You are on page 1of 5

በአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር የኅብረት ሥራ ማኅበር ኤጀንሲ

ገብርኄር የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃላፊነቱ የተወሰነ ኅብረት ሥራ


ማኅበር
1. መግቢያ፡
ገብርኄር የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃላፊነቱ የተወሰነ ኅብረት ሥራ ማኅበር በማኅበረ ቅዱሳን መደበኛ
አገልጋዮች ተነሳሽነት ሐምሌ 30 ቀን 2011 ዓ.ም. በይፋ የተቋቋመ የኅብረት ሥራ ማኅበር ነው። ማኅበሩ
በመደበኛ አገልጋዮች ብቻ የሚወሰን ሳይሆን ሌሎች ማናቸውም በማኅበሩን ደንብና አሠራር ለመመራት
ፈቃደኛ የሆኑ ግለሰቦችን በማስገንዘብ፣ በርካታ አባላትን በማፍራት፣ የምጣኔ ሃብት ዐቅሙን በማሳደግ ልዩ
ልዩ ሥራዎችን ለመሥራት ያለመ ነው። በዚሁ መሠረት በማኅበረ ቅዱሳን ዋና ማዕከልና በልማት ተቋማት
አስተዳደር የሚገኙትን 197 ሠራተኞችን በአባልነት ያቀፈ ሲሆን ከታኅሣሥ 1 ቀን 2012 ዓ.ም. ጀምሮ
ሌሎች አባላትን ለማፍራት በመንቀሳቀስ ላይ ነው። ማኅበሩ አስፈላጊ መመዘኛዎችን በማሟላት ከአራዳ ክፍለ
ከተማ የኅብረት ሥራ ማኅበራት ጽ/ቤት የዕውቅና ምስክር ወረቀት በማግኘት ደረሰኞችና የቁጠባ ደብተሮች
አሳትሞና የባንክ ሒሳብ ቁጥር ከፍቶ ከጥቅምት ወር 2012 ዓ.ም. ጀምሮ ከአባላት ገንዘብ በመሰብሰብ ላይ
ይገኛል። እርስዎም የዚህ ኅበረት ሥራ ማኅበር አባል እንዲሆኑ በአክብሮት እንጋብዛለን።
2. የኅብረት ሥራ ማኅበሩ አገልግሎት ዓላማ
 ማኅበሩ የሚሰጠው ዓቢይ አገልግሎት ቁጠባና ብድር ይሆናል፡፡
 የብድሩ ዓቢይ ዓላማ ከአባላት ከፍተኛ ወለድ ለማሰባሰብና ትርፍ ለማግኘት ሳይሆን አባላት ጠቀም
ያለ ገንዘብ አግኝተው ላቀዱት ዓላማ እንዲያውሉትና ክፍያውም ሳይሰማቸውና በበጀታቸው ላይ
ተጽዕኖ ሳይፈጥር ከፍለው የሚጨርሱበትን መንገድ ለማመቻቸት ይሆናል፡፡
 ከዚህም ባሻገር ከልዩ ልዩ ድርጅቶችና ተቋማት ጋር በመነጋገር ለአባላት ተጨማሪ ብድር
ማመቻቸት፣ የቤት ዕቃዎችና ልዩ ልዩ ቁሳቁሶችን በረጅም ጊዜ ክፍያ እንዲያገኙ ማድረግ፣
አስፈላጊውን መስፈርት በማሟላት ማኅበራዊ ኃላፊነትን በጠበቀ መልኩ ንግድና ኢንቨስትመንት
ውስጥ መሰማራት፣ እና መሰል ሥራዎችን በማከናወን አባላትን ተጠቃሚ ማድረግ ተቀዳሚ ዓላማው
ነው።
3. የአባልነት መስፈርት
 በማኅበሩ መተዳደሪያ ደንብ፣ መመሪያዎችና ውሳኔዎች ለመመራት ፈቃደኛ የሆነ ማንኛውም ግለሰብ
አባል መሆን ይችላል።
 አንድ ሰው አባል ለመሆን የተዘጋጀው የአባልነት ቅጽ መሙላትና 2 ፎቶግራፍ መስጠት ይኖርበታል።
4. የአባልነት ግዴታዎች፡
 በማኅበሩ ስብሰባዎች ላይ መገኘት፣
 ከ1-150 የሚደርሱ ዕጣዎችን መግዛት
 በየወሩ መቆጠብ

