You are on page 1of 6

የአካባቢ ደህንነት ትግበራ መመሪያ (Environmental Contract clauses)

ከቀበሌ 08 ቦሌ አሮጌዉ ተፋሰስ እስከ 30 ሜትር መንገድ ስራ የተፋሰስ ግንባታ

ይህ የአከባቢ ትግባራ መመሪያ በደ/ማርቆስ አስተዳደር ከተማ ልማት ቤቶች ኮንስትራክሽን ግሎት ጽ/ቤት ስር
በሚከናወኑ ስራዎች የሚሳተፉ ኮንትራክተሮች ግንባታዎች በሚከናወኑበት ወቅት ከአካባቢ እና ህብረተሰብ ደህንነት
አንጻር ጥንቃቄ መደረግ ያለባቸው ጉዳዮች የያዘ መመሪያ ሲሆን ለአሰራር ያመች ዘንድ ይህ መመሪያ የውለታ ሰነድ አካል
የሚደረግ ሆኖ ማነኛውም ግንባታ ለማከናወን ከከተማ ልማት ቤቶች ኮንስትራክሽን አገልግሎት ጽ /ቤት ውለታ
በመግባት ግንባታ የሚያከነው ንኮንተራክተርን የተዘረዘሩትን ጉዳዮች የመተግበር ግዴታ አለበት

1 በፕሮጀክት ሳይት አካባቢ ከመተግበር የተከለከሉ ነገሮች፤

 በፕሮጀክት ግንባታ ከተመረጠው ሳይት ውጭ የሚገኝ ማንኛውም አትክልት መቁረጥ


 በአካባቢው የሚገኙ የዱር እንስሳት አደን ማድረግ፤
 ያልተፈቀዱ የተከለከሉ በካይ ኬሚካሎች ከመጠቀም መቆጠብ
 የአከካባቢውን ስነ-ህንጻና ታሪካዊ ጉዳዮች የሚያውኩ ጉዳዮች +ፐማከናወን የተከለከለ ነው
 በአካባቢው ላይ የእሳት አደጋ የሚያስነሱ ማተሪያሎችን ማከማቸትና ለእሳት አደጋ የሚያጋልጡ
ተግባራትን መፍጠር የተከለከለነው

2 ወደ ግንባታ ከተገባ በኋላ የሚደረጉ አጠቃላይ ጥንቃቄዎች

በሳይት ላይ የሚፈጠሩ ቁሳቁሶችን ከማስተዳደር ለጎርፍ አደጋ የሚያጋልጡ ሁኔታዎችን ከመከላከል አ ንፃር መደረግ
ያለባቸው ጥንቃቄዎች

ማንኛውም ግንባታ በሚከናወኑበት ቦታ የሚፈጠር ደረቅና ፍሳሽ ቆሻሻ በተገቢው መንገድ መወገድ ያለባቸው
ሲሆን ይህን ስራ ለመስራት ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ተግባራት መከናወን ይኖርባቸዋል

I ከቆሻሻ አወጋገድ መንገድ ጋር በመያያዝ

 በተቻለ መጠን ግንባታ ሳይት ለይ የሚመነጭ ቆሻሻን ለመቀነስ ጥረት ማድረግ


 በሳየቱ ላይ የሚመነጩና ለግንባታ ግብዓት የሚያገለግሉ አደገኛ የሆኑ ደረቅና ፍሳሽ ቆሻሻዎች
በተገቢው መንገድ መለየት ማስቀመጥ ማጓጓዝ ማስወገድ
 በሳይት ላይ የሚመነጩ ቆሻሻዎች በተፈቀዱ ቦታዎች ላይ እንዲወገድ ማድረግ
 ማንኛዉንም በሳይት ላይ የሚመነጩ ደረቅና ፍሳሽ ቆሻሻ ከማንኛውም የውሃ አከካል ከ 300 ሜትር
ርቀት በላይ መወገድ ይኖርበታል፡፡

II በሳይት ላይ በሚደረግ የተሸከርካሪ ጥገና ወቅት መደረግ ያለበት ጥንቀቄዎች

 ማንኛዉም የሳይት የተሸከርካሪ ጥገና ከማንኛም የውሃ አካል ከ 15 ሜትር ርቀት በላይ በሆነ ቦታ ላይ
መከናወን ይኖርበታል ፡፡
 ማንኛውም የተሸከርካሪ ጥገና ማከናወን ያለበት ለጥገና በተፈቀደው ቦታ ላይ ሆኖ ከጥገና የሚወጡ
ፍሳሾች በካባቢው ወደሚገኝ ወንዝ የጎርፍ ውሃ መውረጃ ቦይና የፍሳሽ ማስወገጃ ቱቦ ውሰጥ
መጨመር የተከለከለ ነው

