መተዳደሪያ ደንብ የመለወጥ ውሳኔ ለመስጠት ስልጣን አላቸው፡፡

በጉባኤው ስለመግባት

ማንኛውም ባለ አክስዮን ያሉት የአክስዮኖች ብዛት ምንም ያህል ቢሆን በድንገተኛ ጉባኤዎች ተሳታፊ

ለመሆን ይችላል፡፡ ይህ ውሳኔ የቀደምትነት መብት ላላቸው አክስዮኖች አምጭወችም ተፈፃሚ

ይሆናል፡፡

የድንገተኛ ጠቅላላ ጉባኤዎች ስለ ድምጽ ብላጫና ኮረም


1. የድንገተኛ ጉባኤው ውሳኔ ዋጋ ያለው እንዲሆን ከተሰጠው ድምጽ ከሶስት እጅ በሁለቱ

የተደገፈ መሆን አለበት ስለ ብልጫውም አቆጣጠር ሂሳብ ድምጽ ያልሰጡትም ሆነ

ቢያጋጥምም ያልተፃፈላቸው የድምጽ መስጫ ወረቀቶች ከግምት ውስጥ አይገቡም፡፡

2. በድንገተና ጉባኤዎች ውሳኔዎች

ሀ/የማህበሩን ዜግነት ለሚለውጥ

ለ/ባለአክስዮኖቹ በማህበሩ ላሉት ገንዛብ ላይ እመንዲጨምሩ በማድረግ የተሰበሰበው ድንገተኛ

ጉባኤ የድምጽ መስጠት መብት ያላቸውን ጠቅላላ አክስዮኖች መሰብሰብና ውሳኔዎች በአንድ

ቃል የተሰጡ እንዲሆኑ አስፈላጊ ነው፡፡

3. በንዑስ ቁጥር ሁለት ከተመለከቱት ሌላ የመተዳደሪያውን ደንብ ለመለወጥ ውሳኔ እንዲሰጡ

የጠደረገው ድንገተኛ ጉባኤ፡-

ሀ/ድምፅ ለመስጠት መብት ካላቸው ባለአክስዮኖቹ በመጀመሪያው ጥሪ ግማሽ

ለ/በሁለተኛ ጥሪ ከሶስት አንድ እጅ ያላቸው ባለ አክስዮኖች

ሐ/በሶስተኛው ጥሪ እጅግ ቢያንስ ከ 10 አንድ ያላቸው ባለ አክስዮኖች ራሳቸው ወይም

መገኘት አለባቸው

4. ከማህበሩ ስለመውጣት መብት የቁጥር 483 ውሳኔዎች እንደተጠበቁ ናቸው፡፡


የውይይቱ ርዕስ፡- የመስራቾች የአስተዳዳሪዎች ሀላፊነት

 መስራቾችና አስተዳዳሪዎች በተነገረው ቃል መሰረት በዚሁ ምዕራፍ ለተሰጡ ድንጋዎች አጠባበቅ

ለማህበራና ስለ አስተፈዳዳሪዎች ሂሳብ ለኢኮኖሚዎች ጉባኤ ስራ አስተዳደር ክፍል

ስለ አስተዳደሮች

 የማህበሩ አስተዳደር ስራ ለማህበርተኞች እንጁ ለሌላ ሊሰጥ አይችልም


 ማህበሩ እጅግ ቢያንስ 3 አስተዳደሮች ሊኖሩት ይገባል ግን ከአስራ ሁለት የበለጡ ሊኖሩት አይችልም፡፡

እነዚህም የአስተዳደር ምክር ቤት ቦርድ ይባላሉ፡፡

 የመመስረቻ ፁሁፍ የአስተዳደሮች ቁጥር ሳወሰን በከፍተኛ በፈረሙና በአነስተኛ ብቻ የወሰነ እንደሆነ

መጀመሪያ አክስዮን ለመግዛት በፈረሙ ሰዎች ጉባኤ ይወሰናል፡፡

 በህግ የሰው መብት የተሰጣቸው ማህበሮች አስተዳደሮች ሊሆኑ ይችላሉ፡፡

 ግን አንድ የአስተዳደር ምክር ቤት ያለ አንድ ሆነ ፕሮዘዳንት አበራ ያለው ሰው መሆን አለበት፡፡

 ማህበሩ ሲመሰረት እጅግ ቢያንስ አምስት ማህበርተኞች አባላት ሊኖሩት ይገባል፡፡

 በህግ በኩል ለመስራቾች የሚባሉት ማህበሩሚመሰረትበትን ጹሁፍ ፈረሙና በሙሉ የማህበሩ

የማህበሩን ዋና ገንዘብ ያዋጡ ናቸው፡፡

 እንዲሁም ሚቋቋመው ማህበር አክስዮን በግልፅ ለህዝብ እንዲሸጥ የወጣ በሆነ ጊዜ የማህበሩን

መግለጫ የሚፈርሙት ለማህበሩ በውይይት መዋጮ የሚያደርጉ ወይም

ፕሪዝዳንት ዋና ስራ አስኪያጅ ፀሀፊ

የባለ አክስዮኖች ወይም መጀመሪያ አክስዮን ለመግዛት በፈረሙ ሰዎች ጉባኤው ያልመረጠው

እንዲሆን የአስተዳደር ምክር ቤት ከአባሎች አንዱን ፕሪዝዳንት

ምክር ቤቱ በ›ማናቸውም ጊዜ ፕሪዝዳንት ፈክረወ ይችላል የአስተዳደር ምክር ቤት አንድ ዋና ስራ

አስኪያጀጅ ይሾማል

ዋናውም ስራ አስኪየሣጅ የማህበሩ ሰራተኛ ነው፡፡ አስተዳደሪም ላይ ሆን ይችላል፡፡ የአስተዳደር

ምክር ቤት አንድ ፀሀፊ ሊመርጥ ይችላል፡፡

የዋስትና አክስዮኖች
አስተዳዳሪዎችም የመመስረቻው ጽሁፍ በስማቸው የተመዘገቡትን አክስዮኖች በማህበሩ ውስጥ

ማስቀመጥ አለባቸው፡፡ እነዚህ አክስዮኖች የአስተዳዳሪው ሰራተኛ እስከ ቆየበት ጊዜ ድረስና

በአስተዳዳሪዎች ስላለባቸው ኃላፊነት እስከያስረዱ ድረስ አክስዮኖች ሊመልሱላቸው አይችሉም፡፡


የውይይቱ ርዕስ፡- ቅድሚያ የሚሰጣቸውን የገጠር ኢንዱስትሪዎች ለይቶ ማስፋፋት

የኢንዱስትሪ ልማት ከእደ ጥበብ እስከ ከባድ ኢንዱስትሪ ባሉ መስኮች ለመሰማራት ዕድል የሚሰጥ ነው፡፡

ሰፈር ቁጥር የሌላቸው ኢንዱስትሪዎችን ለመክፈት የሚያስችል ነው፡፡ ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ እንደእኛ

አይነት በኢንዱሰትሪ ልማት ጀማሪ የሆነ አገር የተመረጡ የኢንዱስትሪ መስኮች ካልተሰማራ በስተቀር

ሁሉንም በአንዴ ለመጀመር ቢሞክር ከውድቀት በስተቀር ሌላ እድል አይኖር፡፡

ያለውን ወድ ካፒታል አጣዳፊነት በሌላቸውና ቅድሚያ በማይሰጣቸው መስኮች ማሰማራት በእርግጥም

ለዘላቂነትና የተሟላ ኢንዱስትሪያዊ ልማት የሚያበቃ ሊሆን አይችልም፡፡

ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን በመስተዳደር ምክር ቤቱ በደንብ ቁጥር 143/2008 ተቋቁሞ ወደ

ስራ እንዲገባ ተደርጓል፡፡

ለኮርፖሬሽኑ ከተሰጠ ዋና ዋና ተግባርና ኃላፊነቶች መካከልም የሁለገብ ኢንዱስትሪ ፓርኮችን በማልማት

መሬት ለባለሀብቶች ማቅረብና በዘላቂነት ማስተዳደር ይገኝበታል፡፡

በመሆኑም ኮርፖሬሽኑ በአፈፃፀም ሂደት ያጋጠሙትን ችግሮች በመፍታት ተቋማዊ ተልዕኮውን በአግባቡ

ለመወጣት ይችል ዘንድ የሚከተሉት የአሰራር መመሪያዎች እንዲወርዱ ተደርጓል፡፡

ጉልበትን በሰፊው የሚጠቀሙ አነስተኛ መካከለኛ ኢንዱስትሪዎች የማስፋፋቱ ስራ ከፀሀይ በታች ያሉ

ቀላል ኢንዱስትሪዎችን ሁሉ በማስፋፋት መጀመርን አዋጭ እንደማያደርገው አያከራክርም፡፡

በመሆኑም ከቀላልና መካከለኛ ኢንዱስትሪ ውስጥ መን አይነቶችን በማስፋፋት እንጀምር የሚለው

በማስቀደም የኢንዱስትሪውን አይነቶች መምረጥ የግድ ይላል፡፡


ምርጫው በነሲብ መካሄዱ ሌለበት በመሆኑም ለውሳኔ መነሻ ሆነው የሚያገለግሉንን መስፈርቶች በጥራት

ማስቀመጥ ያስፈልጋል፡፡

የገጠር ኢንዱስትሪ ምን አይነት መሆን እንዳለበት ከገበያ ፍላጎት በመነሳት መወሰን መቻል የኢንዱስትሪ

ልማቱ በግምት የሚመራ እንዳይሆን ከማድረግ አልፎ በተጨባጭ የገበያ ተፈላጊት ያለው እንዲሆን

ያስችለናል፡፡
የውይ
ይቱ ርዕስ፡-የአክስዮን ማህበር ጠቅላላ ድንጋጌዎች

1. የአክስዮን ማህበር ትርጓሜ

የአክስዮን ማህበር የሚባለው ዋናው ገንዘቡ አስቀድሞ ተወስኖ በአክስዮኑ የተከፋፈለና ለዕዳውን

ንብረቱ ብቻ ዋስ የሆነ ማህበር ነው፡፡

ማህበርተኞች ለማህበሩ ግዴታዎች አላፊ የሚሆኑት ባላቸው ድርሻ ልክ ብቻ ነው፡፡

2. የማህበሩ መጠሪያ

ለጠቅላላው ፀጥታ ተቃራኒ ካልሆነና የሶስተኛ ወገኖች መብት ካልተነካ የማሁበሩ መጠሪያ

እንደፈቀደው ሊመረጥ ይችላል፡፡

ከመጠሪያው ቀጥሎ የአክስዮን ማህበር የሚል ጽሁፍ መኖር አለበት፡፡

3. የማሁበሩ አነስተኛ ዋና ገንዘብና በእየአዳንዱ አክስዮን ላይ ተፃፈው ዋጋ ፡-

የማህበሩ ዋና ገንዘብ ከ 50 ሺ የኢት ብር ያነሰ መሆን አይችልም፡፡

ያንዱ አክስዮን ዋጋ ከ 10 የኢት ብር ያነሰ ለመሆን አይችልም፡፡

4. መስራቾች
ማህበሩ ሲመሰረት እጅግ ቢያንስ አምስት ማህበርተኞች አባላት ሊኖሩት ይገባል፡፡

በህግ በኩል ለመስራቾች የሚባሉት ማህበሩሚመሰረትበትን ጹሁፍ ፈረሙና በሙሉ የማህበሩ

የማህበሩን ዋና ገንዘብ ያዋጡ ናቸው፡፡

እንዲሁም ሚቋቋመው ማህበር አክስዮን በግልፅ ለህዝብ እንዲሸጥ የወጣ በሆነ ጊዜ የማህበሩን

መግለጫ የሚፈርሙት ለማህበሩ በውይይት መዋጮ የሚያደርጉ ወይም

ከትርፍ ላይ ልዩ ተካፋይነት እንዶኖራቸው መብት ያላቸው ሁሉ መስራቾች ይባላሉ፡፡

በማህበሩ ያልገቡ ማንኛዎችም ሰዎች ማህበሩ መቋቋም እንዲፀና ሲሉ ማንኛውም እርምጃና ለማህሩ

ስራ ያደረጉ ሁሉ እንደመሰራቾች ይቆጠራሉ፡፡

5. መስራቾች ገቡበት ግዴታዎች፡-

ማህበሩ ለማቋቋም ሲሉ ለገቡባቸው ግዴታዎች መስራቾቹ ለሶስተኛ ወገኞች በአንድነትና ሳይከፋፈል

ያለወሰን ሀላፊዎች ናቸው፡፡

ይህ ሀላፊነት ማህበሩ ለንግድ መዝገብከመመዝገቡ በፊት ስለ ማህበሩ ሆነው በሰሩት ሰዎችም ላይ

ይሆናል፡፡

6. የመስራቾች ኃላፊነት

መሰራቾች ለማህበሩና ለሶስተኛ ወገኖች ባንድነት ላይከፋፈል ከዚህ በታች በተመለከተቱት ምክንያቶች

ለሚደርሱት ጉዳቶች ኃላፊ የሚሆኑት


የውይይቱ ርዕስ፡- የሁለገብ ኢንዱስትሪ ፓርኮችን ለማልማትና ለማስተዳደር የአተገባበር መመሪያ

በክልሉ የማምረቻና ማቀነባበሪያ ኢንዱስትሪውን ዘርፍ ለማስፋፋት የኢንዱስትሪ መሰረተ ልማቶችን

በተቀናጀ መልኩ በመገንባት በዘርፉ ለተሰማሩና ለሚሰማሩ ባለሀብቶች ተደራሽ በማድረግ ለልማቱ ምቹ

ሁኔታዎችን የሚፈጥር ተቋም ማደራጀት አስፈላጊ በመሆኑ የአብክመ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት

ኮርፖሬሽን በመስተዳደር ምክር ቤቱ በደንብ ቁጥር 143/2008 ተቋቁሞ ወደ ስራ እንዲገባ ተደርጓል፡፡

ለኮርፖሬሽኑ ከተሰጠ ዋና ዋና ተግባርና ኃላፊነቶች መካከልም የሁለገብ ኢንዱስትሪ ፓርኮችን በማልማት

መሬት ለባለሀብቶች ማቅረብና በዘላቂነት ማስተዳደር ይገኝበታል፡፡

በመሆኑም ኮርፖሬሽኑ በአፈፃፀም ሂደት ያጋጠሙትን ችግሮች በመፍታት ተቋማዊ ተልዕኮውን በአግባቡ

ለመወጣት ይችል ዘንድ የሚከተሉት የአሰራር መመሪያዎች እንዲወርዱ ተደርጓል፡፡

 በነባርም ሆነ በአዲስ በተከለሉ የሁለገብ ኢንዱስትሪ ፓርኮች በተለይ በታላላቅ ከተሞች ያለውን

ከፍተኛ የመሬት አቅርቦት ችግር የምንፈታበት አንዱ አማራጭ በየከተሞች ባለፉት ጊዜያ ለኢንዱስትሪ

ኢንቨስትመንት ቦታ ተረክበው አስፈላጊው ድጋፍ ተደርጎላቸው ወደ ልማት ሊገቡ ባልቻሉ ባለሀብቶች ላይ

መሬት የማስመለስ እርምጃ በመውሰድ ነው፡፡ በመሆኑም ኮርፖሬሽኑ በነባርም ሆነ አዲስ ሁለገብ

ኢንዱስትሪ ፓርኮች ወደ ልማት ሊገቡ ያልቻሉ ባለሀብቶችን በመለየትና በራሳቸው ጥፋት ያልሰሩ

መሆናቸውን በመለየትና ከንግድ ኢንዱስትሪና ገበያ ልማት መምሪያ ወይም ጽ/ቤት ጋር

 በመመካከር እንዲነጠቅ መወሰንና የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ በማምከን መሬቱን ለሌሎች ልማታዊ

ባለሀብቶች እንዲያስተላልፍ ከዚህ አኳያ ኮርፖሬሽኑ ባለሀብቱ ባለማልማት


 በሁለገብ ኢንዱስትሪ ፓርኮች የሚመለመሉ ፕሮጀከቶች የመሬት መጠን ውሳኔ አልፎ አልፎ ችግሮች

የሚስተዋልበት በመሆኑ ከዚህ ጋር በተያያዘ በቀጥታ ከተማ አስተዳደሩ ከሚላኩ ፕሮጀክቶች መካከል

ኮርፖሬሽኑ ጉልህ ችግር አለባቸው ብሎ ባመነባቸው ላይ እስፈላጊውን ማስተካከያ እያደረገ

እንዲያስተናግድ፡፡ ይህን ተግባር ለማስፈፀምም ለሚመለመሉ ፕሮጀክቶች ፕሮፖዛል ሰነድ ፕላንት ሌይ

አውት እና ሌሎች አስፈላጊ መረጃዎች ከተማ አስተዳደሮች ከተመለመሉ ፕሮጀክቶች ዝርዝር ጋር ተያይዞ

ለኮርፖሬሽኑ እዲላ

 በሁለገብ ኢንዱስትሪ ፓርኮች የገቡ የኢንዱስትሪ ፕሮጀክቶች ነባር ይዞታ ማረጋገጫ ካርታዎችን

በማስመለስና በማምከን አዲስ የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ እንዲሰጥ እንዲሁም ከመሬት አጠቃቀም አኳያ

በተለይ ከፍተኛ ብክነት በሚስተዋልባቸው ነባር የሁለገብ ኢንዱስትሪ ፓርኮች የሚገኙ የተቆራረጡ እና

ራሳቸውን ችለው ሊለሙ የማይችሉና ለሌላ አገልግሎት የማይውል መሬቶችን አስፈላጊነቱን

በመገምገም ለትክክለኛው አልሚ በማካተት የባለሀብቱን የመሬት እጥረት በመፍታት ውጤታማ

የመሬት አጠቃቀም ስርዓት ተግባራዊ ማድረግ

የውይይቱ ርዕስ፡- ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽኑ በሚያስተዳድሩቸው ሁለገብ ኢንዱስትሪ

ፓርኮች የገቡ የኢንዱስትሪ ፕሮጀክቶችን አፈፃፀም መሰረት በማድረግ የሚወሰድ እርምጃዎች

የአብክመ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ኮርፖሬሽን ስራ አመራር ኮሚቴ ታህሳስ 2/2010 ባደረገው ስብሰባ በሁለግ

ኢንዱስትሪ ፕርኮች የገቡ ፕሮጀክቶችን አፈፃፀም መሰረት በማድረግ ተቋሙ በሚያስተዳድራቸው

ሁለገብ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ረጅም ጊዜ ወደ ልማት ሊገቡ ባለመቻሉ ፕሮጀክቶች ላይ መወሰድ

የሚገባውን የማስተካከያ እርምጃ በሚመለከት የሚከተሉትን ውሳኔዎች አሳልፈዋል፡፡

1. መሬት የሚነጠቁ

 እስከ 2008 ዓ.ም መሬት ወስደው ምንም አይነት ግባታ ያልተጀመረበት ባዶ ቦታ


 በ 2007 ዓ.ም መሬት ወስደው ቶፕ ታይ ቢም አስሮ ብሎኬት ያልደረደረ ማንኛውም አይነት

ግንባታ

 2006 ዓ.ም መሬት ወስደው በህንፃ ሹም በፀደቀላቸው ዲዛይን መሰረት አንድም አይነት

የፋብሪካ መትከያ ህንፃ/ሸድ ካልገነቡ

 በ 2005 ዓ.ም እና በፊት መሬት ተረክበው ወደ ማምረት ያልገቡ ፕሮጀክቶች

 መሬቱን በመያዝ ብቻ ሲባል ከህንፃ ሹም የግንባታ ዲዛይን አፀድቀው ሳያፀድቁ

2. ማስጠንቀቂያ የሚሰጣቸው

 በ 2006 ዓ.ም መሬት ተረከረበው አንድ እና በላይ የማምረቻ ህንፃ ያጠናቀቁ

 በ 2006 ዓ.ም እና በኳላ መሬት ተረክበው ግንባታ በማጠናቀቅ ከታለመለት ዓላማ ውጭ እየተጠቀው

ያሉ ባለሀብቶች

 በየትኛውም ጊዜ መሬት ተረከረበው ግንባታ አጠናቀው ማሽነሪ ወይም ማሽን ተከላ ላይ ያሉ

 በ 2007 ዓ.ም መሬት ወስደው ብሎኬት የደረደሩና ግንባታ ያጠናቀቁ

 በህንፃ ሹም በፀደቀላቸው ዲዛይን መሰረት የሚፈለግባቸውን የብሎኬት መጠን ሳይገነቡ እያመረቱ

ያሉ ባለሀብቶች ግንባታ በፀደቀው ዲዛይን መሰረት በማጠናቀቅ በአንድ አመት ጊዜ ውስጥ በሙሉ

አቅማቸው እንዲያመርቱ ይህን ካልፈፀሙ አሁን እያመረቱ ካለው የይዞታ መጠን ውጭ ያለው መሬት

ተቀንሶ ወደ መሬት ባንክ እንዲገባ ተወስኗል፡፡


-
የውየይቱ ርዕስ፡ የኢንቨስትመንት ፈቃድ አሰጣጥና ተያያዥ ጉዳዮች፣

ደረጃ ስለሚያስፈልጋቸው ፕሮጀክቶች የኢንቨስትመንት ፈቃድ አሠጣጥ

ከዚህ ፕሮጀክት በባህሪያቸው ደረጃውን ለማግኘት የሚያስፈልጉ የካፒታል ዕቃችን ቀድመን መሟላት ያስፈልጋቸዋል፡፡

በመሆኑም ባለሀብቱ አሟላዋከሁ በሚል ደረጃ ኢንቨስትመንት ፈቃድ ልንሰጠውና የካፒታል ዕቃዎችን ከቀረፅ ነፃ እንዲያስገባ

ሊደረግለት ይገባል፡፡ በመሆኑም በዚህ ኢንቨስትመንት መስኮች መሰማራት የሚገቡ ባለሀብቶች ደረጃውን ቀድመው

እንዲያሟሉ መጠየቅ የለብንም፡፡

ለመንገስት፣ለሀገር ውስጥ ባለሀብቶና ለውጭ ባለሀብቶች ስለተከለሉ የስራ መስኮች፡-

 በመንግስት ብቻ የሚካሄዱ የስራ መስኮች

 በብሄራዊ ዋና ዋና መስኮች /መስመሮች/የኤሌክትሪክ ሀይል ማስተላለፍና የማሰራጨት ስራ

 ፈጣን የፖስታ አገልግሎትን ሳይጨምር የፖስታ አገልግሎት

የሀገር ውስጥ ባለሀብቶች የተከለሉ የሥራ መስኮች

 የባንክ፣የኢንሹራንስና አነስተኛ የብድርና ቁጠባ ተቋም ስራዎች

 ዕቃዎችን የማሸግመ፣የማስተላለፍና የመረከብ ውክልና አገልግሎቶች

 የብሮድካስቲንግ አገልግሎት

 የብዙሀን መገናኛ ስራዎች


 የጥብቅናና ህግ ማማከር አገልግሎት

 የማስታወቂያ፣የፕሮሞሽንና የትርጉም ስራዎች

 እስከ 50 መንገዶች የመጫን አቅም ያለው የአየር ትራንስፖርት አገልግሎት በአጠቃላይ ለመንግስና ለሀገር ውስጥ

ባለሀብቶች ከተከለሉ የስራ መስኮች ውስጥ በሁሉም የስራ መስክ መሰማራት ይቻላል፡፡

1. አዲስ የኢንቨስትመንት ፈቃድ


በራሳቸውና በማስተዋወቅ የሚመጡ አዲስ ባለሀብቶች ፈቃዳቸው በኢንቨስትመንት አዋጅ መሰረት የተሰረዘባቸውና
የአንድ አመት የቆይታ ጊዜ ያላቸውን ጨርሰው ድጋሚ ፈቃድ የሚያወጡ በሚቀርባቸው ቅድመ ሁኔታዎች ላይ

የማማከር ድጋፍ ማድረግ ማበረታቻ በሚገኙባቸው ዘርፎች እንዲያውቁ ማድረግ በየ 3 ወሩ ሪፖርት ማድረጊያ ፎርም

2. ማስፋፊያ የኢንቨስትመንት ፈቃድ


እንደ ኢንቨስትመንቱ አይነት በኢንቨስትመንት አዋጁ መሰረት በአይነት/በመጠን 50 ፐርሰንት/100 ፐርሰንት
ሲያሳድጉ ማስፋፊያ ፈቃድ ይሰጣቸዋል
4. ትክ የኢንቨስትመንት ፈቃድ
 ፈቃድ ጠያቂዉ ግለሰብ ከሆነ የመታወቂያ ካርድ 2 የቅርብ ጊዜ ፎቶ
 ድርጅት ከሆነ የመመስረቻ ጽሁፍ የመተዳደሪያ ደንብ የማህበሩ ስራ አስኪያጅ ጉርድ ፎቶ
 ተወካይ ከሆነ ከሙስና ማረጋገጫ ሰነድ ፎቶግራፍ
 ጠያቂዉ ሞግዚት ከሆነ የቤተዘመድ ጉባኤ ወይም ጽ/ቤት ዉሳኔ ማስረጃ

 የኢንቨስትመንት ፈቃድ ወስደዉ ለተለያዩ ምክንያቶች የተከሰሰ ወይም የጠፋበት ባለሀብት


ፈቃድ ሰርተፊኬት እንደሰጠ መጀመሪያ ፈቃድ ከወሰደበት ጥያቄ ስናቀርብ በጥያቄዉ መሰረት
በፊት ያለዉ ምንም ለዉጥ ፈቃድ ይሰጣል፡፡
ማስፋፊያ ፈቃድ የሚሰጠዉ
ማንኛዉም የኢንቨስትመንት ማስፋፊያ ፈቃድ የሚጠይቅ ባለሀብት አዲስ ኢንቨስትመንት
ፈቃድ ለማሰጠት የሚያስፈልገዉ መስፈርት በተጨማሪ የነበረ ድርጅቱ የማስፋፊያ ፈቃድ
ይሰጠዋል፡፡

-
የውየይቱ ርዕስ፡ የኢንቨስትመንት ፈቃድ አሰጣጥና ተያያዥ ጉዳዮች፣
የውይይቱ ርዕስ፡- የሁለገብ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማትና አስተዳደርን ለመወሰን የወጣ መመሪያ ቁጥር 4/2009

በሁለገብ የቦታ መጠን አወሳሰን ኢንዱስትሪ ፓርክ ውስጥ መሬት እንዲሰጠው ጥያቄ የሚያቀርብ ባለሀብት የሚሰጥ
የቦታ መጠን የሚወሰነው ባለሀብቱ ከካፓኒው በፕሮፎርም ያቀረበውን የፋብሪካውን ፕላንት ሌይ አውት እና የፕሮጀክት
ሃሳብ ዝርዝር በመገምገም ይሆናል፡፡
መሬት ስለማስተላለፍ
 በሁለገብ ኢንዱስትሪ ፓርክ በተከለለ ቦታ መሬት ለባለሀብት የሚተላፈው በተቻለ መጠን የመንገድ፣የውሃና
የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት ከተሟላለት በኋላ ነው፡፡
 መሬት የሚተላለፍለት ባለሀብት በሚቀርብበት ዲዛይንና ስራ ዝርዝር መሰረት በራሱ ወጪ መሰረተ ልማት
ለማሟላት ፈቃደኛ ከሆነ ማስተላለፍ ይችላል፡፡
በሁለገብ ኢንዱስትሪ ፓርኩ የኢንዱስትሪዎች የቦታ አደረጃጀት
 በሁለገብ ኢንዱስትሪ ፓርኮች አንድ አካባቢ የሚመደቡ ኢንዱስትሪዎች ተመሳሳይነት ያላቸው ወይም የግብአት እና
የምርት ውጤት ቅብብሎሽ ያላቸው ሊሆኑ ይገባል፡፡

 አንድ ከተማ ከአንድ በላይ የኢንዱስትሪ ፓርክ ሳይቶች ካሉት ከፍተኛ ብክለት ያላቸውንና በተነፃፃሪ ዝቅተኛ ብክለት
ያላቸውን በመለያት የሚያሰፍርበትን አሰራር ሊከተል ይገባል፡፡

 በሁለገብ ኢንዱስትሪ ፓርክ ውስጥመሳሳይነት ወይም ግንኙነት የሌላቸው ኢንዱስትሪዎች በአንድ ቦታ መመደበ፡፡

 የብክለት ማከሚያ ማቋቋምና መልስ መጠቀም እንደተጠበቀ ሆኖ ከፍተኛ ጭስና ብናኝ ያላቸውን ኢንዱስትሪዎች
ከነፋስ አቅጣጫ በተቀራኒጫፍ መሆን ያለባቸው ሲሆን ከፍተኛ ፍሳሽ የሚለቁ ኢንዱስትሪዎች ደግሞ እንደ ባህሪያቸው
በፐርኩ መደራጀት አለባቸው፡፡

