Professional Documents
Culture Documents
FCD-CEO 2016 2st Qurter Report
FCD-CEO 2016 2st Qurter Report
ቀን 26/04/2016 ዓ.ም
የኢ.ኅ.ሥ.ኮ
በፋይናንስ ኅብረት ሥራ ልማት መሪ ሥራ አስፈጻሚ የ 2016 በጀት ዓመት የሁለተኛ ሩብ ዓመት ዕቅድ
አፈጻጸም -----ገጽ ሪፖርት ከዚህ ማስታወሻ ጋር አያይዘን ያቀረብን መሆናችንን እንገልጻለን፡፡
ከሠላምታ ጋር!!
እንዲያውቁት፡-
ለኮሚሽነር ጽ/ቤት፣
የኢ.ኅ.ሥ.ኮ
የፋይናንስ ኅብረት ሥራ ልማት ዳይሬክቶሬት
3.2. ኦሬንቴሽን................................................................................................................................................2
4. የትግበራ ምዕራፍ...............................................................................................................................................2
4.1. የፕሮግራም በጀት ዕቅድ ክንውን..................................................................................................................2
i
1. መግቢያ
በገጠርና በከተማ ለሚኖረው የኅብረተሰብ ክፍል ሌሎች በተለይም የፋይናንስ ተቋማት የማይሸፍኑትንና የማያቀርቡትን የፋይናንስ
አገልግሎት የፋይናንስ የኅብረት ሥራ ማህበራት አገልግሎቱን ተደራሽ በማድረግና ቀልጣፋ የፋይናንስ ስርዓት በገጠርና በከተማ እንዲስፋፋ
በማድረግ ረገድ የማይተካ ሚና አላቸው፡፡ አባላትንና ሌላውን የህብረተሰብ ክፍል ከተለያዩ የፋይናንስ ተቋማትጋር አገናኝ ሰንሰለት ሆነው
እያገለገሉ በመሆኑ የራሳቸውን የፋይናንስ አሠራርና አቅም ማጎልበት አማራጭ የሌለው ጉዳይ እንደሆነ ይታመናል፡፡
ይህንንም በቀጣይ አጠናክሮ ለማስቀጠል የፋይናንስ ኅብረትሥራ ልማት ዳይሬክቶሬትም በበጀት ዓመቱ ዕቅድ አቅዶ ወደ ሥራ ሲገባ
የየራሳቸው ዋና ዋና ተግባርና ዝርዝር ተግባራት ያሏቸው 14 ግቦችንና ከእነዚህ ግቦችም የሚጠበቁው ጤቶችን አስቀምጧል፡፡
በመደበኛው ፕሮግራም የሚከናወኑ ተግባራትን በተጨማሪ በተመረጡ ክልሎችና ወረዳዎች ሠፊ ዕገዛና ድጋፍ የሚያደርጉት የአነስተኛ
የገጠር ፋይናንስ ተቋማት ማስፋፊያ ፕሮግራም፣ በልማታዊ ሴፍቲኔት ፕሮግራም የቤተሰብ ኑሮ ማሻሻያ እና ቆላማ አከባቢ የኑሮ ማሻሻያ
ፕሮጀክት (LLRP) የሚከናወኑ ተግባራትም በዕቅድ ተይዘው ወደ ሥራ የተገባ ሲሆን በአጠቃላይ በፋይናንስ ኅብረት ሥራ ልማት የ 2016
ዓ.ም የሁለተኛ ሩብ ዓመት ዕቅድ ክንውን አፈፃፀምን ተዘጋጅቶ እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡
የፋይናንስ አገልግሎትና ስርዓቱን በማሻሻል፣ በማጠናከርና ተደራሽ እንዲሆን ለማድረግ የፋይናንስ ኅብረት ሥራ ማህበራትን አቅም
ማጎልበት ዋናው ዓላማ ሲሆን፣
የፋይናንስ ኅብረት ሥራ ማህበራትን በማደራጀት ለአባላቱ የፋይናንስ አገልግሎትን ተደራሽ ማድረግ፤
የፋይናንስ ኅብረት ሥራ ማህበራት በውስጥ አሰራራቸው፣ በቁሳቁስና በገንዘብ አቅማቸው የተጠናከሩ እንዲሆኑ ማድረግ፤
የፋይናንስ ኅብረት ሥራ ማህበራትን እርስ በእርሳቸውና ከሌሎች የኅብረት ሥራ ማህበራት ጋር በፋይናንስ ግብይት በማስተሳሰር
የፋይናንስ አገልግሎቶችን እንዲያገኙ ማድረግ፤
የአነስተኛ ገጠር ፋይናንስ ተቋማት ማስፋፊያ ፕሮግራም የተግባር አፈፃፀምን መከታተል፣ መገምገምና ማቅረብ፤
የፋይናንስ ኅብረት ሥራ ልማት መሪ ሥራ አስፈጻሚ ሥራዎችን በማስተባበር፣ በመደገፍና የንዑስ ፕሮግራም ውጤቶችን በማሳካት
የተቋሙን ተልዕኮ መፈፀም ነው፡፡
3. የዝግጅት ምዕራፍ
1
አስፈጻሚ ከተሰጠው ተልዕኮ አኳያ በመቃኘት ሊከናወኑ የሚገባቸው ሥራዎች ተቃኝተው የ 2016 ዓ.ም
በጀት ዓመት ዕቅድ ተዘጋጅቶ እንዲፀድቅ ተደርጓል፡፡
የታቀደውን ዕቅድ የተግባራቱን ነባራዊ ሁኔታ በማያት ለዴስኮች ሸንሽኖ የማስጠት እና የመፈራረም ሥራ
ተከናውኗል፡፡
በፌደራልና በክልል ያሉትን የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኅብርት ሥራ ማህበራትን ለማጠናከር የመስክ ፣ የስልጠና
እና የወርክ ሾፕ እቅዶች ተለይተው ታቀወዷል፣
3.2. ኦሬንቴሽን
የፋይናንስ ኅብረት ሥራ ልማት ዳይሬክቶሬት የ 2016 በጀት ዓመት ዕቅድ ተዘጋጅቶ በበላይ አመራሩ
ከተገመገመ በኋላ ባለሙያዎች እንዲመለከተውና የጋራ እንዲያደርገው ኦሬንቴሽን ተሰጥቶበታል፡፡
4. የትግበራ ምዕራፍ
ተግባር 1፡ በፌደራል ለተደራጁ 4 የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኅ/ሥ/ማህበራትን ማጠናከር እና ድጋፋዊ ክትትል ለማድረግ ታቅዶ 3ቱን (75%)
ማጠናከር ተችሏል፡፡
ተግባር 2፡ በክልል ለተደራጁ 116 የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኅ/ሥ/ማህበራትን ማጠናከር እና ለአደራጅ ተቋሙ ሙያዊ ድጋፍ ለማስጠት ታቅዶ
40 (111 %) የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኅብረት ሥራ ማህበራትን ማጠናከር ተችሏል፡፡
የማጠናከር ዓላማ፡-
የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኅብርት ስራ ማህበራትን፤ በአደረጃጀትና ምዝገባ፤ በአስተዳደር እና አመራር፤በአሰራር ሥርዓት
ዝርጋታ፤ በተግባሮቻቸው እና በአሰራር ግንኙነታቸው በአካል በመገኘት ያሉባቸውን ክፍተቶች ለይቶ ድጋፍና ክትትል
የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኅብርት ስራ ማህበራት አገልግሎታቸውን በማስፋፋት እና ተደራሽ በማድረግ ወጥነት ያለው አሰራር
አዲስ አበባ 11 18 22
አፋር 4 7
2
ሱማሌ 4
ጋምቤላ 1 4
3 በፌዴራል የተመዘገቡ
ድምር 40
3
አመራር ሲቀያየር ርክክብ አለመደረጉ (የፌ/ፍ/ቤ/ሠ/የገ/ቁ/ብ/ኅ/ሥ/ማህበር)
ለአባላት የሚሰጠው ብድር ተጨማሪ ገቢ ማስገኛ ላይ ትኩረት ስላልተደረገ አባላት ብድር መመልስ ሳይችሉ ሲቀሩ ያላቸውን
ቁጠባና እጣ አቻችለው መውጣት አዝማሚያ መኖሩ (የፌ/ፍ/ቤ/ሠ/ የገ/ቁ/ብ/ኅ/ሥ/ማህበር)፣
አደራጅ መስሪያ ቤቱ በእውቀት ላይ የተመሰረተ ድጋፍ አለማድረግ
የአብዛኛው ኅብረት ሥራ ማሀበር የአባላትን የብድር ፍላጎት ለሟሟላት የብድር አቅርቦት ችግር መኖሩ
የፍይናስ ችግርን ለመቅረፍ ከአቻ ኅብረት ስራ ማህበራት ሆነ ከአበዳሪ ተቋማት ትስስር አለመፍጠር