1
III በሳይትና በአካባቢ ላይ የሚከሰት የጎርፍ አደጋን ከመከላከል አንጻር መስራት ያለባቸው ተግባራት

 ለግንባታ ቦታ ተብሎ የአፈር ቆረጣ የተደረገባቸው ቦታዎች ላይ የጎርፍ ውሃ ገብቶ ችግር


እንዳይፈጥር ለመከላከለል ይቻል ዘንድ የውሃ መከላከያ ክትር ወይም ቦይ መስራት ተገቢነው
 በሳይቱ ላይ ሊነሳ የሚችል በነፋስ ሀይል የመሸርሸር አደጋን ለመከላከል ይቻል ዘንድ በሳይቱ ውስጥና
አካባቢ የሚገኙ መንገዶች የአፈር ቁልል እና የተቆፈሩ ቦታዎች ላይ ቢያንስ በቀን ሁለት ጊዜ የውሃ
ርጭት ስራ መናከናወን
 ከሳይት አካባቢ የሚገኙ መንገዶች የሚነሳውን ብናኝ አፈር ለመቀነስ በአካባቢው የሚንቀሳቀሱ
ተሸከርካሪዎች ፍጥነት ከ 10 ኪሎሜትር በስዓት መብለጥ የለበትም
 በሳይቱ የተለዩ ስራዎችን ለመስራት የሚቆፈሩ ጉድጓዶች በጣም ተዳፋት ከሆነ ቦታዎች ለጎርፍ
ተጋላጭ ከሆነ አካባቢ እና ውሃ ከሚፈስበት አካባቢ ተስማሚ በሆነ እርቀት መሰራት ይኖርበታል፡፡
 ለግንባታ የሚያስፈልጉ የተመረጡ አፈርና ድንጋይ የመሳሰሉት ለማውጣትም ሆነ ለመግዛት
እንዲሁም ግበአቶች ለማውጣት ከተፈቀደ ቦታ ላይ ብቻ ላይ መሆን አለበት፡
 የግንባታ አካባቢን ከአላስፈላጊ የቖሻሻ ማጽዳትና ከሳይቱ ላይ የሚመነጩ የቆሻሻ የመድፊያ ቦታዎች
የማመቻቸትና የመጠገን ስራ ወቅቱን በጠበቀ መንገድ መከናወን አለበት

2.2 በግንባታ ስራ ወቅት የሚተገበሩ የደህንነት ህጎች

ማንኛውም ከደ/ማርቆስ ከተማ ልማት ቤቶችና ኮንስትራክሽን አገልግሎት ጽ/ቤት ጋር ውለታ ገብቶ ግንባታ
የሚያከናውን ኮንትራክተር በፕሮክቱ ሳይት አካባቢ የሚገኝ ንብረቶችንና የህብረተሰቡ የደህንነት ተግባራት
የመጠበቅ ግዴታ ያለበት ሲሆን እነዚህ የደህንነት ተግባራት የሚያከናውነው የሃገር አቀፍና ከአካባቢ የደህንነት
ህጎች መሰረት በማድረግ ይሆናል ፡፡ይህንንም መሰረት በማድረግ በግንባታ ስራ ወቅት የሚከተሎት የደህንነት
ተግባራት የሚያከናውን ሲሆን