 የሁለገብ ኢንዱስትሪ ፓርክ ቦታ ዝግጅት በኢንዱስትሪ ልማት ስትራቴጅ ትኩረት ከሚሰጣቸው የኢንዱስትሪ ዘርፎች
ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ባላቸው ሰፋ ያለ ቦታ ድርሻ እንዲይዝ የሚደረግ ሆኖ በአካባቢው እንዳለው የኢንዱስትሪ ፍሰትና
የአካባቢው የሀብት መሰርት እየታየ በሁለገብ ኢንዱስትሪ ፓርክ ውስጥ በእየሰንዳንዱ የኢንዱስትሪ ንዑስ ዘርፍ

የሚዝዘው የበ 0 ታ ድርሻ ዝቅና ከፍ ሊል ይችላል፡፡

 በሁለገብ ኢንዱስትሪ ፓርኩ ውስጥ ቦታ የሚሰጠው ለመሬት መሸራተት፣ለአፈር መሸርሸር፣ለከፍተኛ ኤሌክትሪክ


ተሸካሚ መስመር የሚያርፍባቸውና ሌሎች ፋብሪካዎችን ለአደጋ ሊያጋልጡ ከሚችሉ ችግሮች የራቁ መሆን
አለባቸው፡፡

የውይይቱ ርዕስ፡- የአካባቢ ልማት ፕላን ትርጓሜና ይዘት

1. የአካባቢ ልማት ፕላን በስትራቴጅያዊ አካባቢዎች ላይ በማተኮር አንድን የከተማ ክፍልን ለማሻሻል፣ለማደስና
ለማስፋፋት በመካከለኛ የዕወቅድ በጊዜ እየተከፋሉና እየተቀናጁ የሚከናወኑ የልማት ስራዎችን የሚያሳይና የከተማውን
መዋቅራዊ ፕላን ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችል ህጋዊ ተፈፃሚነት ያለው የከተማ ፕላን ነው፡፡

2. የአካባቢ ልማት ፕላን የከተማውን መዋቅራዊ ፕላን ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችሉ ዋና ዋና ተግባራትን የልማት
ግቦችን ማስፈፀሚየሳ ስልቶችን፣የፈፃሚ አካላት ሚናን፣ተፈላጊ ተቋሞችን፣የአካባቢ ኢኮኖያዊ እንቅስቃሴን፣የከተማ
ዲዛይን መርሆዎችን፣ተጨባጭ መስፈርቶችን፣የአካባቢን መሀቀፍ፣በጀትና ጊዜን በዝርዝር የሚያይ ይሆናል፡፡

3. ማንኛውም የአካባቢ ልማት ፕላን እንደየአግባብነታቸው የሚከተሉትን መያዝ ይኖርበታል፡፡


 የመሬት አጠቃቀም አይነት ዞናዊ አመዳደብ የህንፃ ከፍታና የጥግግት መጠን

 የአካባቢ መንገዶችና ዋና ዋና የመሰረት ልማት አውታሮች

 የትራንስፖርት ስርአቱን አደረጃጀት

 የቤቶችን አይነትና የመደሮችን አደረጃጀት

 የከተማ ማደስ ማሻሻልና እንገና መደልደል የሚጠይቁ የከተማውን አካባቢዎች

 አረጓዴ ቦታዎችን፣ክፍት ቦታወፖችን ውሃ አካላትንና እንዲሁም ለጋራ አገልግሎት ሊውሉ ሚችሉ ቦታዎችን

 አግባብነት ያለውን ሌሎች የአካባቢ ፕላን ነክጉዳዮችን

4. የአካባቢ ልማት ፕላን ለአፈፃፀሙ አስፈላጊ የሆኑትን ተቋማዊ አደረጃቶች ሀብትና የመቆጣጠሪያ ድንጋጌዎች ያካተተ
ዝርዝር የአፈፃፀም ዕቅድ ይኖረዋል፡፡

5. የማስፈፀሚያ ጊዜ
የአካባቢ ልማት ፕላን ተፈፃሚ የሚደረገው መዋቅራዊ ፕላን ፀንቶ በሚቆይበት ጊዜ ውስጥ ይሆናል፡፡

6. የከተማ ፕላኖችን ስለማመንጨት

 መሟላት የሚገባቸው ፍላጎቶች ተለይተው ከመታወቃቸው አስቀድሞ ማናቸው የከተማ ፕላን ዝግጅት
መጀመር የለበትም

 የሚመለከተው ማንኛውም መንግስታዊም ሆነ መንግስታዊ ያልሆነ አካል በከተማ ፕላን ዝግጅት ወቅት
ሊታይና ሊሟላ ይገባል

 የዚህ አንቀፅ ንዑስ አንቀፅ 2 ድንጋጌ እንደተጠበቀ ሆኑ የከተማ ፕላን የማመንጨት ሂደት ሊጀምር ሚችለው
በሚመለከታቸው ቻርተር ባላቸው ከተሞችና የተማ አስተዳሮች የክልልና የፊደራል አካላት አማካኝነት
ይሆናል፡፡

7. የከተማ ፕላኖችን የማዘጋጀትና የመከለስ ስልጣንና ተግባር


በማንኛውም ደረጃ ላይ የሚገኙ ከተሞች መዋቅራዊና የአካባቢ ፕላኖቻቸውን የማዘጋጀትና

የመከለስ/የተመሰከረላቸው የግል/የመንግስት ተቋማት እንዲዘጋጅላቸው እንዲከለስላቸው የማድረግ ስልጣንና ተግባር


አላቸው፡፡ ዝርዝሩ በህግ ይወሰናል፡፡
ውይይቱ ርዕስ፡- የሁለገብ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት እና አስተዳደር መመሪያ ቁጥር 4/2009
1.መካከለኛ ደረጃ ያላቸው ግንባታዎች
 የውጭ ግምታቸው እስከ 5,000,000 የሆኑ
 የይዞታ ስፋታቸው እስከ 5000 ካ/ሜትር
2. ከፍተኛ ደረጃ ያላቸው ግንባታዎች
 የውጭ ግምታቸው እስከ 5,000,000 የሆኑ
 ስፋቱ እስከ ከ 5001 ካ/ሜትር በላ የሆነ
የግንባታ መጀመሪያ ደረጃ ጊዜ የግንባታ ፈቃድ የሚሰጥበት ጊዜ ውል ከተፈፀመበት ጀምሮ
 ለመካከለኛ ግንባታ 3 ወር
 ለከፍተኛ ግንባታ 6 ወር
የግንባታ መጀመሪያ ጊዜ ጣሪያ ግንባታ ፈቃድ ከተወሰደበት
 ለመካከለኛ ግንባታ አስከ 2 ወር
 ለከፍተኛ ግንባታ እስከ 4 ወር
ከአቅም በላይ የሆነ ችግር ሲያጋጥማቸው
 ለመካከለኛ የ 3 ወር
 ለከፍተኛ የ 6 ወር ግንባታ መጀመሪያ ሊራዘም ይችላል
ግንባታን ስለማጠናቀቅ
መሬት ከተረከበበት ጊዜ ጀምሮ
 ለመካከለኛ ግንባታ 24 ወራት
 ለከፍተኛ ግንባታ 36 ወራት

የክላስተር ማዕከላት እና ሸድ ልማት፣አጠቃቀምና አስተዳደር መመሪያ ቁጥር 5/2009

 ክላስተር ማዕከላት ለአነስተኛና መካከለኛ ኢንዱስትሪዎች ለ 5 አመት በኪራይ ይተላለፋል


 ለባለሀብት በሚቀርበው ፕሮጀክት ሰነድ መሰረት በማወዳደር ከ 10-15 አመት ሊከራይ ይችላል
የሸድ ተጠቃሚዎች መመልመያ መስፈርት

1. የስራ ዕድል ፈጠራ 40 ነጥብ

2. የወጭ ምርት 20 ነጥብ

3. የኀኋሎዮሽና የፌትዮሽ ኢኮኖሚያዊ ቸፈ\ዘቨ ቸ\


ዘዘአትስስር 15 ነጥብ

 የኋልዮሽ/የግብአት/ትስስር 13 ነጥብ
 የፊትዮሽ /የምርት/ትስስር 13 ነጥብ
 ምንም ትስስር ከሌለው 6 ነጥብ

4. የኢንቨስትመንት ካፒታል 13 ነጥብ

ከቀረቡት ውስጥ ከፍተኛውን ካፒታል ያቀረበ 13 ነጥብ

5. የቴክኖሎጅ ዕድገት አስተዋፅኦ 12 ነጥብ


 

የውይይቱ ርዕስ፡- የተጀመረውን ገጠርና ግብርና ትራንስፎርሜሽን በልዩ ትኩረት ማጠናከር


በገጠር ኢንዱስትሪያላይዜሽን ፕሮግራም የምናልመው የሀገራችንን ገተሮች የማኒፋክቸሪግ መናሀሪያ

ለማድረግና በእነዚህ ዙሪያ የሚሰባሰቡ መለስተኛ ከተሞችን ለማስፋፋት ነው፡፡ ይህን የመሰለውን የገጠር
ኢንዱስትሪያላዜሽን ስራ ለማስጀመር አስፈላጊ የሆነው የመጀመሪያ ደረጃ የካፒታል ክምችት ደግሞ

ሲጀምር ከከተሞች ሳሆን ከግብርና የሚገኝ ነው፡፡ ምንም እንኳ ኢንዱስትሪዎቹ በግብርና ላይ ተመስርተው

በተስፋፋ ቁጥር ተመልሰው የመጀመሪያ ደረጃ የካፒታል ክምችቱን ይበልጥ የሚያጎላብቱት ቢሆንም ሲጀምር

ግን የክምችቱ መነሻ ግብርና መሆኑ አይቀርም፡፡ ግብርና ለኢንዱስትሪ መስፋፋት የሚያስፈልገውን ካፒታል

ያመነጭ ዘንድ ደግሞ የምግብ ዋስትናን ከማረጋገጥ ባሻገር የሚሄድ ትርፍ ምርት ማስገኘት ማስቻል

ይኖርበታል፡፡

ይህ እንዲሆን ግብርናው ከኋላቀር አመራረት ዘዴዎች በመላቀቅ ዘመናዊ የአመራረት ስልቶችን የሚከተልና

በዋነኛነት በኮርሻል ቅኝት ሊሆን ይገባዋል፡፡

ለኢንዱስትሪና ለውጭ ገበያ የሚሆን ተጨማሪ ምርት ማምረትና ከዚህም አኳያ ገደብ የሌለው የእድገት

አድማስ ሊከፈትለት የሚገባ ሴክተር ነው፡፡ በሰብል ላይ ከፍተኛ ጭማሪ ለማስገኘት ያስቻሉንን ምርጥ

ተሞክሮዎች አጠናቅረን መቀጠል ይኖርብናል፡፡

የተፈጥሮ ሀብታችንን ጥበቃችንን ማስፋትና ውሃ ሀብታችን ማበልፀግ በእያንዳንዱ ማሳ ተጨማሪ የውሃ

ቴክኖሎጅ በመጠቀም በአመት እስከ ሶስት ጊዜ ማምረት የመሬትን ለምነት የሚጨምሩ ልዩ ልዩ ተግባራትን

ማከናወን የምርጥ ዘር የኬሚካል ማዳበሪያ የጸረ አረም መድሀኒቶች ተጠቃሚነትን ማስፋት በተየያዝነው

እድገትና ትራንስፎርሜሽን አመታትም ተጠናክረው እንዲቀፅል ማድረግ ይገባናል፡፡


በራሳችን ተጨባጭ ተግባር እንዳረጋገጥነው እነዚህ አሁን በማስመዝገብ ላይ ያለው የግብርና እድገት መነሻ

ምንጮቻችን ናቸው፡፡የሰብል ምርትና የአርሶ አደር ጥሬ ጉልበት የግብርና መነሻ የእድገት ምንጭ ሆነው

ሲያገለግሉ ከቆዩ በኋላ አስተፅኦ እየቀነሰ መሄድ ሲጀምር በተተኪነት የግብርና እድገት ምንጮች የሚሆኑት

እንደ አትክልትና ፋራፍሬ የእንስሳት ተዋፅኦ ምርቶችና የግብርና ሜካናይዜሽን እንደሚሆኑ የብዙ ሀገሮች

ልምድ የሚያረጋግጠው ነው፡፡

የውይይቱ ርዕስ፡-መሰረታዊ የካይዘን ቴክኒኮች

ሙሪ/muri/ሙራ /mura/

ሙሪ/muri/

የሚለው ቃል ጃፓነኛ ሲሆን ሰውን ጨምሮ እንስሳትንም ሆነ ማሽኖችን ከአቅም በላይ በማሰራትና
በማስጨነቅ ጫና የሚያደርስ አሰራር ነው፡፡ ማንኛውም አምራች ሀይል የማምረትና የመንቀሳቀስ አቅሙ
ውስን ነው፡፡ከአቅሙ በላይ እንዲቀሳቀስ ከተደረገ ህይወት ያለው አምራች ለበሽታና ለሞት ቁስ አካል
ደግሞ ለብልሽት ይዳረጋል፡፡ሙሪ የሚፈጠርባቸው በርካታ መንስኤዎች ቢኖርም የስራ ጫና እና የሰራተኛ
አለመጣጠም ለስራው የተመደበው በጀት አነስተኛ መሆን ለሰራተኞች የሚመች አቋቋም ጠነካራ ስራ ቦታ
ደህንነት አለመኖር ጥራታቸውን የጠበቁ መለዋወጫዎች አለመኖር የአቅርቦት እጥረትና መጓተት
እንዲሁም የንድፍ ወይም የዲዛይን ግድፈቶች ይጠቀሳሉ፡፡

በታዳጊ ሀገሮች የሚገኙ ማምረቻዎች ጥራትን በሚፈለገው ደረጃ ለማሻሻል የካፒታልና ቴክኖሎጅ
አቅማቸው ዝቅተኛ መሆኑ ይታወቃል፡፡ የተሟላ አሰራርና አደረጃጀት በመፍጠር ጥራቱ የተሟላ ምርት
ማምረት ወጪን ይቀንሳል እንጂ አያበዛም፡፡

ይልቁንም ወጪ የሚበዛው በሙሪ የተነሳ በየጊዜው የማሽኖች ብልሽት እየተፈጠረ ለጥገና ወጭ ሲወጣ
ነው፡፡ ከዚህ አንፃር ምርትን ለመቸመር እና ትርፋማ ለመሆን በሚል የተሳሳተ አመለካከት በሰውም ሆነ
በማሽኑ ላይ ጫና መፍጠር ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ ያመዝናል፡፡

ሙራ mura

ሙራ/mura/ እንደሙዳ እና ሙሪ ሁሉ ከጃፓነኛ ቋንቋ የተወሰደ ቃል ነው ትርጉሙም በሰውም ሆነ


በማሽን ላይ ያልተመጣጠነ የስራ ክፍፍል ማድረግ ነው፡፡ በአሰራር ላይ ያልተመጣጠነ የስራ ክፍፍል
ያልተመጣጠነ የማሽን አቅምና የተለያየ የግብዓት አቅርቦት እንዲሁም ወጥ ያልሆነ የስራ ክፍፍል
ይስተዋላል፡፡ ይህም የሚፈጠረው ለሰራተኛው በቂ ስልጠና አለመስጠት፣በቂ የእቃ መለዋወጫዎች
አለመኖር፣የግብዓት ጥራት መጓደል፣አላስፈላጊ እንቅስቃና የመገልገያ ዕቃዎችን በአግባቡ አለመጠቀም
ነው፡፡
የኢንዱስትሪ መንደር የመሰረተ ልማት አስ/ባለሙያ

የመመማር ሰነድ

-
አዘጋጅ፡ አቶ አበበ ቸኮል

ጥር 17/05/2010
የኢንዱስትሪ ዞን ልማት ቡድን መሪ

የመመማር ሰነድ

-
አዘጋጅ፡ አቶ ቸርነት አለማየሁ

የካቲት 08/06/2010
የመወያያ ርዕስ፡-የኢንዱስትሪ መንደር መመሪያ

 ኢንዱስትሪ መንደር ማለት ምን ማለት እንደሆነ የዚህ ሂደት ባለሙያ ሁሉም በይገባኛል ማወቅ አለበት፡፡

 ኢንዱስትሪ መንደር ማለት በከተማው መዋቅራዊ ፕላን/ዕድገት ፕላን መሰረትና እንደ አስፈላጊነቱ

በክልሉ በልዩ ሁኔታ ሚመረጡ አካባቢዎች ለኢንዱስትሪ አገልግሎት እንደ ውል የተመደበ ሆኖ በክልሉ

መንግስት በሚመደብ በጀት መነገድ፣ውሃ፣ኤሌክትሪክና ስልክ የተሟላለት ኩታገጠም የሆነና ቢያንስ

የሚከለለው የመሬት መጠን 20 ሄ/ር ስፋት ያለው ለኢንዱስትሪ ኢንቨስትምንት የተዘጋጀ ቦታ ነው፡፡

ኢንዱስትሪ፡-ማለት በአብዛኛው በሞተር ሃይል የሚንቀሳቀስና በከፍተኛ መካከለኛ ደረጃ ላይ ያለ

የማምረቻ፣የማቀነባበሪያና መገጣጠሚያ ድርጅት ማለት እንደሆነ ማወቅ አስፈላጊ ነው፡፡

ሁለገብ የኢንዱስትሪ ቀጠናዎች፡- ሁሉም አይነት ኢንዱስትሪዎች የሚቋቆምባቸው ሲሆን

አቀማመጣቸውም በዘርፍ የተለየ ነው፡፡ ለምሳሌ አግሮ ኢንዱስትሪ ዘርፍ፣ጨርቃጨርቅና አልባሳት

ዘርፍ፣የቆዳ ውጤቶች ዘርፍ፣የኮንስትራክሽን ዘርፍ፣ኤሌክትሮኒክስ ወ.ዘ.ተ የሚያጠቃልል ሲሆን

ሁሉም በቀጠናው ያሉ ልዩ ልዩ የመሰረተ ልማት አውታሮችንና አገልግሎቶችን የሚጠቀሙ ናቸው፡፡


ልዩ የኢንዱስትሪ ቀጠናወች ፡- ልዩ የኢንዱስትሪ ቀጠናወች የሚለሙት ኢንዱስትሪዎች ተመሳሳይ ምርት

የሚያመርቱ/በምርት የሚተሳሰሩ ናቸው፡፡ እነዚህ አይነት የኢንዱስትሪ ቀጠናዎች ለመግለፅ እንደ ጥሩ

ምሳሌ ሊወሰዱ የሚችሉት የጨርቃ ጨርቅና አልባሳት ኢንዱስትሪዎች ናቸው፡፡

አለምቀረ አሰፋ፡- በዕለቱ ለንግዛቤ ማለትም ሁላችንም የሂደቱ ባለሙያዎች በኢንዱስትሪ ትርጉም

፣ኢንዱስትሪ መንደር ምንነት፣ሁለገብ ኢንዱስትሪ ቀጠናዎችና ልዩ ኢንዱስትሪ ቀጠናዎችን

በተመለከተ የቀረበልን ማብራሪያና ገለፃ በቀለለ እና ግልፅ በሆነ መልኩ በመሆኑ እንደ እራሴ ጥሩ ግንዛቤ

አግኝቸበታለሁ፡፡

የመወያያ ርዕስ፡- የገበያ ማዕከላት ማስተላለፍና አስተዳደር


ገበያ ማዕከል፡- ማለት ምርት አቅራቢዎችና ተጠቃሚዎች የሚገበያዩበት ቦታ/ተቋም ማለት ነው፡፡

መደበኛ ገበያ፡- ማለት የሰሊጥና ነጭ ቦለቄ፣የቡና፣የእንስሳትና ቆዳ/ሌጦ መገበያያ ውጪ ለመገበያያ

የተከለለ ገበያ ማለት ነው፡፡

መደበኛ ገበያ ማቋቋም፡- ከሰሊጥና ነጭ ቦለቄ፣የቡና፣የእንስሳት ቆዳና ሌጦ ገበያ ውጪ ከዚህ በፊት መደበኛ ገበያ

በሌለበት ቦታ ላይ ገበያ ማቋቋም ነው፡፡

መደበኛ ገበያ ማሻሻል፡- ከሰሊጥና ነጭ ቦለቄ፣የቡና፣የእንስሳት ቆዳና ሌጦ መገበያያ ቦታ ውጪ ያለውን ገበያ ያለበትን

ውስጣዊና ውጫዊ ችግር በመለየት ችግሩን መቅረፍና ስርዓት ማስያዝ ነው፡፡

የገበያ አስተዳደር ኮሚቴ፡- ማለት በገጠርም ሆነ በከተማ የተቋቋመውን ገበያ ለማስተዳደር ለመምራት ከተለያየ

ተቋም/ህብረተሰብ ክፍል የተውጣጣና የተቋቋመ አካል ነው፡፡

የገበያ መሰረተ ልማት፡-

የገበያ አስፈላጊነት፡- ለአንድ አገር የኢኮኖሚ እድገት የግብርና ልማት ወሳኝ ነው፡፡ የግብርና ልማት ዕውን ሊሆን

የሚችለው ደግሞ አምራች ከዘመናዊ ገበያ ጋር ሲተሳሰር ምርቱ በገበያ ሲደገፍ እና አምራቹ ተጠቃሚ ሲሆን ብቻ ነው፡፡
በገበያ የተደገፈ የግብርና ልማት ዕውን ለማድረግ እንዲሁም የተረጋጋ የገበያ ቦታ አስተዳደር፣በቂ መገበያያ ስፍራና

ፍትሀዊ የግብይት ስርዓት እንዲኖር የገበያ ማዕከል ወሳኝ መሳሪያ መሆን የሚያጠያይቅ ጉዳይ ነው፡፡

የገበያ ማዕከል አከላልና አደረጃጀት፡

ሀ. የመጀመሪያ ደረጃ የቁም እንስሳት የግብይት ማዕከላት አከላለልና አደረጃጀት፡-

የመጀመሪያ ደረጃ የቁም እንስሳት የግብይት ማዕከላት ሲደራጁ ለአርቢው በቅርብ እርቀት ቢበዛ አስከ 12 ኪ/ሜ ቢሆን

ይመረጣል፡፡

እንደአስፈላጊነቱ ተጨማሪ የግብይት ማዕከላት ሊቋቋሙ ይችላሉ፡፡ የመጀመሪያ ደረጃ የቁም እንስሳት የግብይት

ማዕከላት ብዛትና ስርጭት ሲወሰን ከት/ቤት ከጤና ከምንነትና ሌሎች ማህበራዊ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ቢያንስ

500 ሜትር ርቀት ላይ መገኘታቸውንና ሌሎችም ለግብይት ስርዓት አመቺነት አስፈላጊ የሆነ ነገሮች ከግምት መግባት

ይገባቸዋል፡፡ የመጀመሪያ ደረጃ የቁም እንስሳት የግብይት አከላለል ግብይቱን ለማስተናገድ ያለው መስፈርቶችን

አሟልቶ መገኘት እንጂ አካባቢ አስተዳደር ወሰንን መሰረት ያደረገ መሆን የለበትም፡፡
የመወያያ ርዕስ፡- ኢንዱስትሪ መንደር መሬት ከ 3 ኛ ወገን ነፃ ለማድረግ የካሳ አከፋፈል መመሪያ፣

ኢንዱስትሪ መንደር ውስጥ በተለያዩ የኢንቨስትመንት ዘርፍ ኢንቨስት የሚያደርጉ ልማታዊ ባለሀብቶች ወደ ከተማችን

አስተዳደር ሲመጡ የመሬት አቅርቦት ችግር ከወዲሁ መቀረፍ አለበት፡፡ ስለዚህ ለኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ ወሳኝ

የሆነው መሬት ከ 3 ኛ ወገን ነፃ ለማድረግ መሰራት ያለባቸው ቅደምተከተሎች፡-

በቅድሚያ አርሶ አደሩ እየተጠቀመበት የሚገኘው መሬት ከአመት በፊት ለአ /አደሩ መሬቱ እንደሚፈለግ ሊነገረውና

የማላመን ስራ መሰራት ያስፈልጋል፡፡

የሚፈናቀለው አ/አደሩ ማሳ/መሬት በከተማ አስ/ደረጃ በተቋቋሚ የሶሽዮ ኢኮኖሚ ኮሚቴ በትክክል ልኬቱ ይፈፀማል፡፡

በተያዘው ልኬት መሰረት ግብርና በሚልከው የ 5 ዓመት የምርት ገበያ ዋጋና ምርታማነት መሰረት አ/አደሩ አስፈላጊ

መረጃዎችን እንዲሟላ ይደረግና አግባብ ያለው ተመጣጣኝ ክፍያ በመፈፀም ከ 3 ኛ ወገን ነፃ የሆነውን መሬት መሬት

ልማት ማኔጅመንት ይረከባል፡፡

ይህንን መሬት የኢንዱስትሪ መንደር ገበያ ልማት ዋና የስራ ሂደት ከመሬት ልማት ማኔጅመንት በመረከብ ያስተዳድራል፡፡

የመወያያ ርዕስ፡- የከተማ መሬትን በሊዝ ስለማስተዳደር የወጣ አዋጅ ቁጥር

721/04 በተመለከተ የከተማ መሬት በሁለት ስሪት ማለትም፡-

 በነባር ስሪት እና

 በሊዝ ስሪት የሚተዳደር ሲሆን የህዝብ ቁጥር እየጨመረ ከመሄድ እና የመሬት ዋጋ አላግባብ እያደገ (specaiation)

ጋር በተያያዘ ለከተሞች ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ በሚውል መልኩ ሳይሆን የግለሰቦች መጠቀሚያ እየሆነ በመሆኑ የሊዝ

ህግ በማውጣት ማስተዳደር አላማ አድርጎ አዋጁ ወጥቷል፡፡


 721/04 የመጀመሪያው የሀገሬቱ የሊዝ ህግ አደለም ምክንያቱም ቀደም ሲል 889/86 እና 272/94 በተለያየ ወቅት

መጥተው ለመተግበር ተሞክሯል በተለይ 272/94 ከአዲስ አበባ በተጨማሪ ሌሎች እንደ ደ/ማርቆስ በአሉ ከተሞች

በተሟላ መልኩም ባይሆን ተተግብሯል

 በአዋጅ ቁጥር 721/04 ደግሞ በነባር ስሪት የሚቀጥሉ ይዞታዎች በምደባ የሚተላለፉ መሬት እና በሊዝ

አግባብ/በጨረታ/ለተጠቃሚ የሚቀርብበት አግባብ በግልፅ ተቀምጦ እየተተገበረ ነው፡፡

በዚህም መሰረት ለምደባ፡-

 ለባለ በጀት መ/ቤት ቢሮ መገንቢያ

 ለማኒፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ

 ለህዝብ ጥቅም ሲባል ነባር ይዞታዎችን እና የቀበሌ /የመንግስት ቤት ለማለቁ ትክ የሚሰጥ

 በጥ/አ/በተደራጁ አካላት ለጊዜያዊነት የሚሰጥ ቦታዎች በምደባ አግባብ እንደሚተላለፍ ተደንግጓል፡፡

ከላይ ከተጠቀሰው ውቺ ለአሉ አገልግሎቶች መሬት ለሚመለከተው አካል እንዲለማና እንዲዘጋጅ እየተደረገ ለጨረታ

እንዲቀርብ ተደርጓል፡፡

 ቀደም ሲል የተያዘ ነባር ይዞታ ወደ ሶስተኛ አካል እስካልተላለፈ ድረስ በነባር ይዞታነት ይቀጥላል፡፡ ለነባር ይዞታ

የማጣራት ስራ የክልሉ መንግስት ባወጣው ቀደም ሲል መመሪያ 2/2005 እንዲሁም ይህ መመሪያ ተሻሽሉ መመሪያ

ቁጥር 8/2007 ወጥቶ ሰነድ አልባ ይዞታዎችን የማጣራትና ሰነድ እንዲኖራች የማድረግ ስራ እየተሰራ ነው፡፡

መጋቢት 20/2010 ዓ.ም


መወያያ ርዕስ፡- የከተማ መሬት በሊዝ ለማስተዳደር የወጣ ደንብ ቁጥር 103/04 እና መመሪያ ቁጥር 1/2005

 የሊዝ መብት ማስተላለፊያ ዋጋ ማለት ግንባታ ያልተከናወነበት/ከግማሽ በታች የተገነባ ግንባታ ያረፈበት

የሊዝ መሬት መብት ሲተላለፍ ሻጭ የገዛበት ዋጋ እና ግብይቱ በሚካወንበት ወቅት ያለው የአካባቢ ከፍተኛ
የጨረታ ዋጋ ድምር ለሁለት ተካፍሎ የሚገኝ የሒሳብ ውጤት/አግባብ ያለው አካል በደንብ በተቀመጠው

