Professional Documents
Culture Documents
0
ምዕራፍ 1
መግቢያ
ማንዋል 3 ደ ጥራዝ 2 የደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መንግሥት የሂሳብ አያያዝ ሥርዓትን የሂሳብ አወቃቀር ይይዛል። የሂሳብ አወቃቀር
መንግሥት የፋይናንስ እና የድርጊቶችን ለመለየት አና ለመመዝገብ የሚጠቀምበት የመለያ ቁጥር ሥርዓት ነው። የሂሳብ
አወቃቀር አደረጃጀት የተዋቀረው ሥርዓትን በተከተለ አኳኋን ሆኖ የሂሳብ እንቅስቃሴዎችን እና የመረጃ ሪፖርት
አቀራረብን በበጀት በተመለከተው መሠረት በቀላሉ መመዝገብ የሚያስችል ነው።
በሲቪል ሰርቪስ ማሻሻያ የወጪ አስተዳደርና ቁጥጥር ንዑስ ፕሮግራም የበጀት ማሻሻያ ጥናት ቡድን ከዚህ በታች ለተዘገዘሩ
ዝርዝር መለያ ቁጥር መስጠት እንዲቻል በሂሳብ አወቃቀር ሥርዓት ውስጥ የሂሳብ መለያ ቁጥር አሰጣጥ ሥርዓት
ተዘርግቷል።
ለአገር ውስጥ ገቢ፣ ለውጭ ዕርዳታ እና ለውጭ ብድር የሂሳብ መደቦች ከመለያ ቁጥር 1000 እስከ 3999 ያለውን
በመጠቀም፣
ለውጪ መደቦች ከመለያ ቁጥር 6000 እስከ 6999 ያለውን በመጠቀም
በተጨማሪ የበጀት ማሻሻያ ጥናት ቡደን የመንግሥት መ/ቤቶችን እና የበጀት ተቋሞችን መለየት የሚያስችል የበጀት
አደረጃጀት አዘጋጅቷል። የበጀት ማሻሻያ ጥናት ቡድን ያዘጋጀት የበጀት አደረጃጀት አና የሂሳብ አወቃቀር ሥርዓት በበጀት
ማሻሻያ ጥናት ማንዋል የተሻሻውና የደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መ/በ 1995 የበጀት ዓመት በክልሉ የበጀት ጥናት ማሻሻያ ቡድን
ተሻሽሎና በክለሉ መንግሥት ፀድቆ ተግባራዊ የሆነው በምዕራፍ 2 ተመልክቷል።
በሲቪል ሰርቪስ ማሻሻያ ፕሮግራም የወጪ አስተዳደርና ቁጥጥር ንዑስ ፕሮግራም ሥር ያለው የሂሳብ አያያዝ ማሻሻያ
ጥናት ቡድን ከዚህ በታች ለተመለከቱት ዝርዝር መለያ ቁጥሮቸን አዘጋጅቷል።
የእነዚህ አደረጃጀቶች የሂሳብ አወቃቀር ሥርዓት በዚህ ምዕራፍ 3 ውስጥ ተመልክቷል። የሂሳብ አወቃቀር ሥርዓት
ገጽታ በሠንጠረዥ 1.1 ውስጥ ተመልክቷል።
ሠንጠረዥ 1.1
የደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መንግሥት የሂሳብ አወቃቀር ሥርዓት ገጽታ
የወጪ ዓይነት መለያ ቁጥር
የመ/መ/ቤት በዘርፍ/ንዑስ ዘርፍ አደረጃጀት 0001-0999
የአገር ውስጥ ገቢ ዓይነት 1000-1999
የወጭ አገር ዕርዳታ
1
የውጭ አገር ብድር 2000-2999
የጥሬ ገንዘብ ዝውውር 3000-3999
ሀብት 4000-4099
የአገር ውስጥ ዕዳዎች
4100-4999
የተጣራ ሀብት
5000-5599
የወጪ መደብ ዓይነት
5600-5699
6000-6999
2
ምዕራፍ 2
በዚህ ምዕራፍ ውስጥ የሚገኘው መረጃ ከበጀት ማሻሻያ ጥናት ማንዋል ክፍል 2.1 በ 1995 በጀት ዓመት የኢትዮጵያ
ፌዴራላዊ መንግሥት የፀደቀ በጀተና በሥራ ላይ የዋለ ነው። የማንዋል ክፍል 1 ከዚህ በታች ሰለተመለከቱት ዝርዝር
ማብራሪያ ይዟል።
የመ/መ/ቤቶች እና የበጀት ተቃሞቸን ለመለየት በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ መንግሥት የበጀት ዝግጅት ሂደት
ውስጥ ላይ የሚውለውን የበጀት አደረጃጀት እና
የአገር ውስጥ ገቢ ዓይነቶች
የውጭ ዕርዳታ
የውጭ ብድርና
የወጪ መደብ
በበጀት ማንዋሉ ውስጥ ያሉ መሠረታዊ የሆኑ ዝርዝር ጉዳዮች በዚህ ምዕራፍ ውስጥ ተመልክተነዋል።
የበጀት አደረጃጀት
የበጀት አደረጃጀት በጀት እንዴት እንደሚደራጅ የሚያሳይ መዋቅር ነው። ለሂሳብ አያያዝ ሲባል የበጀት አደረጃጀት በበጀት
ተቋሙን እና የገንዘቡን ምንጭ ይገለፃል።
በሠንጠረዥ 2.1 በተመለከተው የበጀት አደረጃጀት ሥርዓት ውስጥ 13 የበጀት ምደቦች አሉ። በበጀት ውስጥ የሚገኙት
መለያ ቁጥሮች የሚጀምሩት በበጀት ምድቦቸ ውስጥ ከሚገኙት የዘርፍ አደረጃጀት የንዑስ ዘርፍ አደረጃጀት እና
የመንግሥት መ/ቤት የሂሳብ መደብ “አርዕስት” ነው። የመንግሥት መ /ቤቶች ለፕሮግራሞች ለሥራ ክፍሎች ለንዑስ
ፕሮግራሞች እና ለፕሮጀክቶች መለያ ቁጥር የመስጠት ሥልጣን አላቸው። ለእነዚህ የሂሳብ ምደቦች መለያ ቁጥር
የመስጠት ተገባር አያንዳንዱ የመንግሥት መ/ቤት ከፋ/ኢ/ል/ቢሮ ጋር በመመካከር የሚያከናውነው ይሆናል።
3
ፕሮግራም ንዑሰ አርዕስት 2፣ወጥ
የሥራ ክፍል ንዑሰ ንዑሰ አርዕስት 2፣ወጥ
ንዑስ ጥሮግራም ንዑሰ ንዑሰ ንዑሰ አርዕስት 2፣ወጥ
ፕሮጀክት ንዑሰ ንዑስንዑሰ ንዑሰ አርዕስት 3፣ወጥ
የወጪ ዓይነት ዓይነት 4፣ወጥ
የፋይናንስ ምንጭ ምንጭ 4፣ወጥ
4
በሠንጠረዥ 2.1 የተዘረዘሩት አሥራ ሶስት የበጀት ምደቦች መለያ ቁጥራቸው ወጥ የሆኑት ቀጥሎ በሠንጠረዥ 2.2
ተዘርዝረዋል።
5
ዞን/ወረዳ እና ልዩ ወረዳ ኮድ
ሲዳማ ዞን
ሲዳማ ዞን የዞን ጽ/ቤት
አዋሳ ዙሪያ
ሸበዲኖ ወረዳ
ዳሌ ወረዳ
አለታ ወንዶ ወረዳ
ሁላ
በንሣ ወረዳ
አርቤጎና ወረዳ
አሮሬሳ ወረዳ
ዳራ ወረዳ
ቦሪቻ ወረዳ
የይርጋለም ከተማ አስተዳደር
የአለታ ወንዶ ከተማ አስተዳደር
ወንዶ ገነት ወረዳ
ማልጋ ወረዳ
ጎርቼ ወረዳ
ወንሾ ወረዳ
ሎካ ዓባያ ወረዳ
ጩኮ ወረዳ
ቡርሳ ወረዳ
ቦና ወረዳ
ጭሬ ወረዳ
የለኩ ከተማ አስተዳደር
የዳዬ ከተማ አስተዳደር
6
ጌዴኦ ዞን
የዞን መ/ቤቶች
ወናጎ
ይርጋ ጨፌ ወረዳ
ኮቸሬ ወረዳ
ቡሌ ወረዳ
የዲላ ከተማ አሰተዳደር
የይርጋጨፌ ከተማ አስተዳደር
ዲላ ዙሪያ ወረዳ
ገደብ ወረዳ
ከምባታና ጠንባሮ ዞን
ከምባታና ጠምባሮ ዞን የዞን ጽ/ቤት
ቀዲዳ ጋሜላ
ቃጫ ቢራ
አንጋጫ
ጠምባሮ
ዱራሜ ከተማ አስተዳደር
ሀደሮና ጡንጦ ዙሪያ
ዶዮገና
ዳምቦያ
ቃጫ ከተማ አስተዳደር
ሀደሮ ከተማ አስ/ር
7
ወላይታ ዞን
ወላይታ ዞን የዞን ማዕከል
ሶዶ ዙሪያ
ዳሞት ጋሌ
ዳሞት ወይዴ
ቦሎሶ ሶሬ
ኦፋ
ኪንዶ ኮይሻ
ሁምቦ
የወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር
የቦዲቲ ከተማ አስተዳደር
የአረካ ከተማ አስተዳደር
ዳሞት ፑላሳ ወረዳ
ድጉና ፋንጎ ወረዳ
ቦሎሶ ቦምቤ ወረዳ
ዳሞት ሶሬ ወረዳ
ኪንዶ ዲዳዬ ወረዳ
ሀዲያ ዞን
የሀዲያ ዞን ማዕከል
ሌሞ
ምሻ
ሶሮ
ምስራቅ ባደዋቾ
ጊቤ
ሻሾጉ
ዱና
የሆሳዕና ከተማ አስተዳደር
አናሌሞ
ጎምቦራ
ምዕራብ ባዳዋቾ
የሾኔ ከተማ አስተዳደር
ጋሞ ጎፋ ዞን
8
ጋሞጎፋ ዞን የዞን ጽ/ቤት
አርባምንጭ ዙሪያ
ምዕራብ አባያ
ቦንኬ
ከምባ
ጨንቻ ወረዳ
ደራማሎ
ቁጫ
ደምባ ጎፋ
ኡባ ደብረ ፀሐይ
መሎ ኮዛ
ቦረዳ
ዲታ
ዛላ
አርባምንጭ ከተማ አስተዳደር
ሳውላ የከተማ አስተዳደር
ገዜ ጎፋ
ኦይዳ
ጉራጌ ዞን
ጉራጌ ዞን ጽ/ቤት
አበሽጌ
ቀቤና
ቸሃ
እነሞርና ኤነር
ጉመር
እዣ
ገደባኖ ጉታዘረ ወለኔ ወረዳ
መስቃን
ማረቆ
ሶዶ
እንደጋኝ
ሙህርና አክሊል
የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር
9
የቡታጅራ ከተማ አስተዳደር
ጌቶ ወረዳ
ዳውሮ ዞን
ዳውሮ ዞን ጽ/ቤት
ማረቃ ወረዳ
ሎማ
ቶጫ
ጌና ቦሳ
ኢሠራ
ተርጫ ከተማ አስተዳደር
ደቡብ ኦሞ ዞን
ደቡብ ኦሞ ዞን ጽ/ቤት
ደቡብ አሪ ወረዳ
ሐመር ወረዳ
ዳሰነች ወረዳ
ሣላማጎ ወረዳ
ሰሜን አሪ ወረዳ
በና ፀማይ ወረዳ
ጂንካ ከተማ አስተዳደር
ኛንጋቶም ወረዳ
ማሌ ወረዳ
ካፋ ዞን
ካፋ ዞን ጽ/ቤት
ጊምቦ ወረዳ
ዴቻ ወረዳ
ጨና ወረዳ
ቢጣ ወረዳ
ጠሎ ወረዳ
አዲዮ ወረዳ
ጌሻ ወረዳ
ጨታ ወረዳ
10
ሳይለም ወረዳ
ገዋታ ወረዳ
የቦንጋ ከተማ አስተዳደር
ሸካ ዞን
ሸካ ዞን መ/ቤቶች
ማሻ ወረዳ
የኪ ወረዳ
አንደራቻ
ቴፒ ከተማ አስተዳደር
ማሻ ከተማ አስተዳደር
ቤንች ማጂ ዞን
ቤንች ዞን ጽ/ቤት
ደቡብ ቤንች ወረዳ
ሸኮ
ጎለዲያ
ጉራፈርዳ
ሱርማ
ሸዋ ቤንች
ሻሻ
ቤሮ
ማጂ
የሚዛን ተፈሪ ከተማ አስተዳደር
ሰሚን ቤንች ወረዳ
11
ስልጤ ዞን
ስልጤ ዞን ጽ/ቤት
ዳሎቻ
ስልጢ
ላንፉሮ
አልቾ ውሪሮ
ሣንኩራ
ምዕራብ አዘርነት በርበሬ ወረዳ
ምስራቅ አዘርነት በርበሬ
ሁልባራግ
የሰገን አከባቢ ዞን
ዞን ማዕከል
አማሮ ወረዳ
ቡረጂ ወረዳ
ዲራሼ ወረዳ
ኮንሶ ወረዳ
አሌ ወረዳ
የሠገን ከተማ አስ/ር
ልየ ወረዳዎች
ባስኬቶ
12
ኮንታ
የም
አላባ
የአላባ ከተማ አስተዳደር
መደበኛ 1
ካፒታል 2
13
14
ሠንጠረዥ 2.2 /የቀጠለ/
15
ንዑስ ንዑስ ዘርፍ የመንግሥት መ/ቤቶች ኮድ
የጤና ጤና ነክ አገልግሎቶችና ግብአቶች ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን 342
ሠራተኛና ማሕበራዊ ጉዳይ ኤጀንሲ 351
የሴቶች፣ ህጻናትና ወጣቶች ጉዳይ ቢሮ 354
አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና 360
የሥልጣን ወሰን
የሥልጣን ወሰን በጀቱ የሚመለከተውን የመንግሥት እርከን ያሳያል። የፌዴራል መንግሥት ዘጠኙን ብሔራዊ ክልላዊ
መንግሥታት እና ሁለቱን የአስተዳደር ምክር ቤቶች /አዲስ አበባ እና ድሬዳዋ/ የሚጨምሩ አሥራ ሁለት የበጀት ሥልጣን
ወሰኖች አሉ። የበጀት ሥልጣን ወሰኖች በወጥነት የሚሰራባቸው ሁለት አሀዝ ያላቸው መለያ ቁጥሮች አሏቸው። ለምሳሌ
የፌዴራል መንግሥቱ የበጀት ሥልጣን ወሰን መለያ ቁጥር “15” ሲሆን የደቡብ ክልል መለያ ቁጥር “7” ነው።
የበጀት ዓይነት
ሁለት የበጀት ዓይነቶች ያሉ ሲሆን አነዚህም መደበኛና ካፒታል ናቸው። እነዚህ የተሰጠው መለያ ቁጥር በወጥነት
