You are on page 1of 7

--------------- ህብረት ሽርክና ማህበር

------------------ P.L.C
የመመስረቻ ጽሑፍ

አንቀጽ አንድ
ምስረታ

በሰነዱ ግርጌ ፊርማቸውን ባሰፈሩት መካከል በኢትዮጵያ ንግድ ሕግ በዚህ የመመስረቻ ጽሑፍ ስምምነቶች
የሚገዛና ዓላማውም ከዚህ በታች በአንቀጽ 4 ስር የተመለከቱትን የንግድ ስራ ተግባራትን ማከናወን የሆነ የ
ኃ/የተ/የግ/ማኅበር/ P.L.C/ ለመመስረት ስምምነት ተደርጓል፡፡

አንቀጽ ሁለት
የማኅበርተኞች ስም፣ ዜግነትና አድራሻ

አድራሻ
ተ.ቁ የማኅበርተኛው ሙሉ ስም ዜግነት ክልል ክ/ከተማ ወረዳ የቤት
ቁጥር
1 አቶ
2 ወ/ሮ ------------------
በትውልድ ኢትጵያዊ ፓስፖርት ቁጥር ------------------
3 ወ/ት ኢትዮጵያዊ

አንቀጽ ሦስት
የማኅበሩ ስም እና ዋና መሥሪያ ቤት

3.1. የማኅበሩ ሥም የህብረት ሽርክና ማህበር ነው፡፡ የማኅበሩ ዋና


መሥሪያ ቤት በአዲስ አበባ ከተማ ክ/ከተማ ወረዳ የቤት ቁጥር ውስጥ
የሚገኝ ሲሆን እንደ አስፈላጊነቱም በኢትዮጵያ ውስጥ ወይም ከኢትዩጵያ ውጭ ቅርንጫፍ መሥሪያ
ቤቶች ሊኖሩት ይችላል፡፡

አንቀጽ አራት
የማኅበሩ የንግድ ሥራ ዓላማዎች
ማህበሩ የተቋቋመበት ዓላማዎች፡- ከዚህ ስር ማህበሩ የሚሰማራባቸውና ወደፊት ሊሰማራባቸው
የሚችሉበትን የስራ ዘርፎች ይዘረዘራሉ፤
4.1 ---------
4.2 ---------
4.3 ---------
4.4 ---------
4.5 ---------
4.6 --------
4.7 --------
4.8 --------
4.9 --------

4.10.---------

44.11.-------- ወ.ዘ.ተ.

አንቀጽ አምስት
የማኅበሩ ካፒታል እና የአክሲዮን ድልድል
5.1 የማኅበሩ ካፒታል ብር ሲሆን ይህም ገንዘብ በጠቅላላ በጥሬ ገንዘብ
በአባላቱ ተከፍሏል፡፡ (የዓይነት መዋጮ ካለ እንዲካተት ይደረጋል) የአንድ ማህበርተኛ መዋጮ ዋጋ ብር
ዋጋ ባላቸው መዋጮዎች ተከፋፍሏል፡፡
በዚህም መሰረት የመዋጮው ድልድሉ እንደሚከተለው ነው፡፡

ተ.ቁ የማኅበርተኞች ሙሉ ስም ጠቅላላ መዋጮ


1 አቶ
2 ወ/ሮ
3 ወ/ሪት

ድምር

አንቀጽ ስድስት
የማህበርተኞቹ ኃላፊነት
6.1. አባላቱ ከላይ የተጠቀሰው ካፒታል በጥሬ ገንዘብ በሙሉ የተከፈለ መሆኑን በአንድነት እና በነጠላ
አረጋግጧል፡፡ ስለሆነም የማህበርተኞቹ ኃላፊነት በማኅበሩ ውስጥ ባላቸው መዋጮ ድርሻ ዋጋ ልክ
የተወሰነ ይሆናል፡፡

አንቀጽ ሰባት
የትርፍና ኪሳራ ክፍፍል
ማህበሩ የሚያገኘው የተጣራ ትርፍ ለማህበርተኞች የሚከፈለው እያንዳንዳቸው በማህበሩ ላይ ባሏቸው መዋጮ ብዛት
ላይ በመመስረት ነው፡፡ በተመሣሣይ ሁኔታ ማህበሩ ኪሣራ ከገጠመው ኪሣራው በማህበርተኞቹ የመዋጮ ይዞታ መጠን
ይከፋፈላል፣ ኪሳራ ካጋተመ አባላቱ በማህበሩ ውስጥ ካለው ካፒታል በላይ ተጠያቂ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡በአባላቶች
ስምምነት ትርፉ ለድርጅቱ ስራ ሊውል ይችላል፡፡