መሰረት ስምምነት የሰጠበት ዋጋ ነው፡፡

 ሰነድ አልባ ይዞታ ማለት በህጋዊ አግባብ የተያዘ /በተለያዩ የመንግስት መዋቅር እውቅና የሰጠው ይዞታ ሆኖ

አግባብ ባለው አካል የሚሰጥ የይዞታ ምስክር ወረቀት የሌለው ይዞታ ነው፡፡

 ልዩ ጨረታ ማለት በአዋጅ አንቀፅ 11/07 እና 8 ላይ የተመለከቱት ፕሮጀክቶች በጨረታ አግባብ የሚሰጡበት

የጨረታ አይነት ነው፡፡

 የከተማ ቦታ በሊዝ የሚፈቀደው፡-

ሀ/በዋናነት በጨረታና ለ/በምደባ ይሆናል፡፡

 በሊዝ የሚፈቀደው ቦታ የከተማውን መዋቅራዊ ፕላን እና ዝርዝር የአካባቢ ልማት ፕላን እንዲሁም ሌሎች

ተገቢ የሆኑ የመሬት አጠቃቀም ፕላኖችን መሰረት በማድረግ ይሆናል፡፡ ይህ ስራ ሲሰራ ወደ ተግባራዊ

እንቅስቃሴ ከመግባት በፊት ለህዝቡ ይፋ መደረግ አለበት፡፡

 ነባር የከተማ ቦታ በሊዝ ስሪት ስለማስተዳደር፡-

1. ነባር ይዞታዎች በአዋጅ አንቀፅ 6/3 መሰረት ከውርስ በስተቀር በማንኛውም መንገድ ወደ ሶስተኛ ወገን

ሲተላለፍ በሊዝ ስሪት እና መነሻ ዋጋ ይሆናል፡፡

2. ይዞታ ተላለፈለት ሰው ይዞታው አገልግሎት በከተማው መዋቅራዊ ፕላን/በአካባቢው የልማት ፕላን

መሰረት የሚወሰን ሆኖ ውል ዘመኑም በአዋጁ ለአገልግሎቱ በተወሰነው የሊዝ ዘመን መሰረት ይሆናል፡፡

3. ይዞታው አገልግሎት እየሰጠ የነበረው ለድርጅት እና ለመኖሪያ/ለድብልቅ/ከሆነ ውለታ የሚፈፀመው

በአካባቢው መዋቅራዊ ፕላን የመሬት አጠቃቀም በተመለከው መሰረት ይሆናል፡፡

4. ወደ 3 ኛ ወገን የሚተላለፉ ነባር ይዞታ ወደ ሊዝ የሚገባው በሚቀርበው ሰነድ በተመለከተ የቦታ ስፋት

መሰረት ይሆናል፡፡
5. ከዚህ በላይ በተ/ቁ 4 የተደነገገው ቢኖርም በመስክ ልኬት የተገኘው የቦታ ስፋት በሰነድ ገተገኘው ካነሰ

በመስክ ልኬት በተገኘ የቦታ ስፋት የሚወሰን ይሆናል፡፡ ሆኑም በመስክ ልኬት የተገኘው የቦታ ስፋት በሰነድ

ከተገኘው ከበለጠ በመመሪያ የሚወሰን ይሆናል፡፡

6. ቀደም ሲል ሲከፈል የነበረው አመታዊ የቦታ ኪራይ ቀሪ ሆኖ የቦታው የሊዝ መነሻ ዋጋ በቦታው ስፋት

ተባዝቶ የሚገኘው የገንዘብ መጠን ለአገልግሎቱ ለተቀመጠው የመክፈያ ጊዜ ተካፍሎ የሚገኘው ውጤት

በየአመቱ ይከፈላል፡፡

7. ገዥው የሊዝ ቅድሚያ ክፍያ እንዲፈፅም ባይገደድም የመክፈል ፍላጎት ካለው ከጠቅላላው የሊዝ ክፍያ

የሚታሰብ ቅድሚያ ክፍያ አግባብ ላለው አካል የመፈፀም መብት አለው፡፡

8. ከዚህ በላይ በተ/ቁ 7 መሰረት ባለመብቱ የቅድሚያ ክፍያ በመፈፀም የችሮታ ጊዜ እንዲሰጠው ጥያቄውን

በፁሁፍ ካቀረበ የ 2 አመት የችሮታ ጊዜ ይፈቀድለታል፡፡

9. የሊዝ ዘመኑ መቆጠር የሚጀምረው የሊዝ ውል ከተፈረመበት ጊዜ ጀምሮ ይሆናል፡፡

10. የቤቱ ስፋት ከቦታው ስፋት ምጣኔ የክፍፍል ድርሻ ተሰልቶ በሚሰጥ የንብረት ባለቤትነት ማረጋገጫ

ደብተር የተያዙ ንብረቶች ከውርስ በስተቀር ወደ 3 ኛ ወገን ሲተላለፉ በጋራ ግቢው የክፍፍል ምጣኔ ድርሻ

ላይ የተናጠል ተጠቃሚነቱ እስካልተረጋገጠ ድረስ ቤቱ ብቻ በሊዝ አግባብ ይስተናገዳል፡

የውይይት ርዕስ፡- የኢንቨስትመንት አዋጅ

 የኢንቨስትመንት/ማሻሻያ/አዋጅ ቁጥር 849/2006

 የኢንዱስትሪ ልማት ቀጠና ማለት የኢንዱስትሪ ዕድገትን የአካባቢ ብክለት ተፅዕኖ መቀነስንና የከተሞች እድገትን

በዕቅድና በስርአት የመምራት አበይት አላማዎች የያዘ ሆኖ ዕቅድን መሰረት አድርጎ እንደ መንገድ፣ኤሌከትሪክ፣ውሃ

የመሳሰሉት አስፈላጊ መሰረተ ልማቶችና የተለያዩ አገልገሎቶች ተሟልተውለትና ልዩ የማበረታቻ ዕቅድ ኖሮት

አንድ አይነት/ተመሳሳይ/ተመጋጋቢ ያላቸው ኢንዱሰትሪዎችን በስብስብ ለማልማት/ሁለገብ ኢንዱስትሪዎችን

ለማልማት የሚቋቋም ድንበር የተበጀለት አግባብ ባለው አካል የሰየመ የተወሰነ ቦታ ሲሆን ልዩ የኢኮኖሚ

ቀጠና፣የኢንዱስትሪ ፓርክን፣የቴክኖሎጂ ፓርክን፣የኤክስፖርት ማቀነባበሪያ ቀጠና፣ነፃ የንግድ ቀጠናንና

በኢንቨስትመንት ቦርድ የሚወሰኑ የመሳሰሉትን ይጨምራል፡፡

 በዚህ አዋጅ ውስጥ በማናቸውም ስፍራ/ኤጄንሲ/የሚለው ስያሜ ተሰርዞ /ኮሚሽን/በሚለው ተተክቷል፡፡


የውጪ ባለሀብት ማለት፡- የውጪ ካፒታል ወደ ኢትዮጵያ በማስገባት ኢንቨስት ያደረገ የውጪ ሀገር ዜጋ /ሙሉ

በሙሉ በውጪ ሀገር ዜጋ ባለቤትነት የተያዘ ድርጅት /ሀገር ውስጥ ባለሀብት ጋር በቅንጅት ኢትዮጵያ ውስጥ

በተቋቋመው ድርጅት ኢንቨስት ያደረገ የውጪ ሀገር ዜጋ/ድርጅት ሲሆን እንደ ውጪ ባለሀብት መቆጠር የፈለገ

መደበኛ ኗሪነቱ በውጪ ሀገር የሆነ ኢትዮጵያዊ ይጨምራል፡፡

የውጪ ካፒታል፡- ማለት ከውጪ ምንጭ የተገኘ ካፒታል ሲሆን በውጪ ባለሀብት ወደ ካፒታል የተለወጠ ባሀገር

ውስጥ የተገኘ ትርፍና የትርፍ ድርሻን ይጨምራል፡፡

ማስፋፋት/ማሻሻል/፡- ማለት ሊደረስበት የሚችል የነባር ድርጅትን የማምረት/አገልግሎት የመስጠት አቅም

ቢያንስ ፶ በመቶ በመጠን ማሳደግ/ነባር ድርጅትን አዲስ የማምረቻ/አገልግሎት መስጫ መስመር

በመጨመር/አገልግሎትን/ሁለቱንም ማሳደግን ይጨምራል፡፡

የቴክኖሎጅ ሽግግር፡- ማለት ምርትን ለማምረት/የአመራረት ሂደትን ተግባራዊ ለማድረግ/ለማሻሻል/አገልግሎት

ለመስጠት የሚረዳ ስርዓት ያለው ዕውቀት ማስተላለፍ ሲሆን የስራ አመራርና የቴክኒክ ዕውቀት እንዲሁም

ግብይት ሁኔታ ቴክኖሎጅንም ይጨምራል፡፡ሁኖም እቃዎችን ከተቻለ መሸጥ/ለማከራየት የሚደረግን ግንኙነት

አይሸፍንም፡፡
የመወያያ ርዕስ፡- የከተማ መሬትን በሊዝ ለማስተዳደር ከወጡ መመሪያዎች መካከል የስመ ንብረት ዝውውር

መመሪያ ቁጥር 4/2006/ላይ ውይይት ማካሄድ ነው

የስመ ንብረት ዝውውር ለመፈፀም መሟት ያለባቸው መስፈርቶች፡-

 የይዞታ ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት/ካርታ

 የግንባታ ፕላን፣የስራ ዝርዝር ግምት/የፀደቀ የነባር ግንባታ ፕላን

 በፕላኑ መሰረት ስመ ንብረቱ ግምትና ግንባተው ያለበት ሁኔታ

 ውዝፍ የሊዝ የኪራይ ዕዳ የሌለበት

 የባንክ ዕዳ/የፍ/ቤት ዕግድ የሌለበት እንዲሁም የገቡዎች ዕዳና ዕግድ የሌለበት

 በግለሰቦች ግዥና ሽያጭ/ስጦታ ስምምነት በስመ ንብረት ዝውውር ባለሙያ ፊት ያፈፀማል፡፡

 ከይገባኛል ነፃ ስለመሆኑ በከተማ/በቀበሌ ደረጃ ለ 5 የስራ ቀናት በማስታወቅያ ይገለፃል፡፡

በሽያጭ/በስጦታ ለማስተላለፍ

 በተሰጠው ዲዛይን መሰረት 50 በመቶና በላይ የተሰራ

 በንብረት ግምት ላይ የንብረት ክፍያ ለገቢዎች ሲፈፀም

የመወያያ ርዕስ፡- የስመ ንብረት ዝውውር መመሪያ ቁጥር 4/2006 የቀጠለ

 የኮንደሚኒየም/የአክሲዎን የጋራ ህንፃ ቤት ስመንብረት ዝውውር ለመፈፀም


 ቤቱ ለመጀመሪያ ለተጠቃሚ የተላለፈበት ዋጋ/

 የተሸጠው ክፍል ቤት የግባታ ዋጋና በግለሰቡ ግንባታ ማሻሻያ ዋጋ

 ቤቱ በሚገኝበት ፍሎር ውስጥ የተሸጠ ሌላ ቤት ግምትን ለማነፃፀር ለስመ ንብረት ዝውውር

አገልግሎት የቤት ግምት የሚሰላ ይሆናል፡

 ክፍያዎችን በተመለከተ የከተማ አገልግሎት ክፍያ ከውርስ ውጪ ግዥና ሽያጭ ሌሎች ከአባት/ከእናት

ወደልጅና ከልጅ ወደአባት/እናት ውጪ ሁሉም 3 ፐርሰንት ክፍያ እንዲከፈል መመሪያው ይደነግጋል፡፡

 የገቢዎች ክፍያን በተመለከተ በማንኛው ሁኔታ 2 ፐርሰንት የሚከፈል ሲሆን ----------------ታክስ እና

የካፒታል ዋጋ ዕድገት ከመጀመሪያ ደረጃ ውርስ ውጪ ለመኖሪያ 2 ፐርሰንት ለድርጅት 15 ፐርሰንት

እንዲከፈል መመሪያው ያዝዛል፡፡

የመወያያ ርዕስ፡- የከተማ ቦታን በሊዝ ለማስተዳደር ከወጡ መመሪያዎች መካከል የከተማ መሬትን መልሶ ማልማትና

ማደስ መመሪያ አንዱ ነው

በመጀመሪያ ከትርጉም አንፃር፡

መልሶ ማልማት፡- የከተማ የደቀቀ/የተጎዳ አካባቢን በሙሉ/በከፊል በማንሳትና ሙሉ በሙሉ ነፃ በማድረግ

ከተማ ማደስ፡- የከተማ የተጎዳ አካባቢን መሰረታዊ አቅርቦቶችን በመዘርጋት

ለመልሶ ማልማት/መልሶ ማደስ፡-

 ፕላን መከለልና በካርታ የሚመለከቱ

 ዝርዝር የአካባቢ ፕላን ለማዘጋጀትና በከተማው ም/ቤት ማስፀደቅ

 የተዘጋጀ የአካባቢ ልማት ፕላን(LDP) ለማዘጋጀት የሚተገበር ነው፡፡


በመልሶ ማልማት የሚለማ አካባቢ በአማካይ በአንድ ሄ/ር 60 ፐርሰንት እና በላይ የሆነው ግንባታ ዝቅተኛው የፕላን ስታንዳርድ

ያላሟላ 50 ፐርሰንትና በላይ የሆነው ግንባታ ደቀቀና ደረጃ አካባቢው በቂ መሰረተ ልማት ዝርጋታ የሌለው እና ኗሪዎች

በፍግፍግ ሚኖሩ በአማካይ በአንድ ሄ/ር 50% እና በላይ የሆነው ግንባታ ይዞታ አስተዳደር መመሪያ ሚፈቀደውን ዝቅተኛን

ስታንዳርድ የቦታ ስፋት ያላሟላ፡፡

የዉየይይቱ ርዕስ፡- የአካባቢየመኖሪያ ቤት ህ/ስ/ማህበት

 በመልሶ ማልማት አግባብ በሚለዉ የደቀቁ አካባቢዎች የቀበሌ ቤት (የመንግስት ቤቶች አስተዳደር) ተከራይቶ ተገቢዉ

አደረጃጀት ሲኖራቸዉ

1. የማህበሩ አባል በስማቸዉ ወይም በትዳር አጋራቸዉ የመኖሪያ ቤት የሌላቸዉ

2. በጊዜ ሰሌዳዉ ለማልማት ግዴታ ሲገቡ

3. ለባለይዞታ ካሳ መክፈል ሲችሉ (ለተጋቢዎች)

በግል አልሚዎች በከፍተኛ የልማት ፕሮጀክት ደረጃ

የከተማ አስተዳደሩ የሚከተለዉን አሟልቶ ሲቀርቡ ቦታዉን የሚፈቅድላቸዉ ይሆናል፡፡

1. ዝርዝር የልማት ፕሮጀክቱን ለከተማዉ አስተዳደር አቅርበዉ ተቀባይነት ሲያገኝ

2. የግንባታ መጀመሪያና ማጠናቀቂያ የጊዜ ገደብ ዉስጥ ለመፈጸም ግዴታ ሲገቡ

የተከራዮችን የመንግስት የድርጅት ቤትና ይዞታ በጋራ ተደራጅዉ ስለሚያለሙ ግለሰቦች

በመልሶ ማልማት አግባብ እንዲለማ በተከለለ ቦታ በጋራ በመደራጀት የተከራዮችን የድርጅት ቤት ማልማት የሚፈልጉ ማልማት ይችላሉ፡፡
የዉይይቱ ርዕስ፡- የዕምነት ተቋማት የአምልኮና የመቃብር ቦታ አሰጣጥ መመሪያ

በመጀመሪያ የአምልኮ ቦታ ጥያቄ አቀራረብ

1. ነባር የአምልኮ ተቋማትን ሳይጨምር ከ 18 አመት በላይ እድሜ ያላቸዉ ከዕምነቱ ተከታዮች ብዛት ከታች በተጠቀሰዉ

መሰረት ቀረበና በእምነት ተቋመ ማህተም ተረጋገጠ

የከተማ ደረጃ የተከታይ ብዛት

ሜትሮ ፖሊታን 1000

መካከለኛ 600

ለአነስተኛና በታች 100

ከአባላቱ ሙሉ ስምና ፊርማ በእምነት ተቋሙ ተወካይ እና በቀበሌ አስተዳደሩ በኩል በማህተም ተረጋግጦ ሲቀርብ

2. በከተማ ደረጃ ለመጀመሪያ ጊዜ ለማቅረብ የእምነትና የመቃብር ቦታ ጥያቄ የዘማኞች ብዛት

የከተማ ደረጃ የተከታይ ብዛት

ሜትሮ ፖሊታን 200 ከ 18 አመት በላይ የሆናችሁ

መካከለኛ 150 ከ 18 አመት በላይ የሆናችሁ

በሌሎች ከተሞች 100 ከ 18 አመት በላይ የሆናችሁ


የተከታይ ቁጥር ከላይ በሰንጠረዦች እንደተጠቀሰዉ ሆኖ ሌሎች መስፈርቶችን በተመለከተ

 የዕዉቅና ሰርተፊኬት

 ቃለ ጉባኤ (በእምነቱ አመራሮች የተፈረሙ)

 በ 5 አመት ጊዜ ዉስጥ ለመገንባት በደብዳቤ ሲረጋገጥ

 የቦታዉ የካሳ ክፍያ በአንድ ጊዜ ለመክፈል የስምምነት ማረጋገጫ

 በከተማዉ የአምልኮ ማከናወኛ የሌላቸዉ በአቅራቢያ የሌለ

 በተመሳሳይ የእምነት ተቋም መካከል ሊኖር የሚገባዉ ርቀት

 ለሜትሮ ፖሊታን እና ለመካከለኛ ከተሞች ከ 2 ኪ/ሜ የማያንስ

 በሌሎች ከተሞች ከ 1.5 ኪ/ሜ ያላነሰ

 ለሁሉም እምነቶች ቦታ ሊሰጣቸዉ የሚቻለዉበከተማዉ ክልል እምነታቸዉን የሚያካሂዱበት ቦታ የሌላቸዉ፡፡

የዕምነት ተቋማት የአምልኮና የመቃብር ቦታ አሰጣጥ መመሪያ

ለአምልኮ የሚውል ምደባ ጥያቄን ማጣራት፣ማረጋገጥ፣መመዝገብ በተመለከተ፡-

1. ካረጋገጡ በኋላ መመዝገብ፣

2. ለከንቲባ ኮሚቴ ማቅረብ፣

3. በፕልን ምደባ ከሌለ ጥናትና ዝግጅት ማካሄድ፣

4. ወደ ዞን ስራና ከተማ ልማት መምሪያ መላክ፣


የአምልኮ ቦታ ፕላን ጥናት አካሄድን በተመለከተ፡-

 ከሌላ እምነት የአምልኮ ማከናወኛ ቦታ ቢያንስ ከ 500 ሜ/ር ሬዲየስ በላይ መሆን አለበት

 ከጤና፣ከትምህርት ተቋማትና ከአስተዳደራዊ ተቋማት ቢያንስ 200 ሜ/ር ሬዲየስ መሆን አለበት

የአምኮ ቦታ ስፋትና አጠቃቀም

 የመቃብር ቦታን ሳይጨምር ከ 200 እስከ 300 ካ/ሜ

 40 ፐርሰንት ለግንባታ 60 ፐርሰንት ለእንቅስቃሴ አረጓዴ ልማት ከግንባታ ነፃ እንዲሆን ከተደረገው ቦታ 3/4 ኛው ቦታ

በአረጓዴ መሸፈን አለበት

የመቃብር ቦታ አወሳስንና አሰጣጥ

 ማዘጋጃ ቤቱ የመቃብር ቦታ በመሬት ፕላኑ መሰረት ይከልላል

 ለዞን ኢ/ከ/ል/መምሪያ በማቅረብ አስተያየት ተሰጦ ቦታው ይከለላል

 የመቃብር ቦታ በካርታ ተደግፎ መሰጠት አለበት

በአንድ ላይ ከተሰጠ የአምልኮና የመቃብር ቦታ መጠናቸው ተለይቶ መመላከት አለበት፡፡

 የአምኮ ማከናወኛ ቦታና የመቃብር አገልግሎት በአንድ ላይ ለሚሰጡ የእምነት ተቋማትና የመቃብር ቦታ በፓላን ላይ

የተመደበላቸው እምነት ከ 1000-3000 ከማንኛውም ክፍያ ነፃ ሆኖ ይሰጣል

የአምልኮና የመቃብር ቦታ ዝግጅትና የካሳ ክፍያ አግባብ

 በፕላን መሰረትና በእቅድ በተያዘው

 መሰረታዊ የመዳረሻ መንገድ ያለውና ከ 3 ኛ ወገን ነፃ የሆነ

 የወሰን ድንጋይ የተተከለለትና ሳይት ፕላን የተዘጋጀለት መሆን አለበት፡

የመወያያ ርዕስ፡- በአብክመ ለህዝብ ጥቅም ሲባል መሬታቸውን የሚለቁ የገጠር ባለይዞታዎችን መልሶ ለማቋቋምና

ይዞታቸውን ለማስተዳደር የወጣ የክልል መስተዳደሩ ም/ቤት መመሪያ፡-


 በከተማ አስተዳደራዊና የፕላን ወሰን በተጠቃለሉ የገጠር ቀበሌዎች ውስጥ ስለሞኖሩ የመሬት ተጠቃሚዎች

ባለመብቶች መሬት ቆጠራ፣ምዝገባና ይዞታ ማረጋገጫ ደብተር አሰጣጥ

 ስለመሬት ይዞታ ምዝገባ ፡-

1. ወደ ሜትሮፖሊታን ከተማ የፕላንና የአስተዳደር ክልል የተጠቃለሉ የገጠር ቀበሌዎች መሬት ቆጠራና ምዝገባ ስራ

ጉዳዩ በሚመለከተው ከተማ ግብርና መምሪያ ጽ/ቤት በኩል ይከናወናል

2. በዚህ ንዑስ አንቀፅ አንድ ስር የተደነገገው እንደተጠበቀ ሆኖ በከተማ አሰተዳደሩ አደረጃጀት ውስጥ የግብርና

መምሪያ/ጽ/ቤት የሌለ እንደሆነ የተባለው የመሬት ቆጠራና ምዝገባ ስራ ከተማው በታቀፈበት ወረዳ ገጠር መሬት

አጠቃቀምና አስተዳደር ጽ/ቤት በኩል ይከናወናል፡፡

3. በዚህ ንዑስ አንቀፅ 1 እና 2 ስር የተደነገገው እንደተጠበቀ ሆኖ ይዞታቸው በሰነድ ለተረጋገጠላቸው ባለይዞታዎች

ተገቢው ካሳ በቅድሚያ የተከፈለ መሆኑን ገልፆ ተቀባይነት ባለው ሰነድና ለከተማ አስተዳደሩ ያስረክባል፡፡

 ስለ መሬት ይዞታ ማረጋገጫ ደብተር አሰጣጥ

1. በክልሉ ውስጥ በየትኛውም ከተማ ፕላንና የአስተዳደሩ ወሰን የሚገኝበትን ህጋዊ የመሬት ባለይዞታዎች በማጣራት

ከአሁን በፊት ያልተሰጡ መብቶቻቸው ቢኖሩ የመጀመሪያና የሁለተኛ ደረጃ የይዞታ ማረጋገጫ ደብተር

ይሰጣቸዋል፡፡

2. የዚህ ንዑስ አንቀፅ ድንጋጌ ቢኖርም ቀደም ሲል ለባለይዞታዎች የመጀመሪያ ደረጃ ይዞታ ማረጋገጫ ደብተር

ተሰጧቸው ከነበረ ሌላ ሰነድ በድጋሚ እንዲሰጣቸው ማድረግ አስፈላጊ አይሆንም፡፡ ይህው የመጀመሪያ ደረጃ

የይዞታ ማረጋገጫ ደብተር ያልተሰጣቸውን ባለይዞታዎች ብቻ አስመልክቶ የመሬት ቆጠራና ምዝገባው ይካሄዳል፡፡

3. በከተማ አስተዳደራዊና የፕላን ወሰን የመሬት ቆጠራና ምዝገባ ከተካሄደ በኋላ ከተሰጠው የመጀመሪያ ደረጃ የይዞታ

ማረጋገጫ ደብተር በኋላ ባለይዞታዎች ሁለተኛ ደረጃ የይዞታ ማረጋገጫ ደብተር እንዲያገኙ ይደረጋል፡፡መረጃውን

በአግባቡ ተደራጅቶና ደህንነቱ ተጠብቆ በሀርድና ሶፍት ኮፒ ከተዘጋጀ በኋላ እንዲያዝና እንዲጠበቅ መደረግ

ይኖርበታል፡፡

4. በመሬት ቆጠራውና ምዝገባው ወቅት የሚለዩ የወል ይዞታዎችን አስመልክቶ የይዞታ ማረጋገጫ ደብተር በወል

መሬቱ ተጠቃሚዎች ስም ተዘጋጅቶ ይሰጣቸዋል፡፡


5. በዚህ አንቀፅ ንዑስ ስር የተደነገገው እንደተጠበቀ ሆኖ የሞተ ከዳ የጥሎ ሂያጅ ይዞታዎች ቢኖሩ አስፈላጊው

ማጣራት ከተካሄደ በኋላ ይዞታዎቹ በታቀፉበት ቀበሌ ስም ተመዝግበው ይያዛሉ፡፡

6. በዚህ አንቀፅ ከዚህ በላይ የሰፈሩትን ድንጋጌዎች መሰረት በማድረግ ለመሬት ተጠቃሚዎች የመጀመሪያም ሆነ

የሁለተኛ ደረጃ ይዞታ ምዝገባ ስራው ለሚመለከተው ነዋሪ ህዝብ በሪፖርት መልክ ቀርቦ በይፋ ከተተቸ በኋላ

ይሆናል፡፡

የመወያያ ርዕስ፡- በከተማ አስተዳደራዊ የፕላን ወሰንም ሆነ ከከተማ ክልል ውጪ በልማት ምክንያት ከመሬታቸው ለሚነሱ

ባለይዞታዎች ትክ የሰፈራ የእርሻም ሆነ የመኖሪያ ቤት መስሪያ ቦታ ስለሚዘጋጅበትና

ስለሚሰጥበት ሁኔታ

 ትክ ቦታ ስለመለየትና ስለማዘጋጀት

1. በልማት ምክንያት ከይዞታቸው ለሚነሱና በከተማ ውስጥ ለሚገኙ የገጠር ቀበሌ ነዋሪዎች በትክነት ሲሰጥ

የሚችል ስፋራ የሚመለከታችን ከተማ መፃኢ እድገት ታሳቢ በማድግ በጥናት ላይ ተመስርቶ ይመረጣል፡፡

2. በትክነት ስለሚመረጠው ቦታ ተገቢነት በቅድሚያ የጋራ ዉይይት ከተካሄደ በኋላ ቁጥራቸዉ ከ 5 የሚያንሱ የገጠር

ቀበሌ ነዋሪዎች ህዝብ ተወካዮች ከከተማ አገልግሎት ጽ/ቤት (ማዘጋጃ ቤት) ጋር የስምምነት ሰነድ ይፈራረማሉ፡፡

3. ትክ ቦታ ሆኖ እንዲሰጥ በተመረጠዉ ስፍራ ላይ የሚገኙ ቀደምት የመሬት ባለይዞታዎች ቢኖሩ አግባብ ባላቸዉ

የካሳ አከፋፈል እና ትክ ቦታ አሰጣጥ መመሪያ መሰረት ተገቢዉ የንብረትና የመፈናቀያ ካሳ እንዲከፈላቸዉ ተደርጎ

ቦታዉ ከ 3 ኛ ወገን ነጻ ይደረጋል፡፡

4. በትክነት የተመረጠዉ ቦታ ለሚመለከተዉ ከተማ አማካኝነት አስፈላጊዉ የማስፋፊያና የሽንሻኞ ፕላን

ተዘጋጅቶለት የከተማዉ የዕድገት ፕላን አካል ሆኖ እንዲጸድቅና በዚሁ ፕላን መሰረት ልማት እንዲሟላለት

ይደረጋል፡፡

5. የሚዘጋጀዉ የትክ ቦታ ስፍራ ፕላን ምደባ ቅይጥና መኖሪያን የያዘ መሆን ይኖርበታል፡፡

6. ከዚህ በላይ በሰፈሩት የዚህ አንቀጽ ድንጋጌዎች መሰረት ትክ ቦታ ሆኖ እንዲሰጥ በማሰብ የመሬት ይዞታቸዉ

ለሚወሰድባቸዉ ባለይዞታዎች የሚከፈለዉ የንብረት የቋሚ መፈናቀያ ካሳ እና ለዝግጅት የሚወጣዉ ወጭ

በተገቢዉ መንገድ ተሳልቶና ተደራጅቶ በመረጃነት መያዘ ይኖርበታል፡፡


የመወያያ ርዕስ፡- የመኖሪያ ቤት መስሪያ ቦታ ለማግኘት መሟላት ስላለባቸዉ ቅድሚያ ሁኔታዎች

 ትክ ቦታ ሆኖ እንዲሰጥ በተከለለ በየትኛዉም ስፍራ የመኖሪያ ቤት የመስሪያ ቦታ የማግኘት መብት ያለዉ ማንኛዉም

ሰዉ ቦታዉን ከመረከቡ በፊት ከዚህ በታች የተመለከቱትን ቅድመ ሁኔታዎች ማሟላት ይኖርበታል፡፡
1. ወደ ከተማዉ በተከለለ የገጠር ከተማ ዉስጥ ህጋዊ የመሬት ይዞታ ያለዉ

