Professional Documents
Culture Documents
5 lVCompleted
5 lVCompleted
የቅርብ ኃላፊ የሥራ መደብ /ተጠሪነት በሲቪል ሰርቪስ ሚኒስቴር /ቢሮ/ ብቻ የሚሞላ
የአረንጓዴና አካባቢ ጥበቃ መሰረተ ልማት የሥራው ደረጃ የሥራው ኮድ
ስታንዳዳይዜሽን ዴስክ ኃላፊ
መስሪያ ቤቱ የሚገኝበት ቦታ
1
የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስቴር የሥራ ዝርዝር መግለጫ ቅጽ
የአረንጓዴ ልማት የሚካሄድባቸው ህንጻዎች፣ ፓርኮች፣ የመንገድ አካፋዮች፣ ለተቋማት ወዘተ የሚሆን
የአረንጓዴነት ልማት ቦታዎች ማኔጅመንት ሞዴል አሰራር ስርዓት ይቀርጻል፣
በአረንጓዴ የልማት ቦታዎች ማለትም ፓርክ፣ የመንገድ ዳርቻ፣ መናፈሻዎች የውስጥ አደረጃጃትን(መቀመጫ፣
የአገልግሎት መስጫ ወዘተ) ከሚመለከተው አካል ጋር በመሆን ሞዴል አሰራር ይቀርጻል፣
በአረንጓዴና አካባቢያዊ መሰረተ ልማት ስታንዳርድ ዝግጅት ላይ ይሳተፋል፣ ግብረመልስ ይሰጣል፣
ዉጤት 3. በከተሞች የአረንጓዴና አካባቢ ጥበቃ መሰረተ ልማቶች ላይ ሰነድ በማዘጋጀት ስልጠና መስጠት
በከተሞች አረንጓዴ መሰረተ ልማቶች ላይ የእፅዋቶች ዝርያ መረጣ፣ አተካከልና እንክብካቤ ላይ ስልጠና ለመስጠት
የሚያስችል እቅድ ያዘጋጃል፣
ለባለሙያዎች በከተሞች የእፅዋት ዝርያ መረጣ ላይ የስልጠና ሰነድ ያዘጋጃል፤ ለውይይት በማቅረብና በማዳበር
ያስጸድቃል፤
በተዘጋጀዉ ሰነድ መሰረት ስልጠና ይሰጣል፣ በተሰጠዉ ስልጠና መሰረት ለዉጥ መምጣቱንም ይከታተላል፣
ውጤት 4. ክትትልና ድጋፍ ማድረግ
በከተሞች አረንጓዴ መሰረተ ልማቶች ላይ የእፅዋቶች ዝርያ መረጣ፣አተካከልና እንክብካቤ በሳይንሱ መሰረት
እየተካሄደ መሆኑን ለመከታተልና ለመደገፍ የሚያስችል እቅድ ያዘጋጃል፣
ከተሞች በእቅዱ መሰረት እየተገበሩ መሆናቸዉን ለመከታተል የሚያስችል ዝክረ ተግባር በማዘጋጀት ስራዎች
በከተሞች ተግባራዊ ስለመሆናቸዉ ክትትልና ድጋፍ ያደርጋል
በክትትልና ድጋፍ ወቅት በተለዩ ችግሮች ላይ የመንግስት ፖሊሲዎችን፣ ህጎችን፣ ስትራቴጅዎችንና ፕሮግራሞችን
ተመርኩዞ የመፍትሄ አቅጣጫ ይሰጣል
III. የሥራው ባህሪ መግለጫዎች
3.1. የሥራ ውስብስብነት
ሥራው በከተሞች አረንጓዴ መሰረተ ልማቶች ላይ የእፅዋቶች ዝርያ መረጣ፣ አተካከልና እንክብካቤ ላይ ጥናት
ማድረግ፣ በአረንጓዴ መሰረተ ልማቶች አያያዝና ማኔጅመንት ላይ ለፖሊሲ የሚሆኑ ሀሳቦችን ማመንጨት፣
በከተሞች ያለውን የአየር ስነምህዳር ሁኔታ ታሳቢ በማድረግ፣ ለህንጻዎች፣ ለፓርኮች፣ ለአካፋዮች፣ ለመንገድ
ዳርቻዎች፣ ለፕላዛዎች ወዘተ የሚሆኑ ችግኞችን መምረጥ፣ የአረንጓዴ ልማት የሚካሄድባቸው ህንጻዎች፣
ፓርኮች፣ የመንገድ አካፋዮች፣ ዳርቻዎች፣ ደኖች፣ ለተቋማት ወዘተ የሚሆን የአረንጓዴነት ልማት ማኔጅመንት
አሰራር ስርዓት መቅረጽ፣ በአረንጓዴ የልማት ቦታዎች ማለትም ፓርክ፣ የወንዝ የመንገድ ዳርቻ፣ መናፈሻዎች
