You are on page 1of 13

ርእስ

ቁጥር 01/2016
የካቲት 2016 ዓ.ም

የዱቤ አገልግሎት አሰጣጥ መመሪያ 0


ምእራፍ አንድ............................................................................................................................................................2
1.1 መግቢያ...........................................................................................................................................................2
1.2. አጭር ርዕስ.....................................................................................................................................................3
1.3. ትርጓሜ.........................................................................................................................................................3
1.4 የፆታ አገላለጽ..................................................................................................................................................5
1.5. የመመሪያው አስፈላጊነት.................................................................................................................................5
1.6. የመመሪያ ቁጥር - 01/2016 ተብሎ ይጠራል፡፡.....................................................................................................6
1.7. የመመሪያው ዓላማ..........................................................................................................................................6
ምእራፍ ሁለት...........................................................................................................................................................7
ምእራፍ ሶስት............................................................................................................................................................7
3.1 የዱቤ አገልግሎት መመሪያው ጠቀሜታ...............................................................................................................7
3.2 የዱቤ አገልግሎት የሚሰጣቸው አካላት................................................................................................................7
3.3 የዱቤ አገልግሎት የሚሰጥበት መስፈርት..............................................................................................................8
3.3.1 በቀጥታ እና በውስጥ ሽያጭ ባለሙዎች ለሚመጡ ደንበኞች፣.........................................................................8
3.3.2 በማስታወቂያ ወኪል ለሚመጡ የስራ ትእዛዞች፣...............................................................................................9
3.3.3 በተባባሪ አዘጋጆች ለሚመጡ ውሎች፣.........................................................................................................9
3.4 የዱቤ አገልግሎትን ስለመከልከል.......................................................................................................................10
3.5 የዱቤ አገልግሎት ክፍያ ሥርዓት.......................................................................................................................10
3.6 የዱቤ አገልግሎት የመፍቀድ ኃላፊነቶች..........................................................................................................11
3.6.1 የኃላፊዎች ሥልጣን፤................................................................................................................................12
3.7 የተቋም የዱቤ አገልግሎት አስተዳደር.............................................................................................................13
3.8 የተጠያቂነት አግባብ........................................................................................................................................13
ምእራፍ አራት.........................................................................................................................................................14
ልዩ ልዩ ድንጋጌዎች...................................................................................................................................................14
4. የተፈፃሚነት ወሰን...........................................................................................................................................14
4.1 መመሪያው ስለሚሻሻልበት ሁኔታ...............................................................................................................14
4.2 መመሪያው ሥራ ላይ የሚውልበት ጊዜ........................................................................................................15

የዱቤ አገልግሎት አሰጣጥ መመሪያ 1


ምእራፍ አንድ
1.1 መግቢያ
ፋና ብሮካስቲንግ ኮርፕሬት አ.ማ በሚዲያ ኢንዱስትሪው ከ 29 ዓመት በላይ ዕድሜን አስቆጥሯል፡፡ በሀገሪቱ
የመጀመሪያው የንግድ የግል ሚዲያ በመሆንም ፈር ቀዷል፡፡ ሚዲያው ከመንግሥት ባጀት ውጪ በራሱ ገቢ ሊተዳደር
እንደሚችል በተግባርም አሳይቷል፡፡

የሚዲያ ቢዝነሱን ብቻ ሳይሆን ተደራሽነቱንም በማስፋት በአሁኑ ጊዜ በአዲስ አበባና በክልል 13 የኤፍ ኤም
ጣቢያዎች ብሄራዊ ስርጭትን ጨምሮ እና በቴሌቪዥን ደግሞ የሁለት ቻናል እንዲሁም በድጅታል ሚዲያው እና
በሌሎች የስልጠናና ማማከር አገልገሎቶች በመስጠት በሚዲያው ዘርፍ የራሱን አሻራ በማሳረፍ ሀገራዊ ተልኮውን
በመወጣት ላይ ይገኛል፡፡

ኮርፕሬቱ የእስከዛሬው የሚዲያ ቢዝነስ ሂደት ትርፋማና ስኬታማ ቢሆንም ከተቋሙ ዕድገት ጋር ተያይዞ እንደ ንግድ
ሚዲያ ማሻሻያ ሊያደርግባቸው የሚገቡ ጉዳዮች አሉ፡፡ ከእነዚህም አንዱ የተቋማችን የዱቤ አገልግሎት ነው፡፡
በየትኛውም የንግድ ሥራ ዘርፍ ተቋሙ ስኬታማ የሚሆነው እጅ በእጅ ሺያጭ ብቻ ሳይሆን ታማኝ ለሆኑ ደምበኞች
የዱቤ አገልግሎት በመስጠትና ይህንን ተግባር ሊመራ፣ ሊቆጣጠር የሚችልበት የተደራጀ አሠራር ሲኖር ብቻ ነው፡፡

ባለፉት ዓመታት ኮርፕሬታችን ለተለያዩ ደምበኞች የዱቤ አገልግሎት የሚሰጥበት አሠራር በሺያጭ ማንዋሉ ውስጥ
በተለያዩ አንቀፆች ውስጥ የተጠቀሰ ቢሆንም ወጥነት ስሌለውና የቴሌቭዥን ሺያጭንና ሌሎች የገቢ አማራጮችን
ያገናዘበ ባለመሆኑ በተቋሙ የፋይናንስ አሠራር ላይ ተፅዕኖ አሳድሯል፡፡ ዱቤ የሚሰጥበት አካሄድ የጠራና የተሟላ
ሕጋዊ ማዕቀፍን ባለመከተሉ፤ በተለይ በአንዳንድ አካባቢዎችና ጣቢያዎች የተሰጠ የሺያጭ ዕቅድን ለማሟላት
ብለው የሚሰጡ ዱቤዎች ለአሰባሰብ ብዙ ችግር ፈጥረው ቆይተዋል፡፡