አንቀጽ ስምንት
የማህበሩ ስራ አስኪያጅ ተግባረና ሀላፊነት
የማህበሩ ሥራ አስኪያጅ ሥልጣንና ተግባሩ በዚህ የመመስረቻ ጽሁፍ ሰነድ ላይ በዝርዝር የተመለከቱ ከአባላቱ
መካከል ወይም ከውጭ በአባላቱ በሚመረጥ፣ የሥልጣን ዘመኑ ላልተወሰነ በሆነ አንድ ዋና ሥራ አስኪያጅ
ይመራል፡፡ በዚህ መሠረት አቶ/ወ/ሮ/ት የመጀመሪያ የማኀበሩ ዋና ሥራ
አስኪያጅ እንዲሁም አቶ/ወ/ሮ/ት የማህበሩ ም/ሥራ አስኪያጅ ሆነው ተመርጠዋል፡፡

8.1. የዘርፍ ሥራ አስኪያጅ ይሶማል፣ ይመራል፣ ተግባራቸው በዝርዝር ይሰጣል ይቆጣጠራል፡፡

8.2. የሥራ አስኪያጅ የሥራ ዘመን ላልተወሰነ ጊዜ ይሆናል፣


8.3. ማህበሩን በመወከል በማናቸውም ሰነዶች ላይ ይፈርማል፣
8.4. ለማህበሩ ቴክኒካዊና አስተዳደራዊ ተግባሮች ኃላፊ ነው፣
8.5. የጠቅላላ ውሳኔዎች ስራ ላይ ያውላል፣
8.6. ለማህበሩ የሚከፈል ገንዘብ መቀበል የማህበሩን ዕዳዎች መክፈል ማናቸውንም የሐዋለ ወረቀት፣ የተስፋ
ሰነድ፣ የባንክ ሰነድ ማዘጋጀትና በጀርባ ላይ መፈረም፣ ማደስና መክፈል በማህበሩ ስም የጨረታ
ማስታወቂያ ደረሰኞች፣ የቦንድ ሰርተፍኬቶችን ወይም ማናቸውንም ሰነዶች ማጽደቅና መፈረም፣

8.7. የማህበሩን ወኪል ወይም ሰራተኞች ይቀጥራል፣ ያሰናብታል፣ ክፍያውን ደሞዙን ጉርሻና ሌሎት ከመቅጠርና
ከማሰናበት ጋር የተያያዙ ሁኔታዎችን ይወስናል፣

8.8. የማህበሩ ዋና ስራ አስኪያጅ በማህበሩ ስም የባንክ ሂሳቦችን ይከፍታል፣ በተከፈተው አካውንት ገንዘብ ገቢና
ወጪያደርጋል፣ ሂሳቦችን በፊርማው ያንቀሳቅሳል፣ ቼክ ላይ ይፈርማል፣

8.9. ለማህበሩ ንግድ በመልካም ሁኔታ መካሄድ የሚጠቅሙ ግዢዎችን ሽያጭና የእነዚህ ማዘዣዎች ይወስናል፣

8.10. ከማህበሩ ንግድ ጋር የተያያዙ ማናቸውንም ንግድ ልውውጥ በተመለከተ ከሶስተኛ ወገኖች ጋር ውል
ይዋዋላል፣

8.11. የማህበሩ ዋና ስራ አስኪያጅ የማህበርተኞቹ የጋራ ስምምነት ከሆነ ብቻ በማህበሩ ስም የሚንቀሳቀስም


ሆነ የማይንቀሳቀስ ንብረት ይገዛል፣ የማህበሩን የሚንቀሳቀስም ሆነ የማይንቀሳቀስ ንብረት በዋስትና
እንዲሁም ያለዋስትና በማስያዝ ከባንክም ሆነ ከአበዳሪ ድርጅቶች ከተቋም ገንዘብ መበደር እና ማበደር
ይችላል፣ መያዣና የብድር ውል ይዋዋላል፡፡ እንደአስፈላጊነቱ ለማህበሩ አጠቃላይ ስራ እንቅስቃሴ ጠቃሚ
ሆኖ ሲገኝ የሌሎች ሶስተኛ ወገኖችን የሚንቀሳቀስም ሆነ የማይንቀሳቀስ ንብረቶችን በማስያዝ ለማህበሩ
ስራ ከንግድ ባንኮች እና ከሌሎች የገንዘብ ተቋሞች ብድር መበደር ይችላል፣

