You are on page 1of 3

ለስራ ግብር አወሳስን የተዘጋጁ ምሳሌዎች

ለስራ ግብር አወሳስን የተዘጋጁ ምሳሌዎች


የግብር/ታክስ አወሳስን ምሳሌዎች
በአቶ ስንታየሁ ታደለ ..... // ..... የታክስ ባለሙያ
 በገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 240/2008 ዓ.ም እና ደንብ ቁጥር 162/2010 ዓ.ም እና የታክስ አስተዳደር አዋጅ
ቁጥር 241/2008 ዓ.ም እና ደንብ ቁጥር 163/2010 ዓ.ም ላይ በመመስረት፡-
 የግብር አወሳስን ዘዴዎች፡- በሂሳብ መዝገብ፣ በሦስተኛ ወገን መረጃ እና በቀን ገቢ ግምት ጥናት መረጃ ላይ
በመመስረት ግብር ይወሰናል፡፡
ከመቀጠር የሚገኝ ገቢ ግብር አወሳስን
1. በአልሳም ትሬዲንግ ሀ/የተወሰነ የግል ማህበር 8 ዓመታት ሲሰሩ የነበሩት አቶ ክንዴ ደርበው በሰኔ 01 ቀን
2012 ዓ.ም ከስራ በመሰናበታቸው በሰኔ 30 ቀን 2012 ዓ.ም የሚከተሉት ጥቅማጥቅሞች ታስቦላቸዋል፡፡
o የአገልግሎት ክፍያ ብር 18,000 ብር
o የስራ መፈለጊያ ብር 12,000 ብር
 አቶ ክንዴ ደርበው ከስራ ሲሰናበቱ የመጨረሻው ወር ደመወዛቸው ብር 6,000 ብር ነው፡፡
 ከላይ በመግለጫው ለመረዳት እንደተቻለው አቶ ክንዴ በሰኔ 1 ቀን 2012 ዓ.ም ከስራ ተሰናብተዋል፡፡ ከስራ
በተሰናበቱበት ጊዜ የአገልግሎት ክፍያ ብር 18,000 እና የስራ መፈለጊያ ብር 12,000 ሊከፈላቸው እንደሚገባ
ትዛዝ ተላልፋል፡፡
በዚሁ መሰረት የስራ ግብር ስሌት፡-
 ጠቅላላ ገቢ
o የአገልግሎት ካሳ ክፍያ …………………. ብር 18,000.00
o የስራ መፈለጊያ ………………………….. ብር 12,000.00
o ጠቅላላ ገቢ ………………………………. ብር 30,000.00
o ግብር የሚከፈልበት ጠቅላላ ገቢ ብር 30,000.00 ነው፡
 የስራ ግብር፡-
o የአቶ ክንዴ የስንብት ክፍያ ብር 18,000.00 እንደሚከተለው በመደበኛ የወር ደመወዝ ብር 6,000.00
ተንትኖ ይሰላል፡፡
o የአገልግሎት ክፍያው በደመወዝ ሲሰላ የወር (18,000 ÷ 6,000= 3) ይሆናል፤
o የአንድ ወር ሥራ ግብር ብር 935 (6,000 x 25%-565) ነው፤
o የ 3 ወር ስራ ግብር ብር 2,805(935x3) ይሆናል፤
o የስራ ግብር መፈለጊያ ክፍያው የ 2 ወር ደመወዝ (12,000÷ 6,000) ይሆናል፤
o የአንድ ወር ስራ ግብር 935(6,000 x 25%-565) ይሆናል፤
o የሁለት ወር ስራ ግብር ብር 1,870 (935 x 2) ይሆናል፤
o የተቀናሽ ድምር 4,675 (2,805 + 1,870)፤
 ለሠራተኛዋ የሚደርሰው የተጣራ ተከፋይ /ሌሎች ተቀናሾችን በመተው/
o ጠቅላላ ገቢ ብር ………………….. 30,000.00
o ተቀናሽ የስራ ግብር ብር ………. (4,675.00)
o የተጣራ ተከፋይ ………………….. 25,325
2. ወ/ሮ ሰናይት ብዙነህ በህብረት ባንክ ውስጥ ሲሰሩ መደበኛ ደመወዝ ብር 7,200 የሚከፈለው ቋሚ ሰራተኛ
ሲሆኑ በነሀሴ ወር 2012 ዓ.ም በአሜን ሆቴል ድርጅት ውስጥ በትርፍ ጊዜዋ በመስራት በወር ውስጥ ያገኙት
ገቢ ብር 5,000 መሆኑን እና ድርጅቱ የስራ ግብር መቀነሱን አሳውቀዋል፡፡ እንዲሁም በቋሚነት የምትሰራበት
ባንክ በዓመቱ መጨረሻ ውስጥ ተቋሙ ትርፍ በማግኘቱ ለወ/ሮ ሰናይት ብዙነህ በወሩ ብር 14,400 ቦነስ