በጥናት ላይ ያልተመሰረተ የአርቦን መጠን ማሰባሰብ እና ጊዜው ያለፈበትን አርቦን ለይቶ አለማስቀመጥ (ከአዋጭ በስተቀር)
በተለያ አሚጎስ 2-3፣ የወረዳ 11 ቀበሌ 14 ነዋሪዎች የገ/ቁ/ብ/ኅ.የተ/ኅ/ሥ/ማህበር 4.2 በመቶ የህይወት መድህን አርቦን
ማስከፈል፣
1 ጽ/ቤት ለ 3 ኅብረት ሥራ ማህበራት በጋራ የሚጠቀሙ መሆኑ(አቦ የሴቶች እድር ገ/ቁ/ብ/ኅ/ሥ/ማህበር)
ዓመታዊ ዕቅድ የማያዘጋጁ ሆኑ(አቦ የሴቶች እድር ገ/ቁ/ብ/ኅ/ሥ/ማህበር
የአባላት ቁጥር 896 /2014 አደረጃጀት መመሪያ ላይ ከተቀመጠው በታች የአባላት ቁጥር ያላቸው መሆኑ
አነስተኛ የብድር መድን ዋስትና አተገባበር ከወጣው መመሪያ ውጪ ሁሉም አባል 10 ብር ከራሳቸው አውጥተው እንዲከፍሉ
መደረጋቸው
የኅብረት ሥራ ማህበሩ አመራር አደራጅ መ/ቤቱ በሚያዘጋጀው ስልጠና ላይ የመሳተፍ ፍላጎት የሌለው መሆኑ በተጨማሪም
የተወሰነው ብድር ወለድ ምጣኔ (6.25%) ከቁጠባ መለድ (7%) ያነሰ መሆኑ (አቦ የሴቶች እድር ገ/ቁ/ብ/ኅ/ሥ/ማህበር)
የአባላት ገንዘብ በነባር አመራርና በባለሙያዎች ሲመዘበር ክትትል አለመደረጉ (አዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት የገ/ቁጠባና ብድር
ኅብረት ሥራ ማህበር)
አብዛኛው ኅብረት ስራ ማህበራት ላይ ከወለድ ምጣና በተጨማር 1 በመቶ የአገልግሎት ክፍያ ማስከፈል (በተለይ አሚጎስ 4
በመቶ የአገልግሎት ወጪ ማስከፈል)
አመራሮች ሳይመረጡ ከሁለት ምርጫ ዘመን በላይ በአመራርነት መቆየታቸው(ሲቪል ሰርቪስ፣ አለርት. ወዘተ)
የተወሰኑ ኅ/ስ/መህበራት ከተቋቋሙለት አላማ ውጭ በሌሎች የካፌ አገልግሎት ስራ ላይ መሰማራታቸው(አለርት)
አብዛኛው ኅብረት ስራ ማህበራት ከዝቅጠኛ መደበኛ ቁጠባን በላይ አባላት ሲቆጥቡ መደ/ባልሆ ቁጠባ ማስቀመጥ (ከ 200-
300 ብሎም ማስቀመጥብዙሃን የ/ገ/ቁ/ብ/ኅ/ሥ/ማህበር)
ሁሉም ኅ/ስ/ማህበራት የውክልና ድምጽ አሰጣጥን ተግባራዊ ለማድረግ ስራ አለመጀመራቸው
አብዛኛው ኅብረት ስራ ማህበራት ጊዜውን ጠብቆ ጠቅላላ ጉባኤ አለማድረግ
አብዛኛው ኅብረት ስራ ማህበራት በየሶስት አመቱ ዕድሳት አለማድረጋቸው
አብዛኛው ኅብረት ስራ ማህበራት ወቅቱን የጠበቀ የኦዲት ሪፖርት አለማድረግ
የፋይናንስ አቅርቦት እያለ ለአባላት የብድር ሥርጭት ተደራሽ አለማድረግ(የተባበሩት የሸማ ነጋዴዎች የገ/ቁ/ብ/ኅብረት ሥራ
ማህበራት
በኅብረት ስራ ማኅበራት አዋጁ ቁጥር 985/2009 አንቀጽ 32 ንዑስ አንቀጽ 3 መሰረት እንደ ስራ አመራርና ቁጥጥር ኮሚቴ
ሁሉ ሌሎች ንዑሳን ኮሚቴዎችም በጠቅላላ ጉባኤ እንደሚመረጡ በሁልም ኅ/ስ/ማህበራት ዘንድ ግንዛቤ አለመኖር፤
4
ወለድ አልባ ፋይናንስ አገልግሎት ላይ ለው ግንዛቤ በሚፈለገው ደረጃ ማደግ አለመቻል በተለይም ከቀርድሃሰን በስተቀር
ለሌች አገልግሎቶች መስጠት አለመቻል (አፋርና ሱማሌ)፣
ሕጋዊ ሰውነት እና መተዳደሪያ ደንብ ሳይኖራቸው የሚሰሩ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኅብረት ሥራ ማህበራት መኖራቸው
(ጋምቤላ ክልል)፣
ለብድር ወለድ አከፋፈል አሰራርን የተከተለ አለመሆን እና የሚያስከፍሉ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኅብረት ሥራ ማህበራት
መኖራቸው ለ 10000 ብር 15000 ብር (50 ከመቶ) (ጋምቤላ ክልል)፣
5
የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ መምህራንና ሰራተኞች የገ/ቁ/ብ/ኅ/ሥ/ማህበር የኦዲት አገልግሎትና ሌሎች ድጋፎች
እንዲደረግለት በተደጋጋሚ ቢጠየቅም ምላሽ አለማግኘት( የ 4 አመት ኦዲት አለመደረግ፣በተሻሻለው አዲሱ አዋጅ
አለመተግበሩ)
ከኅብረት ሥራ ማህበራት አዋጅ 985/2009 እና አስፈላጊ የሆኑ የተለያዩ መመሪያዎች ከአደራጅ መስሪያ ቤቶች ለኅብረት ሥራ
ማህበራት በማውረድ መተግበር አለመቻሉ (ለምሳሌ የሰው ሀብት መመሪያዎች ሳይኖር ቅጥር መቅጠር እና የፋይናንስ መመሪያ
አለመኖር)
ሌሎች የፋይናንስ አገልግሎት አማራጮችን በግንዛቤ ማነስ የተነሳ ማስፋት አለመቻል(መ/ያልሆነ ቁጠባ፣የመድን
ዋስትና፣የወለድ አልባ …)፣
የገ/ቁ/ብ/ኅ/ስራ ማህበራት ከተሰማሩበት የስራ መስክ ውጪ ተሰማርቶ መገኘት (ምሳሌ ክበብ ማቋቋም፣የቤት ኪራይ
መስጠት፣የሻውር አገልግሎት)፣
6
ተግባር 3፡ በፌደራል ደረጃ በተመዘገቡት 4 የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኅብረት ሥራ ማህበራት በበጀት ዓመቱ 40,000 (ሴት 20,000)፣
በዚህ ሩብ ዓመት 10,000፣ እስኪህ ሩብ ዓመት 18,000 አዳዲስ አባላት ለማፍራት ታቅዶ በዚህ ሩብ ዓመት የተከናወነ
11,010 (ሴት 3,242) ሲሆን እስከዚህ ሩብ ዓመቱ 16,815 (ሴት 5,595) የእቅዱን 93% ማፍራት ተችሏል፡፡
ግብ 2፡ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኅብረት ሥራ ማህበራትን አገልግሎት
ተግባር 1፡- በሚሰጡትን አገልግሎት ላይ ለአባላት ግንዛቤ እንዲፈጥሩ ለ4 የገንዘብ ቁጠባና ብድር የኅብረት ስራ ማህበራት ክትትልና ድጋፍ
ለማድረግ ታቅዶ ለ3ቱ (75ከመቶ) መስጠት ተችሏል፣
ግብ 3፡- የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኅብረት ሥራ ማህበራትን አመራር ስርዓት ማሻሻል፣
ተግባር 1፡- በሥራ አመራራቸው ውስጥ የአማካሪ ባለሙያዎችን እንዲያካትቱ ለ 2 በፌዴራል ደረጃ ለተደራጁ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኅብረት ሥራ
ተግባር 2፡- ጠቅላላ ጉባዔአቸውን በውክልና አሰራር እንዲመሩ ለ 2 የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኅብረት ሥራ ማህበራት ድጋፍና ክትትል ለማድረግ ታቅዶ
ግብ 4፡- በሪፎርም የትግበራ አሰራር የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኅብረት ሥራ ማህበራትን ማደራጀት
ተግባር 2፡ በሚቀርበው የመደራጀት ጥያቄ መሠረት በፌዴራል ደረጃ በዓመቱ 3 በሩብ ዓመቱ 1 አዳዲስ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኅብረት ሥራ
ማህበር ለማደራጀት የታቀደ ሲሆን
በተለያዩ ክልሎች የተደራጁ 13 ከፍታ የወጣቶች መሠረታዊ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኅብረት ሥራ ማህበር ተዋህደን በፌደራል
የእንደራጅ የሚል ጥያቄ ለሥራ አስፈጻሚው ቀርቧል፣
በዚህ መሠረት የባለሙያ ቡድን በማደራጀት ጥያቄውን በመፈተሽ የውሳኔ ሃሳብ እንዲያቀርቡ በተደረገው መሰረት ጥናት በማድረግ
የውሳኔ ሃሳብ ያቀረቡ ሲሆን የውሳኔ ሃሳብ ከተሰጠበት በኋላ ቀጣይ ሂደቱ የሚቀጥል ይሆናል፡
