You are on page 1of 7

ና ው

እርሻ የመመስረቻ ፅሑፍና የመተዳደሪያ ደንብ

ልማት Memorandum of Association and

ኃላፊነቱ Articles of Association

የተወሰነ
የግል
ማህበር ነሀሴ፣

2012
NAW ጋምቤላ

AGRIC
ULTUR
AL ናው እርሻ ልማት ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር

DEVEL የመመስረቻ ፅሑፍ

OPME አንቀፅ አንድ

NT የማህበሩ ምስረታ

P.L.C
እኛ ሥምና ፊርማችን በዚህ ሰነድ መጨረሻ ላይ በአሰፈርነው መካከል በኢትዮጵያ የንግድ ህግ በዚህ
የመመስረቻ ፅሑፍ እና ተያይዞ በሚገኘው የመተዳደሪያ ደንብ ስምምነቶች የሚገዛ እና ዓላማው ከዚህ በታች
በአንቀጽ 4 ስር የተመለከቱትን ተግባራት ማከናወን የሆነ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ለመመስረት
ስምምነት ላይ ደርሰናል፡፡

አንቀጽ ሁለት

የማህበሩ አባላት ሥም፣ ዜግነትና አድራሻ

ተ. ሙሉ ሥም ዜግነት ፆታ አድራሻ ከተማ



1 አቶ ሲሳይ ደጀኔ አረዳ ኢትዮጵያዊ ወ ጋምቤላ
2 ወ/ሮ በቀለች ደምስ ሁንዴ ኢትዮጵያዊ ወ ጋምቤላ
አንቀጽ ሦስት

የማህበሩ ስምና አድራሻ

1. የማህበሩ ስም ፡- ናው እርሻ ልማት ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር በሚል ስያሜ ይጠራል፡፡
2. የማህበሩ ዋና መስሪያ ቤት፡- ጋምቤላ ከተማ
3. ማህበሩ ወደፊት በሌሎች የክልሉ ከተሞችም ሆነ የኢትዮጵያ ከተሞች ቅርንጫፍ የመክፈት መብቱ
የተጠበቀ ነው፡

አንቀጽ አራት

የማህበሩ ዓላማ

1. ማኅበሩ የተለያዩ ሰብሎችንና ፍራፍሬዎችን በማምረት በአለበት ሁኔታ ወይም በማቀነባበርና


በማደራጀት ለሀገር ውስጥና ለውጭ ገበያ ማቅረብ፣
2. ለኢንዱስትሪ ግብአት የሚውሉ የእርሻ ምርቶችን በማምረት ለሀገር ውስጥና ለውጭ ገበያ
ማቅረብ፣
3. በምርምር የተገኙ ምርጥ ዘሮችን የማባዛትና የማዘጋጀት ስራ በማከናወን መሸጥ ማከፋፈል አቅም
በፈቀደ ሁኔታም ለአካባቢው አርሶ አደሮች በነፃ ወይም በአነስተኛ ክፍያ ተጠቃሚ እንዲሆኑ
ማድረግ፣
4. በአካባቢው የሚመረቱ የእርሻ ውጤቶችን በመግዛት በአለበት ሁኔታ ወይም በኢንዱስትሪ
በማደራጀትና በማቀነባበር ለሀገር ውስጥም ሆነ ለውጭ ገበያ ማቅረብ፣
5. የእርሻ መሳሪያዎችንና የምርት ማሳደጊያ ግብአቶችን ከውጭ በማስመጣት ሆነ ከሀገር ውስጥ
በመግዛት በተመጣጣኝ ዋጋ ማከራየት መሸጥ፣
6. ፀረ-አረምና ተባይ ኬሚካሎችን በማስመጣት መሸጥ ማከፋፈልና የመርጨት አገልግሎት መስጠት፣
7. የእንስሳት እርባታና የማደለብ ስራ በማከናወን ለገበያ ማቅረብ፣
8. የእንስሳት ተዋጽኦዎችን ባሉበት ሁኔታ ወይም በማቀነባበር ለሀገር ውስጥና ለውጭ ገበያ ማቅረብ፣
9. የጎጆና መለስተኛ የእርሻ ውጤት ኢንዱስትሪዎችን ማቋቋም ማደራጀትና የማምረት ሥራ ማከናወን፣
10. በትራንስፖርትና በመጋዘን አቅርቦት ስራ መሰራት፣
11. በኮንስትራክሽን ስራ ዘርፍ በመሰማራት ግንባታዎችን ማካሄድ ፣ የኮንስትራክሽን
ማሽነሪዎችን ማከራየት
12. በአስመጪና ላኪ ስራ መሰማራት እንዲሁም የጅምላና ችርቻሮ ንግድ ማካሄድ
13. ንብ በማነብ ምርቱን ለገበያ ማቅረብ
14. ሌሎችም
አንቀጽ አምስት

የማህበሩ ካፒታል

1. የማህበሩ ጠቅላላ ካፒታል ብር 3,000,000/ሶስት ሚሊዮን ብር/ ሲሆን ይህም ካፒታል በጥሬ ገንዘብ
የተከፈለ ነው፡፡
2. የማህበሩ ጠቅላላ ካፒታል እያንዳንዳቸው ብር 1,000 /አንድ ሺህ ብር/ ዋጋ ባላቸው 1500/አንድ ሺህ
አምስት መቶ/ አክሲዮኖች ተከፋፍሏል፡፡ አክሲዮኖቹ በሙሉ ለአባላት ተሸጠዋል፡፡
3. በማህበሩ መስራች አባላት የተገዙ የአክሲዮኖች ብዛት ከዚህ በታች ባለው ሠንጠረዥ ተመልክቷል፡፡
ተ. የባለአክሲዮኖች ሙሉ ስም የአክሲዮን የአንድ ጠቅላላ የአክሲዮን ብዛት
ቁ መጠን አክሲዮን መዋጮ በብር የተሸጠ ያልተሸጠ
ዋጋ/በብር
1 አቶ ሲሳይ ደጀኔ አረዳ 1500 1,000 1,500,000 1500 -
2 ወ/ሮ በቀለች ደምስ ሁንዴ 1500 1,000 1,500,000 1500
ድምር 3000 - 3,000,000 3000