ከእዚህ በተጨማሪ የዱቤ አሰጣጥ መመዘኛ ባለመኖሩ በዱቤ ላይ ዱቤ በመስጠት የተቋሙ ጤናማ ያልሆነ ዱቤዎች
እንዲከማች አድርጓል፡፡ ከዱቤ አገልግሎትና አሠራር አንፃር ተጠያቂ የሚያደርግና ኃላፊነት ኖሮት ሂደቱን የሚከታተል
የተደራጀ አካል አለመኖር የተቋሙ የቢዝነስ ሥራዎች፣ ደምበኞችና የዱቤ አገልግሎት ጠያቂዎች መበራከት ይህን
የዱቤ አገልግሎት ማንዋል እንዲዘጋጅ ግድ ብሏል፡፡

በሚዲያዎች መሀል እየተፋፋመ ከመጣው የገበያ ውድድር አንጻር ነባር ደንበኞችን ከማቆየትና አዳዲስ ደንበኞችንም
በመሳብ የገበያውን ፉክክር ሰብረን ለመውጣት ከሚያስችሉን አሰራሮች መሀል አንዱ ሆኖ በመገኘቱ በዱቤ ላይ ዱቤ
ማኑዋሉ ወይም የአሰራር ስርአቱ በሀገሪቱ ያለውን ምርጥ የሰው ሃይልና የቴክኖሎጂ አቅም ለመጠቀም የሚያስችል
የአሰራር ቁመና ለተቋሙ የመስጠት መሠረታዊ ዓላማ ያለው ነው፡፡

በሌላ በኩል በአሁኑ ጊዜ የሚታየው የሚዲያ ኢንዱስትሪው ጠንካራ የገበያ ውድድር የዱቤ አገልግሎት መሰጠት
አዳዲስ ደምበኞችን ለመሳቢያ እንደ አንድ ስልት እየተጠቀመበት ነው፡፡ ተቋማችን በእዚህ ፉክክር አሸንፎ ለመውጣት
ሳቢና ደምበኛን ማቆየት የሚችል፣ ተጠያቂነትን የሚያረጋግጥና የዱቤ ማንዋል ማዘጋጀት ሊታለፍ የማይገባ ተግባር

የዱቤ አገልግሎት አሰጣጥ መመሪያ 2


ነው፡፡ ከእዚህ በተጨማሪ ከአገልግሎቱ ጋር ተያያዥነት ያላቸው የሥራ ዳይሬክቶሬቶችና አስተባባሪዎች የዱቤዎች
አሰጣጥ ሥርዓት ወጥ በሆነ መንገድ የመምራት አስፈላጊነት ለእዚህ ማንዋል አደረጃጀት እንደ አንድ ምክንያት ተደርጎ
ሊወሰድ ይችላል፡፡

1.2. አጭር ርዕስ


ይህ መመሪያ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ዓ.ማ የዱቤ ሺያጭ አገልግሎት አሰጣጥ መመሪያ (ማንዋል) ተብሎ
ሊጠራ ይችላል፡፡
1.3. ትርጓሜ
የቃሉ አግባብ ሌላ ትርጉም የሚያሰጠው ካልሆነ በስተቀር በእዚህ መመሪያ ውስጥ
ሀ. አክሲዮን ማህበር ማለት ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፕሬት ማለት ነው፤
ለ. “ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት አ.ማ” ማለት ሕጋዊ ዕውቅና የተሰጠው የግል የንግድ ሚዲያ ተቋም ነው፤
ሐ. “ዋና ሥራ አስፈፃሚ” ማለት የፋና ብሮካስቲንግ ኮርፕሬት አ.ማ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ማለት ነው፤
መ. የቢዝነስና አስተዳደር ዘርፍ ማለት የተቋሙን የቢዝነስና አስተዳደር የማስተዳደር ኃላፊነት የተሰጠውና
የተቋሙ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ዓ.ማ አንድ የሥራ ዘርፍ ነው፤
ሠ. የፋይናንስና ግዥ ዳይሬክቶሬት ማለት የተቋሙን የፋይናንስና የግዥ ሂደት የማስተዳደር ኃላፊነት
የተሰጠው የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፕሬት የሥራ ክፍል ነው፤
ረ. “የክልል ጣቢያዎች” ማለት በአክሲዮን ማህበሩ አማካኝነት በየክልሎች የተቋቋሙ የሚዲያ አገልግሎት
የሚሰጡ ጣቢያዎች ናቸው፤
ሰ. ቡድን መሪ ማለት በሁሉም ዳይሬክቶሬቶች ከዳይሬክተር ቀጥሎ የሚገኝን ቡድን የሚያስተባብር የስራ
ኃላፊ ማለት ነው፡፡
ሸ. “የክልል ጣቢያዎች አስተባባሪ ዳይሬክቶሬት” ማለት በተቋሙ ውስጥ ያለ የክልል ኤፍ ኤም እና
የቴሌቪዥን ጣቢያዎችን የሚያስተባብር ዳይሬክቶሬት ነው፤
ቀ. “የዱቤ አገልግሎት” ማለት ደምበኛው ከተቋም ከክፍያ በፊት አገልግሎት የሚያገኝበት ሁኔታና ክፍያው
በሁለቱ አካላት ስምምነት በተደረሰበት አግባብ የሚከፈል ነው፤
በ. “የማስታወቂያ ወኪል” ማለት ከመንግሥት የንግድ ፍቃድ ያለውና በሕጋዊ መንገድ ተመዝግቦ ዕውቅና ያገኘ
በኮሚሽን የሚሠራ ተቋም ነው፤
ተ. “ደምበኛ” ማለት ከድርጅቱ ጋር ቢያንስ ለተከታታይ ዓመታት በደምበኝነት የቆየ ተቋም ወይም ግለሰብ
ማለት ነው፤
ቸ. “አቅም ያለው ደምበኛ” ማለት በማንኛውም መልኩ ከድርጅቱ ጋር ለመሥራት የሚያስችል ኢኮኖሚያዊ
አቅም ያለው ግለሰብ ወይም ተቋም ማለት ነው፡፡
ነ. “ተባባሪ አዘጋጅ” ማለት ከድርጅቱ ጋር በሬድዮና በቴሌቭዥን ተባባሪ ሆኖ ለመሥራት የሚያስችለውን