ግብ 5፡ የኅብረት ሥራ ማስፋፊያ አካላት እና የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኅብረት ሥራ ማህበራትን የማስፈፀም እና የመፈፀም
አቅም ማሳደግ
ተግባር 4፡- የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኅብረት ሥራ ማኅበራት እንዲጠቀሙበት የተዘጋጀውን ሶፍት-ዌር ጥቅም ላይ እንዲውል ለ 50
የገ/ቁ/ብ/ኅ/ሥ/ማኅበራት ሁለት ዙር ሥልጠና መስጠት የተያዘ ሲሆን በታቀደው መሠረት ስልጠናው ተሰጥቷል፡፡
በመጀመሪያው ዙር ስልጠና፡-
የስልጠናው ተሳታፊዎች የኮሚሽኑ የፋይናንስ ኅብረት ሥራ ልማት መሪ ሥራ አስፈፃሚ 12 ባለሙያዎች፣ ከኢንፎርሜሽን
ኮሚኒኬሽን ሥራ አስፈጻሚ 2 ባለሙያዎች እንዲሁም የወልታኔ አምቦ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኅብረት ሥራ ዩኒዬን 1 ባለሙያ
ተሳትፈዋል፡፡
የስልጠናው ህደት፡-
ስልጠናው የተሰጠው የተሸሻለው ሶፍት ዌር ከሶፍትዌር አበልጻጊው ድርጅት እንድመጣ ተደርጓል፣
የተሸሻለው ሶፍትዌር አንድ በአንድ በመፈተሸ ያሉ እንድስተካከል የተሰጡ አስተያየቶች መስተካከላቸውን በተግባር የማረጋገጥ ሥራ
ተሰርቷል፣
ሁሉም ተሳታፉ የተሸሻለውን ሶፍትዌር በኮምፒዩተሩ ላይ እንዲቻን በማድረግ ስልጠናውን እንድያገኝ ተደርጓል፡
በሁለተኛው ዙር ስልጠና፡-
7
የስልጠናው ተሳታዎች ከ40 የገ/ቁ/ብ/ ኅ/ሥራ ማህበራት ሥራ አስኪያጆችና የሕሳብ ሰራተኞች እና 4 የክልል
የፋይናንስ ኅብረት ሥራ ልማት የተውጣጡ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኅብረት ሥራ ባለሙያዎች እና የIT ባለሙያዎች
ናቸው፡፡
ቶሎ ወደሥራ ልገቡ የሚችሉ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኅብረት ሥራ ማህበራት ከክልሎች ጋር በመሆን ተለይቷል፣
ስልጠናው የተሸሻለው ሶፍ ዌር ሲሞከርባቸው የነበሩ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኅብረት ሥራ ማህበራት ዩኒዬኖች
መካከል ወልታኔ አምቦ ዩኒዬን በ acural base accounting system እና ጃቢ ዩኒዬን cash base accounting system
ስልጠናው የተግባር ስልጠና እንድሆን ለማድረግ ሁሉም ተሳታፊዎች የራሳቸውን የሕሳብ ቋት ይዞ እንዲመጡ
በማድረግ እና ሁሉም ኮምፕዩተር ይዞ እንድመጡ በማድረግ በተግበር የተደረፈ ስልጠና እንድሰጥ ተደርጓል፡፡
የስልጠናው ውጤቶች፡-
ተሳታፊ ባለሙያዎች በተሸሸለው ሶፍት ዌር ላይ በቂ ግንዛቤ ተፈጥሯል፣
በፊት የተጨነው እና የተሸሻለው መካከል ያለውን ልዩነት መረዳት ተችሏል፣
የተሸሸለው ሶፍት ዌር የሚይዛቸው ቴክንካል ጉዳዮች ላይ መግባባት ለመድርስ ተችሏል፣
ተግባር 5፡- የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኅብረት ሥራ ማህበራት በሶፍትዌር አጠቃቀም ላይ ለ 50 የገ/ቁ/ብ/ኅ/ሥ/ማኅበራት ሙያዊ ድጋፍ
ማድረግ 40 ዎቹ ያሉበትን ደረጃ ለማወቅ ክትትል የተደረገ ማድረግ ተችሏል፡፡
ተግባር 6፡- ለፌዴራል አስፈፃሚ አካላት የፋይናንስ አገልግሎት አሰጣጥ ላይ አንድ ዙር የአሰልጣኞች ስልጠና ለመስጠት ታቅዶ በታቀደው
መሰረት ተከናዎኗል፣
የስልጠናዉ ዓላማ፡-
የፋይናንስ ኅብረት ሥራ ዘርፍ የሚፈልገውን ክህሎት በማጠናከር የባለሙያን የመፈጸምና የማስፈጸም አቅም
በማሳደግ የተገልጋይን ፍላጎት ማርካት፤
ከሌሎች መሪ ሥራ አስፈጻሚዎች ጋር ያለውን ቅንጅታዊ አሰራርን በመፍጠር እና የተሻለ ውጤትን ለማምጣት፤
የተከናወኑ ተግባራት፡-
ለስልጠናው የሚያስፈልገውን ቅድመ-ዝግጅት በማድረግ አዳማ ከተማ ላይ ከነሐሴ 01 እስከ 07 2015 ዓ.ም
ለተከታታይ ሰባት ቀን ተሰጥቷል፣
በሥልጠናው ላይ የተሳተፉ ባለሙያዎች ከኅብረት ሥራ ማስፋፊያ መሪ ስራ አስፈፃሚ ከአርብቶ አደርና ቆላማ
አካባቢ ኅብረት ሥራ ማኅበራት ማደራጀት፣ ማጠናከር እና ማዘመን ዴስክ፣ ከኅብረት ሥራ የህግ አገልግሎት እና
ኢንስፔክሽን መሪ ስራ አስፈፃሚ፣ ከኅብረት ሥራ ማኅበራት የብቃት ማረጋገጫ መሪ ስራ አስፈፃሚ፣ ከኅብረት ሥራ
ማኅበራት ኦዲት መሪ ስራ አስፈፃሚ እና ከፋይናንስ ኅብረት ሥራ ልማት መሪ ሥራ አስፈፃሚ ናቸው፣
8
የስልጠናው አሰጣጥ ሂደት፡-
በተሰጡ የስልጠና ሪዕሶች ላይ የተሸለ ተሞክሮ ያላቸው ባለሙያዎች እንድሰጡ ተደርጓል፡
ስልጠናው በተግባር እና በተሞክሮ የታገዘ እንዲሆን ለማድረግ በዘርፉ የተሸለ ክህሎት ያላቸው ባለሙያዎች ከፍርቄ
የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኅብረት ሥራ ማህበራት ዩኒዬን፣ ከነፃነት ፋና ከፍርቄ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኅብረት ሥራ
ማህበራት ዩኒዬን እና ከአዋጭ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኅብረት ሥራ ማህበር በመጋበዝ በተጨማሪነት ስልጠናውን
እንዲሰጡ ተደርጓል፣
ስልጠናው የተሰጠባቸው ሪዕሶች፡
የኅብረት ሥራ ማህበራት አደረጃጀት ጽንሰ-ሃሳብ እና መመሪያ፣
• አሰልጠኞች ከገንዘብ ቁጠባና ብድር ኅብረት ሥራ ማህበራት በጋበዛቸው ስልጠናው በተግባር የተደገፈ ማድረጉ፣
• የሰልጣች ስብጥር /አደራጅ፤ ኦዲት፤ እንስፔክሸን፤ ሰርትፍኬሼን/ መሆኑ እርስ በርስ ለመማማር ምቹ ሁኔታ የፈጠረ
መሆኑ፣
የስልጠናው ውጤቶች፡-
የተገኙ ልምዶች፡-
በፌዴራል ደረጃ ያሉ ባለሙያዎችን ለብቻው ማሰልጠን በጋራ እንዲወያዩ እድል የሚፈጥር በመሆኑ የጋራ አረዳድ
እንዲኖር እድል የሚፈጥር መሆኑ፣
9
አነስተኛ ቁጥር ያላቸው ሰልጣኞችን በአንድ ላይ ማሰልጠን ግንዛቤ ለመፍጠር የተሸለ መሆኑ፣
የስልጠና ሪዕሶችን በመለየት በዘርፉ የተሸለ ክህሎች ያላቸው ባለሙያዎች እንዲያሰለጥኑ ማድረግ የተሸለ ግንዛቤ
መፍጠር እንደምችል፣
በስልጠናዎች በተግባር ሥራ ውስጥ ያሉ የኅብረት ሥራ ማህበራት ባለሙያዎችን በአሰልጣኝነት መጠቀም የተሸለ
ክህሎት ማስጨበጥ እንደምቻል፣
ግብ 6፡- የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኅብረት ሥራ ማህበራት የመረጃ አቅርቦት ተደራሽነትን ማሳደግ
ተግባር 1፡- በዓመቱ የ 2016 አራት የሩብ ዓመት ሪፖርቶችና የ 2017 ዓመታዊ ዕቅድ በድምሩ 6 ሪፖርቶች በሩብ ዓመቱ 1
ዕቅድ እና 2 ሪፖርት ለማዘጋጀት በታቀደው መሠረት የዓመቱ የዘርፉ የሴክቴር፣ የፕሮግራም በጀት፣ የ PSNP-
LH, LLRP እና RUFIP ዕቅዶች እና የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ሪፖርት ተዘጋጅቶ ለሚመለከተው አካል ቀርቧል፣