እነርሱም፡-

 ማንኛውም የግንባታ ስራ የእግረኞችን እንቅስቃሴ መገደብ የለበትም


 የግናባታ ሰራው የሚከናወነው ት/ቤት አካባቢ ከሆነ ተማሪዎች በሚገቡትና በሚወጡበት ጊዜ የትራፊክ
አደጋ እንዳይከሰት ይህን ሁኔታ የሚያስፈጽም ባለሙያ ሊመደብ ይገባል
 ማንኛውም ግንባታ በሚከናወንበት ቦታ በአካባቢው ላይ የሚንቀሳቀሱ ተሸከርካሪዎችና ብሎም
ግለሰቦች ከአደጋ መከላከል ይቻል ዘንድ አመች በሆነ አካባቢዎች የትረፊክና ሌሎች የአደጋ መከላከያ
ምልክቶች ማድረግ የግድነው፡፡
 የግንባታ ስራ ከመጀመሩ በፊት ለሰራተኞቹ የደህንነት ህጎች በተመለከተና በአጠቃላይ ማድረግ
ስላለባቸው ጥንቃቄወዎች ስልጠና መስጠት ይኖርበታል ፡፡
 በግንባታ ስራለሚሳተፉ ሰራተኞች የደንብ ልብስና ሌሎች የደህንነት መከላከያ የራስ ቅል መከላከያና
መጫሚያ ማቅረብና በስራ ስዓት እንዲጠቀሙበት ማድረግ ይኖርበታል
 ለግንባታ ግብአትነት የሚያገለግሉ ኬሚካሎች በሳይት ላይ የሚገኙ ከሆነ መደረግ ያለበትን ጥንቃቄ
የሚያሳይ ማስታወቂያ በኬሚካሎች መያዣ ላይ መለጠፍ ይኖርበታል፡፡
 በግንባታ ላይ የሚገኙና መወገድ ያለባቸው አደገኛ ኬሚካሎች ሌሎች አደጋ ሊፈጥሩ ቆሻሻ በጥንቃቄና
በሰለጠነ ባለሙያ መወገድ አለባቸው፡፡

2
 በግንባታ ወቅት በጣም ዝናብ የሚጥል ከሆነ የግንባታ ሰራ ሙሉ በሙሉ መቆም ይኖርበታል
 የግለሰቦች ነጻ እንቅስቃሴ የሚገድቡ ግንባታዎችን የሚያከናውን ማንኛውም ኮንተራክተር እንቅስቃሴን
የሚገድቡ ችግሮችን የማስወገድ ግዴታ አለበት

2.3 የድምፅና የብናኝ ችግር ለማስወገድ መደረግ ያለባቸውን ጥንቃቄዎች

 በግንባታ ሳይት 200 ሜትር ሬድየስ ውስጥ የማድረግ የትራፊክ እቅስቃሴ በስዓት 15 ኪሎ ሜትር
እና በታች በሆነ ፍጥነት እንዲከናወን ቁጥጥር ማድረግ አለበት
 በሳይት ውስጥ የሚደረግ የትራፊክ እንቅስቃሴ ከ 10 ኪሎሜትር እና በታች በስኣት መብለጥ
የለበትም
 በሳይት ውስጥ የሚመነጭ ማንኛውም የድምጽ መጠን ከ 90 ዴሲ ቤል በታች መሆን ይኖርበታል
 በጤና ተቋማትና በት/ቤቶች አካባቢ በተለየ ሁኔታ ከፍተኛ የሆነ ድምጽ እንዳይከሰት ጥንቀቄ
ማድረግ አለበት
 በግንባታ በሳይት አካባቢ የሚመነጭ አቧራና ሌላም ብናኝ በአካባቢው ላይ ተፅእኖ እንዳይፈጥር
የተለያዩ ማስወገጃ መንገዶችን በመጠቀም ማስወገድ ይኖርበታል
 በንፋስ የሚመጣ የአፈር ከለትን ይቻል ዘንድ በሳይቱ ላይ የሚገኝ በሳር የተሸፈነ መሬት መቆፈረና
እንዲሁም ዛፍ መቁረጥ የተከለከለ ተግባር ነው
 በአካባቢው የሚገኙ የመኖሪያ ቤቶች የንግድ ቤቶችና የመናፈሻ ቦታዎች ከአቧራና ከሌላም
ከሚወጣ ብናኝ ብክለት ለመከላል ይቻል ዘንድ ግንባታ የሚከናወንበትን ቦታ አቧራና ብናኝ
በማያሳልፍ ወንፊት ነገር መከላከል የግድነው
 በሳይቱ ውሰጥ የሚመነጭ የአቧራ ብክለት ለመቀነስ በቀን ቢያነስ 2 ግዜ የውሃ ርጭት ስራ
ማከናወን አለበት
 በሳይት ውሰጥ የሚደረግ የመደቅደቅ ስራ /ኮምፓክሽን ስራ በአካባቢው በሚገኙ የግለሰብ ቤቶችና
ሌሎችም መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት ላይ ጉዳት እንዳያደርስ በጣም ከፍተኛ የሆነ
ጥነቃቄ መደረግ አለበት

