You are on page 1of 4

ኢትዮ ወርልድ የማዕድን ሥራዎች ኃላፊነቱ

የተወሰነ የግል ማህበር


ETHIO WORLD GENERAL
MINING WORK PLC

የመመስረቻ ጽሑፍ

የካቲት/2013 ዓ/ም

አንቀጽ .1 ምሰረታ
በሰነዱ ግርጌ ፊርማቸውን ባሰፈሩት መካከል በኢትዮጵያ ንግድ ህግ በዚህ የመመስረቻ ጽሁፍና ተያይዞ
በሚገኘው የመተዳደርያ ደንብ ስምምነት የሚገባና አላማውም ከዚህ በታች አንቀጽ 4 ስር የንግድ ሥራ
ተግባራት ማከናወን የሆነ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ለመመስረት ስምምነት ተደርጓል፡፡
አንቀጽ .2 የአባላቱ ስምና ዜግነትና አድራሻ
ተ.ቁ ስም ከነአያት ዜግነት አድራሻ ፊርማ
ክልል ዞን ወረዳ ቀበሌ
1 ኢ/ያዊ

2 ኢ/ያዊ

3 ኢ/ያዊ

አንቀጽ .3 የማህበሩ ስምና ዋና መሥሪያ ቤት


3.1. የማህበሩ ሥም፡- ኢትዮ ወርልድ አጠቃላይ የማዕድን ሥራዎች ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል
ማህበር/በአማረኛ/ETHIO WORLD MINING WORK PLC/በእንግሊዘኛ/ተበሎ ይጠራል፡፡

3.2.አባላቱ ወደፊት በሌሎች ከተሞች ቅርንጫፍ የመክፈት መብታቸው እንደተጠበቀ ሆኖ የተመዘገበው

3.3. የማህበሩ ዋና መ/ቤት አሶሳ ከተማ ቀጠና 04 ዉስጥ ነው፡፡

አንቀጽ .4 የማህበሩ የንግድ ሥራ ዓላማዎች


1. አጠቃላይ ማዕድን ማምረት ንግድ ሥራ ዘርፍ ላይ በመሰማራት መሽጥና እንዲሁም በመግዛት ለገበያ
በማቅረብ ማሳተፍ
2. በራስ በመተማመን ማጎልበትና በመንግስት ጎን በመስለፍ ኢኮኖሚን መገንባት
3. ምርትና ምርታማነት በማሳደግ ለአካባቢዉ ህብርተስብ በማዕድን ማምረት ሥራ የተሻለ እና አጠቃቀም
ዘመናዊ በማድረግ ለአካባቢዉ አርአያ በመሆን
4. ለድርጀቱ ልማታዊ ቦታ የአካባቢዉ ህብርተስብ እንደያአስፈላጊነቱ በማህበራዊና በኢኮሚያዊ ጉዳዮች ዘርፍ
ንቁ ልማታዊ ተሳትፎ በማድረግ፡፡
አንቀጽ .5 ካፒታል
የማህበሩ ካፒታል ብር 24.000.000/ሀያ አራት ሚሊዮን ብር/ ሲሆን ይኸው ገንዘብ በጠቅላላው በጥሬ ገንዘብ
በአባላቱ ጠቅላላው ካፒታል እያንዳንዱ ብር 6.000.000/ ስድስት ሚሊዮን ብር ዋጋ ብቻ ብዛት
3/ሦስት/አክሲዮኖች ተከፋፍሏል፡፡ በመስራች አባላት የተያዘው የአክሲዮን መጠን የሚከተለው ነው፡፡

ተቁ ስም ከነ አያት የአክስዮን ያንዱ የተከፈለ ጠቅላላ ወጪ ምርም


ብዛት የአክስዮን ገንዘብ ራ
ዋጋ
1. 1 6.000.000 6.000.000 6.000.000
2. 1 6.000.000 6.000.000 6.000.000

3. 1 6.000.000 6.000.000 6.000.000

ጠቅላላ ድምር 3 24,000,000 24,000,000


አንቀጽ .6 የአባላቱ ኃላፊነት
አባላቱ ላይ የተጠቀሰውን ካፒታል በጥሬ ገንዘብ እና በዓይነት ብር 24,000.000/ሀያ አራት ሚሊዮን ብር ብቻ/
ብር የተከፈለ መሆኑን በአንድነት እና በነጠላ አረጋግጠዋል፡፡ ስለሆነም የአባላቱ ኃላፊነት በማህበሩ ውስጥ
ባላቸው አክስዮን መጠን የተወሰነ ነው፡፡

አንቀጽ . 7 የትረፍና ኪሳራ ከፍፍል


አባላቱ በተለየ ሁኔታ ካለተስማሙ በስተቀር ከጠቅላላው ዓመታዊ ትርፍ ህጋዊ የመጠባበቂያ ገንዘብና
እና ሌሎች ጠቅላላ ወጪዎች ከተቀነሰ በኋላ ቀሪው በአባላቱ መካከል እንደ አክሲዮን ይዞታቸው ይከፋፈላል፡፡
ሆኖም በማንኛውም ሁኔታ አባላቱ በማህበሩ ውስጥ ካለው የአክሲዮን ካፒታል በላይ ተጠያቂ ሊሆን
አይችልም፡፡