8.12. የማህበሩ ዋና ስራ አስኪያጅ ከማህበርተኞቹ ይውንታን ካገኘ በማህበሩ ስም ተመዝግቦ የሚገኘውን


የሚንቀሳቀስም ሆነ የማይንቀሳቀስ ንብረት ይሸጣል፣ ይለውጣል፣ ያከራያል፣ ያኮናተራል፣ ይከራያል፣
ያፈርሳል፣ ውል ይዋዋላል፣ ውል ያፈርሳል፣

8.13. በማናቸውም ፍርድቤት ማህበሩ ከሳሽ ተከሳሽ ጣልቃ ገብ በሚሆንበት ጉዳይ ላይ በራሱ ወይም ጠበቃ
በማቆም አስፈላጊውን ይፈጽማል፡፡

8.14. በሙሉም ሆነ በከፊል ለሶስተኛ ወገን ውክልና መስጠትም ሆነ መሻር ይችላል፡፡ ጠበቃ ይወክላል ይሽራል፣

8.15. ማህበርተኞች ሊቀበሉትና ሊያፀድቁት እንዲችሉ የሂሳብ ወጪና የገቢ መዝገብ በደንብ እንዲያዝ
አስፈላጊውን እርምጃ ይወስዳል፡፡ የማህበሩ ዓላማ ግቡን እንዲመታ አስፈላዊ መስሎ በታየው ጊዜ ከላይ
ከተገለፁት ተግባራት መሀል ማናቸውንም በሌላ ሶስተኛ ሰው እንዲፈጽም በማህበሩ ውክልና መስጠት
ይችላል፣
8.16. የማህበሩ ዋና ስራ አስኪያጅ በማይኖሩበት ጊዜ ምክትል ስራ አስኪያጅ እንደ ዋና ስራ አስኪያጅ በሙሉ
ስልጣን ተክተው ይሰራሉ፡፡

አንቀጽ ዘጠኝ
መዋጮን ስለማስተላለፍ
9.1. መዋጮ በማህበርተኞች መካከል ያለምንም ገደብ ሊተላለፍ ይችላል፣ሆኖም የማህበሩን ድርሻዎች
ለማስተላለፍ ማህበርተኞች ሁሉም እንዲሰማሙበት ያስፈልጋል፣

9.2. ከማህበሩ ካፒታል በላይ ያለው ማሀበረተኞች ካልፈቀዱ ወይም ሁሉም ማሀበርተኞች ካልወሰኑ በድተቀር
ማንኛውም ማህበርተኛ በስሙ የተመዘገበውን የመዋጮ ድርሻ ለ 3 ኛ ወገን ሊያሰተላልፍ አይችልም፡፡

9.3. አንድ ማህበርተኛ በሞት ሲለይ በድርሻው የተመዘገበውን ሃብት ለህጋዊ ወራሾቹ ወይም እሱ ለመረጠው
3 ኛ ወገን ሊተላለፍ ይችላል፣ስራውን ለመቀበል የተለየ ስምምነት ያስፈልጋል፡፡

9.4. የማህበርተኛው ወራሾች ድርሻቸውን ለቀሩት የማህበሩ አባላት ቅድሚያ በመስጠት ለመሸጥ፣በስጦታ
ለማስተላለፍ፣ወይም በአባልነት ለመቀጠል ይችላል፣