ተግባር 2፡ መሠረታዊ መረጃዎችን በማሰባሰብ፣ በመተንተንና በማደራጀት በተሟላ ሁኔታ (100%) ለተጠቃሚዎች
ተግባር 3፡ የክልሎች አንድ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኅ/ሥ/ማ ሪፖርት ማቅረቢያ ፎርማቶችን በማሻሻል ለማዘጋጀት
ተግባር 1፡- በፌዴራል ደረጃ ለተደራጁ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኅብረት ሥራ ማህበራት በማጠናከር ያሰባሰቡትን ቁጠባ
እና ካፒታል በዓመት ብር 3 ቢሊዮን እና የሩብ ዓመቱ ብር 0.75 ቢሊዮን እስከዚህ ሩብ አመት 1.35 ቢሊዮን
ለማሰባሰብ ታቅዶ በሩብ ዓመቱ የተሰበሰበ የቁጠባ መጠን ብር 70,162,382 እስከዚህ ሩብ አመት
ተችሏል፣
ተግባር 2፡- በፌዴራል ደረጃ ለተደራጁ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኅብረት ሥራ ማህበራት በማጠናከር ከህፃናት በዓመቱ ብር
ተግባር 1፡- በፌዴራል ደረጃ ለተደራጁ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኅብረት ሥራ ማህበራት በማጠናከር በዓመቱ ብር 5 ቢሊየን
በሩብ ዓመቱ ብር 2.5 ቢሊየን ለማሰራጨት ታቅዶ ብር 2,094,031,798 ብር አፈጻጸሙ 83.6% ለ 2,835
10
2,094,031,798 ብር በማሸፈን ብር 57,469,708 ከዕቅድ በላይ አርቦን ማሰባሰብ የተቻለ ሲሆን ጉዳት የደረሰባቸው
ብር 101,810.57 ተክፍሏቸዋል፤
ግብ 10፡- በገንዘብ ቁጠባና ብድር ኅብረት ሥራ ማህበራት የሚሰጠውን የወለድ አልባ የፋይናንስ አገልግሎት ማስፋፋት፣
ተግባር 1፡ በፌዴራል የተደራጁ 2 የገንዘብ ቁጠባና ብድር የኅ/ሥ/ማህበራት የወለድ አልባ የፋይናንስ አገልግሎትን መስጠት እንዲጀምሩ
ድጋፍ እና ክትትል ለማድረግ ታቅዶ ለ 2 ቱ ተሰጥቷል፤
ተግባር 2፡ በዓቱ 40 በሩብ ዓመቱ 20 የወለድ አልባ የፋይናንስ አገልግሎት የሚሰጡ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኅ/ሥ/ማህበራትን ማጠናከር
እና ለክልሎች ድጋፋዊ ክትትል ለማድረግ ታቅዶ ለ 11 (55 ከመቶ) ተደርጓል፤
ተግባር 3፡- በወለድ አልባ የፋይናንስ አገልግሎት ላይ ለክልሎች ድጋፍና ክትትል ለማድረግ በታቀደው መሠረት አንድ ዙር
መስጠት ተችሏል፡፡
በወለድ አልባ የፋይናንስ አገልግሎት አሰታጥ ላይ ለሶማሌ ክልል ኅብረት ሥራ ኤጀንሲ ላይ ቴክኒካል ድጋፍ ተሰጥቷል፣
ድጋፉ የተደረገው ከሥራ ክፍላችን መሪ ሥራ አስፈጻሚ እና የወለድ አልባ ዴስክ ኃላፊ የተገኙ ሲሆን በተጨማሪም
የተሸለ ክህሎትና ተሞክሮ ያላቸው ከኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ሼህ ሙሀመድዘይን ዘህረዲን
እና የፍርቄ የገንዘብ ቁ/ብ/የኅ/ስ/ማህበራት ዩኒዬን የሸሪዓ አማካሪ የሆኑት ኡስታዝ አብዱልሀዲ ነስሩን በመጋበዝ
እንዲገኙ በማድረግ በአተገባቡ ላይ ሰፊ ውይይት በማድረግ መስተካከል የሚገባቸው ጉዳዮች እንዲስተካከሉ ማድረግ
እንዲቻል ድጋፍ ተደርጓል፣
ድጋፉ የተሰጠው ክልሉ አዘጋጅቶት በነበረው የወለድ አልባ የፋይናንስ አገልግሎት አተገባበር ውይይት ላይ ጠገኙተው
የነበሩ የሶማሌ ክልል የፋይናንስ ኅ/ስራ ልማት መሪ ስ/አስፈፃሚ፣ የሶማሌ ክልል የክልል እና የወረዳ LLRP
አስተባባሪዎች፣ የሶማሌ ክልል የሸሪዓ አማካሪዎች፣ የሶማሌ ክልል የወረዳ ኅብረት ሥራ ጽ/ቤት ኃላፊዎች፣ የሶማሌ
ክልል የክልል እና የወረዳ ኅብረት ሥራ ቡድን መሪዎች፣ የሶማሌ ክልል የክልል እና የወረዳ ኅብረት ሥራ ባለሙያዎች
ናቸው፣
በገንዘብ ቁጠባና ብድር የኅብረት ሥራ ማህበራት ስለሚሰጡ የወለድ አልባ የፋይናንስ አገልግሎቶች የነበረውን
የተሳሳተ ግንዛቤ በተለይም ስለቁጠባ አገልግሎቶች አሰራር ስርዓት እና ስለብድር አገልግሎትቶች አሰራር ስርዓት
ለማረም ጥረት ተደርጓል፡፡
የወለድ አልባ የብድር አገልግሎት አሰራር ስርዓት ከሸሪዓ ድንጋጌዎች አንጻር በኡለሞች እና በሸሪዓ አማካሪዎች
መካከል በተለይም የሙራባሃ ብድር አገልግሎት ላይ የነበረው አከራካሪ ነጥቦች ዙሪያ ሰፊ ውይይት በማካሄድ ግልፅነት
ለመፍጠር ተሞክሯል፤
በክልሉ ሸሪዓ-መር የሆነ ወለድ አልባ የፋይናንስ አገልግሎትን በመስጠት የአባላትን የፋይናንስ ፍላጎት ለማሟላት እና
ተደራሽነቱን ለማሳደግ ከማን ምን ይጠበቃል በሚል ከሚመለከታቸው ኃላፊዎች እና የሸሪዓ አማካሪዎች ጋር
የወደፊት አቅጣጫ አስቀምጠናል፡፡
11
ግብ 11፡- በገንዘብ ቁጠባና ብድር ኅብረት ሥራ ማህበራት የሴቶችን እና ወጣቶችን ተጠቃሚነት ማሳደግ
ተግባር 1፡ በፌዴራል ደረጃ የተደራጁ 4 የገ/ቁ/ብ/ኅ/ሥራ ማህበራት የሴቶችን ተሳትፎ በአባልነት 20,000፣ በአመራርነት 13 እና 2 ቢሊዮን ብር ብድር ለሴቶች
ተግባር 2፡ በፌዴራል ደረጃ ከየተደራጁ 4 የገ/ቁ/ብ/ኅ/ሥራ ማህበራትን በማጠናከር የወጣቶችን ተሳትፎ በአባልነት 8,000፣ ድጋፍ እና ክትትል ለማድረግ ታቅዶ ለ 3 ቱ
ተደርጓል፣
ግብ 12፡- የበጀት አጠቃቀም ውጤታማነትን ማሳደግ
ተግባር 1፡ ለፋይናንስ ኅብረት ሥራ ልማት መሪ ሥራ አስፈፃሚ የተመደበ መደበኛ በጀትን ውጤታማ በሆነ መንገድ ሙሉ በሙሉ 100% ለመጠቀም ታቅዶ ---------
ከመቶ መጠቅም ተችሏል፤
ተግባር 2፡- በፕሮግራሞችና ፕሮጀክት ለዘርፉ የተመደበ በጀትን ውጤታማ በሆነ መንገድ ሙሉ በሙሉ 100% ታቅዶ ---------ከመቶ መጠቅም ተችሏል፤
ግብ 13፡- የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኅብረት ሥራ ማህበራት የዲጂታል ኢኮኖሚ ትግበራን ማሳደግ
ተግባር 1፡- በፌደራል የተደራጁ 3 የገ/ቁ/ብ/ ኅ/ሥራ ማህበራት የዲጂታል ኢኮኖሚ ትግበራ ውስጥ ማስገባት ታቅዶ 1 (33.3 ከመቶ) ማስገባት
ተችሏል፤
ተግባር 2፡ በፌደራል የተደራጁ 3 የገ/ቁ/ብ/ ኅ/ሥራ ማህበራት የፋይናንስ መረጃ ቋት እና ዘመናዊ የሂሳብ አያያዝ ትግበራ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ድጋፍ
ለማድረግ ታቅዶ 1 (33.33 ከመቶ) ማስገባት ተችሏል፣
ተግባር 6፡- የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኅብረት ሥራ ማህበራት ላይ ተዘርግቶ የነበረውና የተሻሻለውን software ለ 50 ለገንዘብ
ቁጠባና ብድር ኅብረት ሥራ ማህበራት መጫን በዕቅድ የተያዘ ሲሆን የ software ተጠቃሚ የሆኑ 40
ተግባር 1፡ አንድ የገ/ቁ/ብድር ኅ/ሥራ ማህበራት የፋይናንስ አገልግሎት አሰጣጥ መመሪያ ማጠናቀቅ ታቅዶ ተጠናቆ ለሚመለከተው አካል ተልኳል፡፡
ተግባር 2፡-የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኅብረት ሥራ ማህበራት ህጋዊ ሰውነት እድሳት ማስፈጸሚያ አንድ ማኑዋል ለማዘጋጀት ታቅዶ ተከናውኗ፣