2. መደበኛ ነዋሪነቱ በከተማዉ አስተዳደራዊ ወሰን ሆኖ እድሜዉ ከ 18 አመትና ከዚያ በላይ የሆነ

3. በአካባቢዉ አስተዳደር አቅም የቀረበለትን ቦታ ለመረከብ ፈቃደኛ ሆኖ የተገኘ

4. እስታንዳርዱ በሚፈቅደዉ መሰረት ግንባታዉን ለማከናወን አቅም ያለዉ ለመሆኑ ተገቢዉን ማስረጃ ማቅረብ

የሚችልና

5. በደንቡዉስጥ በተቀመጠዉ የግንባታ መጀመሪያና ማጠናቀቂያ ጊዜ ገደብ ለመገንባትና ስለዚህም ዉል ለመግባት

ፈቃደኛ የሆነ

 በከተማ ፕላን ወሰን በግል ይዞታ ላይ የመኖሪያ ቤት (የንግድ ድርጅት) ለመገንባት መሟላት ስላለባቸዉ ቅድመ

ሁኔታዎች ፡-

1. በየትኛዉም ከተማ ፕላን ወሰን የሚገኙ ባለይዞታዎች በግል ይዞታቸዉ ላይ የመኖሪያ ቤት (የንግድ ድርጅት)

ለመገንባት የሚችሉት ከዚህ በታች የተመለከተዉን ቅድመ ሁኔታወች አሟልተዉ ሲገኙ ይሆናል፡፡

 ወደ ከተማዉ የተከለለ የገጠር ቀበሌ ነዋሪ ሆኖ መገኘት

 በህግ የተቋቋመና የተረጋገጠና የግል ይዞታ መኖር

 የመኖሪያ ቤት ለመገንባት ጥያቄ በቀረበበት ቦታ ላይ ባለይዞታዉ ቋሚ የመኖሪያ ቤት ይዞታ ያለዉ

መሆኑ ተረጋግጦና ይኸዉም ይዞታዉ በከተማዉ ፕላን ምደባ መኖሪያ ወይም ቅይጥ ሆኖ መገኘት

 ባለይዞታዉ በደንብ ቁጥር 103/2004 ዓ.ም በተቀመጠዉ የግንባታ መጀመሪያና ማጠናቀቂያ ጊዜ

ገደብ ለመገንባት የሚያስችለዉን የዉል ስምምነት ለመፈረም ፈቃደኛ ሆኖ መገኘት

2. በዚህ መመሪያ አንቀጽ 7 ንኡስ አንቀጽ 5 እና በዚህ አንቀጽ 1 ተራቁጥር 4 ድንጋጌዎች መሰረት የሚያደርገዉ

የዉል ስምምነት የከተማ ገጠር ቀበሌ ነዋሪ ባለይዞታዎች መብትና ግዴታ የዉል ሰጭን ተግባርና ሃላፊነት

የይዞታዉን አስተዳደራዊ ሁኔታዎችና ከቦታዉ ጋር ተያያዥነት ያላቸዉን ልዩ ባህሪያት በዝርዝር መዘመልከት

ይኖርበታል፡፡

3. በዚህ አንቀጽ ከዚህ በላይ የተመለከቱትን መስፈርቶች እንደተጠበቁ ሆነዉ መስፈርቶችን አሟልተዉ

የሚገኙት አባወራ (እማወራ) በሚያቀርቡት ህጋዊ ማስረጃ መሰረት እስከ 500 ካ/ሜ ድረስ የመኖሪያ ቤት

ያለበት ይዞታቸዉ እንዲጸድቅላቸዉ ከተደረገ በኋላ በነባር ስሪት ካርታ ተዘጋጅቶ ይሰጣቸዋል፡፡
የመወያያ ርዕስ፡- የከተማ መሬትን በሊዝ ለማስተዳደር የወጣ አዋጅ ቁጥር 721/2004 ለማስፈጸም ከወጡ

መመሪያዎች መካከል ቀደም ሲል ወጥቶ ስራ ላይ የነበረ የተሟላ ሰነድ የሌላቸዉና ሰነድ አልባ

ይዞታዎች ማጣሪያ መመሪያ ቁጥር 2/2005 እና እንደገና ተሻሽሎ የወጣዉ መመሪያ ቁጥር 8/2007

ይገኙበታል

በመጀመሪያ ስለትርጓሜ

 የተሟላ ሰነድ የሌላቸው የሚባሉ ይዞታዎች

1 ኛ. በምሪት የተያዘ ስለመሆኑ

2 ኛ. የምሪትና የቦታ ኪራይ ካርኒ ማቅረብ የሚችሉ

3 ኛ. የቀደም ካርታ/የምሪት ካርኒ/የይዞታ ማረጋገጫ ደብተር ያላቸው

4 ኛ. በምሪት ተይዘው ቤት ተሰርቶባቸው የነበሩና ቤቱ ፈርሶ የግንባታ ፈቃድ በመጠየቅ ሂደት ላይ ያሉ እንደመስፈርት

ይወሰዳሉ፡፡

 ሰነድ አልባ ይዞታዎች ከላይ የተጠቀሱ ሰነዶች የሌላቸው ነገር ግን፡-

1 ኛ. በአዋጅ ቁጥር 47/67 ያልተወረሰ ስለመሆኑ የሚያረጋግጥ

2 ኛ. ከ 1970 ዓ.ም በፊት ለቤተክርስቲያን የገበረበት

3 ኛ. ከአዋጅ 80/86 በፊት በራስ አገዝ መኖሪያ ቤት ህ/ስራ ማህበር የተደራጁ

4 ኛ. ከ 1983 በፊት የቦታ ኪራይ የተከፈለበት ሆኖ የመብራት/ውሃ ያስገቡ ስለመሆኑ ሰነድ/ውል የሚያቀርቡ

5 ኛ. ከገጠር መሬት ሽግሽግ ወቅት በከተማ ክልል ይዞታ ስለመያዙ የሚረጋገጥ

ከላይ ከተጠቀሱት መስፈርቶች አንዱን የሚያሟሉ ግለሰቦች በቀበሌ ይዞታ አጣሪ ኮሚቴ ተጣርቶ ይቀርብና በአብይና

በከንቲባ ኮሚቴ ተረጋግጦና እንዲፀድቅ ተደርጎ ሰነድ ይሰጣቸዋል፡፡

 በህጋዊ መንገድ በምሪት የተያዘ ከሆነ ሌላ ይዞታ ቢኖራቸውም ይስተናገዳሉ


 ይዞታዎቹ ሰነድ አልባ ከሆኑ ፕላን ምደባቸው ተለይቶ የሁሉም ይዞታዎች ተመሳሳይ አገልግሎት ከሆነ በመረጡት

ተስተናግደው ሌሎች ሌላ መመሪያ እንዲጠብቁ ይደረጋል፡፡በሚል መመሪያ ቁጥር 2/2005 የሚደነገግ ቢሆንም

ተሻሽሎ የወጣው መመሪያ ቁጥር 8/2007 ግን እስከ ተጠሩ ድረስ ሁሉም ሰነድ ሊሰጣቸው እንደሚገባ ያስቀምጣል፡፡

 በግዥ/በስጦታ ለመገኘቱ የፍ/ቤት ማስረጃ ያቀረበ ውዝፍ የግብና ስመ ንብረት ዝውውር ክፍያ እንዲፈፀም በማድረግ

ተጠርቶ ሰነድ ይሰራላቸዋል

 ፕላን ምደባው አሁን Green Area እና open space ላይ ያሉ ሰነድ አልባና የተሟላ ሰነድ የሌላቸው ፕላን ምደባው

ይስተካከል ከተባለ/ይጠበቅ/ከተባለ ትክ ቦታ ይሰጣቸዋል ካልሆነ አሁን ያለውን ግንባታ የሚያሳይ ፕላን ምደባውን

በመግለፅ ሰነድ ይሰጣቸዋል፡፡

የውይይቱ ርዕስ፡- የተሟላ ሰነድ የሌላቸው እንዲሁም ሰነድ አልባ በተመከተ

 በምሪት ካርኒያቸው መሰረት ይወሰናል

 ከምሪት ካርኒያቸው በላይ ይዘውና ግንባታ ገንብተው ከሆነ ግንባታውን አፍርሰው እንዲለቁ በማድረግ ይሰራላቸዋል

 በልኬት የተገኘው ከምሪት ካርኒያቸው ከነሱ የልኬታው ይወሰዳል

 ከ 100 ካ/ሜ በታች የሆነ ሰነድ አልባ የመኖሪያ ይዞታዎች ሰነድ እንዲያገኙ ይደረጋል

 ሰነድ አልባ ሆነው የመኖሪያ ቤት ይዞታዎች ከ 500 ካ/ሜ (1994)በፊት እና ከ 250 ካ/ሜ(1994)በኋላ ሆኖ ትርፍ ያለው

ከሆነ ነፃ ተደርጎ ወደ መሬት ባንክ ገቢ ይደረጋል


 በመሀል ከተማ የቀበሌ ቤቶች ከግለሰብ ይዞታዎች ጋር የተቀላቀለበት

 በፕሮፓሪሽን እየተዘጋጀ ሰነድ ይሰጣቸዋል

 የቀበሌ ቤቶችም በቀበሌውና በማዘጋጃ ቤቱ ስም በ 2 ኮፒ ካርታ ይሰራል

ባህላዊ ግዥ/ስጦታ የተገኘ ሰነድ አልባና የተሟላ ሰነድ የሌላቸው

የተሟላ ሰነድ የሌላቸው እና ሰነድ አልባ የሚያስብሉ መስፈርቶች መካከል አንዱን የሚያሟላ ሆኖ በግዥ፣በስጦታ፣በውርስና

በፍ/ቤት ውሳኔ የተገኘ ስለመሆኑ ማስረጃ የሚያቀርቡ ማለት ነው፡፡

 ቀደም ሲል በመመሪያ ቁጥር 2/2005 ባህላዊ ግዥና ስጦታ በፍትህ ፀድቆ እንዲቀርብ የሚያስገድድ የነበረ ቢሆንም

መመሪያ ቁጥር 8/2007 ግን ከሰኔ 30/2007 በፊት የተያዘ የባህላዊ ግዥና ስጦታ ውል በይዞታ አጣሪ እየተፈተሸ

እንዲፀድቅ ይደነግጋል፡፡
የመወያያ ርዕስ፡- ለማህበራት የቦታ አቅርቦት መመሪያ

 የመኖሪያ ቤት ህብረት ስራ ማህበር አባልነት ምዝገባ መስፈርቶች፡-

 አጠቃላይ የአባልነት ምዝገባ መስፈርቶች

1. ዕድሜው ከ 18 ዓመትና ከዚያ በላይ የሆነ በህግና በፍርድ ያልተከለከለ ኢትዮጵያዊ

2. በሚደራጅበት/በሚኖርበት ከተማ ለተከታታይ ሁለት ዓመታት ነዋሪ የሆነ እንዲሁም ሰራተኛ ከሆነ ደግሞ በሚኖርበት

ከተማ በሚገኙ ተቋማት ውስጥ ቢያንስ ሁለት አመት በቋሚነት ተቀጥሮ የሰራና እየሰራ ያለ

3. ለሁለት ተከታታይ ዓመታት በከተማው ውስጥ ባይኖርም በስራ በትምህርት/በህክምና ምክንያት ከከተማው ውጪ

የኖረበትን ተጨባጭ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፡፡

4. የህብረት ስራ ማህበር አባልነት መመዝገቢያ ክፍያ መክፈል የሚችል

5. የቤቱን የግንባታ ወጪ 20 በመቶ ከተደራጁ በኋላ በዝግ ሂሳብ የሚያስቀምጥ 30 በመቶውን የግንባታ ፈቃድ መሬት

ተዘጋጅቶ የመኖሪያ ቤት በህብረት ስራ ማህበሩ ህጋዊ እውቅና በሚያገኘበት ወቅት መክፈል የሚችል መሆን

ይኖርበታል፡፡

6. ቀሪውን 50 በመቶ በሂደት በመቆጠብ በግንባታው ሂደትና በማጠናቀቂያ ወቅት የሚከፈል ይሆናል፡፡

7. ለመኖሪያ ቤት ህብረት ስራ ማህበሩ ለተሰጠው ቦታ የመሬት ካሳ የራሱን ድርሻ መክፈል የሚችል፡፡

8. የህብረት ስራ ማህበሩን ዓላማና መርሆዎች ለማጠናከርና የማህበሩን መተዳደሪያ ደንብ ለመቀበል ፈቃደኛ የሆነ
9. በሚደራጅበት ከተማ ከዚህ በፊት በራሱም ሆነ በትዳር ጓደኛው/የመኖሪያ ቤትም ሆነ የመኖሪያ ቤት መስሪያ ቦታ

የሌለው/ቦታ ኖሮት ለ 3 ኛ ወገን ያላስተላለፉ ቦታ ለማግኘት አይመዘገብም

10. በመንግስት በተዘረጉት ሌሎች የቤት ልማት ፕሮግራሞች ላይ በራሱም ሆነ በትዳር ጓደኛው ስም ተጠቃሚ

ያልሆ/ለመጠቀም ያልተመዘገበ/ተመዝግቦም ከሆነ ምዝገባውን መሰረዙን/መተውን ግዴታ መግባት የሚችል መሆን

ይኖርበታል፡፡
የመወያያ ርዕሰ፡-ለማህበራት የቦታ አቅርቦት መመሪያ

 በአዲስ በመኖሪያ ቤት ህብረት ስራ ማህበራት በመደራጀት የሚያበቁ መስፈርቶች በህብረት ስራ ማቋቋሚያ አዋጅ

134/98 ያደረጃጀት መስፈርት መሰረት፡-

 በመኖሪያ አካባቢ የሚደራጁ የመኖሪያ ቤት ማህበራት ስራ ማህበር አባላትን በተመለከተ

1. በመኖሪያ አካባቢ የሚተዋወቁ ተመሳሳይ የቤት አይነት ፍላጎትና አቅም ያላቸው እና በፈቃደኝነት በጋራ ለመስራት

የተስማሙ መሆኑን ግዴታ መግባትና አስፈላጊ ቅፃቅፆችን መሙላትና አደራጅ አካል ዘንድ መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

2. በመኖሪያ አካባቢ የተሰበሰቡ የመኖሪያ ቤት ህብረት ስራ ማህበር አካላት የስም ዝርዝራቸውን በመያዝ ወደ ህብረት ስራ

ማህበራት ማስፋፊያ አካል ከመቅረባቸው በፊት በሚኖሩበት ከተማ ውስጥ ነዋሪ መሆናቸውን ማረጋገጫ በቀበሌው

አስተዳደር አማካኝነት በከተማው አስተዳደር ማግኘት ይጠበቅባቸዋል፡፡

 በስራ አካባቢ የሚደራጁ የመኖሪያ ቤት ህብረት ስራ ማህበር አባላትን በተመለከተ

1. በስራ ቦታቸው የሚተዋወቁ ተመሳሳይ የቤት ዓይነት ፍላጎትና አቅም ያላቸው እና በፈቃደኝነት በጋራ ለመስራት

የተስማሙ መሆኑን ግዴታ መግባትና አስፈላጊ ቅፃቅፆችን መሙላትና አደራጁ አካል ዘንድ መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

2. በመስሪያ ቤቶች የሚደረግ ምዝገባን በተመለከተ መስሪያ ቤቱ የማህበሩ አባላት ዝርዝር በማረጋገጥና ምህተም

በማድረግ ለአደራጁ አካል በሽኝ ደብዳቤ መላክ ይኖርበታል፡፡

 በአሰሪ መሰሪያ ቤት የሚደራጁ የመኖሪያ ቤት ህብረት ስራ ማህበር አባላትን በተመለከተ

1. በአንድ መስሪያ ቤት/ተቋም/ ውስጥ የሚሰሩ ተመሳሳይ የቤት አይነት ፍላጎትና አቅም ያላቸው እና በፈቃደኝነት በጋራ

ለመስራት የተስማሙ መሆኑን ግዴታ መግባት ይኖርባቸዋል፡፡

2. በአሰሪ መስሪያ ቤት የተረጋገጠ አባላትን ዝርዝር በየአንዳንዱ አባል ስም የተቆጠበና ከመስሪያ ቤት የሚሸፈንለት የቤት

የግንባታ ወጪ ግምት የሚገነባውን የቤት ብዛት የዲዛይን አይነትና ተቅላላ ዋጋ የያዘ ሰነድ ለአደራጁ አካል ማቅረብ

ይኖርባቸዋለል፡፡ በራስ አገዝ የመኖሪያ ቤት ህብረት ስራ ማህበር የሚገነቡ ቤቶች የቤቶች የግንባታ ዋጋ በጋራ

የሚሰራው 20 ካ/ሜ ክፍል ታሳቢ በማድረግ ብር 32,000 ይሆናል፡፡


3. ከላይ በአንቀፅ 11.1 እና 2 የተጠቀሰው የመነሻ ዋጋ ሲሆን እቸንደ አካባቢው ሁኔታ ሊለዋወጥ እንደሚችል ታሳቢ

መደረግ አለበት፡፡

4. የዲዛይኑን አይነት በራሳቸው መርጠው ለሚሰሩ የቤቱ ግንባታ ዋጋ በዚህ አንቀፅ ንዑስ አንቀፅ 11.1 የተጠቀሰው ሊሆን

አይችልም፡፡ሆኖም ማህበሩ የሚያቀርበውን ዲዛይን መሰረት በማድረግ የሚመለከተው አካል በሚገምተው ግንባታ ዋጋ

ይሆናል፡፡

5. ግንባታው የሚከናወነው ለልማት ተነሽወች ቦታ ላይ ከዋለ ከቤቱ የግንባታ ዋጋ በተጨማሪ ለማስነሻ የካሳ ክፍያ

በህብረት ስራ ማህበሩ አባላት የሚሸፈን ይሆናል፡፡

6. የቤቶች ግንባታ ዋጋ የማጠናቀቂያ ስራንና ወለድን አያካትትም ዋጋውን በወቅቱ እንደሚኖረው የገበያ ዋጋ

ሊጨምር/ሊቀንስ እንደሚችል ታሳቢ መደረግ ይኖርበታል፡፡


የመወያያ ርዕስ፡- ከባለፈውበ ሳምንት የቀጠለ የመኖሪያ ቤት ህብረት ስራ ማህበር አባላት ቁጥር በ 2004 ዓ.ም በማዕከላዊ

ስታስቲክስ ኤጄንሲ ይፋ በተደረገው የከተሞች

የህዝብ ብዛት መረጃ መሰረት፡-

1. የህዝብ ብዛታው ከ 100,000 በላይ በሆነ ከተሞች አንድ መኖሪያ ቤት በህበረት ስራ ማህበር ዝቅተኛ ከ 14 ያላነሱ

ከፍተኛው 24 ያልበለጡ አባላት ይኖሩታል፡፡

2. የህዝብ ብዛታቸው ከ 1000 ሺ በታች በሆኑ ከተሞች አንድ የመኖሪያ ቤት የህብረት ስራ ማህበር ከ 10 ያላነሱ ከ 24

ያልበለጡ አባላት ይኖሩታል፡፡

3. በዚህ አንቀፅ 1-2 የተጠቀሱት ቢኖሩም አደራጁ መ/ቤት በጥናት በተረጋገጠ አዋጭ የሆነውን የመነሻ ቁጥር በአደረጃጀት

መመሪያወረ ሊወሰን ይችላል፡፡

4. ከ 2,000 ሺ ህዝብ በታች ባላቸው ከተሞች በማህበር መደራጀት አይጠበቅበትም፡፡

5. ሁሉም የመኖሪያ ቤት የህብረት ስራ ማህበራት የአባላት ብዛት ሙሉ ቁጥር መሆን አለበት፡፡


የመወያያ ርዕስ፡- ተሸከርካሪዎችን ከጉምሩክ ቀረጽ ነጻ ለማስገባት መሟላት ያለባቸዉ ቅድመ ሁኔታዎች

 የሰራተኛ ማጓጓዣና ለተለየ አገልግሎት የሚዉሉተሸከርካሪዎችን ስለማስገባት

 ባለሀብቱን መሬት ስለማግኘቱ ወይም ተከራይቶ ከሆነ ህጋዊ የኪራይ ማስረጃ

 የፕሮጀክቱ ተግባራዊ እንቅስቃሴ ስለመጀመሩ ማለትም የመሬት ዝግጅት፣ መሰረተ ልማት፣ መጋዝን፣

መንገድና የመሳሰሉት ስራዎች እየተከናወኑ ስለመሆናቸዉ መረጃ

 ለፕሮጀክቱ የሚያስፈልጉ የካፒታል ዕቃዎች ከዉጭሀገር ስለመግባታቸዉ ቢልኦፍ ሎዲንግ ወይም ኤርዌይ

ቢል ወይም ትራክ ዌይ ቢል እና የግዥ ደረሰኝ ወይም

 የካፒታል እቃዎቹ ከሀገር ዉስጥ የተገዙ ከሆነ የግዥዉ ዉል ካስፈላጊ ማስረጃዎች ጋር የጉምሩክ ቀረጽ ነጻ

መብቱን ለሚፈቅደዉ አካል ሲያቀርብ ብቻ ነዉ፡፡

 ከላይ የተጠቀሱት ቅድመ ሁኔታዎች እንደተጠበቁ ሆነዉ ማንኛዉም ባለሀብት ከፒካፕ እና ሞተር ብስክሌት

በስተቀር ሌሎችን ተሸከርካሪዎች ከጉምሩክ ቀረጽ ነጻ ለማስገባት የሚፈቅድለት ኢንቨትመንት ትግበራዉን አጠናቆ

የሙከራ ምርት ማምረት ስለመጀመሩ አግባብ ካለዉ አካል የተሰጠዉን ማስረጃ የጉምሩክ ቀረጽ ነጻ መብቱን

ለሚፈቅደዉ አካል ሲያቀርብ ብቻ ይሆናል፡፡

 ባለሀብቱ የኢንቨስትመንት ትግበራዉን አጠናቆ የማምረት ስራ ሲጀምር ያለማዉ የመሬት ስፋት (ያለዉ)

የእንስሳት ብዛት ወይም የሰዉ ሰራሽ ኩሬ ይዘት ወይም ለፕሮጀክቱ የዋለዉ የመሬት መጠን ወይም ስፋት

መጠን የተሟላ ስለመሆኑ የሚያረጋግጥ የንግድ ስራ ፈቃድ ከወጣበት አካል የተሰጠዉን ማስረጃ የጉምሩክ

ቀረጽ ነጻ መብቱን ለፈቀደዉ አካል ማቅረብ ያለበት ሲሆን መጠኑ ከተመለከተዉ በታች ሆኖ ከተገኘ

ከጉምሩክ ቀረጽ ነጻ ላስገባቸዉ ተሽከርካሪዎች ተገቢዉን የጉምሩክ ቀረጽ እንዲከፈል ይደረጋል፡፡

 የሰራተኛ ማጓጓዣና ለተለየ አገልግሎት የሚዉል ተሸከርካሪዎች ስለማስገባት

ከላይ በተፈቀዱት የተሸከርካሪ ማበረታቻዎች በተጨማሪ በግብርና የኢንቨስትመንት መስኮች የተሰማሩ

ባለሀብቶች የሰራተኛ ማጓጓዣና ለተለየ አገልግሎት የሚዉሉ ተሸከርካሪዎችን ከጉምሩክ ቀረጽ ነጻ

ማስገባት ይችላሉ፡፡
የመወያያ ርዕስ፡- ነባር የከተማ ቦታን በሊዝ ስሪት ስለማስተዳደር

1. ነባር ይዞታዎች ከዉርስ በስተቀር በማንኛዉም መንገድ ወደ 3 ኛ ወገን ሲተላለፉ በሊዝ ስሪትና መነሻ ዋጋ ሆኖ፡-

 ይዞታ የተላለፈለት ሰዉ የይዞታዉ አገልግሎት በከተማዉ መዋቀራዊ ፕላን ወይም በአካባቢዉ የልማት ፕላን

መሰረት የሚወሰን ሆኖ የዉል ዘመኑም በአዋጅ ለአገልግሎቱ በተወሰነዉ የሊዝ ዘመን መሰረት ይሆናል፡፡

 ይዞታዉ አገልግሎት እየሰጠየነበረዉ ለድርጅትና ለመኖርያ (ለድብልቅ) ከሆነ ዉለታ የሚፈጸመዉ በአካባቢዉ

መዋቅራዊ ፕላን የመሬት አጠቃቀም በተመለከተዉ መሰረት ይሆናል

 ወደ 3 ኛ ወገን የሚተላለፉ ነባር ይዞታ ወደ ሊዝ የሚገባዉ በሚቀርበዉ ሰነድ፣ በቀረበዉ የመሬት ስፋት መጠን

ይሆናል

 ከዚህ በላይ የተጠቀሰ ቢሆንም በመስክ ልኬት የተገኘዉ የቦታ ስፋት በሰነድ ከተገኘዉ ካነሰ በመስክ ልኬት በተገነዉ

የቦታ ስፋት በሰነድ ከተገነዉ ከበለጠ በመመሪያ የሚወሰን ይሆናል፡፡

 ቀደም ሲል ሲከፈል ነበረዉ የመነሻ ዋጋ በቦታዉ ስፋት ተባዝቶ የሚገኘዉ የገንዘብ መጠን ለአገልግሎት

በተቀመጠዉ የመክፈያ ጊዜ ተካፍሎ የሚገኘዉ ዉጤት በየ አመቱ ይከፈላል፡፡

 ገዥዉ የሊዝ ቅድሚያ ክፍያ እንዲፈጽም ባይገደድም የመክፈል ፍላጎት ካለዉ ከጠቅላላዉ የሊዝ ክፍያ የሚታሰብ

ቅድሚያ ክፍያ አግባብ ላለዉ አካል የመፈጸም መብት አለዉ፡፡

 ከዚህ በፊት ባለሀብቱ የቅድሚያ ክፍያ በመፈጸም የችሮታ ጊዜ እንዲሰጠዉ ጥያቄዉን በጽሁም ካቀረበ የ 2 አመት

የችሮታ ጊዜ ይፈቀድለታል፡፡
 የሊዝ ዘመኑ መቆጠር የሚጀምረዉ የሊዝ ዉል ከተፈራረሙበት ቀን ጀምሮ ይሆናል፡፡

 የቤቱ ስፋት ከቦታዉ ስፋት ምጣኔ የክፍልፍል ድርሻ ተሰልቶ በሚሰጥ የንብረት ባለቤትነት ማረጋገጫ ደብተር

የተያዘ ንብረት ከዉርስ በስተቀር ወደ ሶስተኛ ወገን ሲተላለፍ በጋራ ግቢዉ የክፍፍል ምጣኔ ድርሻ ላይ የተናጠል

ተጠቃሚነቱ እስካልተረጋገተ ድረስ ቤቱ ብቻ በሊዝ አግባብ ይስተናገዳል፡፡

የመወያያ ርዕስ፡-ክፍል 6 የከተማ ቦታ የሊዝ ዋጋ እና የክፍያ አፈጻጸም

የከተማ ቦታ የሊዝ መነሻ ዋጋ

1. የከተማ ቦታ የሊዝ መነሻ ዋጋ የቅመራ ስልት

 በርካታ መሬትና መሬት ነክ ግብይቶችን

 የጊዜ ልዩነት ማስተካከያን

 የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ሁኔታዎችን


 ወቅታዊና የወደፊት የእድገት እንድምታ ጥናቶችን በማካሄድና

 የመሬት አጠቃቀምና የቦታ ደረጃን ታሳቢ በማድረግ መዘጋጀት አለበት

2. በዚህ አንቀፅ (1) ላይ የተጠቀሰው እንደተጠበቀ ሆኖ የሊዝ መነሻ ዋጋው፡-

 ቦታውን ለማዘጋጀት ለተነሽዎች የተፈፀመ የካሳ ክፍያ

 የቦታ ዝግጅት

 የመሰረተ ልማት ዝርጋታ

 የስራ ማስኬጃና

 ሌሎች ተጨባጭነት ያላቸው ተጓዳኝ ወጪዎችን የሚያገናዝብ ይሆናል፡፡

 የከተማ ቦታን በዋጋ ቀጠና ስለመክፈል እና አተገባበሩ፡-

1. በዚህ ደንብ አንቀፅ(28) (1) እና (2) ላይ በተደነገገው መሰረት የተሰላውን የከተማ ቦታዎችን ዝርዝር የሊዝ መነሻ

ዋጋ መሰረት በማድረግ የዋጋ ቀጠናን ካርታ መዘጋጀት አለበት፡፡

2. የሊዝ መነሻ ዋጋ ወቅታዊነቱ ተጠብቆ እንዲሄድ በየበጀት አመቱ/በየሁለት አመቱ የሚካሂዱትን የመሬት ሊዝ

ጨረታዎች ሁሉንም የቦታ ቀጠናና የአገልግሎት ዘመን አይነት ታሳቢ በማድረግ መዘጋጀት አለበት፡፡

3. ከዚህ በላይ (1) በተደነገገው መሰረት የተዘጋጀ የዋጋ ቀጠና ካርታ በወቅቱ አግባብ ባለው አካል በማፀደቅ በከተማው

መሰረታዊ ካርታና በፁሁፍ ተዘጋጅቶ በማንኛውም ተደረሽ የመረጃ መረብና ለእይታ በሚመች የማስታወቂያ ሰሌዳ

መደረግ አለበት፡፡

4. ከዚህ በላይ(3)መሰረት የፀደቀው የመነሻ ዋጋ በጨረታ በሚቀርቡና በምደባ በሚሰጡ ቦታዎች ላይ ተግባራዊ

ይሆናል፡፡

5. የትኛውም ቦታ ለቦታው ደረጃ በተቀመጠው የመነሻ ዋጋ በታች በጨረታ ሊተላለፍ አይችልም፡፡

6. ለራስ አገዝና አነስተኛ ገቢ ላላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች በሚወጣው የሀገሬቱ የከተማ ቤት ፖሊሲ መሰረት