9.5. የድርሻው መተላለፍ በፅሁፍ ሆኖ በአባላቱ መካከል በሚፈፀም ስምምነትና በኢትዮጵያ ንግድ ህግ መሰረት
የሚከናወን ይሆናል፣

አንቀጽ አስር
መዋጮ ስለማስተላለፍ መርህ

10.1

አንቀጽ አስራ አንድ


የማኅበሩ አባላት መብትና ግዴታዎች

11.1 እያንዳንዱ አባል የሚከተሉት መብቶች ይኖሩታል፡-


ሀ) በማናቸውም የአባላት ስብሰባ ላይ የመካፈል፣

ለ) በማናቸውም ስብሰባ ላይ ባለው መዋጮ መጠን ድምጽ የመስጠት፣


ሐ) በዋናው መስሪያ ቤት ውስጥ ያሉ የቆጠራ ውጤቶችን፤ የወጪና ገቢ ምዝገባዎችና የኦዲተር ሪፖርቶች
የመመርመር መዝግቦ የመያዝ፣
መ) በሕግ፣ በማኅበሩ የመመስረቻ ጽሑፍ የተመለከቱትን መብቶች መጠቀም አለበት፡፡
11.2 ከላይ የተመለከተው የአባላት መብት እንደተጠበቀ ሆኖ፡-
ሀ) ማኅበሩ ለአንድ አባል ድርሻ ከአንድ በላይ ባለ ንብረት አይቀበልም፡፡ ስሰሆነም በዚህ መሠረት
የመዋጮው የጋራ ባለንብረቶች ቢኖሩ የአባልነት መብታቸውን ሊጠቀሙበት የሚችሉት
ከመካከላቸው አንድ እንደራሴ በመሾም ብቻ ነው ፡፡

ለ) ከመዋጮ ድርሻ ጋር የተያያዙ መብቶች ድርሻውን ይከተላል፡፡ የመዋጮው ድርሻ ባለቤት የሆነ የተፈጥሮ
ሰውም ሆነ በሕግ የሰውነት መብት የተሰጠው አካል በደንቡ መሠረት በመብቶቹ ሊገለገል ይችላል፡፡
በአንፃሩም ባለቤት መየመዋጮ ባለድርሻ ሆን ለዚህ ለመመስረቻ ጽሑፍና በአግባቡ ለሚተለላፍ
የአባላት ውሳኔዎች ተገዢ የመሆን ውጤቶች ያስከትላል፡፡
ሐ) የሟች ማኅበርተኛ ወራሾችም ሆኑ ወኪሎች በማኅበሩ ንብረቶች ላይ ማኅተም እንዲደረግ ወይም
እንዲታሸግ የማድረግ መብት አይኖራቸውም፡፡ ስለሆነም በመብታቸው በሚጠቀሙበት ጊዜ ሁሉ
የመመስረቻ ጽሑፍ የመተዳደሪያ ደንብና በአግባቡ የሚተላላፍ የማኅበርተኞች ውሳኔዎች ሁሉ
በአነርሱም ላይ ተፈፃሚነት አላቸው፡፡

አንቀጽ አስራ ሁለት


ሰነዶች የማወቅ መብት
12.1.ማናቸውም ባለአክሲዮን ከማህበሩ ዋና መሥሪያ ቤት ከዚህ ቀጥሎ ያሉትን ሰነዶች ለማወቅ ወይም
ቅጂዎቻቸውን ለመውሰድ በማናቸውም ጊዜ ሁሉ መብት አለው፡፡
እነዚህም፡-
ሀ/ የሂሳብ ሚዛኖች፣ የትርፍና የኪሳራ ሂሳቦች፣
ለ/ አስተዳዳሪዎቹና ተቆጣጣሪዎች ባለፉት የመጨረሻ ሶስት የሂሣብ ማጠቃለያ ጊዜዎች ስለሥራው
ለባለ ድርሻዎች ያቀረቡዋቸው ሪፖርቶች፣
ሐ/ የጉባኤ ቬርቫሎችና ሌሎች የማስረጃ ወረቀቶች ናቸው፡፡