ተግባር 3፡ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኅብረት ሥራ ማህበራት አንድ የውህደት አሰራር ለማዘጋጀት ታቅዶ ተከናውኗል፤
ተግባር 2፡ ዓለም-አቀፍ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኅብረት ሥራ ማህበራት አመታዊ በዓል አንድ ዙር ማክበር ታቅዶ
ተከናውኗል፡፡
12
አጠቃላይ ጥሪ የተደረገላቸው ተሳታፊዎች 400 ሲሆን የተገኙ ተሳታፊዎች ብዛት 382 (ሴት 104) 95.5% ናቸው፡፡
ክብረ በአሉ የተካሄደበት ቦታና ቀን፡- ኢንተርኮንትኔታል ሆቴል ህዳር 27 ቀን 2016 ዓ.ም ነበር፡፡
የክብረ በዓሉ ዋና ዓላማ፡-
የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኅብረት ሥራ ማህበራት በአገሪቷ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ልማት ስኬቶችና ያሉባቸው ተግዳሮቶች
በባለድርሻ አካላት እንዲታወቁና የዘርፉን ውጤታማነት ለማሳደግ ምቹ ሁኔታዎችን ለመፍጠር ነው፡፡
በገንዘብ ቁጠባና ብድር ኅብረት ሥራ ማህበራት አንቅስቃሴ የተገኙ ስኬቶችን በየደረጃው በሚገኙ አካላት እንዲታወቁ ማድረግ፣
በገንዘብ ቁጠባና ብድር ኅብረት ሥራ ማኅበራት የሥራ እንቅስቃሴ ላይ ያሉ ማነቆዎች በሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት
እንዲታወቁ ማድረግ፣
በገንዘብ ቁጠባና ብድር ኅብረት ሥራ ማኅበራት የሥራ እንቅስቃሴ ላይ ያሉ ማነቆዎች እንዲፈቱ ምቹ መደላድል በመፍጠር የአባላት
ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥና የሚኖራቸውን አገራዊ አስታዋፅኦ ለማሻሻል፣
ተሳታፊ አካላት በገንዘብ ቁጠባና ብድር ኅብረት ሥራ ማህበራት የተገኙ ምርጥ ተሞክሮዎችን እንዲለዋወጡና እንዲሰፋፉ ለማድረግ፤
ባለድርሻ አካላት በሚመለከታቸው ተግባር ላይ የነቃ ተሳትፎ እንዲያደርጉ የጋራ መግባባት ላይ ለመድረስና ተቀናጅቶ በመስራት
ለዘርፉ ውጤታማነት ምቹ ሁኔታዎችን ለመፍጠር፤
ክብረ በዓሉ አስፈላጊነት፡-
የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኅብረት ሥራ ማህበራት የአገራችንን የኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ፖሊሲዎችን፣ ስትራቴጂዎችን፣ የድህነት ቅነሳ
ፕሮግራሞችንና ዕቅዶችን በማስፈፀም ረገድ ሃገራዊ ዕድገቱን በመደገፍና ፍትሃዊ ተጠቃሚነትን በማረጋገጥ በኩል አስተዋፅኦ የሚያደርጉ
ተቋማት ናቸው፡፡
በተለይም፡-
ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚውል የብድር ፍላጎት በማሟላትና የግብይት ሥራውን በማሳለጥ፣
በገጠር አነስተኛ የፋይናንስ አገልግሎቶችን በቀላሉ ተደራሽ በማድረግ፣
ከአርሶ አደር፣ አርብቶ አደርና ከተማ የሚኖር ህብረተሰብ ቁጠባን በማሰባሰብ እና የብድርና የኢንሹራንስ አገልግሎት ችግሮችን
በቅርበት ሆነው በመፍታት እንዲሁም አገልግሎቶችን በማመቻቸት የህብረተሰቡን የኑሮ ደረጃ እንዲሻሻል በማድረግ፣
ኢኮኖሚውን በመደገፍና በማሳደግ አስተዋፅኦ ያላቸው ተቋማት በመሆናቸው፣
የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኅብረት ሥራ ማህበራት በገጠርና በከተማ የሚኖረውን ህብረተሰብ በኢኮኖሚ በማስተሳሰር የሚሰሩ
በመሆናቸው ፣
በአብዛኛው በዝቅተኛና መካከለኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኘውን የህብረተሰብ ክፍል በተለይ ወጣቶችንና ሴቶችን በብዛት በማሳተፍና
ተጠቃሚ በማድረግ የላቀ ድርሻ ያላቸው ተቋማት ናቸው፣
ሆኖም በገንዘብ ቁጠባና ብድር ኅብረት ሥራ ማኅበራት የሥራ እንቅስቃሴ ፈርጀ ብዙ ስኬቶች ቢመዘገቡም የሚጠበቅባቸውን ድርሻ
በሚፈለገው ደረጃ እንዳያወጡ ዘርፈ ብዙ ውስጣዊና ውጫዊ ማነቆዎች አሉባቸው፡፡ ስለሆነም ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር
በመቀናጀት የኅብረት ሥራ ማኅበራቱን መልካም ተምክሮዎች እንዲታወቁ በማድረግና በማስፋፋት እንዲሁም በሥራ ሂደት
13
ያጋጠሙ ችግሮችን በመፍታት የተቋማቱን ውጤታማነትና የአባላትን ተጠቃሚነት በማሳደግ የሚኖራቸውን አገራዊ ፋይዳ ለማጎልበት ምቹ
ሁኔታዎችን ከመፍጠር አንፃር ይህን አገራዊ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኅብረት ሥራ ማኅበራት ክብረ በዓል ማካሄድ አስፈላጊ ነው፡፡
በመጀመሪያ በተያዘው የድርጊት መርሃ ግብር መሠረት የበዓሉን አጠቃለይ ፕሮግራም የማስተዋወቅ ተግባር በታዋቅ የመድረክ
አስተዋዋቅ እንድመራ ተደርጓል፡፡ መድረኩ በማርች ባንድ በመታጀብ እና ከፍተኛ የመንግስት የሥራ አመራሮች የተከፈተ
ሲሆን በዓሉን አስመልክቶ የተዘጋጀው የመወያያ ጹሑፍ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበት በመጨረሻም የኢለቱ ክቡር እንግድች
ማጠቃለያ እና የሥራ መመሪያ ሰጥቶበታል፡፡
የቀረቡ ጥያቄዎች
ከፖሊሲ አንፃር
የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኅብረት ሥራ ማኅበራት እያደጉ ሲመጡ ምን አንደሚሆኑና መዳረሻቸውም ምን መሆን
እንዳለበት የሚያሳይ ፍኖተ ካርታ ቢኖር?
የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኅብረት ሥራ ማኅበራትን ከማጠናከር አንፃር በኅብረት ሥራ ማኅበራት መካከል በትብብር
ለመስራት እንዲቻል አደረጃጀቱ ምን መምሰል እንዳለበት ተፈትሾ ቢስተካከል?
14
የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኅብረት ሥራ ማኅበራት በሰለጠነ የሰው ኃይል እና በዕውቀት እንዲመሩ ለሁሉም የገንዘብ ቁጠባና
ብድር ኅብረት ሥራ ማህበራት አመራር አካላት በሥራ አመራር ስልጠና ቢሰጥ?
ከአደረጃጀት፡-
ቀደም ሲል በነበሩት ግዜያት በተለያዩ አካላት የኅብረት ሥራ ባንክን ለማቋቋም ጥረት ተደርጎ ስኬታማ አልነበረምና
ክቡር የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ምክትል ገዥ ዛሬ ከገቡት ቃል አንፃር በአሁኑ ስዓት ለማቋቋም የሚቻለው ከባለፈው
የተለየ ምን ነገር ቢኖር ነው?
ልክ አንደ አዋጭ የገንዘብ ቁጠባና ብድር (ኃ/የተ) ኅብረት ሥራ ማህበር በሥራ ላይ ያሉ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኅብረት
ሥራ ማህበራት አደረጃጀትና ማስፋፋት ሞዴሎችን በመቃኘትና በማሻሻል በሌሎች የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኅብረት
ሥራ ማህበራት ተግባራዊ ማድረግ ቢቻል?
