Professional Documents
Culture Documents
Product Brief Final One
Product Brief Final One
ድጋፍ አነስተኛ ብድር አቅራቢ አክሲዮን ማኅበር የሚስጣቸው አገልግሎቶች የዋጋ ዝረዝር እና
የአከፋፍል ሁኔታ
መግቢያ
ድጋፍ አመስተኛ ብድር አቅራቢ በሁሉም ደረጃ ለሚገኙ የሀገራችን የኅብረተሰብ ክፍሎች የፋይናንስ
አገልግሎትን ተደራሽ ለማድረግ በማለም የተመሰረተ እና በዘርፉ ከአስር ዓመታት በላይን ያስቆጠረ ተቋም
ነው፡፡ ድጋፍ አነስተኛ የብድር አቅራቢ አክሲዮን ማኅበር በአሁን ወቅት ለግለሰቦች እና ለአነስተኛ
አነስተኛ ብድር አቅራቢ የፋይናንስ አገልግሎት ኢንዱስትሪውን ቀጣይነት ባለው እና ሁሉን አቀፍ በሆነ ደረጃ
ወደፊት ለማሻግር ራዕይ አድርጎ ራሱን በማስፋፋት በተለያዩ ቦታዎች ቅርንጫፎችን ከፍቶ እንቅስቃሴ
የሚያደርግ አክሲዮን ማኅበር ነው፡፡
በመሆኑም አክሲዮን ማኅበሩ በገንዘብ ብቻ ሳይሆን በአይነት የሚመደቡ አገልግሎቶችን ከተለያዩ ድረጅቶች ጋር
በመተባበር ለግሰቦችም ሆነ ለአነስተኛ ተቋማት ያለምንም መስተጓጎል በምቹ መንገዶች ተደራሽ እንዲሆኑ
ሌት ተቀን ይተጋል፡፡ ይህም ከጊዜ ወደ ጊዜ ተመራጭ የፋይናንስ አገልግሎት ተቋም እንዲሆን አስችሎታል፡፡
በዚህም መሠረት ድጋፍ አነስተኛ ብድር አቅራቢ አክሲዮን ማኅበር የሚሰጣቸው አቅርቦቶች እና አገልግሎቶች
የሚከተሉትን ይመስላሉ፡፡
ዋና ዋና አቅርቦቶች እና አገልግሎቶች
ገፅ |1 https://digafmfi.et/
Access beyond Limits!
የአከፋፍል ሁኔታ
አገልግሎት ተጠቃሚው የብድር አከፋፈሉን የሚያከናውነው ብድሩን በወሰደበት ወቅት ከሚያገኘው ደሞዝ
ሲሆን መበደር የሚችለው ከፍተኛ መጠን 10000 ብር ይሆናል፡፡ ይህ የብድር አገልግሎት ከወለድ ነፃ ነው፡፡
1. የታደስ መታወቂያ
2. አንድ ጉርድ ፎቶ
3. ቋሚ ስራተኛ ስለመሆናቸው እና የደሞዝ መጠንን የሚገልጽ ደብዳቤ
4. የሶሰት ወር የቅረብ ጊዜ ተከታታይ ደሞዝን የሚያሳይ ባንክ መግለጫ
ምሳሌ፡-
ገፅ |2 https://digafmfi.et/
Access beyond Limits!
“ሀሁ” የተባለ ተበዳሪ ደሞዙ 6000 ብር ቢሆን መበደር የሚቻለው የደሞዙን 1/3 ኛ ማለትም 6000/3 = 2000
ብር ይሆናል፡፡ በዚህም መሠረት ሰኔ 17 ቀን 2015 ዓ.ም ብድሩን ቢወስድ እና የሰኔ ወር 2015 ዓ.ም ደሞዝ ሰኔ
27 ቀን 2015 ዓ.ም የሚወጣ ቢሆን ከደምወዙ 2200 ብር ማለትም 2000 ብር በዋና ክፍያነት 200 ብር ደግሞ
በአግልግሎት ክፍያነት ወደ ድጋፍ የባንክ አካውንት ገቢ ወይም ተቆራጭ ይደረጋል፡፡
1. ወደ 6575 መደወል
ማስታወሻ ፡- በማመልክት ሂደት ውስጥ ችግር በሚያጋጥምበት ወቅት ዕርዳታ ለመጠየቅ ወደ 6575 በመደወል
መፍትሔ ማግኘት ይቻላል፡፡
ይህ አገልግሎት አንድ ደሞዝተኛ የብድር ተጠቃሚ የአንድ ወር ደሞዙን አምስት እጥፍ ወይም የአምስት ወር
ደሞዙን በአንዴ መበደር የሚያስችለው ነው፡፡ በዚህም መሠረት ትልቁ የብድር መጠንም 150,000 ብር ነው፡፡
በመሆኑም የአገልግሎቱን መስፈርት የሚያሟላ ማንኛውም ስራተኛ ለተለያዩ ጉዳዮች ወይም ዓላማ
የሚያውለውን ጠርቀም ያለ ገንዘብ በብድር መልክ በዚህ አማራጭ ማግኘት ነው፡፡
ገፅ |3 https://digafmfi.et/
Access beyond Limits!