ፈቃድ አግኝተውና ሕጋዊ የሥራ ውል ፈጽመው የአየር ሰዓት ወስደው የሚሠሩ አካላት ናቸው፡፡
የዱቤ አገልግሎት አሰጣጥ መመሪያ 3
ኘ. “የገቢ ዕቅድ ፈፃሚዎች” (የሺያጭና ማርኬቲንግ፣ የደምበኞችና ሌሎች ገቢ አመንጪ ክፍሎች የክልል ጣቢያዎች
አስተባባሪ) የዱቤ አገልግሎትን ከተቋሙ አሠራር አንፃር በማገናዘብ አስፈላጊውን መረጃ ከፋይናንስና ግዢ
ዳይሬክቶሬት እየወሰዱ ጤናማ የዱቤ አገልግሎት የሚሰጡ ናቸው፡፡
አ. “የዱቤ አገልግሎት አስፈፃሚዎች” ማለት የተቋሙን የዱቤ አገልግሎትን የክፍያ ሥርዓትን የሚከታተሉና
ተጠሪነታቸውም ለቢዝነስ አስተዳደር ዘርፍ እና ለዋና ሥራ አስፈፃሚ የሆኑ አካላት ናቸው፡፡
ከ. “ታማኝ ደምበኛ” ማለት ከተቋሙ ጋር ለረዥም ጊዜ የሠራና የተሰጠውን የዱቤ አገልግሎት በተቀመጠው
የክፍያ የጊዜ ገደብ ከፍሎ ግዴታውን የሚወጣ ግለሰብ ወይም ተቋም ነው፡፡

ወ. “አጭር ጊዜ የዱቤ አገልግሎት” ማለት የዱቤ አገልግሎቱ እስከ ከ 45-60 ቀን የጊዜ ርዝመት ያለውና
በደምበኛው በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ ተከፍሎ የሚጠናቀቅ የዱቤ አገልግሎት ነው፤
ዐ. “መካከለኛ ጊዜ የዱቤ አገልግሎት” ማለት የተሰጠው የዱቤ አገልግሎት የክፍያ ጊዜ ከ 61 ቀን እስከ 6 ወር
ባለው ጊዜ ደምበኛው የዱቤ አገልግሎት ግዴታ የሚመጣበት አሠራር ነው፡፡
ዘ. “የረዥም ጊዜ የዱቤ አገልግሎት” ማለት ከ 6 እስከ 12 ወራት ባሉት ጊዜያት ወይም በዋና ሥራ አስፈፃሚ
ወይም በሀብት አስተዳደር ቢዝነስ ዘርፍ በልዩ ሁኔታ የሚፈቀድ የዱቤ አገልግሎት ዓይነቶች ናቸው፡፡
ዠ. “የዱቤ አገልግሎት ወሰን” ማለት ተቋሙን ለደምበኞቹ በዱቤ ሺያጭ የሚፈቀደው ዝቅተኛና ከፍተኛ
የብር እና ጊዜ ወሰን ነው፡፡
የ. “የዱቤ አገልግሎት የክፍያ ጊዜ” ማለት ደምበኛው የዱቤ አገልግሎት ፈቃድ ካገኘበት ጊዜ ጀምሮ ክፍያውን
አጠናቆ የሚጨርስበት የጊዜ ገደብ ነው፡፡

1.4 የፆታ አገላለጽ


በእዚህ ሰነድ ውስጥ በወንድ ፆታ የተገለፀው የሴትን ፆታ ያካትታል

1.5. የመመሪያው አስፈላጊነት


1. ዱቤ ሊሰጣቸው የሚገቡና የማይገባቸው ደምበኞችን በአግባቡ ለመለየት እንዲያግዝ፤
2. ተጠያቂነት ያለበት የዱቤ አገልግሎት አሠራር መዘርጋት የሺያጭ ማሳደጊያ አንዱ ስልት በመሆኑ፤
3. ተቋሙ የደረሰበትን የዕድገት ደረጃ የሚመጥን አሰራር ለመዘርጋትናየዱቤ አሰጣጥ፣አፈቃቀድና
አፈፃፀም ላይ የሚወስኑ አካላት ኃላፊነትና ተግባር በግልጽ ለማስቀመጥ፤
4. ከቆይታ ብዛት ሳይሰበሰቡ የሚዘገዩ ብሮች መብዛታቸው በተቋሙ የፋይናንስ ማኔጅሜንትና የገንዘብ ፍሰት
ላይ ችግር መፍጠሩ እንዲሁም ለደንበኞች ውዝፍ እዳ ሆኖ ለመክፈል አዳጋች መሆናቸው፡፡
5. ብሮች ከረጅም ጊዜ የዱቤ ቆይታ በሁዋላ ሊሰበሰቡ ሲሉ ተቁዋማት ፈርሰው፣ ለሁለት ተከፍለው
ወይም አመራሮች በሚቀየሩበት ሰአት የአከፋፈል ሁኔታውን ውስብስብ በማድረጋቸው፡፡