ገብርኄር የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃላፊነቱ የተወሰነ ኅብረት ሥራ ማኅበር - ኅዳር ፳፻፲፪ ዓ.ም.
1
 የወሰደውን ብድር በተሰጠው የጊዜ ገደብ መመለስ፣
 የጠቅላላ ጉባኤና የሥራ አመራር ውሳኔዎችን ማክበር፣ ማስከበር፣
 በማኅበሩ ላይ የሚደርሰውን ኪሳራ በጋራ መክፈል፣
5. የመመዝገቢያ ክፍያ
 ለመሥራች አባላት የዕጣ መግዣ እና የክፍያ ጊዜ እስከ ኅዳር 30 ቀን 2012 ዓ.ም. ብቻ ነው።
 በመተዳደሪ ደንቡ አንቀጽ 15 መሠረት የመመዝገቢያ ክፍያ ለመሥራች አባላት እስከ ኅዳር 30 ቀን
2012 ዓ.ም. ድረስ ብር 50፣ መሥራች ላልሆኑ አባላት ከታኅሣሥ 1, 2012 ዓ.ም. ጀምሮ ብር 200
(ሁለት መቶ ብር) ነው።
 የመመዝገቢያ ክፍያ ለል ልዩ አስተዳደራዊ መጪዎች የሚውል በመሆኑ አባሉ ሲወጣ ተመላሽ
አይደረግም።
6. የዕጣ ግዢና ክፍያ፡
 አንድ አባል ከ1-150 ሃምሳ የሚደርሱ ዕጣዎችን እንዲገዛ ይጠበቃል። ይህ ማለት አንድ አባል
ቢያንስ 1 ዕጣ የመግዛት ግዴታ ያለበት ሲሆን ቢበዛ ደገሞ 150 ዕጣ የመግዛት መብት አለው።
 የአንድ ዕጣ ዋጋ ብር 200 ነው።
 የዕጣ ግዢ ክፍያ የሚጠናቀቀው ለመሥራች አባላት እስከ ኅዳር 30 ቀን 2012 ዓ.ም. (ከነሐሴ
2011 እስከ ኅዳር 30 2012 ዓ.ም. ድረስ ለ4 ወራት የቆየ) ሲሆን ከምሥረታ በኋላ ለሚመጡ
ከተመዘገቡበት ቀን ጀምሮ በአራት ተከታታይ ወራት ውስጥ ከፍለው ማጠናቀቀው አለባቸው።
 የዕጣ ክፍያ ተመላሽ የሚሆነው አባሉ ማኅበሩን ሲለቅ ብቻ ነው።
 የማኅበሩ ዕጣ መጠን የሚያገለግለው ለትርፍ ክፍፍል ነው። ይህም ማለት በርካታ ዕጣ የገዛ የትርፍ
ድርሻው ከፍ ያለ ሲሆን አነስተኛ ዕጣ የገዛ ደግሞ የሚያገኘው ድርሻ ዝቅተኛ ይሆናል ማለት ነው።
7. የክፍያ ሁኔታ፡
 የዕጣ ገንዘብ የሚከፈለው በባንክ ሒሳብ ቁጥር ገቢ በማድረግ ነው።
 ገንዘብ ገቢ የሚደረግበት የባንክ ሒሳብ ቁጥር “ለገብርኄር የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃላፊነቱ የተወሰነ
ኅብረት ሥራ ማኅበር፡ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ …. የቁጠባ ሒሳብ ቁጥር 1000 29600 7227 ወይም
ወጋገን ባንክ …. የቁጠባ ሒሳብ ቁጥር 0790 9539 30301” ነው።
 በማኅበረ ቅዱሳን ተከፋይ የሆኑ ሰዎች ከወራ ደመወዛቸው የተጣራ ገቢ ላይ ከፔሮል ተቀንሶ ወደ
ኅብረት ሥራ ማኅበሩ በስማቸው እንዲቀመጥ ፈቅደው ሲፈርሙ ተቀናሽ ሆኖ ገቢ ይሆናል።
 አባላት ገንዘብ በባንክ ገቢ ካደረጉ በኋላ ወደ ኅብረት ሥራ ማኅበሩ ገንዘብ ያዥ በመቅረብ ገቢ
ያደረጉበትን የባንክ ስሊፕ በመስጠት በምትኩ በኅብረት ሥራ ማኅበሩ ስም የታተመ የገቢ ደረሰኝ
መውሰድ ይኖርባቸዋል።
8. የክፍያ አመዘጋገብ
 ማንኛውም አባል ወደ ኅብረት ማኅበሩ ገቢ ላደረገው የዕጣም ሆነ የቁጠባ ገንዘብ ደረሰኝ መውሰድ
አበለት።