የሚሰራበት አንድ አሀዝ አለው። የመደበኛ መለያ ቁጥር “1” ሲሆን የካፒታል መለያ ቁጥር “2” ነው።
ዘርፍ
ዘርፍ ለትንተና እና ለብሔራዊ ሂሳብ አያያዝ የሚያገለግሉ ሰፊ የወጪ ክፍሎችን የያዘ አደረጃጀት ነው። ለዘርፍ መለያ ኮድ
የተሰጠው “1” ሲሆን ወጥ ነው። የዘርፍ መለያ 2 ምደቦች አሉት። 1 ኛ/ የመንግሥት መ/ቤት 2/. ሌሎቸ ወጪዎች
ናቸው
የመንግሥት መ/ቤቶች አደረጃጀትና አመዳደብ በወጪ ሲታይ አስተዳደርና ጠቅላላ አገልግሎት የኢኮኖሚ አገልግሎትና
የማህበራዊ አገልግሎት ናቸው። የአስተዳደርና ጠ/አገ/ዘርፍ ለሚከተሉት አገልግሎቶች የሚወጣውን ወጪ ያካተታል።
አስፈፃሚ ህግ አውጪ የፍትህ አካላት ማረሚያ ቤቶቸ አስተዳደር ሚሊሽያ እና ጠቅላላ አገልግሎት ማለትም የሠራተኛ
አስተዳደር እና የደረጃዎች ምደባ።
የኢኮኖሚ ዘርፍ በቀጥታ የኢኮኖሚ አገልግሎት ለመሰጠት የሚውሉ ወጪዎቸን የሚሸፍን ሲሆን “የማህበራዊ” ዘርፍ
የማህበራዊ አገልግሎት ለመሰጠት የሚያስችሉ አገልግሎቶች ላይ የሚወሉ ወጪዎች ይሆናል። ይህም ለትምህርት፣
ለባህል፣ ለሰፖርት እና የጤና ንዑስ ዘርፎችን ይጨምራል።
ዘርፍ
ሶስት አሀዝ ካለው የአርዕስት መለያ ቁጥር ውስጥ የመጀመሪያው አሀዝ ነው። ለምሳሌ የኢኮኖሚ ወጪ የዘርፍ መለያ ቁጥር
200 ነው። ሶስት አሀዞች ያሉት መለያ ቁጥር ሁለተኛው አሀዝ የንዑስ ዘርፍ ሲሆን፣ ሶስተኛው አሀዝ የመንግሥት መ /ቤት
መለያ ቁጥር ነው።
ንዑሰ ዘርፍ
16
አራቱ ዘርፎች እንደገና በወጪ ንዑስ ዘርፎች ተካፍለዋል። ንዑሰ ዘርፍ ሶስት አሀዝ ካለው የ”አርዕስት” መለያ ቁጥር
ሁለተኛው አሀዝ ነው።
ንዑሰ ዘርፍ እንደገና በወጪ ንዑስ ንዑሰ ዘርፎች ተከፋፍለዋል። ንዑሰ ንዑሰ ዘርፉ ሶስት አሀዝ ካለው የ።አርዕስት” መለያ
ቁጥር ሶስተኛው አሀዝ ነው። ሶስቱ አሀዞች ያሉት “አርዕስት” ኮድ የሚያመለክተው የመንግሥት መ/ቤቶች መለያን ነው።
የመንግሥት መ/ቤቶች
የመንግሥት መ/ቤቶች በጀት ለመጠየቅ አና ለማግኘት መብት ያላቸው ተቋሞች ናቸው። በማሻሻያ ጥናቱ መሠረት
የመንግሥት መ/ቤት የህግ ሥልጣን የተሰጠው በጀቱን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል አግባብ ካለው የፋይ /ኢ/ል/ቢሮ የሚያገኝ
የመጨረሻውን/ ዓመታዊ ሂሳብ በቀጥታ ለፋ/ኢ/ል/ቢሮ የሚያቀርብ አና በክልሉ ም/ቤት ፀድቆ በወጣ የመንግሥት
መ/ቤቶች ዝርዝር ውስጥ የተመለከተው ነው።
በሠንጠረዥ 2.1 በተመለከተው የበጀት አደረጃጀት ሥርዓት ውስጥ የመንግሥት መ/ቤቶች ሶስት አሀዝ ያለው የተለየ
የአርዕስት መለያ ቁጥር ተሰጥቷቸዋል።
የአርዕስት መለያ ቁጥር የመጀመሪያ አሀዝ የመንግሥት መ/ቤቱ ዘርፍ፣ ሁለተኛ አሀዝ ንዑስ ዘርፍን የሚያሳይ ሲሆን፣
ሶስተኛው አሀዝ በንዑሰ ዘርፍ ውስጥ ለአንድ መንግሥት መ/ቤት የተሰጠ የተለየ ቁጥር ነው።
ሠንጠረዥ 2.2 በአሁኑ ወቅት ያሉትን የክለሉ የመንግሥት መ/ቤቶች ዝርዝር እና የተሰጧቸውን የአርዕስት መለያ ቁጥሮች
ይይዛል።
ፕሮግራሞች
አንድ የመንግሥት መ/ቤት ሰፊ የወጪ ዓላማዎችን የያዘ ፕሮግራሞች ሊኖሩት ይችላሉ። ፕሮግራሞች የንዑስ አርዕስት
የሂሳብ ምድብ ሲሆኑ ከፋ/ኢ/ል/ቢሮ ጋር ምክክር በማድረግ በመንግሥት መ/ቤቶች ሁለት አሀዝ ያለው መለያ ቁጥር
ይሰጣቸዋል።
የሥራ ክፍሎች
የመንግሥት መ/ቤቶች አብዛኛውን ጊዜ በአስተዳደር ክፍሎች ወይም በሥራ ክፍሎች ይከፋፈላል። የሥራ ክፍሎች የንዑስ
ንዑስ አርዕስት የሂሳብ ምድብ ሲሆኑ ከፋ/ኢ/ል/ቢሮ ጋር በሚደረግ ምክክር በመንግሥት መ /ቤቶች ሁለተ አሀዝ ያለው
መለያ ቁጥር ይሰጣቸዋል።
17
የሂሳብ አወቃቀር ሥርዓት
የበጀት ማንዋል ለኢት/ፌዴራላዊ መንግሥት የሂሳብ አወቃቀር ሥርዓት የሚያገለግሉ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የሂሳብ
መለያ ቁጥሮች አዘጋጅቷል።
ለአገር ውስጥ የገቢ መደብ ከ 1000 – 1799 ያሉትን የሂሳብ መለያ ቁጥሮች በመጠቀም፣
ለአገር ውስጥ ገቢ መደብ የተሰጡት የሂሳብ መለያ ቁጥሮች በሠንጠረዥ 2.3 ተመልክተዋል። የአያንዳንዱ የሂሳብ መለያ
ቁጥር መግለጫ ከዚህ ይቀጥላል። በሠንጠረዥ 2.3 የተዘረዘረው የገቢ መደብ መግለጫ ያልተሰጠበት ከሆነ በራሱ ግልጽ
አንደሆነ ተደርጎ ይወሰዳል።
18
ሠንጠረዥ 2.3
1000-1399 1. የታክስ ገቢ
1130-1140 - --
1131 - የፕላስቲክ ውጤቶች
1132 - ጥጥ፣ ድርና ማግ
1133 - ጨርቃ ጨርቅና ልብሶች
1134 - ኬሚካልና የኬሚካል ውጤቶች
1135 - ብረት ያለሆኑ የማዕድን ውጤቶች
1136 - ብረታ ብረትና ቆርቆሮ
1137 - ተሽከርካሪውችና መለዋወጫውች
1138 - ማሽኖች፣ ቋሚ ዕቃዎችና መለዋወጫዎች
1139 - እንጨትና እንጨት ውጤቶች
1140-1150 - --
1141 - ምግብ
1142 - የኤሌክትሪክ ዕቃዎችና መለዋወጫዎች
1143 - የጽህፈትና ሕትመት መሣሪያዎች
1144 - የእርሻና ደን ጤቶች
19
1160-1170 - --
1169 - ሌሎች ዕቃዎች
1170-1190 - የአገልግሎት ተጨማሪ ታክስ
1190-1199 - --
1200-1299 - --
1200-1220 - አክሳይዝ ታክስ
1201 - ነዳጅና የነዳጅ ውጤቶች
1202 - ስኳር
1203 - ጨው
1204 - ለስላሳ መጠጥ
1205 - ሚኒራል ውሃ
1206 - አልኮልና የአልኮል ውጤቶች
1207 - ቢራ
1208 - ትምባሆና የትምባሆ ውጤቶች
1209 - ጨርቃ ጨርቅና ልብሶች
1211 - ቆዳ
1212 - የፕላስቲክ ዕቃዎች
1213 - ከወርቅና ሌሎች ጌጣጌጦች
1219 - ወርቅና ሌሎች ጌጣጌጠች
1220-1240 - በሀገር ውስጥ ከሚመረቱ የቃዎች ሽያጭ ተርን ኦቨር ታክስ
1221 - ነዳጅና የነዳጅ ውጤቶች
1222 - ስኳር
1223 - ጨው
1224 - ምግብ
1225 - ለስላሳ መጠጥ
1226 - ሚነራል ውሃ
1227 - አልኮልና የአልኮል ውጠቶች
1228 - ቢራ
1229 - አልኮልና የአልኮል መጠጦች
1231 - ጥጥ፣ድርና ማግ፣ጭርቃ ጨርቅና ልብሶች
1232 - ቆዳና የቆዳ ውጤቶች
1233 - ኬሚካሎችና የኬሚካል ውጤቶች
1234 - ብረታብረትና ቆርቆሮ
1235 - የጽህፈት መሣሪያ
1236 - ብረት ያልሆኑ የብረት ውጤቶች
1237 - እርሻና የእርሻ ውጤቶች
1238 - እንጨትና የእንጨት ውጤቶች
1240-1250 -
1242 - ጋራ ዥ
1247 - የሂሳብ ምርመራ
1249 - ሌሎች እቃዎች
1250-1269 - የአገልግሎት ተርን ኦቨር ታክስ
1239 - ሌሎች ዕቃዎች
1244 -የልብስ ስፌት
1245 - ጥብቅና
1248 - ሥራ ተቋራጭ
1251 - ቴሌኮሙኒኬሽን
20
1252 - ጋራዠ
1253 - የልብስ ንፅህና መሰጫ
1254 - ልብስ ስፌት
1255 - ጥብቅና
1256 - ፎቶገራፍና ፎቶ ኮፒ ማንሳት
1257 - የሂሣብ ምርመራ
1258 - ሥራ ተቋረጭ
1259 - መኝታ ቤት
1261 - አማካሪነት
1262 - ኮሚሽን ኤጀንት
1263 - የህዝብ መዝናኝ
1264 - ፀጉር ማስተካከልና የቁንጅና ሳሎን
1265 - ቱሪስት ማስተናገድ
1266 - ዕቃ ማከራየት
1267 - ማስታወቂያ
1268 - የፀረ ተባይ መርጨት አገልግሎት
1269 - የፋይናንስ አገልግገሎት
1270-1279 - --
1279 - ሌሎች ዕቃዎች
1400-1420 - ከፈቃድና ከሌሎች ክፍያዎች
1401 - ከማዕድን ፈቃድ
1402 - ከጦር መሣሪያ ፈቃድ
1403 - ከደንና አፈር ጥበቃ አገልግሎት
1404 - ከከብት ገበያና ከዘላን አካባቢ ከሚኖር የከብት በረት አገልግሎት
1405 - ከአካባቢ ጥበቃ አገልግሎት
1406 - ከካርታና ፕላን አገልግሎተ
1407 - ከፖሊስ አገልግሎት
1408 - ከከተማ አስተዳደር አገልግሎት
1411 - ፓስፖርትና ቪዛ
1412 - የውጭ ሀገር ዜጎች ምዝገባ
1413 - የሥራ ፈቃድ
1414 - የፍርድ ቤት መቀጫ
1415 - ዳኝነት
1416 - ከተወረሱ ዕቃዎች ሽያጭ ገቢ
1417 - የንግድ ድርጅቶችና የባለሙያዎች ምዝገባና የንግድ ፈቃድ ክፍያ
1418 - የመጋዘን ኪራይ
1419 - የቴሌቪዥን አገልግሎት ክፍያ
1420-1430 - --
1430-1459 - ከመንግሥት የዕቃና የአገልግሎት ሽያጭ
1431 - የመንግሥት ጋዜጦች፣ መጽሔቶችና ህትመቶች ሽያጭ
1432 - የሕዝብ መገናኝኛ ዘዴዎች
1433 - የማስታወቂያ
1434 - የእንስሳት ህክምና አገልግሎት
1435 - የጤና አገልግሎት
1436 - የመድሃኒትና የህክምና ዕቃዎች ሽያጭ
1437 - የጤና ምርመራና ህክምና
1438 - የዕደ ጥበብ ውጤቶች ሽያጭ
21
1439 - የታተሙ ቅጾች
1441 - የወህኒ ቤቶች አስተዳደር
1442 - የምርምር እና ልማት
1443 - የሙያና የትምህርት ተቋሞች
1444 - መዝናኛ
1445 - የኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪዎች
1446 - የባህል አገልግሎት
1447 - የሜትሪዮሎጂ አገልግሎት
1448 - የካርታ ሥራ አገልግሎት
1449 - የሲቪል አቬሽን አገልግሎት
1451 - የመንገድ ትራንስፖርት አገልጎሎት
1452 - የሣይንስና ቴክኖሎጂ አገልግሎት
1453 - የብሄራዊ ፈተናዎች አገልግሎት
1454 - የፖስታ አገልግሎት
1455 - የግብርና ውጨቶች ሽያጭ
1456 - የደን ውጠቶች ሽያጭ
1459 - ከሌሎች ዕቃዎችና አገልግሎቶች
1460-1469 - የመንግሥት ኢንቨስትመንት ገቢ
1461 - የዘቀጠ ትርፍ