ከፖሊሲ አንፃር፡-
በኅብረት ሥራ አዋጁ ላይ በተቀመጠው መሰረት መሬት በነጻ የሚያኙበት ተግባራዊነቱ ላይ የሚመለከታቸው አካላት
ትኩረት ሰጥተው መስራት ይገባቸዋል
የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኅብረት ሥራ ማኅበራት ለአባላት ፈጣንና ተደራሽ አገልግሎት ለመስጠት አሰራራቸውን
ማዘመንና በቴክኖሎጂ ማስደገፍ ይገባቸዋል፣
የኅብረት ሥራ ማኅበራት ሁለት መሠረታዊ ችገሮች ያሉባቸው ሲሆን እነሱም፡ የቦታ አቅርቦት እና የፋይናንስ አቅርቦት
ችገሮች ናቸው፣ እነዚህንም ችገሮች ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት ለመፍታት ጥረት ይደረጋል፣
የመሬት ይዞታን በብድር ማስያዣነት በመጠቀም ብድር ማግኘት እንደሚቻል በብሄራዊ ባንክ የወጣው መመሪያ
የገ/ቁ/ብ/ኅ/ሥ/ማህበራት የፋይናንስ ተቋማት ባለመሆናቸው ምክንያት የመመሪያው ተጠቃሚ አለመሆናቸው እንዴት
ይታያል?
15
የቀረቡ ልሞዶች እና ተሞክሮዎች ተስፋ ሰጪ ናቸው፡፡ በዚህ ውስጥ ግን ብዙ ማነቆዎች እንዳሉ ሊታወቅ ይገባል፡፡
ማነቆዎችን ለመፍታትም ሁላችንም የበኩላችንን ርብርብ ማድረግ ይገባል፣
ለአዋጭ ውጤታማ መሆንና ለከፍተኛ ዕድገት መድረስ ምክንት የሆኑ ጉዳዮች በጥናት ቢለዩ፣በዚህም መሠረት ከጥናቱ
ከሚገኝ ውጤት በመነሳት ወደ ተሻለ ውጤት እንበቃለን፣
ከአደረጃጀት አንፃር፡-
ከፖሊሲ አንፃር፡-
የኅብረት ሥራ ማኅበራት የኅብረት ሥራ ባንክ ለማቋቋም ከፈለጉ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አስፈላጊው እገዛ
እንደሚደረግ የብሔራዊ ባንክ ምክትል ገዥ ቃል ገብተዋልና ለስኬታማነቱ
የኅብረት ሥራ ማኅበራት አዋጅ 985/2009 ማስፈፀሚያ ደንብ እስካሁን ድረስ ያለመውጣቱ በአሰራር ላይ ከፍተኛ
ችግር እያስከተለ ስለሆነ በአጭር ግዜ ውስጥ ፀድቆ ተግባራዊ የሚሆንበት መንገድ ቢመቻች፤
በየኅብረት ሥራ ማኅበራቱ ጥቅም ላይ ያልዋለ መጠባበቂያ ገንዘብ አለና ጥቅም ላይ የሚውልበት ሁኔታ ቢፈጠር፣
የአዋጭ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኅብረት ሥራ ማኅበር የሥራ ተሞክሮ መሠረት በማድረግ የተገኙ መልካም ልምዶችን
በሁሉም ክልሎች በሚገኙ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኅብረት ሥራ ማኅበራት ለማስፋፋት በየደረጃው በሚገኙ
የሚመለከታቸው አካላት ጥረት ቢደረግ፣
የኅብረት ሥራ ማኅበራት ያላቸው ተሰሚነትና ጠቃሚነታቸው ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ነው፡፡ ስለሆነም ለዘርፉ የሥራ
እንቅስቃሴ መጠናከር የሁሉም ባለድርሻ አካላት ቅንጅታዊ ድጋፍ ያስፈልጋል፣
በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በኩል አብዛኛው ከውይይቱ የተነሳው ሃሳብ ለወደፊት ልናከናውነው የሚገባ የቤት ሥራ
የሚሰጠንና የኅብረት ሥራ ማኅበራትን ችግሮችን ለመፍታት ተቀራርቦ መስራትን ይጠይቃል፣
16
በኢትዩጵያ ኅብረት ሥራ ኮሚሽን በኩል የተጀመረው ከሌሎች የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት የሚደረግ ቅንጅታዊ
አሰራር ቢጠናከር፣
የኅብረት ሥራ ማኅበራት እንዲያድጉ በዕውቀት የተመሰረተ እንቅስቃሴ ማድረግ አለባቸው፡፡ ለስኬታማነቱም ሁሉም
በየደረጃው የሚገኙ የሚመለከታው አካለት በመቀናጀት የዘርፉን አቅም ለመገንባት አስተዋፅኦ ማድረግ ይኖርባቸዋል፣
የኅብረት ሥራ ማኅበራት ዋናው ማነቆ የውስጥ አቅማቸው አለመጠናከር ነው፡፡ ስለሆነም የውስጥ አቅማቸውን
ለማጠናከር ትኩረት ቢሰጠው፤
ከአደረጃጀት አንፃር፡-
የኅብረት ሥራ ማህበራትን ቁጥር ከማብዛት ይልቅ ከውጤታማነት አንፃር ጥራት ላይ ትኩረት ቢደረግ፣ ሲደራጁ
በአነስተኛ የአባላት ቁጥር ሊጀምር ይችላል፡፡ ሆኖም ግን የአባላት ቁጥር እንዲያድግ ትኩረት ቢሰጠው፣
የማጠቃለያ ሃሳብና ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች፡-
ከክብረ በዓሉ ተሳታፊዎች መብራራት የሚገባቸውና ግልፅ ያልሆኑ ጉዳች ተነስተው ሰፊ ማብራሪያ ተሰጥቷል፡፡ በተጨማሪም
የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኅብረት ሥራ ማኅበራት የሥራ እንቅስቃሴ ልማቱን ለማጠናቀር የሚያገለግሉ ገንቢ ሃሳቦችና
አስተያየቶች ቀርበው የጋራ መግባባት ላይ ተደርሷል፡፡ በሌላ መልኩ መድረኩ መማሪያ እና ሁሉንም ባለድርሻ አካላት ወደ
የአስተሳሰብ አንድነት ያመጣ ነበር ብሎ መውሰድ ይቻላል፡፡
በአጠቃላይ የአገራችን የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኅብረት ሥራ ማኅበራትን በገጠርና በከተማ በማስፋፋት የአርሶና አርብቶ
አደሩን የቁጠባ ባህልና ልምድ በማሳደግና የብድር አገልግሎት ተደራሽ በማድረግ ዘርፉ ህብረተሰቡን የሚያሳትፍ
ተከታታይ፣ዘላቂና ፈጣን ልማት ለማረጋገጥና በዜጎች መካከል ፍትሃዊ የሃብት ክፍፍል እንዲፈጠር ወሳኝ ሚና የሚጫወቱ
የልማት ተቋማት መሆናቸውን መገንዘብ ተችሏል፡፡
ስለሆነም የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኅብረት ሥራ ማኅበራት በአገር ልማት እየተጫወቱ ያለውን ሚና በመገንዘብ በዘርፉ
ተከታታይ፣ ዘላቂና ፈጣን ልማትን ለማረጋገጥና በዜጎች መካከል ፍትሃዊ የሃብት ክፍፍል እንዲፈጠር በየደረጃው የሚገኙ
የኅብረት ሥራ ማኅበራት ማስፋፊያ አካላት ያሉ መልካም ተሞክሮችን ከየአካባቢው ነባራዊ ሁኔታ በሚጣጣም መልኩ
በማስፋፋት ተግባራዊ በማድረግ የኅብረት ሥራ ማኅበራቱን ለውጤት ማብቃት ይኖርባቸዋል፡፡ በተጨሪም በየደረጃው
በሚገኘው ፈፃሚ፣ አስፋፃሚና ባለድርሻ አካላት የተጀመረውን የኅብረት ሥራ ማህበራት ሪፎርም ተግባራዊ ማድረግ፣
አገልግሎት አሰጣጥ ማዘመን፣ ጠንካራ የኅብረት ሥራ መፍጠር፣ አደረጃጀቱን ማጠናከር እና የፋይናንስ አገልግሎትን
ማስፋፋት፡፡
17
ባለንበት ወቅት ለገንዘብ ቁጠባና ብድር ኅብረት ሥራ ማኅበራት እንቅስቃሴ መጠናክር እክል የሆኑ ጉዳዮችና አሰራሮች
እየተሻሻሉ ስለሆነ ለመጪው ጊዜ መሻሻል የሚገባችውን ችግሮች ለይተን ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመቀናጀት
እንዲስተካከሉ እናደርጋለን፣
የኅብረት ሥራ ማኅበራትን የአባላትን የእውቀት፣ የግንዛቤ፣ አመራር፣ የክህሎት፣ አደረጃጀት፣አሰራር፣የቴክኖሎጂ
አጠቃቀም በየግዜው መፈተሸና ማሻሻል እንዲሁም ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት መስራት፣
የኅብረት ሥራ ማኅበራትን የፋይናንስ አቅርቦት ችግር ለመፍታት የአባላትን ቁጠባ ባህልን በማዳበር የውስጥ የፋይናንስ