ገብርኄር የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃላፊነቱ የተወሰነ ኅብረት ሥራ ማኅበር - ኅዳር ፳፻፲፪ ዓ.ም.
2
 የኅብረት ሥራ ማኅበሩ አባል በስሙ የተመዘገበ የራሱ የቁጠባ ደርበት ይሰጠዋል።
 በዚህ ደብተር ላይ አባሉ የከፈለው የዕጣ ግዢና የቁጠባ ገንዘብ በየወሩ ይመዘገባል።
9. ቁጠባ፡
 በኅብረት ሥራ ማኅበሩ ሁለት የቁጠባ ዓይነት ያለ ሲሆን አንደኛው በየወሩ በቋሚነት የሚደረግ
የመደበኛ ቁጠበ ነው። ይህንን ቁጠባ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ማሳደግ እንጂ መጠኑን መቀነስ አይቻልም።
 ሌላው የቁጠባ ዓይነት የፈቃደኝነት ቁጠባ ሲሆን መጠኑ እንደ አባሉ ፍላጎት በየጊዜው ሊጨምርና
ሊቀንስ ይችላል።
 መደበኛ ቁጠባ ግዴታ ሲሆን የፈቃደኝነት ቁጠባ በአባሉ መልካም ፈቃድ የተወሰነ ነው።
 አንድ አባል ከተጣራ ገቢው ከ7% ወይም በገንዘብ ከ350 ብር ጀምሮ በየወሩ በቋሚነት መቆጠብ
አለበት።
 የመደበኛ ቁጠባ ገንዘብ ተመላሽ የሚሆነው አባሉ ማኅበሩን ሲለቅ ብቻ ነው። የፈቃደኝነት ቁጠባ ግን
ቁጠባው ከተጀመረበት ከ6 ወራት በኋላ አባሉ በጠየቀ ጊዜ ወጪ መሆን ይችላል።
10. ብድር መጠየቅ
 አንድ አባል ብድር መጠየቅ የሚችለው ለተከታታይ 6 ወራት ባለማቋረጥ ከቆጠበ ብቻ ነው።
 ብድር የሚፈልግ አባል ለብድር የተዘጋጀውን የማመልከቻ ቅጽ በመሙላት በ3 ቀናት ጊዜ ውስጥ
ለብድር ኮሚቴ ማቅረብ አለበት።
11. የብድር መፈቀድ
 የብድር ኮሚቴው የብድር ጥያቄው በቀረ በ15 ቀናት ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ ውሳኔ የመስጠት ግዴታ
አለበት።
 የብድር ኮሚቴው ያስተላለፈውን ውሳኔ ከ2 ቀናት ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ ለሥራ አመራር ኮሚቴው
ማስተላለፍ ይኖርበታል፡፡
 የሥራ አመራር ኮሚቴው የብድር ኮሚቴውን ውሳኔ በተረከበ 3 ቀናት ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ ብድሩን
ለተበዳሪው የመክፈል ግዴታ አለበት፡፡
 ብድር የተፈቀደለት አባል በ7 ቀናት ውስጥ ብድሩን ካልወሰደ ወይም ሌላ ስምምነት ካልፈረመ ብድሩ
ይሰረዛል፤ በዚህ ምክንያት የደረሰውን ኪሳራ እንዲከፍል ያደርጋል፡፡
 ከማኅበሩ አገልግሎት አባል አስተማማኝ ዋስትና እስከ አላቀረበ ድረስ መበደር የሚችለው ቁጠባውንና
የዕጣውን ድርሻ ብቻ ይሆናል፡፡
12. ብድር ማግኘት
 አንድ አባል ብድር ማግኘት የሚችለው የቆጠበውን 3 (ሦስት) እጥፍ ነው፡፡ ይህም ማለት 10,000
ብር የቆጠበ አባል ብር 30,000 ብድር ያገኛል።
 ከፍተኛው የብድር ጣሪያ ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር) ነው። ይህም ማለት 17,000 ብር እና
ከዚያ በላይ የቆጠበ አባል የሚያገኘው ብር 50,000 እንጂ የቆጠበው በ3 ተባዝቶ አይደለም። ይህ
የሚሆነው የበርካታ አባላትን ብድር የማግኘት ዕድል ለማስፋት በማሰብ ነው።