በምደባ ለመኖሪያ አገልግሎት ለሚሰጥ ቦታ ለማኒፋክቸሪንግ፣ለከተማ ግብርናና ለቢዝነስ አገልግሎት እንደየ

አገልግሎቱ አይነት የተለያየ የመነሻ ዋጋ በማጥናት ተግባራዊ ይደረጋል፡፡

7. የከተሞች የሊዝ መነሻ ዋጋ ተመን ሁኔታ ቢሮ በሚያቀርበው ዝርዝር ጥናት ላይ ተመሰርቶ በመመሪያ የሚወሰን

ይሆናል፡፡
8. ከዚህ በላይ የተመለከተውን እንደተጠበቀ ሆኖ በአሁኑ ጊዜ የሊዝ መነሻ ዋጋ ባላቸው ከተሞች የተወሰኑ አስፈላጊ

የሆኑ ማስተካከያዎችን በማድረግ አዋጅ ከወጣበት ቀን ጀምሮ አስከ ሁለት አመት ድረስ ባለው ጊዜ መነሻው

ሳይሻሻል ሊቆይ ይችላል፡፡

መወያያ ርዕስ፡- የአብከመ ነባርና አዲስ የመኖሪያ ቤት ህብረት ስራ ማህበራትን የመኖሪያ ቤት ግንባታ ቦታ አቅርቦት፣አሰጣጥና

ግንባታን ለመወሰን ተሻሽሎ የወጣ ክልል መስተዳደር ም/ቤት መመሪያ

መመሪያ ቁጥር 28/2009

 የመኖሪያ ቤት ህብረት ስራ ማህበር አባልነት ምዝገባ መስፈርቶች አጠቃላይ የአባላት ምዝገባ መስፈርቶች

1. እድሜ ከ 18 አመት እና ከዚያ በላይ የሆነ በህግና በፍ/ቤት ያልተከለከለ ኢትዮጵያዊ

2. በሚደራጅበት ወይም በሚኖሩበት ከተማ በተከታታይ ሁለት አመት ነዋሪ የሆነ እንዲሁም የመንግስት ሰራተኛ ከሆነ

ደግሞ በሚገኝበት ከተማ በሚገኙ ተቋማት ውስጥ ቢያንስ ሁለት አመት በቋሚነት ተቀጥሮ የሰራና እየሰራ

3. በንዑስ አንቀፅ 2 ስር የተገለፀው እንደተጠበቀ ሆኖ በስራቸው ጠባይ ቋሚ የመኖሪያ አድራሻ የሌላቸውን የመከላከያ

ሰራዊት፣የፊደራል ፖሊስ፣የክልሉ ልዩ ሃይል የቀይታ ጊዜው የማይመለከታቸው ሆኖ የመሬት አሰጣጡን በተመለከተ

ቀጣይ ራን ችሎ በሚወጣው መመሪያ ይወሰናል፡፡

4. ለሁለት ተከታታይ አመታት ከታማው ውስጥ ባይኖርም በስራ፣በትምህረት፣በህክምና ምክንያት ከከተማው ውጪ

የኖረበትን ተጨባጭ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፡፡

5. የህንረት ስራ ማህበር አባልነት መመዝገቢያ ክፍያ መክፈል የሚችል፡፡

6. ከ 100 ሺ እና በላይ ህዝብ በሚኖርባቸው ከተሞች የቤቱን የግንባታ ወጪ ሲመዘግቡ 20 ፕርሰን ሲቆጥቡና መሬት

ለመረከብ 10 ፕርሰንት በድምሩ 30 ፐርሰንት መቆጠቡ ሲረጋገጥ ማህበሩ ቦታ ተረክቦ ወደ ግንባታ ይገባል፡፡

በሌሎች ከ 100 ሺ ህዝብ በታች በሚኖርባቸው ከተሞች የቤቱን የግንባታ ወጪ ሲመዘገቡ 20 ፐርሰንት

መቆጠባቸው እንደተጠበቀ ሆኖ መሬት ለመረከብ 15 ፐርሰንት መቆጠቡ ሲረጋገጥ በድምሩ 35 ፐርሰንት መቆጠቡ

ሲረጋገጥ ማህበሩ ቦታ ተረክቦ ወደ ግንባታ ይገባል፡፡

7. ቀሪውን በሂደት በመቆጠብ በግንባታ ሂደትና ማጠናቀቂያ ወቅት የሚከፍል


8. ለመኖሪያ ቤት ህብረት ስራ ማህበሩ በምደባ የሚሰጠው ቦታ በመነሻ ሊዝ ዋጋ ሲሆን ማህበራቱ ቀድሞ የካሳ

የከፈሉት የገንዘብ መጠን ከሊዝ መነሻ ዋጋው ታሳቢ ይናል፡፡ ይህንን ለማድረግ ፈቃደኛ የሆነ፡፡

9. የህብረት ስራ ማህበሩ አላማና ምሆዎችን ለማክበርና የማህበሩን መተዳደሪያ ደንብ ለመቀበል ፈቃደኛ የሆነ

10. በመንግስት በተዘረጉት ሌሎች የቤት ልማት ፕሮግራሞች ላይ በራሱም ሆነ በትዳር ጓደኛው ስም ተጠቃሚ ያልሆነ

ወይም ለመጠቀም ያልተመዘገበ ወይም ተመዝግቦም ከሆነ ምዝገባውን መሰረዙን ወይም መተውን ግዴታ መግባት

የሚችል፡፡

11. የሚሰራው ስራ የታወቀ ሆኖ የመቆጠብ አቅሙ እንደ ማህበር አባል የሚኖርበትን ድርሻ በመክፈል ለመገንባት አቅም

ያለው መሆኑን ተገምግሞ በከተማ አስተዳደሮች በየከተማ አስተዳደሩ በመሪ ማዘጋጃ ቤቶች በማዘጋጃ ቤቱ ስራ

አስፈፃሚ እንዲሁም በንዑስና በታዳጊ ከተሞች በወረዳው አስተዳደር እየተረጋገጠ እና እየተወሰነ እንዲገኙ

ይደረጋል፡፡

የመወያያ ርዕስ፡- የቦታ ስፋት የቤቶች አይነት የግንባታ ዋጋና የአባላት ብዛት

1. የቦታ ስፋት፡- በማህበራት ልማት የትግበራ ማዕቀፍ በተቀመጠው አግባብ በከተማ ደረጃ የቦታ መጠን፡-

 በመሪ ማ/ቤት፣በን/ማ/ቤትና ታዳጊ ከተሞች እስከ 250 ካ/ሜ

 በመካከለኛና አነስተኛ ከተሞች እስከ 150 ካ/ሜ

 በሜትሮፖሊታን ከተሞች እስከ 100 ካ/ሜ የቦታ መጠን በቤት ስራ ማህበር ተደራጅተው ለመጡ ማህበራት

የሚስተናገዱ ይሆናል፡፡

2. የቤቶች አይነት፡-

 የሚገነባው የቤት አይነት እንደየከተማው ደረጃ ሊለያይ ይችላል፡፡ በሜትሮፖሊታን ከተሞች G+1 እና በላይ ሆኖ ፊትና

ኋላ በሆነ የጋራ ግድግዳና መሰረትን መሰረት አድርጎ ዝቅተኛው 4 ሰው በማድረግ ብሎኩ እንደሚይዘው የቦታ መጠን

የሚሰራ ይሆናል፡፡
 በመካከለኛና በዞን ዋና ከተሞች G+0 እና በላይ በሌሎች አነስተኛ ከተሞች ቪላ ወይም ታውን ሃውስ መሆን

ይኖርበታል፡፡

 በሜትሮፖሊታን ከተሞች በማህበር በመደራጀት ግራውንዱን ንግድ በማድረግ በጋራ ኮንዶሚኒየም ለመገንባት

የሚመጡ ማህበራት ቅድሚያ ይሰጣቸዋል፡፡

 በሜትሮፖሊታን ከተሞች ዙሪያ የሚገኙ ሳተላይት ከተሞች የሚደራጁ ማህበራት አቅማቸውን ያገናዘበ የእንጨት ቤት

እና ከዛ በላይ መገንባት ይችላሉ፡፡ ከተማ አስተዳደሩ ሳተላይት በመሄድ ለመገንባት ፍላጎት ያላቸውን ዜጎች በስራ

ሁኔታ እና አቅምን ያገናዘበ አውጥቶ እንዲስተናገድ ያደርጋል፡፡

 የቤቶች አማካኝ ስፋት ባለአንድ መኝታ ክፍል ቤት 45 ካ/ሜ ባለሁለት መኝታ ክፍል ቤት 65 ካ/ሜ ባለ ሶስት መኘውታ

ክፍል ቤት 80 ካ/ሜ በአማካኝ ይሆናል፡፡

 የዲዛይኑን አይነት በራሳቸው መርጠው ለሚያሰሩና አቅምና ፍላጎት ላላቸው ማህበራት የቤቶች አማካኝ ስፋት ከላይ

በአንቀፅ 10 ንዑስ አንቀፅ 5 የተገለፀው ካ/ሜ በላይ የግንባታ አቅም ካላቸው የሚያሲዙት የገንዘብ መጠን ተሰልፈቶ

የሚጨመር ይሆናል፡፡

 በአነስተኛ ከተሞች በራስ አገዝ የሚገነቡ ቤቶች አንድ ክፍል ከተሰራ በኋላ እያደገ የሚሄድ ይሆናል፡፡
የውይይቱ ርዕስ፡- የቤቶች ግንባታ ዋጋ

 የሚገነባው ቤት ቢላ ሆኖ ስፋቱ በአንቀፅ 10(2)የተገለፀው ከሆነ፡-

1. ለባለ አንድ መኝታ ክፍል ቤት ብር 90,000 ለባለሁለት መኝታ ክፍል ቤት ብር 130,000 እና ለባለ ሶስት መኝታ ክፍል

ቤት 160,000 ብር ይሆናል፡፡

2. በራስ አገዝ የመኖሪያ ቤት ህ/ስራ ማህበር የሚገነቡ ቤቶች የቤቶች የግንባታ ዋጋ በጋራ የሚሰራ 20 ካ/ሜ ክፍል ታሳቢ

በማድረግ ብር 32,000 ይሆናል፡፡

3. ከላይ አንቀፅ 11.1 እና 2 የተጠቀሰው የመነሻ ዋጋ ሲሆን እንደ አካባው ሁኔታ ሊለዋወጥ እንደሚችል ታሳቢ መደረግ

አለበት፡፡

4. የዲዛይን አይነት በራሳቸው መርጠው ለሚያሰሩ የቤት ግንባታ ዋጋ በዚህ አንቀፅ ንዑስ አንቀፅ 11.1 የተጠቀሰው ሊሆን

አይችልም፡፡ሆኖም ማህበሩ የሚያቀርበው ዲዛይኑን መሰረት በማድረግ የሚመለከተው አካል በሚገምተው የግንባታ ዋጋ

ይሆናል፡፡

5. ግንባታው የሚከናወነው ለልማት ተነሽዎች ቦታ ላይ ከዋለ ከቤቱ ግንባታ ዋጋ በተጨማሪ ለማስነሻ የካሳ ክፍያ በህብረት

ስራ ማህበሩ አባላት የሚሸፈን ይሆናል፡፡

6. የቤቶች ግንባታ ዋጋ የማጠናቀቂያ ስራንና ወለድን አያካትትም ዋጋው በወቅቱ ለሚኖረው የገበያ ዋጋ ሊጨምር/ሊቀንስ

እንደሚችል ታሳቢ መደረግ ይኖርበታል፡፡

 መኖሪያ ቤት ህ/ስራ ማህበራት አባላት ቁጥር በ 2004 ዓ.ም በማዕከላዊ ስታስቲክ ኤጄንሲ ይፋ በተደረገው የከተሞች

ህዝብ ብዛት መረጃ መሰረት፡-

1. የህዝብ ብዛታቸው ከ 100 ሺ በላይ በሆኑ ከተሞች አንድ የመኖሪያ ቦታ ህብረት ስራ ማህበር ዝቅተኛው ከ 14 ያላነሱ

ከፍተኛው 24 አባላት ይኖሩታል፡፡

2. የህዝብ ብዛታቸው ከ 100 ሺ በታች በሆኑ ከተሞች አንድ የመኖሪያ ቤት ህብረት ስራ ማህበር ከ 10 ያላነሱ ከ 24

ያልበለጡ አባላት ይኖሩታል፡፡


3. በዚህ አንቀፅ ከ 1-2 የተጠቀሱት ቢኖሩም አደራጁ መስሪያ ቤቱ በጥናት በተረጋገጠ አዋጭ የሆነውን የመነሻ ቁጥር

በአደረጃጀት መመሪያው ሊወሰን ይችላል፡፡

4. ከ 2,000 ህዝብ በታች ባላቸው ከተሞች በማህበር መደራጀት አይጠበቅም

5. ሁሉም የመኖሪያ ቤት ህብረት ስራ ማህበራት የአባላት ባዛት ሙሉ ቁጥር መሆን አለበት፡፡

የመወያያ ርዕስ፡- የካይዘን ሽግግርና የትግበራ አቅጣጫ በኢትዮጵያ

1.1 የኢትዮጵያ ካይዘን ኢንስቲትዩት አመሰራረት

እ.ኤ.አ 2008 ግብፅና ቱኒዚያ በጃፓን አጋዥነት የካይዘንን የስራ አመራር ፍልስፍና ተገበሩ ስለነበር የዚያን ውጤት ሪፖርት

ከጃፓን መንግስት ጋር ሲገመግሙ የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስተር አቶ መለስ ዜናዊ ተገኝተው ጉዳዩን ይከታተሉ ነበር፡፡

እርሳቸውም የካይዘን የስራ አመራር ፍልስፋና ለሀገራቸው እንደሚጠቅም ለመገንዘብ ጊዜ አልወሰደባቸውም ከጃፓን የካይዘን

ምሁራን ጋራ በጉዳዩ ላይ በስፋት ከተወያዩ በኋላ የካይዘን የስራ አመራር ፍልስፍናን ወደ ኢትዮጵያ ለማስገባት ወሰኑ፡፡ድጋፍ

እንዲደረግላቸውም የጃፓንን መንግስት ጥያቄ አቀረቡ፡፡የጃፓን መንግስትም አወንታዊ ምላሽ ስጡ በጃፓንና ኢትዮጵያ መካከል
በተደረገው ስምምነት መሰረት የካይዘን የሙከራ ትግበራ ፕሮጀክት ተቀረፀ፡፡በጃፓን አለምአቀፍ ትብብር ኤጄንሲ አማካኝነት

ለሀገራችን ድጋፍ እንዲሰጡ ከተላኩ የካይዘን አማካሪዎች ጋር በመሆን በአዲስ አበባና አንድ አመት ኪሎ ሜትር ዙሪያ የሚገኙ

30 ኩባንያዎች ተመርጠው ከጥቅምት 2002 እስከ ግንቦት 2003 ዓ.ም የሙከራ ትግበራ ተከናወኑ በሙከራ ትግበራቸውም ጥሩ

ውጤት ከመገኘቱም በላይ የካይዘን ተሸጋጋሪነቱና ጠቀሜታ አረጋገጠ፡፡ሙከራውን የተገበሩ ኩባንያዎችም በአመራሩና

በሰራተኛው መካከል ጥሩ የአመለካከት ለውጥ ስላአመጣላቸው የምርታቸው ጥራት አይነትና ምርታማነትን ጨመረ፡፡በዚህም

ኩባንያዎችም ሆኑ ሰራተኞች ተጠቃሚ ሆኑ፡፡

በሙከራ ትግበራው በተገኘው አበረታች ውጤት መሰረት መንግስት የፍልስፍናውን ልማታዊ ሚና በመገንዘብና ለልማታዊ

መንግስት አመራር ያለውን አመቺነት በመረዳት የካይዘን ፍልስፍና የአመራር ፍልስፍናው እንዲሆን ወሰነ፡፡ሌሎችን የለውጥ

መሳሪያዎች ከዚህ ፍልስፍና ጋር በማጣጣም መጠቀም እንደሚገባም አቅጣጫ አስቀመጠ፡፡በቀጣይነት ፍልስፍናውን

ለማሸጋገር፣ለማጣጣምና ለማሰራት የኢትዮጵያ ካይዘን ኢንስቲትዩት በሚኒስትሮች ም/ቤት ደንብ ቁጥር 256/2004

እንዲመሰረት አደረገ፡፡ኢንስቲትዩት በኢንዱስትሪው ልማትና በሌሎችም በርካታ ዘርፎች ህዝባዊና መሰረተ ሰፊ የጥራትና

ምርታማነት ንቅናቄ በመፍጠር ቀጣይነት፣ተከታታይነትና ፈጣን የተሻለ ለውጥ በማምጣ ምርታማነትና ጥራትን ማሳደግ

የሀገሪቱ አንዱ ባህል እንዲሆን ቋሚ ተግባሩ አድርጎ እንዲያከናውን ይጠበቅበታል፡፡ ለዚህ ተልዕኮ ብቁ ለመሆን እንዲረዳው

አላማውን ከግብ ለማድረስ ማናቸውንም የስራ አመራር መሳሪያ ሁሉ እንደ አግባቡ መጠቀም የሚያስችል የአሰራር ስርዓት

በመዘርጋት ቀልጣፋ አገልግሎት መስጠት ይጠበቅበታል፡፡በመሆኑም ኢንስቲትዩቱ ለተገልጋዮች ተገቢውን

እገዛ፣ክትትል፣ግምገማና ድጋፍ ለማድረግ ይህንን የካይዘን ልማት ቡድን መመሪያ አዘጋጅቷል፡፡መመሪያ በየትኛውም ደረጃ

ያለፈፃሚ በቀላሉ እንዲረዳው ተደርጎ የተዘጋጀ ነው፡፡

1.2 የካይዘን አመራር ፍልስፍና

ካይዘን፡- የሚለው ቃል የተመሰረተው `kaj` እና `zen” ከተባሉ በጃፓንኛ ቃላት ሲሆን `kaj`ለውጥ ማለት ሲሆን

`zen”ማለት ደግሞ የተሻለ ማለት ነው፡፡ከዚህ አንፃር ካይዘን በቀጣይነት ላይ የተመሰረተ የተሻለ ለውጥ ማምጣት የሚያስችል

የአመራር ፍልስፍና ነው፡፡ የካይዘን አመራር ፍልስፍና ቀጣይነትና ተከታታይነት ያለው የተሻለ ለውጥ በማምጣት ላይ የተመሰረተ

ሲሆን ፍልስፍናው ከሁሉም በላይ የዐመለካከት ለውጥ ማምጣት የሚያስችል ነው፡፡ ነባራዊ ሁኔታን በመረዳት አመራሩንና

ሰራተኛውን አሳታ በማድረግ ለተሻለ ለውጥ በጥራትና ምርታማነት ያነሳሳል፡፡ዋና የለውጥ ተዋናይ አድርጎ የሚወሰደውም የሰው

ሀይሉን በተለይም ፈፃሚውን ነው፡፡ ሰራተኛው የካይዘን አመራር ፍልስፍና በቂ ግንዛቤ ካለው ቀጣይነት ላለው የተሻለ ለውጥ
በንቃት ተሳታ ይሆናል፡፡የካይዘን አመራር ፍልስፍናን ለመረዳት በቅድሚያ በጃፓን በሂደት የደበሩ የስራ አመራር የጥራት

ምርታማነት ማሻሻያ ዘዴዎችን ከመሰረታቸው መገንዘብ ያስፈልጋል፡፡

ጃፓን የኢንዱስትሪዎች ዘርፍ ያሳደገችው በአነስተኛና በመካከለኛ ኢንዱስትሪዎች ላይ ትኩረት ሰጥታ በመስራቷ ነው፡፡ ለዚህም

የካይዘን አመራር ፍልስፍናን በእጅጉ ተጠቅማበታለች፡፡ ከሁለተኛውም የአለም ጦርነት በኋላ ጃፓን ለዓለም ገበያ ታቀርብ

የነበረውን ምርት ከምዕራብያዊያን/አሜሪካና አውሮፓ/ምርት ጋር ሲነፃፀር ጥራቱ በጣም ዝቅተኛ በመሆኑ ተወዳዳሪ መሆን

አልቻለም ነበር፡፡ይህን የጥራት ችግር ለመፍታት የምዕራባዊያንን ተሞክሮ ለመቅሰም ወሰነች፡፡ በተለያዩ ሙያዎች የተሰማሩ

ምሁሮቹ ወደ አውሮፓን አሜሪካ በመላክ የእነሱን አሰራርና ቴክኖሎጂ ቀስመው እንዲመለሱ አደረገች፡፡የቀሰሙትንም እውቀት

ከራሷ ተጨባጭ ሁኔታ ጋር አጣጥመው እንዲቀምሩ ካደረገች በኋላ ካይዘን የሚል ስያሜ ሰጠች፡፡ ዜጎቿም ካይዘንን ተግተው

በመተግበር የአመራር ፍልስፍናአቸው ባህላቸውና የህይወት መመሪያቸው በማድረግ ሀገራቸው በጥራትና በምርታማነት ላይ

የተመሰረተ ፈጣን የቴክኖሎጂና የኢኮኖሚ ልማት እንደታስመዘግብ አድርጎ በአሁኑ ወቅት ጃፓን በዓለም በኢኮኖሚ ከበለፀጉ

ሀገራት ማለትም ከአሜሪካና ቻይና በመቀጠል በሶስተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች፡፡

የውይይቱ ርዕስ፡- የሊዝ ፋይናንሲንግና የአነስተኛ መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ትርጉምና አገልግሎት

ትርጉም(Definition) ሊዝ ፋይናንሲንግ ማለት ባንኩ ለአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች የካፒታል ዕቃዎችን ገዝቶ በዱቤ

ግዥ ስርዓት ለኪራይ የሚያቀርበው አገልግሎት ማለት ነው፡፡

አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ከተሰጠው ተልዕኮ አንፃር አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ማለት የእርሻ ፕሮጀክቶች የግብርና

ምርቶች ማቀነባበሪያ የመፈብረኪያ የሀገር ጉብኝት የማዕድናት ቁፋሮ የኮንስትራክሽ ሆነው ከስድስት በላይ ሰራተኞችን የያዘ

የሚቀጥሩ እንዲሁም አጠቃላይ ካፒታላቸው ከብር 500 ሺ እስከ 7.5 ሚሊየን የሆነ ማለት ነው፡፡
የሚከተሉት ንዑስ የኢኮኖሚ ዘርፎች በባንኩ የሊዝ ፋይንሲግ አገልግሎት የሚሰጣቸው ናቸው፡፡

1. የእርሻ ፕሮጀክቶች

 የመስኖ ርባታ

 ንብ ማነብ

 የወተት ምርቶች

 የዶሮ እርባታ

 የአሳ እርባታና የመሳሰሉት ናቸው፡፡

2. የእርሻ ውጤቶች ማቀነባበሪያ ኢንዱስትሪዎች

 የወተት ተዋፅኦ ማቀነባበሪያ

 የእንስሳት መኖ ማቀነባበሪያ

 የዶሮ ምርት ማቀነባበሪያ

 የቅመማቅም ከእፅዋት የሚገኙ መድሀኒቶችና ዘርቶች መጭመቂያና ማቀነባበሪያ

 የዓሳ ምርት ማቀነባበሪያ

 የምግብ ዘይት መጭመቂያና ማቀነባበሪያ

 የዱቄት ፋብሪካ

 የአትክልትና የፍራፍሬ ምርት ማቀነባበሪያ እና የመሳሰሉት

3. የመፍብረኪያ ኢንዱስትሪ

 የቆዳና ቆዳ ውጤቶች ማምረቻ

 የጨርቃ ጨርቅ ማምረቻ

 ብረታና ብረት ያልሆኑ ዕቃዎች ማምረቻ

 የዕደ ጥበብ ውጤቶች ማምረቻ

 ሳሙናና የፅዳት ዕቃዎች ማምረቻ


 የጌጣጌጦች ማምረቻ

 የቀለም ማምረቻና የመሳሰሉት

4. የግንባታ ኢንዱስትሪዎች

 ብሎኬት ቱቦና ጡብ ማምረቻ

 ባዞላ ማምረቻ

 ሴራሚክ ማምረቻ

 ጅብሰም ማምረቻ

 የግንባታ ዕቃዎች ማምረቻና የመሳሰሉት ናቸው፡፡

5. የማዕድን ልማት

 ዕብነ በረድ ማምረቻ

 የወርቅና የከበሩ ማዕድናት ማምረቻ

 ጠጠር ማምረቻና የመሳሰሉት ናቸው፡፡

 የሊዝ ፋይናንሲንግ አገልግሎት

 ባንኩ የሊዝ ፋይናንሲንግ አገልግሎት የሚሰጣቸው አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ሆነው በመንግስት

የኢኮኖሚ የትኩረት መስኮች ላይ የሚሰሩና የካፒታል ዕቃዎችን ለፕሮጀክቶቻቸው መጠቀም የሚችሉ መሆን

አለባቸው

 ባንኩ ለአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፓራይዞች ለማምረት የሚያገለግሉ የካፒታል ዕቃዎች ገዝቶ በኪራይ

መልኩ ያቀርባል፡፡
የውይይቱ ርዕስ፡-የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች የማምረቻ፣የማሳያና የመሸጫ ማዕከላት አጠቃቀምና እስተዳደር

መመሪያ

ይህ መመሪያ የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች የማምረቻ የማሳያና የመሸጫ

ማዕከላት አጠቃቀምና አስተዳደር መመሪያ ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል፡፡