አቅምን ለማሳደግ ቅድሚያ በመስጠት መስራት፤
የኅብረት ሥራ ማኅበራትን ቀጣይነት ለማረጋገጥ እና የዜጎችን ተሳታፊነት እና ተጠቃሚነት ለማሳደግ ለወጣቶች እና
ሴቶች ልዩ ትኩረት መስጠት፣
የኅብረት ሥራ ማኅበራት ዘመናዊ የቴክኖሎጂ ውጤቶችን እንዲጠቀሙ ሙያዊ ድጋፍ ማድረግ፣
በየደረጃው በሚገኙ ፈፃሚ፣ ሌሎች አስፋፃሚና ባለድርሻ አካላት ላይ የሚታዩ የትኩረት፣ የቁርጠኝነት፣
የክህሎት፣የግብአት አቅርቦትና አሰራር ማነቆዎችን በመፈተሸና በማስተካከል ሁሉም የሚመለከታቸው የልማት
ኃይሎች ለስኬታማነቱ በተደራጀና በተቀናጀ አግባብ ሰፊ ርብርብ ማድረግ ትኩረት ሊደረግባቸው የሚገቡ ዋና ዋና
ጉዳዮች ናቸው፡፡
ተግባር 4፡- ከሌሎች የሥራ ክፍሎች ጋር ለመስራት የሚያስችል አንድ የጋራ ዕቅድ ለማዘጋት ታቅዶ ተከናውኗል፣
የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኅብረት ሥራ ማህበራት በዲጂታል ኢኮኖሚ ትግበራ ዙሪያ ላይ ስልጠና መስጠት እና ከሌሎች
የፋይናንስ ተቋማት ጋር በድጅታል ማስተሳሰር የሚል ሲሆን ከፌዴራል እና ክልሎች የተውጣጡ የአደራጅ ተቋማት
18
ኃላፊዎችና ባለሙያዎች፣ ከኢትዮጵያ ብሐየራዊ ባንክ ጋር በመቀናጀት ከባንኮች፣ ገንዘብ ቁጠባና ብድር ኅብረት ሥራ
የኅብረት ሥራ ማህበራት ጽንሰ-ሃሳብ እና የፋይናንስ አቅርቦት ነባራዊ ሁኔታ በኢትዮጵያ ኅብረት ሥራ ኮሚሽን
ቀርቧል፣
የፋይናንስ አካታችነት፣ ዲጂታል ፋይናን አገልግሎት፣ የፋይናንሻል ክህሎት (Financial Literacy) እና የተጠቃሚዎች
የፋይናንስ ደህንነት ጥበቃ (Consumer Protection) ከሔራዊ ባንክ በመጡ 2 ከፍተኛ ባለሙያዎች ቀርቧል፣
ከኢትዮ ቴሌኮም ቴሌ ብር፣ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሲቢኢ-ብር፣ የኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ፣ (Gize pay) አቢሲኒያ
ባንክ እና ዳሽን ባንክ ያሉዋቸውን አገልግሎቶችና ለገ/ቁ/ብ/ ኅ/ሥራ ማህበራት ሊያስገኙ የሚችሏቸውን ጥቅሞች
በጥልቀት አቅርበዋል፣
19
የፋይናንስ ተቋማት ብድር በማግኘት ላይ ናቸው፡፡ CBO በኩል Innovation HaB የሚባል የተደራጀ ክፍል ሁሉንም
አገልግሎቶች የሚገመግም፣ የሚያሻሽልና አዳዲስ አገልግሎቶችን የመፍጠር ሥራ ያከናውናል፡፡
የተሰጡ አስተያየቶች፡-
በምርት ወቅት ገበሬው ገንዘብ ተሸክሞ ወደ ቤት በሚሄድበት ወቅት የመሰረቅና ለአደጋ የሚያጋልጥ በመሆኑ በቅርበት
ገንዘብን ለመሰብሰብ ስለሚያስችል በፍጥነት ወደ ስራ ቢገባ፡፡
ባንኮች ኅብረት ሥራን የሚያስተናግዱበት ዲፓርትመንት ወይንም አሰራር ቢኖራቸው፡፡
Agent Banking አገልግሎት ተከታታይነት ያለው ተጠያቂነት፣ ኃላፊነት የሚፈልግ ስራ እንደሆነና በጥንቃቄ ሊያዝ
የሚገባው ነው፡፡
በተበጣጠሰ መልኩ የምንሰማቸው የፋይናንስ ተቋማት የአገልግሎት ዓይነቶች ሰብሰብ ባለ በልኩ መቅረባቸው በቂ
በተጠናከረ መልኩ ወደ ስራ ለመግባት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ እና የኢትዮጵያ ኅብረት ሥራ ኮሚሽን አሰራር
በመጨረሻም የድርጊት መርሃ ግብር የተቀረጸ ሲሆን ተግባራት በዝርዝር ቀርበው መችና ማን እንደሚያከናውናቸው
በግልጽ ተቀምጠዋል፡፡
በማጠቃለያም ኅብረት ሥራዎች ለጠቅላላ ጉባኤ፣ ለቦርድ እና ለመሠረታዊ ኅብረት ሥራ ማኅበራት የማሳወቅ ስራ
እንዲያጠናቅቁ፣ ለባንኮች Product segmentation ከኅብረት ሥራ አንፃር ለይተው እንዲያጠናቅቁ፣ ከክልል ኅብረት
የኅብረት ሥራ በግባት ካለባቸው መለየት፣ በብሔራዊ ባንክ በኩል ተጨማሪ ባንኮች መካተት ከፈለጉ እንዲካተቱ
ፕሮጀክቱ ክልሎች የሆኑት አፋር፣ ሶማሌ እና ጋምቤላ ክልሎች ውስጥ የሚገኙ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኅብረት ሥራ
ማህበራትን የማጠናከር ተግባር ተከናውኗል፣
በፕሮጀክቱ በተያዘው በጀት በሬጉላቶሪ እና በኦዲት የሥራ ክፍሎች ለኢንስፔክሽ እና ለኦዲት ባለሙያዎች የአሰልጣኞች
ስልጠና ተሰጥቷል፣
በአዋጭ ኃላፊነቱ የተወሰነ መሰረታዊ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኅብረት ሥራ ማህበር የወለድ አልባ የፋይናንስ
አገልግሎትን ለማስጀመር መነሻ-ሀሳብ (PROPOSAL) ተዘጋጅቶ ተልኳል፡፡
20
በ GIZ ፕሮጀክት ከታቀፉ ክልሎች መካከል በኦሮሚያ ክልል ውስጥ ለሚገኙ ለ 3 ሴት እና 4 ወንድ በድምሩ ለ 7
የዘር ብዜት ህብረት ሥራ ማህበር ለዩኒየን ሥራ አስኪያጆችና ለባለሙያዎች የፋይናንስ ክህሎት ማሳደጊያ እና
የአነስተኛ መድን ዋስትና ስልጠና ላይ ለ 3 ተከታታይ ቀናት የፋይናንስ ክህሎት ማሳደጊያ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡
የአዲስ አበባ ኅብረት ሥራ ኤጀንሲ በአዘጋጂነት ስልጠና ላይ 2 ባለሙያዎችን በማሳተፍ ከ 11 ከፍለ ከተሞች
ለተውጣጡ ለ 31 ወንድ እና ለ 11 ሴት በድምሩ ለ 42 የገንዘብ ቁጠባና ብድር ባለሙያዎች በቁጠባና ብድር፤
በስጋት አስተዳደር እና በአነስተኛ መድን ዋስተና ለ 5 ቀናት ስልጠና ተሰጥቷል፡፡
የ 2016 በጀት ዓመት ዕቅድ ሲዘጋጅ ከሚመለከታቸው ክፍሎች ጋር በመናበብ የጋራ ለማድረግ ጥርት መደረጉ፣
አገልግሎቱን ለማግኘት የሚመጡ ተቋማትና ግለሰቦች በሚጠይቁት ጥያቄ መሰረት ግንዛቤ መስጠት መቻሉ፣
የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኅብረት ሥራ ማህበራትን የማጠናከር ተግባር በጥራትና በወቅቱ ማከናወን መቻሉ፣
የ 2016 በጀት ዓመት ዕቅድ ዝግጀት ረጅም ጊዜ መውሰዱ በመጀመሪያ ሩብ ዓመት የታቀዱ ሥራዎችን ማዘግየቱ፣
በፕሮግራምና ፕሮጀክት የታቀዱ ተግባራት በሚመለከታቸው አካላት ፀድቆ አለመምጣትና ከተጠየቀው በጀት በታች
መፈቀዱ፣
መረጃዎችንና ወቅታዊ ሪፖርቶችን ከሁሉም ክልሎች ማግኘት እንዲቻል የተለያዩ ፎርማቶችን በማዘጋጀት
የአደረጃጀት መመሪያዎች፣ አዋጅና ማስፈፀሚያ ደንቦች ወቅታዊ ማሻሻያ የሚደረግባቸውን ነጥቦች በመለየትና
በሪፎርም የተያዙ ተግባራት መረጃ ማጥራት፣ በደረጃ መለየት እና የውህደት ተግባራትን በትኩረት መስራት፣
21
የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኅብረት ሥራ ማህበራትን ማጠናከር፣
የተጀመረውን የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኅብረት ሥራ ማህበራት የመረጃ ቴክኖሎጅ ዝርጋታን ተግባራዊ ማድረግ፣
22
የ 2016 የመጀመሪያ ሪብ ዓመት በጀት ዓመት የፕሮግራም በጀት ዓመታዊ ዕቅድ ክንውን ሪፖርት ከሐምሌ 01/2015 እስከ መስከረም 30/2016 ዓ.ም.
