You are on page 1of 6

ኢትዮ ወርልድ የማዕድን ሥራዎች ኃላፊነቱ

የተወሰነ የግል ማህበር


ETHIO WORLD MINING WORK
PLC

መተዳደርያ ደንብ

የካቲት/2013 ዓ/ም

ኢትዮ ወርልድ የማዕድን ሥራዎች ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር

ETHIO WORLD MINING WORK PLC


መተዳደርያ ደንብ

አንቀጽ 1 ጠቅላላ
ይህ መተዳደርያ ደንብ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር የመመስረቻ ፅሁፍ ጋር በአንድነት የማይነጣጠል
አካል ሆኖ ያገለግላል፡፡

ማህበሩ በኢትዮጵያ ንግድ ህግ ሁለተኛ መጽሐፍ ከቁጥር 510 እስከ 543 በተመለከቱ ድንጋጌዎች
የተቋቋመና በዚሁ መተዳደርያ ደንብና ተያይዞ በሚገኘው መመስረቻ ጽሁፍ የሚገዛ ኃላፊነቱ
የተወሰነ የግል ማህበር ነው፡፡ ስለሆነም በመተዳደርያ ደንብና በመመስረቻ ጽህፍ ያልተሸፈኑ ጉዳዮች
ሲያጋጥሙ በኢትዮጵያ የንግድ ህግ ውስጥ ስለ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር የተመለከተ
ድንጋጌዎች ተፈፃሚነት ይኖረዋል፡፡

አንቀጽ 2 ካፒታል ስለመጨመር


የማህበሩ ካፒታል በጥሬ ገንዘብ ብር 24,000,000/ሀያ አራት ሚሊዮን ብር ይህ ገንዘብ ሙሉ በሙሉ
በጥሬ ተከፍሏል፡፡

ከማህበሩ አባላት ቢያንስ የካፒታሉን ¾ ድርሻ የያዙት ሲስማሙ የኩባንያውን ካፒታል አንድ ጊዜ
ወይም ብዙ ጊዜ ማሳደግ ይቻላል፡፡ በዚህ ጊዜ አክሲዮኖች በተጨማሪነት የሚመደቡት ማህበርተኞች
ቀደም ሲል በነበራቸው የአክሲዮኑች ድርሻ መጠን ልክ ይሆናል፡፡ የካፒታል ጭማሪ በኢትዮጵያ ንግድ
ህግ በሚፈቅደው በማንኛውም መንገድ መሆን ይችላል፡፡

አንቀጽ 3 አክሲዮኖች
አክስዮኖች በአባላት መካከል ያለምንም ገደብ ሊተላለፉ ይችላሉ፡፡ እንዲሁም የሟች አባል አክስዮኖች
ያለምንም ገደብ ወራሽነታቸዉን ላረጋገጡ ወራሾች ይተላለፋል፡፡

አክስዮኖች ከማህበሩ ዉጭ ላለ ሰዉ ማስተላለፍ የሚቻለዉ በቅድሚያ ቢያንስ ቢያንስ ከማህበሩ


ካፒታል ¾ የያዙትን አባላት ስምምነት ማግኘት ሲቻል ነዉ፡፡ የአባላቱ ስምምነት ካልተገኘና አክስዮን
ማስተላለፍ የፈለገዉ አባል በሀሳብ ከፀና ለሽያጭ የቀረበዉን አክስዮን የመግዛት ቅድሚያ የሚሰጠዉ
ከአባላቱ መካከል ቀደምት ለሆነዉ ይሆናል፡፡ ከአንድ በላይ ቀደምትነት ያላቸዉ ሰዎች አከስዮን
ለመግዛት ያላቸዉን ቅድሚያ መብት ለመጠቀም የፈለጉ እንደሆነ ባላቸዉ የአክስዮን ድርሻ መሰረት
እንዲገዙ ይደረጋል፡፡

ከላይ በተመለከተዉ ሁኔታ የተደረገዉ የአክስዮን ማስተላለፍ በፅሁፍ መሆን ያለበት ሲሆን በአክስዮን
መዝገብ ካልተመዘገበ ዋጋ አይኖረዉም፡፡