ሌላ ትርጉም የሚሰጠው ካልሆነ በስተቀር በዚህ መመሪያ ውስጥ፡-

 ማዕከላት ማለት ለማኒፋክቸሪንግ ዘርፍ አገልግሎት የሚውሉ በመንግስት የተገነቡና የሚገነቡ የማምረቻ፣የማሳያና

የመሸጫ ዕንጦች ናቸው፡፡

 ማምረቻ፣ማሳያና መሸጫ ማዕከላት ማለት፡-በመንግስት ተገንብተው የማምረቻ፣የማሳያና የመሸጫ ዕንዎች ናቸው፡፡

 አንቀሳቃሽ ማለት በግል በህ/ስራ ማህበርና በንግድ ማህበር በመደራጀት በጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይ ስትራቴጂ

መሰረት ባለቤት በመሆን በማምረት ተግባር ላይ የተሰማሩ ሀብት ፈጣሪና ተጠቃሚ የሆኑ ግለሰብ፣የህ/ስራ

ማህበር/የንግድ ማህበር ባለቤት ናቸው፡፡

 የምርት ማምረቻና ማሳያ መሸጫ ትኩረት በተሰጣቸው በማኒፋክቸሪንግ ዘርፍ የጨርቃጨርቅና ስፊት ቆዳና

የቆዳ፣ውጤቶች ፣አግሮፕሮሰሲንግ፣የብረታ ብረትና የኢንጂነሪንግ ምርቶች፣የእንጨት ስራዎች፣ባህላዊ የእደጥበብና

የጌጣጌጥ ስራዎች የተሰማሩት ኢንተርፕራይዞች/አንቀሳቃሾች የሚያመርቱበት የሚያሳዩበትና የሚሸጡበት ቦታ ነው፡፡


ጥቃቅንና ኢንተርፕራይዝ ማለት፡-

 በኢንዱስትሪ ዘርፍ በማፋክቸሪንግ፣በኮንስትራክሽን፣በማዕድን፣የኢንተርፕራይዙን ባለቤት ጨምሮ እስከ

5/አምስት/ሰዎች ቀጥሮ የሚያሰራ/የጠቅላላ ንብረታቸው በጠን በዋጋ ከብር 100 ሽ ያልበለጠ ይሆናል፡፡

 በአገልግሎት ዘርፍ በችርቻሮ ንግድ፣ትራንስፖርት፣ሆቴልና ቱሪዝም፣የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂና የጥገና

አገልግሎት፣የኢንተርፓራይዙን ባለቤት ጨምሮ እስከ 5/አምስት/ሰዎች ቀጥሮ የሚያሰራ/የጠቅላላ

ንብረታቸው መጠን በዋጋ በብር 50 ሽ ያልበለጠ ይሆናል፡፡

አነስተኛ ኢንተርፓራይዝ ማለት፡

 በኢንዱስት ዘርፍ ማኒፋክቸሪንግ፣ኮንስትራክሽን፣ም,ማዕድን፣ከ 6-30 ሰዎች ቀጥሮ የሚያሰራ/ጠቅላላ ንብረታቸው

መጠን በዋጋ ከብር 100 ሽአንድ እስከ ብር 1.5 ሚሊየን ያልበለጠ ይሆናል፡፡

 በአገልግሎት ዘርፍ በችርቻሮ ንግድ፣ትራንስፖርት፣ሆቴልና ቱሪዝም፣የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂና የጥገና አገልግሎት

ከ 6-30 ሰዎች ቀጥሮ የሚያሰራ/የጠቅላላ ንብረታቸው መጠን በዋጋ ከብር 50 ሽ አንድ እስከ 500 ሽ ብር ያልበለጠ

ይሆናል፡፡

የመመሪያው አላማ

 የመመሪያው ዋና አላማ የማምረቻ/የማሳያ የመሸጫ ህንፃችን በዘርፉ ተደራጅተው ህጋዊ ሰውነት ላገኙ ብቃት

ላላቸውና ግንባር ቀደም ለሆኑ ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች በኪራይ ለማስተላለፍ ግልፅ የአሰራር ስርዓት

መዘርጋት ሲሆን ዝርዝር ዓላማዎቹ


 አስፈፃሚ አካላት ተጠቃሚዎችን በመመልመል ረገድ ግልፅነትና ተጠያቂነት ያለው አሰራር እንዲከተሉ ለማድግ፣

የውይይቱ ርዕስ፡- የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ የማምረቻ የማሳያና የመሸጫ ማዕከላት አጠቃቀም አስተዳደር መመሪያ

ላይ ከባለፈው ሳምንት የቀጠለ

ክፍል ሁለት

የማዕከላት አይነቶች

 የጨርቃ ጨርቅና አልባሳት ማምረቻ ማሳያና መሸጫ

 እንጨትና ብረታ ብረት ማምረቻን ማሳያ መሸጫ

 የምግብና ምግብ ነክ ማምረቻ ማሳያና መሸጫ


 የቆዳና ቆዳ ውጤቶች ማምረቻ ማሳያና መሸጫ

 የእደ ጥበብ ውጤቶች ማምረቻ ማሳያና መሸጫ

 የአግሮ ፕሮሰሲንግ ማዕከላትንና

በሌሎች ዘርፎች የሚገነባባቸውን ማዕከላትንና በሂደት ኤጀንሲው በሌሎች የስራ ዘርፎች የሚገነባቸውን ማዕከላትን

ይጨምራል፡፡

የማዕከላቱ አጠቃቀምና አስተዳደር

 ማዕከላቱ የተገነቡትና በመገንባት ላይ ያሉት በመንግስት በጀት በመሆኑ ባለቤትነቱ የከተማ አስተዳደር ሆኖ

ከጥ/አ/ኢ/ል/ኤጀንሲ ማዕከላቱ/ህንፃው የሚገኙበት ከተማ ወይም ወረዳ አስተዳደር ጥቃቅንና አነስተኛ ኢ/ል/ጽ/ቤት

በስሙ መዝግቦ ይረከባል ከዚያም ህንፃው ለሚገኝበት የአንድ ማእከል አገልግሎት ጣቢያ በተጠሪነት እንዲያስተዳድረው

ያስረክባል፡፡

 የማምረቻ ማሳያና መሸጫ ማዕከላት ብቃት ላላቸው ኢንተርፕራይዞች ብቻ ቢበዛ ለ 5/አምስት/ዓመት በኪራይ

ይተላለፋል፡፡

 ኢንተርፕራይዞች የሚመለመሉትና ተመርጠው ወደ ማምረቻ ማዕከላት የሚገቡት ማዕከላቱ ከሚገኙበት ከተማ የአንድ

ማእከል አገልግሎት መስጫ

 ጣቢያ ጀምሮ ብቃትን ማዕከል ባደረገ መስፈርት ተመልምለው በጽ/ቤት ሲረጋገጥ እና በከተማ አመራሩ ሲፀድቅ ነው፡፡

 በማዕከላቱ ለኢንተርፕራይዞች በኪራይ የሚሰጠው የቦታ ስፋት እንደየስራ መስኩ የሚለያይ በመሆኑ በባለሙያ በጥናት

በሚቀርበው መረጃ መሰረት በኤጀንሲው ይወሰናል፡፡

 በከተማው ውስጥ በየትኛውም ቀበሌ ነዋሪ የሆኑ ኢንተርፕራይዞች በሚኖሩበት ቀበሌ የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ

ጣቢያ በብቃታቸው ተመልምለው በከተማው ጽ/ቤት ሲረጋገጥና በከተማ አመራሩ ሲፀድቅ ወደ ሌላ ቀበሌ ህንፃ

ተሻግረው የማእከሉ ተጠቃሚ ይሆናሉ፡፡

ኢንተርፕራይዞች መምረጫ መስፈርቶች

 እድገት ተኮር ምርቶች ለማምረት ከሚመከተው አካል ተገቢውን ፈቃድ አግኝተው ቢያንስ አንድ አመት በስራ ላይ

የቆዩና ዛሬም በስራ ላይ ያሉ


 አዳዲስና ቦታ ቆጣቢ ማሽኖች በራሳቸው ገንዘብ ወይም በመሳሪ ሊዝ /በብድር ገዝተው/ለመጠቀም ፈቃደኛ የሆኑና

ይህንኑ በጹሁፍ ያረጋገጡ

 ቢቻል በማህበሩ ተደራጁ ወይም ወደ ማዕከላቱ ከገቡ በኋላ ለስራ አመቺ በሆነ መንገድ ለመደራጀት ፈቃደኛ የሆኑና

የህንኑ በጹሁፍ ያረጋገጡ

 ካፒታላቸው በንግድና አገልግሎት ከሆነ ከብር 500,000 ብር በኢንዱስትሪና ኮንስትራክሽን ዘርፍ ከሆነ 1.5 ሚሊየን

ያልበለጠ

 ያላቸውን የስራ አመራርና የቴክኒክ ዕውቀት ለማስተላለፍ ማዕከሉን በጋራ ለማስተዳደርና ለመምራት ፈቃደኛ ሆነው

የገንዘብ የዕውቀትና የጉልበት አስተዋፅኦ ለማድግ ዝግጁ የሆነ

 የኢንተርፓራይዙ አንቀሳቃሾች ሙሉ ለሙሉ ባለቤት የሆኑና ይህንኑ መረጃ የሚያረጋግጡና የተቋማቸውን ወጪና ገቢ

በአግባቡ የሚይዙ መሆኑ የተመሰከረላቸው

 በተዘጋጁት ማእከላት ተጠቃሚ የሚሆኑት በታዳጊ/ባብቃት እድገት ደረጃ የሚገኙ መሆን ይኖርባቸዋል

 በስራቸው ህጋዊ ሰውነት/የንግድ ፈቃድ ያላቸው በብድር አመላለስ ፣በግብር አከፋፈል፣በመልካም የንግድቨ ስነምግባር

የሚታወቁና ለሌሎች አርያ መሆን የሚችሉ

 በሴቶች የሚመሩ ኢንተርፕራይዞች ቅድሚያ ይሰጣል መስፈርቱን አሟልተው እስከተገኙ ድረስ፡፡

 በስራቸው ብቃት ባላቸው ተወዳዳሪና ጥራት ያለው ምርት አምርተው ውጤት በማስመዝገብ ላይ የሚገኙ

ማኒፋክቸሪንግ ዘርፍ ለተሰማሩና መስፈርቱን ላሟሉ ቅድሚያ ይሰጣል፡፡


የውይይቱ ርዕስ፡- የገጠር ኢንዱስትሪያላይዜሽን ትራንስፎርሜሽንና የኢትዮጵያ ህዳሴ

መግቢያ

አገራችንን ከድህነት ከኋላቀርነት በአስተማማኝ ደረጃ ለማላቀቅና የህዝቡን የኑሮ ደረጃ በከፍተኛ ደረጃ

ለማሻሻል ወሳኝ ጉዳይ ከግብርና በመጀመር በኢንዱስትሪ የለማች ሀገር መገንባት እንደሆነ በማመን

ልማታዊ ዲሞክራሲያዊ መንግስታችን ጥራት ያላቸውና ውጠየታማ የልማት ፖሊሲና ስትራቴጂዎችን

ነድፏል፡፡ከእነዚህ መሰረታዊ ፓሊሲና ስትራቴጂዎች መካከልም የኢንዱስትሪ ልማት ፖሊሲና ስትራቴጂ

አንዱ ሲሆን ባለፉት አስራ ሁለት አመታት በዚሁ ፖሊሲና ስትራቴጂ በመምራት ፖለቲካ ኢኮኖሚውን

ለመቀየር ተንቀሳቅሰናል፡፡ያሰብነውን ያህል ባይሆንም የተወሰነ መልካም ውጤትም አምጥተናል፡፡ሀገራችን

የኢንዱስትሪ ልማት ስትራቴጂ በተነደፈው ጊዜ ግልፅ እንደሆነው ስትራቴጂው የሚነሳባቸውና

የሚገዛባቸው መርህዎች በጠራ አኳኋን ተቀምጠዋል፡፡በዚህም መሰረት በሀገራችን የሚካሄድ


ኢንዱስትሪያላይዜሽን የግል ባለሀብቱን በሞተርነት የሚቀበልና የሚያንቀሳቅስ መሆን እንዳለበት

ተሰምሮበታል፡፡አሁን በምንገኝበት የእድገት ደረጃ ግብርናና ኤክስፖርት መር የኢንዱስትሪ ልማት

አቅጣጫን መከተል መላው ህብረተሰብ ለኢንዱስትሪ ልማት በጋራ እንዲሰለፍና እንዲረባረብ ማድረግና

መንግስት ጠንካራ የአመራር ሚና የሚጫወትበት የኢንዱስትሪ ልማት አቅጣጫ መከተል የፖሊሲና

ስትራቴጂ ዋነኛ መነሻዎች ሊሆኑ እንደሚገባ መቀመጡ ትክክለኛነቱ የማያከራክር ነው፡፡ኢንዱስትሪ ልማት

ሰነዳችን በእነዚህ መነሻዎች ላይ በመመስረት ለልማቱ ወሳኝ እንደሆኑ የታመነባቸውን ሰባት ያህል

መሰረታዊ ስትራቴጂዎችን አስቀምጧል፡፡የፖሊሲና ስትራቴጂ ሰነዳችን እንደማንቸኛውም ስትራቴጂን

በትክክልየመግለፅ ችሎታ ያለው ሰነድ በአንድ በኩል ፖሊሲውንች የሚያስፈፅሙ ኃይሎችን ለይቶ እነዚህን

ለመገንባት በሌላ በኩል ደግሞ ፖሊሲውን የሚያደናቅፍ ኃይሎችን በመለየት እነዚህን ለማምከን በሚያስችል

ሳይንሳዊ ይዘት የተዋቀረ ነው፡፡በመሆኑም ለኢንዱስትሪ ልማትና ለልማታዊ ባለሀብት መጎልበት የተመቸ

ሁኔታ ለመፍጠር ሲባል የጥገኝነት አረቋን ማድረቅ ቀዳሚው የስትራቴጂው አካል ተደርጎ ተቀምቷል፡፡ በዚሁ

ማዕቀፍ ተረጋጋና ለልማት የሚያመች የማክሮ ኢኮኖሚ ሁኔታን መፍጠር ዘመናዊና ለልማት የተመቻቸ

የፋይናንስ ስርዓት መፍጠር አስተማማኝ የመሰረተ ልማት አገልግሎትን ማቅረብ የሰው ኃይል ስልጠናን

በብቃት በመፈፀም ለልማቱ አስፈላጊ የሆነውን የሰው ኃይል ማቅረብ ቀልጣፋና ልማትን የሚደግፉ

አስተዳደር መገንባትና ቀልጣፋ የፍትህ አስተዳደር ስርዓት መፍጠር ዋና ዋናዎቹ የስትራቴጂው አቅጣጫ

እንደሆኑ ተሰምሮበታል፡፡

የኢንዱስትሪ ልማት ሰነዳችን በመስኩ የምንመራባቸውን ስትራቴጂዎች ከመዘርዘር በተጨማሪ ልማታችንን

ለማፋጠን ልናተኩርባቸው በሚገባን ዋና ዋና ሴክተሮች ላይ የተሟላ ግልፅነት በሚፈጥር አኳኃን የተቀረፀ

ነው፡፡ከእነዚህ መሰረታ ጉዳዮች በመነሳት ሀገራችን በእርግጥም በጥራት የተነደፈ የኢንዱስትሪ ልማት

አቅጣጫ ባለቤት እንደሆነች ለመገንዘብ ይቻላል፡፡


የመወያያ ርዕስ፡- የመለስ አስተሳሰብና የገጠር ኢንዱስሪያላይዜሽን

የገጠር ኢንዱስትሪያላይዜይሽን ፅንሰ ሃሳብ ምን እንደሆነ ዘርዘር አድርጎ ከመመልከት በፊት በጉዳዩ ላይ

ከዚህ ቀደም በጓድ መለስ የተካሄዱ ጥናቶችና ተቀመጡ አቅጣጫዎች አጠር አድርጎ መመልከት ለተሟላ

ግልፅነት ያግዛል፡፡የገጠር ኢንዱስትሪያላዜሽን በተመለከተ በጓድ መለስ በተዘጋጁ የአማረኛ ሰነዶች ላይ

በፅንሰ ሃሳብ ደረጃ በዝርዝር ከቀረቡት መሰረታዊ ኢንዱስትሪ የገጠር ኢንዱስትሪ ጭምር ልማት ፅንሰ

ሃሳቦች ባሻገር ቃል በቃል የገጠር ኢንዱሰትሪያሌዜሽን የሚል አገላለፅ አልተጠቀመበትን ማለት ስራዎቹ

ሁሉ በገጠር ኢንዱስትራላይዜሽንን የሚያካትቱ ወይም የሚፈቅዱ አልነበሩም ማለት አይደለም፡፡ጓድ

መለስ በመሰረተ ሃሳብ ደረጃ በገጠር ኢንዱስትራይሌዜሽን ላይ አላፃፈም ወይም ጥናት አላደረገም

ማለትም አይደለም፡፡እነዚህ እንደተጠበቁ ሆኖ ጓድ መለስ በዓለም አቀፍ ኢኮኖሚክስ ትምህርት

ለማስተርሱ ማሟያ የውድቀት መዳረሻው ኚዮ-ሊበራላዊ ፈለግና የአፍሪካ ህዳሴ በሚል ርዕስ ባቀረበው

ጥናታዊ ፁሁፍ ላይ በምስራቅ እስያ ነብሮች በተለይ ደግሞ በታይዋን ገጠር ትራንስፎርሜሽን ላይ

በማተኮር ባካሄደው ጥናት ከገጠር ወደ ከተሜነት ከግብርና ወደ ኢንዱስትሪው ልማት በተካሄደው ሽግግር

የኮሪያና የታይዋን ጉዞ በመሰረቱ በገጠር ኢንዱስትሪ ማስፋፋት ጉዞ እንደሆነ አስደግፎ አረጋግጧል፡፡ ሰፊ

መልካምድራ ሽፋን ያለው የግብርና ዕድገት ያለውና ይህን ተከትሎ የሚከናወን የከተሞች መስፋፋት
ከፍተኛ ብዜታዊ ተፅኖ አለው፡፡ የግብርና ዕድገትና ኮመርሻላይዜሽንን ተከትሎ የሚፈጠረው ዕድገትን

ከግብርና ውጪ ያሉ ኢንዱስትራላዊ ኢንተርፕራይዞችን የሚያሳድግ ይሆናል፡፡ በመጀመሪያዎቹ

አመታት ኢንዱስትራይሌሽን ጨምሮ የሚኖረውን እድገት የሚያመጣው ዋና ሞትር የግብርና እድገት

ነው፡፡ በሀገሪቱ የቁጠባ ምጣኔ እጅግ ከፍተኛ ነበር፡፡

በታይዋን የነበረው ከውጪ የሚገቡ ምርቶችን የመተካት ምዕራፍ ይህን በመሰለ የግብርና ስኬታማ

ፈጣን እድገት ላይ የተመሰረተ ነው፡፡

መለስ በገጠር ኢንዱስትሪ ልማት ላይ ይህን የመሰሉ ግልፅ ሃሳቦችን በማስቀመጥ ባቻ ሳይወሰን በገር

የተፈጠርው ካፒታል ከግብርና ወደ ገጠር ኢንዱስትሪ ስለተሸጋገረበት መንገድም ግልፅ ሃሳቦችን

አመላክቷል፡፡

በኢንዱስትሪና በግብርና መካከል ያለው ጥምረት ትርፍ ሀብት ከግብርና ወደ ኢንዱስትሪ የሚሸጋገርበትን

ሁኔታ የሚያካትት ነው፡፡

እነዚህ እንደተጠበቁ ሆኖ ዋናው ሽግግር የተከናወነው በገጠር ከግብርና እድገት ጋር ተየያዞ ለኢንዱስትሪ

ምርቶችነ አገልግሎቶች መፈጠር የጀመረውን ፍላጎት ተከትሎ ነው ይላል፡፡

በገጠር ግብርና ነክ ያልሆኑ የስምሪት መስኮች እንዲስፋፉና የመስሪያ ማህበራትን ሀብታም አ/አደሮችን

አጠናቅሮ መቀጠል አለበት፡፡

የገጠር መሰረተ ልማት በተለይ ገጠር መንገድና በተለይ ደግም የገጠር ኤሌክትሪኬሽን ማስፋፋት መርሃ

ግብር ዋናኛ ፋይዳ በገጠር የማኒፋክቸሪንግ አቅምን ለመገንባት እንደሆነም በዝርዝር የቀረበና የሚታወቅ

ነው፡፡
ይህን መነሻ በማድረግ ስለገቢያ ስርዓት ባህሪያት ጥቂት መሰረታዊ ጉዳዮችን በመመልከት የሌሎች

ሀገሮችን የገጠር ኢንዱስትሪያላይዜሽን ልምድ ወደ ማየት እንሸጋገር

የመወያያርዕስ፡- የገበያ ስርአት መሰረታዊ ባህሪያትና ልዩ ልዩ መልኮች፣

ካፒታሊስታዊ የገበያ ስርአት በአለማችን ከሰፈነ አምስት መቶ ያህል አመታት አስቀጥሯል፡፡ ከ 16 ኛው

ክፍለ ዘመን ጀምሮ መጀመሪያው እንደፍሎረንስና ቬንስ በመሳሰሉ የጣሊያን ከተሞች ከዚያን

የተባበሩት የደች መንግስታት መሪነት በአለማችን መስፋፋት የጀመረው ካፒታሊዘም በመሰረቱ

አውሮፓዊ መነሻ ያለው ሰርአት ነው፡፡ የገበያ ስርአት የበላይነት በያዘባቸው አገሮች ሁሉ በመሰረታዊ

ባህሪው ተመሳሳይ ሲሆን በአንዳንድ መልኮቹ ደግሞ ከአገር አገር የሚለያይ ስርአት ነው፡፡ እነዚህን አንድ

በአንድ መመልከት በጉዳዩ ላይ የተሟላ ግልፅነት ለማስያዝ ያስችላል፡፡

እንደእኛ በዋነኝነት በግብርናና ገጠር ላይ ተወስነውና በኋላ ቀርነት ተተብትበው ለሚኖሩ ህዝቦች

ካሉበት ዝቅተኛ ደረጃ ለመላቀቅ የሚቻለው በቅድሚያ ግብርናና ገጠሩን በማልማት ቀጥሎ ደግሞ

ኢንዱስትሪውንበከፍተኛ ፍጥነት ስፋት በማልማት እንደሆነ ይታወቃል፡፡ከመታወቅም አልፎ ባለንበት

የእድገት ደረጃ ግብርና መር የኢንዱስትሪ ልማት አቅጣጫ በማለት የነደፍነው መሰረታዊና አማራጭ

የሌለው አቅጣጫ በዚህ ልማታዊ መንገድ ምሳሶነት የተዋቀረ ነው፡፡ በእርግጥ በአለማችን ከቅድመ

ካፒታሊስት ህብረተሰብ ወደ ዳበረና የበለፀገ ህብረተሰብ የተካሄደው ሽግግር ሁሉ የተሳካው ከግብርናና

ከገጠር በመጀመር ብቻ አይደለም፡፡ ለምሳሌ እንግሊዝ በረዥም ርቀት የውጪ ንግድ ጀምራ ካፒታል

በማጠራቀም ኢንዱስትሪዋን ካለማች በኋላ ግብርናዋን በመጨረሻም በጣም ዘግይታ ነው ነው

ያለማችው፡፡ ነገር ግን በብዙ ሌሎች አገሮች እንደታየው


በተለይ ደግሞ ሰፊው ህብረተሰብ በገጠርና በግብርና መስክ ተሰማርቶበሚኖርባቸው ድሃና ኋላቀር

ሃገሮች ከግብርናና ገጠር ከመጀመር ወይም ግብርና መር የእድገት አማራጭን ከመከተል ውጪ የተሸለ

አማራጭ የለም፡፡ እኛን በመሰሉ አገሮች ተጨባጭ ሁኔታ የሚካሄደው ልማታዊ እንቅስቃሴ ውጤታማ

ሊሆን የሞችለው እስከ ተወሰነ ጊዜ ድረስ ግብርና መር የኢንዱስትሪያሌዜሽን አቅጣጫን በመከተል

ብቻ ነው፡፡ የህ ወሳኙ የእድገት መነሻ መሆኑ እንደተጠበቀ ግን ማንኛውም ህብረተሰብ ለአስተማማኝ

ዘላቂ እድገት መብቃት የሚችለው የማታ ማታ በኢንዱስትራሌዜሽን መስፋፋት ብቸ ነው፡፡ የአገራዊ

ልማት ዘለቄታዊ ግብ ኢንዱስትራሌዜሽንን እውን ማድግ የሚሆነውም በዚህ ምክንያት ነው፡፡ ይህን

መነሻ በማድረግ ከሁሉ በፊት በኢንዱስትሪ የለማ ሃገር የሚገለፅባቸው ዋና ዋና ባህሪያት ምን

እንደሚመስሉና በኢንዱስትሪያሌዜሽን መሰረታዊ ፅንሰ ሃሳቦች ዙሪያ መግባባት ያስፈልጋል፡፡


የመወያያ ርዕስ፡- የዳበረ የገበያ ስርአት ስኬታማ የመጀመሪያ ደረጃ የካፒታል ክምችት በማካሄድ

የሚገነባ መሆኑ

በገቢያ የሚመራው የኢኮኖሚ ስርአት በተለይ መጀመሪያ በእንግሊዝ የተካሄደውን የኢንዱስትሪ

አብዮት ተከትሎ በአውሮፓ ውስጥ ታላቁን የኢንዱስትሪ አብዮት በመቀስቀስ አውሮፓን ወደ

ተሟላ ካፒታሊስታዊ የገበያ ስርአት ለመቀየር እንደበቃ የሚታወቅ ነው፡፡ የአውሮፓው

የኢንዱስትሪ አብዮት እንዲካሄድ ወሳኝ ሚና የተጫወተው ደግሞ በእግሊዝ ሀገር የተካሄደውና

የመጀመሪያው የካፒታል ክምችት በመባል የሚታወቀው ሂደት ነው፡፡የዳበር ካፒታሊስታዊ የገበያ

ስርዓት የመገንባት ጉዳይ በመሰረቱ የቴክኖሎጂያዊ አቅም ግንባታ እንደሆነው ሁሉ መነሻ ነጥብ

ደግሞ የመጀመሪያ ደረጃ የካፒታል ክምችት ነው፡፡ ስለሆነም ስለገበያ ስርአት ግንባታ ሲታሰብ

የመጀመሪያ ደረጃ የካፒታል ክምችት ሂደትን በአንድ ወይም በሌላ መንገድ በስኬት መፈፀም

ነው፡፡ለኢንቨስትመንት ተፈላጊ የሆነውን መነሻ ካፒታል ራሱን የቻለ የዕድገት ምዕራፍ ተደርጎ

በሚወስደው የመጀመሪያ ደረጃ የካፒታል ክምችት ሂደት ለመፍጠርና በማያቋርጥ ሁኔታ

ለማሳደግ የቻሉ ሁሉ የገበያ ስርአትን ለመገንባት ችለዋል፡፡ስለሆነም ስለ ገበያ ስርዓት ግንባታ

ሲታሰብ ከሁሉ በፊት በተሳካ ሁኔታ መፈፀም ስላለበት የመጀመሪያ ደረጃ የካፒታል ክምችት

የተሟላ ግልፅነት መያዝ ያስፈልጋል፡፡

ከህበረተሰቡ የስራ ሃይል መካከል ትርጉም ያለው በኢንዱስትሪያዊ የስራ መስክ የተሰማራበት

ነው፡፡ በተጨማሪ በግብርና ሰራ ላይ ተሰማርቶ ይኖር የነበረው አርሶ


አደር በልዩ ልዩ አግባቦች በመታገዝ በግብርና ወደ ኢንዱስትሪ የስራ ሀይልነት እንዲቀየር

በማድረግ የሚፈፀም ነው፡፡

ካፒታል በሌለበት ማኒፋክቸሪንግ ሊስፋፋ አይችልም፡፡ ኢንዱስትሪያዊ የስራ ሀይል /ላብ

አደር/በሌለበትም ማፋክቸሪንግ ተቋማትን ማንቀሳቀስ አይቻልም፡፡ ስለሆነም ነው ለኢንዱስትሪ

ልማት ቁልፍ ተፈላጊነት ያላቸው ካፒታልና ጉልበት በመጀመሪያ ደረጃ የካፒታል ክምችት

አማካኝነት ለኢንዱስትሪ መስፋፋት በሚያበቃ ሁኔታ አስቀድመው መፍጠርና ማሰባሰብ

የሚገባቸው፡፡የመጀመሪያ ደረጃ የካፒታል ክምችት በሁሉም የለሙ ሀገሮች በተለያየ አግባብ

የተፈፀመ ሂደት ነው፡፡

ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ የመጀመሪያ ደረጃ የካፒታል ክምችት ከአውሮፓ ውጪ በተለይ ዘግይተው