የሩብ ዓመት ዕቅድ ክንውን አፈፃፀም ንፅፅር በ%
ዝርዝር ተግባራት መለኪያ የዓመቱ
ዕቅድ በዚህ ሩብ እስከዚህ በዚህ ሩብ እስከዚህ ሩብ የዚህሩብ እስከዚህ ሩብ ምርመራ
ዓመት ሩብ ዓመት ዓመት ዓመት ዓመት ዓመት
ፕሮግራም በጀት
ግብ 1፡- የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኅብረት ሥራ ማህበራት አደረጃጀትን ማሻሻል
ማዘመን
በፌደራል ለተደራጁ 4 የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኅ/ሥ/ማህበራትን ማጠናከር እና ድጋፋዊ በቁጠር 4 4 4 3 3 75 75
ክትትል ማድረግ፤
በክልል ለተደራጁ 116 የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኅ/ሥ/ማህበራትን ማጠናከር እና ለአደራጅ በቁጠር 116 36 36 40 40 111 111
ተቋሙ ሙያዊ ድጋፍ መስጠት፤
በፌዴራል ደረጃ የተቋቋሙ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኅ/ሥ/ ማህበራትን በማጠናከር
የፈሩ አባላት
የፈሩ አባላት በጥቅል ቁጥር 40,000 8,000 18,00 16,815 16,815 93 93
ወንድ ቁጥር 20,000 4,000 09,000 11,220 11,220
ሴት ቁጥር 20,000 4,000 9,000 5,595 5,595
ግብ 2፡ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኅብረት ሥራ ማህበራትን አገልግሎት አሰጣጥ
በሚሰጡትን አገልግሎት ላይ ለአባላት ግንዛቤ እንዲፈጥሩ ለ 4 የገንዘብ ቁጠባና
ማሻሻል፣ ቁጥር 4 4 4 3 3
ብድር የኅብረት ስራ ማህበራት ክትትልና ድጋፍ ማድረግ፣
75 75
ግብ 3፡- የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኅብረት ሥራ ማህበራትን አመራር ስርዓት ማሻሻል፣
በሥራ አመራራቸው ውስጥ የአማካሪ ባለሙያዎችን እንዲያካትቱ የገንዘብ ቁጠባና ቁጥር 2 2 2 2 2 100 100
ብድር ኅብረት ሥራ ማህበራት ድጋፍና ክትትል ማድረግ
ጠቅላላ ጉባዔአቸውን በውክልና አሰራር እንዲመሩ ለ 2 የገንዘብ ቁጠባና ብድር ቁጥር 2 2 2 2 2 100 100
ኅብረት ሥራ ማህበራት ድጋፍና ክትትል ማድረግ፣
በሚቀርበው የመደራጀት ጥያቄ መሠረት በፌዴራል ደረጃ አዳዲስ የገንዘብ ቁጠባና ብድር በጅምር
ቁጥር 3 1 1 50% 50% 50
ኅብረት ሥራ ማህበር ማደራጀት
1
ግብ 5፡ የኅብረት ሥራ ማስፋፊያ አካላት እና የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኅብረት ሥራ
ማህበራትን የማስፈፀም እና የመፈፀም አቅም ማሳደግ
ለክልሎች፣ ለገ/ቁ/ብ/ማ ዩኒዬኖች እና ለፌዴሬሽኖች ባለሙያዎች በአነስተኛ-ኢንሹራንስ ላይ በዙር 1 1 1 አልተከናወ
አንድ ዙር ስልጠና መስጠት፣ ነም
ለክልሎች፣ ለገ/ቁ/ብ/ኅ/ሥ/ማ ዩኒዬኖች እና ለፌዴሬሽኖች ባለሙያዎች የፋይናንስ ግብይት በዙር 1 1 1 አልተከናወ
(Financial Marketing) አንድ ዙር ስልጠና መስጠት ነም
የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኅብረት ሥራ ማኅበራት እንዲጠቀሙበት የተዘጋጀውን ሶፍት-ዌር
ጥቅም ላይ እንዲውል ለ 50 የገ/ቁ/ብ/ኅ/ሥ/ማኅበራት ሁለት ዙር ሥልጠና መስጠት፣ በዙር 2 1 1 2 2 100 100
መሠረታዊ መረጃዎችን በማሰባሰብ፣ በመተንተንና በማደራጀት በተሟላ ሁኔታ (100%) 100 100 100 100
በመቶኛ 100 100 100
ለተጠቃሚዎች ተደራሽ ማድረግ
የክልሎች አንድ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኅ/ሥ/ማ ሪፖርት ማቅረቢያ ፎርማቶችን ማሻሻል ሰነድ 1 1 1 1 1 100 100
በፌዴራል ደረጃ ለተደራጁ የገ/ቁ/ብ/ኅ/ሥ/ማህበራት በማጠናከር ያሰራጩትን የብድር መረጃ በቢሊየን 5 2,094,031,79 2,094,031,7
2.5 2.5 83.6 83.6
ማደራጀት፤ ብር 8 98
በፌደራል ደረጃ የተቋቋሙ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኅብረት ሥራ ማህበራት ለአባለት በመቶኛ 99.5 99.5 99.5 99 99
ከተሰራጨ ብድር ውስጥ የመመለሻ ጊዜው የደረሰ የብድር አመላለስ መረጃ ማሰባሰብና
ማደራጀት፤
2
ግብ 9፡- የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኅብረት ሥራ ማህበራት የአደጋ ስጋትን መቀነስ
በፌደራል ደረጃ ተቋቋሙ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኅብረት ሥራ ማህበራት በብር 50 25 25 57,469,708 57,469,708
>100 >100
የአነስተኛ ብድር መድህን ዋስትና አገልግሎት በመስጠት አረቦን ማሰባሰብ
የወለድ አልባ የፋይናንስ አገልግሎት የሚሰጡ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኅ/ሥ/ማህበራትን በቁጥር 40 20 20 11 11
55 55
ማጠናከር እና ለክልሎች ድጋፋዊ ክትትል ማድረግ፤
ለወለድ አልባ የብድር አገልግሎት የሚውል ተዘዋዋሪ ፈንድ የሚያቀርቡ እና ለዘርፉ ሌሎች
ድጋፎችን የሚያደርጉ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን፣ ፕሮጀክቶችንና
ሰነድ 1 1 1 0 0
ፕሮግራሞችን መለየት አንድ ሰነድ ማዘጋጀት፤ 0 0
በፕሮግራሞችና ፕሮጀክት ለዘርፉ የተመደበ በጀትን ውጤታማ በሆነ መንገድ ሙሉ በሙሉ 100 100 100 100
100% መጠቀም፤ በመቶኛ
3
ግብ 13፡- የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኅብረት ሥራ ማህበራት የዲጂታል ኢኮኖሚ
ትግበራን ማሳደግ
በአገር አቀፍ ደረጃ ለሚቋቋም የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኅብረት ሥራ ማህበራት 1 1 1 0 0 አልተከናወ
በቁጥር 0 0
ፌዴሬሽን ቅድመ-ሁኔታ ጥናት ማካሄድ፣ ነም
የዓይነት ቁጠባ በሚያካሂዱ ኅብረት ሥራ ማህበራት ላይ የዳሰሳ ጥናት በማድረግ አንድ ሰነድ 1 1 1 0 0 አልተከናወ
ማዘጋጀት በሰነድ 0 0
ነም
አንድ የፋይናንስ አገልግሎት ውጤታማነት መገምገሚያ እና መመዝገቢያ ማኑዋል 1 1 1 አልተከናወ
ማዘጋጀት ሰነድ ነም
የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኅብረት ሥራ ማህበራት ህጋዊ ሰውነት እድሳት ማስፈጸሚያ 1 1 1 1 1
አንድ ማኑዋል ማዘጋጀት ሰነድ 100 100
4
አለማቀፍ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኅ/ሥ/ማ አመታዊ በዓል አንድ ዙር ማክበር በዙር 1 1 1 1 1
100 100
ከክልል የዘርፉ አስፈፃሚ አካላት ጋር ሥራዎችን በጋራና በትብብር ለመስራት እንዲቻል በበጀት በዙር 2 1 1 0 0
ዓመቱ 2 የጋራ ምክክር መድረክ ማካሄድ፤
ከሌሎች የሥራ ክፍሎች ጋር ለመስራት የሚያስችል የጋራ ዕቅድ ማዘጋት በቁጥር 1 1 1 100 100