የውስጥ አደረጃጃትን(መቀመጫ፣ የአገልግሎት መስጫ ወዘተ) ከሚመለከተው አካል ጋር በመሆን አሰራር መቅረጽ፣
አዳዲስ የአሰራር ስልቶችንና የሀገራት ተሞክሮዎችን ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችል ተሞክሮ መቀመር፣
ከተሞች ስራዎችን በእቅዱ መሰረት እየተገበሩ መሆናቸዉን ለመከታተል የሚያስችል ዝክረ ተግባር ማዘጋጀት፣
በክትትልና ድጋፍ ወቅት በተለዩ ችግሮች ላይ የመንግስት ፖሊሲዎችን፣ ህጎችን፣ ስትራቴጅዎችንና ፕሮግራሞችን
2
የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስቴር የሥራ ዝርዝር መግለጫ ቅጽ
ተመርኩዞ የመፍትሄ አቅጣጫ መስጠት፣ የዘርፉን የስልጠና ሰነድ ማዘጋጀት የሚያካትት ነው፡፡
ሥራው በሚከናወንበት ወቅት በርካታ አዳዲስ አሰራሮችን ማለማድ የሚጠይቅ መሆኑና ይህን አለመቀበል፣
ለተለያዩ አካላት የሚደረገው ለስራው ትኩረት እንዲሰጠው የማድረግ ስራ አጥጋቢ ምላሽ አለማግኘት፣ የሚዘጋጁ
ዓለም አቀፍና ሀገራዊ ምርጥ ተሞክሮዎችን ማጣጣም የሚጠይቅ መሆኑ፣ ዝክረ ተግባር ዝግጅት ላይ ያለው ልምድ
አናሳ መሆን፣ ከክፍሉ ሰራተኞችና ከባለድርሻ አካላት ጋር ያለው ቅንጅታዊ አሰራር ደካማ መሆን የሚያጋጥሙ
ችግሮች ሲሆን
እነዚህን ችግሮች ለመፍታት የተለያዩ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና በመስጠት፣ የልምድ ልውውጥ በማድረግ፣
ምርጥ ተሞክሮዎችን በመቀመር፣ ቅንጅታዊ አሰራር የሚኖርበትን ስልት በመቀየስ እና ጥናቶችን በማድረግ
ይፈታሉ፡፡
3.2. ራስን ችሎ መስራት
3.2.1 ሥራው የሚከናወንበት አግባብ
ሥራው ደንብና መመሪያን እና የስራ ክፍሉን ዕቅዶች፣ በዘርፉ ያሉ ጥናቶችና የአሰራ ሰነዶች መሠረት በማድረግ
ይከናወናል፡፡
3.2.2 ሥራው የሚጠይቀው የክትትልና ድጋፍ ደረጃ
ሥራው ተፈላጊውን ውጤት ከማምጣት አንጻር በመጨረሻ በአጠቃላይ ግምገማ ይደረግበታል፡፡
3.3. ተጠያቂነት
3.3.1 ተጠያቂነት ለሥራ ውጤት /Responsibility for Impact/፣
ሥራው በከተሞች አረንጓዴ መሰረተ ልማቶች ላይ የእፅዋቶች ዝርያ መረጣ፣ አተካከልና እንክብካቤ ጥናት ማካሄድ፣
በከተሞች ያለውን የአየር ስነምህዳር ሁኔታ ታሳቢ በማድረግ፣ ለህንጻዎች፣ ለፓርኮች፣ ለአካፋዮች፣ ለመንገድ
ዳርቻዎች፣ ለፕላዛዎች ወዘተ የሚሆኑ ችግኞችን መምረጥ፣ የአረንጓዴ ልማት የሚካሄድባቸው ህንጻዎች፣
ፓርኮች፣ የመንገድ አካፋዮች፣ ዳርቻዎች፣ ደኖች፣ ለተቋማት ወዘተ የሚሆን የአረንጓዴነት ልማት ማኔጅመንት
አሰራር ስርዓት መቅረጽ፣ በአረንጓዴ የልማት ቦታዎች ማለትም ፓርክ፣ የወንዝ የመንገድ ዳርቻ፣ መናፈሻዎች
የውስጥ አደረጃጃትን(መቀመጫ፣ የአገልግሎት መስጫ ወዘተ) ከሚመለከተው አካል ጋር በመሆን አሰራር መቅረጽ፣
ስልጠና ለመስጠት እና ክትትልና ድጋፍ ለማድረግ የሚያስችል የስልጠና ሰነድና ቢጋር ማዘጋጀት፣ በከተሞች