የዱቤ አገልግሎት አሰጣጥ መመሪያ 4


1.6. የመመሪያ ቁጥር - 01/2016 ተብሎ ይጠራል፡፡
1.7. የመመሪያው ዓላማ
1.7.1. ታማኝ የሆኑና የረዥም ጊዜ ያላቸውን ደምበኞችን በጣቢያው ለማቆየት፤

1.7.2. ተቋሙ የደረሰበትን የዕድገት ደረጃ የሚመጥን የዱቤ አስተዳደር ሥርዓት ለመፍጠር

1.7.3. በዱቤ አሰጣጥ፣ አፈቃቀድና አፈፃፀም ላይ የሚወስኑ አካላት ኃላፊነትና ተግባር በግልጽ ለማስቀመጥ፣

1.7.4. የማይሰበሰብ የዱቤ አሰጣጥ ሥርዓትን ማስቆም፤ /ዱቤ በዱቤ ላይ የመስጠት ስራን ለመከላከል፤
1.7.5. በማዕከልና በክልል ጣቢያዎች ወጥ የሆነ የዱቤ አሰጣጥ ሥርዓት ተግባራዊ ለማድረግ፤
1.7.6. ዱቤ ሊሰጠው የሚገባና የማይገባውን ደንበኛ መለያመስፈርት በማዘጋጀት መርህ የተከተለ የዱቤ
አሰጣጥ ስረዓት በመዘርጋት የተሻለ የዱቤ አስተዳደር ለመፍጠር፤
1.7.7. በአከፋፈል ሰአት በቆይታ ምክንያት የሚፈጠሩ የሂሳብ መወሳሰቦችን ለመቀነስ

ምእራፍ ሁለት
2. የዱቤ አገልግሎት አሰጣጥን በተመለከተ ሊከተላቸው የሚገቡ መርሆዎች

የዱቤ አገልግሎት አሰጣጥ መመሪያ 5


2.1 የሀገሪቱ ህግ በሚፈቅደው መሰረት ለመንግስት ተሰብሳቢ የሆኑ ክፍያዎችን በህጉመሰረት
እንዲከፍሉ ያለአድሎአዊነት ይሰራል፤
2.2 በመመሪያው የዱቤ አገልግሎት እንዲሰጣቸው ለማይፈቀድላቸውምሆነ ለሚፈቀድላቸው በዘር፣
በሀይማኖት፣ በፖለቲካልውግናም ሆነ ከሌላ አተያይ ነጻ በሆነ መልኩ ውሳኔ መስጠት፤
2.3 ለሁሉም ደምበኛ ተመሳሳይ አገልግሎትን መስጠትና ከአድሎ የጸዳ አገልግሎት መስጠት፤
2.4 ኃላፊነት ከተሰጠው አካል ካልተወሰነ በስተቀር ተደራራቢ ዱቤዎችን አለመስጠት፤

ምእራፍ ሶስት
3. የዱቤ አገልግሎት መመሪያው ጠቀሜታ፣ የዱቤ አሰጣጥ መስፈርት፣ የቆይታ ጊዜ፣
የዱቤ አከፋፈል ስረዓትና ክልከላ
3.1 የዱቤ አገልግሎት መመሪያው ጠቀሜታ
1. ለመሰብሰብ የተያዘውን የገቢ እቅድ የዱቤ ክፍያ ግብ ያሳካል፤
2. የተደራጀና ትክክለኛ የሆነና ተጠያቂነትና ኃላፊነትን የሚያመላክት የአመራር ሥርዓት ለመዘርጋት
ያመቻል፤
3. ከተፎካካሪ ድርጅቶች ጋር በሚደረገው የገበያ ሽሚያ ውስጥ አሰራርን በማቀላጠፍ እንደ አንድ
መወዳደርያ በመሆን ያገለግላል፤
4. በአሰራር ምክንያት የሚፈጠርን የገበያ ስጋትን በመቀነስ ሺያጭን ለማሳደግ ያገለግላል፤

3.2 የዱቤ አገልግሎት የሚሰጣቸው አካላት


ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት አ.ማ እንደ ንግድ ሚዲያ የዱቤ አገልግሎት የሚሰጣቸውን ደምበኞች የሚመዝንበት
መስፈርቶች አሉት፡፡ ዱቤ ለመስጠት የጠየቀው አካል ሕጋዊ ሰውነትና የኢኮኖሚ አቅም ብቻ ሳይሆን ደምበኛው
በቀጣይ የተቋሙ የሚዲያ ሺያጭ ላይ የሚኖረውን ጠቃሚነት ከግምት ውስጥ ያስገባል፡፡ በእዚሁ አግባብ ተቋማችን
የብድር ጠያቂውን የኋላ ታሪክ፤ ታማኝነቱንና የዱቤ ጥያቄውን መጠን ከግምት ውስጥ በማስገባት ዱቤውን
የሚፈቅደው አካል የዱቤ አገልግሎቱ መቼ መመለስ እንዳለበትና በተቀመጠው የጊዜ ገደብ የማይከፈል የዱቤ
አገልግሎት እንደአስፈላጊነቱ ቅጣትና ተጠያቂነት እንደሚያመጣበት ከደንበኛው ጋር በሚያዘው ውል ውስጥ ሊካተት
ግድ ይላል፡፡
በመሆኑም በማዕከልም ሆነ በክልል ጣቢያዎቻችን የዱቤ አገልግሎት የሚሰጣቸው፡-
ሀ. በቀጥታ እና በውስጥ ሽያጭ ባለሙዎች የሚመጡ ደንበኞች፣
ለ. በማስታወቂያ ወኪሎችና የትብብር ፕሮግራሞች ደምበኞች፤