1462 - የመንግሥት የአክሲዮን ትርፍ ድርሻ
1463 - የብሔራዊ ሎተሪ
1464 - ከመልሶ ማበደር የወለድ ክፍያ ገቢ
1465 - ለመንግሥት ሠራተኞች ከተሠጠ ብድር ወለድ
1466 - ከመንግሥት የባንክ ሂሣቦች የሚገኝ ወለድ
1467 - የካፒታል ክፍያ
1468 - የገጠር መሬት መጠቀሚያ ክፍያ
1469 - የከተማ ቦታ ሊዝ
1470-1479 - --
1471 - የመንግሥት ድርግቶችን በሊዝ ከመሸጥ የሚገኝ ገቢ
1479 - ሌሎች ዕቃዎች
1480-1489 - መደበኛ ያልሆኑና ልዩ ልዩ ገቢዎች
1481 - በጨረታ ከሚሸጥ ስኳር የሚገኝ ገቢ
1482 - የቅድመ ጭነት ምርመራ አገልግሎት
1483 - የአገር ውስጥ እርዳታ ገቢ
1485 - ሌሎች ልዩ ልዩ ገቢዎች
1489 - ልዩ ልዩ ገቢዎች
1500-1599 - የካፒታል ገቢ
1501 - የተንቀሳቃሽና የማይንቀሳቀስ ንብረት ሽያጭ
1502 - በመጋዘን ያለ ዕቃ ሽያጭ
1503 - ከመንግሥት ንብረት የሚገኝ ሮያሊቲ
1504 - የፕራይቬታይዜሽን ገቢ
1505 - ከመልሶ ማበደር የዋና ገንዘብ ተመላሽ
1506 - የመንግሥት ካልሆኑ ምንጮች የሚደረግ የካፒታል ዝውውር
1600-1699 - የክልሎች/የወረዳ የበጀት ድጋፍ ገቢ
1600-1610 - ጥቅል የበጀት ድጋፍ ከገኢልሚ
1601 - የመደበኛ በጀት ድጋፍ
1602 - የካፒታል በጀት ድጋፍ
22
1620-1629 - ጥቅል የበጀት ድጋፍ ከገኢልቢ
1620 - ጥቅል የበጀት ድጋፍ ከገኢልቢ
1621 - የመደበኛ በጀት ድጋፍ
1622 - የካፒታል በጀት ድጋፍ
1000-1399 የታክሰ ገቢ
የታክስ ገቢዎች ለመንግሥት በህግ የተወሰኑ ክፍያዎች ናቸው። ከሌሎች መንግሥታት /ዓለም አቀፍ ድርጅቶች
ከሚገኝ ዕርዳታ በሰተቀር/ ሌሎች በፈቃደኝነት የሚደረጉ ክፍያዎች ታክስ ያልሆኑ ገቢዎች ስር ወይም ለካፒታል
ሀብት ማፍሪያ አንዲውሉ የተገኙ ከሆነ በካፒታል ገቢነት አንዲታዩ ይደረጋል።
1102 የኪራይ ገቢ
ኪራይ የሚባለው በአንድ ንብረት ለመጠቀም በውል መሠረት የሚከፈል ገንዘብ ነው። ከተከራዩ መኖሪያ ቤቶች፣
የቢሮ ህንፃዎች፣ የማምረቻ መሣሪያዎች፣ ዕቃዎች ወዘተ.. በሚገኝ ገቢ ላይ የሚከፈል ታክስ ለዚህም በምሳሌነት
ሊጠቀስ ይችላል።
23
1107 ከግብርና ሥራ ገቢ ግብር
ከግብርና ሥራ እንቅስቃሴ በሚገኝ ማናቸውም ዓመታዊ ገቢ ላይ የሚከፈል ግብር ነው። የገጠር መሬት
መጠቀሚያ ክፍያ እና የከተማ ቦታ ሊዝ፣ ታክስ ባልሆኑ ገቢዎች ክፍል ሥር ባለው የመንግሥት ገቢ ንዑስ ክፍል
ስር የሚካተቱ ናቸው።
1108 ሮያሊቲ
ሮያሊቲ የሚባለው የመሬት ኪራይ ወይም የስርሰት ወይም የቅጂ መብት በተቋቋመባቸው ነገሮች ለመጠቀም
የሚከፈል ነው። የሮያሊቲ ክፍያ አብዛኛውን ጊዜ በተፈጥሮ ሀብቶች/ምሳሌ ማዕድናት፣ ደኖች ወዘተ…/
የመጠቀም መብትን ለማገኘት የሚከፈል ነው።
በአዋጅ ቁጥር 68/85 አንደተሻሻለ በተደነገገው በአገር ውስጥ በሚመረቱ በተወሰኑ ዕቃዎች የተጣለ ታክስ ነው።
ኤክሳይዝ ታክስ ተፈጻሚ የሚሆንባቸው የሚከተሉት ምርቶቸ ናቸው።
በአዋጅ ቁጥር 68/85/በተሻሻለው/መሠረት በአገር ውስጥ በሚመረቱ ዕቃዎች ላይ የሚከፈል ታክስ ነው።
24
1226 - ሚነራል ውሃ
1227 - አልኮልና የአልኮል ውጠቶች
1228 - ቢራ
1229 - አልኮልና የአልኮል መጠጦች
1231 - ጥጥ፣ድርና ማግ፣ጭርቃ ጨርቅና ልብሶች
1232 - ቆዳና የቆዳ ውጤቶች
1233 - ኬሚካሎችና የኬሚካል ውጤቶች
1234 - ብረታብረትና ቆርቆሮ
1236 - ብረት ያልሆኑ የብረት ውጤቶች
1237 - እርሻና የእርሻ ውጤቶች
1238 - እንጨትና የእንጨት ውጤቶች
1239- ሌሎች ዕቃዎች
የአገልግሎት ሽያጭ ታክስ የሚባለው አገልግሎቱን በሰጠው ግለሰብ /ድርጅት/ በአገር ውስጥ ለተሰጠ አገልግሎት
በተፈጸመ ክፍያ ላይ እየተሰላ የሚከፈል ታክስ ነው። የትምህርት፣ የጤና፣ የውኃ አና የኤሌክትሪክ አገልግሎቶች
ከዚህ ታክሰ ነፃ ናቸው።
አብዛኞቹ የአገልግሎት የሽያጭ ታክሶች በአዋጅ ቁጥር 68/85 መሠረት የሚሰበሰቡ ናቸው።
1242 - ጋራ ዥ
1244 -የልብስ ስፌት
1245 - ጥብቅና
1251 - አማካሪነት
1252 - ኮሚሽን ኤጄንት
1253 - መዝናኛ
1254 - ፀጉር ማስተካከልና
1255 - ጥብቅና
1256 - ፎቶገራፍና ፎቶ ኮፒ ማንሳት
1257 - የሂሣብ ምርመራ
1258 - ሥራ ተቋረጭ
1259 - መኝታ ቤት
1269 - ሌሎቸ አገልግሎቶች
25
1271 የቴምብር ሽያጭ
1272 የቴምብር ቀረጥ
ይህ የመንግሥት ገቢ ክፍል ከታክስ፣ ከዕርዳታ፣ ከብድር ከቋሚ ንብረት ሽያጭ በመጋዘን ከሚገኙ ዕቃዎች ግዑዛዊ
ህልዎት ከሌላቸው ንብረቶች ሽያጭ እና ለካፒታል ንብረት ማፍሪያ እንዲውል በመንግሥት ስር ካልሆኑ
ድርጅቶች የሚገኘውን ሰጦታ አይጨምርም።
26
1431 - የመንግሥት ጋዜጦች፣ መጽሔቶችና ህትመቶች ሽያጭ
1432 - የሕዝብ መገናኝኛ ዘዴዎች
1433 - የማስታወቂያ
1434 - የእንስሳት ህክምና አገልግሎት
1435 - የጤና አገልግሎት
1436 - የመድሃኒትና የህክምና ዕቃዎች ሽያጭ
1437 - የጤና ምርመራና ህክምና
1438 - የዕደ ጥበብ ውጤቶች ሽያጭ
1439 - የታተሙ ቅጾች
1441 - የወህኒ ቤቶች አስተዳደር
1442 - የምርምር እና ልማት
1443 - የሙያና የትምህርት ተቋሞች
1444 - መዝናኛ
1445 - የኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪዎች
1446 - የባህል አገልግሎት
1447 - የሜትሪዮሎጂ አገልግሎት
1448 - የካርታ ሥራ አገልግሎት
1449 - የሲቪል አቬሽን አገልግሎት
1451 - የመንገድ ትራንስፖርት አገልግሎት
1452 - የሣይንስና ቴክኖሎጂ አገልግሎት
1453 - የብሄራዊ ፈተናዎች አገልግሎት
1454 - የፖስታ አገልግሎት
1455 - የግብርና ውጨቶች ሽያጭ
1456 - የደን ውጠቶች ሽያጭ
1459 - ከሌሎች ዕቃዎችና አገልግሎቶች
1500 የካፒታል ገቢ
27
የካፒታል ገቢ ከሚከተሉት ቋሚ ንብረቶች ሽያጭ የሚገኘውን ገቢ ይጨምራል። የመኖሪያ ህንፃዎች፣ መኖሪያ
ያልሆኑ ህንፃዎቸ፣ ሌሎች ግንባታዎች፣ ተሽከርካሪዎች ማሽኖች ሌሎች መሣሪያዎች በመጋዘብ የሚገኙ ዕቃዎች
ሽያጭ ግዙፋዊ ህልዎታ የሌላቸው ንብረቶች ሽያጭ አንዲሁም የካፒታል ንብረት ለማፍራት እንዲውል
የመንግሥት ካልሆኑ ምንጮች የሚገኝ እርዳታ ናቸው።
ሆኖም መሬት ማዕድናት አነስተኛ የእጅ መሣሪያዎች መለዋወጫች እና አነስተኛ ዋጋ ያላቸው መሣሪያዎች
ለወታደራዊ አገልግሎት የተያዙ ቋሚ ዕቃዎች እና ለመኖሪያ ከተያዙት በስተቀር ለወታደራዊ አገልግሎት የተያዙ
ህንፃዎች በዚህ የገቢ ዓይነት ሥር አይታቀፉም። የመንግሥት የልማት ድርጅቶች የካፒታል ንብረቶች መንግሥት
በእነዚህ የልማት ድርጅቶች ውስጥ ባለው የሀብት ድርሻ የተያዙ እንደሆነ ብቻ ተደርጎ ይወሰዳል። የሀብት ድርሻ
ሽያጭ በዚህ የገቢ ዓይነት ሥር የሚታይ አይደለም።
ገበያ የማረጋጋት ዓላማ ያላቸው በመንግሥት የሚሸጡ ስትራቴጂካዊ ጠቀሜታ ያላቸው በመጋዘን የሚገኙ
ዕቃዎች የአደጋ ጊዜ መጠባበቂያ ክምችት እና ገበያን ለማረጋጋት በመጋዘን የሚከማቹ ዕቃዎች በዚህ ሥር
ይጠቃለላሉ። ያገለገሉ ወይም ጥቅም የማይሰጡ ዕቃዎች ሽያጭ በዚህ ሥር መታየት የሌለበት ሲሆን በገቢ
ዓይነት 1485 ሌሎች ልዩ ልዩ ገቢዎች በሚለው ስር ሊጠቃለል ይገባል።
ሮያሊቲ የሚባለው በመሬት በመጠቀም ወይም በድርሰት ወይም በቅጂ የመጠቀም መብት በማግኘት የሚፈፀም
ክፍያ ነው። አብዛኛውን ጊዜ ክፍያ የሚፈጸመው በተፈጥሮ ሀብቶች ለመጠቀም በሚሰጥ መብት ነው። /ምሳሌ
፣ማዕድን ደን ወዘተ../
ይህ የገቢ ዓይነት የመንግሥት ካልሆኑ ምንጮት የካፒታል ንብረት ለማፍራት እንዲውል ለመንግሥት በፈቃደኝነት
የሚደረገውን ስጦታ ያካትታል። የመንግሥት አገልግሎት መስጫ ህንፃዎች ለመገንባት /የካፒታል መሣሪያ
ለማፍራት/ የሚደረገውን የካፒታል ስጦታ ሊጨምር ይችላል። ከግለሰቦች ለትርፍ ካልተቋቋሙ የግል ድርጅቶች
መንግሥታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች ከንግድ ድርጅቶች እና ከግል ክፍሉ ንግድ ድርጅቶች እንዲሁም ከመንግሥት እና
28
ከዓለም ዓቀፍ ድርጅቶች በስተቀር ከሌሎች ከማናቸውም ምንጮች በጥሬ ገንዘብ የሚደረገውን የካፒታል ስጦታ
ያጠቃልላል።
ከፋ/ኢ/ል/ቢሮ ለዞን ፋ/ኢ/ል/መምሪያ ለወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤቶች የሚላኩ የመደበኛ በጀት ወጪዎች ድጎማ የገቢ
ዝውውሮችን መመዝገቢያ
ከፋ/ኢ/ል/ቢሮ ለዞን ፋ/ኢ/ል/መምሪያ ለወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤቶች የሚላኩ የካፒታል በጀት ወጪዎች ድጎማ የገቢ
ዝውውሮችን መመዝገቢያ
ሠንጠረዥ 2.4
29
የወጭ አገር እርዳታ
የሂሳብ መደብ የለጋሽ ሥም
2010 - የፐብሊክ ሴክተር አቅም ግንባታ ፕሮግራም
2011 - ዓለም አቀፍ የአቶሚክ ሃይል ድርጀት
2012 - ዓለም አቀፍ የስንዴና በቆሎ ምርምር ማዕከል
2013 - ዓለም አቀፍ የሲቪል አቪዬሽን ድርጅት
2014 - ዓለም አቀፍ የልማት ማህበር/አይዲኤ
2015 - የዓለም አቀፍ የልማት ምርምር ማዕከል
2016 - ዓለም አቀፍ የእርሻ ልማት ፈንድ/ኢፋድ/
2017 - የአለም የስራ ድርጅት/አይኤልኦ/
2018 - ዓለም አቀፍ የገንዘብ ድርጅት/አይ.ኤም.ኤፍ.