አንቀጽ 4 የማህበሩ አባላት መብትና ግዴታዎች


4.1. እያንዳንዱ አባል የሚከተሉት መብቶች ይኖሩታል፡፡

ሀ/ በማናቸዉም አባላት ስብሰባ ላይ የመካፈል


ለ/ በማናቸዉም ስብሰባ ላይ በያዘዉ የአክስዮኖች ብዛት መጠን ድምጽ የመስጠት

ሐ/ በዋናዉ መ/ቤት ዉስጥ ያሉ የቆጠራ ዉጤቶችን የወጪና የገቢ መዝገቦችን የኦዲተር ሪፖርቶች
የመመርመር መዝገብ የመያዝ

መ/ በህግ በማህበር መመስረቻ ጽሁፍና መተዳደሪያ ደንብ የተመለከቱትን መብቶች የመጠቀም

4.2. ከላይ የተመለከተዉ ያአባላት መብት እንደተጠበቀ ሆኖ

ሀ/ ማህበሩ ለአንድ አክስዮን ከአንድ በላይ ባለንብረት አይቀበልም፡፡ ስለሆነ በዚህ መሰረት የአክስዮን
የጋራ ባለንብረቶች ቢኖሩ የአባልነት መብታቸዉን ሲጠቀሙበት የሚችሉት ከመካከላቸዉ አንድ
እንደራሴ በመሾም ብቻ ነዉ፡፡

ለ/ ከአክስዮኖች ጋር የተያያዙ መብቶች አክስዮኑን ይከታተላሉ፡፡ የአክስዮን ባለቤት በመሆን የተፈጥሮ


ሰዉም ሆነ በህግ የሰዉነት መብት የተሰጠዉ አካል በደንቡ መሰረት መብቶቹ ሊገለገል ይችላል፡፡
በአንጻሩም የአክስዮን ባለቤት መሆን ለዚህ መተዳደሪያ ደንብ ለመመስረቻ ጽሁፍና በአግባቡ
ለሚተላለፉ የአባላት ዉሳኔዎች ተገዥ የመሆን ዉጤት ያስከትላል፡፡

ሐ/ የሟች ማህበርተኛ ወራሾችም ሆኑ ወኪሎች በማህበሩ ንብረቶች ላይ ማህተም እንዲደረግ ወይም


እንዲታሸግ የማድረግ መብት አይኖራቸዉም፡፡ስለሆነም መብታቸዉን በሚጠቀሙበት ግዜ ሁሉ
የመመስረቻ ጽሁፍ የመተዳደሪያ ደንብና በአግባቡ የሚተላለፉ የማህበርተኛ ዉሳኔዎች ሁሉ በእነሱ ላይ
ተፈጻሚነት አላቸዉ፡፡

አንቀጽ 5 ያለ ስብሰባ ስለሚተላለፉ ዉሳኔዎች


ጉባኤ እንዲሰበሰብ ህግ ወይም ማህበሩ መተዳደርያ ደንብ በሚያስገድድበት ጊዜ ዋናው ሥራ
አስኪያጅ ድምጽ ሊሰጥበት ተፈለገውን ጉዳይ ለእያንዳንዱ አባል በጽሁፍ በመላክ በጉዳዩ ላይ አባላት
በጽሁፍ ድምፅ እንዲሰጡበት መጠየቅ አለበት፡፡

አንቀጽ 6 ስብሰባዎች
6.1 የማህበሩ የሂሳብ ዓመት ከተዘጋ በ 1 ወር ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ የማህበሩ ጠቅላላ ጉባኤ መጥራት
አለበት፡፡

6.2 ዋናው ሥራ አስኪያጅ ዓመታዊ የማህበርተኞች ስብሰባ ከመደረጉ በፊት ሃያ ቀን ባላነሰ ጊዜ


አስቀድሞ ለአባላት በአደራ ደብዳቤ ስብሰባ ጥሪ ማሳወቅና ለውሳኔ ወይም ለውይይት ቀረበው ሃሳብ
ምን እንደሆነ በግልጽ ማስረዳት አለበት፡

6.3. ኦዲተሩ ወይም ዋናው ገንዘብ ከግማሽ በላይ የሚወከሉ ማህበርተኞች በማንኛውም ጊዜ የማህበሩ
ጠቅላላ ጉባኤ እዲሰበሰብ ሊያደርግ ይችላል፡፡