የዱቤ አገልግሎት አሰጣጥ መመሪያ 6


ሐ. በይዘት ዝግጅት ላይ የሚሠሩ ተባባሪ አዘጋጆች የዱቤ አገልግሎት ሊሰጣቸው ይችላል፡፡ ይህም በሥልጣን
ውክልና በተፈቀደው የፊርማ ወሰን አግባብ የሚፈፀም ይሆናል፡፡

3.3 የዱቤ አገልግሎት የሚሰጥበት መስፈርት


3.3.1 በቀጥታ እና በውስጥ ሽያጭ ባለሙዎች ለሚመጡ ደንበኞች፣
የተለያዩ ተቋሞች በሬድዮና በቴሌቭዥን እንዲሁም ሌሎች አገልግሎቶች ለማግኘት ሲሉ በቀጥታና በውስጥ ሽያጭ
ባለሙያዎች የስራ ትእዛዞችን ይሰጣሉ፡፡ የስራ ትዝዛዞቹም በህጋዊ ደብዳቤ ወይም በውል ስምምነት ሊሰጡ ይችላሉ፡፡
ሆኖም ደብዳቤውም ሆነ የውል ስምምነቱ ውስጥ የክፍያ እና የስርጭት ጊዜ ብዛትና ሰዓት የሚያመላክት
መርሐግብር መኖር አለበት፡፡በእዚሁ መሠረት የዱቤ አገልግሎቱ፡-

ሀ. በበጀት ዓመቱ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያለው ንግድ ተቋም፣


ለ. መንግስታዊ እና መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት፣ ማህበራት….
ሐ. አዲስ የተቋቋመ ድርጅት ካልሆነ
መ. ከዚህ ቀደም በጣቢያው የዱቤ እዳ ያሌለባቸው እንዲሁም ክፍያን በማዘግየት ማይታሙ እና
ሠ. በተቋሙ የዱቤ አከፋፈል ሥርዓት ታማኝ የሆነ ድርጅት በህጋዊ ደብዳቤ ጥያቄ ሲያቀርቡ እና የተሟላ የስራ ትእዛዝና
የስርጭት ጊዜ ሰሌዳ የያዘ ውል ስምምነት ሲፈርም የዱቤ አገልግሎት ይሰጣል፣ ደንበኛውም ይስተናገዳል፡፡

3.3.2 በማስታወቂያ ወኪል ለሚመጡ የስራ ትእዛዞች፣


የማስታወቂያ ወኪሉ ሕጋዊ ዕውቅና ያለው እና ከፋና ጋር ለመስራት ማመልከቻ አቅርቦ የተፈቀደለት ሆኖ፣

ሀ. ከተቋሙ ጋር የሚሰራውን የገቢ መጠን፣ የሚስተናገድበትን የገቢ ስራ ሥርዓት እና የአከፋፈል ሁኔታ


የሚያመላክት ህጋዊ ዓመታዊ ውል ስምምነት በልዩ ሁኔታ ለሚፈርም ማስታወቂያ ወኪል፣
ለ. የዱቤ አገልግሎት ከ 30 - 60 ቀን ሆኖ በማስታወቂያ አስነጋሪ ደንበኛ ህጋዊ ደብዳቤ /ስሙ በደብዳቤ ውስጥ
ተጠቅሶ የስራ ትእዛዝ ይዞ ለመጣ ማስታወቂያ ወኪል፣
ሐ. ማስታወቂያ ወኪሉ፣ ማስታወቂያ አስነጋሪ ድርጅት እና ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር የሶስትዮሽ ውል ስምምነት
ለተፈረመለት የሥራ ትእዛዝ፣(በልዩ ሁኔታ የሚታይ)
መ. ለክልል ጣቢያ የተለያዩ የስራ ትእዛዞችን ከሚሰጥ ደንበኛ የማስታወቂያ ስራ ይዞ የሚመጣ ማስታወቂያ
ወኪል፤
ሠ. በክልል ጣቢያ የሚወስደውን የዱቤ አገልግሎት በሚዘጋጀው ቅጽ መሠረት የሚጠይቅና ግዴታውን
ለመወጣት ዝግጁ የሆነ፤
ረ. የተሰጠው የዱቤ አገልግሎት ከማስታወቂያ አስነጋሪ ደምበኛው በወቅቱ ወይም በተቀመጠበት የጊዜ መርሐ ግብር መሰረት
ክፍያው ለፋና እንዲፈፀም የራሱን ጥረት ለማድረግ ግዴታ የሚገባ ማስታወቂያ ወኪል፣
ሰ. የአገልግሎት ክፍያው በወቅቱ ለፋና መክፈል ካልቻለ ተጨማሪ የቅጣት ክፍያ ለመክፈል የውል ግዴታ የገባ፤

