You are on page 1of 2

መልካምዘር፤ሲሳይና ጓደኞቻቸው የአካባቢ ብክለት ክትትልና ቁጥጥር ጀማሪ አማካሪ

የህ/ሽ/ማህበር በኮ/ቀ/ክ/ከተማ በወረዳ 13፣14፤15 አስተዳደር ስር በአዲስ አበባ የአካባቢ

ጥበቃና አረንጓዴ ልማት ኮሚሽን አማካኝነት የተቐቐመ ማህበር ከጥር 8-14 ሣምንታዊ

ሪፖርት፡፡

1. ከኮ/ቀ/ክ/ከ አካባቢ ጥበቃ ጽ/ቤት ጋር የስራ ውል የስምምነት ሰነድ ተፈራርመናል


2. የማህበሩ አባላት በጋራ በመሆን የ 3 ወር፤የወርና ሣምንታዊ ዕቅድ አዘጋጅተናል

3. የማህበሩ አባላት ከየወረዳዎቹ(13፤14፤15) አካባቢ ጥበቃ ጽ/ቤት ሀላፊዎች ጋር በጋራ በመሆን

ባለድርሻ ሴክተር የመንግስት መስሪያ ቤቶችን ለይተናል

4. የማህበሩ አባላት ከየወረዳዎቹ(13፤14፤15) አካባቢ ጥበቃ ጽ/ቤት ሀላፊዎች ጋር በጋራ በመሆን

የአካባቢ ብክለት ምንጭ ሊሆኑ ይችላሉ ተብለው የታሰቡ አገልግሎት ሰጪ ተቐማትን

ያጋጠሙ ችግሮች
 ማህበሩ አንዳንድ ስራዎችን ሊሰራበት የሚችልበት ቐሚ የሆን ቢሮ በ 3 ቱም
ወረዳዎች ላይ አለማግኘት
 ለስራው የሚሆኑ የጽህፈት አገልግሎት የሚውሉ ግብዓቶችን በበቂና በተፈለገው
ጊዜ አለማግኘት

የተወሰዱ የመፍትሄ እርምጃ


 የቢሮ ችግሩን ለመፍታት ከየወረዳዎቹ ስራ አስፈፃሚዎች ጋር መነጋገርና ለጊዜው
በወረዳ 14 ጊቢ ውስጥ የማህበሩ አባላት በመንግስት የስራ ሰዓት በአግባቡ መገናኘት
 ለስራው የሚውሉ ግብዓቶችን(ለኮፒ፤ለፕሪንተር፤ለፅህፈት ወዘተ) የማህበሩ አባላት
መዋጮ እንዲያዋጡ ተደርጋል

በቀጣይ ሳምንታት ማህበሩ የሚሰራቸው ስራዎች


 የአካባቢ ብክለትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚያስችል አሰራርን በመዘርጋት አገልግሎት ሰጭና ማምረቻ
ተቋማት ላይ ክትትልና ቁጥጥር ማድረግ
 የግንዛቢ መፍጠሪያ ሰነድ ማዘጋጀት
 ግንዛቤ መፍጠር-ለማህበረሰብ፤የብክለት ምንጭ ለሆኑ ተቐማት፤ወዘተ
 በተዘጋጀው የመረጃ መሰብሰቢያ ፎርማት መሰረት መረጃ መሰብሰብ መጀመር
 ከፍተኛ ብክለት እያስከተሉ ያሉ አምራችና አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶችን መለየት
 በሂደቱ ከብክለት ምንጭነት ያልታቀቡ ተቐማትን ለኮሚሽኑ ማሳወቅ
 መድረኮች በአካባቢ ብክለት ችግሮችና መፍትሄዎች ላይ ለተለያዩ የወረዳው አገልግሎት ሰጪ ተቐማት የግንዛቤ
ማስጨበቻ ስራ መስራት

You might also like