አንቀጽ አስራ ሶስት


የዋና ስራ አስኪያጅ ክፍያ
13.1.የዋና ሥራ አስኪያጅ ደመወዝ፣ አበልና ሌሎች ጥቅሞች በማህበርተኞች የሚወሰን ይሆናል፡፡

አንቀጽ አስራ አራት


ስብሰባዎችን ስለመጥራትና የውሳኔ አሰጣጥ ምልዓተ ጉባዔ
14.1.የማህበሩ ስብሰባ ሊካሄድ የሚችለው ከጠቅላላ ባለ ድርሻ ከ 75% በላይ ድምጽ የሚወክሉ ማህበርተኞች
ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በስብሰባው ላይ ሲገኙ ነው፣ በዚህ አይነት ስብሰባዎች ላይ ውሳኔዎች
የሚተላለፉት ማህበሩ ውስጥ ባላቸው የመዋጮ ድርሻ ልክ በድምጽ ብልጫ ይሆናል፡፡
14.1. ማህበሩ የበጀት ዓመቱ ሲያልቅ መደበኛ ስብሰባ ያካሂዳል፡፡የማህበሩ የሂሳብ አመት ከተዘጋጀበት አራት ወር
ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ የማህበሩ ጠቅላላ ጉባኤ መጠራት አለበት፣ዋናው ስራ አስኪያጅ አመታዊ
የማህበርተኞች ስብሰባ ከመደረጉ በፊት 15 ቀን ባላነሰ ጊዜ አስቀድሞ ለአባላት በአደራ ደብዳቤ
የስብሰባውን ጥሪ ማሳወቅና ለውሳኔው ወይም ለውይይት ያቀረበው ሀሳብ ምን እንደሆነ በግልጽ
ማስረዳት አለበት፡፡
14.2. ለማህበሩ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ዋና ሥራ አስኪያጅ በማናቸውም ጊዜ ስብሰባ ሊጠራ ይችላል፣
14.3. ማህበሩ ስብሰባ በንግድ ህግ በተደነገገው መሠረት የማህበርተኞች ስብሰባ ሊጠራ ይችላል፣
14.4. የማህበሩ መመስረቻ ጽሁፍና መተዳደሪያ ደንብን ለማሻሻል፣ የማህበሩን እድሜ ለመወሰን ከሌላ ማህበር
ጋር በመቀላቀል ለማደራጀት፣ የማህበሩን ተፈጥሮ ለመለወጥ፣ ካፒታል ለመቀነስ ወይም ለመጨመር፣
አዲስ አባላትን ለመቀበል ድርሻን ለውጪ ሰዋች ለማስተላለ 75% የመዋጮ ድርሻ ያላቸው የማህበሩ
አባላት በማንኛውም ጊዜ የማህበሩ ጠቅላላ ጉበኤ እንዲሰበሰብ ሊያደርጉ ይችላል፣
14.5. ሌሎች ጉዳዮች በንግድ ህግ ቁጥር መሠት ይወስናሉ፡፡
አንቀጽ አስራ አምስት
የሂሣብ ዓመትና የትርፍ ክፍፍል
15.1. የማህበሩ የሂሣብ ማጠቃለያ ጊዜ በየአመቱ ከሐምሌ 1 ቀን እስከ ሰኔ 30 ድረስ ወይም በሌላ በጀት ዓመት
ይሆናል፡፡ ሆኖም የመጀመሪያ ጊዜ ማህበሩ ከተመዘገበበት ጀምሮ እስከ ሰኔ 30 ወይም በሌላ
ከተመዘገበበት በጀት ዓመት መጨረሻ ወር ይሆናል፡፡
15.2. የንብረት ቆጠራ የሂሣብ ማመዛዘኛ የዓመቱ ትርፍና ኪሳራ ሰንጠረዥ /ሪፖርት/ በዋና ሥራ አስኪያጅ
ይዘጋጃል፡፡
15.3. ከዓመቱ የተጣራ ትርፍ በመሀበርተኞች የሚወሰን የመጠባበቂያ ተቀማጭና ሌሎች ወጪዎች ተቀናንሶ
የሚገኘውን የተጣራ ትርፍ ለማህበርተኞች እንደ መዋጮ ድርሻቸው ይከፋፈላል፡፡
15.4. በንግድ ሕጉ አንቀፅ 528 እንደተደነገገው በተጣራው ትርፍ ላይ በየአመቱ መጠባበቂያ የሚሆነውን ቢያንስ
5 በመቶ እየተነሳ ይቀመጣል፡፡ ይኸውም መጠባበቂያ ከማህበሩ ዋና ካፒታል አንድ አስረኛ እጅ ሲደርስ
ግዴታ መሆኑ ይቋረጣል፡፡

አንቀጽ አስራ ስድስት


የጠቅላላ ጉባኤ ሥልጣንና ተግባር
16.1 የማኅበሩን ሥራ አስኪያጅ መግለጫ ሰምቶ ተቀባይነት ያለው ሆኖ ካገኘው ያጸድቃል፡፡
16.2 የማኅበሩ ሒሳብ ተቆጣጣሪ (ኦዲተር) ዓመታዊ የሂሳብ መግለጫ መርምሮ ተገቢውን እርምጃ ይወስዳል፡፡