3 የሚከናወኑ ተግባራት በግንባታ አካባቢ ከሚገኝ ህብረተብ ጋር የሚደረግ ግንኙነት በተመለከተ

ማንኛውም ግንባታ በደ/ማርቆስ ከተማ የሚከናወን ኮንተራክተር የሚያከናወነው ግንባታ በህብረተሰቡ ተቀባይነት
እንዲኖረውና መልካም የሆነ የስራ አካባቢ ለመፍጠር ከዚህ በታች የተዘረዘሩን ተግባራት ማከናወን ይኖርበታል

 ለአካባቢ ህብረተሰብ ኮንተራከተሩ ስለሚያከህደው የግንባታ ስራ ግንባታው የሚወስደው ግዜ ግንባታ


የሚያከናወንበት የስራ ስዓት በግንባታ ስራ ምከንያት የሚቋረጡ አገልግሎቶች ተለዋጭ መንገዶችን
በተመለከተ በተገቢው መንገድ ግዛቤ መፍጠር ይኖርበታል
 በሌሊት የሚካሄዱ ስራዎች ማከናወን የተከለከለ ነው ሆኖም ግን የግንባታ ስራውን በሌሊት ማከናወን
አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ ግንባታው በሚካሄድበት አካባቢ ለሚገኙ ህብረተሰብ የግንዛቤ ፈጠራ ስራ
መስራት አለበት
 በግንባታው ምክንያት ማንኛውም የህዝብ አገልግሎት (ውሃ መብራት የቴሌፎን አገልግሎት) የሚቋረጥ
ከሆነ አገልግሎቱ ለሚቋረጥበት ህብረተሰብ ከአምስት ቀን በፊት አገልግሎት እንዲቋረጥ መገለጽ
አለበት፡፡

3
Environmental Management Plan /የአካባቢ አያያዝ እቅድ/
ከቀበሌ 08 ቦሌ አሮጌዉ ተፋሰስ እስከ 30 ሜትር መንገድ ስራ የተፋሰስ ግንባታ

አየአካባቢ አያያዝ እቅድ ወይም /Environmental Management plan/ ማለት አንድ ፕሮጀክት በሚሰራበት
ወቅት ፕሮጀክቱ በሚሰራበት አካባቢ ላይ ሊደርስ የሚችለዉን አሉታዊ ተጽእኖ ለማስቀረት ወይም ለመቀነስ
የሚከተሉትን ተግባራት ዝርዝር ሁኔታዎችን የያዘ እቅድ ነዉ፡፡ በዚህም መሰረት ይህ ፕሮጀክት በሚሰራበት
አካባቢ ለሚሰራዉ የመሰረተ ልማት ስራ በአካባቢዉ ላይ ሊደርስ የሚችለዉን አደጋዎች ለመቀነስ
የሚተገበሩትን ስራዎችንና ማን እንደሚተገብራቸዉ የሚያሳይ እቅድ ነዉ፡፡ በመሆኑም በሚከተለዉ ሰንጠረዥ
መሰረት የሚመለከተዉ አካል ማለትም የዚህ ኮብል ስቶን ተቋራጭ ዝርዝር ተግባራቱን ምንም ሳይሸራርፍ
መተገበር ይጠበቅበታል ፡፡

እነዚህም ተግባራት የሚከተሉት ናቸዉ ፡፡

1. በቁፋሮ የተገኘን አፈር ማንሳት በሚያስፈልግበት ግዜ ፈጥኖ የማነሳት ግዴታ አለበት


2. የስራ ተቋራጩ ስራዉን በሚሰራበት ግዜ በቸልተኝነት ለሚፈጠረዉ ማንኛዉም የአካባቢና ማህበረዊ
ተጽእኖ ችግር ሙሉ ተጠያቂ ነዉ፡፡
3. ስራዉ በሚሰራበት ግዜ በአካባቢዉ ላይ ከባድ ተጽእኖ የሚስከትል መሆኑ በባለሙያዉ ከተነገረዉ
ፈጥኖ ባለሙያዉ የሚዝዘዉን የተጽእኖ ማቅለያ ስራ መስራት አለበት
4. ከዚህ በላይ ከተዘረዘሩት ዉጭ የሚያጋጥሙ ማነኛዉም ተጽእኖዎች ዉለታዉን በሰጠዉ አካል
ማለትም በደብረማርቆስ ከተማ ልማት ቤቶችና ኮንስትራክሽን ጽ/ቤት ፍላጎት መሰረት መሰራት
አለባቸዉ፡፡
5. የስራ ተቋራጩ ስራዉን በሚሰራበት ግዜ ያለ አግባብ ስራ በማጓተት የአካባቢዉን ማህበረሰብ የእለት
ተእለት ስራና ማህበራዊ ሁኔታዎችን የሚስተጓጉል ከሆነ ሙሉ ተጠያቂ ይሆናል ፡፡
6. ማነኛዉም ስራ ተቋራጭ በቀን ሰራተናነት የሚይዛቸዉን ሰራተኞች በአግባቡ የመያዝ ግዴታ አለበት
7. የስራ ተቅራጩ ስራዉን በሚሰራበት ግዜ ለሚያሰራዉ መሰረተ ልማት ማለትም ኮብልስቶን መንገድ፣
የመብራት ፖል ፣የስልክ ፖልና ኬብል እንዲሁም የዉሃ መስመሮችን ከቆረጠ ተጠያቂ ይሆናል ፡፡
8. የስራ ተቋራጩ ለህብረተሰቡ ጥቅም ሲባል ስራዉን በጥራት በተሰጠዉ ስፔስፊኬሽን መሰረት
የመስራት ግዴታ አለበት፡፡