በለሙ ብዙ የምስራቅ እስያ አገሮች በተሳካ ሁናቴ የተፈጸመና አገሮቹን ለተፋጠነና ፍትሀዊ

እድገት ያበቃ መሆኑ ተረጋግጧል፡፡በልማታዊ መንግስታቱ በተመራው የለውጥ ጉዞ ከጃፓን እስከ

ኮሪያ ከታይዋን እስከ ቻይና የተካሄደው የካፒታል ክምችት ሀገራቱ የአርሶ አደሩን ጉልበት

በሰፊው በማንቀሳቀስ በገጠር ለኢንዱሰውትሪ ልማት ማስፋፋት ቁልፍ ተፈላጊነት የነበረውን

ካፒታል እንደፈጠሩ ያሳያል፡፡

ለእኛ በጣም የቀረበ ልማታዊ ፈለገ የሚከተሉት ምስራቅ እስያ ሀገሮች በሌሎች ሰነዶችን ግልፅ

እንደተደረገው የመጀመሪያ ደረጃ የካፒታል ክምችት ያካሄዱት

ከሁሉ በፊት ግብርናን በተለይ የአነስጠኛ አርሶ አደር ግብርና በልማትና ሀብት ፈጣሪ በማድረግ

ነው፡፡ ለዚህም ሲሉ መሬትን አከፋፍሏል፡፡


መሬትን ከፋፍሎ ነፃ ለወጣው የመላ ሀገራቸው አርሶ አደር አቅም የፈቀደውን ያህል

የፋይናንስ፣የቴክኒክ፣የግብይት፣የስራ አመራርና የመሰረተ ልማት ድጋ አድርገውለታል፡፡

ለዚህ ነው የዳበረ የገበያ ስርዓት ለመገንባት የሚያልሙ ሀገሮች ሁሉ ሊያሟሏቸው ከሚገባቸው

ቅድመ ሁኔታዎች ቀዳሚው የመጀመሪያ ደረጃ የካፒታል ክምችትን በአንድ ወይም በሌላ መልከ

በስኬት መፈፀም ሆኖ የሚገኘው፡፡


የመወያያ ርዕስ፡- የገጠር ኢንዱስትሪያላይዜሽን የቻይና ልምድ

ከገጠር ኢንዱስትሪያላይዜሽን አኳያ እንደ ጀርመን ከመሳሰሉት ቀደምት የኢንዱስትሪ ልማት

አገሮችም ሆነ ዘግይተው ከለሙት የምስራቅ እስያ ነብሮች ልምድ ብዙ ትምህርት መቅሰም

እንደሚቻልና እንደሚገባ አያከራክርም፡፡

ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ በረከት ባሉ መሰረታዊ ምክንያቶች ከቻይና የገጠር ኢንዱስትሪ ልማት

ልምድ መማር አስፈላጊና ጠቃሚ ሆኖ ይገኛል፡፡ የመጀመሪያው ምክንያት ቻይና በጣም ከፍተኛ

የህዝብ ቁጥር ያላት ብቻ ሳትሆን ልክ እንደኛ ሁሉ ገጠር ኢንዱስትሪያላይዜሽን ከመጀመሩ

በፊት 85% ያህል ህዝቧ በገጠር ይኖር የነበረና ይህ ሰፊ ህዝብ በተሳካ ሁኔታ በኢንዱስትሪ

ልማትና የገጠር ትራንስፎርሜሽን አቅጣጫ ወደ ብልፅግናና ከተሜነት ለማሸጋገር የቻለች ሀገር

በመሆኗ በተነፃፃሪ ከታይዋንም ሆነ ከኮሪያ የሰፋ ህዝብ ላላቸው እንደ እኛ ለመሰሉ አገሮች

የቻይና ልምድ ብዙ ትምህርት የሚቀሰምበት በመሆኑ ነው፡፡

ከዚሁ በማይነጠል መልኩ ቻይና በተለይ ደግሞ እየሰሩ በመማር አቅጣጫ አየወደቀች እየተነሳች

ያሳካችው ሰፊ የገጠር ኢንዱስትሪያላይዜሽን ልምድ የሚገኝበት አገር መሆኗ ነው፡፡ በሶስተኛ

ደረጃ ደግሞ አለማችን በኒዮ ሊቨራሊዝም ማዕበል በተመታችበትና ይህን ተከትሎም ካፒታል

ከመላው

ዓለም ወደ አሜሪካ መጉረፍ በጀመረበት 1980 ዎቹ ለኢንዱስትሪ ልማት ከፍተኛ ተፈላጊነት

የነበረውን የመጀመሪያ ደረጃ የካፒታል ክምችት በተለይ ከአሜሪካና ላቲን አሜሪካ በተለየ አኳ
ኋን ጉልበትን በሰፊው የሚጠቀሙ የገጠር ኢንዱስትሪዎች በማስፋፋት እዚያው በአገሯ ውስጥ

በመፍጠር ልትፈታው ከመቻሏ ጋርተያይዞ በጣም ጠቃሚ ልምድ

የሚገኝባት አገር በመሆኗ ነው፡፡እነዚህን በጥቂቱ ዘርዘር አድርጎ መመልከት ለግንዛቤ ያግዛል፡፡

የቻይና የገጠር ኢንዱስትሪ የቻይና ፈጣን ኢኮኖሚያዊ እድገት አንቀሳቃሽ ሞተር ታምር እስከ

መሆን ደርሷል፡፡ ይህን የመሳሰለውን ክስተት ቀደም ሲል ከለሙ ሀገሮች የልማት ሂደት

ልንመለከተው አንችልም፡፡ አሁን ባለው የግሎባላይዜሽን ማዕበል ግን የቻይና ኢኮኖሚ እጅግ

ፈጣን የእድገት ምጣኔ በማረጋገጥ የዓለምን የኢኮኖሚ ስርዓት እየተቀላቀለ ነው፡፡ በዓለም

ኢኮኖሚ ላይም ትርጉም ያለው ተፅኖ በማሳረፍ ላይ ሲሆን የሀገሪቱ የገጠር ኢንዱስትሪ ደግሞ

እጅግ የተለየ ሚና እየተጫወተ ይገኛል፡፡

ጨርቃ ጨርቅ አልባሳትን ጨምሮ በብዙ ምርቶች ረገድ የቻይና የገጠር ኢንዱስት ለዓለም ገበያ

ትርጉም ያለው አስተዋፅኦ ያበረክታል፡፡

የማይነጥፍ የጉልበት አቅርቦትና ተመጣጣኝ ዋጋ የቻይና የገጠር ኢንዱስትሪ በዓለም ላይ ጠንካራ

ተወዳዳሪ እንዲሆን ያበቁት ምክንያቶች ናቸው፡፡

ከዚህ በረጅሙ ከቀረበው ጥቅስ ለመገንዘብ እንደሚቻለው ቻይናን ለመሰረታዊ ለውጥ ብቻ

ሳይሆን በዓለማችን ላይ ከባድ ተፅዕኖ አድራጊ አገር እንድትሆን ካበቋት ጥንካሪዎቿ መካከል

ሀገሪቱ ለገጠር ኢንዱስትሪያላይዜሽን የሰጠችው የተለየ ትኩረት ነው፡፡ አብዛኛው ጊዜ የከተማ

ባህሪ ብቻ ያለው የሚመስለንን የቴክስታይል ኢንዱስትሪ ሳይቀር በገጠር ያሥፋፋችው ቻይና

በርግጥም የገጠር ኢንዱስትሪያላይዜሽን አይነተኛ ተምሳሌት ነች፡፡ወቅቱ በዓለም የበላይነቱን


ያረጋገጠውና ከቬትናም ጦርነት ሽንፈት በኋላ በከባድ ማሽቆልቆል ውስጥ መግባት የጀመረው

የአሜሪካ ካፒታል የዓለምን ትርፍ ካፒታልና በግበስበስ የጀመረበት ወቅት ነው፡፡ የገበያ ስርአትን

የአምስት መቶ አመታት ጥናት በማጥናት በልዕል ኃያልነት የመነሳትና የማሽቆልቆል ክስተቶችን

ከነምክንያታቸው የዘረዘረው ጆቫኒ አሪጊ

የውይይቱ ርዕስ፡- የጉምሩክ ቀረጥ ነፃ ማበረታቻ

አንቀጽ 12 የካፒታልና የግንባታ ዕቃዎች ከጉምሩክ ቀረጥ ነፃ ስለመሆን

በዚህ አንቀፅ ንዑስ አንቀፅ(1) አፈፃፀም ባለሀብቱ ከጉምሩክ ቀረጥ ነፃ እንዲያስገቡ

የሚፈልጓቸውን የካፒታልና ግንባታ ዕቃዎች ዝርዝር ለሚመለከተው የኢንቨስትመንት አካል

በቅድሚያ በማቅረብ ማስፈቀድ ይኖርበታል፡፡


የጉምሩክ ቀረጥ ነፃ ማበረታቻ ተጠቃሚ የሆነ ባለሀብት በአገር ውስጥ የማመረቻ

ኢንዱስትሪዎች የካፒታል ወይም የግንባታ ዕቃዎችን ሲገዛ ዕቃችን ለማምረት በግብአትነት

በዋሉት ጥሬ ዕቃዎች ወይም አካሎች ላይ የተከፈለው የጉምሩክ ቀረጥ ተመላሽ ይደረጋል፡፡

በዚህ አንቀፅ መሰረት የጉምሩክ ቀረጥ ነፃ ማበረታቻ የሚፈቀድለት ማንኛውም ባለሀብት

ዋጋቸው ከካፒታል ዕቃዎች ጠቅላላ ዋጋ 15 በመቶ የማይበልጡ መለዋወጫዎችን ፕሮጀክቱ

ማምረት ወይም አገልግሎት መስጠት ከጀመረበት ጊዜ ጀምሮ እስከ አምስት አመት ድረስ

ከጉምሩክ ቀረጥ ነፃ እንዲያስገባ ይፈቀድለታል፡፡

በዚህ አንቀፅ ን/አንቀፅ/የተደነገገው እንደተጠበቀ ሆኖ በማምረቻ ኢንዱስትሪ ወይም በግብርና

የስራ መስኮች የተሰማራና ቢያንስ 200,000 የአሜሪካን ዶላር ወይም በወቅቱ ምንዛሪ

ተመጣጣኝ የኢትዮጵያ ብር ካፒታል ኢንቨስት ያደረገና ቢያንስ


የውይይቱ ርዕስ፡- በቻይና ኢንዱስትሪን የማንቀሳቀስ ክህሎት ያለው ላብ አደር የመፍጠር ሂደት

ከፍ ሲል እንደተገለፀው ኢንዱስትሪያላይዜሽን መሰረት ሰፊ የማኒፋክቸሪንግ አቅም ግንባታ

ከመሆኑ በማይነጠል አኳኋን መሰረተ ሰፊ ኢንዱስትሪያዊ የስራ ሃይል ወይም ላባደር የመፍጠር

ጉዳይ ነው፡፡

ይህም በመሆኑ በኢንዱስትሪ የለማ ሃገር በመሰረቱ በአብዛኛው ህዝቡ በከተሞች የሚኖር ብቻ

ሳይሆን በጣም ሰፊ የሰለጠነና የምርታማነት ደረጃው ከፍተኛ የሆነ የስራ ሃይል ያለው ሃገር ሆኖ

ይገኛል፡፡ ይህን የመሰለው መጠነ ሰፊ የሰለጠነ የሰው ሃይል ግን አስቀድሞ ተፈጥሮ የማይገኝ

ይልቁንም በምርት ተግባር ውስጥ በማለፍ እየወደቁ እየተነሱ ብቻ የሚገነባ ሃይል ነው፡፡ የገጠር

ኢንዱስትሪ የማልማት ጉዳይ ረጅም አዝጋሚና ችግር የማይለየው ሂደት ነው፡፡ ይህም አብዛኛው
የክህሎት ግንባታና ትምህርት ከመደበኛ ይልቅ ኢ-መደበኛ ስለሆነና እየሰሩ በመማር ሂደት

የሚጠራቀም በመሆኑ ነው፡፡ በእነዚህ ምክንያቶች በዘመናችን የሚገኙ ታዳጊ አገሮች ያላቸው

ዕድል በቪክቶሪያዊው ዘመን የነበሩት የአትላንቲክ ኢኮኖሚዎች ከነበራቸው እጅግ ያነሰ ነው፡፡

በተለምዶ እንደሚታወቀው አርሶ አደሩ በአንድ ጣራ ስር የሚያመርት ሳይሆን በሰማይ ስር ሆኖ

የእንቅስቃሴ ገደብ ሳይኖርበት

የሚያመርት የህብረተሰብ ክፍል ነው፡፡ በእጅ በአብዛኛው በተናጠል ማሳው ላይ በተበተነ አኳኋን

መሰማራት የለመደም ነው፡፡ ይህ ሃይል ከግብርና ወደ ኢንዱስትሪ በሚሸጋገርበት ጊዜ በአንድ

ጣራ ስር ከሌሎች ሰራተኞች ጋር በሚኖር የስራ ክፍፍል እንደዚሁም ለረጅም ጊዜ አንድ ቦታ

ቆሞ አንድ አይነት አሰልች ስራ በማከናወን ረገድ የዳበረ ልምድና ዲስፕሊን የሌለው ይልቁንም

ኋላቀር የስራ ባህልና ደካማ ዲስፕሊን ያለው ሃይል ሆኖ ይገኛል፡፡

ቻይና ደረጃ በደረጃ ወደ ከባድና የተራቀቀ ኢንዱስትሪ ግንባታ እየተሸጋገረች በሄደች ቁጥር

ደግሞ ይህው የቴክኖሎጂያዊ አቅም ግንባታ ስራዋ የገጠር ኢንዱስትሪን የምርታማነትና

የተወዳዳሪነት ባቃት በቀጣይነት የማሳደግ ችሎታን አጎናፅፏል፡፡


የውይይቱ ርዕስ፡-ከትልልቅ ከተሞችና ከባድ ኢንዱስትሪ ልማት ጋር እየተመጋገበ የተገነባ የገጠር

ኢንዱስትሪያላይዜሽን

በቻይና የገጠር ኢንዱስትሪ ልማት የተካሄደው በሶስቱም ምዕራፎች ተከፋፍሎ በዋነኝነት አርሶ

አደሩን ከግብርና ስራ ደረጃ ወደ ኢንዱስትሪና ከተሜነት በማሸጋገር ነበር፡፡

ይህም በመሆኑ በገጠር የተካሄደና እራሱን የቻለ ባህሪ ያለው የልማት እንቅስቃሴ ነበር፡፡ ይህ

መሰረታዊ ጉዳይ እንደተጠበቀ ሆኖ የቻይና የገጠር ኢንዱስትሪ በባህሪው ከትልልቅ ከተሞችና

ከባድ ኢንዱስትሪ ጋር ተደጋጋፊና ተመጋጋቢ ሆኖ ያደገ ነበር፡፡ ከዚህ አኳያ ለኢንዱስትሪው

መስፋፋት ትላልቅ ከተሞችና ከባድ ኢንዱስትሪ የየራሳቸውን አወንታዊ አስተዋፅኦ ያበረከቱበት

ነበር፡፡ ከዚህ አኳያ ሲታይ የገጠር ኢንዱስትሪ ቻይናን በተለይ ከዝቅተኛ እድገት ወደ መካከለኛ

ገቢ ህብረተሰብ በተደረገውሽግግር ለፈጣን እድገት ያበቃት መሆኑ እንደተጠበቀ ለቻይና ፈጣን

እድገት የራሳቸው ቁልፍ አስተዋፅኦ የነበራቸውን የከተሞች በተለይ ደግሞ ለወደብና ለባህር በር

በቀረቡ እንዲሁም በተመረጡ የኢኮኖሚ ዞኖች የተካሄደው ልማት ሚና ዝቅ ተደርጎ ሊቀመጥ

የማይችልና የማይገባው ነበር፡፡

የገጠር ኢንዱስትሪያላይዜሽን የቻይና እድገት እንዲፋጠን ከተጫወተው ሚና ጎን ለጎን


በቻይና የባህር በርን ተጠግተው የተስፋፉት ከተሞችና የኢንዱሰትሪ ማዕከላትም ልዩ ሚና

ተጫውተዋል፡፡ በምስራቅ ቻይና ለሆንግ ኮንግ በቀረቡ ቦታዎች ላይ የተስፋፉት የመሳሰሉ

ከተሞች እንዲሁም በሻንጋ አካባቢ የተፈጠሩት ዘመናዊ የኢኮኖሚ ልማት ቀጠናዎች በቻይና

እድገት የነበራቸው አስተዋፅኦ እጅግ ከፍተኛ ነበር፡፡ በእነዚህና መሰል ከተሞች የተስፋፉት መጠነ

ሰፊ የማኒፋክቸሪ ተቋማት በአንድ በኩል በቻይና የገጠር ኢንዱስትሪዎች የሚመረቱ በከፊል

ያለቀላቸውን ምርቶች ተቀብለው ይበልጥ እሴት በመቸመር በሌላ በኩል ደግሞ ለገጠር

ኢንዱስትሪ ልማት ተፈላጊ የሆነውን ግብዓትና ራሱን የማምረቻ መሳሪያውን በማቅረብ ላምቱ

እንዲፋጠን ቁልፍ ሚና ተጫውተዋል፡፡

ከእነዚህ ለመገንዘብ እንደሚቻለው የቻይና ፈጣን እድገት የዚህኛው ዘርፍ ብቸኛ አስተዋፅኦ

ውጤት አይደለም፡፡ ወይም ቻይና አንዱን ሴክተር ከሌላው ነጥሎ በማሳደግና በብቸኝነት

በመገንባት ያሳካችው አይደለም፡፡ የገጠር ኢንዱስትሪን ስትገነባ የከተማውን ሳትዘነጋ

የከተማውን ስትነባ ደግሞ የገጠሩን ሳትዘነጋ የገነባችው ሃገራዊ እድገት ነው፡፡

መጀመሪያ ላይ ለከባድ ኢንዱስትሪ ልማት የተለየ ትኩረት እሰጣለሁ ብላ እድገቷን ካጓተተችው

በኋላ በሂደት ግን በተስተካከለ ቅደም ተከተል ለሰፊ የጥቃቅንና አነስተኛ እንዲሁም የቀላልና

መካከለኛ ጉልበትና ገበያ ተኮር ኢንዱስትሪ ልማት ተገቢውን ትኩረት በመስጠት ያረጋገጠችው

እድገት ነው፡፡
የውይይቱ ርዕስ፡- የኢንቨስትመንት ፈቃድ አሰጣጥና ተየያዥ ጉዳዮች

1. ኢንቨስትመንት

አዲስ ድርጅትን ለማቋቋም ወይም ነባር ድርጅትን ለማስፋፋት ወይም ለማሻሻል ባለሀብት በገንዘብ

ወይም በዓይነት ወይም በሁለቱም የሚደረግ የካፒታል ወጪ ነው፡፡

2. ኢንቨስትመንት የሚያካሂድባቸው ቅርጾች

2.1 በግለሰብ፡- ኢትዮጵያዊ አንደ ኢትዮጵያን የሚቆጠር የውጪ ሀገር ዜጋ

2.2 የንግድ ማህበር በኢትዮጵያ ወይም በውጪ ሀገር ህግ መሰረት የተቋቋመ

2.3 የመንግስት ልማት ድርጅት

2.4 የህብረት ስራ ማህበር


3. የኢንቨስትመንት ፈቃድ የሚያስፈልጋቸው እነማን ናቸው

የውጪ ባለሀብቶች

በቅንጅት ኢንቨስት የሚያደርጉ የአገር ውስጥና የውጪ ባለሀብቶች እንደ ሀገር ውስጥ ባለሀብት

በመቆጠር ኢንቨስት የሚያደርግ በትውልድ ኢትዮፕያዊ ያልሆኑ የውጪ ሀገር ዜጎች

የኢንቨስትመንት ማበረታቻ በሚሰጥበት የስራ መስክ ኢንቨስት የሚያደርጉና የማበረታቻ ተጠቃሚ

መሆን የሚፈልጉ የሀገር ውስጥ ባለሀብቶ ናቸው፡፡

4. የኢንቨስትመንት ፈቃድ ለማውጣት መሟላት ያለባቸው ጉዳዮች፡-

4.1. አዲስ ኢንቨስትመንት ለማውጣት

ባለሀብቱ የማመልከቻ ቅጽ በመሙላት ከሚከተሉት ሰነዶች ጋር አየይዞ አግባብ ባለው

የኢንቨስትመንት መ/ቤት በአንድ ቅጂ ማቅረብ አለበት፡፡

ማመልከቻው የተፈረመው በወኪል ከሆነ የውክልና ስልጣን ማረጋገጫ ሰነድ ፎቶ ኮፒ

ኢንቨስትመንቱ የሚካሄደው በግለሰብ ከሆነ የባለሀብቱ መታወቂያ ካርድ ፎቶ ኮፒ ወይም የአገር

ውስጥ ባለሀብትነት መታወቂያ ካርድ ፎቶ ኮፒ እና ሁለት የቅርብ ጊዜ ጉርድ ፎቶ ግራፍ

ኢንቨስትመንቱ የሚካሄደው በንግድ ማህበር ከሆነ የማህበሩ የመመስረቻ ጹሁፍና የመተዳደሪያ

ደንብ ፎቶ ኮፒ ወይም ማህበሩ አዲስ የሚቋቋም ከሆነ ከዚህበተጨማሪ የማህበርተኞቹ

መታወቂያ ካርድ ፎቶ ኮፒ ወይም የሀገር ውስጥ ባለሀብትነት መታወቂያ ካርድ ፎቶ ኮፒ

ኢንቨስትመንቱ የሚካሄደው በመንግስት የልማት ድርጅት ከሆነ ድርጅቱ የተቋቋመበት ደንብ

ፎቶ ኮፒ

4.2 የማስፋፊያ የኢንቨስትመንት ፈቃድ ለማውጣት የማመልከቻ ቅፁ የተፈረመው በወኪል

ከሆነ የውክልና ስልጣን ማረጋገጫ ሰነድ ፎቶ ኮፒ


ኢንቨስትመንቱ የሚካሄደው በግለሰብ ከሆነ እንደ ሁኔታው የባለሀብቱን ማንነት ሚያሳዩ

አግባብነት ያላቸው የጸና ፓስፖርት ገፆች ፎቶ ኮፒ ወይም እንደ አገር ውስጥ ባለሀብት

ተቆጠረበት መታወቂያ ካርድ ፎቶ ኮፒና የቅርብ ጊዜ ሁለት ጉርድ ፎቶ ግራፎች


የውይይቱ ርዕስ፡- የካፒታል ዕቃዎች ከጉምሩክ ቀረፅ ነፃ እንዲያስገቡ የሚፈቀድላቸው የቱሪስት አገልግሎት

ሰጪ ድርጅቶች

1. የኢንቨስትመንት ፈቃድ ያወጣ ባለሀብት አዲስ የቱሪስት አገልግሎት ሰጪ ደርጅት ለማቋቋም ሲፈለግ

ወይም ነባር የቱሪስት አገልግሎት ሰጪ ድርጅት በኢንቨስትመንት አዋጅ ላይ በተጠቀሰው ሁኔታ

መስፋፋት/ማሻሻል ሲፈለግ ወይም በአዋጁ ላይ ከተጠቀሰው ባነሰ ሁኔታ ኢንቨስትመንቱን ማስፋፋት

ሲፈለግ ወይም በዚህ መመሪያ መሰረት ለፕሮጀክቱ የሚያስፈልጉትን የካፒታል ዕቃዎች ከጉምሩክ

ቀረፅ ነፃ እንዲያስገባ ይፈቀድለታል፡፡

2. የዚህ አንቀፅ ንዑስ አንቀፅ /1/ ድንጋጌ ቢኖርም የቱሪስት አገልግሎት ሰጪ ድርጅት ለማቋቋም የፈለገ

ባለሀብት የኢንቨስትመንት ፈቃድ አውጥቶ ፕሮጀክቱን ተግባራዊ በሚያደርግበት ወቅት እና የንግድ

ስራ ፈቃድ ካወጣ በኋላ ደግሞ ቢያንስ 2000 የአሜሪካን ዶላር ወይም በወቅቱ ምንዛሪ ተመጣጣኝ

የኢትዮጵያ ብር ኢንቨስት ካደረገ እና ቢያንስ 50 ቋሚ ሰራተኛ የስራ ዕድል የሚፈጥር ፕሮጀክት ከሆነ

የንግድ ስራ ፈቃድ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ የሚቆተር ሆኖ እስከ አምስት አመት ባለው ጊዜ ውስጥ