አንቀጽ 7 ምልዓተ ጉባኤ


የማህበሩ ስብሰባ ሊካሄድ የሚችለው ከዋናው ገንዘብ ¾ በላይ ያላቸውን የሚወክሉ ማህበርተኞች
ስብሰባው ላይ ሲገኙ ነው፡፡

በዚህ ዓይነት ስብሰባዎች ላይ ውሳኔዎች የሚተላለፉት በድምፅ ብልጫ ይሆናል፡፡

አንቀጽ 8 ዋና ሥራ አስኪያጅ
ከማህበሩ የንግድ አላማ ጋር በተያያዘ መልክ በማህበሩ ጠቅላላ ጉባኤ ውሳኔዎች መሠረት
የሚከተሉትን ተግባራት የማከናወን ስልጣን አለው፡-

1. የዘርፉ ሥራ አስኪያጆችን ይሾማል ይሽራል፤ተግባራቸውን ዘርዝሮ ይሰጣል ይቆጣጠራል፡፡


2. ማህበሩን በመወከል ይፈርማል
3. ለማህበሩ ቴክኒካዊና አስተዳደራዊ ተግባሮች ኃላፊ ነው
4. የጠቅላላ ጉባኤውን የቦርዱን ውሳኔዎች ሥራ ላይ ያውላል
5. ለማህበሩ የሚከፈል ገንዘብ መቀበል፤የማህበሩን ዕዳዎች መክፈል ማናቸውንም ሀዋላ
ወረቀት፤የተስፋ ሰነድ የባንክ ሰነድ ማዘጋጀትና በጀርባው ላይ መፈረም ማደስና መክፈል
እንዲሁም የጭነት ማስታወቂያ ደረሰኞችን የቦርድ ሰረተፊኬቶችን ወይም ማናቸውንም
ሰነዶች ማጽደቅና ከጀረባው መፈረም
6. የማህበሩን ወኪል ወይም ሠራተኛ ይቀጥራል፤ያሰናብታል፤ክፍያውን፤ደመወሁን ፤ጉርሻዎችንና
ሌሎች ከመቀጠርና ከመሰናበት ጋር የተያያዙ ሁኔታዎችን ይወስናል፡፡
7. በማህበሩ ሥም የባንክ ሂሳቦችን ከፍቶ ገንዘብ ገቢ ያደርጋል ሂሳቦቹን በፊርማው
ያንቀሳቅሳል::
8. ለማህበሩ ንግድ በመልካም ሁኔታ መካሄድ የሚጠቅሙ ግዢዎችን፤ሽያጮችንና የነዚህን
ማዘዣዎችን ይወስናል፡፡
9. ከማህበሩ ንግድ ጋር የተያያዙ ማናቸዉንም የንግድ ልዉዉጥ በተመለከተ ከሶስተኛ ወገኖች
ጋር ዉል ይዋዋላል፡፡
10. በማናቸዉም ፍርድ ቤት ማህበሩ ከሳሽ ተከሳሽ ወይም ጣልቃ ገብ በሚሆንበት ጉዳይ
ሁሉ ማህበሩን በመወከል አስፈላጊዉን ይፈጽማል፡፡
11. ማህበርተኞች ሊቀበሉትና ሊያፀድቁት እንዲችሉ የሂሳብ ወጪና የገቢ መዝገብ በደንቡ
እንዲያዝ አስፈላጊዉን እርምጃ ይወስዳል፡፡
12. የማህበሩ አላማ ግቡን እንዲመታ አስፈላጊ መስሎ በታየዉ ጊዜ ከላይ ከተገለጹት
ተግባራት መሀል ማናቸዉንም በሌላ ሦስተኛ ሰው እንዲፈጽሙ በማህበሩ ስም ውክልና
ሊሰጥ ይችላል ፡፡

አንቀጽ 9 ምክትል ሥራ አስኪያጅ ሥልጣንና ተግባራት


1. የማህበሩ ዋና ሥራ አስኪያጅ በሌለበት ተክቶ ይሠራል፡፡

2. ማህበሩ በመወከል በማንኛዉም መ/ቤት ስብሰባ ቦታ ይገኛል፡፡

3. ማህበሩ ለማሳደግ ይጠቅማሉ የሚላቸዉ ሀሳቦች በማመንጨት ከዋና ሥራ አስኪያጅ ጋር


በመወያየት ለአባላት በሙሉ በማሳወቅ ዉሳኔዉን ተግባር ላይ ያዉላል፡፡
አንቀጽ 10 የገንዘብ ያዥ ሥልጣንና ተግባራት
1. የማህበሩ ማንኛዉም ወጪና ገቢ በመመዝገብ ዓመታዊ ሪፖርት ያቀረባል፡፡