ተከፍሏቸዋል፡፡ ስለዚህ በነሀሴ ወር መከፈል ያለበት የስራ ግብር ስንት ይሆናል?
መልስ
o ከቋሚ ስራው ያገኘው ገቢ ……………………………...………………….. ብር 7,200.00
o ከአሜን ሆቴል በትርፍ ሰዓት ያገኘችው ገቢ …………………………..… ብር 5,000.00
o ከማበረታቻ ወይም ቦነስ የተገኘ ገቢ ……………………………...………. ብር 14,400.00
o በሁለቱም ተቋማት የሚከፈለው ገቢ ተደምሮ ግብር ይሰላል፤
o ጠቅላላ ግብር የሚከፈልበት ገቢ ……………………………………………. ብር 26,600.00
የስራ ግብር
o ከመደበኛ ስራቸው ያገኙት ገቢ እና በትርፍ ሰዓት ክፍያ ያገኙት ገቢ ላይ መከፈል የሚገባው ግብር ብር
2,770.00 (12,200 x 35% -1,500)
o በቋሚ ስራ በተናጠል የተከፈለ ግብር ብር 1,235 (7,200.00 x 25% - 565)
o ከአሜን ሆቴል በትርፍ ጊዜዋ ተቀጥራ ለሰራችበት ብር 697.50 (5,000.00 x 20% - 302.5)
o በልዩነት መከፈል ያለበት የስራ ግብር (ቦነሱን ሳይጨምር) ብር 837.50 (2,770.00 – (1,235.00+697.50))
o ከቦነስ የተገኘ ግብር ብር 1,200 (14,400/12)
o ከመደበኛ ደመወዝ ጋር ሲደመር ብር 8,400 (7,200+1,200)
o የስራ ግብር ብር 1,565 (8,400x30%-955)
o ተከፋይ የስራ ግብር የማበረታቻ የስራ ግብር ሲቀነስ በመደበኛ ደመወዝ የተከፈለ ብር 330(1,565-1,235)
o ከቦነስ የሚከፈል የስራ ግብር ብር 3,960 (330x12)
o ከቦነስ የተጣራ ተከፋይ ብር 10,440 (14,400-3,960)
o ጠቅላላ የስራ ግብር ብር 6,032.50 (1,235+837.50+3,960)
o የተጣራ ተከፋይ ……………… ብር 20,567.50 (26,600-6,032.5) ይሆናል፡፡
አሰተዳደራዊ ቅጣትና ወለድ
3. ኮምቦልቻ ጨርቃጨርቅ ፋብሪካ የሀምሌ ወር 2012 ዓ.ም የሰራተኞች የስራ ግብር ብር 12,500 መክፈል
በነበረበት ጊዜ ሳይከፍል ህዳር 01/2013 ክፍያ ከፍለዋል፡፡
በዚህም መሰረት:-
o በታክስ አሰተዳደር አዋጅ ቁጥር 241/2008 አንቀጽ 103 መሰረት የታክስ ማስታወቂያ ዘግይቶ ማቅረብ=
የዘገየው ለሁለት ወራት እና የሶስተኛ ወር አንድ ቀን በመሆኑ ያልተከፈለውን ግብር ሲባዛ 15%= 12,500x
15%= 1,875 ይህ ቅጣት ከ 10,000 በታች እንዲሁም በታክስ ማስታወቂያው ላይ መታዩት ካለበት 12,500
ያነሰ በመሆኑ 10,000 ብር ይቀጣል፡፡
o በታክስ አሰተዳደር አዋጅ ቁጥር 241/2008 አንቀጽ 104 መሰረት ታክስን ዘግይቶ መክፈል= ክፍያው የዘገየው
ለሶስት ወራት በመሆኑ፡-
 ለመጀመሪያው ወር 12,500 x5%=625፣
 ለቀሪ ሁለት ወር 12,500x2% x 2 ወር =500 በድምሩ 1,125 ይቀጣል፡፡
o በታክስ አሰተዳደር አዋጅ ቁጥር 241/2008 አንቀጽ 37 መሰረት ለዘገዩ ክፍያ የሚከፈል ወለድ ለሶሰት ወር
የዘገዩ በመሆኑ በባንክ ከፍተኛ የማበደሪያ ወለድ ምጣኔ 16.25% ላይ 15% ተጨምሮ ይሰላል፣
 ወለድ= (12,500 x61 ቀናት/365)18.68% =390.23 ይከፍላል፡፡
o ጠቅላላ ስራ ግብር፣ አሰተዳደራዊ ቅጣትና ወለድ ድምር (12,500 +1,125+390.23+10,000)= 24,015.23

You might also like