2019 - ዓለም አቀፍ የተፈጥሮ እንክብካቤ ማሕበር
2021 - የኖርዲክ ልማት ፈንድ
2022 - የነዳጅ ላኪ ሐገሮች ድርጅት/ኦፔክ/
2023 - የቴክኒክ ተራድኦ ፈንድ
2024 - የተ.መ.ካፒታል ልማት ፈንድ
2025 - የተ.መ.የሕፃናት መርጃ ድርጃት/ዩኒሴፍ/
2026 - የተ.መ.እንክብካቤና ልማት ፈንድ/ዩኤንሲዲኤፍ/
2027 - የተ.መ.የልማት ፕሮግራም/ዩኤንዲፒ/
2028 - የተ.መ.የትምህርት የሳይንስና የባሕል ድርጅት/ዩኔስኮ/
2029 - የተ.መ.የሕዝብ ጉዳይ ፈንድ/ዩኤንኤፍፒኤ/
2031 - የተ.መ.የሱዳኖ ሳህሊያን ቢሮ/ኢንሶ/
2032 - አለም ባንክ
2033 - የአለም የምግብ ፕሮግራም/ደብሊውኤፍፒ/
2034 - የአለም የጤና ድርጅት/ደብሊውኤኤችኦ/
2035 - አለም አቀፍ የዱር አራዊት ፈንድ
2036 - የተ.መ.ኢንዱስትሬ ልማት ድርጅት/ዩኒዶ/
2037 - የጀርመን የሥገ ደዌ መከላከየ ማህበር
2038 - የምስራቅና ደቡብ አፍሪካ የንግድ ቀጣና/ኮሜሳ/
2039 - የናይጄሬያ ተረስት ፈንድ/ኤንቲኤፍ/
2041 - ዓለም ዓቀፍ የአካባቢ እንክብካቤ ፈንድ
2042 - የበሽታዎች መቆጣጠሪያ ማዕከል
2043 - ዓለም አቀፍ ፈንድ
2044 - የጤና ስነሕዝብና ምጣኔ ምግብ ቡድን/ኤችፒኤን
2045 - ለክትባት ዓለም አቀፍ ትብብር/ጂኤቪአይ
2046 - ጋላክሶ ስሚዝ
2047 - ላየንስ ክለብ ኢንተርናሽናል/ኤልሲአይ
2048 - ሜርኮ ኩባኒያ
2067 - ኔዘርላንድ
የለጋሽ የገቢ ኮድ ከ 2000-2099 የለጋሽ ኮድ መለያ ነው። የውጭ ዕርዳታ በሚገኝበት ጊዜ እነዚህ ኮዶች
ይወስዳሉ። ወርኃዊ የካፒታል ወጪዎች በበጀት ተቋም ኮድና በለጋሽ የገቢ ኮድ ሪፖርት መደረግ ይኖርባቸዋል።
30
በበጀት ማሰታወቂያ እንደደረሰ እያንዳንዱ ፕሮጀክት አራት አሀዝ ያለው የፋይናንስ ኮድ/ የፋይናንስ ምንጭ
የሚያመላክቱ/ የእያንዳንዱ ለጋሽ ለውጭ ዕርዳታ ያደረጋቸው የዕርዳታ አስተዋጽኦ በየፕሮጀክቱ የኮድ ቁጥር
ከ 2100-2999 የሚዘረዘር ይሆናል። እነዚህ የመለያ ኮዶች ለዚሁ ተገባር አንጂ ለሌሎች ሂሳብ ሥራዎች
አያገለግሉም።
የአበዳሪ የገቢ ኮድ ከ 3000-3099 ያሉት አበዳሪዎችን የሚያመለክቱ ናቸው። የውጭ ብድር በሚገኝበት ጊዜ
እነዚህ ኮዶች ይስተናገዳሉ። ወርኃዊ የካፒታል ወጪዎች በበጀት ተቃም ኮድና በአበዳሪ የገቢ ኮድ ሪፖርት መደረግ
ይኖርባቸዋል።
የበጀት ማሰታወቂያ አንደደረሰ አያንዳንዱ ፕሮጀክት አራት አሀዝ ያለው የፋይናንስ ምንጭ ኮድ የአያንዳንዱን
አበዳሪ የወጭ ብድር በፕሮጀክት ስምና መለያ ኮድ ከ 3100-3999 ተዘርዝሮ መታየት አለበት። አነዚህ የመለያ
ኮዶች ለዚሁ ተግባር እንጂ ለሌሎች ሂሳብ ሥራዎች አያገለግሉም።
ሠንጠረዥ 2.6
የወጪ መደብ
መለያ ቁጥር ክፍል/ንዑሰ ክፍል/የወጪ መደብ
6100- ሰብአዊ ለሆኑ አገልግሎቶች
6110- ለሠራተኛ የሚከፈል ክፍያዎች
6111 - ለቋሚ ሠራተኞች ደመወዝ
6112 - ለመከላከያ ሠራዊት ደመወዝ
6113 - ለኮንትራት ሠራተኞች ምንዳ
6114 - ለቀን ሠራተኞች ምንዳ
6115 - ለውጭ የኮንትራት ሠራተኞች ምንዳ
6116 - ለሠራተኞች የሚደረጉ የተለያዩ ክፍያዎች
6120- አበል / ጥቅማ ጥቅም
6121 - ለቋሚ ሠራተኞች አበል
6122 - ለመከላከያ ሠራተኞች አበል
6123 - ለኮንትራት ሠራተኞች አበል
6124 - ለውጭ የኮንትራት ሠራተኞች አበል
6130- የመንግሥት የጡረታ መዋጮ
6131 - ለቋሚ ሠራተኞች የጡረታ መዋጮ
6132 - ለመከላከያ ሠራዊት አባላት የጡረታ መዋጮ
6200- ለዕቃዎች እና አገልግሎቶች
31
የወጪ መደብ
መለያ ቁጥር ክፍል/ንዑሰ ክፍል/የወጪ መደብ
6210- ዕቃዎችና አቅርቦቶች
6211 - ለደንብ ልብስ፣ ለልብስ፣ ለፍራሽና አልጋ ልብስ
6212 - ለአላቂ የቢሮ ዕቃዎች
6213 - ለሕትመት
6214 - ለአላቂ የሕክምና ዕቃዎች
6215 - ለአላቂ የትምህርት ዕቃዎች
6216 - ለምግብ
6217 - ለነዳጅና ቅባቶች
6218 - ለሌሎች አላቂ ዕቃዎች
6219 - ለተለያዩ መሣሪያዎች
6221 - ለግብርና፣ ለደን እና ለባህር ግብዓቶች
6222 - ለእንስሳት ሕክምና የሚያገለግሉ አላቂ ዕቃዎች እና መድሀኒቶች
6223 - ለምርምር እና ለልማት አላቂ ዕቃዎች
6224 - ለጦር መሣሪያና ጥይት
6230- ለጉዞና ለመስተንግዶ አገልግሎቶች
6231 - የውሎ አበል
6232 - ለትራንስፖርት ክፍያ
6233 - ለመስተንግዶ
6240- ለዕድሳት እና ጥገና አገልግሎቶች
6241 - ለተሽከርካሪዎች እና ለሌሎች መጓጓዣዎች ዕድሳት እና ጥገና
6242 - ለአውሮፕላን እና ጀልባዎች ዕድሳት እና ጥገና
6243 - ለፕላንት፣ ለማሽነሪ እና ለመሣሪያ ዕድሳት እና ጥገና
6244 - ለህንፃ፣ ለቁሳቁስ እና ለተገጣጣሚዎች ዕድሳት እና ጥገና
6245 - ለመሠረተ ልማት ዕድሳት እና ጥገና
6246 - ለወታደራዊ መሣሪያዎች ዕድሳት እና ጥገና
6250- በውል ለሚፈፀሙ የአገልግሎት ግዠዎች
6251 - በውል የሚፈጸሙ የሙያ አገልግሎቶች
6252 - ለኪራይ
6253 - ለማስታወቂያ
6254 - ለኢንሹራንስ
6255 - ለጭነት
6256 - ለአገልግሎት ክፍያዎች
6257 - ለኤሌክትሪክ አገልግሎት ክፍያ
6258 - ለቴሌኮሙኒኬሽን አገልግሎት ክፍያ
6259 - ለውኃ፣ ፖስታ እና ለሌሎች አገልግሎት ክፍያዎች
6270- ለሥልጠና አገልግሎቶች
6271 - ለአገር ውስጥ ሥልጠና
6272 - ለውጭ አገር ሥልጠና
6280- ለአደጋ ጊዜና ለእስትራቴጂካዊ ዕቃዎች ክምችት
6281 - ለመጠባበቂያ ምግብ ክምችት
6282 - ለነዳጅ ክምችት
6283 - ለሌሎች የመጠባበቂያ ክምችት
6300- ቋሚ ንብረቶች እና ግንባታ
6310- ቋሚ ንብረቶች
6311 - ለተሽከርካሪዎች እና ለሌሎች እንደተሽከርካሪ ላሉ መጓጓዣዎች መግዣ
32
የወጪ መደብ
መለያ ቁጥር ክፍል/ንዑሰ ክፍል/የወጪ መደብ
6312 - ለአውሮፕላኖች፣ ለጀልባዎች ወ.ዘ.ተ. መግዣ
6313 - ለፕላንት፣ ለማሽነሪ እና ለመሣሪያ መግዣ
6314 - ለሕንፃ፣ ለቁሳቁስ እና ለተገጣጣሚዎች መግዣ
6315 - ለቀንድ ከብቶች እና ለማጓጓዣ የሚውሉ እንስሳት መግዣ
6316 - የወታደራዊ መሣሪያዎች መግዣ
6320-ግንባታ
6321 - ለቅድመ ግንባታ ሥራዎች
6322 - ለመኖሪያ ሕንፃዎች ግንባታ
6323 - ለመኖሪያ ያልሆኑ ሕንፃዎች ግንባታ
6324 - ለመሠረተ ልማት ግንባታ
6325 - የወታዊ አገልግሎት ለሚውሉ ግንባታዎች
6326 - ለግንባታ ሱፐርቪዥን
6400- ሌሎች ክፍያዎች
6410- ድጎማ፣ ኢንቨስትመንት እና ስጦታ ክፍያዎች
6411 - ለክልሎች እና ለመስተዳድር ምክር ቤቶች ድጎማ
6412 - ለተቋሞች እና ድርጅቶች እርዳታ፣ መዋጮና ድጎማ
6413 - ለመንግስት ኢንቨስትመንት መዋጮ
6414 - ለዓለም አቀፍ ድርጅቶች መዋጮ
6415 - ለመጠባበቂያ
6416 - ለግለሰቦች እና ድርጅቶች ካሣ
6417 - ለግለሰቦች እርዳታ እና ስጦታ
6418 - ለጥሪት ፈንድ መዋጮ
6419 - ክፍያዎች
6430- የዕዳ ክፍያዎች
6431 - ለውጭ አገር ብድር የዋና ገንዘብ ክፍያ
6432 - ለውጭ አገር ብድር የወለድ እና የባንክ አገልግሎት ክፍያ
6433 - ለአገር ውስጥ ብድር የዋና ገንዘብ ክፍያ
6434 - ለአገር ውስጥ ብድር የወለድ እና የባንክ አገልግሎት ክፍያ
ሰብዓዊ የሆኑ አገልግሎቶች በአራቱ የወጪ ክፍሎች ውስጥ አንዱ የወጪ ክፍል ነው። ሰብዓዊ በሆኑ አገልግሎቶች
የወጪ ክፍል /6100/ ሥር ወጪዎች በሶስት ንዑሰ የወጪ ክፍሎች ተከፋፍለዋል። 6110 “ለሠራተኛ የሚከፈል
ክፍያ ፣ 6120 “ለአበልና ጥቅማ ጥቅም” አና 6130 “የመንግሥት ጡረታ መዋጮ” ። መንግሥት ለጡረታ
የሚያደርገው ክፍያ “ሌሎች ክፍያዎች” /6400/ ስር ተመዝግቧል። ለአንደ የወጪ ማዕከል የተደረጉ ሰበዓዊ የሆኑ
አገልግሎቶች ጠቅላላ ወጪ በ 6100 የወጪ ክፍል ሰር ካሉት መደቦች ሊሰጥ ይችላል፡፡ አንድ ግለሰብ ለመንግስት
33
ለሚሰጠው አገልግሎት የተደረገ ጠቅላላ ወጪ ፣ ደመወዝ፣ አበል ካለ እና መንግሥት የሚያደርገውን መዋጮ /ካለ/
ይጨመራል፡፡
ለሠራተኞች የሚከፈል ክፍያ ነው፡፡ ለሠራተኞች ክፍያ ለመንግስት አገልግሎት በሚሰጡ የሠራተኞች ምድብ
የተከፋፈለ ነው፡፡ እነዚህም ቋሚ ሠራተኞች፣ መካከል ሠራዊት፣ የኮንትራት ሠራተኞች እና ራሳቸውን ችለው
የኮንትራት አገልግሎት የሚሰጡ ሠራተኞች ናቸው፡፡ ለሠራተኞች የሚከፈል ክፍያ ከጥሬ ገንዘብ ውጪ ያለውን
እና ለሠራተኞች ያለምንም ክፍያ ወይም በዝቅተኛ ዋጋ በዓይነት የሚሰጠውን ምግብ፣ ልብስ እና መጠለያ
የሚጨምር አይደለም፡፡ በዓይነት የሚደረግ ክፍያ በ 6120 " አበል" በሚለው ስር ይሸፈናል፡፡
በመደብ 6111 ከተገለጹት ቋሚ ሰራተኞች በስተቀር የኮንትራት ሰራተኞች የሚባሉት በሲቪል ሰርቪስ ኪሚሽን
ወይም ነፃ የአስተዳደር አቋም በተሰጣቸው የመንግስት መ/ቤቶች የዳይሬክተሮች ቦርድ የጸደቀ ደመወዝ
የሚከፈላቸው ሆነው ነገር ግን በተጠቀሱት አካላት የተፈቀደ የሥራ መደብ የሌላቸው ሠራተኞች ናቸው፡፡
የቀን ሠራተኞች የሚባሉት የተፈቀደ የሥራ መደብ የሌላቸው እና የሚከፈላቸው ደመወዝ በሲቪል ሰርቪስ
ኮሚሽን ያልጸደቁ ሠራተኞች ናቸው፡፡ እነዚህ ሠራተኞች ጊዜያዊ ሠራተኞች ሲሆኑ የሥራቸው ሁኔታ
የሚወስነው የሚሰሩበት መ/ቤት ነው፡፡
የውጭ የኮንትራት ሰራተኞች የሚባሉት በቴክኒክ እርዳታ ስምምነት መሠረት አገልግሎት ለመስጠት
የኮንትራት ሠራተኞች ውል የገቡ ራሳቸውን ችለው የሚሰሩ ግለሰቦች ናቸው፡፡ የኮንትራት የአገር ውስጥ ውይም
ከውጭ አገር የመጡ ሠራተኞች ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ እነዚህ ሠራተኞች በሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ወይም ዕዳ
34
የአስተዳደር አቋም በተሰጠው የመንግሥት መ/ቤት የዳይሬክተሮች ቦርድ የፀደቀ የሥራ መደብ እና ደመወዛቸው
የላቸውም ፡፡
ይህ የውጪ መደብ ሠራተኞች ለሚሰጡ አገልግሎት ከዚህ በላይ ከተገለጹው ደመወዝ በተጨማሪ ወይም
በደመወዝ ምትክ የሚፈጸም ክፍ በሚኖርበት ጊዜ ያለገግላል፡፡ ለምሳሌ ይህ ወጪ የትርፍ ሰዓት ክፍያን እና
ጉርሻን /ቦነስ/ ይጨምራል፡፡
አበል እና ጥቅማ ጥቅም በቅጥር ውል በተመለከተው መሠረት ለሠራተኞች ጥሬ ገንዘብ የሚከፈል ወይም