4
የግንባታግ የትግበራወ የሚደርሰዉ አሉታዊ የማቃለያ እርምጃ ሃላፊነቱን የሚወስደዉ አካል የሚስፈልገዉ ዋጋ
ዜ ቅት ተጽእኖ
ከግንባታበ ቦታዉን የአገልግሎት በሚመለከተዉ የአገልግሎቱን መስመር ለሚያስተዳድረዉ የደ/ማ/ --
ፊት ከ 3 ኛ ወገን መስመሮች ላይ መስሪቤት ወይም ድርጅት ካሳ በመክፈል በተገቢዉ ቦታ ከተማቤቶችልማትኮንስትራክሽንአ
ነጻ ማድረግ ተጽእኖ መፍጠር እንዲዛወሩ ማድረግ ገ/ጽ/ቤት
ቴሌ፣መብራትሃይልናዉሃአገ/ጽ/
ቤት
-የግለሰቦች፣ የንግድ -ወቅታዊ ዋጋን ባገናዘበ መልኩ ተገቢዉን ካሳ መክፈል -የደብረማርቆስ ከተማ ቤቶች ልማት --
ቤቶች ጉዳት -ሙሉ በሙሉ ለሚፈናቀሉ ግለሰቦች ማህበራ ኮንስትራክሽን አገ/ጽ/ቤት
ማድረስ ዊኑሮአቸዉን በማይነካ መልኩ በአካባቢቸዉ ወይም -ቴሌ፣ መብራት ሃይልና ዉሃ
እንደግለሰቦች ፍላጎት በአይነትና በጥሬ ገንዘብ ካሳ መክፈል አገ/ጽ/ቤት

በግንባታወ የመሬት አቧራ መነሳት -ሰራተኞች የአቧራ መከላከያ አልባሳት መጠቀም ኮንትራክተሩ በምህንድስና ስራ
ቅት ዝግጅት -መሬቱን በሚጠቀጠቅበት ግዜ አቧራ እንዳይከሰት ዝርዝሩ የተካተተ
ጠወዋት ጥዋት ዉሃ ማርከፍከፍ
-ለአካባቢዉ ማህበረሰብ ስራዉ ከመጀመሩ በፊት እዉቅና
መፍጠር
ለተቆፈረዉ አፈር -የተቀፈረዉን አፈር ከግንባታዉ ቦታ ለስራ እና በሰዎች ኮንትራክተሩ በምህንድስና ስራ
የመድፊያ ቦታ ላይ ተጽእኖ እንዳያደርስ ቶሎ ማንሳት ዝርዝሩ የተካተተ
ማስፈለግ -የተቆፈረዉን አፈር በከተማዉ እስከ 5 ኪሎሜትር ባለዉ
ክልል ዉስጥ በሚገኙ የተጎዳ መሬት ባለበት አካባቢ
የመድፋት ግዴታ አለበት
የድምጽ ብክለት -የድምጽ መከላከያ መሳሪያ መጠቀም ኮንትራክተሩ በምህንድስና ስራ
-ጠንካራ አለት በሚቆፈርበት ግዜ ከ ፍተኛ ድምጽ ዝርዝሩ የተካተተ
ስለሚፈጠር ለአካባቢዉ ማህበረሰብ ቀድሞ ማሳወቅ
-ከህብረተሰቡ ጋር መግባባት ሳይደረስ የጠንካራ አለት
ቁፋሮ በምሽት ወቅት አለማከናወን

5
6

You might also like