ገብርኄር የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃላፊነቱ የተወሰነ ኅብረት ሥራ ማኅበር - ኅዳር ፳፻፲፪ ዓ.ም.
3
13. ስለ ብድር አሰጣጥ
ማኅበሩ የሚሰጠው የብድር አገልግሎት የሚከተሉትን መሠረት ሐሳቦች ያገናዘበ መሆን ይገባዋል፡፡
 የአባሉ የገንዘብ አጠቃቀም ልምድ
 አባሉ የሚያቀርበው የዋስትና ብቃት
 የአባሉ የመክፈል ብቃትና ችሎታ
 የአባሉ ቁጠባና ዕጣ ድርሻ መጠን
 የማኅበሩ የገንዘብ አቅም የመሳሰሉትን ያካትታል
14. ብድር ለማግኘት የሚያበቁ ሁኔታዎች
 ለሕክምና
 በቤተሰብ ላይ ለሚደርስ ችግር
 ለቤት ሥራ፣ ግዥና ዕድሳት
 ለትምህርትና ሥልጠና
 ለንብረት ግዥና ዕድሳት
 ለቀለበትና ለሠርግ አገልግሎት
 ለመድህንና ዋስትና
 ኑሮን ለማሻሻል ለሚያስችሉ ምክንያቶች ይሆናል፡፡
15. ብድር ሊያስከለክሉ የሚያስችሉ ምክንያቶች፣
ማኅበሩ ከዚህ በታች በተጠቀሱት ምክንያቶች የብድር ጥያቄዎችን ለማስተናገድ አይገደድም፡፡
 በዕቅድና በዓላማ ላይ ያልተመሠረተ ሲሆን
 ትክክለኛና በቂ ባልሆነ ምክንያት የሚጠየቅ ብድር
 የታማኝነት መጓደል
 በቁጠባ ወደኋላ መቅረትና ማቋረጥ
 የመክፈል አቅም አለመመጣጠን
 ብድር ያለመክፈል የኋላ ታሪክ
 የዋስትና ብቃት ማነስ
 የጤና ሁኔታ
 ግዴታን አለመወጣት
 ከማኅበሩ ውጭ ሌላ ለሶስተኛ ወገን ብድር መጠየቅ
 በሌሎች ተመሳሳይ ምክንያቶች ብድር ሊከለከል ይችላል፡፡
16. የብድር ወለድ
a. ማኅበሩ ላበደረው ገንዘብ በዓመት 12% ወለድ ያስከፍላል፡፡
b. ወለዱ በየወሩ ከዋናው ብድር ክፍያ ጋር በአንድነት ተከፋይ ይሆናል፡፡