በዓይነት የሚሰጥ ነው፡፡ ለምሳሌ ተሸከርካሪ፣ ቤት የመዘዋወሪያ አበል፣ የበረሀ አበል እና የዳይሬክተሮች ቦርድ
አባል በመሆን ለተሰጠ አገልግሎት የሚፈጸም ክፍያን ይጨምራል፡፡
የቋሚ ሠራተኞች አበል የሚባለው ወይም በዓይነት የሚሰጥ ነው፡፡ ለምሳሌ የሚከተሉትን ይጨምራል፡፡ ለፖሊስ
ሠራዊት አባላት ምግብ፣ ነዳጅ እና የመኖሪያ ወጪን ለመሸፈን የሚከፈል አበል ሌላው ለሆን የሚችለው
ሠራተኞች ለሚገኙት የሕክምና አገልግሎት በግል ወይም ለመንግሥት የሕክምና ተቋማት የሚፈጽም ሙሉ
ወይም ከፊል ክፍያ ነው፡፡
ለኮንትራት ሠራተኞች የሚከፈል አበል የሚባለው በሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን የጸደቀ፣ ለእነዚህ ሠራተኞች በጥሬ
ገንዘብ የሚከፈል በዓይነት የሚሰጥ አበል ነው፡፡
በውጭ የገንዘብ እርዳታ ለሚመደቡና ራሳቸውን ችለው ለሚተዳደሩ የኮንትራት ሠራተኞች በውሉ መሠረት
በጥሬ ገንዘብ የሚከፈል ወይም በዓይነት የሚሰጥ አበል ነው፡፡
ይህ የወጪ ንዑስ ክፍል ለአንድ ሠራተኛ የጡረታ ክፍያ እንዲውል መንግሥት የሚያደርግው መዋጮ ነው፡፡
ለቋሚ የመንግስት ሠራተኞች ጡረታ እንዲውል መንግስት ለጡረታ ፈንድ የሚያደርግ መዋጮ ነው፡፡
ይህ ንዑስ የወጪ ክፍል በዕለት ተዕለት የሥራ እንቅስቃሴ ውስጥ ጥቅም ላይ የሚውሉ አላቂ ዕቃዎች
ይጨምራል፡፡ አላቂ ዕቃዎች ከአንድ ዓመት በላይ ለሆነ ጊዜ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ሊኖራቸው የሚችል ቢሆንም
በአንድ ዓመት ውስጥ እንደሚያልቅ ተደርጎ ሊወሰድ ይባል፡፡ የቢሮ አላቂ ዕቃዎች እና ምግብ ለዚህ ምሳሌ ሊሆን
ይችላል፡፡
ይህ የወጪ መደብ ለመከላከል እና ለፖሊስ ሠራዊት አባላት የደንብ ልብስ፣ የሆስፒታል ሠራተኞች የሥራ ልብስ
እንዲሁም የሥራ ልብስ ለሚገባቸው ሠራተኞች እና ለቴክኒሽያኖች የሚውል ወጪ ነው፡፡ ድንኳን፣ የአልጋ
ልብስ፣አንሶላ፣ የትራስ ልብስ፣ ብርድ ልብስ እና የመክላክያ ሠራዊት አባላት ጠይት ለመያዝ የሚመጣባቸው
በምላሌነት ሊጠቀሱ ይችላል፡፡
ይህ የወጪ መደብ የቢሮ ሥራን ለማሄድ ጥቅም ላይ የሚውሉ አላቂ ዕቃዎች ሁሉ ያካተታል፡፡ የጽሕፈት
መሣሪያ፣ የታተሙ ቅጾች፣ የታይፕራይተር ሪባኖች፣ የፕሪንተር ካርትሪጅ፣ ዲስኬት ወ.ዘ.ተ. በምሳነት ሊጠቀሱ
ይችላል፡፡
ግዙፋዊ ህልዎት የሌላቸው ንብረቶች የሚባሉት ከዕዳ ጋር ባለመዛመዳቸው ሌሎች የይገባኛል ጥያቄ የሚያስነሱ
ናቸው፡፡ እነዚህ የማዕድን ክምችቶችን እና የዓሣ ሀብትን የመጠቀምን መብቶች እና መሬትን ፣ የፈጠራ
መብትን፣ የድርሰትና የክነ-ጥበብ ጥበቃ መብትን እና የንግድ ምልክቶችን በኮንትራት ወይም በሊዝ የመያዝ
መብትን ይጨምራል፡፡
6213 ሕትመት
36
ይህ የወጪ መደብ በመንግስት ወይም በግል ማተሚያ ቤቶች ለሚከናወን ለማናቸውም የሕትመት ስራ
የወጣውን ወጪ ሁሉ ይጨምራል፡፡ የትምህርት ሚኒስተር የሚያሳትማቸው የመማሪያ መፃሐፍት ግን በዚህ
የወጪ መደብ ሳይሆን በወጪ መደብ 6215 " የትምህርት አቅርቦት" በሚለው ስር የሚመደቡ ይናል፡፡
ይህ የወጪ መደብ በሕክምና ተቋምች ውስጥ ሕመምን ለማዳን ወይም ለመከላከል አገልግሎት ላይ የሚውሉ
ማናቸውንም ዕቃዎች እና መድኋኒቶች ይጨምራል፡፡ ለምሳሌ የሕክምና ዕቃዎች የሚባሉት የደም ናሙናዎች
ለመቀበያነት የሚያለግሉ መስታወቶችን እና መርፌዎችን ይጨምራል፡፡ ኦፕራሲዮን ክፍል ውስጥ የሚለበሰ
ልብስ፣ ፍራሽና አልጋ ልብስ በሚለው ሥር ይመደባሉ፡፡ ኦፕራሲዮን ክፍል ውስጥ የሚለብስ ልብስ እና ጓንትን
ጨምሮ የስራ ልብሶች በወጪ መደብ 6211 የደንብ ልብስ ፣ የሥራ ፔኒስሊን፣ ክሎሮኪን እናፔታነስን
ጨምራሉ፡፡ ለሆስፒታሉ፣ ጤና ጣቢያዎች ለጤና ማዕከሎች እና ለሕክምና ላባራቶሪዎች የሥራ መከናወኛ
የሚያለግሉ አላቂ ዕቃዎችን እና አቅርቦቶችን ለመግዛት የሚወጣው ወጪ ሁሉ በዚህ የወጪ መደብ ስር
ይመደባል፡፡ እንደ ማይክሮስኮፕ፣ ራጂ፣ ማቀዝቀዣ ያሉ መሣሪያዎችን ለመግዛት የሚወጣው ወጪ ሁሉ በወጪ
መደብ ቁጥር 6313 የፕላንት፣ ማሽነሪ እና የመሣሪያ ግዥ በሚለው ስር ይመዘገባል፡፡
ይህ የወጪ መደብ በመማር ማስተማር ተግባር በማመሳከሪያነት የሚያለግሉትን የተፃፉ፣ በጆሮ ሚደመጡ እና
በዓይን የሚዩትን ሁሉ ይጨምራል፡፡ ለትምህርት መሣሪያዎች ምሳሌ ሊሆኑ የሚችሉት መማሪያ መፃሕፍትን፣
ማመሳከሪያ መፃሕፍትን፣ ጆርናሎችን፣ መጽሐፍቶችን ፣ ጋዜጣዎችን፣ ጠመኔ፣ ወረቀት፣ እርሳስ መዛግብት፣
የሥነ ጥበብ ዕቃዎችን ወ.ዘ.ተ ይጨምራሉ፡፡ የትምህርት ሚኒስቴር የሚያሳትማቸው የመማሪያ መፃሕፍት
በዚህ የወጪ መደብ ይካተታሉ፡፤
6216 ምግብ
ይህ የወጪ መደብ በሆስፒታሎች ውስጥ ተኝተው ለሚታከሙ ህሙማን ፣ በማሪሚያ ቤቶች ውስጥ ለሚገኙ
ታራሚዎች እና በትምህርት ተቋማት ውስጥ ላሉ ተማሪዎች የሚውለውን ምግብ ይጨምራል፡፡ በአደጋ ጊዜ
ወይም ለምግብ መጠባበቂያ ክምቶች በብዛት የሚገዛው ወይም በእርዳታ የሚገኘው ምግብ በዚህ የወጪ መደብ
ስር ሳይሆን በወጪ መደብ 6281 ስር ይጠቃላል፡፡
ይህ የወጪ መደብ በችርቻሮ እና በጅምላ የሚገዛውን ነዳጅ እና ቅባት ያካትታል፡፡ ለጋራ አገልግሎት ለሚውሉ
ማዳያዎች በጅምላ የሚገዛ ነዳጅ እና ወይም ቅባት ወይም ለጀኔሬተሮች ለዚህ ምሳሌ ሊሆን ይችላል፡፡
37
6218 ሌሎች ዕቃዎች እና አቅርቦቶች
ይህ የወጪ መደብ ሌሎች ማናቸውንም አላቂ ዕቃዎችን ወይም አቅርቦቶችን ያካትታል፡፡ የሚከተሉት
በምሳሌነት ሊጠቀሱ ይችላሉ፡፡ የእንስሳት መኖ እና የጽዳት ዕቃዎች/ሳሙና፣ የመጸዳጃ ቤት መርዞች ፣ ቡሩሾች
ወ.ዘተ…/ልዩ ልዩ መሣሪያዎች ይህ የወጪ መደብ ዋጋቸው ከብር 200 በታች የሆነ ወይም በመደበኛ ከአንድ
ዓመት በላይ አገልግሎት የሚሰጡ መሣሪያዎች ይጨምራል፡፡ የሚከተሉት በምሳሌነት ሊጠቀሱ ይችላሉ፡፡
አነስተኛ የእጅ መሣሪያዎች እና እንደ ስቴፕለር ያሉ የቢሮ መሣሪያዎች፣
እነዚህ መሳሪያዎች የጠቀሜታ ዋጋቸው ከ 200 ብር ያነሰ የአገልግሎት ዘመናቸው ከአንድ ኣመት የበለጠ፣
ለአብነት አነስተኛ ዕቃዎችና መሣሪያዎች እንደሰቴፕለር የመሳሰሉት ያካትታል፡፡
ይህ የወጪ መደብ የመንግስት የግብርና ፣ የደን እና የባህር ሀብት ልማት ተቋማት የሚጠቀሙባቸው ግብዓቶች
ሁሉ ይጨምራል፡፤ የሚከተሉት በምሳሌነት ሊጠቀሱ ይችላሉ፡፡ ማዳበሪያ ፣ ዘር፣ ተባይ ማጥፊያ እና የግብርና፣
የደን እና የባህር ሀብት ምርቶችን የሚረዱ የመንግስት ተቋማት የሚጠቀምባቸው ሌሎች ማናቸውም
ግብዓቶች፣
ይህ የወጪ መደብ የእንስሳት ሕክምና አገልግሎት የሚሰጡ የመንግስት ተቋሞች የሚጠቀሙባቸውን እንስሳት
አቅርቦቶች እና መድኃኒቶችን ይጨምራል፡፡ ሚከተሉት በምሳሌነት ሊጠቀሱ ይችላሉ፡፡ የሳይንስ መሳሪያዎች
ኬሚካሎች እና በመስታወት የተሰሩ የላባራቶሪ ዕቃዎች፣
ይህ ወጪ መደብ በፖሊስ ሰራዊት፣ በሕዝብ ፀጥታ ሠራተኞች እና በመከላክያ ሠራዊት የሚገዙትን ጥይቶች
እና የጦር መሣሪያዎች ይጨምራል፡፡ የሚከተሉት በምሳሌነት ሊጠቀሱ ይችላሉ፡፡ የቀላል መሣሪያ ጥይቶች፣
የመድፍ ጥይት እና ተወንጫፊ መሣሪያዎች፣
38
ይህ ንዑስ የወጪ ክፍል የመንግስት ሰራተኞች ከሚያደርጉት ጉዞ ጋር የተያያዙ ወጪዎችን የሚያጠቃልል
ሆኖ የሚከተሉትን አይጨምርም፡፡ የወጪ መደብ 6241 የተሸከርካሪዎች እና የሌሎች መጓጓዣዎች
እድሳት፣ ጥገና እና ወጪ መደብ 6217 ነዳጅ እና ቅባቶች፣ የመስተንግዶ የአገልግሎት ወጪ
የሚመለከተው ከመንግስት ስራ ጋር የተያያዘውን ብቻ ነው፡፡
6231 ውሎ አበል
ውሎ አበል ማለት ጉዞ ለሚያደርጉ የመንግስት ሠራተኞች የሚከፈል መጠኑ የተወሰነ ክፍያ ሲሆን፣
የመኝታ፣ የምግብ ፣ እና ተጓዳኝ ወጪዎችን ያጠቃልላል፡፡
ይህ የወጪ መደብ ቀጥተኛ የሆኑ የመጓጓዣ ወጪዎችን ይጨምራል፡፡ ሚከተሉት በምሳሌነት ሊጠቀሱ
ይችላ፡፡ የአውሮፕላን ትኬትቶች ፣ የአውቶብስ ወጪ፣ የታክሲ ወጪ፣ የኮቴ ክፍያ እና ማዘዋወሪያ
ክፍያ፡፡ ይህ የወጪ መደብ፣ በወጪ መደብ 6217 ነዳጅ እና ቅባት በሚለው ስር የሚጠቃለሉትን
የተሸከርካሪዎች ማንቀሳቀሻ ወጪዎች እንዲሁም በወጪ 6241 የተሸከርካሪዎች እና ሌሎች ማጓጓዣዎች
ዕድሳት እና ጥገና በወጪ መደብ 6242 የአውሮፕላን እና የጀልባዎች ዕድሳት እና ጥገና ስር የሚከተሉትን
የመጓጓዣጫች ሚመለከት አይደለም፡፡
6233 መስተንግዶ
39
ይህ የወጪ መደብ ለተሸከርካሪዎች፣ ለሞተር ብስክሌቶች፣ ብክሊቶች፣ እድሳት የሚወጣውን
የመለዋወጫ ዕቃዎች እና የጉልበት ዋጋ የሚያካትት ነው፡፡
ይህ የወጪ መደብ የመንገድ፣ የግድብ፣ የአውሮፕላን ማረፊያ መንገዶች ማስተናገጃ፣ የድልድይ፣ የውኃ
ቦይ፣ የመስኖ ስራ፣ የፈሳሽ ማስወገጃ እና የሌሎች መሠረተ ልማት አውታሮች ቀላል ዕድሳት፡፡
ይህ ንዑስ የወጪ መደብ ክፍል በአገር ውስጥ ወይም በውጭ አገር ከግለሰቦች ወይም ከድርጅቶች
የሚፈጸም ማናቸውን የአገልግሎት ግዥ የሚመለከት ነው፡፡ የህትመት ውሎች እና የምክር አገልግሎት
በምሳሌነት ሊጠቀሱ ይችላሉ፡፡
40
በምሳለኔት ሊጠቀሱ ይችላሉ፡፡ የምክር አግልግሎት ጥናት የሕክምና ምርመር በመንግስት መ/ቤቶች
የሚከናወን የካርታ እና የቅየሳ ስራ እንዲሁም የምህንድስና ምክር አገልግሎት፣
6252 ኪራይ
ይህ የወጪ መደብ ለቋሚ ንብረት በጥሬ ገንዘብ የሚከፈል የኪራይ ወጪን ይጨምራል፡፡ የሚከተሉት
በምሳሌነት ሊጠቀሱ ይችላሉ፡፡ ኮምፒውተሮች ፣ማሽን፣ ሕንፃ እና የመሠረት ልማት አውታሮች ሊዝ፣
ለምሳሌ ወደ ማጋዝን ፣
6253 ማስታወቂያ
በሕዝብ መገናኛ ዘዴዎች ፣በሬዲዮ፣ በጋዜጣ እና በቴሌቪዥን ለሚነገር ማታወቂያ ሚደረግ ማናቸውም
ክፍያ በዚህ የወጪ መደብ ስር ይጠቃለላል፡፡ ለክፍያ የሥራ መደቦች፣ ለጨረታ እና ለተመሳሳይ ጉዳዮች
ለሚናገር ማስታወቂያ የሚደረግ ክፍያ ለዚህ ዓይነቱ ወጪ በምሳሌነት ሊጠቁ ይችላሉ፡፡
6254 ኢንሹራንስ
6255 ጭነት
41
6258 የቴሌኮሙኒኬሽን አግልግሎት ክፍያ
ለውኃ፣ ለውኃ መስመር መዘርጊያ እና በሌሎች የአገልግሎት ክፍያ የወጪ መደቦች ያልተመለከቱ
ክፍያዎችን ያጠቃልላል፡፡
ይህ ንዑስ የወጪ ክፍል ለመንግስት ሠራተኞች በአገር ውስጥና በውጭ አገር የሚሰጠውን ስልጠና
ያካትታል፡፡
ይህን ንዑስ የወጪ ክፍል ለመጠባበቂያ የሚቀመጥ እህል እና ለአገሪቱ ልዩ ጠቀሜታ ላላችው ሌሎች