ለፕሮጀክቱ/ለድርጅቱ/ የሚያስፈልጉትን የካፒታል ዕቃዎች ከጉምሩክ ቀረፅ ነፃ እንዲያስገቡ

ይፈቀድላቸዋል፡፡
የውይይቱ ርዕስ፡- ከግሙርክ ቀረፅ ነፃ ሆኖ የገባ ዕቃ ስለማስተላለፍ እና የገቢ ግብር ነፃ ማበረታቻ ተጠቃሚ

የሚሆኑ ፕሮጀክቶች

ከጉምሩክ ቀረፅ ነፃ ሆኖ የገባ ማንኛውም የካፒታል ወይም የግንባታ እቃ ወይም ተሸከርካሪ ተመሳሳይ

የጉምሩክ ቀረፅ ነፃ መብት ላለው ሰው ሊተላለፍ ይችላል፡፡

በዚህ አንቀፅ ንዑስ አንቀፅ 1 የተደነገገው ቢኖርም አስቀድሞ ተገቢው የጉምሩክ ቀረፅ ተከፍሎ ካፒታል ወይም

የግንባታ ዕቃው ወይም ተሸከርካሪው የጉምሩክ ቀረፅ ነፃ መብት ለሌለው ሰው ሊተላለፍ ይችላል፡፡

ባለሀብቱ ከጉምሩክ ቀረፅ ነፃ ሆኖ ያስገባው የካፒታል ወይም የግንባታ ዕቃ ወይም ተሸከርካሪ ከአገር እንዲወጣ

ማድረግ ይችላል፡፡

በዚህ አንቀፅ ድንጋጌ የተላለፈ ማንኛውም ባለሀብት አግባብ ባለው የጉምሩክ አዋጅ ድንጋጌ መሰረት

ይቀጥላል፡፡
የገቢ ግብር ነፃ ማበረታቻ ተጠቃሚ የሞሆኑ ፕሮጀክቶች

- የማምረቻ ኢንዱስትሪ

- የግብርና ፕሮጀክቶች

- የመረጃ ና መገናኛ ቴክኖሎጂ ልማት

- ኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጨት፣ማስተላለፍና ማሰራጨት

- የገቢ ግብር ነፃ ማበረታቻ ተጠቃሚ የሚሆኑ ፕሮጀክቶች

- ትምህርትና ስልጠና

- የጤና አገልግሎት

-የአርቲክቸርና የኢንጂነሪንግ ስራዎች የቴክኒክ ምርመራና ትንተና የአሳታሚነት ስራ

- የገቢ ንግድና ወጪ ንግድ

- የማምረቻ ኢንዱስትሪ
- መሰረታዊ ምር ት

- ዱቄት ማምረት

- የማተሚያ ኢንዱስትሪ

- የህንፃ ግንባታ

የውይይቱ ርዕስ፡- የካይዘን ሽግግርና የትግበራ አቅጣጫ በኢትዮጵያ

1.1 የኢትዮጵያ ካይዘን ኢንስትዩት አመሰራረት

በ 2008 ግብፅና ቱኒዚያ በጃፓን አጋዥነት የካይዘንን የስራ አመራር ፍልስፍና እየተገበሩ ስለነበረ

የዚያን ውጤት ሪፖርት ከጃፓን መንግስት ጋር ሲገመግሙ የቀድሞውን የኢትዮጵያ ጠቅላይ

ሚኒስተር አቶ መለስ ዜናዊ ተገኝተው ጉዳዩን ይከታተሉ ነበር እርሳቸውም የካይዘን የስራ

አመራር ፍልስፍና ለሀገራቸው እንዲጠቅም ለመገንዘብ ጊዜ አልወሳደባቸውም ከጃፓን የካይዘን

ሙህራን ጋር በጉዳዩላይ በስፋት ከተዋያዩ በኋላ የካይዘን የስራ አመራር ፍልስፍናን ወደ


ኢትዮፒያ ለማስገባት ወሰኑ፡፡ ድጋፍ እዲደረግላቸዉም የጃፓን መንግስት ጥያቄ አቀረቡ ፡፡

የጃፓን መንግስትም አዉንታዊ መልስ ሰጠ

በኢትዮፒያና በጃፓን ምንግስታት መካካል በተደረሰዉ ስምምንነት መሰረት የካይዘን የሙከራ

ተግበራ ፕሮጀክት ተቀረጸ፡፡ በፓን አለም አቀፍ ትትብብር ኢጀንሲ አማካኝነት ለሀገራችን

ድጋፍ እንዲሰጡ ለሀገራችን ድጋፍ እንዲሰጡ ከተላኩ የካይዘን አማካሪዎች ጋር በመሆን በአዲስ

አበባ አንድ ኪሎ ሜትር ዙሪያ የሚገኙ 30 ኩባናያዎች ተመርጠው ከጥቅምት 2003 እስከ 2003

አመተ ምህረት የሙከራ ትግበራ ተከናወነ፡፡

በሙከራ ተግባሩም ጥሩ ውጤት ከመገኘቱ በተጨመ፣ሪ የካይዘን ተሸጋጋሪነትና ጠቀሜታ

አረጋገጠ ሙከራውን የተገበሩ ኩባንጣዎች በአመራሩና በሰራተኛው መካከል ጥሩ የአመለካከት

ለውጥ ሰስለመጣላቸው የምርታቸው ጥራት አይነትና ምርታማነትን ጨመረ፡፡

1.2 የካይዘን አመራር ፍልስፍና

ካይዘን የሚለወረ ቃል የተመሰረተው ከተባሉ የጃፓነኛ ቃላት ሲሆን ለውጠው ማለት ገሲሆን

ደግሞ የተሸ ማለት ነው፡፡ ከዚህ አንፃር ካይዘን በቀጣይነት ላይ የተመሰረተ የተሸለ ለውጥ

ማምጣት የሚያስችል የአመራር ፍልፍና ነው፡፡ የካይዘን አመራር ፍልስፍና ቀጣይነት

ተከታታይነት ያለው የተሸለ ለውጥ ያለው በማብቃት ላይ የተመሰረተ ሲሆን ፍልስፍናው

ከሁሉም በላይ የአመለካከት ለውጥ ማምጣት የሚያስችል ነው፡፡ በተለያዩ ሙያዎች


የተመሰማሩ ሙህሮችን ወደ አውሮፓ አሜሪካ በመላክ የእነሱን አሰራር እና ቴክኖሎጁ ቀስመው

እንዲመለሱ አደረገች፡፡የቀሰሙትንም ዕውቀት በራሻ ተጨባጭ ሁኔታ ጋር አጣጥሞ

እንዲቀምሩ አደረገች፡፡

የውይይቱ ርዕስ፡- ፈጣን የግብርና ልማት ፈጣን አገራዊ የኢንዱስትሪ ልማትን መጠየቅ መጀመር፣

በሀገራችን ተፋጠነ የኢንዱስትሪ ልማት ማምጣት ሁሌም ቢሆን የምናልመውና የምንጓጓለት ግብ

ነው፡፡ ይህ ብቻውን የኢንዱስትሪ ልማትን ለማስፋፋት በቂ ምክንያት እንደሆነ አያከራክርም፡፡ ነገር ግን

በዕኛ ሀገር ተጨባጭ ሁኔታ እጅግ ለተፋጠነ አገራዊ የኢንዱስትሪ ልማት እንድንገታ የሚያስገድዱን

በርካታ ልዩነት አጣዳፊ ምክንያቶች አሉ፡፡


ከእነዚህ ምክንያቶች ቀዳሚ በግብርና መስክ በማምጣት ላየ ያለው ስኬት በጠንካራ የአግሮ

ፕሮሰሲብግ ኢንዱስትሪ ክልተደገፈ በስተቀር ውሎ አድሮ እድገቱ የሚገታበት ሁኔታ አይቀሬ መሆኑ

ነው፡፡ እንደሚታወቀው በግብርና መስክ በማካሄድ ላይ ባለነው እንቅስቃሴ በተለይ በሰብል ምርት ላይ

ከፍተኛ ጭማሪ እያመጣን ነው፡፡ የመስኖ የበልገ ምርቶች ሳይጨምር የተገኘው የሰብል ምርት ከሞላ

ጎደል ለአንድ ኢትዮጵያዊ በነብስ ወከፍ እስከ ሶስት ኩንታል ያህል የሚችል ነው፡፡ ከግብርና ልማት አኳያ

የሚመዘገበው ይህ ድል በራሱ ከፍተኛ ስኬት ቢሆንም በከተሞች የሚኖረው ህዝብ ቁጥር

ትርጉም ባለው ሁኔታ ካልጨመረ በስተቀር አብዛኛው ምርት በራሱ በአርሶ አደሩ ቤተሰብ ብቻ ጥቅም

ላይ እንዲውል የሚያስገድድ መሆኑ አይቀርም፡፡

ኢንዱስትሪ ካልተስፋፋና በግብርና ምርቶች ላይ እሴት ካልተጨመረ በስተቀርም በጥሬው የሚደረግ

ኤክስፖርት ዞሮ ዞሮ የአርሶ አደሩን ተጠቃሚነት ዘላቂ ያደርገዋል ተብሎ አይወሰድም፡፡

ማኒፋክቸሪንግ በጥድፊያ እንድናስፋፋ የግድ የሚለው ሌላው ምክንያት ስኬታማው የግበርና

ልማታችን በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ አርሶ አደሮች ከገጠር ወደ ከተማ ከግምታችን በላይ በሆነ ፍጥነት

እንዲፈልሱ ሊያደርጋቸው የሚችል መሆኑ ነው፡፡

ስኬታማው የግብርና ልማታችን ካስገኛቸው ወይም በቅርብ ርቀት ከሚያስገኛቸው ከባድ ተፅዕኖ

አድራጊ ውጤቶች አንዱ የግብርና የሰው ሃይላችን የማምረት ብቃት በከፍተኛ ደረጃ እንዲጨምር

ማድረጉ ነው፡፡

እንደሚታወቀው የአርሶ አደሩ ማሳ ላይ ብዙ የሰው ሃይል ተሰማርቶ እያለም የሚያሥገኘው ምርት

ትንሽ ነበር፡፡
የውይይቱ ርዕስ፡- በማምረቻ ኢንዱስትሪ ለተሰማሩ እና ለሚሰማሩ ፕሮጀክቶች በሚፃፍ የድጋፍ ደብዳቤ ላይ መሟላት
የሚገባቸው ጉዳዮች

የጉምሩክ ቀረፅ ነፃ መብት ተጠቃሚ ለሆኑ ፕሮጀክቶች በሚፃፍ ደብዳቤ ላይ አዋጅ ቁጥር 849/2006 ከመሸሻሉ በፊት
በማኒፋክቸሪንግ ኢነ ዱስትሪና ሌሎች ፕሮጀክቶች ላይ ለተሰማራ ማንኛውም ባለሀብት የድጋፍ ደብዳቤው ፕሮጀክቱ ባለበት
ሁሉም ዞንና 3ቱ ሜትሮፖሊታንት ከተሞች ድጋፍ ሲሰጥ የቆየ መሆኑ ይታወቃል፡፡

በኢንቨስትመንት አዋጅ ቁጥር 769/2004 በአንቀፅ 30 ንዑስ አንቀፅ 2 የፊደል ተራ ቁጥር ሀ መሰረት ለማምረቻ
ኢንዱስትሪዎች ለግምሩክ ቀረፅ ነፃ ማበረታቻ የመፍቀድ ስራ በክልል ደረጃ እንዲሰራ የተወሰነ ቢሆንም ሲሰራበት አልቆየም፡፡

የፊደራል ኢንቨስትመንት ኮሚሽን በአዋጁ መሰረት በማምረቻ ኢንዱስትሪዎች የጉምሩክ ቀረፅ ነፃ ማበረታቻ የመፍቀድ ስራው
በክልል እንዲሰራ ወስኗል፡፡

የማምረቻ ኢንዱስትሪ ፕሮጀክቶች የካፒታልና የግናባታ ዕቃችን እንዲሁም ተሸከርካሪዎችን ከጉምሩክ ቀረፅ ነፃ ለማስገባት ከዞንና
ከከተማ አስተዳደሮች የሚፃፍ የድጋፍ ደብዳቤ መሟላት ያለበት ቅድመ ሁኔታዎች፡-

1. ለግንባታ ዕቃዎች
 የታደሰ ኢንቨስትመንት ፈቃድ ኮፒ
 የመሬት ኪራይ ውልና ካርታ
 የግንባታ ፈቃድ
 በሚመለከተው በመንግስት ተቋም የፀደቀ የግንባታ ዕቃዎች ዝርዝር ሰነድ
 የፕሮጀክቱ የአፈፃፀም ደረጃ ማለትም የመሬት ዝግጅት፣መሰረተ ልማት፣መካዘን፣መንገድእና የመሳሰሉትን ስራዎች
እየተከናወኑ ለመሆናቸው የሚገለልፅ የድጋፍ ደብዳ

2. ለካፒታል ዕቃዎች
2.1 ምርት ማምረት ባልጀመሩ ፕሮጀክቶች
 የታደሰ የኢንቨስትመንት ፈቃድ ኮፒ
 የ መሬት ኪራይ ውል ማስረጃ/የፋብሪካ ህንፃ ተከራይቶም ከሆነ ህጋዊ የከራይ ውል ማስረጃ
 ካርታ
 የግንባታ ፈቃድ
 የፕሮጀክቱ የአፈፃፀም ደረጃ ማለትም የመሬት ዝግጅት፣መሰረተ ልማት፣መካዘን፣መንገድእና የመሳሰሉትን
ስራዎች እየተከናወኑ ለመሆናቸው የሚገለልፅ የድጋፍ ደብዳ
2.2 በነባር ደችርጅቶች/ምርት ማምረት በጀመሩ ፕሮጀክቶች
 ኢንቨስትመንት ፈቃድ ከፒ
 የንግድ ፈቃድ ኮፒ
 በማምረት ላይ የሚገልፅ የድጋፍ ደብዳቤ
 ከ 50 በላይ የሖኑ ድርጅቱ ቋሚ ሰራተኞች ያሉት ሆኖ ለ 3 ተከታታይ ወራት የደሞዝ መክፈያ ሰነድ እና የቋሚ
ሰራተኛ የተከፈለበት የስራ ግብር ደረሰኝ
 ለኢንቨስትመንት ፈቃዱ ላይ የተመዘገበው የካፒታል መጠን 200,000 የአሜሪካን ዶላር/በወቅቱ ምንዛሪ
ተመጣጣኝ የኢንዮጵያ ብር ኢንቨስት ያደረጉትን ብቻ የሚመለከት ይሆናል፡፡
3. ተሸከርካሪዎችን በተመለከተ
 በተሸከርካሪ መመሪያው በሰንጠረዡ የተመለከቱትን ተሸከርካሪዎች ከጉምሩክ ቀረፅ ነፃ ማስገባት ቢያንስ 10,000 ብር
ካፒታል ያስመዘገበ
 የታደሰ ኢንቨስትመንት ፈቃድ ኮፒ/የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃደፍ ኮፒ
 የመሬት ኪራይ ውል
 ካርታ
 የግንባታ ፈቃድ
 የፋብሪካ ህንፃ ተከራይቶ የሚሰራ ከሆነ ህጋዊ የኪራይ ውልና የመሳሪያ ተከላ ስለመጀመሩ ማስረጃ
 የፕሮጀክቱ የአፈፃፀም ደረጃ ማለትም የመሬት ዝግጅት፣መሰረተ ልማት፣መካዘን፣መንገድእና የመሳሰሉትን ስራዎች
እየተከናወኑ ለመሆናቸው የሚገለልፅ የድጋፍ ደብዳቤ/በግንባታ ላይ ላሉ ፕሮጀክቶች
 በማምረት ላይ መሆኑን የሚገልፅ የድጋፍ ደብዳቤ

የውይይቱ ርዕስ፡-ብክንነትን የማስወገጃ ዘዴዎች

የአመራረት ሂደት ውስጥ ለሚመረተው ምርት እሴት የሚጨምሩ በርካታ ግብዓቶች እንዳሉ ይታወቃል፡፡ እነዚህን ግብአቶች

በካይዘናዊ የአሰራር ስልቶች በብቃትና በጥራት ከተተገበሩ ብክንነት በአነስተኛ ወጪ ማስወገጃ ይቻላል፡፡ በማንኛውም የአሰራ

ሂደት ውስጥ አስፋላጊ እና ጠቃሚዎችን ብቻ በማስቀረት ማንኛውም ብክነት ማስወገድ ይቻላል፡፡ ብክንነት የማወቅ አቅም

በአደገ ቁጥር ከጅምሩ ሲከሰት ለማየት ይረዳል፡፡ ስለሆነም ንክንነትን ለማስቀገድ ከፍተኛ ትኩረት በብልሀትና ቁርጠኝነትን

ይጠይቃል፡፡ ብክንነት ለማስወገድ የሚከተሉት በቅደም ተከተል መተግበር ያስፈልጋል፡፡


 ብኩንነቱ በግልፅ እንዲታይ ማድረግ

የሰራተኛን ቁጥርና እንቅስቃሴ፣የአሰራር ቅደም ተከተልና የአሰራር አይነትን ለማየት የአሰራር ፍሰት ሰጠረዥ ማዘጋጀት

ያስፈልጋል፡፡ነባር የአሰራ ፍሰት እና ሁኔታ መሳልና በትክክል ማጤን፡፡

 ምንጊዜም ብኩንነት እንዳይከሰት በንቃት መከታተል

አንድ ነገር እንደ ብክነት መታየት ካልቻለ ብክነትን ማቆም ስለማይቻል የስራ መደራረብና ደረጃን በትክክል መፈተሸ

ብክት ገና ከጅምሩ እንደታየ ማስወገድ፡፡

 ለሚፈጠር ብኩንነት ተጠያቂ መሆን

አንድ ሰራተኛ ለሚሰራው በጎ ስራ ከምስጋና ጀምሮ እስከ ደረጃ እድገት ድረስ የተለያዩ ጥቅሞችን እንዲያገኝ

እንደሚደረግ ሁሉ ብክነትን ሲፈጥር ደግሞ ለፈጠረው ብክነት ተጠያቂ መሆን አለበት፡፡

 ብክነትን መለካት

 ከየትኛው አቅጣጫ የሚቀርቡ መመዝገብና ደንበኛን ቃለ መጠይቅ ማድረግ

 የምልስ ርቀትን መለካት

 የስራ ቦታን ፎቶ ማንሳት

 አጠቃላይ ቅደም ተከተልን መለከታ

 ዕቃዎችን/ምርቶች/መዘርዘርማን እንዳበረታታቸውና እንደሚጠቀምባቸው መለየት

 በማካማቻ ቤት ውስጥ ያሉትን ሁሉንም በዝርዝር መያዝ


 ነባራዊ የምርት ዕቅድን፣የጊዜ ሰሌዳንና ፍጥነትን መለካት

 የጊዜ ጥናትን በንዑስ ርዕስ ከፍፍሎ መስራት

 የመጎጓዣ ስርዓትን ወይም ዘዴን መገንዘ ብና ርቀትን መለካት

 የግድፈትን ቁጥር ወይም መጠን መመዝገብ

 ብክነትን መቀነስ/ማስወገድ/

በማንኛውም ሁኔታና አመራረት ሂደት ውስጥ አስፈላጊና ጠቃሚዎችን ብቻ በማስቀረት የትኛውንም አይነት ብክነት

ማስወገድ ያስፈልጋል፡፡ይህ ደግሞ ብዙ ወጪ የሚጠይቅ አይደለም፡፡

የውይይቱ ርዕስ፡- የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች የማምረቻ፣የማሳያና የመሸጫ ማዕከላት

አጠቃቀምና አስተዳደር መመሪያ

1. የማእከላቱ አይነት
1.1 የጨርቃ ጨርቅና አልባሳት ማምረቻ፣ማሳያና መሸጫ
1.2 እንጨትና ብረታ ብረት ቨማምረቻ፣ማሳያና መሸጫ
1.3 የምግቭና ምግብ ነክ ማምረቻ፣ማሳያና መሸጫ
1.4 የቆዳና ቆዳ ውጤቶች ማምረቻ፣ማሳያና መሸጫ
1.5 የእደ ጥበብ ውጤቶች ማምረቻ፣ማሳያና መሸጫ
1.6 የአግሮፕሮሰሲንግ ማዕከላትንና በሂደት ኤጀንሲው በሌሎች የስራ ዘርፎች የሚገነበ ቸውን
ማዕከላትን ይጨምራል
2. የማዕከላቱ አጠቃቀምና አስተዳደር
2.1 ማዕከላቱ የተገነቡትና በመገንባት ላይ ያሉት በመንግስት በጀት በመሆን ባለቤትነት የከተማ
አስተዳደር ሆኖ ከጥ/አ/ኢ/ል/ኤጀንሲ ማዕከላቱ ህንፃው የሚገኝበት ከተማ ወይም ወረዳ
አስተዳደር ጥቃቅንና አነስተኛ ኢ/ል/ጽ/ቤት በስሙ መህግቦ ይረከባል ከዚይም ህንፃው ለሚገኝበት
የአንድ ማዕከል አገልግሎት ጣቢያ በተጠሪነት እንዲያስተዳድረው የስረክባል፡፡
2.2 የማምረቻ ፣ማሳያና መሸጫ ማዕከላት ብቃት ላላቸው ኢንተርፕራይዞች ብቻ ቢበዛ ለ 5 አመት
በኪራይ ይተላለፋሉ

2.3 ኢንተርፕራይዙ ማዕከላቱ ከሚገኙበት ከተማ አስተዳደር ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች


ጽ/ቤት ጋር የኪራይ ውል ፎርሙ የሚሰሩበትን ክፍል የስራ ቦታ ይረከባል
2.4 በማዕከላቱ ለኢንተርፕራይዞች በኪራይ የሚሰጠው ቦታ ስፋት እንደየስራ መስኩ የሚለያይ
በመሆኑ በባለሙያ በጥናት በሚቀርበው መረጃ መሰረት በኤጀንሲው ይወሰናል
3. የኢንተርፕራይዞች ምርጫ መስፈርቶች
3.1 እድገት ተኮር የሆነ ምርቶች ለማምረት ከሚመለከተው አካል ተገቢውን ፈቃ አግኝተው ቢያንስ
አንድ አመት በስራ ላይ የቆዩና ዛሬም በስራ ላይ ያሉ
3.2 አዳዲስ ቦታ ቆጣቢ ማሽኖች በራሳቸው ገንዘብ ወይም በመሳሪ ሊዝ /በብድር
ገዝተው/ለመጠቀም ፈቃደኛ የሆኑና ይህንኑ በጹሁፍ ያረጋገጡ
3.3 ቢቻል በማህበሩ የተደራጁ ወይም ወደ ማዕከላቱ ከገቡ በኋላ ለስራ አመች በሆነ መበንገድ
ለመደራጀት ፈቃደኛ የሆኑና በጹሁፍ ያረጋግጡ
3.4 ካፒታላቸው በ ንግድና አገልግሎት ከሆነ ከብር 500,000 ብር በኢንዱስትሪና ኮንስትራክሽን ዘርፍ
ከሆነ ከብር ቨ 1.5 ሚሊየን ያልበለጠ
3.5 ያላቸውን የስራ አመራርና የቴክኒክ ዕውቀት ለማስተላለፍ ማዕከሉን በጋራ ለማስተዳደርና
ለመምራት ፈቃደኛ ሆነው የገንዘብ የዕውቀትና የጉልበት አስተዋፅኦ ለማድረግ ዝግጁ የሆኑ
3.6 በተዘጋጁ ማዕከላት ተጠቃሚ የሆኑት በታዳጊ ወይም በመብቃት የእድገት ደረጃ ላይ የሚገኙ
መሆን ይኖርባቸዋል
3.7 በሴቶች ለሚመራ ኢንተርፕራይዞች ቅድሚያ ይሰጣል መስፈርቱን አሟልተው እስከተገኙ ድረስ
3.8 በስራቸው ብቃት ላላቸው ተዋዳደሪና ጥረት ያለው ምርት አምርተው ውጤት በማስመዝገብ ላይ
የሚገኙ በማኒፋክቸሪንግ ዘርፍ

የመወያያ ርዕስ፡- የማዕከላት የኪራይ ዋጋ ዝርዝር

የከተሞች የማምረቻ ማሳያና መሸጫ ማዕከላት የኪራይ ዋጋ ተመን እንደ ተጨባጭ ሁኔታው በየከተማው

የሚለያይ ቢሆንም በክልል አቀፍ ደረጃ ወጥነት ያለው የኪራይ ዋጋ ተመን እንዲኖር ለመነሻና ለመድረሻ

የሚሆን ዝቅተኛና ከፍተኛ ዋጋ ተለይቶ በሚቀጥለው ሰንጠረዥ ተቀምጧል፡፡ዝቅተኛ፣መካከለኛና ከፍተኛ

ዋጋ መወሰን መብት ለከተማ አስተዳደሩ ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ምክር ቤት ይሆናል፡፡

በምክር ቤቱ የተወሰነው ዋጋ ኪራይ 100 ሆኖ ኢንተርፕራይዞች ውል በወሰዱበት ጊዜ በመጀመሪያ አመት

የኪራይ 25 በሁለተኛው አመት 50 በሶስተኛው አመት 75 በአራተኛው አምስት አመት 1000 ይሆናል፡፡

1. የማምረቻ ማዕከል ክፍያ በካ/ሜ/ለጨርቃ ጨርቅ አልባሳት


1.1 ለሽመና ዝቅተኛ 10 ብር ከፍተኛ 26 ብር

1.2 ለልብስ ስፊት ዝቅተኛ 10 ብር ከፍተኛ 30 ብር

1.3 ለቆዳና ቆዳ ውጤቶች ዝቅተኛ 10 ብር ከፍተኛ 25 ብር

1.4 ለሹራብ ስራ ዝቅተኛ 7 ብር ከፍተኛ 20 ብር

1.5 ለጥልፍ ስራ ዝቅተኛ 7 ብር ከፍተኛ 20 ብር

2. ለምግብና ምግብ ንኡስ ዘርፍ

2.1 ባልትና ዝግጅት ዝቅተኛ ብር 7 ከፍተኛ ብር 22

2.2 ደረቅ እንጀራ ዝቅተኛ ብር 7.000 ከፍተኛ ብር 22.000

2.3 ወተትና የወተት ተዋፅኦ ዝቅተኛ ብር 7 ከፍተኛ ብር 15

2.4 ማር አጣርቶ መሸጥ ዝቅተኛ ብር 7 ከፍተኛ ብር 17

2.5 ድፎ ዳቦ አምባሻ ዝቅተኛ ብር 7 ከፍተኛ ብር 20

2.6 ለምግብ ዝግጅት ዝቅተኛ ብር 7 ከፍተኛ ብር 17

2.7 ለአትክልትና ፍራፊሬ ማቀነባበሪያ ዝቅተኛ 10 ብር ከፍተኛ

የመሬት ወለል በካሬ ሜትር የሚወስነው ሙሉ ዋጋ ይከፈላል

1 ኛ ወለል በካሬ ሜትር ለመሬት ወለል ከተወሰነው ኪራይ መጠን 5 ይቀንሳል


2 ኛ ወለል በከሬ ሜትር ለመሬት ወለል ከተወሰነው የኪራይ መጠን 10 ይቀንሳል

3 ኛ ወለል በካሬ ሜትር ለመሬት ወለል ከተወሰነው የመሬት መጠን 20 ይቀንሳል

4 ኛ ወለል በካሬ ሜትር ለመሬት ወለል ከተወሰነው የመሬት መጠን 30 ይቀንሳል

የውይይቱ ርዕስ፡-መሰረታዊ የካይዘን ቴክኒኮች

ሙሪ/muri/ሙራ /mura/
ሙሪ/muri/

የሚለው ቃል ጃፓነኛ ሲሆን ሰውን ጨምሮ እንስሳትንም ሆነ ማሽኖችን ከአቅም በላይ በማሰራትና
በማስጨነቅ ጫና የሚያደርስ አሰራር ነው፡፡ ማንኛውም አምራች ሀይል የማምረትና የመንቀሳቀስ አቅሙ
ውስን ነው፡፡ከአቅሙ በላይ እንዲቀሳቀስ ከተደረገ ህይወት ያለው አምራች ለበሽታና ለሞት ቁስ አካል
ደግሞ ለብልሽት ይዳረጋል፡፡ሙሪ የሚፈጠርባቸው በርካታ መንስኤዎች ቢኖርም የስራ ጫና እና የሰራተኛ
አለመጣጠም ለስራው የተመደበው በጀት አነስተኛ መሆን ለሰራተኞች የሚመች አቋቋም ጠነካራ ስራ ቦታ
ደህንነት አለመኖር ጥራታቸውን የጠበቁ መለዋወጫዎች አለመኖር የአቅርቦት እጥረትና መጓተት
እንዲሁም የንድፍ ወይም የዲዛይን ግድፈቶች ይጠቀሳሉ፡፡

በታዳጊ ሀገሮች የሚገኙ ማምረቻዎች ጥራትን በሚፈለገው ደረጃ ለማሻሻል የካፒታልና ቴክኖሎጅ
አቅማቸው ዝቅተኛ መሆኑ ይታወቃል፡፡ የተሟላ አሰራርና አደረጃጀት በመፍጠር ጥራቱ የተሟላ ምርት
ማምረት ወጪን ይቀንሳል እንጂ አያበዛም

ይልቁንም ወጪ የሚበዛው በሙሪ የተነሳ በየጊዜው የማሽኖች ብልሽት እየተፈጠረ ለጥገና ወጭ ሲወጣ
ነው፡፡ ከዚህ አንፃር ምርትን ለመቸመር እና ትርፋማ ለመሆን በሚል የተሳሳተ አመለካከት በሰውም ሆነ
በማሽኑ ላይ ጫና መፍጠር ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ ያመዝናል፡፡

ሙራ mura

ሙራ/mura/ እንደሙዳ እና ሙሪ ሁሉ ከጃፓነኛ ቋንቋ የተወሰደ ቃል ነው ትርጉሙም በሰውም ሆነ


በማሽን ላይ ያልተመጣጠነ የስራ ክፍፍል ማድረግ ነው፡፡ በአሰራር ላይ ያልተመጣጠነ የስራ ክፍፍል
ያልተመጣጠነ የማሽን አቅምና የተለያየ የግብዓት አቅርቦት እንዲሁም ወጥ ያልሆነ የስራ ክፍፍል
ይስተዋላል፡፡ ይህም የሚፈጠረው ለሰራተኛው በቂ ስልጠና አለመስጠት፣በቂ የእቃ መለዋወጫዎች
አለመኖር፣የግብዓት ጥራት መጓደል፣አላስፈላጊ እንቅስቃና የመገልገያ ዕቃዎችን በአግባቡ አለመጠቀም
ነው፡፡
የኢንዱስትሪ ዞን ልማት ቡድን መሪ
የመመማር ሰነድ

-
አዘጋጅ፡ አቶ ቸርነት አለማየሁ
ሰኔ 28/10/2010

የኢንዱስትሪ ዞን ልማት ቡድን የመሰረተ ልማት አስ/ባለሙያ

የመመማር ሰነድ

-
አዘጋጅ፡ አቶ አበበ ቸኮል
ሰኔ 14/10/2010
የኢንዱስትሪ ዞን ልማት ቡድን ሴክሬታሪ

የመመማር ሰነድ

አዘጋጅ፡ - ጤና ገበየሁ

ጥር 10/05/2010
የኢንቨስትመንት ማስፋፊያ ቡድን

የመመማር ሰነድ

-/
አዘጋጅ፡ ወ ሮ ትእግስት የኔአባት

ታህሳስ 24/04/2010
ኢንዱስትሪ ዞን ልማት ቡድን ሲቪል መሀዲስ ባለሙያ

የመመማር ሰነድ

-
አዘጋጅ፡ አቶ መኳንንት እጅጉ

ሰኔ 21/10/2010
የኢንዱስትሪ ዞን ልማት ቡድን  ኸርባን ፕላነር ባለሙያ

  

የመመማር ሰነድ

-
አዘጋጅ፡ አቶ አለምቀረ አሰፋ

የካቲት 15/06/2010

You might also like