የአከፋፍል ሁኔታ
አንድ ተበዳሪ የአንድ ወር ደሞዙን ቢወስድ በሶሰት ወር፤ የሁለት ወር ደሞዙን ቢወስድ በስድሰት ወር እና
የአምሰት ወር ደሞዙን ቢወስድ በአስራአምሰት ወራት ክፍሎ ማጠናቅቅ ይኖርበታል፡፡
ምሳሌ፡-
አቶ “ሀሁ” ደሞዛቸው አምሰት ሺ ብር ቢሆንና የሶሰት ወር ደሞዛቸውን ያህል መጠን ያለው የ 15000 ብር
ብድር ቢፈልጉ ከሚበደሩት ብር ላይ የአገልግሎት ክፍያ 5% እና የሕይወት ዋሰትና ክፍያ 1.5% ተቀናሽ ተድርጎ
በሂሳብ ቁጥራቸው ገቢ እንዲሆን ይደረጋል፡፡ በዚህም መሠረት ከ 15000 ብር ብድር ላይ
5%*15000 =750 ብር
1.5%*15000 = 225 ብር
750 ብር+ 225 ብር= 975 ብር ተቀናሽ ሆኖ 14,025 ብር ወደ ሀሁ የባንክ ሂሳብ ቁጥር ገቢ ይሆናል:: አቶ
“ሀሁ” ብድሩን ከወስዱ በኋላ በየወሩ በተቀናሽ ወለድ አስራር /Declining balance method/ ከዋናው
ብድር ጋር የተደመረ 15,985.32 ብር ለዘጠኝ ተከታታይ ወራት (15,985.32 /9 ወራት=1776.15 ብር በየወሩ)
በመክፈል ያጠናቅቃሉ፡፡1
ድጋፍ ዱቤ
ድጋፍ ዱቤ የብድር አገልግሎት ደንበኞች ከተለያዩ ሱቆች እና ድርጅቶች በዱቤ አገልግሎት የወደዱትን እና
የመረጡትን መሸመት የሚያስችላቸው የብድር አስራር ነው፡፡ በአሁን ወቅት ከድጋፍ አነስተኛ ብድር አቅራቢ
አክሲዮን ማኅበር ጋር ‘’የድጋፍ ዱቤ ‘’ የብድር አገልግሎትን ለማቅረብ በትብብር የሚሰሩ ጥቂት ሱቆች እና
ድርጅቶች የሚገኙ ሲሆን እንደአስፈላጊነቱ እና እንደ ደንበኞች ፍላጎት ቁጥራቸው የሚጨምር ይሆናል፡፡
“ዱቤ እቃ” የዱቤ አገልግሎት አንድ ደንበኛ ከታች የተጠቀሱትን አገልግሎቶች መጠቀም በሚፈልጉብት
ወቅት በድጋፍ አነስተኛ ብድር አቅራቢ አ.ማ አማካኝነት በቀላሉ ዱቤ ማግኛት የሚችልበት አማራጭ ነው፡፡
እነዚህ አገልግሎቶች
1
ተበዳሪ ደምበኞች ጠቅላላ ወለዱን እንደዚሁም በየወሩ የሚከፈለውን የክፍያ መጠን በይነመረብ ላይ “calculatornet” ብለው
ገፅ |4 https://digafmfi.et/
Access beyond Limits!