የተደረገውን ወጪ እንዲሁም ገቢያን የማረጋጋት ተግባር ያላቸው የመንግስት አካላት ለገዙዋቸው
በመጋዝን ለሚገኙ ዕቃዎች የተደረገውን ወጪ ይይዛል፡፡ በብዛት ለሚገዙ እህል እና ነዳጅ በምሳሌነት
ሊጠቀሱ ይችላሉ፡፡ ይህ የወጪ መደብ የሚካትተው የሸቀጡን የፎብ ዋጋ ሲሆን የትራንስፖርት፣
የመጋዝን እና የማከፋፍያ ወጪን አይጨምርም ፡፡ የማጓጓዣ ወጪ፣ በወጪ መደብ 6252 ጭነት ስር፣
የመጋዝን ወጪ በወጪ መደብ 6252 ኪራይ ስር የሚጠቃለል ነው፡፡
42
ለመጠባበቂያ እህል ክምችት ግዥ የሚለውን ወጪ የሚመለከት ነው፡፡ የወጪ መደቡ የግዥውን ዋጋ
እንጂ የመጋዝን፣ የማጓጓዣ ወይም የማከፋፊያ ወጪን አይጨምርም፡፡
ቋሚ ንብረት የሚባለው ከገቢያ ውስጥ ለሚገዙ እቃዎች ወይም በመንግስት መ/ቤቶች ለሚመረቱ
አዳዲስ ወይም ነባር ቋሚ ንብረቶች የሚደረገውን ክፍያ ይጨምራል፡፡ ይህን የሚያካትተው በመደበኛነት
ከአንድ ዓመት በላይ የሚያለግሉ እና ዋጋቸውም ከብር 200 በላይ የሆኑትን ዕቃዎች ብቻ ነው፡፡ የዚህ
ዓይነቶች ቋሚ ንብረቶች የማይንቀሳቅሱ ቋሚ ንብረቶች/የመኖሪያ እና ለመኖሪያ የሚያገለግሉ
ሕንፃዎች፣ የመሠረት ልማት አውታሮች፣ የቤት ዕቃዎችእና በቤት ውስጥ የሚገጠሙ ልዩ ልዩ ነገሮች/
እንዲሁም የመጓጓዣ ተሸከርካሪዎችን እና እንስሳት፣ መሣሪያን እና ማሽንን የሚያካትቱ ተንቀሳቃሽ
ዕቃዎች ናቸው፡፡ ቋሚ ንብረት የማይበሉት በመደበኛ ሁኔታ ከአንድ ዓመት በላይ የሚያገለግሉ ቢሆንም
ዋጋቸው ከብር 200 በታች የሆነ አነስተኛ የእጅ መሣሪያዎች ናቸው፡፡ እነዚህ መሣሪያዎች በወጪ መደብ
6219 ልዩ ልዩ ዕቃዎች ግዣ ዋጋ ታክስና መጠቃለል አለባቸው፡፡ የቋሚ ንብረቶች እና የግንባታ
ዕቃዎች ግዣ ዋጋ ታክስ ቀረጥን ጨምሮ ሌሎች ቅንስናሾ ሳይደረጉ በጥቅል መታየት አለባቸው፡፡ ግንባታ
ቋሚ ንብረት መሥራትን ይጨምራል፡፡
6310 ቋሚ ንብረት
ይህ ንዑስ የወጪ ክፍል በመደበኛ ሁኔታ ከአንድ ዓመት በላይ አገልግሎት የሚሰጡና ዋጋቸው ከብር 200
በላይ የሆነ ማናቸውንም ቋሚ ንብረቶች ይመለከታል፡፡ ተሸከርካሪ፣ መሣሪያ፣ የቤት ዕቃ እና በቤት
ውስጥ የሚገጠሙ ልዩ ልዩ ነገሮች ለዚህ በምሳሌነት ሊጠቀሱ ይችላሉ፡፡
43
ይህ ወጪ መደብ ለወታደራዊ አገልግት የማይውሉ አውሮፕላኖች እና ጀልባዎች ግዥን ይመለከታል፡፡
ለወታደራዊ አገልግሎት የሚውሉ አውሮፕላን እና ጀልባዎች ግዥ በወጪ መደብ 6316 የወታደራዊ
መሣሪያ ግዥ በሚለው ስር የሚካተት ነው፡፡
ለመንግስት አገልግሎት የሚውል የማናቸውም ሕንፃ፣ የቤት ዕቃ ወይም በቤት ውስጥ የሚገጠሙ ልዩ
ልዩ ነገሮች በዚህ የወጪ መደብ ስር ይጠቃለላል፡፡ የሚከተሉት በምሳሌነት ሊጠቀሱ ይችላሉ፡፡ ለበሪ
ወይም ለመኖሪያ ወይም ለሁለቱም አገልግሎት እንዲውል በወጭ አገር የሚገዛ ቤት፣በውች እና በቤት
ውስጥ የሚገጠሙ መብራቶች፣ የቤት ዕቃ፣ ምንጣፍ እና መጋረጃዎች፣
6320 ግንባታ
ይህ ንዑስ የወጪ ክፍል የጉልበት እና የግንባታ ቁሳቁስን ጨምሮ ከቅድመ ግንባታ እና ከግንባታ ጋር
የተያያዙ ማናቸውንም ወጪ ይጨምራል፡፡
ለግንባታ ፕሮጀክት ዝግጅት የሚደረግ የመጀመሪያ ደረጃ ጥናት፣ የቅየሳ፣ የአዋጭነት ጥናት ፣
የመሀንዲስ እና ሌሎች የቴክኒክ ንድሮችን ወጪ ይመለከታል፡፡
44
ለሠራተኞች የመኖሪያ ሕንፃ፣ለመኖሪያ ቤት ሥራ ፕሮጀክት ወ.ዘ.ተ. የሚውለው ወጪ በዚህ የወጪ
መደብ ውስጥ ይካተታል፡፡ የሚከተሉት በምሳሌነት ሊጠቀሱ ይችላሉ፡፡ የመኝታ ሕንፃ/የሥራተኞች
መኖሪያ ቤት እና ለመንገስት ሠራተኞች መኖሪያ የሚሆኑ ቤቶች በሌለበት አከባቢ የሚሰራ ካምፕ፣
45
6326 የግንባታ ቁጥጥር ሥራዎች
ይህ የወጪ ክፍል መንግስት በገባው ግዴታ መሠረት ለአገር ውስጥ ወይም ለውጭ አገር ተቋማት
ወይም ለግለሰቦች በጥሬ ገንዘብ የሚከፈለውን ድጎማ፣ እርዳታ ወይም የብድር ዕዳ ይመለከታል፡፡
ይህ የገንዘብ እርዳታ መንግስት ለበጎ አድርጎት ወይም ለሀይማት ድርጅቶች ዪሰጠውን እርዳታ
ያካትታል፡፡
6415 መጠባበቂያ
46
በመንግስት ወይም በፍርድ ቤት በተወሰኑ የተለያዩ ጉዳዮች ለግለሰቦች፣ለቡድኖች እና ለድርጅቶች ካሣ
ለመክፈል የሚደረገውን ወጪ ይመለከታል፡፡ ለዚህ ምሳ የሚሆነው መንግስት ለተለያዩ አገልግሎቶች
ከግለሰብ ለሚፈለገው መሬት የሚከፈል ካሣ ነው፡፡ ካሣ ማለት ግለሰብ ወይም ድርጅት ለደረሰበት
ኪሣራ በሕግ ወይም በሞራል ግዴታ ምክንያት የሚከፈል ገንዘብ ነው፡፡ ከዚህ በፊት "ዳረጎት" ይባል
የነበረው የወጪ መደብ በዚህ ውስጥ ተካቷል፡፡
6419 ልዩ ልዩ ክፍዎች
ልዩ ልዩ ክፍያዎች የሚባሉት በሌሎች የወጪ መደቦች ስር ያልታዩ ተጓዳኝ ወጪዎች ናቸው፡፡ መቀጫ
እና በገበሬ ማህበራት ለሚሰበሰብ ግብር የሚከፈል አባል ለዚህ በምሳሌነት ሊጠቀስ ይችላሉ፡፡
ይን ንዑስ የወጪ ክፍል ለአገር ውስጥ እና ለውጭ አገር ብድር የሚያደርገውን የዋና ገንዘብ፣ የወለድ
እና ከእነዚህ ጋር የተያያዙ ክፍያዎች ያካትታል፡፡
ከንግስት የአገር ውስጥ ዕዳ ጋር በተያያዘ የሚደረጉ የወለድ እና የባንክ አገልግሎት ክፍያዎችን ያካትታል፡፡
47
ምዕራፍ 3
ይህ ምዕራፍ የደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መንግስት የሂሳብ አወቃቀር ሥርዕት የተሟላ ለማድረግ መለያ ቁጥር 4000 እስከ
5999 ያሉትን በመጠቀም ለሂሳብ ሥራ እንቅስቃሴዎች ዝርዝር የመለያ ቁጥር የሚሰጥ ነው፡፡ በዚህ ምዕራፍ
የተመለከተው የአደረጃጀት እና የመለያ ቁጥር አሰጣጥ ዋነኛ ዓላማ ለደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መንግሥት የሂሳብ አያያዝ
ሥርዓት አስፈላጊ የሆኑ ቋሚ ሂሣቦች ቦታ እንዲኖራቸው ለማድረግ ነው፡፡ የዝውውር ሂሣቦችም በዚህ ምዕራፍ
ውስጥ ተመልክተዋል፡፡ በዚህ ምዕራፍ የቀረቡት የሂሳብ አደረጃጀቶች በሚከተሉት መርሆዎች የሚመሩ ናቸው፡፡
1. በዋና የሂሳብ መደብ መለያ ቁጥሮቸ የገንዘብ ዝውውር ሀብት፣ ዕዳ እና የተጣራ ሀብት በሚል ተለይተው
ከ 4000 እስከ 4099 ያሉት መለያ ቁጥሮች ለገንዘብ ዝውውሮች የተያዙ ናቸው፡፡
ከ 5600 እስከ 5699 ያሉት መለያ ቁጥሮች ለተጣራ ሀብት የተያዙ ናቸው፡፡
ቅደም ተከተሉ ተገንዘብ ዝውውርን በመጀመሪያ ደረጃ ያስቀመጠበት ምክንያት የገንዘብ ያዥው መ/ቤቶች
ውስጥ ብቻ የሚከናወነው የጥሬ ገንዘብ እና የጥሬ ገንዘብ ነክ ያልሆነ እንቅስቃሴ /እንደ ጥሬ ገንዘብ
ለመመዝገብ ስለሚችል ነው፡፡ ቀሪዎቹ የሂሳብ መለያ ቁጥሮች ቋሚ ሂሳቦቸ ናቸው፡፡ እነዚህ ተለይተው
2. በዋና የሂሳብ መደብ መለያ ቁጥሮች ውስጥ ያሉት የሂሳብ መለያ ቁጥር ምድቦች ተለይተው በቅደም
በተጣጣመ ሁኔታ ነው፡፡ በሀብቶች ውስጥ የተደረገው የቅደም ተከተል አቀማመጥ የሚያሳየው ሀብቶቹ ወደ
ጥሬ ገንዘብ የመለወጥ ችሎታቸውን ወይም በአንፃራዊ ሲታይ እያንዳንዱ ወደ ጥሬ ገንዘብ በቀላሉ መለወጥ
መቻሉን ነው፡፡
በዕዳዎቹ ውስጥ የተደረገው የቅደም ተከተል አቀማመጥ የሚያሳየው ዕዳው ተመልሶ የሚከፈልበትን ጊዜ
ቅደም ተከተል እንደ ጊዜው ርዝመት በአንድ ዓመት ተከፋይ መሆን መደረግ ካለባቸው በግዴታዎች ጀምሮ
48
በረጅም ጊዜ የሚከፈሉትና አከታትሎ በማስቀመጥ ነው፡፡ የተጣራ ሀብት ለጠቅላላ እና ለተለየ ዓላማ
3. የሂሳብ እንቅስቃሴን ምዝገባ ቀላል ለማድረግ የሂሳብ አወቃቀር ሥርዓት በጥራዝ እንደተገለጸው በጥሬ
ገንዘብ እንቅስቃሴ ላይ የተመሠረተ የተሻሻለ የሂሳብ አያያዝ ዘዴ ውጤት የሆነውን ሀብትና ዕዳ በጥራዝ
እንደተገለጸው ወጪን መሠረት ያደረገ የሂሳብ አያያዝ ዘዴ ውጤት ከሆነው ሀብትና ዕዳ ለይቶ ማሳየት
ለእያንዳንዱ የሂሳብ መለያ ቁጥር የተሰጠው ምድብ ዝርዝር በሠንጠረዥ 3.1 ተመልክቷል፡፡
ሠንጠረዥ 3.1
ቋሚ እቃዎች 4500-4599
49
በሚከተሉት የሂሳብ መለያ ቁጥር ምድቦች ውስጥ የሚገኙ ሂሳቦች በዚህ ማንዋል ጥራዝ 1 በተገለጸው በጥሬ
ገንዘብ እንቅስቃሴ ላይ የተመሰረተ የተሻሻለ የሂሳብ አያያዝ ዘዴ መሠረት የሂሳብ እንቅስቃሴዎችን ለመመዝገብ
የሚያገለግሉ ናቸው፡፡
ወጪ 6000-6999
ቀሪዎቹ ሂሳቦች ሌሎች ሀብቶችና ወደፊት በተናጠል ለመመዝገብ የሚያገለግሉ ናቸው፡፡ እነዚህ
50
ሠንጠረዥ 3.2 በአሁን ጊዜ ለእያንዳንዱ የሂሳብ መለያ ቁጥር ምድብ የተሰጡትን ዝርዝር የሂሳብ መለያ ቁጥሮች
ሠንጠረዥ 3.2
51
ሠንጠረዥ 3.2/የቀጠለ/
52
ሠንጠረዥ 3.2/የቀጠለ/
ሌሎች 4402
4403
በጉዞ ላይ ያሉ ዕቃዎች
4404
አላቂ ዕቃዎች
4405
ቋሚ ዕቃዎች 4406
አላቂ ዕቃዎች 4407
የደንብ ልብስ፣ የሥራ ልብስ የመኝታ ልብስ 4408
ጥይትና ፈንጂ
መለዋወጫዎች
የፋብሪካ ጥሬ ዕቃዎች
53
ሠንጠረዥ 3.2/የቀጠለ/
54
ሠንጠረዥ 3.2/የቀጠለ/
የተጣራ ሀብት
55
ሠንጠረዥ 3.2/የቀጠለ/
መጠባበቂያ
56
የእያንዳንዱ የጥሬ ገንዘብ ዝውውር ሀብት ዕዳ እና የተጣራ ሀብት የሂሳብ ምድብ እና መለያ ቁጥር ከዚህ በታች ማብራሪያ
ተሰጥቶበታል። ማብራሪያ ያልተሰጠበት የሂሳብ ኮድ ቢኖር ኮዱ በራሱ ራሱን በሚገባ አንደሚገልጽ ታስቦ ነው።
የገነዘብ ዝውውር መለያ ቁጥሮች ተጨማሪ መረጃ የሚያስፈልጋቸውን ግዴታዎች ወይም መተኪያ የሚያሰከትሉ
በመንግሥት መ/ቤቶች ውስጥ በተክክል የተፈጸሙ የጥሬ ገንዘብ እንቅስቃሴዎች አና የጥሬ ገንዘብ ነክ ያልሆኑ የሂሳብ
እንቅስቃሴዎችን ለመመዝገብ የሚያገለግሉ ናቸው።
የገንዘብ ዝውውሮች
ከክልሉ መንግሥት ለወረዳዎች የሚተላለፍ የደጎማ ገንዘብ ዝውውር አይባልም። ይህም የሚሆንበት ምክንያት
ለወረዳዎች የሚሰጠው ድጎማ በበጀት የተፈቀደው እና በወጪ መደብ ቁጥር 6411 ሥር የሚመዘገብ ስለሆነ
ነው። ለደመወዝ ክፍያ እንዲውል በየወሩ ከማዕከላዊ ግምጃ ቤት ለባለበጀት መ/ቤቶች የሚፈጸመው ክፍያ
የገንዘብ ዝውውር ነው።
የዝውውር ሂሳቦች ጊዜያዊ ሂሳቦች ናቸው። በበጀት ዓመቱ መጨረሻ የሚፈጸመው የሂሳብ መዝጊያ አካል ሲሆኑ
አዲሱን የበጀት ዓመት የሚጀምሩት በዜሮ ሚዛን ነው። የደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መንግሥት የሂሳብ አወቃቀር ሥርዓት
ውስጥ የገንዘብ ዝውውር ምደቦች የጥሬ ገንዘብ ዝውውር እና ጥሬ ገንዘብ ነክ ያልሆኑ ዝውውር ናቸው።
እያንዳንዱ ምድብ እና ተዛማጅ የሆነው የሂሳብ መለያ ቁጥር ከዚህ በታች ተብራርቷል።