2. የማህበሩ ማንኛዉም ወጪና ገቢ በማመዛዘን ትርፍና ኪስራ ለይቶ ያወጣል፡፡


3. ለአባላቱ በማሳወቅ ዉይይት መድረኮች ተመቻችቶ የተለያዩ ሀሳቦች እንዲቀረቡ እና እንዲፈፀሙ
ያደረጋል፡፡

አንቀጽ 11 የጠቅላላ ጉባኤ ስልጣን


የማህበሩ ዋና ስራ አስኪያጅ መግለጫ ሰምቶ ተቀባይነት ያለዉ ሆኖ ካገኘዉ ያፀድቃል፡፡

የማህበሩ ሂሳብ ተቆጣጣሪ/ኦዲተር/ዓመታዊ መግለጫ መርምሮ ተገቢዉን አርምጃ ይወስዳል፡፡

የማህበሩ ዋና ስራ አስኪያጅ ይሾማል በቂ ምክንያት ሲኖር በንግድ ህግ ቁጥር 527 በተደነገገዉ መሰረት
ይሸራል፡፡

ለዋና ስራ አስኪያጅ ሊከፈል የሚገባዉ የአገልገሎት ዋጋ ይወስናል፡፡ በዚህ ስብሰባ ዋናዉ ስራ አስኪያጅ
አባል ቢሆንም ይከፈለዋል፡፡

የማህበሩን የስራ አፈፃፀም በመመልከት ለዋናዉ ስራ አስኪያጅ መመሪያ ይሰጣል::

ስለዓመታዊ ትርፍ ዉሳኔ ይሰጣል፡፡

አንቀፅ 12 የማህበሩ የበጀት የሂሳብ መግለጫ ህጋዊ የመጠባበቂያ ገንዘብ


10.1.የማህበሩ የሂሳብ ዓመት በየዓመቱ ከሰኔ 1 ቀን እስከ ሰኔ 30 ቀን ይፈፀማል፡፡ስለሆነም የመጀመሪያ
ሂሳብ ዓመት የመመስረቻ ጽሁፍና ይህ የመተዳደሪያ ደንብ ከተፈፀመ ቀን ጀምሮ እስከ 30 ቀን ድረስ
ይሆናል፡፡

10.2.በሂሳብ አመት መጨረሻ የማህበሩን ንብረቶች የሚያሳይ ሚዛን በዋናዉ ማህበርተኞች


ይተላለፋል፡፡

10.3.የማህበሩ ዓመታዊ ሁኔታ የሂሳብ ሚዛን የትርፍና ኪሳራ ሁኔታ የንብረት በየጊዜዉ ለአባላት
ይላካል፡፡

10.4. በንግድ ህጉ አንቀጽ 539 እንደተደነገገዉ በተጣራዉ ትርፍ ላይ በየአመቱ መጠባበቂያ የሚሆነዉ
ቢያንስ አምስት በመቶ /5%/ እየተነሳ ይቀመጣል፡፡ይኸዉ መጠባበቂያ ከማህበሩ ዋና ገንዘብ አንድ
አስረኛ እጅ ሲደርስ ግዴታ መሆኑ ይቋረጣል፡፡

አንቀጽ 13 ስለ ማህበሩ መፍረስ


ማህበሩ በንግድ ሕግ ቁጥር 217፣218፣511፣542 እና 543 መሰረት በቂ በሆነ ምክንያት በፍርድ ቤት
ዉሳኔ ይፈርሳል፡፡

አንቀጽ 14 ደንቡ ስለሚሻሻልበት ሁኔታ


ይህ ደንብ ከማህበሩ ዋና ገንዘብ 3/4 ኛ ድርሻ ባላቸዉ አባላት ድምጽ ብልጫ ሊሻሻል ይችላል፡፡

አንቀጽ 15 ደንቡ የሚፀናበት ጊዜ


ይህ ደንብ ማህብሩን መርምሮ የመመዝገብ ስልጣን በተሰጠዉ አካል ፊት ቀርቦ ከተመዘገበበት ቀን
ጀምሮ የፀና ይሆናል:፡

የመስራች አባላት ስም ዝርዝር

ተ.ቁ ስም ከነአያት ዜግነት አድራሻ ፊርማ


ክልል ዞን ወረዳ ቀበሌ
1 ኢ/ያዊ

2 ኢ/ያዊ

3 ኢ/ያዊ

You might also like