16.3 የማኅበሩን ዋና ሥራ አስኪያጅ ይሾማል እንዲሁም የዘርፍ እና ክፍል ሀላፊዎችን በሥራ አስኪያጅ አቅራቢነት
ያጸድቃል፣ በቂ ምክንያት ሲኖረው በንግድ ሕግ በተደነገገው መሠረት ይሽራል፡፡
16.4. የማኅበሩን የሥራ አፈፃፀም በሚመለከት ለዋናው ሥራ አስኪያጅ መመሪያ ይሰጣል፡፡
16.5. የማኅበሩን ማስፋፋት ወይም ማፍረስ አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው ውሳኔ ይሰጣል፡፡
16.6. ስለዓመታዊ ትርፍ አከፋፈል ውሳኔ ይሰጣል፡፡
አንቀጽ አስራ ሰባት
ኦዲተር
17.1. በማህበርተኞች የሚመረጥ የተረጋገጠለት የኦዲት ባለሙያ ግለሰብ ወይም ድርጅት ይኖረዋል፣
17.2. የአገልግሎት ክፍያው በማህበርተኞች ይወሰናል፣
17.3. የማህበሩን ሂሣብ በመመርመር ለአባላት ወይም ለጠቅላላ ስብሰባ ሪፖርት ያቀርባል፣
17.4. ቋሚ ንብረትና ዕዳውን አጣርቶና ለይቶ በማወቅ የማህበሩን ዕዳ ለጠያቂዎች ያከፋፍላል፣
17.5. ዕዳ ተከፍሎ የሚቀር ትርፍ ለማህበርተኞች እንደየድርሻቸው ያከፋፍላል፣
17.6. ማሕበሩ በንግድ ሕግ መሠረት በቂ በሆኑ ምክንያቶች በፍርድ ቤት ውሳኔ ይፈርሳል፡፡
አንቀጽ አስራ ስምንት
የማህበሩ መፍረስ

18.1.በማህበርተኞች ችሎታ ማጣት፣ መክሰር፣ እዳውን መክፈል ካልቻለ ወይም በሞት ማህበሩ አይፈርስም፣
18.2.ማህበሩ በሚፈርስበት ጊዜ በማህበርተኞች የተሰጠ ሶስተኛ ወገን ሒሣብ አጣሪ ይሆናል፣
18.3. ሒሳብ አጣሪው የተመረጠበትን በመወጣት ረገድ ሙሉ ስልጣን አለው፣
18.4. ቋሚ ንብረትና ዕዳውን አጣርቶና ለይቶ በማወቅ የማህበሩን ዕዳ ለጠያቂዎች ያከፋፍላል፣
18.5. ዕዳ ተከፍሎ የሚቀር ትርፍ ለማህበርተኞች እንደየድርሻቸው ያከፋፍላል፣
18.6. ማሕበሩ በንግድ ሕግ መሠረት በቂ በሆኑ ምክንያቶች በፍርድ ቤት ውሳኔ ይፈርሳል፡፡
አንቀጽ አስራ ዘጠኝ
መመስረቻውን ስለማሻሻል
19.1. አግባብ ባላቸው የንግድ ህግ ድንጋጌዎች መሠረት ማህበርተኞች ይህን የመመስረቻ ጽሑፍ አስፈላጊ
በሚሆንበት ጊዜ ሁሉ ለመለወጥ ለማሻሻልና ተጨማሪ ሃሳቦችንም ለማከል ይችላሉ፡፡

አንቀጽ ሃያ
ውዝግብን ስመፍታት
20.1. በማህበርተኞች መካከል የሚነሱ ማህበር ነክ አለመግባባቶች በኢትዮጵያ ፍትሐብሔር ህግና የሥነ
ሥርዓት ሕግ ስለግልግል በተመለከቱት ደንቦች መሠረት ይወሰናል ውሳኔው አስገዳጅና የመጨረሻ
ነው፡፡

አንቀጽ ሃያ አንድ
ማኅበሩ የሚቆይበት ጊዜ
21.1. አባላቱ በተለየ ሁኔታ ለመወሰን ያላቸው መብት እንደተጠበቀ ሆኖ ማኅበሩ ላልተወሰነ ጊዜ ተቋቁሟል፡፡
ከዚህ በላይ በዝርዝር በሰፈሩት ጉዳዮች ላይ መስማማታችን ይታወቅ ዘንድ እኛ ማህበርተኞች
ፊርማችንን አኑረናል፡፡

አንቀጽ ሃያ ሁለት
መመስረቻ ጽሁፉ በሥራ ላይ የሚውልበት ጊዜ
ይህ የመመስረቻ ጽሁፍ በህግ አግባብ ከፀደቀበት ጊዜ ጀምሮ በሥራ ላይ ይውላል፡፡

ተ.ቁ ስም ፊርማ

1
2
3

You might also like