የዱቤ አገልግሎት አሰጣጥ መመሪያ 7


ሸ. ተከታታይ ሥራ ለሚያመጡና ለደምበኛቸው የሚሰጠው ዱቤ ከ 3 ወር የማይበልጥ፤

3.3.3 በተባባሪ አዘጋጆች ለሚመጡ ውሎች፣


ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት አ.ማ ጋር የሚሰሩ የቴሌቪዥንና የሬድዮ ተባባሪ አዘጋጆች አሉ፡፡ ሁሉም ተባባሪ
አዘጋጆች የይዘትና የገቢ ዕቅድ ለተቋሙ በማቅረብ የውል ስምምነት የፈረሙ ናቸው፡፡ ስለሆነም፡-
ሀ. ማንኛውንም በተባባሪ አዘጋጆች የሚመጡ የዱቤ አገልግሎቶች በልዩ ሁኔታ በዋና ስራ አስፈፃሚ ካልተፈቀደ
በስተቀር በሶስትዮሽ ውል ስምምነት ብቻ የሚሰራ ይሆናል፡
ለ. በውል ስምምነቱ ፋና ውል ተቀባይ ሆኖ ከማስታወቂያ አስነጋሪ ደንበኞች በመሰብሰብ /ገንዘቡ ገቢ ሲደረግ/ለተባባሪ
አዘጋጁ ድርሻውን የሚያገኝ ይሆናል፡
ሐ. ተባባሪ አዘጋጁ ከማስታወቂያ አስነጋሪ ደንበኛ ጋር የሁለትዮሽ ውል ስምምነት የሚፈርም ከሆነ ውሉን ለተቋሙ /ፋብኮ/
በማቅረብ የፋናን ድርሻ ብቻ በካሽ የሚከፍል ይሆናል ወይም የደንበኛውን ውል አባሪ በማድረግ ሌላ የዱቤ
አገልግሎት ውል ከፋና ጋር ስምምነት ይፈርማል፡፡
መ. ተባባሪ አዘጋጁ ወይም ደንበኛው የዱቤ ክፍያውን በተቀመጠለት የጊዜ ገደብ የማይከፍል ከሆነ ተጨማሪ
ቅጣት የሚከፍል ይሆናል፤ ይህም ግዴታ በውል ስምምነት ውስጥ የሚካተት ይሆናል፡፡
3.4 የዱቤ አገልግሎትን ስለመከልከል
ማንኛውም የዱቤ አገልግሎት ጠያቂ ተቋም እንዳስፈላጊነቱ የዱቤ አገልግሎት ሊፈቀድለት ይችላል፡፡ ሆኖም በልዩ
ሁኔታ ካልተፈቀደ በስተቀር የዱቤ አገልግሎት
ሀ. አዲስ ለተቋቋመ ንግድ ድርጅት፣
በተለይም ድርጅቱ የመክፈል አቅሙ ጥያቄ ውስጥ የሚገባ ከሆነ
ተአማኒነት ከሌለው
ድርጅቱ በገበያ ውስጥ ተወደዳሪ ሆኖ የመቆየት ብቃቱ አስጊ ከሆነ
ለ. በመቋቋም ላይ ላለ አክሲዮን ማህበር፣
የመክፈል አቅሙ እና ጥያቄ ውስጥ የሚገባ ከሆነ
ተአማኒነት ከሌለው
እራሱን ችሎ እንደተቋም መቆም መቻሉ ጥዯቄ ውስጥ የሚገባ ከሆነ
ሐ. የንግድ ፈቃድ ለሌለው ድርጅት፣
መ. የንግድ ፈቃዱን ላላደሰ ድርጅት እና
ሠ. ዱቤ በዱቤ ላይ ለሚጠይቁ ደንበኞ የዱቤ አገልግሎት መሰጠት የተከለከለ ነው፡፡
3.5 የዱቤ አገልግሎት ክፍያ ሥርዓት
ማንኛውም የዱቤ አገልግሎት የክፍያ ስርዓት በውል ስምምነት ውስጥ በሚዘጋጀው የክፍያ መርሐ ግብር መሠረት ሆኖ
ተቋም ወይም ድርጅት ክፍያ የሚፈፅመው፡-

የዱቤ አገልግሎት አሰጣጥ መመሪያ 8


ሀ. መንግስታዊ የሆኑ ተቋማት በመንግስት የግዢ ፖሊሲ መሰረት ከ 30-50 በመቶ ቅድመ ክፍያ በመፈጸም
ቀሪውን ክፍያ ሁለቱ አካላት ስምምነት በደረሱበት በክፍያ አፈፃፀም መርሐግብር ወይም አገልግሎቱ
እንደተጠናቀቀ የሚከፈል ይሆናል፤
ለ. ቋሚ የግል እና የበጎ አድራጎት ድርጅት ሆነው የደንበኛነት ቆይታው ከ 2 ዓመት በላይ የሆነ እና በተደጋጋሚ
የሽያጭ የአገልግሎት ግዥ ለሚፈፅም ደንበኛና እዳውን በተቀመጠለት መርሃ ግብር የሚፈፅም አካል
የዱቤ አገልግሎት ከ 25--40 በመቶ በመፈፀም ቀሪውን በውል ውስጥ በተቀመጠው የክፍያ አግባብ
የሚፈፅም ይሆናል፤
ሐ. በተቋሙ ማስታወቂያ ለማስነገር የሚመጡ ቋሚ የመንግሥት ተቋማት፣ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችና የግል
ተቋማት "የክፍያ መጠየቂያ እንደደረሰን ክፍያ እንፈፅማለን" በሚል ህጋዊ በደብዳቤ ሊስተናገድ ይችላል፤
(ለመንግስታዊ ተቁዋማት በህጋዊ ደብዳቤ ክፍያ ሲጠየቅ ያለውል አንከፍልም የሚል ምክንያት አንዲሁም ውል
እንዲፈርሙ ሲጠየቁ በተለይም ስራው ተሰርቶ ያለቀ ከሆነ ቢሮክራሲ ሚበዛበት ስለሆነና ክፍያ ስለሚዘገይ ውል
ከደብዳቤው በተጨማሪ በውል ይታሰራል፡፡)
መ. የዱቤ አገልግሎት ተጠቃሚው በተቀመጠው የጊዜ ወሰን ዱቤውን የማይከፍል ከሆነ በውል ስምምነቱ
በሚጠቀሰው አግባብ ወሩ ካለፈ በወሰደው የዱቤ መጠን ላይ በየወሩ 1.5 ወይም በዓመት 9.5 በመቶ
ተጨማሪ ክፍያ ይፈጽማል፡፡
ሠ. ማንኛውም የዱቤ አገልግሎት ተጠቃሚ በልዩ ሁኔታ ከበላይ የሥራ ኃላፊ ፈቃድ እስካላገኘ ድረስ የዱቤ
ክፍያውን በውል ስምነቱ መሰረት መፈጸም ግዴታ አለበት፤ አለመክፈሉ ከተረጋገጠ በኋላ ባሉት ከ 45
ቀናት ውስጥ ጉዳዩ ለሕግ ክፍሉ ይላካል፡
ረ. የክፍያ ሰብሳቢ አካል እነዚህን መርሐግብር መሠረት በማድረግ የሚዲያ ሥራ የፕሮግራም ቅጅዎችና
ሌሎችም ለክፍያ አስፈላጊ የሆኑ ሰነዶች በሚመለከተው አካል ለደምበኛው መደረሱን በሚደርሰው
ግልባጭ ወይንም የስርጭት መርሀ ግብር አረጋግጦ በወቅቱ የዱቤ ክፍያውን መሰብሰብ አለበት፡፡
ሰ. የበአል ተባባሪ አዘጋጆችና የማስታወቂያ ወኪሎች ለሚያመጡዋቸው የበአል ፕሮግራም ስፖንሰሮች