አንቀጽ ስድስት

የትርፍና ኪሳራ ክፍፍል

ከማህበሩ ጠቅላላ ዓመታዊ ትርፍ የመጠባበቂያ ገንዘብና ሌሎች ጠቅላላ ወጪዎች ከተቀነሱ በኃላ ቀሪው
በአባላቱ መካከል እንደ አክሲዮን ድርሻቸው ብዛት ይከፋፈላል፡፡ ኪሳራም ካለ በተመሣሣይ ሁኔታ በአባላቱ
መካከል ይከፋፈላል፡፡ ሆኖም የማህበሩ አባላት በማናቸውም ሁኔታ በማህበሩ ውስጥ ካላቸው የአክሲዮን
ካፒታል በላይ ተጠያቂ ሊሆኑ አይችሉም፡፡ ማህበሩ አስፈላጊ ሁኖ ሲገኝ ክፍት በማድረግ አክስዮን መሸጥ
ይችላል፡፡

አንቀጽ ሰባት

የማህበሩ ስራ አመራር

1. ማህበሩ የሚከተሉት የአመራር አካላት ይኖሩታል፡፡


ሀ. ጠቅላላ ጉባኤ
ለ. አንድ ዋና ስራ አስኪያጅ
ሐ.አንድ ምክትል ሥራ አስኪያጅና
መ. ኦዲተሮች
2. በዚህም መሠረት አቶ አቶ ሲሳይ ደጀኔ አረዳ ስራ አስኪያጅ አቶ ወ/ሮ በቀለች ደምስ ሁንዴዋና
ምክትል ዋና ስራ አስኪያጅ ሆነው ላልተወሰነ ጊዜ ተመርጠዋል፡፡

አንቀጽ አስራ አራት

ስለማህበሩ መፍረስ
ማህበሩ

1. በጠቅላላ ጉባኤ ውሳኔ


2. በፍርድ ቤት ውሳኔ ወይም
3. በህግ መሠረት ሊፈርስ ይችላል፡፡

አንቀጽ አስራ አምስት

የማህበሩ የሥራ ዘመን

የማህበሩ አባላት በተለየ ሁኔታ ለመወሰን ያላቸው መብት እንደተጠበቀ ሆኖ ማህበሩ የተቋቋመው ላልተወሰነ
ጊዜ ነው፡፡

የመስራች አባላት ስምና ፊርማ

ስም ፊርማ

1. አቶ ሲሳይ ደጀኔ አረዳ

2. ወ/ሮ በቀለች ደምስ ሁንዴ


ናው እርሻ ልማት ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር

የመተዳደሪያ ደንብ

አንቀጽ አንድ

ጠቅላላ

1. ይህ የመተዳደሪያ ደንብ ከመመስረቻ ጽሑፉ ጋር የማይነጣጠል የመመስረቻ ጽሑፉ አካል


ሆኖያገለግላል፡፡
2. ማህበሩ በኢትዮጵያ የንግድ ሕግ መሠረት የተቋቋመ እና በዚሁ የመተዳደሪያ ደንብ እና ተያይዞ
በሚገኘው የመመስረቻ ፅሑፍ የሚገዛ ሲሆን በመተዳደሪያ ደንቡ እና በመመስረቻ ፅሑፉ ያልተሸፈኑ
ጉዳዮች ሲያጋጥሙ የንግድ ሕጉድንጋጌዎች እና ሌሎች አግባብነት ያላቸው የሀገሪቱ ህጎች
ተፈፃሚነትይኖራቸዋል፡፡

አንቀጽ ሁለት

የአክሲዮን መዝገብ

በማህበሩዋና መ/ቤት የሚቀመጥ የአክሲዮን መዝገብ ይኖራል፡፡ ይህም መዝገብ

ሀ. የአባላትን ስምና አድራሻ

ለ. እያንዳንዱ አባል ያስገባው መዋጮ በገንዘብ /በዓይነት ከሆነ ግምቱ

ሐ. የአክሲዮኖች ዝውውር

መ. ማናቸውንም ስለዚህ ሁኔታዎች የተደረገውን ማሻሻያ የሚያሳይ ይሆናል፡፡

አንቀጽ ሶስት

አክሲዮን ስለ ማስተላለፍ

አክሲዮን ለማስተላለፍ የሚቀርቡ ጥያቄዎች ለዋና ሥራ አስኪያጅ እንዲቀርብ ተደርጎ ዋና ሥራ አስኪያጁም


በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ በጉዳዩ ውሳኔ ይሰጥበት ዘንድ ለማህበሩ ጠቅላላ ጉባኤ ያቀርባል፡፡
አንቀጽ አስራ ሶስት

የሚፀናበትጊዜ

ይህ የመተዳደሪያ ደንብ እና የመመስረቻ ፅሑፍ አግባብ ባለው የመንግስት መስሪያ ቤት ከፀደቀበት ቀን


ጀምሮ የፀና ይሆናል፡፡

የመስራች አባላት ሥም ፊርማ

1. አቶ ሲሳይ ደጀኔ አረዳ

2. ወ/ሮ በቀለች ደምስ ሁንዴ ----------------------

You might also like