አንቀጽ . 8 የሥራ አመራር


የማህበሩ ሥራ ስልጣንና ተግባርሩ በመተዳደሪያ ደንቡ በዝርዝር የተመለከተ ሲሆን ከአባላቱ መካከል ወይም
ከውጭ አባላቱ በሚመረጥ የስልጣኑ ዘመን 2 ዓመት በሆነ በአንድ ዋና ሥራ አስኪያጅ ይመራል፡፡

8.1. የዘርፍ ሥራ አስኪያጅ ይሾማል፤ይሽራል ተግባራቸውን ዘርዝሮ ይሰጣል፤ይቆጣጠራል፤

8.2. የማህበሩ ዋና ሥራ አስኪያጅ ሥራ ዘመናቸው ሲያለቅ በድጋሚ ሊመረጡ ይችላሉ፤

8.3. የማህበሩ ዋና ሥራ አስኪያጅ እንደ አስፈላጊነቱ የሚሾሙ የዘርፍ ሥራ አስኪያጆች ሊኖሩት ይችላል፡፡

8.4. ማህበሩን በመወከል ይፈርማል

8.5. ለማህበሩ ቴክኒካዊ አስተዳደራዊ ተግባሮች ኃላፊ ነው

8.6. የጠቅላላ ጉባኤውንና ቦረዱን ውሳኔዎች ሥራ ላይ ያውላል

8.7. ለማህበሩ የሚከፈል ገንዘብ መቀበል፤የማህበሩን እዳ መክፈል፤ማንኛውም የሀዋላ ወረቀት፤የተስፋ


ሰነ፤የባንክ ሰነድ ማዘጋጀትና በጀርባው ላይ መፈረም፤ሰነዶች ማጽደቅና ከጀርባው መፈረም

8.8. የማህበሩ ወኪል ወይም ሠራተኛ ይቀጥራል፤ክፍያውን፤ደመወዙን፤ጉረሻውን እና ሌሎች ከመቅጠርና


ከመሰናበት ጋር የተያያዙ ሁኔታዎችን ይወስናል፤

8.9. በማህበሩ ስም የባንክ ሂሳብ ከፍቶ ገንዘብ ገቢ ያደርጋል፡፡ሂሳብ በፊረማው ያንቀሳቅሳል


8.10. የማህበሩን ሥራ በመልካም ሁኔታ ማካሄድ የሚጠቅሙ ግዥዎችን ሽያጭና የነዚህን ማዘዣዎች
ይወስናል፡፡
8.11. ከማህበሩ ሥራ ጋር የተያያዙ ማንኛውም የንግድ ልውውጥ በተመለከተ ከሦስተኛ ወገን ጋር ውል
ይዋዋላል፡፡
8.12. በማንኛውም ፍርድ ቤት ማህበሩ ከሳሽ ተከሳሽ ወይም ጣልቃ ገብ በሚሆንበት ጉዳይ ሁሉ ማህበሩን
በመወከል አስፈላጊውን ይፈጽማል፡፡
8.13. ማህበርተኞቹ ሊቀበሉትና ሊያጸድቁት እንዲችሉ የሂሳብ ወጪና ገቢ መመዝገብ በደንብ እንዲያዝ
አስፈላጊውን አርምጃ ይወስዳል፤የማህሩ ዓላማ ግቡን እንዲመታ አስፈላጊ መስሎ በታየ ግዜ ከላይ
ከተገለፀው ተግባራት መሀል ማናቸውንም በሌላ ሶስተኛ ሰውእንዲፈፀም በማህበሩ ስም ውክልና
መስጠት ይችላል፡፡

አንቀጽ 9 ምክትል ሥራ አስኪያጅ ሥልጣንና ተግባራት


1. የማህበሩ ዋና ሥራ አስኪያጅ በሌለበት ተክቶ ይሠራል፡፡

2. ማህበሩ በመወከል በማንኛዉም መ/ቤት ስብሰባ ቦታ ይገኛል፡፡

3. ማህበሩ ለማሳደግ ይጠቅማሉ የሚላቸዉ ሀሳቦች በማመንጨት ከዋና ሥራ አስኪያጅ ጋር


በመወያየት ለአባላት በሙሉ በማሳወቅ ዉሳኔዉን ተግባር ላይ ያዉላል፡፡

አንቀጽ 10 የገንዘብ ያዥ ሥልጣንና ተግባራት


1. የማህበሩ ማንኛዉም ወጪና ገቢ በመመዝገብ ዓመታዊ ሪፖርት ያቀረባል፡፡

2. የማህበሩ ማንኛዉም ወጪና ገቢ በማመዛዘን ትርፍና ኪስራ ለይቶ ያወጣል፡፡


3. ለአባላቱ በማሳወቅ ዉይይት መድረኮች ተመቻችቶ የተለያዩ ሀሳቦች እንዲቀረቡ እና እንዲፈፀሙ
ያደረጋል፡፡

አንቀጽ .11 ኦዲተር


ማህበሩ በአባላቱ የሚመረጡ ኦዲተር/ኦዲተሮች /ይኖሩታል፡፡

አንቀጽ .12 የማህበሩ የስራ ዘመን


አባላቱ በተለየ ሁኔታ የመወሰን መብት እንደተጠበቀ ሆኖ ማህበሩ የተቋቋመው ላልተወሰነ ጊዜ ነው፡፡

የመስራች አባላት ስምና ፊርማ


ተ.ቁ ስም ከነአያት ዜግነት አድራሻ ፊርማ
ክልል ዞን ወረዳ ቀበሌ
1 ኢ/ያዊ

2 ኢ/ያዊ

3 ኢ/ያዊ

You might also like