በቅድሚያ ቼክ እንዲያስይዙ የሚገደዱ ሲሆን የስፖንሰርሺፕ ሙሉ ክፍያ በወቅቱ እንዲሰበሰብ ካላደረጉ


በቀር ምንም አይነት የኮሚሽን ክፍያ አይከፈላቸውም፡፡ ያስያዙትም ቼክ ተመላሸ አይሆንም፡፡

3.6 የዱቤ አገልግሎት የመፍቀድ ኃላፊነቶች


የተቋሙ የሥራ ኃላፊዎች የዱቤ አገልግሎት መጠን የመፈቀድ አቅማቸው ብቻ ሳይሆን በዱቤ አሰጣጥ
መከተል የሚገባቸውን የአሰራር መርሆዎች እና ሌሎችም አስፈላጊ ጉዳዮችንም በዝርዝር ሊያውቁ ይገባል፡፡
የዱቤ አሰጣጥ ላይ የሚደረግ ጥንቃቄ ጤናማ የዱቤ አገልግሎት ሥርዓትን የሚፈጥር በመሆኑ ትኩረት
ሊሰጠው ይገባል፡፡ በእዚሁ መሠረት፡-

የዱቤ አገልግሎት አሰጣጥ መመሪያ 9


ሀ/ አጠቃላይ የገንዘብ መጠናቸው እስከ 150,000.00 ብር ለሚደርስ ዱቤ አገልግሎት በዳይሬክተር ደረጃ
መፍቀድ ይቻላል፤

ለ/ አጠቃላይ የገንዘብ መጠናቸው ከ 150,000.00 ብር በላይ ለሆነና እስከ 5,000,000.00 ብር ዱቤ አገልግሎት


በምክትል ስራ አስፈጻሚ ደረጃ ታውቆ መፍቀድ ይቻላል፤

ሐ/ አጠቃላይ የገንዘብ መጠኑ ከ 5,000,000.00 ብር በላይ በስራ አስፈጻሚ ደረጃ ታውቆ መፍቀድ የሚቻል
ሲሆን ከዚህ ብር በላይ የሚጨምር ከሆነ በዋና ስራ አስፈጻሚ ታውቆና ሲፈቀድ ብቻ የሆናል፤

በተመሳሳይ

1. የአጭር ጊዜ የዱቤ አገልግሉት ጥዯቄዎች በዳይሬክተር ደረጃ መፍቀድ ይቻላል፤


2. የመካከለኟ ጊዜየዱቤ አገልግሎት ጠያቄዎች በምክትል ስራ አስፈጻሚ ደረጃ ታውቆ መፍቀድ
ይቻላል፤
3. የረጅም ጊዜ የዱቤ አገልግሎት በስራ አስፈጻሚ ደረጃ ታውቆ መፍቀድ ይቻላል

3.6.1 የኃላፊዎች ሥልጣን፤


ሀ. የዱቤ ተሰብሳቢ ሂሳብን በውሉ መሠረት የመሰብሰብ ኃላፊነት የፋይናንስና ግዢ ዳይሬክቶሬት ኃላፊነት
ነው፡፡ የሺያጭና የማርኬቲንግ፤ የደምበኞች አገልግሎት ዳይሬክቶሬት እንዲሁም የክልል ጣቢያዎች
ዳይሬክቶሬት እና ሌሎች የገቢ ክፍሎች የተሰሩ ሥራ ደግሞ ከአቅም በላይ የሆኑ የዱቤ ክፍያዎች
ለማስፈፀም እገዛ የማድረግ ግዴታ አለባቸው፤
ለ. ማንኛውም ኃላፊ ለፈረመው ውል ትክክለኛነት ኃላፊነቱን የሚወስድ ሲሆን ተሰብሳቢነቱ ላይ አስፈላጊውን እገዛ
ከፋይናንስና ግዢ ሲጠየቅ ትብር የማድረግ ግዴታ አለበት፡፡
ሐ. ማንኛውም የሚዲያ ይዘት የውል ስምምነት ግልባጭ (ኮፒ) እንዳስፈላጊነቱ ለዋና ሥራ አስፈፃሚ፣ ለኦፕሬሽን ዘርፍ፣
ለደምበኞችና ሥርጭት አገልግሎት ዳ/ት ለፋይናንስና ግዥ ዳይሬክቶሬት፣ ለኦፕሬሽን ዘርፍ እና ለሪከርድና
ማህደር መድረስ አለበት፡፡
መ. የሥራ ውሉ በዓይነት የአገልግሎት ልውውጥ የሚደረግበት ከሆነ በዋና ስራ አስፈጻሚ ሲፀድቅ ብቻ የሚፈጸም
ይሆናል።
ሠ. የዱቤ አገልግሎትን አስመልክቶ ለሚነሱ ማንኛውም ክርክሮች የመጨረሻ ውሳኔ የሚሰጠው የተቋሙ ዋና
ሥራ አስፈፃሚ ነው፡፡