እነዚህ መለያ ቁጥሮች በጥሬ ገንዘብ እንቅስቃሴ በእርግጥ የተከናወነ በሚሆንበት ጊዜ የገንዘብ ዝውውርን
ለመመዝገብ የሚያገለገሉ ናቸው።
ይህ መለያ ቁጥር ከፀደቀው መደበኛ በጀት ላይ የደመወዝና አበል ክፍያ ለመፈፀም በባለበጀት መ/ቤቶች እና
በፋ/ኢ/ል/ቢሮ መካከል በእርግጥ የተከናወነውን የጥሬ ገንዘብ እንቅስቃሴ ለመመዝገብ የሚያገለግል ነው።
ይህ መለያ ቁጥር ከፀደቀው መደበኛ በጀት ላይ የሥራ ማስኬጃ ወጢ ክፍያ ለመፈፀም በባለበጀት መ/ቤቶች እና
በፋ/ኢ/ል/ቢሮ መካከል በእርግጥ የተከናወነውን የጥሬ ገንዘብ እንቅስቃሴ ለመመዝገብ የሚያገለግል ነው።
57
4003 የካፒታል ደመወዝና አበል
ይህ መለያ ቁጥር ከፀደቀው የካፒታል በጀት ላይ የደመወዝና አበል ክፍያ ለመፈፀም በባለበጀት መ/ቤቶች እና
በፋ/ኢ/ል/ቢሮ መካከል በእርግጥ የተከናወነውን የጥሬ ገንዘብ እንቅስቃሴ ለመመዝገብ የሚያገለገል ነው።
ይህ መለያ ቁጥር ከፀደቀው የካፒታል በጀት ላይ የካፒታል ወጪ ክፍያ ለመፈፀም በባለበጀት መ/ቤቶች እና
በፋ/ኢ/ል/ቢሮ መካከል በእርግጥ የተከናወነውን የጥሬ ገንዘብ እንቅስቃሴ ለመመዝገብ የሚያገለግል ነው።
ይህ መለያ ቁጥር ከረጅም ጊዜ የደመወዝ ቅድሚያ ክፍያ እና ወይም ብድር ጋር የተያያዘ የሠራተኞች የቅድሚያ
ክፍያ ለመፈፀም በባለበጀት መ/ቤቶች እና በፋ/ኢ/ል/ቢሮ መካከል በእርግጥ የተከናወነውን የጥሬ ገንዘብ
እንቅስቃሴ ለመመዝገብ የሚያገለግል ነው።
ይህ መለያ ቁጥር ከጸደቀው የካፒታል በጀት ላይ ለማህበራዊ ዘርፍ ልማት ፕሮግራም የሚውለውን ወጪ ክፍያ
ለመፈፀም በባለበጀት መ/ቤቶች እና በፋ/ኢ/ል/ቢሮ መካከል በእርግጥ የተከናወነውን የጥሬ ገንዘብ እንቅስቃሴ
ለመመዝገብ የሚያገለግል ነው።
ይህ መለያ ቁጥር በችሮታ ጊዜ ተከፋይ ለመሆን የሚችሉ ወጪዎችን ክፍያ ለመፈፀም በባለበጀት መ/ቤቶች እና
በፋ/ኢ/ል/ቢሮ መካከል በእርግጥ የተከናወነውን የጥሬ ገንዘብ እንቅስቃሴ ለመመዝገብ የሚያገለግል ነው።
ይህ መለያ ቁጥር በአንድ በባለበጀት መ/ቤት አና በሌላ በባለበጀት መ/ቤት ወይም በአንድ በባለበጀት መ/ቤት እና
በአንድ ክልል መካከል በእርግጥ የተከናወነውን የጥሬ ገንዘብ እንቅስቃሴ ለመመዝገብ የሚያገለገል ነው።
ይህ መለያ ቁጥር በሌሎች የገነዘብ ዝውውር መለያ ቁጥሮች ሊሸፈን ያልቻለውን በእርግጥ የተከናወነውን የጥሬ
ገንዘብ እንቅስቃሴ ለመመዝገብ የሚያገለግል ነው።
58
4010 በባለበጀት ተቋም በጥሬ ገንዘብ የሂሳብ ዩኒት በባንክ የሂሳብ ዩኒት ወይም በፋ/ኢ/ል/ቢሮ
ውስጥ
ይህ የሂሳብ መደብ የሚያገለገለው ቀጥተኛ የሆኑ የጥሬ ገነዘብ እንቅስቃሴዎችን ከላይ በተጠቀሱት የሂሳብ አካላት
ውስጥ ለመመዝገብ ነው።
ይህ መለያ ቁጥር በጸደቀው መደበኛ በጀት ለደመወዝና አበል ክፍያ ከተያዘው ሂሳብ ላይ የጥሬ ገንዘብ እንቅስቃሴ
በሌለበት ሁኔታ በባለበጀት መ/ቤቱ እና በፋ/ኢ/ል/ቢሮ መካከል የተፈፀመውን ዝውውር ለመመዝገብ የሚያገለግል
ነው።
ይህ መለያ ቁጥር በጸደቀው መደበኛ በጀት ለሥራ ማሰኬጃ ወጢ ክፍያ ከተያዘው ሂሳብ ላይ የጥሬ ገንዘብ
እንቅስቃሴ በሌለበት ሁኔታ በባለበጀት መ/ቤቱ እና በፋ/ኢ/ል/ቢሮ መካከል የተፈፀመውን ዝውውር ለመመዝገብ
የሚያገለግል ነው።
ይህ መለያ ቁጥር በጸደቀው የካፒታል በጀት ለደመወዝና አበል ክፍያ ከተያዘው ሂሳብ ላይ የጥሬ ገንዘብ እንቅስቃሴ
በሌለበት ሁኔታ በባለበጀት መ/ቤቱ እና በፋ/ኢ/ል/ቢሮ መካከል የተፈፀመውን ዝውውር ለመመዝገብ የሚያገለግል
ነው።
ይህ መለያ ቁጥር በጸደቀው የካፒታል በጀት ለካፒታል ወጪ ከተያዘው ሂሳብ ላይ የጥሬ ገንዘብ እንቅስቃሴ
በሌለበት ሁኔታ በባለበጀት መ/ቤቱ እና በፋ/ኢ/ል/ቢሮ መካከል የተፈፀመውን ዝውውር ለመመዝገብ የሚያገለግል
ነው።
ይህ መለያ ቁጥር በሌሎች የገነዘብ ዝውውር መለያ ቁጥሮች ሊሸፈን ያልቻለውን የጥሬ ገንዘብ የጥሬ ገንዘብ
እንቅስቃሴ በሌለበት ሁኔታ የተፈፀሙትን ዝውውር ለመመዝገብ የሚያገለግል ነው።
ሀብቶች 4100-4999
59
ሀብቶች አንድ አካል ባለፈው ጊዜ ከተፈጸሙ ድርጊቶች የሚያገኛቸው እና ለወደፊት ኢኮኖሚ ጠቀሜታ ወይም
አገልግሎት የመስጠት አቅም ያስገኙለታል ተብለው የሚታሰቡ ናቸው። በደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መ/ የሂሳብ አወቃቀር
ሥርዓት ውስጥ የሀብት ምደቦች የሚከተሉት ናቸው።
እያንዳንዱ ምድብና ተዛማጅ የሆነው የሂሳብ መለያ ቁጥር ከዚህ በታች በዝርዝር ተመልክቷል።
ጥሬ ገንዘብ በሳጥን የሚገኝ እና በባንክ የተቀመጠ ገንዘብ ነው። ከጥሬ ገንዘብ ጋር በእኩል የሚታዩ በቀላሉ
ወደታወቀ የገንዘብ መጠን ሊለውጡ የሚቸሉ እና በልልውጥ ሂደት ዋጋቸው የመቀነሱ አጋጣሚ አነስተኛ የሆነ
በአጭር ጊዜ ወደ ጥሬ ገንዘብ የመለወጥ አቅማቸው ከፍተኛ የሆነ ኢንቨስትመንቶች ናቸው። የመንግሥት የባንክ
ሂሳቦች በሙሉ በፋ/ኢ/ል/ቢሮ ባለቤትነት ስም ያሉ ቢሆንም የአንዳንዱ የባንክ ሂሳቦች የዕለት አስተዳደር ኃላፊነት
በባለበጀት መ/ቤቶች በውክልና ተሰጥቷል።
ይህ መለያ ቁጥር በባለበጀት መ/ቤት ውስጥ በሚገኝ ካዝና ውስጥ በገነዘብ ያዥ ቁጥጥር ስር የተቀመጠን በገንዘብ
ለመመዝገብ የሚያገለግል ነው።
ይህ መለያ ቁጥር በባለበጀት መ/ቤት በብር በባንክ ሂሳብ ያስቀመጠውን በገንዘብ ለመመዝገብ የሚያገለግል ነው።
ይህ መለያ ቁጥር ገደብ በሌለበት ሁኔታ ለአጠቃላይ የበጀት ክፍያ እንዲውል ከአገር ውስጥ ምንጮች ተሰብሰቦ
በፋ/ኢ/ል/ቢሮ ስም የተቀመጠን በገንዘብ ለመመዝገብ የሚያገለግል ነው።
60
ይህ መለያ ቁጥር ለማህበራዊ ዘርፍ ልማት ፕሮግራም ማስፈጸሚያ እንዲውል በብድር ተገኝቶ በፋ/ኢ/ል/ቢሮ
የተያዘውን ገንዘብ ለመመዝገብ የሚያገለግል ነው።
ይህ መለያ ቁጥር ለማህበራዊ ዘርፍ ልማት ፕሮግራም ማስፈጸሚያ እንዲውል በእርዳታ ተገኝቶ በፋ/ኢ/ል/ቢሮ
የተያዘውን ገንዘብ ለመመዝገብ የሚያገለግል ነው።
ተሰብሳቢ ሂሳብ በፋ/ኢ/ል/ቢሮ ከባለበጀት መ/ቤት ከሌላ ባለበጀት መ/ቤት ግለሰብ ወይም መንግሥታዊ ያልሆነ
ድርጅት የሚፈለገው የአከፋፈሉ ሁኔታ በተፈረመ ስምምነት ውስጥ በዝርዝር ያለተመለከተ የገነዘብ መጠን
ነው። የቅድሚያ ክፍያ የገንዘብ ዝውውር አይደለም። የገንዘብ ዝውውር ተጨማሪ ሰነድ ማቅረብ አስፈላጊ
የሚሆንበት /ተመልሶ/ የሚከፈል አይደለም። ተሰብሳቢ ሂሳብ ግን ወደፊት የሚወራረድ ነው።
ተሰብሳቢ ሂሳቦች ለተሻለ ቁጥጥር እና ክትትል በዓይነት የተመደቡ ናቸው። የተሰብሳቢው ሂሳብ ዓይነት
በተከናወነው የሂሳብ እንቅስቃሴ ዓይነት ይወሰናል።
እነዚህ የተሰብሳቢ ሂሳቦች ምደብ የፋ/ኢ/ል/ቢሮ አና ባለበጀት መ/ቤቱ ከሌላ ባለበጀት መ/ቤት ከክልሎች ወይም
ከመንግሥት ሠራተኞች የሚፈለገውን ተሰብሳቢ ሂሳብ የሚይዝ ነው።
61
ይህ መለያ ቁጥር ለገንዘብ ያዥ ተመላሽ የሚሆነውን ከአንድ ወር ባነሰ ጊዜ መወራረድ ያለበትን የቅድሚያ ክፍያ
ለመመዝገብ የሚያገለግል ነው።
ይህ መለያ ቁጥር በባለበጀት መ/ቤቱ ሠራተኞች የሚፈለግ ከአንድ ወር በበለጠ ጊዜ ተከፋይ መሆን የሚገባው
የረጅም ጊዜ ብድር የሚመዘገብበት ነው።
ይህ መለያ ቁጥር በካፒታል በጀት ውስጥ ለማህበራዊ ዘርፍ ልማት ፕሮግራም ወጪ እንዲውል ከተያዘው በጀት
ላይ ለባለበጀት መ/ቤቱ በፋ/ኢ/ል/ቢሮ የተሰጠ የቅድሚያ ክፍያ የሚመዘገብበት ነው።
ይህ መለያ ቁጥር በባለበጀት መ/ቤቱ ሠራተኞች ደመወዝና አበል ክፍያ እንዲውል ከሚቀጥለው ዓመት በጀት ላይ
ታሰቦ ለባለበጀት መ/ቤቱ በፋ/ኢ/ል/ቢሮ የተሰጠ የቅድሚያ ክፍያ የሚመዘገብበት ነው።
ይህ መለያ ቁጥር የሥራ ማስኬጃ ወጪን ለመሸፈን እንዲውል ከሚቀጥለው ዓመት በጀት ላይ ታሰቦ ለባለበጀት
መ/ቤቱ በፋ/ኢ/ል/ቢሮ የተሰጠ የቅድሚያ ክፍያ የሚመዘገብበት ነው።
ይህ መለያ ቁጥር ለካፒታል ወጪዎች ለመሸፈኛ እንዲውል ከሚቀጥለው ዓመት በጀት ላይ ታሰቦ ለባለበጀት
መ/ቤቱ በፋ/ኢ/ል/ቢሮ የተሰጠ የቅድሚያ ክፍያ የሚመዘገብበት ነው።
62
4209 ለባለበጀት መ/ቤቶች የሚሰጡ ሌሎች የቅድሚያ ክፍያዎች
ይህ መለያ ቁጥር በሌላ ማንኛውም መለያ ቁጥር ስር የማይወድቀውን አና በፋ/ኢ/ል/ቢሮ ለባለበጀት መ/ቤቱ
የተሰጠ የቅድሚያ ክፍያ ለመመዝገብ የሚያገለግል ነው።
ይህ መለያ ቁጥር በሁለት በባለበጀት መ/ቤቶች ወይም በባለበጀት መ/ቤቶች እና በክልል መካከል የሚፈጸመው
የቅድሚያ ክፍያ ለመመዝገብ የሚያገለግል ነው።
ይህ የተሰብሳቢ ሂሳብ ምድብ ዕቃ ወይም አገልግሎት ከመቅረቡ በፊት ለአቅራቢዎች የቅድሚያ ክፍያ በመፈፀሙ
ምክንያት የፋ/ኢ/ል/ቢሮ ወይም በባለበጀት መ/ቤቱ የሚፈለገውን የገንዘብ መጠን የሚይዝ ነው። አብዛኛውን ጊዜ
ኮንትራክተሮች አማካሪዎችና አገልግሎት አቅራቢዎች የተሟላ ዕቃና አገልግሎት ከማቅረባቸው በፊት የቅድሚያ
ክፍያ ይጠይቃሉ። እነዚህ ዕቃዎችና አገልግሎቶች ተሟልተው ርክክብ እስካልተፈጸመ ድረስ የቅድሚያ ክፍያው
ተሰብሳቢ ሂሳብ ይሆናል።
ይህ መለያ ቁጥር ከሥራ ተቋራጮች የሚፈለገውን የቅድሚያ ክፍያ ለመመዝገብ የሚያገለግል ነው።
ይህ መለያ ቁጥር ከዕቃ አቅራቢዎች የሚፈለገውን የቅድሚያ ክፍያ ለመመዝገብ የሚያገለግል ነው።
63
4252 ለአማካሪዎች ቅድሚያ ክፍያ
ይህ መለያ ቁጥር በሌላ የመለያ ቁጥር የማይሸፈኑ የዕቃ እና አገልግሎት ግዥ የቅድሚያ ክፍያዎቸን ለመመዝገብ
የሚያገለግል ነው።
ይህ ምደብ የፋ/ኢ/ል/ቢሮ ወይም ባለበጀት መ/ቤት ከመንግሥታዊ አና ከግል ድርጅቶች ከግለሰቦች ከማህበራት
እና ከሀይማኖት ድርጅቶች እና ከመሳሰሉት የሚፈለገውን ተሰብሳቢ ሂሳብ የሚይዝ ነው።
ይህ መለያ ቁጥር ከገበሬ ማህበራት የሚፈለገውን ተሰብሳቢ ሂሳብ ለመመዝገብ የሚያገለግል ነው።
ይህ መለያ ቁጥር ከኀብረት ሥራ ማህበራት የሚፈለገውን ተሰብሳቢ ሂሳብ ለመመዝገብ የሚያገለግል ነው።
ይህ መለያ ቁጥር ከግለሰቦች እና የግል ድርጅቶች የሚፈለገውን ተሰብሳቢ ሂሳብ ለመመዝገብ የሚያገለግል ነው።
4274 ሌሎች
ይህ መለያ ቁጥር በሌሎች መለያ ቁጥሮች የማይሸፈኑ ተሰብሳቢ ሂሳቦችን ለመመዝገብ የሚያገለግል ነው።
በጉዞ ላይ ያሉ ዕቃዎች ባለበጀት መ/ቤቱ ከውጭ አገር የገዛቸው ነገር ግን ገና ያልተረከባቸው አላቂ ዕቃዎች
ወይም ቋሚ ንብረቶች ናቸው። ባለበጀት መ/ቤቶች ዕቃዎቸን እና አገልግሎቶቸን ከውጭ አገር ሲገዙ አብዛኛውን