ገብርኄር የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃላፊነቱ የተወሰነ ኅብረት ሥራ ማኅበር - ኅዳር ፳፻፲፪ ዓ.ም.
4
c. የብድር ክፍያ ከነወለዱ በወሩ ውስጥ ተከፋይ ካልሆነ በቆየበት ቀናት መጠን ተጨማሪ ወለድ
ያስከፍላል፡፡
17. የብድር መመለስ
o አባሉ የወሰደውን ብድር ገንዘብ ከወሰደበት ጊዜ ጀምሮ በ48 ወራት (4 ዓመታት) ውስጥ
አጠናቅቆ የመመለስ ግዴታ አለበት፡፡
o ተበዳሪው ከተወሰነው የብድር ዘመን በፊት ከፍሎ ማጠናቀቅ ይችላል፡፡
o በድጋሚ አባል እንዲሆን የሚፈቅድለት አመልካች ብድር ለማግኘት እንደ አዲስ አመልካች
ለ6 ወራት በአባልነት መቆየት ይኖርበታል፡፡
o አንድ አባል ከማኅበሩ አገልግሎት ከመውጣቱ ሁለት ወራት በፊት ከማኅበሩ የተበደረውን
ገንዘብ ከፍሎ ማጠናቀቅ ይኖርበታል ወይም የዋሱ የመክፈል አቅምና አስተማማኝነት
መረጋገጥ ይኖርበታል፡፡
18. የብድር ጊዜ ስለማራዘም
 ተበዳሪው በብድር ክፍያ ጊዜ ከፍሎ ማጠናቀቅ ካልቻለ ጊዜው እንዲራዘምለት አሳማኝ ምክንያት
በማካተት በጽሑፍ ማመልከቻ መጠየቅ ይኖርበታል፡፡
 በመረጃ ሊረጋገጥ የሚችል ከአቅም በላይ የሆነ ችግር ካላጋጠመ በስተቀር የብድር መክፈያ ጊዜ
ሊራዘም አይችልም፡፡
 የብድር መክፈያ ጊዜ ሊራዘም የሚችለው እንደቀሪው የገንዘብ መጠንና የአከፋፈል ሁኔታ ይሆናል፡፡
 የብድር ክፍያ ጊዜ እንዲራዘም ሲፈቀድ አመልካች አዲስ ውል እንዲፈርም ያደርጋል፡፡
 የብድር ክፍያ ጊዜ እንዲራዘም ሲደረግ ዋሱ እንዲያውቀው ስለመስማማቱ በጽሑፍ ማረጋገጥ
ይኖርበታል፡፡
 የብድር ክፍያ ጊዜ ሊራዘም የሚችለው ከተፈቀደው የብድር ዘመን ውስጥ ለ36 ወራት ያለማቋረጥ
ለከፈለ አባል ሆኖ ከተወሰነው የብድር ዘመን ውስጥ ለ12 ወራት ብቻ ይሆናል፡፡
19. ተጨማሪ መረጃ

ኅብረት ሥራ ማኅበሩ በማኅበረ ቅዱሳን ዋና ማዕከል ሕንጻ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 206 የሚገኝ ሲሆን 5 አባላት
ያሉት የሥራ አመራር ኮሚቴ አዋቅሮ በመሥራት ላይ ይገኛል። ተጨማሪ መረጃ ማግኘት ከፈለጉ፣ ጥያቄ፣
አስተያየት፣ ጥቆማ ካለዎት የሚከተሉትን አድርሻዎች መጠቀም ይችላሉ።

1. ሰብሳቢ፡ ንጉሴ መብራቱ፡ 0912 100585፣ 2. ም፣ሰብሳቢ፡ ዲያቆን ደሳለኝ አበባው፡ 0911
707042፣ 3. ጸሐፊ፡ ደመላሽ አሰፋ፡ 0911 729654፣ 4. ሒሳብ ሹም፡ ካሳሁን ኃይሌ፡ 0911
898990፣ 5. ገንዘብ ያዥ፡ ለምለም መንግሥቴ፡ 0967 894062

ገብርኄር የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃላፊነቱ የተወሰነ ኅብረት ሥራ ማኅበር - ኅዳር ፳፻፲፪ ዓ.ም.
5

You might also like