3.7 የተቋም የዱቤ አገልግሎት አስተዳደር


ሀ. የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፕሬት የዱቤ አገልግሎት በገቢ ዕቅድ ፈፃሚዎች፣አስተዳደርና ቢዝነስ ዘርፍና ም/ዋና ሥራ
አስፈፃሚ ይህም ቀደምሲል በተጠቀሰው የገንዘብ መጠን መሠረት የሚፈፀም ይሆናል፡፡

የዱቤ አገልግሎት አሰጣጥ መመሪያ 10


ለ. በተቋሙ የሚካሄዱ የዱቤ ሺያጮች በማንዋሉ መሠረት መፈፀሙንና ጤናማ የዱቤ አገልግሎት መሆኑን
ተከታትሎ በየጊዜው ለሚመለከታቸው ሪፖርት ማድረግ የፋይናንስና ግዢ ዳይሬክቶሬት የማረጋገጥ
ኃላፊነት አለበት፤
ሐ. የፋይናንስና ግዢ ዳይሬክቶሬት ከዱቤ ሺያጭ የአፈፃፀም ችግሮች ጋር በተያያዘ ጉዳዩ የሚመለከታቸው የገቢ
ዕቅድ ፈፃሚ ዳይሬክቶሬት ጋር ይመክራል የመፍትሔ ሀሳቦችን ያፈላልጋል፡፡

3.8 የተጠያቂነት አግባብ


ሀ.ካለ አግባብ በዱቤ ላይ ዱቤ የፈቀደ የሥራ ኃላፊ በአስተዳደር መመሪያ መሠረት ማለት ተቋሙ ላይ ለደረሰው ጉዳት
ተጠያቂ ይሆናል፤

ለ. አስፈላጊ መመዘኛዎቹን በመተላለፍ ለማይገባቸው አካላት ዱቤ የሰጠ በአስተዳደር መመሪያ መሠረት በዲሲፕሊንና
በፍትሐብሔር ሊጠየቅ ይችላል፤

ሐ. የአስተዳደርና ቢዝነስ ዘርፍ ከዱቤ ሺያጭ ጋር ተያይዞ ማንኛውንም ከዱቤ መመሪያ ወጪ የሚፈፅሙና የአሠራር
ግድፈቶች በየጊዜው እየገመገመ እርምት የመውሰድ ግዴታ አለበት፡፡

ምእራፍ አራት

ልዩ ልዩ ድንጋጌዎች
4. የተፈፃሚነት ወሰን

ሀ. ይህ ማንዋል በፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፕሬት አ.ማ በተቋሙ ለሚካሄዱ የዱቤ ሺያጮች (በሺያጭና
ማርኬቲንግ፣ በደምበኞችና ስርጭት አገልግሎት በክልል ጣቢያዎች) ያገለግላል፤
ለ. ማንዋሉ ሥራ ላይ ከዋለ በኋላ በመመሪያው ያልተሸፈኑ ወይም ያልተካተቱ ተቃርኖ ያመጡ ወይም በሌላ
ለማናቸውም ምክንያት ለአሠራር ያስቸገሩ ሥራዎች ቢያጋጥሙ በገቢ ዕቅድ ፈፃሚ ዳይሬክቶሬቶች

የዱቤ አገልግሎት አሰጣጥ መመሪያ 11


አቅራቢነት በሀብት አስተዳደር ቢዝነስ ዘርፍ ም/ዋ/ሥ/አ እና በዋና ሥራ አስፈፃሚ በሚሰጥ መመሪያ
ይስተናገዳል፤
ሐ. የኃላፊነት ግዴታዎች፡- የሺያጭና ማርኬቲንግ፣ የደምበኞችአገልግሎት ዳይሬክቶሬት ያሉና በሌሎችም
የገቢአመንጪ ክፍሎች ላይ የክልል ጣቢያዎች ዳይሬክቶሬቶች እንዲሁም የፋይናንስና ሺያጭ
ዳይሬክቶሬት ማንዋሉን ተግባራዊ ማድረግ ኃላፊነት አለባቸው፡፡
4.1 መመሪያው ስለሚሻሻልበት ሁኔታ

ሀ. ተቋማቱ ከደረሰበት የዕድገት ደረጃና የቢዝነስ መስፋፋት አንፃር አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ፤


ለ. ለአሠራር አመቺ ያልሆኑ አንቀፆች ወይም አዳዲስ የዱቤ አገልግሎትና የሺያጭ አሠራሮች ተፈጥረው
ማንዋሉ ለአሠራሩ እንቅፋት ነው ተብሎ ሲታሰብ፤
ሐ. የሺያጭና ማርኬቲንግ፣ የደምበኞችና አገልግሎት፣ የክልል ጣቢያዎች ማስተባበሪያ፣ እና ሌሎች የገቢ
አመንጪ የስራ ክፍሎች፣ የፋይናንስና ግዢ ዳይሬክቶሬት መነሻ ሲያቀርቡና በዋና ሥራ አስፈፃሚ
ሲፈድቅ መነሻ ቀርቦ ውይይት ከተደረገበት በኋላ ሊቀየር ይችላል፡፡
4.2 መመሪያው ሥራ ላይ የሚውልበት ጊዜ
ይህ መመሪያ ከ-----------------ጀምሮ ተግባራዊ ይሆናል፡፡

የዱቤ አገልግሎት አሰጣጥ መመሪያ 12

You might also like