o የሱፍ ልብስ
o አስቤዛ
o የጤና መድኅን
o የትምህርት ቤት ክፍያ
o ሞባይል ቀፎ ናቸው፡፡
1. ዱቤ ሱፍ ልብስ (Garment)
ድጋፍ አነስተኛ ብድር አቅራቤ ይህንን አገልግሎት ለደንበኞቹ ለማቅረብ ከ አምስት የልብስ ስፌት ድርጅቶች
ጋር በትብብር ይሰራል፡፡
1.1 . አማዞን ሱፍ
የሁሉም የሱፍ ልብስ ወጥ የሆነ የ 6500 ብር ዋጋ ያለው ሲሆን ሁሉም አይነት የወለድ፣ የአገለልግሎት እና
የሕይወት መድኅን ክፍያዎች አማዞን ሱፍ በሚያደርገው ልዩ ቅናሽ /discount/ የሚሸፈን በመሆኑ ደንበኛው
መክፍል የሚጠበቅበት የተጠቀስውን ዋጋ ብቻ ይሆናል፡፡
የአከፋፈል ሁኔታ
አንድ አግልግሎቱን ለማግኘት ፍላጎት ያለው ደንበኛ ከሚከፈለው የደሞዝ መጠን ላይ በሚሰራበት ድርጅት
ፋይናንስ በኩል ተቆራጭ ተደርጎ ለድጋፍ አነስተኛ ብድር አቅራቢ አ.ማ በባንክ ቋሚ ክፍያ ትዕዛዝ /standing
instraction/ ገቢ ይሆናል፡፡
ምሳሌ፡-
አቶ “ሀሁ” የተባለ ደንበኛ ከአማዞን ሱፍ በ 6500 ብር ሙሉ የሱፍ ልብስ ቢወስድ በስድሰት ወር ውስጥ
እዳውን ከፍሎ ማጠናቀቅ ይጠበቅበታል፡፡
ይህም “6500/6 = 1083 ብር” ለስድሰት ተከታታይ ወራት በየወሩ ከደሞዙ ተቆራጭ ተድርጎ በባንክ ቋሚ
ክፍያ ይከፍላል እንደማለት ነው፡፡
በተጨማሪም ድሞዛቸው አነስተኛ የሆነ ስራተኞች ይህንኑ ሙሉ የሱፍ ልብስ ዋጋ ለ 12 ወራት ማለትም
6500/12 = 541.67 ብር ብቻ ተቆራጭ አድረገው ክፍያቸውን ማጠናቀቅ ይችላሉ፡፡
ገፅ |5 https://digafmfi.et/
Access beyond Limits!
ሀ. አማዞን ጫማ
የአከፋፈል ሁኔታ
አንድ አግልግሎቱን ለማግኘት ፍላጎት ያለው ደንበኛ ከሚከፈለው የደሞዝ መጠን ላይ በሚሰራበት ድርጅት
ፋይናንስ በኩል ተቆራጭ ተደርጎ ለድጋፍ አነስተኛ ብድር አቅራቢ አ.ማ በባንክ ቋሚ ክፍያ ትዕዛዝ /standing
instraction/ ገቢ ይሆናል፡፡
ምሳሌ፡-
አቶ “ሀሁ” የተባለ ደንበኛ ከአማዞን ሱፍ በ 2500 ብር ጫማ ቢወስድ በስድሰት ወር ውስጥ እዳውን ከፍሎ
ማጠናቀቅ ይጠበቅበታል፡፡
ይህም “2500/6 = 416.67 ብር” ለስድሰት ተከታታይ ወራት በየወሩ ከደሞዙ ተቆራጭ ተድርጎ በባንክ ቋሚ
ክፍያ ይከፍላል እንደማለት ነው፡፡
በተጨማሪም ድሞዛቸው አነስተኛ የሆነ ስራተኞች ይህንኑ ሙሉ የሱፍ ልብስ ዋጋ ለ 12 ወራት ማለትም
2500/12 = 208 ብር ብቻ ተቆራጭ አድረገው ክፍያቸውን ማጠናቀቅ ይችላሉ፡፡
ለ. አማዞን ሽሚዝ
ይህ የአማዞን ሙሉ ልብስ ጥቅል ከሚይዛቸው አገልግሎቶች መካከል አንዱ ሲሆን ደንበኛው ከወለድ፣
ከአገልግሎት እና ከሕይወት መድኅን ተጨማሪ ክፍያዎች ነፃ የሆነ የ 1300 ብር የብድር አገልግሎት ማግኘት
የሚችል ይሆናል፡፡
የአከፋፈል ሁኔታ
ገፅ |6 https://digafmfi.et/
Access beyond Limits!
ደንበኛ ከአማዞን ሱፍ በ 1300 ብር ሸሚዝ ቢወስድ በስድሰት ወር ውስጥ እዳውን ከፍሎ ማጠናቀቅ
ይጠበቅበታል፡፡
ይህም “1300/6 = 216 ብር” ለስድሰት ተከታታይ ወራት በየወሩ ከደሞዙ ተቆራጭ ተድርጎ በባንክ ቋሚ ክፍያ
ይከፍላል እንደማለት ነው፡፡
በተጨማሪም ድሞዛቸው አነስተኛ የሆነ ስራተኞች ይህንኑ ሙሉ የሱፍ ልብስ ዋጋ ለ 12 ወራት ማለትም
1300/12 = 108.33 ብር ብቻ ተቆራጭ አድረገው ክፍያቸውን ማጠናቀቅ ይችላሉ፡፡
በእነዚህ ሁለት የዱቤ ልብስ አቅራቢ ድርጅቶች የሚቀርቡ አገልግሎቶች ሶሰት አይነት የዋጋ ደረጃ ያላቸው
ሲሆን ምንም አይነት ልዩ ቅናሽ ያልተደረገባቸው ናቸው፡፡
በዚህም መሰረት
1. 12000 ብር
2. 15000 ብር
o 15.5 % = ወለድ
ገፅ |7 https://digafmfi.et/