ጊዜ ክፍያው የሚፈጸመው ዕቃዎቹ በመርከብ ሲጫኑ ነው። በጉዞ ላይ እያለ የዕቃዎቹ ባለቤትነት ወደ ባለበጀት
መ/ቤቱ የሚተላለፍ ቢሆንም ባለበጀት መ/ቤቱ ዕቃዎቹን በይዞታው ስር አያደርግም።
64
በጉዞ ላይ ያሉ ዕቃዎች ሁለት የሂሳብ ምድቦች ተሰጥቷቸዋል። 4301 በመጋዘን ያለ አላቂ ዕቃዎች እና 4302
ለቋሚ ሀብቶች በሠንጠረዥ 3.2 ተዘርዝሯል።
አላቂ ዕቃዎች የሚባሉት የአገልግሎት ዘመናቸው ከአንድ ዓመት በታች የሆኑ ዕቃዎች ናቸው። በዕለት ተዕለት
መደበኛ የሥራ እንቅስቃሴ ውስጥ ጥቅም ላይ የሚውሉ አላቂ ዕቃዎች ገቢ የሚደረጉት የሚያዙት እና ወጪ
የሚደረጉት በዕቃ ግምጃ ቤት ኃላፊው አማካኝነት ነው።
የሂሳብ መለያ ቁጥሮች በሂሳብ አወቃቀር ሥርዓት ውስጥ ካሉ /ምዕራፍ 2 ተመልከት/ ወጪ መደቦች 6210-6224
ጋር አንድ ዓይነት አመዳደብን ይከተላሉ። የአላቂ ዕቃዎች መለያ ቁጥሮች ጋር በሠንጠረዥ 3.3 ተመልክተዋል።
65
ሠንጠረዥ 3.3
የአያንዳንዱ የሂሳብ መለያ ቁጥር መግለጫ ተዛማጅ በሆነው የወጪ መደብ መግለጫ ውስጥ ይገኛል። በዩነት
የሚታዩት ከሂሳብ መለያ ቁጥሮች 4413-4418 ያሉት ናቸው።
የወጪ መደብ ቁጥር 6218 ለሌሎች ዕቃዎች እና መሳሪያዎች የሚያገለግል ነው። ሌሎት ዕቃዎች እና
አገልግሎቶችን በአንድ የአላቂ ዕቃዎች መደብ ስር ከማሰባሰብ ይልቅ የሂሳብ መደቡ አላቂ ዕቃዎችን ለይቶ
ያሳያል።
66
4413 የሕንፃ እና የግንባታ ዕቃዎች
ይህ መለያ ቁጥር በመጋዘን የሚገኙ የሕንፃ እና የግንባታ ዕቃዎቸን የገንዘብ ልክ ለመመዝገብ የሚያገለግል ነው።
ይህ መለያ ቁጥር በመጋዘን የሚገኙ የመለዋወጫ ዕቃዎቸን የገንዘብ ልክ ለመመዝገብ የሚያገለግል ነው።
ይህ መለያ ቁጥር በምርት ሂደት ውስጥ ጥቅም ላይ የሚውሉና በመጋዘን የሚገኙ የመለዋወጫ ዕቃዎቸን የገንዘብ
ልክ ለመመዝገብ የሚያገለግል ነው።
ይህ መለያ ቁጥር ተመርተው አገልገሎት ላይ ለመዋል የተዘጋጁ ዕቃዎቸን የገንዘብ ልክ ለመመዝገብ የሚያገለግል
ነው።
ይህ መለያ ቁጥር በሌሎች መለያ ቁጥሮች የማይሸፈኑ ዕቃዎቸን እና አገልግሎቶቸን ለመመዝገብ የሚያገለግል
ነው።
4500-4599 ቃሚ ንብረቶች
ቋሚ ንብረቶች የጠቀሜታ ጊዜያቸው ከአንድ ዓመት በላይ ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዋጋቸው ከተወሰነ የገንዘብ
መጠን በላይ የሆነና ግዙፋዊ ህልዎት ያላቸው ንብረቶች ናቸው። ቃሚ ንብረቶቸን ለይቶ ማወቅ እንዲቻል
መንግሥት ቋሚ ንብረቶች የሚባሉት ከምን ያህል ገንዘብ በላይ ዋጋ ያላቸው እንደሆኑ ይወሰናል። የፋይናንስ
ደንብን መሠረት በማድረግ የወጣው የመንግሥት ንብረት አስተዳደር መመሪያ ቋሚ ንብረት የሚባሉት
የጠቀሜታ ጊዜያቸው ከአንድ ዓመት በላይ የሆነና የተገዙት ዋጋ ከብር 200 በላይ የሆነ ግዙፋዊ ህልዎት ያላቸው
ንብረቶች መሆናቸውን ይገልጻል። አዲሱ የሂሳብ አወቃቀር ሥርዓት ቋሚ ንብረቶችን አንደ አግባብነቱ
በማሰባሰብ በሁለት ምደቦች ማለትም በመከናወን ላይ ያለ የግንባታ ሥራ እና ንብረትና መሳሪያ በሚል
ይከፍላቸዋል።
67
በመከናወን ላይ ያለ የግንባታ ሥራ መለያ ቁጥር ለባለበጀት መ/ቤት የሕንፃ ግንባታዎችን የሚሰራበት ጊዜ
ያደረገውን ወጪ ለመመዝገብ እና በአንድ ላይ ለማሰባሰብ የሚያገለግል ነው። ለገንባታ ሥራ የተደረገ ወጪ
የሚፈቀደው በሂሳብ አወቃቀር ሥርዓት/ ምዕራፍ 2 ተመልከት/ እነዚህም ከ 6321-6325 ያሉት የወጪ መደቦች
ናቸው።
ሠንጠረዥ 3.4
የእያንዳንዱ የመለያ ቁጥር ነግለጫ ከተዛማጅ የወጪ መደብ መግለጫ ጋር አንድ ዓይነት ነው።/ ምዕራፍ 2
ተመልከት/
የወጪ መደብ ቁጥር 6321 የቅድመ ገንባታ እንቅስቃሴዎችን ወጪ ይይዛል። ቃሚ ንብረቶችን ለመመዝገብ
ሲባል የግንባታ ሥራው ዓይነት መለየት እና የቅድመ ግንባታ ወጪዎች በተገቢው የቋሚ ንብረቶች ሂሳብ ስር
መመዝገብ ይኖርባቸዋል።
ሠንጠረዥ 3.5
68
ለንብረት እና መሳሪያ የተሰጠ መለያ ቁጥር አግባብነት ያለው የወጪ መደብ መለያ ቁጥር እና በመካሄድ ላይ ያለ
ግንባታ፣ ግንባታ መለያ ቁጥር ከዚህ ሠልጠረዥ መግለጫ በሚለው ሥር ያሉት ማብራሪያዎች፣ የሂሳብ መለያ
ቁጥር ከ 4521-4530 የወጪ መደብ ከ 6311-6315 አና በመካሄድ ላይ ያለ ገንባታ መለያ ቁጥር ከ 4501-4504
ከነጠላ የንብረት እና መሳሪያ መለያ ቁጥር ጋር የማይዛመድ የወጪ መለያ ቁጥር የወጪ መደብ 6314 ብቻ ነው።
የወጪ መደብ ቁጥር 6314 ለህንፃዎች ለቤትና ቢሮ ዕቃዎች እና የቤት ውስጥ ተገጣጣሚዎች ግዥ የሚያገለግል
ነው። ይሁን እንጂ የንብረት እና የመሳሪያ ቋሚ ምዝገባ በሚደረግበት ጊዜ ከሚውለው ዓላማ አንፃር ለህንፃዎች
የተደረገው ወጪ ለቢሮ ለቤት ዕቃዎቸና ለቤት ውስጥ ተገጣጣሚዎች ከዋለው ወጪ ተለይቶ መያዝ አለበት።
የረጅም ጊዜ ብድር በፋ/ኢ/ል/ቢሮ ተከፋይ የሆነ እና በተፈረመ ስምምነት የውል ቃሎች መሠረት የመክፈያ
ጊዜው ከአንድ ዓመት በላይ የሆነ ብድር ነው። በአሁኑ ጊዜ የረጅም ጊዜ ብድሮች በሙሉ ከመንግሥት የልማት
ሥራ ድርጅቶች የሚፈለጉ ናቸው።
4800-4899 ኢንቨስትመንቶች
5000-5499 ዕዳዎች
69
በአንድ ዓመት የጊዜ ገደብ ውስጥ ተከፋይ የሚሆኑ ዕዳዎች የአጭር ጊዜ ዕዳዎች ተብለው ይመደባሉ። የዕዳዎች
የሂሳብ ኮድ ከዚህ እንደሚከተለው ተዘርዝሯል።
የተከፋይ ሂሳቦች
በመንግሥት መ/ቤቶች መካከል ያሉ ተከፋይ ሂሳቦች
የመያዣዎች እና
የሥራ ተቋራጭ መያዣዎች
ተከፋይ ሂሳቦች መንግሥት የሚያደርጋቸው የሂሳብ እንቅስቃሴዎች ውጤት የሆኑ ተከፋይ ሂሳቦች ናቸው።
መንግሥት ከክፍያ በፊት ዕቃ ወይም አገልግሎት ያገኘ በሚሆንበት ጊዜ ከመንግሥት የሚፈለገው ሂሳብ ተከፋይ
ሂሳብ ይሆናል።
ይህ መለያ ቁጥር በችሮታ ጊዜ ውስጥ ተከፋይ ለመሆን ብቁ የሆኑ ለአቅራቢዎች የሚፈጸሙ ክፍያዎቸን
ለመመዝገብ የሚያገለግል ነው።
ይህ መለያ ቁጥር በችሮታ ጊዜ ተከፋይ ሂሳቦች በስተቀር ለሌሎች ማናቸውም ባለገንዘብ ተከፋይ መሆን ያለበት
የገንዘብ መጠን የሚመዘገብበት ነው።
ይህ መለያ ቁጥር ለጡረታ ፈንድ ገቢ መደረግ ያለበትን የገንዘብ ልክ ለመመዝገብ የሚያገለግል ነው።
ይህ የሂሳብ ኮድ አገልግሎት ለሠራተኞቸን ከሚከተለው ደመወዝ ተቀንሶ የሚያዝ ሂሳቦችን የሚያሳይ ሲሆን
የጡረታ ቅንስናሽን አያካትትም።
70
ይህ መለያ ቁጥር ከፋ/ኢ/ል/ቢሮ እና ከባለበጀት መ/ቤት ለባለበጀት መ/ቤቶች ለክልሎች ወይም ለመንግሥት
ሠራተኞች መከፈል የሚገባውን የገንዘብ ልክ የሚይዝ ነው።
ይህ መለያ ቁጥር በባከበጀተ መ/ቤቱ ለሠራተኞች የሚከፈል የገንዘብ ልክ ለመመዝገብ የሚያገለግል ነው።
ይህ መለያ ቁጥር ከሚቀጥለው ዓመት በጀት ላይ በሚታሰብ ለሠራተኞች የደመወዝና አበል ክፍያ ለበጀት መ/ቤቱ
ቅድሚያ ክፍያ ሲፈጸም ከፋ/ኢ/ል/ቢሮ የሚፈለገውን የገንዘብ ልክ ለመመዝገብ የሚያገለግል ነው።
ይህ መለያ ቁጥር ከሚቀጥለው ዓመት በጀት መደበኛ በጀት ላይ በሚታሰብ የሥራ ማስኬጃ ወጪን ለመሸፈን
ለባለበጀት መ/ቤቱ ቅድሚያ ክፍያ ሲፈጸም ከፋ/ኢ/ል/ቢሮ የሚፈለገውን የገንዘብ ልክ ለመመዝገብ የሚያገለግል
ነው።
ይህ መለያ ቁጥር ከሚቀጥለው ዓመት በጀት የካፒታል በጀት ላይ በሚታሰብ የሥራ ማስኬጃ ወጪን ለመሸፈን
ለባለበጀት መ/ቤቱ ቅድሚያ ክፍያ ሲፈጸም ከፋ/ኢ/ል/ቢሮ የሚፈለገውን የገንዘብ ልክ ለመመዝገብ የሚያገለግል
ነው።
ይህ መለያ ቁጥር የፋ/ኢ/ል/ቢሮ ለክልሎት መከፈል የሚገባውን የገንዘብ መጠን ለመመዝገብ የሚያገለግል ነው።
ይህ መለያ ቁጥር ለባለበጀት መ/ቤቱ ቅድሚያ ክፍያ ሲፈጸም ከፋ/ኢ/ል/ቢሮ የሚፈለገውን በሌሎች መለያ
ቁጥሮች የማይሸፈን የገንዘብ ልክ ለመመዝገብ የሚያገለገል ነው።
71
ይህ መለያ ቁጥር በሁለት የባለበጀት መ/ቤቶች ወይም በባለበጀት መ/ቤት እና በክልል መካከል ያሉ ሌሎች ተከፋይ
ሂሳቦችን ለመመዝገብ የሚያገለገል ነው።
5050-5059 አደራዎች
የአደራ ገነዘብ የተወሰኑ ሁኔታዎች ሲሟሉ ለአስቀማጩ ተመላሽ የሚደረግ መንግሥት በጊዜያዊነት በአደራ
የያዘውን ገንዘብ የሚያሳይ ነው።
ይህ መለያ ቁጥር በሌሎች መለያ ቁጥሮች ያልተሸፈኑ በመንግሥት የተያዙ ሂሳቦችን ለመመዝገብ የሚያገለግል
ነው።
ይህ የሂሳብ ኮድ በባለበጀት መ/ቤት ጨረታን ለማስከበሪያ የሚያዙ ገንዘቦቸን ለመመዝገብ የሚያገለግል ነው።
ይህ መለያ ቁጥር የሥራ ተቋራጩ ወይም ሌሎች አቅራቢዎች በሙሉ የገቡትን ግዴታ ለመፈጸማቸው ዋስትና
እንዲሆን በውሉ መሠረት ከተከፋይ ሂሳብ ላይ በጊዜያዊነት ተቀንሶ የሚቀር ሂሳብ ለመመዝገብ የሚያገለግል
ነው።
ይህ መለያ ቁጥር የገንባታ ሥራው ከተጠናቀቀ በኋላ የመጨረሻ ርክክብ እስከሚፈጸም ድረስ ተይዞ የሚቆየውን
የገንዘብ ልክ ለመመዝገብ የሚያገለግል ነው።
5100-5399 የረጅም ጊዜ ዕዳ
በሚቀጥለው የበጀት ዓመት ተከፋይ መሆን የሌለባቸው ዕዳዎች የረጅም ጊዜ ዕዳ በመባል ይታወቃሉ። የረጅም
ጊዜ ዕዳ ዋነኛ ክፍሎች የአገር ውስጥና የውጭ ብድር ናቸው።
72
5100-5149 የአገር ውስጥ ብድር
73
5101 ቦንዶች
5102 ልዩ ቦንዶች
የተጣራ ሀብት ሂሳብ ማናቸውም ዕዳ እና ሌተር ኦፍ ክሬዲት ከተቀነሰ በኋላ ቀሪውን የድርጅቱን የተጣራ ሀብት
የሚያሳይ ነው። አንድ አጠቃላይ የተጣራ ሀብት ሂሳብ እና የመጠባበቂያ ሂሳብ ተብሎ የሚጠራ የሂሳብ መለያ
ቁጥሮች ምድብ ይኖራል።
ይህ መለያ ቁጥር በጠቅላላ ሀብት እና በጠቅላላ ዕዳና ሌተር ኦፍ ክሬዲት መካከል ያለውን ልዩነት ለመመዝገብ
በአጠቃላይ ሌጀሮች ሁሉ ጥቅም ላይ የሚውል ነው።
74
ማጠቃለያ
ሠንጠረዥ 3.6
የሂሳብ መለያ ቁጥሮች
የዘርፍ ምድቦች (001-999)
የገቢዎች/ዕርዳታ/ብድር (1000-3999)
ዝውውሮች (4000-4099)
ጥሬ ገንዘብና ከጥሬ ገንዘብ በእኩሌታ የሚታይ (4100-4199)
ተሰብሳቢ ሂሳቦች (4201-4299)
በጉዞ ላይ ያሉ ዕቃዎች (4300-4399)
አላቂ የመጋዘን ዕቃዎች (4400-4499)
ቋሚ ዕቃዎች (4500-4599)
ተሰብሳቢ ሂሳቦች (4700-4799)
ኢንቨስትመንት (4800-4899)
ተከፋይ ሂሳቦች (5001-5099)
የረጅም ጊዜ ዕዳ (5100-5399)
ሌተር ኦፍ ክሬዲት (5500-5599)
የተጣራ ሀብት (5601)
መጠባበቂያ (5601-5699)
ወጪዎች (6000-6999)
75