አዳዲስ የአሰራር ስልቶችንና የሀገራት ተሞክሮዎችን በከተሞች ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችል ልምድ መቀመርና
ማስፋት፣ በአረንጓዴ መሰረተ ልማቶች አያያዝና አስተዳደር ላይ ለፖሊሲ የሚሆኑ ሀሳቦችን ማመንጨት፣ ከተሞች
ስራዎችን በድጋፍና ክትትል ወቅት በተለዩ ችግሮች ላይ የመንግስት ፖሊሲዎችን፣ ህጎችን፣ ስትራቴጅዎችንና
ፕሮግራሞችን ተመርኩዞ የመፍትሄ አቅጣጫ መስጠት፣ የዘርፉን የስልጠና ሰነድ የማዘጋጀት ተግባራት መስራት
የሚጠይቅ ነው፡፡
ሥራው በሚፈለገው ደረጃ ባይከናወን ወይም በሥራ ክንውን ወቅት የሚፈጠሩ ስህተቶች ባይታረሙ በከተሞች
3
የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስቴር የሥራ ዝርዝር መግለጫ ቅጽ
የአካባባውን ስነምህዳ ያላማከሉ ችግሮች ስለሚተከሉ የከተሞችን ገጽታ ይበላሻል፣ የሚተከሉ ችግኞች ተገቢው
የእንክብካቤ ደረጃ የማይደረግላቸው ከሆነ የከተሞች ለአየር ንብረት ብክለትና ተጽዕኖ ይጋለጣሉ፣ የከተሞች
የወንዝ ዳርቻዎች አካቢያቸው ካልለማ የከተማ ነዋሪ ለጎርፍ አደጋ ተጋላጭ ይሆናል፣ ፓርኮች መናፈሻዎች ወዘተ
ደረጃውን በጠበቀ መልኩ የማይለሙ ከሆነ የከተማው ህብረተሰብ የአኗኗር ዘይቤን በአሉታ ይቀይራሉ፣ በከተሞች
ውበትና አረንጓዴ ልማት ዕቅድ አፈጻጸም ላይ ተጽዕኖ ይኖረዋል ይህም በተቋሙ እቅድ አፈፃፀም ላይ አሉታዊ
ተፅእኖ ያሳድራል፡፡
4
የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስቴር የሥራ ዝርዝር መግለጫ ቅጽ
5
የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስቴር የሥራ ዝርዝር መግለጫ ቅጽ
የአረንጓዴነት ልማት ማኔጅመንት የተለያዩ አማራጭ አሰራር ሰነዶችን ማንበብና ስርዓት መቅረጽ፣ በአረንጓዴ
የልማት ቦታዎች ማለትም ፓርክ፣ የወንዝ የመንገድ ዳርቻ፣ መናፈሻዎች የውስጥ አደረጃጃትን(መቀመጫ፣
የአገልግሎት መስጫ ወዘተ) ከሚመለከተው አካል ጋር በመሆን የተለያዩ አማራጭ አሰራር ሰነዶችን ማንበብና
ስርዓት መቅረጽ፣ ስልጠና ለመስጠት እና ክትትልና ድጋፍ ለማድረግ የሚያስችል የስልጠና ሰነድና ቢጋር ማዘጋጀት
፣ በከተሞች አዳዲስ የአሰራር ስልቶችንና የሀገራት ተሞክሮዎችን በከተሞች ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችል
ልምድ መቀመርና ከሀገራችን ተጨባጭ ሁኔታ ጋር ማጣጣም፣ በአረንጓዴ መሰረተ ልማቶች አያያዝና አስተዳደር
ላይ ለፖሊሲ የሚሆኑ ሀሳቦችን ማመንጨት፣ የንባብና የጽሕፈት ሥራዎችን በኮምፒውተር ማከናወን እይታን
የሚያደክሙ ሲሆኑ፣ ይህም ከቀን የሥራ ጊዜው 35 በመቶ ይወስዳል፡፡
6
የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስቴር የሥራ ዝርዝር መግለጫ ቅጽ